You are on page 1of 15

2ኛ ትምህርት

የሚመጡ ፈተናዎች

ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ 1
ጴጥ 4:12-19, 1 ጴጥ 5:8-11, ሮሜ 1:21-32, ኤር 9:7-16, 2 ቆሮ
12:7-10.

የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ወዳጆች ሆይ በእናንተ መካከል እንደ እሳት


ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደመጣባችሁ አትደነቁ ነገር
ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሀሴት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ በክርስቶስ
መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።( 1ኛ ጴጥ 4፡ 12-13)

በኬሚስትሪ ላብራቶሪ ውስጥ አንድ ሰው ብዙውን ጊዜ የተለያዩ ነገሮችን


በትንሽ ዕቃ ውስጥ በማድረግ በከፍተኛ ሙቀት እንዲግሉ ያደርጋቸዋል።
የዕቃው መያዣ ሲግል በውስጡም ያሉ ነገሮች ይግላሉ፣ ከዚያም
እንደተሰሩበት ዕቃ አይነት ተቃጥለው ከጥቅም ውጪ ይሆናሉ፣
ይቀልጣሉ፣ወይም ተቃጥለው ነጣ ወዳለ ቀለም ይለወጣሉ። ይህ የተለያዩ
ነገሮች በአንድነት ገብተው በእሳት የሚፈተኑበት ድስት ወይም መያዣ ዕቃ
መፈተኛ ድስት ይባላል። ክሩስብል የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የመዝገበ
ቃላት ትርጉሙ( 1). ለመቅለጥ በጣም ከፍተኛ ሙቀት የሚፈልጉ ነገሮችን
ማቅለጫ ድስት (ዕቃ) ( 2). በጣም የከፋ ፈተና (3). ሁለት ኃይሎች ለውጥ
ለማምጣት የሚነጋገሩበት ቦታ ወይም ሁኔታ ተብሎ ይገለጻል።
እነዚህ ትርጓሜዎች በመንፈሳዊ ህይወታችን ምን እንደሚከሰት ጠቃሚ
ሐሳቦችን ይሰጡናል ። የዚህ ሳምንት ትምህርት አንዳንዴ ሳናስበው በከፍተኛ
ተጽዕኖ እና ፈተናን የምንለማመድባቸው ሁኔታዎች የእኛን ባህሪይ ሊለውጡ፣
ሊያሳድጉ እና ሊያበለጽጉ በሚችሉበት ቦታ ራሳችንን የምናገኝበትን ምክንያት
እንማራለን። ይህ ፈተና ውስጥ በምንገባበት ጊዜ፣ በህይወታችን
እግዚአብሔር ምን እየሰራ እንደሆነ መልስ መስጠት እንድንችል ይረዳናል።
ሳምንቱን በአጭር እይታ፡ በህይወታችን የሚያጋጥሙን ከባድ ጊዜያት
ምክንያቶች ምንድናቸው?

የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሐምሌ 2 አጥንተው ይዘጋጁ

እሁድ:- ሰኔ 26

አስደናቂዎቹ ነገሮች

“ወዳጆች ሆይ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው


መከራ ድንቅ ነገር እንደመጠባችሁ አትደነቁ” (1ጴጥ 4:12)። አስደናቂ
ነገሮች፣ የሚያሳምሙ አስደናቂዎች፣ በብዙ መንገዶች ወደ ህይዎታችን
ይመጣሉ። ልክ መስመሩን ስቶ ወደ አንተ አቅጣጫ እንደሚበር ፈጣን
መኪና፣ በድንገት ስራዎትን እንዲለቁ የተነገረ ዜና፣ ያልተጠበቀ ክፉ የጤና
ምርመራ ውጤት፣ እርሶ የሚወዱት እና ይወደኛል ብለው ከሚያምኑት ሰው
የሚደርስ ክህደት። ድንቅ( አስደናቂ) ነገሩ በሚያመጣው ህመም ልክ ነገሩ
እየከፋ ሄዳል።

በዚህ ሳምንት ጥቂት ዘርዘር ያሉ የሚያሳምሙ ሁኔታዎችን ወይም ፈተናዎች


ሆነው የማያስደንቁንን እንመለከታቸዋለን። ለመጀመር ያህል ወደ 1ጴጥ
4:12 እንሒድ። በጴጥ 4 ፡ 12 ላይ መደነቅ ለሚለው ጥቅም ላይ የዋለው
የግሪኩ ቃል ማለት ከሌላ አገር የመጣ የሚል ትርጉም የሚሰጥ ነው።
ጴጥሮስ አንባቢዎቹን በክርስቲያኖች ልምምድ መከራ እና አስቸጋሪ ነገሮች
የማይታወቁ ከውጪ የሆኑ እንግዳ ነገሮች ናቸው ብለው በማመን ወጥመድ
ውስጥ እንዳይገቡ ደጋግሞ እያሳሰባቸው ነው። ይልቁንም ፣ እነርሱ
የተለመዱ እና የሚጠበቁ ናቸው።

እንደ እሳት የሚያቃጥል ፈተና ለሚለው ሌላ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹


መንደድ›› ማለት ነው። በሌላ ቦታ ከፍተኛ የሚያቀልጥ ሙቀት ተብሎ
ተተርጉሟል። ስለዚህ የዚህ ዓይነቱ ለእምነታችን ስንል የሚደርስብን ስቃይ
የሚፈለገው ማንነት ከውስጥ ወጥቶ እንዲታይ የሚደረግበት የፈተና ሂደት
ነው።

1 ጴጥ 4:12-19ን ያንብቡ እዚህ ቦታ የጴጥሮስ መልዕክት ምንድነው?

ከእኛ ብዙዎቻችን ስለ መከራ እንደነቃለን ምክንያቱም ስለ ክርስትና ህይወት


ያለን አመለካከት በጣም ቀላል በመሆኑ ነው። ሁለት ጎራዎች እንዳሉ
እናውቃለን፣ እግዚአብሄር መልካሙ እና ሰይጣን የክፉው ምንጭ ናቸው።
ከዚያም ብዙውን ጊዜ መልካም የሆኑትን ነገሮች በእግዚአብሔር ጎን
ስናስቀምጥ ክፉ የመሰሉንን ነገሮች ሁሉ በሳይጣን ጎን እናስቀምጣለን።
ነገር ግን ህይወት እንደዚህ ቀላል አይደለችም። ነገሮችን ይህ ከእግዚአብሔር
ነው ወይንም ይህ ከሰይጣን ነው ብለን ለመለየት የራሳችንን ስሜት መጠቀም
የለብንም። አንዳንድ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር መራመድ ከባድና ግድድሮሽ
ያለበት ሊሆን ይችላል። እናም ሰይጣንን በመከተላችን ትልቅ ሽልማት
የሚያስገኝ ሊመስል ይችላል። እዮብ ጻድቅ ሆኖ ሳለ በመከራ ውስጥ
በመሆን እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ የጠየቀው ለዚህ ነው(ኢዮ 21:7)
ጴጥሮስ እያመለከታቸው ያሉ መከራዎች ለክርስቶስ በመቆማችን ምክንያት
ስለሚደርሱብን መከራዎች ነው። ነገር ግን ሌሎችም መከራ ሊመጣባቸው
የሚችልባቸው ምክንያቶች አሉ። 1ጴጥ 4:12-19 በመከራ ውስጥ ያለ
ወዳጅህ በመከራው መደነቅ እንደሌለበት ብልሃት በሞላበት ሁኔታ
ልታስረዳው የምትችለው እንዴት ነው?

ሰኞ:- ሰኔ 27

የሰይጣን ፈተናዎች

“ በመጠን ኑሩ ንቁም ፣ ባለጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ


እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና” (1 ጴጥ 5:8) ከላይ ያለውን ጥቅስ ስታስቡ
ለእኛ ያለው መልዕክት ምንድነው? እነዚህን ቃላት እንዴት ባለ ጥንቃቄ
እንደሚወስዱ ራስዎን ይጠይቁ። እነዚህን ቃላት በጥንቃቄ መውሰድዎን
የሚያሳይ ምን ማድረግ ይችላሉ?

የተራበ አንበሳ አይተው ያውቃሉ? በጣም አስፈሪ ነው ምክንያቱም ያገኘውን


ነገር ሁሉ ይዞ ይበላል። ጴጥሮስ እያለ ያለው በተመሳሳይ ሁኔታ ሳይጣን
እያደባ እንደሆነ ነው። ዙሪያችንን በምናይበት ጊዜ፣ እርሱ ለማጥፋትና
ለመግደል ባለው ምኞት የሚያደርጋቸው ነገሮች ውጤታቸውን እናያለን። ሞት
መከራና የግብረገብ መዛባት በሁሉም ሥፍራ ይታያል። የሰይጣንን ሥራ
ላለማየት አንችልም።

1 ጴጥ 5:8-11ን ያንብቡ። ክርስቲያን ለሰይጣን ፈተና ምን ዓይነት ምላሽ


መስጠት አለበት?

በስቃይ ውስጥ ላሉት የእግዚአብሔር ተስፋ ምንድነው? 1 ጴጥ 5:10::

ጴጥሮስ እነዚህን ቃላት የጻፈው ሰይጣን በክርስቲያን እምነት ላይ ጥቃት


በሚያደርስበት አውድ ውስጥ ሆኖ ነው። ነገር ግን ሰይጣን በብዙ መንገዶች
ሥራ ላይ ነው። እናም እኛ ደግሞ የጠላታችንን ኃያልነት እውነታ መረዳት
አለብን፣ በፍጹም ተስፋ ልንቆርጥ አይገባንም፣ምክንያቱም ሁልጊዜ ማወቅና
ማስታወስ ያለብን ክርስቶስ ሰይጣንን አሸንፎታል ፣ሰይጣን የተሸነፈ ጠላት
ነው፣ ከክርስቶስ ጋር ያለንን ግንኙነት ጠብቀን ካቆየን ፣ በእምነት ከእርሱ ጋር
ከተጣበቅን ፣እኛም በፍጹም አንሸነፍም። በመስቀሉ ምክንያት የክርስቶስ
ድል የእኛም ድል ነው።

ሰይጣን ፈታኝ የሆኑ ችግሮችን ሊያስከትል የሚችልበትን ሌሎች መንገዶች


አስቡ። 1ጴጥ 5፡8-11 ማንበብ በዚህ ሐጢአተኛ ዓለም ውስጥ ስንኖር
በምናሳልፍበትና ሰይጣን ከባባድ አጥፊ ነገሮችን በሚፈጽምበት ሁኔታዎች
ውስጥ ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው?
ማክሰኞ:- ሰኔ 28

የኃጢአት ፈተናዎች

“እውነትን በአመጻ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢዓተኝነታቸውና በአመጻቸው ሁሉ


ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ከሰማይ ይገለጣል።” (ሮሜ 1:18::)

የምናደርጋቸው እያንዳንዱ ነገሮች ውጤት አላቸው። እጅግ በሚያቃጥል


የጸሐይ ሙቀት ላይ አይስክሬም ይዘህ ብትቆም በእርግጠኝነት ይቀልጣል።
መንስኤና ውጤት ሁልጊዜ አብረው የሚሄዱ ነገሮች ናቸው ። ነገሮች
በምንም ያህል ልዩ እንዲሆኑ በጣም ፍላጎት ያለን ብንሆንም፣ የሐጢአት
ጉዳይ ተመሳሳይ ነው። ሁልጊዜ ውጤቱን ያጭዳል። ምክንያቱም
እግዚአብሄር በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ኃጢአትን በሚያደርጉ ሰዎች ምን ዓይነት
መአት እንደሚያመጣ ስለሚያስብ ሳይሆን ኃጢአት ራሱ በውስጡ አብሮት
ያለ ውጤት ያለው በመሆኑ ነው።

ችግሩ ግን እኛ ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔርን የበለጠ አዋቂዎች የሆንን


ይመስለንና፣ ውጤቱን ሳናውቅ ኃጢአትን እንለማመዳለን። ይህ ሊሆን
አይችልም ። ጳውሎስ ይህንን ሲገልጸው ኃጢአትን ማድረግ ውጤት
የሚኖረው በዘላለም ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በምድርም የሚያሳዝንና ህመምን
የሚያስከትል ውጤት አለው።
በሮሜ 1:21-32 ጰውሎስ ሰዎች በኃጢአት የሚወድቁበትን ሁኔታ እና
ውጤቱን ይናገራል። በጸሎትና በጥንቃቄ ይህንን ጥቅስ ያንብቡትና ጳውሎስ
ስለ ኃጢአት ደረጃዎችና ውጤታቸው ማለት የፈለገውን በማጤን በአጭር
አጠቃለው ይጻፉ።

ከዚህ ቀደም ባሉ ጥቅሶች ላይ ጳውሎስ እነዚህን የኃጢአት ውጤቶች


የእግዚአብሔር ቁጣ እንደሆኑ ያሰቀምጣቸዋል። (ሮሜ1:18):: በዚህ ሥፈራ
የእግዚአብሔር ቁጣ ማለት እግዚአብሔር ሰዎች ለሰሩት ሥራ ውጤታቸውን
እንዲያገኙ (የዘሩትን እንዲያጭዱ) ዝም አለ ማለት ነው። ለክርስቲያኖችም
እንኳ ቢሆን፣ በራሳችን ድርጊት ምክንያት ለሚመጡ ችግሮች በፍጥነት(
በቶሎ )ለማስወገድ ጣልቃ አይገባም። ብዙውን ጊዜ የስራችን ውጤት
የሆነውን ነገር ምን እንደሚመስል እንድናየውና በምን ያህል ጥልቀት ጎጂና
አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር መሆኑን እንድናውቅ ዝም ይላል።

በዚህ እየተመለከትን ያለው የእግዚአብሔርን የግብረ-ገብ ህጎችን ስለማፈረስ


ነው። ነገር ግን የጤና ህጎችን አለማክበርስ ? ሰውነቶቻችን የእግዚአብሔር
ቤቶች ናቸው። ሰውነታችንን ጤናማ ምግብ ባለመመገባችን፣ ወይንም
የሰውነት እንቅስቃሴ ባለማድረጋችን፣ ወይም ከአቅም በላይ በመስራታችን፣
ይህም በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ የፈተና
እሳት ውስጥ የሚያስገባንና ውጤቱም በጣም አደገኛ ነው።

በራስዎ ሕይወት፣ የኃጢአትዎን ውጤት በቶሎ አጭደው ያውቃሉ? ከዚያ


ምን ትምህርት ተማሩ? በዚያ ዓይነት ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ
ላለመውደቅ ምን ዓይነት ለውጥ አደረጉ ?
ረቡዕ:- ሰኔ 29

የማጽዳት ፈተና

“ስለዚህ እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፡- እነሆ አቀልጣቸዋለሁ


እፈትናቸውማለሁ፤ ስለ ህዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው
ምንድነው?’” (ኤር 9:7) “የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ልብህ አንድ አንተን
የሚጎዳ ነገር በመንፈስህ ካመጣ፣ በአንተ ውስጥ እግዚአብሔር ሊያጠፋ
የሚፈልገው አንድ ነገር መኖሩን ታረጋግጣለህ።›› (ሁሉን ነገር ለእርሱ ክብር)
”ገጽ. 271. ከላይ ያለውን የመጸሐፍ ቅዱስ ጥቅስና አባበል እንዴት አዩት?
በማጥራት ሂደት ውስጥ ባለው ህመም የእርስዎ የግል ተሞክሮ ምንድነው?

ኤር 9:7-16ን ያንብቡ:: እግዚአብሔር ‹‹አቀልጣቸዋለሁ፣ እፈትናቸዋለሁ››


ይላል። ይሁዳንና የሩሳሌምን ‹‹አቀልጣታለሁ›› እግዚአብሔር ለዚህ
የሚሰጣቸው ሁለት ምክንያቶች ምንድናቸው? (ኤር 9:13 14)። የማጥራት
ስራው የሚከናወነው እንዴት ነው (ኤር 9:15 16).

የእግዚአብሔር የማጥራት ፈተና ሂደት በከባድና በጠለቀ ሁኔታ የሚከናወን


ነው። ይህ የማጥራት ሂደት ትልቅ ፈተና የሚሆንበት ሶስት ምክንያቶች አሉ።
የመጀመሪያው፣ እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ወደ ግንዛቤአችን ሊያመጣው
ሲፈልግ ሁኔታዎች እንዲከሰቱ ይፈቅዳል። “ ‘ወናፍ አናፋ እርሳሱም በእሳት
ቀለጠ፤ አንጥረኛው መልሶ በከንቱ ያቀልጠዋል፤ ኃጢአተኞች አልተወገዱም’
” (ኤር 6:29):፡ ስለዚህ የእኛን ትኩረት ለመሳብ ከባድ ነገሮች መደረግ
አለባቸው። ሁለተኛ፣ ስለ ኃጢአታችን በተጨነቅን ጊዜ ስናዝን ያን ጊዜ
በግልጽ ማየት እንችላለን። ሶስተኛ፣ በተለየያ ሁኔታ ለመኖር በምናደርገው
ሙከራ እንጨነቃለን። በልምምዳችን ምክንያት ከእኛ ጋር የተዋሀዱንን
ባህሪያት ለማቋረጥ የምናደርገው ጥረት ከባድና የማይመች ሊሆንብን
ይችላል።

እርስዎ እየታገሉበት ስላሉት ፈተናዎች ያስቡ። ዛሬ እግዚአብሄር ሊያጠራና


ሊፈትን ቢፈልግ፣ እንዴት ነው የሚያደርገው? እግዚአብሔር በእስራኤል
እንዳደረገው ይህንን ከባድ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ምን ሊያደርጉ
ይችላሉ?

ሐሙስ:- ሰኔ 30

የወጣትነት ፈተና

“ስለዚህ በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፣ እርሱም


የሚጎስመኝ የሰይጣን መልዕክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።
(2ቆሮ 12፡ 7) በመቁረጥና በመገረዝ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። ከዚያ
ጊዜ በኋላ የማንፈልጋቸውን ተክሎች እንቆርጣቸዋለን። የበለጠ ፍሬያማ
እንዲሆኑ የምንፈልጋቸውን ተክሎች ደግሞ እንገርዛቸዋለን። ሁለቱም
ድርጊቶች ግን የሚከናወኑት በስለታም ቢለዋ ነው። በእርግጥ መገረዝ
የተወሰነውን የተክሉን አካል መቁረጥ ለጀማሪ አትክልተኛ አትክልቱን
ማጥፋት ሊመስለው ይችል ይሆናል። በመንፈሳዊ አውድ፣ በሩስ ዊልክንሰን
እንደ ጻፈው፣ ‹‹እጅግ ታላቅ ለሆነው የእግዚአብሔር በረከት እና የእርሱን ልጅ
እንድትመስሉ ትጸልያላችሁ? “መልስዎ አዎ ከሆነ እየጠየቁ ያሉት ከላይ
ያለውን ለማንሳት ለመሸለት ነው። ›› የወይኑ ሚስጥር፣ (በብሩስሊ
ዊለኪነሰን። p. 60.) ጳውሎስ ‹‹የሥጋዬ መውጊያ›› ሲል ብዙ ሰዎች
ተገርመዋል(2ቆሮ 12:7):: የነገሮች ደረጃ ጳውሎስ በተከታታይ ጠላቶች
ከሚያደርሱበት ጥቃት እስከ ንግግር ችግር ድረስ ነው። ይህም ማለት
የዓይኑን ችግር ማለት ነው። ኤለን ዋይት አስገራሚ በሚመስል ሁኔታ
ጳውሎስ ሲናገር ‹‹መውጊያው ተሰጥቶኛል›› The SDA Bible
Commentary, vol. 6, p. 1107) ጳውሎስ ‹‹ተሰጠኝ›› ሲል ምን ማለቱ
ነው? ለእርሱ የሰጠው ማን ነው? እግዚአብሔር ይህንን ለጳውሎስ በረከት
እንዲሆን የሚጠቀመው እንዴት ነው?

የጳውሎስ መውጊያ የተለየ አላማ ያለው መሆኑን ልብ ይበሉ ይኃውም


‹‹እንዳልታበይ›› (2ቆሮ 12:7)::ይህ የሆነው እርሱ የተለየ ኃጢአት አድርጎ
ሳይሆን ፣ ነገር ግን ወደፊት ኃጢአት እንዳያደርግ ለመከላከል ነው። ጳውሎስ
በተፈጥሮ ወደ ኃጢአት የማዘንበል ችግር ያለ መሆኑን በመገንዘብ ይህ
መውጊያ የተፈቀደው ይህንን ለመከላከል እንደሆነ ተረድቷል። 2ኛቆሮ 12 7-
10 ያለውን ያንብቡ ። ጳውሎስ ከመውጊያው ጋር የኖረው እንዴት ነው?
የጰውሎስ ህመም ለመንፈሳዊነቱ የሚፈይደው ነገር አለ? ለዚህ ነገር
ጳውሎስ ምላሽ የሰጠበት ሁኔታ እርስዎ ያሎትን መውጊያ ለመሸከም እንዴት
ያግዛል?
እግዚአብሔር እርስዎን በመንፈሳዊነት ለማሳደግ የሚሄድባቸው መንገዶች
እርሰዎ ከሚያስቡት እጅግ የተለየ መሆኑን ያውቃሉ? በህይዎትዎ በጽድቅ
የበለጠ ፍሬያማ ለመሆን የሚፈልጉባቸውን አከባቢ ያስቡት። እግዚአብሔር
‹‹በመግረዝ ›› እንዲሳድግዎ የሚፈልጉባቸው መንፈሳዊ ለውጦች የትኞቹ
ናቸው?

አርብ:- ሐምሌ 1

ተጨማሪ ሀሳብ

የኤለን ዋይትን “Effectual Prayer,” in Signs of the Times, Nov.


18, 1903; Ellen G. White Comments, p. 1182, in The SDA
Bible Commentary, vol. 4; “እግዚአብሔር እኔን ለማንጻት ሲል
መከራንና ስቃይን ይፈቅዳል ” p. 92, in My Life Today ያንብቡ።
“የሰውን ልብ የሚያነበው እርሱ እግዚአብሔር የሰዎችን ባህሪ እነርሱ ራሳቸው
ከሚያውቁት በላይ ያውቃቸዋል። እርሱ አንዳንዶች ያላቸው ኃይልና በቀላሉ
ሊጎዱ የሚችሉበት ነገር በቀጥታ ለስራው ዕድገት ጥቅም ላይ እንደሚውል
ያውቃል። በእርሱ ታላቅነት እነዚህን ሰዎች ወደተለያዩ ደረጃዎችና ሁኔታዎች
ውስጥ በማስገባት በባህሪያቸው ውስጥ ያሉትን ግድፈቶች ለማጥፋት
ይጠቀማል። እነርሱ ለአገልግሎቱ ብቁ እንዲሆኑ እነዚህን ግድፈቶች
እንዲያስወግዱ ዕድል ይሰጣቸዋል። ብዙውን ጊዜም እነርሱ እንዲጠሩ
ወይም እንዲነጹ ለማድረግ የመከራ እሳትን ፈቅዳል።”–Ellen G. White,
The Ministry of Healing, p. 471.

የመወያያ ጥያቄዎች

1. የኃጢአታችንን ውጤት ማጨድ እጅግ ከባድ ሊሆን ይችላል።


“ከእግዚአብሔር ጋር እንደገና በትክክል ተስተካክዬ መሄድ እችል ይሆን?”
ብለን እንጠይቃለን። በእንደህ ዓይነት ጊዜያት ተስፋ እንዳንቆርጥ
እግዚአብሔር የሚያበረታታን እንዴት ነው? (በኋላ ጳውሎስ በሮሜ 5:1-
11)የተናገረውን ያንብቡ። ይህንን ተመሳሳይ ጥያቄ ለሚጠይቅ ሰው ምን
መልስ ይሰጣሉ?

2. ኤለን ዋይት ‹‹የእግዚአብሔር ጥበቃ ርህራሔ››? ይህ ሊሰራ የሚችለው


እንዴት ነው? አንድ የሆነ ነገር በእግዚአብሔር ጥበቃ ስር የተደረገ መሆኑን
በምን ያውቃሉ? በራስዎ ህይወት ውስጥ የትኞቹ የእግዚአብሔር ስራዎች
ናቸው በእርሱ ጥበቃ የተደረጉት? እንደ ክፍል በዚህ ጊዜ የተማራችሁትን
ተነጋገሩበት። አንዳንድ ድርጊቶች በእግዚአብሔር ጥበቃ እየተከናወኑ
እንደሆነ ለሚደነቅን አንድ ሰው ልትረዱት የምትችሉት እንዴት ነው?

3. በቀጥታ በአሁን ጊዜ በመከራ እሳት ውስጥ እያለፈ ያለ የምታውቁት ሰው


ቢኖር በምን ምክንያት ወደዚያ መከራ እንደገባ ማወቅ ዋና ጉዳይ መሆን
አለበት? ወደ ችግር ያመጣው ምን ይሁን ምን ለመርዳት ዝግጁ ነዎት?
4.በደቡብ አሜሪካ የሚኖር አንድ ክርስትያን ወጣት እጅግ መራራ በሆነ
ፈተና ውስጥ ገባ። ችግሩ ካለፈ በኃላ ወደ አውሮፓ ሄዶ እንደዚህ አለ :-
“ሙት አካሌን በደቡብ አሜሪካ ትቼዋለሁ” ይህ ማለት ምን ማለት ነው?
ሁላችንም ሙት አካላችንን የሆነ ቦታ መተው የሚያስፈልገን እንዴት ነው?

5. እንደ ክፍል ወደ ሆስፕታል ወይም ሌላ የእናንተን እርዳታ የሚፈልጉ በፈተና


ውስጥ ያሉ ሰዎች ያሉበት ሄዳችሁ የፈተናውን ምክንያት ትታችሁ አጽናኗቸው።

You might also like