You are on page 1of 44

መጽሃፍ ቅዱሳዊ መሪነት

በረከት ታዲዎሰ

© መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው 2006 – ዓለም የመሪዎች ተቋም


ዋና እሴት

እግዚአብሄር ለመጽሃፍ ቅዱስ እውነት


በመሰጠት ራእይ ኖሯቸው ግብን የሚተልሙ
የክርስቶስን አካል በማነሳሳት እና
ተግዳሮቶችን በመቋቋም ዓለምን ለክርስቶስ
የሚማርኩ ወንዶችና ሴቶችን ይፈልጋል::
የትምህርቱ አላማ
 ለእግዚአብሄር መንግስት መስፋት የመሪን ወሳኝ ጠቀሜታ
ለማስተማር

 መሪዎች በሙሉ አቅማቸው መስራት እንዲችሉ የ “መጽሃፍ


ቅዱሳዊ መሪነት ትሪያንግል” ለመረዳትና ተግባራዊ
ለማድረግ
መግቢያ
እግዚአብሄር በምድር ላይ የሚወክሉት
ወንድና ሴት አምባሳደሮችን በመምረጥ
ታሪክ ይቀይራል።

(አይዛክ ሊም)
መጽሃፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች

አብርሃም

ታላቅ ህዝብ አደርግሃለሁ


መጽሃፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች

ሙሴ

ህዝቤን ከባርነት ነጻ ታወጣቸው ዘንድ መልሼ እልክሃለሁ።


መጽሃፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች

ዳዊት

በእስራኤል ላይ ንጉስ ትሆን ዘንድ


ቀብቼሃለሁ
መጽሃፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች

አስቴር

ህዝቤን ለመታደግ እጠቀምብሻለሁ


የመሪነት ትርጉም

መሪነት ተጽእኖ መፍጠር ነው


ጄ. ኦስዋልድ ሳንደርስ
መሪነት…

• በቀጣይ ምን መስራት እንዳለብህ


• ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ቦብ ቤል
• ለተፈላጊው ነገር ተገቢውን ሃብት በምን አይነት
መንገድ ማግኘት እንደሚቻል ማወቅ ነው።
የውይይት መድረክ

ሌሎች ትርጉሞች

• ለመሪነት ሌላ የምታውቀው ትርጉም አለን?

• የአንተ የራስህ ለመሪነት የምትሰጠው ትርጉም


ምንድን ነው?
መጽሃፍ ቅዱሳዊ የመሪነት ትሪያንግል

አገልጋይ ለውጥ አምጪ

እግዚአብሄርና
ቃሉ

መንፈሳዊ
መንፈሳዊ መሪነት
መግቢያ

በተፈጥሯዊ መሪና በመንፈሳዊ መሪ ያለው ዋና


ልዩነት በመንፈሳዊው መሪ በኩል ያለው መጽሃፍ
ቅዱሳዊ መሰረትነት ነው:: የእግዚአብሄር ሰዎች
በቅዱሳን ጽሁፋት መንፈሳዊ መሪነትን ያሳዩናል::
በሙሴ ህይወት፦ መንፈሳዊ መሪነት በጥሪ ይጀምራል

እግዚአብሄር እርሱ ይመለከት ዘንድ እንደመጣ ባየ ጊዜ


እግዚአብሄር ከቁጥቋጦው ውስጥ እርሱን ጠርቶ፦ ሙሴ ሙሴ
ሆይ አለ። እርሱም፦ እነሆኝ አለ።
(ዘጸአት ፫፡፬)
ሙሴ፦ መንፈሳዊ መሪነት ከእግዚአብሄር የተሰጠ ራእይ ነው

አሁንም ና ህዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ


ታወጣ ዘንድ ወደ ፈርኦን እልክሃለሁ።
(ዘጸአት ፫፡፲)
ሙሴ፦ መንፈሳዊ መሪነት የእግዚአብሄር መንፈስ በመከተል ነው

“ሙሴም ሚስቱንና ልጆቹን ወሰደ በአህያ ላይም


አስቀመጣቸው ወደ ግብጽም አገር ተመለሰ
ሙሴም የእግዚአብሄርን በትር ይዞ ሄደ።”
(ዘጸዓት ፬፡፳)
ሴ፦ መንፈሳዊ መሪነት በሚያስችለው በእግዚአብሄር ነው
ሙሴ፦
ሚቻለው

እንግዲህ አሁን ሂድ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ


የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ አለው።
(ዘጸዓት ፬፡፲፪)
ሙሴ፦ መንፈሳዊ መሪነት ልእለ-ተፈጥሮአዊ /super-natural/
ከሆነ ስጦታ ጋር ነው

ከወንዙ ውሃን ውሰድ በደረቁም መሬት ላይ አፍስሰው


ከወንዙም የወሰድኸው ውሃ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል።
(ዘጸአት ፬፡፱)
ሙሴ፦ መንፈሳዊ መሪነት የእግዚአብሄርን ባህርይ ያሳያል

ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሠዎች ሁሉ ይልቅ


እጅግ ትሁት ሰው ነበረ።
(ዘሁልቁ ፲፪፡፫)
ተፈጥሯዊና መንፈሳዊ መሪ

ተፈጥሯዊ መንፈሳዊ
በራስ መተማመን በእግዚአብሄር መተማመን
ሰዎችን ያውቃል እግዚአብሄርንም ያውቃል
ውሳኔ በራሱ ፈቃድ ያደርጋል በእግዚአብሄር ፈቃድ ያደርጋል
የሃሳብ አለም ሰው አይቶ የሚንቀሳቀስ ሆኖም
ትሁት ነው
ተፈጥሯዊና መንፈሳዊ መሪ

ተፈጥሯዊ መንፈሳዊ
መንገዶችን በራሱ ያመቻቻል የእግዚአብሄርን መንገድ
ይከተላል
ሌሎችን ማዘዝ ያስደስተዋል እግዚአብሄርን በመታዘዝ ይመራል
በራሱ ግምት ይበረታታል እግዚአብሄርንና ህዝቡን ባለው
መውደድ ይበረታታል
በራሱ ይደገፋል በእግዚአብሄር ይደገፋል
መንፈሳዊ መሪነት በአጭሩ ሲቀመጥ

መንፈሳዊ መሪነት ከእግዚአብሄር ይመነጫል


መሪዎቹም በእርሱ ያድጋሉ። የመንፈሳዊ መሪነት
ልምምድ እግዚአብሄርን ማእከል ያደረገ ሆኖ
የመጨረሻ ግቡም እግዚአብሄርን ለማክበር ነው።
“መንፈሳዊ መሪዎች
እግዚአብሄር መሪያ
ቸው እንደሆነ ይረዳሉ።”

ሄንሪ እና ሪቻርድ ብላካቢይ


የአገልጋይ መሪነት
መግቢያ

“…እርሱ በእግዚአብሄር መልክ ሲኖር ሳለ


ከእግዚአብሄር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ
ነገር አልቆጠረውም ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ
በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ በምስሉም እንደ
ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ ለሞትም ይኸውም የመስቀል
ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
ፊልጵስዩስ ፪:፮-፰
የአገልጋይ መሪ ትርጉም

አገልጋይ መሪ ማለት ዝቅ ብሎ
በማገልገል ለመሪነት አርአያ የሚሆን ማለት
ነው።
ሮበርት ኬ ግሪንሊፍ
የአገልጋይ መሪነት ትርጉም

“ማንም ታላቅ ሊሆን ቢፈልግ የሁሉም አገልጋይ


ይሁን”
የናዝሬቱ ኢየሱስ
አገልጋይ መሪነት መጽሃፍ ቅዱሳዊ አርአያ
ዋናው መሰረት
“ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሄርም
እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሄርም እንዲሄድ አውቆ……”
(ዮሃንስ ፲፫፡፫)

ኢየሱስ የአገልጋይነት ሚናን ወሰደ ምንም ስጋት


አልነበረውምና
ዋናው ቀስቃሽ ምክንያት
“...በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ
መጨረሻ ወደዳቸው ።”
(ዮሃንስ ፲፫: ፩)

ኢየሱስ ለምን የደቀ መዛሙርትን እግሮች አጠበ?


ፍቅር
አርአያነቱ
“እራትም ሲበሉ...ከእራት ተነሳ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ
ወስዶ ታጠቀ በኋላም በመታጠቢያው ውሃ ጨመረ የደቀ
መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበት ማበሻ ጨርቅ
ሊያብስ ጀመረ።

(ዮሃንስ ፲፫፡፪ ፬ - ፭)
አርአያነቱ
እንዲህም አላቸው ፦ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን
እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ እግራችሁን
ትተጣተቡ ዘንድ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ
ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።
(ዮሃንስ ፲፫:፲፪ ፲፬ - ፲፭)
አርአያነቱ

• ኢየሱስ መምህርና ጌታ ነበረ


• በጊዜው አገልጋይ መሪነት የመሪነት አርአያ አልነበረም
• ተገቢ ስለሆነ ሳይሆን እንዲሁ ማገልገል
የፍቅር ብርታት
“ፍቅር ይታገሳል ቸርነትንም ያደርጋል ፍቅር አይቀናም ፍቅር
አይመካም አይታበይም የማይገባውን አያደርግም የራሱንም
አይፈልግም አይበሳጭም በደልን አይቆጥርም ከእውነት ጋር ደስ
ይለዋል እንጂ ስለ አመጻ ደስ አይለውም ሁሉን ይታገሳል ሁሉን
ያምናል ሁሉን ተስፋ ያደርጋል በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር
አይወድቅም....”
(ቆሮ ፲፫ ፡ ፬ - ፰)
የውውይት መድረክ

በአገልጋይ መሪነት የክርስቶስን ፍቅር ሙሉ ጉልበት


ለመገንዘብ እንዲረዳን ስለ ፍቅር ያነበብነውን
መልሰን በመድገም እናስተውለው።
 በ ፩ ቆሮ ፲፫ ፡ ፬ - ፰ ‘ፍቅር’ በሚለው ቦታ ‘ክርስቶስ’
የሚለውን በመተካት አንብብ/ቢ

 አሁንም በመድገም ‘ፍቅር’ በሚለው ቦታ ‘አገልጋይ መሪ’


የሚለውን በመተካት አንብብ/አንብቢ

 በመጨረሻም በ ‘ፍቅር’ ቦታ ‘ስምህን’ በመተካት ምን ያህል


ተግባራዊ እያደረግከው እንደሆነ አሰላስል።
የክርስቶስ ሃይል
“ክርስቶስ ይታገሳል ቸርነትንም ያደርጋል ክርስቶስ አይቀናም
ክርስቶስ አይመካም አይታበይም የማይገባውን አያደርግም
የራሱንም አይፈልግም አይበሳጭም በደልን አይቆጥርም ከእውነት
ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ አመጻ ደስ አይለውም ሁሉን ይታገሳል
ሁሉን ያምናል ሁሉን ተስፋ ያደርጋል በሁሉ ይጸናል። ክርስቶስ
ለዘወትር አይወድቅም....”
(ቆሮ ፲፫ ፡ ፬ - ፰)
የፍቅር ጉልበት
(በግል የማሰላሰል ጊዜ)

“(ስምህን አስገባ) ይታገሳል ቸርነትንም ያደርጋል (ስምህን አስገባ)


አይቀናም (ስምህን አስገባ) አይመካም አይታበይም የማይገባውን
አያደርግም የራሱንም አይፈልግም አይበሳጭም በደልን
አይቆጥርም ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ አመጻ ደስ
አይለውም ሁሉን ይታገሳል ሁሉን ያምናል ሁሉን ተስፋ ያደርጋል
በሁሉ ይጸናል። (ስምህን አስገባ) ለዘወትር አይወድቅም....”
(ቆሮ ፲፫ ፡ ፬ - ፰)
ለውጥ አምጪ መሪነት

መግቢያ

•አካባቢውን ትርጉም ባለው መልኩ የሚለውጥ


•ተከታዮቹን ወደ መሪነት የሚለውጥ ሃዋርያ
ነው።
መሪዎች የለውጥ
ሃዋርያቶች ናቸው

ኢየሱስ ፦ የመጨረሻውና ፍጹም የለውጥ ሃዋርያ


የተራራው ስብከት

• የተገላቢጦሽ (ግርምቢጥ) ፦ የነገሮች እንደምንጠብቃቸው አለመሆን


• ከፍተኛ የስነምግባር ልኬታ ማስቀመጡ
• ለውጥ በማይለወጠው እውነት የተመሰረተ መሆኑ
• የለውጥ ሃዋርያ ለመሆን ያለው ተግዳሮት
የውይይት መድረክ

የሚከተሉትን መጽሃፍ ቅዱሳዊ ገጸ-ባህርያትን መርምር


ኢየሱስ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ መሪነትን እንዴት ይሰራበት ነበር?

 ዘኪዎስ

ማቴዎስ

ጴጥሮስ
ማጠቃለያ

አገልጋይ ለውጥ አምጪ

እግዚአብሄርና
ቃሉ

መንፈሳዊ
እግዚአብሄር እውነተኛ መጽሃፍ ቅዱሳዊ መሪዎችን
ይፈልጋል። ታሪክን ለመለወጥም ይጠቀምባቸዋል።

You might also like