You are on page 1of 6

የዘረኝነት አረንቋ

የዘረኝነት አረንቋ
በወንድም ወሒድ ዑመር

1
የዘረኝነት አረንቋ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

49፥13 *እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች
አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ
ውስጥንም ዐዋቂ ነው*፡፡

“዗ረኝነት”racism” ማለት የራስን ቋንቋና ዗ውግ አተልቆ የሌላውን ማሳነስ፣ ማግለል፣ መቃረን እና ማራከስ

ነው። ዗ረኝነት ትዳርን፣ ቤተሰብን፣ ጉርብትናን፣ ማህበረሰብን፣ ሃይማኖት፣ መንግሥትን፣ አገርን የሚበትን
ክፉ በሽታ ነው። ዗ረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠር዗ኝነት፣ ቡድንተኝነት ምንጫቸው “አህዋ” ማለትም
“ዜንባሌ”inclination” ነው፤ አንድ ሙስሊም ነፍሱንም ከዜንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ
መኖሪያው ናት፦

79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ
በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡

ዜንባሌ ደግሞ ከተከተሉት ሊመለክ የሚችል አደገኛ ጣዖት ነው፦

25:43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?*

዗ረኝነት ምንጯ ዜንባሌ ከሆነ ታዲያ ከ዗ረኝነት በሽታ ለመገላገል መፍትሔው ምንድን ነው? አዎ
አምላካችን አላህ በቅዱስ ቃሉ የሚናገረውን እና ነብያችን”‫ ”ﷺ‬በሐዲሳቸው የተናገሩትን በጥሞና ሰምቶ

መተግበር ነው፤ እስቲ ከቁርኣን እንጀምር፦

4፥1 *እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን
ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ*፡፡

“ነፍሥ” የሚለው ቃል አደምን ያሳያል፤ “መቀናጃዋ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል ”዗ውጀሃ” ሲሆን

የአደም ጥንድን ያሳያል፤ ይህቺም ጥንድ ሐዋ ናት፤ “ነፍሥ” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ከ” የሚል
መስተዋድድ አለ፤ ይህም ከአደም መፈጠራችንን ያሳያል፤ “ከእነርሱም” ተብሎ የተቀመጠው ቃል
“ሚንሁማ” ሲሆን ሙተና ማለትም ሁለትዮሽ”dual” የሚያሳይ ነው፤ እነዙህ ሁለቱ አደምና ሐዋ
ናቸው፤ “እነርሱም” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህም ከአደምና ከሐዋ
መፈጠራችንን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ታዲያ የአንድ እናት እና አባት ልጆች ከሆንን አንዱን ዗ር ማብለጥ
ሌላውን ማሳነስ ጠባብነት አይደለምን? አንድ ሙስሊምስ እንዲህ አይነት ውዜግብ ውስጥ መግባት
የእምነትን ገመድ የሚበጥስ አይደለምን? አላህ ሁላችንንም የፈጠረን ከአንድ አባትና እናት ነው፦

2
የዘረኝነት አረንቋ
49፥13 *እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች
አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ
ውስጥንም ዐዋቂ ነው*፡፡

“ወንድ” እና “ሴት” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህም ሰዎች ከወንድና ከሴት

መፈጠራቸውን ያሳያል፤ አላህ ነገድ እና ጎሳ ያደረገን ብዘ ስለሆንን ለትውውቅ የትውልድ መዜገብ እንጂ
አላህ ዗ንድ ማነስ እና መተለቅ አላህ በመፍራት ብቻ ነው።

አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ወ዗ተ ቋንቋ ነው፤ የቋንቋዎቻችን መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፤ በዙህ
ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት፦

30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ *የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት


ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት*፡፡

ቋንቋዎች ይ዗ውት የመጡት ታሪክ፣ ባህል፣ ልማድ፣ ትውፊት፣ ወግ፣ ክህሎት እና ሙዳየ-ቃላት “዗ውግ”
ethnic” ሆኗል፤ ይህ እራሱ የቻለ ውበት ነው። ነገድ እና ጎሳ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶችና መተዋወቂያ ነው።
዗ረኝነት ግን ከቋንቋ አሊያም ከቀለም የሚመጣ ሳይሆን የልብና የአስተሳሰብ በሽታ ነው። በኢስላም ደሃ
ሃብታም ሳንል፤ ዗መድ ባዕድ ሳንል፣ ዜንባሌ ተከትለን ሳናዳላ ለአላህ ብለን ለሰው ሁሉ በትክክል ፍትሕ
ቀዋሚዎች መሆን አለብን፦

4፥135 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆችና በቅርብ
ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ
ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም
መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡

6፥152 *”በተናገራችሁም ጊዜ በዘመዶቻችሁ ላይ ቢኾንም እንኳ እውነትን በመናገር


አስተካክሉ”*፡፡ በአላህም ቃል ኪዳን ሙሉ፡፡ እነሆ ትገሰጹ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡

ስለዚህ የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ እንጂ መኩሪያ


ወይም ማብጠልጠሊያ አይደለም፤ ዘረኝነት በዲንያ በአላህ ዘንድ ዋጋ የሚያሳጣ ሲሆን በአኺራም
ደግሞ ለጀሃነም ይዳርጋል፦

ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 344

አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”‫ ”ﷺ‬አሉ፦ *”አላህ ዐዘ ወጀል ከእናንተ


የዘመነ-ጃሂሊያን ኩራት አስወግዷል፤ ይህም በዘር መኩራት ነው። ይህ ለጥንቁቁ አማኝም ወይም
ለአደገኛው ካሃዲ አንድ ብቻ ነው። እናንተ የአደም ልጆች ናችሁ፤ አደም ከአፈር ነው የመጣው፤

3
የዘረኝነት አረንቋ
ሰዎች በዘራቸው የሚኮሩ ከሆነ ጀሃነምን ይሞሏታል፤ ወይም አላህ ዘንድ ዋጋቸው ጥንዚዛ
በአፍንጫው ከሚሽከረከር ጉድፍ ያነሰ ከሆኑት ይሆናል*።

የአደም ልጆች የአንድ አባት እና እናት ልጆች ነን ብሎ ማስተንተን መጠበብ ሲሆን በዘረኝነት
አራንቋ መለከፍ መጥበብ ነው፦

ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 150

ጁንደብ ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”‫ ”ﷺ‬አሉ፦ *”ማንም ሰው ግልጽ


ባልሆነ ነገር፣ በዘረኝነት ጥብቅና፣ በዘረኝነት መንገድ የተጋደለ ግድያው የጃህሊያ ነው*።

“ጃህሊያህ” ማለት “መሃይምነት” ማለት ነው፤ ቅድመ-ቁርኣን ያለው ጊዜ ዘመነ-ጃህሊያህ


ይባላል፤ በእርግጥም በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ የነበረችው ዘረኝነት ጥንብ ናት፦

ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 81

ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንዳስተላለፈው፦ “በጉዞ ከነቢዩ”‫ ”ﷺ‬ጋር ነበርን፤ አንድ ሰው ከሙሃጅር
ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው ጀርባውን መታው፤ አንሷሩም፦ “አንሷሪ ሆይ! አለ፤ ሙሃጅሩም፦
“ሙሃጅር ሆይ! አለ። ከዚያም የአላህ መልእክተኛም”‫”* ”ﷺ‬ይህ የጃህሊያህ አጠራር አይደለምን?
አሉ፤ እነርሱም፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ከሙሃጅር ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው
ጀርባውን መታው” አሉ፤ እርሳቸው፦ “እርሷን(ዘረኝነትን) ተዋት ጥንብ ናት” አሉ*።

“ሙሃጅር” ማለት “ስደተኛ” ማለት ሲሆን ከመካ የተሰደዱትን ሶሓብይን ያመለክታል፤ “አንሷር”

ማለት “ረዳት” ማለት ሲሆን ከመካ የተሰደዱት የተቀበሉ የመዲና ሶሓብይን ያመለክታል።

አንዱ ዗ር ተነስቶ ሌላውን ዗ር ሲበድል የተበደለው ያልበደለውን በ዗ሩ ብቻ በቁርሾ ለመበቀል መነሳት
ጠባብነት ነው፤ በኢስላም የቀደሙት ትውልድ በሰሩት ወንጀል የአሁኑን ትውልድ መጠየቅ ወይም መቅጣት
እራሱ ሕግ መተላለፍ ነው፦

ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 162

ዐብደላህ እንደተረከው ነብዩም”‫ ”ﷺ‬አሉ፦.. *ሰው በአባቱ ወይም በወንድሙ ወንጀል


አይቀጣም*።

4
የዘረኝነት አረንቋ
በተጨማሪም አንድ ሰው ባጠፋው ብዘኃኑን ዗ር ማንቋሸሽ ወይም ማዋረድ ሐራም ነው፦

ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 106

ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአላህ መልእክተኛ”‫ ”ﷺ‬እንዲህ አሉ፦ *”ከሰዎች መካከል ትልቁ


ውሸታም ሌላው ሰው ማንቋሸሽ እና መላውን ዘር ማዋረድ ነው*።

እረ እሩቅ ሳንሄድ ወደ ዗ረኝነት የሚጣራ፣ በ዗ረኝነት መንገድ የሚታገል፣ በ዗ረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ
ሰው ከነብያችን”‫ ”ﷺ‬ሱናህ ውጪ ነው፦

ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 349

ጁበይር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”‫ ”ﷺ‬እንዲህ አሉ፦ *”ወደ ዘረኝነት የሚጣራ ከእኛ
አይደለም። በዘረኝነት መንገድ የሚታገኝ ከእኛ አይደለም። በዘረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ ከእኛ
አይደለም*።

በድንበር፣ በክልል፣ በወሰን የከፋፈሉን ሰዎች ናቸው። ምድር እኮ የአላህ ናት፤ ተቸግረን ብንሰደድ ሰፊ ናት፤
ዋናው ይህቺ አንድ የተውሒድ መንገድ ሃይማኖታችን ናትና አላህን በብቸኝነት ማምለክ ነው፦

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! *ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ እኔንም ብቻ
አምልኩኝ*፡፡

21፥91 *ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና
አምልኩኝ*፡፡

እንግዲህ ዲነል ኢስላምን የመሰለ ሰውን የሚያስተሳስር የአላህ ገመድ እያለ በ዗ረኝነት፣ በጎጠኝነት፣
በጠር዗ኝነት፣ በቡድንተኝነት መለያየት “አትለያዩ” ያለን አላህ አለመታ዗ዜ ነው። በ዗መነ-ጃህሊያህ ጊዛ
ጠበኞችም በነበርን ጊዛ በእኛ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ እናስታውስ፤ በልቦቻችሁም መካከል አስማማን፤
በጸጋውም ወንድማማቾች ሆንን፥ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ በነበር ጊዛ አዳነን፦

3፥103 *የአላህንም የማመን ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ


በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም
ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፡፡ ከእርስዋም አዳናችሁ*፡፡
እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡

በተሰጠን ጸጋ ልክ ወንድማማች መሆን ሲገባን ዚሬ በመሃይምነት አራንቋ ተጠቅተን በማህበራዊ ሚድያ


዗ረኝነትን ስናራግብ እንውላለን፤ ኢስላም ዓለም-ዐቀፍ ሆኖ ሳለ ምነው ጠበብንሳ? ምነው ይህ ያህል

5
የዘረኝነት አረንቋ
ኢማናችን ወረደሳ? የኢሥላም ልዕልና ከ዗ር፣ ከብሔር፣ ከቋንቋ፣ ከቀለም፣ ከፓለቲካ በላይ ነው። አላህ
ሁላችንም ያስተካክለን፥ ሂዳያ ይስጠን፣ ከጥንቧ ዗ረኝነት ይጠብቀን! አሚን።

ወሰላሙ አለይኩም

ወንድም ወሒድን በቴሌግራም ለመከታተል በሚከተለው አድራሻ ጆይን በማለት ያገኙታል።

https://t.me/Wahidcom

You might also like