You are on page 1of 15

በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

ቅድስት፡ ሥላሴ፡ መካነ፡ አእምሮ፡


ክፍለ-ትምህርት: - ሥነ-መለኮት ፡ (ቲኦሎጂ) ፡፡
ማዕረግ ፡- የመጀመሪያ፡ ማዕረግ ፡ (ድግሪ) ፡፡
ርእስ ፡- በወርቶዶክሳዊት ፡ ቤተክርስቲያን ፡ የክህነት ፡ አገለግሎት ፡ የሚሰጥ ፡ አንድ ፡ ካህን ፡
በሆስፒታል ፡ ውስጥ ፡ መንፈሳዊ ፡ ፍዚሽያን ፡ ቢሆን ፤ ምንዓይነት ፡ ተልዕኮ ፡ ሊኖረው ፡ ይችላል?
ወይም ፡ ምንዓይነት ፡ ተልዕኮ ፡ ይኑረው ፡ የሚለውን ፡ ሐሳብ ፡ ከሐዋርያዊት ፡ የቤተክርስቲያን ፡
ተልዕኮ ፡ አንጻር ፡ ጠቅለል ፡ አድርጋችሁ ፡ በማዘጋጀት ፡ አቅርቡ ፡ የሚል ፡ ነው ፡፡

የተሰጠ ፡ ሥራ ፡ II : በትምህርተ ኖሎት ፡፡


የቡድን ፡ ኣባላት ፡ ስም:-…………………..…….……………..የመለያ ፡ ቁጥር
 ስብሐት ፡ ገበየሁ፡-…………....................................................................E-0180/12
 ሲሳይ ፡ ፀዳሉ፦…………....................................................................... E-0183/12
 ዮሐንስ ፡ አይነኩሉ፦ …………................................................................E-0213/12
 ኪዳኔ ፡ ኃይሉ፦………….........................................................................E-0751/12
 አብርሃም ፡ ደሴ፦…………......................................................................E-0083/12
 ዘካርያስ ፡ ወንድምነህ፦…………..............................................................E-0216/12
 ደርቡሽ ፡ የኔፀጋ፦…………......................................................................E-0119/12
 ፍቃዱ ፡ መኮንን፦………….....................................................................E-0136/12

 ክፍል፦…………………………………………………………………..IVC1 : እና ፡ IVC2

የተሠራው ሥራ ፡ የሚሰጣቸው ፡ መምህር: - ቆሞስ ፡ አባ ፡ ገብረሃና ገብረጻድቅ (M.PTH) ፡፡


ጳጉሜን ፡ ፳፻፲ወ፭ ፡ ዓ.ም

አዲስ ፡ አበባ ፡ ኢትዮጵያ


I
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

Contents
መቅድም፦ ...................................................................................................................................................... 1
መግቢያ፦ ...................................................................................................................................................... 3
፩. በኦርቶዶክስ ፡ ተዋህዶ ፤ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ፦ ................................................................ 5
፩.፩. ኦርቶዶክሳዊ ፡ የክህነት ፡ አገልግሎት ፡ በሆስፒታሎች፦ ............................................................. 7
፩.፪. ዶክተር (የሕክምና ፡ ባለሙያ) ፡ የሆኑ ፡ ኦርቶዶክሳዊ ፡ ካህናት ፡ ሚና ፡ እና ፡ ሃላፊነት ፡
በሆስፒታሎች፦ .......................................................................................................................................... 8
፩.፫. የኦርቶዶክሳዊ ፡ ዶክተር (የሕክምና ፡ ባለሙያ) ፡ ተልዕኮ ፡ በሆስፒታሎች፦ ................................. 9
፩.፬. በሕክምና ፡ ሙያ ፡ የተሠማሩ ፡ ኦርቶዶክሳዊ ፡ ካህናት ፡ ሊአደርጋቸው ፡ የሚገቡ ፡ ነገሮች፦ 11
ማጠቃለያ፦ .................................................................................................................................................. 12
ማጣቀሻ ፡ መጻሕፍት፦ ................................................................................................................................ 13

2
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

መቅድም፦
በዚህ ፡ ፈተና ፡ በበዛበት ፡ ዓለም ፡ የኦርቶዶክሳውያን ፡ አገለጋዮች ፡ ማለትም (ሊቀ ፡
ጳጳስት ፣ ኤጲስቆጶሳት ፡ ካህናት ፡ እና ፡ ዲያቆናት ፡ እንዲሁም ፡ ምዕመናን ፡ ወምዕመናት) ፡
ዓለም ፡ በዘረጋቻቸው ፡ የተለያዩ ፡ የሕዝብ ፡ መገልገያ ፡ ቦታዎች፦ ማለትም ፡ በእሥርቤቶች ፤
በመንግሥት ፡ የፖለቲካ ፡ ሥልጣን ፡ ውስጥ ፣ በፍርድቤቶች ፣ በሕብረተሰቡ ፡ የንሮ ፡ ዘይቤ
፡ ውስጥ ፣ በንግድ ፡ ድርጅቶች ፣ በሆስፒታሎች ፣ በቤተሰብ ፡ መካከል ፡ ወዘተ ፡ በሀገር ፡
ውስጥም ፡ ሆነ ፡ በውጩ ፡ ዓለም ፡ የሚኖሩ ፡ አገልጋዮች ፡ በወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ማከላዊነት
፡ የአገልግሎት ፡ ተልዕኳቸው ፡ ምን ፡ መምሰል (መሆን) ፡ አለበት ፡ የሚለውን ፡ ተኩረት ፡
በመስጠት ፡ ወቅቱ ፡ በሚፈልገው ፡ ልክ ፡ ለማስቀመጥ ፡ ዘመኑን ፡ በዋጀ ፡ መልኩ ፡
የአገልጋዮችን ፡ ሐዋርያዊ ፡ ተልዕኮ ፡ በመለየት ፡ ግንዛቤ ፡ መፍጠርና ፡ ማስጨበጥ ፡ አስፈላጊ
፡ ነው ፡፡ ስለሆነም ፡ አንድ ፡ የቤተክርስቲያን ፡ አገለጋይ ፡ በተሰማራበት ፡ የሥራ ፡ ዘርፍ ፡
ሁሉ ፡ በወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ሐዋርያዊ ፡ ተልዕኮ ፡ በመያዝ ፡ የቤተክርስቲያኗን ፡ ተልዕኮና
፡ ዓላማ ፡ በወንጌል ፡ ማወጅና ፡ መተርጎም ፡ እንዳለበት ፡ በየዕለቱ ፡ ኦርቶዶክሳዊት ፡
ቤተክርስቲያናችን ፡ ታሳስባለች ፡፡

ይህ ፡ ማለት ፡ አንድ ፡ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ ፡ የተሰጠው ፡ አገልጋይ ፡


በመጀመሪያ ፡ መንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ምንድን ፡ ነው? የሚለውን ፡ መሰረታዊ ፡ ጥያቄ ፡
ማውቅና ፡ መመለስ ፤ በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ውስጥ ፡ የሚኖረውን ፡ ሚና ፡ ለማወቅ ፡
የመጀመሪያው ፡ እርምጃ ፡ ነው ፡፡ መንፈሳዊ ፡ አገልግሎት፦ “መንፈሳዊ ፡ (Spiritual)” ፡ እና ፡
“አገልግሎት ፡ (Service)” ፡ የሚሉትን ፡ ቃላቶች ፡ የያዘ ፡ ሲሆን ፡ “መንፈሳዊ” ፡ የሚለው ፡
ገላጭ ፡ የአገልግሎቱን ፡ ዓላማና ፡ መሪ ፡ የሚያሳይ ፡ ነው ፡፡ የመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡
ዓላማም ፡ የሰው ፡ ልጆች ፡ ድኅነት ፡ ነው ፡፡ መሪውም ፡ ከሦስቱ ፡ አካል ፡ አንዱ ፡ የሆነው ፡
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ነው፡፡ በአጠቃላይ ፡ የሰው ፡ ልጆች ፡ ለመንግሥተ ፡ ሰማያት ፡ እንዲበቁ ፡
የሚደረግ ፡ ማንኛውም ፡ እንቅስቃሴ ፡ “መንፈሳዊ ፡ አገልግሎት” ፡ ሊባል ይችላል ፡፡ ይህም :
የሕይወትን : ቃል : ያላወቁ : ወገኖች : እንዲያውቁና : እንዲያምኑ : ማድረግ ፣ ያመኑትን :
ደግሞ : እንዲጸኑና : መንፈሳዊ : ትሩፋት ፡ እንዲሠሩ ፡ ማድረግን ፡ ያካትተ ፡ ነው ፡፡

የመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ መሰረቱ ፡ በቅዱሳት ፡ መጻሕፍት ፡ የተገለጠው ፡


የእግዚአብሔር ፡ ፈቃድና ፡ ፈቃዱን ፡ ለመፈጸም ፡ የሚያተጋን ፡ አምላካዊ ፡ መመሪያ ፡ ነው ፡
፡ ይህም ፡ ከዘመነ ፡ አበው ፡ ጀምሮ ፡ በዘመነ ፡ ኦሪት ፣ በቅዱሳን ፡ ነቢያት ፡ አድሮ ፡ የመንፈሳዊ
፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮንና ፡ መመሪያን ፡ የሰጠው ፤ በፍፁም ፡ አንድነትና ፡ በልዩ ፡ ሦስትነት
፡ የሚመሰገን ፡ አምላካችን ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡፡ በዘመነ ፡ ሐዲስም ፡ ከሦስቱ ፡ አካላት ፡
አንዱ ፡ አካል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ በሥጋ ፡ ከእመቤታችን ፡ ድንግል
፡ ማርያም ፡ ተወልዶ ፤ ግዕዘ ፡ ሕጻናትን ፡ ሳያፋልስ ፡ በትሕትና ፡ አድጎ ፤ መንፈሳዊ ፡
አገልግሎት ፡ ምን ፡ መምሰል ፡ እንዳለበት ፡ በተግባር ፡ አስተምሮ ፡ ለቅዱሳን ፡ ሐዋርያት ፡
አብነት ፡ የሆነ ፡ የአገልግሎት ፡ ተልዕኮና ፡ መመሪያ ፡ ሰጥቷቸዋል ፡፡ አብነት ፡ የሆነው ፡
የተልዕኮ ፡ ቃል ፡ “እንሆ ፡ እኔ ፡ እንደ ፡ በጎች ፡ በተኲላዎች ፡ መካከል ፡ እልካችዃለሁ” ፡
የሚለው ፡ ሲሆን ፤ መሪ ፡ መመሪያው ፡ ደግሞ ፡ “ስለዚህ ፡ እንደ ፡ እባብ ፡ ልባሞች ፡ እንደ
1
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

፡ ርግብም ፡ የዋሆች ፡ ሁኑ” ፡ የሚለው ፡ ታላቅ ፡ ቃል ፡ ነው ፡ (ማቴ ፡ ፲ ⸭ ፲፮) ፡፡ ጌታችን ፡


ይህንን ፡ ተልዕኮና ፡ መመሪያ ፡ የሰጠው ፡ ለጊዜው ፡ ለደቀ ፡ መዛሙርቱ ፡ ሲሆን ፤ ኋላም ፡
በእነርሱ ፡ እግር ፡ ተተክተው ፡ በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ለሚሳተፉ ፡ ሁሉ ፡ ነው ፡፡

በመቀጠልም ፡ በክርስቶስ ፡ ራስነት ፡ የተመሠረተች ፡ ወርቶዶካሳዊት ፡ ቤተክርስቲያን


፡ የተመሠረተችበትን ፡ ዓላማና ፡ ተልዕኮ ፡ ለማስፈፀም ፡ አምነው ፡ የተቀበሏትን ፡ ልጆቼ ፡ ብላ
፡ በመቀበል ፡ ከልጆቿም ፡ ምካከል ፡ ለክህነት ፡ የተምረጡትን ፡ በማጽናት ፡ የተላያዩ ፡
ተልዕኮችን ፡ በመስጠት ፡ ወደዓለም ፡ ልካለች ፡ እየላከችም ፡ ነው ፤ ስትልክም ፡ ትኖራለች ፡፡
ነገር ፡ ግን ፡ እነዚህ ፡ አገልጋዮች ፡ ለመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ወደዓለም ፡ በሚሠማሩበት ፡
ጊዜ ፡ የአገልግሎት ፡ ተልዕኳቸው ፡ ከቤተክርስቲያኗ ፡ ዐላማ ፡ አንጻር ፡ ምን ፡ መሆን ፡ አለበት
፡ ወይም ፡ ምን ፡ መምሰል ፡ አለበት ፡ የሚለው ፡ ፍሬ-ሐሳብ ፡ በየዘመኑ ፡ በተሱ ፡ የተለያዩ ፡
መንፈሳዊ ፡ አገልጋዮች ፡ ሐተታ ፡ ተሰቶበታል ፡፡ ሰለሆነም ፡ ይህንን ፡ መሠረታዊ ፡ ሐሳብ ፡
መነሻ ፡ በማድረግ ፡ እኛ ፡ የቅድስት ፡ ሥላሴ ፡ መካነ ፡ አእምሮ ፡ የአራተኛ ፡ ዓመት ፡ የቲኦሎጂ
(Theology) ፡ ተማሪዎች ፡ በቡድን ፡ ሆነን ፡ አንድ ፡ የቤተክርስቲያን ፡ አገልጋይ ፡ ካህን ፡
የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ ፡ ይዞ ፤ በተጨማሪም ፡ በሕክምና ፡ ሙያ ፡ መንፈሳዊ ፡
ፊዚሺያን ፡ (Spiritual Physician) : ቢሆንና ፡ በሆስፒታል ፡ ውስጥ ፡ ቢመደብ ፡ ምን ፡ ዓይነት
፡ ተልዕኮ ፡ ሊኖረው (ሊይዝ) ፡ ይገባል ፡ የሚለውን ፡ ጽንሰ ፡ ሐሳብ ፡ ከኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ
፡ ተዋህዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ተልዕኮና ፡ ዓላማ ፡ አንጻር ፡ በማጠቃለል ፡ በአጭሩ ፡ እንድናስቀምጥ
፡ በቅድስት ፡ ሥላሴ ፡ መካነ ፡ አእምሮ : (Holy Trinity Univeristy) : የትምህርተ-ኖሎት ፡
መምህር ፡ በሆኑት ፡ መምህር ፡ ቆሞስ ፡ አባ ፡ ገብረሃና ፡ ገብረጻድቅ ፡ በቀን ፡ ፳፫ ፡ ፲፪ኛ ፡
ወር ፡ ፳፻፲ወ፭ ፡ ዓ.ም ፡ ተሰቶናል ፡፡ በመሆኑም ፡ እኛ ፡ የቡድን ፡ አባላት ፡ በጋራ ፡ በመሆን
፡ የተሰጠው ፡ ጽንሰ ፡ ሐሳብ ፡ ከተለያዩ ፡ መንፈሳዊና ፡ ዓለማዊ ፡ መጻሕፍት ፡ ላይ ፡ በማጣቀስና
፡ እውቀቱ ፡ ያላቸው ፡ አባቶችን ፡ በመጠየቅ ፡ እንደሚከተለው ፡ አስቀምጠናል ፡፡ የአእምሮ ፡
ባለቤት ፡ ለሆነው ፡ ልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ምስጋና ፡ ይሁን ፡ አሜን ፡፡

2
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

መግቢያ፦
በኦርቶዶክሳዊት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ውስጥ ፡ የአገልጋዮች ፡ ሐዋርያዊ ፡ ተልዕኮ ፡
በተለያዩ ፡ ነጥቦች ፡ ሊጠቃለል ፡ ወይም ፡ ሊተነተን ፡ ይችላል ። እንደሚሠማሩበት ፡ ቦታ ፡
ጊዜ ፣ ወቅትና ፡ አገልግሎት ፡ የተለያዩ ፡ ቅርጾች ፣ ዕቅዶች ፣ ይዘቶችና ፡ ዓላማዎች ፡
ሊኖራቸው ፡ ይችላል ፡፡ ማለትም፦ ወንጌልን ፡ መስበክ ፣ ቤተ ፡ እምነት ፡ ማስፋት ፣
ምሥጢራትን ፡ መፈጸም ፣ እምነትን ፡ አንድነትን ፡ እና ፡ ሥርዓተ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያንን ፡
መጠበቅ ፣ ለሥነ ፡ ምግባር ፣ ለቅድስናና ፡ ለሁለንተናዊ ፡ አገልግሎት ፡ በመትጋት ፡ ምሳሌ ፡
መሆን ፣ መንጋዎቹን ፡ መጠበቅና ፡ በመንጋዎቹ ፡ መካከል ፡ ያለውን ፡ ክፍተት ፡ በማጥበብ ፡
መድፈን ፡ የአማናዊቷ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋህዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ አገልጋዮች ፡ የወንጌል ፡
አገልግሎት ፡ ተልዕኮ ፡ መሠረት ፡ ነው ፡፡

በጌታችን ፡ ትምህርት ፡ በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ ፡ ውስጥ ፡ በግና ፡ ተኩላ


፡ ተጠቅሰዋል ፡፡ በግ ፡ የየዋሀን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጆች ፡ ምሳሌ ፡ ነው ፡፡ ጌታችን ፡ “በጎቼ
፡ ድምፄን ፡ ይሰማሉ” ፡ በማለት ፡ በእርሱ ፡ የሚያምኑትን ፡ “በጎቼ” ፡ ብሏቸዋል ፡ (ዮሐ ፡ ፲ ፥
፳፯) ፡፡ እንዲሁም ፡ ለደቀ ፡ መዝሙሩ ፡ ለቅዱስ ፡ ጴጥሮስ ፡ “በጎቼን ፡ አሰማራ” ፡ በማለት ፡
በጎች ፡ የተባሉ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ የሚኖሩ ፡ ምዕመናን ፡ መሆናቸውን ፡ አስተምሮናል
፡ (ዮሐ ፳፩ ፥ ፲፯ ) ፡፡ በመጨረሻው ፡ የፍርድ ፡ ቀንም ፡ “በጎችን ፡ በቀኙ ፡ ያቆማቸዋል” ፡
ያለው ፡ በጎች ፡ የጻድቃን ፡ ምሳሌ ፡ ስለሆኑ ፡ ነው ፡ (ማቴ ፳፭ ፥ ፴፫) ፡፡ ክርስቶስም ፡
በትምህርቱ ፡ “የበጎች ፡ እረኛ ፡ እኔ ፡ ነኝ” ፡ ያለው ፡ ለዚሁ ፡ ነው ፡ (ዮሐ ፡ ፲ ፥ ፳፯) ፡፡ የዋሁ
፡ አቤል ፡ የበጎች ፡ እረኛ ፡ እንደነበር ፡ ተገልጿል ፡ (ዘፍ ፡ ፬ ፥ ፪) ፡፡ በነቢየ ፡ እግዚአብሔር ፡
ክቡር ፡ ዳዊት ፡ “እኛ ፡ የማሰማርያው ፡ በጎች ፡ ነን” ፡ (መዝ ፡ ፺፱ ፥ ፫) ፡ የተባለውም ፡ ሁሉ
፡ በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ ያሉ ፡ የዋሀንን ፡ ይመለከታል ፡፡

በአንጻሩ ፡ ተኩላ ፡ የነጣቂዎች ፣ የተንኮለኞችና ፡ የከሳሾች ፡ ምሳሌ ፡ ነው ፡፡ ጌታችን


፡ “የበግ ፡ ለምድ ፡ ለብሰው ፡ ከሚመጡባችሁ ፡ በውስጣቸው ፡ ግን ፡ ነጣቂ ፡ ከሆኑ ፡ ተኩላዎች
፡ ተጠበቁ” (ማቴ ፡ ፯ ፥ ፲፭) ፡፡ ያለው ፡ ተኩላዎች ፡ ተመሳስለው ፡ የሚያታልሉ ፡ ጉዳትም ፡
የሚያደርሱ ፡ ስለሆኑ ፡ ነው ፡፡ ተኩላ ፡ እረኛ ፡ የሌላቸውን ፡ ወይም ፡ ሰነፍ ፡ እረኛ ፡ ያላቸውን
፡ በጎች ፡ ይነጥቃል ፡ (ዮሐ ፲ ፥ ፲፪) ፡፡ በአጠቃላይ ፡ ተኩላ ፡ የክፉዎች ፡ ምሳሌ ፡ ሆኖ ፡ ነው
፡ የሚወሰደው ፡፡ “ብንያም ፡ ነጣቂ ፡ ተኩላ ፡ ነበር” ፡ የተባለው ፡ ጠዋት ፡ ሌላ ፡ ማታ ፡ ሌላ ፡
ስለነበር ፡ ነው ፡ (ዘፍ ፵፱ ፥፳፯) ፡፡ ቅዱስ ፡ ጳውሎስ ፡ “ከእኔ ፡ በኋላ ፡ ለመንጋይቱ ፡ የማይራሩ
፡ ነጣቂዎች ፡ ተኩላዎች ፡ እንደሚመጡ ፡ እኔ ፡ አውቃለሁ ፡፡ ደቀ ፡ መዛሙርትንም ፡ ወደ ፡
እነርሱ ፡ ይመልሱ ፡ ዘንድ ፡ ጠማማ ፡ ትምህርትን ፡ የሚያስተምሩ ፡ ሰዎች ፡ ከእናንተ ፡
መካከል ፡ ይነሳሉ” ። (ሐዋ. ፳ ፥ ፳፱-፴) ፡ ያለው ፡ ከዚያን ፡ ዘመን ፡ ጀምሮ ፡ በእውነተኛ ፡
የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ጠማማ ፡ ነገርን ፡ ያስተማሩትንና ፡ የሚያስተምሩትን ፡ ሁሉ ፡
ይመለከታል ፡፡ በመንፈሳዊ ፡ ተልዕኮ ፡ የሚሰማሩ ፡ ሰዎች ፡ እንደየግብራቸው ፡ በበጎችና ፡
በተኩላዎች ፡ የተመሰሉ ፡ ሲሆን ፡ እንደ ፡ በጎች ፡ በእግዚአብሔር ፡ የተወደደ ፡ ተልዕኮ ፡
ለመፈጸም ፡ በተለዕኮው ፡ ውስጥ ፡ ሊኖሩ ፡ የሚገባቸውን ፡ ዋና ፡ ዋና ፡ ነገሮችን ፡ ማስተዋል
፡ ያስፈልጋል ፡፡ እነዚህም ፡ ማንኛውም ፡ አገልጋይ ፡ ለመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ሲሰማራ ፡
3
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

ገንዘብ ፡ ሊያደርጋቸው ፡ የሚገቡ ፡ ናቸው ፡፡ የአገልግሎቱ ፡ ባለቤትና ፡ መሪ ፡ ማን ፡ እንደሆነ


፡ ማወቅ ፡ ለእርሱም ፡ መታመን ፡ ያስፈልጋል ፡፡

በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ተልእኮ ፡ ላኪው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡፡ ተልዕኮውን ፡


ለመፈጸም ፡ ፍላጎት ፣ እውቀትና ፡ ክህሎት ፡ ቢያስፈልግም ፡ ሰው ፡ ለመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት
፡ የሚላከው ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ እንጂ ፡ በእውቀቱ ፡ ብዛት ፡ አይደለም ፡፡ አገልጋይ ፡
በሰዎች ፡ ጋባዥነት ፡ ወደ ፡ አገልግሎት ፡ ቢቀርብም ፡ ሰዎች ፡ የተልዕኮው ፡ ምክንያት ፡ እንጂ
፡ ላኪዎች ፡ አይደሉም ፡፡ በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ውስጥ ፡ የተልዕኮውን ፡ ባለቤት ፡ (ላኪውን)
፡ ማስተዋል ፡ እጅግ ፡ መሠረታዊና ፡ የመጀመሪያው ፡ ነጥብ ፡ ነው ፡፡ መልእክተኛ ፡ የላኪውን
፡ ፈቃድ ፡ እንደሚፈጽም ፡ ሁሉ ፡ መንፈሳዊ ፡ አገልጋይም ፡ የጠራውንና ፡ የላከውን ፡
የእግዚአብሔርን ፡ ፈቃድ ፡ ሊፈጽም ፡ እንጂ ፡ የራሱን ፡ ፈቃድ ፡ ወይም ፡ የሌሎች ፡ ሰዎችን
፡ ፈቃድ ፡ ሊፈጽም ፡ አይገባም ፡፡ የተጠራንበትንና ፡ የተላክንበትን ፡ ዓላማ ፡ (ለምን ፡ ተላክን ፡
የሚለውን) ፡ ማወቅ ቀዳሚው ፡ ተግባር ፡ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ፡ ሰውን ፡ ለመንፈሳዊ ፡
አገልግሎት ፡ የሚልከው ፡ መንፈሳዊ ፡ ለሆነ ፡ ሥራ ፡ ነው ፡፡ ይህም ፡ እውነተኛውን ፡
የእግዚአብሔርን ፡ ቃል ፡ በቃልና ፡ በሕይወት ፡ በመስበክ ፡ ሰዎችን ፡ ለድኅነት ፡ ማብቃት ፡
ነው ፡፡ መንፈሳዊ ፡ አገልጋይ ፡ የሚያገለግልበት ፡ ዓለማ ፡ ሌሎች ፡ እንዲድኑ ፡ እርሱም ፡
በመክሊቱ ፡ እንዲያተርፍበት ፡ ነው ፡፡ ጌታችን ፡ በመክሊቱ ፡ ምሳሌ ፡ እንዳስተማረው ፡
የአገልግሎቱ ፡ ዋናውም ፡ (ጸጋው) ፡ ይሁን ፡ በአገልግሎቱ ፡ የሚገኘው ፡ ትርፍ ፡ የእርሱ ፡
የባለቤቱ ፡ እንጂ ፡ የአገልጋዩ ፡ አይደለም ፡፡ አገልጋይ ፡ የአገልግሎቱን ፡ ዋጋ ፡ የዘላለም ፡
ሕይወትን ፡ ያገኛል ፡፡ በጥቂት ፡ በመታመኑ ፡ በብዙ ፡ ይሾማል ፡፡ መንፈሳዊ ፡ አገልጋይ ፡
እምነት ፡ እንዲሰፋ ፤ መልካም ፡ ስነምግባር ፡ እንዲስፋፋ ፤ ሰው ፡ የእግዚአብሔርን ፡ መንግሥት
፡ እንዲወርስ ፤ የእርሱም ፡ ጽናቱ ፡ ይረጋገጥ ፡ ዘንድ ፡ ያገለግላል ፡፡ መንፈሳዊ ፡ አገልግሎት
፡ ከዚህ ፡ የተለየ ፡ ዓላማ ፡ ከያዘ ፡ መንፈሳዊ ፡ መሆኑ ፡ ያበቃል ፣ (አስተምህሮ ፡ ዘተዋህዶ ፣
ታህሳስ ፣ 7 ፣ 2019 ፡ G.C.) ፡፡
ስለዚህ ፡ የኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋህዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ይህንን ፡ መሠረታዊ ፡
የሆነ ፡ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ : ከመሠረታት ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፣ ከአፀኗት ፡
ሐዋርያነ ፡ አበው ፡ ተቀብላ ፡ በሥሯ ፡ ለሚገኙ ፡ እንደተቋም ፡ ለጠቅላይ ፡ ቤተ ፡ ክህነት ፣
ለሀገረ ፡ ስብከት ፣ ለወረዳ ፡ ቤት ፡ ከህነት ፡ ለአጥቢያ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ፡ እና ፡ ለሰበካጉባኤ
፡ እንዲሁም ፡ እንደግለሰብ ፡ ለኤጲስቂጶሳት ፣ ለካህናት ፣ ለዲያቆናት ፣ ለመመናን ፡ እና ፡
ለመመናት ፡ በቅደም ፡ ተከተል ፡ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኳን ፡ እየሰጠች ፡ ወደተለያዩ
፡ ዓለማት (እሥርቤቶች ፤ የመንግሥት ፡ መሥሪያቤቶች ፣ ፍርድቤቶች ፣ የሕብረተሰቡ ፡ የንሮ
፡ ዘይቤ ፡ ውስጥ ፣ ንግድ ፡ ድርጅቶች ፣ ሆስፒታሎች ፣ ቤተሰቦች ፡ ወዘተ) ፡ ትልካለች ፡፡
ሰስለሆነም ፡ ከንዚህ ፡ መካከል ፡ እንደኛ ፡ ቡድን ፡ አንድ ፡ የኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋህዶ
፡ ቤተክርስቲያን ፡ አገልጋይ ፡ ካህን ፡ ይህንን ፡ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ ፡ ይዞ ፡
የመንፈሳዊ ፡ ሕክምና ፡ ባለሞያ ፡ ቢሆንና ፡ በሆስፒታሎች ፡ ውስጥ ፡ ቢመደብ ፡ የተስጠውን
፡ ተልዕኮ ፡ እንዴትና ፡ በምን ፡ መልኩ ፡ ተግባራዊ ፡ ያደርገዋል ፣ ተልዕኮውስ ፡ ምን ፡ መሆን
፤ ምንስ ፡ መምሰል ፡ አለበት ፡ የሚለውን ፡ መሠረታዊ ፡ ነገር ፡ ከኦርቶዶክስ ፡ የክህነት ፡
አገልግሎት ፡ ሥርዓት ፡ ጋር ፡ በማጣመር ፡ እንደሚከተለው ፡ አስቀምጠናል ፡፡

4
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

፩. በኦርቶዶክስ ፡ ተዋህዶ ፤ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ፦

በኦርቶዶክሳዊ ፡ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ ፡ ውስት ፡ የመጀመሪያው ፡ ሥራ


፡ የላኪውን ፡ ማንነት ፡ ማውቅ ፡ እና ፡ የተሸከሙትን ፡ የወንጌል ፡ ተልዕኮ ፡ ዓላማ ፡ በሚገባ
፡ መገንዘብ ፡ አስፈላጊ ፡ ነው ፡፡ በመቀጠልም ፡ የተልዕኮው ፡ ስፍራ ፡ ፈተና ፡ የሚበዛበት ፡
መሆኑን ፡ ማስተዋል ፡፡ በወንጌሉ ፡ እንደተገለጸው ፡ የተልዕኮው ፡ ስፍራ ፡ በተኩላዎች መካከል
፡ እንጂ ፡ በበጎች ፡ መካከል ፡ አይደለም ፡፡ በዚያም ፡ ስፍራ ፡ የተልዕኮው ፡ የመጀመሪያ ፡ ኣላማ
፡ በተቻለ ፡ መጠን ፡ የተኩላ ፡ ጸባይ ፡ ያላቸውን ፡ የበግ ፡ ጸባይ ፡ እንዲይዙ ፡ ማስቻል ፡ ነው
፡፡ ይህ ፡ ባይሆንኳ ፡ ተኩላዎቹ ፡ ሌሎች ፡ በጎችን ፡ እንዳይነጥቁ ፡ መከላከል ፡ የሁሉም ፡
የወንጌል ፡ አደራ ፡ ተቀባይ ፡ ኣላማና ፡ ተልዕኮ ፡ ነው ፡፡ ይህም ፡ ካልተቻለ ፡ ደግሞ ፡ አገልጋዩ
፡ በተላከበት ፡ ሥፍራ ፡ ሁሉ ፡ የራሱን ፡ ግዴታ ፡ እንዲወጣ ፡ ይላካል ፡፡ ተኩላ ፡ ያው ፡ ተኩላ
፡ ነውና ፡ በተኩላ ፡ መካከል ፡ የሚፈጸም ፡ አገልግሎት ፡ መሰደብ ፣ መከሰስ ፣ መንገላታትና ፡
መከራ ፡ መቀበል ፡ ያለበት ፡ ተልዕኮ ፡ ነው ፡፡ በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ ፡ ክርስቶስ
፡ በጎችን ፡ ወደ ፡ ተኩላዎች ፡ ይልካል ፡፡ ከዚህ ፡ ተቃራኒ ፡ በሆነ ፡ መልኩ ፡ ደግሞ ፡ ዲያብሎስ
፡ ተኩላዎችን ፡ ወደ ፡ በጎች ፡ ይልካል ፡፡ እንግዲህ ፡ መንፈሳዊው ፡ አገልግሎት ፡ እንደዚህ ፡
ፈታኝ ፡ በሆነ ፡ ሁኔታ ፡ ነው ፡ የሚከናወነው ፡፡ የመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ መስክ ፡ ፈታኝ ፡
ቢሆንም ፡ አለማገልገል ፡ ግን ፡ አማራጭ ፡ መፍትሔ ፡ አይደለም ፡፡ ከተኩላዎች ፡ ጋር ፡
መደራደርም ፡ አይቻልም ፡፡ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮን ፡ ተሸክሞ ፡ መታገል ፡ እንጂ፡፡

በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ለመሠማራት ፡ በግ ፡ ሆኖ ፡ መገኘት ፡ የአንድ ፡ መንፈሳዊ ፡


አገልጋይ ፡ ካህን ፡ ቀዳሚ ፡ ግብሩ ፡ ነው ፡፡ ጌታችን ፡ መቶ ፡ በጎች ፡ ያሉት ፡ ሰውን ፡ ምሳሌ
፡ አድርጎ ፡ ያስተማረውም ፡ በሰማይ ፡ ያሉ ፡ ዘጠና ፡ ዘጠኙ ፡ ነገደ ፡ መላእክትንና ፡ ጠፍቶ ፡
የነበረውን ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ የሚያሳይ ፡ ነው ፡ (ሉቃ ፡ ፲፭ ፥ ፫) ፡፡ መጥምቀ ፡ መለኮት ፡
ቅዱስ ፡ ዮሐንስ ፡ መድኅን ፡ ዓለም ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስን ፡ “የእግዚአብሔር ፡ በግ” ፡ ያለው ፡
ስለ ፡ እኛ ፡ በፈቃዱ ፡ በተቀበለው ፡ ሞቱ ፡ ሞትን ፡ ስላስወገደልን ፡ የመዳናችንም ፡ መሠረት
፡ ስለሆነልን ፡ ነው ፡ (ዮሐ ፡ ፩ ፥ ፳፱) ፡፡ መንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ላይ ፡ ለመሰማራት ፡
ራሳችንን ፡ መልካም ፡ በግ ፡ አድርጎ ፡ መገኘት ፡ ያስፈልጋል ፡፡ በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡
በግ ፡ ወደ ፡ ተኩላ ፡ ይላካል ፡ እንጂ ፡ ተኩላ ፡ ወደ ፡ ተኩላ ፡ አይላክምና ፡፡ ቢላክምኳ ፡
አይጠቅምም ፡፡ መንፈሳዊ ፡ አገልጋይ ፡ እንደ ፡ በግ ፡ በተኩላ ፡ መካከል ፡ ሲላክ ፡ በዚያው ፡
በተኩላ ፡ ተበልቶና ፡ ጠፍቶ ፡ እንዳይቀር ፡ መንፈሳዊ ፡ ትጋትን ፡ ገንዘብ ፡ ማድረግ ፡ ግዴታ
፡ ነው ፡፡ ለማትረፍ ፡ እንጂ ፡ ዋናውን ፡ ለማጣት ፡ የሚነግድ ፡ ነጋዴ ፡ እንደሌለ ፡ ሁሉ ፡
መንፈሳዊ ፡ አገልጋይም ፡ ለማትረፍ ፡ ካልሆነም ፡ ለመትረፍ ፡ ሊተጋ ይገባል ፡፡

በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ መመሪያ ፡ ውስጥ ፡ ርግብና ፡ እባብ ፡ ተጠቅሰዋል ፡፡


ርግብ ፡ የየዋሀን ፡ ምሳሌ ሆና ፤ የጥፋት ፡ ውኃን ፡ መጉደል ፡ ለኖኅ ፡ ያበሰረች ፣ በኖኅ ፡
መርከብ ፡ ውስጥም ፡ እንቁላሏን ፡ በእባብ ፡ አፍ ፡ ውስጥ ፡ የጣለች ፡ የዋህ ፡ እንስሳ ፡ ናት ፡
(ዘፍ ፡ ፰ ፥ ፲፩) ፡፡ ጌታችን ፡ በዮርዳኖስ ፡ ሲጠመቅ ፡ የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ በእርሱ ፡ ላይ
፡ በርግብ ፡ አምሳል ፡ እንደወረደ ፡ ርግብ ፡ የመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ምሳሌ ፡ ናት ፡ (ማቴ ፡ ፫ ፥
፲፮) ፡፡ ርግብ ፡ በብሉይ ፡ ኪዳን ፡ ለኃጢአት ፡ ማስተስረያነት ፡ መስዋዕት ፡ ሆና ፡ ትቀርብም ፡

5
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

ነበር ፡ (ዘፍ ፡ ፭ ፥ ፯) ፡፡ የእግዚአብሔርን ፡ ቃል ፡ የወለደችልም ፡ ቅድስት ፡ ድንግል ፡


ማርያምም ፡ “መልካሚቱ ፡ ርግብ” ፡ ትባላለች ፡ (የእሑድ ፡ ውዳሴ ፡ ማርያም) ፡፡ በሌላ ፡ በኩል
፡ እባብ ፡ ልባም ፣ ጥበበኛ ፣ ተንኮለኛና ፡ መርዘኛ ፡ እንስሳ ፡ ነው ፡፡ “ከምድር ፡ አውሬ ፡ ሁሉ
፡ እባብ ፡ ተንኮለኛ ፡ ነበር” ፡ እንደተባለ ፡ (ዘፍ ፡ ፫ ፥ ፩) ፡፡ እባብ ፡ ተንኮለኛ ፡ አውሬ ፡ ነበር
፡፡ እባብ ፡ በኖኅ ፡ ዘመን ፡ የርግብን ፡ እንቁላል ፡ ያልዋጠ ፡ ወደውጭ ፡ እንዳይጣል ፡ ነበር ፣
ውሃ ፡ በሚጠጣበት ፡ ጊዜ ፡ መርዙን ፡ ውጭ ፡ አስቀምጦ ፡ ይጠጣል ፡ እንዳይገድለው ፡
ለመጠንቀቅ ፣ የዕፀ ፡ ዘዌን ፡ ቅተል ፡ መመገብ ፡ በጣም ፡ ይወዳል ፡ ነገር ፡ ግን ፡ ጥለው ፡
ያድክመዋልና ፡ በጥበብ ፡ ይመገባል ፡፡ ልባም ፍጡር ነውና ፤ እባብ ፡ በገነት ፣ በፈርዖን ፡
ቤተመንግስት ፣ በበረሀ ፣ እንዲሁም ፡ በመላጥያ ፡ ደሴት ፡ እንደተገኘ ፡ መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡
ያስረዳል ፡፡ በርግብና ፡ በእባብ ፡ ምሳሌነት ፡ ከመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ተልዕኮ ፡ ጋር ፡ አብረው
፡ የተሰጡ ፡ የመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ መመሪያዎች ፡ ሁለት ፡ ናቸው ፡፡ እነሱም፡-

ሀ/ እንደ ፡ ርግብ ፡ የዋህ ፡ መሆን ፡ (innocence)፦ ጌታችን ፡ እንደ ፡ ርግብ ፡ የዋህ ፡ ሁኑ


፡ ሲል ፡ ለመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ ፡ ታመኑ ፡ (የቁራ ፡ መልእክተኛ ፡ እንዳትሆኑ) ፣
በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ሰላምን ፡ ስበኩ ፡ (ጥልና ፡ ክርክር ፡ ከእናንተ ፡ ይራቅ) ፣ በመንፈስ
፡ ቅዱስ ፡ ተመሩ ፡ (የራሳችሁን ፡ ፍላጎት ፡ ግቱ) ፣ ሰው ፡ የሚፈልገውን ፡ ሳይሆን ፡ ለሰው ፡
የሚያስፈልገውን ፡ በመስበክ ፡ አስፈላጊ ፡ ሆኖም ፡ ሲገኝ ፡ መስዋዕትነት ፡ ክፈሉ ፡ ማለቱ ፡
ነው ፡፡ ነገር ፡ ግን ፡ “እንደ ፡ ርግብ ፡ የዋህ ፡ ሁኑ” ፡ አለ ፡ እንጂ ፡ “ርግብ ፡ ሁኑ” ፡ አላለም
፡፡ ርግብን ፡ መምሰል ፡ ያለብን ፡ በሦስት ፡ ነገሮች ፡ ነው ፡፡

በርህራሄ፡- ይቅር ፡ የምንልና ፡ በሌሎች ፡ ላይ ፡ ቂም ፡ የማንይዝ ፡ በመሆን ፡፡

በየዋህነት፡- የማናታልል ፡ የማንጎዳ ፡ በመሆን ፡ (ርግብ ፡ አትዋጋም ፣ አትናከስም ፣ ግን ፡


ትበራለችና) ፡፡

በንጽህና፡- ራሳችንን ፡ ከኃጢአት ፡ በመጠበቅና ፡ በንስሐ ፡ ሕይወት ፡ በመኖር ፡፡

ለ/ እንደ ፡ እባብ ፡ ብልህ ፡ መሆን ፡ (intelligence)፦ መድኃኒታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡


በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ መመሪያው ፡ “እንደ ፡ እባብ ፡ ብልህ ፡ ሁኑ” ፡ ያለው ፡ አገልጋይ ፡
ሲያገለግል ፡ ዋናውን ፡ እንዳያጣ ፣ ራሱን ፡ እንዲጠብቅ ፣ ለሌሎች ፡ እንቅፋት ፡ እንዳይሆን ፣
በሌሎች ፡ ክፋት ፡ ተስቦ ፡ እንዳይፈተንና ፡ ካለው ፡ መንፈሳዊ ፡ ጽናት ፡ እንዳይወድቅ ፡
ለማስገንዘብ ፡ ነው ፡፡ እዚህ ፡ ላይ ፡ ማስተዋል ፡ የሚገባን ፡ ነጥብ ፡ አለ ፡፡ ጌታችን “ብልህ/ልባም”
፡ እንጂ ፡ “ብልጥ ፡ ሁኑ” አላለም ፡፡ ሌላውን ፡ እንዳንጎዳ ፡ “እንደ ፡ እባብ ፡ ልባም ፡ ሁኑ” አለ
፡ እንጂ “እባብ ፡ ሁኑ” ፡ አላለም ፡፡ መንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ከራስ ፡ ይልቅ ፡ ሌላውን ፡
ማስቀደም ፡ ይጠይቃልና ፡ እንደ ፡ እባብ ፡ ልባም ፡ ሁኑ ፡ ሲባል ፡ በሦስት ፡ ነገሮች ፡ ነው ፡፡

ፈጣን ፡ ዐይኖች (sharp eyes) ፡- ዐይኖቻችንን ፡ በእውቀት ፡ በማብራት ፡ ፈጣን ፡ መሆን ፡፡

የማይደለሉ ፡ ጆሮዎች (Focused ears) ፡- በአስመሳዮች ፡ አሉባልታና ፡ ወሬ ፡ የማይታለሉ ፣


የማይረቱ ፡ ጆሮዎች ፡እንዲኖሩን ፡፡

በጥበብ ፡ መኖር (Wisdom)፡- ራስን ፡ በመጠበቅ ፡ እምነታችንን ፡ በማጽናት ፡ መኖር ፡፡ ነገር ፡


ግን ፡ ከእባብ ፡ መውሰድ ፡ የሌለብን ፡ ነገሮችም ፡ እንዲሁ ፡ አሉ፦
6
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

 የእባብ ፡ መብል ፡ ትቢያ ፡ ነው ፡፡ (ኢሳ ፡ ፷፭ ፥ ፳፭) ፡፡


 የእባብ ፡ መንገድም ፡ በአለት ፡ መካከል ፡ ነው ፡፡ (ምሳ ፡ ፴ ፥ ፲፱) ፡፡
 እባብ ፡ ቆዳውን ፡ ይቀይራል ፡፡ (ማቴ ፡ ፲፪ ፥ ፵፭) ፡፡
 እባብ ፡ መርዛማ ፡ ነው ፡፡ (መዝ ፡ ፶፰ ፥ ፬) ፡፡
 እባብ ፡ ተንኮለኛ ፡ ነው ፡ (ዘፍ ፡ ፫ ፥ ፩-፳) ፡፡
 እባብ ፡ የዲያብሎስ ፡ ማደርያ ፡ በመሆን ፡ ለአዳም ፡ መሳሳት ፡ ምክንያት ፡ ስለነበር ፡
በእግዚአብሔር ፡ ተረግሟል ፡፡ እነዚህን ፡ ከመሳሰሉት ፡ የእባብ ፡ ባህርያት ፡ ልንርቅ ፡
ይገባናል ፡፡

በአጠቃላይ ፡ በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ውስጥ ፡ ያለ ፡ አገልጋይ ፡ የመንፈሳዊ ፡


አገልግሎት ፡ ተልዕኮና ፡ መመሪያዎቹን ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ ማስተዋልና ፡ የአገልግሎቱም ፡ መመሪያ
፡ ማድረግ ፡ አለበት ፡፡ የመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ባለቤቱ ፡ በመንፈስ ፡ የምናገለግለው ፡
እግዚአብሔርን ፡ መሆኑን ፣ የአገልግሎቱም ፡ ዓላማ ፡ መንፈሳዊ ፡ መሆኑን ፣ የአገልግሎቱም
፡ መሪ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ መሆኑን ፣ የአገልግሎቱም ፡ መስክ ፡ ለሰው ፡ ሕይወት ፡ ፈታኝ ፡
መሆኑን ፡ ማስተዋል ፡ ይገባል ፡፡ ከዚህ ፡ ዓይነት ፡ ማስተዋል ፡ ጋር ፡ የዋህነትንና ፡ ብልህነትን
፡ አመጣጥኖና ፡ አዋሕዶ ፡ በመያዝ ፡ መንፈሳዊ ፡ አገልግሎትን ፡ መፈጸም ፡ ይገባል ፡፡ ከዚህ
፡ ውጭ ፡ የሚያስጨንቅ ፡ ነገር ፡ ሲመጣ ፡ ግን ፡ በጸሎትና ፡ በምልጃ ፡ ወደ ፡ አገልግሎቱ ፡
ባለቤት ፡ ማመልከት ፡ ይገባል ፡ እንጂ ፡ ወደ ፡ ከንቱ ፡ ክርክርና ፡ ንትርክ ፡ መግባት ፡
አያስፈልግም ፡፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ መሪ ፡ በማድረግ ፡ ችግሮችን ፡ በመፍታት ፡ ሰላምን ፡
ማውረድ ፡ ያስፈልጋል ፡ እንጂ ፡፡

፩.፩. ኦርቶዶክሳዊ ፡ የክህነት ፡ አገልግሎት ፡ በሆስፒታሎች፦

የኦርቶዶክስ ፡ ተዋህዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ክህነት ፡ የእምነት ፣ የፍቅር ፡ እና ፡ የተስፋ


፡ እንዲሁም ፡ የመተሳሰብ ፡ አገልግሎት ፡ ነው ። ካህናት ፡ “ግልገሎቼን ፡ አሠማራ ፣ ጠቦቶቼን
፡ ጠበቅ ፣ በጎቼን ፡ አሰማራ” ፡ (ዮሐ ፡ ፳፩ ፥ ፲፭-፲፯) ፣ ኢያለ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ በቅዱስ
፡ ዼጥሮስ ፡ አማካኝነት ፡ ለካህናት ፡ ሁሉ ፡ በተሰጠው ፡ አምላካዊ ፡ ትዕዛዝ ፡ መሠረት ፡ በእግረ
፡ ዼጥሮስ ፡ የተተኩ ፡ ካህናት ፡ ሁሉ ፡ ተቀዳሚ ፡ ተግባራቸው ፡ የመንጋዎቹን ፡ መንፈሳዊ ፡
ፍላጎቶቻቸውን ፡ ለማሟላት ፡ በእምነት ፣ በፍቅር ፣ በተስፋና ፡ በመተሳሰብ ፡ እንዲፀኑ ፡
ያለመታከት ፡ የተሥፈውን ፡ መንግሥት ፡ ማሳየት ፡ ነው ፡፡ በተጨማሪም ፡ መንጋዎቹን ፡
እንዲጠብቁ ፣ እንዲያጸኑና ፡ እንዲንከባከቡ ፡ ተጠርተዋል ፡፡ ይህ ፡ ደግሞ ፡ በእምነት ፡
የደከሙትን ፣ የጠነከሩትን ፣ በጤና ፡ ያሉትን ፣ የታመሙትንና ፡ በህመም ፡ ውስጥ ፡
የሚሠቃዩትን ፡ ሁሉ ፡ ይጨምራል ። በአማናዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ፡ ቤተክርስቲያን ፡
የመጀመሪያዎቹ ፡ ክፍለ ፡ ዘመናት ፡ ካህናት ፡ ብዙውን ፡ ጊዜ ፡ የታመሙትንና ፡ የሚሞቱትን
፡ ቀዳሚ ፡ ተንከባካቢ ፡ ሆነው ፡ ያገለግሉ ፡ ነበር ። ዛሬም ፡ ቢሆን ፡ ምንምኳ ፡ እንደጥንቱ ፡
ባይሆንም ፡ የኦርቶዶክስ ፡ ተዋህዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ አገልጋይ ፡ ካህናት ፡ በተለያዩ ፡ ዓለማት
፡ ውስጥ ፡ በሚገኙ ፡ የህሙማን ፡ ማረፊያ ፡ ቦታዎች ፡ በመገኘት ፡ ለህሙማኑ ፣
ለአስታማሚዎችና ፡ ህሙማኑን ፡ ለማከም ፡ ለሚድክሙ ፡ የሕክምና ፡ ባለሙያዎችም ፡ ሳይቅር
7
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

፡ በዓለም ፡ ዙሪያ ፡ በሚገኙ ፡ ሆስፒታሎች ፡ መንፈሳዊ ፡ እንክብካቤ ፡ ማድረጋቸውን ፡


አላቆሙም ፡፡ መንፈሳዊ ፡ አገልግሎታቸውን ፡ ቀጥለዋል ፡ እንጂ ፤ ስለሆነም ፡ በሆስፒታሎች
፡ ውስጥ ፡ ያለው ፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፡ የክህነት ፡ አገልግሎት ፡ ሙያ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል ፣
ነገር ፡ ግን ፡ ሙያ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፤ ጥሪም ፡ ጭምር ፡ እንጂ ፡፡ በሐኪምነት ፡ በሆስፒታሎች
፡ ውስጥ ፡ ለመሥራት ፡ የሚመርጡ ፡ ካህናት ፡ ተቀዳሚ ፡ ተለዕኳቸው ፡ ለተቸገሩት ፤ ሁሉ
፡ መንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ መስጠት ፡ ነው ፡፡ ይህም ፡ የሚሆነው ፡ ካህናቱ ፡ የሕክምና ፡
አገልግሎት ፡ ለመስጠት ፡ ከኣላቸው ፡ ፍቅር ፡ የተነሳ ፡ ነው ። በደዚህ ፡ ዓይነት ፡ አገልግሎት
፡ ለመሠማራትና ፡ ከሙያው ፡ ጋር ፡ የሚመጡትን ፡ ተግዳሮቶች ፡ ለመጋፈጥም ፡ ፈቃደኞች
፡ ናቸው ።

፩.፪. ዶክተር (የሕክምና ፡ ባለሙያ) ፡ የሆኑ ፡ ኦርቶዶክሳዊ ፡ ካህናት ፡


ሚና ፡ እና ፡ ሃላፊነት ፡ በሆስፒታሎች፦

በኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋህዶ ፡ ቤተ ፡ ከረስቲያን ፡ ሥርዓት ፣ ቀኖና ፡ እና ፡


ዶግማ ፡ መሠረት ፡ የወንጌል ፡ አገልገሎት ፡ ተልዕኮ ፡ ተሠቶት ፡ በመንፈሳዊ ፡ ሕክምና ፡
የአገለግል ፡ ዘንድ ፡ የተመደበ ፡ የሕክምና ፡ ባለሙያ (ዶክተር) ፡ ካህን ፡ የታወቁ ፡ ሚናዎችና
፡ ሃላፊነቶች ፡ አሉት ፡፡ እነሱም፦

 ለታካሚዎችና ፡ ለቤተሰቦቻቸው ፡ ምክር ፡ እና ፡ መንፈሳዊ ፡ መመሪያ ፡ መስጠት ፡፡


 ለታካሚዎች ፡ የሕክምና ፡ እንክብካቤ ፡ ማድረግ ፡፡
 በኦርቶዶክስ ፡ ተዋህዶ ፡ የክርስትና ፡ ጉዞ ፡ ውስጥ ፡ ሊያዙ ፡ የሚገባቸውን ፡
ሥነምግባር ፡ እና ፡ ትምህርቶች ፡ ማስተማር ፡ ወይም ፡ የመጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡
መሠረታዊ ፡ ሕጎች ፣ ትዕዛዞች ፡ ሥርዓቶችና ፡ ዓላማዎች ፡ በሚገበው ፡ መጠን ፡
ማስረዳት ።
 ኦርቶዶክስኣዊ ፡ ካህን ፡ በመሆኑና ፡ በሆስፒታል ፡ ውስጥ ፡ በዶክተርነት ፡
የሚያጋጥሙ ፡ ፈተናዎች ፣ ተግዳሪቶች ፡ እና እንከኖች፦ (የታካሚዎችን ፡ እና ፡
የቤተሰቦቻቸውን ፡ ስሜታዊ ፡ እና ፡ መንፈሳዊ ፡ ህመም ፡ መቋቋም ።
 የሚኒስቴር ፤ መስሪያ ፡ ቤቱን ፡ ፍላጎት ፡ ከህክምና ፡ ሙያ ፡ ፍላጎት ፡ ጋር ፡
ማመጣጠን ።
 በመድኃኒት ፡ እና ፡ በሃይማኖት ፡ መጋጠሚያ ፡ ላይ ፡ የሚነሱትን ፡ የሥነ ፡ ምግባር ፡
ችግሮች ፡ ማስተናገድ ፡ እነዚህ ፡ ነገሮች ፡ ካባዶች ፤ ይሁን ፡ እንጂ ፡ የኦርቶዶክስ ፡ ካህን
፡ መሆን ፡ እና ፡ በሆስፒታል ፡ ውስጥ ፡ የሕክምና ፡ ባለሙያ ፡ ሆነው ፡ መገኘታቸው ፡
የሚያስገኘው ፡ ሽልማትም ፡ ብዙ ፡ ነው ። አንዳንድ ፡ ሽልማቶች ፡ የሚከተሉትን ፡
ያካትታሉ፦
 ለተሰቃዩ ፡ ሰዎች ፡ ተስፋ ፡ እና ፡ ፈውስ ፡ ማምጣት ፡ መቻል ፡፡
 ለተቸገሩት ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ፍቅር ፡ ማካፈልና ፡ መስጠት ፡ መቻል ፡፡
 በአንድ ፡ ሰው ፡ ሕይወት ፡ ላይ ፡ ለውጥ ፡ እንዳመጣ ፡ በማወቅ ፡ የሚገኘው ፡
የእርካታ ፡ ስሜት ፡ ከፍተኛ ፡ ሽልማት ፡ ነው ።
እንደ ፡ ዶክተር ፡ በሆስፒታሎች ፡ ውስጥ ፡ የኦርቶዶክስ ፡ ክህነት ፡ አገልግሎት ፡ አስፈላጊነት
፡ ከሐኪሙም ፡ በላይ ፡ በጣም ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ነው ፡፡ ምክንያቱም ፡ ለታመሙት ፣

8
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

ለአስታማሚዎች ፡ በአጠቃላይ ፡ በሆስፒታሉ ፡ ወስጥ ፡ ለሚገኘው ፡ ማሕበረሰብ ፡ መንፈሳዊ ፡


እና ፡ ሥጋዊ ፡ ህክምና ፡ መሥጠት ፡ የመንፈስ ፡ እርካታ ፡ ያጎናፅፋል ፡፡ ሰዎች ፡ ብዙውን ፡
ጊዜ ፡ ሞትን ፡ እና ፡ ሕመምን ፡ በሚፈሩበት ፡ ዓለም ፡ ውስጥ ፡ ሐኪሙ ፡ ካህን ፡ ሆኖ ፡
ሲገኝ ፡ ደስታቸው ፡ ወደር ፡ የለውም ፡ መክንያቱም ፡ መንፈሳዊውንም ፡ ሥጋዊውንም ፡
ሕክምና ፡ በተሟላ ፡ መልኩ ፡ እናገኛለን ፡ የሚል ፡ ተስፋ ፡ በመሰነቅ ፡ ይፅናናሉና ፡፡ ካህን ፡
ሆኖ ፡ ዶክተር ፡ የሆነ ፡ አገልጋይ ፡ በሥቃይ ፡ ላይ ፡ ላሉ ፡ ሰዎች ፡ ጸሎትን ፣ ፍቅርን ፣
ትምህርትን ፣ በእምነት ፡ መፅናትን ፡ እና ፡ የብርታት (የመዳን) ፡ ተስፋን ፡ መስጠት ፡
ይችላል ፡፡ ስለዚህ ፡ በህመም ፡ ሥቃይ ፡ ውስጥ ፡ የአሉትን ፡ ሰዎች ፡ የሕይዎት ፡ ተስፋ ፡
መስጠት ፡ በወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ ፡ የተሠማራ ፡ ካህን ፡ ተቀዳሚ ፡ ተግባር ፡ ነው
፡፡ ይህም ፡ በህመም ፡ ሥቃይ ፡ ውስጥ ፡ ያሉ ፡ ህሙማንም ፡ ሆነ ፡ አስታማሚዎች ፡ ተስፋ
፡ እንዳይቆርጡ ፡ ያደርጋቸዋል ፣ (ፍትሐ ፡ ነገሥት ፡ ንባቡና ፡ ትርጓሜው ፡ በ፲፱፻፺) ፡፡

፩.፫. የኦርቶዶክሳዊ ፡ ዶክተር (የሕክምና ፡ ባለሙያ) ፡ ተልዕኮ ፡


በሆስፒታሎች፦
በኦርቶዶክሳዊት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ውስጥ ፡ የአገልጋዮች ፡ ሐዋርያዊ ፡ ተልዕኮ ፡
በተለያዩ ፡ ነጥቦች ፡ ሊጠቃለል ፡ ወይም ፡ ሊተነተን ፡ እንደሚችል ፡ ከላይ ፡ በመግቢያው ፡
አስቀምጠናል ። ስለሆነም ፡ የኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋህዶ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ አገልጋይ
፡ ካህናቶዮቿን ፡ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ ፡ ይፈፅሙ ፡ ዘንድ ፡ በተዋረድ ፡ አላፊነት ፡
እየሰጠች ፡ ትልካለች ፡፡ ከነዚህ ፡ ተልዕኮችም ፡ መካከል ፡ በዋነኝነት ፡ የሚጠቀሱት ፡
የሚከተሉት ፡ ዋና ፡ ዋናዎቹ ፡ ናቸው፦

 ወንጌልን መስበክ፦

ኦርቶዶክሳውያን ፡ ካህናት ፡ የክርስቶስን ፡ ወንጌል ፡ ለቤተክርስቲያንና ፡ ለዓለም ፡ ማወጅና


፡ መተርጐም ፡ አለባቸው ። ይህ ፡ ይሆን ፡ ዘንድ ፡ ካህናት ፡ ሲመረጡ (ሲሾሙ) ፡ በይበልጥ ፡
ቅዱሳት ፡ መጻሕፍትን ፡ በማወቃቸውና ፡ ለሌላው ፡ ለማስረዳት ፡ ባላቸው ፡ ችሎታ ፡ መሆን
፡ አለበት ። ለእንዲህ ፡ ዓይነቱ ፡ ካህን ፡ በምሳሌነት ፡ ሊጠቀስ ፡ የሚችለው ፡ ቅዱስ ፡ ዮሐንስ
፡ አፈወርቅ ፡ ነው ። ኦርቶዶክሳውያን ፡ ካህናት ፡ ወንጌልን ፡ በታማኝነት ፡ ሊከተሉና ፡
የአገልግሎታቸው ፡ ማዕከል ፡ ሊያደርጉ ፡ ይገባል ። ይህ ፡ ከሆነ ፡ ወንጌል ፡ ምንድነው? ፡
የሚለውን ፡ ጥያቄ ፡ ለመመለስ ፡ ቀላል ፡ ይሆናል ፡፡ ወንጌል ፡ ማለት ፡ እግዚአብሔር ፡ ወልድ
፡ ሰው ፡ የሆነበት ፣ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ኅብረት ፡ ይመልሰው ፡ ዘንድ ፡ የወደቀውን ፡ የሰው
፡ ልጅ ፡ ሰብእና ፡ ገንዘብ ፡ ያደረገበት ፣ ኃጢአትን ፡ ድል ፡ የነሣበትና ፡ ሞትን ፡ ያጠፋበት ፡
መልካም ፡ ዜና ፡ ነው ። ይህ ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ በማናቸውም ፡ የቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ሕይወት
፡ ሰጪ ፡ አገልግሎቶች ፤ ማለትም ፡ በምሥጢራት ፣ በአምልኮትዋ ፣ በጾምና ፡ በጸሎት ፡
ውስጥ ፡ መሠረት ፡ ሊሆን ፡ ይገባል ። ካህናት ፡ ይህን ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ ማለትም ፡ የክርስቶስን
፡ ሕይወት ፣ ሞትና ፡ ትንሣኤ ፡ ለዓለም ፡ ሕዝብ ፡ ሁሉ ፡ ሊሰብኩ ፡ ይገባል ። በተለይም ፡
ደግሞ ፡ በዚህ ፡ ዓለም ፡ ድካም ፡ በመቃተት ፡ ለአሉት ፡ ሁሉ ፡ የሕይዎት ፡ ተስፋን ፡ መስጠት
፡ የካህናት ፡ ቀዳሚ ፡ ተልዕኳቸው ፡ ነው ፡፡ ሰዎችንም ፡ ወደእምነትና ፡ ፡ ወደንስሐ ፡ ሊጠሩ
፡ ይገባልቸዋል ።

9
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

 ምሥጢራትን ፡ መፈጸም፦

ካህናት ፡ የምሥጢራትን ፡ ምስጋና ፡ በበላይነት ፡ መምራትና ፣ በየአጥቢያዎቹ ፡ እና


፡ በሚፈፀሙበት ፡ ቦታ ፡ ሁሉ ፡ የምስጢራት ፡ ንጽሕና ፡ የተበቀ ፡ እንዲሆን ፡ የቀን ፡ ተቀን ፡
ተግባራቸው ፡ ማድረግ ፡ አለባቸው ። የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ መውረድ ፣ መወለድ ፣ ስቅለት ፣
ሞት ፣ ትንሣኤና ፡ ዳግም ፡ መምጣት ፡ የምሥጢራት ፡ ሁሉ ፡ ዋነኛ ፡ ማዕከል ፡ ነው ።
ካህኑም ፡ ሊሰብከውና ፡ ሊያከናውነው ፡ የተጠራውም ፡ ይኸንኑ ፡ ነው ። ካህኑ ፡ እግዚአብሔር
፡ በልጁ ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ አብዝቶ ፡ የሰጠውን ፡ የፍቅሩን ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ ለመናገር
፡ የአዋጅ ፡ ነጋሪ ፡ ነው ። ሕይወት ፡ የሚሰጠው ፡ እያንዳንዱ ፡ የቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ምሥጢር
፡ በአንድም ፡ ሆነ ፡ በሌላ ፡ መንገድ ፡ የሚያመላክተውም ፡ ይህንኑ ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ ነው
። ለመንጋዎቹ ፡ ይህን ፡ የወንጌል ፡ ምሥጢር ፡ በታማኝነት ፡ መግለጥና፡ የሕይወታቸው ፡
ማዕከል ፡ እንዲሆን ፡ ማድረግ ፡ የካህናት ፡ ተግባር ነው ። አንድ ፡ ካህን ፡ በተሠማራበት ፡
ማናኛውም ፡ ቦታና ፡ ጊዜ ፡ በቤትክርስቲያኗ ፡ ዶግማና ፡ ቀኖና ፡ መሠረት ፡ ተልዕኮውን ፡
መፈፀም ፡ ለተጠራበት ፡ ዓላማ ፡ ግዴታው ፡ ነው ፡፡

 እምነትን ፣ አንድነትን ፡ እና ፡ ሥርዓተ ፡ ቤተክርስቲያንን ፡ መጠበቅ፦

በአሁኑ ፡ ዘመን ፡ የቤተ ፡ ክርስቲያንን ፡ አንድነት ፡ ለመጠበቅ ፡ ኃላፊነትን ፡ መውሰድና


፡ ቆራጥነትን ፡ ይጠይቃል ። የወንጌል ፡ ጠበቃ ፡ መሆን ፡ ማለት ፡ በቀላሉ ፡ ትውፊትን ፡
መጠብቅ ፡ ማለት ፡ አይደለም ። የወንጌል ፡ ጠበቃ ፡ መሆን ፡ ማለት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያንንና ፡
ልጆቿን ፡ ከመንፈሳዊ ፡ ድንቁርና ፣ እርጅና ፡ ዝለት ፡ መጠበቅም ፡ ነው ። ስለዚህ ፡ የቤተ፡
ክርስቲያንን ፡ ተልዕኮ ፡ ተቀብሎ ፡ በኃላፊነት ፡ በሆስፒታል ፡ ውስጥ ፡ የተቀመጠ ፡ ሰው ፡
የውርንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮን ፡ መጠበቀና ፡ ጠበቃ ፡ መሆን ፡ ግዴታው ፡ ነው ፡፡

 በሥነ ፡ ምግባር ፣ በቅድስናና ፡ በሁለንተናዊ ፡ እንቅስቃሴው ፡ ሁሉ ፡ ምሳሌ ፡ መሆን፦

ይህ ፡ የሚያመለክተው ፡ ጳጳስም ፡ ይሁን ፡ ካህን ፡ ዲያቆንም ፡ ይሁን ፡ ምእመን


፡ “እንግዲኽ ፡ ሒዱና ፡ አሕዛብን ፡ ሁሉ ፡ በአብ ፡ በወልድና ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ስም ፡
እያጠመቃችሁ ፡ ያዘዝዃችኹንም ፡ ሁሉ ፡ እንዲጠብቁ ፡ እያስተማራችዃቸው ፡ ደቀ ፡
ሙዛሙርት ፡ አድርጓቸው” ፡ (ማቲ ፡ ፳፰ ፥ ፲፱-፳) ፡፡ በአለው ፡ አምላካዊ ፡ ቃል ፡ መሠረት ፡
በጥምቀት ፡ የግዚአብሔርን ፡ ልጅነት ፡ ከአገኘ፡ ክርስቲያን ፡ ሁሉ ፡ የሚጠበቅ ፡ የሕይወት ፡
አካሄድና ፡ መንፈሳዊነት ፡ ነው ፡፡ ይህ ፡ ደግሞ ፡ የወንጌል ፡ አገልገሎት ፡ ተልዕኮን ፡ ይዞ ፡
ሕሙማንና ፡ የሕሙማን ፡ አስታማሚዎች ፡ በሚበዙበት ፡ ሆስፒታል ፡ የተሠማራ ፡ እረኛ
(አገልጋይ ፡ ካህን) ፡ ሲሆን ፡ ሚናው ፡ የጎላ ፡ የሆናል ፡ ወይም ፡ ቀዳሚው ፡ ግብሩ ፡ ነው ፡፡

 በእረኛው ፡ እና ፡ በመንጋዎቹ ፡ መካከል ፡ ያለውን ፡ ክፍተት ፡ ማጥበብና ፡ መድፈን፦

በዘመናችን ፡ እረኝነት ፡ ከባድ ፡ ነው ፡፡ መክንያቱም ፡ በመካከላችን ፡ የተዘረው ፡


አሚከላ ፡ እንዲሁ ፡ በቀላሉ ፡ ተለቅሞ ፡ የሚጠራ ፡ አይደለም ፡፡ ይህ ፡ ደግሞ ፡ የእረኛውን ፡
ደካም ፡ ከፍ ፡ ያደርገዋል ፡፡ ስለዚህ ፡ እውነተኛ ፣ ተጉህ ፣ ለመንገዎቹ ፡ የሚራራ ፡ እና ፡
ዘመኑን ፡ የዋጀ ፡ እረኛ ፡ የሚአስፈልገበት ፡ ዘመን ፡ ነው ፡፡ እውነተኛ ፡ የክህነት ፡ አገልግሎት
፡ ጥሪ ፡ ደግሞ ፡ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮን ፡ መግለጥና ፡ መንጋውን ፡ በቤተክርስቲያን
፡ ጥላ ፡ ሥር ፡ ማሣረፍ ፡ አማራጭ ፡ የሌለው ፡ የሕይወት ፡ እስትንፋስ ፡ ነው ። ይህ ፡
10
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

ከሆነ ፡ አንድ ፡ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮ ፡ ይዞ ፡ ተስፋ ፡ የቆረጠ ፡ መንጋ ፡ በሚበዛበት


፡ ሆስፒታል ፡ ውስጥ ፡ የተመደበ ፡ ካሀን ፡ (የሕከምና ፡ ባለሙያ ) ፡ የመነጋውን ፡ ተስፋ ፡
ማለምለምና ፡ ወደትክክለኛው ፡ የመሠማሪያ ፡ መስክ ፡ መመለስ ፡ ለነገ ፡ የማይባል ፡ ግዴታው
፡ ነው ፡፡ በተጨማሪም ፡ በመቅበዝበዝ ፡ ላይ ፡ ያለውን ፡ መንጋ ፡ ከውነተኛ ፡ እረኛው ፡ ጋር ፡
ማገናኘትና ፡ የእረኛውን ፡ ድምፅ ፡ እንዲሰሙና ፡ እንዲለዩ ፡ ማድረግ ፡ የጠበቅበታል ፣ (ዶ/ር ፡
ብራድሊ ፡ ናሲፍ ፣ጥር 3, 2013) ፡፡

፩.፬. በሕክምና ፡ ሙያ ፡ የተሠማሩ ፡ ኦርቶዶክሳዊ ፡ ካህናት ፡


ሊአደርጋቸው ፡ የሚገቡ ፡ ነገሮች፦

በክርስቶስ ፡ መሠረትነት ፡ የቆመች ፡ ኦርቶዶክሳዊት ፡ ተዋህዶ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡


ውስጥ ፡ አገልጋይ ፡ ሆኖ ፡ የተመረጠ ፡ ካህን (ዶክተር) ፡ የመረጠውን ፡ እግዚአብሔርን ፣ እና
፡ የተመረጠበተን ፡ ሐዋርያዊ ፡ ተልዕኮ ፡ ተንቅቆ ፡ በማወቅ ፡ የሚከተሉተን ፡ ተግባራት ፡
በየለቱ ፡ መከወን ፡ የተበቅበታል ፡፡

፩. ሥራውን ፡ ሁሉ ፡ በጸሎት ፡ መጀመር ፡ እና ፡ ሥርዓተ ፡ ጸሎትን ፡ ማስተማር ፡፡

፪. ምክር ፡ እና ፡ መንፈሳዊ ፡ መመሪያ ፡ መስጠት ፡፡

፫. የህክምና ፡ አገልግሎት ፡ በመስጠት ፡ ሕሙማኑን ፡ ማበርታት ፡፡

፬. በትሕትና ፡ እና ፡ በፍቅር ፡ በማገልገል ፡ ተሕትና ፡ እና ፡ ፍቅርን ፡ ማስተማር ፡፡

፭. ጊዜንና ፡ ጉልበትን ፡ በአገልግሎት ፡ መሥዋዕት ፡ ማድረግ ፡፡

፮. በሕክምና ፡ ሙያ ፡ ወስጥ ፡ የሚደረጉትን ፡ እንቅስቃሴዎች ፡ ከሃይማኖቱ ፡ አንፃር ፡


ለሕሙማኑ ፡ ማስረዳት ፡፡

፯. በተቻለ ፡ መጠን ፡ ሕሙማኑም ፡ ሆኑ ፡ አስታማሚዎችን ፡ በጸሎት ፡ እንዲበረቱ ፡ እና ፡


ተስፋ ፡ እንዳይቆርጡ ፡ ማድረግ ፡፡

፰. በፍፁም ፡ ቅንነት ፡ ከአድሎ ፡ ነጻ ፡ መሆንና ፡ በሃይማኖቱ ፡ ውስጥ ፡ ያሉትንም ፡ ሆነ ፡


የሌላ ፡ እምነት ፡ ተከታይ ፡ ሕሙማንንና ፡ አስታማሚዎች ፡ በኩልነት ፡ ማገልገል ፡፡ ይህ ፡
ተግባር ፡ ከወርቶዶክሳዊ ፡ ካህናት ፡ ይጠበቃልና ፡፡

፱. መናልባትም ፡ በሆስፒታሉ ፡ ውስጥ ፡ ጥሪ ፡ ደርሧቸው ፡ ይቺን ፡ ዓለም ፡ የተሠናበቱ ፡


ሙታንን ፡ ሥርዓተ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ እንዳይጓደልባቸው ፡ ማድረግ ፡ እና ፡ ጸሎተ ፡ ፈተሀት
፡ መፈፀምና ፡ ማስፈፀም ፡፡

በተጨማሪም ፡ ከላይ ፡ የተጠቀሱትን ፡ ወንጌልን ፡ መስበክ ፣ ምሥጢራትን ፡ መፈፀም ፣


በሁሉም ፡ ነገር ፡ አርዓያ ፡ መሆን ፣ መንጋውን ፡ ማሠማራትና ፡ መጠብቀ ፡ የተለዕኮው ፡
ዋነኛ ፡ ተግባራት ፡ ናቸው ፡፡ (አስተምህሮ ፡ ዘተዋህዶ ፣ ታህሳስ ፣ 7 ፣ 2019 ፡ G.C.) ፡፡
11
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

ማጠቃለያ፦
የምሥራቅ ፡ ኦርቶዶክሳውያን ፡ አገለጋዮች ፡ ከሌለው ፡ ዓለም ፡ አገልጋዮች ፡ የሚለዩት
፡ በዋናነት ፡ የወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ማዕከላቸው ፡ የመድኃኒታችን ፡ የኢየሱስ ፡ ከረስቶስ ፡
ፍፁም ፡ አምላክ ፡ ፍፁም ፡ ሰው ፡ መሆን ፡ በድንግል ፡ ማርያም ፡ የሚለው ፡ ነው ፡፡ ይህ ፡
ደግሞ ፡ የመሥራች ፡ መለካም ፡ ዜና ፡ ለዓለም ፡ ሁሉ ፡ ማወጅ ፡ ነው ፡፡ ወንጌል ፡ ማለት ፡
እግዚአብሔር ፡ ወልድ ፡ ሰው ፡ የሆነበት ፣ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ኅብረት ፡ ይመልሰው ፡
ዘንድ ፡ የወደቀውን ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ ሰብእና ፡ ገንዘብ ፡ ያደረገበት ፣ ኃጢአትን ፡ ድል ፡
የነሣበትና ፡ ሞትን ፡ ያጠፋበት ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ ነው ። ይህ ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ በማናቸውም
፡ የቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ሕይወት ፡ ሰጪ ፡ አገልግሎቶች ፤ ማለትም ፡ ወንጌልን ፡ በመስበክ ፣
ምሥጢራትን ፡ በመፈፀም ፣ በአምልኮትዋ ፣ በጾምና ፡ በጸሎት ፡ በመሳሰሉት ፡ እውን ፡ የሆናል
። ካህናት ፡ ይህን ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ ማለትም ፡ የክርስቶስን ፡ ሕይወት ፣ ሞትና ፡ ትንሣኤ ፡
ለዓለም ፡ ሕዝብ ፡ ሁሉ ፡ ሊሰብኩ ፡ ይገባል ። ስለሆነም ፡ አንድ ፡ የቤተክርስቲያን ፡ አገለጋይ
፡ በተሰማራበት ፡ የሥራ ፡ ዘርፍ ፡ ሁሉ ፡ በወንጌል ፡ አገልግሎት ፡ ሐዋርያዊ ፡ ተልዕኮ ፡
በመያዝ ፡ የቤተክርስቲያኗን ፡ ተልዕኮና ፡ ዓላማ ፡ በወንጌል ፡ ማወጅና ፡ መተርጎም ፡ ይገበዋል
፡፡ በሆስፒታሎች ፡ ውስጥ ፡ የኦርቶዶክስ ፡ ክህነት ፡ አገልግሎት ፡ ሚናው ፡ ከፍተኛ ፡ ነው ፡፡
የሕሙማን ፡ እና ፡ የአስታማሚዎች ፡ ቁጥር ፡ እየጨመረ ፡ በሄደ ፡ ቁጥር ፡ መንፈሳዊና ፡
ሥጋዊ ፡ የሕክምና ፡ እንክብካቤ ፡ ፍላጎት ፡ ይጨምራል ፡፡ ዶክተሮችም ፡ የሆኑት ፡ የኦርቶዶክስ
፡ ካህናት ፡ ይህንን ፡ እንክብካቤ ፡ ለመስጠት ፡ ልዩ ፡ ብቃት ፡ ያላቸው ፡ ናቸው ፡ እና ፡
ለታመሙ ፡ እና ፡ ለሚሰቃዩ ፡ ሰዎች ፡ ፈውስ ፡ ትልቅ ፡ ሚና ፡ ይጫወታሉ ፡፡ በተለይም ፡
ደግሞ ፡ በዚህ ፡ ዓለም ፡ ድካም ፡ በመቃተት ፡ ለአሉት ፡ ሁላ ፡ የሕይዎት ፡ ተስፋን ፡ መስጠት
፡ የካህናት ፡ ቀዳሚ ፡ ተልዕኳቸው ፡ ነው ፡፡ በአጠቃላይ ፡ በመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ውስጥ
፡ ያለ ፡ አገልጋይ ፡ የመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ተልዕኮና ፡ መመሪያዎቹን ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡
ማስተዋልና ፡ የአገልግሎቱም ፡ መመሪያ ፡ በማድረግ ፡ የመንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡ ባለቤት ፡
እግዚአብሔር ፣ ዓላማው ፡ መንፈሳዊ ፣ የአገልግሎቱም ፡ መሪ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ መሆኑን
፣ በመረዳት ፡ የአገልግሎቱ ፡ መስክ ፡ ለሰው ፡ ሕይወት ፡ እረፍት ፡ ማስገኘት ፡ መሆኑን ፡
በማስተዋል ፡ ማወቅ ፡ ይገባል ፡፡ አነሳስቶ ፡ የአስጀመረን ፣ አስጀምሮ ፡ የአስፈፀመን ፡ የአእምሮ
፡ ባለቤት ፡ ልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ የተመስገን ፡ የሁን ፡ አሜን ፡፡

12
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ
በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን ፡፡

ማጣቀሻ ፡ መጻሕፍት፦
፩. አስተምህሮ ፡ ዘተዋህዶ ፣ ታህሳስ ፣ 7 ፣ 2019 ፡ G.C. : ”መንፈሳዊ ፡ አገልግሎት ፡
ተልዕኮና ፡ መመሪያዎቹ“
፪. መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ የብሉይ ፡ እና ፡ የሐዲስ ፡ ኪዳን ፡ መጻሕፍት ፡ በርሃንና ፡ ሰላም ፡
ቀዳማዊ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ማተሚያ ፡ ቤት ፡ ፲፱፶፫ ፡ ዓ . ም ፡፡
፫. ፍትሐ ፡ ነገሥት ፡ ንባቡና ፡ ትርጓሜው ፡ በ፲፱፻፺ ዓ.ም ፡ በትንሣኤ ፡ የመጻሕፍት ፡
ማተሚያ ፡ ድርጅት ፡ አዲስ ፡ አበባ ::
፬. ዶ/ር ፡ ብራድሊ ፡ ናሲፍ ፣ጥር 3, 2013 ፣ “ኦርቶዶክሳዊ ፡ ሕይወት” ፡
፭. ዶ/ር ፡ ብራድሊ ፡ ናሲፍ ፣ጥር 3, 2013 “የኦርቶዶክሳውያን ፡ ጳጳሳት ፡ ሐዋርያዊ ፡
ልዕኮ” ፡ ትርጉም ፡ በሊቀ ፡ ኅሩያን ፡ ቀሲስ ፡ መልአኩ ፡፡

13
ትምህርተ ፡ ኖሎት ፡፡ ገጽ

You might also like