Professional Documents
Culture Documents
10
10
👉1፤በቂሳርያም፡ኢጣሊቄ፡ለሚሉት፡ጭፍራ፡የመቶ፡አለቃ፡የኾነ፡ቆርኔሌዎስ፡የሚሉት፡አንድ፡ሰው፡ነበረ።
#ቂሳርያ የታሪክ ተመራማሪዎች ቆፍረው እንዳዘጋጁትና አሁንም ድረስ ሂዶ መጎብኘት እንደሚቻል ማሳወቅን እንዎዳለን በዚች ቦታ
ለቆርኔሌዎስ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለታል ስለሱ ታላቅነትም በዚች ቦታ ተነግሯል።
በብዙ ስያሜ ትጠራለች ከቴላቪቭ ወደ 30 ማይል ያህል እርቀት አለው በኪ,ሜ 45 -46 ኪ,ሜ አካባቢ የሚሆን ነው።
#ሮማዊያን ይገዟት የነበረች ታላቅ ከተማ ነች ሮማውያን እንደ ዋና ከተማ አድርገው የሚጠቀሙባት ከተማ ነች።
#ቆርኔሌዎስ_ማነው? ሮማዊ አህዛብ ነው ከስሩ ብዙ ሰዎች አሉ የሚገዙለት ሹም ነው በሮማውያን ዘንድ ትልቅ ሥልጣን ያለው መቶ
አለቃ ነው { ማቴ 8÷5-11 }
#ቆርኔሌዎስ፦ታላቅ ሥልጣን እና ክብር ቢኖረውም በምድር ላይ የተንጣለለ ኑሮ ቢኖርም እንኳን እግዚአብሔርን ግን በሓብትና
በሥልጣን ምክንያት አረሳም ከቤተሰቦቹ ጋር እግዚአብሔርን አብዝቶ እፈራና ይፈልግ ነበር ይህም የሚያሳየው ታላቅነቱን ነው።
እንደምሳሌ አስቴርን ብንወስድ አሥቴር ንግስት ነች ነገር ግን በሐማ ምክንያት የመጣውን ያንን የሞት ደብዳቤ መርዶኪዎስ ሲነግራት
ያማረ ነገር ስለበላች ያማረ ነገር ስለጠጣች ያማረ አልጋ ላይ ስለተኛች ስልጧና ትልቅ ስለሆነ ህዝቦቿን ችላ አላለችም እንዲሁም
ቆርኔሌዎስ የተመቻቸ ህይዎት ቢኖረውም አህዛብ ቢሆንም አብዝቶ ግን እግዚአብሔርን ከልቡ ይፈልግ ነበር ያለ ማስመሰል እውነት
በሆነ ፍለጋ ከልቡ እግዚአብሔርን ከቤተሰቦቹጋ ይፈልግ ነበር። { ማቴ 27÷1-ፍጻሜው }
👉2፤ርሱም፡ከቤተ፡ሰዎቹ፡ዅሉ፡ጋራ፡እግዚአብሔርን፡የሚያመልክና፡የሚፈራ፡ለሕዝብም፡እጅግ፡ምጽዋት፡የሚያደርግ፡ወደ፡
እግዚአብሔርም፡ዅልጊዜ፡የሚጸልይ፡ነበረ።
#የተቸገሩ_ሰዎችን_ይረዳል።
#የጸሎት_ሰው_ነው።
እግዚአብሔርን መፍራቱ በተግባር የተገለጸ ነው። ለህዝቡ ብዙ ምጽዋትን ያደርግ ነበር 👉የተቸገሩትን አብዝቶ ይረዳ ነበር እለት እለት
👉3፤ከቀኑም፡ዘጠኝ፡ሰዓት፡ያኽል፦ቆርኔሌዎስ፡ሆይ፡የሚለው፡የእግዚአብሔር፡መልአክ፡ወደ፡ርሱ፡ሲገባ፡በራእይ፡በግልጥ፡አየው።
👉4፤ርሱም፡ትኵር፡ብሎ፡ሲመለከተው፡ደንግጦ፦ጌታ፡ሆይ፥ምንድር፡ነው፧አለ።መልአኩም፡አለው፦ጸሎትኽና፡ምጽዋትኽ፡በእግዚአብሔር፡
ፊት፡ለመታሰቢያ፡እንዲኾን፡ዐረገ።
#ግብጻውያን_የቤተ_ክርስቲያን_አባቶች_ርሱም_ትኩር_ብሎ_ሲመለከተው_የሚለውን_ሀሳብ_ይህ_የተገለጠለት፦እግዚአብሔርንም
ሰውንም የሚወድ ልብ ስላለው ሰማያዊ ነገርን ሊያይ ችሏል ይላሉ።
#ጸሎትህና_ምጽዋትህ_በእግዚአብሔር_ፊት_ለመታሰቢያ_እንዲሆን_ዐረገ_የሚለውን_ቃል_ወስደው_ግብጻዊያን_አባቶች፦የእግዚአብ
ሔር_መልአክ_የተላከው፦ወደ አህዛብ ቤት ነው ወደ ቤተ መቅደስ አይደለም የእርሱን መስዋእት ተቀበለ ይህ የሚያሳየው እግዚአብሔር
የሚቀበለው መስዋእት በፍቅር በመታዘዝ እና በምስጋና የሚደረገውን ነው።
👉5፤አኹንም፡ወደኢዮጴ፡ሰዎችን፡ልከኽ፡ጴጥሮስ፡የሚባለውን፡ስምዖንን፡አስመጣ።
👉6፤ርሱ፡ቤቱ፡በባሕር፡አጠገብ፡ባለው፡በቍርበት፡ፋቂው፡በስምዖን፡ዘንድ፡እንግድነት፡
ተቀምጧል፤ልታደርገው፡የሚገ፟ባ፟ኽን፡ርሱ፡ይነግርኻል።
#አንድም_በአይሁዳዊያን_ዘንድ ቁርበት መፋቅ ንጹህ የሆነ ስራ አይደለም ስለዚህም ያገሉት ነበርና ከሌሎች ሁሉ ቤት እርቆ ተለይቶ
ይገኛል የስምኦን ቤት ይላሉ ሊቃውንቱ።አንድም ቤቱን ለመለየት አይከብድም።
#ስለዚህም_የተናቁትን_የሚያከብር_እግዚአብሔር ሰዎች ባገለሉት በስምኦን ቤት ተገኘ ቅዱስ ጴጥሮስም በተናቀውና ሰው ሁሉ ተጸይፎ
ባገለለው በስምኦን ቤት ተገኘ ይህ ምን ያሳያል እግዚአብሔር ሁሉን እንደሚወድ አንዱን ከአንዱ እንደማይለይ የሁሉ አምላክ የሁሉ ጌታ
ሁሉን በፍቅር አይን የሚያይና የተጠሉ የተናቁትን ከፍ እንደሚያደርግ እንደሚያከብር ያሳያል።
ስለዚህም እውነተኛዋን እምነት አንድም ክርስቶስን ያገኝ ዘንድ ቆርኔሌዎስን እግዚአብሔር ወደጴጥሮስ አንድም ወደ ቤተ ክርስቲያን
ላከው።
#በባህር_ዳር_አለ፦ጃን አርሳሚ ግምጃ ጠቃሚ ነውና ለመንከር እንዲመቸው።አንተም ቤተሰቦችህም እምትድንበትን ገንዘብ እርሱ
ይነግርሀል አለው ይላሉ ሊቃውንቱ።
👉7፤የተናገረውም፡መልአክ፡በኼደ፡ጊዜ፥ከሎሌዎቹ፡ኹለቱን፥ከማይለዩትም፡ጭፍራዎቹ፡እግዚአብሔርን፡
የሚያመልክ፡አንዱን፡ወታደር፡ጠርቶ፥
8፤ነገሩን፡ዅሉ፡ተረከላቸው፥ወደ፡ኢዮጴም፡ላካቸው።
{ ገላ 1÷15-16 }
#ሊቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈዎርቅ፦ሌላውን ሰው ለማዳን ከማይጥር ክርስቲያን ከዚህ በላይ የቀዘቀዘ ነገር የለም ይላል።
ስለዚህም ቆርኔሌዎስ ብቻውን መዳን ሳይሆን የፈለገው በዙሪያው ያሉትም ሁሉ እንዲድኑ መፈለጉ።
#ከቄሳርያ_ኤዮጴ_32_ኪ,ሜ_ይርቃል።
#ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን_የነገረውም_መልአክ_አልፎ_ከሄደ_በኋላ፦ከባለሟሎቹ ሁለቱን
👉9፤እነርሱም፡በነገው፡ሲኼዱ፡ወደ፡ከተማም፡ሲቀርቡ፥ጴጥሮስ፡በስድስት፡ሰዓት፡ያኽል፡ይጸልይ፡ዘንድ፡ወደ፡ጣራው፡ወጣ።
👉10 -11፤ተርቦም፡ሊበላ፡ወደደ፤ሲያዘጋጁለት፡ሳሉም፡ተመስጦ፡መጣበት፤ሰማይም፡ተከፍቶ፡ባራት፡ማእዘን፡የተያዘ፡ታላቅ፡ሸማ፡
የሚመስል፡ዕቃ፡ወደ፡ምድር፡ሲወርድ፡አየ፤
#ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን_ተርቦ_ነበርና_ሊመገብ_ወዶ_ሳለ_ምግብ_እስኪያዘጋጁለት_ድረስ_አርምሞ_መጣበት_ሰማይ_የተከፈተ
_ሆኖ_አየ።
#ባራት_ማእዘን_የተያዘ_ታላቅ_ሸማ_የተባለ ችውን_አባቶች_ሲፈቱ_ቅዱስ_ጴጥሮስ_በራእዩ_ያያት_ይች_ሸማ_የተባለችው፦ዓለም
አቀፍዊ የሆነችው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነች ።የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሚሳሌ ነች ይላሉ።
#አራት_ማእዘን_መባሉ፦ 👉ሰሜን 👉ምስራቅ 👉ምዕራብ 👉ደቡብን ያጠቅሳል ይህም ሐዋርያትና ነብያት በአራቱም ማእዘነ ዓለም ዞረው
ማስተማራቸውንና ቤተክርስቲያንን ማነጻቸውን የሚገልጽ ነው ይላሉ የኢትዮጵያ ሊቃውንትና የግብጽ ሊቃውንቶች በህብረት።
👉12፤በዚያውም፡አራት፡እግር፡ያላቸው፡ዅሉ፡አራዊትም፡በምድርም፡የሚንቀሳቀሱት፡የሰማይ፡ወፎችም፡ነበሩበት።
👉13፤ጴጥሮስ፡ሆይ፥ተነሣና፡ዐርደኽ፡ብላ፡የሚልም፡ድምፅ፡ወደ፡ርሱ፡መጣ።
#እርቦት_ስለነበር_ተርቦ_ባለበት_ስዓት_ተገለጠለት_መንፈስ_ቅዱስ_ያለበትን_ሁኔታ_ተጠቅሞ_ተነስተህ_አርደህ_ብላ_አለው ጴጥሮስ
ግን ግራ ተጋባ እግዚአብሔር ግን እያለው ያለው አስተምር አህዛብ እሮማዊ ግሪካዊ አይሁዳዊ ሳትል ሁሉን አስተምር ሲለው ነው።
#አርደህ_ብላ_የሚለው_ቃል፦አስተምረህ በወንጌል ፍቅር ግደል አስተምረህ ወደ ቤተ ክርስቲያን ጨምር ሲለው እንጅ ሌላ ነገር እረድ
ወይም ግደል ሲል አይደለም። {
👉14፤ጴጥሮስ፡ግን፦ጌታ፡ሆይ፥አይኾንም፤አንዳች፡ርኵስ፡የሚያስጸይፍም፡ከቶ፡በልቼ፡አላውቅምና፡አለ።
👉15፤ደግሞም፡ኹለተኛ፦እግዚአብሔር፡ያነጻውን፡አንተ፡አታርክሰው፡የሚል፡ድምፅ፡ወደ፡ርሱ፡መጣ።
👉16፤ይህም፡ሦስት፡ጊዜ፡ኾነ፥ወዲያውም፡ዕቃው፡ወደ፡ሰማይ፡ተወሰደ።
#ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን_ተመልሶ ወደሰማይ ሲያርግ አየ ሰፊ መጋረጃ የወንጌል በአራት ወገን መያዟ ወንጌል በአራቱ ማእዘን
የመነገሯ ማለትም👉በሰሜን በምስራቅ በደቡ በምዕራብ የመነገሯ ሚስጢርን ሲያስረዱ በአራቱ ክፍል ሆና የመጻፏ ማለትም👉ማቴዎስ
ማርቆስ ሉቃስ ዮሐንስ ።
#ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን_ስዕል_አዕዋፍ_የነብያት_የካህናት_ስዕለ_አራዊት_የምዕመናን_አህዛብ_ስዕለ_እንስሳት_የምዕመናን_እስራ
ኤል_ሪያውንም_አርደ_ብላ_ማለቱ_አህዛብን_አስተምር_ሲለው_ነው።
👉17፤ጴጥሮስም፡ስላየው፡ራእይ፦ምን፡ይኾን፧ብሎ፡በልቡ፡ሲያመነታ፥እንሆ፥ቆርኔሌዎስ፡የላካቸው፡ሰዎች፡ስለስምዖን፡ቤት፡ጠይቀው፡ወደ፡
ደጁ፡ቀረቡ፤
👉18፤ድምፃቸውንም፡ከፍ፡አድርገው፦ጴጥሮስ፡የተባለው፡ስምዖን፡በዚህ፡እንግድነት፡ተቀምጧልን፧ብለው፡ይጠይቁ፡ነበር።
👉19፤ጴጥሮስም፡ስለ፡ራእዩ፡ሲያወጣ፡ሲያወርድ፡ሳለ፥መንፈስ፦እንሆ፥ሦስት፡ሰዎች፡ይፈልጉኻል፤
👉20፤ተነሥተኽ፡ውረድ፥እኔም፡ልኬያቸዋለኹና፡ሳትጠራጠር፡ከነርሱ፡ጋራ፡ኺድ፡አለው።
#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ቤተ_ክርስቲያን_ሊቃውንት_ይህን_ክፍል_ሲፈቱ_መንፈስ_ቅዱስ_ሦስት_ሰዎች_ይሹሀል_አለው_ይ
ላሉ።
#ግብጻዊያን_የቤተክርስቲያን_አባቶች_ደግሞ_መንፈስ_ቅዱስ_ሥራ_እንዲጀምር_አዘዘው_ይህም_የመንፈስ_ቅዱስ_ትእዛዝ_ነው_ይላ
ሉ።
👉21፤ጴጥሮስም፡ወደ፡ሰዎቹ፡ወርዶ፦እንሆ፥የምትፈልጉኝ፡እኔ፡ነኝ፤የመጣችኹበትስ፡ምክንያት፡ምንድር፡
ነው፧አላቸው።
👉22፤እነርሱም፦ጻድቅ፡ሰው፣እግዚአብሔርንም፡የሚፈራ፥በአይሁድም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የተመሰከረለት፡የመቶ፡
አለቃ፡ቆርኔሌዎስ፡ወደ፡ቤቱ፡ያስመጣኽ፡ዘንድ፥ከአንተም፡ቃልን፡ይሰማ፡ዘንድ፥ከቅዱስ፡መልአክ፡ተረዳ፡አሉት።
#ቆርኔሌዎስ_በእግዚአብሔር_የተወደደ #አንድም፦ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው መሆኑን ገለጹለት እርሱ አህዛብ ቢሆንም ሮማዊ
ቢሆንም ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚፈራ ደግ ሰው መሆኑን ነገሩት።
👉23፤ርሱም፡ወደ፡ውስጥ፡ጠርቶ፡እንግድነት፡ተቀበላቸው።በነገውም፡ተነሥቶ፡ከነርሱ፡ጋራ፡
ወጣ፥በኢዮጴም፡ከነበሩት፡ወንድሞች፡አንዳንዶቹ፡ከርሱ፡ጋራ፡ዐብረው፡ኼዱ።
#ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን፦ አሁን ጴጥሮስ ያየው ራእይ እየተገለጸለት ነው እንዴት አንድ አይሁዳዊ ከአህዛብ ጋር ህብረት ያደርጋል
ስለምን ስድስት ሰዎች ጴጥሮስን ተከትለውት ሄዱ ቢሉ፦የዓይን እማኞች ይሆኑ ዘንድ ነው።
👉24፤በነገውም፡ወደ፡ቂሳርያ፡ገቡ፤ቆርኔሌዎስም፡ዘመዶቹንና፡የቅርብ፡ወዳጆቹን፡ባንድነት፡ጠርቶ፡
ይጠባበቃቸው፡ነበር።
👉25፤ጴጥሮስም፡በገባ፡ጊዜ፡ቆርኔሌዎስ፡ተገናኝቶ፡ከእግሩ፡በታች፡ወደቀና፡ሰገደለት።
👉26፤ጴጥሮስ፡ግን፦ተነሣ፤እኔ፡ራሴ፡ደግሞ፡ሰው፡ነኝ፡ብሎ፡አስነሣው።
#አንድም፦ቆርኔሌዎስ_ጴጥሮስን_ሲያየው_መሲሁ_መስሎት_ነበር_ለዚህ_ነው_የሰገደለት።
#የኢትዮጵያ_ሊቃውንት_ደግሞ፡ከግሩ በታች ወድቆ ሰገደለት የአክብሮ ስግደት ነው እንዳንተ ያለሁ ፈራሽ በስባሽ አይደለሁምን ስለምን
ለእኔ ትሰግዳለህ ብሎ አስነሳው ይላሉ።
👉27፤ከርሱም፡ጋራ፡እየተነጋገረ፡ገባ፥ብዙዎችም፡ተከማችተው፡አግኝቶ፦
👉28፤አይሁዳዊ፡ሰው፡ከሌላ፡ወገን፡ጋራ፡ይተባበር፡ወይም፡ይቃረብ፡ዘንድ፡እንዳልተፈቀደ፡እናንተ፡ታውቃላችኹ፤ለእኔ፡ግን፡እግዚአብሔር፡
ማንንም፡ሰው፡ርኩስና፡የሚያስጸይፍ፡ነው፡እንዳልል፡አሳየኝ፤
#ጴጥሮስ በቆርኔሌዎስ ቤት የተቀመጡትን ብዙ የተለያዩ ሰዎች ባየ ጊዜ እግዚአብሔር በራእይ የገለጸለት ሚስጢር እየገባው መጣ ይላሉ
አባቶች ።
{ ዮሐ 3÷16 } { ኤፌ 2÷13-17 }
👉29፤ስለዚህም፡ደግሞ፡ብትጠሩኝ፡ሳልከራከር፡መጣኹ።አኹንም፡በምን፡ምክንያት፡አስመጣችኹኝ፧ብዬ፡እጠይቃችዃለኹ፡አላቸው።
👉30፤ቆርኔሌዎስም፡እንዲህ፡አለው፦በዚች፡ሰዓት፡የዛሬ፡አራት፡ቀን፡የዘጠኝ፡ሰዓት፡ጸሎት፡በቤቴ፡እጸልይ፡ነበር፤እንሆም፥የሚያንጸባርቅ፡
ልብስ፡የለበሰ፡ሰው፡በፊቴ፡ቆመና፦
👉31፤ቆርኔሌዎስ፡ሆይ፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡ጸሎትኽ፡ተሰማ፥ምጽዋትኽም፡ታሰበ።
👉32፤እንግዲህ፡ወደ፡ኢዮጴ፡ልከኽ፡ጴጥሮስ፡የተባለውን፡ስምዖንን፡አስጠራ፤ርሱ፡በቍርበት፡ፋቂው፡
በስምዖን፡ቤት፡በባሕር፡አጠገብ፡እንግድነት፡ተቀምጧል፡አለኝ።
👉33፤ስለዚህ፥ያን፡ጊዜ፡ወዳንተ፡ላክኹ፥አንተም፡በመምጣትኽ፡መልካም፡አድርገኻል።እንግዲህ፡አንተ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የታዘዝኸውን፡
ዅሉ፡እንድንሰማ፡እኛ፡ዅላችን፡አኹን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በዚህ፡አለን።
👉34-35፤ጴጥሮስም፡አፉን፡ከፍቶ፡እንዲህ፡አለ፦እግዚአብሔር፡ለሰው፡ፊት፡እንዳያደላ፥ነገር፡
ግን፥በአሕዛብ፡ዅሉ፡ርሱን፡የሚፈራና፡ጽድቅን፡የሚያደርግ፡በርሱ፡የተወደደ፡እንደ፡ኾነ፡በእውነት፡
አስተዋልኹ።
#ይህ_ክፍል_እሚያሳየው፦እግዚአብሔር አምላክን ያመነና ትእዛዙን የሚፈጽም ሰው ከአህዛብም ወገን ቢሆን የተመረጠ እንደሆነ
ጴጥሮስ መረዳቱን ነው።አንድም እግዚአብሔር አምላክ የሁሉ አምላክ የሁሉ ጌታ መሆኑን መረዳቱን ያሳያል።{ ዮሐ 3÷16 }
#ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን_ይህን_ክፍል_ሲተረጉሙ፦እግዚአብሔርን የሚፈራው የሚወደው የሚያመልከው ትእዛዙን የሚፈጽም
በእርሱ ዘንድ የተመረጠ እርሱ ነው።ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን አስተዋለ።{ ሮሜ 2÷11} { ያዕቆብ 2÷ 1} { ኤፌ 6÷6-11 }
👉36፤የዅሉ፡ጌታ፡በሚኾን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ሰላምን፡እየሰበከ፡ይህን፡ቃል፡ወደእስራኤል፡ልጆች፡ላከ።
#የሁሉ_ጌታ_ሲል፦ለአይሁዳዊያን ብቻ ሳይሆን ለአህዛብም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉ አምላክ የሁሉ ጌታ መሆኑን ሲናገር ነው።
👉37፤ዮሐንስ፡ከሰበከው፡ጥምቀት፡በዃላ፡ከገሊላ፡ዠምሮ፡በይሁዳ፡ዅሉ፡የኾነውን፡ነገር፡እናንተ፡ታውቃላችኹ።
#ግብጻዊያን_አባቶች_ይህን_ክፍል_ሲፈቱ፦ቅዱስ_ጴጥሮስ_በቆርኔሌዎስ_ቤት_ባሉ_በቤተሰቦቹና_በጓደኞቹ_በአህዛብ_ፊት_ቆሞ_ሚ
ተርክላቸው_ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ሐዋርያትን መረጠ አገልግሎቱን ጀመረ እያለ
እየገለጸላቸው ነው።
#ቅዱስ_ዮሐንስ፦ያጠምቅ የነበረው የንስሃ ጥምቀት ነው ታዲያ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ ነውር የሌለበት ንጹህ
ቅዱስ ጌታ ለምን በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ ቢባል ይህንን ሲፈቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፦ለእኛ ጥምቀትን ያስተምር ዘንድ አርአያ
ይሆነን ዘንድ ተጠመቀ ይላሉ።
#ቅዱስ_ጴጥሮስ ከገሊላ ጀምሮ በይሁዳ ሁሉ የሆነውን ነገር እናንተ ታውቃላችሁ ማለቱ፦ቆርኔሌዎስ ከቤተሰቦቹ ጋር የሚኖረው
በቂሳርያ ነው ከቂሳርያ ገሊላ 65 ኪ,ሜ ነው ርቀቱ ይህም ማለት ብዙ አይርቅም እና ቅዱስ ጴጥሮስ ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ የሰራውን
ሁሉ ተአምር በእርሱ የተደረጉትን ብዙ ድንቅ ድንቅ ነገሮች ታቃላችሁ አንድም አይሁዳዊያን ለሮማዊያን አሳልፈው እንደሰጡት
በሮማዊያን መገደሉንም ሁሉ ሰምታችኋል ታውቃላችሁ ሲላቸው ነው።{ ማቴ 10÷1 ሙሉውን }
👉38፤እግዚአብሔር፡የናዝሬቱን፡ኢየሱስን፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡በኀይልም፡ቀባው፥ርሱም፡መልካም፡እያደረገ፡
ለዲያብሎስም፡የተገዙትን፡ዅሉ፡እየፈወሰ፡ዞረ፥እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረና፤
#እርም_እሚለው፦ እግዚአብሔርን ነው
{ ማቴ 14 ሙሉውን } { ዮሐ 3÷16 }
ሌሎች የተመረጡ የተቀቡ የምንላቸውም አሉ ነገር ግን ጌታን የተቀባ ስንል ቅዱሳን ሰዎችን የተቀቡ ስንል ሰፊ ልዩነት አለው ይህም
እነርሱ የተቀቡት በሰው ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር አብ የተቀባ ነው ይህም የሚያሳየው እራሱ እግዚአብሔር መሆኑን
ነው።
#ለዳዳቢሎስም_የተገዙትን_እየፈወሰ_ዞረ፦ተአምራትን አደረገ ወንጌልን በኃይል ገለጠ በአጋንት እስራት ውስጥ የታሰሩትን እየፈታ
በኢየሩሳሌም አውራጃ ዞረ ።
{ ሉቃስ 11÷14 } { ማር 1÷34-35 } { ሉቃስ 4÷35 } {ማቴ 9÷33 } ማቴዎስ ከምዕራፍ 8 ጀምሮ እስከ ምዕራፍ 12 እያንዳንዱን
ምዕራፎች ሙሉ ሙሉውን ማንበብ እንዳይዘነጋ!!
👉39፤እኛም፡በአይሁድ፡አገርና፡በኢየሩሳሌም፡ባደረገው፡ነገር፡ዅሉ፡ምስክሮች፡ነን፤ርሱንም፡በዕንጨት፡ላይ፡ሰቅለው፡ገደሉት።
መድኀኒት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መድኀኒትነቱን አንቀበልም ብለው ሮማዊያን ገደሉት ሲል ነው ቅዱስ ጴጥሮስ።
#ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን፦ቅዱስ ጴጥሮስ እያለ ያለው እኛ ግን በአይሁድ ሀገርና በኢየሩሳሌም ባደረገው ነገር ሁሉ ምስክሮች ነን
ማለቱ፦ባስተማረው ትምህርት በሰራው ቱርፋት ባደረገው ተአምራት ማለቱ ነው። በእንጨት ሰቅለው እንደገደሉት እግዚአብሔር ግን
በሦስተኛው ቀን ከሙታን ለይቶ እብዳስነሳው እኛ ምስክሮች ነን።
አይሁዳዊያን ዘለዓለማዊ ህይዎት የሚሰጠውን ብርሃን የሆነውን ጌታ ህይዎትን እናጠፋለን እናዳፍናለን ብለው በቀራንዮዮ መስቀል ላይ
ገድለው ቀበሩት እነርሱ ግን አላወቁም ዘለዓለማዊ ህይዎትን እናጠፋለን ብለው የራሳቸውን ህይዎት አጠፉ ይላሉ ሊቃውንተ ቤተ
ክርስቲያን።
👉40፤ርሱን፡እግዚአብሔር፡በሦስተኛው፡ቀን፡አስነሣው፡ይገለጥም፡ዘንድ፡ሰጠው፤
#እግዚአብሔር_አስነሳው_ሲል፦ከሦስትነተ አይጎልም በአባቱ በአብ ፈቃድ በራሱ ፈቃድ በባህሪ ህይዎቱ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ
ከሙታን መካከል ተለይቶ መነሳቱን የሚገልጽ ነው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአንድነትና በሦስትነት መተካከላቸውን የሚገልጽ ነው
{ ሮሜ 8÷11 } { ዮሐ 2÷19-25 }
#ይገለጥም_ዘንድ_ሰጠው፦በአባቱ ፈቃድ በራሱ ፈቃድ በባህሪ ህይዎቱ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ
👉41፤ይኸውም፡ለሕዝብ፡ዅሉ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡አስቀድሞ፡የተመረጡ፡ምስክሮች፡
ለኾን፟፡ለእኛ፡ነው፡እንጂ፤ከሙታንም፡ከተነሣ፡በዃላ፡ከርሱ፡ጋራ፡የበላን፡የጠጣንም፡እኛ፡ነን።
👉42፤ለሕዝብም፡እንድንሰብክና፡በሕያዋንና፡በሙታን፡ሊፈርድ፡በእግዚአብሔር፡የተወሰነ፡ርሱ፡እንደ፡ኾነ፡እንመሰክር፡ዘንድ፡አዘዘን።
#በህያዋንና_በሙታን_ሊፈርድ_በእግዚአብሔር_የተወሰነ_እርሱ_እንደሆነ_እንመሰክር_ዘንድ_አዘዘን_ማለቱ፦በመጨረሻው ዘመን
ዳግም የሚመጣው ለጻድቃን የሚፈርድላቸው በኀጥአን ላይ የሚፈርድባቸው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ማለት ነው { ዮሐ
5÷22÷23 }
👉43፤በርሱ፡የሚያምን፡ዅሉ፡በስሙ፡የኀጢአቱን፡ስርየት፡እንዲቀበል፡ነቢያት፡ዅሉ፡ይመሰክሩለታል።
👉44፤ጴጥሮስ፡ይህን፡ነገር፡ገና፡ሲናገር፡ቃሉን፡በሰሙት፡ዅሉ፡ላይ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ወረደ።
#ይህ ክፍል ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን ነገር ገና ሲናገር ቃሉን በሰሙት፦በሮማዊያን ላይ መንፈስ ቅዱስ እንደወረደ ይናገራል። { የሐዋርያት
ሥራ 15÷8 }
👉45፤ከጴጥሮስም፡ጋራ፡የመጡት፡ዅሉ፡ከተገረዙት፡ወገን፡የኾኑ፡ምዕመናን፡በአሕዛብ፡ላይ፡ደግሞ፡የመንፈስ፡ቅዱስ፡ስጦታ፡ስለ፡ፈሰሰ፡
ተገረሙ፤
#ተገረሙ_መባሉ፦በአይሁዳዊያንና በሮማዊያን በአህዛብ መካከል የነበረው ያየጥል ግድግዳ ሲፈርስ ባዩ ጊዜ አንዱ እግዚአብሔር
አምላክ ለአይሁዳዊያም ለአህዛብም አንድ አምላክ አድሎ የሌለው መሆኑን አይተው በሐዋርያት ላይ የወረደው መንፈስ ቅዱስ በአህዛቡ
በቆርኔሌዎስ ቤት በአህዛቦች ላይም ሲወርድ ባዩ ጊዜ ተገረሙ ።
👉46፤በልሳኖች፡ሲናገሩ፥እግዚአብሔርንም፡ሲያከብሩ፡ሰምተዋቸዋልና።
#ሊቁ_አውገስጢኖስ፦መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ በህዝቦች ልሳን መናገራቸው ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ቋንቋ መናገር እንዳለባት ያሳያል
ይላሉ።
#አንድም፦ ቤተ ክርስቲያን ኩላዊት ሁለገብ አንድም ዓለም አቀፋዊት መሆኗን ያሳያል።
👉47፤በዚያን፡ጊዜ፡ጴጥሮስ፡መልሶ፦እነዚህ፡እንደ፡እኛ፡ደግሞ፡መንፈስ፡ቅዱስን፡የተቀበሉ፡እንዳይጠመቁ፡ውሃን፡ይከለክላቸው፡ዘንድ፡
የሚችል፡ማን፡ነው፧አለ።
#ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን፦በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምናችሁ ተጠመቁ አላቸው ከዚህ በኋላ ጥቂት ቀን ከእኛ ዘንድ
ሰንብት ብለው ማለዱት።
1 ኛ ወንጌልን እንዲሰብክላቸው ነገረ ክርስቶስን እንዲያላብሳቸው ነው ቆርኔሌዎስን ሐዋርያዊ ተልእኮ እንዲያስተምረው እርሱን ብቻ
ሳይሆን ቤተሰቦቹን ጓደኞቹንም ጭምር።
ስብአት ለአብ🍀 ስብአት ለወልድ🍀 ስብአት ለመንፈስ ቅዱስ 🍀ወለዓለም ዓለም አሜን