You are on page 1of 8

ሁለተኛ ሳምንት

መጽሐፈ ልደቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ መጽሐፍ ብሎ ቁጥር ይላል ወበውእቱ መዋዕል

ወጽአ… ከመይጸሐፍ ኩሉ ዓለም

2. ወግ ታሪክ ይላል፡፡ ሳማ ለዳቤር ትካት…

ሀገረ መጽሐፍ ይላል ፡፡

3. ልደቱ ለእግዚእነ አለ ብዙ ልደታት አሉና ከነዚያ ሲለይ ነው፡፡ ለምሳሌ ልደተ አዳም
እምድር፣ ልደተ ኄዋን እምገቦ፣ ልደተ ሙታን እመቃብር ነው፡፡

ምዕራፍ አንድ

 ጠቅላላ 25 ቁጥሮች እና 2 ንኡሳን ክፍሎች አሉት እነሱም፡-


1. 1-17 ስለ ሐረገ ትውልድ፣
2. 18-25 ስለ ልደተ ክርስቶስ ናቸው፡፡
ወንጌላውያን ሲጽፉ ራሳቸውን መሠረት አላደረጉም፡፡ ምክንያቱም ጌታ የተናገረውና
የሰራውን እንጂ ከራሳቸው አንቅተውና ስለራሳቸው አይጽፉምና፡፡ አያያዥ ቃላትን
ከመጠቀም በቀር የራሳቸውን ሀሳብና ቃላት መሠረት አያደርጉም፡፡
ዮሐ.ም. 3 ቁ.1
1. የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ተውልድ መጽሀፍ
ሀ. ለምን ዳዊትንና አብርሃምን ለይቶ አርእስት አደረጋቸው?
ሀ.1. የሚበዛ ትንቢትን የተነገረ ለእነዚህ ነውና፡፡
ሀ.2. ተስፋ ለተስፋ ለማነጻጸር ነው፡፡ ኦ.ዘፍ ም.22 ቁ.18፣ መዝ. 131(132) ቁ.11
ሀ.3. ዳዊት ሥርወ መንግስት አብርሃም ሥርወ ሃይማኖት ነውና፡፡
ሀ.4. ያላመኑት ያመኑትን ክርስቶስ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ መሆኑን ሠፍራችሁ
ቆጥራችሁ አስረክቡን ብለዋቸው ነበርና፡፡
ሀ.5. ክፍለ ዘመንን ለመናገር ፈልጎ ነው፡፡
ለ. ለምን ለዳዊትን ከአብርሃም አስቀደመው?
ለ.1. አባቱን አያውቅ አያቱን ናፈቀ ይሉኛል ብሎ ነው፡፡
ለ.2. ጌታን የዳዊት ልጅ ዳዊትን የአብርሃም ልጅ ማለቱ ነው፡፡
ለ.3. የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ ዋዌ የቀረው ነው፡፡
ለ.4. የዳዊት ልጅ የጌታ ጥቅል ስሙ ነው፡፡ ማቴ.ም.20.ቁ.30
ለ.5. ከሚመጣው ሀሳብ ለማያያዝ ፈልጎ ነው፡፡
ለ.6. እስራኤል እግዚአብሔር ፈጣሪያቸው ዳዊት ንጉሳቸውን ሲያነሱላቸው ስለሚወዱ ነው፡፡
ት/ሆሴ ም.3 ቁ.5፣ ማቴ. ም. 12 ቁ.13
ሐ. መጽሐፍ ሲል ምን ማለቱ ነው?
- የልደቱ ሐረግ ማለት ነው፡፡ (ሉቁ.ም.2.ቁ.1)
- የልደቱ ወግ ማለት ነው፡፡ (መ.አያ.ም.15.ቁ.13)

2. አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፣ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን


ወለደ፡፡
ሀ.1. የአብርሃምን ታሪክ የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ እናገኘዋለን? (ኦ.ዘፍም.11
ቁ፣25)
ሀ.2. ለአብርሃም ክርስቶስ ከሱ ዘር እንደሚወለድ የተገለጸው የት ነው? (ኦ.ዘፍ ም.22.
ቁ 18 “የምድር አሕዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ”)
ሀ.3. አብርሃም ይስሐቅን ሊሰዋው በተዘጋጀ ጊዜ ምሳሌ የሚሆነው ለምን ለምን ነው?
- አብርሃም የእግዚአብሔር አብ፣ ይስሀቅ የእግዚአብሔር ወልድ ምሳሌ ነው፡፡
- በሌላ መንገድ ደግሞ ኦ.ዘፍ ም.22 ላይ እንደተገለጸው 3ቱ ቀናት የረቡዕ፣ ሐሙስና
አርብ ምሳሌዎች፣ ይስሐቅ የአዳም፣ በግ የወልድ እግዚአብሔር ሕቱም ዕፀ ሳቤቅ
የሕቱም ማሕጸን፣ እንጨት የመስቀል፣ ወቅለምት የሥልጣን እግዚአብሔር፣ 2ቱ
ብላቴኖች የ2ቱ ወንበዴዎች፣ 6ቱ ቀናት የ6ቱ ቀናት ሕማማት ምሳሌ ናቸው፡፡
ሀ.4. የይስሐቅን ታሪክ የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ እናገኘዋለን? (ኦ.ዘፍ.ም21 ቁ.3)
ሀ.5. ለይስሀቅ ክርስቶስ ከሱ ዘር እንደሚወለድ የተጠቀሰው የት ነው?
- ኦ.ዘፍ 21፡12 “በይሥሐቅ ዘር ይጠራልሃል፡፡”
- ኦ.ዘፍ 26፡4 “የምድር አሕዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፡፡”
ሀ6. ይስሀቅ ክርስቶስን የሚመስለው በምኑ ነው?
- ይስሐቅ ለመስዋዕት ቀረበ ክርስቶስም መሥዋዕት ሆኖ ቀርቧል፡፡
- “ሀ.3”ን ተመልከት (ቁ.2)
ሀ.7. የያዕቆብን ታሪክ የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ እናገኘዋለን?
- ኦ.ዘፍ 25፡21
ሀ.8. ለያዕቆብ ክርስቶስ ክሱ ዘር እንደሚወለድ የተገለጸው የት ላይ ነው?
- ኦ.ዘፍ. 28፡14 “የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ፡፡”
ሀ.9. ያዕቆብ የጌታ ምሳሌ የሚሆነው በምኑ ነው?
- ኦ.ዘፍ ም.29 ላይ እንደተገለጸው ያዕቆብ የጌታ፣ ደንጊያው የመርገመ ሥጋ የመርገመ
ነፍስ፣ ውሃው የጥምቀት፣ በጎች የምዕመናን፣ እረኞች የነቢያት (ካህናት) ምሳሌዎች
ናቸው፡፡
ሀ.10. የይሁዳን ታሪክ የትኛው የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል ላይ እናገኘዋለን?
- ኦ.ዘፍ 29፡35
ሀ.11. ለይሁዳ ክርስቶስ ከሱ ዘር እንደሚወለድ የተጠቀሰው የት ላይ ነው?
- ኦ.ዘፍ 49፡10 “በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል
ገዢ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል፡፡
ሀ. 12. ይሁዳ በክርስቶስ ሥራ ውስጥ ምሳሌነቱ በምኑ ነው?
- ኦ.ዘፍ ም.38 ላይ እንደተገለጸው ይሁዳ የእግዚአብሔር አብ፣ ኤራስ አዶሎማዊ
የቅ/ገብርኤል፣ የፍየል ጠቦት የእግዚአብሔር ወልድ፣ ቀለበት የሃይማኖት፣ በትር
የመስቀል፣ አምባር የአክሊል ሶክ፣ ትዕማር የቤተተ ምኩራብ አንድም ትዕማር
የምኩራብ፣ ምኩራብ የቤተክርስቲያን ምሳሌዎች ናቸው፡፡
ሀ.13. ይሁዳንና ወንድሞቹን ብሎ ወንድሞቹንም ለምን ጨምሮ ጠራቸው?
- ጌታ ከ12ቱ ነገረ ይወለዳልና፣
- አይሁድ ወንጌልን ከመቀበል ወደኋላ እንዳይሉ፣
- ለምሳሌው ይመቸው ዘንድ ነው (ከአስራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ያልተወለደ ምድረ
ርስትን አይወርስምን ምሳሌው፡- 12ቱ ነገደ እስራኤል የ12ቱ ሐዋርያት፣ ያዕቆብ፣
የጌታ ምድረ ርስት የመንግስተ ሰማይ ምሳሌዎች ናቸው፡፡
3. ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፡፡
ሀ.14. ለምን ትዕማርን ከሴቶች ሁሉ ለይቶ አነሳት (ጠቀሳት)?
- ልትጠራ የሚያስፈልግበት ምክንያት ስላለ ነው፡፡
- ትዕማር በሃይማኖት እንደከበረች አሕዛብም በሃይማኖት እንደሚከብሩ ለማስረዳት፣
- በእስራኤል ዘለፋ ለአሕዛብ ተስፋ ለመሆን ምክንያቱም እስራኤላውያን በልደተ ሥጋ
ይመካሉና ለእኛስ ክርስቶስ ከትዕማር ተወልዶልን የለምን ለማለት፣
- ክርስቶስ በዳዊት ከበረ ይላሉና ዳዊት በክርስቶስ ከበረ እንጂ እሱማ የትዕማር ልጅ
አይደለምን ለማለት፡፡
ሀ.15. ትዕማር የምን የምን ምሳሌ ናት?
- “መ.3” ተመልከት (ቁ.2 ላይ)
ሀ.16. የትዕማርን ታሪክ በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናገኘዋለን?
- ኦ.ዘፍ. ም. 38
ሀ. 17. ፋሬስንና ዛራን 2ቱንም ለምን ጠቀሳቸው?
- ምሳሌውን ለመግለጥ ያመቸው ዘንድ ነው፡፡ ምሳሌውም በኦ/ዘፍ.28 እና በኦ.ዘፍ. 14
ላይ እንደተገለጸው ፋሬስ የኦሪት፣ ዛራ የወንጌል፣ ኅብስትና ወይን የቅዱስ ቁርባን፣
መልከ ጼዴቅ የካህናት፣ አብርሃም የምዕመናን፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት፣ የዛራ ልጅ
የቀሳውስት፣ ቀዩ ሀር የሥጋው ደሙ ምሳሌዎች ናቸው፡፡
ሀ.18. ኤስሮም ከፋሬስ እንደተወለደ የሚገልጸው የብሉይ ኪዳን ክፍል የትኛው ነው?
- መጽ.ሩት፣ 4፡18
4. ኤስሮምም አራምን፣ አራምም አሚናዳብን፣ አሚናዳብም ነእሶንን፣ ነአሶንም ሰልሞንን
ወለደ፡፡

5. ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፡፡


ሀ.19. ራኬብን ከሴቶች ለይቶ ለምን አነሳት?
- የዚህች ሴት ስም መጠቀሱ ምክንያት ስለአለው ነው፡፡ ምክንያቱም በቁ.3 “ሀ.1”
ተመልከት
ሀ.20. ራኬብ የምን ምሳሌ ነች?
- መጽ.ኢያ. ም2 ላይ እንደተገለጸው ራኬብ የአሕዛብ፣ ሰልሞንና ካሌብ የኦሪትና
የወንጌል፣ ኢያሱ የጌታ፣ ኢያሪኮ የምዕመናን፣ አሕዛብ የአጋንንት፣ መስኮት የከናፍረ
ምዕመናን፣ ሐር የሥጋወደሙ ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ምሳሌዎች ናቸው፡፡
ሀ.21. ሩትን ከሴቶች ለይቶ ለምን ጠቀሳት?
- የዚህች ሴት ስም መጠቀሱ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡
ሀ.22. የሩትንና የቦኤዝን እንዲሁም የኢዮቤድን ታሪክ የት እናገኘዋለን?
- መጽ/ሩት 1፡4
6. ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፡፡ እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፡፡
ሀ.23. የዳዊትን ታሪክ የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ እናገኘዋለን?
- 1ኛ. ሳሙ፣ 16፡1፣ 1ኛ. ነገ. 2እና 1ኛ ዜና 11፡4
ሀ.24.ለዳዊት ክርስቶስ ከሱ ዘር እንደሚወለድ የተገለጸው የት ነው?
- መዝ.131 (132) ቁ.11 “ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ፡፡”
ሀ.25. ንጉሥ ዳዊት ብሎ ቅጽል ለምን ጨመረለት?
- ዳዊት ሥርወ መንግስት ስለሆነ ነው፡፡ ኦ.ዘፍ. 49፡10
ሀ26. ለእሴይ የተነገረው ትንቢት የት ይገኛል?
- ኢሳ. 11፡1 “ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል ከሥሩን ቁጥቋጦ ያፈራል”
7. ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፡፡ ሮብዓምም አቢያን ወለደ
አቢያም አሣፍን ወለደ፡፡
ሀ.27. ከኦርዮ ሚስት ብሎ ለመግለጽ ለምን ፈለገ?
- ማማውን ግርማውን ቢፈራ ኃጢያቱን ሳይገልጽበት ቀረ እንዳይሉት፤
- ለሰው ፊት የማያዳላ ሀዋርያ መምህርና ገሳጭ እንደሆነ ለማጠየቅ፤
- በተነሳህያን ፍርሀት እንደሌለባቸው ለማጠየቅ፤
- በዐቂበ ሕግ ይመካሉና እናንተስ የሕግ አፍራሽ ልጆች አይደላችሁምን ለማለት፤
- ክርስቶስ በዳዊት ከበረ ይላልና ዳዊት በክርስቶስ ከበረ እንጂ ለማለት
ሀ.28. የኦርዮንና የሚስቱ የቤርሳቤህን ታሪክ የት እናገኘዋለን?
- 2ኛ ሳሙ. ም11
ሀ.29. የሰሎምንን ታሪክ በየትኛው የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል እናገኘዋለን?
- 1ኛ ነገ.ም1-11 እና 1ኛ ዜና ም.22 2ኛ መ/ሳሙ. ም12 ቁ. 24ልደቱ
ሀ.30. ለነቢዩ ዳዊት በሰሎሞን በኩል የተነገረው ትንቢት ምን የሚል ነው?
- 2ኛ. ሳሙ. 7፡13 “ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሳለሁ
መንግስቱንም አጸናለሁ፡፡”
ሀ.31. የዳዊት መንግሥት ምሳሌነቱ ለየትኛው መንግሥት ነው?
- ለክርስቶስ መንግሥት (ኢሳ. 9፡7፣ ሉቃ 1፡32)
ሀ.32. የሮብዓም፣ የአቢያ፣ የአሳፍ ታሪክ በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ይገኛል፡፡
- 1ኛ. ነገ 11፡43፣ 12፡21፣ 2ኛ ዜና 9፡31፣ 11፡4፣
- 2ኛ ዜና ም.13 (አቢያ)፣
- 1ኛ.ነገ 15፡9-24፣ ዜና 14፡1 (ኢሳ.)
8. አሳፍም ኢዮሳፍጥን ወለደ ኢዮሳፍጥም ራዮራምን ወለደ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፡፡
ሀ.33. ኢዮሣፍጥ የኢዮራም የዖዝያንን ታሪክ የት እናገኘዋለን?
- 2ኛ. ዜና 17፡1፣ 1ኛ ነገ22፣ 2ኛ ነገ ም.3 (ኢዮሳፍጥ)
- 2ኛ. ዜና 21፣ 2ኛ ነገ 8፡16-24 (ኢዮራም)
- 2ኛ. ነገ 14፡21-22፣ 15፡1-7፣ 2ኛ ዜና ም26 (ዖዝያንን (አዛርያስ))
ሀ.34. በ1ኛ. ዜና 3፡11 ላይ የተዘረዘሩት የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣
የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ ለምን ተተው?
- አካዝያስን፣ ኢዮአስን፣ አሜስያስን የሚጽፍም የሚጽፍም ይገኛል፡፡
- ያልጻፈ ከሆነ ግን ግድፈተ ፀሐፊ ነውው፡
ሀ.35. የአካዝያስ የኢዮአስ የአሜስያስ ታሪክ የትኛው የብሉይ ኪዳን ክፍል ላይ ይገኛል?
- 2ኛ. ዜና 22፡1-9 (አካዝያስ)
- 2ኛ ነገ ም.11 እና ም.12፣ 1ኛ ዜና ም.22 ቁጥር10፣ ም.24 ቁ. 27 (ኢዮአስ)
- 2ኛ. ነገ ም.14 ቁ. 1-22፣ 2ኛ ዜና ም. 25 (አሜስያስ)
9. ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ ኢዮአታንም አካዝን ወለደ
ሀ.36. የኢዮአታምና የአካዝን ታሪክ በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናገኘዋለን?
- 2ኛ. ነገ 15፡5፣ 32-38፣ 2ኛ. ዜና 26፤21፣ 27፡9 ኢሳ. 1፡1፣ ት/ሚክ. 1፡1
(ኢዮአታም)
- 2ኛ. ነገ 16፡ 2ኛ. ዜና 28 (አካዝ)
10. አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ ምናሴም አሞጽን ወለደ
ሀ.37.የሕዝቅያስን የምናሴንና የአሞጽን ታሪክ በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናገኘዋለን?
- 2ኛ. ነገ 18፡9፤ 10፡13፣ 2ኛ.ነገ18፡5፣ 20፡12-13፣ 18፡20፣ 2ኛዜና. 29-32፣
ት/ኢሳ. ም.36-39 (ሕዝቅያስ)
- 2ኛ. ነገ. 20፡21፣ 21፡1-18፣ 2ኛ ዜና. 33፡1-10፣ ት.ኤር 15፡4 2ኛ ዜና 33፡11-20
(ምናሴ)
- 2ኛ. ነገ 21፡18-26፣ 2ኛ ዜና 33፡20-25 (አሞጽ)
11. አሞጽና ኢዮስያስን ወለደ ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ

ሀ.38. የኢዮስያስን የኢኮንያንና የባቢሎን ምርኮ ታሪክን የት እናገኘዋለን?


- 2ኛ.ዜና 34 እና 35፣ 2ኛ. ነገ 21፡24፣ 23፡30 (ኢዮስያስ)
- 2ኛ ነገ. 24፡8-17፣ ሕዝ. 1፡2፣ መ.አስ 2፡6፣ 1ኛ ዜና.3፡16-17፣ ት.ኤር 22፡24-30
(ኢኮንያን (ዮአኪን)) 2ኛ ነገ.25 እና 2ኛ ዜና 36 (የባቢሎን ምርኮ)
ሀ.39. የኢኮንያን (ዮአኪን) አባት ኢዮአቄም ሳለ አያቱን ኢዮስያስን ለምን አባት አደረገው?
- የልጅ ልጅን ልጅ ያለው ልማድ ይዞ ነው፡፡ (ኦ.ዘፍ 31፡28) (የላባና የያዕቆብ)
እንደነገሰ የተደረገውን ለልደቱ ሰጥቶ የተናገረው ልማድ ይዞ ነው (ኦ.ዘፍ 15፡13፣
ኦ./ዘጸ 12፡41)
ሀ.40.ለምን አጎቶቹን ወንድሞቹ አላቸው?
- ልማድ ይዞ ነው፡፡ (ኦ.ዘፍ 13፡8)
- አጎቶቹ ሴዴቅያስና ኢዮአክስ ይባላሉ፡፡ ት.ኤር 36
- የባቢሎን ምርኮ መጠቀሱ ለትምህርትና ለተግሳጽ ለምሳሌም እንዲሆን ነው፡፡
12. ከባቢሎንም ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ
ሀ.41.ከባቢሎን ምርኮ መልስ፣ የስካትያልና የዘሩባቤልን ታሪክ የት እናገኘዋለን?
- ዕዝ. ም1-2 (ከባቢሎን ምርኮ መልስ)
- ዕዝ. 5፡2 (ስላትያል)
- 1ኛ. ዜና 3፡16-19፣ ዕዝ 2፡3፡2፣ ት;ሐጌ1፡1እና 14፣ ት/ዘካ 4፡6-10 (ዘሩባቤል)
ሀ.42.የባቢሎን ምርኮ የምን ምሳሌ ነው?
- ወደ ባቢሎን መግባት- ወደ ሲዖል መግባት፣
- እንደገና ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም መግባት ወደ ገነት መግባት ምሳሌ ነው፡፡
13. ዘሩባቤልም አብዮድን ወለደ አብዮድም ኢልያቄምን ወለደ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፡፡
14. አዛርም ሳዶቅን ወለደ ሳዶቅም አኪምን ወለደ አሚምም ኤልዮድን ወለደ፡፡
15. ኤልዮድም አልዓዛርን ወለደ አልዓርንም ማታንን ወለደ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፡፡
16. ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ፡፡
ሀ.43. ለምን ማርያምን በቅጽል አመጣት?
- በሀገራቸው ሴትና ወንድን አቀላቅሎ መቁጠር የለምና ሥርዓት እንዳይፋለስ
- በልማድ በ3 ቤት እንድታጭ መደረገጓን ለማመልከት ነው (ኦ.ዘ ፍ27፡1-11)
ሀ.44. የዮሴፍና የማርያም ዝምድና ምን ዓይነት ነው?
- አልዓዛር ማትያንንና ቅስራን ይወልዳል፣ ማትያት ያዕቆብን ያዕቆብ ዮሴፍን
ይወልዳል፡፡
- ቅስረ ኢያቆምን ኢያቄም እመቤታችንን ይወልዳል፡፡
ሀ.45. ዮሴፍ ለምን ታጨላት?
- በመከራዋ ጊዜ ሊከተላለት፣ ከርስት ገብቶ ሊቆጠርላት፣ ከውግረት ሊያድናት፣ ከዕፀት
ሊያድናት
- ለጊዜው የሚገያገባ መስሎት ነበር (ሳዊሮስ ዘእስሙናዲን፣ ያዕቆብ ዘሮሃ)
- ሥላሴ ንጽሕናውን ባወቁ አስጠብቀውታል (አትናቴዎስ፣ ጎርጎርዮስ፣ ዘኒሲስ፣
ዮሐንስ አፈወርቅ)
17. እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት 14 ትውልድ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን
ምርኮ 14 ትውልድ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ 14 ትውልድ ነው፡፡
ሀ.46.እንዴት 14 መጣ (እያንዳንዱ ሲቆጠር)
- አብርሃም- ይስሐቅ- ያዕቆብ - ይሁዳ - ፋሬስ - ኤስሮም - አራም - አሚናዳብ- ነአሶን
ሰልሞን - ቡዔዝ - ኢዮቤድ - ዕሴይ- ዳዊት
- ዳዊት - ሰሎሞን- ሮብዓም- አቢያ- አሳፍ- ኢዮሳፍጥ- ኢዮራም - ዖዝያን ኢዮአታም -
አካዝ- ሕዝቅያስ- ምናሴ - አሞጽ - ኢዮስያስ - ኢኮንያን
- ኢኮንያን - ሰላትያል- ዘሩባቤል- አብዮድ - ኤልያቆም - አዘር- ሳዶቅ- አኪም- ኤልዩድ
- አልዓዛር - ማታን - ያዕቆብ - ዮሴፍ - ክርስቶስ
o ከፍ ብሎ 46 ዝቅ ብሎ 41 ቢል የፀሐፊ ግድፈት ነው፡፡
o ተርትቶ መቁጠር የሶስትነት ደምሮ መቁጠር የአንድነት ምሳሌ ነው፡፡
 14+ 17 +12 = 43
 14+ 17+ 14 = 45
 14 + 14+ 14 = 42
 14 + 17 + 13= 43

You might also like