You are on page 1of 2

አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ

ኢስላማዊ ተብለው የሚለቀቁ ፊልሞች ላይ ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል በአጭሩ ፡-

1) በዚህ መልኩ ዳዕዋ ማድረግ ቢድዓህ መሆኑ ፤


ከአሏህ ዘንድ ምንዳ ያስገኛል ተብሎ የሚሰራ ስራ በአጠቃላይ አጅር ያስገኝ ዘንድ ሁለት መስፈርቶችን መሟላት
አለበት፡፡

I. ኢኽላስ፡- ስራው ለአሏህ ብቻ ጥርት ብሎ መሰራት አለበት፤


II. ሙታበዓህ፡-ነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) የነበሩበትን መንገድ የተከተለ መሆን አለበት፤

ነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) ስለ አለፉ ሰዎች ታሪክ ለማስተማር አቡበክርን ፣ ዑመርን እንዲሁም ሌሎችን ሶሃቦች በመሰብሰብ
ድራማ በማሰራት አላስተማሩም፡፡ ይልቁንም ያለምንም ተከሉፍ (ከአቅም በላይ መጨናነቅ) ታሪኩን ግልጽ በሆነ
ቋንቋ በማስተማር ይኸው አለም ከምእራብ እስከ ምስራቅ ሀዲስን በማንበብ ላይ ይገኛል፡፡ በድራማ መልክ
ማስተማር ይበልጥ ጠቃሚና የተፈቀደ ቢሆን ኖሮ ለአለም ብርሀን ይሆኑ ዘንድ የተላኩት ነብይ በሰሩት
ነበር፡፡ሸይኽ ዓብዱሰላም ኢብኑ በርጀስ "አልሁጀጁል ቀዊያህ " በተሰኘው ኪታባቸው ገጽ 40 ላይ እንደጠቀሱት
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሂመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፡-"ማጠቃለያ፡-ሸሪዓህ ጥቅም ያለውን ነገር በፍጹም
ቸላ አይልም፡፡ይልቁንም አሏህ (ሱ.ወ) ሀይማኖታችንን አሟልቶልናል ፤ ሌሊቱ እንደ ቀን በሆነበት ሁኔታ ላይም
ትቶናል ፤ ይህንን መንገድ የሳተ ሰው ጠፊ ነው፡፡"

2) ነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) ድራማ በግልጽ ማውገዛቸው ፤


እመት ዓኢሸህ ባወራችው ሶሂህ የሆነ ሀዲስ ነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-"(ዱንያ ላይ ካሉት ምርጥ ነገሮች)
እሄን ፣ እሄን ትሰጣለህ ብባል እንኳ ሌላን ሰው መስየ መስራት አልፈልግም፡፡" ኢማሙ አህመድና ቲርሚዚይ
አውርተውታል፡፡

3) ከካህዲያን የተወረሰ በመሆኑ ፤


ሸይኹል ኢስላም ኢብ ተይሚያህ "ኢቅቲዷኡ ስ-ሲራጡል ሙስተቂም"በተሰኘው ኪታባቸው ውስጥ ነሷራዎች "ዒይደ
ሸዓኒን " በማለት በሚያከብሩት ክብረ በአል ውስጥ ድራማ በመስራት ያከብሩ እንደነበር ይገላጻሉ፡፡ ከዚህም
የምንረዳው ድራማ ከካህዲያን የተወረሰ መሆኑን ነው ፡፡(ከነርሱ ጋር ከመመሳሰል አሏህ ይጠብቀን!!!)
4) ውሸትን ማካተቱ ፤
እነደሚታወቀው ድራማና ውሸት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው ፤ አይላቀቁም፡፡ ውሸት ደግሞ ሀራም
ነው፡፡ ነገር ግን ሶስት ቦታዎች ላይ ውሸት መፈቀዱ በሶሂህ ሀዲስ ተረጋግጧል፡፡

a) ሁለት ሰዎችን ለማስታረቅ፤


b) ባልና ሚስት በመካከላቸው፤
c) በጦርነት ወቅት( አሚሩ ለጦሩ ደህንነት ሲል) ፤

ከነዚህ ሶስት ነገሮች ውጭ ለማስተማር ውሸት ይፈቀዳል የሚል መረጃ የት አለ?

5) ከተራራ የከበዱ ቃላትን መናገር ፤


አንዳንዱ ለማስተማር ብሎ ነብዩን ይሳደባል ፤ አንዳንዱ ደግሞ አቡጀህልን ወክሎ ይሰራል፤ ሌላው ቄስ መስሎ
መስቀል ይይዝና ሰዎችን እያሳለመ ድራማ ይሰራል፡፡ ሱብሃነሏህ የቢድዓህ መዘዙ የከፋ ነው!!!

6) የታላላቅ ሰዎችን ክብር ማጉደፍ ፤


አንድ ተራ ሰው ነብያትን ወይንም ሶሀቦችን መስሎ መስራቱ ያለምንም ጥርጥር ክብራቸውን ማጉደፍ ነው፡፡
ይህንን እውነታ ፊልሙን የሚያዘጋጁ ሰዎች ራሳቸው ያውቁታል፡፡ አር-ሪሳላህ (የሀምዛ ፊልም) የተሰኘውን ፊልም
ብንመለከት መግቢያው ላይ የነብዩንና የአራቱን ኸሊፋዎች ምስል እንደማያሳዩ ፤ ምክኒያቱንም ሲገልጹ
ክብራቸውን ለመጠበቅ እንደሆነ ይገልጻሉ ፡፡ጥያቄያችን አጭርና ግልጽ ነው፡፡ የሌሎች ሶሃቦች ክብርስ ? ማንም
ተራ ፣ ሰካራም ምናልባትም ሙስሊም ያልሆነ ሰው ሶሃባን ወክሎ መስራቱ የተዎገዘ መሆኑ አእምሮ ካላቸው
ሰዎች ዘንድ አወዛጋቢ አይመስለኝም ፡፡ ነገሩ ግን በዚህ አላበቃም ፤ ጊዜው ረዘመና ልባቸውም ደረቀ ፤
ነብያትን ፣ መላኢካዎችን ፣ ጀሃነምን ጨምሮ በቴሌቪዥን መስኮት አሳዩን ፤ በተለይ የሀሰን ፊልም ተብሎ
ሽዓዎች የሰሩት ፊልም ኢስላም ለማንኮታኮት ታስቦበት የተሰራ ፊልም ነው፡፡ መለከል መውትንና እሳትን ፊልሙ
ላይ የተመለከቱ አንዳንድ ሰዎች በተለይ ህጻናት ሞትንና ጀሃነምን አቃለው ለማየት በቅተዋል፡፡(አሏሁል
ሙስተዓን) ይህ ሁሉ ነጥብ ሲጠቀስ አንዳንድ ሰዎች ለማስተማር ከሆነ ምን ችግር አለው ? እንዲሁ ከማስተማር
ስእላዊ በሆነ መንገድ ማስተማር ይሻላል የሚል ሀሳብ ያነሳሉ፡፡ እነዚህን ሰዎች ቁጥር አንድ ላይ የጠቀስኩትን
ነጥር በአጽንኦት እንዲያነቡ እየጋበዝኩ የሚከተለውን እጨምራለሁ ፤ ብዙ ቢድዓዎች የተፈጠሩት ምናለበት ፤
መልካም ነው እና በመሳሰሉት የሸይጧን መሸንገያዎች ነው፡፡ ከዚህም ለመዳን የሰለፎችን መንገድ አጥብቆ መያዝ
ነው፡፡ እውቀትን ሰለፎች ባስተላለፉበት መልኩ እናስተላልፍ፡፡የነብዩን ታሪክ ማዎቅ የፈለገ ቡኻሪን ፣ ሙስሊምን
ሌሎችንም የሀዲስ ኪታቦችን ይቅራ፤ የነብዩሏህ ዩሱፍን ታሪክ ማወቅ የፈለገ ሱረቱል ዩሱፍን ይቅራ ፤
የመርየምን ታሪክ ማወቅ የፈለገ ሱረቱል መርየምን ይቅራ ፤ ከአሏህ የበለጠ ተናጋሪ የለምና፤ ይህ ሁሉ በአጭሩ
ነው፡፡በዚህ ዙሪያ የሚነሱ ማስመሰያዎችንና መልሶቻቸውን በስፋት ለማወቅ "አተምሲል" የሚለውን የሸይኽ በክር
አቡ ዘይድ ኪታብ እንዲሁም "አጅዊበቱል ሙፊዳህ" የሚለውን የሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን የጥያቄና መልስ
ኪታብ ጥያቄ ቁጥር 37ትን ይመልከቱ፡፡አሏህ ሁላችንንም ወደ መልካሙ መንገድ ይምራን!!!
ወሏሁ አዕለም!!!

You might also like