You are on page 1of 8

የግሥ አንቀጽ ክለሳ ፩

የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፬፥ ፩ እስከ ፬


፩ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ
ወደ ምድረ በዳ ወሰደው። ፪ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ
ተራበ። ፫ፈታኝም ቀርቦ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ
ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል” አለው። ፬ ኢየሱስ ክርስቶስም
መልሶ “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ
ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል” አለው።
 
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፬፥ ፭ እስከ ፯
፭ ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን
በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ።፮  “መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤
እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ
ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን
ወርውር” አለው። ፯ ኢየሱስም “ጌታን አምላክህን አትፈታተነው
ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል” አለው።
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፬፥ ፰  እስከ ፲፩
፰ ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም
መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ ፱ ”ወድቀህ ብትሰግድልኝ
ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለው። ፲ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
“ሂድ አንተ ሰይጣን! ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ
ተብሎ ተጽፎአልና” አለው። ፲፩ ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው፥ እነሆም፥
መላእክት ቀርበው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያገለግሉት ነበር።
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፬፥ ፩ እስከ ፲፩
፩ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው። ፪ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም
ከጦመ በኋላ ተራበ። ፫ፈታኝም ቀርቦ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል” አለው። ፬
  ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል”
አለው።
፭ ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ።፮  “መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤
እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች
ራስህን ወርውር” አለው። ፯ ኢየሱስም “ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል” አለው።
፰ ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ ፱ ”ወድቀህ
ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለው። ፲ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሂድ አንተ ሰይጣን! ለጌታህ ለአምላክህ
ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና” አለው። ፲፩ ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው፥ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያገለግሉት ነበር።
የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች ወደ
የእንግሊዘኛ ትርጉም (English translation)
እንግሊዘኛ ተርጉማችሁ ጻፉ።
፩ ኢየሱስ ክርስቶስን ይፈተን ዘንድ ወደ ምድረ በዳ ሄደ። (tempt)፩

፪ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል” አለው። (be)
 

፫ ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም። (live) ኛ

፬ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል። (order) ኛ
፭ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል። (tumble) ፬

፮ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ። (tempt) ፭
፯ ወድቀህ ብትሰግድልኝ። (worship/bow down) ኛ
፮ኛ
፰ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው። (give)

፱ ሂድ አንተ ሰይጣን!። (go)
 


፲ መላእክት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያገለግሉት ነበር።

(serve) ፱

፲ኛ
ተውላጠ ስም ሥርወ ግሥ የግሡ ዓይነት የአንቀጹ ዓይነት የአንቀጹ ጊዜያት የአንቀጹ ቅርጽ
(ዓምድ) (አዎንታዊ/አሉታዊ)
(መሆን/መኖር/ድርጊት) (ዓቢይ/ንዑስ/ትዕዛዝ/ዘንድ) (አሁን/አላፊ/ወደፊት)

፩ኛ

፪ኛ

፫ኛ

፬ኛ

፭ኛ

፮ኛ

፯ኛ

፰ኛ

፱ኛ

፲ኛ
ቅድስት (the Second Sunday/week of Lent)
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው የዓቢይ ጾምን ሁለተኛ እሑድ ቅድስት ተብሎ ሰይሟታል። ቅድስት የሚለው ቃል "ቀደሰ” ከሚለው ሥርው ግሥ የተገኘ
ሲሆን ትርጉሙም “ለየ፣ አከበረ፣ መረጠ” ማለት [_ የመሆን ግሥ __]። ቅድስት ለሴት አንቀጽ የሚነገር ሲሆን “የተየች፣ የተመረጠች፣ የከበረች ማለት ነው። ቅዱስ
የሚለው ቃል እንደ ለፈጣሪም ለፍጡርም ያገለግላል። እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንል የባሕሪይው የሆነ ዘላለማዊ ሲሆን ለቅድስናውም ተወዳዳሪ [_የመኖር ግሥ_] ።
ፍጡራንን ግን ቅዱሳን ስንላቸው ቅድስናቸው ከእግዚአብሔር በጸጋ ያገኙት የነጻ ስጦታ [__ የመሆን ግሥ __] ነው። መላእክት፣ ሰዎች፣ መካናት፣ ዕለታት
፣አልባሳት፣ንዋያት ሁሉ ለእግዚአብሔር ሲለዩ ቅዱሳን ተብለው [_ጠራ___] ።

የሰንበትን ቀን አስቀድሞ የቀደሰ የባረከ ራሱ እግዚአብሔር [__ የመሆን ግሥ __] " እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው
ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና"ዘፍ.2፥3 "የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ [__አሰበ__] " ዘጸ 20፥8 እንዲል።

በዚህች ዕለት በተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ስለ ቅድስና ሕይወት “ለእግዚአብሔር ተገዙ ስሙንም [_ ጠራ_] ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሯቸው ለስሙም
ምስጋናን [__ አቀረበ__] ፤ ሰንበትን አክብሩ እውነትንም አድርጉ ብል የማያበላሸው ሌባም የማያገኘው በሰማያት ያለ መዝገብን ለእናንተ
[_ሰበሰበ___] ፤ ተዘጋጅታችኹም [_ተቀመጠ___] ክርስቶስ ወዳለበት ወደ ላይ አስቡ።” በማለት ታስተምራለች።
ሰንበት የእኛ ቀን ሳትሆን ለጌታችን የምንሠራባት የምንለይባት ፣የምንቀደስባት፣ ነገረ እግዚአብሔርን የምንዘከርባት የጌታ ቀን [_የመሆን ግሥ___] ። ለቅድስና የተለየች
ቅድስት ሰንበተ ክርስቲያን እሑድ "በኵረ በዓላት" [__
ተባለ__] ። የመዳናችን መሠረት የተወጠነባት የጌታ የፅንሰቱ ቀን ዕለተ ሰንበት ናት [__ የመሆን ግሥ __]
፤የመዳናችን ማረጋገጫ ፣የእምነታችን መሠረት ፣ቅድስት ትንሣኤው የተፈጸመባት ዕለተ ሰንበት [__የመሆን ግሥ __] ።
በዕለተ ሰንበት ራሳችንን በተለየ ሁኔታ ለቅዱስ ተግባር እንድንለይ ለሥጋችን ከምንፈጽማቸው ተግባራት ይልቅ ነፍሳችን እንድናደላ ያስረዳናል። እንግዲህ በዚች ቅድስት
ዕለት፥-ለቅድስና በተለየች ዕለተ ሰንበት እሑድ ማንም በምንም ምክንያት ወደ ቤተ እግዚአብሔር ከመሄድ እንዳያስታጉል በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ተቀምጦልናል።
ምንጭ፡ http://nohamin.blogspot.com/2016/03/blog-post_5.html

You might also like