You are on page 1of 25

ነቢዩ ዳንኤል

ዝክረ ዐበይት ነቢያት


ማውጫ

ጭብጥ

ጸሐፊ

ይዘት
ማውጫ
THE BUSENESS PLAN

01
ጭብጥ
• ከናቡከደነጾር እስከ ክርስቶስ ድረስ ስለሚነሱ የዓለም ኃያላን መንግስታት ትንቢት ነው።

• የትንቢተ ዳንኤል መጽሐፍ መልዕክት አማጺ የዓለም መንግስታት ላይ ስለሚፈርደውና


ፍጹም ስለሚያጠፋቸው፤ እንዲሁም በሱ እምነት የጸኑትን የቃልኪዳኑን ሕዝብ ለማዳን
ስለሚታመነው የእግዚአብሔር አምላክ ፍጹም ሉአላዊነት መግለጽ ነው።
• ትንቢተ ዳንኤል የአምላክን ሉአላዊነት የሚያበክረው በመጻኢው መሲህ በኩል ነው።

• ትንቢቱ ስለ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር፣ ስለ ጥበብ አሰራር፣ ስለ ነገስታትና ስርወ


መንግስታት መነሳትና መውደቅ፣ እንዲሁም የፈጣሪን የሁሉ የበላይነትን ይተነትናል።
ማውጫ
THE BUSENESS PLAN

2
ጸሐፊ
• “በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም
አያደርግም” አሞጽ 3:7 ተብሎ እንደተነገረው ነብይነት በፍላጎት ወይም በምኞት
የማይገኝ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።

• ከአራቱ ዓበይት ነቢያት አንዱ ነው፡፡

• በነብይነት የነበረበት ዘመን ከ625 – 526 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ነው።


• ዳንኤል ማለት ፍትሐ እግዚአብሔር፣ ዳኛ እግዚአብሔር ማለት ነው።

• የአይሁድ ንጉሣዊ ቤተሰብ በመሆኑ ቤተሰቦቹ በባቢሎን በ604 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ
በተማረኩ ግዜ በልጅነቱ ተማርኮ ተወስዶአል።

• ዳንኤል መንግስተ ባቢሎን ከወደቀ በኋላ በመንግስተ ፋርስ እስከ ንጉሥ ዳርዮስ ዘመነ
መንግስት ኖሮአል።
• የዳንኤል እናትና ሠለስቱ ደቂቅ የኤልያቄም ልጆች ናቸው።

• ከሦስቱ ወጣቶች ጋር ነብዩ ዳንኤል በናቡከደነጾር መንግስት ባለሟል ሆኖ ተሹሟል።

• ዳንኤልና ሠለስቱ ደቂቅ የትውልድ ስማቸው በባቢሎን መንግስት የጃንደረባ አለቃ


ተቀይሮባቸዋል።
የዳንኤልና የሦስቱ ወጣቶች ስም ትርጓሜ

የአይሁድ ስም ትርጉም የባቢሎን ስም


ዳንኤል እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ብልጣሶር
አናንያ እግዚአብሔር መሐሪ ነው ሲድራቅ
ሚሳኤል ማን እንደ እግዚአብሔር ሚሳቅ
አዛሪያ እግዚአብሔር ረድቶናል አብደናጎ
ማውጫ
THE BUSENESS PLAN

3
ይዘት
• ትንቢተ ዳንኤል ከመጻኢው ትንቢት ሌላ በዘመኑ ወደ ሰባ ሦስት አመታት 607-534
ቅ.ል.ክ ማለትም ከባቢሎን ንጉሥ ከናቡከደነጾር እስከ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ የሚሸፍን
ነው።

• ትንቢተ ዳንኤል በሁለት አበይት ክፍላት ይከፈላል።

• ከምዕራፍ አንድ እስከ ስድስት ስለ ነብዩ ዳንኤልና ስለ ሰለሥቱ ደቂቅ ገድልና ተአምራት
ይይዛል።

• ከምእራፍ ሰባት እስከ አስራ ሁለት የትንቢትና ራእይ ክፍል ነው።


ምዕራፍ 1 - ዳንኤልና ሠለስቱ ደቂቅ
• አራቱ ነውር የሌለባቸውና መልከ መልካሞች፥ በጥበብ ሁሉ የሚያስተውሉትን፥ እውቀትም የሞላባቸውን
ብልሃተኞችና አስተዋዮች የሆኑትን ብላቴኖች የመንግስት ባለሟል ይሆኑ ዘንድ ተመረጡ።

• ዳንኤልም በንጉሡ መብልና በሚጠጣው ጠጅ እንዳይረክስ በልቡ አሰበ፤ እንዳይረክስም የጃንደረቦቹን አለቃ
ለመነ።

• ለጣኦታት የተሰዋውን የንጉሡን ምግብም መመግብ ተዉ። የእግዚአብሔር ጸጋ ግን በነርሱ ላይ ነበር።


• ለፈተናም ቀርበው የመንግሥቱን ምግብ ከተመገቡት ይልቅ ያማሩና የወፈሩ ሆነው
ተገኙ።

• ስለዚህም ከላመው ከጣመው ምግብ ይልቅ የለመኑትን ጥራጥሬ


ይበሉ ዘንድ ተፈቀደላቸው።

• እግዚአብሔር በትምህርትና በጥበብ ሁሉ እውቀትንና ማስተዋልን


ሰጣቸው፤ ዳንኤልም በራእይና በሕልም ሁሉ አስተዋይ ነበረ።
ምዕራፍ 2-7 - በመንግሥታት ላይ የሚበረታው የእግዚአብሔር ሉአላዊነት
• እግዚአብሔር ናቡከደነጾርን ሕልም አሳለመው።

• ከነብዩ ዳንኤል በቀርም ማንም ሊፈታው አልቻለም።

• ሕልሙም ጌታ በወንጌል “የአሕዛብ ዘመን” ብሎ


በጠራው (ሉቃ 21:24) ዘመን ስለሚነሱና ስለሚወድቁ
የዓለም መንግሥታት ነው።
• ከተለያዩ ማዕድናትና ብረታት የተገነባ ግዙፍ የሰው ምስልን ንጉሡ
አለመ።

• የዚህም ምስል ራስ ጥሩ ወርቅ፥ ደረቱና ክንዶቹም ብር፥ ሆዱና


ወገቡም ናስ፥ ጭኖቹም ብረት፥ እግሮቹም እኩሉ ብረት እኩሉም
ሸክላ ነበረ።

• ምስሉ የተገነባባቸው የማዕድናት ክብር ከራሱ ጀምሮ እስከ እግሮቹ


እየቀነሰ መሄዱ ስለ መንግሥታቱ ክብርና ኃይል መዳከም
ያመለክታል።
የራሱ ወርቅ የናቡከደነጾርን የባቢሎን መንግስት 606-538
ቅ.ል.ክ ያመለክታል።

የደረቱና ክንዶቹም ብር ከባቢሎን የሚያንሱ የሜዶንና


የፋርስ መንግሥታትን 538-338 ቅ.ል.ክ ያመላክታል።

የሆዱና ወገቡም ናስ የሚያሳየው የግሪክ መንግሥትን


330-30 ቅ.ል.ክ ነው።

የጭኖቹም ብረት ስለሮም መንግሥት ነው።

እኩሉ ብረት እኩሉም ሸክላ የሆኑት እግሮቹ ስለ አውሮጳ


ናቸው።
• የጭኖቹም ብረት ስለሮም መንግሥት ነው።

• ሁለቱ እግሮች የሚያመላክቱት የሮም መንግሥት በሁለት ምስራቅና ምዕራብ ተብሎ መከፈሉን ነው።

• አስሩ ጣቶች በመጨረሻው ዘመን ስላሉት አስር መንግሥታት ያነሳል።

• አንዳንድ ምሁራን የአስሩ መንግሥታት ትንቢት በ European Economic Community ወይም


በተለምዶ Common Market በሚባለው መፈፀሙን ያምናሉ።

• የ ECC አባል ሀገራት ጣልያን፣ ጀርመን፣ ነዘርላንድ፣ ቤልጅየም፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ለክሰምበርግ፣
ዴንማርክ፣ አየርላንድና ግሪክ ነበሩ።
• እጅም ያልነካው ከተራራው ተፈንቅሎ ከወርቅ፣ ብር፣ ብረትና ሸክላ የሆነውን
የምስሉን እግሮች የፈጨው ድንጋይ የክርስቶስ ምሳሌ ነው።

• የምስሉ መውደምና የድንጋዩ ታላቅ ተራራ መሆን የአሕዛብ መንግሥታትን


መውደቅና የክርስቶስ ኢየሱስ መንግሥት መመስረትና መስፋፋትን
ያመለክታል።
ምዕራፍ 3
• ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት
ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም
አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው። ሕዝቡንም
እንዲሰግዱለት አዘዛቸው።

• ሠለስቱ ደቂቅ ንጉሡ ላቆመው ምስል አንሰግድም


በማለታቸውና ንጽህይት ሐይማኖታቸውን በመመስከራቸው
እሳት ውስጥ ቢጣሉም አምላክ በቸርነቱ አድኗቸዋል።

• የአምላክ ልጅ የመሰለ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ ተአምራቱንና


ተራዳኢነቱን አሳይቶናል።

• ምዕራፍ አራት የናቡከደነጾርን ቅጣትና ምሕረት ያሳያል።


ምዕራፍ 5 - የብልጣሶርና የባቢሎን መንግሥት ወድቀት
• ናቡከደነጾርን የተካው ብልጣሶር በእግዚአብሔር የቤተ መቅደስ ንዋየ ቅዱሳት ላይ ድፍረት
ፈጸመ።

• የእግዚአብሔር ጣትም በተአምራት በግምጃ ቤቱ ግድግዳ ላይ ተገልጻ ማኔ፥ ቴቄል፥ ፋሬስ


ብላ ጻፈች። ከዳንኤልም በቀር ማንም ሊያነበውና ሊተረጉመው የቻለ አልነበረም።

• ብልጣሶርም በነብዩ ዳንኤል ትንቢት መገለፅ ምክንያት ሐምራዊ ግምጃ እንዲያለብሱት፥


የወርቅ ማርዳም በአንገቱ ዙሪያ እንዲያደርጉለት አዘዘ፤ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዥ
እንዲሆን አዋጅ አስነገረ።
የጽሕፈቱ ትርጓሜ

• ማኔ ማለት፥ እግዚአብሔር መንግሥትህን ቈጠረው ፈጸመውም ማለት ነው።

• ቴቄል ማለት፥ በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀልለህም ተገኘህ ማለት ነው።

• ፋሬስ ማለት፥ መንግሥትህ ተከፈለ፥ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ ማለት ነው።
• በምዕራፍ 6 የነብዩ ዳንኤል ከአናብስት አፍ የዳነበት ታዋቂ ተአምራት ተጽፎአል።

• በምዕራፍ 7 የአራቱ ታላላቅ አራዊት ራእይ ተጽፎአል። ናቡከደነጾር ካየው የታላቁ ምስል
ሕልም ጋር የሚነጻጸር ሲሆን ስለ ኃያላን መንግሥታት መነሳትና መውደቅ ያትታል።

• አስሩ ቀንዶች አስሩን ነገሥታት ሲወክሉ አንደኛው ቀንድ ደግሞ ሌሎች ሦስት ነገሥታትን
ስለሚያስገብር አንድ ንጉሥ ይመሰላል።

• ሁሉም መንግሥታት በዘመናት በሸመገለውና በቅዱሳኑ በመጨረሻም ይረታሉ።


ምዕራፍ 8-12 - ስለእግዚአብሔር ሕዝብ ራዕይ
• በምዕራፍ 8 ነብዩ ዳንኤል ያየው የአውራው በግና የአውራው ፍየል ጠብ ሊመጣ ያለውን
የግሪክና ፋርስ ጠብ ያመለክታል።

• በምዕራፍ 9 እስከ መሢሁ መምጣት ሰባ ሳምንታት እንደሚቆጠር ተጽፏል።

• የነብዩ ዳንኤል የመጨረሻው ራእይ በምዕራፍ 10-12 የተገለጸው ሲሆን ስለ እግዚአብሔር


ክብር፣ በግሪክ ስለሚፈጸመው የፋርስ መንግሥት ውድቀት፣ ስለ ሰሜንና ደቡብ ነገሥታት፣
ስለ ታላቁ መከራና ስለ ድህነት ይናገራል።
感谢观看 THANKS!
汇报:第一PPT 导师:1PPT

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

You might also like