You are on page 1of 59

መግቢያ

1. በኢትዮጵያ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ /ተሙማን/ ለመጀመሪያና ለሁለተኛ ደረጃ


ት/ቤቶች መምህራን፣ የት/ቤት አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮችን ሊጠቅም በሚችል መልኩ
አዲስ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል፡፡

2. በዚህ አዲስ ማዕቀፍ ተ.ሙ.ማ ታሳቢ የሚያደርገው በአብዛኛው በት/ቤቶችና በመምህራን


ላይ ነው፡፡ በአብዛኛው በአመዛኙም አካባቢያዊ ነው፡፡ ይህ የተግባር መሣሪያዎች ቋት አዲሱን ማዕቀፍ በአግባቡ
ለመገልገል ይረዳል፡፡
3. ይህ ማለት ት/ቤቱ የግድ፡-:
4. የተ.ሙ.ማን ፍላጉቶች ይለያል፡፡
5. አመታዊ የተ.መ.ማን እቅድ ያዘጋጃል፡፡
6. ት/ቤቱ የራሱን የተሙማ ሞጁል ይዘትን ይተገብራል፡፡
7. የተግባር መሳሪያው ቋት ለማን ነው?

8. ርዕሰ መምህር ነዎት?


9. የተ.ሙ.ማ አስተባባሪ ነዎት?
10. የት/ቤት መምህር ነዎት?
11. የሥራ ላይ ስልጠና የሚሰጡ አሠልጣኝ ወይም ሱፐርቫይዘር ነዎት?
12. የአማራጭ መሠረታዊ ትምሀርት ወይም የጐልማሶች ትምህርት አመቻች ነዎት?
13. ከሆኑ ይህን የተግባር መሣሪያዎች ቋት ሊገለገሉበት ይችላሉ?

የዚህ የተግባር መሣሪያዎች ቋት አላማ ምንድን ነው?

አንድ ህንፃ ለመገንባት ብትፈልጉ ለእያንዳንዱ ስራ የሚሆን ትክክለኛውን መሣሪያ መጠቀም አለባችሁ፡፡ ለምሳሌ፡- መሠረቱን
ለመቆፈር ዶማ፣ ለግድግዳዎቹ የሚሆን እንጨት ለመቁረጫ መጋዝ ወዘተ...ያስፈልጋችኋል፡፡ ይህም የተግባር መሳሪያዎች ቋት
ተ.ሙ.ማን ለማቀድና በስራ ላይ ለማዋል የሚረዳ በተግባር መልክ የሚገለፁ መሣሪያዎች ይሠጧችኋል፡፡፡፡

ምን አይነት ለውጥ ለማየት ትሻላችሁ?

1
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
በትምሀርት ጥራት መሻሻል ውስጥ
የተማሪው የስራ ክንውን ውጤት መሻሻል፣
በመማሪያ ክፍል ትግበራ መሻሻል፣
መምህራን ሙያዊ ብቃታቸውን በማሳደግ ወደተሻለ መምህርነት ማምጣት
የተ.ሙ.ማ.ዓላማ ከላይ የተጠቀሱትን ለማሳካት ነው፡፡

ሁሉም ዓለማቀፋዊ ጥናቶች የሚያመላክቱት ተ.ሙ.ማ ውጤታማ የሚሆነው፡-


 በት/ቤት ላይ የተመሠረተና ከት/ቤት መሻሻል ጋር የተቆራኘ ሲሆን ነው፡፡
 የት/ት ሥራ ባልደረቦች ተቀራርበው የራሳቸውን ልምድ የት/ቤታቸውን የስራ ብቃትና በስተመጨረሻም የተማሪዎቻቸውን ውጤት ለማሻሻል
በአንድነት በጥብቅ ሲሰሩ ነው፡፡

ይህን የተግባር መሣሪያዎች ቋት እንዴት መጠቀም ይቻላል?

የተ.መ.ማ ዑደት

ፍተሻ

2
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ሁሉም ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ መርሃ ግብሮች የሚከተሉት የጋር ባህርያት አሏቸው፡፡
 መርሃ ግብሩ የግለሰቡን፣ የቡድኑን ወይም የተቋሙን የስልጠና ፍላጎት ለማሳካት ሲባል
የሚካሄድ ነው፡፡
 የሥልጠና ፍላጐቱ የሚለየው በትንተና ወይም በፍተሻ ሂደት አማካኝነት ነው፡፡

ከላይ ያለው ምስል የተ.ሙ.ማን ኡደት አራት ዋና ዋና እርከኖች ያሳያል፡፡ የተግባር መሳሪያዎች ቋቱ እነዚህን እርከኖችን
እንድትረዱና እንድትጠቀሙባቸው ይረዳችኋል፡፡ ተ.ሙ.ማ አመርቂ እንዲሆን ከተፈለገ መምህራን የግድ እያንዳንዱን የዑደቱን
እርከን በተከታታይ መፈተሽ ይኖርባቸዋል፡፡

- ፍተሻ ማለት ሊሠራ የተወሰነው ተግባር በትክክል መሠራቱን ወይም አለመሠራቱን የምንገመግምበት ሂደት ነው፡፡
የታቀደው ስራ በትክክል እየተሠራ ከሆነ ስራው ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚሠራ ሲሆን በትክክል ካልተሠራ ግን
የእቅዱን አላማ ለማሳካት ምን ለውጥ መደረግ እንዳለበት የሚቃኝበት ነው፡፡ ፍተሻ በኡደቱ እምብርት የተቀመጠው
በእያንዳንዱ የኡደቱ እርከን የሚሠራ ሥራ በመሆኑ ነው፡፡
በዚህ ሒደት ወቅት ቢያንስ ከአንድ የስራ ባልደረባ ጋር ሁልጊዜ መስራት ይመከራል፡፡

እያንዳንዱ የዑደት እርከን ቀጠሎ ያሉትን ገለፃዎች ያዘለ ነው፡-


 በእያንዳንዱ እርከን የምትገለገሉባቸውን መሣሪያዎች
 መሣሪያዎቹን እንዴት እንደምትገለገሉባቸው፡፡
 በምናባዊ ት/ቤት ላይ የተመሠረቱ የተጠናቀቁ ምሳሌዎች ተሰጥተዋል፡፡
ጥሎ መሣሪያዎቹን ለራሳችሁ ት/ቤት ተጠቀሙባቸው፡፡
በእያንዳንዱ እርከን መጨረሻ የተማራችሁትን እንድታንፀባርቁ ትጠየቃላችሁ፡፡ ለዚህ የተግባር መሳሪያዎች ቋት ትግበራ
የፅብረቃ ባለሙያ ችሎታ ወሳኝ ነው፡፡

ምልክቶቹ ምን ማለት ናቸው?


የተግባር መሳሪያዎች ቋት ውጤታማ ተ.ሙ.ማ እንዴት እንደምታዘጋጁ ይመራችኋል፡፡

 ይህን ምልክት ስታዩ አንድ የሚሰራ ስራ አለ ማለት ነው፡፡

የተሙ.ማን ዑደት የተሟላ ለማድረግ እነዚህን ስራዎች መስራት


አለባቸው፡፡
3
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
በዚህ የመሣሪያ ቋት ውስጥ የተጠቀሠው ምናባዊ ት/ቤት የተሙማ ኡደት እርከኖች እንዴት እንደሚሟሉ በምሳሌ ለማሳየት
የቀረበ ት/ቤት ነው፡፡
ምናባዊ ት/ቤት በተጠቀሰበት ጊዜ ሁሉ ይህ ዓይነት የአፃፃፍ ዘዴ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

ይህ ስዕል ምናባዊ ት/ቤትን ይወክላል፡፡

ይህ ስዕል ምናባዊ ት/ቤት መምህር የሆነን አንድን ግለሰብ ይወክላል


በሚቀጥለው ገፅ የምናባዊ ት/ቤትን ዝርዝር ሁኔታ ታገኛላችሁ፡፡

ይህን አይነት ምስል ባያችሁ ጊዜ አጥብቃችሁ ማሰብ አለባችሁ ማለት ነው፡፡

ይህን የመስታወት ምስል ባያችሁ ጊዜ ምን መሠረት አድርጋችሁ ማንፀባረቅ ይኖርባችኋል


ማለት ነው፡፡ ተ.ሙ.ማን በት/ቤታችሁ ልትተገብሩ በራስ መተማመን ይሰማችኋል ወይስ ገና ተጨማሪ
ልምምድ ያሻችኋል፡፡

ይህ የማቀፊያ ምስል ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት እንደምትችሉ ማሳያ ነው፡፡ በተጨማሪ አባሪ ውስጥ
ያሉትን ባዶቅፆች ለት/ቤታችሁ ተጠቀሙባቸው፡፡

ምናባዊ ት/ቤት

ምናባዊ ት/ቤት በዚህ የተግባር መሳሪያዎች ቋት ውስጥ ያሉትን መሳሪያዎች እንዴት እንደሚጠቅሙ ምሳሌዎችን በማቅረብ
ለማሳየት የተፈጠረ ምናባዊ ት/ቤት ነው፡፡
በዚህ ምናባዊ ት/ቤት የሚያስተምሩ መምህራን ስለ ት/ቤታቸው የፃፏቸው ጥቂት ዝርዝር ገለፃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
እነሱ ይህን በማድረጋቸው የት/ቤቱን ስኬትና ክፍተቶች ይረዳሉማለትነው፡፡
እናንተም የተ.ሙ.ማን ዑደት ከግቡ ለማድረስ ለት/ቤታችሁ ተመሳሳይ ዝርዝር መረጃ ያስፈልጋችኋል፡፡
ምናባዊ ት/ቤቱ ከአንድ ሰፊ ከተማ 40 ኪ.ሜ ያህል ወጣ ያለ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ነው፡፡ 2100
ተማሪዎች ሲኖሩት ከ 1 ኛ-8 ኛ ክፍል ያሉትን ያጠቃልላል፡፡

ት/ቤቱ በገጠርማው አካባቢ ስለሚገኝ አንዳንድ ተማሪዎች በቀን 20 ኪ.ሜ የደርሶ መልስ ጉዞ ያደርጋሉ፡፡
የሁለት ፈረቃ ትምህርት ይሠጣል፡፡ አብዛኞቹ መምህራን ሁለቱንም ፈረቃዎች ያስተምራሉ፡፡ በት/ቤቱ

4
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ውስጥ 54 መምህራን ሲኖሩ በዚህ አመት 11 አዳዲስ ጀማሪ መምህራን ተቀጥረዋል፡፡ 18 መምህራን ዲፕሎማ ሊኖራቸው
ሲገባ የሰርተፊኬት ምሩቃን ናቸው፡፡
ከሁለተኛ ሳይክል ይልቅ በመጀመሪያ ሳይክል በርካታ ተማሪዎች አሉ፡፡ የት/ቤቱ የክፍል ተማሪ ጥምርታ ጨምሯል፡፡ ጥምርታው
በመጀመሪያ ሳይክል 76 እና በሁለተኛ ሳይክል 63 ነው፡፡ ባለፉት ሶስት አመታት ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች ቁጥር ስለጨመረ
በአሁኑ ጊዜ 25 ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች በት/ቤቱ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
በተጨማሪ አሰራ አንዱ አዳዲስ መምህራን ስራ ጀምረዋል፡፡ በት/ቤቱ አብርሃም የሚባል
የ 31 ዓመት ያለው አዲስ ር/መምህር የተመደበ ሲሆን ከዚህ ቀደም በወረዳው ሌላ ት/ቤት
ውስጥ የሂሳብ መምህር ነበር፡፡ በወረዳው የት/ቤት ሱፐርቫይዘር ሀሰን ሲሆን እሱም ለስራው አዲስ
ነው፡፡ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት በተመለከተ በክልል ት/ቢሮ በተካሔደው ኮርስ ላይ ተሳታፊ
ነበር፡፡ አዲሦቹን መማሪያ መፅሀፍትና የሁለተኛ ሳይክል ፊዚክስና እንግሊዝኛን ግምገማዎች አይቷል፡፡

የወረዳው የክልል ት/ቢሮ የቅርብ ጊዜ መረጃ ከ 1 ኛ ክፍል እስከ 4 ኛ እና ከ 5 ኛ ክፍል እስከ 8 ኛ ክፍል ት/ቤቱ የደጋሚን ብዛት
በመቀነስ ዙሪያ መልካም እንደሰራ ያመለክታል፡፡
ከ 68% በላይ ተማሪዎች 5 ኛ ክፍልና ከ 50% በላይ 8 ኛ ክፍል ደርሰዋል፡፡ እነዚህ ውጤቶች ለክልል ት/ቢሮና ለሀገሪቱ
ከተቀመጠው ግብ ከአማካይ በላይ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ባለፈው ዓመት 21% ያህሉ ትምህርታቸውን ከ 1 ኛ ክፍል ሲያቋርጡ
ከነዚህም አብዛኛዎቹ ሴቶች ተማሪዎች ነበሩ፡፡ በተጨማሪም በ 3 ኛ ክፍል ከፍተኛ የደጋሚዎች ቁጥር ነበር፡፡
በ 4 ኛ ክፍል የሙከራ ፈተና በአብዛኛው የት/ዓይነት ጥሩ ውጤት ተመዝግቦ የነበረ ቢሆንም የሒሳብ አማካይ ውጤት በ 15%
ዝቅ ብሏል፡፡ በ 8 ኛ ክፍል ፈተና በሁሉም የት/አይነቶች ጥሩ ውጤት በመገኘቱ 100% ማሳለፍ ቢቻልም በእንግሊዝኛ ሴት
ተማሪዎች ያስመዘገቡት ነጥብ ከወንዶቹ በ 25% አንሶ ታይቷል፡፡ እንዲሁም 8 ኛ ክፍልን ካለፋት 162 ተማሪዎች ውስጥ 65
ብቻ የ 9 ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ሊቀጥሉ ችለዋል፡፡

ት/ቤቱ በአካባቢው ማህበረሰብና በአንድ የዕርዳታ ድርጅት ድጋፍ ያሰራው አንድ ክፍል ብቻ ያለው
ቤተመጽሀፍት አለው፡፡ ክፍሉ አስፈላጊውው መገልገያ ዕቃ የተሟላለትና በውስጡ የሳይንስና ሒሳብ
ትምህርት የሆኑ ጥቂት መጻሀፍት አሉት፡፡ ቤተ መፅሀፍቱ የመብራት አገልግሎትና የዕርዳታ ድርጅቱ

የለገሳቸው አራት ያገለገሉ ኮምፒውተሮች አሉት፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎት የለውም፡፡

ጥቂት መምህራን በተለይ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ሰርዓት የሌላቸው መሆኑን አስመልክተው ለአደሱ ርዕሰ መምህር
ተቋውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ መምህራኑም “ በሚያስተምሩበት ወቅት ተማሪዎች እንደማይሰሟቸው፣ አብዛኞቹ ተማሪዎች
በተለይ ወንዶቹ የቤት ስራቸውን አጠናቀው እንደማይመጡና በተጨማሪም የተወሰኑ ተማሪዎች በየቀኑ አርፍደው ስለሚመጡ
ትምሀርቱን በሰዓቱ ለመጀመር አስቸጋሪ መሆኑን ገልፀዋል “፡፡
አብርሀም ስራ በጀመረባቸው በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት የመምህራኑን
የማስተማር ሥራ ጥሩ አድርጐ አስተውሏል፡፡ በርካታ ጥሩ ትምህርት

5
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
አሰጣጦችን አይቷል፡፡ ቢሆንም አብዛኞቹ ተመሳሳይ የአሠራር ሒደት እንደሚከተሉ አስተውሏል፡፡ መምህራኑ ጥቁር ሰሌዳ
ላይ ይፅፋሉ፣ ቀጥሎም ተማሪዎቹ ይገለብጣሉ፡፡ ተማሪዎቹ ምሳሌዎችን ከመፅሀፎቻቸው ይሰራሉ፡፡ የተማሪዎቹን ስራ
እያረሙ በክፍሉ ውስጥ ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ አብርሀም በጥቂት የት/አይነቶች የተወሰኑ የቡድን ስራዎች እንደሚሰጡ
ቢመለከትም በአብዛኛው የት/አይነቶች ክፍለጊዜ ተማሪዎች ባለፈው ምሽት ያዩትን የእግር ኳስ ጨዋታ አንስተው አፍለአፍ
ገጥመው ሲያወሩ አይቷል፡፡
ቀድሞ በነበረው ርዕሰ መምህር የተቋቋመ ጠንካራ የተማሪዎች መማክርት አለ፡፡ አብርሀም አባላቱን ባነጋገረበት ሰዓት ጥቂት
ትምህርቶች ፍላጐት ቀስቃሽ አለመሆናቸውን ሲገልፁ በት/ቤቱ ውስጥ አጓጊ ሁኔታዎች እንደሌሉ በመናገር ተቃውሟቸውን
አሰምተዋል፡፡

ከመምህራን አንዱ መጪውን ህይወታቸውን አስመልክቶ አብርሀምን አነጋግሮት ነበር፡፡ ገዛን ጅሩ


የተባለው መምህር ኮምፒውተር መማር ስለሚፈልግ ዘወትር አርብ ጠዋት ነፃ ጊዜ እንዲኖረው ርዕሰ
መምህሩን ጠየቀው፡፡
ት/ቤቱ የተ.ሙ.ማ አመቻችና ኮሚቴ አለው፡፡ ሁሉም መምህራን ፖርትፎሊዮ አላቸው፡፡ የተ.ሙ.ማ
ስብሰባ በየሳምንቱ ሀሙስ ከሰዓት የትምህርት ጊዜ ካበቃ በኋላ ት/ሚኒስቴር ባዘጋጀው ሞጁል ላይ
ውይይት ያካሔዳሉ፡፡ በት/ቤቱ አራት ብቻ የሞጁሉ ቅጂዎች አሉ፡፡ አብዛኛቹ መምህራን በሞጁሉ ውስጥ
ያለውን እንግሊዝኛ ለመረዳት አስቸጋሪ በመሆኑ ቅሬታቸውን ያሰሟሉ፡፡

እርከን አንድ

የተ.ሙ.ማ ፍላጐቶችን መተንተን

ደረጃ አንድ (Stage 1)


የማን ፍላጐቶች ናቸው?
ደረጃ ሁለት (Stage 2)
የት/ቤታችሁን ፍላጐት እንዴት መወሰን ትችላላችሁ?
ደረጀ ሦስት (Stage 3)
የት/ቤታችሁን ተ.ሙ.ማ ቅድሚያ ትኩረቶች እንዴት መወሰን ትችላላችሁ?
ደረጃ አራት (Stage 4)
የግልህን/ሽን ተ.ሙ.ማ ፍላጐቶችና ቅድሚያ ትኩረቶች እንዴት መወሰን ትችላለህ/ያለሽ?

6
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
በዚህ እርከን መጨረሻ ላይ የሚከተሉትን ማድረግ መቻል አለባችሁ፡፡

 የት/ቤታችሁን የተ.ሙ.ማ ፍላጐቶች መለየት፣


 የትኞቹ በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ መወሰን፣
 ከተዘረዘሩት ውስጥ ሶስቱን ለመስራት መምረጥ፣

የተ.ሙ.ማ ፍላጐቶችን መለየት የት/ቤታችሁ የመሻሻል ዕቅድ አካል ሊሆን ይችላል፡፡


ደረጃ አንድ (Stage 1)
የማን ፍላጐቶች ናቸው?
በኢትዮጵያ በርካታ የተ.ሙ .ማ ፍላጐቶች አሉ፡፡ እነዚህም ፍላጎቶች ግለሰቦችንና ቡድኖችን ብቻ ሳይሆን
ሀገርንም የሚያሳትፉ ናቸው፡፡
የፍላጐቶች ምሳሌ

የ.ሙ.ማ ተሳታፊው ማን
ደረጃ ፍላጐት ምሳሌ
ነው?

ግለሰብ እራሰን ለማሻሻል ተለይቶ የታወቀ  ከምስክር ወረቀት ወደ ዲፕሎማ ደረጃ በግል
ግላዊ የተሙማ ፍላጐትና ከፍ ማድረግ
የማስተማር ስራን ማሻሻል
 በክፍልህ/ሽ ያለን ማየት የተሳነው ህፃን
እንዲማር መርዳት

ት/ቤት በት/ቤት፣የክፍል ደረጃ፣ በት/አይነት፣  የ 1 ኛ ደረጃ ተማሪዎችን የሒሳብ  የተመረጡ የመምህራን


ተለይቶ የታወቀ ፍላጐት፣ የተማሪን መማር ብቃትን ማሳደግ፡፡ ቡድኖች
የመማር ብቃት ለማሻሻል
 የ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎችን የችግር  የት/ቤቱ መምህራን በመሉ
ፈቺነት ክህሎት ማሻሻል፡፣

የጉድኝትት/ መማርና ማስተማርን በጉድኝት የአማካሪዎችን ከአዲስ ጀማሪ መምህራን  የተመረጡ ቡድኖች
ቤቶች ት/ቤቶች ተለይተው የታወቁ ጋር የመስራትን ክህሎት ማሻሻል መምህራን
Cluster) ፍላጐቶች፡፡
 በጉድኝቱ ውስጥ ያሉ
መምህራን በሙሉ
 የርዕሳነ መምህራን ቡድን

ዞን ወረዳ የተማሪዎችን የመማር አቅም የርዕሳነ መምህራንና የሱፐርቫይዘሮችን  ርዕሰ መምህራን፣


ክ/ከተማ ለማሻሻል ተለይተው የታወቁ የዞን ክህሎት ለማሳደግ በት/ቤታችሁ መሻሻል
የወረዳ የክ/ከተማ ፍላጐቶች እቅድ ላይ የፈጠራ አቅማቸውን መጨመር  ም/ርዕሰ መምህራንና
ሱፐርቫይዘሮች

ክልላዊ በክልሉ ባሉት ት/ቤቶች ላይ የር/መምህራንና የሱፐርቫይዘሮችን መረጃ ር/መምህራን፣ ም/ር መምህራንና
አዎንታዊ ጫና የሚያሳድር በክልሉ የመሰብሰብና የመተንተን ክህሎት ማሻሻል ሱፐርቫይዘሮች
ተለየቶ የታወቀ ፍላጐት

ሀገር አቀፍ በሁሉም ቦታና በት/ቤቶች ላይ የስነህዝበና የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት ሁሉም መምህራን፣ ርዕሰ
አዎንታዊ ጫና የሚያሳድር በሀገር መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች

7
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
አቀፍ ተለይቶ የታወቀ ፍላጐት

ደረጃ ሁለት (Stage 2)


የት/ቤትን ፍላጐት እንዴት መወሰን ይቻላል፡፡
አንድ ት/ቤት የሚያልፍባቸው በርካታ ደረጃዎች አሉ:-
 ለዓመቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በወረዳ፣ በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለአመቱ ቅድሚያ የሚሠጧቸውን
የተሙማ ጉዳዮች መለየት፣
 የት/ቤትና የአካባቢውን ህዘብ የሚያሳትፍ ምክክር ማድረግ
 የት/ቤቱን ተ.ሙ.ማ ፍላጐቶች ዝርዝር ማዘጋጀት

1. በወረዳ በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ፍላጎቶች መለየት

የክልሉ ት/ቢሮ እና የወረዳው ት/ጽ/ቤት ቅድሚያ ከሚሰጧቸው ትኩረቶች የትኞቹ የት/ቤታችሁን (ተ.ሙ.ማ) ጊዜ
ሊሻሙ እንደሚችሉ ለማወቅ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት መፍጠር እንዳለባችሁ መዘንጋት የለባችሁም፡፡

2. የአካባቢውን ህዝብና የት/ቤቱን ማህበረሰብ የሚያሳትፍ ምክክር ማድረግ


በት/ቤቱ ላይ የሚሰጡ አስተያየቶችን ማሰባሰብ የት/ቤታችሁን የተሙማ ፍላጐቶች ለይታችሁ እንድታውቁ ይረዳችኋል፡፡

የት/ቤታችሁን ባለድርሻ አካላት ጠይቁ፣

ተማሪዎችን፣

መምህራንን፣

ወላጆችንና አሳዲጊዎችን፣

የአካባቢውን ማህበረሰብ፣

ከምናባዊ ት/ቤቱ የተወሠደ ምሳሌ፡-


ለሁሉም ተማሪዎች

ት/ቤታችን ምን ጥሩ ስራ ሠርቷል? ት/ቤታችን ምን መሻሻል ያስፈልገዋል?

በቤተ መፃህፍታችን ውስጥ የቤት ስራችንን አንዳንድ ልጆች ዘወትር ይረብሻሉ የኛ መምህራን
ለመስራት አመቺ መሆኑ፣ አንድ ነገር ማድረግ አለባቸው
በት/ቤታችን ውስጥ የኮምፒውተር አገልግሎት በክፍል ውስጥ ብዙ ጊዜያችንን የምናጠፋው ፅሁፍ
መኖሩ፣ በመገልበጥ ነው፡፡

8
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ለመምህራን
ት/ቤታችን ምን ጥሩ ስራ ሰርቷል? ት/ቤታችን ምን መሻሻል ያስፈልገዋል?

ት/ቤታችን በወረዳው ከሚገኙ አንዳንድ ት/ቤቶች ተማሪዎች በት/ቤታቸው አዘወትረው እንዲገኙ


በተሻለ ሁኔታ የደጋሚ ተማሪዎችን ቁጥር ቀንሷል ጥረት ማድረግ አለብን፡፡
በ 8 ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ጥሩ ውጤት በመጀመሪያ ደረጃ አንደኛ ሳይክል የሒሳብ
አስመዝግበናል፡፡ የማስተማር ስራ ላይ ጥራት ማምጣት

ለወላጆች/ለአሳዳጊዎች

ት/ቤታችን ምን ጥሩ ሥራ ሠርቷል? ት/ቤታችን ምን መሻሻል ያስፈልገዋል?


ር/መምህር የተወሰኑ መምህራንን የማስተማር ስራ በት/ቤቱ ውስጥ በርካታ አዳዲስ መምሀራን ቢኖሩም
መመልከቱ ጥሩ ነው፡፡ ተማሪዎች በበቂ ሁኔታ አያውቋቸውም፡፡
ከ 5 ኛ ክፍል እስከ 8 ኛ ክፍል ያለው የፈተና ውጤት ት/ቤቱ በየክፍሉ ያሉትን ተማሪዎች ቁጥር መቀነስ
ጥሩ ነው፡፡ አለበት፡፡

ለአካባቢው ማህበረሰብ
ት/ቤታችን ምን ጥሩ ሥራ ሠርቷል? ት/ቤታችን ምን መሻሻል ያስፈልገዋል?
ት/ቤቱ የመማሪያ ህንፃዎችን ለማሻሻል ገንዘብ ለት/ቤቱ ቤተመፅሀፍት መጽሀፍ መግዣ ገንዘብ
ለማሰባሰብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ለማሰባሰብ የጓሮ አትክልት ስፍራ ያስፈልገዋል፡፡
ተማሪዎች ጧት ጧት ወደ ት/ቤት ሲሔዱ ንቃት አንዳንድ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ መልካም ስነምግባር
ይታይባቸዋል፡፡ እንደሌላቸው እንሰማለን፣፡


ለት/ቤትህ ከባለድርሻ አካላት አጠቃላይ መረጃ መሰብሰብ፡፡

ከሁሉም መምህራን ጋር ስብሰባ ማድረግ አለብህ/ሽ፡፡ በስብሰባውም ሁሉም አስተዋፆኦ እንዲያደርግ ጠይቅ/ቂ፡፡

ከትምህርት ስራ ውጪ ካሉ አካላት ከወላጆችና ከተማሪዎች ጋር ተመሳሳይ ስብሰባ ማድረግ መቻል አለብህ/ሽ፡፡

በፅሁፍ የሚሰጥ ግብረመልስ መሰብሰብ መቻል አለብህ/ሽ፡፡

በማህበረሰቡ ውስጥ ስብሰባ ማድረግ መቻል አለብህ/ሽ፡፡


በተጨማሪ አባሪ ውስጥ ባዶ ቅፆች አሉ፡፡
ይህ የመረጃ ስብስብ የ/ት/ቤትህ/ሽ መሻሻል ዕቅድ አካል ሊሆን ይችላል፡፡

9
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
3. የት/ቤቱን ፍላጐቶች ዝርዝር ማዘጋጀት

ሁሉም መምህራን የሚሳተፉበት ስብሰባ ጥራ/ሪ፡፡ ሁሉም የየድርሻቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጠይቅ/ቂ፡፡

ት/ቤቱ የሠራቸውን መልካም ስራዎች ዘርዝረህ/ሽ ፃፋቸው/ፊያቸው፡፡

ሁሉንም የት/ቤቱን መሻሻል የሚገባቸውን ፍላጐቶች ዝርዝር አዘጋጅ/ጂ፡፡

ዝርዝሩ ቢረዝም አትደነቅ/ቂ፡፡

የትኛው የበለጠ ጠቃሚ ነው ብለው እንደሚያስቡ መምህራኑን ጠይቅ/ቂ፡፡

ከምናባዊ ት/ቤቱ የተወሰደ ምሳሌ፡-

የተ.ሙ.ማ ፍላጐቶች
በተለይ የወንዶች ተማሪዎችን ፀባይ ማሻሻል በመጀመሪያ ሳይክል የሒሳብ ትምሀርትና የማስተማር
ስራን ማሻሻል
በክፍል ውስጥ አብዝቶ ፅሁፍ የመገልበጥና በገለፃ ወደሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚገቡ ተማሪዎችን ቁጥር
የማስተማር ዘዴን ለማስቀረት የተሳትፎ የመማር ማሳደግ፡፡
ዘዴን ማጐልበት፡፡
የአዲስ ጀማሪ መምህራንን የማስተማር ክህሎት የሰርተፊኬት መምህራንን ወደ ዲፕሎማ ደረጃ ከፍ
ለማሻሻል ለአማካሪ መምህራን ስልጠና መስጠት፡፡ ማድረግ፡፡

እና ወዘተ …… ወዘተ ……. ወዘተ …………..


አሁን ስብሰባህን/ሽን አዘጋጅና/ጂና የተ.ሙ.ማህን ፍላጐቶች ዝርዝር ንድፍ
ጥሩ የሰራኸውን/ሽውን ማድነቅህን/ሽን አትርሣ/ሺ፡፡

10
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ደረጃ ሦስት(Stage 3)
የት/ቤታችሁን ተ.ሙ.ማ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች እንዴት ትወስናላችሁ?

አስቀድመህ/ሽ የት/ቤትህ/ሽን በጣም ጠቃሚ ጉዳዮች ወስን/ኚ

ይህን ስራ ለመስራት ለሁሉም አባላት በጣም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደዚህ ያሉ ጉዳዮች ብዙ ጊዜ ያጋጥማሉ፡፡ ጥቂት
አባላት ያሉት ቡድን ቢሆን የተሻለ ነው፡፡ ቡድኑም የት/ቤቱን ርዕሰ መምህር - ማካተት አለበት፡፡ ሌሎች መካተት ያለባቸው
ተሳታፊ አባላት:-

 የት.ቤቱ የተ.ሙ.ማ አስተባባሪ

 የት/ቤቱ ሱፐርቫይዘር

 የት/ቤቱ ተ.ሙ.ማ ኮሚቴ

 ከፍ ያለ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው መምህራን

 ሌሎች መምህራን

ከባለድርሻ አካላት የስበሰብከውን/ሽውን የጉዳዮች ዝርዝር ውሰድ/ጂ ዝርዝሩ የተሟላ ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን/ኚ፡፡
ለት/ቤትህ/ሽ ቢበዛ አስር ያህል በጣም ጠቃሚ ጉዳዮችን ምረጥ/ጪ፡፡
ቀጥሎ ከነዚህ የትኞቹ ከተ.ሙ.ማ ጋር ተዛምዶ እንዳላቸው አመዛዝን/ኚ፡፡

ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ማለት የሚከተሉትን የሚያደረግልህ/ሽ መሆኑን አሰታውስ/ሺ:-

 የተሻለ መምህር እንድትሆን/ኚ ይረዳሀል/ሻል፡፡


 የተማሪዎችን ትምህርት መማርና ውጤት እንድታሻሽል/ሽይ ይረዳሀል/ሻል፡፡
 የመማሪያ ክፍል የስራ ልምድህን/ሽን ያሻሽልልሀል/ሻል፡፡

አሁን ለት/ቤትህ/ሽ 3 የተ.ሙ.ማ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ትኩረቶች ያስፈልግሀል/ሻል፡፡ ይህ ቀላል ሥራ አይደለም!!!!

እያንዳንዱን ቅድሚያ የሚሰጠውን ትኩረት ስትወስን/ኚ ሊነሱ ስለሚችሉ በርካታ ጥያቄዎች በጥሞና ማሰብ አለብህ/ሽ፡፡

የቅድሚያ ትኩረት ጉዳዮች


- ተገቢ ናቸው?
- በጥሩ ሁኔታ ልንተገብራቸው እንችላለን?
- በተማሪዎች ሥነ ምግባር ውጤት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ሊያመጡ ይችላሉ?
- ወጪውን እንችለዋለን?
- በአሁኑ ጊዜ አንገብጋቢ ናቸው?

11
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ከምናባዊ ት/ቤት የተወሰደ ምሳሌ

የምናባዊ ት/ቤታችን የዚህ ዓመት የተ.ሙ.ማ ቅድሚያ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች፣


1. ት/ቤት አቀፍ አሳታፊ ማስተማር ዘዴ ማጐልበት
የተመረጠበት ምክንያት፣

አሳታፊ የማስተር ዘዴ ማጠንከሩ በተማሪዎች ሥነ ምግባር ሰዓት አክባሪነት ብሎም በውጤታቸው ላይ አዎንታዊ
ተፅዕኖ ይኖረዋል ብለን እናስባለን፡፡ አንገብጋቢ ስለሆነም በት/ቤቱ በጀት ልናካሒደው እንችላለን፡፡
2. ለአዳዲስ ጀማሪ መምህራን አማካሪዎችን ማሰልጠን
የተመረጠበት ምክንያት
ለአስራ አንዱ አዳዲስ ጀማሪ መምሀራን የሚሰጥ የተሳካለት የማማከር ስራ የመማርና የማስተማሩን ጥራት ለማሻሻል
ይረዳል፡፡
እነዚህ ለት/ቤታችን የቅድሚያ ትኩረት ጉዳዮች ናቸው፡፡ ከተ.ሙ.ማ ጋር ይዛመዳሉ?
“አዎን” ወይም “አይደለም”
ሌሎች
በመጀመሪያ ሳይክል የሒሳብ ትምህርት አሰጣጥን ማሻሻል አዎን በጉድኝቱ
ለአዳዲስ ጀማሪ መምህራን አማካሪዎችን ማሰልጠን አዎን ውስጥ ያሉ
የተማሪዎችን ፀባይ ማሻሻል አዎን ት/ቤቶች
በት/ቤቱ ሁሉ የተሳትፎን ትምሀርት ማጐልበት አዎን
ይህንን
በት/ቤቱ ውስጥ ውሀ ማስገባት አይደለም
የቅድሚያ
ሰዓት አከባበርን ማሻሻል አዎን
ትኩረት
ጉዳዮች በመምረጣቸው ወጭውን በመጋራት በጋራ ልንተገብር እንችላለን፡፡

12
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
3. በመጀመሪያ ሳይክል የሒሳብ አስተምህሮን ማሻሻል
የተመረጠበት ምክንያት፣
የመጀመሪያ ሳይክል ውጤታችን ቀንሷል፣ ቢሆንም በሌሎቹ የት/ዓይነቶች ጥሩ ውጤት አላቸው፡፡ የመጀመሪያ ሳይክል
መሻሻል በሁለተኛ ሳይክል የሚሰጠውን የሒሳብ ትምህርት አሰጣጥ እንዲሻሻል ይረዳል፡፡ አቶ አብርሀም የሒሳብ
ትምህርት ባለሙያ ስለሆነ ተ.ሙ.ማን ሊመራ ይችላል፡፡


አሁን ስብሰባ አዘጋጅና/ጂና በጣም ጠቃሚ የሆኑ ቅድሚያ የትኩረት ጉዳዮችህን/ሽን ዝርዝር ፃፍ/ፊ፡፡ ዝርዝሩን ተመልከትና
የትኞቹ ከተ.ሙ.ማ ጋር እንደሚዛመዱ ወስን/ኚ፡፡
የት/ቤትህን/ሽን ሶስት በጣም ጠቃሚ ፍላጐቶችን ምረጥ/ጪ፡፡
እነዚህ ለተ.ሙ.ማ ቅድሚያ ትኩረትህ/ሽ የተሰጣቸው ጉዳዮች ይሆናሉ፡፡

ደረጃ አራት (Stage 4)


የግልህን/ሽን ተ.ሙ.ማ ፍላጐቶችና ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮች እንዴት ትወስናለህ/ኛለሽ?

“ የተሻለ መምህር መሆን ያስፈልገናል“ ወይም


“ በክፍል ውስጥ የተሻልኩ ሆኜ መገኘት ያስፈልገኛል “ ብቻ ማለት በቂ አይደለም፡፡
የግድ እነዚህን ጥያቄዎች እራስህን/ሽን መጠየቅ አለብህ/ሽ
“ ያንን ለማሳካት በትክክል ምን ማድረግ ያስፈልገኛል?”

እንደ አንድ መምህር በስራህ ልታንፀባርቀው መቻል አለብህ/ሽ፡፡


በመጀመሪያ የስራ ክንውን በ “ሀገር አቀፍ የመምህራን የሙያ ብቃቶች ማዕቀፍ” ውስጥ ካሉት አምስቱ የሙያ ብቃቶች አንፃር
መፈተሽ አለብህ/ሽ፡፡
1. የተማሪዎችን መማር ማመቻቸት፡፡
2. የተማሪዎችን የመማር ውጤት መዳሰስና ሪፖርት ማቅረብ፡፡
3. በተ.ሙ.ማ መሳተፍ፡፡
4. የትምህርትና ስልጠና ፖሊስን፣ መርሀ ትምህርትንና ሌሎች የመርሀ-ግብር ማበልፀጊያ ሀሳቦችን ለማወቅ መነሳሳት፡፡
5. በት/ቤቱ ማህበረሰብ መካከል ዝምድናን ለመመስረት ግልፅና የተግባር ሰው መሆን ያስፈልግሀል/ሻል፡፡
ከዚያም የተሙማ ፍላጐትህን/ሽን ለመለየት የሚያስችሉህን/ሽን እነዚህን ጥያቄዎች ራስህን/ሽን ጠይቅ/ቂ፡፡

መማር ማስተማር
13
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
 ከየትኞቹ ክፍሎች ጋር መልካም ግንኙነት አለኝ? ይህ ለምን ሆነ?
 ለማስተማር በጣም አስቸጋሪ የሆኑብኝ የክፍል ደረጃዎች አሉ? ይህ ለምን ሆነ?
 በጥሩ ሁኔታ አብሬያቸው የምሰራ የተለያዩ ተማሪዎች ወይም ችግር በመሀከላችን ያለ ተማሪዎች አሉ?
 የማስተምረውን ትምህርት በጥንቃቄና በዝርዝር አቅጃለሁ?
 የማስተምራቸው የት/አይነቶች በጥሩ ሁኔታ ተጀምረው በጥሩ ሁኔታ ያበቃሉ?
 የማስተምረው ትምህርት የተለያዩ ተግባራዊ ስራዎችን ያካትታል?
 በትምህርቱ መጨረሻ ምን ያህል ተማሪዎች ትምህርቱን እንደተከታተሉ እንዴት አውቃለሁ ?
 በቂ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችና ግብአት አለ?
 ከሌሎች መምህራን ጋር ስለማስተማር ስራዬ ሀሳብ እለዋወጣለሁ?
 የማስተምራቸው የትምህርት ይዘቶች ወቅታዊ ናቸው?
 የማልተማመንባቸው ጥቂት ርዕሶች ይኖሩ ይሆን?
 የማስተማር ክ/ጊዜዬ አጓጊ የማስተማር ድባብ አለው?
 ልደርስበት የፈለግኩት ሙያዊ ብቃት አለ ?
 ሌሎች ሙያዊ የተ.ሙ.ማ ፍላጐቶች አሉኝ?

አመራርና አስተዳደር
 ጊዜዬን በአግባቡ እጠቀማለሁ?
 የት/ቤት መሻሻል ዕቅድ ገብቶኛል?
 በጀት ለማስተዳደር የተሻልኩ ነኝ?
 ተደማጭነት ያለው ተናጋሪ ነኝ?
 ስብሰባ ለመምራት ብቃት አለኝ?
 በጥሩ ሁኔታ አቅጃለሁ?
 አንድን ቡድን ለተልዕኮ ማሰማራት እችላለሁ?
 የሙያ ባልደረቦቼን የስራ ክንውን የመቆጣጠርና የመገምገም ብቃት አለኝ ልደርስባቸው የሚገቡ ሙያዊ ብቃቶች
አሉ?
 ሌሎች ሙያዊ የተ.ሙ.ማ ጉዳዮች አሉኝ?

ስለራስህ/ሽ ሌሎች መምህራንን እንዚህን ጥያቄዎች ልትጠይቅ/ቂ ትችላለህ/ያለሽ


እነሱም ስለፍላጐቶችህ/ሽ እንድታስብ/ቢ ይረዱሀል/ሻል፡፡

በተጨማሪ ተማሪዎች ስለአንተ/ቺ ያላቸውን አመለካከት መጠየቅ ትችላለህ/ያለሽ፡፡


ግላዊ ጥንካሬዎችህንና/ሽንና ማሻሻል የሚገባህን/ሽን ጉዳዮች ዝርዝር አውጣ/ጪ
14
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
የምናባዊ ት/ቤት ምሳሌ

ስላስ መኮንን

ጥንካሬዎቼ ምንድን ናቸው? ምን ማሻሻል ያስፈልገኛል?


ጓደኞቼ ሌሎች መምህራንን የመርዳት ችሎታ የተማሪዎች ልዩ ፍላጐት ላይ በመመስረት ማስተር፣
እንዳለኝ ይናገራሉ፡፡
ስነ ጥበብ ማስተማር ደስ ይለኛል፡፡ ምክንያቱም የሒሳብ ትምሀርት ማስተማር እወዳለሁ\ ግን
ተማሪዎችን በርካታ የተግባር ስራዎችን በክፍል የክፍል ውጤቴ ዝቅተኛ ነው፡፡ ሰለዚህ ጥሩ አድርጌ
ውስጥ ለማሰራት አስባለሁ፡፡ ማስተማር እንደማልችል ይገባኛል፡፡
ተማሪዎች እንደሚወዱኝ እናገራለሁ፡፡ ምክንያቱም ሰርትፍኬትን ወደ ዲፕሎማ ማሳደግ እፈልጋለሁ፡፡
ችግራቸውን በጥሞና አዳምጣለሁ፡፡
ስለሆነም ሶስቱ የተ.ሙ.ማ ቅድሚያ የሰጠኋቸው ጉዳዮች

1. ልዩ ፍላጐት ላላቸው ተማሪዎቼ የማስተማር ብቃት ማሻሻል


2. ሒሳብ የማስተማር ብቃቴን ማሻሻል
3. የሰርትፍኬት ደረጃዬን ወደ ዲፕሎማ ማሳደግ
በእነዚህ ሶስት ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮች ዙሪያ ለመስራት ጥቂቶቹን ብሔራዊ የመምህራን የሙያ ብቅቶችን ማሳካት
እችላለሁ፡፡


የተ.ሙ.ማ ፍላጐቶችህን/ሽን በምታንፀባርቅበት/ቂበት ጊዜ በሠንጠረዥ ውስጥ ልትሞላቸው/ያቸው ይገባሀል/ሻል፡፡

የዚህ ሠንጠረዥ ቅጂ በአባሪ ውስጥ ይገኛል፡፡

ጠንካራ ነኝ የምትልባቸውን/ይባቸውን ሶስት ነገሮች ምረጥ/ጪ፡፡


ልታሻሽላቸው/ያቸው የምትፈልጋቸውን/ጊያቸውን ሶስት ነገሮች ምረጥ/ጪ፡፡
ይህ ስለ ተ.ሙ.ማ ፍላጐቶችህ እንድታስብ/ቢ ሊረዳህ/ሽ ይችላል፡፡

በነገራችን ላይ!!!
ጥንካሬህ/ሽ ሌሎች መምህራን የተ.ሙ.ማ ፍላጐታቸውን እንዲያዩ በመርዳት በኩል በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡

ሶስቱ ልታሻሽላቸው /ያቸው የወሰንካቸው/ሻቸው ነገሮች የተ.ሙ.ማህ/ሽ ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮች ይሆናሉ፡፡
አሁን አመታዊ የተ.ሙ.ማ ዕቅድህን/ሽን ልታጠናቅቅ/ቂ ተዘጋጅተሀል/ሻል፡፡

15
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ፅብረቃ
ይህ አሁን ልታደርገው/ጊው የሚገባህ/ሽ ተግባር ነው፡፡

 የት/ቤትህን/ሽን ተ.ሙ.ማ ፍላጐቶች ላይ


 የትኞቹ በጣም ጠቃሚ እንደሆኑ ወስን/ኚ
 ሶስቱን ተ.ሙ.ማ ለመተግበር ምረጥ/ጪ


በእውቀትህና/ሽ በዕቅድህ/ሽ ዙሪያ ፅብረቃ አካሒድ/ጂ፡፡ የተ.ሙ.ማ ደረጃ ‘ትንተና’ ለማድረግ በራስ መተማመን
ይሰማሀል/ሻል፡፡

ተጨማሪ ልምምድ ያስፈልግሀል/ሻል፡፡

16
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -

ገማ
ግም
ትን
ተና

እርከን ሁለት
ተ.ሙ.ማ ፍላጐትን ማቀድ ት ፍተሻ ት


ትግ


ዕቅ
ደረጃ አንድ

አመታዊ የተሙ.ማ እቅድህን/ሽን እንዴት ታቅዳለህ/ሽ?

ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮችን ለይ/ዩ፡፡


ኃላፊነቶችን፣ ጊዜዎችንና ውጤቶችን ወስን/ወስኝ፡፡
ቅድሚያ የተሰጣቸውን ጉዳዮች ውጤት ለይ/ዩ፡፡

ደረጃ ሁለት
የተ.ሙ.ማ የት/ቤት ሞጁል እንዴት ታቅዳለህ/ጃለሽ?

የት/ቤት ሞጁል ተከታታይነት ያላቸው የዕቅድ ክፍለ-ጊዜያት ተደጋግፈው የሚያስገኙት ውጤት ነው፡፡

ደረጃ ሦስት
የተሙ.ማ ክፍለ-ጊዜዎችን እንዴት ታቅዳለህ/ጃለሽ?

ለእያንዳንዱ የተ.ሙ.ማ ክፍለ-ጊዜ የሚስማማውን ዘዴና ተግባራት ምረጥ/ጪ፡፡ የተ.ሙ.ማ ዕቀድ የት/ቤትን፣ በት/ቤት የሚገኙ
ቡድኖችና፣ የግል ዕቅድን ያካትታል፡፡

ደረጃ አንድ
አመታዊ የተ.ሙ.ማ ዕቅድህን/ሽን እንዴት ታቅዳለህ/ጃለሽ?
ከዚህ የዕቅድ ደረጃ በኃላ:-
 ተ.ሙ.ማን ማቀድ አስፈላጊ መሆኑን ማወቅ አለብህ/ሽ፣
 በት/ቤት፣ በቡድንና በግል ዕቅዶች መካከል ያለውን ተያያዥነት መረዳት አለብህ/ሽ፡፡
 የሚያስፈልገውን ጊዜ በመወሰን አመታዊ የት/ቤትና የግል ተ.ሙ.ማ ዕቅድ ማዘጋጀት አለብህ/ሽ፣

ይህ ደረጃ በሁለት ክፍሎች ይከፈላል፤

የመጀመሪያው ክፍል አጠቃላዩን የትምህርት ቤት አመታዊ ተ.ሙ.ማ ዕቅድ ዝግጅት ሲሆን ሁለተኛው ክፍል የግለሰቦች
የራሳቸው አመታዊ የተሙ.ማ ዕቅድ ዝግጅት ነው፡፡

የትምህርት ቤት አመታዊ ተሙ.ማ እቅድ

17
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
በትንተና ደረጃ የመረጥካቸውን/ሻቸውን ሦስት ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮችን ውሰድ/ጂ፡፡ ሶስት ቅድሚያ የሚሰጣቸው
ጉዳዮች በተ.ሙ.ማ የት/ቤት የዕቅድ ቅጽ የመጀመሪያ አምድ ስር የቅድሚያ ሰንጠረዥ ውስጥ በመጻፍ አመታዊ የት/ቤት
ተ.ሙ.ማ እቅድህን/ሽን ጀምር/ሪ፡፡ የአመቱ ተ.ሙ.ማ ቅጽ ኮፒ በአባሪ ውስጥ ተያይዞአል፡፡
ከሶስቱ ቅድሚያ ጉዳዮች አንዱ ለሁሉም መምህራን መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህም በመማሪያ ክፍል ውስጥ ቀጥተኛ ተፅዕኖ
ሊኖረው ይገባል፡፡
የት/ቤቱ ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮች የሚከተሉትን ሊይዝ ይችላል:-

 በትምሀርት ክ/ጊዜ የተማሪዎች ተሳትፎ፣

 የትምህርት ዕቅድ ዝግጅትን ማሻሻል፣

 ውጤታማ ተከታታይ ምዘና ስልቶች

 ሁሉንም ተማሪዎች ማካተት

 በት/ቤቱ አጠቃላይ የባህርይ ለውጥ/መሻሻል ማምጣት፣

 ሰዓት ማክበርና በት/ቤት መገኘት፡፡

የት/ቤት ቅድሚያ የተሰጣቸው ሌሎች ጉዳዮች፡- ተ.ሙ.ማ ለተወሰኑ መምህራን


አንዳንድ ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮች በት/ቤትህ/ሽ ለሚገኙ ለሁሉም መምህራን ተስማሚ ላይሆኑ ቢችሉም ለአጠቃላይ
የት/ቤቱ መሻሻል ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በነዚህ ቅድሚያ በተሰጣቸው ጉዳዮች ጥቂት መምህራን ብቻ ሊሳተፉ ይችላሉ፡፡
ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚችሉ ሌሎች ጉዳዮች፡-

ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮች ተሳታፊ መምህራን


የምናባዊ
የመጀመሪያ ሳይክል የሂሳብ ትምህርት ማሻሻል፣ የመጀመሪያ ሳይክል የሂሳብ መምህራን፣

ትምህርት ቤት ምሳሌ፡- ጥሩ የማማከር ስርዓት መፍጠር፣ ለአማካሪነት የተመረጡ መምህራን፣

በፖርትፎልዮ አጠቃቀም ላይ አመራርን ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች፣


የት/ቤት አመታዊ ማሳደግ/ማዳበር፣
ተ.ሙ.ማ ዕቅድ

የት/ቤቱ ስም ምናባዊ ት/ቤት

በተ.ሙ.ማ በተ.ሙ.ማ ኃላፊነት መቼ ተጀምሮ ምን ለውጥ ማየት


ቅድሚያ ተሳታፊው የተሰጠው መቼ እንፈልጋለን?
የተሰጣቸው ማነው? ማነው? ይጠናቀቃል?
ተግባራት
1. አሳታፊ
ትምህርትን
በት/ቤት
18
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ማስፋፋት

2. ለአዲስ ጀማሪ
መምህራን
አማካሪ
መምህራንን
ማሰልጠን

3. በ 1 ኛ ሳይክል
የሂሳብ
ትምህርት
አስተምህሮን
ማሻሻል


በአባሪነት የተያያዘውን አመታዊ የተ.ሙ.ማ እቅድ ቅጽኮፒ በመጠቀም የት/ቤትህን/ሽን ቅድሚያ የተሰጣቸውን ጉዳዮች
አስፍር/ሪ\ ሙላ/ይ፡፡ በቅድሚያ የቅጹን የመጀመሪያ አምድ ብቻ መሙላትህን/ሽን አስታወስ/ሽ፡፡

አሁን የሚቀጥሉትን ሶስት ረድፎች መሙላት ያስፈልግሀል/ሻል፡፡ ለዚህም እንዲረዱ ቀጥለው የቀረቡት ሃሳቦች ጠቃሚ ናቸው፡፡
በተ.ሙ.ማ የሚሳተፍ ማነው?
ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ በት/ቤትህ/ሽ የሚገኙትን መምህራን በሙሉ ያሳትፋል?
የመምህራንን ቡድን ያሳትፋል? ምሳሌ ትምህርት ክፍሎችን ወይም የመጀመሪያና የሁለተኛ ሳይክል ጥቂት መምህራንን
ያካትታል?
ጥቂት መምህራንን ምሳሌ ሶስት የማኔጅመንት አካል መምህራንን ያሳትፋል?

ኃላፊነት የተሰጠው ማነው?

ለእያንዳንዱ ቅድሚያ ለተሰጠው ጉዳይ አንድ ሰው ኃላፊ መሆኑ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ግለሰቡ ሁሉንም ማዘጋጀት
አለበት ማለት አይደለም፡፡ ዕቅዱ መተግበሩን ለማረጋገጥ ከሌሎች ሰዎች ጋር ይሰራል፡፡
መቼ ተጀምሮ መቼ ይጠናቀቃል?
ዕቅዱን ለማከናወን የተወሰነ ጊዜ መስጠቱ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም የ ተ.ሙ.ማ ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ መቼ ተጀምሮ መቼ
ይጠናቀቃል? ጥቂቶቹ ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮች ዓመት ሊፈጁ ሲችሉ ሌሎች ደግሞ ሴሚስተር ወይም ወር ሊፈጁ
ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ቅድሚያ የተሰጣቸውን ጉዳዮች ለመተግበር ምን ያህል ሰዓት እንደሚወስድ አስቀድሞ መወሰን
ያስፈልጋል፡፡

ከምናባዊ ት/ቤት የተወሰደ ምሳሌ

19
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
የት/ቤት አመታዊ ተሙ.ማ ዕቅድ
የት/ቤቱ ስም ምናባዊ ትም/ቤት

በተ.ሙ.ማ ቅድሚያ በተ.ሙ.ማ ተሳታፊ ኃላፊነት የተሰጠው መቼ ተጀምሮ መቼ ምን ለውጥ ማየት


የተሰጣቸው ጉዳዮች ማነው? ማነው? ይጠናቀቃል? እንፈልጋለን?
1. አሳታፊ
ትምህርትን
ሁሉም የ 1 ኛ ና
የ 2 ኛ ሳይክል
የተሙ.ማ
አስተባባሪ
ከ 1 ኛ ሴሚስተር
መጀመሪያ እስከ 2 ኛ

በት/ቤት
መምህራን ሴሚስተር መጨረሻ በተሙ.ማ የሚሳተፍ
ማስፋፋት ማነው?
2. ለአዲስ መምህራን ኃላፊነት የተሰጠው
ሁሉም ር/መምህር ከ 1 ኛ ሴሚስተር
አማካሪ ማነው?
አማካሪዎች መጀመሪያ እስከ 2 ኛ
መምህራንን
ሴሚስተር መጨረሻ
ማሰልጠን መቼ ተጀምሮ መቼ
3. በ 1 ኛ ሳይክል
ይጠናቀቃል?
የሂሳብ ትምህርት ሁሉም የሂሳብ ከ 1 ኛ ሴሚስተር
አስተምህሮን የመጀመሪያ ዲፖርትመንት መጀመሪያ እስከ 1 ኛው
ማሻሻል
የመጨረሻውን አምድ
ሳይክል የሂሳብ ተጠሪ ሴሚስተር መጨረሻ
መምህራን በመተው የአመታዊ
ተሙ.ማ እቅድ ቅጽ
ኮፒ ተጠቅመህ/ሽ ሰንጠረዡን ሙላ/ይ፡፡

ምን ለውጥ ማየት እንፈልጋለን?

ይህ በጣም አስፈላጊ የሰንጠረዡ ክፍል ነው፡፡

 በተ.ሙ.ማ ቅድሚያ ከተሰጣቸው ጉዳዮች ክንውን በኋላ ምን ይለወጣል?


 መለወጡንስ እንዴት ታውቃለህ/ቂያለሸ ?
ይህን መፈፀም ሁልጊዜ ቀላል አይሆንም፡፡ ምን ማግኘት/ውጤት እንደምትፈልግ/ጊ ወስደህ/ሽ ወስን/ኝ፡፡ እነዚህን ለውጦች
መለካት መቻል አለብህ/ሽ፡፡

የዚህን ሰነድ እርከን 4 “ግምገማ” መጠቀም ለውጦችን ለመለካት የሚያስችሉ መንገዶችን ለመለየት ይረዳሃል/ሻል፡፡

ምሳሌ ምናባዊ ት/ቤት

የት/ቤት አመታዊ ተሙ.ማ እቅድ

የት/ቤቱ ስም ምናባዊ ትም/ቤት

የተሙ.ማ በተሙ.ማ ኃላፊነት የተሰጠው መቼ ተጀምሮ መቼ ምን ለውጥ ማየት


ቅድሚያ ውስጥ ማነው? ይጠናቀቃል? እንፈልጋለን?
የተሰጠው ጉዳይ የሚሳተፈው
20
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ማነው?
1. አሳታፊ ሁሉም የ ተሙ.ማ አስተባባሪ ከ 1 ኛ ሴሚስተር በትምህርት ክ/ጊዜ የተማሪዎች
ትምህርትን የመጀመሪያ መጀመሪያ እስከ 2 ኛ የላቀ ተሳትፎ፣ በሁሉም ክፍል
በት/ቤት ሳይክል እና ሴሚስተር፣ ደረጃ የፈተና ውጤቶች መሻሻል፣
ውስጥ የ 2 ኛ ሳይክል የባህርይ በተለይ የወንዶች ባህርይ
ማስፋፋት፣ መምህራን መሻሻል፡፡

2. ለጀማሪ ሁሉም ር/መምህራን ከ 1 ኛ ሴሚስተር አማካሪዎች ሚናቸውን


መምህራን መምህራን መጀመሪያ እስከ 2 ኛ ለማከናወን በራሳቸው
አማካሪ ሴሚስተር መጨረሻ መተማመን፡፡ የጀማሪ መምህራን
መምህራንን የትም/ዕቅድ፣ ማስተማርና
ማሰልጠን ግምገማ መሻሻል፡፡

3. በመጀመ ሪያ ሁሉም የሂሳብ ዲፖርትመንት ከ 1 ኛ ሴሚስተር የክፍል ውስጥ ምልከታ


ሳይክል የሂሳብ የመጀመሪያ ተጠሪ መጀመሪያ እስከ 1 ኛ የማስተማር መሻሻልን አሳይቷል፡፡
አስተምህሮን ሳይክል የሂሳብ ሴሚስተር መጨረሻ የፈተና ውጤቶች ተሻሽለው
ማሻሻል መምህራን ቢያንስ ከሌሎች ትምህርቶች
አማካይ ውጤት ጋር እኩል
ሆነዋል፡፡ ተማሪዎች የሂሳብ
ትምህርትን ይወዳሉ፡፡

. 
ምን ለውጥ ለማየት ትፈልጋለህ?/ ትፈልጊያለሽ?
የመጨረሻውን አምድ የአመታዊ ተሙ.ማ ዕቅድ ቅጽ በመጠቀም ለትምህርት ቤትህ/ሽ! ሙላ/ዪ፣
አስታውስ/ሺ እነዚህን ለውጦች መለካት መቻል አለብህ/ሽ ፣ .

የአመቱን የግል ተሙ.ማ እቅድህን/ሽን ማዘጋጀት


እስካሁን ሶስት ቅድሚያ የተሰጣቸውን የተሙማ ጉዳዮች ለይተሃል/ሻል፡፡ አሁን ደግሞ እነዚህን ጉዳዮች እንደአስፈላጊነታቸው
በቅደም ተከተል አስቀምጣቸው/ጪያቸው፡፡ የሥራ ባልደረባህ/ሽ እንዲረዳህ/ሽ መጠየቅ ትችላለህ/ያለሽ፡፡ አሁን የአመቱን የግል
ተሙ.ማ እቅድህን/ሽን ለማጠናቀቅ ዝግጁ ነህ/ሽ?
አንተን/ቺን የሚመለከት ሀገር አቀፍ፣ ክልላዊ ወይም የት/ቤት ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ ካለ በመጀመሪያ በእቅድህ/ሽ
ታካትታለህ/ችያለሽ፡፡ ከዚህ የተረፈ ጊዜ ካለ የራስህን/ሽን ቅድሚያ ተግባር/ተግባራት ትጨምራለህ/ሪያለሽ፡፡ (ለተሙ.ማ
የተወሰነው ጊዜ በዚህ ምዕራፍ የሚከተለው ክፍል ውስጥ ተብራርቷል)፡፡
ምናባዊ ት/ቤት ምሳሌ፡-

የግል አመታዊ የተሙ.ማ ዕቅድ


ስም ስላስ መኮንን
የተ.ሙ.ማ በተ.ሙ.ማ ውስጥ ኃላፊነት መቼ ተጀምሮ መቼ ምን ለውጥ ለማየት ትፈልጋለህ/ጊያለሽ?
ቅድሚያ የሚሳተፈው የተሰጠው ይጠናቀቃል?
የተሰጠው
21
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ጉዳይ ማነው? ማነው?
1. አሳታፊ የመጀመሪያና የተ.ሙ.ማ ከ 1 ኛሴሚስተርመጀመሪያ የተማሪዎች ተሳትፎ መጨመር፣ የፈተና
ትምህርትን የ 2 ኛ ሳይክል አስተባባሪ እስከ ሁለተኛ ሴሚስተር ውጤቶች በሁሉም ክፍል ደረጃ መሻሻል፣
በት/ቤቱ ሁሉም መምህራን መጨረሻ የባህርይ መሻሻልበተለይየወንድተማሪዎች፡፡
ማስፋፋት

2. በመጀመ ሪያ ሁሉም የመጀመሪያ የሂሳብ 1 ኛ ሴሚስተር መጀመሪያ እስከ የክፍል ውስጥ ምልከታ የአስተምህሮ መሻሻልን
ሳይክል የሂሳብ ሳይክል የሂሳብ ዲፖርትመንት 2 ኛ ሴማስተር መጨረሻ ያመለክታል፡፡የፈተና ውጤቶች ተሻሽለው ቢያንስ
አስተምህሮን መምህራን ተጠሪ ከሌሎች ትምህርቶች አማካይ ውጤት ጋር እኩል
ማሻሻል ሆነዋል፡፡፣ ተማሪዎች ሂሳብ ትምህርትን ይወዱታል፡፡

3.የልዩፍላጐት የሥራ ባልደረባዬና የሥራ ከ 2 ኛ ሴሚስተር መጀመሪያ የተማሪዎችን ልዩ ፍላጐት ለመመለስ ማቴሪያሎች
አስተምህሮን እኔ ባልደረባዬና እኔ እስከ 2 ኛ ሴሚስተር መጨረሻ ተስተካክለዋል፣ ተማሪዎች በሁሉም ትምህርት
ማሻሻል ይሳተፋሉ፡፡

. 
የተ.ሙ.ማ እቅድ ዝግጅትህን/ሽን አጠናቅ/ቂ፡፡
ዕቅድህን/ሽን በት/ቤት፣ በክልል እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅድሚያ ከተሰጣቸው ጉዳዮች መጀመርህን/ሽን አስታውስ/ሺ፡፡

ለተ.ሙ.ማ ጊዜ እንዴት ታገኛለህ/ሽ?


በት/ቤትህ/ሽ ያለ እያንዳንዱ መምህር ቢያንስ በዓመት 60 ሰዓት በተሙ.ማ ላይ ማዋል ይጠበቅበታል/ባታል፡፡
ተሙማ የማያካትታቸው ! (Exception)

አዲስ ጀማሪ መምህራን የሙያ የትውውቅ ኮርስን እንደ ተ.ሙ.ማ ያካሂዳሉ፡፡ ለመጀመሪያዎቹ
ሁለት አመታት ሌላ ተጨማሪ ተሙማ እንዲያካሂዱ አይጠበቅባቸውም፡፡ ፍላጐት ካላቸው ግን ሌላ የተሙ.ማ እንቅስቃሴ
ውስጥ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

የትኞቹ ተግባራት በተ.ሙ.ማ 60 ሰዓት ውስጥ ይካተታሉ?

ማንኛውም ተመ.ማን በመተግበርና ራስን ወቅታዊ በማድረግ ላይ የዋለ ሰዓት ከመደበኛ የመምህራን ሥራ ውስጥ
እስካልተካተተ ድረስ በግል 60 አመታዊ የተሙማ ሰዓት ይቆጠራል፡፡

በተ.ሙ.ማ 60 ሰዓቶች ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ተግባራት ምሳሌዎች :-

 በተ.ሙ.ማ አውደጥናት፣ የመምህራን ስብሰባ ወይም የቡድን ውይይት መሳተፍ፣

22
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
 ሌላ መምህር/ት ሲያስተምር/ስታስተምር መመልከት፣
 በጋራ ማቀድ ወይም የአቻ ግምገማ፣
 የአማካሪ ክህሎትን እንደ ግል ተ.ሙ.ማ መተግበር፣
 ሌላ ት/ቤት መጐብኘት
 የቡድን አስተምህሮ (ከሌላ መምህር/መምህራን ጋር በክፍል ውስጥ መሥራት)

በተሙ.ማ 60 ሰዓቶች ውስጥ ሊካተቱ የማይችሉ ተግባራት ምሳሌዎች:-

 አዲስ ክህሎትን ለመደበኛ የሥራ ጊዜ በተመደበ ሰዓት ውስጥ መለማመድ፣


 በሥራው ላይ የቆዩና የማማከር ልምድ ያላቸው መምህራን ለጀማሪ መምህራን የሚሰጡት የምክር አገልግሎት፣
 ከሰርተፊኬት ወደ ዲፕሎማ ራስን ማሳደግ፣
 ሌላ የክረምት ትምህርት መርሃ ግብሮች

በእርከን አንድ ” የተ.ሙ.ማ ፍላጐትን መተንተን“ እንደተገለፀው ፍላጐቶች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ይመነጫሉ፡፡
 ግለሰቦች
 ዲፖርትመንቶች
 ት/ቤቶች
 የጉድኝት ማዕከላት
 ወረዳዎች
 ክልሎችና ዞኖች
 ሀገር አቀፋዊ

አንዳንድ ጊዜ ት/ቤትህ/ሽ ጊዜን በሀገር አቀፍ ፍላጐት ላይ ማዋል አለበት፡፡ አንዳንድ ጊዜ የክልል
ወይም የወረዳ ፍላጐቶች መስተናገድ ይኖርባቸዋል፡፡

እነዚህ ፍላጐቶች ከአመቱ ስልሳ ሰዓት ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ከሌሎች የአስተዳደር እርከኖች ምንም ፍላጐት ስለማይኖር ሙሉው ስልሳ ሰዓት

23
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ለት/ቤትና ለግል ፍላጐት ይውላል፡፡.

እያንዳንዱ ዓመት የተለየ ይሆናል፡፡

መጀመሪያ የት/በትህን/ሽን ተሙ.ማ ዕቅድና የሚመደብለት ጊዜ መወሰን አለበት፡፡

ቀጥሎ የራስህን የግል ዕቅድ ማጠናቀቅ ትችላለህ/ያለሽ፡፡

እያንዳንዱ ቅድሚያ ተግባር የሚፈጀው ጊዜ የሚመደበው ሥራው ሊወሰድ የሚችለውን ጊዜ በመገመት ነው፡፡ ሞጁሉን
ስታቅድ/ጅ ወይም ስትተገብር/ሪ በሚካሄድ ፍተሻ ሊለወጥ ይችላል፡፡

የ ተ.ሙ.ማ ጊዜን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚከተሉት ምሳሌዎች ያሳያሉ፡፡

ምሳሌ አንድ፣

ሁሉም መምህራን የሚተገብሩት በአንድ አይነት ሰዓት ነው፤ ምከንያቱም እያንዳንዱ ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ እያንዳንዱን
መምህር ስለሚያሳትፍ ነው፡፡ በዚህ ምሳሌ ውስጥ ያሉ የእያንዳንዱ መምህር ተ.ሙ.ማ ሰዓቶች የሚውሉት በሀገር አቀፍ፣
በክልልና በት/ቤት ቅድሚያ ተግባራት ላይ ነው፡፡

የት/ቤቱ ጊዜ አመዳደብ፣

የት/ቤት ቅድሚያ የተሰጣቸው የፍላጐቱ የሚሳተፉ መምህራን ጊዜ-ጠቅላላ


ምንጭ 60 ሰዓት

ጉዳዮች

የስነ ሕዝብና የቤተሰብ አኗኗር ትምህርት ሀገር አቀፍ ሁሉም መምህራንና 15


ዕውቀትን ማዳበር ር/መምህራን

የፖርትፎልዮ ጥራትን ማሻሻል ክልላዊ ሁሉም መምህራንና 15


ር/መምህራን

በት/ቤት ውስጥ የተከታታይ ምዘናን ት/ቤት ሁሉም መምህራንና 30


አጠቃቀም ማሻሻል ር/መምህራን

አንድ መምህር ጊዜ አመደደብ

24
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
እንደ መምህር የእኔ ቅድሚያ የፍላጐት ከእኔ ጋር የሚሳተፈው ጊዜ ጠቅላላ 60
ምንጭ ማነው? ሰዓት

የሰጠኋቸው ጉዳዮች በት/ቤት ውስጥ

የስነ ሕዝብና የቤተሰብ አኗኗር ትምህርት ሀገር አቀፍ ሁሉም መምህራንና 15


ዕውቀትን ማዳበር ር/መምህራን

የፖርትፎልዮ ጥራትን ማሻሻል ክልላዊ ሁሉም መምህራንና 15


ር/መምህራን

በት/ቤት ውስጥ የተከታታይ ምዘናን ት/ቤት ሁሉም መምህራንና 30


አጠቃቀም ማሻሻል ር/መምህራን

ምሳሌ ሁለት

ት/ቤቱ በራሱ ቅድሚያ በሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ማተኮር ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሀገር አቀፍ ወይም በክልል ደረጃ ቅድሚያ
የተሰጣቸው ጉዳዮች የሉም፡፡ በዚህ ምሳሌ መሠረት እያንዳንዱ መምህር ለግል ተሙማ የተወሰነ ጊዜ ይኖረዋል/ራታል፡፡

የት/ቤቱ የጊዜ አመደደብ

የፍላጐት ተሳታፊ መምህራን ጊዜ ጠቅላላ


ምንጭ 60 ሰዓት

የት/ቤት ቅድሚያ
የተሰጣቸው ጉዳዮች

ሰዓት ማክበርና መገኘት ት/ቤት ሁሉም መምህራንና 20


ር/መምህራን

የኬሚስትሪ ማስተማሪያ ተግባራዊ ዘዴዎች ት/ቤት ሁሉም መምህራንና 20


ር/መምህራን

የ 8 ኛ ክፍል የእንግሊዝኛ ፈተና ውጤትን ት/ቤት ሁሉም መምህራንና 20


ማሻሻል ር/መምህራን

የ 2 ኛ ሳይክል የኬሚስትሪ መምህር የግል ጊዜ አመዳደብ

የፍላጐት ተሳታፊ መምህራን ጊዜ ጠቅላላ


ምንጭ 60 ሰዓት
በት/ቤት ውስጥ በ 2 ኛ ሳይክል
የሳይንስ መምህርነቴ ያሉኝ ቅድሚያ
የተሰጣቸው ጉዳዮች

ሰዓት ማክበርና መገኘት ት/ቤት ሁሉም መምህራንና 20

25
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ር/መምህራን

የኬሚስትሪ ማስተማሪያ ተግባራዊ ዘዴዎች ት/ቤት የኬሚስትሪ መምህራን 20

የግሌ ቅድሚያ የሰጠሁት ጉዳይ የግል እኔ 20

ምሳሌ ሦስት

በዚህ ምሳሌ አንድ ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ ብቻ ሁሉንም መምህራን ያሳትፋል/ያካትታል፡፡ በመሆኑም አብዛኛው መምህራን 20 ሰዓት
ይተርፋቸዋል፡፡ ይህን 20 ሰዓት ለግል ተሙ.ማ ቅድሚያ ለተሰጠው ጉዳይ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

የት/ቤቱ ጊዜ አመደደብ

የፍላጐት ተሳታፊ መምህራን ጊዜ ጠቅላላ


ምንጭ 60 ሰዓት

የት/ቤት ቅድሚያ የተሰጣቸው


ጉዳዮች

መረጃ የመተንተን ክህሎትን ማሻሻል ወረዳ ር/መምህራን 20


ም/ር/መምህራን
ጉድኝት ማዕከላት
ሱፐርቫይዘሮች

የማማከር ክህሎትን ማሻሻል ጉድኝት የጀማሪ መምህራን 20


ማዕከላት አማካሪዎች

በት/ቤት ውስጥ የተማሪዎችን የክፍል ውስጥ ት/ቤት ሁሉም መምህራንና 40


ተሳትፎ ማሻሻል ር/መምህራን
የመጀመሪያ ደረጃ የመጀመሪያ ሳይክል የኤስቴቲክስ መምህር ጊዜ አመዳደብ፣

የፍላጐት ተሳታፊ መምህራን ጊዜ ጠቅላላ


ምንጭ 60 ሰዓት
በት/ቤት ውስጥ እንደ የመጀመሪያ
ሳይክል የኤስቴቲክስ መምህርነቴ ቅድሚያ
የሰጠኋቸው ጉዳዮች

በት/ቤት ውስጥ የተማሪዎችን የክፍል ውስጥ ት/ቤት ሁሉም መምህራንና 40


ተሳትፎን ማሻሻል ር/መምህራን

የግሌ ቅድሚያ የሰጠኋቸው ጉዳዮች ግለሰብ እኔ 20

ምሳሌ አራት

26
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
በዚህ ምሳሌ አብዛኛዎቹ መምህራን 50 ሰዓት ተመድቦላቸዋል፡፡ ቀሪውን 10 ሰዓት በራሳቸው የተ.ሙ.ማ ቅድሚያ
ለተሰጣቸው ጉዳዮች ሊያውሉት ይችላሉ፡፡ የበለጠ ሰዓት መጠቀምም ይፈልጉ ይሆናል፡፡ በዚህ ምሳሌ ተጨማሪ ኃላፊነት
ያለባቸው መምህራን ከ 60 ሰዓት የበለጠ ጊዜ በት/ቤቱ ቅድሚያ ለተሰጣቸው ጉዳዮች መጠቀም እንዳለባቸው ተመልክቷል፡፡

የት/ቤቱ ጊዜ አመዳደብ
የፍላጐት ተሳታፊ መምህራን ጊዜ-ጠቅላላ
ምንጭ 60 ሰዓት

የት/ቤት ቅድሚያ
የተሰጣቸው ጉዳዮች
በት/ቤት ውስጥ የትምህርት ዕቅድ ዝግጅትን ት/ቤት ሁሉም መምሀራንና 50
ማሻሻል ር/መምህራን
የት/ቤቱን ቤተመጻሕፍት አጠቃቀም ማሻሻል ት/ቤት የዲፖርትመንት 20
ተጠሪዎች
የት/ቤት መሻሻል ዕቅድ ዝግጅት ክህሎትን ክልላዊ ር/መምህራን 20
ማሻሻል ም/ር/መምህራን እና
የጉድኝት ማዕከል
ሱፐርቫይዘሮች
የእንግሊዝኛ መምህር የግል ጊዜ አመዳደብ
የፍላጐት ተሳታፊ መምህራን ጊዜ ጠቅላላ
ምንጭ 60 ሰዓት
የት/ቤት ውስጥ በዲፖርትመንት
ተጠሪነቴ ቅድሚያ የሰጠኋቸው ጉዳዮች
በት/ቤት ውስጥ የትምህርት ዕቅድ ዝግጅትን ት/ቤት ሁሉም መምህራንና 50
ማሻሻል ር/መምህራን
የት/ቤቱን ቤተመጻሕፍት አጠቃቀም ማሻሻል ት/ቤት የዲፖርትመንት 20
ተጠሪዎች
የግሌ ቅድሚያ የሰጠሁት ጉዳይ ግለሰብ እኔ 10

አሁን ለት/ቤትህና ለግልህ የለየሃቸውን/ሻቸውን ቅድሚያ የተሰጣቸውን ጉዳዮች ተመልከት/ቺ፡፡ ከተ.ሙ.ማ ስልሳ ሰዓቶች
ውስጥ ለእያንዳንዱ ቅድሚያ ለተሰጠው ጉዳይ ስንት ሰዓት መመደብ እንዳለበት አስብ/ቢ፡፡ ይህ ውስብስብ ሂደት ነው፡፡ እናም
አንድ ትክክለኛ መልስ የለውም፡፡ እያንዳንዱ ት/ቤት የጊዜ አመዳደብን በተለያየ ሁኔታ ይመለከታል፡፡ የመጨረሻ ውሳኔ
የመስጠቱ ኃላፊነት የር/መምህሩ ወይም የተ.ሙ.ማ ኮሚቴ ነው፡፡

.  በመጀመሪያ የት/ቤትህን/ሽን ተ.ሙ.ማ እቅድ አጠናቅና/ቂና ቀጥሎ የራስህን/ሽን የግል ተ.ሙ.ማ ዕቅድ አዘጋጅ/ጂ፡፡
በሀገር አቀፍና በክልል ቅድሚያ ለተሰጣቸው ጉዳዮች ቅድሚያ መስጠት እንዳለብህ/ሽ አስታውስ/ሽ
ይህ የጊዜ አመዳደብ ተገቢ የሚሆነው የት/ቤት ሞጁል ማቀድ ከቻልክ/ሽ ነው፡፡

27
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ፅብረቃ/Reflection
ይህ አሁን ማድረግ መቻል ያለብህ/ሽ ጉዳይ ነው፡፡
 ተሙ.ማ ማቀድ ዋና ፍሬነገር መሆኑን ማወቅ፡፡
 ት/ቤቱ በቡድንና በግል ዕቅድ መካከል ያለውን ተያያዥነት መረዳት፡፡
 አመታዊ የት/ቤትና የግል ተ.ሙ.ማ እቅዶችን ማዘጋጀት መቻል፡፡


የራስህን/ሽ ግንዛቤና መሻሻል ገምግም/ሚ፡፡
የት/ቤትና የግል አመታዊ ተሙ.ማ ዕቅድ ለማዘጋጀት በራስህ/ሽ ትተማመናለህ/ኛለሽ?
ተጨማሪ ልምምድ ትፈልጋለህ/ጊያለሽ?

ደረጃ ሁለት

የት/ቤት የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ሞጁል እንዴት ማቀድ ይቻላል?


አሁን የት/ቤት እና የግል የተሙማ እቅዶች አላችሁ፡፡ ይህ ዕቅድ ወደ ት/ቤት እና የግል ሞጁል ደረጃ ማደግ ይኖርበታል፡፡ ሞጁል ያቀድነው
ዕቅድን ወደ ተግባር መቀየሪያ መሣሪያ ነው፡፡
ሞጅሎች ‘ምንድን ነው የምንሰራው?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣሉ፡፡
የት/ቤት ሞጁል የተሳካ የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሊያስገኙ የሚችሉ ተከታታይነት ያላቸውና እርስበርስ ግንኙነት ወይም ትስስር ያላቸው
የክ/ጊዜ ዕቅዶች ማለት ነው፡፡

የት/ቤት ሞጁል እቅድን ካጠናቀክ/ሽ በኋላ የሚከተሉት ነገሮች ይጠበቁብሀል/ሻል: -


 የት/ቤት ሞጁል እንዴት መታቀድ እንዳለበት ማወቅ፣
 በተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሞጁል ውስጥ ያሉት ክ/ጊዜያት እንዴት መያያዝ እንዳለባቸው
መረዳት፣
 አንድ የት/ቤት እና አንድ የግል ሞጁል እቅድ ማዘጋጀት፡፡

የት/ቤት ሞጁል እቅድ ማውጣት የማን ሀላፊነት ነው ?

በት/ቤት ውስጥ ከዚህ በፊት የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ የት/ቤት ሞጁል ዝግጅት ላይ አስተባባሪ ሆነህ/ሽ ተመድበህ/ሽ ትውቃለህ/ቂያለሽ?
ይህ ከሆነ ደግሞ የት/ቤት ሞጁል እቅድ ቅፅ በትክክል መሙላት ያንተ/ቺ ስራ ነው፡፡ ይህ ሲባል ግን ሌሎች ቅፁን በመሙላት
አያግዙህም/ሽም ማለት አይደለም፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን በስተመጨረሻ ሃላፊነቱን የምትወስደው/ጂው አንተ/ቺ፡፡ ነህ/ሽ፡፡

ይህ ማለት ግን አሁንም ቢሆን የት/ቤት ሞጁል ማዘጋጆችን ጨምሮ ሁሉንም ነገር አንተ/ቺ ብቻ መስራት አለብህ/ሽ ማለት አይደለም፡፡

የሚከተሉት ጉዳዮች በትክክል መከናውናቸውን እርግጠኛ ለመሆን ከሌሎች ጋር መስራት ይጠቅምሀል/ሻል፡


 ትክክለኛ የት/ቤት ሞጁል ትግበራ መዘጋጀቱን፣
 የት/ቤት ሞጁል በትክክል ስራ ላይ መዋሉን፣

28
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
 ትክክለኛና ተፈላጊ የሰው ሀይል በት/ቤት ሞጁሉ ላይ መሳተፋቸውን፣
 የተገኘው ውጤት ከታቀደው ጋር የተጣጣመ መሆኑን፡፡

የት/ቤት ሞጁልን የማቀናጀት ሀላፊነት የማን ነው?


ይህ ጥያቄ “የት/ቤት ሞጁልን ለማዘጋጀት የማን እገዛ ያስፈልገኛል?” ለሚለው ምላሽ የሚሰጥ ነው፡፡

የሚከተሉትን ጠይቅ/ቂ የት/ቤት ሞጁል እቅድን ለማቀናጀት ሀላፊነት የሚሰጣቸው የስራ ባልደረቦች

ከት/ቤቱ አመታዊ የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ዕቅድ ውስጥ የት/ቤቱን ፍላጎት በቅደም ተከተል የለዩትን አባላት፣
ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ ሁሉንም መምህራን የሚያሳትፍ
 ሁሉንም የቡድን አባላት ትፈልጋቸዋለህ/ጊያቸዋለሽ?
ነው?
 የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ አስተባባሪውና ኮሚቴው ግን የግድ መሣተፍ አለባቸው፡፡
አዎ
አይደለም

ከት/ቤት አመታዊ እቅድ ላይ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ አስተባባሪውና ኮሚቴው አስፈላጊዎች ናቸው፡፡
የተወሰኑ መምህራንን ብቻ የሚያሳትፍ ነው?
በተመረጠው የት/ቤት ሞጁል እቅድ ላይ ሌሎች በሙያው የተካኑና የበለጠ ልምድ ያላቸውን የሥራ
አዎ  ባልደረባዎች በተጋባዥነት ማሳተፍ ትፈልጋለህ/ጊያለሽ ?
የት/ቤት ሞጁል ዝግጅት አመራርን ወይም አመራሮችን በማቀናጀት ስራም ላይ ማሳተፍ ተመራጭ
አይደለም
ስልት ነው፡፡

ከት/ቤት አመታዊ የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ እቅድ ላይ ምንም እንኳን የሌሎች እገዛ ቢያስፈልግህም/ሽም የራስህን/ሽን አመታዊ ሞጁል እቅድ የማቀናጀት
ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ አንድን ግለሰብ ብቻ የሚያሳትፍ ሀላፊነት የራስህ/ሽ ይሆናል፡፡
ነው?
እገዛ ሊሰጥህ/ሽ የሚችለውን በራስህ/ሽ ወስን/ኚ፡፡ ማን ሊሆን ይችላል?
አዎ
 የራስ አቻ?
 ልምድ ያካበተ/ች የስራ ባልደረባ?
 አማካሪህ/ሽ?
አይደለም
 ወይስ የተሙማ አስተባባሪው/ዋ?

ተመራጭ ነው የምትለውን /ይውን/ ወስን/ኝ፣
የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ሞጁል የዕቅድ ማዘጋጃ ቅፅ

የት/ቤቱ ወይም የግሰቡ/ቧ ስም ……………………………………………………

የት/ቤቱን የሞጁል ዕቅድ ለማዘጋጀት ሃላፊነቱን የወሰደው/ችው ሰው ስም ..............................

1. የት/ቤት ሞጁል ርዕስ (ቅድሚያ የተሰጠው … ሌላም ……


የተሙ.ማ ጉዳይ) ሌላም ………
2. ምን ለውጥ ማየት ትሻለህ/ሽ? ሌላም …….
3. ተሳታፊዎች
4. አመራር(አመራሮች)
5. ለት/ቤት ሞጁል የተመደበ ጊዜ
6. የሚጀመርበት እና የሚጠናቀቅበት ቀን
7. ቦታ
8. የሚያስፈልጉ
በኢትዮጵያ ግብአቶች
የመጀመሪያ 29
ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
9. የክ/ጊዜው
ተከታታይ ሙያአይነት 10. የክ/ቋት
ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ጊዜው አላማ 11. የሚፈጀው ጊዜ
- -
ክፍል ጊዜ አንድ

ክፍለ ጊዜ ሁለት
ከላይ የዘረዘርናቸውን እያንዳንዳቸውን በዝርዝር በማየት እንዴት የት/ቤት ሞጁል ዕቅድን ማጠናቀቅ እንደምንችል እንረዳለን፡፡

1. የት/ቤት ሞጁል ርዕስ (ቅድሚያ የተሰጠው


የተ.ሙ.ማ ጉዳይ)

የት/ቤት ሞጁል ርዕስ በት/ቤትም ይሁን በግል ከተሰሩት አመታዊ የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ዕቅድ ውስጥ ቅድሚያ ከተሰጣቸው ጉዳዮች
አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡

2. ምን ለውጥ ማየት ትሻለህ/ሽያለሽ?

ይህ ቀደም ተብሎ በግል ወይም በት/ቤት አመታዊ የተከታታይ የሙያ ማሻያ ዕቅድ ላይ ያሰፈርነው ነው፡፡.

3. ተሳታፊዎች

ይህም የት/ቤት ወይም የግል አመታዊ የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ዕቅድ ሲወጣ የተካተተ ጉዳይ ነው፡፡
 በዕቅዱ ላይ ሊሳተፍ የሚገባው በትክክል ተለይቷል?
 ብዥታ የሚፈጥር ጉዳይ አለ?
 ማንኛውም ሰው “…. እኔ አለሁበት ወይስ የለሁበትም?” ብሎ ሊጠይቅ አይገባም፡፡

የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ስራ የሚካሔደው በአብዛኛው በጋራ በሚሰሩ የስራ ባልደረቦች ነው፡፡ የተሳካ የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ
የሚባለውም ይህ አይነቱ ነው፡፡ የግል የተከታታይ የሙያ ማሻሻያም ቢሆን ከባልደረቦች ጋር በጋራ የተሰራ ቢሆን በእጅጉ ተመራጭ ነው፡፡

አስፈላጊ ከሆነም የተሳታፊዎችን ስም ዝርዝር መፃፍም ይቻላል፡፡

የቡድን አባላቱ በትክክል የታወቁና የተለዩ ከሆነ የቡድኑን ስም ብቻ መፃፍም በቂ ነው፡፡ ለምሳሌ ያክል በመጀመሪያ ሳይክል ሂሳብ
ከሚያስተምሩ የአንዱን ስም ብቻ ወይም የአንድ ፕላዝማ ክ/ጊዜ ሊያስተምር የተዘጋጀውን የአንዱን ስም ብቻ መፃፍ ይቻላል፡፡ ይህም
ማለት የቡድኑን አባላት ስም በሙሉ መፃፍ ላያስፈልግ ይችላል ማለት ነው፡፡

የተሳታፊዎችን የስም ዝርዝር በትክክል መለየት ምን ያክል ሰው ሊሳተፍ እንደሚችልም ለማወቅ ይረዳል፡፡ የተሳታፊዎች ብዛት
የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ አይነቱን እንዴት መቀናጀት አለበት የሚለውንም ለመወሰን ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

ብዙ ተሳታፊዎች ካሉ በዛ ያለ አቅርቦትና ሰፋ ያለ ቦታም ይጠይቃል፡፡

4. አመራር (አመራሮች)

የት/ቤት ሞጁል ዝግጅት መሪው ሞጁሉን በማቀናጀት ላይም ተሳታፊ ሊሆን ይችላል፡፡ መሪው ከአንድ በላይ ሊሆን ይችላል፡፡ በመሆኑም
ተሳታፊዎቹ ቅድሚያ በተሰጠው ፍላጎት ላይ ተፈላጊው እውቀት፣ ክህሎትና ልምድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ለምሳሌ:-
 የሒሳብ ትምህርት አመራር በመጀመሪያ ሳይክል የሒሳብ ማስተማር ስልት ማሻሻልን መሠረት አድርጐ የተዘጋጀ የት/ቤት
ሞጁልን ሊመራ ይችላል፡፡

30
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
 የካበተ ልምድና ክህሎት ያለው መምህር በክፍል ውስጥ ያለን ባህርይ በማሻሻል ላይ የታቀደን የተከታታይ የሙያ ማሻሻያን ሊመራ
ይችላል፡፡
የሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መሪ ወይም አመራሮችን ለመምረጥ ያግዛሉ፡፡ አንድ ላይ በጋራ የሚሰሩ ሁለት ወይም ሦስት ሠዎችን
በአመራርነት መምረጥ ተገቢ የሚሆንበትም ጊዜ አለ፡፡ ይህን ለማድረግ የት/ቤት ሞጁል ርዕሱንና ልናየው የምንፈለገውን ለውጥ ከግምት
ውስጥ ማስገባትም ጠቃሚ ነው፡፡

የሚከተሉትን ሁሉ ሊያሟላ የሚችል የሥራ ባልደረባ አለን?


 በተፈለገው ጉዳይ ላይ በቂ ዕውቀት ወይም ክህሎት ያለው/ላት
 ይህንን አይነት ስነ ዘዴ ተግባራዊ የማድረግ ክህሎት ያለው/ላት
 ከዚህ በፊት የተካሄዱ መሰል ስልጠናዎችን በተሳካ ሁኔታ የመራ/ች
 የተከታታይ የሙያ ማሻሻያን በመምራት ሙያውን የበለጠ ለማሳደግ ፍላጎት ያለው/ላት
 የት/ቤት ሞጁሉን ለማጠናቀቅ ተነሳሽ የሆነ/ች
 በራሱ የሚተማመንና ሌሎችን የሚያከብር/ምታከብር
 የአመራር ብቃት አለው/አላት ተብሎ ታምኖበት/ባት የተመረጠ/ች
አመራሩ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሙሉ የግድ የሚያሟላ መሆን አይጠበቅበትም/ባትም፡፡ ያምሆኖ ግን ምርጫው ላይ
ጥንቃቄ ማድረግ ይጠይቃል፡፡

ከምናባዊ ት/ቤት የተወሰደ ምሳሌ

ትምህርት ቤት
የመሪው ስም “ሰለሞን ደስታው”፣ የመጀመሪያ ሳይክል የአማርኛና የእንግሊዝኛ ቋንቋ
መምህር ውስጥ የት/ቤት
ሞጁሉን በትክክል
መስፈርት  ወይም 
ሊመራ የሚችል ሰው
በተፈለገው ጉዳይ ላይ በቂ እውቀት ወይም ክህሎት ያለው፡፡ 
ካልተገኘ ወይም
X የሌሎችን እገዛ
ከዚህ በፊት መሰል ስልጠናዎች በተሳካ ሁኔታ የሰጠ፣

የት/ቤት ተሙ.ማ ሞጁልን በመምራት ሙያዊ ክህሎትን ለማሳደግ ፍላጐት ያለው፣  ይፈልጋል ተብሎ

 ከተገመተ የወረዳ
የት/ቤት ሞጁልን ለማጠናቀቅ ተነሳሽነት ያለው፣
ወይም የጉድኝት
በራሱ የሚተማመንና ሌሎችን የሚያከብር፣ 
ማዕከል ሱፐርቫይዘር
x
የአመራር ብቃት አለው ተብሎ ታምኖበት የተመረጠ
ወይም የመምህራን
ይህንን አይነት ስነ ዘዴ ተግባራዊ የማድረግ ክህሎት ያለው  ማሰልጠኛ ኮሌጅ
አሰልጣኝን እገዛ መጠየቅ ተመራጭ ነው፡፡

5. የት/ቤት ሞጁል የሚፈጀው ጊዜ


31
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
የት/ቤት ሞጁል የቆይታ ጊዜ የሚወሰነው በሞጁል ውስጥ ቅድሚያ በተሰጠው ጉዳይ ርዕስ ምንነት ነው፡፡

ጊዜ የመመደቡ ስራ አስቸጋሪ ነው፡፡ ጊዜውን ለመወሰን የሚያስችልና በጋራ የሚያስማማ ቀመር ወይም ስልት የለም፡፡ ይህ
ጉዳይ አንዳንዴ የሌሎችንም እገዛ ሊፈልግ ይችላል፡፡

የትምህርት ቤት ሞጁሉ ጊዜ ወደስራው ከተገባም በኋላ እንደየአስፈላጊነቱ ሊሻሻልና ማስተካከያ ሊደረግበት ይችላል፡፡

ሞጁል የሚፈጀውን ጊዜ ለመወሰን ራስህን/ሽን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ/ቂ፡፡

 ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ ለግለሰቡ ወይም ለት/ቤቱ አዲስ ነገር ነውን?

 በተመረጠው ጉዳይ ላይ ተሳታፊዎች በየጊዜው የተግባር ልምምድ ያስፈልጋቸዋል?

 በተመረጠው ርዕስ ዙሪያ ተሳታፊዎች የተግባራዊ ምርምር የሚሰሩበት ወይም ሌሎች ት/ቤቶችን የሚጎበኙበት ጊዜ
ያስፈልጋቸዋል?

 የተመረጠው ጉዳይ ለትምህርት ቤቱ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገዋል?

ከምናባዊ ት/ቤቱ የተወሰደ ትክክለኛ የጊዜ ሰሌዳ ምሳሌ

የት/ቤት ምጁል ርዕስ ክ/ጊዜያት የሚፈጀው ጊዜ


በት/ቤት ውስጥ ተሳትፏዊ  የመምህራን ስብሰባ 1 ሰዓት
መማርን ማጎልበት  የት/ቤት ጉብኝት 5 ሰዓቶች
 የግምገማ ስብሰባ 1 ሰዓት
 የአቻ እቅድ፣ የክፍል ውስጥ ምልከታ እና ግብረመልስ 12 ሰዓቶች
 የመምሀራን ስብሰባ 1 ሰዓት
 ፖርትፎሊዮን ማጠናቀቅ 2 ሰዓቶች

ለአዲስ ጀማሪ መምህራን  የጉድኝት ማዕከል ስብሰባ 1 ሰዓት


አማካሪ መምህራንን ማፍራት  በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውንና “ተግባራዊ 18 ሰዓቶች
የማማከር ክህሎት” የተሰኘውን ሰነድ ከጉድኝት
ማዕከል አባላት ጋር መጠቀም 1 ሰዓት
 ፖርትፎሊዮን ማጠናቀቅ

የሒሳብ ትምህርትን  የመምህራን ስብስባ 1 ሰዓት


በመጀመሪያ ሳይክል ማሻሻል  በባለሙያ የሚመራ የአንድ ቀን ስልጠና 5 ሰዓቶች
 የሰርቶ ማሳያ ክ/ጊዜ 2 ሰዓቶች
 በራስ ክ/ጊዜ ልምምድ ማድረግ 10 ሰዓቶች
 ከአቻ መምህር ጋር ግምገማ ማካሄድ 1 ሰዓት
 ፖርትፎሊዮን ማጠናቀቅ 1 ሰዓት

6. የሚጀመርበት እና የሚጠናቀቅበት ቀን

ይህ በአመታዊ የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ዕቅድ ላይ በቅድሚያ የተወሰነ ነው፡፡


32
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
7. ቦታ

የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ የሚካሔድበትን ቦታ መምረጥ አስፈላጊ ነው፡፡ አንዳንዴ እዚያው ት/ቤት ውስጥ የአቻ የክፍል
ውስጥ ምልከታ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ ሌላ ት/ቤት በመሄድ ጉብኝት ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

በመሆኑም የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ትግበራው የሚካሄድበትን ቦታ በቅድሚያ መወሰን ተገቢ ነው፡፡ በት/ቤት ውስጥ፣ ሌላ
ት/ቤት ወይም ሌላ ቦታ፣ የጉድኝት ማዕከል የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ የመሳሰሉትን ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ተገቢ ነው፡፡

8. የሚያስፈልጉ ግብአቶች

ግብአቶቹ ለት/ቤት ሞጁሉ ተገቢና አስፈላጊ እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር ት/ቤቱ ባለው የበጀት አቅም ሊከናወኑ የሚችሉ መሆን
ይጠበቅባቸዋል፡፡ ግብአት ሲባል የሰው ሀይል እና ማቴሪያል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ማን ሊረዳህ/ሽ ይችላል?

የት/ቤት ሞጁል በማጠናቀቅ ተግባር ላይ ሊረዱህ/ሽ የሚችሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ በጣም አስፈላጊ የሚባሉት የሚገኙት ደግሞ
በዚያው በት/ቤት ውስጥ በተደጋጋሚ የምታገኛቸው/ኚያቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ፡-

 አቻዎችህ/ሽ
 ብዙ ያገለገሉና ልምድ ያላቸው የሥራ ባልደረቦች፣
 በጉድኝት ማዕከላት፣ በቀበሌና በወረዳ የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች ወዘተ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ከነዚህም በተጨማሪ

 በሌላ ት/ቤት የሚገኙ መምህራን


 የወረዳና የክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያዎች
 በመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ያሉ ባለሙያዎች
 የዩኒቨርሲቲ ምሁራን
 የትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎች
 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አባላት
 የማህበረሰቡ አባላት

ሌላ ምን ልትጠቀም/ሚ ትችላለህ/ያለሽ?
የምትጠቀማቸው/ሚያቸው መሣሪያዎች የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል
 ከትምህርት ሚኒስቴር የሚገኙ አጋዥ ማቴሪያሎች
 ከትምህርት ቢሮ “ “ “

33
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
 ሙያዊ ፅሁፎች
 ከመረጃ መረብ የሚገኙ መረጃዎች
ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ያስፈልጉኛል የምትላቸውን/ያቸውን ነገር ግን በት/ቤት ውስጥ ልታገኛቸው/ኚው
የማትችላቸውን/ችይውን ማቴሪያሎችንም በዝርዝር መያዝ ይጠበቅብሀል/ሻል፡፡ ለምሳሌ፡- የማስታወሻ ደብተር፣
እስክሪፕቶዎች፣ ሀገር አቀፍ ወይም በክልል ደረጃ የተዘጋጀ ሞጁል፣ የፎቶ ኮፒ ማሽን ወዘተ…

ስለተከታታይ የሙያ ማሻሻያ አጋዥ ማቴሪያሎችን ተጨማሪ መረጃ “የኢትዮጵያ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
መምሀራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች የተሙማ - ማእቀፍ (frame work)” የተባለ ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

አሁን ቅድሚያ ከሰጠሀቸው/ሻቸው ጉዳዮችህ/ሽ መካከል አንዱን በመውሰድ ከላይ ያየናቸውን ደረጃዎች በመጥቀስ ሞጁል
አዘጋጅ/ጂ

ከምናባዊ ትምህርት ቤቱ የተወሰደ ምሳሌ

የት/ቤት ሞጁል እቅድ ምናባዊ ት/ቤት


1. የት/ቤት ሞጁል ርዕስ (የተመረጠው ተሳትፏዊ ትምህርትን በት/ቤት ውስጥ ማጎልበት
ተ.ሙ.ማ ጉዳይ)
2. ምን ለውጥ ማየት ትሻለህ/ሽ?  የብዙ ተማሪዎች የክፍል ውስጥ ተሳትፎ መጨመር
 በሁሉም ክፍሎች ውስጥ የተማሪዎች የፈተና ውጤት መሻሻል
 የተማሪዎች በተለይም የወንድ ተማሪዎች ባህርይ ሥነ-ምግባር
መሻሻል
3. ተሳታፊዎች ሁሉም መምህራን
4. አመራር(አመራሮች) አስተባባሪ አቶ ሀሰን
(አስተባባሪዎች)
5. ለት/ቤት ሞጁል የተመደበው ጊዜ 20 ሰዓቶች
6. የሚጀመርበት እና የሚጠናቀቅበት ቀን ከአንደኛው ሰሚስተር መጀመሪያ እስከ ሁለተኛው ሰሚስተር
መጨረሻ
7. ቦታ በራስ ት/ቤት፣ በአንድ የጉድኝት ማዕከል ት/ቤት
8. የሚያስፈልጉ ግብአቶች  2 እሽግ A4 ወረቀት
 ፎቶ ኮፒ የተደረጉ ማቴሪያሎች
 በተሳትፏዊ ትምህርት ዙሪያ የተዘጋጁ ሀገር አቀፍ ሞጁሎች
 ወደ ጉድኝት ማዕከል መሄጃ ትራንስፖርት
 ካሜራ
 የክፍል ምልከታ ቅፅ
 መርጃ መሣሪያ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች

ከምናባዊ ት/ቤቱ የተወሰደ ምሳሌ

የግል ሞጁል ዕቅድ ስላስ መኮንን

34
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
1. የመምህሩ የግል ሞጁል ርዕስ (ቅድሚያ ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸውን ተማሪዎች የማስተማር ዘዴ
የተሰጠው የተ.ሙ.ማ ጉዳይ) ማሻሻል

2. ምን ለውጥ ማየት ትሻለህ/ሽ?  የተማሪዎችን ፍላጎት የሚያሟሉ መፅሀፍት መኖር


 የተማሪዎች ተሳትፎ በሁሉም ክ/ጊዜ መታየት
3. ተሳታፊዎች ስላስ መኮንንና መሠረት ተክሉ

4. አመራር(አመራሮች) የልዩ ፍላጎት ት/ክፍል ሀላፊ

5. ለመምህሩ ሞጁል የተመደበ ጊዜ 20 ሰዓቶች

6. የሚጀምርበትና የሚጠናቀቅበት ቀን ከሁለተኛ ሴሚስተር መጀመሪያ እስከ መጨረሻ

7. ቦታ በት/ቤት ውስጥ

8. አስፈላጊ ግብአቶች  ወደብሬይል የተለወጡ የ 7 ኛ ክፍል መፅሀፍት


 የክፍል ምልከታ ቅፅ
 መረጃ መሣሪያ ለማዘጋጀት የሚረዱ ማቴሪያሎች

 ከላይ የተጠቀምንባቸውን መሠረት በማድረግ የት/ቤት ወይም የግል ሞጁል እቅድ አጠናቀህ/ሽ ሙላ/ይ፡፡

የዚህን እቅድ ማዘጋጃ ቅፅ በአባሪው ውሰጥ ታገኛለህ/ሽ፡፡

አሁን ወደ ቀጣዩ የት/ቤት የሞጁል ክፍል!


እስካሁን ድረስ በመጠኑ ቀላል የሚባለውን ሰርተሃል/ሻል፡፡ አስቸጋሪ የሚባለው ክፍል ደግሞ የት/ቤት ሞጁልን ራሱን መፍጠር
ወይም ማዘጋጀት ነው፡፡

የሞጁል ዝግጅት ቡድኑ የሚጠቀምበትን የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ስነ-ዘዴ፣ (methodology) ክፍለ ጊዜና (session)
ተግባራት (activities) መወሰን ይጠበቅበታል፡፡

ስነ-ዘዴ (methods) የምንላቸው ምንድን ናቸው?

ስነ ዘዴዎች የምንላቸው የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሂደቱን ለማከናወን የምንጠቀምባቸው ስልቶች ማለታችን ሲሆን በቀጥታ ከመማሪያ
ክፍሎች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ የተለያዩ ዘዴዎች ለተለያዩ አላማዎች የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

የት/ቤት ሞጁልን ስናቀናጅ የሚከተሉትን ስነ ዘዴዎች ልንጠቀም እንችላለን፡፡


 በስርአተ ትምህርት ዙሪያ የሚካሄዱ  ተግባራዊ ምርምር
ስብሰባዎች  ሌሎች ት/ቤቶችንም ሆነ መምህራንን
 የሰርቶ ማሳያ የት/ት አሰጣጥ ዘዴ በመጎብኘት ልምድ ማግኘት፣
35
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
 ትምህርታዊ ዝግጅትን በጋራ ማቀድ  የራስህን/ሽን ልምድ በት/ቤት ውስጥ
 የአቻ የክፍል ምልከታ ማካፈል፣
 የክፍል ምልከታ እና ግብረመልስ  ፖርትፎሊዮን በትክክል መያዝ

 ተማሪዎችን በትምህርት ገበታ ላይ  የቡድን ማስተማር


መመልከት  አውደጥናቶች
 ከተማሪዎች ጋር መወያየት  ባለሙያዎችን ማወያየት
 ከተግባር በፊትም ሆነ በኋላ የተማሪዎችን  የማማከር ዘዴ
ሁኔታ መገምገም  የውይይት መድረኮች
 የተማሪዎችን ስራዎች ማረም፣ ግብረመልስ  ሙያዊ ንባብና ጥናት
መስጠትና ማሻሻል ያለባቸውን አካባቢ
መጠቆም
 የሞዴል መምህራንን ፈለግ መከተል

ክ/ጊዜ (session) ምንድን ነው?


ክ/ጊዜ የምንለው በሞጁል ውስጥ ያካተትናቸው የተለያዩ ሰነ-ዘዴዎች በተ.ሙ.ማ እንዴት እንደምንጠቀምባቸው የሚገልፅ
ነው፡፡ የራሱ የሆነ አላማ እና የጊዜ ሰሌዳ ያለው ሲሆን ተከታታይነት ባላቸው ተግባራት የተገነባ ነው፡፡ እያንዳንዱ ክ/ጊዜ
የቀጣዩን የትምህርት ሂደት አመልካች ነው፡፡
ተግባር ምንድን ነው?
ተግባራት የምንላቸው የክ/ጊዜ አነስተኛ ክፍሎች ሲሆኑ የክ/ጊዜውን መዋቅር የሚያሳዩ ናቸው፡፡ የተለያዩ ተግባራት ለተለያዩ
አላማዎች ይውላሉ፡፡
የት/ቤት ሞጁል ለማዘጋጀት ሲፈለግ የሚከተሉትን ቁልፍ ነጥቦች ከግምት ውስጥ ማስገባት ተገቢ ነው፡-
 በት/ቤት ሞጁል ውስጥ የምናካትታቸው ክ/ጊዜያት በሙሉ ከክፍል ውስጥ ትምህርት ጋር የተገናኙ መሆን አለባቸው፡፡
 በት/ቤት ሞጁሉ ውስጥ የተለያዩ ስነ ዘዴዎችን ማካተት ይገባል፡፡
 የተሳታፊዎች ብዛት የምንጠቀምባቸው ዘዴዎች ምርጫ ላይ ተፅእኖ አላቸው፡፡
 በምናቀርበው ጉዳይ ላይ አዲስ ሀሳብ ወይም መረጃ ካለ ከት/ቤት ውጭ ያሉ ባለሙያዎችን ማማከር አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡
 ክ/ጊዜያት አሳታፊ የመማር ዘዴን ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 አንዳንድ ክ/ጊዜያት ተሳታፊዎችን በጋራ እንዲሰሩ የሚያደርጉ መሆን አለባቸው፡፡
 የት/ቤት ሞጁል ሲዘጋጅ ለግብረመልስ እና ለክ/ጊዜ ክለሳ የሚሆን ጊዜ መመደብ፡፡ አስፈላጊ ነው፡፡

“በኢትዮጵያ ለመጀመሪያና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች የተ.ሙ.ማ-ማዕቀፍ”


የተሰኘው ሰነድ ስለ ስነ ዘዴዎች የራሱ የሆነ ክፍል ስላለው መመልከት ይቻላል፡፡

ለአጠቃላይ መረጃ ያህል:

36
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
አንድን ፍላጎት በትክክል ሊያሳካ የሚችል ብቸኛ መንገድ የለም፡፡ የምንመርጣቸው የት/ቤት ሞጁሎችና ዘዴዎች ለታስበው ፍላጎት፣
አውድ፣ ሁኔታና ግብአት ምቹ የሆኑት ናቸው፡፡

37
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ከዚህ በታች ከምናባዊ ት/ቤት የተወሰዱ የት/ቤት ሞጁል ምሳሌዎች ይገኛሉ

የት/ቤት ሞጁል ክፍለ


ጊዜ ምሳሌ
በክትትል ተግባራት በተማሪዎች ላይ የሚታዩ የስነ ምግባር ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ስብሰባዎችን የምናባዊ ት/ቤት
የተደገፉና ተከታታይነት ር/መምህር በየወሩ ለሁሉም መምህራን ያዘጋጃል፡፡ በእያንዳንዱ ስብሰባ ላይ ተሳታፊዎች ስለሚወሰዱ
ያላቸው አጫጭር እርምጃዎችና ለውጦች ይስማማሉ፡፡ እስከሚቀጥለው ስብሰባ ድረስ ይህንን በተግባር ሲያውሉና ሲለማመዱ
ስብሰባዎችን ረዘም ላለ ቆይተው በቀጣዩ ስብሰባ በጋራ ውጤታማነቱን ይገመግማሉ፡፡ ለ 8 ጊዜያት ለ 1 ሰዓት የሚቆይ የአጠቃላይ ስብሰባ
ጊዜ ማዘጋጀት፡፡ ለ 8 ሰዓት ደግሞ በተግባር እየታየ ባጠቃላይ ለ 16 ሰዓት ይካሄዳል፡፡

ተማሪዎች በሌሉበትና የምናባዊ ት/ቤት መምህራን ፖርትፎሊዮ እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ይስማማሉ፡፡ የተ.ሙ.ማ አስተባባሪው
በተግባራዊ ልምምድ እና ሁሉም መምህራን ተገናኝተውና ፖርትፎሊዮን በማስመልከት ፖሊሲው ምን እንደሚል የሚወያዩበት አንድ ቀን
ግምገማ የታገዘ ያመቻቻል፡፡ ከዚህ ስብሰባ በኋላ የተሙ.ማ አስተባባሪው ከየትምህርት ክፍል ሃላፊዎችና ከአማካሪ መምህራን ጋር
ለ 5 ሰዓታት የሚቆይ የ 1 በመሆን መምህራን ይህንን እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጉት ክትትል ያደርጋል፡፡ በትምህርት ዘመኑ መጨረሻ
ቀን የተ.ሙ.ማ ጊዜ፣ ሁሉም መምህራን ተገናኝተው ልምድ ይለዋወጣሉ፣ ስለ ፖሊሲውም በመነጋገር ይገመግማሉ፡፡ (1 ቀን
ለ 5 ሰዓታት ያክል፣ 10 ሰአታት ስለ ፖርትፎሊዮ አደረጃጀት፣ 1 ሰዓት በአመቱ መጨረሻ የክለሳ ስብሰባ ባጠቃላይ
16 ሰዓታት)

ለክትትል እና ግምገማ የቡድን ስራን ማጎልበት ለ 2 ኛ ሳይክል መምህራን የቅድሚያ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ አንዲት የሳይንስ
በሚያስችሉ ተግባራት መምህርት የቡድን ስራን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በክረምት የስራ ላይ ስልጠና ልዩ ኮርስ ከመውሰዷም በላይ
የተደገፈ የአንድ ቀን በክፍል ውስጥ ተግባራዊ በማድረግም የተመሠከረላት ናት፡፡ በዚህም መሠረት መምህርቷ የቡድን ስራን የማስተማር
አውደጥናት፣ ቴክኒክን አስመልክቶ የ 1 ቀን አውደጥናት ትሰጣለች፡፡ ከዚያም መምህራን ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር ጥምረት
በመፍጠር በዚህ ጉዳይ ላይ ያቅዳሉ፣ የክፍል ውስጥ ልምምድም ያደርጋሉ፤ ሀሳብም ይለዋወጣሉ፡፡ በየሰሚስተሩ
መጨረሻም ሁሉም መምህራን በመገናኘት ልምድ ይለዋወጣሉ፡፡ (1 ቀን ለ 5 ሰዓት፣ ከሙያባልደረባ ጋር የጥምረት
ስራ ለ 8 ሰአታት፣ የልምድ ልውውጥ ሰብሰባ ለ 2 ሰዓታት ባጠቃላይ 15 ሰአታት)

የት/ቤት ሞጁል ክፍለ-


ጊዜ ምሳሌ
የ 1 ኛ ሳይክል መምህራን አሀዳዊ ትምህርትን እንዴት ማዳበር እንዳለባቸው እገዛ ይፈልጋሉ፡፡ የጉድኝት ማዕከሉ
በየመሀሉ ተግባራዊ ሱፐርቫይዘር የተወሰኑ ባለሙያዎች ለእገዛ አዘጋጅቷል፡፡ መምህራኑ ለ 1 ቀን ያክል አውደጥናት ከተከታተሉ በኋላ
ልምምድ የሚካሄድባቸው የተማሩትን በየክፍላቸው በሚሰጣቸው ተጨማሪ ተግባራት በመታገዝ ይተገብራሉ፡፡ ከ 1 ወር በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ
የሦስት ቀናት አውደጥናት አውደጥናት ይካፈላሉ፡፡ የልምድ ልውውጥ በማድረግም የበለጠ ይማራሉ፡፡ ከዚያም እንደገና በክፍል ውስጥ
ልምምድ ያደርጋሉ፡፡ይህ ሂደት ለልምምድ ሰፊ ጊዜ በመስጠት ለሦስተኛ ጊዜ ይደገማል፡፡ በዚህም አዳዲስ ነገሮችን
ይማራሉ፡፡ ( 5 ሰአታት ለ 3 ቀናት፣ 4 ሰአታትን የሚፈጅ ተግባራዊ ስራ ላይ ያተኮረ አውደጥናት 1 ሰአት

38
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ፖርትፎሊዮ ማጠናቀሪያ፣ ባጠቃላይ 20 ሰአታት)

የተለያዩ ጉዳዮችን የያዙና የምናባዊ ት/ቤቱ ቤተመፅሀፍቱን ማሳደግ እንደ አንድ የትምህርት ቤት መሻሻል እቅድ አድርጎ ይዟል፡፡ ይህ ጉዳይ
ረዘም ያለ ጊዜ የሚቆዩ እንዴት መቀጠል እንዳለበት መምህራን ስብሰባ አላቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በትኩረት የሚሳተፉት አንዳንድ
አጫጭር ክፍለጊዜያት መምህራን ለዚህ ነገር ከሚያውሉት ሰአት ውስጥ የተወሰነው ወደ ግል ተ.ሙ.ማ እንዲቆጠርላቸው ይፈልጋሉ፤
አንዳንዶቹ ሌላ ት/ቤትን ሄደው ይጎበኛሉ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ እዚያው ያሉትን መፅሀፍት ይጠቀማሉ፡፡ ሁሉም
አንድ ላይ እየተገናኙ የልምድ ልውውጥ በማካሄድና ሪፖርት በመፃፍ ቤተመፅሀፍትን መጠቀም በተማሪዎች ውጤት
ላይ ያለውን ተፅእኖ በጋራ ይገመግማሉ፡፡ ከነዚህ ቡድኖች የሚገኘው ጠቃሚ መረጃ በምክትል ርዕሰ መምህሩ
አማካኝነት ይሰበሰባል፡፡ (የሚመደበው ሰዓት እንደ መምህሩ ሁኔታ የሚወሰን ነው)

አሁን የተቀሩትን የተ.ሙ.ማ ሞጁል እቅድ በመጠቀም ለማንም በሚገባ መልኩ የራስህን /ሽን የክፍለ-ጊዜ እቅድ ማስቀመጥ
ይጠበቅብሀል/ሻል
.9. የክፍለ-ጊዜው አይነት 10. የክፍለ ጊዜው አላማ 11. የሚፈጀው ጊዜ

ከምናባዊ ት/ቤት የተወሰደ ምሳሌ ከዚህ ቀጥሎ ይቀርባል፡፡

አሳታፊ መማርን በት/ቤቱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማስረፅ የተዘጋጀ የት/ቤት ሞጁል

9. የክፍለ ጊዜው አይነት 10. የክፍለጊዜው አላማ 11. የሚፈጀው


ጊዜ
የመምህራን ስብሰባ አሳታፊ ትምህርት በሁሉም ክፍሎች ውስጥ ያሉ 1 ሰዓት
ተማሪዎችን ውጤት እንዴት እንደሚያሻሽል
የሚያሳየውን ሞጁል ለማስተዋወቅና ስምምነት ላይ
ለመድረስ
የሌላ ት/ቤት ጉብኝት መልካም ተሞክሮን ለመለዋወጥ 5 ሰአታት

የፍተሻ ስብሰባ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በመነጋገርና ልምድ በመለዋወጥ 1 ሰአት


በክፍል ውስጥ መተግበር የሚያስችሉ ስልቶች ላይ
ለመስማማት፣
ከአቻ ጋር በጋራ ማቀድ፣ የክፍል በፍተሻ ስብሰባው ጊዜ መስማማት በተደረሰባቸው 12 ሰአታት
ምልከታና ግብረ መልስ ስልቶች ተግባራዊ ልምምድ ለማድረግ እና እርስ በርስ
መስጠት በመተጋገዝ የክፍል ውስጥ ምልከታዎችን በትክክል
ማስታወሻ ለመያዝና በፖርትፎሊዮ ውስጥ ለማካተት፣
የመምህራን ስብሰባ የልምድ ልውውጥ ለማድረግና ውጤታማነቱን 1 ሰአት
ለማብሰር

39
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ሙያዊ ፖርትፎሊዮን የራስን ልምድ ለማንፀባረቅ፣ በተማሪዎች መማር ላይ 2 ሰአታት
ማጠናቀር ያለውን ተፅፅኖ ለመመዝገብና የወደፊቱንም ለማቀድ

. 
አሁን ለት/ቤትህ አንድ የት/ቤት ሞጁል እቅድን በትክክል አጠናቅ/ቂ፡፡

የዚህን ዕቅድ ማዘጋጃ ቅጽ በአባሪ ውስጥ ታገኛለህ/ሽ፡፡

የት/ቤትን ሞጁል መቅረፅ ቤት እንደመገንባት መሆኑን ማስተዋል ይገባል፡፡ ቤት ደረጃውን ተከትሎ መሰረት፣ ግድግዳ፣ ጣሪያ
ወዘተ ተብሎ ይገነባል፡፡ ልክ እንደቤቱ ሁሉ እያንዳንዱ የተ.ሙ.ማ ተግባር የመጨረሻ ግብን ለማሳካት የምንከተላቸው የግንባታ
ደረጃዎች ናቸው፡፡

ከምናባዊ ት/ቤቱ የተወሰደ የግል ሞጁል እቅድ ምሳሌ

ስላስ መኮንን፡- የልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን የማስተማር ስልት ማሻሻል

9. የክ/ጊዜው አይነት 10. የክፍለ ጊዜው አላማ 11. የሚፈጀው


ጊዜ
ከመሠረት እና ከልዩ ፍላጎት ምን አይነት የተግባር ትምህርቶች ሊረዱን 1 ሰዓት
ትምህርት ክፍል ሀላፊው ጋር እንደሚችሉ እና ያለንን ጊዜ እንዴት መጠቀም
የሚደረግ ስብሰባ፣ እንዳለበን ለመወሰን
የትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት መጠቀም ስለሚገባን ግብአቶችና ለየት ያሉ ሙያዊ 4 ሰአታት
ባለሙያዎችን ማማከር፣ እውቀትና ምክር ለማግኘት
የማስተማሪያ ግብአቶችን ለየት ያሉ የመማር ፍላጎቶችን ማሟላት የሚያስችሉ 5 ሰአታት
ማዘጋጀት የማስተማሪያ መሣሪያዎችን በተለየ ሁኔታ
ለመጠቀም
ከመሠረት ጋር በጋራ በማቀድ በተመረጡ ተማሪዎች ላይ ያዘጋጇቸውን 8 ሰአታት
ከክፍለ ጊዜ በኋላ ልምድ የማስተማሪያ ግብአቶች ለመለማመድና
መለዋወጥ፣ ውጤታማነታቸውን ለመገምገም፡-
እርስ በርስ ለመማማር፣
የክፍል ውስጥ ምልከታዎችን ማስታወሻ ለመያዝ እና
ግብረመልስ በመሰጣጣት በፖርትፎሊዮ ለማስቀመጥ፣

ከመሰረት እና ከልዩ ፍላጎት የተገኘውን ውጤት ለመለየትና ወደፊት ስለሚሰሩ 2 ሰአታት


ትምህርት ክፍል ሀላፊ ጋር ስራዎች ስምምነት ላይ ለመድረስ
ስብሰባ ማድረግ፣ ፖርትፎሊዮን ለማጠናቀቅ፣

40
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -

የግል ሞጁል እቅድህን አጠናቅ/ቂ፣
የዚህን ዕቅድ ማዘጋጃ ቅፅ በአባሪው ውስጥ ታገኛለህ/ሽ፣

ፅብረቃ (Reflection)

በዚህ ሰአት የሚከተሉትን መስራት መቻልህን/ሽን አረጋግጥ/ጪ፡፡

 የት/ቤት የተሙ.ማ ሞጁል ማቀድ ማወቅን፣


 በተ.ሙ.ማ የት/ቤት ሞጁል ውስጥ ባሉ ክ/ጊዜያት (session) መካከል ያለውን ትስስር መረዳትን፣
 አንድ የት/ቤት እና አንድ የግል የተ.ሙ.ማ ሞጁል እቅድ ማዘጋጀትን፣


አረዳድህን/ሽን እና ያሳየኸውን/ሽውን ለውጥ ተመልከት/ች፡፡

የት/ቤት እና የግል አመታዊ የተ.ሙ.ማ ዕቅድ ለማዘጋጀት በራስ መተማመን ይታይብሀል/ሻል?


ተጨማሪ ልምምድ ያስፈልግሀል/ሻል?

ደረጃ ሶስት
ክፍለ-ጊዜያት እንዴት ይደራጃሉ?

በዚህ እርከን፣ ደረጃ ሶስት እንደተጠናቀቀ፣


 የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ክፍለ-ጊዜ እንዴት እንደሚታቀድ ታውቃለህ/ቂያለሽ፡፡
 የተለያዩ አሳታፊ ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የመማር ዘዴዎችን ታውቃለህ/ቂያለሽ፡፡
 አንድ የት/ቤት ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ክፍለ-ጊዜ ታዘጋጃለህ/ለሽ፡፡

ታስታውሳለህ/ሻለሽ?
ክፍለ-ጊዜ ምንድን ነው ?

41
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ክፍለ-ጊዜ የምንለው በሞጁል ውስጥ ያካተትናቸው የተለየዩ ሥነ-ዘዴዎች በተ.ሙ.ማ እንዴት እንደምንጠቀምባቸው የሚገልፅ
ነው፡፡ የጊዜ ድልድልና ዓላማ አለው፡፡ በተከታታይ ተግባራት የተገነባ ነው፡፡ እያንዳንዱ ክፍለ-ጊዜ ለሚቀጥለው የመማር ሂደት
መነሻ ይሆናል፡፡ ስለሆነም እያንዳንዱ ክፍለ-ጊዜ ቀደም ሲል በቀረበው ትምህርት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
ቀደም ሲል የታቀደው ክፍለ-ጊዜ ከመተግበሩ በፊት ቀጣዩን ክፍለ-ጊዜ ዝርዝር ተግባራት ማቀድ አስቸጋሪ ነው፡፡
ቀጣዩ የእቅድ ሂደት የሚከናወነው ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እየተተገበረ ባለበት ሂደት ነው፡፡
ታስታውሳለህ/ሻለሽ?
ተግባር ምንድን ነው?
ተግባራት የምንላቸው የክፍለ-ጊዜ አነስተኛ ክፍሎች ሲሆኑ የክፍለ-ጊዜውን መዋቅር የሚያሳዩ ናቸው፡፡ የተለያዩ ተግባራት
ለተለያዩ ዓላማዎች ይውላሉ፡፡
ለአውደጥናትና ለሌሎች ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ክፍለ-ጊዚያት የሚያገለግሉ የተለያዩ በርካታ ተግባራት ይኖራሉ፡፡ ቀጥሎ
የቀረቡት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

42
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ክፍለ-ጊዜን ለመጀመር የሚያገለግሉ ተግባራት

ስም ምን መቼና ለምን
ማነቃቂያ እነኚህ እንድንነቃቃና ዝግጁ በአውደጥናቱ መጀመሪያ ላይ ሰዎች እርስ በእርሳቸው
(Energizers) እንድንሆን ይረዱናል እንዲተዋወቁ ለማድረግ ይረዳል፡፡ በረጅም ክፍለ-ጊዜ መሃል
የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ያገለግላል፡፡

በፓወር ፖይንት በፕሮጀክተር የሚቀርቡ ተከታታይ ማቅረቢያ መሳሪያው የሚገኝ ከሆነ የሚታዩ ነገሮችን በማቅረብ
ማቅረብ (Power ስላይዶች መረጃ የሚተላለፍበት መልካም ጅማሮ ይሆናል፡፡
point presentation)

ሃሳብ ማፍለቅ (Brain ያልተገደበ ውይይት በማድረግ በክፍለ-ጊዜው መጀመሪያ ላይ እያንዳንዱ ተሳታፊ ስለጉዳዩ
Storming) (ትላልቅ ቡድኖች ወይም አጠቃላይ እንዲያስብ የሚደረግበት ነው፡፡ ቀደም ሲል ያላቸውን እውቀትና
ተሳታፊዎች) ችግሮችን ለመፍታት ምን እውቀት ለመጨመር እንደሚፈልጉ የሚገልፁበት ነው፡፡
በርካታ ሃሳቦችን የሚያፈልቁበት
ነው፡፡

ሁለት ሁለት ወይም ለ1 ወይም ለ2 ደቂቃ ያህል በክፍለ-ጊዜው መጀመሪያ ላይ እያንዳንዱ ተሳታፊ ስለጉዳዩ
ሶስት ሶስት በመሆን በጥቃቅን ቡድኖች በአብዛኛው እንዲያስብ የሚደረግበት ነው፡፡ ቀደም ሲል ያላቸውን እውቀትና
ለአጭር ጊዜ የሚደረግ ሁለት ወይም ሶስት በመሆን ምን እውቀት ለመጨመር እንደሚፈልጉ የሚገለጽበት ነው፡፡
ውይይት (Buzz) በፍጥነት የሚደረግ ውይይት ነው፡፡ በትንሽ ቁጥር የተመሠረተ ቡድን ለተሳታፊዎች የተሻለ በራስ
መተማመን በመፍጠር ሃሳባቸውን እንዲገልፁ ይረዳቸዋል፡፡

43
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
በክፍለ-ጊዜው ትግበራ ወቅት ለውይይት የሚያግዙ ተግባራት

ስም ምን መቼና ለምን
ሃሳብ ማፍለቅ ያልተገደበ ውይይት በማድረግ (ትላልቅ ቡድኖች ወይም አጠቃላይ በማንኛውም የክፍለ-ጊዜ ትግበራ ሂደት አዲስ ርዕስ
(Brain ተሳታፊዎች) ችግሮችን ለመፍታት በርካታ ሃሳቦችን የሚያፈልቁበት በሚጀምርበት ጊዜ ወይም ችግር በሚከሰትበት ወቅት
Storming) ነው፡፡ ያገለግላል፡፡ በማንኛውም ወቅት ተሳታፊዎችን ሃሳብ
ለማለዋወጥ ያገለግላል፡፡
ሁለት ሁለት ለ1 ወይም ለ2 ደቂቃ ያህል በጥቃቅን ቡድኖች በአብዛኛው ሁለት ወይም በማንኛውም የክፍለ-ጊዜ ትግበራ ሂደት አዲስ ርዕስ
ወይም ሶስት ሶስት በመሆን በፍጥነት የሚደረግ ውይይት ነው፡፡ በሚጀምርበት ጊዜ ወይም ችግር በሚከሰትበት ወቅት
ሶስት በመሆን ያገለግላል፡፡ ተሳታፊዎች ብዙ አባላት ባሉት ቡድን
ለአጭር ጊዜ ውስጥ ሃሳባቸውን ለመግለፅ ችላ በሚሉበት ወቅት
የሚደረግ ያላቸውን መልካም ሃሳብ እንዲያካፍሉ ለማድረግ
ውይይት ያግዛል፡፡
(Buzz)
የቡድን በአንድ በተወሰነ ጉዳይ ላይ ከ4 እስከ 6 አባላት ባሉት ቡድን ሰፊ ውይይት ሰዎች ርዕሰ ጉዳዩን በአግባቡ መገንዘብ ሲፈልጉ
ውይይት የሚደረግበት ነው፡፡ ይካሄዳል፡፡ ውይይት ማድረግና በጉዳዩ ላይ ስምምነት
(Group መድረስ ሲያስፈልግ የሚደረግ ነው፡፡ ሰፋ ያለ ውይይት
discussion) ማድረግ ተሳታፊዎች ችግሮችን ከራሳቸው አውድ አንፃ
እንዲረዱና ሃሳባቸውንና ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ
ያደርጋል፡፡
ፒራሚዳው የተለያዩ ጥንዶች በአንድ ርዕሰ-ጉዳይ ላይ ይወያያሉ፤ በመቀጠል ከሌላ ይህ ተግባር ለውይይት በቀረቡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሁሉ
ውይይት ጥንድ ጋር ሃሳብ ይለዋወጣሉ፡፡ በ2 ወይም 3 ነጥቦች ላይ ከስምምነት ተሳታፊዎች ከስምምነት እንዲደርሱ ማድረግ አስፈላ
(Pyramid በመድረስ ከሌላው ባለ 4 አባላት ቡድን ጋር ሃሳብ ይለዋወጣሉ፡፡ 8 አባላት ሆኖ ሲገኝ የሚያገለግል ዘዴ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰ
work) በመሆን 3 እጅግ ጠቃሚ ነጥቦችን ለመላው አባላት ለውይይት ያቀርባሉ፡፡ ሃሳቡን የመግለፅ እድል ያገኛል፡፡ ቡድኑ እየሰፋ ሲሄ
በዋና ዋና ነጥቦች ላይ ከስምምነት እየተደረሰ ይሄዳል፡፡

በነጠላ ጉዳይ አንድን ጉዳይ ለመተንተን ሲባል የተዘጋጀ መግለጫ ነው፡፡ ሰዎች መልካም ወይም መጥፎ ተሞክሮዎችን
የተመሠረተ በመተንተን በትምህርት ሰጪነቱ እንዲጠቀሙበት
ጥናት (case ለማድረግ ይረዳል፡፡ ይህ ተግባር ሰዎች ስለተማሩት ጉዳ
study) እንዲያስቡና ከተጨባጭ ሁኔታው ጋር በማጣጣም
እንዲተገብሩት ያግዛል፡፡ በግል ተግባራቸውም
እንዲያንፀባርቁት ይረዳቸዋል፡፡
ተቆራርጠው የተቆራረጠ ሰንጠረዥ ወይም ጥያቄና መልስ አዘበራርቆ በማቅረብ ተሳታፊዎች እንዲረዱት የተፈለገ ሰንጠረዥ ሲኖር
የተዘበራረቁ የየቡድኑ አባላት ሰሜት በሚሰጥ መልኩ መልሰው እንዲገጣጥሙት ለመተግበር ያገለግላል፡፡ በቁርጥራጭ ወረቀቶች ላይ
44
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ስም ምን መቼና ለምን
ነገሮችን ማድረግ፡፡ የተፃፉ ነገሮችን በማንበብና ቦታቸውን በመቀያየር
መልሶ መልእክቱን መግለፅ እንዲችሉ በማድረግ አደራጅቶ
መገጣጠም ሰንጠረዡን የተሻለ ለመረዳት ያስችላል፡፡
(Jigsaw)
በየቡድኖቹ ቡድኖች የተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ይሰጧቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ቡድን በርዕሰ- ይህን ስልት በርካታ የውይይት ርዕሰ-ጉዳዮች ሲኖሩ፣ በ
በተሰራ ስራ ጉዳዩ ላይ ያለውን ሃሳብ እንዲፅፍ ጊዜ ይሰጠዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቡድኖች ጊዜ ሳይኖር ሲቀርና ሁሉም ተሳታፊ እንዲወያይበ
ላይ ተጨማሪ ቦታቸውን እየቀያየሩ በየቡድኖቹ የቀረቡ ሃሳቦች ላይ የራሳቸውን ሃሳብ ማድረግ ሲያስፈልግ መጠቀም ይቻላል፡፡ ይህ ስል
ሃሳብ እያከሉ በየተራ ያክላሉ፡፡ እያንዳንዱ ተሳታፊ አንድን ጉዳይ በጥልቀ
መሄድ (Bus እንዲወያይበትና የራሱን ሃሳብ ለመጨመር እድ
stop) ይሰጠዋል፡፡
ግላዊ ፅብረቃ ግለሰቦች ስለተማሩት ነገር እንዲያስቡና በስራቸው ላይ የሚኖረውን ከእያንዳንዱ ትግበራ በኋላ ለ3 ደቂቃዎች ያህል
(Individual ተፅዕኖ እንዲገነዙቡና አስተያያታቸውን እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡ ትግበራውን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ማሰብ፡፡
reflection)

45
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
የግብረ-መልስ ተግባራት
ስም ምን መቼና ለምን
የቡድን ሥራዎችን በተለያዩ ቡድኖች የተዘጋጁ ሃሳቦች በውይይቱ ክፍለ-ጊዜ ማብቂያ ላይ ማንኛውም
እየተዘዋወሩ መመልከት በአዳራሹ ግርግዳ ላይ ይለጠፉና ተሳታፊ በየቡድኖቹ ከስምምነት የተደረሰባቸውን
(Gallery walk) ሌሎች እየተዘዋወሩ እንዲያነቧቸው ሃሳቦች ያነባል፡፡
ይደረጋል፡፡
ገለፃ (presentation) ግኝቶች ወይም የቡድን ውይይቶች በውይይቱ ማብቂያ ላይ አንድ ቡድን ወይም
ለሌሎች ሰዎች ወይም ቡድኖች የተለያዩ ቡድኖች የደረሱባቸውን ስምምነቶች
ይቀርባሉ፡፡ የሚያቀርቡበት ነው፡፡ አንድን ሃሳብ ለማቅረብ
ዝግጅት ሲደረግ የውይይቱ ውጤት ምን ሊሆን
እንደሚችል አስቀድሞ በጥንቃቄ እንዲታሰብ
ያደርጋል፡፡ ከሌሎች ጋር የተሻለ የሃሳብ ልውውጥ
እንዲደረግም ያግዛል፡፡

በፖወር ፖይንት ማቅረብ በፕሮጀክተር የሚቀርቡ ተከታታይ በክፍለ-ጊዜው ማብቂያ ላይ የተወሰኑ ስላይዶችን
(Power point ስላይዶች በመጠቀም እስካሁን የተማሩትን ማስታወስ
presentation) ይቻላል፡፡ ሌሎች ስላይዶችንም በተጨማሪነት
መጠቀም ለፅብረቃና ለግምገማ ይረዳል፡፡

የፅብረቃና የግምገማ ተግባራት


የአቻ ፅብረቃና ግምገማ በክፍለ-ጊዜው ውስጥ የተማሩት ምን በክፍለ-ጊዜው ወይም በአውደጥናቱ መጨረሻ ላይ
(Peer reflection and እንደሆነና በመጨረሻም እያንዳንዱ ሁሉም ሰው ለተመሳሳይ ግብ በጋራ ይሰራል፡፡
evaluation) ሰው ምን እንደሚያደርግ በጋራ በክፍለ-ጊዜው ውስጥ በጥንድ የሚከናወን ተግባር
መወሰን፡፡ ሲኖር በጋራ እቅድ ሲሰራና በጋራ የማስተማር
ተግባር ላይ ጠቃሚ ስልት ነው፡፡ ይህ ሲሆን
የሚቀጥለው ክፍለ-ጊዜ ግብረ-መልስ ለሁሉም
ሰው ጠቀሜታ ያለው ይሆናል፡፡
ግላዊ ፅብረቃ (Personal በክፍለ-ጊዜው ሊሻሻል በሚገባው በክፍለ-ጊዜው ወይም በአውደጥናቱ ማጠቃለያ
reflection) ተግባር ላይ ፅብረቃ ማድረግ ማሻሻያ ሊደረግበት በሚገባ ተግባር ላይ
ከስምምነት ለመድረስ ያግዛል፡፡ ከአቻ ፅብረቃና
ግምገማ በተጨማሪ በቁልፍ ግብነት ከተቀመጠው
ሌላ በክፍለ-ጊዜው ትግበራ ወቅት የተከሰቱ
ተጨማሪ ነጥቦችን ለማንፀባረቅም ይረዳል፡፡
የትግበራ እቅድ የተለያዩ ተግባራትን ወይም ክፍለ- በክፍለ-ጊዜው ወይም ከአውደ-ጥናቱ ማብቂያ
(Action planning) ጊዜያት መረጃዎች፣ ግብዓትን፣ ቀጥሎ ምን እንደሚከናወን ለማቀድ ያግዛል፡፡
ትግበራዎችንና ስኬትን መሠረት አንድን ነገር ውጤታማ ለማድረግ እጅግ ጠቃሚ
በማድረግ ማቀድ፡፡ ጉዳይ ነው፡፡ ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ውጤታማ
የሚሆነው በየክፍለ-ጊዜያቱ የተገኘው እውቀት
በመማርያ ክፍል ውስጥ ወይም በስራ ቦታ
ሲተገበር ነው፡፡

ምናባዊ ትምህርት ቤቱ የተጠቀመባቸው ዘዴዎች ምሳሌ፡-

ክፍለ ጊዜ-የመምህራን ስብሰባ


 የክፍለ-ጊዜው ዓላማ-ሞጁሉን ለማስተዋወቅና አሳታፊ የትምህርት አቀራረብ ዘዴ በሁሉም
ክፍሎች የተማሪዎችን ውጤት ሊያሻሽል እንደሚችል ከስምምነት ለመድረስ፣

46
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ተግባር ዝርዝር ተግባር ግብዓቶች ጊዜ
ማነቃቂያ የተለያዩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ በአሳታፊ የትምህርት አቀራረብ ዘዴ ላይ 5 ደቂቃ
(Energizers) ሃሳብ ከተሳታፊዎች መቀበል፡፡ መምህራን በአንድ ጫፍ ወይም በሌላኛው
ጫፍ በመቆም ሃሳባቸውን ይገልጻሉ፡፡ በአንድ ጫፍ “እስማማለሁ” የሚል
ሃሳብ ያላቸው ሲቆሙ “አልስማማም” የሚሉት በሌላው ጫፍ ይቆማሉ፡፡
1. አሳታፊ የትምህርት አቀራረብ ዘዴ
የተማሪዎችን ውጤት ያሻሽላል፡፡
2. ትምህርት በሚቀርብበት ጊዜ ተማሪዎች
ፀጥ ሊሉ ይገባል፡፡
3. ትምህርቱ በሚቀርብበት ጊዜ ተማሪዎች
በክፍል ውስጥ ወዲያና ወዲህ ለማለት
ሊፈቀድላቸው ይገባል፡፡
4. መምህራን ዘወትር ማስተማሪያ
መጽሐፉን ሊከተሉ ይገባል፡፡
5. ተማሪዎች ከጥቁር ሰሌዳ መገልበጥ
ትምህርታቸውን እንዲማሩ ያግዛቸዋል፡፡
የሞጁሉ አውድ መሪው ከክፍል ምልከታ እንዲሁም ለተማሪዎችና ለወላጆች ከቀረበው በሰሌዳ ወይም በትልቅ 10 ደቂቃ
(context of module) መጠይቅ በተገኘው መረጃ መሠረት አሳታፊ የማስተማር ዘዴን የመጠቀም ወረቀት ላይ የተፃፉ ቁልፍ
ሁኔታ አነስተኛ በመሆኑ ተማሪዎች እየተሰላቹ መሆኑን ገለፁ፡፡ ስለዚህ ነጥቦች
በት/ቤት ውስጥ የተማሪዎችን ተሳትፎ ማሻሻል አስፈላጊ ነው፡፡
ሃሳብ ማፍለቅ አሳታፊ የማስተማር ዘዴ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከ1 ወይም ከ2 አቻዎች 10 ደቂቃ
(Brain storming) ጋር እንዲወያዩ ማድረግ፡፡
ከቡድን ውይይት በኋላ 6 አባላት ያሉት ቡድን ቀላቅሎ በማደራጀት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ወረቀትና እስክሪብቶ 20 ደቂቃ
የቡድን ስራዎችን መጠየቅ፡፡
እየተዘዋወሩ
መመልከት፣(Group  የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ምን አይነት አሳታፊ የማስተማር
discussion followed ዘዴዎችን መጠቀም ይቻላል?
by gallery walk)  የትኛው ተገቢነት አለው? የትኛው ተገቢነት የለውም?

ተግባር ዝርዝር ተግባር ግብአቶች ጊዜ


ግላዊፅብረቃ(personal በየትኛው ላይ ጥሩ ችሎታ አለህ/ሽ? ማሻሻል የምትፈልገው/ጊው የትኛውን ነው? 5 ደቂቃ
reflection)
ቀጣዩስ? መሪው በቡድን ውይይት ወቅት የተሰነዘሩ ሃሳቦችን በማጠቃለል፣ የት/ቤት በሰሌዳወይምበቻርት ላይ 10 ደቂቃ
(What next) ጉብኝቱን የትኩረት አቅጣጫ ያስተዋውቃል፡፡ የተፃፉ ቁልፍ ነጥቦች

ለሌላ ክፍለ - ጊዜ ማቀድ

አንዳንዶቹ ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ክፍለ - ጊዜያት የተለየ እቅድ ይፈልጋሉ፡፡ ለማንኛውም የክፍለ - ጊዜው ዓላማ ዘወትር ግልፅ ሊሆን
ይገባዋል፡፡
ቀጥሎ 3 ምሳሌዎች ቀርበዋል፡፡
1. ሌላ ት/ቤት ለመጐብኘት 2. የአቻ ምልከታ ክፍለ - ጊዜ

እቅዱ የሚያካትታቸው ጉዳዮች: እቅዱ የሚያካትታቸው ጉዳዮች:


 መጓጓዣ

47
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
 የግንኙነት ስልት  የምልከታ ጊዜ
 ምቹ ሁኔታ (Access)  የምልከታው የትኩረት አቅጣጫ
 የጉብኝት ጊዜ  የግብረ-መልስ ጊዜ
 ፅብረቃን በፖርትፎሊዮ ውስጥ  ፅብረቃን በፖርትፎሊዮ ውስጥ የመፃፊያ
የመፃፊያ ጊዜ ጊዜ

3. የተማሪዎችን ስራ ከትምህርት በፊትና በኋላ ወይም ከተወሰኑ ተከታታይ ክፍለ


ጊዜያት በኋላ መመዘን

እቅዱ የሚያካትታቸው ጉዳዮች:


 የምትጠቀምበት/ሚበት ትምህርት/ቶች
 የተማሪዎችን ውጤት ከትምህርት በፊት የምትመዝንበት/የምትመዝኚበት ጊዜ
 የምዘና አይነት
 በትምህርቱ ሂደት ወይም ከትምህርቱ በኋላ ምዘና ለማካሄድ የሚያስፈልግ ጊዜ
 ፅብረቃን በፖርትፎሊዮ ውስጥ የመፃፊያ ጊዜ

.  አሁን ለትምህርት ቤትህ/ሽ ሞጁል የክፍለ-ጊዜ እቅድ አዘጋጅ/ጂ፡፡


የዚህን እቅድ ቅፅ በአባሪው ውስጥ ማግኘት ትችላለችሁ፡፡

አስታወሱ - የክፍለ-ጊዜ ዓላማ እጅግ ጠቃሚ መነሻ ነጥብ ነው፡፡

ሞጁሉን ስታጠናቅቅ/ቂ ምንድን ነው የምታደርገው/ጊው?


ሞጁሉን ማጠናቀቅ ማለት መማር የሚገባህን/ሽን ነገር ሁሉ ተምረሃል/ሻል ማለት አይደለም፡፡ በቀጣይም ልምምድ ታቆማለህ/ሚያለሽ
ማለትም አይደለም፡፡ ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ማለት እነኚህን የተገኙትን ክህሎቶች በተጨማሪ “ ትግበራ ” እና “ ፍተሻ “ በተከታታይ
ማዳበር ማለት ነው፡፡

በሞጆሉ ማጠቃለያ:-
 በተማርከው/ሺው ጉዳይ ላይ እና የክፍል ውስጥ የመማር ማስተማር ትግበራ ምን ያህል እንደተሻሻለ ፅብረቃ ታካሂዳለህ/ጃለሽ፡፡
 የተካንካቸውን/ሻቸውን ብቃቶች ትለያለህ/ሽ፡፡
 የተማርካቸውን/ሻቸውን ክህሎቶች መለማመድ ትቀጥላለህ/ያለሸ፡፡

ፅብረቃ
ይህ ልታውቀው/ቂው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
 ክፍለ-ጊዜ እንዴት እንደሚታቀድ ማወቅ፣
 የተለያዩ ተከታታይ ሙያ ማሻሻያን በመተግበር ለመማር የሚያግዙ ተግባራትን ማወቅ፣
 የት/ቤት ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ክፍለ-ጊዜ እቅድን ማዘጋጀት፣
48
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -

- በግንዛቤህ/ሽ እና በተገኘው መሻሻል ላይ ፅብረቃ አድርግ/ጊ፡፡
- የት/ቤትና የግለሰብን አመታዊ ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ ለማዘጋጀት በራስ
መተማመንን ፈጥረሃል/ሻል ?
- ተጨማሪ ልምምድ ትፈልጋለህ/ጊያለሽ?

እርከን 3

የተ.ሙ.ማ ትግበራ

እስካሁን ፍላጐትህን ተንትነሃል/ሻል፣


ቅድሚያ ተግባራትህን ለይተሃል/ሻል፣
አመታዊ እቅድህን ነድፈሃል/ሻል፣
የት/ቤት የተ.ሙ.ማ ሞጁል አቅደሃል/ሻል፣
የሞጁሉን እያንዳዱን ክፍለ-ጊዜ
እንዴት እንደምታቅድ/ጂ አስበሃል/ሻል፣

አሁን የት/ቤትህን ሞጁል ለማከናወን ተዘጋጅተሃል/ሻል፡፡

የት/ቤትህን/ሸን ተ.ሙ.ማ ሞጁል እንዴት ተግባራዊ ታደርጋለህ/ጊያለሽ?


የተ.ሙ.ማ ኡደት ሶስቱን እርከኖች ተጠቀም/ሚ፡፡

ትግበራ የዕቅድ፣ የመፈፀምና የመፈተሽ ድግግሞሽ ቅደም ተከተል ነው፡፡


1. የመጀመሪያውን ክ/ጊዜ ተግብር/ሪ፡፡
2. ውጤቱን ፈትሽ/ሺ፡፡
3. በመጀመሪያው ክ/ጊዜ ላይ በመመስረት ቀጣዩን ክ/ጊዜ አቅድ/ጂ፡፡
4. ሁለተኛውን ክ/ጊዜ ተግብር/ሪ፡፡
5. ለውጥህን/ሽን ፈትሽ/ሺ፡፡
6. እስካሁን በተከናወነው ላይ በመመስረት 3 ኛውን ክ/ጊዜ አቅድ/ጂ፡፡
7. የተገኘውን ጥሩ ውጤት አድንቀህ/ሽ በት/ቤቱ ሞጁል ውስጥ መለወጥ ያለበትን ወስን/ኚ፡፡
8. የሚቀጥለውን ክ/ጊዜ በማቀድ ሥራህን/ሽን ቀጥል/ዪ ወዘተ. ወዘተ.

49
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
የሞጁሉ አተገባበር እንዴት ይፈተሻል?
የተሙ.ማ ሞጁል ፍተሻ በተከታታይ መካሄድ አለበት፡፡ የፍተሻው ተግባር በሌሎች ተሳታፊዎች በመረዳት የሞጁሉ መሪዎች በኃላፊነት
የሚያከናውኑት ነው፡፡
በእያንዳንዱ ክፍለ-ጊዜ
በተ.ሙ.ማ ክፍለ-ጊዜ ሂደት የተገኘውን ለውጥ ጠቃሚነት ገምግምና/ሚና አስፈላጊ ከሆነ ተገቢውን ማሻሻያ
አድርግ/ጊ፡፡
ከክፍለ - ጊዜ በኋላ
የተሳታፊዎችን ምላሽና የራስህን/ሽን ግምገማ በመጠቀም የክፍለ-ጊዜው ይዘት ውጤታማ መሆኑን ወስን/ኚ፡፡ አስፈላጊ ከሆነ
የሚቀጥለውን ክፍለ-ጊዜ አሻሻል/ሽይ፡፡ ለምሳሌ ተሳታፊዎች ዓላማውን በደንብ አልተረዱት ይሆናል ወይም ያቀድከውን/ ሽውን
ሁሉ ማጠናቀቅ በቂ ጊዜ አላገኘህ/ሽ ይሆናል፣
ለፍተሻው በታቀደው ጊዜ የሚፈፀሙ ድርጊቶች
ለፍተሻ በታቀደው ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ ድርጊቶችን በመመልከት ማሻሻያዎችን ማድረግ ካስፈለገ አሻሽል/ዪ፡፡

ተሙ.ማን ለማጠናቀቅ በግል ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነጥቦች


 የት/ቤትን ሞጁል ለመተግበር ቁርጠኛ መሆን፣
 ሊያጋጥሙ ለሚችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ራስን ማዘጋጀት፣
 ችግሮችን መፍታት፣
 የማይሰራ ከሆነ እቅድን መለወጥ፣
 አዲስ ነገር መማር ሁልጊዜ ቀላል እንዳልሆነ መገንዘብ፣
 አንዳንድ መምህራን አንዳንድ የተ.ሙ.ማ ተግባራትን ለመፈፀም ፈቃደኛ ላይሆኑ እንደሚችሉ መጠበቅ፣
 የተ.ሙ.ማ ተግባራትን በመፈፀም ሂደት ወደ ኋላ አለመቅረት ወይም አለመዘናጋት፣
 ለተግባራት ቅደም ተከተል ማውጣት፣
 ነገሮችን እንደሁኔታው መመልከት፣

አስታውሱ፣ ደጋግማችሁ ስትሰሩ እየቀለለ ይመጣል!

50
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
እርከን አራት

ተከታታይ ሙያ ማሻሻያን እንዴት ትገመግማለህ/ሚያለሽ?

የት/ቤት ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ሞጁል ስኬታማ መሆን አለመሆኑን እንዴት


ታውቃለህ/ቂያለሽ?
እርከን አራት ሲጠናቀቅ፡-
 የት/ቤት ሞጁል እንዴት እንደሚገመገም ታውቃለህ/ቂያለሽ፡፡
 ተገቢው መረጃ እንዴት እንደሚገኝ ትረዳለህ/ጃለሽ፡፡
 ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ኡደትን በተሟላ ሁኔታ ለማጠናቀቅ በራስህ/ሽ
ትተማመናለህ/ኛለሽ፡፡
እቅድህ/ሽ ከመነሻው በአግባቡ ከተዘጋጀ ውጤታማነቱን መመዘን ቀላል ይሆናል፡፡

በት/ቤት ሞጁል ትግበራ ወቅት በእያንዳንዱ ተግባር ፅብረቃና ግምገማ ለማካሄድ እድሉ አለ፡፡ ይሁን እንጂ ከሞጁሉ ማብቂያ
ላይ አጠቃላይ ሞጁሉን መገምገም ይኖርብሃል/ሻል፡፡
ግምገማ በሚደረግበት ወቅት በሞጁሉ የተ.ሙ.ማ እቅድ ማዘጋጃ ቅፅ ውስጥ ያለውን የመጨረሻ ረድፍ ወይም ሊመጣ
የተፈለገውን ለውጥ ማየትና ስኬታማ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ሂደት የሚገኘው ውጤት በሶስት ደረጃዎች ተከፍሎ ሊታይ ይችላል፡፡ እነርሱም፡-
በአግባቡ አከናውነናል?
ሊሻሻል የሚገባው ነገር አለ?

በሁለቱ መሃከል ነው?


ማስረጃ ያስፈልጋል፡፡
ሰዎች የሚያንፀባርቁትን ብቻ በመመልከት ከድምዳሜ መድረስ ሁልጊዜ ትክክል ላይሆን ይችላል፡፡ ምሳሌ፡- “ሁሉም ሰው
ደስተኛ ነበር፤ ምግቡ ጥሩ ነበር፤ ርዕሰ-መምህሩ ደስተኛ ይመስላል፤ የክልሉ ት/ቢሮ ሃላፊ በጣም እየሳቀ ነበር.....”

ታዲያ ማስረጃ የሚገኘው ከየት ነው?


ለውጥን ከሚያመላክቱ ከማናቸውም የመረጃ ምንጮች!

51
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ቀጥሎ ምሳሌዎች ቀርበዋል:-

 የምዘና ውጤቶች

 የሰዓት መቆጣጠሪያ ሰነድ

 የመምህራን መዝገብ

 የትምህርት ዕቅድና ግምገማ

 የክፍል ምልከታ መዝገብ

 የተማሪዎችን ሥራ ማየት

 የተስተዋለ የባህርይ ለውጥ

 ለመምህራን ወይም ተማሪዎች ቃለመጠይቅ ማድረግ

 ከመጠይቅ የተገኙ ውጤቶች

 በክፍል ውስጥ በሚታይ ነገር

 የስብሰባ መዝገቦች

 የትምህርት ቤት መሻሻል እቅድ ግምገማ

 ፖርትፎሊዮ

 አመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ

ከሰዎች አስተያየት የሚሰበሰብ ከሆነ አስተያየቱ በአግባቡ ሊተነተን ይገባል፡፡

የምናባዊ ት/ቤት ምሳሌ፡-

ምን ለውጥ ማየት እንፈልጋለን?


የትምህርት ምልከታው የተሻሻለ የማስተማር ሂደትን አመላክቷል?

መረጃ – የሒሳብ ትምህርት የክፍል ምልከታና የተሰጠ ግብረ-መልስ

የሙከራ ፈተናዎች ከሌሎች የትምህርት ዓይነቶች አንፃር በአማካይ መሻሻልን አሳይተዋል?


መረጃ – የሙከራ ፈተናዎችን ከአሁኑና ካለፉት ሁለት አመታት የሁሉም የትምህርት አይነቶች ውጤት ጋር ማወዳደር፡፡
ተማሪዎች በሒሳብ ትምህርት ደስተኞች ናቸው?
መረጃ –የተጠናቀረ መጠይቅና የተማሪዎች ቃለ-መጠይቅ፣

52
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -

የትምህርት ቤት ወይም የግለሰብ ሞጁልን ማጠቃለያው ላይ መገምገም ይቻላል፡፡

በተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ኡደት አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ሶስተኛ እርከኖች ሲጠናቀቁ ወደ አራተኛ እርከን ተመለስ/ሺ፡፡

በመቀጠልም ለእያንዳንዱ የት/ቤት ሞጁል ግምገማ የሚያገለግሉ መረጃዎችን ወስን/ኝ፡፡

በት/ቤት ወይም በግለሰብ ሞጁል ማብቂያ ላይ በመረጃ ላይ የተመሠረተ አጭር ሪፖርት ተጽፎ በተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ፋይል
ውስጥ ይቀመጣል፡፡ በት/ቤት ሞጁል ትግበራ ላይ ግለሰቦች ያደረጉት አስተዋፅኦ በግል ፖርትፎሊዮአቸው ተመዝግቦ መያዝ
አለበት፡፡ ት/ቤቱ ለዚህ ተግባር በአግባቡ መፈፀም ጊዜ ሊሰጥ ይገባል፡፡

ከምናባዊ ት/ቤቱ የተወሰደ ምሳሌ፡-

በሁለተኛ ደረጃ ቅድሚያ የተሰጠው የሙያ ማሻሻያ ፍላጐት ሪፖርት


ቅድሚያ የተሰጠው ተከታታይ - ለአዲስ ጀማሪ መምህራን አማካሪዎችን
ሙያ ማሻሻያ ጉዳይ ማሰልጠን፡፡

 በተከታታይ ሙያ ማሻሻያው የሚሳተፉ - ሁሉም አማካሪ መምህራን


 ኃላፊነት ያለበት ሰው - ርዕሰ መምህሩ
 የሚጀመርበትና የሚጠናቀቅበት ቀን - ከ 1 ኛ ሰሚስተር መጀመሪያ እስከ 2 ኛ
ሰሚስተር ማብቂያ፣
 ምን ለወጥ ለማየት እንችላለን? - አማካሪ መምህራን ሃላፊነታቸውን
ለመወጣት በራስ
መተማመንን ያዳብራሉ፡፡
አዲስ ጀማሪ መምህራን የትምህርት እቅድ፣ የማስተማርና የግማገማ ችሎታቸው ይሻሻላል፡፡
ከአንድ አማካሪ መምህር በስተቀር ሁሉም መምህራን የት/ቤት ሞጁሉን አጠናቀዋል፣፡ ህይወት በግል ምክንያት ከአራት ሳምንት በኋላ ወደ
ሌላ ት/ቤት ተዛውራለች፡፡ ሞጁሉ በወቅቱ ተጀምሮ በወቅቱ ተጠናቋል፡፡
የሞጁሉን መጠናቀቅ ተከትሎ የታዩ ለውጦች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. አማካሪ መምህራን ኃላፊነታቸውን ለመወጣት በራሳቸው መተማመንን አዳብረዋል፡፡

መረጃው የተሰበሰው
 ለአዲስ ጀማሪ መምህራንና አማካሪዎች ቃለ-መጠይቅ በማድረግ
 ከስብሰባዎች ምልከታ
አዲስ ጀማሪ መምህራን አማካሪዎቻቸው በአግባቡ ድጋፍ ያደረጉላቸው መሆኑን፣ መልካም አቀራረብ የነበራቸውና ያግዟቸው እንደነበር
ተናግረዋል፡፡ ለማስተማር ስራቸው ጥሩ ሃሳብ ያቀርቡላቸው እንደነበርና ሁልጊዜ ሊደግፏቸው ዝግጁ እንደነበሩም መስክረዋል፡፡
ስብሰባዎች በአግባቡ ታቅደው ጊዜያቸውን ጠብቀው ተካሂደዋል፡፡ የፅህፈት ሥራዎችም በወቅቱ ተደራጅተው ተጠናቀዋል፡፡
አማካሪ መምህራን በተሰጣቸው ኃላፊነት ደስተኞች መሆናቸውንና ግምት ተሰጥቷቸው ለት/ቤት መሻሻል መርሀ-ግብር አስትዋፅኦ እያደረጉ
በመሆናቸው ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
2. የአዲስ ጀማሪ መምህራን የትምህርት እቅድ፣ የማስተማር ስራና ግምገማ ተሻሽሏል፡፡

53
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
መረጃ የተሰበሰበው፡-
 ከትምሀርት ምልከታ መዝገቦች
 ከትምህርት እቅድና ግምገማዎች
 ከምዘና ውጤቶች

በሁለተኛው ሴሚስተር ማብቂያ ምልከታ በተደረገባቸው ትምህርቶች ላይ የትምህርት እቅዶች ቀርበዋል፡፡ በትምህርት እቅዱ ላይ ከቀረቡ
ዓላማዎች መካከል 80% ከግብ የደረሱ ሲሆን ከተማሪዎች ችሎታ ጋርም የተመጣጠኑ ነበሩ፡፡ በሁለተኛው ሴሚስተር የተማሪዎች ተሳትፎ
በስፋት ታይቷል፡፡ ስራው የሚያስፈልገው ግብአትም በአመዛኙ በአግባቡ ስራ ላይ ውሏል፡፡ በሁለተኛው ሴሚስተር ከአስራ አንዱ አዲስ ጀማሪ
መምህራን መካከል አስሩ ትምህርታቸውን በአግባቡ ገምግመው ቀጥሎ ላለው እቅድ ዝግጅት ሂደት ተጠቅመውበታል፡፡ በአዳዲስ ጀማሪ
መምህራን የሚሰጡ ትምህርቶች የተማሪዎቹ ውጤት ከአምናው ይልቅ ተሻሽሏል፡፡ ከአስራ አንዱ አዲስ ጀማሪ መምህራን ዘጠኙ ስኬታማ
ተከታታይ የምዘና ስልት ተጠቅመዋል፡፡

ውጤቶች (Out comes)


በአመዛኙ ቅድሚያ የተሰጣቸው የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የስልጠና ጉዳዮች ስኬታማ ሆነዋል፡፡ እራሳችንን በደረጃ ስናስቀምጥ መካከል ላይ
እንሆናለን፡፡ ዘጠኙ አዲስ ጀማሪ መምህራን ከአገልግሎታቸው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ችሎታ ታይቶባቸዋል፡፡
ሁለቱ በተማሪዎች አመራርና ምዝና ስልቶች ላይ ተጨማሪ ስልጠና ይፈልጋሉ፡፡ በማማከር አገልግሎትና በአዲስ ጀማሪ መምህራን ሥራ አፈፃፀም
መካከል ግልፅ ግንኙነት አለ፡፡ ስለዚህ ሁለቱ አማካሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ ቀሪዎቹ አማካሪ መምህራን በተሰጣቸው የሥራ ድርሻ ላይ
በራስ የመተማመን ስሜት ፈጥረዋል፡፡ በሚቀጥሉት ጊዜያት አዳዲስ አማካሪዎችን ለመደገፍና ለማሰልጠንም ይጠቀሙበታል፡፡
የሚቀጥለው ደረጃ
ሁለቱን አማካሪ መምህራን ለመደገፍና እንዲሻሻሉ ለማድረግ የሚቀጥሉት እርምጃዎች ይወሰዳሉ፡፡
1. በተጓዳኝ ትምህርት ማእከላት በተከታታይ ምዘና ስልጠና ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ፡፡
2. በተከታታይ ግምገማ አፈፃፀማቸው የተሻለ ችሎታ ያላቸውን አቻዎች እንዲመለከቱ ማድረግ፡፡
3. የትምህርት ስራውን ለመገምገም ሲባል ከጉድኝት ሱፐርቫይዘር ጋር ውይይት ማድረግ፡፡
4. በማማከር ስራቸው ስኬታማ የሆኑ አማካሪዎችን ፈለግ ለአንድ ሳምንት መከተል

የሚቀጥለው ምንድን ነው?


በት/ቤት ወይም በግለሰብ ሞጁል ስኬታማነት ግምገማ ላይ በመመስረት የተለያዩ አማራጮች ይኖራሉ፡፡
ውጤታማ ከሆንህ/ሽ የሚቀጥለውን የስልጠና ጉዳይ ወደ መተግበር መሄድ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ለውጤታማነቱ
እርግጠኛ ካልሆንክ/ሽ ይህን የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የስልጠና ጉዳይ በድጋሚ መተግበር የሚገባ መሆን አለመሆኑን መወሰን
ይገባል፡፡

በአግባቡ አከናውነናል?
የት/ቤት ሞጁል ውጤታማ ከሆነና የሚፈለገው ግብ
ከተደረሰ ወይም ከተቃረበ ከእንግዲህ ቅድሚያ
የሚሰጠው የሙያ ማሻሻያ ጉዳይ ሊሆን አይችልም፡፡
ይሁን እንጂ ሁኔታው በዚሁ መልክ የሚቀጥል መሆኑን 54
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
መከታተል ተገቢ ነው፡፡
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ሊሻሻል የሚገባው ነገር አለ?
የመሻሻል ሂደቱ አዝጋሚ ከሆነና ለውጡ ዝቅተኛ ከሆነ
በሚቀጥለው ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ጉዳይነት አመታዊ
ተ.ሙ.ማ እቅድ ላይ ቅድሚያ ሊሰጠው ይችላል፡፡

በሁለቱ መካከል ነው?


ከት/ቤቱ ሞጁል ከሚጠበቅ ውጤት ውስጥ የተወሰነ መሻሻል
ከተገኘ በሚቀጥለው አመታዊ እቅድ ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጠው
የሙያ ማሻሻያ ጉዳይ ላይሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ለጊዜው በሙያ
ማሻሻያ ፍላጐትነት ቅድሚያ ሳያገኝ ሊቀርና ከተወሰነ ጊዜ በኋላ
ግን በድጋሚ ሊታቀድበት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ክትትሉ መቀጠል
ይኖርበታል፡፡

እንኳን ደስ ያለህ/ሽ -- አንዱን ዙር ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ኡደት አጠናቀሃል/ሻል፡፡


አሁን ምን ታደርጋለህ/ጊያለሽ?
የተ.ሙ.ማ ዑደት

ፍተሻ

እንደገና ጀምር/ሪ !!!


የግል ተ.ሙ.ማ ልምዶች

የተ.ሙ.ማ ልምዶች ከምናባዊ ትም/ቤት

ስም : አብርሃም

55
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ኃላፊነት - የምናባዊ ትም/ቤት ር/መምህር

ባለፈው ዓመት ከተ.ሙ.ማ ፍላጐቶችህ አንዱ ምን ነበር?


በምናባዊ ት/ቤት ር/መምህርነት ቦታ ላይ አዲስ ነኝ፡፡ ሂሳብን በማስተማር ብዙ
ልምድ ያለኝ ቢሆንም በስርዓተ ትምህርት ውስጥ ባሉ ሌሎች ትምህርት ዓይነቶች ያለኝ ልምድ ውስን ነው፣ ሌሎች የትምህርት
አይነቶች እንዴት እንደሚገመገሙ የበለጠ ለማወቅ/ለመማር ፈልጌ ነበር፡፡
የተሙ.ማ ፍላጐትህን ለማሳካት ምን አደረግህ?

በስርዓተ ትምህርት ውስጥ ባለው መማር ማስተማር መልካም ስም ያለውን የጉዳኝት ማዕከል ለመጐብኘት አቀድኩ፣ ለሁለት
ወራት ዘወትር ረቡዕ ጠዋት እየሄድኩ የተወሰኑ በዋነኝነት የመጀመሪያ ሳይክል የነበሩትን ክፍሎች እመለከት ነበር፡፡
የተ.ሙ.ማ ሞጁልህን ከተገበርክ በኋላ ምን ለውጥ አገኘህ?
ልምድ ያላቸው መምህራን በመማሪያ ክፍል ውስጥ ሲሰሩ መመልከት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ምክንያቱም መምህራን በክፍል ውስጥ
ያለውን መሻሻል ለማረጋገጥ ተከታታይ ምዘናን እንዴት እንደተጠቀሙ ማየት በመቻሌ ነው፡፡ በተጨማሪም ግብአቶችን ከሂሳብ
ውጭ ላሉት የትምህርት ዓይነቶች እንዴት ውጤታማ በሆነ መንግድ መጠቀም እንደሚቻል የተሻለ ግንዛቤ አግኝቻለሁ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ከምናባዊ ት/ቤት ወጣ ብዬ ጊዜዬን መጠቀም በጣም ይከብደኝ ነበር፣ ምክንያቱም ብዙ የምሰራው ስለነበረኝ ነው፡፡
በጣም በመጠንቀቅ በታቀደው መሠረት ወደ ጉድኝት ማዕከል መሄዴን ማረጋገጥ ነበረብኝ ፣ ከሌሎች መምህራን ጋር በመስራቴ
አሁን ሁሉንም የምናባዊ ት/ቤት መምህራንን ለማገዝ የበለጠ በራሴ መተማመን ችያለሁ፡፡

የተ.ሙ.ማ ተሞክሮ ከምናባዊ ትምህርት ቤት

ስም: አልማዝ
ኃላፊነት ፡ የ 2 ኛ ሳይክል አዲስ አጀማመር መምህርነት በምናባዊ ት/ቤት

ባለፈው አመት ከተሙ.ማ ፍላጐቶችሽ አንዱ ምን ነበር?

ከገጠሙኝ ነገሮች ከባድ ሆኖ ያገኘሁት ክፍል ውስጥ በማስተምርበት ጊዜ ሁሉንም ተማሪዎች መቆጣጠር ነበር፡፡ በተለይ የ 2 ኛ
ሳይክል ተማሪዎችን በማስተምራቸው ርዕሶች ላይ ፍላጐት እንዲኖራቸው ማድረግ ከብዶኝ ነበር፡፡ በትምህርት ጊዜ ያወሩ ነበር፣
እንዲሁም የምሰጣቸውን የቤት ሥራዎች አይሰሩም ነበር፡፡
የተ.ሙ.ማ ፍላጐትሽን ለማሳካት ምን አደረግሽ?
ከአማካሪዬ ጋር ባካሄድነው አንድ ስብሰባ እርሱ በሚያስተምርበት ክፍል በመግባት የክፍል አያያዝ ክህሎት ላይ እንዳተኩር
ተስማማን፣ ከክፍል ምልከታው በኋላ አማካሪዬ በመማሪያ ክፍል ውስጥ ልጠቀምባቸው የምችለውን ስልቶች ከወረዳው
ሱፐርቫይዘር ሐሰን ጋር እንድወያይ አመቻቸልኝ፣ በተጨማሪም በሶስት ሳምንት ውስጥ ሶስት ክ/ጊዜዎችን ሳስተምር በመመልከት
የተማሪዎቿን ባህርይ እንዴት እንደምትቆጣጠር ልምድ እንድቀስም በምናባዊ ት/ቤት መሪ መምህራን ከሆኑት አንዷን ጠይቆልኝ
ነበር፡፡
የተ.ሙ.ማን ሞጁል ከተገበርሽ በኃላ ምን ለውጥ አገኘሽ?

56
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
ከሀሰን ጋር ከተወያየሁ በኃላ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ሙሉውን ጊዜ ሥራ ላይ እንዲውሉ የትምህርት ዕቅድን በጥንቃቄ
ማዘጋጀት ጀመርኩ፡፡ ይህም የተማሪዎችን መጥፎ ባህርይ ይቀርፋል፡፡ ተማሪዎችን ማመስገንና ማበረታታት ጀመርኩ፡፡ ይህም
ለመማር እንዲነሳሱ አስቻላቸው፡፡ እስካሁን የመሪ መምህርቷን ክፍለ-ጊዜ አንድ ጊዜ ብቻ ነው ልመለከት የቻልኩት፡፡
ምክንያቱም በጣም ሥራ ስለሚበዛበት ነው፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሜ ለመመልከት እሞክራለሁ፡፡ ምከንያቱም ከርሷ ብዙ የምማረው
ስላለ ነው፡፡ ከምልከታው በኋላ የቤት ስራ መስጠት ከማጠቃለያ በኋላ ሳይሆን በፊት መስጠት ጠቃሚ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡
ይህም ስለቤት ስራው ምን እንደፈለግሁ ለመግለጽ የተሻለ ጊዜ ሰለሚሰጠኝ ተማሪዎችን ግራ ከማጋባት ያድናል፡፡

የተ.ሙ.ማ ተሞክሮ ከምናባዊ ት/ቤት

ስም፡ ሀሰን
ኃላፊነት: የወረዳ ሱፐርቫይዘር በምናባዊ ት/ቤት
ባለፈው አመት ከተ.ሙ.ማ ፍላጐቶችህ አንዱ ምን ነበር?
በወረዳ ሱፐርቫይዘር የምመደብ መሆኑን መጀመሪያ ስሰማ በጣም ተደስቼ ነበር፡፡ ምክንያቱም በአካባቢው በሚገኘው ሁለተኛ
ደረጃ ት/ቤት በፊዚክስ መምህርነት በጣም እሰራ ስለነበረና ይህ ተገቢ ዕድገት ነው ብዬ ተሰማኝ፡፡ ሆኖም ሥራውን መስራት
ስጀምር ኃላፊነቱን ስለመውጣቴ እርግጠኛ አለመሆኔን ተረዳሁ፡፡ ለተማሪዎች፣ ለመምህራን እንዲሁም ጉድኝት ማዕከል ለሚገኝ
ማህበረሰብ አቅሜ የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ ከር/መምህራን ጋር የመስራት ልምድ አልነበረኝም፡፡ እነርሱም ከእኔ ምን
እንደሚጠብቁ እርግጠኛ አልነበርኩም፡፡
የተ.ሙ.ማ ፍላጐትህን ለማሳካት ምን አደረግህ?
“የክላስተር ሱፐርቫይዘር ሚና” በሚል በክልል የትም/ቢሮ የተካሄደውን አውደጥናት ተሳተፍኩ፣ በጣም ልምድ ያለውን የወረዳ
ሱፐርቫይዘር እንቅስቃሴ ለሁለት ቀናት በመከታተል ልምድ ቀሰምኩ፡፡
የተ.ሙ.ማን ሞጁል ከተገበርክ በኃላ ምን ለውጥ አገኘህ?
የአምስቱ ቀን አውደጥናት በኢንስፔክሽንና በሱርቪዥን መካከል ያለውን ልዩነት እንድረዳ አግዞኛል፡፡ ጉድኝት ማዕከል ውስጥ
የሚገኙ ት/ቤቶችን ስጐበኝ ምን ምን እንደምመለከት በመረዳቴ የበለጠ በራሴ እንድተማመን አስችሎኛል፡፡ የምከታተለውን
እንዳልረሳ የክትትል ቅጽ አዘጋጅቻለሁ፣ በአውደጥናቱ ውጤታማ ትምህርትን የሚያስገኘው ምን እንደሆነ ተረድቻለሁ፡፡ አሁን
የክፍል ውስጥ ምልከታ ሶስት ክፍሎች እንዳሉት አውቄአለሁ፤ እነርሱም ቅድመ ምልከታ ግንኙነት፣ የክፍል ውስጥ ምልከታ፣
ከምልከታ በኋላ/ድህረ ምልከታ ግንኙነት/ስብሰባ ናቸው፡፡
አሁን የበለጠ ልምድ ያላቸው ባልደረቦቼ ት/ቤቶችን ሲጐበኙ ስመለከት ር/መምህራንና መምህራን ከኔ ምን እንደሚጠብቁ
የተረዳሁ ይመስለኛል፡፡ አሁንም ቢሆን የረጅም ጊዜ የተ.ሙ.ማ ፍላጐቴን ለይቼ ከወረዳው ተ.ሙ.ማ ቅድሚያ ከተሰጣቸው
ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ሌላ ተ.ሙ.ማ ሞጁል ማዘጋጀት እፈልጋለሁ፡፡

References
Anderson, L. (2004) Increasing Teacher Effectiveness. Paris. UNESCO

Anderson, S.E. (Ed). 2002. School Improvement through Teacher Development. Lisse, The Netherlands.

57
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
Boyle, B., Boyle, T. & While, D. (2003) A Longitudinal Study of Teacher Change: What Makes Professional
Development Effective? Working Paper No.1, Institute for Political and Economic Governance (IPEG),
Manchester.

Craig, H.J., du Plessis, J. & Kraft, R.J. (1998) Teacher Development: Making an Impact. Washington DC,
USAID/ World Bank.

Egan, D. & Simmons, C. (2002) The Continuing Professional Development of Teachers: International and
professional contexts, Cardiff, UCW.
Engels, J. (2001) Making Classrooms Talk: Uganda Sustains Its Teacher Improvement and Support System.
Washington DC.
Feiman-Nemser, S., (2001) From Preparation to Practice: Designing a Continuum to Strengthen and Sustain
Teaching

Fredriksson, U. (2004) Quality Education: The Key Role of Teachers. Working Paper No. 14, Brussels,
Education International.

Hawley, W. & Valli, L. (1999) The Essentials of Effective Professional


Development: A New Consensus, in Darling-Hammond, L. & Sykes, G. (eds), Teaching as the Learning
Profession: Handbook of Policy and Practice, Jossey Bass, San Francisco.
Kubow, P. K. & Fossum, P.R. (2003) Comparative Education: Exploring Issues International Context. Upper
Saddle River NJ: Merrill Prentice Hall.

Leu, E. (2004) The Patterns and Purposes of School Based and Cluster Teacher Professional Development.
Washington, DC, USAID.

Leu, E. (2005) The role of teachers, schools and communities in quality education: A review of the Literature.
AEDGEC.

Leu, E., Hays, F., Leczel, D.K. & O’Grady, B. (2005) Quality Teaching: Building a Flexible and Dynamic
Approach. AEDGEC.
Lewin, K. M. & Stuart, J.S. (2003) Research Teacher Education: New Perspectives on Practice,
Performance and Policy. DFID Research Series 49a.
MacNeil, D. J. (2004) School- and Cluster-based Teacher Professional Development: Bringing
Teacher Learning to Schools. Working Paper 1. Washington DC. USAID, EQUIP1.

OECD Report, (2005:128)


Perspectives on Practice, Performance and Policy. (2003) MUSTER Synthesis Report, Sussex, DFID
Educational Papers.

Schwille, J. & Dembele, M. (2007). Global Perspectives on Teacher Learning: Improving policy and
practice. Paris, UNESCO.

Simpkins, K. (2009) Quality Education and the Essential Need for School Improvement. Unpublished
paper, Ministry of Education, Addis Ababa

58
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -
Soler, J., Croft, A. & Burgess, H. (eds) (2001) Teacher Development: Exploring our own practice.
London.

Sparks, D., and Loucks-Horsley, S., (1990) Handbook of Research on Teacher Education

Uganda Government. Development and Management Systems (TDMS) Programme, Kampala,


Ministry of Education and Sports.
Uganda Government. (2000) Final Report on the Evaluation of the Teacher. Kampala, Ministry of
Education and Sports.

Villegas-Reimers, E. (2003) Teacher Professional Development: An international review of the


literature. Paris, IIEP-UNESCO.

59
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች
ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ የተግባር መሳሪያዎች ቋት - -

You might also like