Professional Documents
Culture Documents
(
(
መልሱን ለምሁራን
1. ኢብኑል አዕራቢ ረሒመሁላህ ከቀዳሚዎቹ የዐረብኛ ቋንቋ ምሁራን ውስጥ ነው፡፡ ስለ “ኢስተዋ” እንዲህ
ይላል፡ “አሕመድ ኢብኑ አቢ ዱኣድ በዐረብኛ ቋንቋ ውስጥ ‘አረሕማኑ ዐለል ዐርሺ ኢስተዋʼ የሚለው
በ‘ኢስተውላʼ መልእክት የመጣበትን እንድፈልግለት ጠይቆኝ እንዲህ አልኩት ‘ወላሂ እንዲህ አይሆንም
አላገኘሁትም!ʼ(ኸጢቡልበግዳዲ ወላለካኢ፡3/399)፡፡
በነገራችን ላይ ይሄ ፈልግልኝ ባዩ አሕመድ ኢብኑ አቢዱኣድ ለነ ኢማሙ አሕመድ ፈተና ላይ መውደቅ ምክኒያት
የሆነው ጀህሚይ ነው፡፡ ከዚህ የምንረዳው “ኢስተዋን” በ“ኢስተውላ” መተርጎም የነኢማሙ አሕመድ ጠላቶች
አካሄድ እንደሆነ ነው፡፡
2. አልኸሊል ኢብኑ አሕመድ ረሒመሁላህ ከዐረብኛ ቋንቋ ምሁራን ውስጥ ከቀዳሚዎቹ ነው፡፡ “‘ኢስተዋንʼ
በ‘ኢስተውላʼ ትርጉም ያገኘህበት አለ?” ተብሎ ሲጠየቅ “በዚህ መልኩ ዐረቦች አያውቁትም፡፡ ቋንቋቸውም
አይፈቅደውም” ብሏል(መጅሙዑልፈታዋ፡5/146)
4. ኢብኑ ዐብዱል በር፡ “ኢስተዋን ኢስተውላ ማለታቸው ትርጉም የለውም ምክኒያቱም በዐረብኛ የተለመደ
ስላልሆነ” (አተምሂድ፡7/131)
ስለዚህ “ኢስተዋን” በ“ኢስተውላ” ለመጀመሪያ ጊዜ የተረጎሙት ዘግይተው የመጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ለዚህም
አቋማቸው ሰነዱ የማይታወቅ ግጥም ማጠናከሪያ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ኢብኑ ከሢር ይህንን ግጥም መረጃ
የሚያደርጉት ጀህሚያዎች እንደሆኑ ከጠቀሰ በኋላ “እንደ ጀህሚያ ደካማ ማስረጃ ያለው አናገኝም፡፡ የመረጃ
ድህነታቸው አንድ አስቀያሚ የክርስቲያን ግጥም እስከሚጠቀሙ አድርሷቸዋል” ይላል (አልቢዳያ ወኒሃያህ፡9/295)
፡፡መቼም ግጥም ቀርቶ ሐዲሥን እንኳ ማስረጃ አድርጎ ለማቅረብ ሶሒሕነቱ እንደሚፈተሽ ይታወቃል፡፡
በመጨረሻም
ኢማሙ ማሊክ “ኢስቲዋእ የታወቀ ነው” ብለዋል፡፡ ይህንን ንግግር የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን
የሚያስተባብሉም ሰዎች መልእክቱን አንሻፈው ይጠቀሙበታል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ ይሄ የታወቀው የኢስቲዋእ ትርጉም
ምንነት ላይ ነው ማለት ነው፡፡ ሰለፎች ዘንድ የሚታወቀው የ“ኢስቲዋእ” መልእክት ደግሞ አላህ ከዐርሹ በላይ
እንደሆነ በግልፅ ይጠቁማል፡፡ ይህም ከኢብኑ ዐባስ፣ ከሙጃሂድ፣ ከኢብኑ ዓሊያህ፣ ከኢስሓቅ ኢብኑ ራህዊያህ
በሶሒሕ ሰነድ መጥቷል፡፡ “ኢስተዋን” በ“ኢስተውላ” የሚተረጉሙ ሰዎች ግን ከዚያ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
ምርጥነቱን ከመሰከሩለት ትውልድ አንድም ቀጥተኛ ማሳመኛ ማምጣት አይችሉም- አንድም!!