Professional Documents
Culture Documents
4
4
1፤እንግዲህ፡በጌታ፡እስር፡የኾንኹ፡እኔ፡በተጠራችኹበት፡መጠራታችኹ፡እንደሚገ፟ባ፟፡ትመላለሱ፡ዘንድ፡እለምናችዃለኹ፤
#
ቅዱስ_ጳውሎስ_በጌታ_እስር_የሆንኩ_እኔ_እያለ_ደጋግሞ_የሚጽፍበትን_ምክኒያት_ስሁለት_ነገር_ነው_ይላሉ_የቤተክርስቲያን_አ
ባቶች
1 ኛ,የክርስቶስ እስረኛ መሆኑን ሲመለከቱ ልባቸው እንዲራራ በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ ለኤ ፌሶን ሰዎች መልእክቱን እየጻፈላቸው
መሆኑን አውቀው ልባቸው እንዲመለስ።
2 ኛ, በክርስትና ስደት መከራ እንግልት ፈተና እስር ስላለ በዚህም መከራና ስደት ፈተና እስር ቢደርስባቸው የኤፌሶን ሰዎች
መምህራችን ከታሰረ መከራ ከደረሰበት ብለው የኤፌሶን ሰዎች እነሱም በእስር በስደት በመከራ እንዲጸኑና በክርስቶስ ክርስቲያን
የተባልን እኛም የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስን እንግልት እና ጽናት እያሰብን በመከራ እንድንጸና ነው።
2፤በትሕትና፡ዅሉና፡በየዋህነት፡በትዕግሥትም፤ርስ፡በርሳችኹ፡በፍቅ ር፡ታገሡ፤
# ቅዱስ_ጳውሎስ_አባታዊ_ምክርን_እየመከራቸው ነው📚።
👇👇👇👇👇
3፤በሰላም፡ማሰሪያ፡የመንፈስን፡አንድነት፡ለመጠበቅ፡ትጉ።
4፤በመጠራታችኹ፡ባንድ፡ተስፋ፡እንደ፡ተጠራችኹ፡አንድ፡አካልና፡አንድ፡መንፈስ፡አለ፤
# በአንድ_ተስፋ_ሲል÷ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ለማመን የተጠራ ሁሉ አንድ መንግስተ ሰማይን ለመውረስ ተስፋ ይዞ
እንደተከተለው የሚያስረዳ ነው ይላሉ ሊቃውንቱ ። ክርስቲያን ሁሉ ተስፋ የሚያደርገው አንድ ነገር አለ እሱም ከኢየሱስ ክርስቶስ
ጋር በአድሲቷ ሰማይ በአድሷ ኢየሩሳሌም መኖር ( 1 ኛ ጴጥ 1÷3 ) ( ቆላስያስ 1÷3-5 )
#አንድ_መንፈስ_ማለቱ÷አንድ ልብ አንድ ሀሳብ ማለት ሲሆን በአንድ ልብ በአንድ ሀሳብ በፍቅር ሁኑ ሲላቸው ነው። ( ኤፌሶን
4÷1-3 )
5፤አንድ፡ጌታ፡አንድ፡ሃይማኖት፡አንዲት፡ጥምቀት፤
#ሊቃውንተ_ቤተክርስቲያን_
# አንድም÷ መታመንና መመለክ የሚገባው አንድ ጌታ ስለሆነ አንድ ጌታ መሆኑን ሲያስረዳ አንድ ሐይማኖት ሊ ል ችሏል
ሐዋርያው አንድ ሐይማኖት ሲል የክርስትናን ሐይማኖት መሆኑን አንዲት ጥምቀት በማ ለት አረጋግጧል አንዱን ጌታ በማምለክ
ልዩነቶች አሉ የእግዚአብሔር ልጅ ሰው መሆኑ የተገለጠ ሲሆን እግዚአብሔር አይወርድም አይወለድም የሚሉም አሉ ይላሉ
ሊቃውንቱ።
6፤ከዅሉ፡በላይ፡የሚኾን፡በዅሉም፡የሚሠራ፡በዅሉም፡የሚኖር፡አንድ፡አምላክ፡የዅሉም፡አባት፡አለ።
7፤ነገር፡ግን፥እንደክርስቶስ፡ስጦታ፡መጠን፡ለያንዳንዳችን፡ጸጋ፡ተሰጠን።
8፤ስለዚህ፦ወደ፡ላይ፡በወጣ፡ጊዜ፡ምርኮን፡ማረከ፡ለሰዎችም፡ስጦታን፡ሰጠ፡ይላል።
# ወደ_ላይ_ በወጣ_ጊዜ_ሲል÷ጌታችን ሞትና መቃብርን ድል አድርጎ መነሳቱን ነው በአረገ ጊዜ ማለቱ ነው እርገቱን ይናገራል።
# ምርኮ ን_ማረከ_ማለቱ÷በሲኦል በዲያቢሎስ ባርነት ተይዘው የሚኖሩ ነፍሳትን ማርኮ ወደ ገነት መውሰዱን ያመለክታል። ( 1 ኛ
ጴጥ 3÷19 )
ጌታችን ወደመቃብር ወረደ ካላልን ተነሳ ወደ ላይ አረገ ድል አደረገ ማለት አንችልም ።ይህ ክፍል ስለትንሳኤው ይናገራል።
10፤ይህ፡የወረደው፡ዅሉን፡ይሞላ፡ዘንድ፡ከሰማያት፡ዅሉ፡በላይ፡የወጣው፡ደግሞ፡ያ ው፡ነው።
11፤ርሱም፡አንዳንዶቹ፡ሐዋርያት፥ሌላዎቹም፡ነቢያት፥ሌላዎቹም፡ወንጌል
ን፡ሰባኪዎች፥ሌላዎቹም፡እረኛዎችና፡አስተማሪዎች፡እንዲኾኑ፡ሰጠ፤
# እንዲሆኑ_ሰጠ_ማለት_እግዚአብሔር_አምላክ_ የተለያየ_ጸጋን_ሰጣቸው_ሲል_ነው
# እርሱ_ያለው_ኢየሱስ_ክርስቶስን_ነው_ኢየሱ_ክርስቶስን_ነው።
# ወንጌል_ሰባኪያን_የሚላቸው÷ ጳጳሳትን ነው
#አስተማሪዎች_የሚላቸው÷ተርጓሚዎችን ነው።
12-13፤ዅላችን፡የእግዚአብሔርን፡ልጅ፡በማመንና፡በማወቅ፡ወደሚገኝ፡አንድነት፥ሙሉ፡ሰውም፡ወደ፡መኾን፥የክርስቶስም፡ሙላቱ፡
ወደሚኾን፡ወደ ፡ሙላቱ፡ልክ፡እስክንደርስ፡ድረስ፥ቅዱሳን፡አገልግሎትን፡ለመሥራትና፡ለክርስቶስ፡አካል፡ሕንጻ፡ፍጹማን፡ይኾኑ፡ዘንድ።
#ለክርስቶስ_አካል_ህንጻ_ሲል÷ምዕመናን የክርስቶስ አካል ለመሆን እንደ ህንጻ ያድጋሉ ማለት ነው።ማለትም በእግዚአብሔር ቃል
እየተሰሩ
#ፍጹማን_ይሆኑ_ዘንድ_ሲል÷በክርስቶስ ኢየሱስ ፍጹማን መሆን ቅዱሳንን መምሰል በፍቅር መሞላት ለተፈጠርንበት ዓላማ መኖር
ማለት ነው።( ኤፌ 2÷10 )
1 4፤እንደ፡ስሕተት፡ሽንገላ፡ባለ፡ተንኰል፡በሰዎችም፡ማታለል፡ምክንያት፡በትምህርት፡ነፋስ፡ዅሉ፡እየተፍገመገምን፡ወዲያና፡ወዲህም፡
እየተንሳፈፍን፡ሕፃናት፡መኾን፡ወደ፣ፊት፣አይገ፟ባ፟ንም፥
#በሰዎችም_ማታለል_ምክንያት_በትምህርት_ነፋስ_ዅሉ_እየተፍገመገምን_ወዲያና_ወዲህም_እየተንሳፈፍን_ሕፃናት_መኾን_ወደ
_ፊት_አይገ፟ባ፟ንም_ሲል_ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን_ይህን_ክፍል_ሲተረጉሙ÷የስህተቱን_ትምህርት_በነፋስ_ይመስለዋል። የነ
ፍስ ኃይል የቆሙ ነገሮችን ገፍትሮ እንደሚጥል ክብደታቸው ቀላል የሆኑ ነገሮችንም እንደሚያንሳፍፍ ሁሉ በስህተተኞች ትምህርት
የምንንሳፈፍ ሕፃናት እንዳንሆን ይመክረናል።#አንድም ስር ሰዳችሁ ተሰሩ ሲል ነው።
15፤ነገር፡ግን፥እውነትን፡በፍቅር፡እየያዝን፡በነገር፡ዅሉ፡ወደርሱ፡ራስ፡ወደሚኾን፡ወደ፡ክርስቶስ፡እንደግ፤
16፤ከርሱም፡የተነሣ፡አካል፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡ክፍል፡በልክ፡እንደሚሠራ፥በተሰጠለት፡በዥማት፡ዅሉ፡እየተጋጠመና፡እየተያያዘ፥ራሱን፡
በፍቅር፡ለማነጽ፡አካሉን፡ያሳድጋል።
17፤እንግዲህ፡አሕዛብ፡ደግሞ፡በአእምሯቸው፡ከንቱነት፡እንደሚመላለሱ፡ከእ ን ግዲህ፡ወዲህ፡እንዳትመላለሱ፡እላለኹ፡በጌታም፡ኾኜ፡
እመሰክራለኹ።
#ከእንግዲህ_ወዲህ_እንዳትመላለሱ_እላለሁ_በጌታም_ሆኜ_እመሰክራለሁ_ሲል_ቅዱስ_ጳውሎስ÷እየገሰጻቸው ነው ምን እያለ
ቢሉ÷እናንተ በቀድሞ ህይዎታችሁ ከንቱ የሆነ ነገር ትከተሉ ነበር ጣኦትን ታመልኩ ነበር አሁን ግን ክርስቲያን ከሆናችሁ በኋላ
ትታችሁት የመጣችሁትን የአህዛብን ልማድ ወይም መንገድ ዞራችሁ እንዳትመለከቱ ሲላቸው ነው። ( ገላ 5÷24 ) ( ሮሜ 12÷2 )
18፤እነርሱ፥ባለማወቃቸው፡ጠንቅ፥በልባቸውም፡ደንዳናነት፣ጠንቅ፣ልቡናቸው፣ጨለመ፥ከእግዚአብሔርም፡ሕይወት፡ራቁ፤
ሴሰኝነት ማለት ዝሙት ነው ሲንል መዘሞት ስንል የስጋን ዝሙት ብቻ ሳይሆን ሰው የተፈጠረበትን አላማ ክርስቶስን ማምለክ
ሆኖ ሳለ የኤፌሶን ሰዎች ግን የተፈጠሩለትን አምልኮ እግዚአብሔር ትተው የፈጠራቸውን አምላክ ትተው ለጣኦትም ሲሰግዱ
እግዚአብሔርን ሲክዱ ዘሞቱ ማለት ነው ግን ይህን ሲያደርጉ ባለማወቅ ነው ሲል ቅዱስ ጳውሎስ ደንዝዘው አለ።
20፤እናንተ፡ግን፡ክርስቶስን፡እንደዚህ፡አልተማራችኹም፤
#ቅዱስ_ጳውሎስ_እናንተ_ግን_ያላቸው_የኤፌሶንን_ክርስቲያኖች_ነው።
#እንዴት_ለምን_ቢሉ÷ ክርስቲያን ከሆናችሁ በኋላ አህዛቦች የሚያደርጉትን ተግባር አታደርጉም ሲላቸው ነው።
21፤በርግጥ፡ሰምታችኹታልና፥እውነትም፡በኢየሱስ፡እንዳለ፡በርሱ፡ተምራችዃል፤
# ቅዱስ_ጳውሎስ_እውነት_ብሎ_እሚጠራው_ወንጌልን_ነው_በእርግጥ_ሰምታችኋልና_ማለቱም_የኤፌሶን_ሰዎች_የወን
ጌልን_እውነት_ሰምተው_ከአህዛብ_ማንነታቸው_ከጣኦት_አምላኪነታቸው_ወጥተው_ወደ_አምልኮተ_እግዚአብሔር_በመምጣታ
ቸው_ነው።
# አንድም_እውነት_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ነው።
# አንድም÷ከብሉይ ኪዳን የተሻለውን የኃዲስ ኪዳንን ትምህርት ሰማያዊ በረከት የሚያላብሰንን ወንጌል ሰምተው ቃለ እግዚአብሔ
ርን ተቀብለው አምነዋልና ነው ።
ስለዚህም ዲያና አምላክ እንዳልሆነች ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ሰምታችኋል
#አንድም÷ወንጌልን ሰምታችኋል እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል አውቃችኋል ሲል ነው። { ዮሐ 14÷6 } { 1 ኛ ዮሐ 2÷23 }
22፤ፊተኛ፡ኑሯችኹን፡እያሰባች ኹ፡እንደሚያታልል፡ምኞት፡የሚጠፋውን፡አሮጌውን፡ሰው፡አስወግዱ፥
23፤በአእምሯችኹም፡መንፈስ፡ታደሱ፥
# ቅዱስ_ጳውሎስ_በአእም ሯችሁም_መን
ፈስ_ታደሱ_ሲል÷እናንተ_የኤፌሶን_ሰዎች__አሁን_አዲስ_ፍጥረት_ናችሁ_በፊተኛው_ኑሮአችሁ_ቀድሞ_ታስቡት_የነበረውን_የኃ
ጢያት_ልምምድ_ቁረጡት_ሲላቸው_ነው።ምድራዊን ሳይሆን ሰማያዊ በረከት ሰማያዊ ጸጋን የሚያላብሰውን ህይዎት አስቡ
ሲላቸው ነው።{ ራእይ 21÷26-ፍጻሜው }
24፤ለእውነትም፡በሚኾኑ፡ጽድቅና፡ቅድስና፡እንደእግዚአብሔር፡ምሳሌ፡የተፈጠረውን፡ዐዲሱን፡ሰው፡ልበሱ።
# እንደ_እግ
ዚአብሔር_ምሳሌ_ሲል÷ኢየሱስ_ክርስቶስ_ወልደ_እግዚአብሔር_ከእግዚአብሔር_አብ_ጋር_አንድ_መሆኑን_ለመግለጽ_ነው
#ይላሉ_ሊቃውንተ_ቤተ ክርስቲያን።
# የተፈጠረውን_ማለቱ÷ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም ስጋ ተዋህ ዶ በስጋ መገለጡን የሚያመለክት
ነው።#ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን የተፈጠረውን የሚለው ቃል ጥያቄ እንዳይፈጥር በምሳሌ እንዲህ አስቀምጠውልናል ለምሳሌ
አንድ ሳይንቲስ ት አንድን ቁስ ከሌላው ቁስ ጋር በማገናኘት አንድ ጠቃሚ የሆነ ነገርን ሊፈጥር እንደሚችል ያም እርሱ የሰራው ነገር
የሳይንቲስት እገሌ ፈጠራ እየተባለ ይነገራል ነገር ግን ሳይንቲስቱ ማዕድኖቹን አልፈጠረም የማዕድኑ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው
ሳይንቲስቱም ማዕድን ስራ ላይ እንዲውል ስላደረገ ብቻ የእሱ ፈጠራ እየተባለ ይነገርለታል ሳይፈጥር ፈጣሪ እንደተባለ እናስተውል
ይላሉ ።
#ቅዱስ_ጳውሎስ_አዲስ_ሰው_ያለው_ለስም_አጠራሩ_ክብርና_ምስጋና_ይግባውና_ኢየሱስ_ክርስቶስን_ነው።
25፤ስለዚህ፥ውሸትን፡አስወግዳችኹ፥ርስ፡በርሳችን፡ብልቶች፡ኾነናልና፥እያንዳንዳችኹ፡ከባልንጀራዎቻችኹ፡ጋራ፡እውነትን፡ተነጋገሩ።
# ስለዚህ_ውሸት_አስወግዳችሁ_ማለቱ÷በኢየሱስ_ክርስቶስ_አካል_ላሉ_እኅቶቻችሁና_ወንድሞ
ቻችሁ_ጋር_በውሸት_ቃል_አትነጋገሩ_በእውነት_ተነጋገሩ_ውሸት_የአህዛቦች_ፀባይ_ነውና_ሲል ነው።
26፤ተቈጡ፡ኀጢአትንም፡አታድርጉ፤
27፤በቍጣችኹ፡ላይ፡ፀሓይ፡አይግባ፥ለዲያብሎስም፡ፈንታ፡አትስጡት።
#ቅዱስ_ጳውሎስ_በቁጣችሁ_ላይ_ጽሓይ_አይግባ_ማለቱን_የኃዲስ_ኪዳን_ትርጓሜ_መምህራን_ሲፈቱት_ጽሓይ_ሳይገባ_ቁጣች
ሁን_አብርዱት #አንድም ጽሓይ ሳይገባ ይቅር ማለት መታረቅ እንደሚያስፈልግ ይመክራል { ማቴ 5÷22-24 } { ሆሴ 6÷6 }
# አንድም መናፍቃን በጉባኤ እንዳይሰለጥኑ #አንድም ምእመናን ከሀይማኖት እንዳይወጡ ከምግባር እንዳይናወጡ ለማድረግ
መቆጣት እንደሚገባ ተገልጧል።
28፤የሰረቀ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይስረቅ፥ነገር፡ግን፥በዚያ፡ፈንታ፡ለጐደለው፡የሚያካፍለው፡እንዲኖርለት፡በገዛ፡እጆቹ፡መልካምን፡
እየሠራ፡ይድከም።
#የሰረቀ_ከእንግዲህ_ወዲህ_አይስረቅ÷#ይህ_ክፍል_የሚያሳየው÷#ሊቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ታላቁ_ተአምር_ይህ_ነው።መጥፎ ነገርን ሲያይ የኖረ ዓይን መልካም ነገርን ሲመልከት ሲሰርቅ ሲዘርፍ የኖረ እጅ ምጽዋትን
በመስጠት ሲጠመድ ክፉ ነገር ሲሰማ የኖረ ጆሮ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል ወንጌልን በመስማት ሲለምልም ክፋትን ስድብን
ሲናገር የኖረ አንደበት በማመስገን በመዘመር ሲቀደስ ይላል። { የሐዋ,ሥራ 2÷45-ፍጻሜ }
30፤ለቤዛም፡ቀን፡የታተማችኹበትን፡ቅዱሱን፡የእግዚአብሔርን፡መንፈስ፡አታሳዝኑ።
31፤መራርነትና፡ንዴት፡ቍጣም፡ጩኸትም፡መሳደብም፡ዅሉ፡ከክፋት፡ዅሉ፡ጋራ፡ከእናንተ፡ዘንድ፡ይወገድ።
#ይህ_ክፍል_የሚያሳየው÷ቅዱስ ጳውሎስ ክፉ ነገሮችን ሁሉ ክርስቲያኖች ሁላችሁ ከናንተ አርቁ እናንተ የክርስቶስ አካል ናችሁና
እርኩስ ነገርን ከሰውነታችሁ አርቁ ሲል ነው
{ 1 ኛ ጴጥ 3÷10 }
32፤ርስ፡በርሳችኹም፡ቸሮችና፡ርኅሩኆች፡ኹኑ፥እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡በክርስቶስ፡ይቅር፡እንዳላችኹ፡ይቅር፡ተባባሉ።
{ ገላ 5÷19-22 }
ስብሐት ለአብ🍀 ስብሐት ለወልድ🍀 ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ 🍀ወለዓለም ዓለም አሜን