You are on page 1of 66

ፈቃደ እግዚአብሔር

ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ


በአሁኑ ጊዜ በምንኖረው ሕይወት ውስጥ ከፍተኛ ግራ መጋባት ከሚፈጥሩብን ነገሮች ፈቃደ እግዚአብሔርን
የተመለከተው ቀዳሚ ሥፍራ የሚወስድብን ይመስለኛል፡፡የምናዝንባቸው፣ የምንበሳጭባቸው፣ መደረጋቸውን መቀበል
እስከሚያቅተን ድረስ የምንረበሽባቸው ድርጊቶች በተፈጸሙ ጊዜ መፈተናችን ይጨምራል፡፡ ነገሮቹ በቤተ ክርስቲያን
አካባቢ ሲሆኑ ደግሞ የበለጠ እንፈተናለን፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ወይ እምነታችን የተሳሳተ ካለበለዚያም
እግዚአብሔር የእኛን ጸሎት መስማት ያቆመ ይመስለናል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ደግሞ መቋሚያቸው ይህ ብቻ
አይደለም፤ ከፍተኛ ጥራጣሬ ላይ ጥለውን ብቻ ሳይሆን ደስታችንንም ሰርቀውብን አጎረምራሚና ወቃሽ አድረገውን፤
በቤተ ክርስቲያናችንና በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አካላትም ላይ እንድናኮርፍ አድርገውን በአጠቃላይ መንፈሳዊ
ሕይወታችንም ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥረውብን ያልፋሉ ወይም እኛን ወደ ሌላ ሕይወት ያሳልፉናል፡፡ በተለይ በእነዚህ
ጊዜያት ‹‹ የእግዚአብሔር ፈቃድ›› ነው ተቀበሉ የሚል ሰው ከገጠመን ልናደምጠው እንቸገራለን፤ አንዳንዴማ
ልባችንን ዘልቆ ከገባው ሐዘን የተነሣ የሚናገርን ሰው ሞኝነቱ ብቻ ሳይሆን በእኛ ኅሊና የተሳለው አላዋቂነቱም
እየታየን ብስጭታችን ሊጨምር ይችላል፡፡ ለመሆኑ ክፉ ሰዎች ግፍ ሲፈጽሙ ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማታለልና
ተንኮል የተፈጸመ ሲመስለን ይህን ሁሉ ፈቃደ እግዚአብሔር ነው ብሎ መቀበል ይቻላልን? ለመሆኑ የፈቃደ
እግዚአብሔር ድንበሩ ምንድን ነው? ክፉ የሚመስሉን ሰዎች ሲሾሙ፣ በሀገርና በሕዝብ ላይ አስከፊ ነገር ሲፈጸም ፣
አደጋና ጥፋት ሲደርስስ ፈቃደ እግዚአብሔር ነው ማለት ይቻላል? የምንፈልገው መልካም ነገር የማይፈጸመውስ
ለምንድን ነው? እግዚአብሔር በጎው እንዲፈጸም አይወድምን? ወይስ ፈቃዱ የሚሆነው መቼ ነው? እነዚህ ሁሉ
ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጥያቄዎች ሆነው የሚያስቸግሩበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ጉዳዮቹን በቀጥታ ከማየታችን በፊት
ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመቀበል የሚፈትኑን ነገሮች እናስቀድም፡፡ ስለ ፈቃደ እግዚአብሔር ካሉን የተሳሳቱ
አስተሳሰቦች ጥቂቶቹ

1) ክፉው ከእግዚአብሔር አይደለም

የፈቃደ እግዚአብሔርን ምንነት እንዳናውቅ የሚጋርዱ ብዙ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች በውስጣችን ሊኖሩ ይችላሉ፡፡
ከእነዚህ ውስጥ አንዱና ዋነኛው ክፉው ከእግዚአብሔር አይመጣም የሚለው ነው፡፡ቅዱሳት መጻሕፍት ግን ይህም
ቢሆን ከእግዚአብሔር ነው ይሉናል፡፡ ‹‹ ደዌና ጥዒና(ጤና)፣ ሞትና ሕይወት፣ ብልጽግናና ችግር መገኛቸው
ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው›› /ሲራ 11፤14-16/፡፡ በትንቢተ አሞጽም ላይ ‹‹ ወይስ ክፉ ነገር በከተማ ላይ የመጣ
እንደ ሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?›› /አሞ 3፡6/ ይላል፡፡ በአጭሩ ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ይመጣል፡፡
ለምን እንደሚመጣ ምክንያቱን ለጊዜው አቆይተን የክፉ ወይም የማንፈልጋቸው ነገሮች መፈጸም የእግዚአብሔር
ፈቃድ ነው እንዴት ሊባል ይችላል? የሚለውን እንመልከት፡፡
እግዚአብሔር ክፉ አድራጊውን ክፉ እንዲሆን አላደረገም፤ አያደርግምም፡፡ በሚፈጽሙት ማንኛውም ክፉ ነገርም
ፈጻሚዎቹን መጠየቁም አይቀርም፡፡ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የሚከፍል አምላክ ነውና፡፡ ክፉው በሚደርስባቸው
ሰዎች ላይ ግን የሚፈጸምባቸውን ነገር እንዳይደርስባቸው ሁልጊዜም አይከላከልላቸውም፡፡ ይህም የሚሆነው ስለ
ሦስት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመሪያውና ዋናው ከበጎ ብቻ የማንማርና የማንጠቀም ሰዎች ስላለን ነው፡፡ ሰዎች
በባሕርያችን ደካሞች ስለሆንን ብዙ ጊዜ በጎውን ነገር ባገኘን ጊዜ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት አንችልም፡፡ ለእኛ
መልካም የመሰለን የሚደረግ ከሆነም ያ ነገር ሌሎቹን የሚጎዳ እንኳ ቢሆን ስለሌሎቹ አንጨነቅም፡፡ ሌላው ቀርቶ
መልካም የመሰለንና እስኪደረግልን የጓጓንለት ነገር በተፈጸመ ጊዜ ከፈነጠዝን በኋላ ያሰብነውን ያህል እንዳልተጠቀምን
በተረዳን ጊዜ እንደገና እግዚአብሔርን ለመውቀስ ወደ ኋላ አንልም፡፡ ምክንያቱም ጥቅም የሚገኝ የሚመስለን እኛ በጎ
ነው ብለን በምናስባቸው ነገሮች መፈጸም ብቻ ስለሚመስለን ነው፡፡ መጥፎ ከምንላቸውና ከማይጠቅሙ ነገሮች
ጥቅም እንደሚገኝ ካለማወቃችን በላይ እግዚአብሔር ከነዛ የሚገኘውን ጥቅም ሊሰጠን ሲፈቅድም በመቃወማችን
ብቻ ሳንጠቀም እንቀራለን፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር የሚጠቅሙን እስከሆነ ድረስ ክፉ የምንላቸውንም ማምጣቱ
አይቀርም፡፡ በአንድ ወቅት በአንድ የቁሪት (ለራሳቸው የሚሆነውን ምግብና ምርት በየራሳቸው ሠርተው በሚኖሩበት)
ገዳም ውስጥ በሚኖሩ አባቶች የተፈጸመው ታሪክ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡ በገዳሙ ከሚኖሩ አባቶች
ውስጥ ሁሉም በሚባልበት ሁኔታ ምርታቸው በቂ ስለማይሆንላቸው ይቸገራሉ፡፡ በተለይ ድርቅ በሚሆንበት ጊዜ
የሚላስ የሚቀመስ አስከማጣት ስለሚደርሱ ድርቅ እንደ እሾህ ይፈራሉ፡፡ ከዚህ የተነሣ በየዓመቱ እግዚአብሔር ድርቅ
እንዳያመጣ ብቻ ሳይሆን ጊዜውን ጠብቆ እንዲያዘንም፣ ነፋሳቱን እንዲያፈራርቅና አስፈላጊውን ሁሉ
እንዲያደርግላቸው በምሕላ በሱባዔ እግዚአብሔርን በኅብረት ይለምናሉ፡፡ ይሁን አንጂ በአብዛኛው ድርቅ
ይመታቸዋል፡፡ እነርሱም ብዙ ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ ያጎረመርማሉ፡፡ አንድ ነገር ደግሞ ሁልጊዜም ያስገርማቸዋል፡፡
በገዳማቸው ከሚኖሩት አባቶች የአንዱ ምርት ሁልጊዜም ከፍተኛ ነው፡፡ ድርቅም ቢሆን ዝናብም ቢበዛ፣ ተምችና
አንበጣ ቢመጣ፣ ውርጭና በረዶ ቢፈራረቅ የዚህ አባት ምርት ሁልጊዜ ተመሳሳይ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት አንዳንዶቹ
ከመደነቅም አልፈው ይህ ሰው ምን የተለየ ነገር አለው እያሉ ወደ መጠራጠርም ሔደው ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን
ጠየቁት፡፡እርሱም ምስጢሩን ነገራቸው፡፡ እኔ ለሱባኤ ስንሔድ እግዚአብሔርን የምለምነው እኛ የምንፈልገውን ሳይሆን
የሚጠቅመንን እንዲያደርግልን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ድርቅ በሆነ ጊዜም እግዚአብሔር ድርቁን ያመጣው ከዝናቡ ይልቅ
ድርቁ ቢጠቅመን ነው ብየ ከልቤ አምናለሁ፡፡ ስለዚህ በአንዳንዱ ዓመት በዝናባማ ጊዜ ከማገኘው የተሻለም በድርቁ
ጊዜ አገኛለሁ፡፡ በዚህም ድርቁ የመጣው በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ በሌላውም ጊዜ ቢሆን
ማንኛውም ነገር ሲከሰት አላጉረመርምም፤ ምክንያቱም ባይጠቅመን ኖሮ እግዚአብሔር አያመጣውምና አላቸው፡፡
እነርሱም የችግራቸው ምንጭ ድርቁ ወይም ሌላው ሳይሆን እነርሱ ክፉ የመሰላቸውን ድርቁን በእግዚአብሔር ፈቃድ
እንደሆነ አለማመናቸው መሆኑን ተረድተው ለንስሐ በቁ፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በነቢዩ በኢሳይያስ አድሮ
‹‹ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ
እግዚአብሔር እኔ ነኝ›› /ኢሳ 45፤7/ የሚለንም በክፋት ፈጣሪነቱ ለመመካት ወይም ‹‹ ምን ታመጣላችሁ››
ለማለት ሳይሆን ከሚደርስብን ክፉ ነገርም መጠቀም የምንችል መሆናችንን ለመንገር ነው፡፡ በርግጥም እግዚአብሔር
በብርሃኑ ብቻ ሳይሆን በጨለማውም የብርሃኑን ያህል እንደጠቀመን እንደሚጠቅመንም ማመን ይገባናል፡፡
ክፉው እንዲገጥመን ፈቃዱ የሚሆንበት ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ነጻ ፈቃድን ሊሸራርፍ ስለማይወድ ነው፡፡
እግዚአብሔር ክፉዉንና በጎውን፣ ሩቁንና ቅርቡን የሚለይ አእምሮ ሰጥቶ ከፈጠረንና እያንዳንዳችንም እንደ ሥራችን
እንደሚከፈለን ከነገረን በኋላ በእያንዳንዷ ሥራችን ላይ ጣልቃ እየገባ ይህንን ወይም ያንን አድርጉ፣ አታድርጉ
አይልም፤ እንድናደርግ ወይም እንዳናደርግም አያስገድድም፡፡ ይህ ሁሉ እንዲሆን ፈቃዱ ነው የሚባለውም በክፉው
ነገር መፈጸም የሚደሰት ሆኖ ሳይሆን ክፉዎችን ለይቶ ያሰቡትን እንዳያደርጉ ስለማይከለክል ነው፡፡ ነጻ ፈቃዳችንን
ተጠቅመን እንድነሠራ አንድ ጊዜ ለሁላችንም ፈቅዷልና፡፡ አንዳንድ ሊቃውንት ይህንን ፈቃዱን የእግዚአብሔር
የፍጹምነቱ መገለጫ አድርገው የሚያቀርቡትም ፍትሑን ረስቶ ፈቃዳችንን ጨልጦ ገርኝቶ አስትቶ እንደ ቁስ አካል
በሠሪው ፈቃድ ብቻ የማይጠቀምብን (ምንም እንኳ ከየትኛውም ድርጊታችን የሚጠቀመው ነገር ባይኖርም
ነጻነታችንን የማይጋፋ) መሆኑን ስለሚያሳይ ነው፡፡
ከዚህም አልፎ ክፉው ሳይደርስብን ብቻ ሳይሆን ደርሶብንም መጠቀም እንደምንችልና ሰዎች ሌሎችን ለመጉዳት ሆነ
ብለው ከሚፈጽሙት ክፉ ድርጊት እንኳ እግዚአብሔር ወዳጆቹን እንዴት ፍሬያማ ማድረግ እንደሚችልና ሁሉን ቻይ
መሆኑንም የሚያስተምረንም ከእነዚህ መሰል ድርጊቶች ነው፡፡ ለምሳሌ በኢዮብ የደረሰውን መከራ ስንመለከት እንዴት
እግዚአብሔር እንዲህ ያደርጋል ሊያሰኘን ይችላል፡፡ በተለይ በቅዱስ መጽሐፍ ሳይጻፍ በእኛ ዘመን ለሁላችን በታወቀ
ሁኔታ ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ‹‹ እግዚአብሔር ወዴት አለ?›› ልንል ሁሉ እንችላለን፡፡ ኢዮብ ግን ያለው
‹‹እግዚአብሔር ሰጠኝ የሳባም ሰዎች ወሰዱብኝ›› ሳይሆን ‹‹ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሣ ›› ነው፡፡ ይህን
ያለው የሳባ ሰዎችን እግዚአብሔር ልኳቸዋል ወይም በክፋታቸውና በግፋቸው እግዚአብሔር ይደሰታል ብሎ ሳይሆን
ፈቃዳቸውን እንዲፈጽሙ ያልከለከላቸው እነርሱ ካደረሱብኝ ግፍም እግዚአብሔር የሚሰጠኝ በጎ ነገር አለ ብሎ
ከልቡ በማመኑ ነው፡፡ በርግጥም ኢዮብ ከነበረው ሁለት እጥፍ ያገኘውና ከቀደመ ክብሩ ወደሚበልጥ ክብር
የተሸጋገረው እግዚአብሔር በክፉውም ውስጥ ያለውን የማዳን ኃይል በማመኑ ነው፡፡
በአንድ ወቅት በአንድ ገዳም በሚኖሩ አባቶችም ተመሳሳይ ታሪክ ተፈጽሞ ነበር፡፡ በገዳሙ ካሉት አባቶች አንዱ ብዙ
ተአምራቶችን የሚያደርጉ በተለይ አጋንንትን በማስወጣት በፈውስ ታላቅ ሀብት የነበራቸው አባት ነበሩ፡፡ ገዳማቸው
ደግሞ ብዙ ጊዜ በሽፍቶች ይዘረፋል፤ ይቃጠላል፤ መነኮሳቱም ይደበደባሉ፤ ብዙ መከራም ይቀበላሉ፡፡ ከዚህ የተነሣም
ብዙዎቹ ያማርራሉ፤ ያዝናሉ፣ ያለቅሳሉ፡፡ ይህ ተአምራት ሚያደርግ አባት ግን ምንም አይልም፡፡ በሁኔታው
የተገረሙት መነኮሳቱም ለምን ዝም ይላል ብለው በአበ ምኔቱ እንዲጠየቅ አደረጉት፡፡ ያ አባትም እነዚህ ሁሉ
መከራዎች የሚመጡብን የእግዚአብሔር ፈቃዱ ስለሆነ ነው፡፡ የሚደጋገሙብን ግን እናነተ ፈቃዱ ነው ብላችሁ
ስለማታምኑና ከአንዱም ለመማር፣ ከመከራ ከሚገኘው ጸጋም ለመሳተፍ ፈቃደኞች ስላልሆናችሁ ነው፡፡ መከራውን
ያላቆመውም እግዚአብሔር ከዚህ የምታገኙት ጥቅም እንዳይቀር ቸል ባይላችሁ ነው አለው፡፡ አበ ምኔቱም
እግዚአብሔር ለዚያ አባት ተአምራት ማድረግን የሰጠው ክፉዉንም ሁሉ ፈቃደ እግዚአብሔር ነው ብሎ በመቀበሉ
እንደሆነ ተረድቶ ተመለሰ ይላል፡፡ ስለዚህ ክፉ ነገር ሁሉ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጎጂ ብቻ ሳይሆን ጠቃሚም ነገር
ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ግን እንዲያው እንደ ፊልምና ልቦለድ ወይም እንደ ነነዌ እሳት አይተነው ደንግጠን
ወይም አዝነን ብቻ በዚያው የሚቀርልን ነው ማለት አይደልም፡፡ በትክክል ደርሶብን ሥጋችንንም ቆንጥጦን ተሰምቶን
አንዳንድ ጊዜም እንደ ኢዮብ አስጨንቆንም የሚያልፍ መሆኑን መርሳት የለብንም፡፡
ወደ ሦስተኛው ከመሸጋገራችን በፊት ግን ከላይ በተጠቀሱት ሁለቱ ምክንያቶች የሚጠቀሙት እነማን እንደሆኑ ጠቆም
አድርጌ ልለፍ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ በጻፈው መልእክቱ ‹‹ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት
እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን›› /ሮሜ 8፤28/ ብሏል፡፡ ስለዚህ ከክፉው እንኳ
ሳይቀር መልካም ፍሬ ማፍራት የሚቻላቸው ክፉው የደረሰባቸው ሁሉ አይደሉም ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ‹‹ ነገር
ሁሉ ለበጎ›› የሚሆንላቸው ‹‹እግዚአብሔርን የሚወዱትና እንደ አሳቡም የተጠሩት›› ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ በተረፈ
ጥቅሱን ስላስታወስንና የተረበሹ ሰዎችን ለማረጋጋት ስንል ‹‹ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው›› ስላልን ብቻ ነገር ሁሉ ለበጎ
ሊሆን አይችልም፡፡ እግዚአብሔርን የሚወዱት ደግሞ ትዕዛዙን የሚጠብቁት ናቸው፡፡ እኛ ትእዛዙን ሳንጠብቅ ወይም
እግዚአብሔርን ሳንወድ ልክ እንደ መለወጫ ማሽን ክፉውን በጎ የሚያደርግልን ኃይል ሊመጣ አይችልም፡፡ ስለዚህ
ነገር ሁሉ ‹‹ ክፉውም ጭምር ›› ለበጎ እንዲሆንልን የምንፈልግ ከሆነ የመጀመሪያው ደረጃ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ
ሳንልከሰከስ መጠበቅ ይገባናል፡፡ ሁሉተኛውና ከባዱ ግን ‹‹ እንደ አሳቡም የተጠሩት›› የሚለው ነው፡፡ ነገሩ እንደ
አሳቡ እንደ ፈቃዱ መኖር ማለት ነው፡፡ ይህም በአጭሩ ከላይ በበረሐውያን አባቶች መፈጸሙን እንዳየነው ድርቁንም
ውርጩንም ሕማሙንም ድብደባ መከራውንም እግዚአብሔር እንድቀበለው ፈቃዱ ከሆነ እርሱ ይሻለኛል ብሎ
የሚቀበል ልቡና ወይም ፍጹም እምነት ላይ መድረስን ይጠይቃል፡፡ በአጭር ቃል ከክፉው ለመጠቀም እንዲህ ያለ
እምነትና ተእዛዛተ እግዚአብሔርን መፈጸምን ወይም እግዚአብሔርን መውደድን ገንዘብ ሳያደርጉ የሚያገኙት ነገር
አይደለም ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ክፉ ነገር ደርሶብን ሳንጠቀም እንቀራለን፤ መጠቀም ስላልቻልንና ይሔ
ስላልገባንም ገና አልገባቸውም ተብሎም አይቀርልንም ማለት ነው፡፡
ሦስተኛው እግዚአብሔር ክፉ ነገርን የሚያመጣበት ምክንያት ደግሞ ከኃጢአታችን የተነሣ ለመቅጣት ነው፡፡ ለምሳሌ
ወዳጁን ዳዊትን እንዴት እንደቀጣው ማስታወስ እንችላለን፡፡ ‹‹ ... ናታንም ዳዊትን አለው። ያ ሰው አንተ ነህ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በእስራኤል ላይ ንጉሥ ልትሆን ቀባሁህ፥ ከሳኦልም እጅ አዳንሁህ ፤
የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፥ የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም
አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር። አሁንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሔርን ነገር ለምን
አቃለልህ? ኬጢያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፥ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል፤ እርሱንም
በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል። ስለዚህም አቃልለኸኛልና፥ የኬጢያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን
ዘንድ ወስደሃልና ለዘላለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር
አስነሣብሃለሁ ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ፥ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፥ በዚህችም ፀሐይ ዓይን ፊት
ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል። አንተ ይህን በስውር አድርገኸዋል እኔ ግን ይህን በእስራኤል ሁሉ ፊትና በፀሐይ ፊት
አደርገዋለሁ ›› /2 ኛ ሳሙ 12፤ 6 - 12/ ተብሎ እንደተጻፈው በዳዊት ላይ የመጣው ነገር ሁሉ ከክፉ ሥራው
የተነሣ ነው፡፡ እግዚአብሔርም በማያሻማ መንገድ ‹‹ እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ›› ያለው ለመቅጣትም
ክፉ ነገርን የሚያመጣ እርሱ ስለሆነ ነው፡፡ እንዲያው በዚህ ዓይነት የበቀል ጊዜ ክፉ ሰዎችን ወደጆቹን እንዲቀጡ
ያነሣሣቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ‹‹ በተጎበኛችሁበት ቀን፥ መከራም ከሩቅ በሚመጣበት ዘመን ምን ታደርጉ ይሆን?
ለረድኤትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ክብራችሁንስ ወዴት ትተዉታላችሁ?›› / ኢሳ 10፤3/ እያለ የሚዘልፋቸውን
እሥራኤልን ሊቀጣ በወደደ ጊዜ ስላስነሣው ስለ አሦር ‹‹ ለቍጣዬ በትር ለሆነ፥ የመዓቴም ጨንገር በእጁ ላለ ለአሦር
ወዮለት! እርሱንም በዝንጉ ሕዝብ ላይ እልካለሁ፥ ምርኮውንና ብዝበዛውንም ይወስድ ዘንድ እንደ አደባባይም ጭቃ
የተረገጡ ያደርጋቸው ዘንድ በምቈጣቸው ሰዎች ላይ አዝዘዋለሁ። እርሱ እንዲሁ አያስብም፥ በልቡም እንዲህ
አይመስለውም፤ ነገር ግን ማጥፋት፥ ጥቂት ያይደሉትንም አሕዛብን መቍረጥ በልቡ አለ ›› / ኢሳ 10፤ 5-7/ እያለ
የሚናገረው ተበቃዩን አስነሹም እርሱ ስለሆነ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ደግ የነበረውን ሰው ለመበቀል ሲል እርሱ
አከፍቶታል ማለት አይደለም፡፡ ‹‹ጥቂት ያይደሉትንም አሕዛብን መቍረጥ በልቡ አለ›› ተብሎ እንደ ተጻፈው
በሰውየው ዘንድ ማጥፋ ወይም ክፋት ነበረ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ያን ክፉ ሰው ቀደም ብለን እንደገለጽነው
ክፋቱን ይፈጸም ዘንድ ካለመከልከሉ በላይ ልቡን ሌሎቹን ከማጥፋት እግዚአብሔር ሊቀጣቸው ወደ ፈቀደው ወደ
እሥራኤል አነሣሣው ማለት ነው፡፡ ‹‹ እርሱ እንዲህ አያስብም፤ በልቡም እንዲህ አይመስለውም›› የተባለውም
ሰውየው ቀድሞ ይህን የመሰለ ክፋት ማድረግ በልቡ ስላለ ባጠፋ ጊዜ እግዚአብሔር በእኔ አድሮ አጠፋ ብሎ ሊያስብ
አይችልም፤ ምክንያቱም ክፋቱ የራሱ ነውና፡፡ እግዚአብሔር ግን ይህን ክፋቱን እርሱ ሊቀጣቸው በወደደው ሕዝብ
ላይ እንዲፈጽም በማድረግ አሦርም ክፋቱን እግዚአብሔርም ቅጣቱን በአንድ ሕዝብ ላይ አደረጉ ማለት ነው፡፡
ለዚህም ነው እግዚአብሔር አሥራኤልን በአሦር መቅጣቱ አሦርን ከፍርድ ነጻ የማያደርገው፡፡ ‹‹ ለቍጣዬ በትር
ለሆነ፥ የመዓቴም ጨንገር በእጁ ላለ ለአሦር ወዮለት!›› /ኢሳ 10፤5/ ተብሎ የተጻውም ለዚህ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር
የቀጭወቻችን ወይም መከራ የሚያመጡብን ሰዎች ከሐዲነትና ክፋት እኛን ጻድቅ አያደርገንም ወይም ደግሞ
መከራውንና ስቃዩን የማይገባን ሊያደርገው አይችልም፤ እግዚአብሔር ለእነርሱ ፈቅዶ እኛን እንድንቀጣ ማድረጉም
ቀጭዎቹን ጻድቃን ወይም እግዚአብሔርንም የተሳሳተ አያደርገውም፡፡ ስለዚህም ክፉ ሰዎችን አስነስቶ የሚቀጣ፣
መከራና ስቃይ የሚያመጣም እግዚአብሔር ነው ማለት ነው፡፡
አማኞች የሆኑ ሰዎች ግን ከዚህም መንፈሳዊ ፍሬን ሊያጭዱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ከላይ በጠቀስነው የቅዱስ ዳዊት
ታሪክ ውስጥ ቅዱስ ዳዊት ተነግሮትና ጥፋቱንም አምኖ የተቀበለው ስለሆነ በሁለት መንገድ ተጠቅሟል፡፡ በመጀመሪያ
ቅጣቱን ወይም መቅሰፍቱን ይገባኛል ብሎ ስለተቀበለ መንግሥቱ ጸንቶለታል፤ እጂግ ከከፋ መከራም ድኗል፡፡
ሁለተኛውና ዋናው ጥቅሙ ግን እግዚአብሔር ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፍላልና ኃጢአቱ የምታመጣበትን ፍዳ
በምድር ላይ በመቀበሉ ስለ ኃጢአቱም ሥርየት በማግኘቱ በሰማይ ሊገጥመው ከሚችለው የዘላለም ቅጣት አመለጠ
ማለት ነው፡፡ ስለዚህም በምድር የገጠመችው ቅጣት ሊነጻጸር ከማይችል ዘላለማዊ የነፍስ ቅጣት ስላዳነችው ከፍተኛ
ተጠቃሚ ሆኖአል፡፡ ‹‹ እንደ አሳቡም ለተጠሩት›› የሚለው የሐዋርያው ቃል ከተፈጸመላቸው ሰዎችም አንዱ ዳዊት
ነው፡፡ እንደርሱ የእገዚአብሔርን አሳብ ወይም ፈቃድ የሚቀበል ሰው አልነበርምና፡፡ ይህም ሳዖል ያህልን አሳዳጁን
ሁለት ጊዜ ለመግደል ተመቻችቶ ባገኘው ጊዜ ከዘፈረ ልብሱ እየቆረጠ ማድረግ የሚችል መሆኑን እያሳየ ለፈቃደ
እግዚአብሔር ሲል (ቀብቶ ያነገሠውን አልገድልም) ብሎ የተወ በርግጥም እንደ እግዚአብሔር አሳብ የሚኖር ሰው
ነበርና፡፡ እንኳን እግዚአብሔር ለቀባው ለሳዖል ይቅርና ለፍልስጤማውያንም ‹‹ ልሂድን? እነዚህንስ
ፍልስጥኤማውያን ልምታን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ሂድ፥ ፍልስጥኤማውያንን ምታ
ቅዒላንም አድን አለው›› /1 ኛ ሳሙ 23፤2/ ብሎ ይጠየቅ ነበርና፡፡ እግዚአብሔርም ለዳዊት ‹‹እንደ ልቤ የሆነ ሰው
ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ›› /ሐዋ 13፤22/ ሲል የመሰከረለት የዳዊት ጦርነትና
ግድያ የእግዚአብሔርን አሳብ የተከተለ እንጂ እንደነ አሦር በጭካኔና ለራሱ ገናንነት ሲል የሚያደርገው ስላልነበረ
ነው፡፡
በዚህ ዘመን የምንኖር እኛ ፈቃደ እግዚአብሔር ሳናውቅ አሳቡንም ሳንረዳ የምንኖረውና የምንቸገረውም ስለ ክፉ
ነገሮች ካለን የተሳሳተ አሳብ የተነሣ ነው፡፡ እኛ ምቾትን እንደ ነዌ ጽድቅንም ወይም በአብርሃም እቅፍ መቀመጥንም
እንደ አልዓዛር የምንፈልግ ሰዎች ነን፡፡ ይህ ደግሞ ከባድ ነገር ነው፡፡ ለመጽደቅ የግድ እንደ አልዓዛር መደኸየትም
በደዌ መሰቃየትም የማያስፈልግ ቢሆንም ቢያንስ ግን ስለ ኃጢአታችን የሚመጣውን መከራና ስቃይ ለመቀበል
ፈቃደኞች ካልሆንን ስለጠላነው ብቻ ክፉው እንዴት ሊቀር ይችላል? ክፉዎችንስ በክፋት እንዴት ልናስወግዳቸው
እንችላለን? ዘዴያችን እንደ አታላይ ፖለቲከኞች፣ ሀሳባችን እንደ ብልጦች ሆኖ ጽድቃችን እንደነ ዳዊት እንዴት ሊሆን
ይችላል? ኃጢአታችን እንደ ሰዶም እንደ ገሞራ ሰዎች፣ ቸልተኝነታችንም እንደ ኖኅ ዘመን ሰዎች መሆኑ ፍጥጥ ብሎ
እየታየ መሪዎቻችን እንደ ዳዊት እንደ ሰሎሞን በረከቱና ሰላሙስ እንደ ብሔረ ሕያዋን እንዴት ሊሆን ይችላል?
የምንሠራውን ሥራና ያለንበትን ሕይወት እንደ ጽድቅ ቆጥሮ እግዚአብሔርን እንበደለኛ ከመቁጠርስ የሚበልጥ ምን
ድፍረት አለ? ትልቁ ፈቃደ እግዚአብሔርን ለላማወቃችን መጋረጃ የሆነብንንም ይሔው እየደረሰብን ነው የምንለውን
ክፉ ነገር ፈቃደ እግዚአብሔር ነው ብለን መቀበል አለመቻላችን ነውና ክፉውን ከእግዚአብሔር ነው ለማለት
እንጀምር፡፡
Like

ፈቃደ እግዚአብሔር (ክፍል ሁለት)

ባለፈው ዕትም ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመቀበል እንዳንችል ከሚያደርጉን ምክንያቶች አንደኛውንና ‹‹ ክፉው
ከእግዚአብሔር አይደለም›› የምንለውን የተሳሳተ ሀሳባችንን ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር ተመልክተን ነበር፡፡ ዛሬ
ደግሞ ሁለተኛውን ብቻ እንመለከታለን፡፡
2) ‹‹ ክፉ›› የትኛው ነው?
ሁለተኛውና ከፈቃደ እግዚአብሔር በቀላሉ የሚለየን ነገር ደግሞ ‹‹ ክፉ›› ስለምንለው ነገር ያለን ግንዛቤ ነው፡፡
ለመሆኑ ክፉ ልንለው የሚገባው የትኛውን ነው? ክፉ ሰዎችስ እነማን ናቸው? ይህም ጥንቃቄ የሚያስፈልገውና
ከእግዚአብሔር እንዳያጣላን ልናስብበት የሚገባ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም በቅዱሳት መጻሕፍት ተደጋግሞ
እንደተገለጸው ክፉ በሚሏቸው ሰዎችም ሆነ ድርጊቶች ብዙ የእምነት ልዩነት ይታያል፡፡ ለምሳሌ እሥራኤል በቀቲሎተ
አምላክ የተሰማሙት ሰዎች ጌታን ክፉ አድርገው ሰለሳሉላቸውና እነርሱም ስለተቀበሉት ነው፡፡ በዘመነ ቅዱስ ዳዊት
ጊዜም እሥራኤል ከደገኛው ንጉሣቸው ከዳዊት ይልቅ ሸንጋዩን አቤሴሎምን ለመከተል የበቁት የማታለል ሥራውን
የደግነት አድርገው ስለ ቆጠሩት ነው፡፡ ከእነዚህ ታሪኮች በቀላሉ ለመረዳት እንደምንችለው ‹‹ ክፉ›› የሚመስሉን
ሰዎች ክፉ ላይሆኑ የሚችሉበት አጋጣሚ መኖሩን ነው፡፡ ይህን በማድረጋችን ቢያንስ ከሁለት ታላላቅ ኃጣውእ
ልንጠበቅ እንችላለን፡፡ የመጀመሪያው ‹‹ አትፍረዱ...›› ከሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ትእዛዙ ከተላለፈበት
ምክንያት ማለትም ጻድቁን ኃጥእ ፣ ኃጥኡንም ጻድቅ ከማለት እንድናለን፡፡ ‹‹ኀጥኡን የሚያጸድቅና በጻድቁ ላይ
የሚፈርድ፥ ሁለቱ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው›› /ምሳ 17፥15/ ተብሎ ተጽፏልና፡፡ በዚህም ክፉ
ያልሆነውን ክፉ ፣ በጎ ያልሆነውንም በጎ ከማለትና ከእግዚአብሔርም ፈቃድ ከመውጣት እንድናለን፡፡
ሌላውና መሠረታዊው ነገር ደግሞ በእኛ ላይ የሚደርሱትና ክፉ የሚመስሉን ነገሮች በርግጥ ክፉ ናቸው ወይ?
የሚለው ነው፡፡ ለምሳሌ ብዙ ጊዜ ሕማምን፣ ረሃብንና ችግርን፣ ድርቅንና ስደትን፣ መታሠርንና መገፋትን፣
መደኸየትን፣ ከነበረን ክብር ማነስን፤ ... በተለምዶ ወይም ብዙ ጊዜ ክፉ አድርገን እንቆጥራቸዋለን፡፡ በርግጥ እነዚህና
የመሳሰሉት ነገሮች ክፉ ናቸውን? አሁንም በእኛ ዘንድ ክፉ ተደርገው ሊቆጠሩ ቢችሉም በእግዚአብሔር ዘንድስ ክፉ
ሊሆኑ ይችሉ ይሆንን? በርግጥ በመጀመሪያው ክፍል ጽሑፍ ላይ እንዳየነው እግዚአብሔር ‹‹ ክፉ ነገሮችን የማመጣ
እኔ ነኝ›› ብሎ ተናግሯል፡፡ ነገር ግን ይህ ንግግሩ በእኛ ስሜት ለመናገር ነው እንጂ በእርሱ ዘንድ ክፉ ሆነው
አይደለም፡፡ ምክንያቱም እነዚያን ሁሉ ነገሮች በእኛ ላይ የሚያመጣው ከነፍስ ቁሳላችን ለመፈወስና ከሚመጣብንም
ከባድ ቅጣት ለማዳን ነው እንጂ ለመጉዳት አይደለም፡፡ለጊዜው ለእኛ ጉዳት ሆነው ቢሰሙንም ለእግዚአብሔር ግን
አንደኛ ፍርዱ ትክክል ስለሆነና ስለማያዳላ የሚገባንን እንጂ ከሚገባን በላይ ስለማያመጣ እየጎዳን አይደለም፡፡
ሁለተኛም እንደተገለጸው እኛን ከስሕተቶቻችን ለመመለስ የሚያደርጋቸው ስለሆኑ የሚያስተምርባቸው እንጂ
ለማማረር ያመጣቸው አይደሉምና ክፉ አይደሉም፡፡
በአንድ ወቅት በአንድ ገዳም የነበረ አባት ታምሞ በተኛ ጊዜ ከሌላው አባት የተላከለት መልእክት ፈቃደ
እግዚአብሔርን የተረዱት ሀሳባቸው ምን እንደሆነ የሚያሳይ ድንቅ ነገር ነው፡፡ ያልታመመው አባት ለታመመው ‹‹
ታምመህ በመተኛትህ ጤነኛ ብሆን ኖሮ ይህን ይህን እሠራ ነበር እያልክ አታስብ፡፡ ጤነኛ ሆነህ እግዚአብሔር
እንድትሠራው ያልፈቀደልህን ከምትሠራ ታምመህ ፈቃዱን ብትፈጽም ይሻልሃልና፡፡ መታመመህ ፈቃዱ ከሆነ ቶሎ
መዳንና መነሣት አለብኝ ማለትም አይገባህም፡፡ መታመምህ ፈቃዱ ሆኗልና›› በማለት ልኮለት ነበር፡፡ በርግጥም በእኛ
ዘመን ብዙ ሰው ከእግዚአብሔር እየተለየ ወደ ባዕድ አምልኮዎችና ጠንቋዮች ወደ አታላይና ነጋዴ አጥማቂዎች ወይም
በጥምቀት ሰብብ ብዙ ጥፋት ወደሚሠሩ አስመሳዮች እስከመሔድ የሚደርሰው መታመምን፣ ማጣትን፣ መዋረድን፣
መሻርን፣ በሰው ዘንድ ያለንን ክብር ማጣትንና የመሳሰሉትን እንደ ክፉ ብቻ ተገላቢጦሹን ደግሞ እንደ በጎ ብቻ
የመውሰድ አባዜ ስላለብን ነው፡፡ ከእነዚህ ስንላቀቅም ደስተኞችና እግዚአብሔርን አገልጋዮች የምንሆንም
ይመስለናል፡፡ በእውነተኛው የክርስትና ሕይወት ግን ፈቃደ እግዚአብሔር ማለት ለነፍሳችን ጥቅም ሊያገለግሉ
የሚችሉትንና ምንአልባትም ሥጋችንን ግን ሊቆነጥጡ የሚችሉትን ጭምር በደስታ መቀበልን ያጠቃልላል፡፡
ምክንያቱም እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ለእኛ መልካም እንዲሆንልን የተሰጡ ናቸውና፡፡ ዮሴፍ ወልደ ያዕቆብ
ከብዙ የስቃይ ዘመናት በኋላ ከብሮና ተሹሞ ሳለ ልብሱን ገፍፈው ራቁቱን የሸጡት ወንድሞቹ ባገኙትና
በድርጊታቸው አፍረውና ተሳቅቀው ባያቸው ጊዜ፦ ‹‹ ወደ እኔ ቅረቡ፤ ... ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ እኔ ወንድማችሁ
ዮሴፍ ነኝ። አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትዘኑ፥ አትቈርቈሩም እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከእናንተ በፊት
ሰድዶኛልና ›› /ዘፍ 45 ፤4- 5/ በማለት የመለሰላቸው ክፉ የሚመስለን ሁሉ ክፉ እንዳልሆነ ያምን ስለነበረነና
በተገግበባረርመም ስላረጋገጠ ነው፡፡
ብዙዎቻችን ክፉ የምንለውና የሚመስለን ቢርቅ ደስተኞች የምንሆን ይመስለናል፡፡
ሁል ጊዜም ደስተኛ ሆኖ መኖር የሚፈልግ አንድ ሰው እንዲሁ መስሎት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ነገር
እንዲያደርግለትና ይህን እንዴት እንዲያስተምረውም አብዝቶ ይጸልይ ነበር፡፡ ታዲያ አንድ ቀን እግዚአብሔር ተገለጸና
ደስተኛ መሆን የሚችልበትን ነገር መማር ይችል ዘንድ ወደ አንድ ገዳም መራው፡፡ ወደ ቦታው ሲደርስ ያስተምርሃል
የተባለውን ሰው ተቀምጦ ሲለምን አገኘው፡፡ እንደ ደረሰም ወደ ለማኙ ጠጋ ብሎ ‹‹ መልካም ቀን ይሆንልህ
ወንድሜ እንደምን ዋልክ?›› በማለት ሰላምታ ይሰጠዋል፡፡ ሰውየውም ‹‹ ስለመልካም ምኞትህ አመሰግናለሁ፤ ነገር
ግን ክፉ ቀን የሚባልም አላውቅም፤ አላጋጠመኝምም›› ይለዋል፡፡ ከዚያ መመላለስ ቀጠሉ፡፡ ‹‹ስለዚህ እግዚአብሔር
ደስተኛ ሕይወትን በርግጠኝነት ሰጥቶሃላ›› ሲለው፤ ያም አባት ‹‹ እውነት ነው፤ ደስተኛ ያልሆንኩበት ጊዜ የለም፡፡
ይህን ስል ዝም ብየ ተራ ነገር እየተናገርሁም አይደለም፡፡ ምክንያቱም ምንም ምን የምበላው ባጣሁ ጊዜም ስለማጣቴ
እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በዘነበ ወይም በረዶ በወረደ ጊዜም እንዲሁ አምላኬን አከብራለሁ፤ ሰዎች በሰደቡኝ፣
ባሳደዱኝ፣ ወይም ባመናጨቁኝ ጊዜም ለእግዚአብሔር ክብር እሰጣለሁ፡፡ ያልተደሰትኩበት ጊዜ የለም የምለውም
በርግጥም ደስተኛ ስለሆንኩ ነው ፤ ይህም የሆነው እኔ የምፈልገው ባይሆንም እግዚአብሔር የፈቀደው እንዲሆን
በሕይወቴ ስለተለማመድኩ ነው፡፡ መራራም ሆነ ጣፋጭ፤ ምንም ነገር ይግጠመኝ ለእኔ መልካም መሆኑን አምኜ
ሁሉንም ከእጁ በደስታ እቀበላለሁ፡፡ ስለዚህም የማይወሰድ ደስታ ተሰጠኝ›› ሲል መለሰለት፡፡ ሊማር የመጣውም
ሰው ‹‹ ይህን ሁሉ ያደርግልህ ዘንድ ፈጣሪን (እግዚአብሔርን) የት አገኘኸው?›› አለው፡፡ ያ አባትም ‹‹
ራሴን(ትኩረቴን) ከፍጥረታት ስለይና ፈቃዴን ወደ ፈቃዱ ሳነሣ አገኘሁት›› አለው፡፡ በመልሱ እየተገረመ ያለው ይህ
ሰው በመደነቅ ‹‹ ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?›› ሲል ጥያቄውን ቀጠለ፡፡ ያ አባትም በልበ ሙሉነት ‹‹ እኔ ንጉሥ ነኝ››
ሲል መለሰለት፡፡ ‹‹ግዛትህ የት ነው?›› ሲል እንደገና እየተገረመ ጠየቀው፡፡ ‹‹ፈቲው ለእውቀት፣ እውቀትም ለፈጣሪ
በሚገዙበትና ሁሉም ነገር በሥርዓት በሚኖርበት ከተማ በነፍሴ ላይ ነው›› ሲል መለሰ፡፡ በመጨረሻ ፍጹምነት ላይ
እንደደረሰ ስለተረዳ ‹‹ ወደዚህ ፍጹምነት እንዴት ልትደረስ ቻልከ?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ያ አባትም ‹‹ በዝምታ፤
ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን ባዘወተርኩ ጊዜ ከሰዎች ጋር በዝምታ መኖርን ተለማመድኩ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር
መነጋገር ደግሞ ነፍስን በሰላም የመጠበቂያ መንገድ መሆኑን ተረድቻለሁ›› በማለት መለሰለት፡፡ በዚህ ምልልስም ያ
ሰው ክፉ የሚመስሉን ነገሮች ሁሉ ክፉ አለመሆናቸውንና ከእኛ አስተሳሰብ ወይም የእምነት ጉደለት የተነሣ እንጂ ጎጂ
የሚመስሉን ሁሉ ጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ አውቆ የእውነተኛ ደስታ ምንጩም ይህን ተቀብሎ መኖር መሆኑን
ተረድቶ ተመለሰ፡፡
በርግጥም እኛ ደካሞች ነን፡፡ ‹‹ እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥ ጌታ ግን ያስብልኛል›› /መዝ 40 ፤ 17/ ተብሎ
እንደተጻፈው እግዚአብሔር ግን ያስብልናል፤ ስለዚህም የሚጠቅመንን ነገር ያደርጋል፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ
ዳዊትም ልጁ አቤሴሎም ጦርነት በከፈተበትና በመንግሥቱ ላይ በተነሣበት ጊዜ ሸሽቶ ወደ ደብረ ዘይት ሲሻገር ሳሚ
ወልደ ጌራ መንገድ ላይ ጠብቆ ሰደበው፡፡ ‹‹... በፋንታው ነግሠሃልና እግዚአብሔር የሳኦልን ቤት ደም ሁሉ
መለሰብህ፤ እግዚአብሔርም መንግሥትን ለልጅህ ለአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቶታል፡፡ እነሆም፥ አንተ የደም ሰው
ነህና በመከራ ተይዘሃል ... ›› እያለ ሲራገም ከንጉሡ ጋር የነበረው አቢሳ ‹‹ ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን ስለምን
ይረግማል? ልሂድና ራሱን ልቍረጠው ›› ሲል ንጉሡን ጠየቀ፡፡ ቅዱስ ዳዊት ግን ‹‹ እናንተ የጽሩያ ልጆች፥ እኔ
ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? እግዚአብሔር፦ ዳዊትን ስደበው ብሎ አዝዞታልና ይርገመኝ ለምንስ እንዲህ ታደርጋለህ?
የሚለው ማን ነው? አለ›› / 2 ኛ ሳሙ 16፤ 8 - 10 / ይላል፡፡ በርግጥ ንጉሡ ዳዊት እግዚአብሔር ለሳሚ ተገልጾ
ሒድና ስደበው እንደማይል ያውቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ከፉና ውርደት የመሰለው ነገር ለእርሱ ጠቃሚ እንደሆነ
ኃጢአቱን የሚያስተሠርይለት መሆኑንና እግዚአብሔር የእርሱን ትሕትናውንም እንደሚፈልገው ስለገባው መዋረዱን
በደስታ ተቀበለው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሳሚ ተገልጦ አነጋግሮ አልላከውም፤ በሳሚ ተሳዳቢነትና በስሕተቱም
ተሳታፊ አይደለም ማለት ነገሩን እግዚአብሔር ያልፈቀደው አያሰኘውምና ፡፡ በሠራዊቱ አባላት ዘንድ እንደ መደፈርና
ከፉ የተወሰደው ስድብና ርግማን በዳዊት ኅሊና ለመልካም ነበረ፡፡ በርግጥም ለመልካም ሆነለት ፡፡ እንደ
እምነትህ(ሽ) ይደረግልህ(ሽ) ማለት ይኸው ነውና፡፡ ስለዚህ በሕይወታችን የሚገጥሙን መዋረድ የሚመስሉን፤
ስድቦች፤ ርግማኖች፣ መከራዎች፤ እስራትና ግርፋቶችም ለአንድ ክርስቲያን ክፉ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ እንዲያውም
የድኅነት፣ የክብር፣ የጸጋና የዘላለማዊ ደስታ በሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ‹‹ ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ
ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ›› /ሐዋ 5፤41/ ተብሎ እንደተጻፈው ሐዋርያት በተገረፉ ጊዜ የተደሰቱት
ክፉ የሚመስለን ሁሉ ክፉ ባይሆን ነው፡፡ እግዚአብሔርም ከመገረፍ ማዳን የማይችል ሆኖ ሳይሆን ሐዋርያቱ
እንዳሉት ነገሩን መናቅ የተገባን ብለው ስለቆጠሩት ነው የተደሰቱት፡፡ አሁን በእኛ ዘመን ካለ ክርሲቲያን
የማያጉረመርም ማን አለ? አንዲትን መከራ እንኳ ለመቀበልስ የሚፈቅድ ማን ነው? ለመሆኑ በእኛ ዘመን
እግዚአብሔር የሚወዳቸው ብለን የምንናገርላቸው ሰዎች እነማን ናቸው? በሀብት ያልተምነሸነሸ፣ በኑሮው
የማይቀማጠልን ሰው እግዚአብሔር ረዳህ እነለዋለንን? ለመሆኑ ከታመሙት ወይም ከታሠሩት ወይም ይህን የመሰለ
ነገር ከሚቀበሉት እግዚአብሔር የሚወዳቸው ያሉ ይመስለን ይሆን? በርግጥ ይህ ሁሉ የገጠማቸው ጻድቅና ፍርድ
ወይም መከራ የመማይገባቸው ናቸው ማለት አይደለም፡፡ መከራዎቹና ፈተናዎቹ በሠራናቸው ስሕተቶች ያለ
ስሕተታችንም ሊገጥሙን ይችላሉ፡፡ በሁለቱም መንገዶች ላለነው ክፉዎች አይሆኑም፡፡ በርግጥም ለምንቀበለው መከራ
የሚያበቃ ኅጢአትና በደል ፈጽመንም ከሆነ መከራው ለንስሐ፤ ለሥርየትና ለድኅነት ይሆንልናል፡፡ ባልፈጸምነውም
ከሆነ ለክብርና ለጸጋ ይሆንልናል፡፡ ሁለቱንም ማግኘት የሚቻለው ግን ስሕተት ያልሠራው እንደ ዮሴፍ እንደ ዳዊት
ለበጎ አድርጎ ሲቀበለው የበደልነው ደግሞ እንደ ፈያታዊ ዘየማን ለእኛስ በጥፋታችን ነው ይገባናል ማለት ስንችል
ነው፡፡ የማንቀበለው ከሆነ በግራ እንደተሰቀለው ሽፍታ መከራውንም ኩነኔውንም እንቀበላለን እንጂ ስለጠላነው ብቻ
አይቀርልንም፡፡ አሁን አሁን እኮ ሌላው ቀርቶ ሰዎችን እግዚአብሔር ባረካቸው የሚባልላቸው በመኪና ላይ መኪና፣
በቤት ላይ ቤት፣ በሀብት ላይ ሀብት ሲያገኙ እየሆነ ብቻ ነው፡፡ በርግጥ እንዲህ ዓይነት ነገሮችም ከመባረክ የተነሣ
ሊገኙ ይችላሉ፤ ከአሁን በፊትም በዚህ የተባረኩ ነበሩ፤ አሁንም የሚባረክላቸው ይኖራሉ፡፡ ነገር ግን ምድራዊ ሀብትና
ሹመት የበረከት መለኪያ ተደርገው ማስተማሪያዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ እኛም በመንፈሳዊ ዕውቀትም ሆነ ሕይወት
ወርደን ወርደን እዚህ ደረጃ የደረስነው ‹‹ ከፉ›› የሚመስሉን ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር መኖሩን እየተቀበሉ
ከመኖር ስለወጣንና ፈቃደ እግዚአብሔርንም በተሳሳተ መንገድ የምንተረጉም ስለሆነ ነው፡፡( ይቆየን፤ ይቀጥላል፡፡)
በብዙዎቻችን ዘንድ ከእግዚአብሔር እንዳንታረቅና ፈቃዱን በመፈጸም እንዳንኖር ከሚያደርጉን ነገሮች አንዱ ቀደም
ብለን በጠቀስነው በራስ መረዳት መጠን ነገሮችን ከወስንን በኋላ የሚከተለው እኛ የምንቃወመው ወይም የምንጠላው
ነገር እንዲጠፋ እግዚአብሔርን እንደ መሣሪያ የመጠቀም ፍላጎት ነው፡፡ ሙሴ ከጠራቸው ሰባ ሁለት ሰዎች ውስጥ
በሰፈር የቀሩት ኤልዳድና ሞዳድ በሰፈር ትንቢት በተናገሩ ጊዜ የቀናው ብላቴናው ኢያሱ ‹‹ጌታዬ ሙሴ ሆይ፥
ከልክላቸው አለው /ዘኁ 11 ፤ 28/ ሲል ሙሴን መሣሪያ አድርጎ መከልከል እንደፈለገው ወይም የዮሐንስ ደቀ
መዛሙርት ወደ ጌታ የሚሔደው ሕዝብ ወደ ዮሐንስ ከሚሔደው መብልጡ አስከፍቷቸው እንደተናገሩት / ዮሐ 3
፤30 /ብዙዎቻችን በእኛ ሀሳብ መሠረት የማይሔደው ሁሉ ምንም መልካምና ከእኛ ጋር ካለው የተሻም ቢሆን
አያስደስተንም፡፡ በዚህ ጊዜ ከላይ እንዳየናቸው ታሪኮች ከምንቀርባቸው ሰዎች ጀምሮ እግዚአብሔርንም ጭምር እንደ
መሣሪያ ተጠቅመን የሐሳባችን በላጭነት ወይም የእኛን የበላይነት ማሳየት እንሻለን፡፡ ልክ አይሁድ ጾምን ቅዱስ
ጳውሎስን ለመግደል መሣሪያ አድርገው ሊጠቀሙበት እንደሞከሩት ማለት ነው /ሐዋ 23 ፤ 14 /፡፡ በእኛም ዘመን
የነገሮቹን እውነተኛ ሁነት ሳንመረምርና የእግዚአብሔርንም ሃሳብ ሳንረዳ‹‹ እግዚአብሔር እንዲህ ቢያደርጋቸው፣
ይህን ቢጨምርባቸው፣ ... ›› እያልን ለክፋታችንና ላለማስታዋላችን እግዚአብሔርንም እንደ መሣሪያ ልንጠቀምበት
እንሻለን፡፡ በመራገም ጊዜ ብቻ ሳይሆን በስብከትና በጽሑፍም ጊዜ ለሀሳባችን የሚስማሙ ጥቅሶችን በመፈለግ
እግዚአብሔር ሀሳባችንን የሚደግፈው ለማስመሰልና ኅሊናችን ከሚያመጣብን ወቀሳ በእግዚአብሔር ቃል ለመደበቅ
የምንሽሎከለክነው ቁጥራችን ጥቂት አይደለም፡፡ ከዚህም አልፎ ያንን ሀሳባችንና ነገራችን ተመልክቶ እንደ ቀናኢነትና
እውነተኝነትም ቆጥሮ ሌሎቹን ቢያጠፋልን ወይም አንድ ነገር ቢያደርግልን ደስታውን አንችለውም፡፡ እግዚአብሔርን
እንደ መሣሪያ የመጠቀም ፍላጎት ማለትም ይኼው ነው፡፡

በእኛ ዘንድ ያለውና ከእግዚአብሔር እያራቀን ያለው ግን በእጂጉ ሌላ ነው፡፡ በእኛ ዘንድ ትዳር መሠርቶ መኖር ከሚፈልገው አንሥቶ ሥራ መቀየር
እስከሚፈልገው ድረስ ልዩ ምልክትን ማየት ይሻል፡፡ ከግብዝነታችንም የተነሣ እኛ የተውነው መሥሪያ ቤት ሲዳከም ወይም እኛ ያላጨነው ሰው
ተጎድቶ በማየት እኛ የእግዚአብሔር በመሆናችን ከዚያ እንደተረፍን በመንገር ብቃታችን ለማሳየት ስንል ይህን ዓይነት ምልክት የምንሻው እንኳ
ቁጥራችን ጥቂት የሚባል አይመስለኝም፡፡ ከዚህም የተነሣ ምልክት መሻትን ወይም ራስን አጽድቆ ማየትን የተንተራሱ ብዙ ታላላቅ ኃጢአቶችን
እንሠራለን፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ራሱን ከብዙዎች በሆነ ምክንያት ለይቶ እነርሱ ሲጎዱ እርሱ ተርፎ በማየት እግዚአብሔር ወዳጅ መሆኑን
ለማረጋገጥ የሚሻ ከሆነ ሀሳቡ ላዩን ሲያዩት ራስን የእግዚአብሔር አድርጎ የመቁ...
See More

Birhanu Admass Anleye

May 16 ·

ፈቃደ እግዚአብሔር (ክፍል ሦስት)

ባለፉት ጊዜያት ፈቃደ እግዚአብሔርን እንዳንረዳ ያደረጉንን ሁለት ምክንያቶች ተመልክተን ነበር፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ ከችግሮቹ ውስጥ ሦስቱን አቀርባለሁ፡፡ በሚቀጥለውና
በመጨረሻው ክፍል ግን ፈቃደ እግዚአብሔርን እንዴት እንደምንረዳ አይተን ጽሑፉ ይጠናቀቃል፡፡ መልካም ንባብ

3) ፈቃደ እግዚአብሔርን በራስ የመረዳት መጠን ልክ መወሰን

ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመረዳትና ለመቀበል እንድንቸገር የሚያደርገን አንዱና መሠረታዊው ችግር ደግሞ ብዙ ነገሮችን በራሳችን መረዳት መጠን የመወሰን ችግር ነው፡፡ የዚህ
ምክንያቱ ደግሞ ጥንቱንም እምነታችንም ሆነ ስለቤተ ክርስቲያናችን ያለን ግንዛቤ በእኛ ጭንቅላት ውስጥ በተወሰነው ልክ ብቻ መሆኑ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በፊት ስለ አምልኮተ
እግዚአብሔር ባሉን ዕወቀቶች ላይ ተመሥርተን ብቻ የሆነ ነገር እናደርግና ለምን የምንሻውን አይፈጽምልንም በማለት የምንጠይቅ ብዙዎች ነን፡፡ ለምሳሌ ሳዖል ንጉሠ እሥራኤል
ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን የመሥዋዕት ዓይነት በማወቁ ከተማረኩት ውስጥ ደኅና ደኅናውን ለእግዚአብሔር በማምጣቱ ብቻ እግዚአብሔርን የሚያስደስት መስሎት ነበር፡፡
ነገር ግን ምንም እንኳ ያመጣቸው እንስሳት ለመሥዋዕተ እግዚአብሔር ሊሆኑ የሚችሉ ቢሆኑምና እግዚአብሔርም መሥዋዕት የሚወድ ቢሆንም በእነዚህ ላይ ተመሥርቶ ብቻ
ፈቃዱ ይሆናል ብሎ ማቅረብ አይገባውም ነበር፡፡ ልናደርግ የምናስበው ነገር ከዚህ በፊት በሌሎች ተደርጎ የተወደደና ድርጊቱም ጥሩ ቢሆንም እንኳ በዚህ ላይ ተወስነን ብቻ
ድርጊቱን በመፈጸም ፈቃደ እግዚአብሔርን ፈጽመናል ማለት አይቻልም፡፡ አንድ ገዳማዊ አባት ‹‹ በራሴ ፈቃድ ተስቤ ከሱራፌል እንደ አንዱ መሆን ከምችል በእግዚአብሔር
ፈቃድ ከምድር ትሎች እንደ አንዱ ብሆን ይሻለኛል›› ያለው ምንም ከሱራፌል እንዳንዱ ሆኖ እግዚአብሔርን ማመስገንን የመሰለ ትልቅ ነገር ባይኖርም ፈቃዱ ካልሆነ መተውን
ያህል የተሻለ ነገር ስለሌለ ነው፡፡ የመንፈሳዊነትና የቅድስና ብቃት ትልቁ መለኪያም ሁልጊዜም በራስ ዕውቀት፣ መረዳትና ልክ ተመሥርቶ እግዚአብሔርን አስደስታለሁ ብሎ
መድከም ሳይሆን አስቀድሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነውን ለመቀበል መዘጋጀትና መጸለይ ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹ አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ
አስተምረኝ ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ ›› /መዝ 143 ፤ 10/ እያለ እንደጸለየውና በሕይወቱም በዚሁ ሲመራ እንደኖረው እርሱን መምሰል ተገቢ ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላካችንም ‹‹እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ ›› /ሐዋ 13 ፤22/ ሲል የመሰከረለት ዳዊት ከራሱ ሀሳብና
ዕውቀት ወጥቶ የሚፈጸመውን ሁሉ በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ ተመሥርቶ ይፈጽም ስለነበረ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በደማስቆ ጎዳና በተአምራት ከተመለሰ በኋላ ‹‹
ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?›› /ሐዋ 9 ፤ 6/ ሲል የጠየቀው ትልቁ ነገር የራስ ፈቃድን ትቶ የእግዚአብሔር የሆነውን መከተል ስለሆነ ነው፡፡ ጌታም ‹‹ይህ
በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነው ›› /ሐዋ 9 ፤ 15/ ሲል ያዘጋጀውና የመሰከረለት ሰው የራሱን ፈቃድ ትቶ
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም ከተነሣሣ ከዚህ የሚበልጥ ምንም ዓይነት ውድ ሥጦታ ስለሌለ ነው፡፡ አንድ ሰው የራሱን ፈቃድ ከተወ ያልቶወውና የቀረለት ምንም ነገር
የለምና፡፡
በሕይወታችን ውስጥ በሀብት፣ በሥልጣንና የመሳሰለው በጎ ነገር በገጠመን ጊዜ የሆነልንን ወይም የተደረገልንን ነገር ፈቃደ እግዚአብሔር ነው ብሎ ለመቀበል አንቸገርም፡፡
በእንዲህ ያለው ጊዜ ማንም ኃጥእ ቢሆን ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመቀበል አይቸገርም፡፡ ከባድ የሚሆነው በመከራ፤ በድህነትና በውርደት ወይም በሕማምና በችጋር ውስጥ
ስንሆን ነው፡፡ ከባድ ሊሆን የሚችልበት ምክንያት ደግሞ እኛ ነገሮችን የምንለካው በራሳችን ዕውቀት ላይ መመሥራችንና ከግንዛቤያችንም ድንበር ፈቀቅ ለማለት እንኳን ዝግጁ
ባለመሆናችን ነው፡፡ ቅዱሳንን ከእኛ የተለየ የሚያደርጋቸውም በመከራና በፈተና ጊዜ ሰውነታቸው ሳይሰቀቅ፣ ፊታቸው ሳይከፋና ልቡናቸው ሳያዝን ልክ በጎውን ሁሉ
በሚቀበሉበት መጠን ክፉውንም ለመቀበል መቻላቸውና ከዕወቀታቸውና ከግንዛቤያቸው በላይ የሆነውን ሁሉ ‹‹ ፈቃዱ ነው›› ብለው የመቀበላቸው ብርታት ከፍተኛ መሆኑ
ነው፡፡ አንድ አባትም ‹‹ በማግኘትና በደስታ ጊዜ ከሚቀርብ ዕልፍ ዝማሬና ምስጋና ይልቅ በፈተናና በመከራ ጊዜ የምትቀርብ አንዲት ተመስገን እጂግ ታላቅ ዋጋ አላት›› ያሉት
ለዚህ ነበር፡፡
ከራስ ዕውቀትና ግንዛቤ ተጽእኖ ተላቅቆ ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑን መቀበል እንደምንናገርለት ቀላል አይደለም፡፡ እንኳን እኛና በተጥባበ ነገር የተሞላ ጭንቅላት ያለን የዚህ
ዘመን ክርስቲያን ነን ባዮች ደካማ ሰዎች ቀርቶ ጌታችን ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ የተማሩትና ተአምራት ለማድረግና አጋንንትን ለማስወጣት በቅተው የነበሩት ሐዋርያት
እንኳን ተቸግረው ነበር፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን በአይሁድ እጅ ተላልፎ እንደሚሰጥና እንደሚሞት በገለጸበት ጊዜ ‹‹ ጌታ ሆይ አይሁንብህ›› በማለቱ ‹‹ ወደ ኋላዬ
ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል›› /ማቴ 16 ፤23/ ተብሎ የተገሰጸው ቅዱስ ጴጥሮስ ፈቃደ እግዚአብሔርን በራሱ
መረዳት ወስኖ በማሰቡ ነበር፡፡ በፈቃዱ ሊቀበላት ያላትን የሞት ጽዋ ይቀበል ዘንድ በምሴተ ሐሙስ ተላልፎ በአይሁድ እጅ በሚያዝበት ዕለትም ቀናኢው ቅዱስ ጴጥሮስ ሰይፍ
አንሥቶ የማልኮስ ጆሮ እስከመቁረጥ ደርሶ ነበር፡፡ ቀድም ብለን ካየነው ከዚያ ተግሣጽ በኋላም ይህን ያደረገው ነገሮችን በራሱ ዕውቀት ላይ ተመሥርቶ ከማድረግ ገና ነጻ
ስላልወጣ ነበር፡፡ጌታም ‹‹ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ። ወይስ አባቴን እንድለምን እርሱም አሁን ከአሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበዙ
መላእክት እንዲሰድልኝ የማይቻል ይመስልሃልን? ›› /ማቴ 26 ፤ 52-53/ ሲል የመለሰለት ቅንዓቱን ጠልቶበት ሳይሆን እንዲህ ያለ በጻድቅና በእውነት ላይ የሚደረግ ክፉ
ነገርም ብታዩ ፈቃደ እግዚአብሔር ከሆነ ተቀበሉት፤ በተሳሳተ መንገድም አትመልሱ ለማለት ነው፡፡ በርግጥም ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንደነገረው ግፍና መከራ በምንም መንገድ
እንዳይፈጸሙ መከላለከል ብቻ ጠቃሚና አስተማማኝ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ሰዎች እስኪነግሩት የሚጠብቅ ሊሆን አይችልም ፤ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዳደረገውም ሰይፋችንም
ሆነ ሌላው ነገራችንም አያስፈልገውም ነበር፡፡ እንደተጻፈውም እግዚአብሔር በዚህ መንገድ የሚደረጉትን ቢወድ ኖሮ የሰማይ መላእክት አያንሱትም ነበር፡፡ እረ አንድ መልአክም
ብቻ ይበቃው ነበረ፡፡ ነገር ግን እኛ አሁንም በራሳችን ዕውቀትና ግንዛቤ ከመታጠር ለመውጣት አቅም ስለሌለን ቅዱስ ጴጥሮስ ያን ጊዜ እንዳደረገው ያለችንን ሰይፍም ሆነ ጎራዴ
ዱላም ሆነ ምናምን ይዘን ከመንደፋደፍ አልቦዘንንም፡፡ በዚህ መንገድ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም ግን አይቻልም፡፡ ስለዚህም ከዚያ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ከፈቃደ
እግዚአብሔር እንድንለይ እያደረገን ያለው አንዱና መሠረታዊው ችግር በራስ ዕውቀትና ግንዛቤ ላይ ታጥሮ ለማገልገል መጣደፍ መሆኑን መገንዘብና ራስን በዚህ ከመታጠር ነጻ
ለማውጣት መጣር ተገቢ ነው፡፡

4 ኛ) የተለየ ምልክት መፈለግ

ፈቃደ እግዚአብሔርን በተመለከተ ውይይትም ሆነ ትምህርት በሚሰጥበት ጊዜ ተደጋግሞ የሚነሣው ጥያቄ ‹‹ ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑን በምን አውቃለሁ›› የሚለው ነው፡፡
ጥያቄው በራሱ ክፉ ባይሆንም መነሻውን ስንመረምረው ግን በብዙዎቻችን ውስጥ የሚኖር አንድ መሠረታዊ ችግርን ያመለክታል፡፡ እርሱም ፈቃደ እግዚአብሔርን በሆነ ምልክት
የማወቅ መሻት ነው፡፡ አብዛኛዎቻችን በተሳሳተ መንገድና ለተሳሳተ ዓላማ ሱባኤ እስከመግባት የሚያደርሰን በውስጣችን በስሱም ቢሆን የተደበቀው ምልክት የማየት ፍላጎት
ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ እሥራኤል ብዙ ጊዜ ምልክትን ሲሹ እንመለከታቸዋለን፡፡ በርግጥ በብሉይ ኪዳን ዘመኑ ዘመነ ረድኤት ስለነበረ ምልክት መሻት የሚያስነቅፍ አልነበረም፡፡
ምክንያቱም የሰው ዘር ገና ከኃጢአት ባርነት ነጻ ያልወጣ ስለነበር እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር መሆኑን ወይም ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑንና አለመሆኑን ለማወቅ ምልክትን
ይጠቀሙ ነበር፡፡ ለምሳሌ እሥራኤል ከአማሌቅ ጋር ጦርነት ተፋጥጠውና ፈርተው በነበሩበት ጊዜ ዮናታን ወልደ ሳዖል ለጋሻጃግሬው ‹‹ እነሆ፥ ወደ ሰዎቹ እናልፋለን
እንገለጥላቸውማለን፤ እርሱም፦ ወደ እናንተ እስክንመጣ ድረስ ቆዩ ቢሉን በስፍራችን እንቆማለን፥ ወደ እነርሱም አንወጣም። ነገር ግን፦ ወደ እኛ ውጡ ቢሉን እግዚአብሔር
በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና እንወጣለን ምልክታችንም ይህ ይሆናል ›› /1 ኛ ሳሙ 14 ፤ 8 - 10/ የሚል ምልክት እንደሚጠቀሙ ነግሮት ነበር፡፡ በርግጥም በምልክቱ
መሥራት ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑን አውቀው ጦርነት ውስጥ ገብተው አሸንፈዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የጌዴዎንን ጸምርና ጠል ምልክት የመሰሉ ብዙ ምልክቶች ተገልጸው
ይገኛሉ፡፡
በዘመነ ሐዲስ ግን ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሰው መሆን የጎሰቆለ ባሕርዩ ታድሶ የተገፈፈው ጸጋ ስለተመለሰለት አማኑኤል ተብሎ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለሆነ የተለየ ከእኛ
ጋር የመኖሩ ምልክት አያስፈልግም፡፡ እርሱ በዘመነ ሥጋዌው እንዳስተማረው ምልክትን መሻትም የከፉነትና የአመንዝራነት መገለጫዎች ሆነዋል /ማቴ 12 ፤ 39/ ፡፡ ሆኖም
ግን እስካሁን ድረስ ይህ ፍትወት ከሰው ፈጽሞ ስላልተወገደ ማድረግ የፈለግነውን ነገር የሚያረጋግጥልን ምልክት ብዙ ጊዜ እንሻለን፡፡ የፈለግነውን ባጣን ጊዜም እናዝናለን፡፡
ሌላው ቀርቶ መጥፎ ድርጊት እየፈጸሙ ነው በምንላቸው ሰዎች ላይ እንኳን አንድ መቅሰፍት ወርዶ እኛ የምንቃወመውን እግዚአብሔር የሚቃወመው ነው ለማለት የሚያስችል
ፍላጎታችን እጂግ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህንኑ ድካማችን የሚያውቅ ሰይጣንም ከዚሁ ድብቅ ፍላጎታችን ጋር ተጣጥሞ ሊተረጎም የሚችል ክስተት ሲያሳየን የእኛን ትክክለኛነት
የሌሎቹንም ስሕተትነት እግዚአብሔር ያረጋገጠልን አድርገን እንድንወስደውና ቀስ በቀስም በምልክት የምንመራ ሰዎች አድርጎ ይወስንናል፡፡ ነገሩን በቀላሉ ለመረዳት ይህን
የመሰለ ድርጊት የተደጋገመላቸውን ሰዎች መመልከቱ በቂ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ነገር የተደጋገመላቸው ሰዎች ከትንሽ ጊዜ በኋላ ራሳቸውን የበቁ አድርገው ይወስዳሉ፤ በዚህም
ሳይወሰኑ የእነርሱን ምልክት፣ መልእክትና የመሳሰለውን የማይቀበሉ ሁሉ ኃጥኣንና የእግዚአብሔርን መንገድ የሚቃወሙ ሰዎች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ ‹‹ ወዳጆች ሆይ፥
መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና ›› / 1 ኛ ዮሐ 4፥1/ የተባለውንም
ረስተው የሚመራቸውን መንፈስ እንኳ ሳይመረምሩ የማያውቁት መንፈስ ባሪዎች ሆነው ለመገዛትና ከነበሩበትና ከእውነተኛው መንገድ እስከመውጣት ይደርሳሉ፡፡ ሐዋርያው
ቅዱስ ጳውሎስ መናፍስትን መለየት ራሱ ልዩ ጻጋ መሆኑን /1 ኛ ቆሮ 12 ፤10/ ቢገልጽም መናፍስትን ለይቶ ከጉዳታቸው ለመጠበቅ የሚደረግ ነገር አይታይም፡፡ የዚህ ሁሉ
ጥፋት መነሻ ግን ምልክትን የማየት ከፍተኛ ድብቅ ፍላጎት መኖሩ ነው፤ ፈቃደ እግዚአብሔርን ላለመረዳት ዋናውና ትልቁ እንቅፋትም ይኼው ሁሉን በምልክት የማረጋገጥ
ፍላጎት ነው፡፡
በርግጥ በሐዲስ ኪዳንም ቢሆን ምንም ዓይነት ምልክትና ጠቋሚ መልእክት አልነበረም፤ ፈጽሞም አይደረግም ለማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ጴጥሮስ ቆርኔሌዎስን
ለማጥመቅ አልሔድም ብሎ እንዳያስቸግር አስቀድሞ እግዚአብሔር በራእይ ገልጾለት ነበር፡፡ /ሐዋ 10 / ይህን የመሰሉ ብዙ መገለጦችም በቅዱሳን ሕይወት ውስጥ ይገኛል፡፡
እነዚህ ዓይነት ምልከቶችና መገለጦች ግን ከላይኞቹ እጂግ በብዙዉ ይለያሉ፡፡በመጀመሪያ ደረጃ ቅዱስ ጴጥሮስም ሆነ ሌሎቹ እንዲህን ዓይነት ምልክቶችን በመሻት የሚደክሙት
ድካም አልነበረም፡፡ ከዚያም አልፎ እግዚአብሔር ያደረባቸው መሆኑንና ያም ቢሆን ግን ከሥጋዊ ደማዊ ጠባያቸው ተነሥተው ሳያውቁ የእግዚአብሔርን ሥራ እንዳይቃወሙ
ወይም ደግሞ ፈቃዱን በከፍተኛው መዓርግ በብቃትም ጭምር የሚረዱ መሆናቸውን ለመግለጽ በውስጣቸው ካደረው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ የሚደረጉላቸው እንጂ ያን
ምልክት ባያዩ ግራ የሚገባቸውና የሚያደርጉትን የማያውቁ አይደሉም፡፡ በእኛ ዘንድ ያለውና ከእግዚአብሔር እያራቀን ያለው ግን በእጂጉ ሌላ ነው፡፡ በእኛ ዘንድ ትዳር መሠርቶ
መኖር ከሚፈልገው አንሥቶ ሥራ መቀየር እስከሚፈልገው ድረስ ልዩ ምልክትን ማየት ይሻል፡፡ ከግብዝነታችንም የተነሣ እኛ የተውነው መሥሪያ ቤት ሲዳከም ወይም እኛ
ያላጨነው ሰው ተጎድቶ በማየት እኛ የእግዚአብሔር በመሆናችን ከዚያ እንደተረፍን በመንገር ብቃታችን ለማሳየት ስንል ይህን ዓይነት ምልክት የምንሻው እንኳ ቁጥራችን ጥቂት
የሚባል አይመስለኝም፡፡ ከዚህም የተነሣ ምልክት መሻትን ወይም ራስን አጽድቆ ማየትን የተንተራሱ ብዙ ታላላቅ ኃጢአቶችን እንሠራለን፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ራሱን ከብዙዎች
በሆነ ምክንያት ለይቶ እነርሱ ሲጎዱ እርሱ ተርፎ በማየት እግዚአብሔር ወዳጅ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚሻ ከሆነ ሀሳቡ ላዩን ሲያዩት ራስን የእግዚአብሔር አድርጎ የመቁጠር
ስሜት ብቻ ቢመስልም በጥላው የተሸከመው ትልቅ የገዳይነት ኃጢአት አለበት፡፡ ሰውየው ይህን የሚያስበው የራሱን ብቃት ለማሳየት ቢመስለውም በዚያ የተለዩ ሆኖ የመታየት
ምልክት መሻት ግን ብቻውን አይደለም፡፡ ምንም እንኳ በዚህ ዓይነት ሀሳብ ውስጥ ገዳይ ወይም እኛ በሌለንበት አደጋውን ያደርሳል ብለን የምናስበው ሌላ አካል ቢሆንም
ሀሳቡን እያሰበ ያለው አደጋ ያደርሳል ብለን የምንስለው ራሱ ሳይሆን እኛው በመሆናችን የአደጋ ጣዩ ፈጣሪዎች እኛው ነን ማለት ነው፡፡ አደጋ ፈጣሪውን ከፈጠርነው ደግሞ
አደጋ አድራሾቹም እኛው እንሆናለን፤ በዚህም ሳናውቀው የበቃንና መንፈሳዊ የሆንን በሚመስል ሕይወት ውስጥ ገዳይነትንና ወንጀለኝነትን እናሳድጋታለን ማለት ነው፡፡ ጊዜ
የገጠማት ጊዜም በአርበኝነት ሰበብ ብቅ ብላ ሀሳቧን ወደ ገቢር የምትለውጥ ፍትወትን ትልቅ መኖሪያ ሠራንላት ማለት ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ወንጀል ዋሻ ሆና የምታገለግለው ግን
ያችው ‹‹ ምልክትን›› የመሻት ኃጢአት ናት፡፡ ይህ ችግር ደረጃው ይለያይ እንደሆነ እንጂ በዓለም ያለነውን ብቻ ሳይሆን በገዳም ከሚገኙትም ቢያንስ ጥቂቶቹን ጭምር
የሚያንገላታ መምህር ከደቀመዝሙር ጋርም የሚያላጋ ትልቅ ፈተና ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችንም እሥራኤልን በኃይልና በተግሣጽ ‹‹ዘርሽና ትውልድሽ ከከነዓን ምድር ነው
፤ አባትሽ አሞራዊ ነበረ እናትሽም ኬጢያዊት ነበረች / ሕዝ 16፥3 / የሚላቸው ምንም በአምልኮተ እግዚአብሔር ቢኖሩ በውስጣቸው ሊወጣ ያልቻለ ድብቅ የእምልኮ ጣዖትና
የጥንቆላ ፍላጎት ስላለ ነበር፡፡ አሁንም እኛ ምንም ክርስቲያን የሆንን ቢመስለንም በውስጣችን ተደብቀው የሚያንገላቱ የጥንቆላ፤ ምልክትን የመሻት፣ ያለ መንፈሳዊ ግብር ቶሎ
የመብቃት፣ የተለዩ መንፈሳዊ መስሎ የመታየትና የመሳሰሉት አደገኛ ነገሮች አሉብን፡፡ ከፈቃደ እግዚአብሔር ወጥተን የምንቀርበት ጠባብ መሳይ ሰፊ በርም ይኸው ይመስለኛል፡፡

5 ኛ) እግዚአብሔርን መሣሪያ የማድረግ ፍላጎት

ለዚህ ጽሑፍ ፈቃደ እግዚአብሔርን ላለማወቅ እንደ መጨረሻ ምክንያት የምናየው እግዚአብሔርን ለእኛ ሀሳብ መሣሪያ አድርጎ የመጠቀምን ፍላጎት ነው፡፡ በብዙዎቻችን ዘንድ
ከእግዚአብሔር እንዳንታረቅና ፈቃዱን በመፈጸም እንዳንኖር ከሚያደርጉን ነገሮች አንዱ ቀደም ብለን በጠቀስነው በራስ መረዳት መጠን ነገሮችን ከወስንን በኋላ የሚከተለው እኛ
የምንቃወመው ወይም የምንጠላው ነገር እንዲጠፋ እግዚአብሔርን እንደ መሣሪያ የመጠቀም ፍላጎት ነው፡፡ ሙሴ ከጠራቸው ሰባ ሁለት ሰዎች ውስጥ በሰፈር የቀሩት ኤልዳድና
ሞዳድ በሰፈር ትንቢት በተናገሩ ጊዜ የቀናው ብላቴናው ኢያሱ ‹‹ጌታዬ ሙሴ ሆይ፥ ከልክላቸው አለው /ዘኁ 11 ፤ 28/ ሲል ሙሴን መሣሪያ አድርጎ መከልከል እንደፈለገው
ወይም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ ጌታ የሚሔደው ሕዝብ ወደ ዮሐንስ ከሚሔደው መብልጡ አስከፍቷቸው እንደተናገሩት / ዮሐ 3 ፤30 /ብዙዎቻችን በእኛ ሀሳብ
መሠረት የማይሔደው ሁሉ ምንም መልካምና ከእኛ ጋር ካለው የተሻም ቢሆን አያስደስተንም፡፡ በዚህ ጊዜ ከላይ እንዳየናቸው ታሪኮች ከምንቀርባቸው ሰዎች ጀምሮ
እግዚአብሔርንም ጭምር እንደ መሣሪያ ተጠቅመን የሐሳባችን በላጭነት ወይም የእኛን የበላይነት ማሳየት እንሻለን፡፡ ልክ አይሁድ ጾምን ቅዱስ ጳውሎስን ለመግደል መሣሪያ
አድርገው ሊጠቀሙበት እንደሞከሩት ማለት ነው /ሐዋ 23 ፤ 14 /፡፡ በእኛም ዘመን የነገሮቹን እውነተኛ ሁነት ሳንመረምርና የእግዚአብሔርንም ሃሳብ ሳንረዳ‹‹ እግዚአብሔር
እንዲህ ቢያደርጋቸው፣ ይህን ቢጨምርባቸው፣ ... ›› እያልን ለክፋታችንና ላለማስታዋላችን እግዚአብሔርንም እንደ መሣሪያ ልንጠቀምበት እንሻለን፡፡ በመራገም ጊዜ ብቻ
ሳይሆን በስብከትና በጽሑፍም ጊዜ ለሀሳባችን የሚስማሙ ጥቅሶችን በመፈለግ እግዚአብሔር ሀሳባችንን የሚደግፈው ለማስመሰልና ኅሊናችን ከሚያመጣብን ወቀሳ
በእግዚአብሔር ቃል ለመደበቅ የምንሽሎከለክነው ቁጥራችን ጥቂት አይደለም፡፡ ከዚህም አልፎ ያንን ሀሳባችንና ነገራችን ተመልክቶ እንደ ቀናኢነትና እውነተኝነትም ቆጥሮ
ሌሎቹን ቢያጠፋልን ወይም አንድ ነገር ቢያደርግልን ደስታውን አንችለውም፡፡ እግዚአብሔርን እንደ መሣሪያ የመጠቀም ፍላጎት ማለትም ይኼው ነው፡፡ እንዲህ ያለው ነገር
ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ለዚህ ዓለም የሚመች ቢሆንም ( እንደ መሠልጠን ወይም እንደ ሁሉን አወቅም ሊያስቆጥር ይችላል) ለመንፈሳዊ ሕይወት ግን ጠቃሚ አይደለም፡፡ ‹‹
ነገር ግን ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍ ራቅ፤ ኃጢአተኝነታቸውን ከፊት ይልቅ ይጨምራሉና፥ ቃላቸውም እንደ ጭንቁር ይባላል፤ ›› /2 ኛጢሞ 2፥16/ ሲል
እንደገለጸው የዚህ ዓይነት አገላለጽ እንደ ጭንቁር የሚባላ እንጂ እግዚአብሔርን የሚያስደስት ነገር አይደለም፡፡ ሳናውቀውም ቢሆን ‹‹ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት
እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ›› /ዮሐ 3 ፤ 15/ ተብሎ ከተገለጸውና እግዚአብሔር ለኃጥአን ካለው
ፈቃድ ጋር እንጋጫለን፤ የእግዚአብሔርንም የማዳን ሀሳብ እንቃወማለን፡፡ በዚህም ምክንያት ዋናውን እግዚአብሔር ለዓለም ወይም ለኃጥኣን ካለው ሀሳብ ወይም ፈቃድ
መቃወም ስለምንጀምር በየትኛውም መንድ ከእግዚአብሔር ፈቃድ እየወጣን እንሔዳለን፡፡ ቀደም ብለን እንዳየነውም የዚህ ሁሉ መሠረታዊ ምክንያቱ እግዚአብሔርን ለሀሳባችን
እንደመሣሪያ ለመጠቀም ካለን ፍላጎት የሚመነጭ ነው፡፡ሌላው ቀርቶ ሱባኤ በተሳሳተ መንገድ እስከመግባት የሚያደርሰን ይኼው እኛ ከምንፈልገው አንጻር እግዚአብሔርን አንድ
ነገር አድርጎ የማየት ችላጎታችን ታላቅ በመሆኑ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ነገር ግን ቀደም ብለን ካየነው አይሁድ ቅዱስ ጳውሎስን ለመግደል እንደ ጾሙት ያለ ጾምና ሱባኤ ነው፡፡
በአጭሩ የእግዚአብሔርን ስም እየጠሩና ለቤቱም በሚደረግ ቅንዓት የሚያንቦገቡጋቸው ሀሳቦች ውስጥ ሌላውን የማጥቃትና የማሰደድ ሀሳቦችን መሰንዘር ለድክመታችን ወይም
ከአእምሮ ወቀሳችን ለማምለጥ እግዚአብሔርን መሣሪያ ማድረግ እንጂ የእግዚአብሔር መሆናችንን አያሳይም፡፡ ይልቁንም በዚህ ሰበብ ሳናውቀው የእግዚአብሔርን ፈቃድ
እንቃወማለን፡፡ ታዲያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት እናውቃለን? የጽሑፋችን መጨረሻ የሆነውንና ፈቃዱን የማወቂያ መንገዶቹን በሚቀጥለው እትም እናያለን፤ ይቆየን፡፡

Birhanu Admass Anleye

3 hrs ·

ፈቃደ እግዚአብሔር ( ክፍል አራት ፤ የመጨረሻ ክፍል)

የእግዚአብሔርን ፈቃድ በምን አውቃለሁ? የሚለው ጥያቄ በራሱ በእኛ ውስጥ የተለየ ምልክት መሻት መኖሩን
ያመለክታል፡፡ ይህን ዐይነት ምልክትን የመሻት አካሔድ ደግሞ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ባለፈው
ጊዜ በሦስተኛው ክፍል ጽሑፍ አይተን ነበር፡፡ ለቅዱሳን የሚደረገው መገለጥ ራሱ ቅዱሳን ራሳቸውን ክደው ሙሉ
በሙሉ ማንነታቸውን ለእግዚአብሔር ስለሰጡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ማለትም መጻኢው ቀድሞ በእነርሱ የሚገለጸው
የደረሱበትን መዓርግ ለማሳየት ነው እንጂ በእያንዳንዱ ነገር ላይ ምልክትን እየሻቱ ያም እየተደረገላቸው አይደለም፡፡
ታዲያ እኛ ኃጥአኑና ደካሞቹ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ይህን ጥያቄ ለመረዳት አስቀድመን
ስለ ፈቃደ እግዚአብሔር ሦስት መሠረታዊ ነጥቦችን እንመለከታለን፡፡

ሀ) የእግዚአብሔር ፈቃድ በራሱ ሁለት ዓይነት ነው

የመጀመሪያውና ዋናው እግዚአብሔር ለፍጥረቱ በአጠቃላይ ሊታይ የሚችለውና ስለሁላችን ያለው ፈቃድ ነው፡፡
ይህንንም ‹‹ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው›› / ዮሐ 6
፤ 40/ ሲል በወንጌል ገልጾልናል፡፡ ከነገረ ድኅነት ጋር ባናያይዘውም እግዚአብሔር በዓለም ያለው ፈቃድ የሁላችንም
ደኅንነት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን የፐርሻውያን ትልቅ ከተማ ወደነበረችው ወደ ነነዌ ነቢዩ ዮናስን ከላከው
በትምህርቱ አምነውና ጾመው ከዳኑ በኋላ ነቢዩ ዮናስ ሲቆጣ በመጀመሪያ እግዚአብሔር አንዲት ቅል አብቅሎ
መጠለያ በመስጠትና በማስጠለል ደስ አሰኘው፡፡ ነገር ግን ወዲያውኑ በማድረቅ ደግሞ አበሳጨው፡፡ ዮናስም በሐዘንና
በንዴት ሆኖ እግዚአብሔር ለምን ይህን እንደሚያደርግ ሲጠይቀው ‹‹ እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ
ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን? አለው›› /ዮና 4፤11/
ተብሎ እንደተጻፈው እግዚአብሔር በሕግ በአምልኮ ለማይኖሩ ሕዝቦች እንኳ ፈቃዱ ሁልጊዜም መዳናቸው ብቻ
ነው፡፡ ቢቻልና የእግዚአብሔር መንግሥት ቢሰበክላቸው በነፍሳቸውም ቢድኑ ደስ ይለዋል፤ ካልሆነ ከመቅሰፍትና
ከጥፋት ቢድኑም ደስ ይለዋል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ለየትኞቹም ሰዎች ያለው ፈቃድ መዳናቸው መሆኑን
መረዳት ተገቢ ነው፡፡ በዚህ ታሪክ ላይ እግዚአብሔር ያደርገው ዘንድ ዮናስ ይፈልገው የነበረው ከእግዚአብሔር
ፈቃድ ምን ያህል የራቀ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡

ሁለተኛው ፈቃዱም ለእያንዳንዳችን በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ላይ ያለው ፈቃዱ ነው፡፡ ይህም ቢሆን ድኅነታችንን
የሚያስቀድም ነው፡፡ ድኅነታችን የሚያስቀድም ነው የሚባለውም መከራ፣ ስደት፤ እስራና ሞትም ጭምር እንኳ
እንዲመጣ ፈቃዱ ቢሆን በእኛ በሚደርሰው የሚደሰት ሆኖ ሳይሆን ከዚያ ነፍሳችን ልታጭደው የሚገባውን ምሕረትና
ይቅርታ ወይም ማስተዋል በማሰብ ነው፡፡ ‹‹አካዝያስም ወደ ኢዮራም በመምጣቱ ይጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ
ነበረ ›› /2 ኛ ዜና 22 ፤ 7/ ወይም ‹‹ የኤዶምያስንም አማልክት ስለ ፈለጉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ይሰጣቸው
ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበረና›› / 2 ኛ ዜና 25 ፤ 20/ ተብሎ እንደተጻፈው እግዚአብሔር ሰዎችን
ለመቅጣትም ሆነ ለማጥፋት ፈቃዱ የሚሆንበት ጊዜ አለው፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ቀደም ብለን ባየነው
አጠቃላዩንና ዋናውን የእግዚአብሔር ፈቃድ በመቃወም የሚሠሩትን አስወግዶ አብዛኞቹን ለማዳን ፈቃዱ ስለሚሆን
ነው፡፡በታሪክ እንደ ታየው እንደ ዘመነ ኖኅ ሰዎች የጎሰቆለውን ሁሉ አስወግዶ አዲስ ትውልድ ያስነሣል፤
እሥራኤልንም ብትንትናቸውን አውጥቶ ለሁለት ሺሕ ዘመን ያለ ሀገር ያኖራቸው እነርሱን ለመበቀልና በጥፋታቸውም
ስለሚደሰት ብቻ አይደለም፡፡ በመጀመሪያ እንዲህ ያደረጋቸው ‹‹ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን›› ብለው
በራሰቸው ላይ ፈርደው ወድደው ፈቅደው መከራውን ራሳቸው ስለጠሩት ነው፡፡ ዳግመኛም እነርሱ ከዚያች ምድር
ባይርቁ ኖሮ የክርስትና ተአምራት የተፈጸመባቸውን ቦታዎች ሁሉ አጥፍተው ሐዋርያትንም ገድለው ክርስትናን ሐሰት
ለማስመሰል ይጥሩ ነበር፡፡ ቅዱስ ያዕቆብን አስገድለው እስጢፋኖስን ወግረው ገድለው ቅዱስ ጴጥሮስን ሊጨምሩ
ሲሉ መልአኩ በሌሊት ከእስር ቤት አወጣው /ሐዋ 12/፡፡ ቅዱስ ጳውሎስንም ሳንገድል አንበላም ብለው ተማምለው
ሳሉ እርሱ የሮም ዜግነት ስለነበረው ገዢው ፈርቶ ወደ ሮማ ላከውና በጥበበ እግዚአብሔር ተረፈ፡፡ ሌሎች
ብዙዎችንም ገድለዋል፡፡ ስለዚህም ጌታ እርሱ ባወቀ በራሳቸው ላይ የፈረዱትን ፍርድ ተቀብሎ አጠፋቸው፤
በታተናቸውም፡፡ በዚህም ምክንያት ያውና እስከዛሬ ድረስ ተአምራቱ የተፈጸመባቸው ቦታዎች እየተጎበኙ ዓለምም ላይ
ክርስትና እንዲሠፋ ተጨማሪ ምክንያት ሆኖአል፡፡ ስለዚህ መሰደዳቸውና መጥፋታቸው ብቻ ሳይሆን ቀደም ብሎም
ከኢየሩሳሌም እስከ ሰፔንና ፖርቱጋል ከሰሜን አውሮፓ እስከ ሰሜን አፈሪካ ድረስ ተንሠራፍቶ የነበረው የሮም
ግዛትም እንዲህ እንዲሆን እግዚአብሔር የፈቀደው በጊዜው ክርስትናን ለማስፋት እንዲያገለግል ነበር፡፡ ስለዚህ
በተናጠል ለእያንዳንዳችን ያለው ፈቃዱም ምንም ዓይነት ቢሆን ለሰው ልጅና ለዓለማችን ጥቅም ካለው ፈቃዱ
የማይቃረንና ሁልጊዜም ፍጹም መሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡

ለ) የእግዚአብሔር ፈቃድ አይለዋወጥም

ለእግዚአብሔር ለባሕርዩ ለውጥ አይስማማውም፡፡ የሚለወጥ አምላክ አይደለም፡፡ /ሚል 3፤ 6/ ከዚህ ባሕርዩ
የተነሣም ፈቃዱ አይለወጥም፡፡ ምክንያቱም ካለማወቅ ወደ ማወቅ የሚያደርሰውና ፈቃዱን ሊያስለውጠው የሚችል
ምንም የለምና፡፡ ፍርዱ የተለወጠ ቢመስል እንኳ ፈቃዱ የሚለወጥ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ቀደም ብለን በገለጽነው
በነነዌ ሰዎች ታሪክ ውስጥ ነቢዩ ዮናስን ‹‹ነነዌ እስከ ሦስት ቀን ትገለበጣለች›› እያለ እንዲያስተምር ልኮታል፡፡ ነገር
ግን ቶሎ በምሕረት አይቷቸዋል፡፡ ይህ የሆነው ፈቃዱ ጥንቱንም መዳናቸው ስለነበረ ነው እንጂ የሚሆነውን ሳያውቅ
ከወሰነ በኋላ እንደሚጸጸት ግለሰብ የሆነ አይደለም፡፡ የንጉሥ ሕዝቅያስን ትሞታለህ ካለው በኋላ ዕድሜውን በ 15
ዓመት ጨምሮለታል፡፡ ይህ እንዲሆን ቀድሞ ፈቃዱ ነበረ፤ ነገር ግን ይምረውና ዕድሜ ይጨምረው ዘንድ እውነተኛ
ንስሐ መግባት እንዲችል ነበር ‹‹ትሞታለህ እንጂ አትድንም›› ሲል የላከበት፡፡ በርግጥ እንዲሞት ብቻ ቢፈልግ ኖሮ
ሳይልክበት ይገድለው ነበርና፡፡ ስለዚህ እነዚህን የመሰሉና ለእግዚአብሔር ተጸጸተ ተብሎ እንኳን ብናነብ የውሳኔ
ለውጥ የሚመስሉን ነገሮች ሁሉ ጥንቱን እንዲያ እንዲሆን ለመርዳት የተደረጉ በመሆናቸው የፈቃድ ለውጥ የሚባሉ
አይደሉም፡፡ ቀደም ብለን እንዳየነውም እንዲያውም ዋናውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ድኅነትን ቀዳሚ ያደረገ መሆኑን
የሚያረጋጡ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለዕብራውያን ሰዎች በላከው መልእክት ‹‹ስለዚህም
እግዚአብሔር፥ የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ፥ እግዚአብሔር
ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት
ይሆንልን ዘንድ፥ በመሓላ በመካከል ገባ፤ ›› / ዕብ 6፥17-18/ ሲል ያረጋገጠልን ይህንኑ ነው፡፡ ስለዚህ
በሕዝቅያስ፣ በነነዌ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር የተላከባቸው መልእክት ሞት ሊያመጣ የሚችል ኃጢአት
መሥራታቸውን አውቀውና ንስሐ ገብተው እንዲድኑ ፈቃዱ ስለነበረ እንጂ ፈቃዱ ተለዋዋጭ ስለሆነ አይደለም፡፡
ነገሮች እንዲለዋወጡ መፍቀዱ የራሱ ፈቃድ መለዋወጥ አይደለምና፡፡

ሐ) ስለነገ ማወቅ ፈቃደ እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት አይደለም

ብዙዎቻችን ፈቃደ እግዚአብሔርን ማወቅ አድረገን የምንወስደው ስለነገ ሕይዎታችን ቀድሞ ቢያሳውቀን ብለን
የምናስበውን ነገር ነው፡፡ በዚህ መንገድ የሚገለጽላቸው ሰዎች ነቢያት ይባላሉ፡፡ አንድን ነገር ከመደረጉ በፊት
እግዚአብሔር ነገሩን አስቀድሞ ገልጾላቸዋልና፡፡ ምንም እንኳ ነቢያት ፈቃደ እግዚአብሔርን ቢያውቁም የሚሆነውን
ማወቅ ግን ፈቃደ እግዚአብሔርን ማወቅ አይደለም፤ ሊሆንም አይችልም፡፡ ለምሳሌ ነገሩ ለመደረጉ የእግዚአብሔር
ፈቃድ ቢሆንም ቀድሞ ማወቅ ቀድሞ ማወቅ ብቻ እንጂ ፈቃደ እግዚአብሔርን ማወቅ ሊሆን አይችልም፡፡ በርግጥ
ቀድሞ ማወቅ ፈቃደ እግዚአብሔርን ለማወቅ አስተዋጽኦ የለውም ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ቀድመው አውቀውም
ፈቃደ እግዚአብሔርን ረስተው ወይም ጠልተው የሚጠፉ ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ይሁዳ የእግዚአብሔርን የሥጋዌ
ዓላማ ምን እንደሆነ ያውቅ ነበር፤ ራሱን ለማዳን ግን አልቻለም፡፡ እንዲያውም ጌታን አሳልፎ የሚሰጥ ባይወለድ
ይሻለው ነበር ሲባል ሁሉ ነበረ፤ ይህን ሁሉ ማወቁ ግን ራሱን ከፈቃደ እግዚአብሔር ጋር አንድ እንዲያደርግ
አልረዳውም፡፡ ለጌታችን ሞቱ በፈቃዱ የተደረገ ቢሆንም ይሁዳ አሳልፎ የሰጠው ሊቃነ ካህናትም የሰቀሉት ዓለሙን
ያድን ብለው ስላልሆነ ከፈቃደ እግዚአብሔር በተቃራኒው እንዳሉ ለመረዳት አያዳግትም ፡፡ ስለዚህ መጻኢውን ማወቅ
ሁሉ ፈቃደ እግዚአብሔርን ማወቅና በዚያም መኖር ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡ ይህ የሚሆነውም ስለ ሁለት
መሠረታዊ ምክንያቶች ጭምር ነው፡፡ የመጀመሪያው የሚሆነው ነገር ሁሉ አስቀድሞ ሊታወቅ ቢችልም የተወሰነበትና
እንዲሆን እግዚአብሔር አድራጊውን የሚያስገድድበት ስላልሆነ ነው፡፡ ይህም ቀደም ብለን ባየናቸው ክፍሎች ውስጥ
ተደጋግሞ እንደተገለጸው እግዚአብሔር የክፉዎችን ክፋት ባይወድም ያሰቡትን ከማድረግ ወይም ነጻ ፈቃዳቸውን
ከማድረግ አይከልክላቸውም፡፡ ስለዚህ ነገሩ የሚፈጸም መሆኑን ቀድሞ ቢገልጸው ደርጊቱ መፈጸሙን ይወድዳል
ማለት አይደለም፡፡ ሆኖም ተጎጂ የምንለው አካል የእግዚአብሔር ፈቃዱ ነው ብሎ ተቀብሎ ከዚያ በረከትን ማጨድ
ይችላል፡፡ሁለተኛው ደግሞ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ያለው ውሕደት የሚመሠረተው እኛ ትእዛዙን ለመፈጸም
በምናደርገው ፈቃደኝነት ላይ እንጂ መጻኢውን ለማወቅ በምናደርገው ሩጫ ላይ ስላልሆነ ነው፡፡

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መኖር እንዴት እንችላለን?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ካስተማራቸው መሠረታዊ ትምህርቶች ውስጥ አንዱ
በፈቃደ እግዚአብሔር መኖር ምን እንደሆነ ያስተማረው ትምህርት ነው፡፡ ‹‹ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው
ሁለት ልጆች ነበሩት፤ ወደ አንደኛው ቀርቦ፦ ልጄ ሆይ፥ ዛሬ ሂድና በወይኔ አትክልት ሥራ አለው፡፡ እርሱም መልሶ፦
አልወድም አለ፤ ኋላ ግን ተጸጸተና ሄደ፡፡ ወደ ሁለተኛውም ቀርቦ እንዲሁ አለው እርሱም መልሶ፦ እሺ ጌታዬ አለ፤
ነገር ግን አልሄደም። ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ ያደረገ ማን ነው? ፊተኛው አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት
እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል›› /ማቴ 21 ፤ 28 -
31/ ሲል አይሁድን በምሳሌ ያስተማረው ቅዱሳት መጻሕፍትን ተሸክመው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለሚቃወሙ
ነበር፡፡ በጥቅሱ ከተገለጸው እንደምንረዳው የእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱሳት መጻሕፍት ተገልጾ ነበር፡፡ ነገር ግን ጌታ
እንዳለው ቀራጮችና ጋለሞቶች ለጊዜው ባይቀበሉትም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም ኅሊናቸው ይታዘዛል፤
ስለዚህም ቃሉን ከምናውቀውና በነገር ከምንራቀቀው ሁሉ ቀድመው ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር ይገባሉ፡፡
‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት
የሚገባ አይደለም›› /ማቴ 7፤21/ ‹‹ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ
አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም›› /ማቴ 10 ፤ 29/ ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ
ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ›› /ማቴ 12 ፤ 50/ የሚሉት ጥቅሶችም ጌታችንን ፈቃዱን አውቀን
እየፈጸምን እንድንኖር የሚሻ መሆኑን ደጋግሞ ከገለጸባቸው ትምህርቶቹ ውስጥ ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው፡፡ ታዲያ
ፈቃዱን እንዴት ልንፈጽም እንችላለን?

1) ፍቅረ እግዚአብሔርን ገንዘብ ስናደርግ

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመረዳት እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ በፍጹም ኃይልና በሁለንተና መውደድ ይጠይቃል፡፡
እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው ደግሞ የእግዚአብሔር ለሆነው ሁሉ ክብርና ፍቅር ይሰጣል፡፡ ፍቅርም ማለት ፍቅሩ
አለን በሚሉ አካላት መካከል የፈቃድ ስምምነት ላይ መድረስ ወይም የአንዱን ፈቃድ አንዱ መቀበል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ አንድ ሰው ፈቃደ እግዚአብሔርን ወደ መረዳት ልደግ ካለ የእግዚአብሔርን ቃል በአግባቡ እየፈጸመ መኖር
የመጀመሪያው ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ጌታ ‹‹የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቅ›› ነው ያለው፡፡ ቃሉን ሲጠብቅ
በፍቅርና በመታዘዝ ከሆነ የራሱን ፈቃድ መተው ይለምዳል፡፡ ምክንያቱም ‹‹ ጠላታችሁን ውደዱ›› የሚለውን ቃል
ቀርቶ ‹‹ ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ›› ከሚለውና በምስጢር ባይራራቁም ከዚህ ወዳጅን እንደ ራስ
አድርጎ ከመውደድ እንጀምረው ብንል እንኳ ምን ያህል በውስጣችን ያሉ ፍላጎቶችን መተው እንዳለብን መረዳት
እንችላለን፡፡ ቢያንስ በዚህ መንገድ የምንጓዝ ከሆነ ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመረዳት መንገዱን ጀምረነዋል ማለት
ነው፡፡ ምክንያቱም ፈቃደ እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ጠንቋይ እንደሚያደርገው በዝርዝርና በየዕለቱ
የሚነገረን ነገር አይደለም፤ ሊሆንም አይችልም፡፡ ቀደም ብለን እንዳየነው በጎውም ይሁን ክፉ የሚመስለን ነገር
ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ብለን ለማመን የምንችለው በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈውን ለመፈጸም ሰንጣጣር ነው፡፡
ካልሆነ ቅዱስ ያዕቆብ ‹‹አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር
የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው ›› /ያዕ 1 ፤ 26/ ሲል እንደገለጸው አምልኮታችን ሁሉ የእልህና የጥላቻ ይሆንብናል፡፡
የፈለገ ያህል ለእግዚአብሔር ቀንተን ነው ብንል የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እየተላለፍንና በራሳችን መሻት መሠረት ብቻ
የምናደርገውን ሁሉ እኛ አምልኮት ስላልነው እግዚአብሔር ይቀበለዋል ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር መጀመሪያ
የሚፈልገው ትዕዛዙን እንድንጠብቅለት ነው፡፡ ሌሎቹን በጉልበታችን ልናስጠብቃቸው አንችልም፡፡ አሁን ችግር
የሆነው እኛ የማንሽረውን የሻሩ የመሰሉንን ሰዎች አሻግረን እያየን በመበሳጨታችን ብቻ እግዚአብሔር ያን ጊዜ ያለንን
ቅንዓታችንን አይቶ ለምን አይሰማንም ማለታችን ነው፡፡ አይሁድ ጌታችን በሚያሰተምርበት ጊዜ መጥተው እናትህና
ወንድሞችህ በውጭ ቆመዋል ብለው በመናገራቸውም ለእርሱ የሚያስቡና የሚያስደስተውም ይመስላቸው
እንደነበረው ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለእርሱ የሚያስቡ እንኳ ቢሆኑ ይህን የሚያውቀው እነርሱ ስለነገሩት
አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ወዳጅና ባለሟል መሆን የሚቻለውም ቃሉን በመስማትና ትእዛዙን በመጠበቅ እንጂ
ለእርሱ ያሰቡ መስሎ በመኖር አይደለም፡፡ ስለዚህ ከእኛ መጀመሪያ የሚጠበቀው ቃለ እግዚአብሔርን እየሰሙ በፍቅረ
እግዚአብሔር መኖር ነው:፡
2) ተነሣሒ መሆን

‹‹እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኃጢአተኞችን
እንዳይሰማ እናውቃለን›› /ዮሐ 9 ፤ 31/ ተብሎ በቅዱስ ወንጌል እንደተገለጸው እግዚአብሔር የኃጥአንን ጸሎት
አይሰማም፡፡ ይህም የተባለው ኃጢአተኞችን ስለሚጠላ ሳይሆን ተነሳሒነትን ስለሚሻ ነው፡፡ እንደዚያማ ባይሆን ኖሮ
ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ይበላል ተብሎ እስኪከሰስ ድረስ እነርሱን አይወድም ነበረ፡፡ ከእነርሱም ጋር የሆነው
ግን በተነሣሒነታቸውና ትእዛዙን ለመጠበቅ ባሳዩት ፈቃድ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይህ ነውና፡፡ ሳምራዊቷን
ሴት ሲያስተምርና ሲፈውስ ደቀመዛሙርቱ ወደ ከተማ ሔደው ነበር፡፡ ሲመለሱ ምግብ ገዝተው ብላ ሲሉት አልበላም
አላቸው ፡፡ በዚህ ጊዜ የእነርሱ ሐሳብ የሚበላውን ሌላ ሰው አምጥቶለት ይሆናል ነበረ፡፡ እርሱም ይህን ሀሳባቸውን
ባወቀ ጊዜ ‹‹የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው›› / ዮሐ 4 ፤ 34/ ሲል
መለሰላቸው፡፡ እግዚአብሔር ፈቃዱን‹‹ምግቤ›› ሲል የጠራው ፈቃዱ ተነሣሒነት ከዚያም በኋላ ድኅነታችን ስለሆነ
ነው፡፡ ስለዚህ እኛ በዚህ ምድር የምንኖር ኃጥአን ፈቃዱን መረዳትና እንደ ፈቃዱ መኖር ከፈለግን የመጀመሪያው
እርምጃ ሁሌም ተነሣሒ ሆኖ መኖር ነው፡፡ ከንስሐና ከመልካም ሥራ የተለየ ሰው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሊያውቅ
የሚችልበት ምንም መንገድ የለውም ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ
የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን
ዓለም አትምሰሉ›› / ሮሜ 12፤ 2/ የሚለው የእግዚአብሔር ፈቃዱ መለወጣችን ስለሆነና ባልተለወጠ ሰውነትም
ፈቃደ እግዚአብሔርን መረዳት ስለማንችል ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በእኔ ሕይወት ላይ ያለው ፈቃዱ ምንድን
ነው የሚል ሰው ቢኖር በእውነት ንስሐ ይግባ፤ የእግዚአብሔር ትልቁና የመጀመሪያው ፈቃዱ ንስሐ መግባታችንና
መዳናችን ነው፡፡ ይህ መሆን እስከቻለ ድረስ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ያለውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ለመረዳትም
ሆነ ለመቀበል አይቸግረንም፡፡
ለምሳሌ ያህል ብዙ ወጣቶችን በአሁኑ ጊዜ እያስጨነቀ የሚገኘው የማንን ላግባ ጥያቄ መልሱ የሚገኘው በምልክትና
በራዕይ አይደለም፡፡ ብዙዎች በዚህ ጥያቄ የሚታወኩት ራሱ በተሳሳቱ አስተሳሰቦች ላይ ተመሥርተው ስለሚሔዱ
ነው፡፡ ከእነዚህ የመጀመሪያው ራስን የእግዚአብሔር ሳያደርጉ የእግዚአብሔርን ሰው መሻት ነው፡፡ እግዚአብሔር
በምሪት ያገኛኛቸውን የብሉይ ኪዳን አባቶች ታሪክ እንኳ ብናየው እግዚአብሔር እንዲያገናኛቸው ምክንያት የሆነው
ሁለቱም የእግዚአብሔር በመሆናቸው ብቻ ነው፡፡ ርብቃ ለይስሐቅ /ዘፍ 24/ ሣራ ወለተ ራጉኤል ለጦብያ ወልደ
ጦቢት የተዘጋጁበትን መንገድ እግዚአብሔር የራሱን ሰዎች እንዴት በሁሉ ነገር እንደሚመራና እንደሚጠብቅ
መመልከት እንችላለን፡፡ ራሱን በንስሐ ሕይወት ሳያኖርና እንደ ቃሉ መመላለስ የማይወድ ሰው ከእግዚአብሔር
በመጠየቁ ብቻ ምን ሊያገኝ ይችላል? ራሱን በሌላ ዓለም የሚያኖር ሰው መልአክ የመሰሉ ሰዎችን በመሻቱ ብቻ
እንዴት እግዚአብሔር ሊሰማው ይችላል? እግዚአብሔር መልአክ የመሰለ ሰው እንዲሰጠው የሚፈልግ ራሱን መልአክ
ማድረግ እንኳ ባይችል ቢያንስ ራሱን ከመልአክ ጋር ለመኖር የሚችል ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ በአጭሩ
የእግዚአብሔርን የሚሻ ሁሉ ራሱን የእግዚአብሔር ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ደግሞ የሚቻለው በንስሐ
በመለወጥና እንደ ቃለ እግዚአብሔር በመኖር ብቻ ነው፡፡

3) ምልከታ አለመሻት

የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም በሕይወታችን ለአንድ ወይም በጣም ለትንሽ ወሳኝ ጉዳዮች ብቻ የምንፈልገው
አይደለም፡፡ አንዱና መሠረታዊ ስሕተታችንም ፈቃደ እግዚአብሔርን ለኑሮአችን ወይም ለሕይወታችን በየዕለቱ
የምንፈልገው ሳይሆን ለአጽድቆተ ነገር ብቻ የምንሻው ምልክት መሆኑ ነው፡፡ ጌታ በወንጌል ‹‹የጌታውንም ፈቃድ
አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል›› /ሉቃ 12 ፤47/ ሲል ያስተማረው ፈቃደ
እግዚአብሔር በማንኛውም ሕይወታችን ውስጥ እግዚአብሔር ሲፈልገው ሊያገኘው የሚገባ ነገር ስለሆነ ነበር፡፡
የዘወትርና የማንኛውም ጸሎታችን ማሳረጊያ በሆነው የአባታችን ሆይ ጸሎት ውስጥ ‹‹ፈቃድህ በሰማያት እንደሆነ
እንዲሁም በምድር ይሁን›› እያልን እንድንጸልይ ያሰተማረን በየዕለቱ ፈቃዱን እየሻን በዚያ መሠረት እንድንጓዝ
ነበረ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ
ፈቃድ አልተወለዱም›› /ዮሐ 1 ፤13 / ሲል የገለጸው በእኛ ወይም በዚህ ዓለም ፈቃድ ሳይሆን በእግዚአብሔር
ፈቃድ ብቻ እንድንኖር መንፈሳዊ ልደት መወለዳችንን ለማሳየት ነበር፡፡ ምክንያቱም ፈቃዱን አንድ የምንፈልገው ነገር
መደረጉን በሆነ መንገድ ወይም ምልክት ለማረጋግጥ የምንሻው ብቻ ሳይሆን በየዕለቱ በሕይወታችን የምንሻው ወይም
ልንሻው የሚገባን ነገር በመሆኑ ነው፡፡ ያ ከሆነ ከመደበኛ ዕቅዳችን ውስጥ የገጠመንን ሥራ አለቃችን አውቆ
እንዲያጸድቅልን የምንፈልግበትን ነገር ይመስልብናል፡፡ እንደዚህ ከሆነ ደግሞ ለፈቃደ እግዚአብሔር ምንም የተለየ
ምልክት አያስፈልገንም ማለት ነው፡፡ ራሱ ጌታችን ሁሉን እያወቀ ራሱን ስለሁላችን አሳልፎ ሊሰጥ በቀረበባት ሰዓት
‹‹ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ›› /ሉቃ 22 ፤ 42/ ሲል
የጸለየው ምን እንደሚሆን ስለማያውቅ ወይም ሞቱን ፈርቶትና ተሰቅቆት ሳይሆን የታወቀ ነገር እንኳ ቢሆን
የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጸሎት እየጠየቁ መቀበል ተገቢ ነው ለማለት ወይም እኛ ምን ማድረግ እንዳለብን አብነት
ለመሆን ነው፡፡ እንዲያውም ከዚህም አለፍ ብሎ ‹‹ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ
ከሰማይ ወርጃለሁና ›› /ዮሐ 6 ፤38/ በማለት ያለ አብ በራሴ (ማለትም በሦስትነት ያለ ቢሆንም ፈቃድ የአንድነት
ነውና) አላደርግሁም ብሎ አርዓያነቱን ይገልጽልናል፡፡ እኛ እርሱን እንድንመስል የተጠራነው ደግሞ የራሳችን ሳይሆን
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ብቻ እንድንፈጽም ነው፡፡

በሕይወታችን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እየተለማመድንና እርሱንም ለማድረግ የምንሻ ከሆነ ፈቃደ እግዚአብሔርን
ለማወቅም ሆነ ለመቀበል አንቸገርም፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ነንና ፈቃዱን እየጠየቅን በቃሉም እየኖርን መልካም ይሆናል
ብለን የምናስበውን ከሠራን በኋላ የሚሆነውን ሁሉ ለመቀበል አንቸገርም፡፡‹‹ የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን››
/ሐዋ 21 ፤14/ የሚለውም ቃል የእግዚብሔርን ፈቃድ ቀድሞ በምልክት ማወቅ ሳይሆን እየጸለዩና በቃለ መጻሕፍት
መሠረት እየኖሩ የሆነውን መቀበል ፈቃደ እግዚአብሔር በመሆኑ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በገሐድ ስሙን
እየጠራ ያናገረው ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ እንኳ ‹‹ምናልባት ብዙ ቆይቼ ወደ እናንተ አሁን እንድመጣ
በእግዚአብሔር ፈቃድ መንገዴን እንዲያቀናልኝ እየለመንሁ ሁልጊዜ ስጸልይ ስለ እናንተ ሳላቋርጥ አሳስባለሁ ›› /
ሮሜ 1 ፤ 10/ ሲል የጻፈላቸው እርሱ እንኳ ፈቃዱ እንዲሆን እየጠየቀ በየዕለቱ ከመጸለይ ውጭ የተለየ ምልክትን
ይሻበት እንዳልነበር ያስረዳናል፡፡ ዳግመኛም ‹‹እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ
ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ›› /ሮሜ 8 ፤5/ የሚለን ስለ ፈቃደ እግዚአብሔር በመንፈስ መረዳት
የምንችለው መጀመሪያውኑ ኑሮአችን በመንፈስ ሲቃኝ እንደሆነ ለማስረገጥ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ‹‹ስለዚህ የጌታ
ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ ›› / ኤፌ 5፤ 17/ ‹‹የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ
እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ›› /ኤፌ 6 ፤ 6/ ሲል አጠንክሮ
ይመክረናል፡፡ ስለዚህ በምልክትና በመሳሰሉት ነገሮች ሳንወሰን በሕይወታችን ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመለማመድና
ለመኖር ያብቃን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ ተፈጸመ፡፡ ( እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ግን ከዚህ በፊት በተለጠፉት
ሦስት ክፍሎች ላይ በውስጥ መልእክትም ሆነ በአስተያየት ጥያቄ ላቀረባችሁልኝ አንድ የማጠቃለያና የጋራ የመልስ
ጽሑፍ ለማቅረብ አስባለሁ፡፡ የእርሱ ፈቃድ ይሁን)፡፡

++ + ቃና ዘገሊላ +++
በዲያቆን ብርሃኑ አድማስ እይታ
የካቲት 23 (የአድዋ ድል ቀን) የቃና ዘገሊላ ተአምር የተፈጸመበት መሆኑን በማሰብ የቀሩትን በቃና ዘገሊላ ዙሪያ ትምህርቶችም እንጋራለን
(ከቪድዮ የተገለበጠ ቪድዮውን https://youtu.be/HXDVtd33CYM በመጫን ይመልከቱ Youtube ፔጁን ሲከፍቱ እባክዎን
Subscribe ያድርጉ )
ቃና ትንሽ መንደር ነች፡፡ እስራኤልን ጨምሮ በሮም ግዛት ሥር በነበሩበት ጊዜ በሜዲትራንያን ባሕር ጫፍ የነበረው የሮማ ነገሥታት ይጠቀሙበት
የነበረ ወደብ የቂሣርያ ወደብ (ሐዋ. 10 ቄርኔሌዎስ የነበረበት) አጠገብ ባለው መንገድ ያለች ትንሽ መንደር ነች፡፡ ጥንትም ሰዎች በተለይ ወደ
ሰሜን እስራኤል ጌታ ወዳስተማረበት ሲወጡ ይጠቀሙ የነበረው መንገድም እንደ አሁኑ ቴልአቪቭ ኢየሩሳሌም መንገድን ሳይሆን ይህን ታሪካዊ
መንገድ ነበር የሚጠቀሙት፡፡
ቃና ብዙ ሥራ ተፈጽሞባታል፡፡ ዛሬ ቦታው የካቶሊኮች ይዞታ የሆነ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶበታል ፤ በአርዎሎጂስቶች የተገኘ ሥፍራ ሲሆን የጥንቱ
ቤት ከመሬት ሥር ሆኖ ዛሬም ድረስ ይጎበኛል ፤ የድንጋይ ጋኖቹም አንድ ሁለቱ ተቀምጠው አሉ ፤ ይጎበኛሉ፡፡ ታሪካዊት ከተማም በመሆኗም ብዙ
ቱሪስቶች ይጎበኟታል፡፡
በዚያ ያሉ ክርስቲያኖች አንዱ ሥራቸው ወይን ሸጦ መተዳደር ነው፡፡ ሁለት ዓይነት የቃና ወይን ይሸጣሉ (አልኮል ያለውና የሌለው) እጅግ ደስ
የምትል ቦታ ናት፡፡ እኔ ደስ ትለኛለች ፤ ታሪካዊነቷ ይስባል፡፡ ታሪካዊ እውነታውን ስለሚያስረዳ ዕድሉን ያኘ ሰው ሊጎበኘው የሚገባ ነው፡፡
የመጀመሪያው የተአምር ወይን የተገኘው በዚያ ነው ፤ ደሙን ወይን አድርጎ የሠጠን ጌታም ያደገው በዚያ ስለሆነ ፤ እመቤታችንም ከቤተ መቅደስ
ከወጣች በኋላም የኖረችው በዚያ አካባቢ ነው፡፡ ማርና ወተት የምታፈስሰው ምድር የተባለችው እስራኤልም በኋላ ወተት የተባለው ወንጌል
የመነጨባት ሥፍራ እስዋ ናት፡፡ ዙሪያው ስታየው የሚያስረዳውም ይህን ስለሆነ ድንቅ ታሪካዊት መንደር ነች፡፡
★★★★
እመቤታችን ከማረፏ በፊት ከልብሶችዋ (ከአጽፎቿ) የሠጠቻቸው ሁል ደናግል ነበሩ፡፡ እነርሱም ይህንን ውድ ነገር ለቤተሰቦቻቸው አውርሰው
ያልፋሉ፡፡ አንዱ ቤተሰብ ላንዱ ቤተሰብ እያለ ሲቀባበል ክርስቲያን ያልሆነች አይሁዳዊት ሴት ጋር ደርሶ ነበር፡፡ ያቺ አይሁዳዊት ይህንን ቅርስ
ጠብቃ ትኖር ነበር፡፡
እና ይኼ ልብስ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ተጠብቆ የኖረባት መንደር ቃና ዘገሊላ ናት፡፡ ይህንን ትውፊት የጻፈው ሰው ከእስራኤል
የተወለደ መክስምያኖስ የሚባል ክርስቲያን ነው፡፡ እርሱ እንደዘገበው ይኼ ልብስ ቃና ላይ ልክ እኛ ሀገር እስላሙም ክርስቲያኑም ጠበል ሔዶ
እንደሚፈወስ የእመቤታችን ጨርቅ ያለበት ሥፍራ እየሔደ ይፈወስ ነበር፡፡ አንዲት ሴት በሳጥን አስቀምጣ ጋርዳው ነበር ፤ ሕሙማን እየመጡ
ነክተው ይፈወሱ ስለነበር ብዙ በሽተኞች በቃና ዘገሊላ መንደር እንደ ሸንኮራ ጠበል ሳጥኑን ከብበው ይቀመጡ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ታሪክ የተፈጸመባት
ናት የቃና ዘገሊላ መንደር!
★★★★
‹ቃና ዘገሊላ› የተሰኘውን የዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መጽሐፍ ለእኔ በጣም ምርጥ ከሆኑ መጻሕፍት ውስጥ ነው የምመድበው፡፡ አንደኛ አቀራረቡ አንድን
ነገር ብቻ ፣ አንድን ክስተት ብቻ አንድ መጽሐፍ ማድረጉ ይኼ አንድ ትልቅ ነገር ያሳያል፡፡
ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ክስተቶችን ብቻቸውን ይጸልዩባቸዋል ፣ ያስቧቸዋል ፣ ይተረጉሟቸዋል
ያስፋፏቸዋል፡፡ ራሳቸውን በዚያ ክስተት ውስጥ ያኖራሉ፡፡ እንዲህ ከሚታሰቡት ውስጥ ለምሳሌ የሥላሴ በአብርሃም ቤት መገኘት ፣ የያዕቆብ
ከእግዚአብሔር ጋር መታገል ዓይነት ናቸው፡፡
በቅዱሳን ሊቃውንት ዘንድ እንዲህ ዓይነቶቹ ክስተቶች እንደዋዛ የሚታለፉ አይደሉም፡፡ ደግመው ደግመው የሚያስቧቸው ፣ ደግመው ደግመው
የሚመረምሯቸው ፣ ደግመው ደግመው የሚጸልዩአቸው ናቸው፡፡ ራሳቸውንም በዚያ ክስተት ውስጥ ያኖራሉ፡፡ ለምሳሌ በቤተ አብርሃም ውስጥ
ራስህን ማኖር ... ስታስበው ድንኳንኑን ታስባለህ ፣ የመምሬ አድባር ዛፍ ፣ የእንግዶቹ አመጣጥ ፣ የበሬው አስተራረድ ፣ ሁኔታዎቹ ... እና አንድ
ዓለም ፣ አንድ ሕይወት ነው ያ! ድርጊቱም በመጽሐፍ ቅዱስ መዘገቡ ብቻ ሳይሆን የተዘገበበት ምክንያት ራሱ ትልቅ ስለሆነ እዛ ውስጥ የሚኖሩ አሉ
፡፡ ይኼ በኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት ዘንድ የተለመደ ነው፡፡
በጣም የሚደንቀው ደግሞ የቃና ዘገሊላው ከእነዚህ ሁሉ ይበልጣል፡፡ በብሉይ ኪዳን ካሉት ይበልጣል ፤ እነዚያ በሐዲስ ኪዳን የሚሆነውን
የሚያሳዩ ሲሆን ይኼ ግን እነዚያ ሁሉ መፈጸማቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ቃና ዘገሊላን ስትወስደው አሁን ሰርግ ቤት ነው፡፡ ብዙ ሰርግ ቤት ሊኖር
ይችላል፡፡ እመቤታችን የተገኘችበት ሰርግ ቤት ፣ ጌታችን የተገኘበት ሰርግ ቤት ፣ ደቀመዛሙርቱ የተገኙበት ሰርግ ቤት መሆኑ ብቻ ልዩ ያደርገዋል፡፡
★★★★
ባለፈው ጊዜ የዓለም መገናኛ ብዙኃን የባራክ ኦባማን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ልዩ አድርገው ይዘግቡ ነበረ፡፡ ልዩ ያደረገው ምንድር ነው? ሥልጣኑ
ላይ እያለ የመጣ ብቸኛ ፕሬዝዳንት ስለሆነ ነው ፤ Sitting president ተብሎ ማለት ነው፡፡ በጣም ይደንቃል! እስቲ እናስበው የሰማይና
የምድር ፈጣሪ የተገኘበት ሰርግ ቤትስ! እንዴት ተራ ክስተት ሊሆን ይችላል? አብርሃም ቤት የተደረገው ያን ያህል የሚያሳስብ ከሆነ ፣ ያን ያህል
ሊቃውንቱን ወስዶ የሚከት ከሆነ ፣ የምንመሠጥበት ከሆነ ከቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ጋርማ ሊነጻጸር የሚችል የለም ማለት ነው፡፡ እና ያ ሰርግ ቤት
ቀላል ሰርግ ቤት አይደለም፡፡ እና ሄኖክ እዚያ ሰርግ ቤት ተገኝቶ እያንዳንዷን ንግግር እየሰማ Live እንደሚያስተላልፍ ጋዜጠኛ ፣ እንደ ቀጥታ
ሥርጭት ተሳታፊ የሚያደርግ ፣ እንደዚህ ዓይቶቹን ጉዳዮች ደግሞ በነበረው ነባር ኦርቶዶክሳዊ ትውፊት መሠረት እያንዳንዳንዷን ነገር..... እንዴ...
በዓለም ቱሪስቶች የሚጎበኟቸው ከተሞች ለምን ይሆን የሚጎበኙት? ለምሳሌ ለንደንን እያት፡፡ ለንደን የቱሪዝም ገበያን የምታጧጡፍ ከተማ ናት፡፡
የምታስጎበኝህ ግን ‹በዚህ ዘመን የእገሌ ፕሬዝዳንት መጥቶ ይኼን ያደረገበት...› እያለች ነው፡፡ ባለፈው ኦሎምፒኳን ስትከፍት እዚያ ድልድይ ላይ
ችቦውን የለኮሰችው ነው፡፡
እንዴት ነው ጌታ የተቀመጠበት ፣ ከእመቤታችን ጋር የተነጋገሩበት ፣ ደቀመዛሙርቱ የነበሩበት ፣ ያ ጥያቄ ያ ጭንቀት ፣ ያ ተአምራት የተፈጸመበት
ቦታን እንዴት ነው ሊታለፍ የሚችለው? ቢቻልህ ቃና ከተማዋን በሕይወት ዘመንህ እየተመላለስህ ልታያት የሚገባት ቦታ ነበረች፡፡
★★★★
ብዙ ጊዜ ትልልቅ ሊቃውንት እንዲህ ዓይነቶቹን ነገሮች ብዙ አይጽፉባቸውን፡፡ የነገሮቹን ትልቅነት ይመለከቱና ራሳቸውን ብቁ አድርገው
አይቆጥሩትም፡፡ በእንግሊዝኛ contemplation (ተመሥጦ) የሚባለው ፤ ምስጥ ብለው በታሪኩ ውስጥ ይገቡና በአካል በዚህ ዘመን
እንደሚደረግ ገብተው ፣ ጎብኝተው ፣ አውርተው ፣ ልክ አሁን ወይኑ እንደተቀየረ ፣ ድግሱ እንዳለ ፣ ምሥጢሩን በልተው ፣ ጠጥተው ፣ ጠግበው ፣
ረክተው ፣ ታላቅነቱን አይተው በተመሥጦ ፣ በዝምታ ጸጥ ብለው ይኖራሉ፡፡ በጣም ይገርማል!
እዚሁ ላይ መረዳት ያለብን አንድ ነገር በኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ መሠረት ጊዜን ለምሳሌ ለሁለት ከፍለን ነው የምንረዳው፡፡ አንደኛ ይኼ
በሊቃውንት አጠራር ዮም የሚባል ሕያው የሆነ ጊዜ አለ ፤ ፈረንጆቹ Sacred time ይሉታል፡፡ መነሻም መጨረሻም የሌለው ፣ መነሻውም
ማእከሉም መድረሻውም እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሆነ ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ የሚባለው ክስተትን
ፍጥረትን ተከትሎ የሚቆጠር ፣ ክዋኔ የሚዘገበብበት ፈረንጆቹ Historical time የሚሉት ነው፡፡ ይህ Historical time የሚባለው
ከዚያ ቅዱሱ ጊዜ ከምንለው ዮም ከሚባለው (ወአነ ዮም ወለድኩከ በእኛ ከሚባለው) ጋር ረዥም ጠረጴዛ ላይ አንዲት ማሥመሪያ ወስደህ
እንደማጣበቅ ወስደህ እየው፡፡ ያኛው ትልቁ ነገር ከኋላ አለ ማለት ነው፡፡ ሕያው ጊዜ መነሻና መድረሻ የሌለው ጊዜ ውስጥ ውስኗ ጊዜ ሔዳ ገጥማ
ይገናኛሉ ማለት ነው፡፡ የእኛ ሊቃውንት ምን ያደርጋሉ መሰለህ? በዚህኛው ጊዜ ወደዚያኛው ጊዜ ይሻገራሉ፡፡ ወደ Sacred time ይሔዳሉ፡፡
በዚህም ምንም ነገር ኃላፊ ድርጊት አይሆንባቸውም፡፡ የተቀደሰው ሕያው ጊዜ ውስጥ ስለሚገቡ አሁን እንደተደረገ ሆኖ ይሰማቸዋል፡፡
ምሥጢራዊነት ፣ መመሠጥ Mysticisms ማለትም ይኼ ነው፡፡
እና ይኼ መጽሐፍ ለዚህ ዘመን ትውልድ ያንን የሚያስተዋውቅ ነው ... ልክ አንድ ልዩ ቤት እያንዳንዷን ግድግዳ ጣሪያ እንደሚናገር መሐንዲስ ቃና
ዘገሊላን እሱ ገብቶ በታዘበው መጠን ... ሊቃውንቱን እያነጋገረ ... ለምሳሌ ብዙ ሊቃውንትን ይጠራል በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡትን ...
በተለያየ ዘመን ያሉ ሊቃውንትን በዚህ ሰርግ ቤት ውስጥ ሲገቡ ታያለህ ... የማገናኘት ሥራ ይሠራል
ክርስትና ደግሞ ሥራው ይኼ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ክርስትና ሲነሣ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን የማገናኘት ሥራ ትሠራለች።
በመጀመሪያ ከራስዋ ከቤተ ክርስቲያን ጋር አንድ እንሆናለን። ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ከሦስት አካላት ጋር ታገናኘናለች። ከክርስትና አባት ወይም እናት
ጋር ፣ ከንስሓ አባት ጋር ፣ ክርስትና ስም ስትሠጥህ ደግሞ ለምሳሌ ወልደ ገላውዴዎስ ብትልህ ከዚያ ጋር አገናኘችህ ማለት ነው።
ከክርስቶስ ጋር የተገናኘው ሰው ፣ ከክርስቶስ ካህን ጋር ይገናኛል ፣ ከክርስቶስ ምእመን ጋር ይገናኛል ፣ ከክርስቶስ ጻድቅ ጋር ይገናኛል። ይኼም
መጽሐፍ የማዋሐድና የማገናኘት ሥራ ነው የሚሠራው።

★★★★

በዘመናዊ መንገድ ካየኸው ደግሞ የምንግባበት ሚድያ እንደመሆኑ የተጠቀመበት መልእክት የማድረሻ ዘዴ ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ነው። ከኦርየንታል
አብያተ ክርስቲያናት በተለይ በእኛና በሶርያ ላይ የሚታየው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የክርስትና አረዳድ ዘዴ አለ። እንደ coding ብትወስደው
biblical coding ን የተጠቀመ መጽሐፍ ነው። ይህም እግዚአብሔር ለነቢያቱ ራሱን የገለጠበት መንገድ ነው ፣ ያንን Interpret
እያደረግህ መረዳት ነው። መለኮታዊ ሃሳብ ጥልቅ ስለሆነ በደረስህበት እያብራራህ የምትሔደው ነው። ይህ በዓለም አቀፍ ሊቃውንትም ዘንድ የታወቀ
ስልት ነው።
ከዚህ መንፈስ ውጪ ሆነህ ልትረዳው አትችልም። ልክ ስልኮቻችን knetwork area ውጪ ነው እንደሚሉት ትሆናለህ። ሄኖክ እዛ ውስጥ
ነው ያደገው ፣ ከዛ ውስጥ ያለውን አውጥቶ ይሠጥሃል። ልክ ከወላጆቹ ቤት ያለውን አውጥቶ እንደመሥጠት ነው።
የምንማረው ዘመናዊው ትምህርት western coding ን የተከተለ ነው። ይነቀፋል ማለት አይደለም። በዛ መንገድ ግን መጽሐፍ ቅዱስን
ለመረዳት ስትሞክር አስቸጋሪ ይሆናል። በዚህ የትምህርት መስመር አድጎ ግን ይኼኛውን ማቅረብ መቻል ትልቅ ሓላፊነትና ብቃት የሚጠይቅ
ተግባር ነው። አንድን ጉዳይ ጥንቅቅ አድርጎ ማቅረብ ማለት ይኼ ነው። ሌላ ሰው ከዚህ በላይ ሊያሰፋው ይችላል። ሄኖክ ግን ቃና ውስጥ ገብቶ
አስገብቶናል። ከሊቃውንቱ ጋር አነጋግሮናል ፣ አጨዋውቶናል። ድንቅ መጽሐፍ ነው የምለው በዚህ ምክንያት ነው።
የሃሳብ ምንታዌም የለበትም ፣ እያንዳንዱ አረፍተ ነገር ብጥር ብሎ የተጻፈ ነው። አንድን ርዕሰ ጉዳይ ጥንቅቅ አድርጎ ሳይጨርስ ወደሌላ አይሔድም።
ሊቃውንቱ ጸሐፊን በብልት አውጪ ይመስሉታል። ይህ መጽሐፍም እያንዳንዱን ነገር በብልት በብልት የሚያወጣ አቀራረብ ያለው ነው።
ሁለተኛ አንድን የእኔ ቢጤ አላዋቂ ሰው ወደ ጫካ ብትወስድና ዕፅዋትን ብታሳየው የሚያየው ነገር ሁሉ አረም ሊመስለው ይችላል። የዕፅዋት
መድኃኒት ባለሙያ ግን ቢያየው እያንዳንዱ ዛፍ ትርጉም ይሠጠዋል። ምን ያህል ክብር እንዳለው ይረዳል። እኛን የማይስበን ዕፅ ቅጠል የአደገኛ
በሽታ መድኃኒት ሊሆን ይችላል።
★★★★
ቃና ዘገሊላ የተሰኘችው መጽሐፍ እንደዚህ ናት።
ትኩረት የማንሠጣቸውን ጉዳዮች በጥልቀት እንድንመረምር ያደርጋል። ለምሳሌ አንቺ ሴት "ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?" በሚለው ቃልና "የሚላችሁን
ሁሉ አድርጉ" በሚሉት ሁለት ዓረፍተ ነገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚመረምርበት መንገድ ምን ያህል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላትን ሰው ተራ
አድርጎ ሊያያቸው እንደማይገባ የሚያስረዳ ነው። ይህችን መጽሐፍ ተጠቅሞ ሌሎቹንም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንዴት መረዳት እንዳለበት
የሚያሳይ በማያሻማ መንገድ ግልፅ ሆኖ የቀረበ ፣ ጥልቅ ሃሳቦችን በቀላል አማርኛና በቅርብ ምሳሌዎች የሚያሳይ ድንቅ መጽሐፍ ነው።
ለምሳሌ እመቤታችን ወይን እኮ የላቸውም ያለችው ንግግር ምልከታ (observation) ብቻ እንዳልሆነ ሲያስረዳ አንዲት እናት "ይኼ ልጅ
ጫማ የለውም" ብትል ምልከታዋ ብቻ ሳይሆን "ግዛለት" ማለትዋም መሆኑን ሊረዳ በሚችል ምሳሌ ያስረዳል። ስለዚህ ለሁሉም ግልፅ የሆነ
አቀራረብ ያለው ድንቅ መጽሐፍ ነው።
(ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ከመጽሐፉ ውስጥ የመረጡት ክፍል በማንበብ አስተያየታቸውን አጠናቅቀዋል። ዲ/ን ብርሃኑ የበርካታ መንፈሳዊ መጻሕፍት
ጸሐፊና አርታኢ ሲሆኑ የፊዚክስና የፊሎሎጂ ባለሙያ ናቸው)

ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው፤ ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው / መዝ 118 ፥ 129/ ።

BIRHANU ADMASS ANLEYE·THURSDAY, MAY 12, 2016


በአሁኑ ጊዜ የተለቀቀው አይሲስ እንደገደላቸው የተነገረላቸው ዐሥራ ስድስት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ የመረጃው
ትክክለኛነት ገና ያልተረጋገጠ ቢሆንም (በእውነት ሐሰት ያድርግልንና) ነገር ግን የቀደሙትን ደግመን እንድናስባቸው
እግዚአብሔር ዕድል ስለሰጠን እናስባቸው፡፡
ሰአሉ ለነ ሰማዕታት መስተጋድላን

በባሕር የሚሰጥመውን፣ በበረሃ አውሬ የሚበላውን፣ ብልት ነጋዴዎች ኩላሊቶቻቸውንና ሌሎች ብልቶቻቸውን እያረዱ
የሚቸበችቡትን እያዩና እየሰሙ ዐይናቸውን ጨፍነው የሚሔዱት ምን ያህል ቢቸገሩ ወይንም ገንዘብ ቢፈልጉ ወይንም
ምን ቢሆኑ ነው እያልን የምናማቸው ሰዎች ለአንተ ሲሆን ነፍሳቸውን ሳይሰስቱ የሚሰጡት እነዚህ በእውነት ምንኛ
ድንቆች ናቸው? ጌታ ሆይ የሐዋርያትንና የሌሎች ቅዱሳንህ ምስክርነት ታላቅ አንደሆነ በደንብ እናውቃለን፡፡ እስካሁን
የተነሱ ቅዱሳንና ሊቃውንትም ስለተጋድሏቸው ጽናት ብዙ ሰብከውልናል፡፡ ሆኖም ከእነርሱ አንዳንዶቹ መከራውን
ከመሰቀቅ የተነሣ ሊሸሹ ሞክረውም እንደነበር ተነግሮናል፡፡ አንዳንዶቹንም አንተ ራስህ ተገልጸህ የት ትሸሻለህ
እንዳልካቸው ልዑካንህ እውነቱን ሳይደብቁ ነግረውናል፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ደግሞ አንተን ብቻ ሊገለግሉ ተመርጠው
ከተሰማሩ በኋላ ነበር፡፡ ብዙ ተአምራትና ኃይልም ካደረጉ በኋላ ነበር፡፡ እንደነ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ያሉትንም እንደ ቅዱስ
ጳውሎስ ያሉት መምህራን ሰማዕትነትን እንዳይሰቀቁ የዐለምንም ጣዕም እንዳይናፍቁ ግሩም ምክር ሰጥተዋቸዋል፤
ሌሎቹም ዘመናቸው ለዚህ የሚያግዝ ብዙ ነገር ሰጥቷቸው ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር ገዳዮቻቸው ጣዖት አምላኪዎች
ስለነበሩ የእጅ ሥራ የሆነውን እንጨት በአንተ ለመለወጥ እንዳይቸገሩ ያግዝ ነበር፡፡ የእነዚህ ገዳዮች ግን የሚገድሉት
በአንድ እግዚአብሔር ስም እያሉ ነው፡፡ በዚሁም ላይ የተገኙት ገንዘብ እንደጽድቅ በሚሰበክበት፤ በንስሐ በሚዘበትበት፤
መልካም ነገር ምቾት ብቻ ተደርጎ በሚቆጠርበት፣ አንተ የምታውቃቸው ባይጠፉም ለእኛ በተረዳው ታላቁና ታናሹ
ካህኑና አገልጋዩ ወዳጅነትን በገንዘብ ፍቅርንም በውለታ በሚለካበት፣ በሁሉ ነገር እጅህ ከምን በሚባልበት ዘመን ነው፡፡
ታዲያ እነዚህ ኑሮ ለመለወጥ በተሰደዱበት ያለአስተማሪና ያለአጽናኝ ስለስምህ ምስክር ሆነው የቆሙ በእውነት ምንኛ
ድንቆች ናቸው? የወጡት ወደ አውሮፓና ሌሎች ዓለማት እንደቀናቸው ተሻግረው የሰለጠነ ማኅበረሰብ የሚባለው ውስጥ
ተቀላቅለው ኑሮ ለመለወጥ ገንዘብ ለመሰብሰብ ነበር፤ መንገድ ላይ ግን ወደ ጻድቃን ከተሞች ወደ በኵራት ማኅበር
ለመቀላቀል ወደ ገነት ተጣደፉ፣ ኑሮአቸውን ሳይሆን ሕይወታቸውን ለወጡ፤ ገንዘቡን ረስተው አክሊላትን ተሻሙ፡፡
ብድር ከፍለን ለቤተሰባችን ልከን የሌሎችን ቤተሰቦቻቸውን ኑሮ ጭምር ለመለወጥ እንችላለን ብለው ያሰቡትንና
የወጡበትን ድንገት ትተው የኃጢአታችን ዕዳ ከፍለው ጽድቅንና በረከትን ለክርስቲያኖች ሁሉ ሊልኩ ወደ ባለጸጋው
ጌታቸው ወደ ሰማይ ተፋጠኑ፡፡ የችግርን ሰይፍ ፈርተው ወጥተው የተቸናቸው ወጣቶች በጨካኞች እጅ ያዩትን ሰይፍ ግን
እንኳን ሊፈሩት እንደ ሽልማት ቆጥረው አንገታቸውን ለሰይፍ ሳይሆን ለሀብል የሚሰጡ አስመስለው በመስጠት
አስደነቁን፡፡ እዚህ ከእኛ ከወገኖቻቸው መካከል የእርሻም ሆነ የኤክስፖርት ተሸላሚዎች ሲሔዱ ሰውነታቸው ሲፈራ
አረማመዳቸው ሲወላገድ ፊታቸው በላብ ሲጨመቅ ይታያል፡፡ እነዚህ ግን በበረሃ ከብዙ ስቃይና ማስፈራሪያ በኋላ
ወደመገደያ ቦታ ሲመሯቸው ፊታቸው የማይሰቀቅ ሰውነታቸው የማይርድ እንዲህ ያሉ ምስክሮችህ እረ ምንኛ ድንቆች
ናቸው? ሥራ ወደሚገኝበት ዕድል ወደሰፋበት እንሒድ ብለው ከወጡ በኋላ ጠባቧን መንገድ ሳይለቁ የእውነት
ምስክርነት ሰጥተው ሞትን የሚመርጡበት ጽናት ምንኛ ድንቅ ነው? ጌታ ሆይ ባለማወቅ ስላደረግሁት ይቅርበለኝ፡፡ ነገር
ግን የሐዋርያት ዘመን ሰማዕታትን ሳስብ ኑ እኔን ምሰሉ የሚሉ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ያሉ ከፊት ለፊታቸው ነበሩላቸው፡፡
ዘመነ ሰማዕታትንም ሳስብ ፈር ቀዳጅ የሆኑ በቅድስና ያጌጡ ብዙ ታላላቅ ሰማዕታት ከፊት ለፊታቸው ይታዩኛል፡፡
ተአምራት እያደረጉ ያላመነውን እያሳመኑ ለሰማዕትነት አይዟችሁ የሚሉ ብዙዎች እንደነበሩ ገድለ ቅዱሳኑ
ይመሰክራሉና፡፡ በእኛ ዘመን ግን ያለነው ሰዎች አገልጋዮችን ጨምሮ ወይ ምን ሞኝ አደረጋቸው ብለን የምንተች
ካለበለዚያም አልህ የሚተናነቀን ለቀስተኞች ነን ፤ቢበዛ በሰብአዊነት መንፈስ አዝነን የምንጮህ የመብት ተሟጋቾች፡፡
ከዚህ አልፎ በመንፈስ የሚመራ በተጋድሎ የሚያስከትል ብዙ አይታየንም፡፡ እንዲህ ባለ ጊዜ ወንጌል በማይገለጥበት፣
ቅዳሴ በማይሰማበት፤ ካህን በማያጋጥምበት ምድረ በዳ ለእንጀራ እየተጓዙ ሞትን አለመሰቀቅ፣ ሰማዕትነትንም ማጣጣም
እንደምን ያለ ድንቅ ነው? እንደምንያለ እምነት፣ እንደምንስ ያለ ጽናት? ጌታ ሆይ በእውነት ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው፡፡
አዎን ይገባናል በመቅደስህና በቅድስናህ አደባባይ እውነቱን ለመመስከር ስናፍርብህ፣ ድንቅ ወዳጆችህንም ስናናቅ፤
እነርሱን የመሰሉ ሳይራቀቁ የሚያምኑ በእውነትና በሕይወት እንደ ወንጌሉ የሚመሰከሩልህ ወዳጆች እንዳሉህ በማሳየት
እየዘለፍከን እንደሆነም እንረዳለን፡፡ ጌታ ሆይ አዎን ምስክሮችህ በርግጥም ድንቆች ናቸው፤ ስለዚህም ነፍሳችን
ትፈልጋቸው መንገዳቸውንም ለመከተል ትተጋ ዘንድ እንድትረዳን ድንቅ በሆኑት ምስክሮችህ እናማጽንሃለን፡፡ በእውነት
ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው፤ ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው፤ በረከታቸው ይደርብን፡፡

የቀኝ ዐይን - ድንግል ማርያም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡


እንኳን ለበዓለ ልደታ ለማርያም ወይም ለግንቦት ልደታ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

አፍጣኒተ ረድኤት ማርያም በጊዜ ምንዳቤ ወአጸባ፤


ለዐይን እምቀራንባ፤
አንቲ ውእቱ ረዳኢተ ያዕቆብ በቤተ ላባ፤
በኩሉ ኅሊናሃ ወበኩሉ አልባባ፤
ዘኢታፈቅረኪ ነፍስ ትሠሮ እምሕዝባ፡፡

የነገረ ማርያም ሊቅ(Marian Doctor) እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ እመቤታችንን በብዙ
ምሳሌ እየመሰለ፣ እየተረጎመና እያመሰጠረ ብዙ ጊዜ አመስግኗታል፡፡ ምንም እንኳ እኛ የምናውቀው የምስጋና ድርሰቱ
ለጸሎት የምንጠቀምበት ውዳሴ ማርያም ቢሆንም ከትርጓሜና ከስብከቶቹ ውጪ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ስንኝ
ያላቸው የምስጋና ድርሰቶች(Hymns) መድረሱን ታሪክ ጸሐፊው ሶዝመን መዝግቦልናል፡፡ ከነዚህ የምስጋና
ድርሰቶቹ መካከልም ‹‹በእንተ ልደት››(On Nativity) እና ‹‹በእንተ ቤተ ክርስቲያን››(On the
Church)በተባሉ ትልልቅ ድርሰቶቹም እመቤታችንን ደጋግሞ ያመሰግናታል፡፡

በተጠቀሱት ሁለቱም ድርሰቶቹ ውስጥ እመቤታችንን ለማመስገን ከተጠቀመባቸው ምሳሌዎች ውስጥ አንዱ ዐይን
ነው፡፡ ሊቁ ስለ ቤተክርስቲያን በደረሰዉ የምስጋና መዝሙሩ ውስጥ እንዲህ ይላታል፤ ‹‹ዐይን ጥርት የሚለው ከፀሐይ
ብርሃን ጋር ተዋሕዶ ከብርታቷ ኃይልን ከውበቷም ነጸብራቅን ሲቀበል ነው፤ በዚህ ጊዜ በግለቷ ይሰነገላል፣ ያበራል፤
በውበቷም ያጌጣል፤… ልክ እንደዚሁ ማርያም ዐይን ናት፤ብርሃን (ጌታ) ማደሪያውን በእርሷ አዘጋጀና መንፈሷን
ጽሩይ አደረገ፤ አሳቦቿን አጠራ፣ ኅሊናዋንም ንጹሕ አደረገ፤ የድንግልናዋንም ክብር አበራው ››/Hymns on
the Church, 36, 1-2/፡፡ ሊቁ በዚሁ ድርሰቱ ውስጥ ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ፤ ‹ለዚህ ዓለም ሁለት ዐይኖች
ተሰጡት፤ ማየት ያልተቻላት የግራ ዐይን ሔዋን ስትሆን፣ የምታበራው የቀኝ ዐይን ደግሞ (እመቤታችን) ማርያም
ናት፡፡በማታየው በጨለማዋ ዐይን ምክንያት መላው ዓለም ጨለመ፤ ስለዚህም ሰዎች በጨለማ ጥላ ውስጥ ሆነው
ሲዳብሱ ያገኙት ሁሉ አምላክ ፣ ሐሰቱም እውነት መሰላቸው፡፡ ነገር ግን ዓለም እንደገና በሌላ ዐይኑ ባበራና (ባየና)
ሰማያዊዉ ብርሃንም በዚች ዐይን ሰሌዳ ውስጥ ባንጸባረቀ ጊዜ ሰዎችም ቀድሞ ያገኙትን(ያመለኩትን) የኑሮአቸው
ውድቀት(የባሕርያቸዉ መጎስቆል) መሆኑን ተረድተዉ ወደ ማንነታቸዉ ተመለሱ (አንድነታቸዉን አገኙ)›› ይላል
/Ibid, 37, 5-7/::

በዚህ መሠረት የእመቤታችን ልደት ዓለም ማየት የጀመረበት ዕለት ነው ማለት ነው፡፡ በርግጥም በነገረ ማርያም
መጽሐፋችን ላይ እንደተገለጸው እመቤታችን በቴክታና በጥሪቃ(ሰባተኛ ቅድመ አያቶቿ) በታየው ሕልም መሠርት
ዓለምን ሰፍኖበት ከነበረዉ ድቅድቅ የኃጢኣት ጨለማ እፎይታ የሰጠችዉ ጨረቃ እርሷ ናት፡፡ በጨለማ ሲያዩት
የሚያስፈራዉና ሌላ ሌላ የሚመስለዉ ጉቶዉ፣ ቁጥቐጦዉ ፣ ድንጋዩ ፣ ጉብታዉ….ሁሉ ተራ ነገር መሆኑ
የተጋለጠባት፤ ሰዎችም የሰገዱለት ሁሉ አምላክና ጌታ መሆኑ ቀርቶ ድንጋይ ጉብታ መሆኑን ማየት የጀመሩባት፣
ከደገኛዉ ፀሐይ ክርስቶስ መውጣታ በፊት ከረጂሙ ዘመን ጨለማ ጭንቀት የተገላገልንባት ጨረቃ፣ ብርሂት የቀኝ
ዐይን እመቤታችን ማርያም ናት፡፡ ስለዚህም ልደቷን የጨለማችን መገፈፍ፣ የዐይናችን ማየት፣ የብርሃናችንም
መውጣት ነውና በፍጹም ደስታ እናስበዋለን፤ እናከብረዋለንም፡፡

ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬምን የምናስታውሰዉም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ብዙ በማመስገኑ ብቻ ሳይሆን


ግሩም አደርጎ በማመስጠሩና እንዲህ ያለ ልዩ ልዩ ነገር በማምጣቱም ጭምር ነው፡፡ ለነገሩ ሰው የመንፈስ ቅዱስ
ማደሪያ ከሆነ በኋላ ይህን ሁሉ ማድረጉ አያስደንቅም፡፡ የሆነዉ ሆኖ የእርሱን ያህል በልዩ ልዩ ሕብረ-አምሳል
ያመሰገናት ያለ አይመስልም፡፡ሊቁ በልደት ድርሰቱም‹‹እናትህ አስደናቂ ናት፤ ጌታ ወደ እርሷ ገባና አገልጋይ ሆነ፤
እየተናገረ ገብቶ በእርሷ ዉስጥ ግን ዝም አለ፤ ወደ እርሷ በነጎድጓድ ድምፅ ገብቶ በእርሷ ውስጥ ጸጥታን አሳደገ፤
የዓለሙ እረኛ ገብቶ በግ ሆኖ ተወለደ፤ እንደ በግም ‹ባ› እያለ ተገለጠ ››/On Nativity, 11, 6/ እያለ
አስደናቂነቷን እየደጋገመ ይናገርላታል፡፡አንድ ብቻ ጨምሬ ወደ በዓሉ ልመለስ፡፡ቅዱሱ ሊቅ ጌታን እንዲህ ይለዋል፤
‹‹አንተና እናትህ ብቻ ተወዳዳሪ የሌላችሁ ውቦች ናችሁ፤ በአንተ ላይ ምንም ምን ትንታ(mark) በእናትህም ላይ
እንከን(stain) የለም››/Carmina Nisibena, 27,8/፡፡ምንኛ ግሩም ምስጋና፣ እንዴትስ ያለ ፍቅር፣
እነደምንስ ያለ መረዳት ነዉ? መብቃት ነዋ! መብቃት! ከሌላ ከምን ይገኛል? እርሱ ካልገለጸ፡፡

ከቅዱስ ኤፍሬም ሌሎች ድርሰቶች የተነሳሁትና ርእሴንም በእርሱ ምስጋና ያደረገሁት እንዲሁ አይደለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ
ውዳሴ ማርያም እየተጣጣለና ድርሰቱም የእርሱ ሳይሆን የኢትዮጵያውያን ነው (ምነው በሆነና ነበር) ፤ ወይም ደግሞ
እርሱ ስለ ሌላ የደረሰውን የእኛ ሰዎች የማርያም ምስጋና ነው ብለው ነው እንጂ እርሱስ እንዲህ አይልም መባል
ስለተጀመረ እረሱ ስለ እርሷ ከደረሰው ወደ ግእዝ የተተረጎመው ትንሽ መሆኑንና ከላይ ለምሳሌነት ካቀርብኳቸው
በላይ በውዳሴ ማርያም ምን አዲስ ነገር አለ ለማለት ነዉ፡፡ ይህችን ታህል ጥቆማ ከሰጠሁ ቦታውም ጊዜውም
የጽሑፉም ዓላማ በዚህ ጉዳይ ላይ መከራከር አይደለምና ወደ እናታችን በዓለ ልደት በረከት ላምራ፡፡

በርግጥም ፍጹም ልዩ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማይጠረጠር መልኩ ከፍጥረት ሁሉ ልዩ ናት፡፡ በድንድልና ላይ እናትነት፣
በክብረ ድንግልና ላይ ክብረ ወሊድ፣ በድንጋሌ ሥጋ ላይ ድንጋሌ ነፍስና ድንጋሌ ኅሊና የተሰጣት ከእርሷ በቀር
ማንም የለም፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ ምንም እንኳ ‹‹በልቧ ትጠብቀዉ ነበር››/ለቃ.2፣51/ ተብሎ እንደተጻፈዉ
አትናገረው እንጂ ከፍጥረት ወገን እንደ እመቤታችን እርሱን ለማወቅ የተቻለው ፍጥረት የለም፡፡ ሊቁ ኦሪገን በሉቃስ
ወንጌል ትርጓሜው ላይ እንደገለጸው ስለ አምላክ ፍጥረት ሊያውቀዉ የሚቻለውን የመጨረሻው የእውቀት ደረጃ ላይ
የደረሰችው እመቤታችን ብቻ ናት፡፡ እንደ እርሱ ትርጓሜ እመቤታችን ፍጡር ለፈጣሪው ክብር ሊጨምርለት
እንደማይቻለው እያወቀች ‹‹ተዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር - ነፍሴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች›› ያለችዉ ፍጡር
ሊረዳው የሚቻለው የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሳ በዚያ መጠን ማመሰገኗን ስትገልጽልን ነው ይላል፡፡በርግጥም
በዚህ መጠን ከርሷ በላይ ሊደርስ የሚቻለዉ እንዴት ሊኖር ይችላል? ይህ የሚያመለክተውም ገና በምድር ሳለች
ለፍጥረት የሚገባው ለዚህ የመጨረሻ ብቃት ከደረሰች ከዚህ ዓለም ከሔደች በኋላማ ይልቁንም እንዴት ያለውን
የተወደደውንና ከፍጥረት ሁሉ የላቀውን ምስጋና ታቀርብልን ይሆን? ምን ጥርጥር አለው? ልዩ የሆነውን ልታቀርብ
የሚቻላት ልዩ እናት፡፡

ለዚህም የበቃችው ራሷን ለሰው በሚቻለው ከፍተኛው መጠን እንደምትጠብቅ አስቀድሞ የሚያውቅ ፈጣሪ እርሱም
ደግሞ ጠበቃትና ከፍጥረት ወገን ልዩ ሆነች፡፡ ቀድም ብለን የተመለከትናቸው የቅዱስ ኤፍሬም ጥቅሶች
የሚያረጋግጡልንም ይህንኑ ነዉ፡፡ ብርሂት የሆነች ዐይን ለሰውነት መብራት የምትሆነው የፀሐይ ብርሃን ሲዋሐዳት
እንደሆነው ሁሉ እርሷም በራሷ ብርሃነ ዐይን ንጽሐ ሥጋ ወኅሊና ላይ የብርሃን ጌታ ብርሃን የተባለ ጸጋውን አሳድሮ
ንጽሕናዋን ወደር የለሽ አደረገው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ርብቃ ለይስሐቅ የታጨችበትን የሚናገረዉ አንቀጽ
ላይ ‹‹ብላቴናይቱም መልክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማያውቃት ድንግልም ነበረች››/ዘፍ. 24፣16/ የሚለውን
ሲተረጉም ‹ወንድ የማያውቃት› የሚለውን ለሥጋ ድንግልናዋ ከሰጠ በኋላ ‹ድንግልም ነበረች› ያለው ደግሞ
ለመደጋገም ሳይሆን በኅሊናዋም ያልባከነች የተጠበቀች ነች ለማለት ነው ይላል፡፡ ይሁን እንጂ እንደዚህ ያለችው
ድንግል ርብቃ ድንገት(ለርሷ) ያገኘችውና ማንነቱን እንኳ በውል የማታውቀዉ ሽማግሌ (የአብርሃም መልክተኛ)
ቤተሰቦቿን በጠየቀው መሰረት ወላጆቿ ጠርተው ‹‹ከዚህ ሰው ጋር ትሄጃለሽን?›› ብለው በጠየቐት ጊዜ ሳታንገራግር
‹‹እሔዳለሁ›› አለች፤ መሰስ ብላም ተከተለችው፡፡/ዘፍ 24፣58/ እመቤታችን ግን የከበረ መልአክ ተገለጾ
ሲያነጋግራት እንኳ የልቡናዋ በር ለወሊድ አልተንኳኳም፡፡ ለልማዱ ሴት ልጅ ‹‹ትጸንሻለሺ፣ ትወልጂያለሺ›› ቢሏት
ምንም ብትመንን መልአክ ተግልጾ ከነገራት ‹‹ይህ እንዴት ይሆናል?›› ልትል አትችልም፤ እንዴት እንደሚሆንማ
ጠንቅቃ ታውቃለችና፡፡ እመቤታችን ከነዚህ ሁሉ ልዩ ስለሆነች ‹‹እፎኑ ይከውነኒ ዝንቱ›› ስትል ፈጽሞ በታተመና
እርሱን በሚያልፍ ኅሊና መልአኩን አስጨነቀችው፡፡ እርሱም‹‹ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም›› የምትል ጥቅስ
አግኝቶ ፈተናውን ተገላገለ፡፡ ሌላው ቀርቶ በዚህ ጥቅስ ተረትታ ብሥራቱን ስትቀበልም ‹‹ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ-
እንዳልከዉ ይሁንልኝ›› ያለች አንተ እንዳልከው የአምላኬ ፈቃዱ ሆኖ እንበለ ዘርዕ፣ እንበለ ሩካቤ ከሆነና ተጸንሶ
የሚወለደውም እርሱ ከሆነ ይሁን ይደረግ አለቺ እንጂ ለሌላው ነገርማ ኅሊናዋ እንደታተመ ነው የቀረው፡፡‹‹ ልጄ
ሆይ ስሚ፣ እዪ ጆሮሺንም አዘንብዪ፤ ወገንሺን የአባትሺንም ቤት እርሺ፣ ንጉሥ ውበትሺን ወድዶአልና፤ እርሱ ጌታሺ
ነውና›› (መዝ 44÷12) ሲል አባቷ ዳዊት በትንቢት እንደተናገረው እርሷ ከሔዋናዊ ጠባይ ተለይታለችና፡፡
ሰሎሞንም‹‹ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሺ ውብ ነው ፤ ነውርም የለብሺም፤ ልቤን በፍቅር አሳበድሺው….›› ያለዉ ለዚህ
ነበር፡፡

ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹የታተመች ደብዳቤ›› ያላትም ለዚህ ነው/ኢሳ 28 ፤ 12/፡፡ ምክንያቱም ለልማዱ
ደብዳቤ ከተጻፈ በኋላ ይታሸጋል፡፡ ስለ እርሷ የተነገረው ግን ከታተመ ወይም ከታሸገ በኋለ ተጻፈበት የሚል ነው፡፡
አብ በድንግልና አትሞ ሲያበቃ በውስጧ አካላዊ ቃልን የጻፈባት ማንበብ የሚችሉም(እሥራኤል) ማንበብ
የማይችሉም(አሕዛብ) እናነበው ዘንድ አንችልም ታትሟልና (በድንግልና በንጽሕና በክብር በምስጢር) አሉ ብሎ
የተናገረላት ደብዳቤ እርሷ ናትና፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ጸጋ ለተሰጣቸው ሰዎች ብሥራት ሊያደርስ ሲመጣ ይህ
የመጀመሪያው አልነበረም፤ ይሁን እንጂ ለዳንኤልም ሆነ ለጻድቁ ካህን ለዘካርያስ ለእርሷ እንዳደረገዉ ለእነርሱ መች
አደረገ? እነርሱ እጅ ነሱት ሰገዱለት እንጂ እርሱ መቼ እጅ ነሳ ሰገደላቸዉ? ከዚህ በላይ ልዩ መሆን በእውነት ወዴት
ይገኛል፡፡
ፍጹም ልዩ መሆኗን ለማስረገጥ ያህል አንድ ነገር ብቻ ላክል፡፡ የጥንቶቹ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ጌታ ለሐዋርያት
ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቛት ዘንድ የሰጠው ሁለት ጊዜ ነው ይላሉ፡፡ አንደኛው ብዙ ጊዜ ሲጠቀስ የምንሰማው ለቅዱስ
ጴጥሮስ የተሰጠው ነው፡፡ይህም ‹‹በጎቼን አሰማራ፣ ጠቦቶቼን ጠብቅ እና ግልገሎቼን አሰማራ››/ዮሐ 21፣15-
17/የሚለው ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከዚህ ቀደም ብሎ በመስቀል ላይ የሰጠው ነው፤ በመስቀል ላይ ጌታ ለዮሐንስ
‹‹እነኋት እናትህ›› ሲል የሰጠው እርሷን ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንንም ነው ይላሉ፡፡ በእነዚህ ሊቃውንት ትርጓሜ
መሠርት ሁለቱም ራሳቸውን የቻሉ ምስጢራትን ይዘዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ሕጋዊ ስለነበር(በጋብቻ የተወሰነ ማለት
ነው) የተሰጠውም አደራ ይህንኑ የሚመለከትና በጎቹን እስከ ገላግልቶቻቸው(ምእመናን) የሚመለከት ነው፡፡ጌታ
በወንጌል ‹‹በጎቼ ድምጼን ይለያሉ›› እንዳለው እነዚህ ድምፅ እንጂ ቃል መለየት የማይቻላቸው ምእመናን ናቸው፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ ግን ከዚህ ሁሉ በእጅጉ ይለያል፡፡ምክንያቱም እመቤታችን ራሷ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ብቻ ሳትሆን
የፍጹማን ደናግልም ምሳሌ ናት፡፡ ስለዚህ ከደምጽ ያለፈ ቃላትን ምስጢራትን መለየት የሚቻላቸው ፍጹማንን
የሚመለከተው አደራ የተሰጠው ለበቃው ብቻ ሳይሆን ለፍጹሙ ድንግል ለዮሐንስ ነው፡፡ ስለዚህ እመቤታችንን
መግፋት ቤተክርስቲያንን መግፋት ነው፡፡ እርሷንም መቀበል የሚቻለው ዮሐንስን የመሰለ ንጹሕ ድንግል ነው፡፡ ቅዱስ
አትናቴዎስ እንደሚለው ጌታ የሰጠው ድንግሊቱን ለድንግል፣ ድንግሉንም ለድንግል፤ ንጹሕንም ለንጹሕ ነዉ፡፡
መላእክት ሲጠብቐት ከኖሩ በኋላ መልአክ ለመሰለ ሰዉ ሰጣት እንጂ ለሌላ አልተሰጠችም፤ ሊቀበላት የሚቻለውም
የለም፡፡በተለ

ይ ኦሪገን ይህንኑ በተረጎመበት አንቀጹ ስለ ቅዱሱ ብቃት ሲናገር ለእርሷም ‹‹እነሆ ልጅሽ›› አላት እንጂ ‹‹ልጅ
ይሁንሽ›› አላላትም፤ ምክንያቱም ዮሐንስ በዚያ የመከራና የጭንቀት የፍርሃት ቀን በዕለተ ስቅለት ሳያፈራ ሳይሰቀቅ
በእግረ መስቀሉ የተገኘው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም፤ ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል›› /ገላ
2፣20/ እንዳለው ዮሐንስ ራሱን ክዶ ስለነበር ለራሱ እየኖረ አይደለምና በእርሱ የሚኖረው ጌታ ነበር፡፡ ‹‹አነሆ
ልጅሽ›› ያላትም በእርሱ አድሬ ያለሁት እኔ ነኝ ማለቱ ስለሆነ ከእርሷ ሰው ከሆነ በኋላ ለማንም አልሰጣትም፤
በዮሐንስ አድሮ የተቀበላትም ራሱ ነው፤ ከዚያ በኋላ እርሷን ሊቀበል የሚቻለው የለምና ይላል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው
እንኳንስ የእርሷን ነገር ለመንቀፍ ቀርቶ ለማመስገንም ትሰጠው ዘንድ ከፈለገ እንደ ዮሐንስ ራሱን በንጽሕና ይጠብቅ
፣ራሱንም ፈጽሞ ይካድ ባይ ነው፡፡
የአሁኖቹ ሰዎች እርሷን ባይቀበሉ፣ በእርሷ አማላጅነት ባያምኑ ለምን እንደነቃለን? እነዚህ በትንሽ ነገር እንኳ
መታመን የማይቻላቸው የእርሷን ነገር ይረዱ ዘንድ ታላቁንና ሰማያዊውን ምስጢር ማን አደራ ሊሰጣቸው ይችላል?
አንዳንድ የዋኃን ደግሞ መሠርይ ተሐድሶዎች ስለ እርሷ የዘመሯቸውን መዝሙር ተብየ ዘፈኖች እየተመለከቱ
ይታለላሉ፡፡ ይህ መናፍቃኑ ስለ እርሷ የሚሉትን መንገድ የተከተለ በእነርሱ ወዝ የታሸ ስለሆነ ተወዳጅ መሥዋዕት
አይደለም፡፡ በኦሪት አንበሳው፣ ተኩላው፣ ቀበሮው፣ … የመሳሰለው አውሬ የገደለውን ሁሉ እንኳን ለመሥዋዕት
ልናቀርበው ቀርቶ ልንበላውም የተከለከለ ነው፡፡ ይህም ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱት አውሬዎች የተባሉት
(አጋንንት፣ ርኩሳን መናፍስት፣ መናፍቃን፣…. ደሙን ያፈሰሱትን ወይም በእነርሱ) የተሰዋዉን ሁሉ እንኳን
ለእግዚኣብሔር ማቅረብ ለእኛም መንካት መርከስ ነዉ ማለት ነው፡፡ ‹አውሬ የቧጨረውንም አትንካ› የሚል ንባብም
ይገኛል፤ ይህ ሁሉ ከእነርሱ የተነካካውን በዚህ ዓለም የዘፈንና የረከሰ መንፈስ የጎሰቆለውን ምንም ለዐይንህ ቢያምርህ
(በዘፈን ላደገ ሁሉ የእነርሱ የሚያምረው መሆኑ አይጠረጠርም) ፈጽመህ አትንካ ተብለን ታዘናልና መልከስከስ
አስፈላጊ አይደለም፡፡ ግጥሙ በኑፋቄ ዜማው በዘፈን ርኩሰት የተቧጨረ ርኩስ ነውና፡፡እርሷ ቤተ ክርስቲያን ናት፤
የቤተክርስቲያናችንም ስጦታ ስለሆነች በእውነት ልዩ ናትና ይህን በመሰለ መልኩ የተቧጨረውን አናቀርብም፡፡
እንግዲህ ዛሬ ተወለደች የምንለዉ ይህችን ልዩ ድንግል ነው፡፡ስለዚህም የእርሷን በዓለ ልደት ማክበር ከዚህ ሁሉ
በረከት መሳተፍ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር በእርሷ በኩል ለባሕርያችን ያደረገውንም ክብር ማወቅና መቀበል ጭምር
ነው፡፡
ከበዓሉ ምን እናገኛለን? የእርሷስ በዓል አልበዛምን?

አንዳንድ ሰዎች በእኛ ቤተክርስቲያን የጌታ በዓል አንሶ የእመቤታችን የበለጠ፤ እኛም ከርሱ ይልቅ ለርሷ የምናደላ
የሚመስላቸው ቁጥራቸው በርከት ማለት ጀምሯል፡፡ ያለማወቅ ነውና አይፈረድባቸውም፡፡ ለነቀፋም የተሰለፉ ስለሆነ
በ‹ምሰለ ፍቁር ወልዳ-ከተወደደዉ ልጇ ጋራ› በምንለው ሥዕል ውስጥ እንኳ በሥዕሉ መጠን እየመሰላቸዉ ጌታ ያነሰ
የሚመስላቸው ማስተዋል የራቃቸው ስለሆኑ በእነርሱ አንገረምም፡፡በቤተ ክርስቲያናችን ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር
፮ ድረስ ከእናቱ ጋር መሰደዱን፣ ከኅዳር ፲፬ ጀምሮ እስከ ልደቱ ይወርዳል ይወለዳል ሲሉ ትንቢት የተናገሩ የነቢያትን
ጾም እየጾምን እርሱን እናስባለን፡፡ ከልደት እስከ ዐቢይ ጾም ድረስም በሥጋዌ፤ በአንድነት በሦስትነት መገለጡ
አስተርእዮ እየተባለ ይታሰባል ይሰበካል፡፡ ከዚያም ዐቢይ ጾም ይገባል፤ ሁለንተናችን እርሱን በማሰብ ይሰበሰባል፤ ቃለ
እግዚአበሔሩም ይህንኑ ያዘክራል፡፡ በትንሣኤውም ሃምሳ ቀናትን እንደ አንድ ቀን እንደ ዕለተ ትንሣኤው በመቁጠር
ትንሣኤውን እንሰብካለን፡፡ ከዚህ በማሰከተልም ርዕደተ መንፍስቅዱስን በዓለ ጰራቅሊጦስን በጾም እናከብራለን፡፡
በየወሩም በዓለ እግዚእ፣ መድኃኔዓለም፣ ኢየሱስ፣ አማኑኤል…. እያልን ከዘጠኙ ዓበይትና ከዘጠኙ ንዑሳን በዓላት
በተጨማሪ በየአጥቢያቸው የሚታሰቡት ትዝ አይሏቸዉም፡፡ ሌላዉ ቀርቶ በየሳምንቱ ሁለት ቀናትን (ረቡዕ እና
አርብ) በጾም ሁለት ቀናትን (ቀዳሚትንና እሑድን) በበዓል ለክርስቶስ መታሰቢያ የሰጠች ብቸኛ ቤተ ክርስቲያን
የእኛይቱ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ብቻ መሆኗን አያስተውሉም፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ የማርያም በዓል ከጌታ
በዓል ይበልጣል ማለትን ምን ዓይነት አለማስተዋል ልንለው እንችላለን? ቢሆንስ በቅዱሳን በዓል ዋናው ተከባሪ
ተመሰጋኝ ማን ሆነና ነው ይሄ ሁሉ ጩኸት? ስለዚህ በዚህም ስም አደረግነው በዚያ እግዚአብሔር በአከበራቸው
ቅዱሳን ስም እስካደረግነው ድረስ በዓሉ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፡፡

የእመቤታችን በዓለ ልደትም በዚሁ መንፈስ የሚከበር በዓል ነው፡፡ነቢዩ ኢሳይያስ ቀደም ብሎ ‹‹ትወጽእ በትር
እምሥርወ እሴይ-ከእሴይ ሥር ወይም ግንድ በትር ትወጣለች››/ኢሳ 11፤6/ ብሎ ስለ ልደቷም ተናግሮላታል፡፡
ይህንንም ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ዘቀዳሚት ድርሰቱ፤ ‹‹ በትረ ሃይማኖት ዘኢትጸንን ምስመኮሙ
ለቅዱሳን-የቅዱሳን መደገፊያቸው ግያዝ የሱነማዊቷን ልጅ ከሞት ያስነሣባት ዘንድ ከነቢዩ ከኤልሳዕ ተቀብሎ
እየተጠራጠረ እንደወሰዳት ያይደለሺ ጽነት ጥርጣሬ የሌለብሽ የሃይማኖት በትር አንቺ ነሽ›› ብሎ ተርጎሞልናል፡፡ አባ
ጀሮምም ይህን የነቢዩን ትንቢት በትር ከግንዱ ላይ ተስተካክሎ የሚወጣ ግዳጂ ለመፈጸም የሚፈልግ ስለሆነ
የእመቤታችን ልዩ መሆን ያሳያል ይላል፡፡ በርግጥም ሊቃውንቱ እንዳሉት ለቅዱሳን መደገፊያ ለአጋንንት ለመናፍቃን
ደግሞ ማባረሪያ የሆነች በትር፤ ድንግል ማርያም፡፡ስለዚህ የእርሷን በዓል ማክበር ከዚህ ጥርጣሬ ከሌለው በረከት
መሳተፍ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአጠቃላይ የበዓላት ይልቁንም በክርስትና ጥቅማቸው ምንድን ነው የሚለውን
እንመልከትና እንፈጽም፡፡
በዓላትን በብዛት እንድናከብር ያዘዘን እግዚአብሔር ነው፡፡የምናከብራቸውም ዝም ብለን አይደለም፡፡በተለይም
በብሉይ ኪዳን በዓላት ብዙ የመሥዋዕት እንስሳትን ማቅረብና መሠዋት በጥብቅ የሚፈጸም ተእዛዝ ነበረ፡፡ የዚያ ሁሉ
መሥዋዕትም ዓላማ ሥርየተ ኃጢኣትን ማስገኘት ነበር፡፡/ዘሌ ፲፯፣፲፩/ በአጭሩ በዓላቱን የማክበሩ ዓላማ ሥርየተ
ኃጢኣትን ማሰገኘት ነው ማለት ነው፡፡በዚህ መሠረታዊ ምክንያት በእያንዳንዱ የኦሪት በዓል እጅግ ብዙ የመሥዋዕት
እንስሳት ይቀርቡ ነበር፡፡በኦሪት በየዕለቱ ሁለት ሁለት ጠቦቶች፣ በየሰንበቱ ሁለት ተጨማሪ የበግ
ጠቦቶች፣በየመባቻው ደግሞ ለየዕለቱ ከሚቀርበው በተጨማሪ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ ሰባት የአንድ
ዓመት የበግ ጠቦቶች፣ አንድ ፍየል ይቀርብ ነበር፡፡ የዓመታዊ በዓላት ደግሞ ከዚህ ሁሉ ይለያል፡፡ለምሳሌ የዳስ
በዓሉን ብቻ ብንመለከት ከዕለቱ፣ ከሰንበቱና ከመባቻዉ እንዲሁም በፈቃድ ከሚቀርቡት በተጨማሪ 73 ወይፈኖች፣
136 አውራ በጎችና ጠቦቶች፣ 10 አውራ ፍየሎች ይቀርቡ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ግን የእህሉን ቁርባንና ሌላውን
መሥዋዕት(ለኃጢኣት ፣ ለበደል፣….የሚባሉትን) ሳይጨምር ነው/ዘጸ ፳፱፣፴፰፣ ዘሌ ፳፬፣፭-፱፣ ዘኁ ፳፰፣፱-፲፭፣ዘኁ
፳፱/፡፡

‹‹ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና››/ዕብ 10፣1 / ተብሎ እንደተጻፈ
እነዚህ ሁሉ ግን ምሳሌዎች ነበሩ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥
አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና
ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ
የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው
ለፍጹማን ሰዎች ነው።›› /ዕብ 5፣ 12-15/ እንዳለው ሊቃውንቱ ለእኛ ወተት ወተቱን እየመገቡ ጠንካራውን
ምግብ አላቀረቡልንም ነበር፡፡ አሁን ግን እስኪ ይህን እንኳ እንሞክረው፡፡

በኦሪት እንደተጻፈው በፋሲካ የሚሠዋው ልዩ የደኅንነት መሥዋዕት በግ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
ምሳሌ ነው፡፡‹‹በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ቆመው ነበር፥ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ። እነሆ
የእግዚአብሔር በግ አለ›› /ዮሐ 1፣ 26/።ተብሎ ተጽፎአልና፡፡በሌሎቹ በዓላት የምናቀርባቸው ደግሞ ቀደም ብለን
እንዳየነው ወይፈኑ፣ አውራበጉ፣ ፍየሎቹ(ወንድም ሴትም ነው የሚቀርበው)፣ ሌላው ሁሉ የማን ምሳሌ ነው
ማለታችን አይቀርም፡፡ ይህ ሁሉ የበዓል መሥዋዕት የቅዱሳን ምሳሌ ነዉ፡፡ ‹‹እንደ በጎች ሊበሉን ሰጠኸን፥ ወደ
አሕዛብም በተንኸን›› /መዝ 44፣12/ ተብሎ ትንቢትም ተነግሮላቸዋልና።ጌታም በወንጌል ‹‹ስለዚህ፥ እነሆ፥
ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም
በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና
በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ
ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል›› /ማቴ 23፣35/ ሲል
እንደተናገረው ቅዱሳን ለእምነታቸው መሥዋዕት ሆነው ቀርበዋል።ደማቸውንም አንዱ እንደ ፍየል፣ ሌላው እንደ
ወይፈን፣ ሌላውም እንደ አውራ በግ አፍስሰዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ የመሥዋዕት ዓይነቶች ለተለያየ የኃጢኣት ማስተሥረያ
እነደነበሩት እነዚህም ደኅነትን ለመፈጸም ከተሰዋው በግ ከጌታ በኋላ ለምናምን ሁሉ ሥርየተ ኃጢኣትን እናገኝ ዘንድ
የሚማልዱ ስለኛም ጭምር ደማቸውን ያፈሰሱ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የሌላው ጊዜ የመሥዋዕት እንስሳ የፋሲካውን
በግ ሊተካው እንደማይችልና የመሥዋዕቱም ዓይነት ፈጽሞ የተለያየ እንደ ሆነው ሁሉ የቅዱሳኑ መሥዋዕትነትና
ሰማዕትነትም እንዲሁ የተለያየ መሆኑና የእነርሱም የጌታን ሊተካ የማይችል መሆኑ ሊዘነጋ አይገባውም፡፡እርሱ
ኃጢኣትህ ተሠረየልህ(ሽ) እያለ ይቅር ሲል እነርሱ ግን የሚያስተሠርዩልን እየጸለዩ ነውና፡፡ ከዚህ በመለስ ግን
የጥንቶቹ ሊቃውንት እንደተረጎሙልን የእነርሱ ተጋድሎና ሰማዕትነት የእኛ የሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች መሥዋዕቶች
ናቸው፤ ስለእነርሱም ሥርየተ ኃጢኣትን እንቀበላለን፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥
የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል ››/ዕብ 4፣6/ ሲል የተናገረው ይህን የሚያረጋግጥልን ነው፡፡
ቀደም ብለን እንዳየነው የመሥዋዕቱ እንስሳት የበዙት ለእሥራኤል ለኃጢኣታቸው አስፈላጊ በመሆኑ እንደሆነው ሁሉ
በሐዲስ ኪዳን ለምንኖር ለእኛም ብዙ ቅዱሳን መኖራቸው ይጠቅመናል፣ ኃጢኣታቸንም ያስተሠረይልናል፡፡
የመሥዋእቱ እንስሳት በሙሉ የተቆጠሩና የታወቁ እንደሆነው ሁሉ ቅዱሳኑም ምን ቢበዙም እንዲሁ የታወቁና
የተቆጠሩ ናቸዉ፡፡

ዳዊት አባታችን ‹‹ዘይኌልቆሙ ለክዋክብት በምልኦሙ፣ ወይጼውዖሙ ለኩሎሙ በበአስማቲሆሙ- ክዋክብትን


በምልዓት ይቆጥራቸዋል፣ ሁሉንም በየስማቸውም ይጠራቸዋል››/መዝ 146፣4/ ሲል እንደተናገረው ክዋክብት
የተባሉ ቅዱሳን ሁሉ በእርሱ ዘንድ በባለሟልነት በቃል ኪዳን የታወቁ በመሥዋዕትነትም የተቆጠሩ ናቸዉ፡፡ ያ ሁሉ የ
መሥዋዕት እንስሳ ፣ የጧቱና የሰርኩ፣ የሰንበቱና የመባቻው፣ የዓመት በዓላቱ፣ የየግለሰቡ የኃጢኣቱ፣ የበደሉ፣
የመንጻቱ፣…በዓይነት በዓይነት እንደሚታወቅ በእረሱም ዘንድ ተቀባይነት እነዳለው ሁሉ የየዕለቱ ቅዱሳንም እንዲሁ
ይታወቃሉ፤ ጸሎታቸውና ምልጃቸውም በእርሱ ዘንድ የከበረ ነዉ፡፡ እመቤታችን ደግሞ ከነዚህ ሁሉ በግንባር
ቀደምነት የምትጠራ ልዩ መሥዋዕታችን ናት፡፡በሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የነበረው የሰረዴሱ
መልይጦን/Melito of Sardis/ በፋሲካ መዝሙሩ ላይ እመቤታችንን የመሥዋዕቱን በግ የወለደችልን ንጽሕት
ሴት በግ (fair ewe) ይላታል፡፡ ስለዚህ የእመቤታችን በዓለ ልደት ከብሉይ ኪዳን ሰዎች የተሻለ ሥርየተ
ኃጢኣት የምናገኝበት ነውና ከነዚያ በተሻለ በዓላችንን መንፈሳዊ አድርገን እናክብር፤ ከመንፈሳዊ በረከትም እንካፈል፡፡
የደራሲውንም ምስጋናና ምልጃ በመሰለ ምስጋና እንዲህ እንበላት፤‹‹ምንተኑ አዐስየኪ ዕሴተ፤በእንተ ኩሉ ዘገበርኪ
ሊተ፤ማርያም ሠናይት ዘታፈቅሪ ምሕረተ፤ሶበሰ ትታአቀቢ ዘዚኣየ ኃጢኣተ፤ እምኢሐየውኩ አሐተ ሰዓተ›› እያልን
ለእርሷ በሚገባ ምስጋና እናመስግናት፡፡ ከዚህ የወጣ ሰው በመጀመሪያ እንደተመለከትነው ብርሂት ቀኝ ዐይኑን
እንደገና እያሳወረ መሆኑን ሊገነዘብ ይገባዋል፡፡ እኛስ ለባሕርያችንን መመኪያ እርሷን የሰጠንን እግዚአብሔርን
‹‹ብርሂት የቀኝ ዐይን ድንግል ማርያምን ›› በዚህ ዕለት የሰጠኸን፣ ከዚህ ዓለም የድንቁርናና የኃጢኣት ጨለማም
የገላገልከን ክብር ምስጋና ለአንተ ይሁን፤ አንተ ለመረጥካትና ላከበርካት ለእናትህም ምስጋና ይድረሳት እያልን
አፋችንን ሞልተን እናመሰግናለን፡፡ ቀይ ዕንቁ እምነት ገንዘባቸው ያልተሰረቀባቸው ወይም በአውሬው ዲያብሎስ
ያልተቧጨሩት ሁሉ አብረውን ያመሰግናሉ፡፡ ቀኝ ዐይናችን ሆይ ዛሬም በአንቺ ብርሃን እናያለንና እናመሰግንሻለን፡፡
እንኳን አንቺን አባትሺን አብርሃምን የሚባርኩት እንደሚባረኩ ልጂሽ አስቀድሞ በሙሴ በኩል በኦሪት ነግሮናልና፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

በዓለ ስቅለት እና በዓለ እግዝእትነ ሲገጣጠሙ ይሰገዳል ወይስ አይሰገድም?

ምንም እንኳ ይህ ጥያቄ በብዙ ሰዎች ዘንድ የተመለሰ ቢሆንም ተደጋጋሚ ጥያቄዎች መምጣታቸው ሁለት ነገሮችን
ስላመለከተኝ እኔም እንደገና በአጭሩ ለመመለስ ጥረት አደርጋለሁ፡፡ የመጀመሪያው ለሁሉም የተሰጠው መልስ እኩል
አለመድረሱ ሲሆን በሁለተኛነት ደግሞ አንዳንዶቻችንም ተደጋግሞ አንድ ዓይነት መልስ በማየት የማረጋገጥ ፍላጎት
ያለን ይመስላል፡፡
ይህን የመሰሉ ተደጋጋሚ ጥቄዎች ሲገጥሙን ነገሩን ማየት ያለብን ከመሠረታዊው የቤተ ክርስቲያን ትውፊትና
አስተምህሮ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ ይህ ጥያቄ የበዓሉን አከባበር የሚመለከት ስለሆነ በቤተ ክርስቲያናችን የበዓላት
ቀኖናም ሆነ ትውፊት መሠረት በዓላት የሚበላለጡ ከሆነ የሚበልጠው የትኛው ነው ከሚለው ቀላል ጥያቄ ልንነሣ
እንችላለን፡፡ በዚሁ መሠረት የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዙት የጌታችን ዐበይት በዓላት ቀጥሎም የጌታችን ንዑሳት
በዓላት መሆናቸውን ለመረዳት አያስቸግርም፡፡

ከሚውሉበት ዕለት አንጻር ካየን ከጌታችን ዘጠኙ ዐበይት በዓላት ውስጥ አምስቱ ዐዋድያት በዓላት (Movable
feasts) ስለሆኑ ዕለት ይጠብቃሉ፡፡ እነዚህም ሆሣዕና፣ ትንሣኤ እና ጰራቅሊጦስ እሑድን ሳይለቁ ሲውሉ ስቅለት
ዐርብን ዕርገት ደግሞ ሐሙስን ባለመልቀቅ ይውላሉ፡፡ የቀሩት አራቱ ማለትም ጽንሰት ወይም ትስብእት፣ ልደት ፣
ጥምቀትና ደብረታቦር ደግሞ ዐዋድያት ስላልሆኑ (Immovable) ወርና ቀን ሳይለዋውጡ በተለያዩ ዕለታት
ይውላሉ፡፡
አሁንም ግን ከእነዚህ ከዘጠኙ ደግሞ ዐራቱ እጅግ የተለየ ክብር አላቸው፡፡ እነዚህም ልደት፣ ጥምቀት፣ ስቅለትና
ትንሣኤ ናቸው፡፡ ልደት፣ ጥምቀትና ትንሣኤ ታላላቅ የደስታ በዓላት ስለሆኑ ደስታው መብልና መጠጥን በማካተትና
ሌሊት በመቀደስ የሚከበሩ ናቸው፡፡ ከዚህ ታላቅነታቸው የተነሣም ሦስቱም የዐርብንና የረቡዕን ጾሞች ሳይቀር
የመሻር ሥልጣን አላቸው፡፡ ልደትና ጥምቀት ዐርብና ረቡዕ ቢውሉ ይበላሉ፡፡ ትንሣኤ ምንም እሑድን ባይለቅም
በሚቀጥሉት 50 ቀናት ውስጥ ያሉትን ረቡዕ እና ዐርብ በሙሉ ያሽራቸዋል፡፡ በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች ትውፊት
ደግሞ ከልደት ጀምሮ እስከ ጾመ ነነዌ ባለው የዘመነ አስተርእዮ ጊዜ ውስጥ ያሉትም ረቡዕ እና ዐርብ ቀናት በሙሉ
በልደቱና በጥምቀቱ (በአስተርእዮው) ታላቅነት ይሻራሉ፡፡ ከዚህም በላይ በትክክል ቀኖናውንና ትውፊቱን ጠብቀን
የምናከብር ቢሆን በእነዚህ ዕለታት ሰው ቢሞት አይለቀስም፤ በአንጻሩ ሰርግና ሌላ ሥጋዊ ተድላ ደስታ ማድረግም
የተከለከለ ነው፡፡ በዓላተ ቅዱሳን ቢገጥምም ማዘከር ይደረግለታል እንጂ በዐቢይነት የሚከበረው የጌታችን በዓል
ነው፡፡ ለምሳሌ በዚህ ዓመት በዓለ ትንሣኤው የሚውለው የዐቢይ ሰማዕት የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ዕረፍት ዕለት
ሚያዚያ 23 ቀን ነው፡፡ ሆኖም በዚህ ዕለት የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ወጥቶ እንደሌላው ጊዜ ንግሥ ተደርጎ ሊከበር
አይችልም፡፡ ይህም ስለማማያመች ብቻ ሳይሆን ስለማይገባም ነው፡፡ በመሆኑም በዓሉ ከትንሣኤ በኋላ ባሉት ቀናት
በአንዱ ይከበራል እንጂ የትንሣኤ ዕለት የሚከበረው የጌታችን የትንሣኤው በዓል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ በዓላት
ማንኛውን ጾምንም ፣ ሐዘንንም ደስታንም ይሽራሉ ማለት ነው፡፡

ልክ እንደነዚህ ደግሞ በዓለ ስቅለት ዐርብን ሳይለቅ ቢውልም ይህም ከዐቢይነቱ የተነሣ እንደ ቀደሙት እንደ ሦስቱ
ራሱን ችሎ የሚሽራቸው ነገሮች አሉት፡፡ እንዚያ ጾምን እንደሚሽሩት ስቅለት ደግሞ በምንም ምክንያት ጾም
ተጹሞባት የማያውቀውንና ከዐሥርቱ ትእዛዛት አንዷ የሆነችውን ቀዳሚት ሰንበትን ሽሮ ከሰንበትነት አውጥቶ የራሱን
ጾምነት አውርሶ ያስጾማታል፤ ስሟንም አስለውጦ ቀዳሚት ስዑር (የተሻረች ሰንበት) አስኝቶ ያስገብራታል፡፡ ስለዚህ
ስቅለት በፍትሐ ነገሥቱ የበዓላት ክብር ቅደም ተከተል መሠረት ከጌታችን ዓበይት በዓላት ቀጥላ የምትከበረውን
ሰንበትን ከሻረ የማይሽረው ሌላ ምንም በዓል ሊኖረው አይችልም ማለት ነው፡፡ የቀደሙት ሦስቱ ከታላቅነታቸውና
ከታሪካዊ ዳራቸው የተነሣ ሌሊት እንደሚቀደሱት ስቅለት ደግሞ በተቃራኒው ምንም ቀን ቢገጥመው ቅዳሴ
አይቀደስበትም፡፡ ለምሳሌ የዚህ ዓመት ስቅለት የእመቤታችን ወርኃዊ በዓል ጋር ስለገጠመ ይቀደስ አይባልም፤
የሚከበረው በሚበልጠው በጌታችን በዓል ስለሆነ፡፡ እንኳን በወርኃዊ የእመቤታችን በዓል ቀርቶ ከዘጠኙ ዐበይት
በዓላት አንዱ ከሆነውና መጋቢት 29 ቀን ከሚከበረው ከትስብእት ጋር ቢደረብ እንኳ በዓሉ ትስብእትን አስቀድሞ
በቅዳሴ አይከበርም፤ ይልቁንም ስቅለትን አስበልጦ በጾም በሰጊድ ይከበራል እንጅ፡፡ ስለዚህ ስቅለት ከዘጠኙ ዓበይት
በዓላትም እንደ ልደት፣ ጥምቀትና ትንሣኤ ሌላውን ይሽራል እንጂ በሌላ በዓል አይሻርም፡፡ እንኳን ራሱን ሊያስደፍር
ሰንበትንም ሽሯልና ፡፡

እንኳን በዓለ ስቅለት ሰሙነ ሕማማትም እነዚህን በዓላት ይሽራቸዋል፡፡ ሆኖም ከሰሙነ ሕማማት ሐሙስ በቅዳሴ
ትሻራለች፡፡ ይህም እንኳ ራሱ ጌታ ሐዲሱን ሥርዓት ስለመሠረተበት ቢሆንም ስግደቱና ሌላው ሥርዓት በሙሉ
በሕማማቱ ሥርዓት የሚሔድ ስለሆነ እንደተሻረ የሚቆጠር አይደለም፡፡ ልክ ቀደም ብለን ልደት፣ ጥምቀትና ትንሣኤ
ሐዘንን ይሽራሉ እንዳልነው ስቅለትም ማንኛውንም ደስታ ትሽራለች፤ ዕለቱ የሐዘን (ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን፣
መከራ መስቀሉን በማሰብ)፣ በለቅሶ፣ በጾም በስግደት የሚከበር ስለሆነ የሌላ በዓል ጠባይን በፍጹም ሊወርስ
አይችልም፡፡ እንደ ትውፊታችንማ ቢሆን እንኳን የራሱ የስቅለት ዕለት የሚውል በዓል ቀርቶ በዐቢይ ጾም የሚውሉ
ዐመታዊ በዓላት እንኳ በንግሥ፣ በማኅሌትና በከበሮ በሌላ ወቅት እንዲከበሩ ነበር የተወሰነው፡፡ ምክንያቱም ልክ
በዓለ ሃምሳን እንደ አንዲት ዕለተ ሰንበት ቆጥረን እደምናከብረው ዐቢይ ጾምም እንደ አንድ ዕለት ጾም በአንድ
ሥርዓት ብቻ እንዲጾም የተወሰነ ነው፡፡

በጥንቱ ዐለም አቀፍ ሥርዓትና ትውፊት ከሆነ በዐቢይ ጾም ፈጽሞ ቅዳሴም አይቀደስም ነበረ፡፡ ምክንያቱም አንደኛ
ጌታ አርባውን ቀን እንደ አንድ ቀን ከቆመ ሳይቀመጥ ከዘረጋም ሳይጥፍ ስለጾመው፡፡ ምንም እንኳ በዐቢይ ጾም
መቀደስን ግብጽ ብትጀምረውም በእኛ ጾመ ድጓ እና ሰዓታት ስለሚቆም በቅዳሴ ማሳረጉን ብዙ ሊቃውንት
ይስማሙበታል፡፡ ከዚህ አልፎ ግን በከበሮ በማኅሌት ማሸብሸብ ጾም ከመሻር ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡ ለዚህም
ነበር የጥንተ ስቅለቱ የመጋቢት መድኃኔ ዓለም በዓል በጥቅምት መድኃኔዓለም፣ የመጋቢት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
በዓልም በጥቅምት፤ መጋቢት ዐሥር የነበረው መስቀሉ የተገኘበትም በዐል ከደመራ ሥርዓት ጋር ተገጣጥሞ ቅዳሴ
ቤቱም ስለሆነ መስከረም 17 እንዲከበሩ የተወሰነላቸው፡፡ ዛሬም በታላላቅ ቦታዎች ይህ ሥርዓት እንደጸና ይገኛል፡፡
ይህን ሁሉ የምዘረዝረው ግን እንኳን በዐለ ስቅለት ዐቢይ ጾምና ሕማማት እንኳ ምን ያህል የተከበሩ ከባድ በዓላት
እንደሆኑ ለመጠቆም ነው፡፡ በሥርዓታችን መሠረት ከሆነ በሕማማት ቤተ ክርስቲያን ለመሔድ ግብረ ሕማማት
ለመስማትና ያቅሙን ያህል ለመስገድ ያልቻለ ሰው ቢኖር ከበዓለ ሐምሳ በኋላ ሰኔ ጾም እንደገባ ግብረ ሕማማትም
እንዲሰማ ስግደቱንም እንዲሰግድ ታዝዟል፡፡ ስለዚህ እነዚህ በዓላት ምን ያህል ታላቅና ከሌሎቹ ጋር ሊነጻጸሩ
እንደማይችሉ በደንብ መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡

ከመሠረቱ የበዓሉ ምንነት ከገባን የስቅለት ዕለት በተደረበ በዓል ምክንያት ይሰገዳል አይሰገድም የሚለው ክርክር
ሊፈጠር አይችልምና፡፡ ስለዚህ በስቅለት ዕለት ቀርቶ በሰሙነ ሕማማት በየትኛውም ዕለት እንዳይሰገድ የሚከለክል
ምንም ዐይነት በዓል የለም፤ ሊኖርም አይችልም፡፡ ቢኖር ኖሮ ቅዳሴም ይቀደስ ነበር፤ ያ ሁሉ ሥርዓትም አይሠራም
ነበር፡፡ የሆነው ሆኖ ግን በዕነዚህ ዕለታት ምክንያት ጸብና ክርክር መነሣት ስለሌበት ተለያይቶና ተጣልቶ በልብም
እየተናናቁና እየተነቃቀፉ ከማክበር ተስማምቶና ተከባብሮ አንዱን ማድረጉ የተሻለ መሆኑን በማሰብ ራስን ከክርክርና
ከጸብ መቆጠቡ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ በዓሉም የሚሻው ዐቢይ ነገር ነው፡፡ በእልህ ከሚቀርብ ማንኛውም
አምልኮት በፍቅር የሚፈጸም መታዘዝ ይሻላልና፡፡

ርግብ ሻጮቹ
ጌታችን ወደ ቤተ መቅደስ ከገባ በኋላ ሻጮችንም ሆነ ገዥዎችን አባርሯል፡፡ ወደ ርግብ ሻጮቹ መቀመጫ ከደረሰ
በኋላ ግን ገበታቸውን ገልብጦ ‹‹ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፏል፡፡ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ
አደረጋችኋት›› ብሏል፡፡ በዚህም ንግግሩ ወንበዴዎች ያላቸው ‹‹ ርግብ ሻጮች›› መሆናቸው ታውቋል፡፡
ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እንደተረጎሙት ‹‹ ርግብ›› የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ስለሆነች ‹‹ ርግብ ሻጮች››
የተባሉት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ሀብተ ክህነትን ለምድራዊ መኖሪያ ብቻ የሚገለገሉበት ናቸው፡፡ እነዚህ ደግሞ ከጥንት
ጀምሮ ገበታቸውን ደርድረው በቤተ መቅደሱ አካባቢ ሲሸጡ ይኖራሉ፡፡ ክህነታቸውን፣ የተሰጣቸውን ጸጋና የቤተ
ክርሰቲያን ኃላፊነት ሁሉ ለገንዘብና ለገንዘብ ብቻ የሚጠቀሙት ሁሉ የዘመናችን ርግብ ሻጮች ናቸው፡፡የእነዚህን
ሰዎች ገበታ ጌታ ይገለብጠዋል፤ ያባርራቸዋልም፡፡ ‹‹ እውነት እውነት እላችኋለሁ አላውቃችሁም ›› /ማቴ 7 ፡ 22/
እላቸዋለሁ ብሏልና ፡፡
በርግጥ ይህ ነገር አገልግሎት ፈጽመው ከቤተ ክርስቲያናቸው ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ የሚቀበሉትን የሚመለከት
እንዳልሆነም ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ እነዚህ ‹‹ የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሠር ›› /1 ኛ ቆሮ 9 ፡ 9/ ተብሎ
የተጻፈላቸው አገልጋዮች ናቸውና አይመለከታቸውም፡፡
ርግብ ሻጮቹ እነማን ናቸው? በፈውስና በተአምራት ስም የቤተ ክርስቲያኒቱን ዐውደ ምሕረት ይዘው ንግዳቸውን
የሚያጧጡፉትን አይደለምን? በመንፈሳዊ ዛር ከብረው ሰውን ሁሉ በቅቻለሁ እያሉ ባለትዳሩን እያፋቱ፣
ዕጮኛሞቹን እየለያዩ በሀብተ መንፈስ ቅዱስ ስም የሚነግዱት አይደሉምን? ቤተ ክርስቲያን በማሠራት፣ ገዳማትን
በመርዳትና በመሳሰሉት ሰበብ አስባቦች እያሰባሰቡ የራሳቸውን ቤቶች የሚገነቡትን፣ ንግዳቸውን የሚያጧጡፉትን
አይደለምን? በክህነትና በአገልግሎት ሰበብ ፖለቲካቸውን የሚቸረችሩበትን አይደለምን ?በቤተ ክርስቲያን ልማት
ሰበብ ራሳቸውን የሚያለሙትን አይደለምን? እኔን እግዚአብሔር ያመለክተኛል፤ እኔ በማዘዝህ ብቻ ሥራ እያሉ
ከባለጸጎቹ ተጠግተው ቤት አሠርተው የቤተ ሰቡ የጸሎት አባት እየተባሉ በሀብተ መንፈስ ቅዱስና በበቁት ቅዱሳን
ስም የሚነግዱትን የአንዳንድ ባለጸጎች የግል ጠንቋዮችን አይደለምን? የሰውን አለማወቅ ተጠቅመው ለንስሐ እንኳ
ትልልቅ ገንዘብ የሚሰበስቡትን አይደለምን? በአገልግሎት ሰበብ የየራሳችንን ግዛት እያስፋፋን የእግዚአብሔርን
መንግሥት ከሰዎች የምናጠበውን አይደለምን? እስኪ ዛሬ በክህነቱ የማይነግድባት የተባረከው ማን ይሆን?
የተሰጠችውን ትንሽ ጸጋ ሳይቀር ለጥቅሙ የማያመቻቻትስ? እረ ለመሆኑ ዛሬ በእኛ ዘመን ሰዎች በእጅጉ የሚከፋቸው
መቼ ነው? በውኑ የቤተ ክርስቲያን ክብር ሲዋረድ ወይስ የእኛ ክብር ትንሽ ሲነካ? የእኛ ጥቅም የሚቆም ሲመስለን
ወይስ የቤተ ክርስቲያን? ማን ይሆን ዛሬ ርግቡን የማይሸጥ? በየሰበካው ያሉት ጠቦች ምክንያታቸው ምን ይሆን?
አንዱ ተባርሮ አንዱ የሚመጣበትስ ምክንያቱ?
ርግብ ጸጋ እግዚአብሔር እንደዚህ ዘመን በቤተ ክርስቲያን የሚሸጥበት ዘመን ይኖር ይሆን? እኔ እንጃ! በርግጥም
የርግብ ሻጮች ዘመን፡፡ ለዚህ ነው ጌታ በዚህ የተጠመዱትን ሁሉ የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት ያለው፡፡
ምክንያቱም ሰዎቹ ወንደዴዎች ቢሆኑም የሚፈጸመው ተግባር መንፈሳዊ የሚያሰኝ የሚያስመስልም ቅባት ስለተቀባ
ደግሞ ሕዝቡ አይለይምና ‹‹ ዋሻ ›› መደበቂያ፣ ማታለያ ለመሆን በቅታለች፡፡ ስለዚህ ዋሻ ያላት ግብራችሁ የወንበዴ
ቢሆንም አንደኛ ክህነታችሁ ከእግዚአብሔር ስለሆነ እውነተኛ መስላችሁ ትኖራላችሁ ለማለት ነው፡፡ አሁንም እየሆነ
ያለው ይኸው ይመስላል፡፡ ጌታ ጅራፉን ገምዶ በሚመጣ ጊዜ ግን የሚቆመውን እንጃ፡፡
እርሱም ይህን አውቆ ይመስላል፤ ‹‹ እንክርዳዱን እንነቅላለን ስትሉ ስንዴውንም አብራችሁ እንዳትነቅሉ ተውት
እስከመከር ጊዜ አብሮ ይቆይ›› /ማቴ 13 ፡ 29/ ሲል ያዘዘው፡፡ ልክ ነው ሁሉም እስከ እርሱ መምጣት በትዕግሥት
ይጠብቃል፤ እንክርዳዱን ከስንዴው፣ ምርቱንም ከገለባው የሚለየው ባለመንሹ እርሱ ነውና፡፡ ልክ ነው እርሱ
ገበታችን እስኪገለብጥ ድረስ ርግብ ሻጮቹ የሆንን በቤተ መቅደሱ እንኖራለን፤ የዋሐን ምእመናንንም እግዚአብሔርን
ያገኙ እርሱንም ያገለገሉ እየመሰላቸው ርግብ ሻጮቹን ሲያከብሩ ይኖራሉ፡፡ ለነገሩ ባለቤቱ ‹‹በዚያን ጊዜ ኢየሱስ
ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው፦ ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል። ስለዚህ
ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ።›› /ማቴ 23 ፡
1- 3/ ሲል ያስጠነቀቀንም ክህነትንና ሰብአዊ ባሕርይን ለይተን ተረድተን ስሕተት የመሰለንን እያወራን እርሱ
በሰጠው ጸጋ ሳንጠቀም እንዳንቀር ነውና እውነታውን ተረድተን በሚያስፈለገን ተጠቅመን ለመንግሥቱ እንድንበቃ
በቸርነቱ ይርዳን፡፡

Like

ራስዎን ፍለጋ ቢመጡስ?

ራስዎን መፈለጊያ ኩራዙን ደግሞ እኛ አዘጋጅተንልወታል፤ ልዩ ዐውደ ርእይ፡፡


እንደእኔ ከሆነ ይህ ዐውደ ርእይ ‘ልዩ’ የሚለው መግለጫ የሚስማማው ይመስለኛል፡፡ ልዩ የተሰኘው ግን ብዙ
ትዕይንቶችን ስለያዘ አይደለም፤ እንዲያውም እንዳሁኑ አጭር ዐውደ ርእይ አሳይተን የምናውቅ አይመስለኝም፡፡
በሚታየው ቁስ ብዛትም አይደለም፤ እርሱም ቢሆን እጅግ የተመጠነ ነው፡፡ ይህ ዐውደ ርእይ በአራት ትእይንቶች
የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ ምንነት አስቀድሞ መሠረታዊ ተልእኮዎቿን ሐዋርያዊነትንና ክርስቲያናዊ ተጋድሎን
አስከትሎ ድርሻችንን እንድንጠይቅ የሚጋብዝ አጭር ዐውደ ርእይ ነው፡፡ ታዲያ ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው ካሉ፤
ልዩ የሚያደርገው ከላይ የጠቀስኳቸውን በትምህርት፣ በጽሑፍ ወይም በጥናታዊ መድረክ ሊቀርቡ የሚገባቸውን
ረቂቅ ሀሳቦች በዐውደ ርእይ ለማሳየት ደፍሮ በመነሣቱ ይመስለኛል፡፡ በአጭር ቋንቋ ለዐውደ ርእይ የሚከብዱ
ሀሳባዊ ነገሮችን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ተጠቅሞ በቀላሉ በዐውደ ርእይ መልክ አዘጋጅቶ ልብዙ ሰዎች
መቅረቡ ልዩ ካሰኙት መሠረታዊ ነገሮች ግንባር ቀደሙ ይመስለኛል፡፡ ሌሎች ተጨማሪ ነገሮቹን ግን የመጣ ሰው ብቻ
ቢያገኛቸው የሚሻል ይመስለኛል፡፡ እንግዲያውስ ወደ ልዩ ዐውደ ርእዩ ቶሎ ይምጡ እልዎታለሁ፡፡
ነገር ግን ዐውደ ርእይ የሚያዩ እንዳይመስልዎት፤ ማየት የሚችሉ ከሆነ የሚያዩት ራስዎን ነው፡፡ ልዩ ያሰኘው ሌላው
ነገር ደግሞ ይህ ይመስለኛል፡፡ በአንድ ዐውደ ርእይ ብዙ ሰዎችን ራሳቸውን እንዲያዩ ለመርዳት ስለሚታትር፡፡
እንግዲያውስ ይምጡና ራስዎን ይፈልጉና ይዩ፡፡ ይህን ስልዎት ፎቶዎን የሰበሰብን እንዳይመስልዎት፡፡ በጥንቃቄ
እያደመጡ ከተመለከቱ ግን ያለጥርጥር ራስዎን ያያሉ ብዬ አምናለሁ፡፡ ዐውደ ርእዩን አይተው ሲጨርሱ ራስዎን ካላዩ
ወይ አልገባዎትም፤ ካለበለዚያም አልተመለከቱትም ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡ ጉድለቱ ከእኛ ከሆነም አይተው ሊነግሩን
እስከመጡ ድረስ እኛ ልንሰማዎት ዝግጁዎች ነን፡፡ ለሁሉም ይምጡና ራስዎን ይፈልጉ፡፡ ሌሎቹን አይፈልጉ
ባልልዎትም የተዘጋጀው ራስዎን ፈልገው እንዲያገኙ ነውና ይምጡ ብዬ በአክብሮት አጋብዘወታለሁ፡፡
አህያና በሬ
ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
ስብከትና ሰባክያን በአሁኑ ጊዜ ያሉበትን ደረጃ ለመረዳት በየዘመኑ ያለፉበትን ሁኔታ ከተፈቀዱበት ተፈጥሮአዊ ጠባይ
አንጻር ማየትን ይሻ ነበር፡፡ ሆኖም ይህን ባለማድረጋችን የቀደመውን ጊዜ ለመገመት ከባድ የሚያደርገው
አይመስለኝም፡፡ የሐዋርያትንና የተከታዮቻቸውን /ዓለምን ትተው፣ ራሳቸውን ክደው/፣ እሥራት ግርፋቱን እንደ
ሹመት እንደ ሽልማት፣ መከራውን ሁሉ እንደቀሚስ አጥልቀው እንደ ካባ ደርበው፤ በእውነት አጊጠው፣ በጽድቅ
አሸብርቀው፤ ሰማዕትነትን /በአሕዛብና ባላመኑ ነገሥታት ተሰቃይቶ መሞትን/ ለክብር አክሊል የሚደረገውን ሩጫ
የመጨረሻ ውድድር አድርገው የሮጡትን፣ የመከራውንም ጽዋ በደስታ የጨለጡትን፣ ስለሚያስተምሩት ወንጌል
ማንኛውም መከራና ፈተና በደስታ የተቀበሉትን እነዚያን የቀደሙትን ከዋክብት የዛሬው ርእሴ አይመለከታቸውም፡፡
እንኳን እነርሱን ለእኛም ዘመን ቀረብ ያሉትን በዚህ ዓለም እየኖሩ፣ በሕግ ተወስነው /ትዳር መሥርተው/፣ ልጅ
አሳድገው፣ ለሚኖሩበት ማኅበረሰብ አርአያ ሆነው፣ ጽድቃቸውን ሳያቃልሉ፣ በወንጌልም ሳይመጻደቁ፣ ሥጋቸውን
ለነፍሳቸው ለማስገዛት እየታገሉ፤ አስገዝተውም የአቅማቸውን ዘርተው ያጨዱትን በብዙ አይመለከታቸውም፡፡ እነዚህ
ሁሉ በሬውን ከበሬ ጋር ያረሱ ስለሆኑ የሚገመገሙት መሬቱን አለሳልሰው ለዘር ባዘጋጁት የመሬት መጠን፣ በዘሩትም
መጠን እንጂ ገና ሲጀመር በሬውን ከአህያ ጠመደው በማረስ አይነቀፉም፡፡ እነዚህ በበሬ አርሰው፣ በበሬ አበራይተው
አዝመራውን የሰበሰቡ ቅዱስ ጳውሎስ እንደገለጸውም ደመዎዝ /ዋጋ/ የሚጠብቃቸው፤ በኖሩበት ምድርም አፋቸው
አይለጎም የተባለላቸው ናቸው፡፡ 1 ኛ ቆሮ.9÷9፣ ዘዳ.25÷4 ስለዚህ የእኔ ጽሑፍ ለሚመለከታቸው ብቻ
ይድረስልኝ፡፡
የእኛ ዘመን የስብከት አገልግሎት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንጻር ስናየው ግን ትላልቅ ፈተናዎች የተጋረጡበት
ይመስላል፡፡ “ስብከት” የሚታየው /የሚሰማው/ በሰባኪው ነውና ስለስብከት መናገር ስለ ሰባኪ መናገር መሆኑ
የሚዘነጋ አይሆንም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በተለይ በብሉይ ኪዳን የተሰጡት ትዕዛዛት በሐዲስ ኪዳን ላለን ሰዎች ምሳሌ
መሆናቸውን ሐዋርያት ተርጉመውልናል፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በኦሪት ዘዳግም 25÷4 ላይ “እህል
የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሠር” ያለው ስለ እኛ ስለ አገልጋዮቹ ነው ሲል የተረጎመው፡፡ 1 ኛቆሮ.9÷9 በዚሁ
መሠረት በሬው የአገልጋዩ ወይም የሰባኪው ምሳሌ ነው ማለት ነው፡፡ በበሬ የተመሰሉትም እንዲሁ አይደለም፡፡ በሬ
በቀዳሚነት በኦሪቱ ትዕዛዝ መሠረት ከንጹሐን እንስሳት ወገን ነው፡፡ዘሌ 11፣3-23 ለመሥዋዕት ከሚዘጋጁት
በቀዳሚነት የሚጠራው እርሱ ነው፡፡ዘሌ 22፣26 በሬ ከአዘመረው አዝመራ ገለባውን፣ ጭዱን እንጂ እህሉን
አይበላም፤ ዘሩንም አይቆረጥምም፡፡ የአዝመራውም ባለቤት አይደልም፤ የሚያገለግለው ገበሬውን ነው፡፡ ንጹሐን
አገልጋዮች /ሰባክያን/ በበሬ የተመሰሉት ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሔር በኦሪት ከሰጣቸው የእርሻ ትዕዛዛት መካከል አንዱ
“በበሬና በአህያ በአንድነት አትረስ” /ዘዳ.22÷4/ የሚለው ነውና፡፡ የዚህ ምክንያቱም ብዙ ነው፡፡ ከንባቡ አንጻር
ስናየው እያንዳንዱ እንስሳ የራሱ ተፈጠሮአዊ ክብርና አቅም ስላለው አንዱን ከሌላው ጋር አጣምዶ መጉዳትም ሆነ
ክብሩን ማዋረድ የተከለከለ በመሆኑ ነው፡፡ ዋናው መልእክት ግን ቀደም ብለን እንዳየነው ምሳሌያዊ ነው፡፡ እንደ በሬ
ሁሉ አህያው የራሱ ምልክትነትና ወካይነት አለው፡፡ ሲጀመር አህያ ከርኲሳት እንስሳት ይመደባል፤ ለመሥዋዕት
አይሆንም፤ እንኳን ለእግዚአብሔር ሊሠዋ ሰውም እንዳይመገበው በኦሪት ተከልክሏል፡፡ አህያ የአዝመራውን ገለባም
አይበላም፤ ይልቁንም ዘሩን /በተለይ ገብስ/ ይቆረጥማል እንጂ፡፡ በዚህም አዝመራውን ለባለቤቱ አይጠብቅም፣
ከተመቸው ይበላዋል፡፡ ከሚበላው የሚበዛውም ቆሻሻ ነው፤ ከቆሻሻ በተለይ ከሰው የሚወጣው ይስማማዋል፡፡ ይህን
በሌላ አንጻር ለመግለጽ ይመስላል ጠቢባኑ “ለአህያ ማር አይጥማትም” ያሉት፡፡ እውነት ነው አይጥማትም፡፡ በዚሁ
መሠረት “በሬና አህያ በአንድ ላይ አትረስ” የሚለውን ስናየው ምሳሌው የያዘው ትርጒም ግልጽ ይሆናል፡፡ ቅዱሱን
ከርኲሱ አታቀናጅ፣ ዘሩንም ገለባውንም አታስበላ፡፡ የሚበላውንና የማይበላውን፤ መሥዋዕት የሚሆነውንና
የማይሆነውን ቀላቅለህ አታቅርብ የሚል መልእክት ይኖረዋል፡፡ ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ /150-215/ እና
ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ /335-394/ የተባሉ ሊቃውንት በዚህ መንገድ ተርጉመውልናል፡፡
በእኛ ዘመን ያለውን አብዛኛውን ስብከት ስንመለከተው ይህን ትዕዛዝ በማፍረስ ሁለቱን አንድ ላይ ጠምዶ የሚያርስ
ነው ማለት ይቻላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንደ አህያው ዘረ ቆርጥምነት /ጥቅምን፣ ገንዘብንና ሀብትን/ ማካበትን ተቀዳሚ
ያደረጉ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ስፍራ ለመያዛቸው ምስክር መጥቀስ አያሻም፡፡ ስብከቱ፣ ጠበሉ፣ …. ሁሉ ዛሬ
የየዋሐንን ልቡና በማዛል ገለባውን ለባለቤቱ ትቶ ዘሩን ለመቆርጠም ዓይነተኛ መንገዶች ከሆኑ ዋል እድር ብለዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ጠበልና ገንዘብ፣ ስብከትና ጥቅም፣ ልብሰ ምንኩስናና ቢዝነስ ተጠምደው እየታረሱ ነው፤ አህያና በሬው፡፡
ዝናው፣ ታዋቂነቱ፣ ከማስተማሩ፣ ቲፎዞና ደጋፊ አድናቂ ማፍራቱ ከአገልግሎቱ በቀንበር የተጠመደ ብቻ ሳይሆን
በተፈጥሮ አብረው የበቀሉ ዛፎች እስኪመስሉ ላይለያዩ ተጣብቀዋል፤ ቅዱስና ርኲስ እንደማኪያቶ ተቀላቅለው የወተቱ
ንጣት በቡናው ጠቁሮ ወይቧል፤ ጣዕሙም እንደዚያው መካከለኛ ሆኖአል፡፡ ማኪያቶ ለለመደው ትውልድ ማኪያቶ
የመሰለ አገልግሎት ቀርቦለታል፡፡ ጥቁሩን ከነጭ ጣፋጩን ከጎምዛዛ የቀላቀለ፡፡ የበሬው ሥጋ ከአህያው ሥጋ ጋር
ከተቀላቀለ የበሬውን ሥጋ ለይቶ ለመሥዋዕት ማቅረብ አይቻልም፤ አማራጩ ሁለቱንም ለውሻ፡፡ የአህያ ሥጋ /ቻይና
አትስማኝና/ ለውሻና ለጅብ ይጣላል እንጂ አይበላም ነበር፡፡ ከበሬ ሥጋ ጋር ያገኘው ግን በሬ ነው እያለ ይበላዋል፡፡
በእኛ ሀገርም ይህን የሞከሩ ሥጋ ቤቶች ብቅ ብለው ነበር፡፡ የበሉት ሰዎች ግን እስካሁን አላወቁም፡፡ በእኛው ዘመን
አገልግሎትም የሆነው ይሔው ነው፡፡ የበሬ ሥጋ እያልን የአህያውን ቀላቅሎ ማቅረብ፤ አሳስቶ ማብላት፤ ርኲሱን
/እግዚአብሔር የጠላውን/ በቅዱሱ /እግዚአብሔር በወደደው ቀላቅሎ መሸቀጥ፡፡ ሐዋርያው “የእግዚአብሔርን ቃል
ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና” /2 ቆሮ.2÷17/ የሚለው መሸቃቀጥ የነበረ ብቻ ሳይሆን
የአብዛኛው ተግባር መሆኑንም የሚያረጋግጥ ማኅተም በመሆኑ ነው፡፡
ርግጥም አሁን ያልተቀላቀለ አገልግሎት ማግኘት የሚቻል አይመስልም፡፡ መዝሙሩ ከዘፈኑ፣ ተረቱ፣ እንቶፈንቶው፣
የሳቅ የስላቅ ንግግሩ፣ ዋዛ ፈዛዛው ከቃሉ ከስብከቱ ተቀላቅሎ ይሸቀጣል፡፡ ሦስቱ የስብከት አላማዎች ያላመኑትን
ማሳመኑ አድናቂ ከማፍራት ጋር ተቀይጧል፤ ያመኑትን ማጽናቱ መጠበቁ /እውቀት ማስጨበጡና የማይነቃነቁ
ማድረጉ/ ድንበር በማፍረስ /ልዩነቱን በማሳካት/ ተለውጧል፣ የጸኑትን መቀደሱ ማንጻቱ /ለቅድስና ማብቃቱም/ ለምን
ችግር አለው በሽታ ረክሷል፡፡ አንዳንድ ጊዜማ መድረኩ የቲያትር ቤት፣ አገልጋዩም ኮሜዲ ይመስላሉ፡፡ ሌላ ጊዜ
ደግሞ ከፉከራና ከቀረርቶ ያልተናነሱ ድንፋታዎችም ይታከሉበታል፡፡ ለእነዚህ ደግሞ ሞት ያለና ያልተቋረጠ
ጭብጨባ ያስፈልጋቸዋል ይባላል፡፡ ሕዝቡም እንደ ኮሚኒስት ደጋፊ እጁ አስኪላጥ አጨብጭቦ ይደግፋል፡፡ እነዚህ
ሁሉ ለጌታ ያስፈልጋሉ፤ ለክብሩ ነው እየተባለ ድጋፍ ይሰጣቸዋል፡፡ ዝምታ አርምሞ ሲሆን ለጌታ አይውልም ሞቅታ፣
ጩኸት ሲሆን ደግሞ ለጌታ ያስፈልጋሉ ይባላል፡፡ ሁኔታውን ለሚያየው ሰው የድሮው እግዚአብሔርና የአሁኑ
የተለያዩ ወይም ራሱ ከሆነ ደግሞ ፍላጎቱም፣ መሥዋዕቱም ራሱም የተለወጠ ይመስላል፡፡ ለነገሩስ እርሱ ራሱ “እኔ
አልለወጥም” ብሎአል፡፡ ሚል.3÷6 እንግዲያውስ የተለወጡት ወይም እየተለወጡ ያሉት ሰዎቹ መሆናቸውን ልብ
ይበሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ለሞራል፣ ለክብር፣…. የቆመው ሰው /ተናጋሪው/ የሚፈልጋቸው እንጂ እግዚአብሔር
የሚፈልጋቸው እንዳልሆኑ የታወቀ ነው፡፡ በንጽሕና በትሕትና፣ በፈሪሐ እግዚአብሔር ደምቆ በመንፈሰ እግዚአብሔር
ከብሮ ከመታየት፣ በአለባበስ ብቻ ተውቦ በኘሮቶኮል ደምቆ ወደ አትሮንሱ መንደርደር የተለመደ ሆኖአል፡፡
እግዚአብሔር ፕሮቶኮሉን፣ መታጀሩን /በከበረ ልብስ መጀነን/ ባይቀበልም በመድረኩ ላይ ከአንዳንዶቹ የሚቀርብለት
የተለመደ መሥዋዕት ሆኖአል፡፡
ንግዱና አገልግሎቱ፣ ማስመሰሉ፣ መተወኑና መግባባቱ፣ ከማስተማሩ፣ ኑፋቄው ደግሞ ጥርጥሩን ባዕድ አስተሳሰቡ
ከስብከቱ ጋር ተቀላቅሏል፡፡ እንደተጻፈው ለዓለም የሚመች ከንቱ መለፍለፍ /1 ኛጤሞ.6÷20/፡፡አንዳንዶቹ ደግሞ
ራሳቸውን የሚመለከቷቸውን ጉዳዮች አይሰብኩባቸውም ወይም ቢጠየቁም ዋና ጉዳዮች አይደሉም ይላሉ፡፡ ይህ ሁሉ
በራስ ፍላጎት የመነዳት ጣጣ አህያውንም የማሰልጠን ነው፡፡ /እስኪ ስለ ገንዘብ፣ ዝና፣…ፈተናን የተሰጡ ትምህርቶችን
ቁጠሯቸውና እንተዛዘብ/፡፡
“ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና÷ አንዳንዶችም ይህን ሲመኙ÷ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ስቃይ
ራሳቸውን ወጉ” /1 ኛጤሞ.6÷10/ የተባለውን ዛሬ በዓይን ማየት ይቻላል፡፡ በምዕራቡ ዓለም የምንሰማት
በወንጌል የማትረፍ ንግድ ተሟሙቃለች፡፡ በዚያ በምዕራቡ I00 times formula ትባላለች፡፡ “ስለ እኔ
እናቱን አባቱን…. የተወ መቶ እጥፍ ይቀባላል” ማር 10፣30 የሚለውን 1 ዶላር የሰጠ 100 ዶላር ከኢየሱስ
ይቀበላል እያሉ ብዙ የከበሩ አሉ፡፡ አንድ የድሃ ልጅ የሚሰጠው ቢያጣ ታጣፊ አልጋውን በ 20 ዶላር ሸጦ ሰጠ፡፡
በ 100 ተባዝቶ 2,000.00 ዶላር ለማግኘት፡፡ ልጁ ጉዳዩን ለሚዲያ ሲያጋልጥ ብሩን ከሰጠ ሁለት ዓመት ሆኖት
ነበር፡፡ እርሱ እንዳለው እንኳን 2,000.00 ዶላር ሊያገኝ ቀርቶ አስከተናገረበት ቀን ድረስ መሬት ላይ ከመተኛት
ያተረፈው አልነበረም፡፡ ይህ ሁሉ የብልጽግና ወንጌል /prosperity gospel/ ይባላል፡፡ የእኛስ ሀገር ምን
ቀረው? እውነት ለመናገር በዚህ በኮምፒውተር ያለው አሠራር የሚቻል ቢሆን ኑሮ ዛሬ ብዙ ሰባኪ ከአእምሮው
ሊጠረግለት /uninstall ሊደረግለት/ የሚገባው ብዙ ሶፍት ዌር ነበረው፡፡ ከየትም ሳያስበው የቃረመው
/download ያደረገው/ አህያና በሬ በአንድ አእምሮ፣ በአንድ ልብ፣ በአንድ ሰው ውስጥ ተጠምደዋልና ይፈቱ፡፡
የወንጌሉ እርሻ የሚፈቀደው በሁለት በሬ ብቻ ነው፡፡ ምንም ዓይነት የአህያ እርሻ አያስፈልግምና እባካችሁን
አህያችሁን ፍቱልን፤ ወይም አስፈቱልን፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሰፊው ግልጽ አድርጎ እንዳስቀመጠው፡- በሀገራችን በኢትዮጵያ የምንገኝ ሁላችን ራሳችን
ለራሳችን የሰጠነው የተለያየ ማንነት ቢኖርም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ልዩነታችን እንደ ዓይን እና ጆሮ፣ እጅ እና
እግር ወይም እንደ ልብና ኩላሊት ከመሆን ያለፈ አይደለም፡፡ አንዳንዶቻችን የተስማማንን ማኅበረሰባዊ የማንነት
መለያዎች ለራሳችን ብንሰጥና በዚያም መለያ ብንመደብ እንኳ ካወቅንበት ይህ ልዩነታችን በአንድ አካል ውስጥ
እንዳሉ ብልቶች በየተሰጠን ጸጋ፣ ሙያና ችሎታ የምንጠቃቀምበት የምንከባበርበት እንጂ የሚጎዳን ሊሆን አይችልም፡፡
በመጀመሪያ በተፈጥሮ ሰው ሆነን በመፈጠራችን ልዩነት የሌለን መሆኑን ማስታወስ ነው፡፡ ያም ባይሆን ደግሞ
ልዩነትን እንደተፈጥሮ ጸጋ ብንወስደው እንኳ ይህ የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ አይደለም፡፡
ቅዱሱ ሐዋርያ በደንብ እንደገለጸው ዓይን እጅን አታስፈልገኝም ልትለው የማትችለውን ያህል በሀገራችንም አንዱ
ሌላውን የኅብረተሰብ ክፍል አታስፈልገኝም ቢለው ተፈጥሮአዊ አይደለምና ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ምንም
እንኳ ጥርስ ምላስን እንደሚነክሰው፣ እግርም እግርን እንደሚረግጠው ወይም እጅ እጅን እንደሚያቆስለው
ካለበለዚያም ጣትም ዓይንን እንደሚያስለቅሰው ሁሉ በቀደመው ታሪካችን አልፎ አልፎ የእርስ በርስ ወይም የብልት
ከብልት መጎዳዳት ተከስቶ የነበረ መሆኑ ቢታወቅም ይህም ከልዩነት የተነሣ ብቻ ሳይሆን ከተፈጥሮም ጠፍቶ
የማያውቅ በመሆኑ በብልቶቻችን ዘንድ በእንደዚህ ዓይነት ምክንያት እስከመጨረሻው መለያየት ሆኖ እንደማያውቀው
ሁሉ ራሳችን ሆን ብለን ካልፈቀድንለት በስተቀር እኛንም እንዲህ ዓይነት ታሪካዊ ምክንያቶች ሊለያዩን አይችሉም፡፡
ምክንያቱም እጅ ዓይንን ብቻ ሳይሆን እጅንም የሚጎዳ መሆኑ እንዲህ ያለ ጉዳት የእርስ በርስ መሆኑንም እንድንረዳ
ፈጣሪ የሰጠን የማስተዋል ወይም የመመርመሪያ መንገድ ይመስለናልና፡፡
ስለዚህም ታሪካዊ ክስተቶችን እያነሣንና እየጣልን በቁስል ላይ ቁስል ከምንጨምር ይልቁንም በአንድ አካል እንዳሉ
ብልቶች የቆሰለውን የማዳን እንጂ ያልቆሰለውን የማቁሰልን ተግባር ልንጸየፈው ይገባናል፡፡

Birhanu Admass Anleye


ጊዜ ዕረፍታ ለቅድስት ድንግል
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ይዞ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እመቤታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ የሔደው
የዕረፍቷ ጊዜ መድረሱን ለማብሠር ነበር፡፡ የድል ምልክት የሆነውን ፍሬው የተንዠረገገ የቴምር ፍሬ የሚያፈራውን
ዘንባባ ይዞ ለሁለተኛ ጊዜ እርሷ ወዳለችበት ይዞ ገብቶ ደስ ይበልሽ ሲላት አሁንም እየሰገዳና እጅ እየነሣ ነበር፡፡
ጌታችን እንዳዘዘውም "ልጅሽና ጌታሽ እናቴ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ ጊዜው ደርሷል ብሏል፡፡ ከሴቶች ተለይተሸ
የተባረክሽ ቅድስት ሆይ ስለዚህም ለሁለተኛ ጊዜ ይህን መልካም የምሥራች እነግረሽ ዘንድ ላከኝ፡፡ ብፅዕት ሆይ
በምድር የሚኖሩትን ሁሉ በደስታ እንደሞላሻቸው አሁን ደግሞ በዕረፍትሽና በዕርገትሽ ምክንያት የሰማይ ኃይላት
በደስታ ይሞሉ ዘንድ በሰማይ ያሉ ነፍሳትም ሁሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ በክብር ያበሩ ዘንድ ምክንያት ትሆኛለሽ፡፡
ደስተኛይቱ ፍስሕት የሚል ማዕረግ ለዘላለም ተስጥቶሻልና ስታዝኝና ስታለቅሽ በኖርሽው መጠን ደስ ይበልሽ፡፡
ጸሎቶችሽና አስተብቁዖቶችሽ በሙሉ በልጅሽ ፊት ወደ ሰማይ ዐርገዋል፤ ስለዚህም ይህን ዓለም ትተሽው ወደ ሰማይ
ትሔጅና ፍጻሜ በሌለው የዘላለም ሕይወት ከልጅሽ ጋር ትኖሪ ዘንድ አዝዟል" ብሎ ዘንባባውንም በእጇ ሰጣት፡፡
የነበረውን ትውፊት ሁሉ አሰባስቦና አጠናቅሮ በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በግሪክ ቋንቋ ሕይወቷንና ተጋድሎዋን በተሻለ
ሁኔታ የጻፈው መክሲሞስ ዘኢየሩሳሌም እንደመዘገበው እመቤታችን የመልአኩን ብሥራት በሰማች ጊዜ እጅግ ተደስታ
እንደ ቀድሞው ሁሉ በፍጹም ትሕትና "እነሆ የእግዚአብሔር አገልጋዩ፤ አሁንም እንደቀድሞው እንደቃልህ ይደረግልኝ
አለችው" ይላል፡፡ ከዚህ በኋላ አሁን በዚህ ጽሑፍ የማልገልጻቸው እጂግ ብዙ ገቢረ ተአምራት ተፈጽመዋል፡፡
እመቤታችን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የሰጣትን ዘንባባ ይዛ በደብረ ዘይት ተራራ ሔዳ ከጸለየች በኋላ ቀድማ
ትነግረው ዘንድ ትፈልገው የነበረውን ወንጌላዊና ነቢየ ሐዲስ ንጹሕ ድንግል ዮሐንስን በደመና አምጥቶላታል፡፡
ከዚያም ልዩ የእግዚአብሔር መቅደስ ወዳደረገቻት ቤቷ ከተመለሰች በኋላ ሐዋርያትና ብዙ ተላውያነ ሐዋርያት ድንገት
አንድ ጊዜ በደመና ደረሱ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ከደመናው ከተቀበላቸው በኋላ ወደ እርሷ ይዟቸው ገባ፡፡ ሁሉም አንድ
በአንድ እየሆኑ በፊቷ እያለፉ ተሳለሟት፤ እርሷም አነጋገረቻቸው፡፡ ከአርድእት አንዱ የሆነው ተላዌ ቅዱስ ጳውሎስ
የሆነውና ከፍልስፍና የተመለሰው የአቴናው ዲዮናስዮስ ከተገኙት አርድእት መካከል እርሱ ቅዱስ ጤሞቴዎስና ቅዱስ
ሔሮቴዎስ እንደነበሩና ቅዱስ ጴጥሮስን፤ ቅዱስ ጳውሎስንና ሌሎቹን ሐዋርያት ስታናግራቸው በዓይኑ እንዳየና ራሱም
በፊቷ አልፈው እማሔ ካደረጉት መካከል መሆኑን ለጢሞቴዎስ በላካት መልእክት ላይ መዝግቦታል፡፡ ከዚያም በኋላ
መንፈስ ቅዱስ ወርዶባቸው ሁሉም ሐዋርያትና አርድእት መንፈስ ቅዱስ እንደሰጣቸው መጠን ተሰምቶ የማያውቅ ልዩ
ምስጋና ማቅረባቸውን መዝግቧል፡፡ ከዚህም በኋላ የተደረጉት ተአምራት ብዙዎች ስለሆኑ በሌላ ጽሑፍ እስክምለስ
ድረስ አሁንም እነርሱን ከመዘርዘር እቆጠባለሁ። በመጨረሻም ጌታችን በሚያስፈራና በልዩ ግርማ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር
መውረዱንና እነሙሴ እነዳዊት በአንድነት ከአእላፋት መላእክት ጋር ሲዘምሩና የሰማይ ሠራዊት በደስታ ሲጥለቀለቁ
ጽዮንም ስትናወጥ ማየታቸውን በእኛ የጥር ወር በልዩ ከብር ማርፏን የነበሩት ሐዋርያትና አርድእት ሁሉ
መስክረዋል፡፡
የአካላዊ ቃልን ወደዚህ ዓለም መምጣት ማብሠር እንደተሰጠህ የድንግሊቱንም ወደዚያኛው ዓለም መሔድ ማብሠር
ድጋሜ የተሠጠህ የታመንህና የከበርክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እባክህ መልካም ነገር እያለ የራቀውን የእኛን ትውልድም
ከመልካሙ ነገር አገናኝልን፤ መልካሙን አሰማን፡፡ ከድንግሊቱና ከደስተኛይቱ እናታችን በረከትም አድርስልን፡፡
ክብሯን ግለጥ ፤ እኛንም ፈጽመህ አማልደን።
እንግዲያውስ ቅዱሳኑን ተከትለን እኛም እየዘመርንና እያመሰገንን የሰው ዘር መመኪያ የሆነችውን የእናታችንና
የእመቤታችን የንጽሕተ ንጹሐን የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያምን በዓለ ዕረፍት በተከበረው ትውፊታችን መሠረት
እናክብር፡፡
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስና ሶርያዊ ማር ኤፍሬም የመሥዋዕቱን በግ ያስገኘሽልን፤ እረኛችን የወልድሽልን
ንጽሕት በግ ሆይ የሚሉሽ ፍጽምትና የታመንሽ አማላጅ ሆይ በፍጹም ምልጃሽ ሁላችን አስምሪ ።
እንኳን ለበዓለ ዕረፍታ ለንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም አደረሳችሁ፡፡

ድንግልማ በእውነት ተነሥታለች

እንኳን ለእመቤታችን በዓለ ዕርገት አደረሳችሁ፡፡

ዘሰ ይብል አፈቅረከኪ ወኢያፈቅር ተአምርኪ[ትንሣኤኪ ወዕርገትኪ] ክርስቲያናዊ፤


ኢክርስቱን ውእቱ አይሁዳዊ ወሠርፀ እስጢፋ ሐሳዊ፤
አንሰ እቤ በማኅሌተ ሰሎሞን ሰንቃዊ፤
አፈቅሮ ለፍግዕኪ ወለተ ይሁዳ ወሌዊ፤
ከመ መርዓቶ ያፈቅር ጽጌኪ መርዓዊ፡፡

እንደ ይሁዳ ስሙን የሚቃረን ግብር ሁልጊዜም የሚሠራውና ራሱን ‹‹ አባ ሰላማ ›› ብሎ የሚጠራው የተሐድሶዎች
ብሎግ አንድ የሚያስደንቅ ጽሑፍ ሰሞኑን አስነብቦናል፡፡ የሚያስደንቅ ያልኩት ራሴን ባስደነቁኝ ሦስት ምክንያቶች
ነው፡፡ የመጀመሪያው ለርእስነትና ሐሳቡን ለማስተላለፍ መሪ አድርጎ የተጠቀመው ጥቅስ መልእክቱ ከነገረ ጉዳዩ
ያለውን ርቀትና አንድ ሰው ከካደ በኋላ ጥቅሶችን እስከምን ድረስ ሊያጣምም እንደሚችል ሳስብ አሁንም
እደነቃለሁ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ክርስትና ከተመሠረተበትና በይፋ በብዙዎች ተቀባይነት እያገኘ ከመጣበት ከዘመነ
ሐዋርያት ጀምሮ ብዙ የዓይን ምስክሮች አይተው ያስተላለፏቸውን ትውፊቶች ሁሉ ምን ያህል እንደሚጠሉ ሳስብ
በዚያ ዘመን የነበሩ አይሁድ በአካለ ሥጋ የመመለስ እድል ገጥሟቸው ቢጠየቁ እንኳ ‹‹ እንዴት ከእኛ በላይ
ጠላችኋቸው›› ብለው የሚገረሙባቸው ስለሚመስለኝ እደነቃለሁ፡፡ ሦስተኛውና ሁልጊዜም ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ
ተሐድሶዎች የምደነቀው ደግሞ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብና ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ባላቸው ጥላቻ ነው ፡፡ አስተውሎ ለሚያይ
ሰው ጽሑፍ ነክ ነገር ላይ ከተነሡ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን ወቅታዊ ነገር ላይ ከተነሡ ማኅበረ ቅዱሳንን አንዳንድ ጊዜ
ሁለቱንም አንድ ላይ ካላመቼም የሚጽፉበትን ሰው ማኅበረ ቅዱሳን ወይም ዘርዐ ያዕቆብ ነክ አድርገው ካላቀረቡ
መንፈሳቸው የሚቀጣቸው ይመስለኛል፡፡ ዓለም አቀፍና ልዩነት የሌለበት የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ነባር ትውፊቶች
መካከል አንዱ የሆነውን የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት ለዘርዓ ያዕቆብ መስጠት ማለት ምን ያህል ድፍን ቅልነት
ይሆን? እንዲህ የምለውና የምደነቀውም ብዙ ጊዜ የስሕተትና የክህደት ጽሑፍ ቢጽፉም እውነቱ የያዙትና በዚያም
እንጸድቃለን ብለው የሚያስቡና ለዚያም ለመሰላቸው የሚተጉ ይመስለኝ ስለነበረ ነው፡፡ ይህን ጽሑፍ ሳየው ግን ‹‹
ኦርቶዶክስን እንዴት እናስጠላለን፤ ሰውንስ ከእምነት እንዴት እንለያለን?›› በሚል መንፈስ ብቻ እንደሚሠሩ
ስለተረዳሁ ነው፡፡ አሁን አሁንማ እንደ መሸታ ቤት በየሥርቻው በከፈቷቸው ብሎጎቻቸው ዓይን ያወጣ ስድብና
ምንም ዓይነት መሠረት የሌለው የስም ማጥፋት ቅርሻቶቻቸውን በመትፋት ላይ መሆናቸውን ሳይ አውሬው ብስጭቱ
እየጨመረ የመጣው ወደፊት ሰማዕትነትን አይቶ እየፈራ ይመስላል ፡፡

በርግጥ ይህ ብሎግ በመኖሩ ‹‹ ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው›› /ራእ 13፤ 5/ ተብሎ
የተነገረለት አውሬው ሥራውን እያበረታ መሆኑን እናያለን፡፡ በማያቋርጠው የሐሰትና የጠብ ፤ የስድብና የስም
ማጥፋት እንዲሁም የኑፋቄና የክህደት ጽሑፎቻችሁም ‹‹ እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ
የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ ›› /ራእ 12 ፤ 15/ የተባለውን አውሬው በገቢር የሚያሳይባችሁ
የክሕደትና የኑፋቄ የአውሬው የትፋት ወንዞች መሆናችሁን ታረጋግጡልናላችሁ፡፡ ነገር ግን ‹‹ምድሪቱም ሴቲቱን
ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው ›› /ራእ 12 ፤16/ ተብሎ
እንደተጻፈው ምድር ቤተ ክርስቲያን የእናንተን የክህደት መርዝ ታሰርገዋለች ፡፡ አሁንም እንደተለመደው ሁሉ
ስሕተቶቻችሁን ከማሳየት እንጀምር፡፡

አውሬ ያበከተውን አትብሉ

በመጽሐፍ ‹‹በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን አውሬም የሰበረውን አይብላ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ›› /ዘሌ 22 ፤


8/ ተብሎ እንደተጻፈ አውሬ ያቆሰለው ደሙን መጥጦ ያበከተው የጫረው ሁሉ እንዳይበላ በኦሪቱ ታዝዟል፡፡
በላይኛው አንቀጽ ላይ ደግሞ አውሬው ማን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ነግሮናል፡፡ አንድ ሰው በጉ ወይም በሬው
የእርሱ ቢሆንም አውሬ ሊበላው ጭሮ ካቆሰለው ደሙን መጥጦ ከገደለው እንዳይበላው እንደተከለከለው ሁሉ
ለሕይወታችን ምግብ በአምልኮታችንም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገን ከምናቀረበው ከመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት
አንዱን ለይተው ልክ አውሬ በጉን ከመንጋው ለይቶ እንደሚበላው ወይም እንደሚያቆስለው አውሬ የተባለ መናፍቅም
ወይም ከሐዲ ከእናቱ ወይም ከመንጋው ለይቶ በተሳሳተ ትርጉም ያቆሰለውን ወይም የጫረውን ወይም በክህደት
አስተምህሮ የገደለውን መብላት ለእኛ የተከለከለ ነው፡፡ በኦሪቱ ትእዛዝ እንዳየነው በጉ ንብረትነቱ የሰው ቢሆንም
አውሬ ስለነካው ብቻ እንደተከለከሉት ጥቅሱ የእኛውና ከእኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ ቢሆንም አውሬ መናፍቅ
በጥርጥርና በክህደቱ መርዙ የወጋውን በልተን እንዳንጎዳ የተከለከለ ነው፡፡ ስለዚህም ጥቅስን እኛ ለነፍሳችን
የምንመገበው በአውሬ መናፍቃን ትምህርት ያልተጫረና ያልረከሰ ሲሆን ብቻ መሆኑን ማስተዋል አስፈላጊ ነው፡፡
ስለዚህ መናፍቃን በተሳሳተ መንገድ ያጣመሙትን ሁሉ ለነፍሳችን ማቅረብ ራስን መቅጣት መሆኑን ማወቅና መጠበቅ
ተገቢ ነው፡፡
ለምሳሌ እመቤታችን አልተነሣችም አላረገችም ብሎ ለመካድ የግድ ጥቅስም የሚያስፈልገው አልነበረም፡፡ ‹‹ከሰማይም
ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ›› / ዮሐ 3 ፤13/ የሚለውን ጠቅሶ እጂግ በተዛባ መንገድ
እመቤታችን አላረገችም ለማለት መጥቀስ ልክ በበጎቹ አውሬ እንደሚያደርገው የበጉን ደሙን ( የጥቅሱን ነፍሱን
ምስጢሩን ወይም ዋና መልእክቱን ) መጥጦ ገድሎ አበክቶ መስጠት ነው፡፡ ቀጥታ በዚህ መንገድ እንተርጉመው
ካልንማ መጀመሪያውኑ የሚለው ወደ ሰማይ የወጣው ከሰማይ የወረደው ከሆነ ክርስቶስ ያረገው በተዋሐደው ሥጋ
ነውና በውኑ ሥጋውን ከሰማይ ይዞ ወርዷልን? እንዲህማ ከሆነ የሰው ልጅ ተብሎስ እንዴት ሊጠራ ይችላል?
እንዲህማ ከሆነ የራሱ ትምህርትና ንግግርም ሆነ ስለ እርሱ ሐዋርያትና ሊቃውንት ያስተማሩት ሁሉ ከንቱ ሆነ፡፡
ከሰማይ በውረድማ ከሆነ መላእክቱን እንኳ ብንተዋቸው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛ ሰማይ የተነጠቀው ጥንቱን
ከዚያ ቢመጣ ነውን? ወይስ ሔኖክና ኤልያስ ያረጉት ድሮውንም ከሰማይ የወረዱ በመሆናቸው ነው? ከዚህ
በተቃራኒው ደግሞ ወርደው ያልተመለሱም አሉ፡፡ ለይስሐቅም ምትክ ሆኖ የተሰዋው ከሰማይ የወረደ ነበር፡፡
ለኤልያስም እንጎቻ በመሶብ ውኃም በማሠሮ ወርዶለት ነበረ፡፡ ጥቅሶችን የምትተረጉሙት እንደዚህ ከሆነ ‹‹ እኔ ስለ
እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም ›› / ዮሐ 5 ፤ 31/ የሚለውንስ ምን ትሉለታላችሁ? በእውነት
ጥቅስን እንዲህ ያለ ቦታውና ያለመልእክቱ መጠቀም በገዳመ ቆሮንቶስ ለጌታም ጥቅስ እየጠቀሰ ለመፈታተን
ያላፈረውንና አሁንም ይህን ከማድረግ የማያፍረውን የማይሰለቸውንም ዲያብሎስን ያስመስላችሁ ወይም በእርሱ
መንፈስ የምትሠሩ ፈታኞች መሆናችሁን ታረጋግጡ ካልሆነ በቀር የምትፈጥሩት ነገር የለም፡፡ ልክ ክፉ አውሬ በጉን
ከመንጋው ለይቶ አድክሞ ይዞ ደሙን መጥጦ እንደሚገድለው ጥቅስንም ከመጽሐፍ ቅዱስ ከመንጋውና ከመልእክቱ
ለይቶ ምሥጢር ደሙን መጥጦ በማብከት ተሐድሶዎችን የሚተካከል ያለ አይመስለኝም፡፡

ይህ ጥቅስ የተጠቀሰለት ዳግም የመወለድ ምስጢር ረቅቆበት አልገባው ላለው የአይሁድ መምህር ኒቆዲሞስ ነው፡፡
ከጥቅሱ ጌታችን ኒቆዲሞስን ከነበረበትም ዕውቀትና እምነት ከፍ እንዲልና ታላቁን ምሥጢረ ሃይማኖት እንዲረዳ
እያደረገው እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ በፊቱ ቆሞ የሚያነጋግረው ጌታ ዕሩቅ ብእሲ ሳይሆን ከሰማይ አካላዊ ቃል
መጥቶ በተዋሕዶተ ትስብእት የተገለጠ መሆኑንና በሚያየው ትስብእት ውስጥ የማያየው መለኮት ተዋሕዶ መኖሩን
ትስብእትም ለዚህ የበቃው በተዋሕዶ እንጂ እንደ ቀደሙት ነቢያት በጸጋ አለመሆኑንና የባሕርይ አምላክ መሆኑን
ነበር ያስረዳው፡፡ በርግጥም ወልደ እጓለመሕያው ጌታ ራሱን አምላክ ያደረገ ፍጡር አይደለም፡፡ አምላክነት ከጥንት
ገንዘቡ ነው፤ ነገር ግን ይህን ሰማያዊነት፣ ቀዳማዊነትና፣ ፈጣሪነት፣ ሁሉን ማወቅና ከመወሰን ሳይወጡ መምላት፣
ከመግዘፍ ሳይወጡ መርቀቅ ( ቀድሞ በሰማይ የነበረውን) ትስብእት ወይ ሥጋ የወረሰው በተዋሕዶ ከቃል ነውና ‹‹
ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም›› ሲል እውነተኛ ተዋሕዶውን አረጋገጠልን፡፡ ጥቅሱ ራሱ
የሚፈጸመው ‹‹ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው ›› በሚል ሐረግ ነው፡፡ ጌታ ራሱ በኒቆዲሞስ ፊት ሆኖ
እያነጋገረው እያለ ራሱን ‹‹ በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው›› ሲል የጠቀሰው በዚያው ቅጽበት ወይም ቃል
ሥጋን ከተዋሐደበት ቅጽበት ጀምሮ ሥጋ ቅድመ እርገትም በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ በክብር ያለና ፍጹም አምላክ
መሆኑን ሲያስረዳው ነው፡፡ ምክንያቱም ከእርሱ ጋር ሲነጋገር ቢየየው በሰማይ የሌለ እንዳይመስለው ተዋሕዶውንና
አምላክነቱን ለማስረዳት የተናገረው መሆኑን በዚህ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ እንደዚህማ ባይሆንና ጥቅሱ ለጌታ ለዕርገቱ
የተነገረ ቢሆን ኖሮ ‹‹ አሁን በሰማይ የሚኖረው›› ለምን ይለዋል፡፡ ገና አላረገም ነበርና፡፡ ስለዚህ ጥቅሱ
ከእመቤታችን ዕርገት ቀርቶ ከጌታም ዕርገት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ፡፡

ለመሆኑ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገትን ያሰተማሩና የሰበኩ እነማን ናቸው? በግእዙ ያለው ታሪካችን ከሆነ
ያስጠላችሁ እስኪ በሦስተኛ ክፍለ ዘመን ስለ እመቤታችን ድንቅ ድንቅ ስብከቶች የሰበከውን ጎርጎርዮስ ገባሬ
መንክራትን ዘርዓ ያዕቆብ አስተማረህ ትሉታላችሁን? ወይስ የእመቤታችን በዓለ ዕረፍቷ ከበዓለ ዕርገቷ ጋር በአንድ
ላይ በጁሊያን አቆጣጠር ኦገስት 15 አንድ ላይ ይከበር ይል ለነበረው ለቁስጥንጥንያው ንጉሥ ለዮስጥንያኖስ ከጥንት
ጀምሮ ከኢየሩሳሌም መጥቶ በመንበረ ማርቆስ ካቴድራል ቤተ መጻሕፍት ተቀምጦ የኖረውን የእመቤታችንን
የዕረፍቷንና የዕርገቷን ዜና መጽሐፍ ተርጉሞ በመስጠት ዕረፍቷ ጥር 21 ዕርገቷ ነሐሴ 16 መሆኑን በመግለጽ
ቢያንስ በዚያ ዘመን ሁለቱም በዓላት በየራሳቸው እንዲከበሩ እንጂ አንድ ላይ መከበሩ እንዳይታወጅ ያደረገው
የ 33 ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ የቴዎዶስዮስን (535 - 566) ሥራ ምን ልታደርጉት ነው? አትደብቁት
በብዙ የዓለም ቋንቋዎች የተተረጎመ ነው፡፡ እንግዲህ እናስተውል ፤ ይህ ቴዎዶስዮስ በጽርእ (ግሪክ) ቋንቋ ተርጉሞ
ለንጉሡ የሰጠው መጽሐፍ በዓሉ ከእርሱ ዘመን በፊት ተለያይቶ ይከበር እንደነበርና ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ያሉት
የምስራቁ ክፍል አባቶች በዚህ ትውፊት ጸንተው ይጠቀሙበት እንደነበር አሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ምርምር
ለሚያደርጉ ማስረጃ ሆኖ ያገልግላል፡፡ በቅርብ ጊዜ አሜሪካን ሀገር ያለው የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የነገረ
መለኮት ከፍተኛ ትምህርት ቤት የሆነው የቅዱስ ቭላድሚር ሴሚናሪ ከሚያሳትማቸው እስከ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን
የነበሩ አባቶች ስብከቶች (Patristic writings) መካከል አንዱ የእመቤታችንን ዕረፍትና ዕርገት
( Dormition and Assumption) በተመለከተ በዚያ በጥንቱ ዘመን የተሰበኩ ስብከተ ሊቃውንትን
አሰባስቦ የያዘ ነው፡፡ ይህ በዓል በጥንታውያኑ አበው ሲያከብሩት የመጣና እመቤታችን ዕረፍቷም ሆነ ዕርገቷ
ከሐዋርያት ጀምሮ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የነበሩ እጂግ ብዙ ደናግል ሴቶች በአካል በነበሩበት የተፈጸመ እንደሆነ
ትውፊቱን የመዘገቡ መጻሕፍት ሁሉ የሚያረጋግጡት እውነታ ነው፡፡ በዚያ የነበሩ ሁሉ አይተው እንዳረጋገጡት ጌታ
በሚያስደንቅ ግርማ የእመቤታችንን ነፍስ ሊቀበል በተገለጸ ጊዜ በአንድነት የሰገዱት ሐዋርያትና ደናግል ፍርሐት
ርቆላቸው ቀና ሲሉ ሙሴ ከፊት ሆኖ ሌሎች ነቢያትና ጻድቃን ጌታን ከብበው ዳዊት በበገናው ‹‹ ተንሥእ እግዚኦ
ውስተ ዕረፍትከ፤ አንተ ወታቦተ መቅደስከ›› የሚለውን መዝሙሩን ሲዘምር ሁሉም በአንድነት አይተዋል፤
ሰምተዋል፡፡ ይህ የተረጋገጠ ታሪክ ነው፡፡ የነበሩት ሁሉ መስክረውታልና፡፡ እንግዲህ ሐዋርያትና ከእነርሱ ጋር የነበሩ
ሁሉ ነበርን አይተናል ብለው አውርሰውት ከሔዱና ሁሉም እየተቀባበለ ለእኛ ካደረሰው በኋላ እናንተ አንቀበልም
በማለታችሁ ከሐዋርያት መንገድ መውጣታችሁን ታረጋግጡልናላችሁ እንጂ እኛ የምንጠራጠር ይመስላችኋልን?
የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት ትውፊት ወይም የቤተ ክርስቲያንን ትውፊት የማትቀበሉ ከሆነ ለመሆኑ መጽሐፍ
ቅዱስን ከየት አገኛችሁት? ማን ሰጣችሁ? ምዕራፍና ቁጥሩንስ ከየት ተቀበላችሁት? ነቢያት ሐዋርያት እንደጻፉትስ
በምን ታረጋግጣላችሁ? በእነማንስ በኩል ተጠብቆ ደረሳችሁ? ለመሆኑ ተነሣች ዐረገችን ለመቀበል ከቸገራችሁ
አልተነሣችም አላረገችምን ለምን አመናችሁት? የተነገረውንና ሲተላለፍ የኖረውን ለማመን የምትቸገሩ እናንተ
ልብወላዳሁን ለማመን የሚያፋጥናችሁ ማን ነው? መቼና እንዴት እንደተፈጸመ ወይም የዕረፍቷንና የአቀባበሯ ሌላ
ትውፊት እንኳ ሳትይዙ የነበረውን ለማቃለል ብቻ የሚያጣድፋችሁ እንዴት ያለ ክፉ መንፈስ ነው? እናንተ
የተረጋገጠ ጽሑፍ ብቻ ነው የምንቀበልስ ካላችሁ ትንሣኤና ዕርገቷ የተመለከተውን ጽሑፍ ማን እንደጀመረው፣
እንዴት እንደተሸጋገረና እንዴት ስሕተት እንደሆነስ ለምን አልመረመራችሁም? ጥላቻ ጊዜ አይሰጥማ፤ ክህደት
የእውነተኛ ዐውቀት ጭላንጭል የለውማ፡፡ እንግዲህ እናነተን በምን መርዳት ይቻል ይሆን? ሐዋርያትን
ካልተቀበላችኋቸው እኛንማ እንዴታ!በክህደት ትምህርታችሁና በስም ማጥፋታችሁ የምንደነግጥ ይመስላችኋልን?
ይህንማ ሥራችሁ እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ እናንተም ሥራችሁን እኛም ሥራችንን እንሠራለን፡፡ በኋላ ዘመን
ዋጋችን እንደ ሥራችን እንዲመዘን እናውቃለንና፡፡ ወይስ እንደ ዲያብሎስ ተስፋ ድኅነት የለንም ብላችሁ ተስፋ
ቆረጣችሁ?

ትንሣኤዋና ዕርገቷ ለክርስቲያኖች ሊቀበሉት የማያስቸገረው ግን የተረጋገጠ ትውፊት በመኖሩ ብቻም አይደለም፡፡
ትልቁና ዋናው ምሥጢር ያለው ደግሞ እመቤታችን ‹‹ ልዩ ›› መሆኗ ላይ ነው፡፡ ዕድገቷና ሕይወቷ ልዩ ነበር፡፡
በእርሷ የተደረገው የአካላዊ ቃል ጽንስና ወሊድም እስካሁን ሊገልጹት ቀርቶ ሲያስቡትም ይከብዳል፡፡ አባ ሕርያቆስ
በቅዳሴው ‹‹ ይህንም ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ የልጅሽን የባሕሩን ጥልቅነት ሊዋኝ ይወዳል፤ የወዳጅሽ የመሰወሪያው
ማዕበልም ያማታዋል፡፡ ... አሁንም ገናንቱን አንመርምር፤ ጥልቅነቱንም አንጠናቀቅ፤ የገናንቱን መጠን ለማመስገን
የነቢያትና የሐዋርያት አንደበት የማይቻለው ነው›› እንዳለው ለማንም የሚቻል አይደለም፡፡ ለዚህ የታደለችው ነገሩን
ሁሉ በልቧ ትጠብቀው የነበረችው እራሷ ድንግል እመቤታችን ብቻ ናት፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ገብርኤልም ቅድስት
ኤልሳቤጥም ‹‹ ልዩ›› መሆኗን አስቀድመው ምስጋናቸውን ያስከትሉላት፡፡ ታዲያ እመቤታችን ልዩ በሆነ መንገድ
ከጸነሰችና ከወለደች ልዩ በሆነ መንገድስ የማትነሣው የማታርገው ለምንድን ነው? መነሣቷና ማረጓ አድሎ ያስመስላል
የሚባለው በድንግልና ጸንሳ በድንግልና መውለዷንስ ለምን አድሎ ነው አይባልም? ጽንሱ ልደቱ ሰለ እርሱ ነው
የምትሉ ከሆነስ ትንሣኤውና ዕርገቷ ምን የሚያረጋግጥ ይመስላችኋል? የእርሱን ትንሣኤና ዕርገት ተሰርቆ ነው ሲሉ
የነበሩ አይሁድ በእርሷ ትንሣኤና ዕርገት ሲያፍሩ ብዙዎቹም ከእነርሱ ወደ ክርስትና ሲመለሱ እናንተ ይህን ከማለት
የማትመለሱ የክርስቶስን ትንሣኤም ሳታውቁ ታቃልላላችሁን? የእናንተ ክሳደ ልቡና በእውነቱ እንደምን ከዚያ ዘመን
አይሁድ ይልቅ ጸና? በውኑ አድሎን ለእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት የምትጠቅሱት በደብረታቦር በዓል ሙሴን
ከሙታን ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሦስቱን ብቻ ይዞ መውጣቱንስ አድሎ ትሉታላችሁን?
በእውነቱ ስንቱን ተመሳሳይ ታሪክ ልንጠቅስ ስንቱንስ ልናስታውሳችሁ እንችላለን? በእውነት የቀደሙትን አበው
ትምህርትና ትውፊት እንዳትቀበሉ የእግዚአብሔርንስ የማይታወቅ መንገድ የደረሳችሁበት አስመስሎ ያሞኛችሁ
ወይንም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? የእመቤታችን ልዩ መሆን ካልገባችሁ በትንሣኤዋና
በዕርገቷም ልዩ መሆኗን እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ? ማስተዋላችሁን የጋረደውን የስድብና የስም ማጥፋት ግብር
ያሰደረባችሁን ከፉን መንፈስ ትቃወሙትና ከዚህም ነጻ ትወጡ ዘንድ በእውነት እግዚአብሔር ይርዳችሁ ከማለት
በቀር ምን ልንል እንችላለን፡፡ድንግልማ በእውነት ተነሥታለች ዐርጋለችም፤ ክብር ምስጋና ለተወደደ ልጇ ይሁን፤
አሜን፤ በረከቷም ይደረብን፡፡

አርምሞትኪ ማርያም ኃለፈ እም አንክሮ፤


እስከ ንሬኢ ሕዝብኪ ለተአምርኪ ግብሮ፤
ገነትኪ ትጽጊ ሰላመ ወተፋቅሮ፤
እለያማስኑ ለዓጸደ ወይንነ ወፍሮ፤
ቆናጽለ ንዑሳነ አፍጥኒ አሥግሮ፡፡

ዘመን እና ሰው
እንኳን ከዘመን ዘመን (ለዚህ ለ 2007 ዓ.ም. ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ) በሰላም አሸጋገረን፡፡
ሁለት ዓይነት ጊዜ እንዳለ ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡ አንደኛውና ይህ ዛሬ "እንኳን ከዘመን ዘመን... "
የምንባባልበትና ፍጥረትና ድርጊቱ በቅደም ተከተል የሚሰነዱበት ጊዜ ነው፡፡ ይህንን ጊዜ ከዚህ በኋላ "የፍጥረት ጊዜ"
ወይም ታሪካዊ (Historical time) ጊዜ የምንለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከሥነፍጥረትም በፊት
በፍጥረትም ጊዜ ከፍጥረት ማለፍም በኋላ የሚኖረውና በፈጣሪ ሕልውና የሚለካው (አስተውሉ እርሱ ራሱ ይለለካል
እንጂ የፈጣሪን ድርጊት የሚለካ አይደለም) ከአሁን በኋላ "ዘላለማዊ ጊዜ" ወይም እንደኛ ሊቃውንት "ዮም"
የምንለው ሌሎቹ በእንግሊዝኛ "የተቀደሰ ወይም ዘላለማዊ ጊዜ" (Sacred time)የሚሉት ጊዜ ነው፡፡ ዮም
የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ዛሬ ማለት ነው፡፡ ይህ ሁለተኛው ጊዜ በእኛ ሊቃውንት ዘንድ "ዮም" የሚባልበት
ምክንያት ከመዝሙረ ዳዊት "እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ፤ ወአነ ዮም ወለድኩከ" ፤ እግዚአብሔር አንተ
ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ (መዝ 2፤7)የሚለውን ጥቅስ መነሻ አድርገው ትርጓሜውን ሲያብራሩ እግዚአብሔር ስለ
ራሱ የገለጸው የጊዜ መጠሪያ ዮም ወይም ዛሬ መሆኑን ስለሚያመሰጥሩ ነው፡፡ ይህም ማለት በእግዚአብሔር ዘንድ
ትናንት እና ነገ፤ አምናና ከርሞ፤ ጥንትና መጪው ጊዜ ወይም ከዚህ ዘመን በኋላ የሚባል ነገር የለም ማለት ነው፡፡
ለእርሱ ሁሉም "ዛሬ" ነው፤ ምክንያቱም እርሱ በፍጥረት ጊዜ ሊለካና ሊታወቅ የሚችል አይደለምና፡፡ ስለዚህም ነው
ስለ እግዚአብሔር ሲሆን "ዮም" ወይም ምዕራባውያን እንደሚሉት ልዩ፤ ቅዱስ ጊዜ (sacred time)
የሚለውን ለመጠቀም የምንገደደው፡፡ ከላይ በተገለጸው ጥቅስ ላይ ‹‹ እኔ ዛሬ ወለድሁህ›› የሚለው የሚገልጸውም
የወልድን ሁለቱንም ልደታት ነው፡፡ በእኛ ሊቃውንት ዘንድ ይህ ኃይለ ቃል ሲብራራ ሁለቱም ጊዜዎች አብረው
የሚነሡትም ለዚህ ነው፡፡ የጌታችንን ሁለት ልደታት የመጀመሪያው ‹‹ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት›› ሁለተኛውን
ደግሞ ‹‹ ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ያለ አባት›› ሲሉ ይገልጹታል፡፡ ይህ አገላለጽ ሙሉ በሙሉ በፍጥረት ጊዜ
ማለትም እኛ ድርጊቶችን በምንለካበትና እግዚአብሔር ሥነ ፍጥረትን ሲፈጥር በፈጠረው ጊዜ ከላይ እንዳልነው
በታሪክ መለኪያው ጊዜ (Historical time) የተገለጸ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ ከጥንት ጀምሮ
እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን
በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ ›› / ዕብ 1 ፤ 1-2/ እያለ የሚናገረው በዚሁ ጊዜ ስሌት
ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ በፍጥረት ጊዜ ሲለካ የእግዚአብሔር ወልድ ቀዳማዊ ልደት ‹‹ ቅድመ ዓለም›› ወይም ከዓለም
መፈጠር በፊት ከሚለው ውጭ መግለጫ የለውም፡፡ ምክንያቱም ከዚያ በፊት ያለውን የሚለካ የፍጥረት ጊዜ
( Historical time ) የለምና፡፡ ከዚሁ ጋር አብረውም ልክ የእርሱን ቀዳማዊ ልደት በፈጣሪ ቅዱስ ጊዜ
እንደገለጹት ሁለተኛውን ልደቱን ማለትም ከእመቤታችን በታወቀ ጊዜ የተወለደውንም በእኛ አቆጣጠር የሚገልጹትን
ያህል በእግዚአብሔር ቅዱስ ጊዜ ‹‹ ዮም ›› ዛሬ ብለው ከታሪካዊው ወይም ከታሪክ መነገሪያው ፍጥረታዊ ጊዜ
አውጥተው ይነግሩናል፡፡ ምክንያቱም በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉም ዛሬ ነውና፡፡ ‹‹ ዛሬ ወለድኩህ›› ማለትም ቀዳማዊ
ልደቱም ደኃራዊ ልደቱም በእርሱ ዘንድ ዛሬ ስለሆነ ነው፡፡ ለሊቃውንቶቻችን ምስጋና ይድረሳቸውና ‹‹ ዘመን
የማይቆጠርለት ዘመን ተቆጠረለት›› የሚለው ግሩም አገላለጻቸውም በዘላለማዊ ጊዜ ያለው በፍጥረታዊው ወይም
በታሪክ መሰነጃው ጊዜና ዓለም ውስጥ መገለጹን የሚያስረዱበት እጅግ ድነቅ አገላለጽ ነው፡፡
ስለ ጊዜ ምንነት እጅግ በቅንጭቡ ይህን ያህል ካልን ዋናው ነገር የእኛ የዘመን ዘመን ሽግግር በእግዚአብሔር ዘንድ
ትርጉም የሚኖረው ምን ስናደርግ ነው የሚለው መሆን ይገባዋል፡፡ ዘመኑን ወይም ጊዜውን የኽኛውና ያኛው፤
ያለፈውና የሚመጣው የሚያሰኘው የራሱ የሰው ድርጊት ብቻ ነውና፡፡ ምክንያቱም በእግዚአብሔር ዘንድማ ቀደም
ብለን እንዳያነው ያው ‹‹ ዛሬ›› ብቻ ነው፡፡ በመጽሐፍም ‹‹ ከዚህ ዘመን ይልቅ ያለፈው ዘመን ለምን ተሻለ? ብለህ
አትናገር የዚህን ነገር በጥበብ አትጠይቅምና›› / መክ 7፤10/ ተብሎ የተጻፈው ምስጢሩን እንደተባለው በወጉ
ስለማንረዳው ነው፡፡ ስለዚህ የሚጠበቅብን ከተቻለን ደግሞ የሚጠቅመንም በፍጥረዊው ጊዜያችን ውስጥ ወደ
ዘላለማዊ ሕይወት ወይም በዘላለማዊው ጊዜ ( Sacred time) የሚኖር ሥራ መሥራት ማለት ነው፡፡ ቀደም
ብየ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ሁሉም ጊዜ ለእግዚአብሔር ዛሬ ስለሆነ ዘላለማዊ ሕይወት የሚያሰጥ ሥራ የምንሠራ
ከሆነ ዘላለማዊው ጊዜ ገና የሚመጣ ሳይሆን ያለ ነውና ሥራችንን በታሪካዊው ጊዜ ብቻ ሳይሆን በዘላለማዊው ጊዜም
ይሰፍራል እኛንም ዘላለማዊ ወደ መሆን ያሸጋግረናል ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት
ሥራ ሲገልጽ ‹‹ ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ›› / ሐዋ 13 ፤ 36/ በማለት
የተጠቀመበት አገላለጽ ይህንን በደንብ የሚገልጽ ይመስለኛል፡፡ ሐዋርያው እንደገለጸው ዳዊት በዘመኑ ማለትም
በፍጥረታዊው ጊዜ ያገለገለው ‹‹ የእግዚአብሔርን አሳብ ›› ማለትም በዘላለማዊ ጊዜ የሚኖረውን የእግዚአብሔርን
ሥራ ፈጽሞ ወደ ዘላለማዊው አምላክ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ተሸጋገረ ማለት ነው፡፡
ቅዱሳንም ይህን የእኛን ታሪካዊውን ወይም ፍጥረታዊውን ጊዜ እያወቁት እየኖሩበትና እየሠሩበት ሳለ የጊዜ ማስላትና
መለዋወጥን ማወቅ ማጥናትና ማወጅ ጥንቱንም ያስፈለገውና የተጀመረው ወደ ዘላለማዊው ጊዜ ( ሕይወት)
ለመድረስ ስለሆነ በዚህ ምድር እያሉም የመዓልቱና የሌሊቱ፤ የአውራህ፤ የወቅቶችና የዘመናትም መሽከርከር ትልቅ
ነገር የማይሆንባቸው ራሳቸውን በዚያኛው ጊዜ ውስጥ ለማኖር ስለሚጋደሉ ነው፡፡ ‹‹ የአሕዛብን ፈቃድ
ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት
ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና›› /1 ኛ ጴጥ 4 ፡10/ ዓይነት አገላለጾች በሙሉ የተለየ ጊዜ
መሰጠትና የበዓል ማክበር ትርጉሙ ሁልጊዜም ሰማያዊ ደስታ የሚፈጸምበት ዘመን መኖሩን እንድናስታውስና ቢቻል
ዛሬም በዚህ ምድር ሁልጊዜም ለዚያ ዓላማ እንድናውለው ካልተቻለም በዓሉን ስናከብር ለውጥ የማይቀር መሆኑን
እንድናስብ ነው፡፡ በተለይ የዘመን መለወጫ በዓል ‹‹ ዘመን ተለወጠ›› የሚባለው ወደ ፊት ይህ ፍጥረታዊ ጊዜ
በዘላለማዊ ጊዜ የሚለወጥና አዲስ ዘመንም ማለት በሚመጣው ዓለም ያለው አዲስ ሕይወት የማይቀር መሆኑን
እንድናውቅና እንድንረዳ ለማስገንዘብ የሚውል ትልቅ ደውል ነው፡፡ ‹‹ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም
በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው ›› / ኤፌ 1 ፤10/ ተብሎ የተጻፈውም የዘመን ሁሉ
መጨረሻው ይኼው በክርስቶስ መጠቅለል ማለትም በዘላለማዊ ጊዜ ውስጥ በሥራችን መሠረት በሚሰጠን የፍርድ
ዋጋ ውስጥ ሆነን መኖር ስለሆነ ነው፡፡ ካለበለዚያ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ
ትጠብቃላችሁ›› / ገላ 4፤ 10/ ሲል እንደ ወቀሳቸው የገላትያ ሰዎች በሚወጣልን የበዓላትና የአጽዋማት መቁጠሪያ
ካሌንደር ተመሥርተን ቀኑን ወሩን ዘመኑን ከመቁጠርና በዚያም ከመብላትና ከመጠጣት በተራ ነገር ብቻ ከደሰትም
በቀር ለምን እንደምንቆጥርና እንደምናከብር ግን የማናውቅ እንሆንና በምድር በቅዱሳንም በሰማይ በእግዚአብሔርም
ተወቃሾች እንሆናለን፡፡
የዘመን መለወጥ በዓል ማክበር ትርጉሙም ሆነ ዋናው መልእክቱም በተሰጠን ዘመን ውስጥ እስካሁን ለበጎ ነገር
ያልተጠቀምንበትን አስባከን ለመጪው ዓመት ብቻ ሳይሆን ለመጪው ዘመናችን ለበጎ ሥራዎች እንድንዘጋጅበት
ለሥራ የተሠጠንም ዘመን ባከበርናቸው በዓላት ቁጥር መጠን እየቀነሰ መሆኑን የምንረዳበት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ
‹‹ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል ›› / ቲቶ 2 ፤
13/ ሲል ፍጥረታዊውን ጊዜ እንደገለጸው ይህ ጊዜ እግዚአብሔርን ለመምሰል ወይም እርሱን የመሰሉ / 1 ኛ ቆሮ
11 ፤1/ ቅዱሳንን ለመምሰልና ወደዚያኛው የፍጹምነት ሕይወት ለመሸጋገር ቅዱስ ተግባርን ለመለማመድ የተሰጠ
ጊዜ ነው ማለት ነው፡፡ ቅዱሳኑ ሁሉ ስለዘመናት ስለበዓላት በተናገሩባቸው አንቀጾች ሁሉ ጉዳዩ የሰዎችን የሕይወት
ለውጥ የሚመለከት እንደሆነ አጽንዖት የሚሰጡት ጊዜ ሁልጊዜም የሥራ መሥሪያ ይሆን ዘንድ የተሰጠ ስለሆነ ብቻ
ነው፡፡ ‹‹ በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ
እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር /1 ኛ ጴጥ 1 ፤ 11/›› ሲል ቅዱስ
ጴጥሮስ እንደገለጸው ዓበይት በዓላት በሙሉ የሚያሳስቡትም ዘላለማዊው እግዚአብሔር በፍጥረታዊ ጊዜ ምን ዓይነት
የማዳን ሥራ እንደሠራ ብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት በዓላት የሥራ መታሰቢያዎች ናቸው፤ ሥራ ትተን
የምናከብራቸውም ዘመኑ የተሠጠን ለመልካም ሥራ በመሆኑና ያ በዓል በተደረገበት ዕለት ግን እኛ ለራሳችን
ልንሠራው የማንችለውን እግዚአብሔር በልጁ ከዚያም በቅዱሳኑ ስለሠራው ይህ መሆኑን አምነንና እርሱን እያሰብን
ስናከብረው በዚያ የማዳን ሥራ የተፈጸመውን ለእኛ ማድረግ ስለምንችል ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ይህም ያንን
የተሠራውን ሥራ ለእኛ አድርገን በመቀበል ዋጋውን የምናተርፍበት መንፈሳዊ ሥራ ነው እንጂ መዘለል ( ሥራ
ፈትነት) አይደለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዘመን የሥራ መሥሪያ እና የምንሠራው ሥራ መለኪያ እንጂ ትርጉም የለሺ
ነገር አይደለም ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ‹‹ እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥
ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም
ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው›› / 1 ኛ ጢሞ 6 ፤ 18 - 19 /
ሲል የገለጸለት ዘመንን እንዲህ ለመልካም ሥራ የዚህን ዓለም ንብረት ብንሰበስብ እንኳ ለሌላቸው በማካፈል በዚህ
ገንዘብ በኩል ሰማያዊ መዝገብን ለመሰብሰብ እንድንጠቀምበት ለማሳሰብ ነው፡፡ ካለበለዚያ ድልቡን ሁሉ ትተነው
መሔዳችን አይቀርምና እንጎዳበታለን እንጂ አንጠቀምበትም፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ
እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፥ እናንተ ደግሞ ያን አሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት፥ በሥጋ መከራን የተቀበለ
ኃጢአትን ትቶአልና›› / 1 ኛ ጴጥ 4 ፤ 12/ እያለ የሚመክረን ከዘመናችን የቀረውን ማለትም የዘመን መለወጫ
በዓላችን ስናስብ እንደቀረን የምናስበውን ዘመናችን በጎ ለመሥራት ሳናስብ እንዳናሳልፈው ለማስጠንቀቅ ነው፡፡ ይህን
ስናደርግ ይህን ፍጥረታዊ ጊዜ ለዘላለማዊው ጊዜ መሸጋገሪያ እናደርገዋለን፡፡ ቅዱሱ ይሁዳም ‹‹ ብቻውን ለሆነ
አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና
ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን›› /ይሁ 1 ፤ 25/ ሲል የገለጸው ዘመን የሚቆጠርለት ጌታ በማይቆጠር
ዘመን ወይም በዘላለማዊነት የሚኖርና እኛንም በዚህ ለማኖር የመጣ ስለሆነ ነው፡፡
እንግዲያውስ በእኛ የጊዜ አቆጣጠር የምንቀበለውን አዲሱን ዘመንና ከዚህ በኋላ የሚመጣውን ዘመናችን ሁሉ እንደ
ቅዱስ ዳዊት ‹‹ የእግዚአብሔርን አሳብ ›› የምናገለግልበት ዘመን ያድርግልን፡፡ እንኳን አደረሳችሁ፤ እንኳን ወደ ሁለት
ሺሕ ሰባቱ ዘመነ ሉቃስ አሸጋገረን፤ አሜን፡፡

የሴት ራስ - ወንድ

እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ ረዘም ላለ ጊዜ በመጥፋቴ ይቅርታ እየጠየቅሁ ለጊዜዉ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ
የሃይማኖት ዐምድ ‹‹ሃይማኖት እና ሴቶች›› በሚለዉ የመወያያ ርእሰ ጉዳይ ላይ ከእኛ እምነት አንጻር ያቀረብኳትን
ትንሽ መጣጥፍ እነሆ ብያለሁ፡፡

ቤልጄየም ዉስጥ በምትገኘዉ የአንትወርፕ ከተማ አይሁድ ይበዙባታል፡፡ በዚሁ ምክንያት በዚያ ሀገር ሱቆች እንኳ
ሳይቀር በብዛት የሚይዙት ለአይሁድ የሚሆኑትን ልብሶችና ሌሎች የእነርሱን ፍላጎት የሚያሟሉ ነገሮች ነዉ፡፡
ምክንያቱም በዚያ ለሁለት ሺሕ ዐመታት በተሰደዱባቸዉ ቦታዎችም ባሕላቸዉንንና ዕሴቶቻቸዉን ጠብቀዉ የሚኖሩ
በመሆናቸዉ ነዉ፡፡ የተማሩት ትምህርትና የደረሱበት ሥልጣኔና ዘመናዊነት ምንም ያህል ተጽእኖ እንዳያመጣ
አድርገዉ መቛቛማቸዉም ሥልጣኔና ዕሴትን አንዴት አስታርቆ መሔድ እንደሚቻልም ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡

ይህም ሆኖ ግን አንዳንድ ጊዜ በሚኖሩበት ሀገር ባህልና ፖለቲካዊ ርእዮት የተማረኩ ትንሽም ቢሆኑ ስለሚኖሩ
በሁለቱ መካከል የሚፈጠሩ ክርክሮች አይጠፉም፡፡ ከማልረሳቸዉ ነገሮች አንዱ የሚመለከተዉ ነበር፡፡ በቅርቡ
ለቤልጄየም ፓርላማ የሚወዳደር አንድ አይሁዳዊ ወንድ ሚስቱ ወጥታ ድምጽ እንድትሰጠዉ ይጠይቃታል፤ ይህንኑ
እንድታደርግም አጥብቆ ይከራከራታል፡፡ በዚህ ጊዜ ሴቲቱ ወደ ሕግ በማምራት ባለቤቷ እምነቷና ባህሏ
የማይፈቅደዉን እንድታደርግ እየወተወታት መሆኑን በመግለጽ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ካለበለዚያም በሕግ እንዲፈታት
በመጠየቅ የሴትነት መብቷን አስከብራለች፡፡ ለአንዲት አይሁዳዊት ሴት ይህም ሴትነትን አለማክበር ነዉና፤ ለዚያዉም
በአዉሮፓ ዉስጥ ከሁለት ሺሕ ዐመታት ኑሮ በኋላ፡፡ ይህም ማለት ለምርጫ መዉጣትና ድምጽ መስጠት
ለአንዳንዶቹ መብትን በማስከበር የተገኘ ክብር ተደርጎ ሲቆጠር ከላይ እንደጠቀስናቸዉ ላሉት ሴቶች ደግሞ
ክብራቸዉ ለምርጫ አለመሰለፍ ነዉ ማለት ነዉ፡፡በሌላ ቛንቛ ክብሩ የሚመነጨዉ ከድርጊቱ ሳይሆን ከእምነቱና
ከፍልስፍናዉ ነዉ ማለት ነዉ፡፡
ከላይ የጠቀስኳቸዉን ሁለቱን ዐይነት ሴቶች ብቻ እንኳ ብንወስድ በሴትነታቸዉ አንድ ሆነዉ ሳለ ነጻነታችን
መብታችን ክብራችን ለሚሉት ነገር የተለያዩት ለምንድን ነዉ ስንል ልዩነቱን የዕሴቶቻችን መለኪያ (value
parameter) ልዩነት እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ይህን በአንድ ሌላ ምሳሌ አስረድቼ ልለፍ፡፡ ከጥቂት ዐመታት
በፊት ኢትዮጵያን መጥቶ ከጎበኘ በኋላ ስለኢትዮጵያ የጻፈ አንድ ፈረንጅ ትዝብቱን ሲጽፍ‹‹ኢትዮጵያዉያን
ለልጆቻቸዉ ፍቅር የላቸዉም፤ ምክንያቱም ከወላጆች አንዳቸዉም ከቤት ሲወጡም ሆነ ሲገቡ ልጆቻቸዉን
አይስሟቸዉም(የዛሬን አያድርገዉና እዉነቱን ነዉ እንደሁኑ ከተሜ ልጅ መሳም አልነበረም፤ አሁንም በገጠሩ
ኢትዮጵያ የለም)›› ብሎ ነበር፡፡ በመጽሐፍ ላሳተመዉ ለዚህ ሀሳቡ በመጽሐፍ መልስ የሰጡት ፕሮፌሰር ኤፍሬም
ይስሐቅ ስሕተቱን የገለጹለት ለአስተሳሰቡ መሠረት ከሆነዉ ግንዛቤ በመነሳት ነበር፡፡ እርሱ የሚያዉቀዉ የፍቅር
መግለጫ መሳም ስለነበር የኢትዮጵያዉያኑን የፍቅር መገለጫ ሳይጠይቅ በድፍረት ‹ፍቅር የላቸዉም› ለማለት የበቃዉ
የራሳችን ዕሴት በመዘንጋቱ ነበር፡፡በእኛ የጥንቱ ባህል ልጅን መደበቅ፣ እንግዳም ሲመጣም ወደ ጓዳ ማስገባት፣ ድንገት
እንግዳ ሲመጣባቸዉም በቀሚሳቸዉ ደበቅ ማድረግና የመሳሰሉት ሁሉ የስስትና የፍቅር መግለጫዎች ነበሩ፡፡
ምክንያቱም ሰዉ ሲያይባቸዉ በዐይን ራሱ የሚጎዳባቸዉ ስለሚመስላቸዉ (ይህ ሁሉ ገና ያልተጠና ስለሆነ ሊነቀፍ
የሚችል አይመስለኝም) እጅግ አድርገዉ ለልጃቸዉ ይሳሳሉ፤ ይንሰፈሰፋሉም፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዉያን ለልጆቻቸዉ
በነበራቸዉ ፍቅር ከምዕራቡ ሰዉ ቢበልጡ እንጂ የሚያንሱ አልነበረም፡፡ ሆኖም ፈረንጁ የእኛን ማኅበረሰብ ዕሴት
ሳይጠይቅ በመጻፉ ትልቅ ስሕተት ለመፈጸም ደፍሯል፡፡

አሁንም ደግሞ የበለጡ ስሕተቶች ሲፈጸሙ የምናየዉ በተመሳሳይ መንገድ ነዉ፡፡ ከጥቂት ዐሥርት ዐመታት ጀምሮ
ያሉ አንዳንድ የኮሚኒስት አስተሳሰብ ግራ ያጋባቸዉ ሰዎች መለኪያቸዉ በሙሉ ያዉ ርእዮተ ዓለም ስለሆነ ብዙ
ነገሮቻችን ያጣጥሏቸዋል፡፡ የእኛ ዘመን ትዉልድ ደግሞ መለኪያዉ ሁሉ ምዕራባዊ ብቻ ይሁን የተባለ ይመስል የብዙ
ነገራችንን ሚዛን አዛብቶታል ማለት ይቻላል፡፡ ምሁራኑም በእዉነተኛ ጥናት ላይ ተመሥርተዉ ለመንግሥት ፖሊሲ
ቀረጻ ለማኅበረሰቡም አስተሳሰብ አቅጣጫ መጠቆም የቻሉ አይመስልም፡፡ ከዚህ የተነሳ ይመስለኛል አንዳንድ ሰዎች
ሁሉንም ነገር በሌሎች መነጽር እያዩ የማኅበረሰብ ብዥታን (confusion) በመፍጠር ላይ የሚገኙት፡፡

ከብዥታዎቹ አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ የሴቶችን እኩልነት አያሳይም፤ ስለዚህ ክርስትናም ለወንዶች ያደላ ነዉ የሚለዉ
ተጠቃሽ ነዉ፡፡ ለዚህ እንደ ማሳያ የሚጠቀሰዉ ደግሞ ‹‹ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደሆነ … ባል የሚስት
ራስ ነዉና›› /ኤፌ 5 ፥21/ የሚለዉ ዋናዉ ሲሆን ሌሎች ተመሳሳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችም ይጠቀሳሉ፡፡

በርግጥ በብሉይ ኪዳን ጊዜ የወንዶች ትምክህት ከፍተኛ እንደ ነበር ይነገራል፡፡ ወንዶች በቀዳሚነት ሔዋን የስሕተት
ምክንያት ነች በማለት ዳግመኛም የቀደመዉ አዳም ሴቲቱን ሔዋንን ያለ ሴት አስገኝቷል ፤ እናንተ ሴቶች ግን ወንድ
ብትወልዱም ያለ ወንድ አትችሉም እያሉ ይመኩ እንደነበር ትዉፊቱን የመዘገቡ መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ እነዚህና መሰል
ትምክህቶች ሁሉ ግን የወንዶቹ እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስ አልነበሩም ፤ ሊሆኑም አይችሉም፡፡ ክርስቶስም ሰዉ ሆኖ
በመገለጥ የማዳን ሥራዉን ሲሠራ የጀመረዉ ይህን የወንዶችን ትምክህት ከመናድ ነዉ፡፡ ስለዚህም እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያምን በመምረጥ ከእርሷ ተወለደ፡፡ በዚህም ሔዋን(ሴት) የስሕተት ምክንያት እንደሆነች ሁሉ
እመቤታችንም (ሴት) የድኅነት ምክንያት ሆነች፡፡ አዳም ሔዋንን ያለ ሴት እንዳስገኘ ሁሉ እመቤታችንም ጌታን
በድንግልና በመዉለድ ወንዱን ያለወንድ በማስገኘት የወንዶችን ትምክህት አፈረሰችዉ፡፡ እመቤታችንም ጌታን
በመዉለድ የከበረች ስለሆነ ከፍጥረት ሁሉ (ከመላእክትም ጭምር) ትበልጣለችና መልዕልተ ፍጡራን ትባላለች፡፡
እመቤታችን የሴቶች መመኪያ የምትባለዉም ለዚህ ነዉ፡፡ ስለዚህ ክርስትና የተጀመረዉ የትዕቢትና የመናናቅ
ምክንያት የሆኑትን አስተሳሰቦች ከማጥፋት ነዉና ተወቃሽ ሊሆን አይችልም፡፡ ከዚህ የተረፈ ካለም የሰዎች እንጂ
የመጽሐፍ ቅዱስ ወይም የቤተ ክርስቲያን አይደለም፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስም ዐላማ ሰዉን ማጽደቅ ስለሆነ በጸጋ፣ በእምነት፣ በሥራ በሚገኝ ዋጋ፣ … በመሳሰሉት ነገሮች
የልዩነት መነሻዉ የራስ እምነት እንጂ ጾታ አይደለም፡፡ የወንዶችም የሴቶችም ቅዱሳን በብዛት አሉንና፡፡

ይሁን እንጂ ቀደም ብለን ያነሳናቸዉን ጥቅሶች መሠረት በማድረግ መጽሐፍ ቅዱስን ተጠያቂ ለማድረግ የሚጣጣሩ
አሉ፡፡ በመሠረቱ አንድ የተማረ ሰዉ እንደሚያደርገዉ የቅዱስ ጳዉሎስን ሌሎች መልእክቶች በማንበብ ብቻ እንኳ
ትርጉሙን ወይም መልእክቱን ለመረዳት ብንጥር በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ያህል ‹‹ ነገር ግን የወንድ ሁሉ
ራስ ክርስቶስ፣ የሴትም ራስ ወንድ፣ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደሆነ ልታዉቁ እወዳለሁ›› /1 ኛ ቆሮ
11፥3/ የሚለዉን ሌላዉን ጥቅሱን ብንመለከተዉ ግልጽ ያደርግልናል፡፡ ከዚህ ጥቅስ ‹‹ የክርሰቶስም ራስ
እግዚአብሔር›› የምትልዋን ስንመለከት የራስ ትርጉም መበላለጥ፣ የበላይነትና የበታችነት ጉዳይ እንዳልሆነ መረዳት
እንችላለን፡፡ምክንያቱም ጌታ ራሱ ‹‹ እኔና አብ አንድ ነን›› // እንዳለ በጌትነት፣ በሥልጣን፣ በመለኮት አንድ
ናቸዉና፡፡ ስለዚህ ራስ የሚለዉ ቃል ትርጉም ከዚህ የራቀ እንደሆነ ይገባናል፡፡ ራስ ማለት መገኛ ማለት ነዉ፡፡
ስለዚህ ‹‹የክርሰቶስ ራስ እግዚአብሔር ነዉ›› ሲል እግዚአብሔር ወልድ ከእግዚአብሔር አብ በዘመን ሳይቀዳደም
በመለኮት ሳይተናነስ ከአብ የተገኘ ነዉ ማለት እንደሆነዉ ሁሉ ‹‹ የሴት ራስ ወንድ ነዉ›› ሲልም ሔዋን በባሕርይ
ሳትተናነስ የተገኘችዉ ከኣዳም ነዉ ለማለት ነዉ፡፡ ስለዚህ የጥቅሱ ትርጉም መገኛነትን የሚያመለክት እንጂ የተለየ
የጨቛኝነት መልእክት የለዉም፡፡

በሌላ መንገድ ስናየዉ ደግሞ (በተለይ ጥቅሱ የተጠቀሰዉ ለባለትዳሮች ነዉና) መልእክቱ እጂግ ደስ የሚያሰኝ
ይሆናል፡፡ ራስ ያለዉ ጭንቅላትን ስለሆነ ለወንዶች የተሰጠዉን ኃላፊነት የሚያመለክት ነዉ፡፡ ምክንያቱም በአንድ
አካል ዉስጥ አንድ ራስ እንዳለ ሁሉ በአንድ ቤተሰብም ዉስጥ አንድ ራስ አለ፤ እርሱም ባል ነዉ፡፡ የዚህ ምክንያቱ
ደግሞ ሁለት ነዉ፡፡ አንደኛ አካል ከህልዉና ተባብሮለት በመገኘት አዳም ይቀድማል፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ሃይማኖታዊ
በሆነዉ ጋብቻ ዉስጥ የወንዱ ዕድሜ መብለጥ ይገባዋል፡፡ይህም የሚሆነዉ በተፈጥሮኣቸዉ ዉስጥ ያለዉን ልዩነት
አጣጥሞ ትዳሩን ዘላቂ ለማድረግ ጭምር ነዉ፡፡ ስለዚህ ወንዱ ከሴቲቱ በዕድሜና በተፈጥሯዊ ሁኔታዎች ይበልጣልና
የራስን ሓላፊነት አሸከመዉ፡፡ በአንድ አካል ዉስጥ ያለ ራስ የትኛዉንም የሰዉነት ክፍል አይጨቁንም፤ ይልቁንም
ብልቶችን ሁሉ ይቆጣጠራል፣ ይመግባል፣ ይንከባከባል እንጂ፡፡ ከሰዉነት ክፍሎች አንዱ ቢታመምም ያንን የታመመ
ብልት የበለጠ ይጠነቀቅለታል፣ ተንከባክቦም ወደ ጤንነት ይመልሰዋል፡፡ ስለዚህ ወንድ ራስ ነዉ ሲባልም ሓላፊነቱ
ልክ እንዲሁ ቤተሰቡን መንከባከብ፣ መመገብ፣ ጤንነቱን መመለስ ነዉ፡፡ አንድ የሰዉነታችን ክፍል ሲታመም ራሳችን
እንደሚያመን ሁሉ ባልም የቤተሰቡን ሁሉ ሕማምና ችግር የሚካፈል የሚፈታም ማለት እንጂ ራስ በመባሉ የበላይ
ገዥ ነዉ ማለት አይደለም፡፡ ከሰዉነት ብልቶች ራስ የሚረግጠዉ ብልት የለም፡፡ ይረግጣል የምንለዉ እግር እንኳ
መሬትን እንጂ አካልን አይረግጥም፡፡ ምናልባት ሚስቱን ወይም ሴቶችን የሚበድል ወንድ እንኳን ራስ ሊሆን እግርም
ለመሆንም አቅቶታል ማለት ነዉ፡፡የሰዉነት ብልቶች ሁሉ ለራስ (ጭንቅላት) ያለማመንታት እንደሚታዘዙ እንዲሁ
የቤተሰብ አባላትም በዚሁ መንገድ ለቤተሰቡ ራስ ለባል መታዘዝ ይኖርባቸዋል ማለት ነዉ፡፡ በሰዉነት ዉስጥ ይህ
መስተጋብር ቢጠፋ ሰዉየዉ ለሞት እንደሚሰጠዉና አካልም እንደሚፈርሰዉ ልክ እንደዚሁ ሁሉ በቤተሰብም ዉስጥ
በሰዉነት ዉስጥ ያለዉን ፍጹም አንድነትና መስተጋብር ከሌለ ትዳርም ማኅበረሰብም ሕይዎት አይኖራቸዉም፡፡
ስለዚህ ወንድ የሴት ራስ የሚለዉ በአንድ አካል ዉስጥ ያለ ሓላፊነትንና ዉሕደትን እንጂ የልዩነትና የመበላለጥ ዋቢ
አይደለም፡፡ የሰዉነት ክፍሎች ሁሉም ራስ ሊሆኑ አይችሉም፤ ቢሆኑም አይጠቅሙም፡፡የአንድ ሀገር ዜጎች ሁሉም መሪ
እንደማይሆኑ ቤተሰብም ሁሉ መሪ ቢሆን ጉዳት እንጂ ጥቅም የለዉም፡፡ ስለዚህ ራስነት ለአንዱ ብቻ ነዉና በሥነ
ተፈጥሮ ሕግ ወንዱ ራስ እንደሆነ ይኖራል፡፡

ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችም ትርጉማቸዉ በዚሁ መንገድ የሚፈታ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ ትልቁ ችግር የተፈጠረዉ
በመጽሐፉ ወይም በእምነቶቹ ሳይሆን ከላይ እንደጠቆምኩት እምነታዊ ቃላቱን ዳርዊናዊ መሠረት ባለዉ ማርክሳዊ
ሌኒናዊ ወይም ደግሞ ፍጹም ሊበራል በሆነ ምዕራባዊ መስፈሪያ ከመለካት ሙከራ የሚመጣ ስሕተት ነዉ፡፡ እያልኩት
ያለሁት የሴቶች መብት አይከበር አይደለም፡፡ እያልኩ ያለሁት የትኛዉ ነዉ ክብራቸዉ፣ መብታቸዉ፣ ጥቅማቸዉ
(በዘመኑ ቛንቛ ለመናገር እንጂ ክብራቸዉ ክብራችን፣ ጥቅማቸዉም ጥቅማችን፣ …ነዉ) የሚለዉን ጠይቀን በእኛዉ
እሴቶች መዝነን፣ አጥንተን መጠቀም ሲገባ ሌሎቹ ጠጥተዉ ባሸተቱን ቁጥር ቀድመን ማግሳቱን እናቁምና ለእኛዉ
በሚጠቅመን መንገድ እናድርገዉ ነዉ፡፡ ለእሥራኤላዊቷ ሴት ክብሯና መብቷ የሆነዉ ነገር በምዕራባዊ እሴት
ለምትኖር አንዲት ሴት ሊሆናት አይችልም፡፡ ስለዚህ ልዩነቱ የፍልስፍና የእምነት የባህልና የዕሴት ሆኖ ሳለ በዚያዉም
ላይ የትኛዉ የተሻለ ጠቃሚ እንደሆነ ሳናጠና ሁሉንም በሰዉ መነጽር እያየን መልኩን ባናክፋፋዉ ይሻለናል፡፡ ስለዚህ
‹‹ወንድ-የሴት ራስ›› የጥቅም እንጂ የጉዳት፣ የክብር እንጂ የዉርደት ፣ የመከባበርና የመዋሐድ ትእዛዝ እንጂ
የመበላለጥና የመለያየት ትእዛዝ አይደለም፡፡ ይልቁንስ ባልገባን ነገር ገብተን አካልን አንገነጣጥል፣ ቤተሰብንም
አንፈትን፡፡
የመገለጥ ሃይማኖት በአስተርእዮ

በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ

ሃይማኖት የምንቀበለውና የምንጠብቀው እንጂየምንሠራውና የምናሻሽለው አይደለም ከታኅሣሥ 29 ቀን ጀምሮ እስከ


ዐቢይ ጾም መግቢያ ድረስ ያለው ወቅት /ጊዜ/ ዘመነ አስተርእዮ /የመገለጥ ወራት/ እየተባለ ይጠራል፡፡ በታኅሣሥ
29 ቀን የጌታችን ልደት ስለሆነ በዚህ አምላክ በሥጋ የተገለጠበት በዓል ይከበራል፡፡ ጥር 11 ቀን ደግሞ በጌታችን
ጥምቀት የሥላሴ አንድነት ሦስትነት በይፋ የተገለጠበት ነው፡፡ ጥር 12 ቀን ደግሞ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በዚህ ምድር ማስተማር በጀመረበት ጊዜ በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን በመለወጥ
አምላክነቱን በይፋ የገለጠበት በዓል ነው፡፡ እነዚህ ሦስት ዓበይት መገለጦች ወቅቱን በአጠቃላይ እግዚአብሔር ለሰው
ልጅ የተገለጠበትን መታሰቢያ አደረጉት፡፡ አምልኮተ እግዚአብሔርን ትክክለኛ ሃይማኖት ከሚያሰኙት መሠረታዊ
ነጥቦች ዋነኛውና ቀዳሚው የመገለጥ ሃይማኖት /Revealed Religion/ መሆኑ ነው፡፡ የአምላክን ማንነት
በእምነት ለሚመረምር ሰው አምላክ ያልተፈጠረና ሁሉን የፈጠረ፣ የማይወሰን፣ በጊዜም የማይለካ ማለት ከጊዜና ቦታ
ውጭ /Out of space time/ መሆኑ ሊጠረጠር አይችልም፡፡ስለዚህ አምላክ ከቦታና ጊዜ ውጭ ከሆነና
በሁሉም ቦታ ደግሞ የመላ ወይም ምሉዕ ከሆነ /Omni present/ በቦታ ጊዜ ውስጥ ያሉ ፍጥረታት አምላክን
ሊያዩት አይቻላቸውም ማለት ነው፡፡ ይህን ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረትነት እናብራራው፡፡ «ከጥንት ጀምሮ
እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም
«ዘመናትን» በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን» /ዕብ 1፥1/ በሚለው የቅዱስ ጳውሎስ
ትምህርት ውስጥ «ዘመን» ወይም ጊዜ ፍጥረት መሆኑን በግልጽ እንረዳለን፡፡ መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞንም «ጥበብ
ቤቷን ሠራች፤ ሰባት ምሰሶዎችንም አቆመች» /ምሳ 9፥1/ በማለት በምሳሌው ተጨማሪ ምስክርነት ሰጥቷል፡፡
ሊቃውንት በትርጓሜ እንዳብራሩት «ጥበብ» የተባለ ጌታ «ቤት» የተባለ ዓለምን ፈጥሮአል፡፡ ዓለሙ የጸናባቸው
«ሰባት ምሰሶዎች» ደግሞ ዓለምን እስከ ዕለተ ምጽአት የሚያጸኑት አዕዋዳት ሰባቱ ዕለታት ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር
ዓለምን የአጸናው ጊዜ ነው ማለት ነው፡፡ሙሴ «በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ» ዘፍ 1፥1
ባለበት የሥነ ፍጥረት መጽሐፍም ጨለማ የነበረ መሆኑን ከተረከልን በኋላ « ብርሃን ይሁን አለ» ይልና ጠዋትም
ሆነ ማታም ሆነ አንድ ቀን በማለት ዓለምና ጊዜ አንድ ላይ መፈጠራቸውን ይነግረናል፡፡ ከዚያም አስከትሎ የቀሪዎቹን
የአምስት ቀን ፍጥረታትና የመጨረሻዋን /የሰባተኛውን/ ዕለት ዕረፍትነት ነግሮን ያጠቃልላል፡፡ ከዚያ በኋላ ዓለም
ይቀጥላል፤ የዕለታቱ ዑደትም ይቀጥላል፡፡ በሰባት ዕለት አጸናው ማለት ይህ ነው፡፡ ሁሉንም እርሱ እንደፈጠረ ደግሞ
« ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳች እንኳ ያለ እርሱ የሆነ የለም፤» ዮሐ 1፥3 «የሚታዩትና የማይታዩት ዙፋናት
ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና፤
ከፍጥረት ሁሉ በፊት በእርሱ ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው፤ ሁሉም በእርሱ
ተጋጥሞአል» /ቆላ.1፥15-17/ ተብሎ ስለተጻፈ አምላክ በቅዱሳት መጻሕፍትም ከቦታ ጊዜ ውጭ መሆኑ
የተረጋገጠ ነው፡፡ፈጣሪ ከቦታ ጊዜ ውጭ ከሆነ ሊያየው የሚቻለው ፍጥረት የለም ማለት ነው፡፡ ወንጌላዊ ዮሐንስ
«መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም» /ዮሐ 1፥18/ እንዳለ፡፡ በመቃብያንም «አንተን ሁሉን
ታያለህ እንጂ አንተን ማየት የሚችል የለም» ተብሎ ተጽፎአል፡፡ 3 ኛ መቃ.9፥26 ቅዱስ ጳውሎስም «ማንም
ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያየውም አይቻለውም» /1 ኛ ጢሞ.6፥16/
ሲል እንዳጸናው ለፍጥረት እግዚአብሔርን ማየት አይቻልም፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ እርሱን በምርምር ማወቅም
አይቻልም፡፡ አካሉ ረቂቅና ምሉዕ፣ በቦታ ጊዜ የማይወሰን ከሆነ ማን በምን ሊመረምረው ይችላል፡፡ በግብሩ በባሕርዩ
እንመርምረው እንዳንል በእኛ ኅሊናችን ኅሊናን የፈጠረውን መመርመር ሸክላ ሠሪውን ለማወቅ ከመጣር የበለጠ
የማይቻል ነው፡፡ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት «ወረሰየ ጽልመተ ምስዋሮ፤ ጨለማን መሰወሪያው አደረገ»
እንዳለው ሊመረመር አይችልም፡፡ በጨለማ ማየት እንደማይቻል ሁሉ የእግዚአብሔር ባሕርይ ሊመረመር የማይቻል
ነውና፡፡ ታዲያ ፈጣሪን እንዴት ማወቅ ይቻላል? የሚለው ጥያቄ በዚህ ጊዜ ሊነሳ የሚገባ ነው፡፡ መልሱም ቀላል
ነው፡፡ የምናውቀው እርሱ ራሱ ሲገለጥልንና ሲገልጥልን ብቻ ነው፡፡ ከተገለጠበትና ከገለጠውም መጠን በላይ ማወቅ
አይቻልም፡፡ ስለዚህ የእውነተኛ ሃይማኖትነት መሠረታዊ ማረጋገጫዎች መካከል አንዱና ዋናው መገለጥ ነው ያልነው
ለዚህ ነው፡፡ እርሱ ራሱን ባይገልጥ ማን በምን መንገድ ሊያውቀው ይችላል፡፡ አምልኮተ እግዚአብሔርን በሦስቱም
ሕግጋት /በሕገ ልቡና፣ በሕገ ኦሪት፣ በሕገ ወንጌል/ ብንመረምረው መንገዱ ሁሉ መገለጥ ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
እግዚአብሔር ራሱን ለመላእክት በመፍጠር ገለጠላቸው፡፡ ለአዳም ተገለጠለት፣ አነጋገረው፣ ትእዛዝም ሰጠው፡፡
ከበደለውም በኋላ ፈለገው፤ አነጋገረው፤... የሚሉት በሙሉ መገለጥን የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በኦሪት
ዘፍጥረት ላይ እግዚአብሔር አዳምን «አዳም አዳም ወዴት ነህ?» አለው የሚለው ያለበትን ያለማወቅ ሳይሆን አዳም
ከበደለም በኋላ ለኃጢአተኛ ባሕርዩ በሚስማማ ሁኔታ መገለጡን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ከዚህም በኋላ በሕገ ልቡና
ለአባቶች ሁሉ በየዘመናቸው እንደ ሃይማኖታቸው ጽናት እንደ አእምሮአቸው ስፋት ሲገለጥላቸው ኖርአል፡፡
«በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት» ተብሎ ስለ
አብርሃም የተጻፈው ነው፤ /ዘፍ. 18፥1/ የሚለው የዚህ ማረጋገጫ ነው፡፡ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በየዘመኑ ለነበሩ
ሰዎች የተገለጠበት መንገድ የተለያየ ከጥንት ወደ አሁን ጊዜ ስንመለከተውም የበለጠ እየተገለጠ እንደመጣ ቅዱሳት
መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ ለምሳሌ የሕገ ኦሪት መሥራች ለምንለው ለሙሴ ሲገለጥለት ለአብርሃም ከገለጠለት በላይ
ለእርሱ እንደገለጸለት ነግሮታል፡፡ «እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፣ አለውም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤
ለአብርሃምም፣ ለይስሐቅም፣ ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፣ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር
አልታወቀላቸውም ነበር» /ዘጸ. 6፥2-3/ ተብሎ የተጻፈው ሌላው ቀርቶ « እግዚአብሔር» የሚለው ስም እንኳ
ከዚያ በፊት ላሉት እንዳልታወቀ ያረጋግጥልናል፡፡ ስለዚህ «እግዚአብሔር» የሚለውና ሌሎች ብዙ ነገሮች ከሕገ
ኦሪት በኋላ እንደተገለጡ መጽሐፍ ቅዱስ ሰፊ ምስክርነት ይሰጠናል፡፡ ይልቁንም ደግሞ ምሳሌያዊ
/Allegorical/ በሆነ መንገድ የተገለጡትን ስንመለከት እጅግ እንደነቃለን፡፡እግዚአብሔር ለነቢያቱም በተለያየ
መንገድ ተገልጦላቸዋል፡፡ ለሙሴ በሐመልማል ወነበልባል /ዘጸ.3፥1/ ለኢሳይያስ በአምሳለ አረጋዊ ነዋሕ፤ /ኢሳ.
6፥1/ ለዳንኤል በአምሳለ ዕብን ቅውም ከረጂም ተራራ ላይ በተፈነቀለ ትልቅ ድንጋይ / ዳን 9፥ /... ለሌሎቹም
በብዙ ኅብርና አምሳል ተገልጦላቸዋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ « በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና» ያለው ይህንኑ ነው፡፡
/ዕብ.1፥1/ በብሉይ ኪዳን የተጻፉ መጻሕፍትን በሙሉ ስንመለከታቸው «እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤...» በሚል መግቢያ የሚጀምሩ ናቸው፡፡ ይህም ቃልና ትምህርቱ በሙሉ
ከእግዚአብሔር የተሰጠ እንጂ የእነርሱ ላለመሆኑ በሌላ አነጋገር የመገለጥ ሃይማኖት፤ ትምህርት መሆኑን እየደጋገመ
ያረጋግጥልናል፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ፤ በብሉይ ኪዳን ብዙ ነቢያት ተነሥተው ቢያስተምሩም ብዙ መጻሕፍት ቢጽፉም
የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ግን እጅግ ምስጢራዊና ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ እንጂ በግልጽ አልታወቀም
ነበር፡፡ ምክንያቱም በሚገባው መንገድ ራሱን ገና አልገለጠም ነበርና፡፡ ለአብርሃም የተገለጡት ሦስት ሰዎች፤ «ኑ
እንውረድ፣» የሚሉት ዓይነት ቃላትና ይህንኑ ከሚመስሉት ጥቅሶች በቀር በጊዜው /ብሉይ ዘመን/ የነበሩ ሰዎች ሁሉ
ስለ እግዚአብሔር የአንድነትና የሦስት ምስጢር በበቂው አልተገለጠላቸውም፡፡ በመጽሐፈ ኢያሱ የተጻፈውንና ስለ
እሥራኤል የዮርዳኖስ ወንዝ ተሻግሮ ከምድረ ርስትን መርገጥን በተመለከተ «ሙሴም እንዳዘዛቸው የሮቤል ልጆች፣
የጋድም ልጆች፣ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ተሰልፈው በእሥራኤል ልጆች ፊት ተሻገሩ፡፡» የሚል ተጽፎአል
/ኢያ.4፥17/፡፡ አንድ የጥንት የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ይህን ሲተረጉመው እነዚህ ቀድመው የተሻገሩት ከአሥራ ሁለቱ
ነገድ ሁለቱ ነገድ በሙሉና ሦስተኛው ከፊሉ መሆኑ በብሉይ ኪዳን ዘመን ስለነበረው የሥላሴ ዕውቀት ምሳሌ ነው፡፡
በዚያ ዘመን ስለ አብና ስለወልድ በመጠኑ ስለመንፈስ ቅዱስ ደግሞ እጅግ በብዥታ ያውቁ ነበር፡፡ ሦስተኛው ነገድ
በከፊል የተሻገረው ለዚህ ነው፡፡ ሦስቱ ነገድ እንኳን አለመሟላቱም በዘመኑ ምስጢረ ሥላሴ በከፊል በምሳሌና በጥላ
ብቻ ይታወቅ የነበረ ስለመሆኑ አሰረጂ ነው በማለት ይተረጉማል፡፡በርግጥም ቀደም ብለን እንዳየነውም የእግዚአብሔር
መገለጥ እየጨመረ እየጨመረ እንደመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ምስክር ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን ዘመን መገለጥ እየጨመረ
እየጨመረ ከመጣ በኋላ ፍጹም መገለጥ ሲመጣ ያኛው የጥላውና የምሳሌው መገለጥ ይደመደማል፡፡ ፍጹሙ
መገለጥም የአምላክ ሰው ሆኖ መገለጥ ነው፡፡ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ «መጀመሪያ ቃል ነበረ፣...» ካለ በኋላ
«ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር፡፡ በዓለም ነበረ ዓለሙም በእርሱ ሆነ
ዓለሙም አላወቀውም» ዳግመኛም ከዚያው አስከትሎ «ቃልም ሥጋ ሆነ፣ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ
አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነውን ክብሩን አየን» ሲል መገለጡን አበሠረ፤ /ዮሐ 1፥1-18/፡፡
ይህን መገለጥ ደግሞ እንኳን ሰዎች መላእክትም ተግተው ይሹት ነበረ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ፤ «ለእናንተ ስለሚሰጠው ጸጋ
ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤ ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ
ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም
ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ» /1 ኛ ጴጥ. 1፥1-12/ ሲል እንደገለጸው፤ መላእክቱ የአምላክን መገለጥ
ለማየት እጅግ ጓጉተው ነበር፡፡ ምክንያቱም እነርሱም ቢሆኑ አምላክን ለማየት ዕድል የሚያገኙት ሰው ሆኖ ሲገለጥ
ብቻ ነውና፡፡ቅዱስ ጳውሎስ፤ «እግዚአብሔርንም የመምስል ምስጢር ያለጥርጥር ታላቅ ነው፡፡ በሥጋ የተገለጠ፣
በመንፈስ የጸደቀ፣ ለመላእክት የታየ፣ በአሕዛብ የተሰበከ፣ በዓለም የታመነ፣ በክብር ያረገ» /1 ኛጢሞ.3፥16/
በማለት ለመላእክት የታየው በሥጋ በመገለጡ እንደሆነ አረጋግጦልናል፡፡ እነርሱም ምስጢረ ሥጋዌን ከሰው በላይ
አጣጥመው ተጠቅመውበታል፡፡ በብሥራቱ ቅዱስ ገብርኤል ብቻ ቢሣተፍም በልደቱ ጊዜ ግን ብዙዎች መላአክት
በአንድነት ለእረኞች ለማብሠር ታድለዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በመዋዕለ ሥጋዌው ሁሉ እየተላላኩ አምላክን ማየት ጠገቡ፡፡
ሲሰቀልና ሲሞትም በአርምሞ በመደነቅ ተመለከቱ፡፡ ትንሣኤውን አበሠሩ፡፡ የቀሩትም በዕርገቱ ዕለት ሐዋርያትን
አረጋግተው ዳግም ምጽአቱን አውጀው ተሰወሩ፡፡ ዳግመኛ ሲመጣ መለከት እየነፉ ከፊት ከፊት እየቀደሙ ከኋላም
እየተከተሉ እንደሚመጡም ተጽፎላቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የአምላክ መገለጥ የመላእክት ደስታ ሆነ፡፡ ስብሐት
ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ፤ እያሉ የዘመሩት ወድደው አይደለም፡፡ ተገልጦ ባዩት ጊዜ
ለመደመማቸው ወሰን ቢያጡ ለሰው ያለውንም ፍቅር ይገልጡት ዘንድ ቢሳናቸው፤ ይህን ምስጋና እያጣጣሙ ክብርና
ቅድስናቸውን ለራሳቸው አስጨመሩ፡፡ ይሁን እንጂ አምላክ ሰው በመሆኑ ከረቂቃኑ መላእክት ይልቅ የበለጠ የቀረቡት
ሰዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ በዘመነ ብሉይ እንደ ነበረው እንደ ሄኖክ፣ እንደ መልከጼዴቅ፣ አብርሃም፣ ይስሐቅና ያዕቆብ፣
ዳዊትና ሰሎሞን፣ ሙሴና ነቢያት ራሳቸውን የቀደሱና ያነጹ ብቻ ሳይሆኑ በኃጢአት የረከሱት እነ ዘኬዎስ፣ ማርያም
እንተ ዕፍረት፣ መጻጉዕ፣ በዝሙት የተያዘችው ሴትና ሌሎቹም ሰውነቱን ዳሰሱት፤ አብረውት በሉ ጠጡ፤ . . .፡፡
ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን መገለጡን በሰፊው አሰበችው፤ በተድላ በደስታ፤ በመብልና በመጠጥም ጭምር
የምታከብረውም ለዚህ ነው፡፡ ከዚህ መገለጥ በኋላ የተላኩ ሐዋርያትም የትምህርታቸው አቀራረብ ተለወጠ፡፡ እንደ
ነቢያት በዚህ መንገድ አየነው፣ እንዲህ ሆኖ ተገለጠልን የሚለው ቀረና ቅዱስ ዮሐንስ እንዳለው፤ «ስለ ሕይወት ቃል
ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም፣ እጆቻችንም የዳሰሱትን
እናወራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ፤ አይተንማል እንመሰክርማለን፤ ከአብ ዘንድ የነበረንም ለእኛም የተገለጠውን፤
የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን» /1 ኛዮሐ. 1፥1-3/ እያሉ ለማስተማር ቻሉ፡፡ ከዕርገቱም በኋላ ቢሆን እርሱ
ከቅዱሳኑ ተሰውሮ አያውቅም፡፡ ይልቁንም ከተዋሕዶ በኋላ ምንታዌ የለምና /ሰው ከሆነ በኋላ መታየቱ፣ መወሰኑ፣
መጨበጡ፣ መዳሰሱ አልቀረምና/ በየዘመኑ ይገለጣል፡፡ በየቅዱሳኑ ሕይወት እንደተጻፈው እነ አባ ብሾ/ሶ/ይ እግሩን
አጠቡት፣ አዘሉት፡፡ በየዕለቱ ለሰማዕታቱ እየተገለጠ አጸናቸው፤ ጻድቃኑንም ምስጢሩን አብዝቶ ገለጠላቸው፡፡
በየገድላቱም ላይ ቅዱሳኑ ሲያርፉ «ይህን ያህል ቅዱሳኑን አስከትሎ መጣ፤ ነፍሱንም ተቀበለ፣. . .» የመሳሰሉት
አገላለጾች ምንኛ ግሩም ናቸው፡፡አንድ ጊዜ ሰው ሆኖአልና እንደቀድሞው ለነቢያቱ እንዳደረገው ሳይሆን አሁን በሥጋ
ተገልጦአልና በየጊዜው ይመጣል፣ ይታያል፣ ይጨበጣል፤ ይዳስሳቸዋል፤ ይስማቸዋል፤ ያወጋቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስን
በሮማ አደባባይ «ወዴት ትሔዳለህ?» ብሎ እንደመለሰው፤ በየዘመኑ እየተገለጸ ይመራቸዋል፤ ያነጋግራቸዋልም፡፡
መገለጥ፤ ግሩምና ድንቅ መገለጥ፤ ሃይማኖቱም የመገለጥ፡፡ እርሱ ራሱ «ይህ ዛሬ እናንተ የምታዩትን ብዙ ነቢያት
ሊያዩ ወደው አላዩም፤ እናንተ የምትሰሙትን ሊሰሙ ወድደው አልሰሙም፤ የእናንተ ግን ያዩ ዓይኖቻችሁ፤ የሰሙ
ጆሮቻችሁ የተመሰገኑ ናቸው» እንዳለ ፤ የሐዲስ ኪዳን፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ባሕታውያን ስውራን ሁሉ ምን ያህል
የተመሰገኑ ናቸው፡፡ በየዕለቱ ጌታቸውን ያዩታልና፤ ለዚህም ተጠርተዋልና፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን
ልዩ የሚያደርጋት ብቻ ሳይሆን ከትክክለኛነቷ ማረጋገጫዎች አሁንም ዋነኛዋ መገለጡ ነው፡፡ የሌሎቹ በተለይም
ከኢንዱስትሪው አብዮት በኋላ የተነሡ የክርስትና ክፍልፋዮች /Denominations/ ሁሉ መሠረተ እምነታቸው
የሚዋቀረው በዩኒቨርስቲዎችና በየተቋማቱ ባሉ ምሁራኖቻቸው አስተምህሮ በጠረጴዛ ዙሪያ ነው፡፡ የኦርቶዶክሳዊት
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚመሠረተው ግን በገዳማውያን ቅዱሳን መገለጥ ላይ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ
እስካሁን ሊቃውንቱ ሁሉ በመማር ብቻ ሳይሆን በገዳም ተወስነው፣ ሱባኤ ገብተው፣ በእርሱ መገለጥ የተሰወረ
ምስጢር ይገለጥላቸዋል፤ የረቀቀው ይጎላላቸዋል፡፡ ያንን ብቻ ያስተምራሉ፤ እርሱንም ብቻ ይዘን እናስተምራለን፤
በተገለጠውም መሠረት እንኖራለን፡፡ በእኛ ሀገር እንኳን እነ ቅዱስ ያሬድ፤ አባ ጊዮርጊስ፣ አባ ዜና ማርቆስ፤ አባ
ተክለሃይማኖት፣. . . ሁሉም በሱባኤ፣ በገዳም፣ በምናኔ፣ በተጋድሎ ተወስነው፤ በተገለጠውና በሚገልጥላቸው
መንገድ ብቻ ተጓዙ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትም የሚያረጋግጡልን ይህንኑ ብቻ ነው፡፡ ሃይማኖትን እንቀበለዋለን ከዚያም
እንጠብቀዋለን እንጂ ልንሠራው አንችልም፡፡ የያዕቆብ ወንድም ቅዱስ ይሁዳ «ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ
ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችኋለሁ» /ይሁ.1፥3/ ሲል እንደገለጸልን፤ ሃይማኖት ለቅዱሳን
በመገለጥ የተሰጠች እንጂ የተሠራች አይደለችም፡፡ ጌታችንም በወንጌል «ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን
ገለጥሁላቸው፡፡ የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው፤ ቃልህንም ጠብቀዋል፡፡ የሰጠኸኝን ሁሉ ከአንተ እንደሆነ ያውቃሉ፤
የሰጠኸኝ ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት. . .» /ዮሐ.17፥22/ ሲል እንዳስተማረው፤ ክርስትና
የተቀበልነውና የምንጠብቀው እንጂ የሠራነውና የምናሻሽለው አይደለም፡፡ በዚያ ጊዜ ያልገለጸልንንም «የምነግራችሁ
ብዙ ነገር አለ፤ አሁን ግን ልትሸከሙት አትችሉም፤ መንፈስ ቅዱስ በመጣ ጊዜ ግን እርሱ ሁሉንም ያሳውቃችኋል»
የሚል ተስፋን ሰጠን፡፡ መንፈስ ቅዱስም ከእኛ ጋር የሚኖረውም እስከ ዕለተ ምጽአት መሆኑን አረጋገጠልን፡፡
ስለዚህም እስከ ዛሬ ድረስ መንፈሳቸውን ላላረከሱት በየጊዜው ይገለጣል፡፡ ለሐዋርያት ገለጠላቸው፤ ለሊቃውንት
ገለጠላቸው፤ ለጻድቃን በየገዳሙ ገለጠላቸው፤ ለየመምህራኑም በየሱባኤያቸው በተቀደሱ ጉባኤዎቻቸው ገለጠላቸው፤
እኛም የተገለጠውን ይዘን እርሱንም እየጠበቅን እንጓዛለን፡፡ ከተገለጠው ውጭ መጓዝም የተወገዘ መሆኑን ቅዱስ
ጳውሎስ፤ «ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ
የተረገመ ይሁን» /ገላ.1፥8/ በማለት አረጋገጡልን፡፡ ስለዚህም በዘመነ አስተርእዮ ይህን የአምላክን መገለጥ እና
የመገለጥን ሃይማኖት የምንዘክርበት ምክንያት፤ ሃይማኖት ሰዎች ያልፈጠሩት ነገር ግን በአምላክ መገለጥና እርሱ
በገለጠው ሃይማኖታዊ ዕውቀት ብቻ መጓዝን ማዘከር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በተገለጠልን ጸንተን ለቅዱሳን
የተሰጠችውን ሃይማኖት ተጉዘንባት ለልጆቻችንም አውርሰናትና ጠብቀናት እንድናልፍ የእግዚአብሔር ቸርነት
የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፤ አሜን፡፡
በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ሃይማኖት የምንቀበለውና የምንጠብቀው እንጂየምንሠራውና የምናሻሽለው አይደለም
ከታኅሣሥ 29 ቀን ጀምሮ እስከ ዐቢይ ጾም መግቢያ ድረስ ያለው ወቅት /ጊዜ/ ዘመነ አስተርእዮ /የመገለጥ ወራት/
እየተባለ ይጠራል፡፡ በታኅሣሥ 29 ቀን የጌታችን ልደት ስለሆነ በዚህ አምላክ በሥጋ የተገለጠበት በዓል ይከበራል፡፡
ጥር 11 ቀን ደግሞ በጌታችን ጥምቀት የሥላሴ አንድነት ሦስትነት በይፋ የተገለጠበት ነው፡፡ ጥር 12 ቀን ደግሞ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ማስተማር በጀመረበት ጊዜ በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ተገኝቶ
ውኃውን ወደ ወይን በመለወጥ አምላክነቱን በይፋ የገለጠበት በዓል ነው፡፡ እነዚህ ሦስት ዓበይት መገለጦች ወቅቱን
በአጠቃላይ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የተገለጠበትን መታሰቢያ አደረጉት፡፡ አምልኮተ እግዚአብሔርን ትክክለኛ
ሃይማኖት ከሚያሰኙት መሠረታዊ ነጥቦች ዋነኛውና ቀዳሚው የመገለጥ ሃይማኖት /Revealed Religion/
መሆኑ ነው፡፡ የአምላክን ማንነት በእምነት ለሚመረምር ሰው አምላክ ያልተፈጠረና ሁሉን የፈጠረ፣ የማይወሰን፣
በጊዜም የማይለካ ማለት ከጊዜና ቦታ ውጭ /Out of space time/ መሆኑ ሊጠረጠር አይችልም፡፡ስለዚህ
አምላክ ከቦታና ጊዜ ውጭ ከሆነና በሁሉም ቦታ ደግሞ የመላ ወይም ምሉዕ ከሆነ /Omni present/ በቦታ
ጊዜ ውስጥ ያሉ ፍጥረታት አምላክን ሊያዩት አይቻላቸውም ማለት ነው፡፡ ይህን ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረትነት
እናብራራው፡፡ «ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ሁሉን
ወራሽ ባደረገው ደግሞም «ዘመናትን» በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን» /ዕብ 1፥1/
በሚለው የቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ውስጥ «ዘመን» ወይም ጊዜ ፍጥረት መሆኑን በግልጽ እንረዳለን፡፡ መፍቀሬ
ጥበብ ሰሎሞንም «ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ ሰባት ምሰሶዎችንም አቆመች» /ምሳ 9፥1/ በማለት በምሳሌው ተጨማሪ
ምስክርነት ሰጥቷል፡፡ሊቃውንት በትርጓሜ እንዳብራሩት «ጥበብ» የተባለ ጌታ «ቤት» የተባለ ዓለምን ፈጥሮአል፡፡
ዓለሙ የጸናባቸው «ሰባት ምሰሶዎች» ደግሞ ዓለምን እስከ ዕለተ ምጽአት የሚያጸኑት አዕዋዳት ሰባቱ ዕለታት
ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር ዓለምን የአጸናው ጊዜ ነው ማለት ነው፡፡ሙሴ «በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን
ፈጠረ» ዘፍ 1፥1 ባለበት የሥነ ፍጥረት መጽሐፍም ጨለማ የነበረ መሆኑን ከተረከልን በኋላ « ብርሃን ይሁን
አለ» ይልና ጠዋትም ሆነ ማታም ሆነ አንድ ቀን በማለት ዓለምና ጊዜ አንድ ላይ መፈጠራቸውን ይነግረናል፡፡
ከዚያም አስከትሎ የቀሪዎቹን የአምስት ቀን ፍጥረታትና የመጨረሻዋን /የሰባተኛውን/ ዕለት ዕረፍትነት ነግሮን
ያጠቃልላል፡፡ ከዚያ በኋላ ዓለም ይቀጥላል፤ የዕለታቱ ዑደትም ይቀጥላል፡፡ በሰባት ዕለት አጸናው ማለት ይህ ነው፡፡
ሁሉንም እርሱ እንደፈጠረ ደግሞ « ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳች እንኳ ያለ እርሱ የሆነ የለም፤» ዮሐ 1፥3
«የሚታዩትና የማይታዩት ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት
ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በእርሱ ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤ እርሱም ከሁሉ
በፊት ነው፤ ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል» /ቆላ.1፥15-17/ ተብሎ ስለተጻፈ አምላክ በቅዱሳት መጻሕፍትም ከቦታ
ጊዜ ውጭ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ፈጣሪ ከቦታ ጊዜ ውጭ ከሆነ ሊያየው የሚቻለው ፍጥረት የለም ማለት ነው፡፡
ወንጌላዊ ዮሐንስ «መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም» /ዮሐ 1፥18/ እንዳለ፡፡ በመቃብያንም
«አንተን ሁሉን ታያለህ እንጂ አንተን ማየት የሚችል የለም» ተብሎ ተጽፎአል፡፡ 3 ኛ መቃ.9፥26 ቅዱስ
ጳውሎስም «ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያየውም
አይቻለውም» /1 ኛ ጢሞ.6፥16/ ሲል እንዳጸናው ለፍጥረት እግዚአብሔርን ማየት አይቻልም፡፡ ይህም ብቻ
አይደለም፤ እርሱን በምርምር ማወቅም አይቻልም፡፡ አካሉ ረቂቅና ምሉዕ፣ በቦታ ጊዜ የማይወሰን ከሆነ ማን በምን
ሊመረምረው ይችላል፡፡ በግብሩ በባሕርዩ እንመርምረው እንዳንል በእኛ ኅሊናችን ኅሊናን የፈጠረውን መመርመር
ሸክላ ሠሪውን ለማወቅ ከመጣር የበለጠ የማይቻል ነው፡፡ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት «ወረሰየ ጽልመተ
ምስዋሮ፤ ጨለማን መሰወሪያው አደረገ» እንዳለው ሊመረመር አይችልም፡፡ በጨለማ ማየት እንደማይቻል ሁሉ
የእግዚአብሔር ባሕርይ ሊመረመር የማይቻል ነውና፡፡ ታዲያ ፈጣሪን እንዴት ማወቅ ይቻላል? የሚለው ጥያቄ በዚህ
ጊዜ ሊነሳ የሚገባ ነው፡፡ መልሱም ቀላል ነው፡፡ የምናውቀው እርሱ ራሱ ሲገለጥልንና ሲገልጥልን ብቻ ነው፡፡
ከተገለጠበትና ከገለጠውም መጠን በላይ ማወቅ አይቻልም፡፡ ስለዚህ የእውነተኛ ሃይማኖትነት መሠረታዊ
ማረጋገጫዎች መካከል አንዱና ዋናው መገለጥ ነው ያልነው ለዚህ ነው፡፡ እርሱ ራሱን ባይገልጥ ማን በምን መንገድ
ሊያውቀው ይችላል፡፡ አምልኮተ እግዚአብሔርን በሦስቱም ሕግጋት /በሕገ ልቡና፣ በሕገ ኦሪት፣ በሕገ ወንጌል/
ብንመረምረው መንገዱ ሁሉ መገለጥ ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እግዚአብሔር ራሱን ለመላእክት በመፍጠር
ገለጠላቸው፡፡ ለአዳም ተገለጠለት፣ አነጋገረው፣ ትእዛዝም ሰጠው፡፡ ከበደለውም በኋላ ፈለገው፤ አነጋገረው፤...
የሚሉት በሙሉ መገለጥን የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እግዚአብሔር አዳምን «አዳም
አዳም ወዴት ነህ?» አለው የሚለው ያለበትን ያለማወቅ ሳይሆን አዳም ከበደለም በኋላ ለኃጢአተኛ ባሕርዩ
በሚስማማ ሁኔታ መገለጡን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ከዚህም በኋላ በሕገ ልቡና ለአባቶች ሁሉ በየዘመናቸው እንደ
ሃይማኖታቸው ጽናት እንደ አእምሮአቸው ስፋት ሲገለጥላቸው ኖርአል፡፡ «በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ
ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት» ተብሎ ስለ አብርሃም የተጻፈው ነው፤ /ዘፍ. 18፥1/
የሚለው የዚህ ማረጋገጫ ነው፡፡ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በየዘመኑ ለነበሩ ሰዎች የተገለጠበት መንገድ የተለያየ
ከጥንት ወደ አሁን ጊዜ ስንመለከተውም የበለጠ እየተገለጠ እንደመጣ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ ለምሳሌ የሕገ
ኦሪት መሥራች ለምንለው ለሙሴ ሲገለጥለት ለአብርሃም ከገለጠለት በላይ ለእርሱ እንደገለጸለት ነግሮታል፡፡
«እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፣ አለውም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአብርሃምም፣ ለይስሐቅም፣ ለያዕቆብም ሁሉን
እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፣ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር» /ዘጸ. 6፥2-3/ ተብሎ
የተጻፈው ሌላው ቀርቶ « እግዚአብሔር» የሚለው ስም እንኳ ከዚያ በፊት ላሉት እንዳልታወቀ ያረጋግጥልናል፡፡
ስለዚህ «እግዚአብሔር» የሚለውና ሌሎች ብዙ ነገሮች ከሕገ ኦሪት በኋላ እንደተገለጡ መጽሐፍ ቅዱስ ሰፊ
ምስክርነት ይሰጠናል፡፡ ይልቁንም ደግሞ ምሳሌያዊ /Allegorical/ በሆነ መንገድ የተገለጡትን ስንመለከት እጅግ
እንደነቃለን፡፡እግዚአብሔር ለነቢያቱም በተለያየ መንገድ ተገልጦላቸዋል፡፡ ለሙሴ በሐመልማል ወነበልባል
/ዘጸ.3፥1/ ለኢሳይያስ በአምሳለ አረጋዊ ነዋሕ፤ /ኢሳ. 6፥1/ ለዳንኤል በአምሳለ ዕብን ቅውም ከረጂም ተራራ ላይ
በተፈነቀለ ትልቅ ድንጋይ / ዳን 9፥ /... ለሌሎቹም በብዙ ኅብርና አምሳል ተገልጦላቸዋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ «
በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና» ያለው ይህንኑ ነው፡፡ /ዕብ.1፥1/ በብሉይ ኪዳን የተጻፉ መጻሕፍትን በሙሉ
ስንመለከታቸው «እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤...» በሚል መግቢያ የሚጀምሩ
ናቸው፡፡ ይህም ቃልና ትምህርቱ በሙሉ ከእግዚአብሔር የተሰጠ እንጂ የእነርሱ ላለመሆኑ በሌላ አነጋገር የመገለጥ
ሃይማኖት፤ ትምህርት መሆኑን እየደጋገመ ያረጋግጥልናል፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ፤ በብሉይ ኪዳን ብዙ ነቢያት ተነሥተው
ቢያስተምሩም ብዙ መጻሕፍት ቢጽፉም የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ግን እጅግ ምስጢራዊና ምሳሌያዊ በሆነ
መንገድ እንጂ በግልጽ አልታወቀም ነበር፡፡ ምክንያቱም በሚገባው መንገድ ራሱን ገና አልገለጠም ነበርና፡፡ ለአብርሃም
የተገለጡት ሦስት ሰዎች፤ «ኑ እንውረድ፣» የሚሉት ዓይነት ቃላትና ይህንኑ ከሚመስሉት ጥቅሶች በቀር በጊዜው
/ብሉይ ዘመን/ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ስለ እግዚአብሔር የአንድነትና የሦስት ምስጢር በበቂው አልተገለጠላቸውም፡፡
በመጽሐፈ ኢያሱ የተጻፈውንና ስለ እሥራኤል የዮርዳኖስ ወንዝ ተሻግሮ ከምድረ ርስትን መርገጥን በተመለከተ
«ሙሴም እንዳዘዛቸው የሮቤል ልጆች፣ የጋድም ልጆች፣ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ተሰልፈው በእሥራኤል ልጆች ፊት
ተሻገሩ፡፡» የሚል ተጽፎአል /ኢያ.4፥17/፡፡ አንድ የጥንት የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ይህን ሲተረጉመው እነዚህ
ቀድመው የተሻገሩት ከአሥራ ሁለቱ ነገድ ሁለቱ ነገድ በሙሉና ሦስተኛው ከፊሉ መሆኑ በብሉይ ኪዳን ዘመን
ስለነበረው የሥላሴ ዕውቀት ምሳሌ ነው፡፡ በዚያ ዘመን ስለ አብና ስለወልድ በመጠኑ ስለመንፈስ ቅዱስ ደግሞ እጅግ
በብዥታ ያውቁ ነበር፡፡ ሦስተኛው ነገድ በከፊል የተሻገረው ለዚህ ነው፡፡ ሦስቱ ነገድ እንኳን አለመሟላቱም በዘመኑ
ምስጢረ ሥላሴ በከፊል በምሳሌና በጥላ ብቻ ይታወቅ የነበረ ስለመሆኑ አሰረጂ ነው በማለት ይተረጉማል፡፡በርግጥም
ቀደም ብለን እንዳየነውም የእግዚአብሔር መገለጥ እየጨመረ እየጨመረ እንደመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ምስክር ነው፡፡
የብሉይ ኪዳን ዘመን መገለጥ እየጨመረ እየጨመረ ከመጣ በኋላ ፍጹም መገለጥ ሲመጣ ያኛው የጥላውና የምሳሌው
መገለጥ ይደመደማል፡፡ ፍጹሙ መገለጥም የአምላክ ሰው ሆኖ መገለጥ ነው፡፡ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ «መጀመሪያ
ቃል ነበረ፣...» ካለ በኋላ «ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር፡፡ በዓለም ነበረ
ዓለሙም በእርሱ ሆነ ዓለሙም አላወቀውም» ዳግመኛም ከዚያው አስከትሎ «ቃልም ሥጋ ሆነ፣ ጸጋንና እውነትንም
ተመልቶ በእኛ አደረ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነውን ክብሩን አየን» ሲል መገለጡን አበሠረ፤
/ዮሐ 1፥1-18/፡፡ይህን መገለጥ ደግሞ እንኳን ሰዎች መላእክትም ተግተው ይሹት ነበረ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ፤
«ለእናንተ ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤ ለእነርሱም
ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን
እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ» /1 ኛ ጴጥ. 1፥1-12/ ሲል
እንደገለጸው፤ መላእክቱ የአምላክን መገለጥ ለማየት እጅግ ጓጉተው ነበር፡፡ ምክንያቱም እነርሱም ቢሆኑ አምላክን
ለማየት ዕድል የሚያገኙት ሰው ሆኖ ሲገለጥ ብቻ ነውና፡፡ቅዱስ ጳውሎስ፤ «እግዚአብሔርንም የመምስል ምስጢር
ያለጥርጥር ታላቅ ነው፡፡ በሥጋ የተገለጠ፣ በመንፈስ የጸደቀ፣ ለመላእክት የታየ፣ በአሕዛብ የተሰበከ፣ በዓለም የታመነ፣
በክብር ያረገ» /1 ኛጢሞ.3፥16/ በማለት ለመላእክት የታየው በሥጋ በመገለጡ እንደሆነ አረጋግጦልናል፡፡
እነርሱም ምስጢረ ሥጋዌን ከሰው በላይ አጣጥመው ተጠቅመውበታል፡፡ በብሥራቱ ቅዱስ ገብርኤል ብቻ ቢሣተፍም
በልደቱ ጊዜ ግን ብዙዎች መላአክት በአንድነት ለእረኞች ለማብሠር ታድለዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በመዋዕለ ሥጋዌው ሁሉ
እየተላላኩ አምላክን ማየት ጠገቡ፡፡ ሲሰቀልና ሲሞትም በአርምሞ በመደነቅ ተመለከቱ፡፡ ትንሣኤውን አበሠሩ፡፡
የቀሩትም በዕርገቱ ዕለት ሐዋርያትን አረጋግተው ዳግም ምጽአቱን አውጀው ተሰወሩ፡፡ ዳግመኛ ሲመጣ መለከት
እየነፉ ከፊት ከፊት እየቀደሙ ከኋላም እየተከተሉ እንደሚመጡም ተጽፎላቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የአምላክ
መገለጥ የመላእክት ደስታ ሆነ፡፡ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ፤ እያሉ
የዘመሩት ወድደው አይደለም፡፡ ተገልጦ ባዩት ጊዜ ለመደመማቸው ወሰን ቢያጡ ለሰው ያለውንም ፍቅር ይገልጡት
ዘንድ ቢሳናቸው፤ ይህን ምስጋና እያጣጣሙ ክብርና ቅድስናቸውን ለራሳቸው አስጨመሩ፡፡ ይሁን እንጂ አምላክ ሰው
በመሆኑ ከረቂቃኑ መላእክት ይልቅ የበለጠ የቀረቡት ሰዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ በዘመነ ብሉይ እንደ ነበረው እንደ
ሄኖክ፣ እንደ መልከጼዴቅ፣ አብርሃም፣ ይስሐቅና ያዕቆብ፣ ዳዊትና ሰሎሞን፣ ሙሴና ነቢያት ራሳቸውን የቀደሱና ያነጹ
ብቻ ሳይሆኑ በኃጢአት የረከሱት እነ ዘኬዎስ፣ ማርያም እንተ ዕፍረት፣ መጻጉዕ፣ በዝሙት የተያዘችው ሴትና ሌሎቹም
ሰውነቱን ዳሰሱት፤ አብረውት በሉ ጠጡ፤ . . .፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን መገለጡን በሰፊው አሰበችው፤ በተድላ
በደስታ፤ በመብልና በመጠጥም ጭምር የምታከብረውም ለዚህ ነው፡፡ ከዚህ መገለጥ በኋላ የተላኩ ሐዋርያትም
የትምህርታቸው አቀራረብ ተለወጠ፡፡ እንደ ነቢያት በዚህ መንገድ አየነው፣ እንዲህ ሆኖ ተገለጠልን የሚለው ቀረና
ቅዱስ ዮሐንስ እንዳለው፤ «ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን
የተመለከትነውንም፣ እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ፤ አይተንማል እንመሰክርማለን፤ ከአብ
ዘንድ የነበረንም ለእኛም የተገለጠውን፤ የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን» /1 ኛዮሐ. 1፥1-3/ እያሉ
ለማስተማር ቻሉ፡፡ ከዕርገቱም በኋላ ቢሆን እርሱ ከቅዱሳኑ ተሰውሮ አያውቅም፡፡ ይልቁንም ከተዋሕዶ በኋላ ምንታዌ
የለምና /ሰው ከሆነ በኋላ መታየቱ፣ መወሰኑ፣ መጨበጡ፣ መዳሰሱ አልቀረምና/ በየዘመኑ ይገለጣል፡፡ በየቅዱሳኑ
ሕይወት እንደተጻፈው እነ አባ ብሾ/ሶ/ይ እግሩን አጠቡት፣ አዘሉት፡፡ በየዕለቱ ለሰማዕታቱ እየተገለጠ አጸናቸው፤
ጻድቃኑንም ምስጢሩን አብዝቶ ገለጠላቸው፡፡ በየገድላቱም ላይ ቅዱሳኑ ሲያርፉ «ይህን ያህል ቅዱሳኑን አስከትሎ
መጣ፤ ነፍሱንም ተቀበለ፣. . .» የመሳሰሉት አገላለጾች ምንኛ ግሩም ናቸው፡፡አንድ ጊዜ ሰው ሆኖአልና እንደቀድሞው
ለነቢያቱ እንዳደረገው ሳይሆን አሁን በሥጋ ተገልጦአልና በየጊዜው ይመጣል፣ ይታያል፣ ይጨበጣል፤ ይዳስሳቸዋል፤
ይስማቸዋል፤ ያወጋቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስን በሮማ አደባባይ «ወዴት ትሔዳለህ?» ብሎ እንደመለሰው፤ በየዘመኑ
እየተገለጸ ይመራቸዋል፤ ያነጋግራቸዋልም፡፡ መገለጥ፤ ግሩምና ድንቅ መገለጥ፤ ሃይማኖቱም የመገለጥ፡፡ እርሱ ራሱ
«ይህ ዛሬ እናንተ የምታዩትን ብዙ ነቢያት ሊያዩ ወደው አላዩም፤ እናንተ የምትሰሙትን ሊሰሙ ወድደው
አልሰሙም፤ የእናንተ ግን ያዩ ዓይኖቻችሁ፤ የሰሙ ጆሮቻችሁ የተመሰገኑ ናቸው» እንዳለ ፤ የሐዲስ ኪዳን፣ ጻድቃን፣
ሰማዕታት፣ ባሕታውያን ስውራን ሁሉ ምን ያህል የተመሰገኑ ናቸው፡፡ በየዕለቱ ጌታቸውን ያዩታልና፤ ለዚህም
ተጠርተዋልና፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ልዩ የሚያደርጋት ብቻ ሳይሆን ከትክክለኛነቷ ማረጋገጫዎች
አሁንም ዋነኛዋ መገለጡ ነው፡፡ የሌሎቹ በተለይም ከኢንዱስትሪው አብዮት በኋላ የተነሡ የክርስትና ክፍልፋዮች
/Denominations/ ሁሉ መሠረተ እምነታቸው የሚዋቀረው በዩኒቨርስቲዎችና በየተቋማቱ ባሉ
ምሁራኖቻቸው አስተምህሮ በጠረጴዛ ዙሪያ ነው፡፡ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ
የሚመሠረተው ግን በገዳማውያን ቅዱሳን መገለጥ ላይ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ሊቃውንቱ ሁሉ በመማር ብቻ
ሳይሆን በገዳም ተወስነው፣ ሱባኤ ገብተው፣ በእርሱ መገለጥ የተሰወረ ምስጢር ይገለጥላቸዋል፤ የረቀቀው
ይጎላላቸዋል፡፡ ያንን ብቻ ያስተምራሉ፤ እርሱንም ብቻ ይዘን እናስተምራለን፤ በተገለጠውም መሠረት እንኖራለን፡፡
በእኛ ሀገር እንኳን እነ ቅዱስ ያሬድ፤ አባ ጊዮርጊስ፣ አባ ዜና ማርቆስ፤ አባ ተክለሃይማኖት፣. . . ሁሉም በሱባኤ፣
በገዳም፣ በምናኔ፣ በተጋድሎ ተወስነው፤ በተገለጠውና በሚገልጥላቸው መንገድ ብቻ ተጓዙ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትም
የሚያረጋግጡልን ይህንኑ ብቻ ነው፡፡ ሃይማኖትን እንቀበለዋለን ከዚያም እንጠብቀዋለን እንጂ ልንሠራው አንችልም፡፡
የያዕቆብ ወንድም ቅዱስ ይሁዳ «ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ
እጽፍላችኋለሁ» /ይሁ.1፥3/ ሲል እንደገለጸልን፤ ሃይማኖት ለቅዱሳን በመገለጥ የተሰጠች እንጂ የተሠራች
አይደለችም፡፡ ጌታችንም በወንጌል «ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው፡፡ የአንተ ነበሩ ለእኔም
ሰጠሃቸው፤ ቃልህንም ጠብቀዋል፡፡ የሰጠኸኝን ሁሉ ከአንተ እንደሆነ ያውቃሉ፤ የሰጠኸኝ ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤
እነርሱም ተቀበሉት. . .» /ዮሐ.17፥22/ ሲል እንዳስተማረው፤ ክርስትና የተቀበልነውና የምንጠብቀው እንጂ
የሠራነውና የምናሻሽለው አይደለም፡፡ በዚያ ጊዜ ያልገለጸልንንም «የምነግራችሁ ብዙ ነገር አለ፤ አሁን ግን
ልትሸከሙት አትችሉም፤ መንፈስ ቅዱስ በመጣ ጊዜ ግን እርሱ ሁሉንም ያሳውቃችኋል» የሚል ተስፋን ሰጠን፡፡
መንፈስ ቅዱስም ከእኛ ጋር የሚኖረውም እስከ ዕለተ ምጽአት መሆኑን አረጋገጠልን፡፡ ስለዚህም እስከ ዛሬ ድረስ
መንፈሳቸውን ላላረከሱት በየጊዜው ይገለጣል፡፡ ለሐዋርያት ገለጠላቸው፤ ለሊቃውንት ገለጠላቸው፤ ለጻድቃን
በየገዳሙ ገለጠላቸው፤ ለየመምህራኑም በየሱባኤያቸው በተቀደሱ ጉባኤዎቻቸው ገለጠላቸው፤ እኛም የተገለጠውን
ይዘን እርሱንም እየጠበቅን እንጓዛለን፡፡ ከተገለጠው ውጭ መጓዝም የተወገዘ መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ፤ «ነገር ግን እኛ
ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን» /ገላ.1፥8/
በማለት አረጋገጡልን፡፡ ስለዚህም በዘመነ አስተርእዮ ይህን የአምላክን መገለጥ እና የመገለጥን ሃይማኖት
የምንዘክርበት ምክንያት፤ ሃይማኖት ሰዎች ያልፈጠሩት ነገር ግን በአምላክ መገለጥና እርሱ በገለጠው ሃይማኖታዊ
ዕውቀት ብቻ መጓዝን ማዘከር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በተገለጠልን ጸንተን ለቅዱሳን የተሰጠችውን ሃይማኖት
ተጉዘንባት ለልጆቻችንም አውርሰናትና ጠብቀናት እንድናልፍ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት
አይለየን፤ አሜን፡፡
LikeShow more reactions

Comment

You might also like