Professional Documents
Culture Documents
ሙዚቃና የሙዚቃ መሳሪያዎች እርምነት
ሙዚቃና የሙዚቃ መሳሪያዎች እርምነት
መሳሪያዎች እርምነት
إعداد:
الشيخ عبدالرزاق بن عبدالمحسن البدر
ትርጉም፡ ዩሱፍ አሕመድ
ምስጋና ለአላህ ይገባው ፡፡ በእርሱ እመካለሁ ፣ ወደርሱ ተጸጽቸ እመለሳለሁ ፡፡ ከአላህ
በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የሌለ መሆኑን ፣ ሙሐመድ ﷺየአላህ አገልጋይና
መልክተኛ መሆናቸውን ፣ እሰከ እለተ ሞታቸው ድረስ ህዝብን በትክክል የመከሩና
የተሰጣቸውን አደራ በአግባቡ የተወጡ መሆናቸውን ፤ መልካም ነገር ኖሮ የተውት ፣
መጥፎ ነገር ኖሮ ያላስጠነቀቁት አንድም ነገር የለም ብየ በእርግጠኝነት እመሰክራለሁ፡፡
በእርሳቸው ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ የአላህ ሶላትና ሰላምታ ይስፈን፡፡
ከዚህ በመቀጠል፡
አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - ሙስሊሞች እርካታን ፣ መረጋጋትንና እድለኛነትን
የሚጎናጸፉበትን ምቹና ቀጥ ያሉ በውስጣቸው በረካ የተሞላባቸውን አቅጣጫዎች የያዘ
መመሪያ አውርዷል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሙስሊሞች ከዚህ ቀጥተኛ ጎዳና በማዘንበል
ጣፋጭ የሆነ ህይዎት ወይም የልቦና መረጋጋትን እናገኛለን በሚል ስሜት ጎጅና ከባድ
ተጽእኖዎችን ወደሚያስከትሉ ተግባራት ፊታቸውን ሲያዞሩ ይስተዋላል፡፡
ዘወትር ሙዚቃ በማዳመጥ ቀልባቸውን የሚያደርቁ በርካታ ወጣቶች አሉ፤ ለምን
እንደሚያዳምጡ ሲጠየቁም የቁርኣንና የሐዲስን መረጃዎች መሰረት ያላደረገ ፈትዋ
ከአንዳንድ ዑለሞች በመስማታቸው እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡
በተለይም አሁን ባለንበት ዘመን ቀልብ የሚስቡ የድምጽ ቅላጼዎች በዘመናዊ
መሳሪያ እየታጀቡ በመምጣታቸው ወጣቱ ትውልድ ለዱንያውም ይሁን ለአኼራው
ጥቅም ከሚያስገኙ ነገሮች ርቆ በማይረቡ ነገሮች ብቻ ተጠምዶ ይስተዋላል ፤ በዚህም
የነገሩ አስከፊነት እየጨመረ ሄዷል፡፡ እነዚህ ነገሮች መስፋፋታቸው ዲናቸው
እንዲዳከም ፣ ስነ-ምግባራቸው እንዲወርድ ፣ ከከፍተኛና መልካም ከሆኑ ባህሪያት
ተርታ ወርደው ወደዘቀጡና ወራዳ ወደሆኑ ባህሪያት ተርታ እንዲሰለፉ አድርጓቸዋል፡፡
የሙዚቃ መሳሪያዎችና ዘፈኖች ክልክል ለመሆናቸውና በሙእሚኖች ላይ እያሳደረ
ያለው የልቦና ፣ የአዕምሮ፣ የዲን እና የስነ-ምግባር ተጽእኖ ከባድ መሆኑን
የሚያብራሩ ከቁርኣንና ከሐዲስ ማስረጃዎችን ይዞ የኢስላም ሸሪዓ መጧል፡፡
1/5
አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡-
اَّلل ِبغ ْ َِْي ِع ْ ٍْل َويَتَّ ِخ َذهَا ه ُُز ًوا
ِ َّ ِيل ِ ﴿و ِم َن النَّ ِاس َمن ي َْش َ َِتي لَه َْو الْ َح ِد
ِ يث ِل ُي ِض َّل َعن َسب َ
﴾اب ُّمه ٌِني ٌ ُأول َ ِئ َك لَه ُْم عَ َذ
“ከሰዎችም ያለእውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ
ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አልለ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት
አላቸው፡፡” ሉቅማን፡
ኢብን አባስ ፣ ኢብን መስዑድ ፣ ሌሎችም ሶሃቦችና ታብዕዮች “አታላይ ወሬን የሚገዛ
አልለ” የሚለውን የቁርኣን አንቀጽ “ዘፈንና የሙዚቃ መሳሪያ ነው” በማለት
ተርጉመውታል፡፡ ታላቁ ታብዕይ ሀሰን አል-በስርይ - ረሂመሁሏህ - ደግሞ “ይህ
የቁርኣን አንቀጽ የወረደው ዘፈን እና የሙዚቃን መሳሪያ አስመልክቶ ነው” በማለት
ይናገራሉ፡፡ ተፍሲር ኢብኑ አቢ ሃቲም
አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡-
ِل َو َش ِار ْكه ُْم ِِف ا َأل ْم َو ِال َ ِ ﴿و ْاس َت ْف ِز ْز َم ِن ْاس َت َط ْع َت ِم ْْنُ ْم ب َِص ْو ِت َك َو َأ ْج ِل ْب عَلَ ْ ِْيم ِ َِب ْي
َ ِ ِل َو َر ِج َ
﴾الش ْي َط ُان االَّ ُغ ُرو ًرا َّ َوا َأل ْوال ِد َو ِع ْد ُ ُْه َو َما ي َ ِعدُ ُ ُُه
“ከእነርሱ የቻልከውን ሰው በድምጽህ አታል፡፡ በእነሱም ላይ በፈረሰኞችህ
ِ
በእግረኞችህም ሆነህ ለልብ፡፡ በገንዘቦቻቸውም ፣ በልጆቻቸውም ተጋራቸው ፣
ተስፋ ቃልም ግባላቸው፡፡ ሰይጣንም ማታለልን እንጂ ተስፋ ቃልን
አይገባላቸውም፡፡ አል ኢስራእ፡
ከሶሃቦች ፣ ከታብዕዮች በርካታዎቹ ይህን የቁርኣን አንቀጽ በሚከተለው መልኩ
ተርጉመውታል፡-
“በዚህ የቁርኣን አንቀጽ የተፈለገው የሰይጣን ድምጽ ሲሆን እርሱም ዘፈን ነው፡፡”
ብለዋል፡፡ ተፍሲር አጥ ጦበሪይ እና ተፍሲር አል ቁርጡቢይ
አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - የአላህ ባሮችን ባህሪ ሲገልጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
َ ُ﴿و َّ ِاَّل َين َال ي َْشهَد
﴾ون ُّالز َور َوا َذا َم ُّروا ِِبلل َّ ْغ ِو َم ُّروا ِك َرا ًما َ
“እነዚያም እብለትን የማይመሰክሩ ፤ በውድቅ ቃልምِ (ተናጋሪ አጠገብ) ባለፉ
ጊዜ የከበሩ ሆነው የሚያልፉት ናቸው፡፡” አል ፉርቃን፡
يعزف على رؤوسهم، يسمونها بغير اسمها، "ليشربن ناس من أمتي الخمر
" ويجعل منهم القردة والخنازير، يخسف هللا بهم األرض، والمغنيات، بالمعازف
“ከኡመቶቸ አስካሪ መጠጦችን የሚጠጡ ሰዎች ይኖራሉ ፤ ያለስሟ ይሰይሟታል ፤
የሴት ዘፋኞችና የሙዚቃ መሳሪያ በአናተቸው ላይ (ከፍ ካለ መድረክ ላይ ሆነው)
ይዘፍኑባቸዋል ፤ አላህ በእነርሱ ላይ መሬትን ይደረምስባቸዋል ፤ ከእነርሱም ዝንጀሮና
ከርከሮዎች ያደርጋቸዋል፡፡” ኢብኑ ማጀህ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል አስ ሶሂህ፡
5/5
ሙዚቃና የሙዚቃ
መሳሪያዎች እርምነት
:إعداد
الشيخ عبدالرزاق بن عبدالمحسن البدر
ትርጉም፡ ዩሱፍ አሕመድ