You are on page 1of 5

ለምን ወቅፍ እናደርጋለን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። ምስጋና ለአላህ ተገባው፡፡ ከአላህ ሌላ የሚመለክ አለመኖሩን፣ ብቸኛ እና አጋር የሌለው መሆኑን፤ ሙሀመድም አገልጋዩና
መልዕክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ፡፡ የአላህ ሰላምና እዝነት በአላህ የነብያት መደምደሚያ በሆኑት የአላህ መልዕክተኛ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን።
ኢስላማዊ ሸሪዓ የተሟላ የተዋበ እና ለሰዎች መልካሙን ሁሉ የሚያመቻች የፍትህ ህግ ነው። የሰው ልጆች በምድራዊ ህይወታችው እንዲተባበሩና እውነተኛ ማህበራዊ መደጋገፍን
እውን እንዲያደርጉ ያስተምራል። አንድ የአላህ ባርያ አላህ ከሰጠው ሀብት ለሌሎች ግልጋሎት በሚሰጥና ጥቅሙ ቀጣይነት ባለው የምፅዋት አይነት (ሰደቃህ ጃሪያህ) እንዲሳተፍ
ያበረታታል። ይህ አይነቱን ቀጣይ ሰደቃ ልዩ የሚያደርገው ገንዘቡን ያወጣው ሰው በህይወት ባይኖር እንኳን ሰው እስከተጠቀመበት ድረስ የመልካም ስራ ምንዳ(አጅር)
የሚያስመዘግብለት መሆኑ ነው። በኢስላም ወቅፍ በመባል የሚታወቀው ይህ አይነቱ ሰደቃ እጅግ ብዙ ጥቅሞች ሲኖሩት ሸሪዓዊ መሰረቶቹም ጠንካራ ናቸው። ይህ ፅሁፍ የ ወቅፍን
ሸሪዓዊ ህግጋት በጥቅሉ ይዳስሳል፤ አውቃፎችን የማስተዳደር እና የመንከባከብ ሀላፊነቶችንም ያስታውሳል። በዚሁ አጋጣሚ፤ በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዳከመ የመጣውን የአውቃፍ
ስራ ለማነቃቃት ሁሉም በጋራ ጥረት ያደርግ ዘንድ አደራ እንላለን። ወቅፎችን የመቆጣጠር ሀላፊነት የተጣለባቸው አካላትም ለወቅፍ አስተዳደር በቂ ትኩረት በመቸር
ሀላፊነታቸውን ባግባቡ እንዲወጡ እንጠይቃለን።

ወቅፍ ምንድነው?
በቋንቋ ደረጃ ወቅፍ ማለት «ማገድ» ወይም «መገደብ» ማለት ነው። በኢስላማዊ ትርጓሜው ግን ወቅፍ ማለት «የአንድ ንብረት ባለቤት፤ ወደ አላህ መቃረብን አላማ በማድረግ
ከንብረቱ የሚገኘው ገቢ እርሱ ለመረጠው መልካም ተግባር እንጂ ለሌላ እንዳይዉል የሚጥለው ገደብ ነው።» የንብረቱ ይዞታ እና ባለቤትነት የማይቀየር በመሆኑ የኢስላም ምሁራን
እንዲህ በማለት ይገልፁታል (ተህቢሱል አስል ወተስቢሉል መንፈዓህ) «ወቅፍ የተደረገዉን ንብረት በማገድ ከንብረቱ የሚገኘዉን ጥቅም ለመልካም ግልጋሎት እንዲዉል ማድረግ»
ማለት ነው። ስለዚህም ወቅፍ የተደረገ ንብረት አይሸጥም አይለወጥም! በወቅፍ አስተዳዳሪነት የተሾመው ግለሰብ፣ ኮሚቴ ወይም ድርጅት ባለንብረቱ ላቀደው አላማ ብቻና ብቻ
ሊያውለው ይገባል።

. ወቅፍ እና ሙስሊሞች

ወቅፍ፤ ያለፉ ሰዎችን በህይወት ካሉት ጋር ያስተሳስራል፣ ማህበራዊ ግንኙነትን ያጎለብታል፣ እውነተኛ ማህበራዊ መደጋገፍን እዉን ያደርጋል። አላህ ለእርሱ ተብሎ ወጪ የተደረን
ገንዘብ እንደሚተካ ቃል በመግባቱ ሙስሊሞች ለበጎ አድራጎት ቀዳሚነታቸውን አስመስክረዋል። ከመጀመሪያዎቹ ሙስሊም ትውልዶች ጀምሮ ብዙ ሙስሊሞች ማህበራዊ
መደጋገፍን ባህሉ አድርጓል ከሚባል ከየትኛዉም ማህበረሰብ በበለጠ የከበረ ንብረታቸዉን ወቅፍ እንዳደረጉ ታሪክ ይዘክራል። የነብዩ ‫ه‬ባልደረቦች አርአያነት ከምንም በላይ ለወቅፍ
መበራከት ዋነኛ አስተዋፃኦ ነበረው። የተለያዩ መስጊዶችን፣ የቁርአን መማርያ መድረሳዎችን፣ አይታሞችን፣ ለችግረኞች ነፃ የምግብ እና የንፁህ ዉሀ የሚያቀርቡ ተቋማትን ወዘተ...
የሚደጉሙ ወቅፎችን ሲያቋቁሙ ቆይተዋል።

ወቅፍና የረሱል ባልደረቦች

ምንም እንኳን የኢስላም ብርሀን በፈነጠቀበትና የረሱል ‫ ه‬ባልደረባ ሰሀቦች በኖሩበት የኢስላም መባቻ ብዙዎቹ ከባድ የሆኑ ችግሮችንና ፈተናዎችን ያለፉ ቢሆንም በሁሉም
ሁኔታዎች አቅማቸው በፈቀደው ልክ ገንዘባቸዉን ከመለገስ ወደኋላ አላሉም። በተለይም የአላህ ፍቃድ ሆኖ ነገሮች በተመቻቹባቸው ግዜያት ድንቅ የወቅፍና በጎ አድራጎት ታሪክ
አስመዝግበዋል። እንግዶችና ስደተኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ፣ የተራበን ማብላት፣ የቲሞችና አረጋውያንን መንከባከብ የዘውትር ተግባራቸው ነበር። መዳሰስ የተፈለገው ይህ ስራቸው
በሞት እንዳይቋረጥና ቋሚ እንዲሆን ንብረታቸውን ወቅፍ በማድረግ የሚገኙ ዘውታሪ ምንድዎችን በማሰብም ብዙ ንብረቶቻቸውን በቋሚነት ያገለግሉ ዘንድ ወቅፍ አድርገዋል። ይህ
አይነቱ ዘውታሪ ሰደቃ ያለዉን ልዩ ጥቅም ጠንቅቀው ያዉቁ ነበር። ተከታዩ ሀዲስ ይህንን በጉልህ ያሳያል።

‫ا‬
‫ وكان النبي‬،‫ وكانت مستقبلة المسجد‬،‫ وكان أحب أمواله إليه بيرحا‬.‫نخًل‬ ‫ كان أبو طلحة أكثر أنصاري في المدينة‬:‫عن أنس بن مالك رضي هللا عنه قال‬
ْ ‫حتَّى تُنف ُِق‬
‫وا‬ ْ ُ‫ {لَن تَنَال‬:‫ يا رسول هللا إن هللا يقول‬:‫ فلما نزلت هذه اآلية قال أبو طلحة‬،‫صلى هللا علبيه وسلم يدخلها ليشرب من ماء فيها طيب‬
َ ‫وا ْال ِب َّر‬
‫ فضعها يا رسول هللا حيث أراك‬،‫ وإنّها صدقة هلل أرجو برّها وذخرها عند هللا‬،‫ن أحب أموالي إلي بيرحا‬ َ ُّ‫ما تُحِب‬
ّ ‫ وإ‬.]92 ‫ من اآلية‬:‫ون} [سورة آل عمران‬ َّ ‫ِم‬
ُ
‫ فقال أبو‬،»‫ وإني أرى أن تجعلها في األقربين‬،َ‫سمعت ما قلت‬ ٌ ‫ ذلك ما‬،‫ل رابح‬
‫ وقد‬.‫ل رابح‬ ٌ ‫ «بخٍ ذلك ما‬:‫ فقال رسول هللا صلى هللا عليه وسلم‬،‫هللا‬
.‫ فقسمها أبو طلحة في أقاربه وبني عمه‬،‫ أفعل ذلك يا رسول هللا‬:‫طلحة‬
ቡኻሪና ሙስሊም ከአነስ ኢብኑ ማሊክ በዘገቡት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል፤ “በመዲና ከነበሩ አንሳሮች ሁሉ አቡ ጠልሀ ብዙ የተምር ሀብት ነበረው። ነገር ግን ከሀብቱ ሁሉ በጣም
የሚወደው በይሩሀዕ የተባለዉን ከነብዩ መስጊድ ፊት ለፊት የሚገኝ የተምር ማሳ ነበር። የአላህ መልዕክተኛ ‫ه‬በዉስጧ ከሚገኘው ንፁህ ዉሀ ለመጠጣት አንዳንዴ ወደ በይሩሀዕ
ይገቡ ነበር። ተከታዩ አንቀጽ በወረደ ጊዜ አቡ ጠልሀ ወደ አላህ መልዕክተኛ ‫ ه‬ሄደና፤ «አላህ በቁርአን እንዲህ ብሏል።

92 ‫} ْلن تَنَالُوا الرِْبَّ َح ََّّت تُْن رف ُقوا رِمَّا ُرُتبُّو َن َوَما تُْن رف ُقوا رم ْن َش ْي ٍء فَإر َّن َّاَّللَ برره َعلر ٌيم ٌٌ{ آل عمران‬
«የምትወዱትን እስከምትለግሱ ድረስ የበጎን ሥራ ዋጋ አታገኙም፡፡ ከምንም ነገር ብትለግሱ አላህ ያውቀዋል» አል-ኢምራን 92

እኔ ዘንድ ከሀብቴ ሁሉ ተወዳጁ በይሩሀዕ ነው። ስለዚህም ማሳዬን ለአላህ ብዬ ሰደቃ በመስጠት አላህ ዘንድ የመልካም ስራን ምንዳ እከጅላለሁ። የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አላህ
ላሳይዎት መልካም አላማ ያውሉት።» አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም ደስታቸዉን በመግለፅ ጎሽ! ይህ ትርፋማ ንብረት ነው! ይህ ትርፋማ ንብረት ነው! ዉሳኔህን ሰምቻለሁ እኔ
የምመርጥልህ ግን ለቅርብ ዘመዶችህ ብታደርገው ነው» አሉት። አቡ ጠልሀም «እሺ እንዳሉኝ አደርጋለሁ» በማለት ለአጎቶቹ ልጆችና ለቅርብ ዘመዶቹ አከፋፈለው።» ቡኻሪ በቁጥር
2769 ሙስሊምም በቁጥር 998 ዘግበዉታል።

ወቅፍና ሸሪዓዊ መሰረቱ


ወቅፍ ቀጣይነት ያለው ሰደቃ ስለሆነ ለመልካም ዓላማ ገንዘብ ማዉጣትን የሚያዙና የሚያስታዉሱ የቁራዓን አንቀፆችና ሀዲሳዊ መረጃዎች ሁሉ ይመለከቱታል። በሙስሊሞች ዘንድ ካለው
ጠንካራ መሰረትና ከአሳሳቢነቱ በመነሳት ብዙ የኢስላም ሊቃዉንት በየጊዜው አስፈላጊነቱን ሲያወሱና ሲያሳስቡ፣ ሸሪዓዊ የአተገባበር ህግጋቱንም ሲገልጹ ቆይተዋል።

የዱንያ ህይወት ለአኼራ ስንቅ የሚሰነቅበት አጭር የስራ ሀገር ነው። የአላህ ችሮታና ፀጋው ከሚገለጽባቸው ነገሮች አንዱ ምንዳቸው በሞት የማይቋረጥ ቀጣይ የመልካም ስራ በሮችን መደንገጉ
ነው።

ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ‫ ه‬እንዲህ ብለዋል «የአደም ልጅ (አንድ ሰው) ሲሞት ከሶስት ነገሮች በስተቀር መልካም ስራው ሁሉ ይቋረጣል፤
ቀጣይ የሆነ ሰደቃ፣ ጠቃሚ ዕዉቀት እና ለእርሱ ዱዓ የሚያደርግለት ሷሊህ (መልካም) ልጅ» አል-ኢማም አል ኢማም አነወዊይ ይህንን ሐዲስ ሲያብራሩ እንዳሉት «የኢስላም
ሊቃዉንት የዚህን ሐዲስ ተርጓሜና መልዕክት አስመልክቶ እንዳሉት፤ ማንኛዉም ሟች ሲሞት መልካም ስራው ይቋረጣል። የሚያገኘውም ምንዳ እንዲሁ ይቋረጣል። ነገር ግን
ለእነዚህ ሶስት መልካም ነገሮች መዘውተር ሟቹ ሰበብ በመሆኑ ምክኒያት ምንዳቸው አይቋረጥበትም። ይህ ሀዲስ ወቅፍ ያለዉን ኢስላማዊ መሰረትና ምንዳው ታላቅ እንደሆነ
ያመለክታል» ።

በዚህ ሀዲስ የተጠቀሱትን ሶስት የመልካም ስራ በሮች ትርጓሜ እና ማዕቀፍ የሚከተለው ሐዲስ ይበልጥ ያብራራዋል።

َ ‫ َو َولَدًا‬، ُ‫عله َمهُ َونَش ََره‬


‫ َو ُمص َحفًا‬، ُ‫صا ِلحًا ت ََر َكه‬ َ ‫ عِل ًما‬: ‫سنَاتِ ِه بَع َد َموتِ ِه‬ َ ‫إِنه ِم هما يَل َح ُق ال ُمؤمِنَ مِن‬: ”‫سله َم‬
َ ‫ع َم ِل ِه َو َح‬ َ ‫علَي ِه َو‬ ُ ‫صلهى ه‬
َ ‫َّللا‬ ِ ‫ قَا َل َرسُو ُل ه‬: ‫عن أَبِي ه َُري َرةَ رضي هللا عنه قَا َل‬
َ ‫َّللا‬ َ
‫ يَل َحقُهُ مِن بَع ِد َموتِ ِه “حسنه األلباني في صحيح ابن‬، ‫ص هحتِ ِه َو َحيَاتِ ِه‬ ِ ‫ص َدقَةً أَخ َر َج َها مِن َما ِل ِه فِي‬َ ‫ أَو‬، ُ‫ أَو نَه ًرا أَج َراه‬، ُ‫ أَو بَيتًا الب ِن السهبِي ِل بَنَاه‬، ُ‫ أَو َمس ِجدًا بَنَاه‬، ُ‫َو هرثَه‬
.‫ماجه‬

አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ ‫ ه‬እንዲህ ብለዋል፤ «አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ከሚከተሉት ነገሮች መክከል፤ ለሰዎች ያስተላለፈው እዉቀት፣ ሷሊህ የሆነ ልጅ፣
ለሰዎች ያወረሰው የቁርአን መጽሀፍ (ሙስሀፍ)፣ የገነባው መስጅድ፣ ለመንገደኞች ማረፍያ የሰራው ቤት፣ ለተገልጋዮች እንዲደርስ የቀየሰው ወንዝ፣ ከገንዘቡ ለጤናዉና ለህይወቱ
ያወጣው ሰደቃ ከሞተ በኋላ ይከተሉታል» ኢብኑ ማጀህ ዘግበዉታል አልባኒም ሀሰን ደረጃ ሰጥተዉታል

ኢጅማዕ፦ ወቅፍ የተደነገገ ለመሆኑ የኡለማዎች ሙሉ ስምምነት(ኢጅማዕ) ተገኝቷል። ከላይ የተጠቀሰው ሀዲስ በተመለከተ የሀዲስ ተንታኙ ኢብኑ
ሀጀር፦ «ይህ የዑመር ሀዲስ የወቅፍን ድንጋጌ በተመለከተ እንደ መሠረት የሚወሰድ ነው» ብለዋል። ቲርሚዚም እንዲህም ብለዋል «የእውቀት ባለቤቶች
ዘንድ የሚሰራበት ይኸው ነው፡፡ የነቢዩ ባልደረቦችም ሌሎችም ዘንድ መሬትን ወይም ሌላ ነገርን ወቅፍ ማድረግን በተመለከተ በቀደምት የኢስላም
ምሁራን መሀከል ምንም አይነት ውዝግብ አናውቅም»። ኢብኑ ሁበይራህ አሸይበኒይ ወቅፍን መደንገግ የተመለከተ የዑለማዎች ስምምነት (ኢጅማዕ)
አስተላልፏል (አል ኢፍሣህ 2/25)

የአራቱ ኹለፋኦች የወቅፍ ሚና

አቡበክር መካ የነበራቸዉን ቤት ወቅፍ አድርገዋል። ሁለተኛው ኸሊፋ ኡዑመር ኢብኑል ኸጧብም በተመለከተ፤ ቡኻሪና ሙስሊም ከዓብድላህ ኢብኑ ዑመር በዘገቡት ሐዲስ ይህን
እናገኛለን፡፡

‫ يا رسول هللا إني‬:‫ أصاب عمر أرضا بخيبر فأتى النبي صلى هللا عليه وسلم يستأمره فيها فقال‬:‫عن عبد هللا بن عمر رضي هللا عنهما قال‬
‫ فتصدق بها‬:‫ "إن شئت حبست أصلها وتصدقت بها" قال‬:‫أصبت أرضا بخيبر لم أصب ماال قط هو أنفس عندي منه فما تأمرني به؟ فقال‬
‫ فتصدق عمر في الفقراء وفي القربى وفي الرقاب وفي سبيل هللا وابن السبيل والضيف‬:‫ قال‬,‫غير أنه ال يباع أصلها وال يوهب وال يورث‬
.]‫" والترمذي‬1632" ‫" ومسلم‬2737" ‫" [البخاري‬

ዑመር ኢብኑል ኸጣብ በኸይበር መሬት አገኙና ነቢዩን ሊያማክሩ እርሳቸው ዘንድ በመምጣት እንዲህ አሏቸው «እኔ ኸይበር ውስጥ ያገኘሁት
መሬት እስከዛሬ ድረስ ካገኘኋቸው ንብረቶች ሁሉ ውዱ ነው፡፡ ምን ትመክረኛለህ» አሏቸው። የአላህ መልዕክተኛም «ፍቃድህ ከሆነ ንብረትነቱን
አግድና ሰደቃ አድርግው ይህን ካደረግክ ደግሞ ንብርረቱ አይገዛም፣ አይሸጥም፣ አይወረስም፣ በስጦታም አይሰጥም፡፡» ዑመርም ሰደቃ አደረጉት፡፡
ለቅርብ ዘመዶች፣ ለችግረኞች፣ በባርነት ስር ላሉ ሰዎች፣ ለደካሞች፣ ለመንገደኞችና በአላህ መንገድ ላይ ለሚታገሉ ሰዎች እንዲውል አደረጉ፡፡» (ቡኻሪይ
ሙስሊም ዘግበዉታል እንዲሁም ቲርሚዚይ)

ኡመር በኸሊፋነታቸው ዘመን ይህንን ወቅፍ ለሙሀጅሮችና አንሳሮች ይፋ አድርገው ሲያስመሰክሯቸው ብዙ ሰሀቦች ተበረታቱ፣ ብዙ ንብረቶቻቸዉንም
ለመልካም ተግባር ወቅፍ ሰጡ።
ሶስተኛው ኸሊፋ ኡስማን ኢብኑ ዓፋንም ብዙ የወቅፍ ታሪክ አላቸው፤ በኸይበር የነበራቸውን ንብረት ሁሉ ለልጆቻቸው ወቅፍ አድርገዋል። እንደዚሁ በመዲና የታወቀዉን እና ‘ቢዕር
ሮማ’ የተባለዉን ኩሬ በአላህ መንገድ ላይ እንዲዉል ሰጥተዋል ።
አራተኛው ኸሊፋ ዓሊይ ኢብኑ አቢጧሊብ በየንቡዕ የነበሯቸዉን ምንጮች የሚገኙባቸው ዓይን አቢ ነይዘር እና ቡገይባህ የተባሉ ሁለት ትናንሽ ይዞታዎችን ወቅፍ አድርገዋል። አስማዕ
ቢንት አቡበክር፣ ዙበይር፣ ሀኪም ኢብኑ ሂዛም፣ አዒሻ፣ ፋጢማ፣ አምር ኢብኑል ዓስ፣ አብድላህ ኢብኑ ዙበይር፣ ጃቢር ኢብኑ አብድላህና ሌሎችም ወቅፍ እንዳደረጉ ይታወቃል፡፡
ኢብኒ ቁዳማህ አል መቅዲሲይ አል-ሙግኒ በተባለው መፅሃፋቸው ቅፅ 8 ገፅ 185 እንዳሰፈሩት ታላቁ ሰሀብይ ጃቢር ኢብኑ ዓብድላህ እንዲህ ብለዋል፡፡ «ከነቢዩ ባልደረቦች
መካከል አንዳቸውም ሳይቀሩ ሁሉም እንደ አቅማቸው ወቅፍ ያደርጉ ነበር» በሌላ ዘገባም እንዲህ ብለዋል «ከነብዩ ባልደረቦች ከሙሃጅሮችም ይሁን ከአንሷሮች
ንብረት ኖሮት ዘውታሪ የሆነ ሰደቃ በማድረግ ያላገደ (ወቅፍ ያላደረገ) አላውቅም» ::

አል ኢማሙ ሻፊዒይ እንዲህ ብለዋል፡፡«ከአንሣሮች ሰማንያ የሚሆኑት ከንብረታቸው ወቅፍ አድርገዋል። አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው» ። ማንኛዉም
ሙስሊም መልዕክተኛዉን ባልደረቦቻቸዉንና ታላላቅ ሙስሊሞችን አርዓያ በማድረግ ለወቅፍ ስራ ሊነሳሳ ይገባል። ነገር ግን ኢኽላስ የሌለበት መልካም ስራ
ተቀባይነት ስለሌለው ወቅፍ የሚሰጥ ሰው በቅድሚያ ኢኽላሱን ሊመረምር እና ሊያስተካክል ይገባዋል። አላህ ዘንድ ልይዩልኝ እና ለይስሙልኝ የተሰራ ስራ ሁሉ ዋጋ
የለዉም።

የወቅፍ መንገዶች
ከሰደቃዎች ሁሉ የበለጠው ግን ለሰዎች የበለጠ ሊጠቅም የሚችልና ረጅም ዘመን ሊቆይ የሚችል ነው። ገቢ ካለዉና እያደገ ሊሎች ወቅፎችን የሚፈጥር ከሆነም የተመረጠ ነው።
ለሰዎች የሚያስፈልጉ የወቅፍ አይነቶች ከጊዜ እና ከቦታ አንፃር ይለያያሉ። በሸሪዓ መሸጥና መለወጥ የሚፈቀድ እና ጥቅም ላይ መዋል የሚችል ሁሉ ወቅፍ መሆን ይችላል። እንደ መሬት
እና ግንባታ ቋሚ ወይም እንደ መጓጓዣ ተንቀሳቃሽ የሆኑ ንብረቶች ሁሉ ወቅፍ ሊሆኑ ይችላሉ። የወቅፍ አላማ ደሀዎችን መርዳት ብቻ አይደለም። ተከታዮቹ እንደምሳሌ የቀረቡ
የወቅፍ አይነቶች ናቸው።

መስጊዶችንና የዒባዳ ቦታዎችን ማስፋፋት እና መንከባከብ፣ የኢስላማዊ ዕዉቀትን የሚያስፋፉ ተቋሞችን መገንባት በመጽሀፍት ማደራጀት፤ ተማሪዎች በነጻ እንዲማሩባቸው
የመድረሳዎችን ወጪ መሸፈን፣ የዲን ተማሪዎችንና አስተማሪዎችን መደገፍ፣ኢስላማዊ ህትመቶችን ማገዝና ማበረታታት፣የቁርአን ታህፊዝ ማዕከላትን ማቋቋም፣ ተዉሂድ እና ሱናን
የሚያስፋፉ መፅሀፍትን እና ካሴቶችን ማባዛት፣ ችግረኞችን የሚያገለግሉ የጤና ተቋማትን መክፈት፣ የዉሀ ጉድጓዶችን መቆፈር፣ የየቲሞች እና የአዛዉንቶች ማረፍያዎችን ማቋቋም
ወዘተ…

ውድ አንባቢ! የኸይር በሮች ብዙ ናቸው። በዚህ ፈተና በበዛበት ዘመን መልካም ነገር ትተው የሚያልፉ የታደሉ ናቸው። የሀገራችንን የወቅፍ ታሪክ ስናይ ከጥንት ጀምሮ የነበሩ
ሙስሊሞች ብዙ ገድል ነበራቸው። የአንዋር መስጊድ ወቅፎች ታሪክ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የወቅፍ ሁኔታ እጅጉን እየተዳከመ መጥቷል። የአላህን ዉዴታ
ከሚያገኙት ሰዎች ያደርገን ዘንድ ሁላችንም የተቻለንን እናድርግ። ጀነት ውድ ናትና ውድ ዋጋ እንክፈል።

አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ

ዳሩ–ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክት

በታሪካዊው የወቅፍ ፕሮጀክት ላይ አሻራዎን ያኑሩ!


በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር አማካኝነት በመካሄድ ላይ ያሉ ህጋዊና ዘርፈ ብዙ የዳዕዋ እንቅስቃሴዎችን በቋሚነት የሚደጉመውን ዳሩ–ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክት ተባብረን
እውን እናድርግ!

የፕሮጀክቱ ቦታ፦ አዲስ አበባ


ተመን፦ 100 ሚልየን
አላማ፦ በኪራይ ገቢ ዳዕዋን በቋሚነት መደገፍ

የወቅፉ ገቢ ለምን ይውላል?


√ ነሲሓ ቲቪ
√ ነሲሓ መስጂድና መድረሳ
√ ዳሩል ሀዲስ ኢስላማዊ ኮሌጅ
√ የቁርአን ሒፍዝ ሀለቃት
√ ኢልም ተኮር ኮርሶች
√ ቃፊላ የዳዕዋ ጉዞዎች
√ ነሲሓ በራሪ ወረቀቶች
እና ሌሎችም አንፀባራቂ የዳዕዋ ስራዎች

َ َ َ َ ُ ‫ۚ َ َ ۡ ُ ۟ ه َ َ ۡ ً َ َ ࣰ ۚ َ َ ُ َ ِّ ُ ۟ َ ُ ُ ِّ ۡ َ ۡ َ ُ ُ َ ه‬
‫َّلل ه َو خ ۡ ۡ ࣰیا َوأ ۡعظ َم أ ۡج ࣰرا‬
‫وأق ِرضوا ٱَّلل قرضا حسنا وما تقدموا أِلنف أسكم من خ ۡ ࣲی ت أجدوه أعند ٱ أ‬

[ለአላህም መልካም ብደርን አበድሩ፡፡ ከመልካም ሥራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ እርሱ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ኾኖ አላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ] ሙዘሚል 20

ድጋፍዎን በ sms ይምረጡ

በቤተሰብ ስም
50,000 ብር ለመነየት 1 ቁጥር

ለአባትና ለእናት ስም ወቅፍ


20,000 ብር ለመነየት 2 ቁጥር

የግለሰብ ወቅፍ
10,000 ብር ለመነየት 3 ቁጥር

በልጆች ስም ወቅፍ
5,000 ብር ለመነየት 4 ቁጥር

አሁኑኑ ኒያዎን ለማሳወቅ ወደ +251972757575 መልእክት ይላኩ!


ኒያዎን ለወቅፍ አካውንት ገቢ ለማድረግ
የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000337985328
ኢብኑ መሰኡድ ኢስላሚክ ሴንተር
T.me/Merkezuna

You might also like