You are on page 1of 62

አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ

‫ شيخ اإلسالم ابن تيمية رحمه هللا‬: ‫تأليف‬


ትርጉም/አቡ ዓብዲል ዓዚዝ ዩሱፍ አሕመድ
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 1/60

ከሐይማኖቶች ሁሉ የበላይ ሊያደርገው ፣ በጠቃሚ እውቀትና በእውነተኛ ሐይማኖት


መልክተኛውን የላከ የሆነው አላህ ምስጋና ሁሉ ይገባው ፤ መስካሪም በአላህ በቃ፡፡
በእርሱ በማረጋገጥና ብቸኛ በማድረግ ፣ ከአሏህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ
፣ ለእርሱ ተጋሪ እንደሌለውና ብቸኛ እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡ ሙሐመድ የእርሱ
አገልጋይና መልክተኛው እንደሆኑ እመሰክራለሁ፡፡ በእርሳቸው ፣ በቤተሰቦቻቸው እና
በባልደረቦቻቸው ላይ ከውዳሴው ተጨማሪ ፣ ሰላምታን አላህ ያስፍንባቸው፡፡

(ነጻ የምትወጣዋ ቡድን)


ከዚህ በኋላ፡ ይህ ፣ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ የምትርረዳ ፣ (በዚህ ዓለም ከሽርክና ከቢድዓ ፣

ይህ ውዳሴ የተወሰደው ከሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ነው፡-


ِ ِ ِ ْ ‫﴿هو الَّ ِذي أَرسل رسولَه ِِب ْْلدى وِدي ِن‬
‫اْلَ ِق ليُظْ ِهَرهُ َعلَى الدي ِن ُكل ِه َوَكَى ِِب ََّّلِ ََ ِه ا‬
﴾‫يدا‬ َ َُ ُ ُ َ َ َ ْ َُ
“እርሱ ያ መልክተኛውን በመሪ መጽሐፍና በእውነተኛ ሃይማኖት ፣ በሃይማኖት ሁሉ ላይ ሊያልቀው
የላከ ነው፡፡ መስካሪም በአላህ በቃ፡፡” ፈትህ ፡

ይህ ፣ ጃቢር ኢብን ዓብዲላህ e ያስተላለፈውና ሙስሊም በቁጥር የዘገበውን ሐዲስ የሚጠቁም ነው፡፡
“ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ሲናገሩ ሰማሁ፡ -
"‫"ال تزال طائفة من أمتي يقاتلون على الحق ظاهرين إلى يوم القيامة‬
“ከኡመቶቸ በሐቅ ላይ የሚጋደሉ ፣ እስከቂያማ ቀን የበላይ የሚሆኑ ፣ አንዲት ቡድን አትወገድም፡፡”
“ፊርቀቱ ናጂያ አልመንሱራ” የሚባሉት የመልእክተኛውን መንገድ ፣ የሙስሊም ጀማዓዎች ያሉበትን ፣
በአጠቃላይ የአላህን ገመድ አጥብቀው የያዙ ፣ መከፋፈልን እና የመከፋፈልን ምክንያቶች በሙሉ የራቁ
አህለሱና ወልጀማዓዎች ናቸው፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 2/60

በወዲያኛው ዓለም ደግሞ ከእሳት) ነጻ የምትሆን የሱናና በሐቁ ላይ የመሰባሰብ ባለቤት


የሆነችው ቡድን እምነት ነው፡፡

(የኢማን ማዕዘናቶች)
እርሱም በአላህ ፣ በመላኢካዎች ፣ በመጽሐፎች ፣ በመልእክተኞች ፣ ከሞት
በኋላ በመቀስቀስ ማመን ነው ፤ መልካምም ይሁን ክፉ በውሳኔው ማመን ነው፡፡

(ያለማጣመም ፣ ያለማራቆት እና ያለማመሳሰል በአላህ መገለጫዎች ማመን)

ያለምንም ማጣመም ፣ ያለማራቆት ፣ አኳኋንን ያለመግለጽ ፣ ያለማመሳል

“ማጣመም” ማለት የአላህን መልካም ስሞችና መገለጫዎች በቃላትም ይሁን በትርጉም መቀየር ማለት
ነው፡፡ ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል'ዑሰይሚን I የሚከተለውን ተናገረዋል፡-
የሐረካ ለውጥ ፡
ِ
﴾‫يما‬ َ ‫﴿ َوَكلَّ َم اَّلُ ُم‬
‫وسى تَكْل ا‬
“አላህም ሙሳን ማነጋገርን አነጋገረው” አን ኒሳእ፡

“አሏሁ” የሚለውን ከረፍዕ ወደነስብ በመቀየር “አሏሀ” ብለው ይቀሩታል፡፡ በዚህም “አላህ ሙሳን
አናገረ” ሳይሆን “ሙሳ አላህን አናገረ” የሚል የተዛባ ትርጉም ይሰጣል፡፡
የትርጉም ለውጥ፡ አላህ ከዓርሽ በላይ መሆኑን የሚገልጸውን “ኢስተዋ” ፣ አንድ ሐርፍ “ላም”
በመጨመር ፣ “ኢስተውላ” ብለው ይተረጉሙታል፡፡ በዚህም ትርጉሙ አላህ ከዓርሽ በላይ ሳይሆን ፣ አላህ
አርሽን ተቆጣጠረ ወይም በአርሽ ላይ ተሾመ የሚል የተዛባ ትርጉም ይሰጣል፡፡
“ተዕጢል” ወይም ማራቆት ማለት የአላህን አምላካዊ ባህሪያት ማራቆት ማለት ነው፡፡
“ተክይፍ” ማለት ለአንድ ነገር አኳኋን ማድረግ ማለት ነው፡፡
“ተምሲል” ማለት ደግሞ አካላዊና ተግባራዊ በሆነው መገለጫው አላህን ከፍጡራን ጋር ማመሳሰል
ማለት ነው፡፡ =
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 3/60

በቁርኣን ውስጥ በእርሱ ነፍሱን በገለጸበት ፣ መልእክተኛውም እርሱን በገለጹበት


ማመን በአላህ ማመን በሚለው ውስጥ (ከሚካተቱ ነጥቦች አንዱ ነው)፡፡

(የአላህን መገለጫዎች አስመልክቶ የአህለሱና ወልጀማዓ አቋም)

ይልቁንም አላህ b የሚመስለው ምንም ነገር የለም ፣ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ


እንደሆነ ያምናሉ፡፡
ነፍሱን የገለጸበትን ነገር ከእርሱ ላይ አያራቁቱም ፤ ንግግሮችን ከቦታቸው ላይ
አያጣምሙም ፤ በአላህ ስሞችና አንቀጾች ዙሪያ አያጣምሙም ፤ መገለጫዎቹን
በፍጡር መገለጫዎች አያመሳስሉም ፣ አኳኋንንም አይገልጹም- ምክንያቱም
ከጉድለትና ከነውር የጸዳው ጌታችን ለእርሱ አምሳያ ፣ ቢጤ ፣ አቻ የሌለው
በመሆኑና በፍጡራንም የሚነጻጸር ባለመሆኑ ነው፡፡

እንሆ ፣ ከፍጡራኖች ይልቅ ስለነፍሱም ይሁን ስሌላው በጣም አዋቂው ፣ ንግግሩ


በጣም የተብራራና በጣም እውነተኛው እርሱ ነው፡፡
=
ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አልኡሰይሚን I የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “በሁለቱ መካከል
ያለው ልዩነት የሚከተለው ነው፡- ማመሳሰል ማለት በሚመሳሰሉ ነገሮች ላይ ብቻ ወስነን ባህሪን
መግለጽ ማለት ሲሆን ፤ አኳኋንን መግለጽ ማለት ደግሞ በሚመሳሰሉ ነገሮች ሳንወስን ባህሪን መግለጽ
ማለት ነው፡፡”
ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል’ዑሰይሚን I የሚከተለውን ተናግረዋል፡- የሚከተሉትን አራት
መስፈርቶች ያሟላ ዘገባው ተቀባይነት ማግኘቱ ግድ ነው፡-
1ኛ፡- ዘገባው እውቀት ካለው አካል ከመጣ ፣ 2ኛ፡- ዘጋቢው እውነተኛ ከሆነ ፣
3ኛ፡- ዘጋቢው የማብራራትና ግልጽ የማድረግ ችሎታ ያለው ከሆነ ፣ 4ኛ፡- ዘጋቢው ሰዎችን ወደመልካም
ለመምራት አላማ ያለው ከሆነ ፣
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 4/60
(አጠቃላይ መልእክተኞች እውነተኛ መሆናቸው)

ከዚያም - የማያውቁትን በሚናገሩ አካላት ተቃራኒ - መልእክተኞቹ ፣ ንግግራቸው


እውነተኛ ፣ ከአላህ ዘንድ ታማኞች ናቸው፡፡

በዚህም ምክንያት አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫ن‬ ِ ِ ‫اْلم ُد ََِّّلِ ر‬


َ ‫ب الْ َعالَم‬
ِ ِ ِ ِ‫كر‬
َ ‫ب الْعَّزةِ َع َّما يَص َُو َن۞ َو َس ََل ٌم َعلَى الْ ُمْر َسل‬ ِ
َ ْ َْ ‫ن۞ َو‬ َ َ ‫﴿ ُسْب َحا َن َرب‬
“የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ በመልእክተኞቹም ላይ
ሰላም ይሁኑ ፤ ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡” አስ ሷፋት፡

የመልእክተኞች ተቃራኒዎች በእርሱ ከገለጹበት ነገር ነፍሱን አጠራ፡፡ የተናገሩት


ከጉድለትና ከነውር ሰላም በመሆኑ በመልእክተኞች ላይ ሰላምን አሰፈነ፡፡

(የማራቆትና የማጽደቅ ትርጓሜ)

እርሱ - ከጉድለት የጠራው ጌታችን - ነፍሱን የሰየመበትንና የገለጸበትን በማራቆትና


በማጽደቅ አጣምሮ ተናገረ፡፡

አህለሱና ወልጀማዓዎች መልእክተኞች ከመጡበት መንገድ መዘንበል የላቸውም -

አህለሱናዎች ፣ በሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ መሰረት የማይስማሙ ባህሪያትን በጥቅል ያራቁታሉ፡-


﴾ٌ‫س َك ِمثْلِ ِه ََ ْيء‬
َ ‫﴿لَْي‬
“የሚመስለው ምን ነገር የለም፡፡” አሽ ሹራ፡

በሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ መሰረት ደግሞ ስሞቹን እና ባህሪያቶቹን በዝርዝር ያጸድቃሉ፡-


ِ ‫الس ِميع الب‬
﴾ُ‫صي‬ َ ُ َّ ‫﴿ َوُه َو‬
“እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡” አሽ ሹራ፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 5/60

ምክንያቱም አላህ ጸጋውን የዋለላቸው አካላት ነብያቶች ፣ ሲዲቆች ፣ ሸሂዶች እና


ደጋግ የአላህ ባሮች የተጓዙበት ቀጥተኛ ጎዳና በመሆኑ ነው፡፡

ክፍል አንድ

(የአላህን ስሞችና መገለጫዎች የሚያጸድቁ የቁርኣን ማስረጃዎች)

1. በአላህ መገለጫዎች ዙሪያ ማጽደቅና ማራቆት ተጣምረው የጸደቁበት

አላህ ነፍሱን የገለጸበትና የቁርኣንን አንድ ሶስተኛ እንደሚመዝን የተነገረለት


የኢኽላስ ምዕራፍ በዚህ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ተካቷል፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ
አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
ِ
َ ‫الص َم ُد۞ ََلْ يَل ْد َوََلْ يُولَ ْد۞ َوََلْ يَ ُكن لَّهُ ُك َُ اوا أ‬
﴾‫َح ٌد‬ َّ ُ‫اَّل‬
َّ ۞‫َح ٌد‬
َ ‫اَّلُ أ‬
َّ ‫﴿قُ ْل ُه َو‬

“በል 'እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ አልወለደም ፤
አልተወለደምም፡፡ ለእርሱም ብጤ የለውም፡፡” አል ኢኽላስ፡

ሲዲቅ (እውነተኛ) ማለት በእምነቱ ፣ በሐሳቡ ፣ በኢኽላሱ ፣ በንግግሩ በተግባሩ እውነት ብሎ ያረጋገጠ
ማለት ነው፡፡
ሸሒድ የሚለው ሁለት ትርጉም ተሰጦታል፡፡ የመጀመሪያው በአላህ መንገድ ላይ ሲታገል መስዋዕት የሆነ
ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ለዑለሞች የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ ለመጀመሪያው ትርጉም ሱረቱ አል'ኢምራን
፣ ለሁለተኛው ትርጉም ደግሞ አል'ኢምራን ማስረጃ ሆኖ ቀርቧል፡፡
ሷሊሆች ፡ የሚባሉት ከነብይነት ፣ ከሲድቅነትና ከሸሂድነት ደረጃ ያልደረሱ በአላህ ሐቅና በባሮች ሐቅ
ላይ ቋሚ የሆኑ ደጋግ የአላህ ባሮች ናቸው፡፡
ጸሐፊው የጠቆመው ቡኻሪ (በቁጥር 5013) ላይ የዘገበውን አቡ ሰዒድ e ያስተላለፈውን የሚከተለውን
የረሡል ‫ﷺ‬ ሐዲስ ነው፡-
=
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 6/60

(አላህ b “በአየተል ኩርስይ” ነፍሱን የገለጸበት)

በመጽሐፉ ውስጥ ነፍሱን የገለጸበት ፣ ከአንቀጾች ሁሉ ትልቁ የሚከተለው ቁርኣናዊ


አንቀጽ ነው፡-

‫ض َمن ذَا الَّ ِذي‬ ِ ‫السماو‬


ِ ‫ات َوَما ِِف الَْر‬ ََ َّ ِ
‫ِف‬ ‫ا‬‫م‬َ ‫ه‬
ُ َّ‫وم الَ ََتْ ُخ ُذهُ ِسنَةٌ والَ نَـ ْوٌم ل‬
َ ْ ‫﴿اَّلُ الَ إِلَـهَ إِالَّ ُه َو‬
ُ ُّ‫اْلَ ُّي الْ َقي‬
ِ ِ ِ ِِ ِ ِ ٍ ِ ِ ‫ي ْشَع ِعْن َده إِالَّ ِبِِ ْذنِِه يـعلَم ما ب‬
ُ‫ن أَيْدي ِه ْم َوَما َخ ْلَ ُه ْم َوالَ ُُييطُو َن بِ َش ْيء م ْن ع ْلمه إِالَّ بَا ََاء َوس َع ُكْرسيُّه‬ َ َْ َ ُ ْ َ ُ ُ َ
﴾‫ودهُ ِح َْظُ ُه َما َوُه َو الْ َعلِ ُّي الْ َع ِظ ُيم‬
ُ ‫ض َوالَ يَـ ُؤ‬
ِ َّ
َ ‫الس َم َاوات َوال َْر‬
“አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡
ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ
ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢሆን እንጅ
የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን
ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም
(አያውቁም)፡፡ ኩርስይ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡
እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡” አል በቀራህ፡

በዚህ ምክንያት - በሌሊት ውስጥ ይህን አንቀጽ ያነበበ ፣ በእርሱ ላይ ከአላህ የሆነ
ጠባቂ የማይወገድ ፣ እስከሚነጋ ድረስ ሰይጣንም የማይቀርበው ሆነ፡፡
=
"‫"والذي نفسي بيده إنها لتعدل ثلث القرآن‬
“ነፍሴ በእጁ በሆነው (ጌታ) እምላለሁ ፣ እርሷ በእርግጥ የቁርኣንን አንድ ሶስተኛ ትመዝናለች፡፡”

ጸሐፊው የጠቆመው ሙስሊም በቁጥር ላይ የዘገበው ፣ ኡበይ ብን ከዕብ e ያስተላለፈውን


የሚከተለውን ሐዲስ ነው፡-
“አባ ሙንዚር ሆይ! ከአንተ ጋር ካለው የአላህ መጽሐፍ በጣም ትልቁ አንቀጽ ማን እንደሆነ ታውቃለህ?”
በማለት የአላህ መልእክተኛ ጠየቁኝ፡፡ “አላህና መልእክተኛው በጣም አዋቂ ናቸው” የሚል ምላሽ ሰጠሁ፡፡
=
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 7/60
2. የበላይነቱን፣ ቅርብነቱን ፣ ከዚህ በፊትም የነበረ ፣ ወደኋላም የሚቀር መሆኑ
የጸደቀበት

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫اط ُن َوُه َو بِ ُك ِل ََ ْي ٍء َعلِي ٌم‬ ِ


ِ ‫اهر والْب‬ ِ
َ َ ُ َّ‫﴿ ُه َو ْال ََّو ُل َو ْاْلخُر َوالظ‬
“እርሱም ፊትም ያለ ፣ ኋላም ቀሪ ፣ ግልጽም ፣ ቅርብም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን
ሁሉ ዓዋቂ ነው፡፡” አል ሐዲድ፡

ِ ْ ‫﴿وتَـوَّكل علَى‬
ُ ُ‫اْلَ ِي الَّذي َال ََي‬
﴾‫وت‬ َ ْ ََ
“በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡” አል ፉርቃን ፡

አላህ የሚከተሉትን ቁርኣናዊ አንቀጾች ተናግሯል፡-


ْ ‫﴿ َوُه َو الْ َعلِ ُيم‬
﴾‫اْلَ ِك ُيم‬
“እርሱም አዋቂው ፣ ጥበበኛው ነው፡፡” አት ተህሪም፡

ْ ‫اْلَ ِك ُيم‬
﴾ُ‫اْلَبِي‬ ْ ‫﴿ َوُه َو‬
“እርሱም ጥበበኛው ፣ ውስጠ ዐዋቂው ነው” ሰበእ፡

=
“አባ ሙንዚር ሆይ! ከአንተ ጋር ካለው የአላህ መጽሐፍ በጣም ትልቁ አንቀጽ ማን እንደሆነ
ታውቃለህ?” በማለት በድጋሜ ጠየቁኝ፡፡ “አሏሁ ላኢላሃ ኢልላ ሁወ አልሀዩል ቀዩም” አልኳቸው፡፡
ደረቴን መቱኝ፡፡ ከዚያም “አባሙንዚር ሆይ! ወሏሂ በዚህ እውቀት አንተ ደስተኛ ነህ (እንኳን ደስ
አለህ)” አሉኝ፡፡

ኢብን አልቀይም I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “መልእክተኞችና የእነርሱ ተከታዮች የሚከተለውን


ተናግረዋል፡ - 'አላህ ህያው ነው ፤ ለእርሱ ህይዎት አለው፡፡ በህይዎቱ አንዳችም እርሱን የሚመስል
የለም፡፡' በዚህ አንቀጽ ውስጥ ህይዎቱ የተሟላ በመሆኑ ሞትን አራቆተ፡፡”
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 8/60

3. እውቀቱ አጠቃላይ ፍጡራንን ያካበበ መሆኑ የጸደቀበት


﴾‫الس َماء َوَما يَـ ْعُر ُج فِ َيها‬ ِ ‫﴿يَـ ْعلَ ُم َما يَلِ ُج ِِف ْال َْر‬
َّ ‫ض َوَما ََيُْر ُج ِمْنـ َها َوَما يَن ِزُل ِم َن‬
“በምድር ውስጥ የሚገባውን ሁሉ ፣ ከእርሷም የሚወጣውን ፣ ከሰማይም
የሚወርደውን ፣ በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ሁሉ ያውቃል፡፡” ሰበእ፡

‫ط ِمن َوَرقٍَة إِالَّ يَـ ْعلَ ُم َها َوالَ َحبَّ ٍة‬ ِ ‫ندهُ َمَاتِح الْغَْي‬
ُ ‫ب الَ يَـ ْعلَ ُم َها إِالَّ ُه َو َويَـ ْعلَ ُم َما ِِف الْ َِب َوالْبَ ْح ِر َوَما تَ ْس ُق‬ ُ َ ‫﴿ َو ِع‬
ٍ ِ‫اب ُّمب‬ٍ َ‫س إِالَّ ِِف كِت‬ ٍ ِ‫ب َوالَ ََيب‬ ٍ ْ‫ض والَ رط‬ ِ
﴾‫ن‬ َ َ ِ ‫ِِف ظُلُ َمات ال َْر‬
“የሩቅ ነገርም መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ከእርሱ በቀር ማንም
አያውቃቸውም፡፡ በየብስና በባህር ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ከቅጠልም
አንዲትም አትረግፍም የሚያውቃት ቢሆን እንጅ፡፡ ከቅንጣትም በመሬት
ጨለማዎች ውስጥ የለም ከእርጥብም ከደረቅም አንድም የለም ግልጽ በሆነው
መጽሐፍ ውስጥ (የተመዘገበ) ቢሆን እንጅ፡፡” አል አንዓም፡

﴾‫ض ُع إَِّال بِعِْل ِم ِه‬ ِ


َ َ‫﴿ َوَما ََْت ِم ُل م ْن أُنثَى َوَال ت‬
“ሴትም አታረግዝም አትወልድምም ፣ በዕውቀቱ ቢሆን እንጂ፡፡” ፋጢር፡

﴾‫َحا َط بِ ُك ِل ََ ْي ٍء ِع ْل اما‬
َ ‫اَّلَ قَ ْد أ‬ َّ ‫اَّلَ َعلَى ُك ِل ََ ْي ٍء قَ ِد ٌير َوأ‬
َّ ‫َن‬ َّ ‫﴿لِتَـ ْعلَ ُموا أ‬
َّ ‫َن‬
“አላህ በነገሩ ሁሉ ቻይ መሆኑን ፣ አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት ያካበበ
መሆኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)” አጥ ጦላቅ፡

﴾‫ن‬ ِ ِ َّ ‫﴿إِ َّن‬


ُ ‫اق ذُو الْ ُق َّوة الْ َمت‬
ُ ‫الرَّز‬
َّ ‫اَّلَ ُه َو‬
“አላህ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ሃይል ባለቤት ነው፡፡” አዝ ዛሪያት፡

4. መስማትና መመልከት የተባሉ ባህሪያቶች የጸደቁበት


ِ ‫الس ِميع الب‬
﴾ُ‫صي‬ َّ ‫و‬ ‫ه‬ ‫و‬ ‫ء‬ ‫ي‬ َ
َ ِ ِ‫﴿لَيس َك ِمثْل‬
‫ه‬
َ ُ ُ
َ َ ٌْ َ ْ
“የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ፣ ተመልካቹ ነው፡፡”(አሽ’ሹራ፡ 11)
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 9/60
ِ ‫﴿إِ َّن اَّل نِعِ َّما يعِظُ ُكم بِِه إِ َّن اَّل َكا َن ََِسيعا ب‬
﴾‫ص ايا‬ َ ‫ا‬ َ َ َ
“አላህ በርሱ የሚገስጻችሁ ነገር ምን ያምር! አላህ ሰሚ ፣ ተመልካች ነው፡፡”
አን ኒሳእ፡

5. “መሽአ” እና “ኢራዳ” የተባሉ ባህሪያት የጸደቁበት

﴾ِ‫اَّلُ َال قُـ َّوَة إَِّال ِِب ََّّل‬


َّ ‫ت َما ََاء‬
َ ‫ك قُـ ْل‬ َ ‫﴿ َولَ ْوَال إِ ْذ َد َخ ْل‬
َ َ‫ت َجنـَّت‬
“አትክልትህንም በገባህ ጊዜ አላህ የሻው ይሆናል ፤ በአላህ ቢሆን እንጂ ሀይል
የለም ፤ አትልም ኖሯልን?” አል ካህፍ፡

ِ َ‫﴿ولَو ََاء اَّل ما اقْـتَـتَـلُواْ ول‬


ُ ‫ـك َّن اَّلَ يَـ َْ َع ُل َما يُِر‬
﴾‫يد‬ َ َُ َْ
“አላህም በሻ ኖሮ ባልተዋጉ ነበር፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ይሰራል፡፡” አል በቀራህ፡

ُ ‫الصْي ِد َوأَنتُ ْم ُحُرٌم إِ َّن اَّلَ َُْي ُك ُم َما يُِر‬


﴾‫يد‬ َّ ‫يمةُ الَنْـ َع ِام إِالَّ َما يـُْتـلَى َعلَْي ُك ْم َغ ْ َي ُِملِي‬ِ
َ ‫ت لَ ُكم ََب‬
ِ
ْ َّ‫﴿أُحل‬
“በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል ፣ የከብት ፣ የበግና የፍየል
እንስሳዎች እናንተ በሐጅ ስራ ላይ ሆናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደርጉ ለእናንተ
ተፈቀዱ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡” አል ማኢዳህ፡

َّ َ‫ضيِ اقا َحَر اجا َكأَََّّنَا ي‬ ِ ِ ِ ِ ِ


‫ص َّع ُد ِِف‬ َ ‫ص ْد َرهُ ل ِإل ْسَلَم َوَمن يُِرْد أَن يُضلَّهُ ََْي َع ْل‬
َ ُ‫ص ْد َره‬ َ ‫﴿فَ َمن يُِرد اَّلُ أَن يَـ ْهديَهُ يَ ْشَر ْح‬
﴾‫الس َماء‬
َّ
“አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ደረቱን (ልቡን) ለኢስላም ይከፍትለታል፡፡
ሊያጠመውም የሚሻውን ሰው ደረቱን ጠባብ ፣ ቸጋራ ወደ ሰማይ ለመውጣት
እንደሚታገል ያደርገዋል፡፡” አል አንዓም፡

6. ፍቅርና ውዴታ የጸደቁበት


﴾‫ن‬ ِِ ُّ ‫َح ِسنُـ َواْ إِ َّن اَّلَ ُُِي‬
َ ‫ب الْ ُم ْحسن‬ ْ ‫﴿ َوأ‬
“በጎ ስራንም ስሩ - አላህ በጎ ሰሪዎችን ይወዳልና፡፡” አል በቀራህ፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 10/60

﴾‫ن‬ ِِ ُّ ‫اَّلَ ُُِي‬


َّ ‫﴿ َوأَقْ ِسطُوا إِ َّن‬
َ ‫ب الْ ُم ْقسط‬
“አስተካክሉም ፣ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና፡፡” አል ሑጁራት፡

﴾‫ن‬ ِ ُّ ‫﴿فَما استـ َقامواْ لَ ُكم فَاست ِقيمواْ َْلم إِ َّن اَّل ُُِي‬
َ ‫ب الْ ُمتَّق‬ َ ُْ ُ َ ْ ْ ُ َ ْ َ
“ለእናንተ ቀጥ እስካሉላችሁ ድረስ ለነርሱም ቀጥ በሉላቸው - አላህ
ጥንቁቆችን ይወዳልና፡፡” አት ተውባህ፡

ِ ُّ ‫ن َوُُِي‬
َ ‫ب الْ ُمتَطَه ِر‬
﴾‫ين‬ ُّ ‫﴿إِ َّن اَّلَ ُُِي‬
َ ِ‫ب التـ ََّّواب‬
“አላህ (ከሐጢያት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል
በላቸው፡፡” አል በቀራህ፡

﴾ُ‫﴿قُ ْل إِن ُكنتُ ْم َُِتبُّو َن اَّلَ فَاتَّبِعُ ِوِن ُُْيبِْب ُك ُم اَّل‬


“በላቸው፡- “አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ- አላህ
ይወዳችኋልና፡፡” አል ዒምራን፡

﴾ُ‫ف ََيِِْت اَّلُ بَِق ْوٍم ُُِيبُّـ ُه ْم َوُُِيبُّونَه‬


َ ‫﴿فَ َس ْو‬
“አላህ (በነርሱ ስፍራ) የሚወዳቸውንና የሚወዱትን በእርግጥ ያመጣል፡፡”
አል ማኢዳህ፡

ِِ ِ ِ َّ ُّ ‫اَّل ُُِي‬ ِ
﴾ٌ‫و‬
ٌ ‫ص‬ َ ‫ين يـُ َقاتلُو َن ِِف َسبِيله‬
ُ ‫ص ًَّا َكأ ََّّنُم بُنيَا ٌن َّمْر‬ َ ‫ب ال ذ‬ ََّ ‫﴿إ َّن‬
“አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደተደረደረ ግንብ የተሰለፉ ሆነው በመንገዱ
(በሃይማኖቱ) የሚጋደሉትን ይወዳል፡፡” አስ ሶፍ፡

﴾‫ود‬
ُ ‫ور الْ َوُد‬
ُ َُ َ‫﴿ َوُه َو الْغ‬
“እርሱም ምሕረተ ብዙ ፣ ወዳድ ነው፡፡” አል ቡሩጅ፡

7. እዝነትና ምህረት የጸደቁበት


አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 11/60

﴾‫الرِحي ِم‬ َّ ِ‫اَّل‬


َّ ‫الر ْْحَ ِن‬ َّ ‫﴿بِ ْس ِم‬
“በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡” አን ነምል፡

﴾‫ت ُك َّل ََ ْي ٍء َّر ْْحَةا َو ِع ْل اما‬ ِ


َ ‫﴿ َربـَّنَا َوس ْع‬
“ጌታችን ሆይ ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በዕውቀት ከበሃል፡፡” ጋፊር፡

﴾‫يما‬ ِ ِ‫﴿وَكا َن ِِبلْم ْؤِمن‬


‫ن َرح ا‬
َ ُ َ
“ለአማኞች በጣም አዛኝ ነው፡፡” አል አህዛብ፡

﴾‫ت ُك َّل ََ ْي ٍء‬ ِ


ْ ‫﴿ َوَر ْْحَِِت َوس َع‬
“ችሮታዬም ነገሩን ሁሉ ሰፋ፡፡” አል አዕራፍ፡

َّ ‫ب َربُّ ُك ْم َعلَى نَـ َْ ِس ِه‬


﴾َ‫الر ْْحَة‬ َ َ‫﴿ َكت‬
“ጌታችሁ በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡” አል አንዓም፡

﴾‫الرِح ُيم‬
َّ ‫ور‬
ُ َُ َ‫﴿ َوُه َو الْغ‬
“እርሱም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡” ዩኑስ፡

﴾‫ن‬ ِِ َّ ‫﴿فَاَّل خي حافِظاا وهو أَرحم‬


َ ‫الراْح‬ ُ َ ْ َ ُ َ َ ٌْ َ ُ
“አላህም በጠባቂነት (ከሁሉ) የበለጠ ነው፡፡ እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ
አዛኝ ነው፡፡” ዩሱፍ፡

8. ውዴታ ፣ ቁጣ እና ጥላቻ የጸደቁበት


ُ ‫﴿ َّر ِض َي اَّلُ َعْنـ ُه ْم َوَر‬
﴾ُ‫ضواْ َعْنه‬
“አላህ ከእነርሱ ወደደ ፤ እነርሱም ከእርሱ ወደዱ፡፡” አል ማኢዳህ፡

﴾ُ‫ب اَّلُ َعلَْي ِه َولَ َعنَه‬ ِ ِ ِ ِ ِ


َ ‫﴿ َوَمن يَـ ْقتُ ْل ُم ْؤمناا ُّمتَـ َعم ادا فَ َجَز ُآؤهُ َج َهن َُّم َخال ادا ف َيها َو َغض‬
“አማኞችን አስቦ የሚገድል ሰው ቅጣቱ በውስጧ ዘውታሪ ሲሆን ጀሐነም ናት፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 12/60

አላህ በርሱ ላይ ተቆጣ ፤ ረገመውም፡፡” አን ኒሳእ፡

ِ
﴾‫ط أ َْع َما َْلُْم‬
َ َ‫َحب‬ ْ ‫اَّلَ َوَك ِرُهوا ِر‬
ْ ‫ض َوانَهُ فَأ‬ َّ ‫ط‬ ْ ‫ك ِِب ََّّنُُم اتَّـبَـعُوا َما أ‬
َ ‫َس َخ‬ َ ‫﴿ َذل‬
“ይህ እነርሱ አላህን ያስቆጣውን ነገር ስለ ተከተሉ ውዴታውንም ስለ ጠሉ ነው፡፡
ስለዚህ ስራዎቻቸውን አበላሸባቸው፡፡” ሙሐመድ፡

﴾‫وَن انتَـ َق ْمنَا ِمْنـ ُه ْم‬


َ َُ ‫آس‬
َ ‫﴿فَـلَ َّما‬
“ባስቆጡንም ጊዜ ፣ ከእነርሱ ተበቀልን፡፡” አዝ ዙኽሩፍ፡

ِ َ‫﴿ول‬
﴾‫ـكن َك ِرَه اَّلُ انبِ َعاثَـ ُه ْم فَـثَـبَّطَ ُه ْم‬ َ
“ግን አላህ (ለመውጣት) እንቅስቃሴያቸውን ጠላ (አልሻውም)፡፡” አት ተውባህ፡

﴾‫اَّلِ أَن تَـ ُقولُوا َما َال تَـ َْ َعلُو َن‬ َ ‫﴿ َك َُب َم ْقتاا ِع‬
َّ ‫ند‬
“የማትሰሩትን ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ፡፡” አስ ሶፍ፡

9. አላህ በባሮች መካከል ፍርድ ሊሰጥ የሚመጣ መሆኑ


የጸደቀበት
ِ ُ‫﴿هل ينظُرو َن إِالَّ أَن َيْتِيـهم اَّل ِِف ظُلَ ٍل ِمن الْغَم ِام والْمئآلِِ َكةُ وق‬
﴾‫ض َي ال َْمُر‬ َ َ َ َ َ ُ َُُ َ ُ ََْ
“የአላህን ከደመና በሆኑ ጥላዎች ጋር መምጣት ፣ የመላእክቱንም

(መምጣትን) እና የነገሩን መፈጸም እንጅ አይጠባበቁም፡፡” አል በቀራህ፡

ِ ‫ك أَو َيِِْت بـعآ آَي‬


َ ِ‫ت َرب‬ ِ ِ ِ
﴾‫ك‬ َ ُ ْ َ َ َ ْ َ ُّ‫﴿ َه ْل يَنظُُرو َن إالَّ أَن ََتْت ُيه ُم الْ َمئآلِ َكةُ أ َْو ََيِِْتَ َرب‬
“መላእክት ልትመጣላቸው ወይም ጌታህ ሊመጣ ወይም ከጌታህ ምልክቶች
ከፊሉ ሊመጣ እንጂ ይጠባበቃሉን?” አል አንዓም፡

ِ
﴾‫ص ًَّا‬
َ ‫ص ًَّا‬
َ ‫ك‬
ُ َ‫ك َوالْ َمل‬ ُ ‫﴿ َك ََّل إِ َذا ُد َّكت ْال َْر‬
َ ُّ‫ض َد ًّكا َد ًّكا۞ َو َجاء َرب‬
“ተው ፤ ምድር ደጋግማ በተሰባበረች ጊዜ ፣ መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ሆነው ፣
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 13/60

ጌታህ በመጣ ጊዜ፡፡” አል ፈጅር፡

﴾‫الس َماء ِِبلْغَ َم ِام َونـُ ِزَل الْ َم ََلِِ َكةُ تَن ِز ايَل‬
َّ ‫﴿ َويَـ ْوَم تَ َش َّق ُق‬
“ሰማይም በደመና የምትቀደድበትንና መላእክትንም መወረድን
የሚወርድበትን ቀን (አስታውስ)” አል ፉርቃን፡

10. ፊት የተሰኘ መገለጫ የጸደቀበት


ِْ ‫اْلَََل ِل و‬
﴾‫اْل ْكَرِام‬ َ ِ‫﴿ َويَـْبـ َقى َو ْجهُ َرب‬
َ ْ ‫ك ذُو‬
“የልቅናና የልግስና ባለቤት የሆነው (በዛቱ ላይ ቋሚ የሆነው) የጌታህ ፊትም
ይቀራል፡፡” አር ረህማን፡

ٍ
ٌ ِ‫﴿ ُك ُّل ََ ْيء َهال‬
﴾ُ‫ك إَِّال َو ْج َهه‬
“(በአላህ ዛት ቋሚ የሆነው) ፊቱ ሲቀር ነገሩ ሁሉ ጠፊ ነው፡፡” አል ቀሶስ፡

11. ሁለት እጆች የጸደቁበት


َّ ‫ت بِيَ َد‬
﴾‫ي‬ ِ ِ ِ َ َ‫﴿ق‬
ُ ‫ك أَن تَ ْس ُج َد ل َما َخلَ ْق‬
َ ‫يس َما َمنَـ َع‬
ُ ‫ال ََي إبْل‬
“በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ?” ሷድ፡

ِ ِ ِ ِ ِ َّ‫ت الْيـهود ي ُد اَّلِ م ْغلُولَةٌ غُل‬


ِ
َ ‫ت أَيْدي ِه ْم َولُعنُواْ بَا قَالُواْ بَ ْل يَ َداهُ َمْب ُسوطَتَان يُنَ ُق َكْي‬
﴾‫ف يَ َشاء‬ ْ َ َ ُ ُ َ َ‫﴿ َوقَال‬
“አይሁዶችም “የአላህ እጅ የታሰረች ናት” አሉ፡፡ እጆቻቸው ይታሰሩ ፣
በተናገሩበትም ነገር ይረገሙ፡፡ አይደለም ፣ (የአላህ) እጆቹ የተዘረጉ ናቸው፡፡
እንደሚሻ ይለግሳል፡፡” አል ማኢዳህ፡

12. ሁለት አይኖች የጸደቁበት


ِ َ ِ‫ك ِِب َْعينِنَا وسبِح ِِبم ِد رب‬ ِ َ ِ‫اصِب ِْل ْك ِم رب‬
﴾‫وم‬
ُ ‫ن تَـ ُق‬
َ ‫كح‬ َ ْ َ ْ َ َ ُ َ َّ‫ك فَإن‬ َ ُ ْ ْ ‫﴿ َو‬
“ለጌታህ ፍርድም ታገስ፡፡ አንተ በአይኖቻችን (ክትትል) ውስጥ ነህና፡፡” አጥ ጡር፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 14/60

﴾‫ات أَلْ َو ٍاح َوُد ُس ٍر۞ ََْت ِري ِِب َْعيُنِنَا َجَزاء لِ َمن َكا َن ُك ََِر‬
ِ َ‫﴿و َْح ْلنَاه علَى ذ‬
َُ َ َ
“ባለሳንቃዎችና ባለሚስማሮች በሆነችም ታንኳ ላይ ጫንነው፡፡ በአይኖቻችን
(በክትትላችን) ሆና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረው ሰው ምንዳ (ይህንን
ሰራን)፡፡” አል ቀመር፡

﴾‫صنَ َع َعلَى َعْي ِّن‬ ِ ِ


ْ ُ‫ك َمَبَّةا م ِّن َولت‬ ُ ‫﴿ َوأَلْ َقْي‬
َ ‫ت َعلَْي‬
“ባንተ ላይም ከእኔ የሆነን መውደድ ጣልኩብህ፡፡ በዓይኔ (በክትትሌ) ልታድግ
ዘንድ፡፡” ጦሃ፡

13. መስማትና መመልከት የተባሉ ባህሪያቶች የጸደቁበት


ِ ‫اَّل يسمع ََتاورُكما إِ َّن ا ََّّل ََِسيع ب‬
﴾ٌ‫صي‬ َِّ ‫اَّل قَـوَل الَِِّت َُت ِادلُك ِِف زوِجها وتَ ْشت ِكي إِ ََل‬ ِ
ٌَ َ َ َ ُ َ ُ َ ْ َ َُّ ‫اَّل َو‬ َ َ َ َْ َ َ ْ َُّ ‫﴿قَ ْد ََس َع‬
“አላህ የዚያችን በባሏ (ነገር) የምትከራከርህንና ወደ አላህ የምታሰሙተውን
(ሴት) ቃል በእርግጥ ሰማ፡፡ አላህም (በንግግር) መመላለሳችሁን ይሰማል፡፡
አላህ ሰሚ ፣ ተመልካች ነውና፡፡” አል ሙጃደላህ፡

﴾‫ين قَالُواْ إِ َّن اَّلَ فَِقيٌ َوََْن ُن أَ ْغنِيَاء‬


َ
ِ َّ‫﴿لََّق ْد ََِسع اَّل قَـوَل ال‬
‫ذ‬ ْ ُ َ
“የእነዚያን 'አላህ ድሃ ነው ፣ እኛ ግን ከበርቴዎች ነን' ያሉትን ሰዎች ቃል አላህ
በእርግጥ ሰማ፡፡” አል ዒምራን፡

﴾‫﴿أ َْم َُْي َسبُو َن أ َََّن َال نَ ْس َم ُع ِسَّرُه ْم َوََْن َو ُاهم بَـلَى َوُر ُسلُنَا لَ َديْ ِه ْم يَ ْكتُـبُو َن‬
“ወይም እኛ ምስጢራቸውንና ውይይታቸውን የማንሰማ መሆናችንን
ያስባሉን? አይደለም ፤ መልክተኞቻችንንም እነርሱ ዘንድ ይጽፋሉ፡፡” አዝ ዙኽሩፍ፡

ْ ‫ال َال ََتَافَا إِنَِّّن َم َع ُك َما أ‬


﴾‫ََسَ ُع َوأ ََرى‬ َ َ‫﴿ق‬
“(አላህም) አለ 'አትፍሩ - እኔ በእርግጥ ከእናንተ ጋር ነኝና፡፡ እሰማለሁ ፤
አያለሁም፡፡” ጦሃ፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 15/60

﴾‫اَّلَ يَـَرى‬ َّ ‫﴿أَََلْ يَـ ْعلَ ْم ِِب‬


َّ ‫َن‬
“አላህ የሚያይ መሆኑን አያውቅምን?” አል ዓለቅ፡

﴾‫يع الْ َعلِ ُيم‬ ِ َّ ‫اج ِدين۞إِنَّه هو‬


ُ ‫السم‬ َ ُ ُ َ ‫الس‬
ِ َّ ‫﴿الَّ ِذي يـر َاك ِحن تَـ ُقوم۞وتَـ َقلُّبك ِِف‬
ََ َ ُ َ ََ
“በዚያ ለሶላት በምትቆም ጊዜ የሚመለከትህ፡፡ በሰጋጆች ውስጥ
መዘዋወርህንም (በሚመለከተው ጌታህ ላይ ተጠጋ)፡፡” አሽ ሹዓራ፡

﴾‫﴿ َوقُ ِل ْاع َملُواْ فَ َس ََيى اَّلُ َع َملَ ُك ْم َوَر ُسولُهُ َوالْ ُم ْؤِمنُو َن‬
“በላቸውም ፡- 'ስሩ አላህ ስራችሁን በእርግጥ ይመለከታልና፡፡ መልክተኛውና
ምእምናንም (እንደዚሁ ይመለከታሉ)፡፡” አት ተውባህ፡

14. አድማ ፣ ሴራ የተባሉ ባህሪያቶች የጸደቁበት


ُ ‫﴿ َوُه َو ََ ِد‬
﴾‫يد الْ ِم َح ِال‬
“እርሱም ሐይለ ብርቱ ነው፡፡” (አር’ረዕድ፡ 13)
﴾‫ين‬
‫ر‬ِ ِ‫﴿وم َكرواْ وم َكر اَّل واَّل خي الْماك‬
َ َ ُْ َ ُ َ ُ َ َ َ ُ َ َ
“(አይሁዶችም) አደሙ አላህም አደመባቸው ፤ አላህም ከአድመኞች ሁሉ
በላጭ ነው፡፡” አል ዒምራን፡

﴾‫﴿ َوَم َكُروا َم ْكارا َوَم َكْرََن َم ْكارا َوُه ْم َال يَ ْشعُُرو َن‬
“አድማን አደሙ ፣ እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ አድማን አደምንባቸው፡፡” አን ነምል፡

ُ ِ‫يدو َن َكْي ادا۞ َوأَك‬


﴾‫يد َكْي ادا‬ ُ ‫﴿إِ َّّنُْم يَ ِك‬
“እነርሱ በእርግጥ አድማን ያድማሉ፡፡ (እኔም) አድማን አድምባቸዋለሁ፡፡”
አጥ ጧሪቅ፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 16/60

15. ይቅር ባይነት ፣ መሐሪነት ፣ አዛኝነት ፣ አሸናፊነት እና ቻይነት


የጸደቁበት
﴾‫﴿إِن تُـْب ُدواْ َخ ْ ايا أ َْو َُتْ َُوهُ أ َْو تَـ ْع َُواْ َعن ُس َوٍء فَِإ َّن اَّلَ َكا َن َع َُ ًّوا قَ ِد ايرا‬
“ደግ ነገርን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁ ወይም ከመጥፎ ነገር (ከበደል)
ይቅርታ ብታደርጉ ፣ አላህ ይቅር ባይ ሃያል ነው፡፡ አን ኒሳእ፡

﴾‫ور َّرِح ٌيم‬ َّ ‫صَ ُحوا أََال َُِتبُّو َن أَن يَـ ْغ ََِر‬
ٌ َُ ‫اَّلُ لَ ُك ْم َوا ََّّلُ َغ‬ ْ َ‫﴿ َولْيَـ ْع َُوا َولْي‬
“ይቅርታንም ያድርጉ ፡፡ (ጥፋተኞቹን) ይለፉም፡፡ አላህ ለእናንተ ሊምር
አትወዱምን ? አላህም መሃሪ አዛኝ ነው፡፡” አን ኑር፡

﴾‫ن‬ ِ ِ ِ ِِ ِ ِ ِ ِ
َ ‫﴿ َو ََّّل الْعَّزةُ َولَر ُسوله َول ْل ُم ْؤمن‬
“አሸናፊነትም ለአላህ ፣ ለመልእክተኛውና ለምእምናን ነው፡፡” አል ሙናፊቁን፡

﴾‫ن‬ ِ ْ ‫ك َلُ ْغ ِويـنـَّهم أ‬


َ ِ‫ال فَبِعَِّزت‬
َ ‫َْجَع‬ ُْ َ َ َ‫﴿ق‬
“(እርሱም) አለ 'በአሸናፊነትህ ይሁንብኝ ፤ በመላ አሳስታቸዋለሁ፡፡” ሷድ፡

16. ለአላህ ስም የጸደቀበትና ከእርሱ ላይ ተመሳሳይነት


የተራቆተበት
ِْ ‫اْلَََل ِل و‬
﴾‫اْل ْكَرِام‬ ْ ‫ي‬‫ذ‬ِ ‫﴿تَـبارَك اسم ربِك‬
َ َ َ ُْ ََ
“የግርማና የክብር ባለቤት የሆነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡” አር ረህማን፡

﴾‫اصطَِ ْب لِعِبَ َادتِِه َه ْل تَـ ْعلَ ُم لَهُ ََِسيًّا‬


ْ ‫اعبُ ْدهُ َو‬
ْ َ‫﴿ف‬
“ተገዛው፡፡ እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን?”
መርየም፡

َ ‫﴿ َوََلْ يَ ُكن لَّهُ ُك َُ اوا أ‬


﴾‫َح ٌد‬
“ለእርሱም አንድም ቢጤ የለውም፡፡” አል ኢኽላስ፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 17/60

َ ‫﴿فََلَ ََْت َعلُواْ َِّلِ أ‬


﴾‫َندادا َوأَنتُ ْم تَـ ْعلَ ُمو َن‬
“እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትሆኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ፡፡”
አል በቀራህ፡

﴾ِ‫ب اَّل‬
ِ ‫وّنُم َك ُح‬ ِ َ ‫ون اَّلِ أ‬
ْ َ ُّ‫َندادا ُُيب‬
ِ ‫َّخ ُذ ِمن د‬
ُ
ِ ‫َّاس من يـت‬ ِ
َ َ ِ ‫﴿ َوم َن الن‬
“ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባላንጣዎችን (ጣዖቶችን) አላህን እንደሚወዱ
የሚወዷቸው ሆነው የሚይዙ አልሉ፡፡” አል በቀራህ፡

17. ለአላህ ባላንጣ የተራቆተበት


ُّ ‫ك َوََلْ يَ ُكن لَّهُ َوِِلٌّ ِم َن‬
﴾‫الذ َّل َوَكِ ْبهُ تَ ْكبِ ايا‬ ِ ‫ك ِِف الْم ْل‬ ِ ِ ‫َّل الَّ ِذي ََل يـت‬
َّ‫َّخ ْذ ولَ ادا وََل يَ ُكن ل‬ ِ ِ ‫اْلم ُد‬
ُ ٌ ‫ي‬
‫ر‬ َ
َ ‫ه‬
ُ َ َ َ ْ ْ َْ ‫﴿ َوقُ ِل‬
“ምስጋና ለአላህ ለዚያ ልጅን ላልያዘው ፣ ለእርሱም በንግስናው ተጋሪ የሌለው ፣
ለእርሱ ከውርደት ረዳት ለሌለው ይገባው በልም፡፡ ማክበርንም አክብረው፡፡”
አል ኢስራእ፡

﴾‫اْلَ ْم ُد َوُه َو َعلَى ُك ِل ََ ْي ٍء قَ ِد ٌير‬


ْ ُ‫ك َولَه‬ ِ ‫السماو‬
ِ ‫ات َوَما ِِف ْال َْر‬
ُ ‫ض لَهُ الْ ُم ْل‬
ِِ ِ
َ َ َّ ‫﴿يُ َسب ُح ََّّل َما ِِف‬
“በሰማያት ውስጥ ያለው በምድርም ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ ያሞግሳል፡፡
ንግስናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ለእርሱ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ
ቻይ ነው፡፡” አት ተጋቡን፡

ِ ‫ض وََل يـت‬ ِ َّ ‫ك‬ ِ ِ ‫﴿تَـبارَك الَّ ِذي نَـَّزَل الْ َُرقَا َن علَى عب ِدهِ لِي ُكو َن لِْلعالَ ِم‬
‫َّخ ْذ‬ َ ْ َ ِ ‫الس َم َاوات َو ْال َْر‬ ُ ‫ن نَذ ايرا۞الَّذي لَهُ ُم ْل‬ َ َ َ َْ َ ْ ََ
﴾‫ك َو َخلَ َق ُك َّل ََ ْي ٍء فَـ َق َّد َرهُ تَـ ْق ِد ايرا‬
ِ ‫يك ِِف الْم ْل‬
ُ ٌ ‫َولَ ادا َوََلْ يَ ُكن لَّهُ ََ ِر‬
“ያ ፣ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ያወረደው
(አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡ (እርሱ) ያ የሰማያትና የምድር ንግስና
የእርሱ ብቻ የሆነ ፣ ልጅንም ያልያዘ ፣ በንግስናውም ተጋሪ የሌለው ፣ ነገሩንም
ሁሉ የፈጠረና ማስተካከልም ያስተካከለው ነው፡፡” አል ፉርቃን፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 18/60
ٍ ‫ض ُه ْم َعلَى بَـ ْع‬
‫آ ُسْب َحا َن‬ ٍ
ُ ‫ب ُك ُّل إِلَه ِبَا َخلَ َق َولَ َع ََل بَـ ْع‬ ‫ه‬ ‫ذ‬ َّ‫اَّلُ ِمن ولَ ٍد وَما َكا َن َم َعهُ ِم ْن إِلٍَه إِذاا ل‬ َّ
َ َ َ َ َ َّ ‫﴿ َما اَتَ َذ‬
﴾‫اَل َع َّما يُ ْش ِرُكو َن‬ َ ‫َّه َادةِ فَـتَـ َع‬ ِ ِ ‫صَو َن۞ع‬ ِ َِّ
َ َ ْ َ ُ َ‫اَّل َع َّما ي‬
‫الش‬ ‫و‬ ‫ب‬ ‫ي‬َ‫غ‬‫ل‬
ْ ‫ا‬ ‫اَل‬
“አላህ ምንም ልጅን አልያዘም (አልወለደም)፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም
አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ (ሌላ አምላክ በነበረ) አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር
በተለየ ነበር፡፡ አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡ ሩቁንና ቅርቡንም ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
(በእርሱ) ከሚያጋሩትም ሁሉ ከፍ አለ፡፡” አል ሙእሚኑን፡

َ َ‫ض ِربُواْ َِّلِ ال َْمث‬


﴾‫ال إِ َّن اَّلَ يَـ ْعلَ ُم َوأَنتُ ْم الَ تَـ ْعلَ ُمو َن‬ ْ َ‫﴿فََلَ ت‬
“ለአላህም አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ አላህ (መሳይ እንደሌለው) ያውቃል፡፡
እናንተ ግን አታውቁም፡፡” አን ነህል፡

‫اْلَِق َوأَن تُ ْش ِرُكواْ ِِبَّلِ َما ََلْ يـُنَـ ِزْل بِِه‬


ْ ‫ش َما ظَ َهَر ِمْنـ َها َوَما بَطَ َن َوا ِْل ْثَ َوالْبَـ ْغ َي بِغَ ِْي‬ ِ َِّ
َ ِ‫﴿قُ ْل إَّنَا َحَّرَم َر‬
َ ‫ّب الَْ َواح‬
﴾‫اَن َوأَن تَـ ُقولُواْ َعلَى اَّلِ َما الَ تَـ ْعلَ ُمو َن‬
‫ُس ْلطَ ا‬
“ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ስራዎችን ፣ ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን
ሀጢአትንም ፣ ያላግባብ መበደልንም ፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን
(ጣኦት) በአላህ ማጋራታችሁን ፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን
ብቻ ነው” በላቸው፡፡” አል አዕራፍ፡

18. አላህ ከዓርሽ በላይ ከፍ ማለቱ የጸደቀበት

ْ ‫الر ْْحَ ُن َعلَى الْ َعْر ِش‬


﴾‫استَـ َوى‬ َّ ﴿
“(እርሱ) አልረህማን ነው፡፡ በዐርሹ ላይ ሆነ፡፡” ጦሃ፡

ٍ ِ ِ َ ‫ات والَر‬ ِ َّ ‫﴿إِ َّن ربَّ ُكم اَّل الَّ ِذي خلَق‬
ْ َّ‫ض ِِف ستَّة أ َََّيم ُث‬
﴾‫استَـ َوى َعلَى الْ َعْر ِش‬ ْ َ ‫الس َم َاو‬ َ َ ُ ُ َ
“ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናቶች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡
ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ አለ፡፡” አል አዕራፍ፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 19/60
ٍ ِ ِ َ ‫ات والَر‬ ِ َّ ‫﴿إِ َّن ربَّ ُكم اَّل الَّ ِذي خلَق‬
ْ َّ‫ض ِِف ستَّة أ َََّيم ُث‬
﴾‫استَـ َوى َعلَى الْ َعْر ِش‬ ْ َ ‫الس َم َاو‬ َ َ ُ ُ َ
“ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡
ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲሆን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ፡፡” ዩኑስ፡

ٍ ِ َّ ‫﴿اَّل الَّ ِذي رفَع‬


ْ َّ‫الس َم َاوات بِغَ ِْي َع َمد تَـَرْوَّنَا ُث‬
﴾‫استَـ َوى َعلَى الْ َعْر ِش‬ ََ ُ
“አላህ ያ ሰማያትን የምታዩዋትን አእማድ ሳትኖር ያነሳት ነው፡፡ ከዚያም
ከዓርሹ ላይ ሆነ (ከፍ አለ)፡፡” አር ረዕድ፡

ْ ‫الر ْْحَ ُن َعلَى الْ َعْر ِش‬


﴾‫استَـ َوى‬ َّ ﴿
“(እርሱ) አልረህማን ነው፡፡ በዐርሹ ላይ ሆነ፡፡” ጦሃ፡

﴾‫استَـ َوى َعلَى الْ َعْر ِش‬


ْ َّ‫﴿ ُث‬
“ከዚያም ከዓርሽ በላይ ሆነ (ከፍ አለ)፡፡” አል ፉርቃን፡

ٍ ِِ ِ َّ ‫اَّل الَّ ِذي خلَق‬


ْ َّ‫ض َوَما بَـْيـنَـ ُه َما ِِف ستَّة أَ ََّيم ُث‬
﴾‫استَـ َوى َعلَى الْ َعْر ِش‬ َ ‫الس َم َاوات َو ْال َْر‬ َ َ َُّ ﴿
“ያ ፣ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ በስድስት ቀኖች
ውስጥ የፈጠረ ፣ ከዚያም ከዐርሹ በላይ ሆነ (ከፍ አለ)፡፡” አስ ሰጅዳህ፡

ٍ ِ ِ َ ‫ات و ْالَر‬ ِ َّ ‫﴿هو الَّ ِذي خلَق‬


ْ َّ‫ض ِِف ستَّة أ َََّيم ُث‬
﴾‫استَـ َوى َعلَى الْ َعْر ِش‬ ْ َ ‫الس َم َاو‬ َ َ َُ
“እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ፤ ከዚያም
ከአርሽ በላይ ሆነ (ከፍ አለ)፡፡” አል ሐዲድ፡

19. አላህ ከፍጡራኖች ሁሉ በላይ መሆኑ የጸደቀበት


ََّ ِ‫ك إ‬ ِ ِ ِ
﴾‫ِل‬ َ ‫يسى إِِِن ُمتَـ َوف‬
َ ُ‫يك َوَرافع‬ َ ‫﴿ ََي ع‬
“ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ፣ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡” አል ዒምራን፡

﴾‫﴿بَل َّرفَـ َعهُ اَّلُ إِلَْي ِه‬


“ይልቁንስ አላህ (ኢሳን) ወደርሱ አነሳው፡፡” አን ኒሳእ፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 20/60
﴾ُ‫الصالِ ُح يَـْرفَـعُه‬ ِ ِ ِ
ْ َ‫﴿إِلَْيه ي‬
ُ ‫ص َع ُد الْ َكل ُم الطَّي‬
َّ ‫ب َوالْ َع َم ُل‬
“መልካም ንግግር ወደርሱ ይወጣል፡፡ በጎ ስራም (መልካም ንግግርን) ከፍ
ያደርገዋል፡፡” ፋጢር፡

‫وسى َوإِِِن‬ ‫م‬ َِ‫ات فَأَطَّلِع إِ ََل إِل‬


‫ه‬ ِ ‫السماو‬ ‫اب‬‫ب‬ ‫َس‬‫أ‬ ‫اب‬ ‫ب‬ ‫َس‬‫ال‬ ‫غ‬ ‫ل‬ ‫ـ‬‫ب‬َ‫أ‬ ‫ي‬ِ‫ال فِرعو ُن َي هاما ُن اب ِن ِِل صرحا لَّعل‬
َ ُ َ ََ َّ َ َ ْ ۞ َ َ ْ ْ ُ ُ ْ َ ‫َْ ا‬ ْ َ َ َ ْ َ ْ َ َ‫﴿ َوق‬
﴾‫َلَظُنُّهُ َك ِاذ اِب‬
“ሃማን ሆይ! መንገዶችን እደርስ ዘንድ ረዢም ሕንጻን ለእኔ ካብልኝ ፣
የሰማያትን መንገዶች (እደርስ ዘንድ) ፣ ወደ ሙሳም አምላክ እመለከት ዘንድ፡፡
እኔም ውሸታም ነው ብዬ በእርግጥ እጠረጥረዋለሁ፡፡” ጋፊር፡

‫الس َماء أَن يـُْرِس َل َعلَْي ُك ْم‬


َّ ‫ور۞أ َْم أ َِمنتُم َّمن ِِف‬ ِ ِ ‫السماء أَن ََيْ ِسف بِ ُكم الَر‬ ِ
ُ ُ‫ض فَإ َذا ه َي ََت‬
َ ْ ُ َ َ َّ ‫﴿أَأَمنتُم َّمن ِِف‬
ِ ‫ح‬
﴾‫اصباا‬ َ
“በሰማይ ላይ ያለው (አሏህ) በእናንተ ምድርን ቢደረምስባችሁ ፣
ወዲያውም እርሷ የምታረገርግ ብትሆን ትተማመናላችሁን?” (አትፈሩምን?)
፤ ወይም በሰማይ ላይ ያለው (አሏህ) በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን
ቢልክባችሁ ትተማመናላችሁ? (አትፈሩምን?) አል ሙልክ፡

20.የአላህ ከፍጡራን ጋር (በእውቀቱ ፣ በእርዳታው ..) አብሮ መሆን


የጸደቀበት
ِ ‫استَـ َوى َعلَى الْ َعْر ِش يَـ ْعلَ ُم َما يَلِ ُج ِِف ْال َْر‬
‫ض َوَما ََيُْر ُج‬ ٍ ِ ِ َ ‫ات و ْالَر‬
ْ َّ‫ض ِِف ستَّة أ َََّيم ُث‬
ِ َّ ‫﴿هو الَّ ِذي خلَق‬
ْ َ ‫الس َم َاو‬ َ َ َُ
﴾ٌ‫صي‬ِ ‫اَّل ِبَا تَـعملُو َن ب‬ ِ َّ ‫ِمْنـ َها َوَما يَن ِزُل ِم َن‬
َ َ ْ َُّ ‫الس َماء َوَما يَـ ْعُر ُج ف َيها َوُه َو َم َع ُك ْم أَيْ َن َما ُكنتُ ْم َو‬
“እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ፤ ከዚያም
በአርሽ ላይ ሆነ ፡፡ በምድር ውስጥ የሚገባውን ፣ ከእርሷም የሚወጣውን ፣
ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ያውቃል፡፡ እርሱም
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 21/60
የትም ብትሆኑ (በእውቀቱ) ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አላህም የምትሰሩትን ሁሉ
ተመልካች ነው፡፡” አል ሐዲድ፡

‫ض َما يَ ُكو ُن ِمن ََّْن َوى ثَََلثٍَة إَِّال ُه َو َرابِعُ ُه ْم َوَال َخَْ َس ٍة إَِّال‬ ِ ‫السماو‬
ِ ‫ات َوَما ِِف ْال َْر‬ َ َ َّ ‫اَّلَ يَـ ْعلَ ُم َما ِِف‬ َّ ‫﴿أَََلْ تَـَر أ‬
َّ ‫َن‬
َّ ‫ك َوَال أَ ْكثَـَر إَِّال ُه َو َم َع ُه ْم أَيْ َن َما َكانُوا ُثَّ يـُنَـبِئُـ ُهم ِبَا َع ِملُوا يَـ ْوَم الْ ِقيَ َام ِة إِ َّن‬
َ‫اَّل‬
ِ ِ
َ ‫ُه َو َساد ُس ُه ْم َوَال أ َْد ََن ِمن ذَل‬
﴾‫بِ ُك ِل ََ ْي ٍء َعلِ ٌيم‬
“አላህ በሰማያት ውስጥ ያለውን በምድርም ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ
መሆኑን አታይምን? ከሶስት ሰዎች መሾካሾክ አይኖርም - እርሱ (በእውቀቱ)
አራተኛቸው ቢሆን እንጅ፡፡ ከአምስትም (አይኖርም) - እርሱ (በእውቀቱ)
ስድስተኛቸው ቢሆን እንጅ፡፡ ከዚያ ያነሰም ፣ የበዛም (አይኖርም) - እርሱ
(በእውቀቱ) የትም ቢሆን እንጂ፡፡ ከዚያም በትንሳኤ ቀን የሰሩትን ሁሉ
ይነግራቸዋል፡፡ አላህ ነገሩን ሁሉ ዓዋቂ ነው፡፡” አል ሙጃደላህ፡

﴾‫﴿الَ ََْتَز ْن إِ َّن اَّلَ َم َعنَا‬


“አትዘን - አላህ (በእገዛው) ከእኛ ጋር ነውና፡፡” አት ተውባህ፡

ْ ‫ال َال ََتَافَا إِنَِّّن َم َع ُك َما أ‬


﴾‫ََسَ ُع َوأ ََرى‬ َ َ‫﴿ق‬
“እኔ በእርግጥ (በእገዛየ) ከእናንተ ጋር ነኝና፡፡ እሰማለሁ ፤ አያለሁም፡፡” ጧሃ፡

﴾‫ين ُهم ُّْم ِسنُو َن‬ ِ َّ ِ َّ ِ


َ ‫﴿إ َّن اَّلَ َم َع الذ‬
َ ‫ين اتَّـ َقواْ َّوالذ‬
“አላህ (በእርዳታው) ከእነዚያ ከሚፈሩትና ከእነዚያም እነሱ መልካም
ሰሪዎች ከሆኑት ጋር ነውና፡፡” አን ነሕል፡

ِ َّ ‫اصِبواْ إِ َّن اَّل مع‬


َ ‫الصاب ِر‬
﴾‫ين‬ ََ َ ُ ْ ‫﴿ َو‬
“ታገሱም - አላህ (በእርዳታው) ከትዕግስተኞች ጋር ነውና፡፡” አል አንፋል፡

﴾‫ين‬ِ
‫ر‬ ِ‫الصاب‬
َّ ‫ع‬ ‫م‬ ‫اَّل‬
‫و‬ ِ‫﴿ َكم ِمن فِئ ٍة قَلِيلَ ٍة َغلَبت فِئةا َكثِياة ِبِِ ْذ ِن اَّل‬
َ ََ ُ َ َ َ َْ َ
“ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት ፤ አላህም
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 22/60
(በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነው” አሉ፡፡ አል በቀራህ፡

21. አላህ ተናጋሪ መሆኑ የጸደቀበት


﴾‫َص َد ُق ِم َن اَّلِ َح ِديثاا‬
ْ ‫﴿ َوَم ْن أ‬
“በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው?” አን ኒሳእ፡

﴾‫َص َد ُق ِم َن اَّلِ قِيَلا‬


ْ ‫﴿ َوَم ْن أ‬
“በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?” አን ኒሳእ፡

﴾َ‫يسى ابْ َن َم ْرَي‬ ِ ِ


َ ‫﴿ َوإ ْذ قَ َال اَّلُ ََي ع‬
“አላህም “የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! በሚለው ጊዜ (አስታውስ)” አል ማኢዳህ፡
﴾‫ك ِص ْدقاا َو َع ْدالا‬ ِ َّ‫﴿وََت‬
َ ِ‫ت َرب‬
ُ ‫ت َكل َم‬
ْ َ
“የጌታህም ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትሆን ተሟላች፡፡” አል አንዓም፡

ِ
﴾‫يما‬ َ ‫﴿ َوَكلَّ َم اَّلُ ُم‬
‫وسى تَ ْكل ا‬
“አላህም ሙሳን ማነጋገርን አነጋገረው፡፡” አን ኒሳእ፡

﴾ُ‫﴿ِمْنـ ُهم َّمن َكلَّ َم اَّل‬


“ከነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አልለ፡፡” አል በቀራህ፡

﴾ُ‫وسى لِ ِمي َقاتِنَا َوَكلَّ َمهُ َربُّه‬


َ ‫﴿ َولَ َّما َجاء ُم‬
“ሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ” አል አዕራፍ፡

﴾‫ب الطُّوِر ْالََْيَ ِن َوقَـَّربْـنَاهُ ََِنيًّا‬


ِ ِ‫﴿و ََن َديْـنَاهُ ِمن َجان‬
َ
“ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው፡፡ ያነጋገርነውም ሲሆን አቀረብነው፡፡” መርየም፡

ِِ ِ ِ َ ُّ‫﴿ َوإِ ْذ ََن َدى َرب‬


َ ‫وسى أَن اِْت الْ َق ْوَم الظَّالم‬
﴾‫ن‬ َ ‫ك ُم‬
“ጌታህም ሙሳን 'ወደ በደለኞች ሕዝቦች ሂድ' በማለት በጠራነው ጊዜ
(አስታውስ)” አሽ ሹዓራእ፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 23/60

﴾ِ‫َّجَرة‬ ِ
َ ‫﴿ َو ََن َد ُاُهَا َرَُّبُ َما أَََلْ أ َّْنَ ُك َما َعن ت ْل ُك َما الش‬
“ጌታቸውም 'ከዚህ ዛፍ አልከለከልኋችሁምን? ሲል ጠራቸው፡፡” (አል’አዕራፍ፡ 22)
﴾‫ن‬ ِ ُ ‫﴿ َويَـ ْوَم يـُنَ ِادي ِه ْم فَـيَـ ُق‬
َ ‫َجْبـتُ ُم الْ ُمْر َسل‬
َ ‫ول َماذَا أ‬
“የሚጠራባቸውንና 'ለመልእክተኞቹም ምንን መለሳችሁ?' የሚልበትን ቀን
(አስታውስ)” (አል’ቀሶስ፡ 65)
﴾ِ‫استَ َج َارَك فَأ َِجْرهُ َح ََّّت يَ ْس َم َع َكَلَ َم اَّل‬
ْ ‫ن‬
ِ ِ ‫﴿وإِ ْن أ‬
َ ‫َح ٌد م َن الْ ُم ْش ِرك‬
َ َ
“ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ
አስጠጋው፡፡” (አት’ተውባህ፡ 6)
‫يق ِمْنـ ُه ْم يَ ْس َمعُو َن َكَلَ َم اَّلِ ُثَّ ُُيَ ِرفُونَهُ ِمن بَـ ْع ِد َما َع َقلُوهُ َوُه ْم‬ ِ
ٌ ‫﴿ ََفَـتَطْ َمعُو َن أَن يـُ ْؤمنُواْ لَ ُك ْم َوقَ ْد َكا َن فَ ِر‬
﴾‫يَـ ْعلَ ُمو َن‬
“ከነሱ የሆኑ ጭፍሮች የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያ ከተረዱት በኋላ እነርሱ
እያወቁ የሚለውጡት ሲሆኑ ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?” (አል’በቀራህ፡ 75)
﴾‫اَّلُ ِمن قَـْب ُل‬ َ َ‫وَن َك َذلِ ُك ْم ق‬
َّ ‫ال‬ َ ُ‫اَّلِ قُل لَّن تَـتَّبِع‬
َّ ‫يدو َن أَن يـُبَ ِدلُوا َك ََل َم‬
ُ ‫﴿يُِر‬
“(በዚህም) የአላህን ቃል ሊለውጡ ይፈልጋሉ፡፡ 'ፈጽሞ አትከተሉንም፤ ይህን
(ቃል) ከዚህ በፊት አላህ ብሏል' በላቸው፡፡” (አል’ፈትህ፡ 15)
﴾‫ك َال ُمبَ ِد َل لِ َكلِ َماتِِه‬ ِ َ‫ك ِمن كِت‬
َ ِ‫اب َرب‬ ِ ‫﴿واتْل ما أ‬
َ ‫ُوح َي إِلَْي‬ َُ َ
“ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ለቃላቶቹ ለዋጭ
የላቸውም፡፡” (አል’ከህፍ፡ 27)
﴾‫يل أَ ْكثَـَر الَّ ِذي ُه ْم فِ ِيه ََيْتَلِ َُو َن‬ِِ‫ص علَى ب ِّن إِسرا‬ ِ
َ َ ْ َ َ ُّ ‫﴿إ َّن َه َذا الْ ُقْرآ َن يَـ ُق‬
“ይህ ቁርኣን በእስራኤል ልጆች ላይ የእነዚያን እነርሱ በእርሱ የሚለያዩበትን
አብዛኛውን ይነግራል፡፡” (አን’ነምል፡ 76)
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 24/60
22.ቁርኣን ከአላህ የወረደ መሆኑ የጸደቀበት
﴾‫َنزلْنَاهُ ُمبَ َارٌك‬ ِ
َ ‫اب أ‬
ٌ َ‫﴿ َوَهـ َذا كت‬
“ይህም ያወረድነው የሆነ የተባረከ መጽሐፍ ነው፡፡” አል አንዓም፡

﴾ِ‫اَّل‬
َّ ‫ص ِد اعا ِم ْن َخ ْشيَ ِة‬ ِ
َ َ‫َنزلْنَا َه َذا الْ ُقْرآ َن َعلَى َجبَ ٍل لََّرأَيْـتَهُ َخاَ اعا ُّمت‬
َ ‫﴿لَ ْو أ‬
“ይህንን ቁርኣን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ ከአላህ ፍራቻ (የተነሳ) ተዋራጅ
፣ ተሰንጣቂ ሆኖ ባየኸው ነበር፡፡” አል ሐሽር፡

‫وح‬ ‫ر‬ ‫ه‬


ُ َ ‫ل‬
‫ز‬ َّ ‫ـ‬
َ‫ن‬ ‫ل‬ُ‫ق‬۞ ‫ن‬َ ‫و‬ ‫م‬ َ ‫ل‬ ‫ع‬
ْ ‫ـ‬‫ي‬ َ‫ال‬ ‫م‬ ‫ه‬
ُ ‫ر‬ ‫ـ‬
َ‫ث‬ ‫ك‬
ْ َ
‫أ‬ ‫ل‬ ‫ب‬ ٍ
‫َت‬
َ َ
ْ ‫م‬ ‫َنت‬
َ ‫أ‬ ‫ا‬ َّ
‫َّن‬
َ ِ‫﴿وإِذَا ب َّدلْنَا آيةا َّم َكا َن آي ٍة واَّل أ َْعلَم ِبَا يـنَـ ِزُل قَالُواْ إ‬
ُ ُ ْ ُ َ ْ ُ ْ َ ُ ُ ُ ُ َ َ َ َ َ
ِ ِِ ِ ِ َّ‫الْ ُق ُد ِس ِمن َّربِك ِِب ْْل ِق لِيـثـبِت ال‬
ُ‫ن۞ َولََق ْد نَـ ْعلَ ُم أ ََّّنُْم يَـ ُقولُو َن إََِّّنَا يـُ َعل ُمه‬ َ ‫ين َآمنُواْ َوُه ادى َوبُ ْشَرى ل ْل ُم ْسلم‬ ‫ذ‬
َ َ َُ َ َ
ٌّ ِ‫بَ َشٌر لِ َسا ُن الَّ ِذي يـُْل ِح ُدو َن إِلَْي ِه أ َْع َج ِم ٌّي َوَهـ َذا لِ َسا ٌن َعَر‬
ٌ ِ‫ّب ُّمب‬
﴾‫ن‬
“በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር
አዋቂ ነው፡፡ 'አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም' ይላሉ፡፡ በእውነቱ
አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም
ለመምራትና ለማብሰር (ቁረኣንን) ንጹሁ መንፈስ (ጅብሪል) እውነተኛ ሲሆን
ከጌታህ አወረደው በላቸው፡፡ እነርሱም 'እርሱን (ቁርኣንን) የሚያስተምረው
ሰው ብቻ ነው' ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ የዚያ ወደርሱ
የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐጀም ነው፡፡ ይህ (ቁርኣን) ግን ግልጽ ዐረብኛ ቋንቋ
ነው፡፡” አን ነህል፡

23.የቂያማ ቀን ሙእሚኖች ጌታቸውን የሚመለከቱ መሆናቸው


የጸደቀበት
ِ ‫﴿وجوه يـومئِ ٍذ َن‬
﴾ٌ‫َّضَرةٌ۞إِ ََل َرَِبَا ََن ِظَرة‬ َ َْ ٌ ُ ُ

“ ዐጀም” ማለት ከዓረብኛ ውጭ የሆነ ቋንቋ ማለት ነው፡፡


አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 25/60
“ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡ ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡”
አል ቂያማህ፡

ِ ِِ‫﴿ َعلَى ْالَرا‬


﴾‫ك يَنظُُرو َن‬ َ
“በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ሆነው ይመለከታሉ፡፡” አል ሙጦፊፈን፡

﴾ٌ‫اْلُ ْس ََن َوِزََي َدة‬ ِِ


ْ ْ‫َح َسنُوا‬ َ ‫﴿للَّذ‬
ْ ‫ين أ‬
“ለእነዚያ መልካም ለሰሩት መልካም ነገርና ጭማሪም አላቸው፡፡” ዩኑስ፡

﴾‫﴿ َْلُم َّما يَ َش ُاؤو َن فِ َيها َولَ َديْـنَا َم ِزي ٌد‬


“ለእነርሱ በውስጧ ሲሆኑ የሚሹት ሁሉ አልላቸው፡፡” ቃፍ፡

ይህ ርዕስ ፣ በአላህ መጽሐፍ (ቁርኣን) ውስጥ በርካታ ነው፡፡ ከእርሱ ቅንን ጎዳና
ፈልጎ ቁርኣንን በደንብ ያስተነተነ ፣ የሐቁ መንገድ ግልጽ ይሆንለታል፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 26/60
ክፍል ሁለት

የአላህን ስሞችና መገለጫዎች የሚያጸድቁ የሐዲስ ማስረጃዎች

ከዚያም የረሡል ‫ﷺ‬ ሱና ነው፡፡ ሱና ፣ ቁርኣንን ትተነትናለች ፤ እርሱንም ግልጽ


ታደርጋለች ፤ በእርሱም ላይ ትጠቁማለች ፣ ስለርሱም ታብራራለች፡፡

ልክ እንደዚሁ የእውቀት ባለቤቶች ሙሉ በሙሉ በተቀበሏቸው ፣ መልእክተኛው


‫ﷺ‬ጌታቸውን በገለጹባቸው ትክክለኛ ሐዲሶች ማመኑ ግዴታ ነው፡፡

1. አላህ ወደቅርቢቱ ሰማይ እንደሚወርድ የጸደቀበት

የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ من‬: ‫ فيقول‬، ‫"ينزل ربنا إلى السماء الدنيا كل ليلة حين يبقى ثلث الليل اآلخر‬
.‫يدعوني فأستجيب له؟ من يسألني فأعطيه ؟ من يستغفرني فأغفر له؟" متفق عليه‬

“ጌታችን ከሌሊቱ መጨረሻ አንድ ሶስተኛው ሲቀር በየሌሊቱ ወደቅርቢቱ ሰማይ


ይወርዳል፡፡ 'ማን ነው የሚጠራኝ ፣ አቤት የምለው?' ፣ 'ማን ነው የሚጠይቀኝ
የምሰጠው?' ፣ 'ማን ነው ይቅርታን የሚጠይቀኝ ፣ ለርሱ ምህረት የማደርግለት?'
ይላል፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

2. አላህ እንደሚደሰት ፣ እንደሚስቅ የጸደቀበት


የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

.‫ متفق عليه‬. ‫" الحديث‬... ‫"هلل أشد فرحا بتوبة عبده من أحدكم براحلته‬

“አንዳችሁ ግመሉ (ጠፍታው ድንገት ሲያገኛት ከሚደሰተው በላይ)… (አሏህ) በባሪያው


አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 27/60

ጸጸት በጣም ተደሳች ነው፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫"يضحك هللا إلى رجلين يقتل أحدهما اآلخر كالهما يدخل الجنة" متفق عليه‬

“አንዱ ሌላውን ገድሎት ፣ ጀነት በሚገቡ ሁለት ግለሰቦች አላህ ይስቃል፡፡” ቡኻሪ፡

ሙስሊም፡

3. አላህ እንደሚደነቅና እንደሚስቅ የጸደቀበት

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ فيظل يضحك‬، ‫ ينظر إليكم أزلين قنطين‬، ‫"عجب ربنا من قنوط عباده وقرب غيره‬
‫يعلم أن فرجكم قريب" حديث حسن‬

“የችግሩ መቀየር ቅርብ ሆኖ ተስፋ በሚቆርጠው ባሪያው አላህ ይደነቃል፡፡ ችግር ላይ


ወድቃችሁ ፣ ተስፋ ቆርጣችሁ እያለ ወደእናንተ ይመለከታል፡፡ የችግሩ መወገድ ቅርብ
መሆኑን እያወቀ ይስቃል፡፡” አህመድ፡ ኢብኑ ማጀህ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል አስ ሶሂህ፡

4. እግር የተባለ መገለጫ የጸደቀበት

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ هل من مزيد؟ حتى يضع رب العزة فيها‬: ‫"ال تزال جهنم يلقى فيها وهي تقول‬
“‫رجله‬

"‫ قط قط‬: ‫ فتقول‬، ‫ "عليها قدمه فينزوي بعضها إلى بعض‬: ‫وفي رواية‬

“ጀሐነም በውስጧ (ሰዎች) የሚጣልባት ከመሆን አትወገድም፡፡ “ጭማሬ አለን?”


አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 28/60

ትላለች፡፡ የልቅና ባለቤት የሆነው (አሏህ) እግሩን ያኖርባታል” በሌላ ዘገባ፡ “በእርሷ
ላይ 'ቀደሙን' ያኖራል ፣ ከፊሏ ወደከፊሉ ይጠቀለላል፡፡ 'በቃኝ ፣ በቃኝ' ትላለች፡፡
(ቡኻሪ፡ 4848, ሙስሊም፡ 2848)

5. ጥሪ ፣ ድምጽ ፣ ንግግር የተባሉ መገለጫዎች የጸደቁበት

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ إن هللا يأمرك أن‬: ‫ فينادي بصوت‬، ‫ لبيك وسعديك‬: ‫ يا آدم ! فيقول‬: ‫"يقول تعالى‬
.‫تخرج من ذريتك بعثا إلى النار" متفق عليه‬

“'አደም ሆይ!' በማለት - ከሁሉ በላይ የሆነው - አሏህ ይናገራል ፣ '“አቤት አቤት
፣ እንድታግዘኝና እንድትረዳኝ እጠይቃለሁ” ይላል (አደም) ፣ 'ከዘሮችህ ወደእሳት
የሚላኩ ጀማዓዎችን እንድታወጣ አላህ ያዝሀል” በማለት (አሏህ) በድምጽ ይጣራል፡፡
(ቡኻሪ፡ 3348, ሙስሊም፡ 222)

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"‫"ما منكم من أحد إال سيكلمه ربه وليس بينه وبينه ترجمان‬

“ከእናንተ አንድም አካል አይኖርም ፣ በእርሱና በእርሱ መካከል አስተርጓሚ ሳይኖር


ጌታው የሚያናግረው ቢሆን እንጅ” (ቡኻሪ፡ 6539, ሙስሊም፡ 1016)

“ቀደም” የሚባለው መገለጫ ከፍጡራኖች አኳያ መሬትን ረግጠው እንደፈለጉ እንዲራመዱ ፣


እንዲሮጡ እና እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርጋቸው የእግራቸው ክፍል ነው፡፡ “ቀደም” የሚለው የአላህ መገለጫ
ግን ከፍጡራን መገለጫ ጋር የስም መመሳሰል ቢኖረውም ፣ አኳኋኑን እርሱ እንጅ ፍጡራኖች ፍጹም
አያውቁትም፡፡ አህለሱና ወልጀማዓዎች ይህን የአላህ መገለጫ ሳያጣምሙ ፣ ሳያመሳስሉ ፣ አኳኋኑን
ሳይገልጹ አላህና ረሡል ‫ ﷺ‬በነገሯቸው መሰረት ከእርሱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ያጸድቃሉ፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 29/60

6. አላህ ከፍጥረታቱ በላይ መሆኑና ከአርሽ በላይ ከፍ ማለቱ


የጸደቀበት
የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የበሽተኛን ፈውስ አስመልክቶ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ كما رحمتك‬، ‫ أمرك في السماء واألرض‬، ‫ تقدس اسمك‬، ‫"ربنا هللا الذي في السماء‬
‫ أنت رب الطيبين‬، ‫ اغفر لنا حوبنا وخطايانا‬، ‫ اجعل رحمتك في األرض‬، ‫في السماء‬
‫ فيبرأ" حديث حسن‬، ‫ وشفاء من شفائك على هذا الوجع‬، ‫ أنزل رحمة من رحمتك‬،
.‫رواه أبو داود وغيره‬

“በሰማይ ያለኸው ጌታችን ፣ ስምህ ንጹህ ሆነ ፣ እዝነትህ በሰማይ ውስጥ እንዳለ ሁሉ ፣


ትዕዛዝህም በሰማይና በምድር ነው ፣ ስለዚህ እዝነትህን በምድር ላይ አድርግ ፣
ሐጢያታችንን ወንጀሎቻችንን ምህረት አድርግ ፤ አንተ የመልካሞች ጌታ ነህ ፤ ከእዝነትህ
እዝነትን አውርድ ፣ በዚህ ህመም ላይ ከፈውስህ ፈውስን አውርድ፡፡ (ይህን ሩቅያ
በሽተኛው ከቀራ) ይድናል፡፡” አህመድ፡ አቡዳውድ፡ ሃኪም ፊል ሙስተድረክ፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫"أال تأمنوني وأنا أمين من في السماء" حديث صحيح‬

“አታምኑኝምን? እኔ በሰማይ ላይ ካለው ታማኝ ነኝ፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

በሰማይ ላይ ያለው አላህ ነው፡፡ ረሡል ‫ ﷺ‬በወህይው - ከሰማይ በሚወርደው ቁርኣን ታማኝ ናቸው፡፡
ረሡል የታማኞች ሁሉ አለቃ ናቸው፡፡ ረሡል እንዲሁም ወደርሳቸው ቁርኣንን የሚያወርደው ጅብሪልን d
ጨምሮ ታማኝ ናቸው፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾‫ن‬ ٍ ‫ند ِذي الْ َعر ِش َم ِك‬
ٍ ‫ن۞ ُمطَ ٍاع َثَّ أ َِم‬ َ ‫ول َك ِرٍي ۞ ِذي قـُ َّوةٍ ِع‬
ٍ ‫﴿ إِنَّه لََقو ُل رس‬
َُ ْ ُ
ْ
“እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡ በአርሽ ባለቤት ዘንድ ባለሟል የሆነው የሀይል ባለቤት፡፡
በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ ፤ ታማኝ የሆነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡” (አት’ተክዊር፡ 19-21) ከአላህ ይዞ
በማስተላለፉ ነው
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 30/60

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ وهو يعلم ما أنتم عليه" حديث حسن‬، ‫ وهللا فوق العرش‬، ‫"والعرش فوق الماء‬
‫رواه أبو داود وغيره‬

“አርሽ ከውሃው በላይ ነው ፤ አላህ ከአርሹ በላይ ነው ፤ እርሱ እናንተ ያላችሁበትን ሁኔታ
ያውቃል፡፡” አህመድ፡ አቡዳውድ፡ ኢብኑ ማጀህ፡ አልባኒ ሐዲሱን ደካማ ብለውታል ዶዒፍ አቡዳውድ

.‫هللا‬ ُ ‫ أَ ْنتَ َر‬: ْ‫ َم ْن أَنَا؟ قَالَت‬:‫ قَا َل‬.‫اء‬


ِ ‫سو ُل‬ َّ ‫ فِي ال‬: ْ‫ أَ ْي َن هللاُ؟ قَالَت‬:‫َوقَ ْولُهُ ﷺ لُ ْل َج ِاريَ ِة‬
ِ ‫س َم‬
.‫ أَ ْعتِ ْق َها فَ ِإنَّ َها ُم ْؤ ِمنَة‬:‫قَا َل‬

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬ለባሪያዋ የሚከተለውን ጥያቄ ጠየቋት “አሏህ የት ነው?” ፣


“ከሰማይ በላይ” በማለት ምላሽ ሰጠች፡፡ “እኔ ማን ነኝ?” በማለት ጠየቋት፡፡ “አንተ
የአላህ መልክተኛ ነህ” በማለት ምላሽ ሰጠች፡፡ “እርሷ አማኝ ነችና ነጻ አድርጋት” በማለት
ምላሽ ሰጡ፡፡ ሙስሊም፡

7. አላህ ከፍጡራን ጋር አብሮ መሆኑ የጸደቀበት


አብሮነቱ ፣ ከዓርሽ በላይ መሆኑን ከሚገልጹ መረጃዎች ጋር የማይቃረን መሆኑ

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ أن تعلم أن هللا معك حيثما كنت" حديث حسن‬: ‫"أفضل اإليمان‬

“የኢማን በላጩ ፡ በማንኛውም ቦታ ብትሆን አላህ (በእውቀቱ) አብሮህ መሆኑን


ማወቅህ ነው፡፡” ሐዲሱን አልባኒ ደካማ ብለውታል ዶዒፍ አል ጃሚዕ፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ فإن هللا قبل‬، ‫ وال عن يمينه‬، ‫ فال يبصقن قبل وجهه‬، ‫"إذا قام أحدكم إلى الصالة‬
‫‪አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ‬‬ ‫‪31/60‬‬

‫وجهه ‪ ،‬ولكن عن يساره ‪ ،‬أو تحت قدمه" متفق عليه‪.‬‬

‫‪“አንድ ሰው ወደሶላት የቆመ ጊዜ ፣ ፊት ለፊትም ይሁን ወደቀኝ አቅጣጫ ምራቁን‬‬


‫‪አይትፋ - አላህ ፊት ለፊት አቅጣጫ ነውና፡፡ ነገር ግን ወደግራው ወይም ከእግሩ ስር‬‬
‫”‪(ይትፋ)፡፡‬‬ ‫‪ቡኻሪ፡‬‬ ‫‪ሙስሊም፡‬‬

‫‪ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-‬ﷺ ‪የአላህ መልእክተኛ‬‬

‫"اللهم رب السماوات السبع واألرض ورب العرش العظيم ‪ ،‬ربنا ورب كل شيء ‪،‬‬
‫فالق الحب والنوى ‪ ،‬منزل التوراة واإلنجيل والقرآن ‪ ،‬أعوذ بك من شر نفسي ‪،‬‬
‫ومن شر كل دابة أنت آخذ بناصيتها ‪ ،‬أنت اآلول فليس قبلك شيء ‪ ،‬وأنت اآلخر‬
‫فليس بعدك شيء ‪ ،‬وأنت الظاهر فليس فوقك شيء ‪ ،‬وأنت الباطن فليس دونك‬
‫شيء ‪ ،‬اقض عني الدين وأغنني من الفقر" رواه مسلم‪.‬‬

‫‪“የሰባቱ ሰማያትና የምድር ፣ የታላቁ አርሽ ጌታ አላህ ሆይ! ጌታችን የሁሉ ነገር ጌታ ፣‬‬
‫‪ቅንጣትንና ፍሬን ፈልቃቂ ፤ ተውራትን ፣ ኢንጅልንና ቁርዓንን አውራጅ ፤ ከነፍሴ ተንኮል‬‬
‫‪፣ ከማንኛውም ተንቀሳቃሽ ነገሮች ተንኮል በአንተ እጠበቃለሁ ፤ ቅንጭላቷን ያዥው‬‬
‫‪አንተ ነህ፡፡ የመጀመሪያው አንተ ነህ ፣ ከአንተ በፊት አንድም ነገር የለም ፤ የመጨረሻው‬‬
‫‪አንተ ነህ ፣ ከአንተ በኋላ አንድም ነገር የለም ፤ የበላዩ አንተ ነህ ፣ ከአንተ በላይ‬‬
‫‪አንድም ነገር የለም ፤ ቅርቡ አንተ ነህ ፣ ከአንተ የቀረበ አንድም ነገር የለም ፤ ከእኔ ላይ‬‬
‫”‪እዳየን ክፈልልኝ ፣ ከድህነትም አክብረኝ፡፡‬‬ ‫‪ሙስሊም፡‬‬

‫اس! ْأربِ ُعوا‬ ‫الصحاب ُة أَصو َاتهم ِب ِ‬


‫الذ ْك ِر‪ :‬أَُّي َها َّ‬
‫الن ُ‬ ‫َوَق ْوُل ُه صلى هللا عليه وسلم َل َّما َرَف َع َّ َ َ ْ َ ُ ْ‬
‫يعا َب ِص ًا‬
‫ير َق ِر ًيبا‪ِ .‬إ َّن‬ ‫ِ‬ ‫ِ‬ ‫ِ‬
‫َعَلى أَْن ُفس ُك ْم؛ َفِإَّن ُك ْم الَ َت ْد ُعو َن أَ َص َّم َوالَ َغائًبا‪ِ ،‬إَّن َما َت ْد ُعو َن َسم ً‬
‫ق َعَلْي ِه‪.‬‬ ‫ِ ِِ‬ ‫ِ ِ‬
‫َّالذي َت ْد ُعوَن ُه أَ ْقَر ُب ِإَلى أَ َحد ُك ْم م ْن ُعُن ِق َراحَلته‪ُ .‬م َّت َف ع‬
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 32/60

ሶሃቦቹ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሏህን በዘከሩ ጊዜ ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን


አሏቸው፡- “እናንተ ሰዎች ሆይ! ለነፍሳችሁ እዘኑ ፣ እናንተ ደንቆሮና ሩቅ የሆነን አካል
አይደለም የምትጣሩት - እናንተ የምትጣሩት ሰሚ ፣ ተመልካችና ፣ ቅርብ የሆነውን
ነው፡፡ ያ የምትጠሩት ወደአንዳችሁ ከግመሉ አንገት በጣም የቀረበ ነው፡፡” ቡኻሪ፡
ሙስሊም፡

8. አማኞች የቂያማ ቀን ጌታቸውን እንደሚመለከቱ የጸደቀበት

‫ فإن‬، ‫ ال تضامون في رؤيته‬، ‫"إنكم سترون ربكم كما ترون القمر ليلة البدر‬
"‫ فافعلوا‬، ‫استطعتم أن ال تغلبوا على صالة قبل طلوع الشمس وصالة قبل غروبها‬
.‫متفق عليه‬

“የአስራ አራተኛው ሌሊት ጨረቃን እንደምትመለከቱት ፣ ጌታችሁን ትመለከታላችሁ፡፡


በእይታው አንዱ አንዱን አይጋርደውም፡፡ ጸሐይ ከመውጣቷ በፊት (የሱብሂ ሶላት) እና
ጸሐይ ከመጥለቋ በፊት ባለው (የአስር ሶላት) ካልተሸነፋችሁ ፣ ስሩ፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

የጌታን ባህሪያቶች የሚያጸድቁ ሐዲሶችን በተመለከተ የአህለሱናዎች አቋም

ከእሳት ነጻ የምትሆነው ቡድን -አህለሱና ወልጀማዓህ- አላህ በቁርኣኑ


በነገራቸው እንደሚያምኑት ሁሉ የአላህ መልእክተኛም ‫ ﷺ‬ከጌታቸው ይዘው በነገሯቸው
እነዚህን የመሳሰሉ ሐዲሶች ያለማጣመም ፣ ያለማራቆት ፣ አኳኋንን ያለመግለጽ ፣
ያለማመሳሰል ያምናሉ፡፡

በዚህ ማህበረሰብ በሚገኙ አንጃዎች መካከል አህለሱና ወልጀማዓ ያላቸው ደረጃ


አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 33/60

ይህ (የሙስሊም) ማህበረሰብ (ካለፉ) ማህበረሰቦች መካከለኛ እንደሆነው ሁሉ


(አህለሱና ወልጀማዓዎች) በዚህ (የሙስሊም) ማህበረሰብ ውስጥ ከሚገኙ
አንጃዎች መካከለኛ ናቸው፡፡ (አህለሱና ወልጀማዓህ) የአላህን መገለጫ አስመልክቶ
በሚያራቁቱ ጀህምያዎች እና አመሳሳዮች መካከል ናቸው፡፡

የአላህን ተግባራቶች አስመልክቶ በጀብርያ ፣ በቀደርያና በሌሎችም መካከል


ናቸው፡፡ የአላህን ዛቻ አስመልክቶ በሙርጅአ እና ከቀደረያና ከሌሎችም በሆኑት
ወኢድያዎች መካከል ናቸው፡፡

በዲን እና በኢማን ስያሜዎች ዙሪያ በሀሩርያ ፣ ሙዕተዚላ እና በሙርጀኣ ፣


በጀህምያ መካከል ናቸው፡፡

(አህለሱና ወልጀማዓዎች) የረሡልን ‫ ﷺ‬ሶሃቦች አስመልክቶ በራፊዷ እና


በኸዋሪጅ መካከል ናቸው፡፡

ይህ ስያሜ በ ሒጅራ አቆጣጠር በተገደለው ጀሕም ብን ሶፍዋን አትቲርሚዝይ የተጠጋ ነው፡፡


የጀሕምያ መዝሐብ የአላህን ስሞችና መገለጫዎች ማራቆት ነው፡፡
'ባሪያ በሚሰራው ስራ እና እንቅስቃሴ ተገዳጅ ነው ፣ ምርጫም የለውም' ይላሉ፡፡
'አላህ የባሮችን ስራ ፈጣሪ ነው የሚለውን በመቃወም ያለአላህ መሽአና ውሳኔ ባሪያ የራሱን ተግባር
ፈጣሪ ነው' ይላሉ፡፡
ኢርጃእ ወደሚለው የተጠጋ ነው፡፡ ኢርጃእ ማለት ማዘግየት ማለት ሲሆን በዚህ የተጠሩበት ዋና
ምክንያት ስራዎችን ከኢማን ወደኋላ በማስቀረታቸው ነው፡፡ (ስራ ከኢማን ትርጉም አይገባም ፤ ኢማን
ካለው መገለጫ አይገባም) 'መታዘዝ ከክህደት ጋር እንደማይጠቅመው ሁሉ ፣ ወንጀልም ከኢማን ጋር
አይጎዳም' ይላሉ፡፡
'ከባድ ወንጀል የሚፈጽሙ ሰዎች ጸጸት ሳያደርጉ ከሞቱ እሳት ውስጥ ዘውታሪ ይሆናሉ' ይላሉ፡፡
ከኸዋሪጅ የሆኑ ቡድኖች ናቸው፡፡ ወደሀሩርያ የተጠጉበት ምክንያት ሀሩራ የምትባል ለኩፋ ቅርብ
የሆነች ቦታ ላይ በመሰባሰብ በዓልይ e ላይ በማመጻቸው ነው፡፡ 'ከባድ ወንጀል የሚፈጽም ካፊር በመሆኑ
እሳት ውስጥ ዘውታሪ ይሆናል' ይላሉ፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 34/60
አላህ ከዓርሽና ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ መሆኑ

የበላይነቱ ከፍጡራኖች ጋር ከመሆኑ ጋር የማይቃረን መሆኑ

ከጉድለት የጠራው አላህ ከፍጡራኑ በተለየ ሁኔታ ከሰማያትና ከዓርሽ በላይ


እንደሆነ ፣ በማንኛውም ቦታ ቢሆኑ (በእውቀቱ) ከፍጡራን ጋር አብሯቸው
እንደማይለይ እና የሚሰሩትን ሁሉ እንደሚያውቅ አሏህ በቁርኣን ሁሉንም ሰብስቦ
በተናገረው ፣ በበርካታ ሰነድ በረሡል ‫ ﷺ‬ሐዲስ በተወራው ፣ የዚህ ኡመት ቀደምቶች
በተስማሙበት ሁሉ ማመን በአላህ ማመን በሚለው ያሳለፍነው ክፍል ውስጥ
ይካተታል፡፡
ِ ‫استَـ َوى َعلَى الْ َعْر ِش يَـ ْعلَ ُم َما يَلِ ُج ِِف ْال َْر‬
‫ض َوَما ََيُْر ُج‬ ٍ ِ ِ َ ‫ات و ْالَر‬
ْ َّ‫ض ِِف ستَّة أ َََّيم ُث‬
ِ َّ ‫﴿هو الَّ ِذي خلَق‬
ْ َ ‫الس َم َاو‬ َ َ َُ
﴾ٌ‫صي‬ِ ‫اَّل ِبَا تَـعملُو َن ب‬ ِ َّ ‫ِمْنـ َها َوَما يَن ِزُل ِم َن‬
َ َ ْ َُّ ‫الس َماء َوَما يَـ ْعُر ُج ف َيها َوُه َو َم َع ُك ْم أَيْ َن َما ُكنتُ ْم َو‬
“እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ፤ ከዚያም
ከአርሽ ላይ ሆነ (ከፍ አለ)፡፡ በምድር ውስጥ የገባውን ፣ ከእርሷም
የሚወጣውን ፣ ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን
ያውቃል፡፡ እርሱም የትም ብትሆኑ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አላህም የምትሰሩትን ሁሉ
ተመልካች ነው፡፡” አል ሐዲድ፡

“እርሱም ከእናንተ ጋር ነው” የሚለው ትርጉም ከፍጡራን ጋር ተቀላቅሏል ማለት

አይደለም፡፡ በዚህ ትርጉም ላይ የዓረብኛ ቋንቋውም አይጠቁምም፡፡ ጨረቃ ከሰማይ ላይ


የተኖረ ፣ ከአላህ ተአምራቶች መካከል አንዱ የሆነ ፣ በማንኛውም ቦታ ቢሆን ሰፈር
ከሚወጡትም ከማይወጡትም ጋር አብሮ የማይለይ አነስተኛ ከሆኑ ፍጡራኖች መካከል
አንዱ ነው፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 35/60

ጥራት የተገባው ጌታ ከዓርሽ በላይ ነው ፣ ፍጡራኑንን በበላይነት ተቆጣጣሪው ነው


፣ እነርሱንም ተመልካች ነው የሚሉትንና ሌሎችንም የጌትነት ትርጉሞችን ባቀፉ
መልእክቶች ሁሉ ማመን በዚህ ክፍል ይካተታል፡፡

የአላህን የበላይነትና ከፍጡራን ጋር መሆኑን ማመን ግዴታ መሆኑ

“ፊሰማእ” ያለው የአላህ ቃል ትርጉምና ማስረጃዎቹ

ይህ አላህ ያወሳው -ማለትም ከአርሽ በላይ መሆኑና ከእኛ ጋር መሆኑ-


ማጣመም ሳያስፈልገው በትክክል እውነት ነው፡፡ ይሁን እንጅ ከውሸት ጥርጣሬዎች
ሊጠበቅ ይገባዋል፡፡ ለምሳሌ ፡- አላህ ከሰማይ በላይ ነው ሲባል ፣ ሰማይ ጥላ ይሆነዋል
ወይም ሰማይ ይሸከመዋል ከሚል ጥርጣሬ መጽዳት ያስፈልጋል፡፡ ይህ አመለካከት
ትክክል ባለመሆኑ የእውቀት እና የኢማን ባለቤቶች የተስማሙበት ጉዳይ ነው፡፡

አላህ b ፣ ኩርሲዩ ሰማያትን እና ምድርን የሰፋ ነው፡፡ እርሱ ሰማያትና ምድር


እንዳይወገዱ ይይዛቸዋል፡፡ በእርሱ ፈቃድ ካልሆነ በቀር ፣ ሰማይ ከምድር ላይ
እንዳይወድቅ ይይዘዋል፡፡ ሰማያትና ምድር በትዕዛዙ መቆማቸው ከእርሱ ተኣምር ነው፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾ِ‫ض ِِب َْم ِره‬ ِِ ‫`﴿وِمن‬


ُ ‫الس َماء َو ْال َْر‬
َّ ‫وم‬
َ ‫آَيته أَن تَـ ُق‬
َ ْ َ
“ሰማይና ምድርም (ያለምሰሶ) በትዕዛዙ መቆማቸው ከአስደናቂ ምልክቶቹ
ነው፡፡” አር ሩም፡

አላህ ለፍጡራኑ ቅርብ እንደሆነ


ቅርብ መሆኑ ከእርሱ የበላይነት እና ከፍ ማለት ጋር የማይቃረን መሆኑ
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 36/60

በሚከተለው ቁርኣን በአንድ ላይ እንደተናገረው ፡ (አሏህ) ለፍጡራኑ ቅርብ ፣ ዱዓን


ተቀባይ በመሆኑ ማመን በዚህ (በአላህ ማመን በሚለው ክፍል) ውስጥ ይካተታል፡፡
ِ ‫َّاع إِ َذا دع‬
﴾‫ان‬ ِ ‫﴿وإِ َذا سأَلَك ِعب ِادي ع ِّن فَِإِِن قَ ِر‬
َ َ ِ ‫يب َد ْع َوَة الد‬
ُ ‫يب أُج‬
ٌ َ َ َ َ َ
“ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን
ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡” አል በቀራህ፡

ሶሃቦች በዚክር ድምጻቸውን ከፍ ባደረጉ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የተናገሩት


ንግግር ነው፡-

‫ إن الذي تدعونه‬، ‫ فإنكم ال تدعون أصم وال غائبا‬، ‫"أيها الناس اربعوا على أنفسكم‬
"‫أقرب إلى أحدكم من عنق راحلته‬

“እናንተ ሰዎች ሆይ! ለነፍሳችሁ እዘኑላት ፣ እናንተ ደንቆሮና ሩቅ (የሆነ አካልን)


አይደለም የምትጣሩት ፣ ያ የምትጠሩት ከግመሉ አንገት ወደአንዳችሁ በጣም የቀረበ
ነው፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

በቁርኣንም ይሁን በሐዲስ ስለቅርበቱና አብሮነቱ የተወሳው ስለበላይነቱና ከፍ


ስለማለቱ ከተወሳው ጋር የሚጋጭ አይደለም፡፡ ጥራት የተገባው ጌታ በማንኛውም
ባህሪው አንድም ነገር እርሱን የሚመስለው የለም፡፡ ቅርብ ከመሆኑ ጋር የበላይ ነው ፣
የበላይ ከመሆኑ ጋር ቅርብ ነው፡፡

ቁርኣን በእርግጠኛነት የአላህ ቃል መሆኑ

ቁርኣን የአላህ ንግግር መሆኑን ፤ ፍጡር ያልሆነና ከእርሱ የተወረደ መሆኑን ፤


ከእርሱ
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 37/60

የጀመረ ፣ ወደርሱ የሚመለስ መሆኑን ፤ አላህ በእርሱ በትክክል የተናገረው ፣


በሙሀመድ ‫ ﷺ‬ላይ ያወረደው ቁርኣን የሌላ አካል ሳይሆን በትክክል የአላህ ንግግር
መሆኑን ማመን በአላህና በመጽሐፎች ከማመን ውስጥ የሚካተት ነው፡፡

ስለአላህ ንግግር “ሂካያ” ወይም “ዒባራ” ነው የሚል ንግግር በአጠቃላይ


መናገር አይፈቀድም፡፡ ይልቁንም ሰዎች ከመጽሐፍ ላይ ቢያነቡትም ወይም ቢጽፉት
በትክክል የአላህ ንግግር ከመሆን አያወጣውም፡፡ ንግግር የሚባለው ወደአስተላለፈው
ወይም ወደአሸጋገረው አካል ሳይሆን የሚጠጋው መጀመሪያ ንግግሩን ወደተናገረው
አካል ነው፡፡ እርሱም - ቁርኣን - ሀርፎቹም ይሁኑ ትርጉማቸውም የአላህ ንግግር
ነው፡፡ ከትርጉሞች ውጭ ቃሉ ብቻውን የአላህ ንግግር ነው አይባልም ፤ ከሀርፎች
ውጭ ትርጉሙ ብቻውን የአላህ ንግግር ነው አይባልም፡፡

አማኞች ጌታቸውን እንደሚያዩና የሚመለከቱባቸው ቦታዎች

በእርሱ (በአላህ) ፣ በመጽሐፎቹ ፣ በመላኢካዎች እና በመልእክተኞቹ ማመን


በሚለው ከዚህ በፊት ባወሳነው ክፍል የሚካተቱ ነጥቦች፡

የቂያማ ቀን አማኞች ጌታቸውን ምንም ደመና በሌለበት ሰዓት ጸሐይን


እንደሚመለከቱት ፣ በአስራ አራተኛው ሌሊት አንዱ ሌላውን ሳይጋርደው ጨረቃን

የቁርኣን መውረድ የጀመረው ከጅብሪልም ፣ ከሌላም አካል ሳይሆን ከአላህ ብቻ ነው፡፡


አጠቃላይ ባህሪያቱ በትክክል የእርሱ ባህሪ ነው፡፡ ንግግሩ በእርግጥም እርሱ የተናገረው ነው ፣ ፍጡር
ሊሆን በፍጹም አይችልም፡፡ ምክንያቱም ባህሪያቱ ነው፡፡ የፍጡር ባህሪ ፍጡር እንደሆነው ሁሉ ፣ የፈጣሪ
ባህሪ ደግሞ ፍጡር አይደለም፡፡
“ሒካያ” ማለት ልክ የተነገረውን ንግግር የገደል ማሚቶ እንደገና እንደሚያስተጋባው ማለት ነው፡፡
“ዒባራ” ማለት በነፍስ ውስጥ ሊባል የታሰበውን በተፈጠረ ድምጽና ቃል መግለጽ ማለት ነው፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 38/60

በቀጥታ እንደሚመለከተው ጌታቸውን በገሀድ በአይናቸው ይመለከቱታል፡፡ ጥራት


የተገባውን (አላህ) በ “አረሷት አልቂያማ” ወይም በቂያማ ሰፊ ሜዳ እንዲሁም
ጀነት ከገቡ በኋላ አላህን እርሱ እንደሻው ይመለከቱታል፡፡
በመጨረሻው ቀን በማመን ውስጥ የሚካተቱ
1. የቀብር ክስተቶች
ከሞት በኋላ በሚከሰቱ ነብዩ ‫ ﷺ‬የተናገሯቸው ነገሮች ሁሉ ያምናሉ፡፡ በቀብር ፈተና
፣ በቀብር ቅጣትና ጸጋ ያምናሉ የሚለው በመጨረሻው ቀን ከማመን ውስጥ ከሚካተቱ
ነጥቦች ነው፡፡

ፈተና፡ ሰዎች በመቃብራቸው ውስጥ ይፈተናሉ፡፡ “ጌታህ ማን ነው?” ፣ “እምነትህ


ምንድን ነው?” ፣ “ነብይህ ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ለግለሰቡ ይቀርብለታል፡፡
እነዚያ ያመኑትን በተረጋገጠው ቃል በዱንያ ህይዎትም ይሁን በአኼራ ያረጋጋቸዋል፡፡
አማኝ ከሆነ፡ “ጌታየ አላህ ነው” ፣ “ሀይማኖቴ ኢስላም ነው” ፣ “ነብዬ ሙሀመድ
ነው” ይላል፡፡

“አረሷቱል ቂያማ” ማለት ምንም አይነት ግንባታ የሌለበት ፣ ሰዎች ሂሳብ የሚደረጉበትና የሚሰበሰቡበት
ሰፊ የሆነ ቦታ ማለት ነው፡፡
በቂያማ ሜዳ ሰዎች በሶስት ይከፈላሉ
1ኛ፡- ውጫቸውም ውስጣቸውም አማኞች የሆኑ ፣
2ኛ፡- ውጫቸውም ውስጣቸውም ከሀዲዎች የሆኑ ፣
3ኛ፡- ውጫቸው አማኝ ሆኖ ውስጣቸው ከሐዲ የሆኑ ሙናፊቆች ናቸው፡፡
ትክክለኛ አማኞች በቂያማ ሜዳም ይሁን ጀነት ከገቡ በኋላ አላህን ይመለከታሉ፡፡
ሙሉ በሙሉ ከሐዲዎች የሆኑት ደግሞ በአጠቃላይ ጌታቸውን አይመለከቱም የሚለው የተወሰኑ ዑለሞች
ንግግር ሲሆን ሌሎች ደግሞ ይመለከቱታል ነገር ግን የቅጣትና የቁጣ መመልከት ነው ይላሉ፡፡
ሙናፊቆች ደግሞ በቂያማ ሜዳ አላህን ይመለከቱታል ፣ ከዚያም ከእነርሱ ይጋረድባቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላ
እስከመጨረሻው አይመለከቱትም፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 39/60

ተጠራጣሪ ከሆነ ደግሞ “ሀህ ፣ ሀህ” ፣ “ሰዎች የሆነ ነገር ሲናገሩ ሰምቸ ተናገርኩ
እንጅ አላውቅም” በማለት ምላሽ ይሰጣል፡፡ በብረት መዶሻ ይመታል፡፡ ከሰዎች በቀር
የሚጮኸውን ጩኸት ሁሉም ነገር ይሰሙታል፡፡ የሰው ልጅ ቢሰማው ራሱን ስቶ ይወድቅ
ነበር፡፡

2. ትልቁ ቂያማና ክስተቶቹ

ከዚህ ፈተና በኋላ እስከትልቁ የቂያማ ቀን ድረስ ቅጣት ወይም ጸጋ ይሆናል፡፡


ነፍሶች ወደአካላቸው ይመለሳሉ፡፡

አላህ በቁርኣኑ ፣ እንዲሁም በረሡል ‫ﷺ‬አንደበት የተናገረው ፣ ሙስሊሞችም


የተስማሙበት የሆነው ቂያማ ይቆማል፡፡ ሰዎች ራቁታቸውን ፣ ጫማ የሌላቸው እና
ያልተገረዙ ሆነው ከመቃብራቸው ተነስተው ከዓለማት ጌታ ፊት ይቆማሉ፡፡

የቂያማ ክስተቶች

ጸሐይ ወደነርሱ ትቀርባለች ፣ ላበታቸው ይለጉማቸዋል፡፡

ሚዛኖች ይተከላሉ ፤ የባሮች ስራዎች በእነርሱ ይመዘናሉ፡፡


አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
‫ين َخ ِسُروا أَن َُ َس ُه ْم ِِف َج َهن ََّم‬ ِ َّ‫﴿فَمن ثـَ ُقلَت موا ِزينه فَأُولَئِك هم الْم َْلِحو َن۞ومن خ ََّت موا ِزينه فَأُولَئِك ال‬
‫ذ‬
َ َ ْ ُُ َ َ ْ َ ْ َ َ ُ ُ ُ ُ َ ْ ُُ َ َ ْ َ
﴾‫َخالِ ُدو َن‬

“ሚዛኖቹም የከበዱለት ሰው እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡


ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰው እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፡፡
በጀሐነም ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡” አል ሙእሚኑን፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 40/60
መዝገቦች ይዘረጋሉ፡፡ እነርሱም የስራዎች መዛግብት ናቸው፡፡ መጽሐፉን በቀኙ የሚይዝ
አለ ፣ በግራው ወይም ከኋላ በጀርባው የሚይዝ አለ፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


ِ ِِ
َ ‫ك َكَى بِنَـ َْ ِس‬
‫ك‬ َ َ‫ورا۞اقْـَرأْ َكتَاب‬ ُ ‫ِج لَهُ يَـ ْوَم الْقيَ َام ِة كِتَ ااِب يَـ ْل َقاهُ َم‬
‫نش ا‬
ِ ٍ ِ‫﴿وُك َّل إ‬
ُ ‫نسان أَلَْزْمنَاهُ طَآَِرهُ ِِف عُنُقه َوُُنْر‬
َ َ
﴾‫ك َح ِسيباا‬ َ ‫الْيَـ ْوَم َعلَْي‬
“ሰውንም ሁሉ በራሪውን (ስራውን) በአንገቱ አስያዝነው፡፡ ለእርሱም
በትንሳኤ ቀን የተዘረጋ ሆኖ የሚያገኘው የሆነን መጽሐፍ እናወጣለታለን፡፡
“መጽሐፍን አንብብ፡፡ ዛሬ ባንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ በቃ” (ይባላል)፡፡”
አል ኢስራእ፡

አላህ ፍጥረታትን ሂሳብ ያደርጋል፡፡ በቁርኣን በሐዲስ እንደተገለጸው ሙእሚን


ባሪያውን ለብቻው በማግለል ሐጢያቱን እንዲያምን ያደርገዋል፡፡ ከሐዲ ከሆነ መልካም
ስራውና መጥፎ ስራው እንደሚመዘንለት ሰው ሂሳብ አይደረግም - ምክንያቱም
መልካም ስራ የለውምና፡፡ ነገር ግን ስራቸው ተቆጥሮ ይያዛል ፣ እንዲያውቁትና
እንዲያረጋግጡት ይደረጋል፡፡

የነብዩ ‫ ﷺ‬ሐውድ ፣ ቦታውና መገለጫዎቹ

በቂያማ ሜዳ ውሃው ከወተት በጣም የነጻ ፣ ከማር በጣም የጣፈጠ ፣


የኩባያዎቹ ብዛትና ውበት ልክ እንደሰማይ ከዋክብት የሆኑ ፣ ርዝመቱ አንድ ወር
የሚያስኬድ ፣ ጎኑ አንድ ወር የሚያስኬድ ፣ ሰዎች ወደርሱ የሚወርዱበት
የነብያችን ‫ ﷺ‬ሐውድ አለ፡፡ ከእርሱ አንድ ጉንጭ የተጎነጨ ፣ ከእርሷ በኋላ
እስከመጨረሻው አይጠማም፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 41/60

ሲራጥ : ትርጉሙ ፣ ቦታው ፣ በእርሱ ላይ የሰዎች አስተላለፍ መገለጫዎች

በጀሀነም ጀርባ ሲራጥ ተተክሏል፡፡ እርሱም በጀነትና በጀሐነም መካከል የተዘረጋ


ድልድይ ነው፡፡ ሰዎች በስራቸው መጠን ያልፋሉ፡፡ ከነርሱ መካከል ልክ በአይን ጨረፍታ
ቅጽበት በፍጥነት የሚያልፉ አሉ፡፡ ከእነርሱም ልክ በብልጭታ ፍጥነት የሚያልፍ አለ፡፡
ከእነርሱም ልክ በነፋስ ፍጥነት የሚያልፍ አለ፡፡ ከእነርሱም ልክ በሰለጠነና ጠንካራ
በሆነ የፈረስ ፍጥነት የሚያልፍ አለ፡፡ ከእነርሱም ልክ በተጫነ ግመል ፍጥነት የሚያልፍ
አለ፡፡ ከእነርሱም በሶምሶማ ፍጥነት የሚያልፍ አለ፡፡ ከእነርሱም በእርምጃ የሚራመድ
አለ፡፡ ከእነርሱም መንፏቀቅን የሚንፏቀቅ አለ፡፡ ከእነርሱም መነጠቅን ተነጥቆ ጀሐነም
ውስጥ የሚጣል አለ፡፡ በድልድዩ ላይ ማስገሪያ መንጦ አለ፡፡ ሰዎችን በስራቸው
ይነጥቃል፡፡

በጀነትና በእሳት መካከል የሚገኝ ቀንጦራ (ድልድይ)

በሲራጥ ድልድይ ያለፈ ጀነት ይገባል፡፡ እርሱን ካለፉ በጀነት እና በእሳት መካከል
በሚገኝ ድልድይ ላይ እንዲቆሙ ይደረጋል፡፡ ከፊሉ በከፊሉ ተመሳሳይ ርምጃ እንዲወስድ
(ባሮች በመካከላቸው የነበረን መበዳደል አንዲካካሱ) ይደረጋል፡፡ በጸዱና ንጹህ በሆኑ
ጊዜ ጀነት እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል፡፡

የጀነትን በር መጀመሪያ የሚያስከፍተው ማን እንደሆነ፣

መጀመሪያ ጀነት የሚገቡት እነማን እንደሆኑና የነብዩ ‫ ﷺ‬ምልጃ

የጀነትን በር መጀመሪያ የሚያስከፍቱት ሙሐመድ ‫ ﷺ‬ናቸው፡፡ ከኡመቱ ሁሉ


መጀመሪያ ጀነት የሚገቡት የርሳቸው ኡመቶች ናቸው፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 42/60

በቂያማ ቀን ሶስት ምልጃዎች ለእርሳቸው አሏቸው፡-

የመጀመሪያው ምላጃ፡- ለመውቂፉ ባለቤቶች ያማልዳሉ፡፡ በመካከላቸው ፍርድን ያገኙ


ዘንድ ምልጃን በመፈለግ - ወደ አደም ፣ ኑህ ፣ ኢብራሂም ፣ ሙሳ ፣ ኢሣ ኢብን
መርየም ከተመላለሱ በኋላ ምልጃዋ በእርሳቸው ትጠናቀቃለች፡፡

ሁለተኛው ምልጃ፡- የጀነት ሰዎች ጀነት እንዲገቡ ያማልዳሉ፡፡

እነዚህ ሁለቱ ምልጃዎች ለረሡል ‫ ﷺ‬ብቻ የተለዩ ናቸው፡፡

ሶስተኛው ምልጃ፡- እሳት ለተወሰነባቸው ሰዎች ያማልዳሉ፡፡ ይህ ምልጃ ለእርሳቸው ፣


ለሌሎች ነብያቶች ፣ ለሲዲቆችና ለሌሎችም የሚሆን ነው፡፡ እሳት የተወሰነባቸው
ሰዎች እሳት እንዳይገቡ ፣ እሳት ለገቡት ደግሞ ከእሳት እንዲወጡ ያማልዳሉ፡፡

አንዳንድ ወንጀለኞች ያለምንም ምልጃ በአላህ እዝነት ብቻ ከእሳት መውጣታቸውና


የጀነት ስፋት

አላህ ሰዎችን - በእርሱ ችሮታና እዝነት - ያለምንም ምልጃ ከእሳት ያወጣል፡፡


የዱንያ ሰዎች ጀነት ከገቡ በኋላ ትርፍ ቦታ ይቀራል ፤ ለእርሷ ሰዎችን ይፈጥራል ፤
ጀነትም ያስገባቸዋል፡፡

የመጨረሻው አገር ከሚያካትታቸው ዓይነቶች ፡ ሂሳብ ፣ ምንዳ ፣ ቅጣት ፣ ጀነት እና


እሳት ይገኙበታል፡፡

የጀነት ሰዎች ሲራጥን እንዳለፉ እንዲቆሙ ይደረጋል፡፡ ከፊሉ በከፊሉ ላይ ተመሳሳይ ማካካሻ ይሰጠዋል፡፡
ይህ ቂያማ ሜዳ ላይ ከሚደረገው ማካካሻ ይለያል፡፡ በሙእሚኖች ልቦች ውስጥ ቂም እና ጥላቻ የሚወገድበት
ነው፡፡ ልባቸው ከጸዳ በኋላ ጀነት እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 43/60
የዚህ ዝርዝር ከሰማይ በተወረዱ መጽሐፎች ፣ ከነብያት በተገኙ የእውቀት ቅሪቶች
ተወስቷል፡፡

በዚህ ዙሪያ በሚያረካ እና በቂ በሆነ ሁኔታ ከነብዩ ሙሐመድ ‫ ﷺ‬ከተወረሰው


እውቀት ይገኛል ፤ ለፈለገው ያገኘዋል፡፡

በቀደርና ከቀደር ጋር ተያያዥነት ባላቸው ነገሮች ማመን

ፊርቀቱ ናጅያ ፣ አህለሱና ወልጀማዓህ ደጉም ክፉውም በአላህ ውሳኔ እንደሆነ


ያምናሉ፡፡
በአላህ ውሳኔ ማመን ሁለት ደረጃዎች አሉት፡፡
የቀደር ደረጃዎች

1. የመጀመሪያው ደረጃ እና ከእርሱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው


ጉዳዮች

የመጀመሪያው ደረጃ፡ አላህ ሁልጊዜ በሚገለጽበት ቀዳማዊ እውቀቱ ፣ ፍጡራኖች ምን


እንደሚሰሩ ቀድሞ አውቆታል ብሎ ማመን፡፡ የእነርሱን አጠቃላይ ሁኔታ -
መታዘዛቸውን ፣ መንቀፋቸውን ፣ ሲሳያቸውን ፣ እድሜያቸውን - አውቆታል፡፡
ከዚያም የፍጥረቱን ውሳኔዎች ጥብቅ በሆነው ሰለዴ ላይ ጽፎታል፡፡ አላህ መጀመሪያ
ቀለምን እንደፈጠረ “ጻፍ” አለው፡፡ “ምን ልጻፍ?” አለ፡፡ “እስከቂያማ ቀን
የሚሆነውን ጻፍ” አለው፡፡

የሰው ልጅ ያገኘው አያመልጠውም ፤ ያመለጠው ደግሞ አያገኘውም፡፡ ቀለሙ


ደርቋል ፣ መዝገቡም ተጠቅልሏል፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 44/60
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾ٌ‫اَّلِ يَ ِسي‬
َّ ‫ك َعلَى‬ ِ ٍ َ‫ك ِِف كِت‬
َ ‫اب إِ َّن ذَل‬
ِ
َ ‫ض إِ َّن ذَل‬ َّ ‫اَّلَ يَـ ْعلَ ُم َما ِِف‬
ِ ‫الس َماء َو ْال َْر‬ َّ ‫﴿أَََلْ تَـ ْعلَ ْم أ‬
َّ ‫َن‬

“አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መሆኑን


አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ (የተመዘገበ) ነው፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር
ነው፡፡” ሐጅ፡

ِ‫اب ِمن قَـب ِل أَن نَّبأَها إِ َّن َذلِك علَى ا ََّّل‬


ٍ َ‫ض وَال ِِف أَن َُ ِس ُكم إَِّال ِِف كِت‬ ٍ ِ ِ ‫﴿ما أَص‬
َ َ َ َْ ْ ْ َ ِ ‫اب من ُّمصيبَة ِِف ْال َْر‬
َ َ َ
﴾ٌ‫يَ ِسي‬

“በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ምንንም) አትነካም ፣ ሳንፈጥራት በፊት


በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትሆን እንጅ ፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡” አል ሀዲድ፡

ይህ ለአላህ እውቀት ተከታይ የሆነው ውሳኔ ጥቅል እና ዝርዝር በሆነ ሁኔታ


በተለያየ ቦታ ላይ ይከሰታል፡፡ ጥብቅ በሆነው ሰሌዳው ላይ እርሱ የሻውን መዝግቧል፡፡
የፅንሱን አካል በፈጠረ ጊዜ ሩህ ከመንፋቱ በፊት መላኢካን ወደርሱ ይልካል፡፡ በአራት
ቃላቶች ይታዘዛል፡፡ “ሲሳዩን ፣ እድሜውን ፣ ስራውን ፣ ጠማማና እድለኛ መሆኑን
ጻፍ” እና የመሳሰሉትን ለእርሱ ይባላል፡፡ ይህን አይነት ውሳኔ ቀደምት ጽንፈኛ
ቀደርያዎች ይቃወሙት ነበር ፣ በአሁኑ ሰዓት ግን ይህን የሚቃወሙት ቀላል ናቸው፡፡

2. ሁለተኛው ደረጃ እና ከእርሱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች

ሁለተኛው ደረጃ፡- ተፈጻሚ የሆነው የአላህ መሽአ ፣ አጠቃላይ የሆነው ችሎታው ነው፡፡
እርሱም “አላህ የሻው ይሆናል ፣ አላህ ያልሻው አይሆንም” ብሎ ማመን ነው፡፡
ተንቀሳቃሽም ይሁኑ የማይንቀሳቀሱ በሰማያትና በምድር ያሉ ነገሮች በእርሱ መሽአ
ካልሆነ በቀር ተፈጻሚ አይሆኑም፡፡ በእርሱ ንግስና ፣ እርሱ የማይፈልገው ነገር
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 45/60
አይሆንም፡፡

በተገኙትም ይሁን ባልተገኙ ነገሮች ሁሉ ቻይ የሆነ ጌታ ነው፡፡ በምድርም ይሁን


በሰማይ አንድም ፍጡር የለም ፣ ፈጣሪው እርሱ ቢሆን እንጅ፡፡ ከእርሱ ውጭ ፈጣሪ ፣
ከእርሱ ውጭ ጌታ የለም፡፡
የመጀመሪያው እና የሁለተኛው ነጥብ
በቀደርና በሸሪዓው ፤ ወንጀልን በመወሰኑና በመጥላቱ መካከል ተቃርኖ አለመኖሩ

ይህ ከመሆኑ ጋር እርሱን በመታዘዝና መልእክተኞችን በመታዘዝ ላይ ባሮቹን አዟል


፤ የእርሱን ትዕዛዝ ከመንቀፍም ከልክሏል፡፡

አላህ እርሱን ብቻ የሚፈሩ ፣ በጎ የሚሰሩና ፍትሐዊ የሆኑ ሰዎችን ይወዳል፡፡


ከአመኑትና መልካም ከሰሩት ስራቸውን ይቀበላል፡፡

ከሀዲዎችን አይወድም ፣ ከአመጸኛ ህዝቦች ስራቸውን አይቀበልም፡፡ በጸያፍ


አያዝም ፣ ለባሮቹ ክህደትን አይወድም ፣ ብልሹነትን አይወድም፡፡

ሶስተኛው ነጥብ ፡ ቀደርን በማጽደቅ እና የባሮች ስራ በትክክል ወደራሳቸው መጠጋቱ


እንዲሁም በራሳቸው ምርጫ መስራታቸው መካከል ተቃርኖ አለመኖሩ

ባሮች በእውነት ሰሪዎች ናቸው፡፡ አላህ ደግሞ ስራቸውን ሰሪ ነው፡፡ ባሪያ


ሙእሚን ፣ ካፊር ፣ በጎ ሰሪ ፣ አመጸኛ ፣ ሰጋጅ እና ጿሚ ነው፡፡ ባሮች ለሚሰሩት ስራ
ችሎታ ፣ ፍላጎትና እቅድ አላቸው፡፡ አላህ እነርሱን ፣ ችሎታቸውን ፣ እቅዳቸውን እና
ፍላጎታቸውን ፈጣሪ ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 46/60
ِ ُّ ‫اَّل ر‬ ِ ِ ِ ِ
﴾‫ن‬
َ ‫ب الْ َعالَم‬َ َُّ ‫﴿ل َمن ََاء من ُك ْم أَن يَ ْستَق َيم۞ َوَما تَ َش ُاؤو َن إَّال أَن يَ َشاء‬
“ከናንተ ቀጥተኛ መሆንን ለሻ ሰው (መገሰጫ) ነው ፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ
ካልሻም አትሹም፡፡” አት ተክዊር፡

ይህን የቀደር ደረጃ “የዚህ ማህበረሰብ መጁስ” በማለት ነብዩ ‫ ﷺ‬የጠሯቸው


አብዛኞቹ ቀደርዮች አስተባብለውታል፡፡ በዚህ ዙሪያ ከአጽዳቂዎች የተወሰኑት ወሰን
አልፈዋል፡፡ ችሎታን እና ምርጫን ከባሪያው ላይ ነጥቀዋል፡፡ ጥበቧንና ፋይዳዋን ደግሞ
ከአላህ ተግባርና ከእርሱ ህግጋት ላይ አውጥተውታል፡፡
የኢማን እውነታና
ከባድ ወንጀሎችን የሚሰሩ ሰዎች ብይን

ዲን እና ኢማን ፡ ንግግር እና ተግባር መሆናቸው ከአህለሱና ወልጀማዓህ


መሰረቶች አንዱ ነው፡፡ ንግግር ሲባል የቀልብና የምላስ ፤ ተግባር ሲባል ደግሞ የአካል
፣ የምላስ እና የልብ ማለት ነው፡፡

ኢማን አላህን በመታዘዝ የሚጨምር ፣ በወንጀል የሚቀንስ መሆኑ (የአህለሱና


ወልጀማዓህ መሰረት ነው)፡፡

ይህ ከመሆኑ ጋር ኸዋሪጆች እንደሚሰሩት (ከኢስላም የማያስወጡ) ወንጀሎችና


ታላላቅ ሐጢያቶች የቂብላ ባለቤቶችን አያከፍሩም፡፡ ይልቁንም (ከኢስላም
የማያስወጡ) ወንጀሎች ጋር ኢማናዊ ወንድማማችነት የተረጋገጠ ነው፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


ِ ‫﴿فَمن ع َِي لَه ِمن أ‬
ِ ‫َخ ِيه ََيء فَاتِباع ِِبلْمعر‬
﴾‫وف‬ُْ َ ٌ َ ٌ ْ ْ ُ َ ُ َْ
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 47/60

“ለእርሱም (ለገዳዩ) ከወንድሙ (ደም) ትንሽ ነገር ምህረት የተደረገለት ሰው


(በመሀሪው ላይ የካሳ ክፍያውን) በመልካም መከታተል” አል በቀራህ፡

‫ُخَرى فَـ َقاتِلُوا الَِِّت تَـْبغِي‬ ِ ‫ان ِمن الْمؤِمنِن اقْـتـتـلُوا فَأ‬
ْ ‫ت إِ ْح َد ُاُهَا َعلَى ْال‬
ْ َ‫َصل ُحوا بَـْيـنَـ ُه َما فَِإن بَـغ‬
ْ َ َ َ ْ ُ َ ِ َ‫﴿ َوإِن طَاَِِت‬
‫ن۞إََِّّنَا‬ ِِ
َ ‫ب الْ ُم ْقسط‬ َّ ‫َصلِ ُحوا بَـْيـنَـ ُه َما ِِبلْ َع ْد ِل َوأَقْ ِسطُوا إِ َّن‬
ُّ ‫اَّلَ ُُِي‬ ْ ‫اءت فَأ‬
َِّ ‫ح ََّّت تََِيء إِ ََل أَم ِر‬
ْ َ‫اَّل فَِإن ف‬ ْ َ َ
﴾‫َخ َويْ ُك ْم‬ ِ ‫الْمؤِمنو َن إِخوةٌ فَأ‬
َ‫نأ‬َ َْ‫َصل ُحوا ب‬ْ َْ ُ ُْ
“ከምእመናንም የሆኑ ሁለት ጭፍሮች ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ፡፡
ከሁለቱ አንደኛይቱም በሌላይቱ ላይ ወሰን ብታልፍ ያችን ወሰን የምታልፈውን
ወደ አላህ ትዕዛዝ እስከምትመለስ ድረስ ተጋደሉ፡፡ ብትመለስም በመካከላቸው
በትክክል አስታርቁ፡፡ በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን
ይወዳልና፡፡ ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም
መካከል አስታርቁ፡፡” አል ሑጁራት፡

ሙዕተዚላዎች እንደሚሉት እስልምና ተከታይ የሆነ ፋሲቅ (አመጸኛ)


እስልምናውን በአጠቃላይ አይነጥቁትም ፣ በእሳት ውስጥም አያዘወትሩትም፡፡
ይልቁንም በሚከተለው ቁርኣን አላህ እንደተናገረው ፋሲቅ (አመጸኛ) የሆነ ሰው
ጠቅላይ በሆነው የኢማን ስም ውስጥ ይገባል፡፡
﴾‫﴿فَـتَ ْح ِر ُير َرقَـبَ ٍة ُّم ْؤِمنَ ٍة‬

“ያመነችን ጫንቃ ነጻ ማውጣት” አን ኒሳእ፡

አንዳንዴ በሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ መሰረት ጠቅላይ በሆነው የኢማን ስም


ውስጥ ላይካተት ይችላል፡፡

‫آَيتُهُ َز َاد ُْْْم إَِيَ ا‬ ِ ِ ِ ِ َّ ِ


﴾‫اَن‬ ْ َ‫وَبُْم َوإِ َذا تُلي‬
َ ‫ت َعلَْي ِه ْم‬ ْ َ‫ين إِ َذا ذُكَر اَّلُ َوجل‬
ُ ُ‫ت قُـل‬ ِ
َ ‫﴿إََّّنَا الْ ُم ْؤمنُو َن الذ‬
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 48/60
“ፍጹም ምእምናን እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት ፣ በነሱም
ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸው ናቸው፡፡” አል አንፋል፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

‫ وال يسرق السارق حين يسرق وهو‬، ‫"ال يزني الزاني حين يزني وهو مؤمن‬
‫ وال ينتهب نهبة ذات شرف‬، ‫ وال يشرب الخمر حين يشربها وهو مؤمن‬، ‫مؤمن‬
"‫يرفع الناس إليه فيها أبصارهم حين ينتهبها وهو مؤمن‬

“ዝሙተኛ ዝሙት በሚሰራበት ጊዜ እርሱ አማኝ ሆኖ ዝሙት አይሰራም ፤ ሌባ


በሚሰርቅበት ጊዜ እርሱ አማኝ ሆኖ አይሰርቅም ፤ አስካሪ መጠጥ በሚጠጣ ጊዜ እርሱ
አማኝ ሆኖ አይጠጣም ፤ እርሱ አማኝ ሆኖ ሰዎች ወደርሱ የአይን ትኩረት የሚስብ
ከሰዎች ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነን ንብረት አይዘርፍም” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

“እርሱ እምነቱ የጎደለ አማኝ ነው ወይም በእምነቱ አማኝ ነው ፣ በከባድ ወንጀሉ


ደግሞ ፋሲቅ (አመጸኛ) ነው፡፡ ሙሉ የሆነው የኢማን ስም አይሰጠውም ፣ ጎደሎ
የሆነው የኢማን ስም ግን አይነፈገውም፡፡” ይላሉ፡፡
ሶሃቦችን አስመልክቶ ያለብን ግዴታ
የእነርሱ ማንነትና ደረጃ ትውስታ

አላህ በሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ እንደገለጸው የረሡልን ‫ ﷺ‬ሶሃቦች


አስመልክቶ ምላሳቸውም ፣ ቀልባቸውም ሰላም መሆኑ ከአህለሱና ወልጀማዓ
መሰረቶች አንዱ ነው፡፡

‫ان َوَال ََْت َع ْل ِِف قُـلُوبِنَا ِغ ًَّل‬


ِ َ‫وَن ِِبِْْلَي‬
َ ‫ين َسبَـ ُق‬ ِ َّ‫﴿والَّ ِذين جاؤوا ِمن بـع ِد ِهم يـ ُقولُو َن ربـَّنا ا ْغ َِر لَنا وِِْلخوانِنا ال‬
‫ذ‬
َ َ َْ َ َ ْ َ َ َ ْ َْ َُ َ َ
﴾‫وف َّرِح ٌيم‬ ِِ
َ َّ‫ين َآمنُوا َربـَّنَا إِن‬
ٌ ‫ك َرُؤ‬ َ ‫للَّذ‬
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 49/60
“እነዚያም ከበኋላቸው የመጡት 'ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት
ለቀደሙን ወንድሞቻችን ምህረት አድርግ፡፡ በልቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ
ለአመኑት (ሰዎች) ጥላቻን አታድርግ፡፡ ጌታችን ሆይ! አንተ ሩህሩህ አዛኝ ነህና'
ይላሉ፡፡” አል ሐሽር፡

በሚከተለው የረሡል ‫ ﷺ‬ንግግር መታዘዛቸውም (ከአህለሱና ወልጀማዓ መሰረቶች


አንዱ ነው፡፡

‫"ال تسبوا أصحابي فواالذي نفسي بيده لو أن أحدكم أنفق مثل أحد ذهبا ما بلغ مد‬
"‫أحدهم وال نصيفه‬

“ሶሃቦቸን አትሳደቡ፡፡ ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ ፣ ከመካከላችሁ አንዱ የኡሁድን


ተራራ ያክል ወርቅ ቢለግስ ከእነርሱ መካከል አንዱ እፍኝ ወይም ግማሽ ከለገሰው
አይደርስም፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

የሶሃቦች ደረጃ
ሶሃቦችን አስመልክቶ የአህለሱና ወልጀማዓ አቋም
በሶሀቦች መካከል ያለው መበላለጥ
ደረጃቸውንና ብልጫቸውን በተመለከተ በቁርኣን ፣ በሀዲስ እና በዑለሞች
ስምምነት የመጣውን ይቀበላሉ፡፡ ከፈትህ - ከሁደይቢያ ስምምነት - በፊት የለገሱትንና
የተጋደሉትን ፣ ከእነርሱ በኋላ ከለገሱትና ከተጋደሉት ያበልጣሉ፡፡ ሙሐጅሮችን
ከአንሷሮች ያስቀድማሉ፡፡

“ሙሐጅር ” ፡ መካ ከመከፈቱ በፊት ወደመዲና የተሰደዱ ሶሃቦች ሙሐጅር በመባል ይጠራሉ፡፡


“አንሷር ” ፡ የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬እና ሶሃቦች የተሰደዱባቸው እና ስደተኞችን ተንከባክበው
የተቀበሉ የመዲና ነዋሪዎች አንሷር በመባል ይጠራሉ፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 50/60
አላህ በድር ዘመቻ ላይ ለተሳተፉት -አንድ መቶ አስራ ሶስት ለሚሆኑ ሶሃቦች-
“የፈለጋችሁትን ስሩ በእርግጥ ለእናንተ ምሬያለሁ” ማለቱን ያምናሉ፡፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬በተናገሩት መሰረት ቁጥራቸው ከአንድ ሽ አራት መቶ


በላይ የሚሆኑ በዛፏ ስር ቃል ኪዳን ከገቡ ሶሃቦች መካከል አንድ እንኳ ቢሆን እሳት
እንደማይገባ ፣ አላህ ስራቸውን እንደወደደ ፣ እነርሱም ከአላህ የተሰጣቸውን
እንደወደዱ ያምናሉ፡፡ የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬በጀነት የመሰከሩላቸውን ይመሰክራሉ፡፡
ለምሳሌ፡- አስሮቹ ፣ ሳቢት ብን ቀይስ ብን ሸማስ e እና ሌሎችም ሶሃቦች ናቸው፡፡

በድር ዘመቻ ላይ የተሳተፉ ሶሃቦች ከሌሎች ሁሉ በደረጃ ይበልጣሉ፡፡ በድር የታወቀው ዘመቻ
የተካሄደባት ቦታ ነው፡፡ ዘመቻው የተካሄደው በሁለተኛው አመተ ሂጅራ ረመዷን ወር ላይ ነው፡፡ ይህ ጦርነት
“የውመል ፉርቃን” (ሀቅና ክህደት በግልጽ የተለየበት) በመባልም ይታወቃል፡፡ ጦርነቱ ታስቦበት የተካሄድ
አይደለም፡፡ አቡሱፍያን ነጋዴዎች ጋር ሆኖ ከሻም ወደመካ መምጣቱ ለረሡል ‫ ﷺ‬መረጃው ሲደርሳቸው
ሶስት መቶ አስራ ሶስት የሚሆኑ ሶሃቦች ነጋዴዎችን በአፋጣኝ እንዲወሩና ንብረታቸው በሙስሊሞች ቁጥጥር
ስር እንዲሆን መመሪያ አስተላለፉ፡፡ በትዕዛዙ መሰረት ከመዲና ተንቀሳቀሱ፡፡ ጦርነት አላማቸው
አልነበረም፡፡ አላህ ለጥበቡ ሙስሊሞችና ከሀዲዎች በበድር እንዲዋጉ አደረገ፡፡ ጦርነቱ በሙስሊሞች
አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
አቡበክር ፣ ዑመር ፣ ዑስማን ፣ ዓልይ ፣ ሰዒድ ብን ዘይድ ፣ ሰዕድ ብን አቢ ወቃስ ፣ ዓብዱረህማን ብን
ዓውፍ ፣ ጦልሃ ብን ዑበይዱሏህ ፣ ዙበይር ብን አልዓዋም ፣ አቡዑበይዳ ዓሚር ብን አልጀራህ ናቸው፡፡
ሳቢት ብን ቀይስ e ድምጹ ከፍተኛ ከሆኑ የነብዩ ኸጢቦች መካከል አንዱ ነበር፡፡ የሚከተለው ቁርኣን
በወረደ ጊዜ በቃ ይህ ቁርኣን የወረደው እኔን በተመለከተ ነው ፣ ስለዚህ ሳላውቅ ስራየ ተሰርዟል በሚል
ከቤቱ ተደብቆ ተቀመጠ፡፡
‫ط أ َْع َمالُ ُك ْم َوأَنتُ ْم َال‬ ٍ ‫ض ُك ْم لِبَـ ْع‬
َ َ‫آ أَن ََْتب‬ ِ ‫َّب وَال ََْتهروا لَه ِِبلْ َقوِل َكجه ِر بـع‬
ْ َ ْ َ ْ ُ ُ َ َ ِ ِ‫ص ْوت الن‬
ِ ‫﴿َي أَيـُّها الَّ ِذين آمنُوا َال تَـرفَـعوا أَصواتَ ُكم فَـو َق‬
َ ْ ْ َْ ُ ْ َ َ َ َ
﴾‫تَ ْشعُ ُرو َن‬
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ድምጾቻችሁን ከነብዩ ድምጽ በላይ ከፍ አታድርጉ፡፡ ከፊላችሁም ለከፊሉ
እንደሚጮህ በንግግር ለርሱ አትጩሁ፡፡ እናንተ የማታውቁ ስትሆኑ ስራዎቻችሁ እንዳይበላሹ
(ተከልከሉ)፡፡” አል ሑጁራት፡ =
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 51/60
በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ከነብዩ ‫ ﷺ‬በኋላ በላጩ አቡበክር ፣ ከዚያም ዑመር ፣
ሶስተኛው ዑስማን ፣ አራተኛው ዓልይ እንደሆነ ከሙእሚኖች መሪ ዓልይ ብን
አቢጧሊብ በተከታታይ የተያዙ ዘገባዎች ያረጋግጣሉ፡፡

አንዳንድ አህለሱናዎች- አቡበክና ዑመር ተቀዳሚ በመሆናቸው ከተስማሙ በኋላ


ከዑስማን እና ከዓልይ በደረጃ ማን ይበልጣል? በሚለው ከመለያየታቸው ጋር በቃል
ኪዳን ዑስማን ለመቀደሙ ሶሃቦች ተስማምተዋል ፣ ከሰለፎች የመጡ ወሬዎችም
ይህንኑ ይጠቁማሉ፡፡

ከሰዎች መካከል ዑስማንን ካስቀደሙ በኋላ ዝም ያሉ ወይም ዓልይን አራተኛ


ያደረጉ አሉ፡፡ ከሰዎች መካከል ዓልይን ያስቀደሙ ፣ ሌሎች ደግሞ ተወቁፍ - ሐሳብ
ከመስጠት የተቆጠቡ - አሉ፡፡

ከአራቱ ኸሊፋዎች ዓልይን ማስቀደም ሸሪዓዊ ብይኑ

ነገር ግን የዑስማንና የዓልይ ጉዳይ - ከአብዛኛው አህለሱና ዘንድ እርሱን


የተቃረነ በጠማማነት የማይፈረጅበት ቢሆንም ዑስማንን አስቀድሞ ከዚያም ዓልይን
ተከታይ በማድረግ ላይ የአህለሱናዎች ጉዳይ የጸና ሆኗል፡፡ የኺላፋ - የመሪነትን -
ጉዳይ መቃረን ጠማማ የሚሆኑበት ጉዳይ ነው፡፡
= ነብዩ ‫ ﷺ‬ከአካባቢው ሲያጡት ወደመኖሪያ ቤቱ አንድ ሰው ላኩ፡፡ ግለሰቡ በምን ምክንያት እንደቀረ ጠየቀው፡፡
“አላህ እኔን በሚመለከት ቁርኣን አውርዷል ፤ ከነብዩ ድምጽ በላይ የምጮህ እኔ ነኝ ፤ ስራየም ተሰርዟል ፤ በዚህ
ምክንያት የእሳት ሰው ነኝ፡፡” የሚል ምላሽ ሰጠው፡፡ ግለሰቡ ሳቢት የሰጠውን መልስ ይዞ ለነብዩ ‫ ﷺ‬ነገራቸው፡፡
ነብዩ ‫ﷺ‬የሚከተለውን ተናገሩ፡-
"‫ ولكنك من أهل الجنة‬، ‫ فقل له إنك لست من أهل النار‬، ‫"اذهب إليه‬
“ወደርሱ ሂድና አንተ ከጀነት ሰዎች እንጅ ፣ ከእሳት ሰዎች አይደለህም” በለው፡፡ ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡ ነብዩ ‫ ﷺ‬በጀነት አበሰሩት፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 52/60
ከረሡል ‫ ﷺ‬በኋላ መሪነቱ የአቡበክር፣ የዑመር ከዚያም የዑስማን ከዚያም የዓልይ
እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል በአንዱ መሪነት ላይ ትችት ያቀረበ ከቤተሰቡ
አህያ የጠመመ ነው፡፡
የነብዩ ቤተሰቦች ደረጃ ከአህለሱና ወልጀማዓ ዘንድ
የረሡልን ‫ ﷺ‬ቤተሰቦች ያፈቅራሉ ፤ ወዳጅ አድርገው ይይዛሉ ፤ የረሡልን ‫ ﷺ‬አደራ
ይጠብቃሉ፡፡
የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬በ “ገዲር ኹም” ቀን የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"‫"أذكركم هللا في أهل بيتي‬

“የቤተሰቦቸን ጉዳይ - መልካም እንድትሰሩላቸው - አላህን አስታውሳችኋለሁ” ሙስሊም፡

አንዳንድ ቁረይሾች በኒ ሐሽሞችን እንደሚጠሉ ለአጎታቸው ዓባስ e ስሞታ በቀረበበት


ጊዜ ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

" ‫ هلل ولقرابتي‬، ‫ ال يؤمنون حتى يحبوكم‬، ‫"والذي نفسي بيده‬

“ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! ለአላህ እና ለቅርብ ዝምድናየ ብለው እናንተን


እስካልወደዱ ድረስ አያምኑም” ቲርሚዚይ፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


ቀኑ ዙልሂጃ አስራ ስምንተኛው ቀን ነው፡፡ “ገዲር” የሚለው “ኸም” ወደተባለ ግለሰብ ነው
የተጠጋው፡፡ ይህ ቦታ በመካና በመዲና መካከል ጁህፋ ቀረብ ብሎ ባለው መንገድ ላይ ይገኛል፡፡ ረሡል ‫ﷺ‬
ከሐጅ ሲመለሱ በዚህ ቦታ አርፈው ነበር፡፡ ለሰዎች ኹጥባ አደረጉ “የቤተሰቦቼን ጉዳይ አላህን
አስታውሳችኋለሁ” በማለት ሶስት ጊዜ ደጋግመው ተናገሩ፡፡ አላህን አስታውሱ ፣ የቤተሰቦቼን ሐቅ
ካጓደላችሁ ፣ ፍርሀቱን ፣ መበቀሉን አስታውሱ ፤ በሐቃቸው ከቆማችሁ ደግሞ እዝነቱን ፣ ምንዳውን
አስታውሱ፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 53/60
‫ واصطفى من‬، ‫ واصطفى من بني إسماعيل كنانة‬، ‫"إن هللا اصطفى بني إسماعيل‬
"‫ واصطفاني من بني هاشم‬، ‫ واصطفى من قريش بني هاشم‬، ‫كنانة قريش‬

“አላህ የኢስማኢልን ልጆች መርጧል ፣ ከኢስማኢል ልጆች ደግሞ ኪናናን መርጧል ፣


ከኪናና ቁርይሾችን መርጧል ፣ ከቁረይሽ ደግሞ በኒ ሐሽምን መርጧል ፣ ከበኒ ሀሽሞች
እኔን መርጧል፡፡” ሙስሊም፡

የነብዩ ሚስቶች ከአህለሱና ወልጀማዓ ዘንድ


የምእመናን እናቶች የሆኑትን የረሡል ‫ ﷺ‬ሚስቶችን ይወዳሉ፡፡ በአኼራ
ሚስቶቻቸው እንደሚሆኑ ያምናሉ፡፡ በተለይም የብዙ ልጆቻቸው እናት ፣ በእርሳቸው
መጀመሪያ ያመነች ፣ በጉዳያቸው ላይ ድጋፍ ያደረገች የሆነችውን ኸዲጃን g ይወዳሉ፡፡
ከእርሳቸው ዘንድ ትልቅ ደረጃ እንደነበራት ያምናሉ፡፡

እውነተኛና የእውነተኛ ልጅ የሆነችውን (ዓኢሻ) g በተመለከተ ረሡል ‫ﷺ‬


የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"‫"فضل عائشة على النساء كفضل الثريد على سائر الطعام‬
“ከሴቶች ሁሉ የአኢሻ ብልጫ ከሌሎች ምግቦች ሰሪድ እንደሚበልጠው ነው” ቡኻሪ፡

ሙስሊም፡

አህለሱና ወልጀማዓዎች ሶሃቦችን እና የረሡልን ቤተሰቦች አስመልክቶ ሙብተዲኦች


ከሚሉት ነገር የጸዱ መሆናቸው
“ከሴቶች ሁሉ” ሲባል ሁለት አይነት ትርጉም ከዑለሞች ዘንድ ተሰንዝሯል፡፡ አንደኛው በአጠቃላይ
በአለም ከሚገኙ ሴቶች ሁሉ ዓኢሻ g በደረጃ ትበልጣለች የሚል ትርጉም ሲሆን ፣ ሁለተኛው ደግሞ
ከኸዲጃ ውጭ በህይዎት ከረሡል ‫ ﷺ‬ጋር ከነበሩት ሚስቶቻቸው መካከል ዓኢሻ g በደረጃ ትበልጣለች የሚል
ትርጉም ነው፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 54/60

ሶሃቦችን ከሚጠሉና ከሚሳደቡ ራፊዷዎች እንዲሁም በንግግር እና በተግባር የረሡልን


‫ ﷺ‬ቤተሰቦች ከሚያውኩ ነዋሲቦች መንገድ ራሳቸውን ያጸዳሉ፡፡

በሶሃቦች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ይቆጠባሉ፡፡ ስለነርሱ መጥፎነት


የተወራው ወሬ “ከፊሉ ውሸት እንደሆነ ፣ ከፊሉ የተጨመረበት ፣ የተቀነሰበት እና
ከነበረበት ይዘት የተቀያየረ ነው” ይላሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ትክክለኛው ወሬ በዲን ጉዳይ
ጥረትና ምርምር ሲያደርጉ ትክክለኛውን ያገኙ ወይም የተሳሳቱ በመሆናቸው
ምክንያት ሊሰጣቸው የሚገቡ ሰዎች ናቸው የሚለው ነው፡፡

ይህ ከመሆኑ ጋር እያንዳንዱ ሶሃባ ከከባድም ይሁን ከትናንሽ ወንጀል ጥብቅ


ናቸው ብለው አያምኑም፡፡ በጥቅሉ ሐጢያት ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጅ ሐጢያት
ከእነርሱ ዘንድ ተከስቶ ከሆነ ሐጢያቶቻቸውን ይቅር የሚያስብል ቀዳሚነትና
ደረጃዎች አላቸው፡፡ ከእነርሱ በኋላ የማይማር ሐጢያት ለእነርሱ ይማራል፡፡
ምክንያቱም ከእነርሱ በኋላ የመጣው ትውልድ ያልሰራው ሐጢያትን የሚያሰርዝ
መልካም ስራዎች አሏቸው፡፡ ከትውልዱ ሁሉ በላጮች መሆናቸው በረሡል ‫ ﷺ‬ንግግር
ተረጋግጧል፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድ እፍኝ የሚለግሰው ፣ ከእነርሱ በኋላ የኡሁድን
ተራራ ያክል ወርቅ ከሚለግሰው ይበልጣል፡፡

“ራፊዷ” ፡ የሚባሉት ለሶሃቦች በጣም ጥላቻ ያላቸው በዓልይ ብን አቢ ጧሊብና e በቤተሰቦቹ ላይ


ደግሞ ድንበር ያለፉ ከቢድዓ ባለቤቶች ሁሉ በጣም ጠማማ የሚባሉ ቡድኖች ናቸው፡፡ “ራፊዷ” የተባሉበት
ምክንያት በአቡበክርና በዑመር ላይ ያለውን አቋም እንዲገልጽላቸው ዘይድ ብን ዓልይ ብን ሁሰይን ብን ዓልይ
ብን አቢጧሊብን ሲጠይቁት እነርሱን እንደሚወድና እንደሚያፈቅር ገለጸላቸው፡፡ ዘይድን ወዲያውኑ
አገለሉት አኮረፉት በዚህ ምክንያት “ራፊዷ” የሚል ስያሜ ተሰጣቸው፡፡
“ነዋሲብ” የሚባሉት ደግሞ በ “ራፊዷ” ተቃራኒ የረሡልን ‫ ﷺ‬ቤተሰቦች የሚጠሉ ፣ የሚያንቋሽሹ እና
የሚሳደቡ ናቸው፡፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 55/60

ከእነርሱ መካከል አንዱ ሐጢያት ቢፈጽም ፣ ከእርሱ ሊጸጸት ወይም እርሱን


የሚያሰርዝ መልካም ስራ ሊሰራ ወይም ለመልካም ስራ ቀዳሚ በመሆኑ ወይም
ከሰዎች ሁሉ ለሙሐመድ ‫ ﷺ‬ምልጃ ተገቢ በመሆኑ ሊማርለት ወይም በዱንያ ላይ
በደረሰበት መከራ ተፈትኖ ወንጀሉ በእርሱ ምክንያት ሊሰረዝለት ይችላል፡፡

ይህ ለተረጋገጠው ወንጀል ከሆነ በዲን ጉዳይ ተመራምረው ስህተት ላይ ለወደቁበት


እንዴት ሊሆን ነው? ትክክለኛውን ካገኙ ሁለት ምንዳ የሚያገኙ ሲሆን ፣ ከተሳሳቱ
ደግሞ ስህተታቸው ተምሮ አንድ ምንዳ ያገኛሉ፡፡

ከእነርሱ መካከል ከፊሎቹ ፈጽመውታል ተብሎ እየተወገዘ ያለው መጠኑ ትንሽ


ወይም ቀላል ከሆነ ካላቸው ደረጃ ፣ ከፈጸሙት መልካም ስራ - በአላህ እንዲሁም
በረሡል ‫ ﷺ‬በማመናቸው ፤ በአላህ መንገድ በመታገላቸው ፤ ለዲን ብለው
በመሰደዳቸው ፤ ዲንን በመርዳታቸው ፤ በጠቃሚ እውቀታቸው እና በአጠቃላይ
ከፈጸሙት መልካም ስራ አኳያ ሲታይ ስህተታቸው እንደሌለ ይቆጠራል፡፡

በእነርሱ ላይ አላህ የለገሳቸውን ደረጃ እንዲሁም ታሪካቸውን በእውቀትና በማስረጃ


የተመለከተ ሰው እነርሱ ከነብያት በኋላ በላጭ ሰዎች መሆናቸውን ፣ የእነርሱ አይነት
ትውልድ ከዚህ በፊት ያልነበረ ፣ ለወደፊትም ሊኖር እንደማይችል በእርግጥ ያውቃል፡፡
በዚህ ክፍለ ዘመን ለሚገኝ ማህበረሰብ የተላቁ ከአላህ ዘንድ በላጭና ምርጦች
መሆናቸውን ይገነዘባል፡፡

የአላህ ወዳጆች ከተለምዶ ወጣ ያለ ክብር መሰጠታቸውን አስመልክቶ አህለሱና


ወልጀማዓ የሚከተሉት መንገድ
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 56/60

ለአላህ ወዳጆች ከተለምዶ ወጣ ያለ ክብር መሰጠታቸውን እውነት ብሎ


ማረጋገጥ ከአህለሱና ወልጀማዓህ መሰረቶች አንዱ ነው፡፡ ከእውቀት አይነቶች ፣ ስውር
ነገሮች መገለጽ ፣ ከችሎታ አይነቶችና ተጽእኖዎች በአጠቃላይ ከልማዱ ወጣ ያሉ
ነገሮች በእጆቻቸው ላይ አላህ እንዲከሰት ማድረጉ ነው፡፡ በከህፍ ምዕራፍ ፣ በሌሎችም
ቀደምት ህዝቦችና በዚህ ትውልድ መጀመሪያ ላይ በነበሩ ሶሃቦች ፣ ታብዕዮች እና
ሌሎች ማህበረሰቦች የተከሰቱ ከልማዱ ወጣ ያሉ ክብሮች ናቸው፡፡ ይህ እስከቂያማ ቀን
የሚገኝ ነው፡፡

የአህለሱና ወልጀማዓ ባህሪያት

ለምን በዚህ ስያሜ ተሰየሙ?

በግልጽም ይሁን በስውር የረሡልን ‫ ﷺ‬ዱካ ፣ ከሙሐጅርና ከአንሷር የሆኑ


የመጀመሪያዎችን ቀዳሚዎች መንገድ መከተል ከአህለሱና ወልጀማዓህ መንገድ አንዱ
ነው፡፡
የሚከተለውን የረሡል ‫ ﷺ‬አደራ መከተል ፡ -

‫ وعضوا‬، ‫"عليكم بسنتي وسنة الخلفاء الراشدين المهديين من بعدي تمسكوا بها‬
"‫ فإن كل بدعة ضاللة‬، ‫ وإياكم ومحدثات األمور‬، ‫عليها بالنواجذ‬

“ሱናየን ፣ ከእኔ በኋላ ሀቅን አውቀው በሰሩ እና አላህ ወደሀቁ የመራቸው የሆኑትን
ምክትሎቸን ሱና (በእጃችሁ) አደራ አጥብቃችሁ ያዙ ፣ እርሷንም በመንጋጋ ጥርሳችሁ
አደራ ነክሳችሁ ያዙ ፣ አስጠነቅቃችኋለሁ ፣ የነገሮችን ፈጠራዎችንም ፣ ማንኛውም
አዲስ ፈሊጥ ጥመት ነው፡፡” አቡዳውድ፡ ቲርሚዚይ፡ ኢብኑ ማጀህ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል
ተህቂቅ አል መሸካት፡
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 57/60
ከንግግሩ ሁሉ በጣም እውነተኛ የአላህ ንግግር መሆኑን ፣ ከመመሪያው ሁሉ
በላጩ የሙሀመድ መመሪያ መሆኑን ያውቃሉ፡፡ ከተለያዩ የሰው ዘር ንግግሮች
የአላህን ንግግር ያስቀድማሉ፡፡ ከማንኛውም መመሪያ የሙሀመድን መመሪያ
ያስቀድማሉ፡፡ በዚህ ምክንያት የ “መጽሐፍና የሱና ባለቤቶች” የሚል ስያሜ
ተሰጧቸዋል፡፡ “የጀማዓ ባለቤት” የሚል ስያሜም ተሰጧቸዋል፡፡ ጀማዓህ የሚለው ቃል
ለተሰባሰበ ማህበረሰብ የተሰጠ ስያሜ ቢሆንም መሰባሰብ የሚል ትርጉምም አለው፡፡
ተቃራኒው ደግሞ ፉርቃ ወይም መከፋፈል ነው፡፡ ኢጅማዕ ማለት ለዲን እና ለእውቀት
የሚደገፉበት ሶስተኛው መሰረት ነው፡፡ ሰዎች በአጠቃላይ ያሉበትን ከንግግርም ይሁን
ከተግባር ፣ ስውርም ይሁን ግልጽ ፣ ከዲን ጋር ተያያዥ ያላቸውን ነገሮች በእነዚህ
ሶስት መሰረቶች ላይ ይመዝኗቸዋል፡፡

የኢጅማዕ ህግና ስርዓት የተመሰረተው ቀደምት ሰለፎች በነበሩበት ላይ ነው፡፡


ከእነርሱ በኋላ ልዩነቱ በዝቷል ፤ ማህበረሰቡም ተበታትኗል፡፡
የዓቂዳ ማሟያዎች
አህለሱና የሚዋቡባቸውየተከበሩ ስነምግባራትና መልካም ተግባራቶች

ከእነዚህ መሰረቶች ጋር ሸሪዓው በሚያዘው መሰረት በመልካም ያዛሉ ፣ ከመጥፎ ይከለክላሉ፡

በመልካም ለማዘዝና ከመጥፎ ለመከልከል የሚከተሉት አራት መስፈርቶች መኖር አለባቸው፡-


1ኛ- በሚያዘው እና በሚከለክለው ነገር ላይ ሸሪዓዊ እውቀት ሊኖረው ፣
2ኛ፡-ሊታዘዝና ሊከለከል የሚገባው ሰው ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን የሚያዘውን ሰው ባህሪ ሊያውቅ

3ኛ፡- በሚያዘው ሰዓት የሚታዘዘውን ሰው ባህሪ ማወቅ ፣ ሊያዘው የፈለገውን ትዕዛዝ ከዚህ በፊት ፈጽሞታል
ወይስ አልፈጸመውም? የሚለውን ማጣራት ያስፈልጋል፡፡
4ኛ፡- በመልካም ለማዘዝና ከመጥፎ ለመከልከል ያለምንም ችግር አቅሙ ሊኖረው ይገባል፣
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 58/60

ሐጅን ፣ ጅሐድን ፣ ጁሙዓን ፣ ዒድን በጎም ይሁን አመጸኛ ከሆኑ መሪዎች ጋር


መከናወን እንዳለበት ይመለከታሉ፡፡

ጀማዓዎችን ይጠብቃሉ ፤ ማህበረሰቡን በትክክል በመምከር ወደአላህ ይቃረባሉ፡፡

የሚከተለውን የረሡል ‫ ﷺ‬ንግግር ያምኑበታል፡-

.‫ يشد بعضه بعضا " وشبك بين أصابعه‬، ‫"المؤمن للمؤمن كالبنيان‬

“ሙእሚን ለሙእሚን (ልክ) እንደ እንድ ግንባታ ነው ፣ ከፊሉ ከፊሉን ያጠነክራል”


በጣቶች መካከል አስተሳሰሩ ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

، ‫"مثل المؤمنين في توادهم وتراحمهم وتعاطفهم كمثل الجسد إذا اشتكى منه عضو‬
"‫تداعى له سائر الجسد بالحمى والسهر‬

“ሙእሚኖች የመዋደዳቸው ፣ የመተዛዘናቸው ፣ አንዱ ለአንዱ ሩህሩህ የመሆናቸው


ምሳሌ ልክ እንደ አንድ አካል አምሳያ ናቸው፡፡ ከእርሱ አንዱ የሰውነት አካል ከታመመ
ሌሎች አካላቶች በሙሉ በትኩሳት እና እንቅልፍ በማጣት ይጠራራሉ፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

በመከራ ጊዜ በትዕግስት ያዛሉ ፤ በደስታ ጊዜ አላህን ያመሰግናሉ ፤ መራራ


የሆነውን የአሏህ ውሳኔ ወደው ይቀበላሉ፡፡ ወደመልካም ስነምግባር ፣ ወደደግ ተግባራት
ይቀሰቅሳሉ፡፡ የሚከተለውን የረሡል ‫ ﷺ‬ንግግር ያምኑበታል፡-

"‫"أكمل المؤمنين إيمانا أحسنهم خلقا‬

“ከእምነት በኩል የተሟላው አማኝ ፣ ስነምግባሩ በጣም ያማረው ነው፡፡” አቡዳውድ፡

ቲርሚዚይ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሐሰን ብለውታል፡ አል መሸካት፡


አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 59/60

ዝምድናህን የቆረጠውን አካል እንድትቀጥል ፣ የከለከለህን እንድትሰጥ ፣


የበለደለህን ይቅር እንድትል ይቀሰቅሳሉ፡፡

ለወላጆች በጎ በመስራት ፣ ዝምድናን በመቀጠል ፣ ለጎረቤት መልካም በመሆን ፤


ለየቲሞች ፣ ለምስኪኖች ለሙሳፊሮች በጎ በመስራት ፤ በስር ለተቆጣጠሯቸው አካላት
በማዘን ላይ ያዛሉ፡፡ ከጉራ እና ከኩራት ፣ ወሰን ከማለፍና ፣ በሐቅም ይሁን ያለሐቅ
በፍጡራን ላይ መንደላቀቅን ይከለክላሉ፡፡

በከፍተኛ ስነምግባር ላይ ያዛሉ ፤ ከወራዳ ስነ-ምግባር ይከለክላሉ፡፡

በዚህም ይሁን በሌላ ፣ በሚናገሩትም ይሁን በሚተገብሩት ሁሉ የሚከተሉት


ቁርኣንን እና ሐዲስን ነው፡፡ መንገዳቸው አላህ ሙሐመድን ‫ ﷺ‬በላከበት የኢስላም
እምነት ነው፡፡

ነገር ግን ነብዩ ‫ ﷺ‬ተከታዮቻቸው ከሰባሶስት እንደሚከፋፈሉ ፣ አንዷ ብቻ ስትቀር


ሌሎች የእሳት እንደሚሆኑ ፣ እርሷም ጀማዓ መሆኗን በመናገራቸው ፣ እንዲሁም
በሐዲሳቸው የሚከተለውን በመናገራቸው ምክንያት ጥርት ያለውን እና ከመቀላቀል
የጸዳውን ኢስላም አጥባቂዎቹ አህለሱና ወልጀማዓዎቹ ሆኑ፡፡

"‫"هم من كان على مثل ما أنا عليه اليوم وأصحابي‬

“እነርሱ ፣ እኔም ሶሃቦቸም ዛሬ በእርሱ ላይ ባለንበት አይነት የሆኑት ናቸው፡፡” ቲርሚዚይ፡

በውስጣቸው ሲዲቆች ፣ ሸሂዶች ፣ ሷሊሆች ይገኛሉ፡፡ ከእነርሱ መካከል


የቅን ጎዳና ምልክቶች ፣ የጨለማ ብርሃኖች ፣ የምስጉን ታሪክና ከሰለፎች የተወረሱ
አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ 60/60

እውቀቶች ባለቤቶች ይገኙበታል፡፡ ከውስጣቸው አብዳሎች ፣ የዲን መሪዎችም አሉ፡፡


በቅን ጎዳና መመራታቸውን ሙስሊሞች የተስማሙባቸውም አሉ፡፡ እነርሱ ረሡል ‫ﷺ‬
በሚከተለው ሐዲሳቸው የተናገሩላቸው አላህ የሚረዳቸው ቡድኖች ናቸው፡፡

‫ وال من‬، ‫ ال يضرهم من خالفهم‬، ‫"ال تزال طائفة من أمتي على الحق منصورة‬
"‫خذلهم حتى تقوم الساعة‬

“ከኡመቶቸ አንዲት ቡድን እስከቂያማ ቀን ፣ በሐቅ ላይ የምትረዳ ከመሆን


አትወገድም፡፡ እነርሱን የተቃረናቸው ፣ ከእነርሱ ላይ እርዳታን ያቆመባቸውም
አይጎዳቸውም፡፡” ሙስሊም፡

ከእነርሱ እንዲያደርገን ፣ ከመራን በኋላ ልቦቻችንን እንዳያጠምብን ፣ ከእርሱ ዘንድ


እዝነትን እንዲለግሰን አላህን እንጠይቃለን - እንሆ እርሱ ለጋስ የሆነ ጌታ ነውና፡፡

ወሏሁ አዕለም

‫وصلى اهلل على حممد وآله وصحبه وسلم تسليما كثريا‬

“አብዳል” የሚባሉት ከሌላው አካል በእውቀትና በአምልኮ የተለዩ ናቸው፡፡ “አብዳል” በሚል ስያሜ
የተጠሩት ከእነርሱ መካከል አንዱ ሲሞት ሌላው ስለሚተካ ወይም በመጥፎ ስራቸው መልካም ስለሚቀይሩ
ወይም የሰዎች መሪዎችና ሞዴሎች በመሆናቸው የሰዎችን መጥፎ ስራ በመልካም ስለሚቀይሩ ነው፡፡
ባህር ዳር በሚገኙ የአህለሱና
መሻይኾች የተቀሩ ጠቃሚ ኪታቦች፣ ከሀገር
ውስጥና ከውጭ በሚመጡ መሻይኾች የተሰጡ
ኮርሶች፣ ሙሓዶራዎች፣ የጁመዓ ኹጥባ፣
በትክክለኛ ማስረጃ የተደገፉ የተለያዩ ኢስላማዊ
መጣጥፎችን የሚከተለውን የቴሌግራም ሊንክ
ጆይን በማድረግ መከታተል ይችላሉ
http://t.me/alateriqilhaq

You might also like