You are on page 1of 33

ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ

ማውጫ
ብዥታ አንድ ገፅ
ገፅ
ብዥታ ሁለት
ብዥታ ሶስት ገፅ
ገፅ
ብዥታ አራት
ገፅ
ብዥታ አምስት
ብዥታ ስድስት ገፅ
ገፅ
ብዥታ ስምንት
ብዥታ ዘጠኝ ገፅ
ብዥታ አስር ገፅ
ብዥታ አስራ አንድ ገፅ
ብዥታ አስራ ሁለት ገፅ
ገፅ
ብዥታ አስራ ሶስት
ብዥታ አስራ አራት ገፅ
ብዥታ አስራ አምስት ገፅ

ብዥታ አስራ ስድስት ገፅ


ብዥታ አስራ ሰባት ገፅ

ብዥታ አስራ ስምንት ገፅ


ብዥታ አንድ
ሙስሊሞች ተሰባስበው ሀይላቸውን በጠላት ላይ ይፋ ማድረግና ፍርሃት መልቀቅ
የተወደደ መሆኑን የነብዩ ‫ ﷺ‬ሱና ይጠቁማል ፤ ለዚህ ነው የተበደሉ ወይም ደካማ
የተደረጉ ሙስሊሞች ሀይላቸውን ለማሳየት በሁለቱ ዒዶች፣ በስቲስቃእ እና በጁሙዓ
ሶላቶች የሚሰባሰቡት፤ ይህ ሙስሊሞች ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንደሚችሉ
የሚያስረዳ መረጃ ነው የሚል ብዥታ ቢያቀርቡ፤

መልስ፡ - ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ ሙስሊሞች ወደአላህ ከጃይ መሆናቸውን ይፋ


ለማድረግ አላህና ረሡል ‫ ﷺ‬የደነገጓቸው የዒባዳ አይነቶች ናቸው፡፡

ሸይኻችን ኢብን ባዝ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

“የጁሙዓ፣ የዒድ፣ የኩሱፍ እና የስቲስቃእ ሶላቶች ነብዩ ‫ ﷺ‬ዳዕዋ


በማድረግ የኢስላምን አርማ ይፋ የሚያደርጉባቸው የሙስሊም ስብስቦች እንጅ
ከሰላማዊ ሰልፍ ጋር ምንም አይነት ቁርኝት እንደሌላቸው ለማንም የሚሰወር
አይደለም፡፡”
ብዥታ ሁለት
ሰነዱን ወደኢብን አባስ - ረዲዬሏሁ ዓንሁማ - በማስጠጋት የዑመር ብን
አልኸጧብን 4 ታሪክ አቡኑዓይም “ሂልያ” በሚባለው ኪታብ ሲዘግብ ከታሪኩ
መካከል የሚከተለውን አስፍሯል፡-
(ዑመር 4 እንዲህ ይላሉ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ብንሞትም ብንኖርም በሐቅ
ላይ አይደለንምን?” በማለት ረሡልን ‫ ﷺ‬ጠየቅኋቸው፤ “አዎ ! ፤ ነፍሴ በእጁ
በሆነችው ጌታ እምላለሁ ፤ በሂዎትም ብትኖሩ ብትሞቱም እናንተ በሐቅ ላይ ናችሁ፡፡”
በማለት ምላሽ ሰጡኝ፤ “ታዲያ ለምንድን ነው መደበቁ?! ፤ በእውነት በላከህ ጌታ
እምላለሁ በእርግጥ ወደአደባባይ ትወጣለህ፡፡” አልኳቸው
“ኩሱፍ”፡ የፀሐይ ግርዶሽ በሚከሰት ጊዜ በጀማዓ የሚሰገድ ሶላት ነው፡፡
“ኢስቲስቃእ”፡ ድርቅ በሚከሰት ጊዜ ዝናብን ከአላህ በመፈለግ በጀማዓ የሚሰገድ የሶላት አይነት ነው፡፡)
(መጅሙዕ አልፈታዋ )
ከዚያም ሶሃቦችን በሁለት ሶፍ አድርገን አስወጣናቸው ፤ ሀምዛ 4 በአንድኛው
ሶፍ ፤ እኔ ደግሞ በሌላኛው ሶፍ፤ መሬቱን በእግራችን እየረገጥን እና አቧራውን
እያስነሳን መስጅድ ደረስን ፡፡ “ቁረይሾች ወደእኔና ወደሀምዛ በቀጥታ ተመለከቱ፡፡”
ልክ የዚያ አይነት ጭንቀትና ትካዜ ደርሶባቸው አያውቅም ፤ ረሡል ‫“ ﷺ‬ፋሩቅ”
የሚለውን ስያሜ ያወጡልኝ ያን ጊዜ ነበር፤
(አላህ በዑመር 4 አማካኝነት ሐቅን ከባጢል ለየ፡፡)
ይህ የተደረገው የሙስሊሞችን ሐይል ለማሳየትና በደልን ከእነርሱ ላይ ለማንሳት
ሲባል በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፍ ይበቃል የሚል ብዥታ ቢቀርብ፡
መልስ፡- ይህ ሐዲስ ትክክለኛነቱ ያልተረጋገጠ ሙንከር (የተወገዘ) ሐዲስ ነው ፤

ሸይኽ አልባኒ - ረሂመሁሏህ - ስለዚህ ሐዲስ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


(ኢስሀቅ ብን ዓብዲላህ ከአባን ብን ሷሊህ ፤ አባን ከሙጃሂድ ፤ ሙጃሂድ ደግሞ
ከኢብን ዓባስ… ይዘው አስተላለፍውታል ብሎ አቡኑዓይም “ሂልያ” ከሚባለው ኪታቡ
ጥራዝ 1/ ገጽ 40 ላይ ዘግቦት ይገኛል፡፡ ሐዲሱ ሙንከር (የተወገዘ) ሲሆን ሰነዱም
በጣም ደካማ ነው ፤ ኢስሃቅ ብን ዓብዲላህ አቢፈርዋ በመባል ይጠራል፤ ኢማም
አልቡኻሪ ይህን ሰው አስመልክቶ “ሰዎች ትተውታል” በማለት ትችት ሰንዝረዋል፡፡
ኢማም አህመድም እንዲሁ ፡ “ከእርሱ ወሬን ይዞ ማውራት ከእኔ ዘንድ አይበቃም፡፡”
ብለዋል፡፡)
ሸይኻችን ኢብን ባዝ - ረሂመሁሏህ - ይህን ሐዲስ አስመልክቶ የሚከተለውን
ተናግረዋል፡-
(ዘገባው ትክክል እንኳ ቢሆን፡ ይህ ጉዳይ ሸሪዓው ገና ከመሟላቱ እና ከሒጅራው
በፊት እስልምና አንድ ብሎ ሲጀምር ሊሆን ይችላል ፤ በማዘዝ እና በመከልከል
እንዲሁ በሌሎች የዲን ጉዳዮች መሰረታችን ከሒጅራው በኋላ በጸናው ወይም
ተጠቃሎ በወረደው ሸሪዓ ላይ መሆኑ ለማንም የሚደበቅ አይደለም፡፡)
(ሂልየቱል አውሊያ ወጦበቃቱል አስፊያእ 1/63)
ሰላማዊ ሰልፍና ለድጋፍ ወይም ለመንቀፍ ሰዎች ተሰባስበው መውጣት ይችላሉ በሚል ዩሱፍ አልቀርዷዊ ከሰጠው ፈታዋ
የተወሰደ፡፡ ፈታዋውን በዩሱፍ አልቀርዷዊ ድህረ ገፅ በሚከተለው ሊንክ ማግኘት ይቻላል፡
(ሲልሲለቱ አልአሃዲሲ ዶዒፈቲ 14/72-73)
(መጅሙዕ አልፈታዋ፡ 8/246)
በተጨማሪ ዘገባው ትክክል ነው ብለን ብንወስድ እንኳ ፡ ይህ የዑመር እና የሐምዛ
መውጣት ከከሀዲዎች ፊት መስለማቸውን ለመጠቆም ያደረጉት ድርጊት እንጂ የታል
ሰላማዊ ሰልፍን የሚያስረዳው?
ብዥታ ሶስት
በራዕ ብን ዓዚብ 4 ባስተላለፈው ቡኻሪ እና ሌሎች በዘገቡት የኡሁድ ዘመቻ
ታሪክ አቡሱፍያን 4 የሚከተለውን ተናግሯል፡-
(“በሰዎች መካከል ሙሐመድ አልለ?” በማለት ሶስት ጊዜ ደጋግሞ ተናገረ፤ መልስ
ለመስጠት የፈለጉትን ሶሃቦች ነብዩ ‫ﷺ‬
ከለከሉ ፤ አቡሱፍያን በመቀጠል፡-
“በሰዎች መካከል ኢብን አቢ ቁሃፋ አልለ?” በማለት ሶስት ጊዜ ደጋግሞ ተናገረ ፤
ከዚያም በመቀጠል “በሰዎች መካከል ኢብን አልኸጧብ አልለ?” በማለት ሶስት
ጊዜ ደጋግሞ ተናገረ፤ ወደጓደኞቹ በመመለስ፡ “እነዚህ (አሁን የጠራኋቸው)
በሙሉ ተገድለዋል” በማለት የውሸት ወሬ ነዛ፤ ዑመር 4 ነፍሱን መቆጣጠር
አቃተው ፡ “አንተ የአላህ ጠላት ዋሸህ ፤ የቆጠርካቸው በሙሉ በህይወት አሉ፤ ለአንተ
የቀረልህ የሚያስከፋህ ነገር ብቻ ነው፡፡” በማለት ምላሽ ሰጠው፤ ከዚያም አቡሱፍያን ፡
“ቀን በቀን ይተካል ፤ ጦርነት አንዱ ሲያሸንፍ ሌላው ሲሸነፍ ነው ፤ እኔ በእርሷ
መመሪያ ባልሰጥም ከናንተ መካከል “ሙስላ” (ተቆራርጦ የሚገደል)
ያጋጥማችኋል ነገር ግን (ድርጊቷ) አታስከፋኝም” በማለት ከተናገረ በኋላ “ኡዕሉ
ሁበል ፤ ኡዕሉ ሁበል” (ሁበል ያሸንፋል፤ ሁበል ያሸንፋል) በማለት የተወሰኑ
ግጥሞችን መደርደር ጀመረ፡፡ ነብዩ ‫“ ﷺ‬መልስ አትሰጡትም?” አሉ፡፡ “የአላህ
መልክተኛ ሆይ! ምን እንበል?” አሏቸው፤ “አሏሁ አዕላ ወአጀል” (አላህ ከሁሉ በላይ
የላቀ ነው፡፡) በሉ፤ አሉ. ከዚያም “ለእኛ ዑዛ አለን ለእናንተ ዑዛ የላችሁም”
በማለት አቡሱፍያን ተናገረ ፤ ነብዩም ‫“ ﷺ‬መልስ አትሰጡትም?” አሉ፤ “የአላህ
መልክተኛ ሆይ! ምን እንበል?” በማለት ሶሃቦች ጠየቁ ፤ “አሏሁ መውላና ወላ መውላ
ለኩም” (አላህ ረዳታችን ጠባቂያችን ነው ፤ ለእናንተ ረዳትና ጠባቂ የላችሁም) በሉ
አሏቸው፡፡)
እንዲህ አይነቱ ተግባር በሰሃቦች መካከል የሚስተዋል ነበር ለምሳሌ አቡዘር አልጊፋሪይ 4 በሰለመ ማግስት የቁረይሽ ሰዎች
በተሰባሰቡበት ቦታ ሄዶ “እኔ ከአላህ ውጭ በሐቅ የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛውና
ባሪያው መሆኑን እመሰክራለሁ” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ እንደተናገረ ኢብኑ ዓባስ -ረዲየሏሁ ዓንሁማ- አውርተዋል)
ቡኻሪ፡
የአቡበክር ሲዲቅ 4 አባት ናቸው ስማቸው ዑስማን ብን ዓሚር 4 ይባላሉ
ቡኻሪ፡
ሶሃቦች ጠላቶቻቸውን ለማሸበር በህብረት እና በአንድ ድምጽ ነው ለአቡሱፍያን
የመለሱለት ፤ ይህም ከሰላማዊ ሰልፍ ላይ ይገኛል ፤ በመሆኑም ሰላማዊ ሰልፍ በዚህ
መረጃ መሰረት ይበቃል በማለት ብዥታ ቢያቀርቡ፡
መልስ፡- አቡሱፍያን ስለነብዩ ‫ ﷺ‬እና ስለሶሃቦች ሲጠይቅ ሶሃቦች መልስ እንዲሰጡ
ነብዩ ‫ ﷺ‬አልፈቀዱም፤ ረሡል ‫ ﷺ‬ለሶሃቦች መልስ እንዲሰጡ ያዘዙት ሙሽሪኮች
በጣዖቶቻቸው ሲንደላቀቁ የሰሙ ጊዜ ነው ፤ ይህም ተውሂድን ይፋ ለማድረግ እና
አላህን ለማላቅ ነው ፤ መልሱን የሰጠውም ዑመር 4 ብቻ ነው፤ ሰላማዊ ሰልፍ
ይበቃል ብሎ ማስረጃ ለማቅረብ የታለ ከሶሃቦች የተገኘው የህብረት ድምጹ እና
ጩኸቱ?
ኢብን በጧል - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
(ነብዩ ‫ ﷺ‬ለአቡ ሱፍያን መልስ ከመስጠት የከለከሉት እርሱ በማይጠቅም ነገር
ሲዘባርቅ ነፍሳቸውን ለመጠበቅ በማሰብ ነው፤ ነብያችን ‫ ﷺ‬ከከለከሉ በኋላ ግን
ዑመር መልስ መስጠቱ ደግሞ ነብዩ ‫ ﷺ‬ተገደሉ ተብሎ ሲወራ የሚያመጣውን
የሶሃቦች ድክመት እና ጥርጣሬ ለመከላከል በሚል ነው፤ በሐቂቃ ከተመለከትነው ይህ
በግልጽ ነቀፌታ ቢመስልም የነብዩን ‫ ﷺ‬ትእዛዝ እንደመንቀፍ ተደርጎ ሊቆጠር
አይችልም፤ ይልቁንም በዚህ ተግባሩ የሚመነዳበት ነው፤
“ለአንተ የቀረልህ የሚያስከፋህ ነገር ብቻ ነው፡፡” በማለት ዑመር 4 መናገሩ ፤
አቡሱፍያን የኢስላምን ሐይል ለመሰባበር ያደረገውን የሽብር ፕሮፖጋንዳ ለመበታተን
ነው፡፡ ነብዩን ‫ ﷺ‬እና ዋና ዋና የሚባሉትን ሶሃቦች ይዞ በመሄድ “ይሄው አልሞቱም
ህያው ናቸው” በማለት አሳወቃቸው፤ ለዚህ ነው “ለአንተ የሚያስከፋህ ነገር እንጅ
ምንም የቀረ ነገር የለም፡፡” በማለት የተናገራቸው፡፡
“ሁበል” የሚባለው በጃሂልያ ጊዜ ሲገዙት የነበረ ጣዖት ነው፡፡
ነብዩ ‫ ﷺ‬መልስ እንዲሰጡ አዘዙ ፤ ምክንያቱም የአላህ ቃል እና ዲኑ የበላይ
እንዲሆን ነው የተላኩ ፤ እንዲህ አይነት (የኩፍር) ንግግር ሲነገሩ የአላህ ቃል የበላይ
እስኪሆን ድረስ በዝምታ ሊያልፉት አልቻሉም፤ ከዚያም በመልሳቸው አላህ ከሁሉ
በላይ የላቀ እና ታላቅ መሆኑን አሳወቋቸው፡፡ ሙሽሪኮች የአላህን የበላይነት እና
ታላቅነት ስለሚያረጋግጡ ረሡል ‫ ﷺ‬በተናገሩት ንግግር አቡሱፍያን ምንም አይነት
ተቃውሞም መልስም አልሰጠም፡፡
ከዚያም አቡሱፍያን “ለእኛ ዑዛ አለን ለእናንተ ዑዛ የላችሁም” በማለት ሌላን
ጣዖት አወሳ፡፡ የአላህ መልክተኛ ‫ ﷺ‬መታገስ ስላልቻሉ ፤ “አሏሁ መውላና ወላ
መውላ ለኩም” በማለት ዑዛም ይሁን ሌሎቹ ጣዖታት ሊረዷቸውና ሊጠብቋቸው
እንደማይችሉ መልስ እንዲሰጡ ለሶሃቦች አዘዙ፡፡ ጠባቂነት ረዳትነት ከጣዖቶች
ሳይሆን ከአላህ ዘንድ ብቻ ሊገኝ እንደሚችል አሳወቋቸው፤ በዚህም በማስረጃ
አሸነፏቸው፤ እነርሱም መልስ ሊሰጡ ፍጹም አልቻሉም፤ ነብዩ ‫ ﷺ‬እራሳቸው
መልስ ሳይሰጡ ሰዎችን የተኩበት ምክንያት አቻቸው ካልሆኑ ሰዎች ጋር መከራከርን
ባለመፈለጋቸውና የእራሳቸውንም ክብር ለመጠበቅ በማሰብ ነው፡፡

ብዥታ አራት
ኢብን ዓባስ - ረዲዬሏሁ ዓንሁማ - የሚከተለውን ተናግሯል፡-
‫ إنما سعى رسول هللا ﷺ ورمل بالبيت ليري‬:‫"عن ابن عباس رضي الله عنهما قال‬
“‫المشركين قوته‬
“ረሡል ‫ ﷺ‬በከዕባ (ዙርያ) የገሰገሱት እና ሶምሶማ የሮጡት ሀይላቸውን
ለአጋሪዎች ለማሳየት ነው፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

በዚህ ሐዲስ ውስጥ ሙስሊሞች ከአምባገነኖች ፊት ሲሆኑ ሐይላቸውን ማሳየት


እንዳለባቸው ነው፤ በዚህ መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ የሚቻል መሆኑን ያስረዳል የሚል
ብዥታ ቢቀርብ፡
መልስ፡- በዚህ ሐዲስ ሰላማዊ ሰልፍ የሚፈቀድ መሆኑን የሚጠቁም አንድም ነገር
የለውም፡፡ ይልቁንም የአላህ ህግጋቶችን ምልክት ይፋ የምናደርግበት መሆኑን ይገልጻል
፤ እርሱም በነባሩ ቤት (ከዕባ) አላህን ለመገዛት ጦዋፍ ማድረግን እንዲሁም በዚህ
የተከበረ ቦታ እስከትንሳኤ ቀን ድረስ ሙስሊሞች ያላቸውን ሀይል ለሙሽሪኮች ይፋ
የሚያደርጉበት ነው፡፡
(ሸርሁ ሶሂህ አል ቡኻሪ ሊብኒ በጧል )
“ዋጂቡል ሙስሊም ወፈሪደቱል ወቅት” በሚባለው ሙሓዶራ ላይ ሐሰን ወሊድ አሽሸንቂጢ ከሰጠው ፈትዋ የተወሰደ
ኢብን በጧል፡ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

(በዚህ ሐዲስ ካዕባ የሚጦወፍበትን (የሚዞርበት) ሶፋና መርዋ ደግሞ


ሙስሊሞች የሚመላለሱበትን ምክንያት ኢብን ዓባስ 4 እንዳወሱ ይገልጻል ፡፡ ረሡል
‫ ﷺ‬ይህን የሰሩት ሙሽሪኮች “የየስሪብ (መዲና) ወባ ያዳከማቸው ሙስሊሞች”
በማለት በሙስሊሞች ላይ በመሳለቃቸው ሙስሊሞች እንዳልደከሙ ይልቁንም ሀይል
እንዳላቸው ለሙሽሪኮች ለማሳየት ነው፡፡ ረሡል ‫ ﷺ‬ካዕባ ላይ ሶምሶማ በማድረግ
የጦወፉት በመስጅዱ ፊት ለፊት ሲሆን ገበያ በሚገበያዩበት በኩል ደግሞ
የሚሰበሰቡበትና የሚቀመጡበት ቦታ ነው፡፡ ለዚህ ነው በዚህ ቦታ ከሙሽሪኮች ጋር
መተያየት ስለማይችሉ ቀስ ብለው በእግራቸው የሚጦውፉት፡፡ ይህን የታሪክ ባለቤቶች
ነው ያወሱት ፤ ፈጠን ፈጠን የምንለው የረሡልን ‫ ﷺ‬ሱና በመከተል ከአላህ በረካ
ለማግኘት ነው፤ ይህም ሶስት ዙር ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱ ተወግዷል ብንል እንኳ ይህ
የሆነበት የአላህን የዒባዳ ምልክቶች ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡)
አልባኒ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
(በካዕባ ዙሪያ ሶምሶማ የተደረገበት ምክንያት ሙስሊሞች ለአጋሪዎች ያላቸውን
ሐይል ለማሳየት ነበር ፤ ነገር ግን አሁን ይህ ምክንያት ተወግዷል ስለዚህ የሶምሶማው
ህጋዊነት ይወገዳል ማለት ነው? የሚል ጥያቄ አንድ ሰው ቢጠይቅ፡
መልሱ፡ አይወገድም የሚል ነው ፤ ምክንያቱም ነብዩ ‫ ﷺ‬ከዚያ በኋላ በመሰናበቻው
ሐጃቸው ሶምሶማ አድርገዋል ፤ በረጅሙ የጃቢር 4 ሐዲስ እና በሌሎችም ሐዲሶች
ይህን እውነታ ነው የሚጠቁመው ፤ ለምሳሌ የኢብን ዓባስ 4 ሐዲስን መውሰድ
እንችላለን ፤ ይህ ሐዲስ የአቡጡፈይል ሪዋያ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ ምክንያት
በትክክለኛው የኢብን ሂባን ሐዲስ በጥራዝ 6/ ገጽ 47 ላይ የሚከተለው ተዘግቧል፡

“ይህ ምክንያት የተወገደ ቢሆንም ፤ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በረሡል ‫ﷺ‬ ተከታዮች
ላይ ሶምሶማው የኢስላም ህግ ሆኖ ይቀጥላል፡፡”
(ሸርሁ ሶሂህ አል ቡኻሪ ሊብኒ በጧል፡ )
(ሲልሲለቱ አልአሓዲሲ ሶሂሃቲ፡ )
ብዥታ አምስት
አቡዳውድ በዘገቡት ሐዲስ ፡ “ኢያስ ብን ዓብዲላህ ብን አቢ ዙባብ የአላህ
መልክተኛ ‫“ ﷺ‬የአላህ ሴት ባሮችን አትምቱ” አሉ ፤ ዑመር ወደረሡል ‫ ﷺ‬ሄዱና ፡
“ሴቶች በባሎቻቸው ላይ ተዳፈሩ እኮ!” አሏቸው ፤ ከዚያም ባሎች ሚስቶቻቸውን
እንዲገርፉ ፈቃድ ሰጡ፤ ከዚያ በኋላ ባሎቻቸው ያደረሱባቸውን በደል አቤቱታ
ለማቅረብ በርካታ ሴቶች በረሡል ‫ ﷺ‬ቤተሰቦች ዙሪያ ተሰባሰቡ፤ ከዚያም ነብዩ ‫ﷺ‬
“በረሡል ቤት ዙሪያ በርካታ ሴቶች ስለባሎቻቸው አቤቱታ ለማቅረብ ተሰባሰቡ ፤ እነዚህ
ባሎች ምርጦች አይደሉም፡፡”) በማለት ተናገሩ፡፡ አቡዳውድ፡
ስለዚህ ይህ ሐዲስ ሰዎች መብታቸውን ለመጠየቅ ወይም የደረሰባቸው በደል
ከእነርሱ ላይ እንዲነሳ በይፋ ወይም በአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንደሚቻል
ማስረጃ ነው የሚል ብዥታ ቢቀርብ፡
መልስ፡ በዚህ ሐዲስ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍን የሚደግፍ ሐሳብ ምንም የለበትም፤
ይልቁንም ሰዎች አቤቱታ ካላቸው ሸሪዓዊ መንገድን ተጠቅመው የሙስሊሞችን መሪ
በቀጥታ ማናገር እንደሚገባ ነው የሚያስረዳው፡፡

ብዥታ ስድስት
አቡዳውድ በዘገቡት ሐዲስ፡ አቡሁረይራ 4 የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-
(ስለጎረቤቱ ስሞታ ለማቅረብ አንድ ግለሰብ ወደረሡል ‫ ﷺ‬ሄደ ፤ “ወደቤትህ
ሂድ ትዕግስት አድርግ” በማለት ረሡል ‫ ﷺ‬መከሩት ፤ ሁለት ጊዜ ወይም ሶስት ጊዜ
ወደረሡል ‫ ﷺ‬ተመላለሰ፡ አሁንም “ወደቤትህ ሂድና እቃህን በሙሉ አውጥተህ
መንገድ ላይ አድርገው” አሉት ፤ ከዚያም እቃውን በሙሉ አውጥቶ ህዝብ
ከሚያልፍበት አውራ ጎዳና ላይ አደረገው፤ ከዚያም ሰዎች ጥያቄ ማቅረብ ጀመሩ፤
እርሱም ያለውን እውነታ ነገራቸው፤ ከዚያ በኋላ አላፊ አግዳሚው ሁሉ ጎረቤቱን
መራገም ጀመረ ፤ አላህ የሚሰራውን ሰራ ፤ ከዚያም ጎረቤቱ ወደርሱ መጣና ፤
“እባክህ ወደቤትህ ተመለስ ፤ ከዚህ በኋላ ከእኔ ላይ የምትጠላው ነገር አታያም፡፡
አለው፡፡ አቡዳውድ፡
“ነዞራቱ ሸርዒየቲ ፊ ወሳኢሊ ተዕቢሪል አስሊየቲ” በሚል ፕሮግራም ላይ ዶ/ር ሱዑድ ፈኒሳን የሰጠውን ፈትዋ ይመልከቱ
መልስ፡ ይህ ሐዲስ ሰላማዊ ሰልፍን በቅርብም ይሁን በሩቅ የሚያስረዳ መረጃ ሊሆን
ፍጹም አይችልም ፤ “ሙዟሀራ” ወይም ሰላማዊ ሰልፍ የሚለው ቃል የት ላይ ነው
ያለው?
ሸይኽ ረቢዕ አልመድኸሊ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
(በሐዲሱ የተመለከትነው የሰዎች መሰባሰብ ከዚህ በፊት እንዳየነው ልክ
በመሪው ላይ ተቀናጅተው አድማ እንደሚያደርጉ ሰዎች አይነት ስብስብ አይደለም ፤
ጉዳዩ ግለሰቡ በሚያስደንቅ ሁኔታ መንገድ ላይ ተቀመጠ፤ ሰዎች ወደስራቸው
ወጠዋል፤ አንድ ሰው ይመጣና ይህን አስገራሚ ትዕይንት ይመለከታል ፤ ሁለተኛው
ሶስተኛው እያለ ቁጥራቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ከዚያ በኋላ በዚህ ጎረቤት ድርጊት ሰዎች
ተቃውሟቸውን ያሰማሉ፤ ስለዚህ አሁን ባወሳንልህ መልኩ የተደረገው መሰባሰብ
ምንም ከሰላማዊ ሰልፍ ጋር ግንኙነት የሌለው መሆኑን ይጠቁማል፤ ምክንያቱም
የሰላማዊ ሰልፍ አይነት ግብ እና አላማ የለውም፤ ስለዚህ አንድን ቃል ከተቀመጠበት
ቦታ ከማጣመም በአላህ እንጠበቃለን፡፡)
ሸይኻችን አብዱልሙህሲን አልዓባድ - ሀፊዞሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡
(ይህ ሐዲስ አዲስ ለተፈጠረው ሰላማዊ ሰልፍ መፈቀድ ምንም አይነት መረጃ ሊሆን
አይችልም፡፡ ረሡል ‫ ﷺ‬እቃውን እንዲያወጣ የፈቀዱለት ግለሰብ ሶሃባ ነው፤ ሶሃቦች
ደግሞ እውነተኞች ናቸው፤ ከእነርሱ በኋላ ለመጣ ሰው ይህ አቅጣጫ የሚሰጥ
አይደለም ፤ ምክንያቱም ይህን አይነት መሰል የሞገተ ሁሉ እውነተኛ ይሆናል ማለት
አይደለም ፤ እንዴውም ነገሮችን የሚያበላሽ ጎረቤቱን የሚያሰቃይ ሊሆን ይችላል፡፡)

ብዥታ ሰባት
ዶክተር ሃቲም አልዓውንይ የሚከተለውን ተናግሯል የሚል ብዥታ ቢቀርብ፡

(ጥቅል የሆኑ መረጃዎች እና የሸሪዓ ግቦች ሰላማዊ ሰልፍን ሸሪዓዊ ለማድረግ


የሚጠቁሙ ናቸው
(“ሁክሙል ሙዟሀራቲ ፊልኢስላም” በሚል ርዕስ ከዶ/ር ሱዑድ ፈኒሳን ጋር ሸይኽ ረቢዕ ካደረጉት ውይይት ከሁለተኛው ክፍል ላይ የተወሰደ)
(አልሙዟሓራቱ ፊሚሃኒ አሽሸሪዓቲል ኢስላሚየቲ ሊዓብዲረህማን ብን ሰዕድ ገፅ/197)
-የተከበሩ ቀደምት ሶሃቦች አሁን ባለው አይነት የሰለማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ
ፈጽመውት አልፈዋል - ለምሳሌ በጀመል የሶሃቦች ጦርነት ቀን የዑስማንን ደም ፍለጋ
የወጡ ሶሃቦችን መመልከት እንችላለን ፤ በዋነኝነት ዙበይር ብን አልዓዋም ፤ ጦልሃ
ብን ዑበይዱሏህ እና ዓኢሻ ፤ እነርሱን ተከትለው በበርካታ ሽዎች የሚቆጠሩ ሶሃቦች
ከሂጃዝ ተነስተው ወደዒራቅ ሲንቀሳቀሱ ፤ የመጀመሪያ አላማቸው ለጦርነት
አልነበረም፤ እነዚህ በሽዎች የሚቆጠሩ ሶሃቦች ለጦርነት ካልወጡ ፤ ለምን አላማ
ወጡ? መልሱ ቀላል ነው ፤ የዑስማንን ገዳይ አውጡና አንጻራዊ ርምጃ ውሰዱልን
የሚል አቤቱታ ለማቅረብ ነው ፤ አቤቱታው በሙእሚኖች ቅን መሪ በዓልይ ብን አቢ
ጧሊብ ላይ ነው፤ ይህ የተከበሩት የሶሃባ ትውልድ ባሉበት የተከሰተ ሰለፍይ የሆነ
ሰላማዊ ሰልፍ ትርጉም ነው ፤ በሽዎች የሚቆጠሩ ሶሃቦች ለአቤቱታ ሲወጡ ዓልይ 4
ምንም አይነት ተቃውሞ አላሳየም፤ በወቅቱ የነበሩ ዑለማዎችም ሀራም አላደረጉትም፤
በውስጡ አንዳንድ ችግር ቢኖርበትም በመሪዎች ላይ ማፈንገጥ ብለው አልገለጹትም፤
ምክንያቱም ችግር ወይም ብልሹነት ከመሰረታዊ ተግባር በኋላ ጣልቃ ገብ የሆነ
ክስተት ነው ፤ እንዲህ አይነት ክስተት ግንዛቤው ከሌላቸው የሰለፎች ጎዳና ተከታዮች
የግድ የሚከሰት ክስተት ነው ፤ ይህ ከሆነ ሰላማዊ ሰልፍን እንደመንሐጅ መያዝ
ይገባናል ማለት ነው፡፡)
መልስ፡- ይህ ከላይ የተገለጸው ሐሳብ ሰላማዊ ሰልፍ ይበቃል ለማለት አንዳች
መረጃነት የለውም፡፡ (እንዴውም “ሙዟሀራ” (ሰላማዊ ሰልፍ) የሚል ቃልም
አልተሰነዘረም) የምእመናን እናት የወጣችው ሶሃቦችን ለማስማማት እና ለማስታረቅ
ነው፡፡
ኢብን ሐዝም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

(የምዕመናን እናት ፤ ዙበይር እና ጦልሃ እንዲሁም ከእነርሱ ጋር የወጡ ሰዎች


የዓልይን ኢማምነት ምንም ውድቅ አላደረጉም፤ ከኢማምነት የሚያወርድ ትችትም
አላቀረቡም፤ አዲስ ቃል ኪዳን ለመግባት ሌላ ኢማምም አልሾሙም፤ ይህን ጉዳይ
ማንም ይሁን ማን ሊሞግተው አይችልም፤ ሁሉም ከዚህ በላይ የጠቀስነው
እንዳልተከሰተ ቁርጠኛ ናቸው፡፡
(“አልኢስላሙ አልየውም” በሚባል ቻናል “ሁክሙል ሙዛሀረቲ አስሰሊመቲ” በሚል ርዕስ ዶ/ር ሃቲም ብን ዓሪፍ አልዓውኒ አሽሸሪፍ
የተናገረው ነው፡፡ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ያገኙታል: )
ሶሃቦች ዓልይን ለመቃወም ወይም ለመውጋት ወይም ቃልኪዳኑን ለማፍረስ
ወደበስራ አለመሄዳቸው በትክክለኛ ዘገባ ተዘግቧል ፤ ይልቁንም ሶሃቦች ወደበስራ
የተጓዙት ዓልይን ለመጋደል ሳይሆን ዑስማን በበደል በመገደሉ ምክንያት በኢስላም
ላይ ተከስቶ የነበረውን ክፍተት ለመዝጋት ፤ ገዳዮችን አጋልጦ ለማውጣት እና
የሙስሊሞችን ቃል አንድ ለማድረግ ነው፤ ለዚህ ማስረጃ የሚሆነን ሌሊት ሶሃቦች
በጉዳዩ ላይ ለመወያየት በተሰባሰቡ ጊዜ የዑስማን ገዳዮች በእኛ ላይ የሚደረግ ሴራ
ነው በሚል በጦልሃ እና በዙበይር ላይ ጦርነት መክፈታቸው ነው ፤ ሶሃቦችም
ከነፍሳቸው ተከላከሉ ፤ ባልታወቀ ሁኔታ የዑስማን ገዳዮች ወደዓልይ ጦር ተቀላቀሉ ፤
ከዚህ በኋላ ጠቡን የቆሰቆሰው አካል ማን እንደሆነ ሊታወቅ አልቻለም ፤ ነገሩ
ተደባለቀ ፤ ሁሉም ከነፍሱ ላይ መከላከል ጀመረ፤ የዑስማን ገዳዮች ጠብ ከማጫር
ጦርነት ከመቀስቀስ ወደኋላ ሊሉ አልቻሉም ፤ ሁለቱም የሶሃባ ቡድን የተነሱበት
አላማ ችግር ላይ በመውደቁ ነፍሳቸውን ለመከላከል ቆርጠው ተነሱ፡፡)
አቡበክር ብን አልዓረቢ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
(ሶሃቦች ወደበስራ የወጡበት ምክንያት የሙስሊም ቡድኖችን ከተበታተኑበት
ለመሰብሰብ ፤ እርስ በርሳቸው እንዳይጋደሉ ለማድረግና በአንድ ህግ እንዲመሩ
ለመመለስ ሊሆን ይመቻል ፤ ይህም ትክክለኛ የሆነው ሐሳብ ሲሆን ከዚህ ውጭ ሌላ
ትክክለኛ ሐሳብ የለም፤ በዚህ ላይ ነው ትክክለኛ ወሬዎችም የመጡት፡፡)
ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዓብዱልወሃብ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን
ተናግረዋል፡-
(ከእርሷ ጋር ዙበይር እና ጦልሃ አብረው እያሉ ለዓኢሻ ወሬው ደረሳት ፤
በሙስሊሞች መካከል የተፈጠረውን መከፋፈል አስማምተው አንድነት ለመፍጠር
ወደበስራ ተንቀሳቀሱ፡፡)

(አልፈስሉ ፊል ሚለሊ ወል አህዋኢ ወኒሃሊ ሊብኒ ሃዝም 4/237-239)

(አልዓዋሲሙ ሚነልቀዋሲሚ ፊትህቂቂ መዋቂፉ ሶሃበቲ በዕደ ወፋቲ ነብይ ‫ﷺ‬ ሊአቢ በክር ብን አልዓረቢ ገፅ/155)

(ሙኽተሶሩ ሲረተ ረሡል ‫ﷺ‬ ሊልኢማም ዓብዱልወሓብ ገፅ/312)


አቡበክር ብን አልዓረቢ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

(የሚከተለውን የቁርኣን ማስረጃ በማድረግ ሰዎች ወደምእመናን እናት


እንዲመለሱ በዚህም የነብዩን ‫ ﷺ‬ክብር እንዲጠብቁ ለማድረግ ጦልሃ ፣ ዙበይር
እና የምእመናን እናት ወጡ፡፡

ْ ‫ص َدقَ ٍة أَ ْو َم ْع ُروفٍ أَ ْو ِإ‬


ِ َّ‫صالَحٍ َبيْنَ الن‬
‫اس‬ َ ‫ير ِمن نَّ ْج َوا ُه ْم ِإالَّ َم ْن أَ َم َر ِب‬
ٍ ِ‫﴿الَّ َخي َْر فِي َكث‬
َ ‫ف نُؤْ تِي ِِ أَ ْج ارا‬
‫َ ِِي اما‬ َ ‫س ْو‬ َ َ‫ت ّللاِ ف‬ ِ ‫ضا‬ َ ‫َو َمن َي ْف َع ْل َذ ِل َك ا ْبتَغَاء َم ْر‬

“ከውይይታቸው በምጽዋት ወይም በበጎ ስራ ወይም በሰዎች መካከል


ለማስታረቅ ከሚያደርጉት ውይይት በስተቀር በብዙው ውስጥ ደግ ነገር
የለበትም፡፡ ይኸንንም (የተባለውን) የአላህን ውዴታ ለመፈለግ የሚሰራ ሰው
ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን፡፡” ኒሳእ፡
ነብዩ ‫ﷺ‬ ከዚህ በፊት ለእርቅ ወጠዋል፤ ሰዎችንም ለእርቅ ልከዋል፡፡

(አህለሱና ወልጀማዓ የምእመናን እናት ወደበስራ የወጣችው ለማስማምት እንጅ


ለሌላ አላማ እንዳልሆነ በአንድ ድምጽ ይስማማሉ ፤ በዚህ ላይ ነው ወሬዎችም
የመጡት፡፡)

ዓኢሻ 6 ወደበስራ በመውጣቷ ተጸጽታለች፡


አልባኒ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል፡ - (ከእርሷ ክብር ጋር የሚሄደውም ይህ
ነው፤.. ኢማም አዝዘይለዒዩ (ነስቡ ራያ) ጥራዝ 4/ ከገጽ 69-70 “ዓኢሻ 6
ጸጸቷን ይፋ አድርጋለች” ብለዋል፤ “ኢስቲዓብ” በሚባለው ኪታብ ኢብን
አብዱልበር ከኢብን አቢ ዓቲቅ ፤ ኢብን አቢ ዓቲቅ ደግሞ ከዓብዱሏህ ብን
ሙሀመድ ብን ዓብዱረህማን ብን አቡበክር ሲዲቅ ይዞ እንዳወራው እና
እንደተዘገበው (ዓኢሻ ለኢብን ዑመር ፡ “አንተ አባዓብዲረህማን ሆይ! ከጉዞየ
ከመከልከል ምን ከለከለህ?” አለችው፤
(አልዓዋሲሙ ሚነልቀዋሲሚ ፊትህቂቂ መዋቂፉ ሶሃበቲ በዕደ ወፋቲ ነብይ ‫ﷺ‬ ሊአቢ በክር ብን አልዓረቢ ገፅ/156)
(ዓቂደቱ አህለሱነቲ ወልጀማዓቲ ፊሶሃበቲ ሊሸይኽ ናሲር ብን ዓልይ ዓኢድ 2/707)
እርሱም፡ “አንድ ግለሰብ ሲያሸንፍሽ ተመልክቸ ነው” አላት፡፡ - እርሱም ብን ዙበይር
ነው - እርሷም፡ “በአላህ እምላለሁ ብትከለክለኝ ኖሮ አልወጣም ነበር፡፡” የሚል
ምላሽ ሰጠች፡፡)
በሌላ ዘገባ ደግሞ፡ ዘህብይ “ሲየር አዕላም አንኑበላእ” ከገጽ 78-79 ላይ
የሚከተለውን ተናግሯል፡- ኢስማዒል ብን ዓልያ ከአቢ ሱፍያን ብን አላእ አልማዚንይ
አቡ ሱፍያን ደግሞ ከኢብን አቡ አቲቅ ይዞ የሚከተለውን አስተላልፏል፡- “ኢብን
ዑመር ሲያልፍ አሳዩኝ” አለች ዓኢሻ ፡ ሰዎች ኢብን ዑመር ሲያልፍ ተመለከቱና
ለዓኢሻ ጠቆሟት ፤ “አንተ አባ ዓብዱረህማን ፤ እኔን ከመከልከል የከለከለህ ምንድን
ነው?” አለችው፡፡ እርሱም “አንድ ሰው አሸንፎሽ ተመልክቸ ነው” አላት፡፡ እርሱም
ብን ዙበርይር ነበር፡፡

ኢስማኢል ብን አቢ ኻሊድ ከቀይስ ይዞ የሚከተለውን አስተላልፏል፡ ዓኢሻ በቤቷ


ውስጥ ለመቀበር አስባ ነበር ፤ ነገር ግን “እኔ ከረሡል ‫ ﷺ‬በኋላ አዳዲስ ነገሮችን
ስለፈጠርኩ ከረሡል ‫ ﷺ‬ሚስቶች ጋር ቅበሩኝ” በማለት ተናዘዘች፡፡ በቂዕ በሚባለው
ቀብርም ተቀበረች፡፡)

አዲስ ነገር ፈጥሬያለሁ ያለችው ፡- በጀመል ቀን ወደበስራ መሄዷን ነው ፤


ከዚያ ተግቧሯ ነው ተውበት ያደረገችው፡፡ ጦልሃ ብን ዓብዲላህ ዙበይር ብን አልዓዋም
እና ታላላቅ ጀማዓዎች ኢጅቲሃድ እንዳደረጉ ሁሉ ዓኢሻም መልካም ነገር አስባ እንጅ
ይህን ተግባር አትሰራውም ነበር፡፡)
ሰላማዊ ሰልፍ የእርሷም የሶሃቦችም መመሪያ ከመሆን በአላህ እንጠበቃለን፤ ወደ
በስራ መውጣቷ ሶሃቦችን ለማስማማት መሆኑ - አልሀምዱ ሊላህ - ዑለሞች በአንድ
ድምጽ ተስማምተዋል፡፡
ብዥታ ስምንት
አቡኑዓይም ከሸይባ ይዞ የሚከተለውን ተናግሯል የሚል ብዥታ ቢቀርብ፡
(ሲልሲለቱ አስሶሂሃቱ 1/473)
(የ “ጀመል” ቀን የተባለው ዓኢሻ 6 ለሐጅ ወደመካ በሄደችበት አጋጣሚ ስለነበር እርሷ በግመል ላይ ሆና ወደ በስራ
ስለተጓዘች ክስተቱ “አያሙል ጀመል” (የጀመል ቀን) የሚል ስያሜ ተሰጠው፡፡)
‫ يسدون‬، ‫ (نعم الشيء الغوغاء‬:‫روى أبو نعيم عن الشعبي رحمه هللا أنه قال‬
)‫ ويشغبون على والة السوء‬، ‫ ويطفئون الحريق‬، ‫السيل‬

“ከሁሉም መልካሞቹ ግብስብሶቹ ናቸው ፤ ጎርፍ ይዘጋሉ፤ ቃጠሎን ያጠፋሉ፤ በመጥፎ


መሪዎች ላይ ፈተናን ይቀሰቅሳሉ፡፡”
መልስ፡ - ይህ ሐዲስ ኢስሃቅ ብን ኢብራሂም አጦበሪይ ስላለበት ሶሂህ አይደለም ፤
ኢብን ዓድይ - ረሂመሁሏህ - ይህን ሀዲስ ሙንከር (የተወገዘ) ብለውታል፡፡

ብዥታ ዘጠኝ
ሰላማዊ ሰልፍ አሁን ላለንበት ዘመን ወደመልካም ለማዘዝ ከመጥፎ ለመከልከል እና
ዳዕዋ ለማድረግ ምቹ የሆነ መንገድ ነው የሚል ብዥታ ቢቀርብ፡
መልስ፡- ሸይኽ ሷሊህ ብን ገስወን - ረሂመሁሏህ - ፡ (በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ
መከልከል እና ዳዕዋ ማድረግ ከአላህ ዲን መሰረቶች ናቸው፡፡
ነገር ግን አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡

َ ‫سنَ ِة َو َجاد ِْل ُهم ِبالَّ ِتي ِه‬


َ ‫ي أَ ْح‬
‫س ُن ِإ َّن َرب ََّك‬ َ ‫ِ ِة ْال َح‬ َ َِ ‫س ِبي ِل َر ِب َك ِب ْال ِح ْك َم ِة َو ْال َم ْو‬ ُ ‫﴿ ا ْد‬
َ ‫ع ِإ ِلى‬
َ‫س ِبي ِل ِِ َو ُه َو أَ َْلَ ُم ِب ْال ُم ْهتَدِين‬
َ ‫َن‬ َ ‫ض َّل‬ َ ‫ُه َو أَ َْلَ ُم ِب َمن‬
“ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡
በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ ጌታህ እርሱ
ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የሆኑትን ሰዎች ዐዋቂ
ነው፡፡” ነሕል ፡
(ሂልየቱል አውሊያ ሊአቢ ኑዓይም አልአስፋሃኒ 4/324 ላይ “አልኩቱቡል ኢልሚየቲ” ባሳተመው የመጀመሪያው
እትም መሰረት)
(“አልካሚሉ ፊ ዱዓፋኢ አርሪጃል ሊብኒ ዓዲይ 1/343 ቁ፡ 173)
(ዶ/ር ዓብዱረዛቅ አሽሻይጂይ
ላይ በሚቀጥለው ከሰጠው
ማስፈንጠሪያ ይገኛል ፈትዋ
እና ሸይኽ ዓልይ አልኹደይሪ የሰጠው ፈትዋ ላይ
በሚከተለው ማስፈንጠሪያ በተጨማሪም
ዶ/ር ሱዑድ አልፈኒሳን “ነዞራቱ ሸርዒየቲ ፊወሳኢሊ አትተዕቢሪ አሽሸርዒየቲ” በሚል ከሰጠው ፈትዋ ላይ ይገኛል)
ሙሳን እና ሐሩንን አላህ ወደ ፊርዓውን ሲልካቸው የሚከተለውን መልእክት አስይዞ
ነው የላካቸው ፡-
‫وال لَُِ قَ ْو اال لَّ ِيناا لَّ َعلَُِّ يَت َ َذ َّك ُر أ َ ْو يَ ْخشَى‬
َ ُ‫﴿ فَق‬

“እርሱም ይገሰጽ ወይም ይፈራ ዘንድ ፤ ለእርሱ ልዝብን ቃል ተናገሩት፡፡” ጧሃ ፡

ነብዩ ‫ ﷺ‬ጥበብን ይዘው መጠዋል ፤ ዳዒዎች በሂክማ እና በትዕግስት ዳዕዋ


እንዲያደርጉ አዘዋል፤
አላህ አሸናፊ በሆነው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡-

َ ‫ت َوتَ َوا‬
‫ص ْوا‬ ِ ‫صا ِل َحا‬ َ ‫سانَ لَ ِفي ُخ ْس ٍر۞ ِإ َّال الَّذِينَ آ َمنُوا َو‬
َّ ‫َ ِملُوا ال‬ ِ ْ ‫ص ِر۞ ِإ َّن‬
َ ‫اْلن‬ ْ ‫﴿ َو ْال َع‬
‫صب ِْر‬َّ ‫ص ْوا ِبال‬َ ‫ق َوتَ َوا‬ِ ‫ِب ْال َح‬
“በጊዜያቱ እምላለሁ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው፤ እነዚያ
ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት ፣ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም
አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡” ዓስር ፡

ወደአላህ ጥሪ የሚያደርግ ሰው ከአላህ የሚያገኘውን አጅር ወይም ምንዳ ታሳቢ


አድርጎ በመልካም ማዘዝ እና በዳዕዋው መንገድ በሚያጋጥመው ችግር ሁሉ
በትዕግስት ሊዋብና ሊሸለም ይገባል፤ ሰው በሰው ላይ ጭካኔን እና ሐይልን ይጠቀማል ፤
አንዱ በአንዱ ላይ በጥርጣሬ የሚመለከትበትን መንገድ ይከተላል ፤ ይህ ሁሉ
ሰይጣናዊ መንገድ ነው፤

ይህ የኸዋሪጅ አንጃ የዳዕዋ መሰረት ነው ፤ ኸዋሪጆች መጥፎን ነገር


የሚቃወሙት በመሳሪያ ነው፤ የእነርሱን እምነት እና አመለካከት ሁሉ የተቃረነን
አካል ሁሉ በመግደልና ደም በማፍሰስ ይቃወማሉ፤ በነብዩ ‫ ﷺ‬ሶሃቦች እና
በኸዋሪጆች ዳዕዋ መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ፡፡ የሶሃቦች ዳዕዋ ጥበብ እና መልካም
ተግሳጽ ፤ ሐቅን በማብራራት ፤ በትዕግስት ፤ በመልካም ባህሪ በመዋብ ፤ ከአላህ
ዘንድ ምንዳን (የሚገኝን መልካም ነገር) ታሳቢ በማድረግ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
የኸዋሪጅ ዳዕዋ በተቃራኒው ሰዎችን በመግደል ደም በማፍሰስ ሰዎችን በማክፈር ፤
ቃልን በመከፋፈል፤ የሙስሊሞችን ሶፍ (አንድነት) በመበጣጠስ ላይ የተመሰረተ
ነው፤ ይህ አስቀያሚ የሆነ እና አዲስ የሆነ ፈጠራ ነው፤ ወደዚህ ነገር ጥሪ
የሚያደርጉ ሰዎች ከእነርሱ መራቅ ይኖርባቸዋል፤ የሙስሊሞችን አንድነት
ስለሚከፋፍሉ እነርሱን በመጥፎ መጠርጠር ይገባል፡፡
አንድነት እዝነት ነው፤ መለያየት ደግሞ ቅጣት ነው፤ የአንድ አገር ሰው
በመልካም ነገር ቢሰባሰብ ፤ ድምጻቸው አንድ ቢሆን ለእነርሱ ደረጃ እና ክብር ነው ፤
በአሁኑ ሰአት ግን የአንድ አገር ተወላጆች የተለያየ ጭፍራ እና ቡድን ሆነዋል ፤
ከነፍሳቸው ውስጥ ከፊሉ ለከፊሉ ጠላት ሆኗል፤ ይህ ከዚህ በፊት እንዳየነው አይነት
ቢድዓ (መጤና) እና ቆሻሻ የሆነ አካሄድ ነው፤ እነዚያ የሙእሚኖችን አሚር
(አዛዥ) ዓልይን እና ሶሃቦችን እንዲሁም የቃልኪዳን ባለቤቶችን የገደሉ ምን
ፈልገው ነው? በነርሱ አመለካከት ማስማማትን ፈልገው ፤ ነገር ግን የፈሳድ የቢድዓ
እና የጭቅጭቅ ቁንጮዎች በመሆናቸው የሙስሊሞችን (እውነተኛ) ቃል ለያዩ፤
የሙስሊሙን (የጥንካሬ) ጎን አዳከሙ፤ ይህን የመከፋፈል መንገድ እንደመልካም
በማውሳት የእኔ ብለው አጥብቀው ያዙ ፤ በመሆኑም ከነዚህ አንጃዎች (ቡድኖች)
እራሳችንን ልናርቅ ይገባል፡፡

አንድ ግለሰብ ለማህበረሰቡ እና አብረውት ለሚቀመጡት ሰዎች ጎጅ ሊሆን


አይገባም፡፡ መሆን የሚገባው ቃሉ እውነተኛ በለዘብታ ወደመልካም የሚጣራ ፤
በተሟላ ሁኔታ መልካምን የሚፈልግ ወንድሞቹን በመልካም ይጠርጥር ፣ ከሰዎች
ዘንድ ሙሉነት ይገኛል ብሎ ተስፋ አያድርግ ፣ ጥብቅ ብሎ ማለት ነብዩ ‫ ﷺ‬ብቻ እና
ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱ ቢወገዱ ከእነርሱ የበለጠ ያማረ አይመጣም ፤ አሁን ያሉት
ዳኞች ሀላፊነት የተሰጣቸው ባለስልጣኖች የእውቀት ፈላጊዎች ወይም ህዝቡ
በአጠቃላይ ቢወገድ ከእነርሱ የከፋ እንጅ ሌላ አይመጣም ፤ አንድ ዘመን አልፎ
ሌላ ዘመን አይተካም ፤ የበለጠ የከፋ ቢሆን እንጅ፡፡
(ዙበይር ብን ዓድይ አነስ ብን ማሊክ ዘንድ ሄደን ከሓጃጅ የሚደርስብንን ግፍ አቤቱታ አቀረብን፤ አነስም፡ “ታገሱ.
ጌታችሁን አስክትገናኙ (እስክትሞቱ) ድረስ አንድም ዘመን በእናንተ ላይ አይመጣም ከዛ በኋላ የሚመጣው ከእርሱ የከፋ
ቢሆን እንጅ ይህንንም ከነብያችሁ ‫ ﷺ‬ነው የሰማሁት” አለን) ቡኻሪ፡
ሰዎች ወደተሟላ ደረጃ ለመሸጋገር ወይም ከስህተት ነጻ ለመሆን የሚፈልጉ አሉ፤ ይህ
አመለካከት ሰዎችን የሚያሰቃዩ ደም የሚያፈሱ የሆኑት ኸዋሪጆች መንገድ ነው፤ ይህ
ጎዳና አህለሱና ወልጀመዓን በቢድዓ የሚቃወሙ የሆኑ የራፊዷ፣ የኸዋሪጅ ፤
የሙዕተዚላ እና መሰል የተንኮል እና የቢድዓ ባለቤቶች መንገድ ነው፡፡ )
ብዥታ አስር
ሰላማዊ ሰልፍ የጅሐድ መዳረሻ እና በዳይ አካል ከበደሉ እንዲቆጠብ ማድረጊያ ስልት
ነው የሚል ብዥታ ቢቀርብ፡
መልስ፡ - ይህ ትክክል አይደለም፡፡ የነብዩ ‫ ﷺ‬መመሪያ ከሁሉም መመሪያ የበለጠ
ነው፡፡ በረሡል ‫ ﷺ‬ዘመን ያልነበረ አዲስ የጅሐድ ስልት የሚፈጥርን አካል ሰለፎች
ይቃወሙ ነበር፡፡
ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
(ጦርነትን አስመልክቶ ሱናው ድምጽን መቀነስ ነው ፤ ይህ እየዘለሉ መሬትን
በእግር መደብደብ፤ ልክ እንደአይሁዶች ጡሩንባ መንፋት፤ ልክ እንደነሷራዎች
ደዎል መደወል ፤ በኹለፋኡ ራሽዲን (በቅን መሪዎች) ዘመን እና ከእነርሱ በኋላ
በነበሩ የሙስሊም መሪዎች አልነበረም ፤ ይህን ቢድዓ በምስራቅ የነበሩ የፋሪስ ንጉሶች
የፈጠሩት ይመስለኛል ፤ ንግስናቸው በዓለም በሰፊው ተሰራጭቶ ስለነበር ያን ጊዜ
በመሪዎች ላይ ሲያምጹና ሲያስገድሉ በርካታ አዳዲስ ነገሮችን ፈጥረዋል፤ በዚሁ
ቢድዓ ላይ ህጻኑም አደገ ትልቁም አረጀ፤ ከዚህ ውጭ ሌላ አያውቁም ፤ እንዴውም
በእነርሱ ተቃራኒ አንድ ሰው ከተናገረ ወዲያውኑ ይቃወማሉ ፤ እንዴውም አንዳንድ
ሰዎች ይህን ቢድዓ ዑስማን ኢብን አፋን 4 እንደፈጠረው አድርገው የሚሞግቱ
አሉ፤ ነገሩ ግን እንደዚህ አይደለም፤ እንዴውም ከዑስማን በኋላ የመጡ መሪዎች
ሁሉ ያልፈጸሙት ተግባር ነው፡፡
(መውቂዑ ሸበከቱ ሲሃቢ አስሰለፊየቲ )
(ሸይኹል ኢስላም ወንጀለኞችን ከወንጀላቸው ለማስቶበት አስቦ ድቢ (ከበሮ) እና የተፈቀዱ የሆኑ ግጥሞችን ያለቅላፄ
(ያለዜማ) ተሰባስበው እንዲሰሙ አድርጎ በዚህ አካሄድ አመፀኞችን ስላስቶበተ ሸይኽ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ
የዳዕዋ አደራረግ ሂደት ምን ሊመስል እንደሚገባ በሚገባ ስለሚያመላክት የፈለገ ቢመለከተው መልካም ነው፡፡ መጅሙዕ
አልፈታዋ 11/620-635 ይገኛል)
(ሸይኽ ዓልይ አልኹደይሪ የሰጠው ፈትዋ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ላይ ይገኛል
)
ነገር ግን ፡ በአሁኑ ሰዓት ነብዩ ‫ﷺ‬የተናገሩት ትንቢት ይፋ ሆኖ እየተመለከትን ነው ፡
ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“ከእናንተ በፊት የነበሩ ማህበረሰቦች የያዙትን በእርግጥ ትይዙታላችሁ፤ ስንዝር
በስንዝር ፤ ክንድ በክንድ፤ “ፋርስ እና ሮም ነው እንዴ?” በማለት ሶሃቦች ጠየቁ ፤
“እነርሱ ካልሆኑ ማን ሊሆን ይችላል?” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ ቡኻሪ፡

በሌላም ሐዲስ ረሡል ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


“ከዚህ በፊት ያለፉ ህዝቦችን መንገድ ላባ በላባ በእርግጥ ትከተላላችሁ፤ የአርጃኖ
(የወከሎ) ጉድጓድ ቢገቡ እንኳ በእርግጥ ትገባላችሁ፤” በማለት ተናገሩ፤ ከዚያም
“የአላህ መልክተኛ ሆይ! አይሁድ እና ነሷራን ነውን?” በማለት ሶሃቦች ጥያቄ
አቀረቡ፤ “እንግዲያ ማንን ነው?” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ (አህመድ፡ 17135, አልባኒ ሲልሲለቱ
አስሶሂሃ 7/915ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው፣ ሀይሰሚይ መጅሙዑ ዘዋኢድ ላይ ዘግበውታል ሐዲሡ ሶሂህ ነው፡፡)

ሁለቱም ሐዲሶች ከረሡል ‫ ﷺ‬የተሰሙ ትክክለኛ ሐዲሶች ናቸው፡፡ ረሡል በዚህ


ማህበረሰብ ውስጥ አይሁድ እና ነሷራን ወይም ፋርስ እና ሮማዎችን የሚመሳሰሉ
ማህበረሰቦች እንደሚኖሩ ነው የጠቆሙት፡፡ ይህን ርዕስ የምናብራራበት ቦታ ከዚህ
ባይሆንም በመሪዎች በንጉሶች በርካታ አዳዲስ ነገሮች ተፈጥረዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ
ቦታ ዋናው አላማችን ጅሐድን አንስተው የጩኸት ቢድዓን በፈጠሩ ሰዎች ላይ ነው፤
አመዛኝ ጥቅም ሊኖረው ይችላል ብለው ገምተው እንኳ ቢሆን መልካሙን ነው
አጥብቀው መያዝ ያለባቸው ፤ አመዛኙ ጥቅም የዚክር ድምጾች ፤ ሶላት እና ከእርሱ
ጋር የተያያዙ ዱዓዎች ፤ ቁርኣን መቅራት እና መስማት ናቸው፤ ሌሎች ጥቅም
የሚያስገኙ ሸሪዓዊ ጉዳዮች አሉ…. ከዚህ በፊት የነበሩት ቀዳሚዎች ታብዒዮች
በማንኛውም ነገር ከኋለኞች የተሻሉ ፤ የሚከተሉት መንገድም የተሟላ ነው፤
ነገር ግን አንድ ሙስሊም ስራዎችን በአቅሙ ሊፈጽም ይገባል፡፡
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡
َ َ‫ّللا َما ا ْست‬
‫ط ْعت ُ ْم‬ َ َّ ‫﴿ فَاتَّقُوا‬
“አላህንም የቻላችሁትን ያህል ፍሩት፤” ተጋቡን ፡
ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“አንድ ነገር ካዘዝኳችሁ የቻላችሁትን ያህል ፈጽሙት፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡
(አልኢስቲቃማ 1/324-331)
ብዥታ አስራ አንድ
የሰብዓዊ መብት ድርጅት አባል የሆነው ዶክተር ዓብዱልዓዚዝ አልፈውዛን
የሚከተለውን ተናግሯል የሚል ብዥታ ቢያቀርቡ፡
(በዓለም በኢስላም ህግ የሚመሩም ይሁን የማይመሩ አገሮች ስርዓት እና ህጉ ሰላማዊ
ሰልፍን የሚከለክል ከሆነ መሪን መቃረን ስለሚሆን መውጣት አይፈቀድም…
በዓለም ደረጃ መብትን ለማስከበር በሁለት መስፈርቶች ህጋዊና የሚፈቀድ ሆኖ
አግኝቸዋለሁ… አንደኛው መስፈርት፡ ሰላማዊ ሰልፍ የሚካሄድበት አገር የሚፈቅድ
ከሆነ ፤ ካልፈቀደ ግን ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት አይበቃም ፤ ሁለተኛው መስፈርት፡
ሰላማዊ ሰልፉ ሰላማዊ መሆን አለበት፡፡

መልስ፡ - ሸይኻችን ሙሀመድ ብን አልዑሰይሚን - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን


ተናግረዋል፡-

(ሰላማዊ ሰልፍ ተንኮል የተሞላበት መሆኑ ጥርጥር የለውም ፤ ሰላማዊ ሰልፍ


በወጡትም ይሁን ባልወጡት ወደ ስርዓት አልበኝነት ይወስዳል ፤ በክብራቸው ወይም
በገንዘባቸው ወይም በአካላቸው ላይ ጉዳት ይደርሳል ፤ ምክንያቱም በዚህ ቦታ ሰው
ልክ እንደሰከረ አይነት ነው ፤ ምን እንደሚናገር ምን እንደሚሰራ አያውቅም ፤
ሰላማዊ ሰልፍ ዳኛ ፈቀደ አልፈቀደ ሁሏም ተንኮልን ያዘለች ነች፤ አንዳንድ መሪዎች
እንኳ ቢፈቅዱም በውስጣቸው ሰላማዊ ሰልፍን በጣም ነው የሚጠሉት ፤ ነገር ግን
ለህዝቡ ነጻነትን ወይም “ዲሞክራሲን” አወጅን ለማለት ያክል ይፈቅዳሉ፤ ይህ
የሰለፎች መንገድ አይደለም፡፡)

(አፍ የሚያዘጋ የሆነው መልስ ደግሞ የሚከተለው ነው፡ የካፊር አገር ስርዓት
መፍቀዱ ማስረጃ ሊሆን በፍጹም አይችልም ፤ ምክንያቱም የሰው ሰራሽ ህግ ነው ፤
እኛ ደግሞ በሸሪዓ ህግ ሀራም እናደርጋታለን፡፡)
(ሁክሙል ሙዛሃራቲ በሚል ዩቲውብ ላይ ሸይኽ ዓብዱልዓዚዝ ፈውዛን የተናገረው)
(ሊቃኡ አልባቡል መፍቱህ 18/179)
ብዥታ አስራ ሁለት
ለመሪዎች ጠንካራ ህዝብ መመስረት ቅንና ኢስላማዊ መንሐጅ በመሆኑ ፤ በኢስላም
ህግ የሚመሩ አገሮች መንግስታቸውን የሚያጠናክሩበት መንገድ አንዱ ሰላማዊ ሰልፍ
በመሆኑ በህጋቸው ውስጥ ማካተት ይኖርባቸዋል፤ ሰላማዊ የሆነች ሰልፍ ህጋዊ መሆን
አለበት ለሚለው የሚከተለውን የዶክተር ሃቲም አልዓውኒይን ንግግር ማስረጃ
አድርገው ብዥታ ቢያቀርቡ፡
(ኢስላማዊ ለሆነች አገር ሁሉ በህዝቡ ላይ ጫና ለማሳደር የሚያግዝ ህግ
መደንገግ ይገባል፤ ምክንያቱም ህዝቡ አደገኛ ወደሆነ ጥመት እና መበታተን
እንዳይሄድ ዋስትና ነው፤ መበታተን በደል ነው፤ በደል ደግሞ በዚህ ዓለምም ይሁን
በወዲያኛው ዓለም ጨለማ ነው፤ አገር በእግሯ ልትቆም የምትችለው በምታሰፍነው
ፍትህ ነው ፤ አንድ መሪ ህዝብን በትክክለኛው ጎዳና ቀጥ አድርጎ መምራት ኢስላማዊ
መንሐጅ ነው፤ በዚህ የመጀመሪያው ኸሊፋ አቡበክር -ረዲየሏሁ ዓንሁማ-
ቀድሟል፤ መሪነትን እንደተሾመ የመጀመሪያው ኹጥባው ላይ የሚከተለውን ተናገረ፡
“ እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ተሹሚያለሁ ነገር ግን በጣም መልካማችሁ
አይደለሁም፤ ካሳመርኩ እገዙኝ፤ ካከፋሁ አስተካክሉኝ…” እርሱ ነው “ካከፋሁ
አስተካክሉኝ” ያለው ፤ በዚህም መሪውን ለማስተካከል በህዝቡ ጫንቃ ላይ
መሰረታዊና መንግስታዊ የስልጣን ህግ ያስቀመጠ እርሱ ነው ፤ እርሱ መስተካከል
ሲያስፈልገው የእርሱን መጣመም ለማስተካከል አስገዳጅ የሆነች ህግ በእርሱ ላይ
ደነገገ፤)
መልስ፡- ከዚህ ቦታ ሰላማዊ ሰልፍ የሚል ቃል የታል? ስህተት ሲገኝ አቡበክርን -
ረዲየሏሁ ዓንሁማ- ለማስተካከል ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ ወጦ ነበር? በፍጹም፤ ሶሀቦችም
ከአቡበክር -ረዲየሏሁ ዓንሁማ- ንግግር ይህን አልተረዱም ፤ እንዴውም የሶሃቦች
አስተያየት ከአቡበክር አስተያየት የተለየ የሆነበት ክስተት በርካታ ነው ፤ ከፊሎቹ
ወደርሱ መጠው ይከራከሩት ነበር፤ ይህ ብቻ አይደለም ወደርሱ የሚከራከር ሰው
ይልኩ ነበር፤ ለምሳሌ ዘካ የከለከሉ አካላትን ለመዋጋት በተነሳ ጊዜ እንዲሁም
የኡሳማን -ረዲየሏሁ ዓንሁማ- ሰራዊት በመላክ ዙሪያ የተከሰተው ጉዳይ ለዚህ ክርክር
ጠቃሚ የሆነ ማሳያ ነው፡፡
(“ሁክሙ አልሙዛሃራቲ አስሰሊመቲ” በሚል ዶ/ር ሃቲም አልዓውኒ አሽሸሪፍ የተናገረው በሚከተለው ማስፈንጠሪያ
ያገኙታል )
ሶሃቦቹ ወደአቡበክር አስተያየት ተመለሱ ምክንያቱም አስተያየቱ ሐቅ ስለነበር፤ ሰልፉ
ሰላማዊ ከሆነ ኢስላማዊ ነው ማለት ባጢል የሆነ ንግግር ነው፡፡

ብዥታ አስራ ሶስት


ሰላማዊ ሰልፍ በዑለሞች መካከል ልዩነት ያለበት ጉዳይ በመሆኑ ተቃውሞ
ሊቀርብበት አይገባም የሚል ብዥታ ቢቀርብ፡
መልስ፡- ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን አብዱልወሃብ - ረሂመሏህ -
የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“ይህ የዑለሞችን አጠቃላይ ስምምነት የሚቃረን ትክክለኛ ያልሆነ ንግግር ነው፤
ሶሃቦችም ይሁኑ ከእነርሱ በኋላ የመጡ ዓሊሞች ከሰዎች አዋቂ እና አላህን ፈሪ
እንኳ ቢሆን ማንም ይሁን ማን ስህተትን ከፈጸመ ወይም ከተቃረነ ከማውገዝ ወደኋላ
አይሉም፤
አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - ሙሐመድን ‫ ﷺ‬በቅን እና በትክክለኛ ሐይማኖት ላይ
ከላከ ፤ እርሱን በመከተል እና እርሱን የተቃረነን ደግሞ በመተው ካዘዘ ፤ ይህን
የሚያሟላው ደግሞ ከዑለማ ተሳሳች ሆኖ የተገኘ ከስህተቱ እንዲነቃ ወይም
በተሳሳተበት ነገር እንዲወገዝ ይደረጋል፡፡
የኢጅቲሃድ መስአላ በሚለው ነጥብ ዙሪያ ውግዘት የማይኖረው ከሁለቱም በኩል
መረጃው ግልጽ ያልሆነ የልዩነት ነጥብ ሲኖር ነው ፤ አንድ ሰው መዝሀቡን ወይም
ልማዱን ስለተቃረነበት ብቻ አንድን ነገር መቃወም የለበትም፤ አንድ ሰው በእውቀት
ካልሆነ ማዘዝ እንደማይችለው ሁሉ ሲቃወምም በእውቀት መሆን አለበት ፤ ይህ ሁሉ
በሚከተለው የአላህ ቃል ውስጥ ይካተታል፡-
َ َ‫ص َر َو ْالفُ َؤا َد ُك ُّل أُولـئِ َك َكان‬
ُِ‫َ ْن‬ َ َ‫س ْم َع َو ْالب‬
َّ ‫ْس لَ َك ِب ِِ َِ ْل ٌم ِإ َّن ال‬ ُ ‫﴿ َوالَ تَ ْق‬
َ ‫ف َما لَي‬
‫َم ْسؤُوالا‬
“ለአንተም በርሱ እውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፡፡ መስሚያ ፣ ማያም ፣
ልብም እነዚህ ሁሉ(ባለቤታቸው) ከእነሱ ተጠያቂ ነውና፡፡” ኢስራእ፡
(ዶ/ር ዓብዱረዛቅ አሽሻይጂይ ከሰጠው ፈትዋ ላይ በሚቀጥለው ማስፈንጠሪያ ይገኛል

(አድዱረሩ አስሰኒያ 4/8-9)


ሸይኽ ሙሐመድ አልኹመይስ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
(ከልዩነት መስአላዎች መካከል ተቃራኒ ከመገኘቱ ጋር ከሁለት አንዱ ዟሂሩ
(ውጫዊ ትርጉሙ) ሁጃ (ማስረጃ) ሆኖ ሊቀርብ ይችላል ፤ ነገር ግን መረጃው
በጣም ደካማ ከሆነ ወደ ትክክለኛው እና ግልጽ ወደሆነው መረጃ እንሄዳለን ፤ አንድ
ንግግር ጠንካራ መረጃ ካለው አሸናፊ ይሆናል ፤ ተሸናፊ የሆነው ንግግር ደግሞ
መረጃው ደካማ በመሆኑ ይተዋል፡፡
ሰላማዊ ሰልፍ የልዩነት ነጥብ በመሆኑ ማውገዙ ግድ አይደለም፤ ይልቁንም
ዝምታን መምረጥ ነው የተሻለ የሚል ጥያቄ ቢነሳ ፡

መልሱ ፡ ሰላማዊ ሰልፍ የልዩነት ነጥብ በመሆኑ ማውገዙ ግድ አይደለም የሚለው


አባባላችሁ ይህ ትክክለኛ ያልሆነ ነው፤ ውግዘት የማይኖረው ከሁለቱም በኩል
መረጃው ግልጽ ያልሆነ የልዩነት ነጥብ ሲኖር ነው፤ ሰላማዊ ሰልፍ ግን አዲስ የተፈጠረ
በመሆኑ ሊወገዝ ይገባዋል፡፡)

(በዚህ ዙሪያ ማን ነው ተቃዋሚው? እርሷን የከለከለው አካል ጋር በእውቀት እኩል


ሊሆን ይችላል? ወይስ እርሱ የፍልስፍናና የፊትና ሰው ነው?)
ብዥታ አስራ አራት
ሰላማዊ ሰልፍ መሷሊሁል ሙርሰላ (ተሸጋጋሪ የሆነ ጥቅም) ነው፡፡ “አነል አስለ
ፊልአሽያእ አልኢባሃ” ማለትም “የነገሮች መሰረት ሀላል ወይም የተፈቀደ ነው፡፡”
በሚለው ህግና መርሆ ውስጥ ይገባል የሚል ብዥታ ቢቀርብ፡
ዶክተር ዩሱፍ አልቀረዷዊ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

(የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ህጋዊነት ባህላዊና የከተማ ህይወት አካል በመሆኑ እንዲሁም
የነገሮች መሰረት መፈቀድ ወይም ሀላል መሆኑ ነው፡፡)
(አልሙዟሀራቱ ወልኢዕቲሷማቱ ወልኢድጢራባት ገፅ/63)
(በዶ/ር ዩሱፍ አልቀርዷዊ ድህረ ገፅ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ይገኛል
)
ዶክተር ሰልማን አልአውዳ ደግሞ የሚከተለውን ተናግሯል፡
(እነዚህን ጉዳዮች አስመልክቶ መሰረቱ መፈቀድ ነው፤ ልዩ የሆነ መረጃ
አያስፈልገውም ፤ ሰነዱ ደካማ ቢሆንም እንኳ ሀምዛ እና ዑመር በሰለሙ ጊዜ በሁለት
ሶፍ መውጣታቸው የሙስሊሞች ታሪክ ሆኖ ተዘግቧል፡፡ ለእኛ በቂ ማስረጃ የሚሆነን
ግን ይህን ጉዳይ ለመከልከልም ለመፍቀድም ምንም አይነት መረጃ አለመኖሩ ነው፡፡)
መልስ፡- ሸይኽ አልባኒ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
( ትክክል ነው፡ ወሳኢል (መዳረሻ ነገሮች) ከሸሪዓ ጋር ካልተጋጩ መሰረቱ
ይበቃል ፤ ይህ ምንም ችግር የለበትም ፤ ነገር ግን ወሳኢሉ (መዳረሻው) ከኢስላም
ውጭ የሆነን መንሀጅ (ጎዳና) ለመከተል መገለጫ ከሆነ ግን እነዚህ ወሳኢሎች
(መዳረሻዎች) ሸሪዓዊ አይሆኑም ፤ አለመውደድን ወይም መውደድን ለመግለጽ
ሰላማዊ ሰልፍ መውጣቱ ወይም ለአንዳንድ ውሳኔዎች ወይም ህጎች ድጋፍ ወይም
ተቃውሞን ለመግለጽ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣቱ ይህ “ፍርድ ለህዝብ” ወይም “ፍርድ
ከህዝብ ወደህዝብ” ከሚለው ሰው ሰራሽ ስርዓት ጋር የሚስማማ ነው፤ ማህበረሰቡ
ኢስላማዊ ከሆነ ግን ጉዳዩ ሰላማዊ ሰልፍ አያስፈልገውም፤ የሚያስፈልገው የአላህን
ህግ በጣሰው ዳኛ ላይ ማስረጃን ማቆም ብቻ ነው፤ ኢስላማዊ ማህበረሰብ ከሆነ
የሰላማዊ ሰልፍ ስርዓት እና ከእርሱ ጀርባ የሚከተሉት ነገሮች ሁሉ አያስፈልጉም፤
ኢስላማዊ ማህበረሰብ ከተረጋገጠ አንድ ሰው አስተያየቱን ማስረጃውን ጉዳዩ
ወደሚመለከተው አካል ወይም ቢያንስ ቢያንስ ለተወከለው አካል ማቅረብ ብቻ ነው፤
በመሆኑም ከምዕራባውያን ባህል በወሰድነው በሰላማዊ ሰልፍ መንገድ አቤቱታን
ማቅረብ አስፈላጊ አይደለም፡፡
እውነታው ግን በአሁኑ ሰዓት ሙስሊሙ ማህበረሰብ የምእራባውያንን ባህልና
ልማድ ወስዶ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ፤ ስለዚህ የግድ ከእነርሱ የምንወስደውን እና
የምንተወውን ነገር ለይተን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ፡ መዳረሻዎቹ ወደ ሸሪዓዊ
አላማዎች የሚያደርሱ ከሆነ ከእነርሱ ብንወስድ ችግር የለውም ፤ ከከሀዲዎች ጋር
መመሳሰል ከሚለው ትርጉም ውስጥ አይገባም፡፡
(ሸበከቱ አድዲፋዕ ዓኒስሱንነቲ በሚል ድህረ ገፅ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ይገኛል
)
ሰላማዊ ሰልፍ ውዴታንም ይሁን ተቃውሞን ለመግለጽ መዳረሻ ሊሆን በፍጹም
አይችልም፤ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ የሰላማዊ ሰልፍን ተጨባጭ ሁኔታ
ሳስተውል ቀስ በቀስ ሙስሊሙን የምዕራባዊ ልማድ ውጦት ክህደት ይቆጣጠረዋል
ብየ አስባለሁ፡፡
ሰላማዊ ሰልፍ የአንድን አገር ስርዓት ሊቀይረው ይችላል? የሚል ጥያቄ ቢነሳ፡
ስንት ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል? ስንት ሰዎች ተገድለዋል? እውነታው ግን
ከሰላማዊ ሰልፉ በኋላ ያለው ሁኔታ ሰላማዊ ሰልፉ ከመደረጉ በፊት ካለው ሁኔታ ጋር
ተመሰሳሳይ ነው፤
ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ከምዕራባውያን የወሰድነው በመሆኑ “አንድ ነገር መሰረቱ ሀላል
ነው ወይም መብቃት ነው፡፡” በሚለው ህግና መርሆ መካተቱ አይታየኝም፡፡)

ብዥታ አስራ አምስት


ዶክተር ሱዑድ አልፈኒሳን የሚከተለውን ተናግሯል፡ (ሸይኽ ኢብን ባዝ የተቃዎሙት
ችግር ያለበትን ውጤቱ ፊትና እና በህብረተሰብ ላይ ችግር የሚያመጣን ሰላማዊ ሰልፍ
እንጅ ከጅምሩ እስከ መጨረሻው በሰላም የሚጠናቀቅ የሆነን ሰላማዊ ሰልፍ
አልተቃወሙም፤ ችግር የሚያመጣ አይነት ከሆነ ግን ያለምንም ጥርጥር ሀራም
ነው፡፡) የሚል ብዥታ ቢቀርብ፡
መልስ፡ - የዶክተር ፈኒሳን ግንዛቤ ትክክል አይደለም፤ ሸይኻችን ኢብን ባዝ
በፈታዋቸውም ይሁን በማብራሪያቸው ውስጥ በአጠቃላይ ሰላማዊ ሰልፍን
አስጠንቅቀዋል፤ ከዚህ መካከል ሸይኽ ዓብዱረህማን ዓብዱልኻሊቅ ምንም ረብሻ
የሌለባት ሰላማዊ ሰልፍ ከሆነች በሀዲስም የተፈቀደ ነው ብሎ በመናገሩ ኢብን ባዝ
በሚከተለው መልኩ በእርሱ ላይ ምላሽ ሰጠዋል፡
(“ፉሱል ሚነሲያሰቲ አሽሸርዒያህ” በሚባለው ኪታባችሁ ገጽ 31 እና 32
የሚከተለውን አውስታችኋል፤ ከነብዩ ‫ ﷺ‬የዳእዋ መንገድ አንዱ ሰላማዊ ሰልፍ ነው
በማለት በተናገራችሁት ላይ አንድም የማውቀው ማስረጃ የለም፡፡
(ሸይኽ አልባኒ የካሴት ቁጥር/210, የፈትዋ ቁጥር/5 ወይም በሚከተለው ድህረ ገፅ ይገኛል
)
(“ነዘራቱ አሽሸርዒየቲ ፊ ወሳኢሊ አትተግይሪ አልአስሪየቲ” በሚል ዶ/ር ሱዑድ ፈይሳን ከሰጠው ፈትዋ የተወሰደ)
ስለዚህ መጠቀም ስለምፈልግ ከየትኛው ኪታብ ላይ ነው ያገኛችሁት?
የምትደገፉበት መረጃ ከሌላችሁ ግን ከነበራችሁበት አቋም መመለስ ግዴታ
አለባችሁ፤ ምክንያቱም ይህን የሚጠቁም መረጃ እስካሁን ስላላገኘሁ ፤ ምክንያቱም
ሰላማዊ ሰልፍ በርካታ ፈሳድ ወይም ብልሹነት ያለበት እንቅስቃሴ ነው፤ በመሆኑም
አበላሽታዎች በዚህ ባጢል በሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንዳይንጠለጠሉ ግልጽ የሆነ
መረጃ ማምጣት ግድ ይላችኋል፡፡)
ብዥታ አስራ ስድስት
ሸይኽ ዓዒድ አልቀረኒ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
(ሊቢያ ውስጥ በመሪዎች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ሀራም እንደሆነ የሚገልጽ
ፈታዋ ተሰራጭቷል ፤ ምናልባት ከፊሎቹ ይህን ጉዳይ በኢስላማዊ ሸሪዓ ለመዳኘት ቃል
በገቡለት መሪ ላይ መውጣትን ወይም ማንም ይሁን ማን በመሪዎች ላይ ሰላማዊ
ሰልፍ መውጣትን ሽተው ሊሆን ይችላል ፤ እኔ የምለው ግን ፡ ጋዳፊ ሊታዘዙት የሚገባ
ወይም በእርሱ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ሀራም የሚሆንበት መሪ ነው? እንደዚሁ
የግብጽ እና የቱኒዚያ መሪዎች? ህዝባቸውን አልበደሉምን? ነጻነትን አልነፈጉምን?
የአላህን ባሮች አላሰቃዩምን? አፎቻቸውን አላፈኑምን? የህዝብ ገንዘብ
አልዘረፉምን? እነዚህ መሪዎች ይህን ሁሉ በደል ሲፈጽሙ የታል የዑለሞች ፈትዋ?
ይህን ሁሉ በደል ሀራም መሆኑን ሳይገልጹ ሰላማዊ ሰለፍ ሀራም መሆኑን የት አገኙ?
ለምን እነዚህን በዳይ የሆኑ መሪዎችን የሚያግዝ እና የሚያጠናክር ፈትዋ ይሰጣሉ?
ለምን ከእነዚህ ህዝብን በአደባባይ ከሚገድሉ ጨካኝ መሪዎች ጎን ይቆማሉ? ዑለሞች
የቱኒዚያ የግብጽ የጋዳፊ መንግስት ለሰላሳ አመታት ያህል እየዘረፉ እየሰረቁ እየገረፉ
የአላህን ባሮች እየቀጡ የአላህን ሸሪዓ እየተዋጉ የአላህን ጠላት ወዳጅ እያደረጉ
ለምን ዝም አሉ?፤ ከዚያም እነዚህ መብታቸው የተገፈፈና የተበደሉ ህዝቦች በእነዚህ
በዳይ መንግስቶቻቸው ላይ መብታቸውን ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ ለምንድን
ነው አንዳንድ ሸይኾቻችን ሰላማዊ ሰልፍ ሀራም ነው ብለው ፈትዋ የሚለቁ? ይህ
ሸሪዓው ከመጣበት አላማ ጋር ሲታይ ምን አይነት ግንዛቤ ነው? ጥቅም እና ጉዳትን
ለማመዛዘን በመጣው የሸሪዓ መሰረት ላይ የታለ ግንዛቤያቸው? አንድ ግንዛቤ አለኝ
የሚል ዓሊም በአንድ ጉዳይ ፈትዋ ሲሰጥ አደገኛ እና አሳሳቢ ነገሮችን ወደጎን ትቶ
እንዲሁ ያስደነቀውን ብቻ ተመልክቶ ፈትዋ መስጠት የለበትም፡፡
አንድ ፈትዋ የሚሰጥ ዓሊም መጀመሪያ በሊቢያ በቱኒዚያ በግብጽ ውስጥ ያሉ
አምባገነን መሪዎች ኢስላማዊ ሸሪዓን በድለው በሰው ሰራሽ ህግ እየተዳደሩ በህዝብ
ላይ የሚያደርሱትን በደል የገንዘብ ዘረፋ የአላህ ባሮችን ማሰቃየት ሀራምነት እና
ድርጊታቸውን በመቃወም ፈትዋ ሳይሰጡ የሰላማዊ ሰልፍ ሀራምነትን ፈትዋ መልቀቅ
የለባቸውም፤ ዑለሞችን መበደል የህዝብን መብት መጣስ ንጹሀንን ማሰር እና ማፈን
ሀራም መሆኑን ቅድሚያ ፈትዋ ሊለቁ ይገባል፤ ነገር ግን ለሰላሳ አመታት ሲፈጸሙ
የነበሩ በደሎችን ዝም ብለው ሲያበቁ አሁን ህዝቡ የውስጥ ስሜቱ ፈንቅሎት መብቴ
ይከበርልኝ ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ሀራም ነው ብሎ ፈትዋ ማውጣት አስገራሚ
ነው፡፡)

ዶክተር ጧሪቅ አስሱወይዳን የሚከተለውን ተናግሯል፡-

(እነዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ፊትና እንደሆነ እና በሽሪዓ እንደማይበቃ የተናገሩ ሰዎች


ጨዋታ ነው (እየተናገሩ ያሉት) ……)

መልስ፡ - አላህ በቁርኣኑ የሚከተለውን ተናግሯል፡


‫َ ِِي ٌم‬ ٌ َ‫﴿ َه َذا بُ ْهت‬
َ ‫ان‬
“ይህ ከባድ ቅጥፈት ነው፡፡” ኑር ፡

የሸሪዓን አህካም (ብይን) ማብራራት ጨዋታ አይደለም ፤ ጋዳፊም ይሁን


ሌሎች አምባገነን መሪዎች ግፍ ሲፈጽሙ ዑለሞች ዝም ብለው አላለፉም ፤ በከሀዲ
መሪዎች ላይ ማፈንገጥ የሚቻለው መቸ እንደሆነም አብራርተዋል፤ በአምባገነኑ
የሊቢያ መሪ ላይ የታላላቅ ዑለሞች ጉባኤ ያወጣውን መግለጫ እና ፈትዋ ቀረኒ
ረሳው እንዴ ?

ከውሳኔዎች መካከል በ 1406 ሒጅራ አቆጣጠር ላይ የሰጡት የሚከተለው


ፈትዋ ይገኝበታል፡-
(መዲና በሚታተመው ጋዜጣ ቁጥር/17538 በቀን 26-05-1436 ሒ “ፈታዋ ዑለማእ ኢስተገለሃ ኒዟሙ
አልቀዛፊ” በሚል ርዕስ ከተናገረው የተወሰደ)
(ዩቲውብ ላይ “አስሰውረቱ ፊሊቢያ ሊጧሪቅ አስሱወይዳኒ” በሚል ከተሰራጨው ንግግሩ የተወሰደ)
(አልሙዛሃራት ፊሚዛኒ አሽሸሪዓቲ አልኢስላሚያ ገፅ/72)
(የታላላቅ ዑለሞች ስብስብ በዚህ ማንነቱ የማይታወቅ በኢስላም እና ሙስሊሞች
ላይ ድንበር እያለፈ የሚገኝ ፤ በረሡል ‫ ﷺ‬ሱና ላይ ተቃውሞውን በማጠናከር በሐጅ
ስርዓት ላይ የሚያሾፍ ፤ እንዲሁም አንዳንድ የኢስላም ህጎችን የሚያቃልል እና
የተሳሳተች ሀጠያተኛ አመለካከትን የሚያሰራጭ በዚህ አመለካከቱ ከሀዲ ወይም
ጠማማ እና አጥማሚ ተብሎ ይወሰንበታል፡፡)

ቀረኒ እና ሱወይዳን እስኪ ሸይኽ ብን ሰህማን እንደተናገሯቸው ሰዎች አይነት


እንዳይሆኑ ይጠንቀቁ፤
ሸይኽ ኢብን ሰህማን ረሂመሁሏህ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
(በዚህ ምንም በማይክዱት ቅጥፈት ምክንያት በሸይኾች ላይ የሚተቹ ሰዎች ስውር
የሆነችው የስሜት አይናቸው ከሐቁ ባልታወረች ኖሮ ሐቅን ከባጢል ባልቀላቀሉ፤
በሰዎች ላይ የበላይነትን ባልፈለጉ ፤ በተራው ማህበረሰብ ላይ ውሸቱን ከሐቁ
ባልደባለቁ ነበር፤ ነገር ግን እይታቸው ታወረ፤ የሸሪዓውን አህካም ማወቅ ተሳናቸው፤
ጥቅጥቅ ባለው ጨለማ የሚጓዙበት ብርሃን ጠፋባቸው፤)

(ስለዚህ አብዛኛውን ሰው ከአላህ ዲን ያገደች በሆነች ዘለፋ - ዑለሞችን አስመሳይ


እና መሰል ስድቦችን በመስደብ - አታላዩ (ሰይጣን) አያታላችሁ፤)

ሸይኽ ሙሐመድ ብን ዓብዱለጢፍ፤ ሸይኽ ሰዕድ ብን ሀምድ ብን ዓቲቅ ፤ ሸይኽ


ዓብደላህ ብን ዓብዱል ዓዚዝ አልዓንቀሪ ፤ ሸይኽ ዑመር ብን ሙሀመድ ብን ሱለይም ፤
ሸይኽ ሙሀመድ ብን ኢብራሂም ብን ዓብዱለጢፍ እና መሰል ታላላቅ ዑለሞች ደግሞ
የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
(በርካታ ጃሂሎች የወደቁበት ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡ በእነርሱ ላይ አላህ
ያዘዘው የሆነውን ግዴታ በመተው ከሐቅ የሚያውቁትን በመደበቅ እርሱን ከማብራራት
ዝምታን በመምረጥ የእውቀት ባለቤቶችን በጉድለት በአስመሳይነት ይጠረጥራሉ፤
(በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ማየት ይቻላል )
(“መንሐጁ አህለ አልሀቂ ወልአትባዒ ፊሙኻለፈቲ አህለ አልጀህሊ ወልኢብቲዳዕ” ገፅ/103)
(አድዱረሩ አስሰኒያ 9/91 ሪሳለቱ አሽሸይኽ ዓብዱለጢፍ -ረሂመሁሏህ-)
እነዚህ ጃሂሎች የእውቀት እና የዲን ባለቤቶችን ማማት ወይም የሙእሚኖችን ስጋ
መብላት ሀጢያቱ ግልጽ ሆኖ ነገር ግን ድብቅ የሆነ በሽታ ፤ ገዳይ የሆነን መርዝ
መብላት መሆኑን አላወቁም ፤
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡
‫احتَ َملُوا بُ ْهتَاناا َو ِإثْ اما ُّم ِبيناا‬ ِ ‫﴿ َوالَّذِينَ يُؤْ ذُونَ ْال ُمؤْ ِمنِينَ َو ْال ُمؤْ ِمنَا‬
َ َ‫ت ِبغَي ِْر َما ا ْكت‬
ْ ‫سبُوا فَقَ ِد‬
“እነዚያንም ምእምናንንና ምእምናነትን ባልሰሩት ነገር (በመዝለፍ)
የሚያሰቃዩ እብለትንና ግልጽ ሃጢያትን በእርግጥ ተሸከሙ፡፡” አህዛብ

እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ዑለሞችን አስመሳይ ወይም በሐቅ ላይ የማይናገሩ ዲዳ


ከማለት ይጠንቀቁ ፤ ይህ - ወሏሂ - አክሳሪ የሆነ መንሸራተት ነው ፤ ታላቅ ነውር
ነው፤ የሰይጣንን ማታለል ተንኮሉን ማስመሰሉን ሽወዳውን ተጠንቀቁ ፤ እንሆ እርሱ
በግራው ተደግፎ በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል ጥላቻ ጠላትነትን መዝራት ልማዱ
ነው ፤ እስካሁን ድረስ ሙስሊሞችን በቃላት መለያየት የተለመደ ባህሪው አድርጎታል
፤ በውስጥም በግልጽም አላህ የጠበቀው በንግግሩም በተግባሩም ፤ በእንቅስቃሴውም
በእረፍቱም ቀጥ ያለ ጎዳና የተከተለ፤ መጨረሻው ምን እንደሆነ ያስተነተነ ወደ
እውቀት ባለቤቶች እና የግንዛቤ ባለቤቶች የተመለሰ ካልሆነ በቀር ከእርሱ ተንኮል
ሰላም የሚሆን የለም፤
አንድ አካል በእናንተ ላይ … የተለያየ ሹቡሃ ቢጥልባችሁ መጥፎውን እንደ ጥሩ ፤
ቢድዓውን እንደ ሱና ጥመቱን እንደ ቅን ጎዳና አድርጎ ቢያሳምርላችሁ እወቁ
ለሰይጣን ክፉ መንፊያ እንዳለው ፤ ቆይቶ የደበቀውን ወናፍ በእናንተ ላይ ይነፋል ፤
ከዚያም ሀይማኖታችሁን ይቀላቅልባችኋል፡፡)

ብዥታ አስራ ሰባት


በሙእታ ጦርነት የወጡ ሶሃቦችን (ያ ፈራር ወይም እናንተ ፈርጣጭ በማለት)
ለመውቀስ ወጣቶች ሲወጡ ረሡል ‫ ﷺ‬ምንም ሳይቃወሙ ድርጊታቸውን
አረጋግጠውላቸዋል፤ የወጣቶችን መውጣት ቢድዓ ነው አላሉም፡፡
(አድዱረሩ አስሰኒያህ 9/113-114)
(አድዱረሩ አስሰኒያህ 9/104-105 ሪሳለቱ አሽሸይኽ ሙሐመድ ብን ዓብዱለጢፍ ብን ዓብዱረህማን
አሊ’ሸይኽ -ረሂመሁሏህ-)
ይህ የሚጠቁመው ሰላማዊ ሰልፍ የሚፈቀድ መሆኑን ነው የሚል ብዥታ ቢቀርብ፡
መልስ፡ - ኢብን ሰዕድ ያወራው ዘገባ ላይ የታለ ሰላማዊ ሰልፍ የሚል ቃል? ትርጉሙ
(ይልቁንም ይህ አባባል ሙንከር ወይም ግልጽ የሆነ ባጢል ነው፤ እንዴት በርካታ
ቁጥር እንዲሁም በመሳሪያ ብዛት እጥፍ ድርብ የሆኑትን ሮማዎች በቁጥርም ይሁን
በትጥቅ ውስን የሆኑት አማኞች የአላህ እርዳታ ከሌለ በቀር እንዴት መጋፈጥ
ይችላሉ? እንዴት እጅግ ቁጥሩ በርካታ በሆነ የሮማ ሰራዊት ላይ አፈር በአይኖቻቸው
በትነው ሸሹ ወይም ፈረጠጡ ይባላል? እውነታው ይህ አይደለም ፤ ጀግና የሆኑት
ሶሃቦች በአላህ እርዳታ ድል እስከሚያደርጉ ድረስ ጸኑ፡፡ ቡኻሪ እንደሚከተለው
ዘግበውታል፡ “ከአላህ ሰይፎች መካከል አንዱ ሰይፍ አላህ አሸናፊ እስኪያደርጋቸው
ድረስ ሰንደቅ አላማን ያዘ፡፡”) ቡኻሪ፡
እነዚህ ወጣቶች ሰራዊቱን ለመቀበል ነው የወጡት ብንል እንኳ የሰራዊቱን መመለስ
ለመቃወም የተደረገ ሰልፍ አይደለም፤ እንዴት ከአላህ ሰይፎች መካከል አንዱ ሰይፍ
ሰራዊቱ ድል እንደሚያደርግ ባንዲራ ይዞ እንደወጣ ነብዩ ‫ ﷺ‬ተናግረው ሲያበቁ
ሶሃቦቹ በመሸሻቸው ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ እንዴት ይባላል? ሰራዊቱ ሲመለስ ሁሉም
የራስ የራስ የሆነውን ዘመዱን አቀባበል አድርጓል፤ ታዲያ ይህ የሰላማዊ ሰልፍ
ትርጉም አለውን? በፍጹም የለውም፡፡

ብዥታ አስራ ስምንት


ሰላማዊ ሰልፍን አስመልክቶ ሸይኽ ዓልይ አልኹዶይሪ የሚከተለውን ተናግሯል፡
(ከኢስላም ባለቤቶች መንገድ ወይም ከዓረቦች ዘንድ ይህን አይነት ይሰሩ ነበር፤ ሸሪዓ
ሳይቃወመው እንዲሁ አጽድቆት ያለፈ ዓረባዊ ድርጊት መሆኑ ይታወቃል ፤
ሙስሊሞች አንዳች ነገር ካሳሰባቸው በጀማዓ ይወጡ ነበር ፤ ተሰባስበው በልኡካን
ቡድን መልክ ይመጣሉ፤ ድሮም አሁንም ሙስሊሞች ይህን ከመስራት
አልተወገዱም፡፡) የሚል ብዥታ ቢቀርብ፡
(“አሽሸሪዓቱ ወልሀያት” በሚል በቀን 2-2-1423 ሒ. ዩሱፍ አልቀርዷዊ ከሰጠው ፈትዋ)
(ዲፋዕ ዓኒልሐዲሲ አንነበዊይ ወስሲረቲ ፊርረዲ ዓለልጁሃላት ዶ/ር አልቡወይጢይ” “ፊቅሁ አስሲረቲ” በሚል ኪታባቸው
አልባኒ ገፅ/30 የተናገሩት)
(ዲፋዕ ዓኒልሐዲሲ አንነበዊይ ወስሲረቲ ፊርረዲ ዓለልጁሃላት ዶ/ር አልቡወይጢይ” “ፊቅሁ አስሲረቲ” በሚል ኪታባቸው
አልባኒ ገፅ/31 የተናገሩት)
(በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ይገኛል )
መልስ፡ - ከኢስላም በፊት ዓረቦች ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣታቸው መረጃው የታለ? ፤
ረሡል ‫ ﷺ‬ከተላኩ በኋላ ሰላማዊ ሰልፍን ኢስላም እንዳጸደቀው መረጃው የታለ?፤
ወደረሱል ወይም ወደኹለፋኡ ራሽዲን ወይም ወደሙስሊም መሪዎች ለተለያዩ የዲን
እና ዱንያዊ ጉዳዮች ሲመጡ የነበሩ ልኡካን ቡድኖች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ ነው
የሚባለው? የታለ የሰላማዊ ሰልፍ ትርጉሙ?

እንዴውም ከኢስላም በፊት ዓረቦች ሰላማዊ ሰልፍ ይወጡ ነበር የሚለው አባባል
ትክክል ነው ብለን ብንቀበለው እንኳ ፤ ይህ ኢስላም ያላጸደቀው የጃሂልያ ባህሪ ነው
የሚል መልስ ይሰጣቸዋል ማለት ነው፡፡

‫الحمد لله‬
‫ عبدالرحمن بن سعد بن علي الشثري‬:‫تاليف‬

ትርጉም፡ ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ

ባህር ዳር በሚገኙ የአህለሱና መሻይኾች


የተቀሩ ጠቃሚ ኪታቦች፣ ከሀገር
ውስጥና ከውጭ በሚመጡ መሻይኾች
የተሰጡ ኮርሶች፣ ሙሓዶራዎች፣ የጁመዓ
ኹጥባ፣ በትክክለኛ ማስረጃ የተደገፉ
የተለያዩ ኢስላማዊ መጣጥፎችን
የሚከተለውን የቴሌግራም ሊንክ ጆይን
በማድረግ መከታተል ይችላሉ

You might also like