Professional Documents
Culture Documents
Jhova
Jhova
ጥምቀት ምን ያመለክታል?
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሕፃናት ጥምቀት ወይም ክርስትና ስለማስነሳት ምን
ይላል?
በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቅ ሲባል ምን ማለት ነው?
ድጋሚ መጠመቅ ኃጢአት ነው?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ስለ ጥምቀት የሚናገሩ ሌሎች ዘገባዎች
የክርስቲያኖችን ጥምቀት በተመለከተ ብዙዎች ያላቸው የተሳሳተ አመለካከት
ጥምቀት ምን ያመለክታል?
ጥምቀት አንድ ሰው ከኃጢአቱ ንስሐ እንደገባና በማንኛውም ሁኔታ ሥር የአምላክን
ፈቃድ ለማድረግ እንደተስማማ በሰዎች ፊት ይፋ ለማድረግ የሚወስደው እርምጃ ነው።
ይህም በመላ ሕይወቱ አምላክንና ኢየሱስን መታዘዝን ይጨምራል። አንድ ሰው ሲጠመቅ፣
ወደ ዘላለም ሕይወት በሚወስደው ጎዳና ላይ መጓዝ ይጀምራል።
ውኃ ውስጥ መጥለቅ፣ አንድ ሰው በሕይወቱ ውስጥ ያደረገውን ለውጥ ጥሩ አድርጎ
የሚገልጽ ምልክት ነው። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ መጠመቅን
ከመቀበር ጋር ያመሳስለዋል። (ሮም 6:4፤ ቆላስይስ 2:12) ግለሰቡ ውኃ ውስጥ መጥለቁ፣
ለቀድሞ አኗኗሩ እንደሞተ ያሳያል። ከውኃው መውጣቱ ደግሞ ራሱን ለአምላክ የወሰነ
ክርስቲያን በመሆን አዲስ ሕይወት መጀመሩን ይጠቁማል።
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሕፃናት ጥምቀት ወይም ክርስትና
ስለማስነሳት ምን ይላል?
“ክርስትና መነሳት” ወይም “ክርስትና ማስነሳት” የሚሉት አገላለጾች በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ አይገኙም።b መጽሐፍ ቅዱስ ሕፃናት መጠመቅ እንዳለባቸውም አያስተምርም።
ሕፃናትን ማጥመቅ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ነገር ጋር አይጣጣምም። መጽሐፍ
ቅዱስ አንድ ሰው መጠመቅ ከፈለገ የተወሰኑ መሥፈርቶችን ማሟላት እንዳለበት
ያስተምራል። ለምሳሌ ቢያንስ መሠረታዊ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች
መረዳትና እነዚህን ትምህርቶች በሕይወቱ ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል። ከኃጢአቱ
ንስሐ መግባት ይጠበቅበታል። እንዲሁም በጸሎት አማካኝነት ራሱን ለአምላክ መወሰን
ያስፈልገዋል። (የሐዋርያት ሥራ 2:38, 41፤ 8:12) ሕፃናት ደግሞ እነዚህን ነገሮች
ማድረግ አይችሉም።
በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቅ ሲባል ምን
ማለት ነው?
ኢየሱስ ለተከታዮቹ የሚከተለውን መመሪያ ሰጥቷቸዋል፦ “ሰዎችን ደቀ መዛሙርት
አድርጉ፤ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፣ ያዘዝኳችሁንም
ሁሉ እንዲጠብቁ [አስተምሯቸው]።” (ማቴዎስ 28:19, 20) “በ . . . ስም” የሚለው
አገላለጽ፣ የሚጠመቀው ግለሰብ አብና ወልድ ያላቸውን ሥልጣንና ቦታ እንዲሁም
የአምላክ ቅዱስ መንፈስ የሚጫወተውን ሚና መረዳትና መቀበል እንዳለበት ያመለክታል።
ነጥቡን በምሳሌ ለማስረዳት ያህል፣ ሐዋርያው ጴጥሮስ ሲወለድ ጀምሮ ሽባ ለነበረው ሰው
“በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነስና ተራመድ!” ብሎታል። (የሐዋርያት ሥራ 3:6) ይህ ምን
ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው፦ ጴጥሮስ የክርስቶስን ሥልጣን የተቀበለ ከመሆኑም ሌላ ሽባ
የነበረው ሰው የተፈወሰው በኢየሱስ እንደሆነ እውቅና ሰጥቷል።
“አብ” የተባለው ይሖዋ c አምላክ ነው። ይሖዋ ፈጣሪ፣ ሕይወት ሰጪና ሁሉን
ቻይ አምላክ እንደመሆኑ መጠን ከሁሉ የላቀ ሥልጣን አለው።—ዘፍጥረት
17:1፤ ራእይ 4:11
“ወልድ” የተባለው ሕይወቱን ለእኛ ሲል የሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (ሮም
6:23) ኢየሱስ፣ አምላክ ለሰው ልጆች ባለው ዓላማ አፈጻጸም ውስጥ
የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና ካልተረዳንና ካልተቀበልን መዳን ልናገኝ
አንችልም።—ዮሐንስ 14:6፤ 20:31፤ የሐዋርያት ሥራ 4:8-12
“መንፈስ ቅዱስ” አምላክ የተለያዩ ነገሮችን ለማከናወን የሚጠቀምበት ኃይል
ነው።d አምላክ ለመፍጠር፣ ሕይወት ለመስጠት፣ ለነቢያቱና ለሌሎች
መልእክቱን ለማስተላለፍ እንዲሁም ፈቃዱን ለመፈጸም የሚያስችላቸውን
ኃይል ለመስጠት ቅዱስ መንፈሱን ተጠቅሞበታል። (ዘፍጥረት 1:2፤ ኢዮብ
33:4፤ ሮም 15:18, 19) አምላክ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የእሱን ሐሳብ
እንዲጽፉ ለመምራትም ቅዱስ መንፈሱን ተጠቅሟል።—2 ጴጥሮስ 1:21
ድጋሚ መጠመቅ ኃጢአት ነው?
ሃይማኖታቸውን ለመለወጥ የሚወስኑ በርካታ ሰዎች አሉ። ሆኖም እነዚህ ሰዎች ቀደም
ሲል በነበሩበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠምቀው ከነበረስ? ድጋሚ ቢጠመቁ ኃጢአት
ይሆንባቸዋል? አንዳንዶች አዎ የሚል መልስ ይሰጣሉ፤ ምናልባት እንዲህ የሚሉት ኤፌሶን
4:5 ላይ የሚገኘውን “አንድ ጌታ፣ አንድ እምነት፣ አንድ ጥምቀት አለ” የሚለውን ጥቅስ
መሠረት በማድረግ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ይህ ጥቅስ አንድ ሰው ድጋሚ መጠመቅ
እንደሌለበት የሚጠቁም አይደለም። እንዴት?
የጥቅሱ አውድ። የኤፌሶን 4:5ን አውድ ስንመለከት ሐዋርያው ጳውሎስ እውነተኛ
ክርስቲያኖች በእምነት አንድ መሆናቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ጎላ አድርጎ እየገለጸ
ነበር። (ኤፌሶን 4:1-3, 16) እንዲህ ያለው አንድነት ሊኖር የሚችለው አንድ ጌታ
ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስን ከተከተሉ፣ አንድ እምነት ካላቸው ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ
ስለሚያስተምረው ነገር ተመሳሳይ አረዳድ ካላቸው እንዲሁም ከጥምቀት ጋር በተያያዘ
አንድ ዓይነት ቅዱስ ጽሑፋዊ መሥፈርት ከተከተሉ ብቻ ነው።
ሐዋርያው ጳውሎስ ቀደም ሲል የተጠመቁ አንዳንድ ሰዎች ድጋሚ እንዲጠመቁ
አበረታቷል። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የተጠመቁት የክርስትናን ትምህርት ሙሉ በሙሉ
ሳይረዱ ነው።—የሐዋርያት ሥራ 19:1-5
አምላክ የሚቀበለው ጥምቀት። ጥምቀት በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ከተፈለገ
በትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። (1 ጢሞቴዎስ
2:3, 4) አንድ ሰው የተጠመቀው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በሚጋጩ የሐሰት ሃይማኖት
ትምህርቶች ላይ ተመሥርቶ ከሆነ ጥምቀቱ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም።
(ዮሐንስ 4:23, 24) ግለሰቡ ይህን እርምጃ የወሰደው ከልቡ ተነሳስቶ ቢሆንም “በትክክለኛ
እውቀት ላይ [ተመሥርቶ]” አይደለም። (ሮም 10:2) በአምላክ ፊት ተቀባይነት ለማግኘት
የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መማር፣ የተማረውን ነገር ተግባር ላይ ማዋል፣ ሕይወቱን
ለአምላክ መወሰንና ድጋሚ መጠመቅ ይኖርበታል። በዚህ ሁኔታ ሥር ድጋሚ መጠመቁ
ኃጢአት አይሆንበትም። እንዲያውም እንዲህ ማድረጉ ተገቢ ይሆናል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ስለ ጥምቀት የሚናገሩ
ሌሎች ዘገባዎች
መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስ ተከታዮች ውኃ ውስጥ በመጥለቅ ከሚጠመቁት ጥምቀት፣
የተለየ ትርጉም ወይም ዓላማ ስላላቸው ሌሎች ጥምቀቶችም ይናገራል። እስቲ አንዳንድ
ምሳሌዎች ተመልከት።
መጥምቁ ዮሐንስ ያከናወነው ጥምቀት።e አይሁዶችና ወደ ይሁዲነት የተለወጡ ሰዎች
የሙሴን ሕግ ማለትም አምላክ በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤላውያን የሰጣቸውን ሕግ
በመጣስ ለፈጸሙት ኃጢአት ንስሐ መግባታቸውን ለማሳየት ወደ ዮሐንስ እየሄዱ ይጠመቁ
ነበር። የዮሐንስ ጥምቀት ሕዝቡ መሲሑን ይኸውም የናዝሬቱን ኢየሱስን ማወቅና
መቀበል እንዲችሉ አዘጋጅቷቸዋል።—ሉቃስ 1:13-17፤ 3:2, 3፤ የሐዋርያት ሥራ 19:4
ኢየሱስ ራሱ የተጠመቀው ጥምቀት። ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ የተጠመቀው ጥምቀት
ለየት ያለ ነበር። ኢየሱስ ፍጹም ሰው ሲሆን ምንም ኃጢአት አልነበረበትም። (1 ጴጥሮስ
2:21, 22) ስለዚህ የእሱ ጥምቀት ንስሐ መግባትን ወይም ‘ጥሩ ሕሊና ለማግኘት
ለአምላክ ልመና ማቅረብን’ አይጨምርም። (1 ጴጥሮስ 3:21) ከዚህ ይልቅ አስቀድሞ
የተነገረለት መሲሕ ወይም ክርስቶስ በመሆን የአምላክን ፈቃድ ለመፈጸም ራሱን
ማቅረቡን የሚያሳይ ነበር። አምላክ ለኢየሱስ ያለው ፈቃድ ደግሞ ለእኛ ሲል ሕይወቱን
መስጠቱን ይጨምራል።—ዕብራውያን 10:7-10
እውነታው፦ አንደኛ ነገር ጥቅሱ ስለ ሰዎቹ ዕድሜ የሚናገረው ነገር የለም። ሌላው ነገር
ደግሞ የእስር ቤቱ ጠባቂና ቤተሰቡ ከመጠመቃቸው በፊት “የይሖዋን ቃል” እንደሰሙና
እንደተቀበሉ ዘገባው ይናገራል። (የሐዋርያት ሥራ 16:31, 32, 34) በመሆኑም
የሚነገረውን ነገር መረዳት እንዲሁም በአምላክና በጌታ በኢየሱስ ላይ ማመን የሚችሉበት
ዕድሜ ላይ ደርሰው መሆን አለበት።
a ቫይንስ ኮምፕሊት ኤክስፖዚተሪ ዲክሽነሪ ኦቭ ኦልድ ኤንድ ኒው ቴስታመንት ወርድስ የተባለው መጽሐፍ
እንደሚገልጸው “መጠመቅ” የሚለው የግሪክኛ ቃል “መግባትን፣ መጥለቅንና መውጣትን” ያመለክታል።
b “ክርስትና ማንሳት” የሚለው አገላለጽ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ለሕፃናት ስም በማውጣት ከዚያም
ራሳቸው ላይ ውኃ በመርጨት ወይም በማፍሰስ የሚፈጽሙትን ሃይማኖታዊ ሥርዓት ያመለክታል።
c ይሖዋ የአምላክ የግል ስም ነው። (መዝሙር 83:18) “ይሖዋ ማን ነው?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።
በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ወይም “በአዲስ ኪዳን” ውስጥ ግን ሁኔታው ከዚህ
የተለየ ነው። በራእይ መጽሐፍ (የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ) የእጅ ጽሑፍ
ቅጂ ውስጥ የአምላክ ስም “ያህ” በሚለው ምህጻረ ቃል (“ሃሌ ሉያ” በሚለው ቃል ውስጥ)
ተጽፎ ይገኛል። ከዚህ በቀር በአሁኑ ጊዜ በእጃችን በሚገኙት ከማቴዎስ እስከ ራእይ
በሚገኙት የጥንት ግሪክኛ የእጅ ጽሑፍ ቅጂዎች ውስጥ የአምላክ ስም ተጽፎ አይገኝም።
ታዲያ የአምላክ ስም በክርስትና ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ መኖር የለበትም ማለት
ነውን? እንዲህ ቢሆን ነገሩ ግራ ያጋባ ነበር። ምክንያቱም የኢየሱስ ተከታዮች የአምላክ
ስም ያለውን ከፍተኛ ቦታ ይገነዘቡ ነበር፤ ኢየሱስም ስለ አምላክ ስም መቀደስ እንድንጸልይ
አስተምሮናል። ታዲያ የአምላክ ስም ከክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች የጠፋው
ለምንድን ነው?
ማቴዎስ የጻፈው በዕብራይስጥ ቋንቋ በመሆኑ በተለይ ‘ከብሉይ ኪዳን’ ጠቅሶ በሚጽፍበት
ጊዜ በአምላክ ስም አልተጠቀመም ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው። ይሁን እንጂ
ሁለተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የጻፉት ሌሎች ጸሐፊዎች መጽሐፎቻቸውን የጻፉት
ለዓለም አቀፍ አንባቢዎች ስለነበረ የጻፉበት ቋንቋ በዘመኑ ዓለም አቀፍ ቋንቋ የነበረው
ግሪክኛ ነበር። በዚህም ምክንያት ከ“ብሉይ ኪዳን” በሚጠቅሱበት ጊዜ ከዕብራይስጡ በኩረ
ጽሑፎች ሳይሆን ከግሪክኛው ሰፕቱጀንት ትርጉም ይጠቅሱ ነበር። የማቴዎስ ወንጌልም
ቢሆን ከጊዜ በኋላ ወደ ግሪክኛ ተተርጉሟል። በእነዚህ የግሪክኛ ጽሑፎች ውስጥ የአምላክ
ስም ይገኝ ነበርን?
በኢየሱስ ዘመን ከነበረው የሰፕቱጀንት ትርጉም እስከ ዘመናችን ድረስ ተጠብቀው የቆዩ
በጣም ያረጁ ብጥስጣሾች ይገኛሉ፤ በእነዚህ ቅዳጆች ላይ የአምላክ ስም ተጽፎ መገኘቱም
ከፍተኛ ግምት ሊሰጠው የሚገባ ነገር ነው። ዘ ኒው ኢንተርናሽናል ዲክሽነሪ ኦቭ ኒው
ተስታመንት ቲኦሎጂ (ጥራዝ 2፣ ገጽ 512) እንዲህ ይላል:- “በቅርቡ በተገኙ የጽሑፍ
ማስረጃዎች ምክንያት የሰፕቱጀንት አጠናቃሪዎች የሐወሐ የሚለውን
ቴትራግራማተን ኪሪዮስ እያሉ ተርጉመዋል የሚለው አስተሳሰብ እውነት መሆኑ በጣም
አጠራጣሪ ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ በሚገኙት እጅግ ጥንታዊ የሆኑ የሰፕቱጀንት ቅጂ ቅዳጆች
ላይ በግሪክኛው ጽሑፍ መካከል ቴትራግራማተኑ በዕብራይስጥ ፊደላት ተጽፎ ይታያል።
በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ አይሁዳውያን የብሉይ ኪዳን ተርጓሚዎችም ይህንኑ
ልማድ ይከተሉ ነበር።” ስለዚህ ኢየሱስም ሆነ ደቀ መዛሙርቱ የሚያነቡት ቅዱስ ጽሑፍ
ዕብራይስጥ ወይም ግሪክኛ ቢሆን መለኮታዊውን ስም ማግኘታቸው አይቀርም ነበር።
በዚህ ምክንያት በአሜሪካ አገር የሚገኘው የጆርጂያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ጆርጅ
ሐዋርድ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል:- “የአዲስ ኪዳኑ ቤተ ክርስቲያን
ይጠቀምበትና ይጠቅሰው በነበረው በሰፕቱጀንት ትርጉም ውስጥ መለኮታዊው ስም
በዕብራይስጥ ፊደላት ተጽፎ ይገኝ በነበረበት ጊዜ ሁሉ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች
ቴትራግራማተንን በጥቅሶቻቸው ውስጥ ይጽፉ እንደነበረ አያጠራጥርም።” (ቢብ ሊካል
አርኪዮሎጂ ሪቪው፣ መጋቢት 1978፣ ገጽ 14) ከዚህ የተለየ ነገር ለማድረግ ምን ሥልጣን
ሊኖራቸው ይችላል?
የመለኮታዊው ስም መወገድ
ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ይመጣል ሲል የተነበየለት ክህደት መከሰት ጀምሮ ስለነበር
የአምላክም ስም በጽሑፎች ላይ ተጽፎ የሚገኝ ቢሆንም ቀስ በቀስ ከአገልግሎት ውጭ
እየሆነ መጣ። (ማቴዎስ 13:24–30፤ ሥራ 20:29, 30) እንዲያውም ከጊዜ በኋላ ብዙ
አንባቢዎች የቴትራግራማተንን ምንነት እንኳን ፈጽመው የማያውቁ ሆኑ። ዤሮም
በዘመኑ “አንዳንድ ደንቆሮዎች [ቴትራግራማተንን] በግሪክኛ መጻሕፍት ውስጥ
በሚያገኙበት ጊዜ ከፊደሎቹ መመሳሰል የተነሣ ΠΙΠΙ (የግሪክኛ ፊደላት ሲሆኑ “ፒፒ”
ተብለው ይነበባሉ) ብለው ያነቡ ነበር” ብሏል።
“በአዲስ ኪዳን” ወይም በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ላይም ተመሳሳይ ድርጊት
ተፈጽሟል። ፕሮፌሰር ጆርጅ ሐዋርድ በመቀጠል እንዲህ ብለዋል:- “በዕብራይስጥ ሆሄያት
ይጻፍ የነበረው የአምላክ ስም በሰፕቱጀንት ውስጥ በግሪክኛ ቃላት መተካት ሲጀመር
በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከሚገኙ የሰፕቱጀንት ጥቅሶችም ተወገደ። . . . ብዙም ሳይቆይ
መለኮታዊው ስም በአንዳንድ ቃላት ላይ ተለጣፊ ሆኖ ከመግባቱና በአንዳንድ ምሁራን
ዘንድ ከመታወቁ በስተቀር ከአሕዛብ ቤተ ክርስቲያን እይታ ፈጽሞ ተወገደ።”
የስሙ አስፈላጊነት
የለም፣ እንዲህ ማለት አንችልም። በኦቶራይዝድ ቨርሽን በሮሜ 10:13 አንጻር የገባው
የህዳግ ማጣቀሻ በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ የሚገኘውን ኢዩኤል 2:
32 ን ይጠቅሳል። ይህን ጥቅስ አውጥተህ ብትመለከት ጳውሎስ ለሮማውያን በጻፈው
ደብዳቤ ላይ የኢዩኤልን ቃል በቀጥታ ጠቅሶ እንደጻፈ መገንዘብ ትችላለህ። ኢዩኤል ደግሞ
በዕብራይስጡ በኩረ ጽሑፍ ያለው “የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል” ነው። (አዲሲቱ
ዓለም ትርጉም ) አዎን፣ ጳውሎስ የይሖዋን ስም መጥራት እንደሚገባን መናገሩ ነበር።
ስለዚህ በኢየሱስ ማመን ቢኖርብንም መዳናችን ግን ለአምላክ ስም ካለን አድናቆትና
ግንዛቤ ጋር በቅርብ የተሳሰረ ነው።
ይህ ምሳሌ የአምላክ ስም ከግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች በመወገዱ ምክንያት ብዙ ሰዎች ስለ
ይሖዋና ስለ ኢየሱስ ማንነት እንዴት ግራ ሊጋቡ እንደቻሉ ያሳያል። ለሥላሴ መሠረተ
ትምህርት መፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገ አያጠራጥርም!
ታዲያ ይሖዋ ስሙን ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያስወጡትን ሰዎች እንዴት ያያቸዋል? አንተ
ደራሲ ብትሆንና አንድ ሰው ሆን ብሎ ስምህን አንተ ከደረስከው መጽሐፍ ውስጥ ጨርሶ
ቢያጠፋ ስለዚያ ሰው ምን ይሰማሃል? በአጠራር ችግር በማሳበብም ሆነ የአይሁዳውያንን
ወግ በመከተል የአምላክን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚያስወጡ ተርጓሚዎች
ኢየሱስ “ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ” ያላቸውን ሰዎች ይመስላሉ።
(ማቴዎስ 23:24) በእነዚህ ትናንሽ ችግሮች ተሰናክለው የመላው ጽንፈ ዓለም የበላይ
የሆነውን አምላክ ስም ራሱ ካዘጋጀው መጽሐፍ ውስጥ በማስወጣታቸው በጣም ከባድ
የሆነ ችግር ፈጥረዋል።
መዝሙራዊው “አቤቱ [አምላክ ሆይ] ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ጠላት ስምህን ሁልጊዜ
ያቃልላልን?” ብሏል። — መዝሙር 74:10 አዓት
በተጨማሪም “ይሖዋ” የሚለውን ስም በ“ጌታ” መተካት አንድ በጣም ወሳኝ የሆነ ነገር
ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲወገድ ምክንያት ይሆናል። እርሱም የአምላክ የተጸውኦ ስም
ነው። ዘ ኢላስተረትድ ባይብል ዲክሽነሪ (ጥራዝ 1፣ ገጽ 572) “እንደ እውነቱ ከሆነ
ብቸኛው የአምላክ ‘ስም’ ያህዌህ ነው” ይላል።
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች አንዱ እንደሚከተለው በማለት ጠይቆ ነበር:- “ነፋስንስ በእጁ
የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን
ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፣ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው?” (ፊደላቱን ጋደል
አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።) (ምሳሌ 30:4) እኛስ የአምላክ ስም ማን እንደሆነ ልናውቅ
የምንችለው እንዴት ነው? ይህ በጣም አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ ነው። ፍጥረት አምላክ
ለመኖሩ ጠንካራ ማረጋገጫ የሚሰጠን ቢሆንም ስሙን ግን አይነግረንም። (ሮሜ
1:20) ፈጣሪ ራሱ ባይነግረን ኖሮ የአምላክ ስም ማን እንደሆነ ለማወቅ አንችልም ነበር።
የራሱ መጽሐፍ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሙን ገልጦልናል።
ታዲያ እንደ ያህዌህ ያሉት አጠራሮች የመጡት ከየት ነው? የመጀመሪያውን የአምላክ
ስም አጠራር ለማወቅ ሙከራ ያደረጉ ዘመናዊ ምሁራን የተሻሉ ናቸው ያሏቸው
አጠራሮች ናቸው። ሁሉም ሳይሆኑ አንዳንድ ምሁራን ከኢየሱስ ዘመን በፊት የነበሩት
አይሁዳውያን የአምላክን ስም ያህዌህ ብለው ሳይጠሩ አይቀሩም ብለው ያስባሉ። ይሁን
እንጂ በእርግጠኛነት ሊናገር የሚችል ሰው የለም። በዚህ ዓይነት አጠራር ሊጠቀሙም
ላይጠቀሙም ይችላሉ።
የይሖዋ ስምም ቢሆን ከዚህ የተለየ አይደለም። በዘመናችን የተለመደው ይሖዋ ወይም
ጅሆቫ የተባለው አጠራር ከመጀመሪያው የጥንት አጠራር ጋር አንድ ዓይነት ላይሆን
ቢችልም የስሙን አስፈላጊነት በምንም ዓይነት መንገድ አይቀንሰውም። ኢየሱስ
“በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ” ያለው ፈጣሪ፣ ሕያው የሆነው
አምላክና የሁሉ የበላይ የሆነው ልዑል ተለይቶ የሚታወቅበት ስም ነው።—ማቴዎስ 6:9
ታዲያ እንዲህ ሲባል ያህዌህ ከሚለው አጠራር ጋር በሚመሳሰል አጠራር መጠቀም ስህተት
ነው ማለት ነውን? በፍጹም አይደለም። ይሖዋ የሚለው አጠራር “በብዙ ቋንቋዎች ጆሮ
የተለመደ” አጠራር በመሆኑ ምክንያት በአንባቢዎች ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት ስለሚያገኝ
ብቻ ነው። ዋናው ነገር በስሙ መጠቀማችንና ስሙን ለሌሎች ማሳወቃችን ነው።
“ሕዝቦች ሁሉ ይሖዋን አመስግኑ! ስሙንም ጥሩ። ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ አሳታውቁ።
ስሙ ከፍ ያለ መሆኑን ተናገሩ።”—ኢሳይያስ 12:4 አዓት
[የግርጌ ማስታወሻዎች]
^ አን.5 በአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም ፣ 1984 እትም ላይ ተጨማሪ ክፍል
(አፔንዲክስ) 1A ተመልከት።
^ አን.22 በአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም የ 1984 እትም ተጨማሪ ክፍል
(አፔንዲክስ) 1A ተመልከት።
‘ሪቫይዝድ ሴጐንድ ቨርሽን’ በተባለው የፈረንሳይኛ መጽሐፍ ቅዱስ የቃላት መፍቻ በገጽ 9
ላይ የሚከተለው አሳብ ተሰጥቷል:- “አንዳንድ የቅርብ ጊዜ ትርጉሞች
የተጠቀሙበት ያህቬ የሚለው አጠራር በማያጠራጥር ሁኔታ የተረጋገጠ ሳይሆን በአንዳንድ
የጥንት መረጃዎች ላይ የተመሠረተ ነው። እንደ ኤልያስ (ኤልያሁ) ያሉትን መለኮታዊው
ስም ተካትቶ የሚገኝባቸውን የተጸውኦ ስሞች ከተመለከትን የአምላክ ስም
አጠራር ያሆ ወይም ያሁ ሊሆን ይችላል።”
አማርኛ – ይሖዋ
አዋባካልኛ – የሖዋ
ቡጎቱኛ – ጂሆቫ
ካንትንኛ – የህወዋህ
ዳንሽኛ– ጅሆቫ
ዳችኛ – ጅሆቫ
ኤፊክኛ – ጅሆቫ
እንግሊዝኛ ጅሆቫ
ፍጅያንኛ – ጅዮቫ
ፍንሽኛ – ጅሆቫ
ፈረንሳይኛ – ዢሆቫ
ፍቱናኛ – እሆቫ
ጀርመንኛ –ይሖቫ
ሀንጋሪያንኛ – ጅሆቫ
እግቦኛ – ጅሆቫ
ጣሊያንኛ – ጅኦቫ
ጃፓንኛ – ኢሆባ
ማውሪኛ – እሆዋ
ሞቱኛ – ኢየሆቫ
ሟላ ሟሉኛ – ጅሆቫ
ናሪንያሪኛ – ጅሆቫ
ኔምቤኛ –ጅሆቫ
ፔታትስኛ – ጅሁቫ
ፖላንድኛ –ጅሁቫ
ፖርቱጋልኛ – ጅኦቫ
ሮማኒያንኛ – ኢየሆቫ
ሳሞአንኛ –ኢየወቫ
ሶቶኛ –ጅሆቫ
ስፓንኛ – ጅሆቫ
ስዋሒሊኛ – የሖቫ
ስዊድንኛ – ጅሆቫ
ታሂቲያንኛ – ኢየሆቫ
ታጋሎግኛ – ጅሆቫ
ቶንጋንኛ – ጅሆቫ
ቤንጃኛ – ይሖቫ
ቆሳኛ – ኡይሆቫ
የሩባኛ – ጅሆፋህ
ዙሉኛ – ኡጅሆቫ
የጀርመን ፌደራል ባንክ በ 1967 አሳትሞ ባወጣው ዶቸ ታለር (የጀርመን ገንዘብ) የተባለ
መጽሐፍ ውስጥ የ“ይሖዋ” ስም የሚገኝበት እጅግ ጥንታዊ ከሆኑት ሳንቲሞች አንዱ
የሆነውና ከሲሌሲያው ግዛት የተገኘው የ 1634 ራይኽታለር ሥዕል ወጥቷል። መጽሐፉ
በሳንቲሙ ጀርባ ላይ ስላለው ሥዕል እንዲህ ብሏል።:- “የብርሃን ነጸብራቅ ከሚወጣበት
ጅሆቫ ከሚለው ስም ግርጌ ከዳመና ውስጥ የሚወጣና አክሊል የደፋ የሲሌስያ ካባ
ይታያል።”