Professional Documents
Culture Documents
ማመሳሰያዎችን ማጋለጥ
ማመሳሰያዎችን ማጋለጥ
ከሽፉ ሹቡሐት
(ማመሳሰያዎችን ማጋለጥ)
ክፍል አንድ
ተውሒድ እርሱ፡ አላህን በአምልኮ ብቸኛ ማድረግ ነው፡፡ እርሱ አላህ መልእክተኞችን ወደባሮቹ
የላከበት እምነት ነው፡፡
ክፍል ሁለት
የአላህ መልእክተኛ የተጋደሏቸው አጋሪዎች የጌትነት የተውሂድ ክፍልን ማረጋገጣቸውና ይህም
በአምልኮ ከማጋራት እንደማያወጣቸው (ሙስሊም እንደማያደርጋቸው) የቀረቡ ማስረጀዎች
የሚብራራበት ክፍል
አላህ እንደተናገረው፡
َُ ْ َ َّ َ َ َّ ْ َ ِّ ون ل َ ُهم ب
َ ُ َ َْ َ ُ َ ُ ْ َ َ َّ َ َ ْ ُ َ ْ َ ُ َ
َش ٍء إَِّل ك َبا ِّس ِّط كفيْهِّ إَِّل ال َماء ِِّلَبْلغ جيب
ِّ ت س ي َل ِّ ه ِّ ن و د ِّن
م ون ﴿َل دعوة اْل ِّق واَّلِّين يدع
َ َ َّ َ َْ ُ ُ َ
﴾ين إَِّل ِِّف ضال ٍل فاهُ َو َما ه َو ب ِّ َبال ِّ ِّغهِّ َو َما د ََعء الَكف ِِّّر
4/37
“ለእርሱ (ለአላህ) የእውነት መጥሪያ አለው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የሚግገዟቸው (ጣዖታት)
ለእነርሱ በምንም አይመልሱላቸውም” (አር’ረዕድ፡ 14)
ክፍል ሶስት
ተውሂደል ዒባዳ የ “ላኢላሃ ኢልለሏህ” ትርጉም መሆኑና
በረሡል ዘመን የነበሩት ከሀዲዎች ሙስሊም ነን ብለው ከሚሞግቱት በበለጠ ሁኔታ ትርጉሟን
እንደሚያውቁ የሚብራራበት ክፍል
“ኢላህ” የሚለው ከእነርሱ ዘንድ ለእነዚህ ነገሮች የሚታሰብ ነው -መላኢካም ይሁን ወይም
ነብይ ወይም ወልይ ወይም ዛፍ ወይም ቀብር ወይም ጅን፡፡ “ኢላህ” በሚለው ፈጣሪ ፣ መጋቢ
እና አስተናባሪ የሚለውን አልፈለጉበትም፡፡ ከዚህ በፊት እንዳስቀደምኩልህ እነርሱ ይህ ለአላህ
ብቻ መሆኑን ያውቃሉ፡፡ “ኢላህ” ሲባል የፈለጉት “ሰይ̕ይድ” በሚል የዘመናችን አጋሪዎች
የፈለጉበትን ነው፡፡ ነብዩ ﷺወደተውሂድ ቃል ሊጠሯቸው መጡ፡፡ እርሷም (ላኢላሃ ኢልለሏህ)
ናት፡፡
5/37
እንዴውም እርሱ ይህ (መመስከር) አንዳች ከትርጉሟ በልብ ምንም አይነት እምነት ሳይኖር
በሀርፎቿ ብቻ መናገር ነው ብሎ ይገምታል፡፡ ከእነርሱ ዘንድ ጥልቅ እውቀት ያለው የእርሷ
ትርጉም ፡ “ፈጣሪ የለም ፣ መጋቢ የለም ፣ ነገርን የሚያስተናብር የለም አላህ እንጅ” ብሎ
ይገምታል (ላኢላሃ ኢልለሏህ ያለውን በተውሂደ ሩቡብያ ብቻ ይፈስረዋል) ፡፡ በ“ላኢሃ
ኢልለሏህ” ትርጉም በጣም ማህይም የሆኑት ከሀዲዎች በእውቀት የበለጡት ሰው ከእርሱ ዘንድ
ምንም መልካም የለውም!
ክፍል አራት
በእርሱ ላይ አላህ ተውሒድን ማጎናጸፉ በእርሱ መደሰትን እና እርሱን ከመንነጠቅ መፍራትን
የሚያመጣ መሆኑን ሙእሚን ማወቅ እንዳለበት የሚያረጋግጥ ክፍል
(1). ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አልዑሰይሚን “ከሽፍ ሹቡሀ” የተባለውን የሸይኽ ሙሐመድ ብን አብዱልወሀብ
መጽሐፍ ትንታኔ ከሰጡበት ኪታባቸው ገጽ 46 ላይ የሚከተለውን ተናግረዋል፡
በዚህ የመጽሐፉ አዘጋጅ ንግግር ላይ የምንሰጠው ማብራሪያ የሚከተለው ነው፡
ሸይኽ ለአለማወቅ ምክንያት አይሰጥም የሚል አቋም አላቸው የሚል ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ነገር ግን ትምህርትን
በመተው ሟጓደል ካልኖረ በቀር፡፡ ለምሳሌ፡ ሀቅን ይሰማል ወደርሱ ፊቱን አያዞርም ፣ አይማርም፡፡ ይህ ባለማወቁ
ምክንያት አይስሰጠውም፡፡ ይህን ጉዳይ ከሸይኽ የማልጠረጥርበት ምክንያት ባለማወቅ ምክንያት መስጠቱን የሚጠቁም
የእርሱ ሌላ ንግግር ስላለው ነው፡፡
ሸይኹ -በእርሱ ላይ ስለሚጋደሉበት ነገር ፣ እንዲሁም በእርሱ ላይ ግለሰብን ስለሚያከፍሩበት ነገር ተጠየቀ
የሚከተለውንም ምላሽ ሰጠ፡-
የኢስላም መሰረቶች አምስት ናቸው፡፡ የመጀመሪያዋ ሁለቱ ምስክሮች ናቸው፡፡ ከዚያም አራቱ ማዕዘናቶች ናቸው፡፡
አራቱን አረጋግጦ በቸልተኝነት ቢተዋት በተግባሯ ላይ ብንጋደለውም በመተው አናከፍረውም፡፡ ያለምንም ማስተባበል
በቸልተኛነት ቢተዋቸው ይከፍራል አይከፍርም በሚለው ዑለሞች ተለያይተዋል፡፡ ሁሉም ዑለሞች በተስማሙበት እንጅ
አናከፍርም፡፡ እርሱም ሁለቱ የምስክር ቃሎች ናቸው፡፡ ካሳወቅነው በኋላ አውቆ ከተቃወመ እናከፍረዋለን፡፡…
وصلى هللا على محمد وآله وصحبه وسلم
7/37
በተለይም የሙሳ ህዝቦች ደጋግ ፣ አዋቂ ከመሆናቸው ጋር የሚከተለውን ተናጋሪ ሆነው
ወደርሱ እንደመጡት አላህ በቁርኣኑ የተረከውን ካሳወቀህ
ٌ َ َ ً َ َ َّ َ ْ
﴾ـها ك َما ل ُه ْم آل َِّهة ﴿اجعل َّلا إِّل
“ሙሳ ሆይ፡- ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዳላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን” (አል’አዕራፍ፡
138)
ክፍል አምስት
ለነብያቶቹ እንዲሁም ለወልዮቹ ከሰውም ይሁን ከጅን ጠላቶችን ማድረግ የአላህ ጥበቡ ማስፈረዱ
የሚብራራበት ክፍል
እወቅ፡ ከአላህ ጥበብ መከከል አንድን ነብይ በዚህ ተውሂድ ላይ አላከም ለእርሱ ጠላትን ያደረገ
ቢሆን እንጅ፡፡ አላህ እንደተናገረው፡
ْ َْ َ ُ ْ ُ ْ َ َ ْ ُ ُ َْ ُ ْ َ َ َ َ ًّ ُ َ ُ َْ َ َ َ َ َ َ
ِّ اْل ِّن ي
وِح بعضهم إَِّل بع ٍض زخرف القو ِّل ِّ نس و
ِّ اإل ِّ ﴿وكذل ِّك جعلنا ل
ِّ ِّك ن ِّ ٍِّب عدوا شيا ِّطني
﴾ورا ً ُغ ُر
“እንደዚሁም ለነብያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የሆኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን፡፡ ከፊላቸው ወደ ከፊሉ
ለማታለል ልብስብስን ቃል ይጥላሉ፡፡” (አል’አንዓም፡ 112)
ከተወሂድ ሰዎች ተራው ሰው ፣ ከእነዚያ አጋሪዎች አሊሞች አንድ ሽውን ያሸንፋል፡፡ አላህ
እንደተናገረው፡
َ َ ْ َ َ َ ُ َّ
﴾ندنا ل ُه ُم الغاْلِّ ُون ﴿ِإَون ج
“ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡” (አስ’ሷፋት፡ 173)
በተውሂድ ሰው ላይ ስጋቱ ከእርሱ ጋር መሳሪያ ሳይኖር መንገድን የሚጓዘው ነው፡፡ (ለሁሉም ነገር
አብራሪ ፣ መሪም…) ያደረገውን መጽሐፍ አላህ በእኛ ላይ ለግሷል፡
9/37
َ ْ ُ ْ َ ْ ُ َ ًَْ َ َ ً ُ َ ْ َ ُ ً َْ
﴾ِّك َش ٍء وهدى ورْحة وبْشى ل ِّلمسل ِّ ِّمني ِّ ﴿ت ِّبيانا ل
“ለሁሉም ነገር አብራሪ ፤ መሪም ፤ እዝነትም ፤ ለሙስሊሞችም አብሳሪ ሆኖ በአንተ ላይ አወረድነው”
(አን’ነህል፡ 89)
“ይህች አንቀጽ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ በእርሷ ማስረጃ ይዞ ለሚያመጣ ማንኛውም የጥመት
ባለቤት ሁሉ (ምላሽ) የምትሆን ነች”
ክፍል ሰባት
ጥቅልም ይሁነ ዝርዝር በጥመት ባለቤቶች ላይ የተሰጠው ምላሽ የሚብራራበት ክፍል
እንላለን፡ ለጥመት ባለቤቶች የሚሰጠው ምላሽ በሁለት መንገዶች ነው፡ ጥቅል እና ዝርዝር፡፡
"إذا رأيتم الذين يتبعون المتشابه ويتركون المحكم فأولئك الذين سمى هللا في كتابه
"فاحذروهم
“ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም ፤ እነሱም አያዝኑም፡፡” (ዩኑሱ፡ 62)
ወይም ምልጃ ሀቅ ነው ወይም ነብያቶች ከአላህ ዘንድ ልቅና አላቸው ወይም በአንድ ነገር ላይ
ለጥመቱ ማስረጃ ይሆነው ዘንድ ከነብዩ ﷺንግግር ቢያዋሳ - እርሱ ያወሳውን ንግግር ትርጉሙን
አንተ የማትገነዘበው ብትሆን፡፡ በሚከተለው ንግግርህ ምላሽ ስጠው፡
እነዚያ በልባቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ግልጽ የሆነውን እንደሚተው ተመሳሳዩን
እንደሚከተሉ አላህ አውስቷል፡፡
ይህ ትርጉሙን አንድም አካል መቀየር የማይችለው የተብራራ ግልጽ ነገር ነው፡፡ አንተ አጋሪ
ሆይ! ከቁርኣን ወይም ከረሡል ﷺንግግር ለእኔ ያወሳህልኝ ትርጉሙን አላውቀውም፡፡ ነገር ግን
በቁርጠኝነት የምነግርህ የአላህ ንግግር እርስ በርስ የማይጋጭ ፣ የነብዩ ﷺንግግር ከአላህ ንግግር
ጋር የማይጋጭ መሆኑን ነው፡፡
“(ይህችንም ጠባይ) እነዚያ የታገሱት እንጅ ሌላው አያገኛትም ፤ የትልቅም ዕድል ባለቤት
እንጅ ማንም አይገጠማትም፡፡” (ፉሲለት፡ 35)
ከዚህ በፊት ባሳለፍነው ምላሽ ስጠው፡ የአላህ መልእክተኛ ﷺየተጋደሏቸው ለእኔ ያወሳሀቸውን
ነገሮች ያረጋግጡ ነበር -አንተ ጠማማ ሆይ! ጣዖቶቻቸው አንድም ነገር ማስተናበር
እንደማይችሉ ያረጋግጡ ነበር፡፡ ከእነርሱ የፈለጉት ልቅናቸውን እና ምልጃን ነው፡፡ አላህ
በመጽሐፉ ያወሳውን እና ግልጽ ያደረገውን አንብብለት፡፡
“የመሬም ልጅ አልመሲህ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
13/37
እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡ (ሁለቱም) ምግብን የሚበሉ ነበሩ ፤ አንቀጾችን ለነርሱ (ለከሀዲዎች)
እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት ከዚያም (ከእውነት) እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት፡፡ ከአላህ
ሌላ ለእናንተ መጉዳትንና መጥቀምን የማይችል ትገዛላችሁን? በላቸው፡፡ አላህም እርሱ ሰሚው ዐዋቂ
ነው፡፡” (አል’ማኢዳ፡ 75-76)
የአላህን ቃል (አውሳለት)፡
َ َ ُ َْ َ َ َُ ُ َّ َّ َ ُ َ ََ َ َ ْ َ َ ْ َ ُ ﴿ِإَوذْ قَ َال
َاّلل ي
ون اّللِّ قالِّ د ِّنم ني
ِّ ـه لِّ إ ّم
ِّ أو وِن
ِّ ذ ِّ اَّت ِّ
اس ِّلن ل لت ق نت أ أ م ير م ن اب ِّيَس
ع ا
َ َ َْ َ ُ َ ْ َ ُ َْ َ ْ َ َ ُ ُْ ُ ُ ُ َ َ ْ َ َ َ َُ ْ َ ُ ُ َ َ َ َ َ ْ ُ
سبحانك ما يكون َِّل أن أقول ما ليس َِّل ِِّب ٍق إِّن كنت قلته فقد علِّمته تعلم ما ِِّف نف َِّس وَل
ُ ُ ْ ُ َّ َ َ َ َ َّ َ ْ َ َ ُ َْ َ
﴾وب
ِّ سك إِّنك أنت عالم الغي ِّ أعلم ما ِِّف نف
“አላህም፡- “የመሬም ልጅ ኢሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ ሁለት አምላኮች
አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን” በሚለው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ “ጥራት ይገባህ ፤ ለእኔ ተገቢዬ ያልሆነን ነገር
ማለት ለኔ አይገባኝም፡፡ ብዬው እንደሆነም በእርግጥ አውቀኸዋል፡፡ በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ
ታውቃለህ፡፡ ግን ከአንተ ነፍስ ያለውን አላውቅም፡፡ አንተ ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህና”
ይላል፡፡ (አል’ማኢዳ፡ 116)
“እነዚያም ከእርሱ ሌላ (ጣኦታትን) ረዳቶች የያዙት “ወደአላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን እንጅ ለሌላ
አንገዛቸውም” (ይላሉ) (አዝ’ዙመር፡ 3)
እነዚህ ሶስት ማስመሰያዎች ከእነርሱ ዘንድ ትልቆቹ መሆናቸውን እወቅ፡፡ አላህ በቁርኣኑ ግልጽ
ያደረገ መሆኑን ካወቅክ ፣ በደንብ እርሷን መገንዘብን ከተገነዘብክ ከእርሷ በኋላ ያለው በጣም
ቀላል ነው፡፡
ክፍል ስምንት
ዱዓ አምልኮ አይደለም ባሉ አካላት ለይ የተሰጠው ምላሽ የሚብራራበት ክፍል
ለእርሱ የሚከተለውን ንገረው፡ አምልኮን ማጥራት አላህ በአንተ ላይ ግዴታ ያደረገው በአንተ ላይ
የእርሱ ሐቁ መሆኑን ታረጋግጣለህ?
15/37
የሚከተለውን ካለ፡ አዎ
ለእርሱ የሚከተለውን ንገረው፡ አላህ በአንተ ላይ ግዴታ ያደረገውን ለእኔ አብራራልኝ፡፡ እርሱም
አምልኮን ማጥራት ነው፡፡ እርሱም በአንተ ላይ የእርሱ ሀቅ ነው፡፡ እንሆ እርሱም አምልኮንና
አይነቶቿንም አያውቅም፡፡
ለእርሱ በሚከተለው ንግግርህ አብራራለት፡ አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡
َ ب ال ْ ُم ْع َت ِّد
﴾ين
َ ُ َّ ً َ ْ ُ َ ً ُّ َ َ ْ ُ َّ َ ْ ُ ْ
ُّ َِّل َُي ﴿ادعوا ربكم تَضَع وخفية إِّنه
በዚህ ካሳወቅከው ለእርሱ የሚከተለውን በለው፡ እርሱ (ዱዓ) ለአላህ አምልኮ ነውን? –
“አዎ! ዱዓ ከአምልኮ ነው” ማለቱ የማይቀር ነው፡፡
ለእርሱ የሚከተለውን ንገረው፡ እንሆ እርሷ አምልኮ መሆኗን ካረጋገጥክ ፣ ሌሊት እና ቀንን
አላህን ፈርተህና ተስፋ አድርገህ ከጠራህ ከዚያም በዚያ ጉዳይ ላይ ነብይን ወይም ሌላን ከጠራህ
በአላህ አምልኮ ሌላን አላጋራህምን?
ለእርሱ የሚከተለውን ንገረው፡ ለፍጡር ካረድክ ፡ ነብይ ወይም ጅን ወይም ከሁለቱ ሌላ - በዚህ
አምልኮ ከአላህ ውጭ አጋራህን?
16/37
“አዎ!” ማለቱ የማይቀር ነው፡፡
ክፍል ዘጠኝ
በሸሪዓዊው ምልጃ እና ሽርክ በሆነው ምልጃ መካከል ያለው ልዩነት የሚብራራበት ክፍል
ለእርሱ ንገረው፡ አልቃወማትም፡፡ ከእርሷም ራሴን ንጹህ አላደርግም፡፡ ይልቁንም እርሱ ﷺ
አማላጅ ፣ ምልጃው ተቀባይነት ያለው ነው፡፡ የእርሱን ምልጃ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ነገር ግን ምልጃ
በአጠቃላይ የአላህ ነች፡፡
አላህ እንደተናገረው፡
ً اع ُة ََج
﴾ِّيعا
َّ َّ ُ
َ الش َف
ِّ﴿قل ِّّلل
ምልጃ ሁሏም ለአላህ ከሆነች ፣ ከእርሱ ፈቃድ በኋላ እንጅ የማትሆን ከሆነ ፣ አላህ በእርሱ
ካልፈቀደ በቀር ነብዩም ይሁኑ ሌሎች አካላት ለአንድም ማማለድ የማይችሉ ከሆነ ፣ ለተውሂድ
ባለቤቶች እንጅ የማይፈቅድ ከሆነ ምልጃ በአጠቃላይ ለአላህ መሆኑ ግልጽ ሆነ ፤ ከእርሱም
እፈልጋታለሁ ፤ “አላህ ሆይ! የእርሱን ምልጃ አትከልክለኝ ፤ አላህ ሆይ! ስለኔ አማላጅ
አድርገው ፣ እና የመሳሰሉትን” እላለሁ፡፡
የእርሱን ነብይ ምልጃ ከአላህ መፈለግህ አምልኮ ነው፡፡ በዚህ አምልኮ አንድንም አካል ማጋራትን
18/37
አላህ ከልክሎሀል፡፡ የእርሱን ነብይ ለአንተ አማላጅ እንዲያደርገው አላህን የምትማጸን ከሆነ
ባሳለፍነው ንግግሩ እርሱን ታዘዘው፡፡
“እንሆ መስጊዶችም (ምድር በአጠቃላይ) የአላህ (አምልኮ መፈጸሚያ) ብቻ ናቸው፡፡” (ጅን ፡ 18)
ክፍል አስር
ወደደጋጎች መጠጋት ሽርክ መሆኑን ማረጋገጥና
የሚከተለውን ከተናገረ፡ “እኔ በአላህ አንድም አላጋራም፡፡ ነፍሴን አጠራለሁ ፣ ተከልከል! ነገር
ግን ወደደጋጎች መጠጋት ማጋራት አይደለም፡፡”
ለእርሱ የሚከተለውን ንገረው፡ አላህ ከዝሙት ሀራምነት በከበደ ሁኔታ ማጋራትን እርም አድርጓል
ብለህ የምታረጋግጥ ከሆነ ፣ አላህ ፍጹም የማይምረው መሆኑን የምታረጋግጥ ከሆነ ፣ ይህ አላህ
ሀራም ያደረገው ነገር ምንድን ነው ፣ አልምረውም ብሎ የተናገረው ምንድን ነው? እንሆ እርሱ
አያውቅም፡፡
ለእርሱም ንገረው፡ የጣዖት አምልኮ ትርጉሙ ምንድን ነውʔ እነርሱ ፣ ዲንጋዮች ፣ እንጨቶች
ለጠራቸው ሰው ይፈጥራሉ ፣ ይመግባሉ ፣ ነገርን ያስተናብራሉ የሚል እምነት አላቸው ብለህ
ትጠረጥራለህንʔ ይህን ደግሞ ቁርኣን ያስተባብለዋል፡፡
የሚከተለውን ከተናገረ፡ እርሱ እንጨትን ወይም ዲንጋይን ፣ ወይም ከቀብር ለይ የተገነባን ግንባታ
ወይም ሌላን አላማ የሚያደርግ ፣ እርሱንም የሚማጸን ፣ ለእርሱ የሚያርድ “ወደአላህ
ማቃረብን ያቃርበኛል ፣ በእርሱ በረከት ከእኛ ላይ አላህ ይከላከላል ፣ በእርሱ በረከት ይሰጠናል”
የሚል ነው፡፡
እንደዚሁ ለእርሱ ይንነገረዋል፡ “ማጋራት የጣዖት አምልኮ ነው” የሚለው ንግግርህ ፤ ማጋራት
በዚህ ብቻ የተለየ ነው የሚል ነው ፍላጎትህ? ወደደጋጎች መጠጋት ፣ እነርሱን መማጸን በዚህ
ውስጥ አይገባም የሚል ነው ፍላጎትህ?
ይህን ደግሞ በመላኢካ ወይም በኢሳ ወይም በደጋጎች (ልቦናው) የተያያዘ (የተጠጋ) ክህደት
መሆኑን አላህ በመጽሐፉ ያወሳው ይመልሰዋል፡፡
“በአላህ አምልኮ ከደጋጎች አንድንም አካል ያጋራ ፣ እርሱ በቁርኣን የተወሳው ማጋራት ነው”
20/37
በማለት ማረጋገጡ አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ ተፈላጊ ነው፡፡
ለእርሱ በለው፡ “ለእርሱ ሸሪካ የሌለው በብቸኛነት አላህን መገዛት ትርጉሙ ምንድን ነው? ለእኔ
አብራራልኝ”
በቁርኣን አላህ እንዳብራራው አድርጎ ከተነተነልህ እርሱ ተፈላጊ ነው፡፡ የማያውቀው ከሆነ ፣
እንዴት እርሱ በማያውቀው ነገር ይሞግታል?
ያለትርጉሙ ካብራራው፡ በአላህ ማጋራት ፣ በቀጥታ በዚህ ዘመን የሚሰሩት የሆነውን የጣዖት
አምልኮ ትርጉም ግልጽ በሆኑ አንቀጾች ለእርሱ ታብራራለታለህ፡፡ በእርሱ ምንም ሳያጋሩ
በብቸኛነት አላህን ማምለክ በእኛ ላይ የሚቃወሙን እርሱን ነው፡፡ ወንድሞቻቸው እንደጮሁት
የሚጮሁበት እርሱ ነው፡፡
እነርሱ ባሉ ጊዜ፡
ٌ َ ُ ٌ ْ َ َ َ َ َّ ً َ ً َ َ َ ْ َ َ َ َ
﴾حدا إِّن هذا لَشء عجابِّ ﴿أجعل اْلل ِّهة إِّلها وا
“አማላክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውንʔ ይህ አስደናቂ ነገር ነው” (አሉ) (ሷድ፡ 5)
“ለአላህም አጋንንትን የፈጠራቸው ሲሆን (በመታዘዝ) ተጋሪዎች አደረጉ፡፡ ወንዶች ልጆችንና ሴቶች
ልጆችንም ያለ እውቀት ለእርሱ ቀጠፉ፡፡” (አል’አንዓም፡ 100)
“ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም ፤ እነሱም አያዝኑም፡፡” (ዩኑስ፡ 62)
የአላህ ዲን በሁለት ጽንፎች መካከል ነው፡፡ በሁለት ጥመት መካከል ያለ ቅን ጎዳና ነው፡፡ በሁለት
ብልሹዎች መካከል ያለ ሐቅ ነው፡፡
የመጀመሪያዎቹ (ትውልዶች) ማጋራት ከወቅታችን ሰዎች ማጋራት በሁለት ነገሮች ቀላል መሆኑን
እወቅ
“የአላህ ቅጣት ቢመጣባችሁ ወይም ሰዓቲቱ (ትንሳኤ) ብትመጣባችሁ ከአላህ ሌላን ትጠራላችሁን?
እውነተኞች እንደሆናችሁ ንገሩኝ በላቸው፡፡ አይደለም እርሱን ብቻ ትጠራላችሁ ቢሻም ወደርሱ
የምትጠሩበትን ነገር ያስወግዳል፡፡ የምታጋሩትንም ነገር ትተዋላችሁ (በላቸው)” (አል’አንዓም፡ 40-41)
َُْ ْ َ ُ ْ َ َ َ َ َ َ ُ ْ ً َ ْ ُ َ َّ َ َ َّ ُ ْ َ ً ُ ُ َّ َ َ َ ٌّ ُ َ َ ْ َّ َ َ
اإلنسان َض دَع ربه منِّيبا إِِّلهِّ ثم إِّذا خوَل ن ِّعمة مِّنه ن َِّس ما َكن يدعو إِِّلهِّ مِّن قبل ِّ ﴿ِإَوذا مس
َّ َ ْ َ ْ َ َّ ً َ َ ْ ُ ْ َّ َ َ ْ ُ َ َ َّ ُ ً َ َ َّ َ َ َ َ
﴾ِّاب اَّلار
ِّ ضل عن سبِّيلِّهِّ قل تمتع بِّكف ِّرك قلِّيال إِّنك مِّن أصح ِّ وجعل ِّّللِّ أندادا ِِّل
“ሰውንም ጉዳት ባገኘው ጊዜ ጌታውን ወደርሱ ተመላሽ ሆኖ ይጠራል፡፡ ከዚያም ከእርሱ ዘንድ ጸጋን
በሰጠው ጊዜ ያንን ከዚያ በፊት ወደርሱ ይማጸንበት የነበረውን (መከራ) ይረሳል፡፡ ከመንገዱ
ለመሳሳትም ለአላህ ባላንጣዎችን ያደርጋል፡፡ “በክህደትህ ጥቂትን ተጣቀም፡፡ አንተ በእርግጥ ከእሳት
ጓዶች ነህ” በለው፡፡ (አዝ’ዙመር፡ 8)
َ ني َ َُل اَل
﴾ِّين ِّ َ َّ لظلَل َد َع ُوا
َ اّلل ُُمْلِّص ُّ َ ٌ ْ َّ ُ َ َ َ
شيهم موج َك ِّ ﴿ِإَوذا غ
ِّ
“እንደጥላዎችም የሆነ ማእበል በሸፈናቸው ጊዜ አላህን ሐይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው
ይጠሩታል፡፡” (ሉቅማን፡ 32)
24/37
አላህ በቁርአኑ ግልጽ ያደረገውን ይህን ጉዳይ የተገነዘበ ፣ እርሱም -የአላህ መልእክተኛ ﷺ
የተጋደሏቸው አጋሪዎች- በደስታ ጊዜ አላህን እና ሌላን እንደሚጠሩ ፤ በብርቱ ችግር ጊዜ ከሆነ
ደግሞ አላህን ብቻ እንጅ ሌላን እንደማይጠሩ ፤ አለቆቻቸውንም እንደሚረሱ (የተገነዘበ) ፣
በዘመናችን ያለውን ሽርክ እና የመጀመሪያዎቹ ሽርክ ልዩነቱ ለእርሱ ግልጽ ይሆንለታል፡፡ ነገር ግን
ይህን ጉዳይ ልቡ ጥልቅ በሆነ ግንዛቤ የሚገነዘብ የታለ? እገዛን ከአላህ እንፈልጋለን፡፡
ሁለተኛው ጉዳይ፡ የመጀመሪያዎቹ ከአላህ ዘንድ ሙቀረብ የሆኑትን ሰዎች ከአላህ ጋር ይጠራሉ
- ነብይ ወይም ወልይ ወይም መላኢካ ወይም ለአላህ ታዛዥ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ወንጀለኛ
ያልሆኑትን ዲንጋይን ፣ ዛፍን ይጠራሉ፡፡
መልሱ፡ አንድ ሰው በአንድ ነገር ረሡልን ﷺእውነት ብሎ ፣ በሆነ ነገር ካስተባበለው ከሐዲ
እንደሚሆን ፣ ወደኢስላም እንደማይገባ በሁሉም ዑለሞች መካከል ልዩነት የለም፡፡ በቁርኣን
በተወሰነው አምኖ በተወሰነው ካስተባበለም ልክ እንደዚሁ ነው፡፡ ልክ በተውሒድ አረጋግጦ
በሶላት ግዴታነት እንዳስተባበለ ነው ወይም በተውሂድ ፣ በሶለት አረጋግጦ በዘካ ግዴታነት
እንዳስተባበለ ነው፡፡ ወይም በዚህ ሁሉ አረጋግጦ በጾም ግዴታነት እንዳስተባበለ ነው፡፡ ወይም
በዚህ ሁሉ አረጋግጦ የሐጅን ግዴታነት እንዳስተባበለ ነው፡፡
“ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መሄድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፡፡ የካደም
ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡” (አል’ዒምራን፡ 97)
በከፊሉ ያመነ ፣ በከፊሉ የካደ በእውነት ከሀዲ መሆኑን አላህ በመጽሐፉ ግልጽ ካደረገ ፣ ይህ
ብዥታ ተወገደ፡፡ ይህን ነው አንዳንድ የ “አህሳእ” ሰዎች ወደኛ በላኩት ደብዳቤ ያወሱት፡፡
አሁንም ይባላል፡ ረሡልን ﷺበአንድ ነገር እውነት ብሎ የሶላትን ግዴታነት ካስተባበለ እርሱ
ከሀዲ ፣ ደሙም ፣ ገንዘቡም የተፈቀደ መሆኑ የዑለሞች ስምምነት መሆኑን የምታረጋግጥ ከሆነ
፣ እንደዚሁ በሁሉም ነገር አረጋግጦ ሞቶ መቀስቀስን ያስተባበለ ፣ ልክ እንደዚሁ የረመዷንን
ጾም ግዴታነት ያስተባበለ ፣ በዚህ ሁሉ እውነት ያለ ፣ በዚህ ዙሪያ (ከሐዲ እንደሚሆን)
መዝሀቦች አይለያዩም - ከዚህ በፊት እንዳስቀደምነው - ቁርኣኑም በዚህ ተናግሯል፡፡
ተውሂድ ነብዩ ﷺበእርሷ ከመጡበት ሁሉ ትልቁ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ እርሱም ከሶላት ፣
ከዘካ ፣ ከጾም እና ከሐጅ የበለጠ ነው፡፡ ረሡል ﷺበመጡበት ሁሉ ቢተገብር አንድ ሰው
ከእነዚህ ነገሮች አንዱን ያስተባበለ ከሀዲ ከሆነ ፣ የመልእክተኞች ሁሉ እምነት የሆነውን
ተውሒድ ያስተባበለ እንዴት ከሀዲ አይሆን?! አላህ ጥራት ይገባው!! ይህንን ድንቁርና ምን
አስደናቂ አደረገው!!
እኛ እንናገራለን፡ ይህ ተፈላጊ ነው፡፡ አንድን ግለሰብ ወደነብይነት ደረጃ ከፍ ያደረገ ከሀዲ ከሆነ ፣
27/37
ከዚያም በርካታ አይነቶችን አወሱ፡፡ ከእርሷ እያንዳንዷ አይነት የሚያከፍር ፤ የግለሰቡን ገንዘብ
እና ደሙን የተፈቀደ የሚያደርግ፡፡ ከሚሰራት ሰው ዘንድ ቀላል የሆኑ ነገሮችን ሳይቀር
አውስተዋል፡፡ ለምሳሌ ከልቡ ሳይሆን በምላሱ የሚናገራት ቃል ወይም በጨዋታ እና በቀልድ
መልኩ የሚያወሳት ቃል?!
በተጨማሪ ይባላል፡ ስለነርሱ አላህ የተናገረላቸው
ْ َ ْ َ ْ َ ْ ُ َ ََ ْ ُ ْ َ َ َ ْ ُ َ ْ َََ ْ ُ َ َ َ ُ َْ
﴾﴿َيلِّفون بِّاّللِّ ما قالوا ولقد قالوا َكِّمة الكف ِّر وكفروا بعد إِّسال ِّم ِّهم
እነዚያ እነርሱ በቀልድ መልክ ቃልን በመናገራቸው ካመኑ በኋላ የካዱ መሆናቸውን አላህ ግልጽ
ያደረገባቸው -በተቡክ ዘመቻ ከረሡል ﷺጋር የዘመቱ ነበሩ-
“ሙሳ ሆይ! ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዳሏቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን” (አል’አዕራፍ፡
138)
ነገር ግን ለአጋሪዎች በዚህ ታሪክ የሚያቀርቡት ማመሳሰያ አላቸው፡፡ እርሷም፡ “በኒ ኢስራኢሎች
በዚህ ከሀዲ አልሆኑም” ይላሉ፡፡
ነገር ግን ይህ ታሪክ፡ አንድ ሙስሊም -ይልቁንም ዓሊም- ከእርሷ ሳያውቅ ከሽርክ አይነቶች
አንዳንዴ ሊወድቅ እንደሚችል ያስጠቅመናል፡፡
ትምህርትን ፣ ጥንቃቄን (ያስጠቅመናል) እንዲሁም “ተውሂድን ተገንዝበናል” የሚለው የጃሂል
30/37
ንግግር ትልቁ ጅህልና ፣ የሰይጣን ሴራ መሆኑን ማወቃችንን ያስጠቅመናል፡፡
የኦሳማ ሐዲስን በተመለከተ፡ ደሙን እና ገንዘቡን ፈርቶ እንጅ ኢስላምን አልሞገተም በሚል
ጥርጣሬ አንድን ግለሰብ ኢስላምን እየሞገተ ገደለው፡፡ አንድ ግለሰብ ኢስላምን ይፋ ካደረገ
ከእርሱ መቆጠብ ግድ ነው -ያንን የሚቃረን ነገር ግልጽ እስከሚሆን ድረስ፡፡ በዚህ ዙሪያ አላህ
ቁርኣን አወረደ፡
ْ ُ َّ َ َ َ َ ْ ُ ْ َ َ َ ْ ُ َ َ َّ َ ُّ َ َ
﴾يل اّللِّ فتبينوا
ِّ ِّ ﴿يا أيها اَّلِّين آمنوا إِّذا َضبتم ِِّف سب
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ (ለመጋደል) በተጓዛችሁ ጊዜ አስረግጡ፡፡” (አን’ኒሳእ፡ 94)
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ሆናችሁ ህዝቦችን እንዳትጎዱና
በሰራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትሆኑ አረጋግጡ፡፡” (አል’ሑጁራት፡ 6)
ሌላም ማመሳሰያ አላቸው፡ እርሷም ነብዩ ﷺያወሱት ሰዎች የቂያማ ቀን በአደም ፣ ከዚያም
በኑህ ፣ከዚያም በሙሳ፣ከዚያም በኢሳ እርዳታ እንደሚፈልጉ ከዚያም ወደአላህ መልእክተኛ ﷺ
እስከሚደርሱ ድረስ ሁሉም ምክንያት እንደሚያቀርቡ ነብዩ ﷺየተናገሩት ሐዲስ ነው፡፡
33/37
እነርሱ አሉ ፡ ይህ የሚጠቁመው ከአላህ ውጭ እርዳታ መፈለግ ሽርክ ላለመሆኑ ነው፡፡
መልሱ የሚከተለውን ማለትህ ነው፡ በጠላቶቹ ልቦና ላይ ያተመ (ጌታ) ጥራት ይገባው! በእርሱ
ላይ በሚችለው በፍጡር እርዳታ መፈለግ አንቃወማትም፡፡ በሙሳ ታሪክ አላህ እንደተናገረው፡
ُ َ ْ َّ َ َ َ َّ ُ َ َ َ ْ َ
﴾ِّ ﴿فاستغاثه اَّلِّي مِّن ِّشيعتِّهِّ لَع اَّلِّي مِّن عدوِّه
“ያም ከወገኑ የሆነው ሰው በዚያ ከጠላቱ ከሆነው ሰው ላይ እርዳታን ጠየቀው፡፡” (አል’ቀሶስ፡ 15)
ከሞቱ በኋላማ እነርሱ ከቀብራቸው ዘንድ ይህንን ጠየቁ ማለት የጠሩ ናቸው ፣ ተከልከል
(እነርሱ ጠይቀዋል ከማለት)፡፡ ከእርሱ ቀብር ዘንድ አላህን ለመማጸን ማሰብን ሰለፎች
አውግዘዋል፡፡ እናቴም አባቴም ለእርሳቸው መስዋእት ይሁኑና እንዴት ነፍሳቸውን (ራሳቸውን)
ይማጸናሉ፡፡
ሌላም ማመሳሰያ አላቸው፡ እርሷም የኢብራሂም ታሪክ ነች፡፡ እሳት በተጣለ ጊዜ በአየር ላይ
ጅብሪል ለእርሱ አቀረበለት፡ አለውም፡ ሀጃ አለህን?
ይህ ልክ እንደ አንድ ሀብታም ሰው ማለት ነው -ብዙ ገንዘብ እንዳለው፡፡ አንድ ፈላጊ (ችግረኛ)
የሆነን አካል እንደሚመለከትና ሊያበድረው ፣ ወይም ሀጃውን ለመፈጸም በስጦታ መልክ
ሊሰጠው ሀሳብ እንዳቀረበ ሀብታም ምሳሌ ነው፡፡ ይህ ፈላጊ (ችግረኛ) ከእርሱ ከመቀበል እምቢ
እንደለና አላህ ሲሳይ እስከሚያመጣለት አንድም ሰው በእርሱ እንዳይመጻደቅበት መታገስን
እንደፈለገ ሰው ምሳሌ ነው፡፡ ከአምልኮ እና ከሽርክ እስቲጋሳ ጋር ይህ የት ነው ያለው? ቢገነዘቡ
ኖሮ!
ያሳለፍነውን እንድንገነዘብ የሚያደርግ ታላቅና አንገብጋቢ የሆነን አንቀጽ በማውሳት ይህን ኪታብ
እናጠናቅ፡፡ ነገር ግን ሁኔታዋ ትልቅ ፣ በእርሷ ዙሪያ ስህተቶችም ስለሚበዙ ንግግርን ለብቻ
እናድርግላት፡፡
የሚከተለውን እንናገራለን፡ ተውሂድ የግድ በልብ ፣ በአንደበት እና በተግባር መሆኑ ምንም ዓይነት
ልዩነት የለም፡፡ ከዚህ መካከል አንዱ ከጎደለ ግለሰቡ ሙስሊም ሊሆን አይችልም፡፡
35/37
ተውሂድን ቢያውቅና በእርሱ ባይሰራ እርሱ ከሀዲና አመጸኛ ነው -ልክ እንደፊርአውን ፣
ኢብሊስ እና እንደመሰሎቻቸው፡፡
ይህ ምስኪን አላወቀም፡ አብዛኞች የክህደት መሪዎች ሀቅን ያውቃሉ ፤ ለሆነ ምክንያት እንጅ
አልተውትም፡፡
አላህ እንደተናገረው፡
َ ْ ََ ْ
﴾ات اّللِّ ث َم ًنا
ِّ ََت ْوا بِّآي ﴿اش
ከአላህ መልእክተኛ ﷺጋር ወደሮማ የዘመቱ አንዳንድ ሶሃቦች በቀልድ መልክ የተናገሯት
በሆነች አንዲት ቃል ምክንያት መካዳቸውን ካረጋገጥክ ፤ ገንዘቡ ፣ ስልጣኑ ይጎድልብኛል ወይም
ከሆነ አካል ጋር ለመተዳደር ብሎ የክህደት ንግግር የተናገረ ወይም በእርሱ የሰራ በቀልድ መልክ
ከተናገረው የከበደ መሆኑ ለአንተ ግልጽ ይሆናልሃል፡፡
“ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው (ብርቱ ቅጣት አልለው)፡፡ ልቡ በእምነት የረጋ ሆኖ (በክህደት ቃል
በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ ግን ልባቸውን በክህደት የከፈቱ ሰዎች በነሱ ላይ ከአላህ ቁጣ
አለባቸው፡፡ ለእነሱም ታላቅ ቅጣት አልላቸው፡፡ ይህ (ቅጣት) እነሱ ቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ
በመምረጣቸው ምክንያትና አላህም ከሀዲዎችን ህዝቦች የማያቀና በመሆኑ ነው፡፡” (አን’ነህል፡ 106-107)
37/37
ልቡ በእምነት የተረጋጋ ከመሆኑ ጋር የተገደደ ሰው ሲቀር አላህ ለእነዚህ ሰዎች ምንም
አይነት ምክንያት አላደረገም፡፡ ከዚህ ውጭ ከእምነቱ በኋላ ካደ፡፡ የተገደደ ሰው ሲቀር ፈርቶም
ይስራው ፣ ወይም ተስፋ አድርጎ ፣ ወይም ከሆነ አካል ጋር መተዳደር ብሎ ወይም አገሩን ወይም
ቤተሰቡን ወይም ዘመዶቹን ወይም ገንዘቡን ወዶ (ሳስቶ) ወይም በቀልድ መልክ ሰራው ወይም
ከዚህ ውጭ ላለ አላማ ሰራው እኩል ነው (አላህ ምንም ዓይነት ምክንያት አይሰጠውም)፡፡
ሁለተኛው፡ የሚከተለው ቃሉ ነው
“ይህ (ቅጣት) እነሱ ቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ በመምረጣቸው ምክንያትና አላህም ከሀዲዎችን
ህዝቦች የማያቀና በመሆኑ ነው፡፡” (አን’ነህል፡ 107)
ይህ ክህደት እና ቅጣት በእምነት ወይም በጀህል ወይም ዲንን በመጥላት ወይም ክህደትን
በመውደድ ምክንያት እንዳልነበረ ግልጽ አደረገ፡፡ ምክንያቱ ለእርሱ ከዱንያ ድርሻዎች የሆነ
ድርሻ እንደነበረውና እርሱንም ከዲን አብልጦ በመምረጡ ነው፡፡ ወሏሁ አዕለም