You are on page 1of 25

[Pick the date]

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማማከር


ብረት ብረትን እንደሚስል ሰውም ባልንጀራውን ይስላል
ምሳ 27፡ 17

አማኑኤል ኅብረት ነገረ መለኮት ኮሌጅ


]

መግቢያ፡-
በሰው ልጆች ላይ የስነ ልቦና ቀውስ የሚያስከትሉ ችግሮች በዚህ ምድር ላይ አሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት
በደርዘን የሚቆጠሩ (ምናልባትም በመቶዎች የሚቆጠሩ) የሳይኮቴራፒ ህክምና ዓይነቶች አሉ ። ብዙዎቹ
ተመሳሳይ ይዘት ያለው አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ ሁሉም የሰዎችን ችግር "ለማስተካከል" በታያቸው መንገድ
መፍትሄ የሚሉትን አሳብ ያቀርባሉ.፡፡ ነገር ግን ክርስቲያናዊ ማማከር ሰዎችን ለመርዳት በሚንቀሳቀስበት ሂደት
ከሁሉም በተለየ ሁኔታ ለመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ልዩ እይታን ይሰጣል።

መጽሐፍ ቅዱስ ከሁሉም መፍትሄ ተብለው ከሚሰጡ መመሪያዎች በላይ የሰዎችን ችግር መፍትሄ በመስጠት
የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ እንደሆነ ያምናል። ምክያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎች ሁሉ መሰረታዊ
ችግር መፍትሄ መስጠት የሚችል የእግዚአብሔር ቃል ነውና፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ዩጠራቸውን ሰዎች
በመንፈስ እየመራ እንዳጻፋቸው ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ስለ ክርስቲያናዊ ማማከር አገልግሎት ትርጓሜ እና
መመሪያዎችን ወይም ትምህርት ለመስጠት እንደ ዋና ምንጭ መጠቀም እጅግ አስፈላጊ ነው ።

1. ማማከር ምንድ ነው?

ከርእሱ ውስብስብነት የተነሳ አንድ ብቻ ትርጉም መስጠት ያስቸግራል፡፡ በመሆኑም ምሁራን የተለያየተ
ትርም ይሰጣሉ ፡፡ የተወሰኑትን እንመልከት

ሀ. የቃል በቃል ትርጉም /እንደ ዌብስተር መዝገበ-ቃላት/ ሥነ ልቦናዊ ዘዴን በመጠቀም የሰውን ፍላጎት
መገንዘብ እና ሥርዓት አዘል መልሰ መስጠት ነው ይላል፡፡

ለ. እንደ ጆን ስታንቶን እና ሪቻርድ ቡልትማን ደግሞ ሞደር ሳይኮትራፒስት በተሰኘ መጽሐፋቸው


የሚከተለውን ጽፈዋል፡፡

 መስዋዕትነት በመክፈል ተመካሪን ማጽናናት፣ ከፍርሃት፣ ከጥርጣሬ ነፃ በማድረግ መርዳት፡፡

 ስሜታዊ ባለመሆን ተገልጋይን ከሀዘን ማውጣት

 በልዩ ልዩ ጉዳይ ተሰፋ የቆረጠን ሰው የማበረታታት ተግባር

 መስዋዕትነት በመክፈል የተገልጋይን የውስጥ ጥያቄ ጠልቆ መረዳት እና መልሱን አብሮ የማፈላለግ
ተግባር ነው፡፡

ሐ. የሕይወት ቀውስ ለደረሰበት ክርስቲያንም ሆነ ዓለማዊ ሰው መልስ ለሚሹ ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት
እንዲችል እገዛ ማድረግ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ማማከር (Postoral Care) ይባላል፡፡

መ. መካሪ ተመካሪዊ ወደ ተፈለገው የሕይወት ድል እንዲደርስ በሕይወት ቀውሶች ላይ ምሪት


ለመስጠት ትግል የሚደረግበት መድረክ ነው፡፡
1
]

• አማካሪነት በቀውስ ውስጥ ላሉ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ወደ ማይፈልግ ችግር ውስጥ እንዳይገቡ


ለጤናማ ሰዎችም ጭምር የሚሰጥ አገልግሎት ነወ።

2. ክርስቲያን ማማከር መጽሐፍ ቅዱስዊ መሰረት

አንድ ጉዳይ በክርስቲያኖች ዘንድ ትከክል ሊሆን የሚችልበት ዋናው መለኪያ መጽሐፍ ቅዱስ ሲደግፈው ነው ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ማማከር በግልጽ ይነግረናል፡፡

1. እግዚአብሔር ግሩም አማካሪ ነው ፡-የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ዋነኛው እና ቀዳሚመው

አማካሪ እግዚአብሔር መሆኑን ከቃሉ በተደጋጋሚ ተዘግቦ ይገኛል፡፡ መዝ 66፡ 5 እግዚአብሔር በምክሩ
ግሩም ነው ፡፡
 የሰው አማካሪ ሰውየው ችግሩን እንዲነግረው እንዲሁም መፍትሄ ማፈላለጉ ላይ ተመካሪው እንዲሳተፍ

ይጋብዘዋል፡፡

 እግዚአብሔርን ሁሉን አዋቂ በመሆኑ የተመካሪውን ችግር ሳይጠይቅ ራሱ ይረዳል ከችግሩ ሊወጣ

የሚችልበትን ተመካሪውን ሳያሳትፍ ይምከረዋል፡፡

ምክሩም በውጤታማነቱ ተስተካካይ የሌለው ይሆናል፡፡

2. ክርስቶስ ድንቅ መካር በሚል ቃል ተጠራ

እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ “ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ” ተብሎ ተጠርቷል (ኢሳይያስ 9፡6)። ይህ ስም የተሰጠው

ኢየሱስ በምክር ውስጥ ያለውን ሚና ለማጉላት ነው፡፡

የኢየሱስ መካርነት እንዴት ይገለጻል

• እርሱ ድንቅ አማካሪ ነው

• ካለንበት ከምንም ችግር ነጻ እንድወጣ ይረዳናል

• እርሱን ሁላችን በምን ውስጥ እያለፍን እንደሆነ ይረዳል

• በሁሉ ሰዓት ብንፈልገው ልናገኘው እንችላልን

• ከማንም በላይ ይራራልናል

• ሚስጢራቸንን ይጠብቅልናል

ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስ ድንቅ ምክር ሊሰጥ የሚችልበትን እውነት ለማስረዳት በቆላስየስ መልእክቱ “

የተሰወረው የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና” (ቆላስይስ 2፡3) በማለት ያስታዋውቃል ።

አማካሪ እውቀት እና ጥበብ በሚገባ የታጠቀ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ክርስቶስ ከዚህ አንጻር ለማንኛውም ሰው ከበቂ በላይ

እውቀት እና ጥበብን የተሞላ መሆኑን ከክፍሉ እንገነዘባለን፡፡

2
]

3. የማማከር ስጦታ ለቤ ተክርስቲያን ተሰጠ ሮሜ 12

የማማከር አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ መሆኑን ለመረዳት የሚያስችለን ግልጽ ማስረጃ አለን፡፡

 አገልግሎቱ ልክ እንደ ወንጌል ሰባኪነት፣ አስተማሪነት ፣ መሪነት በስጦታ መልክ ለቤተ ክርስቲያን ተሰጠ፡፡

 ቤተ ክርስቲያን ይህን ስጦታ ችላ የምትል ከሆነ ቤተ ክተርስቲያን ወደ ውጭ የምትሰፋበትን ወደ ውስጥ

የምትበስልበት መሳሪያ ጥላለች ማለት ይቻላል፡፡ እግዚአብሔር ጸጋውን ሲሰጥ አስፈላጊ በመሆኑ እንደሆነ

ማመን ያስፈልጋል፡፡

 በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን እግዚአአብሔር የሚጠብቅባትን ሁለንተናዊ እድገት ታመጣ ዘንድ ይህን

አገልግሎት ማንሳት ተገቢ ነው

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ማማከር በስፋት የሚያነሳ ለሚያወሳ ሲሆን በመሆኑ ስለ ክርስቲያናዊ ማማከር የጠለቀ

ትምህርት ማግኘት ይቻላል፡፡

በምሳሌ መጽሐፍ እንጀምር

የምሳሌ መጽሐፍ በምክር የተሞላ መጽሐፍ ነው፣ መጽሐፉ የእግዚአብሔር ሕዝብ በዚህ ምድር አምላካዊ

ሕይወት ስለ መኖር እና በቀጣዩ ሕይወት ሽልማት ስለማግኘት ብዙ ምክርና መመሪያ ይሰጣል። በዚህ መጽሐፍ

ምክርን የሚቀበልን ሰው እንደ ባለ አእምሮ ሰው ይቆጥረዋል ምሴ 25 ፡ 5 ምክከር በሰው ልብ ውስጥ እንደ ጠሊቅ

ውሃ ነው አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል፡፡

 ምክር በድል ለመራመድ ቁልፍ ሚና እንዳለው መጽሐፉ ያስረዳል “በመልካም ስርዓት ሰልፍ ታደርጋለህ

ድልም ብዙ ምክር ባለበት ዘንድ ነው ” (ምሳሌ 24፡6)።

 የምሳሌ መጽሐፍ ጸሀፊ ምክር በሰው ሕይወት ላይ ያለውን በጎ ተጽእኖ ለማመላከት የተጠቀመበት ቃል

ሲሆን ምክርን የማይፈልግ ሰው ደግሞ ያለውጤት የሚባክን መና ሰውን ይመስላል፡፡ ምሳ 15፡ 22 ምክር

ከሌለች ዘንድ ደታሰባው ሳይሳካ ይቀራል ፡፡

 አስተዋይ የሆነ ሰው ደግሞ መልካም ምክርን ገንዘቡ እንደሚያደርግም ተጽፎፈልለናል ምሳ 1፡5

 ምክር መልካም ካልሆነ ወደ ጥፋት ሊያደርስ እንደሚችልም መጽሐፉ ጥቆማ ይሰጣል የአኪጦፌል ምክር

የዳዊትን መንግስት ለመገልበጥ አደገኛ ነበረች በሌላ ምክር መከነች እንጂ

አዲስ ኪዳን ስለ ክርስቲያናዊ ማማከር አገልግሎት ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን አስፈላጊነቱን ለመናገር አያቅማም
፡፡ የአገልግሎቱን ጽንሰ አሳብ ለመረዳት ፍቺ ቃሉ በአዲስ ኪዳን በተለያዩ አውድ ውስጥ እንዴት ጥቅም
ላይ እንደዋለ እንመለከታለን ፡፡ በመቀጠል አገልግሎቱ የሚሰጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ሙሉ
ሥዕላዊ መግለጫ ለማየት ብዙ ነጥቦችን በአንድ ላይ ማሰባሰብ እንችላለን።
3
]

ሀ. Gnome: ማወቅ

Gnome ቃሉ ክርስቲያናዊ ማማከርን ለመግለጽ በአዲስ ኪዳን ጥቅም ላይ ውሏል። ማወቅ፣ ማስተዋል፣
ማመዛዘን ወይም የታሰበውን ወይም የታወቀውን መረዳት ማለት ነው። በአሰራር ሂደት ውስጥ፣ አንድን ጉዳይ
ለመፍታት ምን መደረግ እንዳለበት የሚያሳይ እይታን፣ ፍርድን ወይም አስተያየትን ያመለክታል። በእውቀት
ውጤት የሚያመጣ ነገር ማድረግ የሚቻልበትን ጥበብ ያመላክታል ።

ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ ላይ “በዚያም ሦስት ወር ተቀምጦ ወደ ሶርያ በመርከብ ሊሄድ ባሰበ ጊዜ አይሁድም ሴራ
ስላደረጉበት በመቄዶንያ በኩል ይመለስ ዘንድ ወሰነ” (ሐዋ.20፡ 3) የሚለውን ቃል ተጠቅሟል። ጳውሎስ
መፈጸም ያለበትን ሥራ እንዲያጠናቅቅ ከአሳዳጆቹ ያመለጠበትን መንገድ የእውቀት መንገድ ነው፡፡

ለ. Boule ቡሌ፡ ምክር ወይም እቅድ

Boule ቡሌ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቲያናዊ ማማከር ስለመግለጽ የሚያስተምር ሌላ ቃል ነው። ቡሌ


ውጤት የሚያስገኝ የእርምጃን ሂደት ለመወሰን ይጠቅማል፡፡ ማለትም ምክር ጉዳይን በአዎንታዊ ሁኔታ
ለመፍታት ያስችላል።

• ቃሉ ምክር ከእግዚአብሔርም ከሰውም አንጻር ያለውን ጥቅም ለመግለጽ ውሏል፡፡ የእግዚአብሔር ምክር
(ሉቃስ 7: 30 ፤ የሐዋርያት ሥራ 2: 23፤ 4: 28፤ 13: 36፤ 20: 27፤ ኤፌሶን 1: 11፤ ዕብራውያን 6:17)

• እንዲሁም ሰዎች ያደረጉትን ምክር (የሐዋርያት ሥራ 27:12, 42፤ 1 ኛ ቆሮንቶስ 4:5) ለመግለጽ ጥቅም
ላይ ውሏል፡፡

• በሐዋርያት ሥራ ላይ በተገለጠው የአጠቃቀም ምሳሌ “የወታደሩም እቅድ (ቡሌ) እስረኞችን መግደል


ነበር ከእነርሱም አንዳቸውም ዋኝተው እንዳያመልጡ ነበር” (ሐዋ. 27፡42)። በዚህ ክፍል እንደምናነበው
የተግባር እቅድ ለማውጣት በጋራ ምክክር አድርገዋል።

ሐ. Paraklesis ጰራቅሊዝስ፡ ለአንድ ወገን ጥብቅና መቆም

ጰራቅሊዝስ ክርስቲያናዊ ምክርን በመለገስ ለማጽናናት፣ ለማበረታታት፣ ለማረጋጋት ወይም ለመምከር ወደ ጎን


መደወል ማለት ነው። ህጋዊ ወኪል ሆኖ መርዳት ወይም እርዳታን ለአንድ ሰው ለመስጥት መሟገት ማለት ነው
(1 ኛ ዮሐንስ 2፡1)።

• ቃሉን ሐዋርያው ዮሐንስ መንፈስ ቅዱስን እንደ አጽናኝ ወይም ረዳት ለመግለጽ ተጠቅሞበታል (ዮሐንስ
14፡16፣ 26፤ 15፡ 26፤ 16፡7)።

• ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “በእምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲያበረታታችሁ ወንድማችንንና


ከእግዚአብሔር በክርስቶስ ወንጌል ከእኛ ጋር አብሮ የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክን...ስለዚህም ወንድሞች
ሆይ በመከራችን ሁሉ ተጽናናን። (parakaleo) በእምነት ስለ እናንተ…ስለዚህ በዚህ ቃል እርስ በርሳችሁ
ተጽናኑ ( 1 ኛ ተሰ 1፡3-6 ፤ 2፡7)።

መ. Phroneo: በትከክል ማሰብ


4
]

• ፎሮንዮ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክርስቲያናዊ ማማከር ፍቺ የሚሰጠውን ትምህርት የበለጠ ይገልጻል።


ፎርዮን የሚለው ቃቀል ማሰብ ማለት ሲሆን ምክንያታዊ ያልሆነ አስተያየት በማስወገድ ሞራላዊ ጉዳዮች
ላይ በጥንቃቄ የማሰላሰል ሀሳብ አለው።

• ጳውሎስ በዚህ መንገድ ቃሉን ተጠቅሞበታል፡- “እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉ
(ፍሮንዮስ) እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ (ሮሜ 8፡5፤ ቁጥር 6፣7)። እንደ
እግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖር ከቃሉ ምክርን የሚሰጡ አገልጋዮችን ማግኘት ያስፈልጋል፡፡

ሠ. Nouthesia: ወደ አእምሮ ማስገባት

ኑቴዝያ መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያናዊ ምክርን የሚሰጠውን ትምህርት ለመረዳት ቁልፍ ቃል ነው (ቲቶ 1:11፤ 3:10፤
ኤፌሶን 6:4፤ 1 ቆሮንቶስ 4:14፤ 10:11፤ የሐዋርያት ሥራ 20: 31፤ ቆላስይስ 1: 28፤ 3:16፤ 1 ኛ ተሰሎንቄ 5: 12,
14፤ 2 ኛ ተሰሎንቄ 3:15፤ ሮሜ 15:14 )፡፡

• ኑቴዝያ ከዲዳስኮ (ማስተማር) ጋር ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል። ኑቴሲያ ሁለት ቃላት በአንድ ላይ የያዘ
ነው፡፡ ኑቴ (አእምሮ) እና ዝያ (ማስቀመጥ)። ሲሆን በጥሬው ትርጉሙ “በአእምሮ ውስጥ ማስገባት” ማለት
ነው።

• ቃሉ ለምእመናን ለማስራዳት በዐውደ-ጽሑፍ ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል (ቆላስይስ 3፡16)፣

• እንደ የተለየ የአገልጋዮች ተግባር ተጠቅሷል (ቆላስይስ 1፡28)።

• ኑቴሲያ በግለሰቦች ዘንድ ግቡ አእምሮን ማደስ ፣ ፈቃድን መማረክ ፣ በሚያስችል እውቀት በመለገስ
የባህርይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ተፅእኖ ማሳደር ማለት ነው። እንዲሁም በመመሪያ እና ስልጠና ላይ
በተመሰረተ ሂደት የተሳሳቱ እይታዎችን ማጥራት ነው።

3. የማማከር አገልግሎት ምሳሌ ከመጽሐፍ ቅዱስ

ማማከር በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳንም (በመጽሐፍ ቅዱስ) በስፋት ጥቅም ውሎ እንገኛለን

ሀ. ማማከር በብሉይ ኪዳን

ስለማማከር የሚገለፁ ብዙ ክፍሎች በብሉይ ኪዳን ተጠቅሰዋል፡፡

 እግዚአብሔር አዳምን አማከረ ዘፍ 2፡17

 ሰይጣን አዳምና ሔዋንን ዘፍ 3፡15

 አብርሃም ሎጥን ዘፍ 13፡59

 የሙሴ አማት /ዮቶር/ ሙሴን ዘፀ 18፡17-19

 ናታን ዳዊትን 2 ሳሙ 12፡1-15


5
]

 ኢሳያስ ንጉስ ሕዝቅያስን 2 ነገ 18፡17 19፡37

 ዳንኤል ናቡ ከደነጾርን ዳን 2፡56

 ማማከር በመጽሐፍ ምሳሌ 11፡14 12፡15 13፡10 15፡22

ለ. ማማከር በአዲስ ኪዳን

አዴስ ኪዳንም የማማከር አገልግሎት እንደተሠተ ጥሩ ምሳሌዎች ይሰጠናል

 ክርስቶስ ኒቆዲሞስን ዮሐ 3፡18

 ክርስቶሳዊ ሳምራዊቷን ዮሐ 4

 ጳውሎስ ሽማግሌዎችን ሐዋ 20፡ 28-30

 ጳውሎስ ጢሞቲዎችን እንዲጠነቀቅ 1 ኛጢሞ 4፡12-16

4. የክርስቲያን ማማከር አገልግሎት እንዴት ተጀመረ?


የክርስቲያን የማማከር አገልግሎት ተግባር መሠረቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ውስጥ ነው ፡፡ የመጽሐፍ
ቅዱስ የማማከር አገልግሎት መሥራች የሆኑት ጄይ ኢ አዳምስ የአእምሮ ጤና ሁኔታዎችን ፣ የግንኙነት /
ማስተካከያ ጉዳዮችን ፣ የስሜት መቃወስ ፣ የፍላጎት መቃወስ ፣ የበደል ትራኦማ ፣ አደገኛ ሱስ ፣ ወዘተ
ለማከም የክርሰትና እምነት ላይ የተመሠረተ ውይይቶችን አካሂደዋል ፡፡

ይህ አካሄድ በወቅቱ በጣም ተወዳጅ ከሆኑት የሕክምና አቀራረቦች ስለሚለይ በጣም አወዛጋቢ ነበር እና
ብርቱ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ነገር ግን እ.ኤ.አ. በ 1960 ዎቹ መገባደጃ እና በ 1970 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ይህ
አዲስ የማማከር አገልግሎቱ ተጀመረ። አገልግሎቱ ከተጀመረ በኋላ ለክርስቲያኖች እና በሕክምናው ሂደት
ውስጥ እምነታቸውን ለማካተት ከሚፈልጉት በጣም ታዋቂ የሕክምና አማራጮች አንዱ ለመሆን በቃ ፡፡

የክርስቲያን የማማከር አገልግሎት ተግባር መሠረቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ውስጥ ነው ፡፡ የመጽሐፍ

ቅዱስ የማማከር እንቅስቃሴ መሥራች የሆኑት ጄይ ኢ አዳምስ የአእምሮ ጤና ሁኔታዎችን ፣

የግንኙነት / ማስተካከያ ጉዳዮችን ፣ የስሜት መቃወስ ፣ የፍላጎት መቃወስ ፣ የበደል ትራኦማ ፣ አደገኛ

ሱስ ፣ ወዘተ ለማከም የክርሰትና እምነት ላይ የተመሠረተ ውይይቶችን አካሂደዋል ፡፡

ይህ አካሄድ በወቅቱ በጣም ተወዳጅ ከሆኑት የሕክምና አቀራረቦች ስለሚለይ በጣም አወዛጋቢ ነበር እና

ብርቱ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ነገር ግን እ.ኤ.አ. በ 1960 ዎቹ መገባደጃ እና በ 1970 ዎቹ መጀመሪያ ላይ

ይህ አዲስ የማማከር አገልግሎቱ ተጀመረ። አገልግሎቱ ከተጀመረ በኋላ ለክርስቲያኖች እና በሕክምናው

ሂደት ውስጥ እምነታቸውን ለማካተት ከሚፈልጉት በጣም ታዋቂ የሕክምና አማራጮች አንዱ ለመሆን

በቃ ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1968 የክርስቲያን ማማከር ትምህርታዊ ፋውንዴሽን በእምነት ላይ የተመሠረተ

6
]

የህክምና ዘዴን የሚፈልጉ ሰዎችን በትክክል እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ለክርስቲያን አማካሪዎችን

መመሪያ ለመስጠት ተመሠረተ ፡፡

የክርሰቲያን አማካሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ እሴቶችን እና እምነቶችን ማክበር ብቻ ሳይሆን

መመሪያዎችን እና ሥነ-ምግባራዊ ደንቦችን መከተል እንዳለባቸው ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ

ነው ፡፡

5. ክርስቲያናዊ ማማከር አስፈላጊነቱ ለምንድ ነው?

ከላይ እንደተጠቀሰው የክርስቲያን አማካሪዎች የተለያዩ ጉዳዮችን ያስተናግዳሉ፤ የደንበኞች ሕይወት

ከማስተካከል እስከ የአእምሮ ሕመሞችን በተገቢው ሁኔታ እንዲያገግሙ ማገዝ ድረስ ሰፋ ያሉ ግቦችን

ያካትታል፡፡

የማማከር አገልግሎት በጣም የተለመዱ ጉዳዮች እና ግቦች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

ሀ. የጋብቻ ችግሮችን መፍታት

ክርስቲያናዊ የማመከር አገልግሎት በጋብቻ ላይ ትልቅ ዋጋ ይሰጣል ፡፡ ጥንዶች ወደ ትዳር ሲገቡ ለሕይወታቸው

ዘመናቸው ሁሉ ለመፋቀር እና ለመከባበር ቃልኪዳን እየገቡ ነው ፡፡ ነገር ግን ሁል ጊዘዜ እንከን አልባ ግንኙነተረ

አይኖራቸውም፡፡ ችግር በሚፈጠር ጊዜ አብሮ እንዴት መቀጠል እዲችሉ ያስባሉ እንጂ ስለ መፋታት አያስቡም፡፡

በክርስትና እምነት ፍቺ እንደ አማራጭ አይታይም፡፡ ስለሆነም ባለትዳሮች በትዳራቸው ላይ ተስፋ ከመቁረጥ

ይልቅ በጋብቻ ማማከር ውስጥ ማንኛውንም ችግሮች በጋራ እንዲሠሩ ይበረታታሉ ፡፡

እውነታው ግን በትዳር ውስጥ ብዙ ችግሮች ሊከሰቱ መቻላቸው እውነት ነው ፡፡ የተፈጠሩት ችግሮች

በጥንዶች ግንኙነቱ ላይ ከባድ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ ፡፡ አንዳንድ የተለመዱ የጋብቻ ጉዳዮች ታማኝነትን

ማጉደል፣ የመግባባትን ችግሮች ፣የጠበቀ ወዳጅነት ማጣት፣ ሱስ እና መደበኛ ግጭቶች ይጠቀሳሉ፡፡ የክርስቲያን

ማማከር ዓላማ ጥንዶች የተበላሸ ግንኙነታቸውን እንዲያስተካክሉ ለመርዳት ነው ፡፡

ለ. የወላጅነት ፈታኝ ሁኔታዎችን መቋቋም

ልጆችን ማሳደግ ቀላል አይደለም ፡፡ እንደ ወላጅ ብዙ ውጣ ውረዶች ፣ ደስታዎች እና ብስጭት ያጋጥማል ያ

መደበኛ ዬተሰብ ሕይወት ነው። በእርግጥ ልጅን ማሳደግ እጅግ ፈታኝ የሆነባቸው ጊዜያት ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

እሱ / እሷ በወላጅነት ሚናቸው ላይ ክፉኛ የሚያማርር ጉዳይ ሊገጥማቸው ይችላል። ሆኖም የወላጅነት ሚና

መወጣት ለማንም የማይተው የወላጅ ኃላፊነትን መሆኑን ተደርቶ ችግሩን ለማሸነፍ የማማከር አገልግሎት

ጠቀሜታው እጅግ ክፍ ያለ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ልጅዎ የሚያስፈልገውን ለመለየት በማይችሉበት ጊዜ ወይም

ከወላጅነት ጋር ተያይዘው በሚሰጡት ኃላፊነቶች ከተጨነቁ ክርስቲያናዊ ምክር በጣም ጠቃሚ ነው ፡፡

አማካሪዎች የወላጅነት ጭንቀቶችን ለመቋቋም የሚረዱዎ ቴክኒኮችን ሊያስተምሯችሁ ይችላሉ ፡፡


7
]

ሐ. ለአእምሮ ጤና ድጋፍ መስጠት

የአእምሮ ህመም መኖሩ ከባድ ነው ነገር ግን ሊድን የማይችል ቁጣ አይደለም ። ጥሩ አስታማሚ ከተገኘ እንደ

ማንኛውም በሽታ ሊታከም ይችላል፡፡ የማማከር አገልግሎት የአእምሮ ህመም ላለባቸው ሰዎች ድጋፋቸውን

በመስጠት እና ጤናቸው ሊሻሻል የሚችሉበት ዕድል በመስጠት ይረዳል ፡፡

በአእምሮ ሕመም የሚሠቃዩ ሰዎች ድብርት፣ ሁከት፣ ከአሰቃቂ የጭንቀት በሽታ ወይም ከመጠን በላይ የመረበሽ

ዲስኦርደር ይታይባቸዋል፡፡ እንዲሁም ብዙውን ጊዜ የአእምሮ ሕመም ያለባቸው ከሌላቸው ሰዎች ዝቅተኛ

የሆነ የራስ ግምት እና ራስን ያለ መቀበል ስሜት እንዳላቸው መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡ በክርስቲያን

ማመከር አገልግሎት አማካኝነት የእግዚአብሔር ልጅ መሆናቸውን እንዴት መቀበል እንደሚችሉ ይማራሉ ፣

እንደ ማንኛውም ሰው ለራሳቸው ከፍ ያለ ግምት እንዲሠጡ ማበረታታት ይቻላል ፡፡

ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያለውን ሰው ሁሉ ከመንፈስ ጋር ማስተያየት አቋማ ከጸሎት ጋር የማማከር አገልግሎት

መስጠት ይገባታል፡፡

መ. ከሐዘን እና ኪሳራ ለማገገም

የምትወደው ሰው ሞት በጣም አሳዛኝ ነው ፣ እናም የሀዘኑ ጊዜ ማለቂያ የሌለው ሊመስል ይችላል። ነገር ግን

ለብዙዎች በዚህ የሀዘን ጊዜ ውስጥ ጤንነታቸውን ጠብቀው እንዲያልፉ በክርስትና እምነታቸው ላይ በጣም

የሚደገፉበት ጊዜ ነው ፡፡ ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ ሀዘኑ የእግዚአብሔርን ብርሃን ለማግኘት በጣም ሊከብድ

ይችላል ፡፡

በሕይወት የተረፈው ሰው በሀዘን ወቅት - ያለፈውን ለመርሳት የማይቻል ሆኖ ተሰምቶት በከፋ ሀዘን ውስጥ

“ተጣብቆ” ሊገኝ ይችላል፡፡ በእነዚህ አጋጣሚዎች ፣ የክርስቲያን የማማከር አገልግሎት በሐዘን የተጎዱ ሰዎች

እውነታውን እንዲቀበሉ እና ከህመሙ እንዲድኑ ይረዳቸዋል ፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በንግድ ወይም በሌላ ለትርፍ እየሰሩ ያሉ ሰዎች ኪሳራ ሊገጥማች ይችላል፡፡ ከኪሳራው በላይ

ኪሳራው ካስከተለባቸው ጉዳት በላይ ኪሳራው እንደገና መነሳት እንደማችሉ በማሳመን ውስጣቸውን ክፉኛ

ሊሰብረው ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚእሔርን ማመን ላይ የሚመሰረተው የክርስቲያን ማመከር አገልግሎት

ካሉበት እንዲወጡና ሁሉን እንደ አዲስ እንዲጀምሩ ብርታትን በማጎናጸፍ ያግዛል፡፡

ሠ. ከዕፅ ሱሰኝነት ነጻ ማውጣት

ለሱሰኞች እርዳታ መፈለግ ድፍረትን ይጠይቃል ፡፡ ነገር ግን በአደገኛ ዕፅ ፣ በአልኮል እና / ወይም በቁማር ችግር

እንዳለብን አምኖ መቀበል አብዛኛውን ጊዜ ሕይወትን ለመለወጥ የሚፈልጉትን እርዳታ ለመቀበል የመጀመሪያ

እርምጃ ነው ፡፡ አንዴ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ከተቀበሉ አንድ ክርስቲያን አማካሪ “ልማድ”ን ወይም ክፉ

8
]

ሱሰስን ለመተው የሚያስፈልግ ድጋፍ ሊሰጥ ይችላል። በተጨማሪም ፣ የክርስቲያን የማመከር አገልግሎት

በልጅነት አሰቃቂ ወሲባዊ ፣ አካላዊ ፣ ወይም ስሜታዊ ጥቃቶች ለማገገም ያግዛል፡፡

በክርስቲያን የማማከር አገልግሎት ወቅት ፣ ሰዎች በእግዚአብሔር ዓይኖች ውስጥ ምን ያህል አስፈላጊ እና ዋጋ

እንዳላችሁ ይማራሉ ፡፡ እንዲሁም ከእግዚአብሔር በሚገኛ ጸጋ ሱስን ለማሸነፍ የሚያስችል ጥንካሬ

እንደሚያገኙ ይገነዘባሉ ፡፡ በተጨማሪም የክርስቲያን አማካሪዎች ሱሰኞች ከመጠን በላይ ሱሳቸው

ሲያሰቃያቸውና መቋቋም ሲቅታቸው በጸሎት ይረዱዋቸውል፡፡

ረ. እምነትን ማጠናከር እና ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ለማሻሻል

የዛሬው ዘመን የሰው ሕይወት ፍጥነት ባለው እንቅስቃሴ የተሞላን ፣ በቁሳዊ ነገሮች ፍላጎት የተያዘን እንድንሆን

ለማስገደድ ይሞክራል፡፡ ይህ ቅጥ ያጣ ዓለም ከእግዚአብሔር በብዙ ሺህ ማይሎች የራቀ ሲሆን እኛም

ከአምላካችን ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳይኖረን ለመጎተት ይታገላል፡፡ በዚህ ዓለም ውስጥ እምነትን መዘንጋት እና

በሕይወት ዕለታዊ ጫና ውስጥ “መዋጥ” ቀላል ነው። በእነዚህ ሁሉ ጭንቀቶች እምነት ወደ ጎን ሊገፋ ይችላል፡፡

ሆኖም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እምነታችን የሚፈለግበት ጊዜ እነዚህ ከፍተኛ ጫናዎች በሚበዙበት ወቅት

ነው፡፡ ክርስቲያን አማካሪዎች እነዚህን ተግዳሮቶች ተገንዝበው በመንፈሳዊ ጤንነት ከእግዚአብሔር ጋር

እንድንጓዝ ሊረዱን ይችላሉ ፡፡

መንፈሳዊ ጤንነት ምንድነው?

መንፈሳዊ ጤንነት ከእግዚአብሔር ጋር ያለ እውነተኛና መንፈሳዊ ግንኙነት ነው፡፡ ይህ ግንኙነት ከሃይማኖታዊ

ስርዓት ልምምድ መፈጸም በላይ ነው ፡፡ ዛሬ በጣም ብዙ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ጤንነታቸው ተናግቶ እናዳሉ

በግልጽ ይታያል፡፡ ነገር ግን የሃይማኖት ስርዓት መፈጸም ላይ አይታጡም፡፡ በእውነቱ መንፈሳዊነት ከከፍተኛው

ኃይል ካለው ማንነት ጋር ጥልቅ ግንኙነትንም ያካትታል ፡፡ እውነተኛ አምላኪነት ውስጥ ከራስ የበለጠ ትልቅ እና

የተሻለ ነገር እንዳለ በመረዳት ያስፈልጋል፡፡

ያ የምናመልከው አምላክ በምድር ላይ እየተከናወነ ያለውን ነገር የሚያስተዳድር እና / ወይም የሚቆጣጠር

መሆኑን በእርግጠኛነት መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ መንፈሳዊነትን በአስተምህሮ የተዋቀረ ሲሆን መገለጫውም

እምነት ፣ ሥነ ምግባር ፣ እሴቶች እና መርሆዎች ናቸው ፡፡ በመሆኑም ስርዓትን በመፈጸም ብቻ ሳይሆን ለእርሱ

በሙሉ በመገዛት ከእርሱ ጋር በመኖር መንፈሳዊነት መጠበቅ ይገባል፡፡

መንፈሳዊ ለመሆን የአጥቢያ አባል መሆን አስፈላጊ ቢሆንም አጥቢያ በሌለበት ስፍራ መንፈሳዊ መሆን

እንደሚቻል መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡ እርሱ በሁሉ ስፍራ ልናገኘው የምንችል ሉዓላዊ አምላክ በመሆኑ

ሰበብ ሳንፈጥር ሕይወትን ለእርሱ መስጠት መለማድ ወደ መልካም መንፈሳዊ ጤንነት ይመራናል፡፡

መንፈሳዊ ጤንነት ብዙውን ጊዜ በሚከተሉት ይገለጻል-


9
]

• ሌሎችን የመውደድ አቅም እና ከሌሎች ፍቅርን የመቀበል ችሎታ

• ይቅር ባይነት

• ለማኅበረሰብ አገልግሎት ቁርጠኝነት

• በግል መንፈሳዊነት ሕይወት እርካታ

• የርህራሄ ልብ

• ሌሎችን የመንከባከብ ችሎታ - በምላሹ አንድ ነገር ሳይጠብቁ

• ደስታን የማጣጣም እና ደስታን የማስፋፋት ችሎታ

• ራስን መንከባከብን ችሎታ

• ሚዛን የጠበቀ መንፈሳዊ ልምምድ

6. የቤተ ክርስቲያናዊ አማካሪነት አገልግሎት ዓላማ

ቤተ ክርስቲያን ከተለያየ ማሕበረሰብ የሚመጡ ሰዎች በአንድነት አምላካቸውን የሚያመልኩ እና ማሕበራዊነት

የሚጋሩ ናቸው፡፡ ከየትኛውም ስፍራ ከተለያየ ስፍራ የመጡ ነገር አብሮ መኖር የሚጠበቅበት ማኅበረሰብ

ስብስብ ያለበት ናት፡፡ ከተለያየ ስፍራ የመጡ ሰዎች አብረው ሲኖሩ ሊከሰት የሚችል ማኅበራዊ ቀውስ ቀላል

አይሆንም፡፡ እንዲሁም እያንዳንዱ ክርስቲያን በዚህ ዓለም ሲኖር የተለያየ ፈተና ይገጥመዋል፡፡ በተጨማሪም

ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላልመቱ ሰዎችም ቤተ ክረስቲያን እንደ ሕክምና መሰጫ ማእከል አገልግሎት

መስጠት ይገባታል፡፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን የማመከር አገልግትን በአግባቡ ልጥጠቀም ይገባታል፡፡

አገልግሎቱ በርካታ ዓላማ ሲኖሩት የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው

 የቤተ ክርስቲያናዊ አማካሪነት ዓላማ ቅዱሳን ለእግዚአብሔርና ለሌሎች ሰዎች ያላቸው ፍቅር

እንዲጨምር ማድረግ ነው፡፡ ሉቃ 10፡27

 የክርስቲያን አማካሪዎች ዓላማ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ማንኛቸውም ጉዳዮችን በተሻለ ሁኔታ

እንዲያስተዳድሩ እና / ወይም ችግሮችን እንዲፈቱ በእምነት ላይ የተመሰረቱ መርሆዎችን እና ሥነ-

ልቦናዊ መመሪያዎችን መጠቀም ነው ፡፡

 እንደማንኛውም የአእምሮ ጤና ባለሙያ የአእምሮ ሕመሞችን መገምገም ፣ መመርመር እና ማከም

ብቻ ሳይሆን ደንበኞችም ተግዳሮቶቻቸውን መቋቋም የሚችሉበትን መንገድ ከቅዱስ ቃሉ

ያስተምራሉ፡፡

 ስለዚህ አማኞች በሕይወታቸው ውስጥ ሊከሰቱ ከሚችሉ ማናቸውም ለውጦች ጋር ቶሎ በመላመድ

በተሻለ ሁኔታ ሕይወታቸውን ማስተካከል ይችላሉ ፡፡


የማማከር አገልግሎት ዓላማና ግብ
10
]

ሰዎች ምክርን በመፈለግ ወደ አማካሪ ለምን ይመጣሉ ? አማካሪስ በማማከር አገልግሎት ተሳትፎ
ሲያደርግ የመጨረሻ ግብ ሊያደርግ የሚገባው ምንድ ነው?
1. የእግዚአብሔርን ሐሳብ ከግብ ለማድረስ ነው፡፡ ይህም ሰዎች በክርስቶስ እውቀት አድገው ወደ ዘላለማዊ
ደህንነት መድረሳቸው ነው፡፡
2. የሰዎችን ችግር ማቃለልና ደስታ መፍጠር
 ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ለጥያቄው መፍትሔ አገኘ፡፡ ሐዋ 8
 የሳምራዊቱ ሴት ለጥያቄዋ መፍትሔ አገኘች፡፡ ዩሐ 4
a. ራሳቸውን እንዲረዱ መርዳት (Self Understanding)
በፈውስ ሂደት ውስጥ ራስን መርዳት በቅድሚ ሊተኮርበት የሚገባው እርምጃ ነው፡፡ የችግሮች መንስዔ
በአብዛኛው የሚመነጨው የራስን ማንነት ካለመረዳት ነው፡፡ አንድ ሰው (ግለሰብ) በውስጡ
1. ከእውነተኛው አመለካከት የራቀ ሀሳብ (Based Perspective)
2. ጎጂ የሆኑ አዝማሚያና (ሌላውን)
3. ራስን አውዳሚ ዝንባሌ ሊኖረው ይችላል
 እንደ እኔ ያለ መልከመልካም ሴት ትዳር ያጣል ብላችሁ ነው፡፡
b. ግንኙነት ማድረግ እንዲችሉ መቻል (Communication)
የብዙ ችግሮች መንስዔ በተለያዩ አቅጣጫዎች ትክክለኛ ግንኙነት ማድረግ ባለመቻል ላይ ያረፈ ነው፡፡
ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ፡፡ እነርሱም ግንኙነት ማድረግ የማይችሉና ለግንኙነት ፈቃደኛ ያልሆኑ ናቸው፡፡
እነዚህም ሰዎች ያላቸውን፡-
 ስሜት
 ሐሳብና
 ዝንባሌ በትክክል ማስተላለፍ የማይችሉ ወይም ፍቃደኛ የማይሆኑ ናቸው፡፡
c. መማከርና የባህሪ ለውጥ ማድረግ
ማንኛውን ተመካሪ ለመማርና ባገኘውም እውነት እራስን በመለወጥ ለመቅረጽ ፍቃደኛ መሆን
ይኖርበታል፡፡ አንድ የትዳር ጓደኛ ለማጨት ፍርሃት ያለበትን ወጣት እንዴት ትመክረዋለህ /ታማክረዋለህ/?
d. ገቢራዊነትን ማስወገድ
ከእውነት በራቅ አመለካከቶች ምክንያት አንዳንድ ክርስቲያኖች በስሜታቸው በሃሳባቸውና ዝንባሌያቸው
ገቢራዊ ናቸው፡፡ ተግባራዊ ማለት በአሉታዊ ትርጉሙ በውጫዊ ሀይል መንቀሳቀስ ሁል ጊዜ ቀስቃሽ
ኃይል መፈለግ በራስ አለመነሳሳት ማለት ነው፡፡ ስለሆነም የማማከር ግብ ተመካሪን ከገቢርነት ወደ
ተግባራዊነት (From Passiveness to self actualization) መለወጥ ነው፡፡ ፊሊ 2፡13 ዩሐ 16፡13 በተሳሳተ
መንገድ ይተረጎሙና ገቢራዊ የሚሆኑ ክርስቲያኖች አሉ፡፡
e. መንፈሳዊ ክፍተትን መሙላት
ማንኛውም አማኝ ፍጹም እስካልሆነ ድረስ ላሉበት ችግሮች መፍትሔ ለማግኘት ምክር ይፈልጋል፡፡
ምሳሌ 20፡5
7. የማማከር ዓይነቶች
11
]

 ባጠቃላይ ደረጃ ማማከር ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ እነሱም ዓለማዊና መንፈሳዊ (ቤተ ክርስቲያናዊ)
አማካሪነት ተብለው ይጠራሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማማከር እና ዓለማዊ ማማከር ልዩነት እና አንድነት ፡፡

ክርስቲያናዊ የማማከር አገልግሎት ከዓለማዊ ማማከር ሕክምና ጋር ልዩነት እና ተመሳሳይነት ምንድናቸው?

እንደ አጠቃላይ የክርስቲያንም ሆነ ዓለማዊ የማማከር አገልግሎት ሰዎች ችግሮቻቸውን በማሸነፍ ፣

በሕይወት ውስጥ ትርጉም እና ደስታ እንዲያገኙ ፣ በአእምሮም ሆነ በስሜታዊ ጤናማ እና የተስተካከሉ

ግለሰቦች እንዲሆኑ ለመርዳት በመሆኑ ተመሳሳይ ፍላጎት አላቸው ፡፡

 “ማማከር ” የሚለው ቃል በሕይወቱ ችግር ለገጠመው ሰው ምክርና ማበረታቻ መስጠት ፣

ጥበብን እና ክህሎቶችን ማካፈል ፣ ግቦችን ማሳካት፣ ግጭትን መፍታት ፣ ወዘተ ብዙ

ትርጉሞች ሊኖረው ይችላል፡፡

 ዓለማዊ አማካሪዎች ብዙውን ጊዜ ያለፈው ጊዜ በልጅነት ዕድሜ የተከሰተ ክስተትን ይመረምሩና

የአሁኑኑ ለመጠገን ይሻሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የፊዚዮሎጂ ችግር ሊያስከትል የሚችሉ የአካል እና

የኬሚካል መዛባት ተጽዕኖዎችን ይመረምራሉ ፡፡

ምንም እንኳን በማማከር ሥራዎች ውስጥ ክርስቲያን አማካሪዎች ብዙውን ጊዜ ከዓለማዊ ሥነ-ልቦና

እና ከአማካሪነት መርህ የተወሰኑ ክህሎቶችን የሚጠቀሙ ቢሆንም ከዓለማውያን ለየት ያሉ ናቸው ።

የሚለዪበት አንዱ ነጥቦች አሉ፡፡

o ክርስቲያናዊ ማማከር በተለየ ሁኔታ መንፈሳዊ ልኬትን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ በመመስረት

በአንድ ግለሰብ ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈለግን ያካተተ ነው ፡፡

o የክርስቲያን አማካሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰው ፣ ስለ ተፈጥሮ ፣ ስለ ጋብቻ እና ስለ ቤተሰብ ፣

ስለ ሰዎች ስቃይ እና ስለሌሎች ጉዳዮች ተግባራዊ የጥበብ ምላሽ እንዳለው ይገነዘባሉ ፡፡

o በማማከር አገልግሎት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ፅንሰ-ሀሳቦችን በመጠቀም መመሪያ እና ተጠያቂነት

ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ “ምስክርህም ተድላዬ ነው፥ ሥርዓትህም መካሬ ነው። ”( መዝሙር 119፥24 )“

ምስክርነትህ ለእኔ ደስታዩ ነው መካሪም ነው ” ይላል ፡፡

1. የራስን ጥቅም አለማሰቀደም :-_ ክርስቲያናዊ አማካሪነት ከራስ ጥቅም በላይ ለደንበኞቻቸው ጥቅሞች

ያደላሉ ፡፡

2. ቅዱሳት መጻሕፍትን ዋነኛ ምንጭ ማድረግ:- ክርስቲያን አማካሪዎች በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ስለ

ኢየሱስ የተናገረውን የተትረፈረፈ ሕይወት ተመካሪዎች እንዲደሰቱበት የሚያደርጋቸውን መርሆዎች ላይ

ያተኩራሉ ፡፡

12
]

3 እውነተን መቀበል :- የክርስቲያን ማማከር ፍጹም እውነትን ይቀበላል ፡፡ ዓለማዊያን አማካሪዎች

ደንበኞቻቸው ውጤታማ ሕይወት እንዲኖራቸው ልባቸውን እንዲያዳምጡ እና ትክክል ነው ብለው

የሚያስቡትን እንዲያደርጉ ሲያበረታቱ ፣ የክርስቲያን አማካሪዎች በማማከር ሥራቸው ላይ ደንበኞች

የእግዚአብሔርን ቃል መርሆዎች እና እውነት እንዲያዳምጡ ያበረታታሉ ፡፡

4. እግዚአብሔርን ማክበር :-የክርስቲያናዊ ማማከር አገልግሎት ከፍ ያለ ግብ አለው ፡፡ ብዙ አማካሪዎች

ደንበኞቻቸውን ታካሚዎች ደስታን እንዲያሳድዱ ለመርዳት ሲሞክሩ ፣ ክርስቲያን አማካሪዎች ግን

ተመካሪው እግዚአብሔርን በመፈለግ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲኖር እና አምላኩን እንዲያከብር

ለመርዳት ይተጋሉ፡፡

5. ዘላቂ ፈውሰ:- ክርስቲያናዊ የማማከር አገልግሎት እውነተኛ ፈውስን ይሰጣል፡፡ ዓለማዊ አማካሪዎች

ከስሜት በመገኙ መረጃዎችን በማገዝነብ ብቻ የተገደቡ ናቸው። የሚሰጡትም የመፍትሄ አሳብ ስሜትን

በማከም ጊዚያዊ መፍትሄ ለመስጠጥ ይጥራል፡፡ ክርስቲያናዊ የማማከር አገልግሎት ደንበኛው

ከእግዚአብሔር እና ከልጁ ኢየሱስ ጋር እውነተኛ ኅብረት በማድረግ ዘላቂ ፈውስ ወደ ሚያገኝበት የጠበቀ

ግንኙነት ሊያመጣ ይችላል ፡፡

 ባጠቃላይ ደረጃ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አማካሪነት ልዩ ገጽታዎች አሉት፡፡ አገልግሎቱ የሰውን ሁለንተና
የሚዳስስ ነውና እንደ ማንኛውም ሳይካትሪስቲ አገልግሎት አይደለም ፡፡ ለየት ያለ የፈውስ ሂደት
ይከተላል ምክንያቱም
ሀ. ከሳይኮሎጂስቶችና ከሳይኪያትሪስቶች የማማከር ጥበብ ስለሚለይ
ለ. ክርስቲያናዊ ማመከር በመጽሐፍ ቅዱስ የተተቀሱ ንጥረ ነገሮች ስለማይጠቀሙ ለምሳሌ፣
 የመንፈስ ቅዱስ መገኘት ዮሐ 14፡26፣ 16፡13
 የጸሎትን ኃይል
 የእግዚአብሔር ቃልና ኃይልና ብርታት ዕብ 4፡12
 ግቡ መንፈሳዊ ዕድገት (ክርስቶስን መምሰል ) ነው ሮሜ 8፡28

ሐ. አማካሪው ተመካሪውን በጉዳት ውስጥ እንደዳለ እንደ ራሱ ወንድም እንጂ ለቢዝነስ (ጥቅም) ማግኛ
ላለማድረግ ጥንቃቄ (Pastoral Care) ማድረግ ይኖርበታል፡፡
የአማካሪ ባህሪያት
የማመከር አገልግሎት የተጎዳን ሰው ወደ ጤንነት መመለስ ነውና ፣ ማንም ሰው በቀላሉ ሊተገብረው የሚችል

አይደለም፡፡ የሚከተሉት ባህሪያት ሊኖሩት ይገባል፡፡


 ራሰ ወዳድነትን እና የግለኝነት አመለካከቱን የተወ መሆን አለበት
 ኃላፊነት የሚሰማው እና ተጠያቂነትን የሚወስድ፣
 ግልጽ እና ትሁት መሆን አለበት፣
13
]

 የመማር ልብ ያለው ፡-አዲስ የኑሮ ዘዴን ለራሱ ለመማር ዝግጁ እንዲሁም ሌሎችን ለማስተማር
ቅን ልቦና ያለው
 አዎንታዊ የልብ ዝንባሌ ያለው
 ሚስጥር ጠባቂ
 ባለው የሚረካ ፡- በሕይወቱ (ኑሮ) ያረፈ ባለው ነገር የሚረካ በቃኝ የሚያውቅ ከአጉል
ፉኩክር ነጻ የሆነ
8. የማማከር አገልግሎት መርህ

ሀ. የመቀበል መርህ ፡-የተገልጋይን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ፣ ባህላዊ ሁኔታ ፣ እንዳለ መቀበል፡፡

ለ. የተግባቦት መርህ፡-ማማከር በተግባቦት ላይ ይመሰረታል፡፡ በመሆኑም አማካሪ ከተገልጋይ ጋር ያለው ግንኙነት

የቃል እና የቃል አልባ ተግባቦት መርህን በሚገባ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

ሐ› የማክበር መርህ፡-አማካሪ ተመካሪን በሚያገልግልበት ጊዜ አክብሮት በተሞላበት መንገድ ሊሆን ይገባል፡፡

መ. የርህራሄ መርህ ፡-ርህራሄ የሌለበት የማመከር አገልግሎት ውጤታማ ሊሆን አይችልም ፡፡ በመሀኑም አማካሪ

ለተመካሪ መራራት አለበት፡፡

ሠ. ያለ መፍረድ መርህ ፡- አማካሪ በምንም ጉዳይ በተመካሪ ላይ ሊፈርድ አይገባውም ፡፡

ረ. የግለሰብ መብት መርህ ፡- የማማከር አገልግሎት በግል የሚሰጥ እንጂ በቡድን የሚከወን አይደለም፡፡

ሰ. የመተማመን መርህ፡- በአማካሪ እና ተመካሪ መካከል እውነተኛ የሆነ መተማመን ሊኖር ይገባል፡፡

ሁሉን መርሆዎች ጌታ ኢየሱስና ሳምራዊቷ መካከል በተካሄደው ውይይት ውስጥ መመልከት ይቻላል፡፡

የመቀበል መርህ፡- ኢየሱስ ከነ ማንነቷ ሳምራዊቷን ተቀበላት፡፡ ሴቲቱ ከማኅበራዊ ሕይወት የተገለለች

ቢሆንም እርሱ ግን አልናቃትም ፡፡

የተግባቦት መርህ፡- ኢየሱስ ከሴቲቱ ጋር ያደረገው ውይይት የተግባቦት መርህን በመከተል አናገራት ፡፤

ሁለቱም ሊነጋገሩ የሚችልበትን ርእስ ጉዳይ አነሳ፣ እርሷ ስትናገር አዳመጣት

የመራራት መርህ፡- ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሴቲቱ ያለችበትን ሁኔታ በሚገባ የተረዳ በመሆኑ አዘነላት

ያለ መፍረድ መርህ፡- ጌታ ኢየሱስ በሴቲቱ ላይ እንጂ አልፈረደባትም ፡፡

የግለሰብ መብት መርህ፡- ክርስቶስ ሴቲቱን ደቀ መዛሙርት በሌሉበት በግሏ አነጋገራት

መተማመን መርህ፡- ክርስቶስ ልትተማማንበት የምትችልበትን አሳብ ከነገራት በኋላ ጉዴን የነገረኝን ኑ

እዩ እስክትል ደረሰች
9. የማማከር አገልግሎትን ማሳደግ
የተመካሪውን ሃሳብ ማክበር ማለትም (ስሜቱን፣ እሱነቱን፣ ) ዋጋ በመስጠት ግንኙነትን መመስረት። ይህንን
ስንል፡-
14
]

ሀ. በተመካሪው ዘንድ ያለውን መሰረታዊ ችግር ለመረዳት ጥረት ማድረግ


 ተመካሪውን ለመረዳት ፍላጎት ማሳየት
 መልካም አቀባበል እና የተመቸ ሁኔታ በመፍጠርና ነጻነት መስጠት
ለ. የቃል አልባ እንቅስቃሴውን መከታተል
 አጠቃላይ ኦንቅሰቃሴውን መከታተል (የዓይኑ፣ የንግግሩን ቶን ፣ የፊት ገጽታ የሚገለጽበትን ሁኔታ
መከታተል
ሐ. ተመካሪው የልቡን እንዲናገር መጋበዝ ማለትም
 ክፍት ጥያቄዎችን መጠየቅ
 ሐሳቡን እንዲያብራራ ግጊዜ መስጠት
 በጥንቃቄ መስማት እና በቃላት የማይገለጽ መልዕክትን መረዳት
 የተመካሪውን የንግግር ፍሰት መከተል ማለት የንግግሩን ሐሳብ አትቀይርበት
 የራሰን መልስና ገለጻዎችን ከመስጠት በፊት የርሱን ንግግር መድገም እና ዋና ሃሳቡን መልሶ ማስረዳት
 በንግግሩ ውስጥ ዋና ጉዳይ ላይ ትኩረትን በመስጠት የምርመራ ጥያቄ መጠየቅ
 በተነገረው ነገር ላይ ብቻ በመመስረት ውጤታማና አዎንታዊ መልስ ለተመካሪው መስጠት፤ ባልተነገረው
ላይ በግምት ተነስቶ መልስ ለመስጠት አለመመሞከር፡፡
 ተመካሪው የተሳሳተ አቋም የያዘ ቢመስለን እንኳ እርግጠኛ ሆኖ በሃሳቡ ላይ ባለመፍረድ
መ. በችግር ላይ ማተኮር
 የችግሩን ዋነኛነ ነገር በግልጽ መለየት፣
 ግልጽ እና እውነት የሆነውን ነገር ከጠቅላላው አሳብ የሚጠቅመውን ማውጣት
ሠ. ችግሩን ወይም ሁኔታውን መመርመር እና ማመዛዘን
የችግሩን ምክንያት መመልከት
ተመካሪው አገለግሎቱን ለማግኘት የመጣው ለምን? እና! ምን ዓይነት እርዳታ ፈልጎ ነው ነው?
ተመካሪው የግል ችግሩን የሚቀያይር ወይስ የማይቀይር መሆኑን መረዳት
ችግር አድርጎ የሚገልጸውን መመዝገብ
ረ. ያልተለመደ ሁኔታን መመልከት
o በተመካሪው ዘንድ የሚታዩ ለየት ያሉ እንቅስቃሴዎችን ልብ ማለት
o ለተመካሪው ራሱን ችግሩን ሊፈታ የሚችልበትን መንገድ ማሰጀመር የሚያሰችል የቤት ሥራ መስጠት፣
ሰ. ከተመካሪው ጋር ወደ መፍትሄ የሚወሰዱ የተወሰኑ እርምጃዎችን መመስረት
 አማካሪው ተመካሪውን በመርዳት አንድ የወደፈት ራዕይ እንዲኖረው ማድረግ፣ ማለትም “ችግርህ
ቢቃለል ወደ ፊት ምን መሆን ነው የምትፈልገው? ዓይነት ጥያቄ መጠየቅ ፡
 አማካሪው ተመካሪውን በግልጽ በማናገር ወደ መፍትሔ ለማምጣት አብሮ መወሰን፡፡
15
]

 አማካሪው ለተመካሪውን የሚሻለው ምን ይመሰልሀል በማለት ጥያቄዎችን መጠየቅ ማለት፡-


 በሕይወትህ ከአሁን ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ጊዜ ውስጥ መሆን የምትፈልገው ምንድነው ?
የምትተገብረው እንዴት ነው? መልሱ በማስተዋልና ከእውነት ባልራቀ መልኩ እንዲሆን ማሳወቅ ያሰፈልጋል፡፡
 ምንድ ነው በሕይወትህ እንዲሳካልህ የምትፈልገው ምንድ ነው ?
 ሌላ ለውጥን ለማወቅ ለምን አትፈልግም?
ሸ. በተግባር የሚሰራውን የቤት ሥራ እንዲሰራ መስጠት ፡-
 አማካሪና ተመካሪው አስፈላጊ የሆነውን ነገር ለመስራት መስማማት ያስፈልጋቸዋል፡፡
 ነገር ግን ተመካሪው የመፍትሄ ሐሳቦችን ወደ አማካሪው ይዞ መምጣት መቻል አለበት፡፡
 የቤት ሥራ ለውጥን ለመከታተል ጠቃሚ እርምጃ ነው፡
 የቤት ሥራ ወደ ለውጥ ለመድረስ አንድ የመፍትሄ እርምጃ ነው
 የቤት ሥራ ሐሳቦችን ወደ ተግባር ለመቀየር ይረዳል

ቀ. የተመካሪውን ጥንካሬ መገንባት


 በተመካሪ ዘንድ ያሉትን ጥንካሬ በመረዳት በራሱ ላይ፣ ያለውን መተማማን መገንባት፡፡
 አዲስ ኃይልና ጥንካሬ እንዲሞላ ተመካሪን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ማነቃቃት እና ማደፋፈር ፡፡
 ማበረታታትን፣ ተመካሪዎች እንኳ ደህና መጣችሁ መባልን ይፈልጋሉ። ጥሩ አቀባበል ካገኙ የተባሉትን
በመልካም ለመፈጸም ተነሳሽነት ይኖራቸዋል ፡፡
10. 6 ቱ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ አማካሪት አገልግሎት ገጽታዎች
 የመጋቢያዊ አማካሪነት አገልግሎት ስድስት ገጽታዎች፡-
ሀ. ውጤቱ፡- የማማከር ውጤት ግንኙነትን (Relationship) ዕድገትን ማጠናከር
ለ. ፍልስፍናው፡- የማማከር ፍልስፍናው ዕድገትና ፈውስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ይገኛል የሚል ነው
ሐ. መሳሪያው፡- ማማከር አጋፔ ፍቅር ነው
መ. ምንጭ፡- ለማማከር የመጽሐፍ ቅዱስና የቅን (ሁነኛ) አምልኮ ጥቅም (Trans-of genuine Worship)
ሠ. አገልጋዮች፡- የማማከር አገልግሎት የሚሰጡ አገልጋዮች የክርስቶስ አምባሳደሮች ናቸው፡፡
ረ. ከፍተኛው ትኩረት፡-የአገልግሎቱ ትኩረት ተመካሪውን ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እውነተኛ ግንኙነት ማድረግ
11. መንፈስ ቅዱስ በማማከር አገልግሎት ውስጥ ትኩረት የሚፈልጉ
በማማከር አገልግሎት ውስጥ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ሦስት ገጸ ባህሪያት እንዳሉ ልብ ማለት
ያሻል፡፡ እነሱም ሰው አማካሪ፣ ሰው ተመካሪው እና መንፈስ ቅዱስ መካሪው ናቸው፡፡
አንድ አማካሪ የተመካሪውንም ሆነ የመካሪውን የመንፈስ ቅዱስን ሚና እንዳይወስድ ትልቅ ጥንቃቄ
ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የሰው አማካሪ የሚሰራው መንፈስ ቅዱስ ከሚሰራው ጥቂቱን ክፍል እንደሆነ
መገንዘብ አለበት፡፡ በማማከር ሂደት መንፈስ ቅዱስ ብቻ የሚሰራቸው የሰው አማካሪ ግን ፈፅሞ
ሊደርስባቸውና ሊሞክራቸው የማይችሉት ተግባራት አሉ፡፡ ለዚህም የሚከተለውን መመልከት
ይጠቅማል፡፡
16
]

የሰው አማካሪ ሚና የመንፈስ ቅዱስ አማካሪ ሚና


1. የእግዚአብሔርን ቃል ያካፍላል 1. ስለ ኃጢአት ይወቅሳል
2. እውነትን በፍቅር ይናገራል 2. በልቡ ውስጥ ንሰሀን ይፈጥራል
3. ተመካሪዎች እንደ ቃሉ ወደ ውሳኔ እንዴት 3. ለውሳኔ ምሪትን ይሰጣል
እንደሚደርሱ ያስተምራል
4. የተመካሪውን አስተሳሰብ ሳይጫን ይመክራል 4. ወደ ትክክለኛ አቀውጣጫ እንዲጓዝ ያግዛል
5. ስለ ቅጣት ያስጠነቅቃል 5. የእግዚአብሔርን ፈቃድ ያሳያል
6. በመንፈስ ስለመመላለስ ያስተምራል 6. ሰው አማካሪ ያልደረሰበትን አካባቢ ይደርሳል

12. የአማካሪው ባህሪያት


በማማከር አገልግሎት ውስጥ የትኩረት አቅጣጫዎች ማንኛውም መጽሐፍ ቅዱሳዊ (የመጋቢያዊ አማካሪ)
በማማከር አገልግሎት ውስጥ ፈጽሞ ችላ ሊላቸው የማይገቡ መርሆዎች እንዳሉ ጠንቅቆ ማወቅ
ይኖርበታል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

የተሳካ የክርስቲያናዊ ማማከር አገልግሎት አምስት ውጤታማ ባህሪያት አሉት፡፡

5 በጣም-ውጤታማ-ባሕሪያት-በክርስቲያን የማማከር አገልግሎትን በክርስቲያን ማኅበረሰብ ውስጥ እንዳሉ

የክርስቲያን ምሁራን ይሰማማሉ፡፡ እነርሱም ትምህርትና ስልጠና ፣ ማስተዋል ፣ መንፈሳዊ ብስለት ፣ ተጣጣፊነት

(flexble ) እና ርህራሄ እንደሆኑ የዘርፉ ባለ ሙያ ያስረዳሉ፡፡

ክርስቲያን አማካሪ ለመሆን መወሰድ ያለባቸው በርካታ እርምጃዎች አሉ፡፡ እንዲሁም በክርስቲያን መማከር

ውጤታማ ለመሆን ክርስቲያናዊ ባህሪያትን ይጠይቃል።

ሀ. ትምህርት እና ስልጠና

በክርስቲያን የማማከር አገልግሎት ውስጥ የሚሳተፍ ሥልጠና እና ትምህርት በመስክ ላይ ሳሉ መውሰድ ጥሩ

አፈፃፀም እንዲኖር ወሳኝ ነው ፡፡ የማማከር አገልግሎት አስፈላጊነት እየጨመረ በመጣ ቁጥር አማካሪው ብዙ

ተግዳሮቶችን እና ጥያቄዎችን ያጋጥመዋል ፡፡ ጥልቅ ዕውቀት እና የባለሙያ ስልጠና እነዚያን ጥያቄዎች ለመመለስ

እንዲሁም ከደንበኛው ጋር መተማመንን ለማዳበር ይረዳል ፡፡

ለ. ማስተዋል

ማስተዋል እያንዳንዱ ግለሰብ እና ተሞክሮ በተወሰነ ስዕል ውስጥ እንዴት እንደሚገጣጠም የማየት እና የመረዳት

ችሎታ ነው ፣ እናም ማስተዋል በመማከር አገልግሎት ውስጥ ወቅታዊ መፍትሄ ለመስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል ፡፡

አንድ አማካሪ የባለሙያ ስልጠና ሊኖረው ይችላል ፣ ነገር ግን ያለ ማስተዋል ሙሉውን ምስል ለመረዳት ወይም

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ፅንሰ-ሀሳቦችን በብቃት ለመተግበር አይቻለውም።

17
]

ሐ. ተለዋዋጭነት

የሰው ልጅ ከሌላው ፍጥረታት የተለየ አካል ሲሆን የተለየ ባህሪያትን ፣ ልምዶችን እና ፍላጎቶችን ያሳያል።

በማማከር አገልግሎት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ባህሪዎች አንዱ የደንበኞችን ፍላጎቶች ለማሟላት የተለያዩ

የአቀራረቦችን ወይም ዘይቤዎች ይጠቀማል እንጂ ለሁሉም አንድ ዓይነት አቀራረብ አይከተልም፡፡

መ. መንፈሳዊ ብስለት

መንፈሳዊ ብስለት ለክርስቲያናዊ ማማከር አገልግሎት ቁልፍ ነጥብ ነው፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወት ያልበሰለ የመማከር

አገልግሎትን ሊሰጥ አይችልም፡፡ መንፈሳዊ ብስለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት ማካበት ብቻ አይደለም ፡፡ የመንፈሳዊ

ብስለት ጥበብን ፣ ትህትናን ፣ ቅድስናን እና ይቅርታን በራስ ሕይወት ላይ ተግባራዊ የማድረግ ችሎታ ነው ፡፡ በመንፈስ

የጎለመሰው አማካሪ እግዚአብሔርን እና ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደ የእውነት ወይም የመጨረሻ ምንጭ አድርጎ
በመገንዘብ ሕይወቱን በምሳሌነት ይመራል።

ሠ. ርህራሄ

ርህራሄ በስቃይ ውስጥ ላሉ ሰዎች በማዘን በክርስቶስ ብርሃን የራሳቸውን ሕይወት እንዲያዩ እና ሌሎች እውነተኛ

ፈውስ እንዲያገኙ የሚረዳ ባህሪ ነው ፡፡

ዓለማችን በውስብስብ ችግር በተጨናነቁ ሰዎች ተጥለቅልቃለች ፡፡ የክርስቲያን የማማከር መስክ የተጎጂዎችን

ፍላጎቶች ለማርካት እና በክርስቶስ ፍቅር ለመድረስ አንዱ መንገድ ርህራሄ ነው።

የተዋጣለት አማካሪ መሆን (Effective Counselor)


ሀ. ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ
 የክርስቲያን አማካሪ በአገልግሎቱ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው የአማካሪው አነሳሽ ኃይል
(Motivation) ሰውን መርዳት የሚል ሲሆን ነው፡፡ ይህ ዓይነት የልብ ዝንባሌ እግዚአብሔር ይረዳዋል፡፡
 የሰውን የማማከር ዝንባሌ /አነሳሽ ኃይል/ መመዘን አስቸጋሪ ነው፡፡ ይሁንና የክርስቲያን የአማካሪ
ትክክለኛ አነሳሽ ኃይል ሰዎችን በመርዳት ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል፡፡ የራሱን ፍላጎት በማርካት
ላይ ያረፈ አማካሪነት ጥራት ያለው የማማከር አገልግሎት ሊያስገኝ አይችልም ( ሮሜ 15፡1-3)፡፡
 የአክርስቲያን አማካሪ አነሳሽ ኃይል ተመካሪን ለመርዳት ብቻ ሊሆን ይገባል ፡፡
 የማማከር አገልግሎት አነሳሽ ኃይል ተመካሪውን ለመቆጣጠር መሆን የለበትም፡፡ ምክንያቱም በተመካሪው
ቦታ ሆኖ ለችግሮች መፍትሔን ለማስገኘት ውጤታማ አይሆንም፡፡ ይልቁንም ተመካሪን ለማገዝ የሚል
ዝንባሌ ለክርስቲያናዊ አማካሪ ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡
 ይህን ለመፈጸም ይረዳው ዘንድ አማካሪ ከተመካሪው ጋር ጤናማ ግንኙነት መፍጠር አለበት
(Relationship) ይህም ማለት በጓደኝነት ስሜት መቅረብ ነው፡፡ ሆኖም ጓደኝነት ፍጹም የተዋጣ
የአማካሪዎች መርሆ ነው ማለት አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የጠበቀ ግንኙነት መፍጠር ችግር ሊሆን
ይችላልና፡፡
18
]

ለ. ክህሎትና ልምድ ያለው


 አማካሪዎች ብቃት ያላቸው የሚሆኑት የሁለቱን የማማከር ስነ-ጥበብ ሲያውቁና ሲተገብሩ ነው፡፡
ኤሪክ ፎርም እንዳለው ሁለቱ የማማከር ጥበብ ማግኛ መንገዶች የተፈትሮ የማገናዘብ ችሎታ/ እና
ልምምድ ናቸው፡፡ በእነዚህ በሁለቱ የማማከር ስነ-ጥበብ መካከል ከፍተኛ ክፍተት ሊኖር ፈጽሞ
አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም በአንዱ ብቻ የምንመራ ከሆነ ችግሮች ይገጥማሉ፡፡ ለምን በቂ ልምምድ
ያላቸው አማካሪዎች እንኳ አንዳንዴ ችግር ሲገጥማቸው ይታያልና፡፡
ሐ. በእርጋታ ስራን መስራት
 አማካሪ የይድረስ ይድረስ ሥራ መሥራት የለበትም፡፡አማካሪ በጸጥታ፣ በጥሞና በማስተዋል ተመካሪውን
ማዳመጥ ይኖርበታል፡፡ ሥራውን በረጋ መንፈስ በማስተዋል መስራት ያስፈልጋል፡፡
መ. በተቸገረው ሰው ጫማ ውስጥ መሆን
 በተመካሪ ላይ የምናያቸውን ግድፈቶች በማሰብ ወደ ፈራጅነት መንፈስ እንዳናዘነብል ጥንቃቄ ያሻል፡፡
ጉድለቶችን ብናይም ርኀራኄ ልናሳይ ይገባል፡፡ ዮሐ 8፡1
 ፈራጅ በሆነ መንገድ አለመቅረብ፣ ለምሳሌ
o ይህ መከራ የደረሰብሽ ባለመጸለይሽ ነው
o ዋጋህን አገኘህ አይደለም? “አላርፍ ያለች ጣት”
ሠ. . የተመካሪን ነጻነት ማክበር
 ክርስቲያን አማካሪ በአገልግሎቱ ውስጥ ደጋግሞ ማሰብ ያለበት ተመካሪውን እያስረዳሁት ነው ወይስ
እየተቆጣጠርኩት የሚለውን ነው፡፡ ሊቆጣጠረው የሚሞክር ከሆነ ስህተት ወቅስጥ መሆኑ ተረድቶ
መመለስ አለበት፡፡
 አንዳንድ አማካሪዎች ተመካሪዎችን ከተቀበሏቸው በኋላ ምክር አሰጣጣቸው ተስፋ አስቆራጭ
ይሆናል፡፡ ማለትም ከዚህ በኃላ እነርሱ እንደሚጠበቋቸው አድርገው ይነገሩዋቸዋል፡፡
ረ. በተመካሪ ችግር ውስጥ አለመውደቅ
 አማካሪ አቅጣጫን በማሳየት ለጉዳዩ መፍትሄን ማሳየት እንጂ በተመካሪ ችግር ውስጥ ገብቶ
መጠመድ የለበትም፡፡
 አንዳንድ አማካሪዎች ራሳቸውን ጠብቀው አገልግሎቱን ከመስጠጥ ይልቅ በከፍተኛ ስሜት
በተመካሪ ችግር በመዋጥ ራሳቸውን ችግር ውስጥ ይከታሉ፡፡ በሀዘን በመጎዳት ዓላማቸውን
ይለቃሉ ራሳቸው አማካሪ የሚያስፈልጋቸው ይሆናሉ፡፡
ሰ. ስህተትን ማመን
 ማንም የማይሳሳት አማካሪ የለም ሲሳሳቱ ሁልጊዜ ትክክለኛ እንደሆኑ መቁጠር ስህተት ነው፡፡
መሳሳታችን ለወደፊቱ ብቃት ያለው አማካሪ ለመሆን ስለሚረዳን እንደ ተሳሳትን ማመን ያስፈልጋል፡፡
 አማካሪ ሲሳሳት ስህተቱን በመሸፈን ለመከላከል ከመሞከር ይልቅ ይቅርታ ጠይቆና ከስህተቱ ተምሮ
ወደፊት መራመድ ይኖርበታል፡፡

19
]

12. የተመካሪ ባህሪያት

የተለያየ ባህሪ ያላቸው አማካሪዎች እንዳሉ ሁሉ የተለያየ አቋም ያላቸው ተመካሪዎችም እንዳሉ ልብ ልንል
ይገባል፡፡ ጥሩ የማማከር አገልግሎት ለመስጠት የተመካሪዎች ባህሪያትን በቅድሚያ ማጥናት ይጠቅማል፡፡

1. ባህሪያቸውን ለመቀየር ፈቃደኛ የማይሆኑ ይኖራሉ፡፡


 ረዥም ጊዜ ኃይላችሁንና ገንዘባችሁንም ሰውነታችሁ ሰታችዋቸው ልታገለግሏቸው ስትወስኑ አቋማችሁን
ለመለወጥ ፍቃደኛ ማይሆኑ ብዙ አሉ፡፡
2. ችግራቸውን ፈጽሞ የሚደብቁ ወይም በከፊል የሚገልጹ
 ችግራችሁን መግለጽ የሚያቅታቸው እና ያለማቋረጥ የሚያለቅሱ
 አጋንንት ያለባቸው
 የአእምሮ /አካል/ ሕመም
 ስለዚህ የደረሰባቸው ቀውስ እና ችግሩን መለየት ያስፈልጋል፡፡
12. የማማከር ሥነ-ምግባር

በማማከር ሒደት ሁለቱም ገፀ ባህሪያት ማለት አማካሪና ተመካሪ ሊጠብቁት የሚገባ የማማከር ስነ-ምግባር
አለ፡፡ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ድጋፍ በማድረግ ላይ ሁለቱም የሚከተሏቸው መሠረታዊ ግዴታዎች የሚከተሉ
መሆን አለባቸው፡፡

ሀ. እምነት /አመኔታ/፡- አማካሪ በምንም ዓይነት የተመካሪን ሚስጢር በስብከት /በጉባኤ/ መግለፅ ሆነ ምሳ
መስጠት የለበትም፡፡ በተጨማሪም ለሌላ ጓደኛ ወይም ዘመድ ማውራት አያስፈልግም፡፡
ለ. በአካል መነካካትን ማስወገድ፡- ከልክ ያለፈ አካላዊ መነካከት በመካላቸው እንዳይፈጠር መጠንቀቅ
ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም አላስፈላጊ መነካካት ሁለቱንም በአገልሎት ውስጥ ያለውን ዓላማ ሊያስት ይችላልና፡፡
ሐ. በግልጽ መነጋር ፡- ማማከርን ወደ ውጤት የሚመጣው ግልጽ እና የጋራ ዓላማ ላይ ሲመሰረት ብቻ ነው፡፡
ነገር ግን ከሁለት አንዱ የተደበቀ ዓላማ ይዞ ከተንቀሳቀሰ አገልግሎት ከአዎንታዊ ይልቅ አሉታዊ መሆኑ
አይቀሬ ነው፡፡

መ. አቅምን ማወቅ፡- አማካሪ ሰው እንጂ አምላክ አይደለም፡፡ እናም አቅሙ ውስን ነው፡፡ በማማከር
አገልግሎቱ ፍጹም የሆነ አቅም እንዳለው ማብ የለበትም፡፡ እንዲሁም ምን ያህል መስራት እንደሚችል
አቅሙ በሚገባ መረዳት አለበት፡፡ የተመካሪውን ችግር መፍታት ካልተቻለ ለሚመለከተው ክፍል መላክ
ጠቃሚ ነው፡፡ ለምሳሌ በህክምና መፍትሔ የሚያገኝ ችግር ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን እኔ እራሴ እስከ
መጨረሻው ጉዳዩን እይዛለው ብሎ ባለ ጉዳይን መግደል ተገቢ አይደለም፡፤
 አማካሪ ማለት ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አስገኚ ማለት ፈጽሞ አይደለም፡፡
 አማካሪ ከአቅሙ በላይ ከሆነበት ለሌላ ማስተላለፍ /ሪፈር/ መላክ አለበት

ሠ› ሚስጢር ጠባቂነት ፡- ተመካሪዎች ከአማካሪዎች ከሚፈልጓቸው ታላላቅ ነጥቦች (ጉዳዮች) ውስጥ


ዋንኛው ሚስጥር ጠባቂነት ነው፡፡ ስለሆነም አማካሪዎች ሚስጥር ጠባቂ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በስልክ
አለመነጋገርና ለሌሎች ፍንጭ ሰጪ ወሬዎችን ባለማውራት ሚስጥር መጠበቅ ይቻላል፡፡

20
]

13. የችግሮች መንስኤዎችና መፍትሔዎቻቸው


ማንኛውም አማካሪ ለማማከር እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የችግሮች መንስኤዎች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ
እና ማስወገጃ መሳሪያዎችንም ማወቅ ይኖርበታል፡፡ ለዚህም የሚከተሉትን ማየት ይጠቅማል፡፡
 የችግሩ መንስኤዎች
 ስነ-ሕይወታዊ (Biological)፡- ከሰውነት እጢዎችና ሆርሞኖች ጋር በተያያዘ ችግር ሊኖር ይችላል፡፡
 የታሪካዊ አስተዳደግ፡- ለምሳሌ ከህብረተሰብ ተለይተው ያደጉ ልጆች ገጠር ያደጉና ከተማ ሲመጡ
ወዘተ….
 በባህላዊ እና ኅብረተሰባዊ፡- ለምሳሌ ከፖለቲካ የሃይማኖት የስራ ተጽዕኖ
 የሕይወት ውጥረት፡- የስራ ብዛት የህይወት ጣዕም የጠፋበት መሆኑ
 የግል የውስጥ ቀውስ፡- እራስን ዝቅ በማድረግ (ራስን በመኮነን) እና ተከላካይነት (ሌሎችን ምክር
አለመጠየቅ)
 ኢሰብአዊ ተጽዕኖ፡- በልጅነት ወቅት ከተቃራኒ ጾታ የሚደርስ አስገድዶ መድፈር ለምሳሌ ጋብቻን አጥብቄ
ከጠላች
 የአጋንንት ተጽኖ፡- በክፉ መናፍስት የተያዙ ሰዎች በጋብቻ በስራ በትምህርትና በመንፈሳዊ ህይወት ማደግ
ያለመቻል ተጽዕኖ ይደርስባቸዋል፡፡
 መንፈሳዊ ችግር፡- ለእግዚአብሔርን አለመታዘዝ ለምሳሌ የዮናስ ችግር አለመታዘዝ ነው፡፡የችግሩ መፍትሔ
አስገኚ መሳሪያዎች
የሚከተሉት እውነት ለችግሮች መፍትሔ አስገኚ መሳሪያዎች እንደሆኑ መገንዘብ ያሻል፡፡
ሀ. ጸሎት
ለ. በተገለጸው እውነት መመራት
ሐ. ከቅዱሳን ጋር ህብረት መፍጠር
መ. የአእምሮ ህክምና (Cognitive therapy) በእግዚአብሔር ቃል በመማከር የግለሰቦችን እውቀት ማሳደግ
(ምሳ 19፡2)
ሠ. የባህሪ ህክምና (Behavioral therapy)
ረ. የህክምና አገልግሎት (Medication)
ሰ. የቡድን ህክምና (Group therapy)
14. የአማካሪው ጥንቃቄ እና ሶስት የማማከር ደረጃዎች
15.1 የአማካሪ ጥንቃቄ
 ለሌሎች የሚጠነቀቅ አማካሪ በስነ ልቦናውም ሆነ በአካሉ ጉዳት እንዳይደርስበት ልዩ ጥንቃቄ
ሊያደርግ ይገባል፡፡ ለዚህም ራሱን ሳይጎዳ መኖር እንደሚችል የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል
ይኖርበታል፡፡

21
]

o ልትቆጣጠረው የማትችለውን ኃላፊነት አትቀበል በማማከር ሂደት ውስጥ ከባህሪያችን ታጋሽነታችንና


ከዕውቀታችን አንጻር ማድረግ በማንችለው ነገር ላይ እርምጃ መውሰድ የለብንም፡፡ ይህ ቢሆን በኃላ
ራሳችንን ተዋርደን ጌታን ልናሳዝን እንችላለን፡፡
o ለራስህ ያልተጠነቀቀ ለሌላው እጠነቀቃለሁ አትበል፡፡ በአብዛኛው አገልጋይ (አማካሪ) ራሱን የሚለው
ተመካሪዎችን በሙሉ ደስ ለማሰኘት የሚያደርገው ጥረት ነው፡፡ ስለሆነም የተጠየቀውን ሁሉ
ለማድረግ ማዘንበል የለበትም፡፡
o ከአቅም በላይ መወጠር ተግባርን እንዲቆም እና እንዲበላሽ ያደርጋል፡፡
o ግራ ስትጋባና ያልተጠበቀ ውድቀት ሊደርስብህ በህይወትህ እየተካሄደ ባለው ነገር ላይ በማነጣጠር
የሚከተሉትን ሦሥት ሂደቶች በደረጃ ጠይቅ፡፡
ሀ. ምን እየተሰማኝ ነው?
ለ. ምን እፈልጋለሁ?
ሐ. ስለተፈጠረው ነገር ምን ላድርግ?
o ካስፈለገ የሌሎችን እርዳታ መጠየቅና ሰዎች ስሜታቸውን እንዲገለጹ መፍቀድ
o መጥፎ በሆኑ ሁኔታዎች አራት ምርጫዎች እንዳሉህ ልብ በል
 ተወው
 ለውጠው
 ተቀበለው
 በድጋሚ ማቀድ ምንም ስህተት ሰርተህ ካልሆነ ምንም ያልተማረከ መሆንህን እወቅ
 በሚቀጥለው ልትፈጽመው ያለውን ወስን
 ማንኛውም ጊዜ ውሳኔ ማድረግ የምትችለው ባለህ መረጃ ተመስርተህ ነው
 ህይወት ሁልጊዜ ውብ እንዳይደለ እወቅ
15. የማማከር አደጋዎች

ማማከር ጠቃሚ ጎን እንዳለው ሁሉ ጎጂ ገጽታም አለው፡፡ ጥቂቶቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነዚህን ነገሮች
አማካሪ በቅድሚያ ሲያውቅ አደጋዎችን ለማስወገድ ወይም ለመቀነስ እጅግ ይጠቅማል፡፡

ሀ. ከአንድ አቅጣጫ በመጣ መረጃ መደገፍ

አማካሪ በተለይ ቤተሰብ ነክ (ጋብቻ) ጉዳዮችን ሲይዝ ከሁለቱም (ከያቅጣጫው) በቂ መረጃ መሰብሰብ
ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ሊሳሳት ይችላል፡፡ ፈራጅ እና ኮናኝ ከመሆኑም በላይ ጉዳዩን በቅንነት መርዳት
ይቸግራል፡፡

ለ. ነገርን ሳያብላሉ (ሳያጣጥሙ) ወደ ማጠቃለያ መድረስ

 ስለ ጉዳዩ ሙሉ መረጃ ሳይዙ ወደ ድምዳሜ መድረስ

ሐ. ከተቃራኒ ጾታ ጋር የቅርብ ህብረት መፍጠር

22
]

የመጋቢ አማካሪ በተቃራኒ ጾታ ፍቅር ሊነደፍ ይችላል፡፡ ከአማካሪ ከባድ ስራዎች ውስጥ ዋነኛው በተቃራኒ ጾታ
ፍቅር ላለመነደፍ የሚያደርገው ትግል ነው፡፡ ይህንን ፈተና በርቀት ለማስወገድ፡-

 ከተቃራኒ ጾታ ጋር አለማሳሳም (አለመሳም)


 ከተቃራኒ ጾታ ጋር ጎን ለጎን አለመቀመጥ
 ከተቃራኒ ጾታ ጋር ለረዥም ጊዜ ተጨባብጦ አለመቆየት
 ከችሎታ በላይ (ከአቅም በላይ) ቀጠሮ መስጠት

መ. ለቤተ ሰብ ጊዜ ማጣት ፡-

ሠ. የስነ ልቦና ቀውስ ፡- ሁል ጊዜ የሰውን ችግር የሚሰማ ሰው ለራሱ ካልተጠነቀቀ ችግር ውስጥ የመግባት
እድል ይኖረዋል፡፡

ማጠቃለያ

ክርስቲያናዊ የማማከር አገልግሎት (መጽሐፍ ቅዱሳዊ የማማከር አገልግሎት እና የክርስቲያን ሳይኮሎጂ

በመባልም ይታወቃል፣ እምነትን ከስነ-ልቦና መርሆዎች ጋር በማጣመር የአእምሮ ጤንነትን እና ማኅበራዊ

ግንኙነቶችን ለማሻሻል ይረዳል ፡፡ ይህ አገልግሎት የሕይወትን ችግሮች ለመቋቋም እንዲረዳ የቅዱሳት

መጻሕፍትን ጥቅሶችን መሠረት አድርጎ ትምህርቶችን ይሰጣል።

የሚወዱትን ሰው ማጣት ወይም በሥራ ማጣት ፣ በጤና መዛባት፣ በገንዘብ ችግሮች እና / ወይም

በግንኙነት ጉዳዮች ላይ በመሳሰሉ አስጨናቂ የሕይወት ክስተቶች መካከል በምንሆኑበት ጊዜ በእምነት

እንድንጸና ያግዛል።

እንዲሁም በተሰፋ መቁረጥ አጉል እና የተሳሳተ እርምጃ እንዳይወሰዱ ጠንካራ ሆኖው እኖዲገኙ በፈተና

ውስጥ ለመጽናት እና ከሕይወት የጎድለውን መልሶ ለማግኘት ታላቅ ሚና አለው፡፡

የክርስቲያን ማማከር አገልግሎት ዋና ግብ ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ትምህርቶች ጋር የማይጣጣሙ

ባህሪያትን እንዲለዩ ለመርዳት ነው። በዚህም አገልግሎት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመገንዘብ እና

በሕይወት ለመተግበር እንዲነቃቁ ይጠቅማል፡፡

የክርስቲያን አማካሪዎች ሰዎች በተለይም ክርስቲያኖች እንዴት ማሰብ እና ምግባባራቸው ምን መሆን

እንዳለባቸው የመጨረሻ መመሪያ መሰጠት የሚችለው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ ያምናሉ ፡፡ በሌላ

አገላለጽ ይህንን ቅዱስ መጽሐፍ አንድ እና ብቸኛ እውነት አድርገው ይመለከቱታል፡፡

አማኝ መንፈሳዊ ጉዞ በሚያደርግበት ወቅት በመንገዱ ላይ ተግዳሮቶችን እና መከራዎችን ማግኘታቸው

አይቀሬ ነው። ይህ ሁሉንም እውነተኛ ክርስቲያኖች ሊገጥም የሚችል ተሞክሮ ነው፡፡ አንድ ሰው
23
]

በመንፈሳዊ ጤንነቱ በሚመሳሰልበት ጊዜ ከአምላኩ መመሪያ ለመቀበል ክፍት ሊሆን ይገባል፡፡ መመሪያው

በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በፍቅር የሚወደውን ፣ በርህራሄ የሚመለከተውን ፣ በይቅርታ በተደገጋሚ

የሚምረውን አምላክ በማየት ከፉውን ሁኔታ ለመቋቋም የሚረዳ ጸጋ የሚያገኝበትን መንገድ ያመላክታል

። ክርስቲያናዊ ማማከር አገልግሎት በልዩ ልዩ ችግሮች ውስጥ የሚያልፉ መመሪያውውን በአግባቡ


መፈጸም እንዲችሉ ያግዛሉ፡፡
መንፈሳዊ ብዥታ ያለበት፣ ሥነ ልቦናዊ ወይም የጤና ችግሮች ያሉበት ማንኛውም ሰው ክርስቲያናዊ ማማከር

አገልግሎት መጠየቅ ይኖርበታል። ክርስቲያናዊ የማማከር አገልግሎት በአንድ ልዩ ችግር ብቻ ፣ ወይም የአእምሮ

ህመም ላይ ብቻ የተመሠረተ አለመሆኑን መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ የማማከር አገልግሎት ዓላማ ሰፋ ያለ ሲሆን

የግል ሕይወት ፣ የጥንድ ባለትዳር ተግዳሮት ፣ የቤተሰብ ግንኙነት ማለትም የወላጅ እና ልጅ ግንኙነት ፣

ማህበራዊ ጉዳዮችን መፍታት ያካትታል ፡፡ ስለዚህ ፣ ለእነዚህ ጉዳዮች ዓለማዊ ወይም ሃይማኖታዊ ያልሆኑ

ምክሮችን ከመፈለግ ይልቅ ፣ የክርስቲያን ማማከር አገልግሎት የሚያዋጣ ነው።

24

You might also like