You are on page 1of 15

ኢስላማዊ አስተዳደግ

ዝግጅት፡የአፍሪካ አካዳሚ ምሁራን ስብስብ

የመጀመሪያ እትም - መስከረም 2014

1
2
3
4
የአፍሪካ አካዳሚ አስተዳደር መግቢያ

ምስጋና ለአላህ ይሁን ፣ ሰለዋት እና ሰላም ሰዎችን መልካም አስተማሪ በሆኑት በመሐመድ ፣ በቤተሰቦቻ
ቸው እና በባልደረቦቻቸው ሁሉ ላይ ይሁን። ከዛም በመቀጠል የሸሪዓ ትምህርት አላህን ለማሰደሰት እና ወደ
ከፍተኛ የጀነት ደረጃዎች የሚያደርስ መንገድ ነው ፣ እናም እሱ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻው ዓለም ወደ
መልካም ነገር ሁሉ የሚያደርስ ነው ፣ በተጨማሪ የሸሪዐ ትምህርት የግለሰብ እና የህብረተሰብ ደህንነት ጎዳና
ነው ፣ እና በእሱ ማህበረሰቦች ክብራቸውን እና መሪነታቸውን ያገኛሉ ፣ እናም ለእውቀት ፈላጊዎች ጥሩ ክብር
ነው። አላህ ሱ.ወ እንዲህ ይላል- {አላህ በመካከላችሁ ያመኑትን እና እውቀትን የተሰጡትን ከፍ ያደርጋል ፣
አላህም የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ጌታ ነው} [አል- ሙጃደላ 11] እናም እንዲህ ብሏል – {አላህ
በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲኾን ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ መኾኑን መሰከረ። መላእክቶችና
የእውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ)።} (ሱረቱል ዒምራን፡18)

የእውቀት ደረጃ አላህ ዘንድ ላቅ ያለ ስፍራ ስላለው አላህ ነቢዩን ሰ.ወ እውቀት እንዲጨምርላቸው እንዲጠይ
ቁት አዘዛቸው ። አላህ ሱ.ወ እንዲህ አለ ( “ጌታዬ እውቀት ጨምርልኝ”በል)። የእውቀትንና ባለቤቶቿን ደረጃ
የሚያወሱ በርካታ ቁርአናዊ እና ሀዲሳዊ ማስረጃዎች መጥተዋል ። ነብዩ ሰ ዐወ እንዲህ ብለዋል (እውቀትን
ፍለጋ መንገድን የገባ ሰው አላህ ወደ ጀነት የሚወስደውን መንገድ ያቀልለታል) ሙስሊም ዘግበውታል

ለዚያም ነው (አፍሪካ አካዳሚ) አረብኛ ተናጋሪዎች ላልሆኑ ለአፍሪካ ማህበረሰቦች የተዘጋጀ በተለያዩ ቋንቋዎ
ቻቸው የሙስሊሞችን የእስልምና ዕውቀት ፍላጎት ለማሟላት እና የእውቀትን ጥያቄ ለማመቻቸት የመጣ በስራ
ለተጠመዱ እና ብዙ ትርፍ ሰዓት ላላቸው በኢንተርኔት አማካይነት የመጀመሪያው የኤሌክትሮኒክስ አካዳሚ
ይዞ የመጣው ። የአካዳሚው መርሃ ግብር የሚመለከተው በቀደምት ሰዎች ግንዛቤ እና እምነት ላይ በመመ
ርኮዝ ከቁርአን እና ከእውነተኛ ሱና የተገኘውን የሸሪዓ ትምህርት ማስተማር ነው። ሥርዓተ ትምህርቱ ከሸሪዓ
ተማሪዎች ጋር ተመጣጣኝ በሆነ ደረጃ የተቋቋመ ሲሆን በቀላልነት እና ሙስሊሙ የሚያስፈልገውን ዕውቀት
የሰበሰበ ፣ እና የአመለካከት ልዩነቶችን ከማስፋፋት የራቀ ፣ እና በጥሩ ቴክኒካዊ እና በተለያዩ መንገዶች የተ
ነደፈ ነው። ለተማሪዎች አቀባበልን ለማመቻቸት እና ከጊዜው ጋር ለመራመድ የኮርሶች ዲዛይኖች የእውቀት
እድገት እና የዘመናዊ ትምህርት ዘዴዎች የተዘጋጀ ነው።

ይህ የትምህርት ስርጭት ወደ እውቀት መርከብ ለመግባት ውድ የሆነች እድል ናት ። ይህም አንድ ሙስሊም
መዳኛውና ህይወቱ እንዲሁም በዱንያም ሆነ በአኺራ ከፍ ያለ ደረጃ ማግኛ የሆነውን እውቀት የህይወቱ
መመሪያ እስኪያረግ ድረስ ያዘጋጀነው ፕሮግራም ነው። አላህ እንዲህ ብሏል {አላህ በመካከላችሁ ያመኑትን
እና እውቀትን የተሰጡትን ከፍ ያደርጋል ፣ አላህም የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ጌታ ነው} (አልሙጃ
ዲላ 11)
አላህን ለሁላችንም መልካሙን እንዲገጥመን የሸሪዐ እውቀትን በማወቅ እና ተጠቃሚ በመሆን በሱም ላይ
ስራችንን ፍፁም ለአላህ እንድናረግ እንዲያግዘን እማፀነዋለው።

የአፍሪካ አካዳሚ የበላይ ጠባቂ

5
6
የአፍሪካ አካዳሚ
ተከታታይ ትምህርቶች

ክፍል አንድ
7
8
1
መብትና ግዴታዎች

9
10
ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ አላህ ይገባው፣ የአላህ ሶላትና ሰላም ከነቢያት ሁሉ በላጭ በሆኑት ነቢያችን ሙሐመድ፣ በቤተሠቦቻቸው
እና ባልደረቦቻቸው ሁሉ ላይ ይስፈን። ከዚህ በኋላ፦

አላህ  የሠውን ልጅ በተፈጥሮው ከሠዎች ጋር የመቀላቀል ፍላጎት የተፀናወተውና ግብረገብ አድርጎ የፈጠረው ሲሆን ይህ
ተፈጥሯዊ ዝንባሌም ትውውቅንና የተለያዩ ግንኙነቶችን ያስገኛል። ልዑል የሆነው ጌታ እንዲህ ብሏል፦
ُ َ َ َ َ َ َ َ ً ُ ُ ْ ُ َ ْ َ َ َ ٰ َ ُ َ َ َ ّ ُ َ ْ َ َ َّ ُ َّ َ ُّ َ َ
‫ارفوا‬ ‫يا أيها انلاس إِنا خلقناكم مِن ذك ٍر وأنث وجعلناكم شعوبا وقبائِل لِ ع‬ [አልሑጁራት (13)]

“እናንተ ሰዎች ሆይ እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፤ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፤”

ይህን ከሠዎች ጋር መቀላቀልም እያንዳንዱ ሠው ከሌላው ጋር ከሚኖረው ግንኙነት አንፃር እንደ ቅርበትና ርቀቱ ደረጃ የተለያዩ
መብትና ግዴታዎች ይከተሉታል። ለወላጆች የሚኖረው መብት ለትዳር አጋር ከሚኖረው መብት ይለያል፣ ለሙስሊም የሚኖ
ረው መብት ሙስሊም ላልሆነው ከሚኖረው መብት ይለያል፣ ልክ እንደዚሁ የሠው ልጅ በዚህ ረድፍ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ
እያንዳንዱን ባለመብት መብቱን መስጠት ይጠበቅበታል።

በሠልማን  ሐዲስ ውስጥ እንደተገለፀው አቡ ደርዳእ የቤተሠቦቹን መብት ሳይጠብቅ በአምልኮ ተጠምዶ ሳለ : (ሰለማን ለአቢ
ደርዳእ  እንዲህ አለው)

‫ فأتَى النب َيّ صَلَ ّى‬،ُ ‫ح َ ّقه‬


َ ‫َق‬
ٍ ّ ‫ل ذِي ح‬ ّ َ ُ ‫ فأعْطِ ك‬،‫ح ً ّقا‬
َ ‫ك‬ َ ِ ‫ ول ِأَ ه ْل‬،‫ح ً ّقا‬
َ ْ ‫ك عَلَي‬ َ ‫ك‬
َ ْ ‫ك عَلَي‬ َ ‫س‬ ِ ‫ ولِن َ ْف‬،‫ح ً ّقا‬
َ ‫ك‬
َ ْ ‫ك عَلَي‬ ّ َ ‫(إ‬
َ ِّ ‫ن ل ِر َب‬
َ :َ ‫ل النب ُيّ صَلَ ّى الله ُ عليه وس َل ّم‬
)ُ‫صد َقَ سَل ْمان‬ َ ‫ فقا‬،‫ك له‬ َ ‫الله ُ عليه وس َل ّم َ فَذَك َر َ ذل‬
ቡኻሪ ዘግበውታል።

“ጌታህ በአንተ ላይ መብት አለው፣ ነፍስህ በአንተ ላይ መብት አላት፣ ቤተሰቦችህ በአንተ ላይ መብት አላቸው፤ ሁሉንም የመብት
ባለቤት መብቱን ስጥ! ነቢዩም  መጡ፣ እሱም ይህንን (ንግግሬን) አወሳላቸው፣ ነቢዩ  “ሠልማን እውነቱን ነው።” አሉ።

የሠው ልጅ እነዚህን መብቶች ለባለቤቶቻቸው ለማድረስ የሚችለው ጥልቅ እውቀት ሲኖረውና መብቶቹ እርስ በርሳቸው በሚ
ጋጩበት ጊዜ የትኛው እንደሚቀድም እና የትኛው እንደሚከተል የእያንዳንዱን መብቶች ደረጃ መለየት የሚያስችል ዕውቀት
ሲኖረው ነው።

በዚህ ክፍልም አንድ ሙስሊም የሚያስፈልጉትን አንገብጋቢ መብቶች ለማብራራትና ከነዚህ ጋር የሚያያዙ ጉዳዮች ይዳሠሳሉ።
የችሮታ ባለቤት አላህ ነው!

11
የአላህ በባሪያዎች ላይ ያለው መብት
አላህ በባሪያዎቹ ላይ ያለውን መብት ማወቅ ከታላላቅ ግዴታዎች መካከል ዋናውና ትልቁ ሲሆን ይኸውም የአላህ መብት
ከሱ ውጭ ካሉት ሁሉ መብቶች የሚቀደም በመሆኑ ነው። የእሱን  መብት መጠበቅ የሠው ልጅ የተፈጠረለትን ዓላማ
የመጨረሻ እርከን መወጣት ነው።

አላህ በባሪያው ላይ ያለው መብት እሱን በብቸኝነት በመገዛትና በእርሱ ምንንም ከማጋራት በመራቅ ላይ የተገደበ ነው።
َ ُ ْ ُ َ َ َ َّ ُُْ َ
የልቅና ባለቤት የሆነው ጌታ እንዲህ ብሏል፦ ۖ ‫شكوا بِهِ شيْ ًئا‬
ِ ‫[ واعبدوا الل ول ت‬አን_ኒሳእ (36)]
“እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ፡፡”
َ َۡ ُ ُ َ َ َ َ َّ َ َ
‫ـم ٱلۡرض‬ ‫ ٱلِي جعــل لكـ‬٢١ ‫ـم ت َّتقــون‬
َ ُ َ ۡ ُ َّ َ َ ۡ ُ ۡ َ
‫ـن ِمــن قبل ِكــم لعلكـ‬ َ ‫ـم َو َّٱلِيـ‬ ُ ََ َ
ۡ ‫كـ‬ َّ ُ ُ َّ َ ْ ُ ُ ۡ ُ َّ
‫ـم ٱلِي خلق‬ ‫يأ ُّي َهــا ٱنلــاس ٱعبــدوا ربكـ‬ ٰٓ
َ ٗ َ َّ ْ ُ ۡ َ َ َ ُ َّ ٗ ۡ َّ َ ۡ َ َ ٓ ٓ َ َ ٓ ٓ ٗ
ُ ‫ـدادا َوأ‬
ۡ ‫نتـ‬
‫ـم‬ َ ‫ـم فــا ت َعلــوا ِلِ أنـ‬
ۖ ۡ ‫ت رِزقــا لكـ‬
َ ‫ـن ٱثل َمـ‬
ِ ٰ ‫ـر‬ َ ‫ـرج بـهِۦ ِمـ‬ َ ‫ـماءِ َمــا ٗء فأخـ‬ َّ ‫ـن‬
َ ‫ٱلسـ‬ َ ‫ـما َء ب َنــا ٗء َوأنـ‬
َ ‫ـزل ِمـ‬ َّ ‫ف َِرٰشــا َو‬
َ ‫ٱلسـ‬
ِ ِ
َ َ َ
[አል_በቀራ (21-22)] ‫ت ۡعل ُمون‬
“እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠ
ነቀቁ ይከጀላልና፡፡ (እርሱ) ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም ጣራ ያደረገ ነው፤ ከሰማይም (ከደመና) ውሃን ያወረደ
በርሱም ከፍሬዎች ለናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው፡፡ እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድ
ርጉ፡፡”

ኢብኑ ከሲር ከላይ ባለው የቁርአን አንቀጽ ዙሪያ የሚከተለውን ጭብጥ የያዘ ንግግር ተናግረዋል፦ “አላህ  የአምላክነቱን
ብቸኝነት አብራራ፥ እሱም ልቅና ይገባውና ካለመኖር በማስገኘት፣ በግልጽና ሚስጥራዊ ጸጋዎቹ በማዳረስ ባሮቹን በጸጋ
ዎቹ ያጣቀመ ነው። ... ለባሪያዎቹ ሲሳዮችን ለጋሽ በመሆኑ፣ እሱም ፈጣሪው፣ መጋቢው፣ የዚች አለምና ነዋሪዎቿ ተቆጣ
ጣሪያቸውና መጋቢያቸው በመሆኑ ምንም አጋር የሌለው ሲሆን በብቸኝነት ሊመለክ ይገባል። ይህን በሚመለከት እንዲህ
ብሏል፦ “እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ፡፡”
ْ ُ َْ َ ََ
ُ ُ ْ َّ َ ْ ‫ال َّن َو‬
በድጋሜ ልዑሉ ጌታ እንዲህ ብሏል፦ ِ ‫النس إِل ِلَعبد‬
‫ون‬ ِ ِ ‫[ وما خلقت‬አዝ_ዛሪያት (56)]

“ጋኔንንና ሰውን ሊገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም። ”


ከሙዐዝ ብን ጀበል በቡኻሪና ሙስሊም እንደተዘገበው እንዲህ ብሏል፦
‫ن ح ََقّ الله ِ علَى‬ َ : ُ‫ قُلت‬:َ‫ ت َ ْدرِي ما ح َُقّ الله ِ علَى الع ِبادِ؟ وما ح َُقّ الع ِبادِ علَى اللهِ؟ قال‬،ُ ‫( يا م ُعاذ‬
ّ َ ‫ فإ‬:َ‫ قال‬،ُ ‫الل ّه ُ ور َسولُه ُ أع ْلَم‬
: ُ‫ قُلت‬:َ‫ قال‬،‫ل أ ْن لا يُع َ ّذِبَ م َن لا يُشْرِك ُ به شيئًا‬ ّ َ ِ ‫ وح ََقّ الع ِبادِ علَى الله‬،‫ ولا يُشْرِكُوا به شيئًا‬،َ‫الل ّه‬
ّ َ ‫عز وج‬ َ ‫الع ِبادِ أ ْن يَعْبُد ُوا‬
) .‫ لا تُبَش ِّرْه ُ ْم فَيَت ّكِلُوا‬:َ‫ قال‬،‫اس‬ َ ُ ‫ أفَلا ُأبَش ِ ّر‬،ِ‫ل الله‬
َ ّ ‫الن‬ َ ‫يا ر َسو‬

“እኔ ከነቢዩ ጋር በአህያ ላይ ተፈናጥጨ እያለ እንዲህ አሉኝ፦ “አንተ ሙዓዝ ሆይ! አላህ በባሪያዎቹ ላይ ያለውን መብት
ታውቃለህን?” አሉ። እኔም አላህና መልዕክተኛው ያውቃሉ አልኳቸው። እሳቸውም፦ “አላህ በባሪያዎቹ ላይ ያለው መብት
ሊገዙትና በእሱ ምንም ላያጋሩበት ነው። ባሪያዎቹ ደግሞ በአላህ ላይ ያላቸው መብት በእሱ ምንንም ያላጋራን ላይቀጣ
ነው” አሉ። እኔም የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰዎችን ላበስራቸውን? አልኳቸው፤ እሳቸውም “(በስራቸው) እንዳይመኩ አታ
በስራቸው አሉ።”

12
በመሰረቱ ዒባዳ ወይም መገዛት (አምልኮ) የሚለው ቃል ዝቅ ማለት ወይም መገራት ማለት ሲሆን በአረቦች ተለምዶ ተገዢ
መንገድ፣ ተገዢ ግመል ሲባል የተገራ ለማለት ነው።
ትዕዛዝ የተላለፈበት ዒባዳ (አምልኮ) ማለት ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንዳሉት “ግልፅም ሆነ ድብቅ አላህ የሚወ
ዳቸውን ንግግርም ሆነ ተግባርን የሚያጠቃልል ስያሜ ነው።”

አላህ በባሪያዎቹ ላይ ያለው መብት የሚከተለውን ይመስላሉ


በእሱ  ማመን: ልዑሉ ጌታ እንዲህ ብሏል፦
ْ َ‫نف ُقوا ل َ ُه ْم أ‬
ٌ ‫ج ٌر َكب‬ َ ََ ْ ُ َ ‫ني فِيهِ ۖ فَ َّال‬
َ ‫خلَف‬
ْ َ ْ ُّ ُ َ َ َ ُ َ َّ
[ሡረቱል ሀዲድ (7)] ‫ري‬ِ ‫آم ُنوا مِنكم وأ‬
َ ‫ِين‬ ِ ‫آم ُِنوا بِاللِ َو َر ُس‬
ِ ‫ولِ َوأنفِقوا م َِّما جعلكم مست‬
“በአላህና በመልክተኛው እመኑ፤ (አላህ) በርሱ ተተኪዎች ባደረጋችሁም ገንዘብ ለግሱ፤ እነዚያም ከናንተ ውስጥ ያመኑትና
የለገሱት ለነርሱ ታላቅ ምንዳ አልላቸው።”

ጥራት የተገባውንና ምንም አጋር የሌለውን ጌታ በብቸኝነት መገዛት፣ ከእሱ ውጭ ያለን መገዛት እርግፍ አድርጎ መተው
ْ ُ َْ َ ََ
ُ ُ ْ َّ َ ْ ‫ال َّن َو‬
ነው። ልዑሉ ጌታ እንዲህ ብሏል፦ ‫ون‬ِ ‫النس إِل ِلَعبد‬
ِ ِ ‫[ وما خلقت‬አዝ_ዛሪያት (56)]
“ጋኔንንና ሰውን ሊገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም። ” የአላህ መልዕክተኛም  እንዲህ ብለዋል፦
) ‫الل ّه ِ علَى الع ِبَادِ أ ْن يَعْبُد ُوه ُ ول َا يُشْرِكُوا به شيئًا‬
َ ّ‫[ ( ح َُق‬ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

ጥራት የተገባውንና ምንም አጋር የሌለውን ጌታ በብቸኝነት መገዛት፣ ከእሱ ውጭ ያለን መገዛት እርግፍ አድርጎ መተው
ነው። ልዑሉ ጌታ እንዲህ ብሏል፦

በቁርኣንና በሐዲስ እንደወረደ እና ደጋጎቹ ሠለፎች (ቀደምቶች) በተረዱት መሠረት በስሞቹ እና በባህሪዎቹ ማመን:
ይኸውም አላህ  ከእሱ ውጭ ካለ ሁሉ ከማንም ይበልጥ ስለዛቱ፣ ስሞቹና ባህሪዎቹ የሚያውቅ በመሆኑ ነው። ልዑሉ
ْ َ ُ ُ ََ
ጌታ እንድህ አለ፦ ‫ِيطون بِهِ عِل ًما‬ ‫[ ول ي‬ጣሃ ( 110)] “በርሱም ዕውቀትን አያካብቡም፤ (አያውቁም)።”

ከእምነት ግዴታዎች መሃል  እሱን የሚመስል ምንም አለመኖሩን ማመን ይገኝበታል። ልዑሉ ጌታ እንድህ አለ፦
ُ ‫يع ْالَ ِص‬
‫ري‬ ُ ‫الس ِم‬ ْ َ ِ‫لَيْ َس َك ِمثْلِه‬
َّ ‫ش ٌء ۖ َو ُه َو‬ “እሱን የሚመስለው ምንም ነገር የለም፤ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው።”
[ሹራ (11)]

َ ُ َْ ْ ُ َ َ
ً َ‫ون ِ َّلِ َوق‬
አላህን  እጅግ በጣም ማላቅና ማክበር፦ ልዑሉጌታ እንድህ ብሏል ‫ارا‬ ‫ما لكم ال ترج‬ [ኑህ (13)]
“ለአላህ ልቅናን የማትሹት ለናንተ ምን አላችሁ።” ለአላህ ልቅናውን አትፈሩምን? አላህ እናንተ ዘንድ ትልቅ ግምት የለው
ምን? ማለት ነው።

13

You might also like