You are on page 1of 3

የሸይኽ ሙሀመድ ናስሩዲን አል-አልባኒ

የህይወት ታሪክ በአጭሩ

www.nesiha.com
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ምስጋና ለአላህ ተገባው፡፡ እናመሰግነዋለን፤ እገዛን እንጠይቀዋለን፤ ምህረትን እንለምነዋለን፡፡


ከነፍሶቻችን ጥፋት እና ከክፉ ተግባራችን በአላህ እንጠበቃለን፡፡ አላህ የመራውን ማንም
አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ወደ ቅን መንገድ ሚመራው የለውም፡፡ ከአላህ ሌላ
አምላክ አለመኖሩን፣ ብቸኛ እና አጋር የሌለው መሆኑን እመሰክራለሁ፡፡ እንዲሁም
ሙሀመድ የአላህ አገልጋዩና መልዕክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ፡፡
ሙሀመድ ናስሩዲን አል-አልባኒ ከደሃ ቤተሰብ የቀድሞው የአልባኒያ ዋና ከተማ በነበረው
በሽኮድራ ተወለዱ፡፡ አባታቸው ሀጅ ኑህ ነጃቲ አል-አልባኒ የኢስላም ህግ (ሸሪዓ)
በኢስታምቡል ያጠኑ ታዋቂ የአልባኒያ ምሁር ነበሩ፡፡ ቤተሰቦቻቸውም በጊዜው አልባኒያ
በነበረው በምዕራቡ አመለካከት ተጽዕኖ ስር በወደቀው አለማዊው (Secularist) መንግስት
ባለመስማማታቸው ወደ ደማስቆ ተሰደዱ፡፡ በደማስቆም አል-አልባኒ የመጀመሪያ ደረጃ
ትምህርታቸውን አጠናቀቁ፡፡ በተጨማሪም ቁርዓን፣ የቁርዓን አነባብ ሰርዓት (ተጅዊድ)፣
የአረብኛ ቋንቋ፣ የሃነፊያ መዝሀብ ትምህርቶች (ፊቅህን)፣ እና ሌሎች ተዛማች የሃይማት
ትምህርቶችን በተለያዩ የኢስላም ምሁሮች (ከአባታቸው ጓደኞች ጨምሮ) ተማሩ፡፡

አል-አልባኒ ከአባታቸው የሰዓት ጥገና ሙያን ተምረዋል፡፡ በንግድ ስራም በጣም የተካኑ
ነበሩ፡፡ 20 ዓመት ሲሞላቸው በሀዲስ እና ተዛማች ትምህረቶች ጥልቅ ጥናት
(Especialization) ማድረግ ጀምሩ፡፡ አባታቸው ቀላል የትምህርት ክፍል እንዲያጠኑ
በመፈለግ የሀዲስ ጥናታቸውን ቢያጣጥሉባቸውም አል-አልባኒ ፅኑ ፍላጎታቸው መሆኑን
በመግለጽ የተለያዩ መጽሐፍቶችን በመግዛት መግዛት ያልቻሉትን ከታዋቂው ደማስቆ
ውስጥ ከሚገኘው አዝ-ዛህሪያህ ኢስላማዊ ቤተ-መፅሐፍት በመዋስ የሀዲስ ጥናታቸውን

1
በስፋት ቀጠሉበት፡፡ በስራቸውም በጣም በመመሰጣቸው አንዳንዴ ሱቃቸውን ዘግተው
ፈሳሽ ምግብ ይዘው ለ 12 ሰዐት (ለሰላት ብቻ እየወጡ) በቤተ-መፅሐፍት ውስጥ ይቆዩ
ነበር፡፡ ይህን ያዩት የቤተ-መፅሐፍቱ ሀላፊዎች አል-አልባኒ በፈለጉት ሰዓት ገብተው
እንዲያነቡ የቤተ-መፅሀፍቱን የበር ቁልፍ እና ምቹ የሆነ ልዩ የንባብ ክፍል ሰጧቸው፡፡
ከዚያም በኋላ ከጧት ጀምሮ እስከ ኢሻዕ ሶላት ድረስ በዚሁ ቤተ-መጽሐፍት የተለያዩ
ስራዎችን እየሰሩ መቆየት ጀምሩ፡፡ በዚህም ወቅት አብዛኛው ያልታተመ በርካታ ጠቃሚ
ስራዎችን ለህብረተሰቡ አበረከቱ፡፡

ከተወሰነ ጊዜ በኋላም የተለያዩ የ‹አቂዳ› ፣‹ፊቂህ›፣ ‹ኡሱል› እና ‹ሀዲስ› መፃሐፍቶችን


በየሳምንቱ ለሁለት ሰዓታት ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና ፕሮፌሰሮች ማስተማር፤ ወርሃዊ
የዳዕዋ ጉዞ ወደ ተለያዩ የሶሪያና የጆርዳን ከተሞች እንዲደረጉ ማደራጀት ጀመሩ፡፡

ብዙ ሰራዎቻቸው ከታተሙ በኋላ በመዲና ኢስላሚክ ዩኒቨርስቲ የ‹ሀዲስ› መምህር


እንዲሆኑ ተመረጡ፡፡ ለሶስት ዓመታትም (ከ 1381-1383 ዓ.ሂ) የዩኒቨርስቲው የቦርድ አባል
በመሆን አገልግለዋል፡፡ በኋላም ወደ ሀገራቸው በመሄድ በጊዜው የነበራቸውን ሱቅ
ለወንድማቸው በመስጠት ወደ ቀድሞው የአዝ-ዛህርያህ ቤተ መጽሐፍት ጥናታቸው
ተመለሱ፡፡
አል-አልባኒ ደዕዋ ለማድረግና ለማስተማር ብዙ ሃገራትን ጎብኝተዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ
ኳታር ፣ ግብጽ፣ ኩዌት ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬት፣ ስፔን ፣ እንግሊዝ ተጠቃሾች
ናቸው፡፡ አብዛኛውን በ‹ሀዲስ› እና ተጓዳኝ በሆኑ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ወደ 100 የሚሆኑ
የተለያዩ ስራዎችን አበርክተዋል፡፡ ታዋቂ የሆኑ ብዙ ተማሪዎችንም አፍርተዋል፡፡ ከነዚህም
ውስጥ የዘመናችን ታዋቂ ምሁሮች ሸይክ ረቢዕ ኢብን ሃዲ፣ ሸይክ ሀምዲ አብዱል መጂድ፣
ሸይክ ሙቅቢል ኢብን ሃዲ ፣ ሸይክ መሀመድ ጀሚል ዘይኑ፣ ሸይክ አሊ ሀሰን
አብዱልሀሚድ አል ሀለቢ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

የኢስላም ምሁሮች ስለ አል- አልባኒ የተናገሩት


አብዛኛዎቹ ምሁሮች
«አልባኒ የ 20 ኛው ክፍለ ዘመን ታላቁ የኢስላም ምሁር ነው፡፡»

2
አብዱል -አዚዝ ብን ባዝ
“በዚህ ዘመን በአለም ላይ በሀዲስ እውቀት ታላቁን ሙሀመድ ናስሩዲን አል-
አልባኒ የሚያክል አላየሁም፡፡”
ዚያድ ኢብን ፍያድ
“ሼይክ ሙሀመድ ናስሩዲን አል-አልባኒ ብርቅዬና ልዩ ተሰጥኦ ካላቸው
የዘመናችን ታላላቅ ምሁሮች አንዱ ናቸው፡፡ ”
ሂቡዲን አል-ካረብ
“የመልዕክተኛው ሱና (ፈለግ) ዳግም ሕይወት እንዲዘራ ሙሉ ሕይወታቸውን
ከሰጡት ሰዎች ውስጥ አንዱ ወንድማችን ሙሀመድ ናስሩዲን አል-አልባኒ ነው፡፡”
ለህትመት ከበቁት መጽሐፍቶቻቸው ጥቂቱ
 አት-ተርሂብ-ወተርጊብ (ከቅጽ 1-4)
 አት-ተሰፊያህ-ወተርቢያህ
 አት-ተወሱል አንዋኡሁ ወአህካሙህ
 ተልኪስ አህካሙል ጀናዛ
 ሰሂህ ወደኢፍ ሱነን አቡዳውድ (ከቅጽ 1-4)
 ሰሂህ ወደኢፍ ሱነን ኢብንማጃህ (ከቅጽ 1-4)
 ሰሂህ ወደኢፍ ሱነን ቲርሙዚይ (ከቅጽ 1-4)
 አል-አቂደቱ ጠሃዊየህ (ሸርህ ወተዕሊቅ)
 ሲልሲሊቱ ሀዲስ ሶሂህ (ከቅጽ 1-11)
 ሲልሲለቱ ሀዲስ ዶኢፍ (ከቅጽ 1-14)

You might also like