You are on page 1of 101

የግብረ ገብ ትምህርት የመምህሩ መምርያ

የግብረ ገብ ትምህርት
የመምህሩ መምርያ የግብረ ገብ ትምህርት
የመምህሩ መምርያ
6 ኛ
ክፍል 6 ኛ
ክፍል

ስድስተኛ ክፍል

አዲስ አበባ ከተማ


የኢትዮጵያ ፌደራላዊ
አስተዳደር ትምህርት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ
ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ቢሮ
ትምህርት ሚኒስተር
ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ ቢሮ
ትምህርት ቢሮ
የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 11
ትምህርት ሚኒስተር ትምህርት ሚኒስተር
መጽሐፉን በጥንቃቄ ይያዙ

ይህ መማሪያ መጽሐፍ የትምህርት ቤታችሁ ንብረት ነው እንዳይጠፋና


እንዳይጐዳ ጥንቃቄ ያድርጉ ለመጽሐፉ ጥንቃቄ ይረዳችሁ ዘንድ
እነዚህን አስር ነጥቦች ተግብሩ

1. መጽሐፉን በጋዜጣ ወይም በመጽሔት ሸፍኑ

2. መጽሐፉን ንፁህና ደረቅ ቦታ አስቀምጡ

3. መጽሐፉን ሲጠቀሙ እዳችሁ ንፁህ መሆኑን አረጋግጡ

4. በመጽሐፉ ሽፋንም ሆነ በውስጥ ገጽ ምንም ዓይነት ነገር እንዳትጽፉ

5. የመጽሐፉን ገጽ ምልክት ለማድረግ ቁራጭ ወረቀት ወይም ካርቶን ተጠቀሙ

6. ስዕልም ሆነ ገጽ ቆርጣችሀ አታውጡ

7. የተቀደዱ ገፆችን ማጣበቂያ በመጠቀም ጠግኑ

8. መጽሐፉን ቦርሳችሁ ውስጥ በጥንቃቄ አስገቡ

9. መጽሐፉን ለተማሪ ስታውሱ ጥንቃቄ አድርጉ

10. መጽሐፉን ለመጀመሪያ ጊዜ ስትጠቀሙ በጀርባው አስቀምጡ ለጊዜው የተወሰነውን ገጽ ክፈቱና


በጥንቃቄ ተጠቀሙ

እነዚህ የመጽሐፉን ሽፋን ደህንነት ይጠብቃሉ


የግብረ ገብ ትምህርት
የመምህር መምሪያ
6ኛ ክፍል
አዘጋጆች፡-ኢሳያስ ገ/ክርስቶስ (M.A)
ተመስገን ኤሊያስ (M.A)

አርታኢዎች፡-አብዮት ታከለ (M.A) የይዘት አርታኢ


ግርማ ገብሬ (PHD) የቋንቋ አርታኢ
መሰረት አሰፋ (PH.D) የስርዓተ ትምህርት አርታኢ
ሰዓሊ ኤልያስ ወንድምአገኝ (M.Sc.)
ሌይአውት ዲዛይነር ኃይለጊዮርጊስ ተመስገን (አስማምቶ የሰራው)
ዮሐነስ ቢያድግልኝ (M.Sc)
ተርጓሚዎች ደስታ አበባው (M.A)
ነስረዲን ሐሰን (M.A)
አርታኢና ገምጋሚ ገበየሁ አስፋው (M.A)

አስተባባሪ ጌታቸው ታለማ (M.A)

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ
የኢትዮጵያ
ዲሞክራስያዊፌደራላዊ
ሪፐብሊክ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ
ትምህርት ሚኒስተር ትምህርት ቢሮ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ትምህርት ሚኒስተር
የግብረ ገብ ትምህርት
የመምህሩ መምርያ
6ኛ ክፍል

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አዲስ አበባ ከተማ


ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ አስተዳደር ትምህርት
ትምህርት ሚኒስተር ቢሮ
መግቢያ
የሰው ልጅ ምክኒያታዊ ፍጡር መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህም ባህሪ የሰው ልጆችን ከሌሎች እንሰሳት

የሚለይና ራሳቸውን በማሻሻል ወደ አለሙት ግብ ለመድረስ በሚያደርጉት ሂደት የሚገነባ ነው፡፡ ይህን

ልዩ የሚያደርጋቸውን ባህሪ ለመገንባት የሰው ልጅ ድርጊት በምክኒያት እንዲሁም በግብረ ገብ ዕሴቶች

እና መርሆች የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ የሰው ልጆች ከሌሎች እንሰሳት ልዩ የሚያደርጋቸው

ምክኒያታዊ አስተሳሰብን ስለተላበሱ ነው፡፡

የሰው ልጅ ለተተኪው ትውልድ ትምህርት፣ ስልጠና እንድሁም የሂወት መመሪያ በመስጠት በማህበረሰቡ

ውስጥ እንዲኖር የሚያደርግ ብቸኛው ምክኒያታዊ ፍጡር ነው፡፡

የሰው ልጅ ባህሪና ችሎታ በተፈጥሮ የሚወረስ ሳይሆን በትምህርት የሚገኝ ነው፡፡ የሰው ልጅ የመማር

ችሎታው አይተኬ ነው፡፡ ይህ ባህሪ ያለሙትን ግብ ለማሳካት እና ቀጣይነት ያለው ግብረገባዊነትን ለመላበስ

ይረዳቸዋል፡፡ ምንም እንኳን የሰው ልጆች በማህበራዊ ግንኙነትና በማህበራዊ ጉዳይ ያለው ባህሪ ስልጡን

ቢሆኑም ግብረገባዊነታቸው ግን በቂ አይደለም፡፡ የሰው ልጅ መልካም ይሆን ዘንድ መማር እንዳለበት

ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ጥሩነት በሂደት የምናገኘው እንጂ አብሮን የሚወለድ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው

የሰው ልጆች የግብረ ገባዊ ግዴታዎችን የመፈፀም አቅም አላቸው፡፡ መልካምነት ወይም ደግነትን ማጎልበት

ተደጋጋሚ የግብረ ገብ ድርጊቶችን የመፈፀም ጥረትን ይጠይቃል፡፡ በተጨማሪም የሰው ልጆች ማህበራዊ

ፍጡር መሆናቸው ጥርጥር የለውም፡፡ በሌላ አገላለጽ ግብረገባዊነት ከሰው ልጆች የዕለት ተዕለት መሰረታዊ

እንቅስቃሴያቸው ጋር የተያያዘ ማህበራዊ ተግባር ነው፡፡ ያለማህበራዊ ምህዳር የሰው ልጆች ግብረገባዊ መሆን

አይችሉም ፡፡ ማህበረሰቡም የግለሰቦች ድምር ውጤት ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም ገጽታዎች እርስ በርሳቸው

ተመጋጋቢ ናቸው፡፡

ማንኛውም ማህበረሰብ የራሴ የሚላቸው ጤናማ ፣ ታሳቢና የሚጠበቅ መልካም ስብዕናዎች አሉት፡፡ ስለዚህ

እነዚህ የሚጠበቁ የማህበረሰብ ልምዶች ማህበረሰቡ በሰላም እንዲሰራ እንደ የባህሪ መመሪያ በመሆን

የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ማህበረሰብ እንዲቀጥል የተሰማማባቸውን ማህበራዊ ህጐችና ልምዶች

ለትውልድ ማስተላለፍ አለበት፡፡ እርግጥ ነው ሰዎች ማህበራዊ ደንቦችን ካልተማሩ በስተቀር ተገዢ ሊሆኑ
አይችሉም፡፡ በዚህ ሂደት ለ ወጣቱ የህብረተሰቡን ደንብ በማስተማር እንዲሁም መጣስ እንደሌለባቸው

በማሳወቅ ረገድ ማህበረሰቡ ጉልህ ሚና አለው፡፡ ህዝቦች ማህበራዊ ህጎቻቸውን የሚማሩት በአስገዳጅነት
ሁኔታ ነው፡፡ በሌላ አባባል ሰዎች የማህበረሰባቸውን ደንቦች ሲማሩ ለደንቦቹ የመታዘዝ ስሜት ይኖራቸዋል፡፡

የህብረተሰቡ የአኗኗር ዘይቤዎች በዕለት ተዕለት ህይወታቸው የዳበሩ ናቸው፡፡


የግብረገባዊነት መመሪያ ህብረተሰቡ ምን ማድረግ እንዳለበትና እንደሌለበት አቅጣጫ የሚሰጥ ነው፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል I


ግብረ ገብ እያንዳንዱ ሰው ሊከተላቸው የሚገቡ ህጐችን ያካተተ ስለሆነ አብዛኛው ሰው ይገነባበታል፡፡ ምንም
እንኳ ህጐቹ ነፃነት ገዳቢ ቢሆኑም የሰወችን ደህንነት እና አብሮ የመኖር ህልውና ከማስጠበቅ አኳያ ከፍተኛ
ሚና ስላላቸው ሰዎች ሊያከብሯቸው ይገባል፡፡ በአጠቃላይ ግብረ ገብ የሚከተሉት አምስት ዓላማዎች አሉት፡
-

1. ህብረተሳቡን ከመለያየት መታደግ፡፡

2. የሰዎችን ስቃይ መቀነስ፡፡

3. የሰውን ልጅ ማበልፀግ፡፡

4. ፍትሀዊና አግባብነት ባለው መንገድ ግጭቶችን መፍታት፡፡

5. ሙገሳን፣ ወቀሳን፣ ሽልማትን እንድሁም ቅጣትን ተግባራዊ ማድረግ፡፡

ግብረ ገብነት የህብረተሰብ ደህንነት ከመጠበቅ ጋር ተመሳሳይ ከመሆናቸውም ባሻገር የማህበረሰቡ የጋራ
ግብ መዳረሻዋች ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት የግብረ ገብ ትምህርት ለሰው ልጅ ህልውናና ብልጽግና አስፈላጊ ነው፡፡ የሰለጠነና ነፃ ህዝብ
እንዲኖር ለግብረ ገብ ዕሴቶች የበለጠ ዋጋ መሰጠት አለበት፡፡

ግብረ ገብነት የተሻለ ኑሮ ለመኖር የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ እስካሁንም ሰዎች የግብረ ገብ ህግና መርህ
አላቸው፡፡ ግን ህዝቦች ለእነዚህ ህጐች አጽንኦት እና ትኩረት ካልሰጡ የህጎቹ መኖር ብቻ ለመልካምነት
ዋስትና አይኖራቸውም፡፡ ለግብረ ገብ መርሆች ትኩረት መስጠት ለህልውናና ለአብሮነት ብዙ አስተዋጽኦ
እንዲያበረክቱ ያደርጋል፡፡

ይሁን እንጂ የግብረ ገብ እሴቶች የሰው ልጅን በራሱ ወገን መጥፎ እንዳይሰራ ወደሚችልበት ደረጃ
አላደረሱትም፡፡ በዚህ ምክንያት የግብረ ገብ ትምህርት ከወትሮው በበለጠ አስፈላጊ ሆኖ ተግኝቷል፡፡ የግብረ
ገብ ዕሴቶቻችንን በውስጣችን ማስረጽ ከቻልን የሰው ልጅ ኢ ሰብዓዊ ድርጊትን መቀነስ እንችላለን፡፡

II የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ይዘት ------------------------------------------------------------------------------------------------------- v
መግቢያ --------------------------------------------------------------------------------------------------------------VII
1 ተመራጭ የማስተማሪያ ስነ ዘዴ ----------------------------------------------------------------------------VIII
1.1 የማነቃቂያ ተግባራት -------------------------------------------------------------------------------VIII
1.2 ንባብ ------------------------------------------------------------------------------------------------VIII
1.3 ውስን ጥናት ---------------------------------------------------------------------------------------VIII
1.4 ጥያቄና መልስ -------------------------------------------------------------------------------------VIII
1.5 የቡድን ውይይት-----------------------------------------------------------------------------------VIII
1.6 ቡድን ማዋቀር---------------------------------------------------------------------------------------IX
1.7 አካታችነት -------------------------------------------------------------------------------------------IX
1.8 ውስጥን የማየት ተግባር-----------------------------------------------------------------------------X
1 የግብረ ገብ ምሉዕነት------------------------------------------------------------------------------------------------1
1.1ክፍለ ትምህርት 1: የግብረ ገብ ምሉዕነት ምንነት ----------------------------------------------------------1
1.1.1 የመማር ብቃት ----------------------------------------------------------------------------------------1
1.1.2 ይዘት ---------------------------------------------------------------------------------------------------2
1.1.3 አጭር ገለፃ --------------------------------------------------------------------------------------------2
1.1.4 የመማር ማስተማር ሂደት ---------------------------------------------------------------------------2
1.1.5 የተግባራት መልሶች ----------------------------------------------------------------------------------3
1.2 ክፍለ ትምህርት 2: የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫወች -------------------------------------------------4
1.2.1 የመማር ብቃት ---------------------------------------------------------------------------------------4
1.2.2 ይዘት---------------------------------------------------------------------------------------------------4
1.2.3 አጭር ገለፃ --------------------------------------------------------------------------------------------4
1.2.4 የመማር ማስተማ ሂደት------------------------------------------------------------------------------4
1.2.5 የተግባራት መልሶች ----------------------------------------------------------------------------------6

1.3ክፍለ ትምህርት3: የግብረ ገብ ምለዕነት ጥቅም ------------------------------------------------------------7


1.3.1 የመማር ብቃት----------------------------------------------------------------------------------------7
1.3.2 ይዘት ---------------------------------------------------------------------------------------------------7
1.3.3 አጭር ገለፃ --------------------------------------------------------------------------------------------7
1.3.4 የመማር ማስተማር ሂደት ---------------------------------------------------------------------------7
1.3.5 የተግባራት መልሶች --------------------------------------------------------------------------------8
ክፍለ ትምህርት 4: የግብረ ገብ ምሉዕነት ያላቸው ሰወች ባህሪያት--------------------------------------9
1.4.1 የመማር ብቃት.-------------------------------------------------------------------------------------9
1.4.2 ይዘት -------------------------------------------------------------------------------------------------9
1.4.3 አጭር ገለፃ ------------------------------------------------------------------------------------------9
1.4.4 የመማር ማስተማር ሂደት -------------------------------------------------------------------------9
1.4.5 የተግባራት መልሶች -------------------------------------------------------------------------------10
1.5 ክፍለ ትምህርት 5: የግብረ ገብ ምሉዕ አለመሆን የሚያስከትላቸችግሮች -------------------------------11
1.5.1 የመማር ብቃት -------------------------------------------------------------------------------------11
1.5.2 ይዘት ------------------------------------------------------------------------------------------------11
1.5.3 አጭር ገለፃ -----------------------------------------------------------------------------------------11
1.5.4 የመማር ማስተማር ሂደት-------------------------------------------------------------------------11
1.5.5 የተግባራት መልሶች -------------------------------------------------------------------------------13
1.6 የምዕራፉ ትያቄ መልሶች ------------------------------------------------------------------------------13

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል III


2 ለህግ ተገዢ መሆን ------------------------------------------------------------------------------------------15
2.1 ክፍለ ትምህርት 1: ለህግ ተገዥ የመሆን ፅንሰሀሳብ --------------------------------------------------15
2.1.1 የመማር ብቃት ----------------------------------------------------------------------------15
2.1.2 ይዘት ----------------------------------------------------------------------------------------15
2.1.3 አጭር ገለፃ --------------------------------------------------------------------------------16
2.1.4 የመማር ማስተማር ሂደት ----------------------------------------------------------------16
2.1.5 የተግባራት መልሶች -----------------------------------------------------------------------17
2.2 . ክፍለ ትምህርት 2: ለህግ ተገዢ የመሆን አስፈላጊነት ----------------------------------------------18
2.2.1 የመማር ብቃት ----------------------------------------------------------------------------18
2.2.2 ይዘት ---------------------------------------------------------------------------------------18
2.2.3 አጭር ገለፃ --------------------------------------------------------------------------------18
2.2.4 የመማር ማስተማር ሂደት ---------------------------------------------------------------18
2.2.5 የተግባራት መልሶች -----------------------------------------------------------------------20

2.3 ክፍለ ትምህርት3: ለህግ ተገዥ የሆነ ሰው ባህሪያት ----------------------------------------------------21


2.3.1 የመማር ብቃት ----------------------------------------------------------------------------21
2.3.2 ይዘት ---------------------------------------------------------------------------------------21
2.3.3 አጭር ገለፃ --------------------------------------------------------------------------------21
2.3.4 የመማር ማስተማር ሂደት ----------------------------------------------------------------21
2.3.5 የተግባራት መልሶች -----------------------------------------------------------------------22
2.4 ክፍለ ትምህርት 4: ለህግ ተገዥ ያለመመሆን የሚያስከትለው ችግር. ----------------------------------23
2.4.1 የመማር ብቃት ----------------------------------------------------------------------------23
2.4.2 ይዘት -------------------------------------------------------------------------------------------------23
2.4.3 አጭር ገለፃ ------------------------------------------------------------------------------------------23
2.4.4 የመማር ማስተማር ሂደት -------------------------------------------------------------------------23
የምዕራፉ ጥያቄ መልሶች --------------------------------------------------------------------------------25
3 መልካም ስነምግባር -------------------------------------------------------------------------------------28
ክፍለ ትምህርት 1: የመልካም ስነ ምግባር ትረጉም ---------------------------------------------------28
3.1.1 የመማር ብቃት --------------------------------------------------------------------------------------28
3.1.2 ይዘት -------------------------------------------------------------------------------------------------28
.
3.1.3 አጭር ገለፃ ------------------------------------------------------------------------------------------28
3.1.4 የመመር ማስተማር ሂደት -------------------------------------------------------------------------28
3.1.5 የተግባራት መልሶች ---------------------------------------------------------------------------------28
ክፍለ ትምህርት 2: መልካም ስነ ምግባር ያለው ግለሰብ ባህሪያት --------------------------------------30
3.2.1 የመማር ብቃት -------------------------------------------------------------------------------------30
3.2.2 ይዘት ------------------------------------------------------------------------------------------------30
3.2.3 አጭር ገለፃ ------------------------------------------------------------------------------------------31
3.2.4 የመማር ማስተማር ሂደት --------------------------------------------------------------------------31
3.2.5 የተግባራት መልሶች ---------------------------------------------------------------------------------33
ክፍለ ትምህርተ 3: የመልካም ስነ ምግባር ባለቤት የመሆን ጥቅም -----------------------------------35
3.3.1 የመማር ብቃት --------------------------------------------------------------------------------------35

IV የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


3.3.2 ይዘት -------------------------------------------------------------------------------------------------------35
3.3.3አጭር ገለፃ --------------------------------------------------------------------------------------------------36
3.3.4 የመማር ማስተማር ሂደት -------------------------------------------------------------------------------36
3.3.5 የተግባራት መልሶች ---------------------------------------------------------------------------------------37
ክፍለ ትምህርት 4: የመልካም ስነ ምግባር ማሳደጊያ መንገዶች ----------------------------------------------38
3.4.1 የመማር ብቃት --------------------------------------------------------------------------------------------38
3.4.2 ይዘት -------------------------------------------------------------------------------------------------------38
3.4.3 አጭር ገለፃ ------------------------------------------------------------------------------------------------38
3.4.4 የመማር ማስተማር ተግባር ------------------------------------------------------------------------------38
የምዕራፉ ጥያቄ መልሶች
4 የማህበራዊ ምጣኔ ተሳትፎ -----------------------------------------------------------------------------------46
ክፍለ ትምህርት 1: የማህበራዊ ምጣኔ ተግባራት ---------------------------------------------------------------46
4.1.1 የመማር ብቃት --------------------------------------------------------------------------------------------46
4.1.2 ይዘት -------------------------------------------------------------------------------------------------------46
4.1.3 አጭር ገለፃ ------------------------------------------------------------------------------------------------47
4.1.4 የመማር ማስተማር ሂደት --------------------------------------------------------------------------------47

4.1.5 የተግባራት መልሶች


ክፍለ ትምህርት 2 የበጎ ፈቃድ ተግባር ----------------------------------------------------------------------------49
4.2.1 የመማር ብቃት ------------------------------------------------------------------------------------49
4.2.2 ይዘት -----------------------------------------------------------------------------------------------49
4.2.3 አጭር ገለፃ ---------------------------------------------------------------------------------------50
4.2.4 የመማር ማሰተማር ሂደት -----------------------------------------------------------------------50
4.2.5 የተግባራት መልሶች -------------------------------------------------------------------------------51
ክፍለ ትምህርት 3: ትርፍ ጊዜን ለጋራ ጥቅም ማዋል -----------------------------------------------------------52
4.3.1 የመማር ብቃት ------------------------------------------------------------------------------------52
4.3.2 ይዘት------------------------------------------------------------------------------------------------52
4.3.3 አጭር ገለፃ ----------------------------------------------------------------------------------------52
4.3.4 የመማር ማስተማር ሂደት ------------------------------------------------------------------------52
4.3.5 የተግባራት መልሶች -------------------------------------------------------------------------------54

4.4 ክፍለ ትምህርት 4: የታማኝግብር ከፋይና ቁጠባ ለማህበራዊ ምጣኔ ያለው ሚና ---------------------55

4.4.1 የመማር ብቃት -----------------------------------------------------------------------------------55


4.4.2 ይዘት -----------------------------------------------------------------------------------------------55
4.4.3 አጭር ገለፃ ----------------------------------------------------------------------------------------55
4.4.4 የመማር ማስተማር ሂደት -----------------------------------------------------------------------55

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል V


4.5 የምዕራፉ ጥያቄ መልሶች -----------------------------------------------------------------------------------58

5 የሀገር ፍቅር ስሜት -------------------------------------------------------------------------------------------60


ክፍለ ትምህርት 1: የሀገር ፍቅር ትርጉም ---------------------------------------------------------------------60
5.1.1 የመማር ብቃት --------------------------------------------------------------------------------------60
5.1.2 ይዘት--------------------------------------------------------------------------------------------------60
5.1.3 አጭር ገለፃ ------------------------------------------------------------------------------------------61
.
5.1.4 የመማር ማስተማር ሂደት --------------------------------------------------------------------------61
5.1.5 የተግባራት መልሶች --------------------------------------------------------------------------------62
ክፍለ ትምህርት 2: የሃገር ፍቅር መገለጫወች ----------------------------------------------------------------62
5.2.1 የመማር ብቃት --------------------------------------------------------------------------------------62
5.2.2 ይዘት -----------------------------------------------------------------------------------------------62
5.2.3 አጭር ገለፃ ------------------------------------------------------------------------------------------63
5.2.4 የመማር ማስተማር ሂደት -------------------------------------------------------------------------63
5.2.5 የተግባራት መልሶች --------------------------------------------------------------------------------64
ክፍለ ትምህርት 3: ሃገር ወዳድ የመሆን ጥቅም --------------------------------------------------------------64
5.3.1 የመማር ብቃት --------------------------------------------------------------------------------------64
5.3.2 ይዘት ------------------------------------------------------------------------------------------------65
5.3.3 አጭር ገለፃ -----------------------------------------------------------------------------------------65
5.3.4 የመማር ማስተማር ሂደት --------------------------------------------------------------------------------65
5.3.5 የተግባራት መልሶች ----------------------------------------------------------------------------------------66

ክፍለ ትምህርት 4: የሀገር ወዳድ ዜጋ ባህሪያት ----------------------------------------------------------------66


5.4 ክፍለ ትምህርት 4: የሀገር ወዳድ ዜጋ ባህሪያት ----------------------------------------------------------66
5.4.1 የመማር ብቃት፡ ---------------------------------------------------------------------------------------------66
5.4.2 ይዘት --------------------------------------------------------------------------------------------------------66
5.4.3 አጭር ገለፃ --------------------------------------------------------------------------------------------------67

5.4.4 የመማር ማስተማር ሂደት ---------------------------------------------------------------------------------68

5.4.5 የተግባራት መልሶች ----------------------------------------------------------------------------------------68


5.5 ክፍለ ትምህርት 5: የሀገር ፍቅር ---------------------------------------------------------------------------68
5.5.1 የመማር ብቃቶች -------------------------------------------------------------------------------------------68
5.5.2 ይዘት --------------------------------------------------------------------------------------------------------69
5.5.3 አጭር ገለፃ ------------------------------------------------------------------------------------------------69

5.5.4 የመማር ማስተማር ሂደት ---------------------------------------------------------------------------------69


5.5.5 የተግባራት መልሶች ----------------------------------------------------------------------------------------70
5.6 የምዕራፉ ማጠቃለያ መልሶች --------------------------------------------------------------------------------70

VI የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


6 ሰላምና መተባበር -----------------------------------------------------------------------------------------------72
6.1 ክፍለ ትምህርት 1: የሰላም ትርጉም -----------------------------------------------------------------72
6.1.1 የመማር ብቃት ------------------------------------------------------------------------------------72
6.1.2 ይዘት ------------------------------------------------------------------------------------------------72
6.1.3 አጭር ገለፃ -----------------------------------------------------------------------------------------73
6.1.4 የመማር ማስተማር ሂደት ------------------------------------------------------------------------73
6.1.5 የተግባራት መልሶች ------------------------------------------------------------------------------74
6.2 ክፍለ ትምህርት ሁለት 2: መተባበር -----------------------------------------------------------------75
6.2.1 የመማር ብቃት ------------------------------------------------------------------------------------75
6.2.2 ይዘት -----------------------------------------------------------------------------------------------75
6.2.3 አጭር ገለፃ -------------------------------------------------------------------------------------75
6.2.4 የመማር ማስተማር ሂደት -----------------------------------------------------------------------75
6.2.5 የተግባራት መልሶች ------------------------------------------------------------------------------76
6.3 ክፍለ ትምህርት 3: የሰላምና የመተባበር ዝምድና --------------------------------------------------------77
6.3.1 የመማር ብቃት ------------------------------------------------------------------------------------77
6.3.2 ይዘት -----------------------------------------------------------------------------------------------77
6.3.3 አጭር ገለፃ ----------------------------------------------------------------------------------------77
6.3.4 የመማር ማስተማር ሂደት -----------------------------------------------------------------------77
6.3.5 የተግባራት መልሶች -----------------------------------------------------------------------------78

6.4 የምዕራፉ ጥያቄ መልሶች

ዋቢ መፅሐፍት --------------------------------------------------------------------------------------77-83

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል VII


መቅደም
መምህራን እንደሚገነዘቡት የግብረ ገብ ትምህርት ዓላማ ጥሩውን ከመጥፎ የመለየትና የመምረጥ አቅም
ያለው ትውልድ ለመፍጠር ነው፡፡ ይህ እውን የሚሆነው ተማሪዎች ከአፍላ እድሜያቸው ጀምሮ የግብረ ገብ
ዕሴቶችን ሲማሩ ብቻ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የክፍል ደረጃ የተዘጋጀው የግብረ ገብ መጽሐፍ የተማሪዎችን
አማካይ እድሜ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ይህ እንዲሆን የተደረገው ተማሪዎች የግብረ ገብ ጽንስ ሀሳብን
በቀላሉ አንዲረዱት ለማስቻል ነው፡፡ መጽሐፉ ተማሪዎች የሚኖሩበትን የማህበረሰብ እሴቶች እንዲያካትት
ለማድረግ ከፍተኛ ጥንቃቄና ጥረት ተደርጓል፡፡
ይህ ሁሉ ጥረት ፍሬ ሊያፈራ የሚችለው ትምህርቱ ለተማሪዎች ሳቢ እንዲሆን መምህሩ መሰዋዕትነት
የታከለበት ጥረት ሲያደርግ ነው፡፡ ይህን ጉዳይ ከማሳካት አንፃር የተማሪዎች ተሳትፎ የማይተካ ሚና
ይኖረዋል፡፡
የመጽሐፉ መምሪያ የሚጀምረው በመግቢያ ገጽ ሆኖ ዋና የማስተማሪያ ስነ ዘዴ፣ የምዘና ዘዴና ለእያንዳንዱ
ምዕራፍ ሊያገለግሉ የሚችሉ ተጨማሪ አጋዥ ነገሮችን ያካተተ ነው፡፡

1. ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች


እነዚህ ዘዴዋች ተማሪዎች ቀደም ሲል ከ6ኛ ክፍል በፊት በነበረው የግብረ ገብ መጽሐፋቸው ላይ በተካተቱት
እሴቶች ዙሪያ ተወያይተውባቸው ስላለፉ ትምህርቱን እስካሁን ምን ያህል እንደተረዱት ለመፈተሸ
የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ለዚህም የተማሪዎች ተሳትፎ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

በክፍል ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማድረግ

ተማሪዋች ክፍል ውስጥ በንቃት ሲሳተፉ በራሳቸው የመተማመን፣ ከሌሎች ጋር በአብሮነት የመስራት፣
ችግሮችን የመፍታት፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ራሳቸውን የማጎለበት ወዘተ አቅም ያገኛሉ፡፡ ስለዚህም
መምህራን እያንዳንዱን ተማሪ መጽሐፉ ላይ የተካተቱ የተለያዩ ድርጊቶች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ
ማበረታታት አለባቸው፡፡ ለዚህም መምህራን የሚከተሉትን ማረጋገጥ አለባቸው፡-
• እያንዳንዱ የቡድን አባል የራሱን ሀሳብ ተራ በተራ ማቅረቡን

• ተማሪዎች በራሳቸው ርዕስ ምርጫ ተማሪዎች ፊት ንግግር ማቅረባቸውን

• የፆታ ፣ የሀይማኖት፣ የዘር እና የመሳሰሉ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ ማስገባታቸውን

በዚህ የማስተማር ስነ ዘዴ የመምህራን ሚና ተማሪዎች የተሰጣቸውን ተግባራት እንዴት እንደሚያስኬዱ


መመሪያ መስጠት ነው፡፡ ስለዚህ መምህሩ በመማር ማስተማር ሂደት አመቻች መሆን እንጂ በበላይነት
ተግባራት ላይ መሳተፍ የለበትም፡፡

VIII የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


1.1. ማነቃቂያ

ይህ ስነ ዘዴ የእለቱን የትምህርት ርዕስ ለማስተዋወቅ ይጠቅማል፡፡ ተማሪዎች በትምህርቱ ዙሪያ ያላቸውን


አረዳድ ለመፈተሽ ከአርዕስቱ ጋር ተያያዥነት ያለው ጠቅለል ያለ ጥያቄ ማቅረብ ላይ ያተኩራል፡፡ ይህን
ማድረግ ተማሪዎች እንዲነቃቁ ስለርዕሱ ነባር ግንዛቤአቸውን እንዲጠቀሙ፣ መምህሩ የእለቱን የትምህርት
ርዕስ እንዲያስተዋውቅ እና ተማሪዎችን ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማድረግ ያስችላቸዋል፡፡
ውድ መምህር! የማነቃቂያ ተግባሩን ከተማሪዎች ጋር ሲያከናውኑ ከ4-5 ደቂቃ ይጠቀሙ፡፡

1.2. ንባብ
የግብረ ገብ ትምህርት ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ይሰጣል፡፡ ስለዚህ 6ኛ ክፍል ሲደርሱ አሁን በሚማሩት የክፍል
ደረጃ በሚነሱ ጉዳዮች ላይ የተወሰኑ መሰረታዊ ሀሳቦች እንዲኖራቸው ይጠበቃል፡፡ እድሚያቸው እየጨመረ
በሄደ ቁጥር በሚነሱ ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ንባብ እንዲያደረጉ መበረታታት አለባቸው፡፡ እንደ ግብረ ገብ
ምሉዕነት፣ ማህበራዊ ምጣኔ፣ ተግባራትና የሀገር ፍቅር ያሉት ፅንሰ ሀሳቦች ተጨማሪ ንባብ ይጠይቃሉ፡፡

1.3. ውስን ጥናት

የ6ኛ ክፍል የግብረ ገብ ትምህርት በተማሪዎች የወደፊት አርቆ የማሰብ አቅም ላይ ተጽዕኖ መፍጠር
የሚችሉ ውስን ጥናትና ነባራዊ ሁኔታዋች አሉት፡፡ የተማሪዎቹ የመማሪያ መጽሐፍት ውስጥ የሚገኙ ውስን
ጥናቶች የህብረተሰቡን አሁናዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገቡ ናቸው፡፡

1.4. ጥያቄና መልስ

የጥያቄና መልስ ዘዴን አዘውትረው ይጠቀሙ፡፡ በተለይም በገለፃ እና በቡድን ውይይት ወቅት አለፍ አለፍ ብለው
ጥያቄ ይጠይቋቸው መልስም እንዲመልሱ ዕድል ይስጧቸው፡፡ ውድ መምህር ይህን ዘዴ የተማሪዎችን
ተሳትፎና ውጤት ለመገምገም ይጠቀሙበት፡፡ ለዚህ ዘዴ ጥሩው መንገድ ጥያቄ መጠየቅና ጥያቄውን ገታ
አድርጐ ክፍሉን በአይንዎ በመቃኘት አንዳንድ ተማሪዎችን መልስ እንዲመልሱ መጠየቅና መልስ የሚመልሱ
ተማሪዎችን ማድነቅ ነው፡፡ ተማሪዎች ጥያቄውን ለመመለስ ከባድ ሆኖ ካገኙት ጥያቄውን ሰሌዳ ላይ ይጻፉና
ተጨማሪ ማብራሪያ ይስጧቸው፡፡

በጥያቄና መልሱ ጊዜም የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች ይከተሉ፡


• ጥያቄዎቹ አጭርና ግልፅ ይሁኑ

• አስፈላጊ ነው ብለው ካሰቡ ጥያቄውን ረዘም ላለ ጊዜ ይስጡ

• አስፈላጊ ሆኖ ካገኙት የተለያየ የትምህርት አቀባበል ደረጃ ያላቸውን ተማሪዎች ሊያሳትፍ የሚችል
ጥያቄ ይጠይቁ አንድ ጥያቄ በቂ ሆኖ ሳይገኝ ሲቀር ብዛት ያላቸው ጥያቄዎችን ይጠይቁ

• ተሳትፎን በሙገሳ ወይም በሌላ መንገድ ያበረታቱ

1.5 የቡድን ውይይት


የቡድን ውይይት በጥንድ ፣ ክብ በመስራት ወይንም ክፍሉ በሙሉ እንደ ቡድን በመሆን ሊከናወን ይችላል፡፡
ውይይት የተማሪዎችን ተሳትፎ ያሳልጣል፡፡ በተለይ በክፍል ውስጥ ብዙ ተማሪዎች ሲኖሩ፡፡ በሁሉም
ምዕራፍ ተማሪዎች በቡድን የሚሰሯቸው የተለያዩ ተግባራት ተቀምጠዋል፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል IX


ተማሪዎችን በሆነ ርዕስ እንዲወያዩ ሲያረጉ፡-
• እያንዳንዳቸው ተማሪዎች እየተወያዩ መሆን አለመሆናቸውን እንዲሁም እንዴት እንደሚሳተፉ
ይከታተሉ

• በተወሰኑ ቡድኖች የውይይቱ አካል በመሆን ውይይቱ በታለመው መንገድ መሄዱን ይከታተሉና
እንዳስፈላጊነቱ ለተማሪዎችን እገዛ እና አቅጣጫ ይስጡ

• ተማሪዎች በአንዳንድ ነጥቦች ላይ ግራ ሲጋቡ እና ችግር ሲያጋጥማቸው ፍንጭ ይስጡ

• በአንድንድ ሁኔታዎች ውይይቱን ለማሳለጥና በተፈለገው አቅጣጫ እየሄደ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ


ከውይይቱ ርዕስ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ይጠይቁ

• እያንዳንዱ ተማሪ በውይይቱ እንዴት እየተሳተፈ እንደሆነ ይመልከቱ ተሳትፎ የማያደርጉት


ተማሪዎችን እንዲሳተፉ ያድርጉ

• የራስወን መንገድ እና ክህሎት ተጠቅመው ተማሪወችን ያበረታቱ

1.6 የውይይት ቡድን ማዋቀር


ከርዕሱ ባህሪ እና እንዲፈጽሙ ከሚሰጣቸው ተግባር በመነሳት ተማሪዎችን ማዋቀር ይችላሉ፡፡ ተማሪዎችን
በቡድን ለማዋቀር የሚከተሉትን ዘዴዎች መከተል ይችላሉ፡-
• በዘፈቀደ ማቧደንን

• ችሎታን መሰረት ያረገ ማቧደን

• የእጣ ዘዴ በመጠቀም ማቧደን

ቅደም ተከተሎች፡-

• ከሶስት እስከ ስድስት ተማሪዎች በያዘ አወቃቀር ክፍሉን በአነስተኛ ቡድኖች መክፈል
• ወንበሮችን ክብ በመስራት ፊት ለፊት እንዲተያዩ በማድረግ ማስቀመጥ
• የሚወያዩበትን ርዕስ በሚረዱት ቋንቋ ለተማሪዎች መንገር
• የቡድኑ ሰብሳቢና ፀሀፊ መምረጥ
• ለውይይት የሚሰጣቸውን ሰዓት ማሳወቅ
• የውይይት ሰዓታቸው ከማለቁ በፊት የቀራቸውን ደቂቃ ማሳወቅ
• ተማሪዎች ያቀረቧቸውን ሀሳቦች አስመልክቶ ለተማሪዎች መልስ መስጠትና ማጠቃለል

1.7 ማጠቃለያ
ውድ መምህር፡- ክፍል ውስጥ በሚካሄደው እያንዳንዱ የመማር ተግባር የሁሉንም ተማሪዎች ልዩነት
ማለትም የፆታን፣የችሎታን እንዲሁም የአካል ውስንነትን ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርቦዎታል፡፡
• በተማሪዎች መካከል የሚኖሩ ልዩነቶችን ማክበርና መቻቻል እንዳለባቸው ግንዛቢያቸውን
ያሳድጉ

• በመማር ሂደት የሚያጋጥሙ መስናክሎችን መለየት፣ መፍታትና በተማሪዎች መካከል


መተባበርን ያጎልብቱ

X የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


1.8 ሀሳብን ለማሰላሰል የሚያገለግሉ ተግባራት
ሀሳብን ለማሰላሰል የሚረዱ ተግባራት ግልጋሎታቸው አቅጣጫ መስጠት ብቻ ነው፡፡ እነዚህም ተግባራት
በሌላ አማራጭ ድርጊቶች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ተጨማሪ ተግባራቶች ተማሪዎች በእያንዳንዱ ድርጊት ምን
እንደሚያስፈልጋቸው እንዲገነዘቡ ያግዛቸዋል፡፡ ከእያንዳንዱ ድርጊት ቀጥሎ የተሰነዘሩ መልሶች ይቀርባሉ፡፡
ለምሳሌ ለራስ ዋጋ በመስጠት ጽንስ ሀሳብ ውይይት ላይ ተጨማሪ ተግባር የአፈፃፀም መመሪያ ሰጪ
በመሆን ሊካተቱ ይችላሉ፡፡
ማስታወሻ መስጠት
መምህሩ ጥልቅ የሆነ ማስታወሻ ሰሌዳ ላይ መስጠት አይጠበቅበትም ፡፡ ምንም እንኳን መምህሩ/ሯ በእያንዳንዱ
ርዕስ/ ንዑስ ርዕስ ዙሪያ የተሰጠውን ትምህርት አስመልክቶ ማጠቃለያ ማስታወሻ ቢሰጥም ተማሪዎች ሰፋ
ያለ እውቀት እንዲያገኙ ከመማሪያ መጽሀፍትና ከሌላ ማጣቀሻ መጽሀፍት እንዴት ማስታወሻ መውሰድ
እንዳለባቸው አሳውቋቸው፡፡

ተከታታይ ምዘና
በማስተማር ሂደት መምህሩ/ሯ የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል አስመልክቶ መረጃ ለመሰብሰብና
ለመተንተን የተከታታይ ምዘና ዘዴ መጠቀም አለበት/ባት፡፡ መምህሩ/ሯ እያንዳንዱን ተማሪ የእለት ተዕለት
ተግባራት መከታተልና ትምህርት አቀባበል ላይ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች መለየት አለበት/ባት፡፡
ከልየታው በኋላም ውሳኔ ለመወሰን የሚከተሉትን ዘዴዎች ይጠቀሙ፡-
• ምን ላስተምር
• እንዴት ላስተምር
• ተማሪዎችን እንዴት ልመዝን
• ተማሪዎቹ ከትምህርቱ ምን ያህል እውቀት ገብይተዋል የሚለውን
1. የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች፡- ይህ ክፍል የሚያካትተው ማንኛውም የሚታይ የመማሪያ መርጃ
መሳሪያ እና ሌላ በትምህርቱ ክፍለ ጊዜ የሚጠቅሙ ምንጮችን እንዲሁም ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት
ያላቸው የተለያዩ የመማሪያ እቃዎች/ ህያው ቁሳቁሶች ማለትም ምስሎች ፣ካርታዎች ፣ስዕላዊ መግለጫ
ዎች እና አስተማሪ የሆኑ የተለጣጠፉ ነገሮችን ነው፡፡

2. የምዕራፍ ማጠቃለያ ጥያቄዎች መልስ፡- በእያንዳንዱ ምዕራፍ መጨረሻ ለምርጫ ጥያቄ የተቀመጡ
መልሶችና ገለፃ ለሚፈልጉ ጥያቄዎች የተሰነዘሩ ማብራሪያዎች አሉ፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች ተማሪዎች
ግብረገባዊ እንዲሆኑ እና በምክንያት እንዲያስቡ ያበረታታሉ፡፡

3. የትምህርት እቅድ፡- በዚህ የመምህሩ መምሪያ መጽሐፍ መጨረሻ ለናሙና ተብሎ የቀረበውን
የመምህር የትምህርት እቅድ በመጠቀም የራስዎን የትምህርት እቅድ ያዘጋጁ፡፡

· ጥሩ የትምህርት እቅድ አራት መሰረታዊ ነገሮችን ይይዛል፡፡


ሀ. መግቢያ፡-ይህ ክፍል መምህሩ/ሯ አዲሱን ወይም የዕለቱን የትምህርት ርዕስ የሚያስተዋውቁበት እና
ተማሪዎች በቀደመው ክፍለ ጊዜ የተማሩትን ትምህርት ከአዲሱ ጋር የሚያዛምዱበት ነው፡፡
ለ. ገለፃ፡- ይህ መምህሩ /ሯ የእለቱን ትምህርት ለተማሪዎች የሚያቀርቡበትና የሚያብራሩበት ክፍል ነው፡፡
ተማሪዎች ቀደም ሲል የተወያዩባቸውን ተግባራት የሚተገብሩበት ክፍል ነው፡፡
ሐ. ማጠቃለያ፡- በዚህ ክፍል መምህሩ/ሯ በገለፃ ወቅት ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት ለማጠናከር ዋና
ዋና ነጥቦችን በማንሳት ገለፃ የሚያደርጉበት እና ተማሪዎች የተወሰኑ ተግባራትን እንዲፈፅሙ በማድረግ
ከተማሩት ርዕስ ጋር የሚያስማሙበት ክፍል ነው፡፡
መ.ግምገማ፡- ይህ ክፍል መምህሩ/ሯ ተማሪዎች የተማሩትን ርዕስ አስመልክተው በሚፈለገውደረጃ እና
መጠን የሚፈትሹበት ነው፡፡ ግምገማው ተማሪዎችን የተወሰኑ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ወይም አንዳንድ
ተግባራትን እንዲፈጽሙ በማድረግ ይከናወናል፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል XI


ምዕራፍ አንድ
የግብረ ገብ ምሉዕነት
መግቢያ
ይህ ምዕራፍ የግብረ ገብ ምሉዕነት ምንድነው ? ለምን ይጠቅማል የግብረ ገብ ምሉዕነት አለመኖር
የሚያስከትላቸው ችግሮች ምንድናቸው? የሚሉትን የግብረ ገብ ምሉዕነት ጥያቄዎች ለመመለስ ዓላማ
ያደረገ ነው፡፡
ምዕራፉ የሚጀምረው ስለ ግብረ ገብ ምሉዕነት ምንነት በማስተማር እንዲሁም ተዛማጅ መገለጫዎችን
በመዘርዘር ወደ ግብረ ገብ ምሉዕነት ጠቀሜታና የግብረ ገብ ምሉዕነት አለመኖር ወደሚያስከትላቸው ችግሮች
በመሻገር ነው፡፡
የመማር ውጤቶች
ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-

• ስለግብረ ገብ ምሉዕነት ምንነት ይገልፃሉ፤


• ስለምሉዕነት መገለጫ ( ባህሪያት) ያብራራሉ፤
• ለግብረ ገብ ምሉዕነት ጥቅም ዋጋ ይሰጣሉ፤
• የግለሰብ እውነተኛ ምሉዕነት መገለጫን ያሳያሉ፤

የተመደበው ሰዓት 19 ክፍለ ጊዜ ትምህርቶች

- ክፍለ ትምህርት 1 የግብረ ገብ ምሉዕነት ትርጉም


- ክፍለ ትምህርት 2 የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫዎች
- ክፍለ ትምህርት 3 የግብረ ገብ ምሉዕነት ጠቀሜታ
- ክፍለ ትምህርት 4 የግብረ ገብ ምሉዕነት ያለው ሰው ባህሪያት
- ክፍለ ትምህርት 5 የግብረ ገብ ምሉዕነት አለመሆን የሚያስከትላቸው
ችግሮች

የግብረ ገብ ምሉዕነት
1.1. ክፍለ ትምህርት 1 የግብረ ገብ ምሉዕነት ትርጉም
1.1.1. የመማር ብቃቶች

- ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ ለግብረ ገብ ምሉዕነት ፍቺ


ይሰጣሉ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 1


1.1.2 ይዘት
አጠቃላይ የተመደበ ሰዓት - 2 ክ/ጊዜ
• የምሉዕነት ትርጉም
• የግለሰብን ምሉዕነት የሚያንጸባርቁ ተግባራት

1.1.3 አጭር ገለፃ ፤ ይህ ትምህርት ተማሪዎች ከግብረ ገብ ምሉዕነት ትርጓሜ ጋር እንዲተዋወቁ


ይረዳቸዋል፡፡ የግብረ ገብ ምሉዕነት ትርጉምን አስመልክቶ ከተማሪዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው
ምሳሌዎች ተጠቅመው መወያየትና ተማሪዎች የራሳቸውን ድርጊቶች ከግብረ ገብ ምሉዕነት አኳያ
ማድረግ፡፡ የግብረ ገብ ምሉዕነት የሰዎች ውስጣዊ እሳቤና ድርጊት አብሮ በዘላቂነት መሄዱን የሚገልጽ
ነው፡፡
የግብረ ገብ ምሉዕነት ከሰዎች በራስ የመተማመን ችሎታና የድርጊታቸው ውጤት ምንም ይሁን ምን
ከመቀበል ጋር ከፍተኛ ቁርኝነት አለው፡፡ መምህሩ እነዚህን እሳቤዎች ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው
ስዕሎችና ምሳሌዎች በመጠቀም ያስተዋውቃሉ፡፡
1.1.4 የመማር ማስተማር ሂደት

ተመራጭ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች


- ቪድዮ - ስዕሎች

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች


መምህሩ የሚከተሉትን ዘዴዎች በመጠቀም ትምህርቱን ያቀርባሉ፡፡
- ማነቃቂያ - ገለፃ - የቡድን ውይይት
- ትምህርቱን ማስተዋወቅ - ጥያቄና መልስ

ቅድመ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ዝግጅት


• አስፈላጊ የማስተማሪያ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት
• በትምህርቱ ወቅት የሚነሱ ዋና ዋና ጉዳዮችን ለተማሪዎች ማሳወቅና በጉዳዩ ላይ የራሳቸውን ሀሳብ
እንዲያቀርቡ ማበረታታት፡፡

የትምህርቱ አቀራረብ
1. ትምህርቱን ማስተዋወቅ

በጉዳዩ ላይ አጭር ገለፃ ለተማሪዎች ማቅረብና በግብረ ገብ ምሉዕነት ምንነት ላይ አጽንኦት ሰጥቶ መግለጽ
· ስለትምህርቱ ዓላማ ለተማሪዎች ማሳወቅ ፡፡
· ተማሪዎች ስለ ጉዳዩ ያላቸውን አረዳድ ለማወቅ ሲባል በጉዳዩ ላይ ሀሳብ እንዲያፈልቁ ማበረታታት፡

· ሀሳባቸውን ሊያነሳሳ የሚችል ጥያቄ ማንሳት፡፡

2. የትምህርቱ አካል
· የግብረ ገብ ምሉዕነት ትርጉምና ከእርሱ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን የተግባር ምሳሌዎችን
በመግለጽ ውይይቱን ይጀምሩ
· ለግብረ ገብ ምሉዕነት ግንዛቤና ትግበራ አስፈላጊ የሆነ ፅንስ ሀሳቦችን ይግለፁ፡፡

2 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


እነዚህም የሚከተሉት ይካተቱበታል፡-

• በሀሳብ መጽናት
• መሰረታዊ እሴቶች
• ሀቀኝነት
• በራስ መተማመን
• እምነት

1. ማጠቃለያ
3. የትምህርቱን ዋና ዋና ነጥቦች ማንሳትና ማጠቃለል
- የግብረ ገብ ምሉዕነት ትርጉም

2. ክትትል ግምገማና
ሀ. ግምገማ
ተማሪዎቹ ትምህርቱን መገንዘባቸውን ማረጋገጥ፡፡ ይሄ የክፍል የክፍል ስራ ወይም ፈተና በመስጠት
ሊከወን ይችላል፡፡ መምህሩም ተማሪዎችን በቡድን በማዋቀር ከአቻዎቻቸው ጋር ስለ ግብረ ገብ
ምሉዕነትና የራሳቸው የትግበራ ምሳሌዎች ላይ እንዲወያዩ ማበረታታት፡፡

ለ. ክትትል
• ስለግብረ ገብ ምሉዕነት ምንነት መከለስና ተማሪዎቹ በራሳቸው እንዲወያዩበት
ማበረታታት

• ተማሪዎቹ የተማሩትን ትምህርት የተሻለ እንዲረዱት ለማድረግ እያንዳንዱን ቡድን


በግብረ ገብ ምሉዕነት ምንነት ላይ በውይይቱ እንዲሳተፉ ማድረግ

• ተማሪዎች በግብረ ገብ ምሉዕነት ምንነት ላይ ያላቸውን ፅንስ ሀሳብ መገምገም

1.1.5 ለተግባራቱ የተሰጡ መልሶች


ተግባር 1.1. መመሪያ፡- በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ሀሳባችሁን ግለጹ፡፡ መልሶቻችሁንም ከጓደኞቻችሁ
ጋር ተወያዩበት፡፡
1. ምሉዕነት በራሱ ምንድን ነው?

• ምሉዕነት የውስጣችንን ዕሳቤ ከውጫዊ ድርጊቶቻችን ጋር መጣጣሙን የሚገልጽ ነው

• ምሉዕነት ከመሰረታዊ እሴቶች ጋር የመኖር ችሎታ ነው፡፡

2. የአንድን ግለሰብ ምሉዕነት የተወሰኑ መግለጫዎች ይጥቀሱ

• በሀሳብ መጽናት

• ሀቀኝነት

• ተጠያቂነት

• በራስ መተማመን

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 3


1. ግለሰባዊ የስብዕና ምሉዕነት የሚያንፀባርቁ ድርጊቶችን ይግለፁ
• እውነትን መናገር
• ስህተትን አምኖ መቀበል
• የትምህርት ቤትን ንብረቶች መጠበቅ
• አረጋዊያንን መርዳት
• ስህተት የሆኑ ድርጊቶችን መቃወም

1.2 ትምህርት 2: የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫዎች

1.2.1 የመማር ብቃቶች


ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምረው ቃጠናቀቁ በኋላ:
• የግብረ ገብ ምልዑነት መገለጫዎችን ያብራራሉ
• በአካባቢያቸው ያሉትን የግበረ ገብ ምሉዕነት ምሳሌዎችን ይሰጣሉ

1.2.2 ይዘቶች
አጠቃላ ለትምህርቱ የተሰጠ ጊዜ: 6 ክ/ጊዜ
1) የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫዎች
1.2.3. አጭር ገለጻ

የተመደበ ሰዓት: 6 ክፍለ ጊዜ

1) የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫ

1.2.3 አጭር ገለፃ

የግብረ ገብ ምሉዕነት ምንነትን በመወያየት ወደ ግለሰቦች የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫ ባህሪያት


ያመራል፡፡ የግለሰቦች ግብረ ገባዊ መገለጫ ፅንሰ ሀሳብ በቀደመው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ባጭሩ ስለተገለፀ
አሁን በዚህ ክፍለ ጊዜ በሰፊው ይብራራል፡፡ እያንዳንዱ ቃል ተማሪዎች በቀላሉ እንዲረዱት በምሳሌ
መልክ ተካቷዋል፡፡ መምህሩ ስለ ፅንሰ ሃሳቡ አጭር ገለፃ በማድረግ ተማሪዎች ስለ ግብረገባዊ መገለጫ
ባህሪያት እንድወያዩ ማበረታታት ይኖርባቸዋል፡፡ ተማሪዎች ስለ ታማኝነት፣ስለ ጥንካሬ፣የሰውን ችግር
እንደ ራስ ስለ ማየት፣ስለ ትህትና፣ ስለ ተጠያቂነትና ስለ ፅናት ፅንሰ ሀሳብ የተሻለ ግንዛቤ ሊኖራቸው
ይገባል፡፡
1.2.4 የመማር ማስተማር ሂደት
ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች
Ô ምስሎች Ô ፎቶዎች
ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች

• ማነቃቂያ
• ትምህርቱንማስተዋወቅ.
• ገለፃ
• ጥያቄና መልስ.
• የቡድን ውይይት
4 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል
ቅድመ ትምህርት ዝግጅት
¢ አስፈላጊ የማስተማሪያ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት
¢ ተማሪዎች ስለ ፅንሰ ሀሳቡ ያላቸውን ቅድመ ግንዛቤ እንድገልፁ በቂ ጊዜ መስጠት
የትምህርቱ አቀራረብ፡
1. ትምህርቱን ማስተዋወቅ:
• መምህሩ የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫዎችን በማብራራት ትምህርቱን መጀመር ይችላሉ፡፡
• የዕለቱን የትምህርት ዓላማ ለተማሪዎች ያሳውቁ፡፡
• ተማሪዎች ስለ ግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫ እንዲያነቡና ሀሳባቸውን እንዲገልፁ በቂ ጊዜ ይስጧቸው፡

• ተማሪዎችን ሀሳብ እንዲገልፁ የሚያነሳሱ ጥያቄዎችን ያንሱ፡፡ጥያቄዎቹም በሚከተለው መልኩ
ሊሆኑ ይችላሉ፡-
• ስለ ታማኝነት ፅንሰ ሀሳብ ምን ተረዳችሁ?
1. የትምህርቱ አካል:
• መምህሩ መሰረታዊ የግለሰብ ግብረ ገባዊ ባህሪያትን በመግለፅ ትምህርቱን መጀመር ይችላሉ፡
፡ ተማሪዎች ፅንሰ ሀሳቡን ቀለል ባለ መንገድ እንዲረዱት እያንዳንዱ መ ግለጫ በምሳሌ
ተካቷልተማሪዎች ስላላቸው ግንዛቤ ከአቻዎቻቸው ጋር እንድወያዩ ይፍቀዱላቸው፡፡
መገለጫዎቹ:
– ታማኝነት.
– ጥንካሬ.
– የሌሎችን ችግር እንደ ራስ ማየት .
– ትህትና.
– ተጠያቂነት
– ፅናት

2. ማጠቃለያ:
የዕለቱን ትምህርት ዋና ዋና ፅንሰ ሃሳብ ማንሳትና ማጠቃለል፡፡

• የግብረ ገባዊ ምሉዕነት መገለጫ

3. ግምገማና ክትትል:
ሀ) ግምገማ
• ለተማሪዎቹ አጭር ፈተናና የክፍል ስራ በመስጠት ወይም በቡድን እንዲወያዩ
በማድረግ ትምህርቱን መረዳታቸውን ያረጋግጡ፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 5


ለ) ክትትል
የዕለቱን ትምህርት ስለ ግብረገባዊ መገለጫ አጭር ውይይት በማድረግ ማጠቃለል፡፡
• ተማሪዎችዎ ስለ ተማሩት ትምህርት የተሻለ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ በቡድን
የሚሰሩት ስራ ይስጡና እያንዳንዱ የቡድኑ አባላት በውይይቱ መሳተፋቸውን
ያረጋግጡ ፡፡

• ተማሪዎች ስለ ግብረገባዊ መገለጫዎች ያላቸውን ግንዛቤ ይገምግሙ፡፡

1.2.5 ለተግባራቱ የተሰጡ መልሶች

ተግባር 1.2 ትዕዛዝ: በሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ዙሪያ ከጓደኞቻችሁ


ጋር ተወያዩ፡፡

1) የግለሰብ ግብረገባዊ መገለጫዎች ውስጥ የተወሰኑትን ዘርዝሩ፡፡


• ታማኝነት: እውነትን መናገር፣
አለመስረቅና አለማጭበርበር ማለት ነው፡፡
• ጥንካሬ: ችግሮችን ያለ ፍርሃት የማለፍ ችሎታ ማለት ነው፡፡

• የለሎችን ችግር እንደ ራስ ማየት: የሌሎችን ስሜት


ለመረዳት ፍላጎት ማሳየትን ይገልፃል፡፡

• ትህትና: ራስን ከሌሎች አስበልጦ ያለማየት ችሎታን


ያሳያል፡፡

• ተጠያቂነት: ላደረጉት ድርጊት ሀላፊነት ለመውሰድ


ፈቃደኛ መሆን ማለት ነው፡፡

• ፅናት: በግልም ሆነ በህዝብ እይታ ተመሳሳይ


ማንነትን የመላበስ አቅም

2) የውስጣዊ ፅናት ምንነትን ግለፁ

• ውስጣዊ ፅናት ማለት የግለሰብ ውስጣዊ አስተሳሰብ


ከውጫዊ ድርጊቱ ጋር መጣጣም ማለት ነው፡፡
3 በክፍል ውስጥ የሚተገበሩ የግብረገባዊ ተግባር ምሳሌዎችን
ተወያዩ ፡፡

• እውነትን መናገር
• መምህራንን ማክበር.
• የተሰጣቸውን ሀላፊነት በሰዓቱ መፈፀም
• የትምህርት ቤት ንብረቶችን መንከባከብ

6 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


1.3 ፡- የግብረ ገብ ምሉዕነት ጥቅም
1.3.1. የመማር ብቃት
በዚህ የትምህርት ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ተማሪዎች፡-
• የግብረ ገብ ምሉዕነት ጥቅምን ያውቃሉ

• የግብረ ገብ ምሉዕነት ጥቅም ምሳሌዎችን ይጠቅሳሉ፡፡

1.3.2. ይዘት
አጠቃላይ የሚፈጀው ሰዓት ፡- 4 ክፍለ ጊዜ
1. የግብረ ገብ ምሉዕነት ጥቅም

1.3.3 አጭር ገለፃ


በዚህ ደረጃ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ስለግብረ ገብ ምሉዕነትና መገለጫዋች ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ ትምህርቱ
የግብረ ገብ ምሉዕነት ጥቅምን ወደ ማወያየት ይሸጋገራል፡፡ መምህሩ ስለ ግብረ ገብ ምሉዕነት ጥቅም
ሀሳባቸውን የሚገልፁ ተማሪዎችን ያበረታታል፡፡ የግብረ ገብ ምሉዕነት ከግለሰባዊና ማህበራዊ ጥቅም
አንፃር መታየት አለበት፡፡ መምህር ተማሪዎች ስለግብረ ገብ ምሉዕነት ጥቅም ያላቸውን ግንዛቤ በቅርበት
ይመልከቱ፡፡

1.3.4 የመማር ማስተማሪያ ሂደት


ተመራጭ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች
• ምስሎች
ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች፡-
• ማነቃቂያ - ጥያቄና መልስ - ገለፃ
• የእለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ - የቡድን ውይይት

ቅድመ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ዝግጅት


• አስፈላጊ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ እና ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት

• ተማሪዎች በጉዳዩ ላይ ቅድመ ግንዛቢያቸውን እንዲገልጹ ጊዜ መስጠት

የትምህርቱን ክፍለ ጊዜ አጭር ገለፃ

1. የእለቱን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ማስተዋወቅ


መምህሩ ተማሪዎች በራሳቸው አመለካከት አስፈላጊ የግብረ ገብ ምሉዕነት ጥቅሞቻቸውን እንዲገልጹ
በማበረታታት መጀመር ይችላሉ፡፡
• ስለክፍለ ጊዜው የትምህርት ዓላማ ለተማሪዎች ይንገሩ

• ስለግብረ ገብ ምሉዕነት እንዲያነቡና እንዲገልጹ ለተማሪዎች በቂ ጊዜ ይስጧቸው

• ተማሪዎችን ሀሳብ እንዲያፈልቁ የሚያነሳሱ ጥያቄዎችን ያንሱ፡፡

ጥያቄዎቹ በሚከተሉት መልኩ ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡

-- የግብረ ገብ ምሉዕነት ለግለሰብ የሚኖረው ጠቀሜታ ምንድን ነው?


-- የግብረ ገብ ምሉዕነት መኖር ለማህበረሰቡ እንዴት ይጠቅማል?

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 7


2. የትምህርቱ አካል
• ለዚህ ክፍለ ጊዜ፡- መምህሩ ተማሪዎቹ ለግብረ ገብ ምሉዕነት ያላቸውን ግንዛቤ በመገመት
ቢጀምሩ የተሸለ ነው፡፡ ከዚያ መምህሩ የግብረ ገብ ምሉዕነት ጠቀሜታ በግለሰብ እና በማህበረሰብ
ደረጃ ወደ ሚለው መሸጋገር ይችላል፡፡

3. ማጠቃለያ፡- የእለቱን ክፍለ ጊዜ ዋና ዋና ነጥቦች በማንሳት ማጠቃለል፡፡

• የግብረ ገብ ምሉዕነት ጠቀሜታ

4. ግምገማና ክትትል
ሀ. ግምገማ

• ተማሪዎቹ የዕለቱን ትምህርት መረዳታቸውን ማረጋገጥ፡፡ ይህም የክፍል ስራ ወይም ፈተና


በመስጠት ሊከወን ይችላል፡፡ መምህሩ ተማሪዎችን በቡድን በማዋቀር ስለግብረ ገብ ምሉዕነት
ጠቀሜታ ካቻዎቻቸው ጋር እንዲወያዩ ማበረታታት

ለ. ክትትል
• በግብረ ገብ ምሉዕነት ዙሪያ ጥልቅ የሆነ ውይይት በማድረግ ማጠቃለል እና በራሳቸው መንገድ
እንዲወያዩ ማበረታታት፡፡ ተማሪዎቹ ስለትምህርቱ ያላቸውን ግንዛቤ ለማረጋገጥ መምህሩ በቡድን
የሚሰሩትን ስራ መስጠትና ሁሉም የቡድኑ አባላት መሳተፋቸውን ማረጋገጥ

• ስለግብረ ገብ ምሉዕነት ጥቅም የተማሪዎቹን እይታ መገምገም

1.3.5 ለተግባራቱ የተሰጡ መልሶች


1.3 የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱና በመልሶቻቸው ዙሪያም ከጓደኞቻችሁ ጋር ተወያዩ፡፡
1. የግብረ ገብ ምሉዕነትን ተግባራዊ ማድረግ ከሚሰጠው ጥቅም ውስጥ የተወሰኑትን ዘርዝሩ፡፡
የግብረ ገብ ምሉዕነትን ተግባራዊ ማድረግ የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት፡-
• የማህበረሰብ ትስስርን ያጠናክራል
• ማህበረሰባዊ እድገትን ያፋጥናል
• የግለሰቦችን ችግር የመፍታት አቅም ያጎለብታል
• ህዝቦች ታዓማኒነትና ክብርን እንዲያገኙ ያስችላል
1. የግብረ ገብ ምሉዕነት ካላቸው ማህበረሰቦች ጋር መኖር በሚኖረው ጥቅም ዙሪያ ተወያዩ፡፡
• የግብረ ገብ ምሉዕነት ያላቸው የማህበረሰብ ስብስብ እርስ በርሳቸው ታዓማኒነት እንድኖራቸው
ያደርጋል
• እንዲሁም እርስ በርሳቸው ለመደጋገፍና ለመጠባበቅ ይተማመናሉ
• ማህበረሰቡም በሌሎች የተከበረ ይሆናል

1. የግብረ ገብ ምሉዕነትን በክፍል ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ በሚሰጠው ጥቅም ላይ ተወያዩ፡፡


• ተማሪዎች በመምህራቸው ታዓማኒነትን ያገኛሉ
• ተማሪዎች እርስበርሳቸው የተሻለ ጓደኝነት እንዲኖራቸው ያስችላል
• ተማሪዎች እርስበርሳቸው ለመረዳዳት ፈቃደኛ ይሆናሉ

8 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


1.4 ክፍለ ትምህርት 4 ፡- የአንድ ግለሰብ የግብረ ገብ ምሉዕነት መግለጫ

1.4.1. የመማር ብቃት


ተማሪዎች ይህን ክፍለ ጊዜ ከተማሩ በኋላ፡-
• የአንድን ግለሰብ የግብረ ገብ ምሉዕነት መግለጫዎች ይገነዘባሉ
• የግብረ ገብ ምሉዕነት ማሳያ የሆኑ የአካባቢያቸው ሰዎች ይጠቅሳሉ

1.4.2. ይዘት

የተመደበ ሰዓት፡- 3 ክፍለ ጊዜ

1. የአንድ ግለሰብ የግብረ ገብ ምሉዕነት መግለጫዎች

1.4.3 አጭር ገለፃ


አንድ የግብረ ገብ ምሉዕነት አለው የሚባል ሰው ምን ዓይነት ባህሪ ያሳያል? ይህ የትምህርት ክፍል አንድ
የግብረ ገብ ምሉዕነት ያለው ሰው ዋና መገለጫ ባህርያቶች ለተማሪዎች ለማሳወቅ ያለመ ነው፡፡
ተማሪዎች የእውነተኛ ግብረ ገብ ምሉዕነት እሳቤን አስመልክቶ ተገማች ነገሮች ይገልፃሉ፡፡ ከዚህ በተፃራሪ
ያሉትን ድርጊቶች ይገልፃሉ፡፡

1.4.4 የመማር ማስተማር ሂደት


ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዋች፡-
- ምስሎች - ፎቶዎች

ተመራጭ የማስተማሪያ ዜዴዎች፡-

• ማነቃቂያ
• ትምህርቱን ማስተዋወቅ
• ገለፃ
• ጥያቄና መልስ
• የቡድን ውይይት

ቅድመ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ዝግጅት


• ተገቢ የሆኑ አጋዥና የመማሪያ መሳሪያዎች ማዘጋጀት
• ቀደም ብለው ተማሪዎች በእያንዳንዱ ጽንስ ሀሳብ ላይ የራሳቸው አረዳድ እንዲያንፀባርቁ ጊዜ
መስጠት

1.የትምህርቱ አቀራረብ
• የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ
• የዕለቱን የትምህርቱ ዓላማ ለተማሪዎች ማሳወቅ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 9


• የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫዎችን በተመለከተ ተማሪዎች እንዲያነቡና እንዲገልጹ በቂ ጊዜ መስጠት

• ሀሳብ ለማመንጨት የሚያስችሉ ጥያቄዎችን ያንሱ ፡፡

ጥያቄዎቹ ‹‹የግብረ ገብ ምሉዕነት ያለው ሰው ኢፍትሀዊነት ይፃረራልን?›› የሚል ሊሆን ይችላል

2 የትምህርቱ አካል
ይህ ትምህርት የግብረ ገብ ምሉዕነት ያለው ሰው መገለጫዎቹ ምን እንደሆኑ አጠር ባለ ገለፃ
እንድሁም የመወያያ ርዕስ በመስጠት ሊጀምር ይችላል፡፡

3. ማጠቃለያ
የትምህርቱን ዋና ፍሬ ሀሳብ ያጠቃሉ
• የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫዎች

4. ግምገማና ክትትል

ሀ. ግምገማ
• ተማሪዎች ትምህርቱ እንደገባቸው ያረጋግጡ፡፡ ይህ አጠር ያለ ፈተና ወይንም የክፍል
ሥራ በመስጠት ሊደረግ ይችላል፡፡ በተጨማሪም መምህሩ ተማሪዎችን በቡድን በማቧደን
ከአቻዎቻቸው ጋር በመሆን ስለ ተሟላ የግብረ ገብ ስብዕና መገለጫዎች ውይይት እንዲያደርጉ
ማድረግ ይችላል፡፡

ለ .ክትትል
ስለ ተሟላ የግብረ ገብ ስብዕና መገለጫዎች አስመልክቶ ቀለል ያለ ገለፃ በማድረግና ተማሪዎች ከአቻዎቻቸው
ጋር በጉዳዩ እንዲነጋገሩ በማድረግ ትምህርቱን ያጠቃልሉ፡፡
• ተማሪዎች ትምህርቱን በደምብ እንደገባቸው ለማረጋገጥ የቡድን ሥራ ወይንም ሌላ ሥራ
ሊሰጠዋቸው ይችላሉ፡፡ እያንዳንዱ ተማሪ በውይይት መሳተፍን ያረጋግጡ፡፡

• ተማሪዎች ግብረ ገብ ምሉዕነትን አስመልክቶ ያንጸባረቁትን ሀሳብ ይገምግሙ

1.4.5. ለተግባራቱ የጠሰጡ መልሶች


ተግባር 1.4፡- ትዕዛዝ የሚከተሉት ጥያቄዎች መልሱ፡፡
1. የተወሰኑ የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫዎችን ጥቀሱ

ምሉዕ የግብረ ገብ ሰብዕና ያላቸው ሰዎች፡-


 በመርሆቻቸው መሰረት ህይወታቸውን ይመራሉ

 አደርገዋለሁ ያሉትን ነገር ያደርጋሉ

 በተለያየ ሁኔታ ውስጥም ሆነው መርሆቻቸውን ይከተላሉ

 የሚመጣባቸው የውጭ ግፊት በድፍረት ይቋቋማሉ

2. የግብረ ገብ ምሉዕነት ያለው ሰው

 የማያውቀውን ነገር አውቀዋለሁ አይልም

10 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


• ሰዎችን ሰው በመሆናቸው እንጂ ደረጃቸውን ታሳቢ አድርጎ አይቀርባቸውም
• የሚመራበትን መርህ በውጭ ጫና ምክኒያት አይተውም
3. አንድ ተማሪ በክፍል ውስጥ ሊያሳያቸው የሚችሉ የግብረ ገብ ባህሪያትን አስመልክቶ ውይይት
አድርጉ፡፡
• እያንዳንዱን ተማሪ በእኩልነት ማየት
• የተሰጣቸው ተግባር በአግባቡ መፈፀም
• እውነትን መናገር
• መጥፎ ባህሪ የሚያሳዩ ተማሪዎችን ሲመለከቱ ለምን ብለው መናገር

1.5 ክፍለ ትምህርት 5፡ የግብረ ገብ ምሉዕነት አለመኖር የሚያስከትላቸው ችግሮች

.1.5.1 የመማር ብቃት

ተማሪዎች ይህን ክፍለ ጊዜ ከተማሩ በኋላ፡-


· የግብረ ገብ ምሉዕነት አለመኖር የሚያመጣቸውን ችግሮች ያውቃሉ፡፡
· የግብረ ገብ ምሉዕነት አለመኖር የሚያሰከትላቸውን የተወሰኑ ችግሮች ክፍል ውስጥ ይገልፃሉ::

1.5.2 ይዘት
አጠቃላይ የተመደበ ሰዓት ፡ 4 ክፍለ ጊዜ

1. የግብረ ገብ ምሉዕነት አለመኖር የሚያሰከትላቸው ችግሮች

1. የግብረ ገብ ምሉዕነት አለመኖር የሚያሰከትላቸው ችግሮች

1.5.3 አጭር ገለፃ


እሰካሁን ተማሪዎች ስለግብረ ገብ ምሉዕነት ምንነት፣ መገለጫ፣ ጥቅም እንዲሁም የግብረ ገብ ምሉዕነትን
የተላበሱ ግለሰቦች ባህሪያት ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ ይሄ ደግሞ በግብረ ገብ ምሉዕ አለመሆን ስለሚያስከትላቸው
ችግሮች ግንዛቤ ይፈጥርላቸዋል፡፡ በዚህ ክፍል የግብረ ገብ ምሉዕ አለመሆን ስለሚያመጣቸው ችግሮች
በጥልቀት ይወያያሉ፡፡ በችግሮቹ ዙሪያ የሚደረገው ውይይት ከግለሰብና ማህበረሰብ ዕይታ አንፃር ቢታይ
መልካም ነው፡፡

1.5.4 የመማር ማስተማር ሂደት


ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ
-ምስሎች
--ፎቶወች

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴወች፡-

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 11


• ማነቃቂያ
• የዕለቱን ክፍለ ጊዜ ርዕስ ማስተዋወቅ
• ገለፃ
• ጥያቄ እና መልስ

• ቡድን ውይይት

የዕለቱ የትምህርቱ ቅድመ ዝግጅት


* አስፈላጊ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ ማዘጋጀት
* ከመማራቸው በፊት ልጆቹ ስለሚማሩበት ርዕስ ያላቸውን ጽንስ ሀሳብ እንዲገልጹ በቂ ጊዜ መስጠት፡፡

የትምህርቱ አቀራረብ
1. የእለቱ የትምህርት ርዕስ ማስተዋወቅ፡- የእለቱ ትምህርት ተማሪዎች የግብረ ገብ ምሉዕ
አለመሆን በግለሰብ እንዲሁም በማህበረሰብ እንደ አጠቃላይ ስለሚኖረው ችግር ያላቸውን አመለካከት
በመመዘን ወይም በመቃኘት መጀመር ይቻላል፡፡
 ስለ ክፍለ ጊዜው የትምህርት አላማ ለተማሪዎች ይንገሩ
 ተማሪዎች የግብረ ገብ ሙሉ አለመሆን ስለሚያስከትላቸው ችግሮች እንዲገልፁ በቂ ጊዜ ይስጡ
 የተማሪዎችን ንቃተ ህሊና ሊያነሳሳ የሚችል ጥያቄዎች ያንሱ ፡፡
ጥያቄዎቹ በሚከተለው መልኩ መሆን አለባቸው፡-
ማንም የግብረ ገብ ምሉዕነት የለውም እንበል እና ማህበረሰቡ ምን ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ?

2. የትምህርቱ አካል

 ይህ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የሚጀምረው ስለ ግብረ ገብ ምሉዕ አለመሆን ስላሚያስከትለው


ችግር ሰፋ ያለ መግቢያ በመስጠት ነው፡፡ መምህሩ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ የሚወያዩባቸው
የተወሰኑ የውይይት ርዕሶች መስጠት ይችላሉ፡፡
3. ማጠቃለያ
 የክፍለ ጊዜውን ትምህርት ዋና ዋና ፍሬ ሀሳቦች ማጠናከር
 የግብረ ገብ ሙሉ አለመሆን የሚያስከትላቸው ችግሮች ውስጥ ዋና ዋናወቹን ማንሳትና
ማጠቃለል፡፡
4. ግምገማና ክትትል
ሀ. ግምገማ

ተማሪዎች የእለቱን ትምህርት መረዳታቸውን ማረጋገጥ፡፡ ይህ የክፍል ስራ ወይም ፈተና


በመስጠት ሊከወን ይችላል፡፡ መምህሩም ተማሪዎችን በቡድን በማዋቀር ከጓደኞቻቸው ጋር
ስለግብረ ገብ ምሉዕ አለመሆን ስለሚያስከትላቸው ችግሮች እንዲወያዩ ያበረታታሉ፡፡

12 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ለ .ክትትል

የዕለቱን ትምህርት የግብረ ገብ ምሉዕ አለመሆን ስለሚያስከትላቸው ችግሮች ሰፊ ውይይት እንዲያደርጉ


በማበረታት ማጠቃለል፡፡ተማሪወቹ ስለግብረ ገብ ምሉዕነት የተሻለ ግንዛቤ እንደያዙ እርግጠኛ ለመሆን
የቡድን ስራ መስጠትና ሁሉም የቡድኑ አባላት ውይይቱ ላይ መሳተፋቸውን ማረጋገጥ፡፡ ተማሪወች የግብረ
ገብ ምሉዕ አለመሆን ስለሚያስከትላቸው ችግሮች ያላቸውን ግንዛቤ መገምገም፡፡

1.5.5 የተግባራት መልሶች

ተግባር 1.5 ትዕዛዝ: ለሚከተሉት ጥያቄወች መልሳችሁን አሰቀምጡ፡፡.


በመልሶቻችሁ ዙሪያም ከጓደኞቻችሁ ጋር ተወያዩ፡፡

1) ከግብረ ገብ ምሉዕነት ውጭ መኖር ከሚያስከትላቸው


ችግሮች ውስጥ የተወሰኑትን ግለጹ፡፡

 በራስ መተማመንን ማጣት.


 በህዝቦች መካከል ተዓማኒነትን ማጣት.
 እውነተኛ ጓደኝነትን ማጣት.
2) በትምህርት ቤት ውስጥ የግብረ ገብ ምሉዕነት አለመኖር
መገለጫ ድርጊቶች ውስጥ የተወሰኑትን ዘርዝሩ፡፡
 በፈተና መኮራረጅ፡፡.
 ክፍል ውስጥ በትምህርት ክፍለ ጊዜ በአግባቡ አለመከታተል፡፡.
 በመምህራን የሚሰጡ ተግባራትን በአግባቡ አለመከወን፡፡

1.6 የምዕራፉ ጥያቄ መልሶች

መልመጃ 1.1 መልስ


እውነት / ሀሰት
1) እውነት
2) ሀሰት
3) ሀሰት
4) እዉነት
5) ሀሰት
ምርጫ
1) ሐ
2) ሀ
3) ለ
4) ሐ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 13


ለገለፃ ጥያቄዎች የተቀመጡ መልሶች
1) የምሉዕነት ምንነትን ግለፁ፡፡
 ምሉዕነት የሰው ልጅ ውስጣዊ አስተሳሰብ ከውጫዊ ድርጊቱ ጋር መጣጣሙንና
ወጥ መሆኑን የሚገልፅ ፅንሰ ሀሳብ ነው፡፡ ይህ ወጥነት በግለሰብ ወይም
በማህበረሰብ ደረጃ ሊገለፅ ይችላል፡፡
 ምሉዕነት የሰው ልጅ ከራሱ መሰረታዊ ዕሴቶች ጋር የመኖር ችሎታን
የሚገልፅ ነው፡፡

2)እውነትኛ የግብረ ገብ ምሉዕነት የተላበሰ ሰዉ ባህሪያት አብራሩ፡፡.


 ታማኝነት
 ብርታት
 የሰውን ችግር እንደራስ ማየት
 ትህትና
 ተጠያቂነት
 በሀሳብ መፅናት

3) ድርጊቶቻችንን በግብረ ገብ ምሉዕነት መምራት ያለዉን ጥቅም አስረዱ፡፡

 ማህበረሰባዊ ትስስርን ያጠነክራል፡፡

 ማህበረሰባዊ ዕድገትን ያፋጥናል፡፡

 የሰወችን ችግር የመፍታት አቅም ያጎለብታል፡፡

 ተዓማኒነትና ክብርን ያስገኛል፡፡

4)በትምህርት ቤት ደረጃ የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫ ከሆኑት ድርጊቶች ውስጥ

የተወሰኑትን ግለፁ፡፡

• እውነትን መናገር፡፡

• ስህተትን አምኖ መቀበል፡፡

• ቃልን መጠበቅ፡፡

• የትምህርት ቤት ንብረትን መጠበቅ፡፡

• ስህተት የሆኑ ድርጊቶችን መቃወም፡፡

5) እውነተኛ የግብረ ገብ ምሉዕነት ያልተላበሰ ተግባር የሚያመጣዉን አሉታዊ ዉጤቶች ግለፁ፡፡

• በራስ መተማመንን ማጣት፡፡

• የህዝብን ተዓማኒነት ማጣት፡፡

• እውነተኛ ጓደኝነትን ማጣት

14 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ምዕራፍ ሁለት
ለህግ ተገዥነት

መግቢያ
ይህ ምዕራፍ የህግ ተገዥነት ፅንስ ሀሳብ ላይ ያተኩራል፡፡ ውይይቱ በህግ ምንነት አጠር ያለ ገለፃ በመስጠት
ይጀምራል፡፡
ይህ የሚደረገው ለቀጣዩ የክፍለ ጊዜ ትምህርት ጠቃሚ በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ አጭር ገለፃ በኋላ ‹‹ለህግ
ተገዢነት›› ትርጉምና አስፈላጊት ያመራል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ወደ ህግ አክባሪ ግለሰብ ባህሪያት ምንነትና ለሕግ
ተገዥ አለመሆን የሚያስከትለውን ችግር ይፈትሻል፡፡
የመማር ውጤቶች
ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
• ለሕግ ተገዢነት ትርጉም ይሰጣሉ

• ለህግ ተገዢ የመሆን አስፈላጊነትን ይገልፃሉ

• የሕግ አክባሪ ሰው መለያወችን ይዘረዝራሉ

• ለሕግ ተገዢ አለመሆን የሚያስከትለውን ችግር ይናገራሉ

የተደመበው ሰዓት፡- 20 ክፍለ ጊዜ

ትምህርቶች ፡-
• ክፍለ ትምህርት 1 የህግ ተገዢነት ትርጉም
• ክፍለ ትምህርት 2 ለሕግ ተገዢ የመሆን አስፈላጊነት
• ክፍለ ትምህርት 3 ለሕግ ተገዢ የሆነ ሰው ባህሪያት
• ክፍለ ትምህርት 4 ለሕግ ተገዢ አለመሆን የሚያስከትላቸው ችግሮች

2.1 ክፍለ ትምህርት 1፡- የሕግ ተገዢነት ትርጉም


2.1.1. የመማር ብቃት
ተማሪዎች ይህን ክፍለ ጊዜ ከተማሩ በኋላ፡-
ለህግ ተገዢነት ትርጉም ይሰጣሉ

2.1.2. ይዘቶች

የተመደበው ሰዓት፡- 4 ክፍለ ጊዜ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 15


1. የሕግ ተገዢነት ትርጉም
2. የሕግ ዓላማ

2.1.3 አጭር ገለፃ


ይህ ክፍል የአንድ ሀገር ሕጐችን ዓላማ ምን እንደሆነ አጠር ያለ መግቢያ በመስጠት ይጀምራል፡፡ ተማሪዎች
በሕግ ተገዢነት የተሻለ አረዳድ እንዲኖራቸው ከማድረግ አንጻር ይህ አጭር መግቢያ አስፈላጊ ነው፡፡
ቀጥሎ ውይይቱ ወደ ሕግ ተገዢነት ምንነት ያመራል፡፡ ተማሪዎች ለሕግ ተገዢነት ምን ማለት እንደሆነና
ምን ጥቅም እንደሚሰጥ ይገነዘባሉ፡፡

2.1.4 የመማር ማስተማር ሂደት

ተመራጭ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች


• ለሕግ ተገዢ የሆኑ ሰዎች የሚያሳዩ ፎቶዎች
• በህዝቦች/ዜጎች መሀከል መስተግብር የሚያሳዩ ስዕሎች

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች


መምህሩ የሚከተሉትን ዜዴዎች በመጠቀም ክፍለ ጊዜውን ያከናውናል
•ማነቃቂያ
•የት/ት ክፍለ ጊዜው ማስተዋወቅ
•ማብራሪያ
•ጥያቄ
•የቡድን ውይይት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


1. የትምህርቱ አቀራረብ

• ስለ ጉዳዩ አጠር ያለ መግለጫ ለተማሪዎች መስጠትና ለ ‹‹ሕግ ተገዢነት›› ለሚለው ቃል


አጽንኦት መስጠት
• የትምህርቱ ዋና አላማ ለተማሪዎች ማሳወቅ
• ተማሪዎች ስለ ጉዳዩ በደምብ ማወቃቸውን ለማወቅ ለሕግ ተገዢነት ዙሪያ ሀሳብ እንዲያፈልቁ
ማበረታታት
• ሀሳባቸውን ሊያነሳሳ የሚችል ጥያቄ ማንሳት ይቻላል፡፡
ጥያቄው ‹‹ የሕግ ዓላማ ምንድነው?›› በሚል መልክ ሊሆን ይችላል፡፡

16 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


2. የትምህርቱ አካል

* የሕግ ተገዢነት ትርጉምና ከሱ ጋር አብሮ የሚሄዱ የአተገባበር መንገዶች ምሳሌን በመጨመር


ውይይቱን ይጀምሩ
* በሕግ ተገዢነት ፅንሰ ሀሳብ ውስጥ የሚከተሉት ይካተታሉ ፡-
• የሕግ አላማ
• የሕግ ባህሪያት
• ለሕግ መገዛት

3. ማጠቃለያ
 የትምህርቱን ዋና ዋና ፅንሰ ሀሳብ በማንሳት ያጠቃሉ
 የህግ ተገዢነት ምንነት

4. ግምገማና ክትትል

ሀ/ ግምገማ

 ተማሪዎች ትምህርቱን መረዳታቸውን አጭር ፈተና ወይንም የክፍል ሥራ


በመስጠት ያረጋግጡ፡፡ መምህሩ ተማሪዎችን በቡድን አቧድኖ ከአቻዎቻቸው ጋር
‹‹ለሕግ ተገዢነት›› ምንነት ዙሪያ ውይይት እንዲያደርጉ ሊያበረታታቸው ይችላሉ፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ በጉዳዩ የራሳቸው ምሳሌ እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡

ለ. ክትትል
የሕግ ተገዢነት ትርጉምን አስመልክቶ ለተማሪዎች ማጠቃለያ ይሰጧቸው፡፡ በመካከላቸውም
የቃል ምልልስ እንዲያደርጉ ያድርጓቸው
• ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት የበለጠ እንዲረዱ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት
ያላቸው ሥራዎች ይሰጡዋቸው፡፡ ለያንዳንዱ ቡድን በሕግ ተገዢነት ትርጉም
በውይይት ወቅት የሚሳተፉበትን ሥራ ይስጧቸው፡፡

• ተማሪዎች በሕግ ተገዢነት ጽንስ ሀሳብ ዙሪያ የሚያንፀባርቋቸውን ሀሳቦች


ይገምግሙ
2.1.5 ለተግባራት የተሰጡ መልሶች

ተግባር 2.1. ትዕዛዝ ፡- በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ገለጻ ስጡ፤መልሶቻችሁን


ከክፍክ ጓደኞቻችሁ ጋር ተወያዩበት፤

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 17


1. የአንድን ሀገር ሕግ ዓላማ ጥቀሱ
የሚከተሉት የተወሰኑ የሕግ ዓላማዎች ናቸው፡፡
 መብትና ግዴታ ለዜጎች ማሳወቅ
 የዜጎች ባህርይ አቅጣጫ ማስያዝ
 የዜጎች እኩልነት እንዲረጋገጥ ማገዝ

2. ለሕግ ተገዢ የሆኑ ዜጎች ግዴታቸው ምንድን ነው ?


እነዚህ ለሕግ ተገዥ የሆኑ ዜጐች የተወሰኑ ግዴታዎች ናቸው፡፡
 ለሕግ ተገዥ የሆኑ ዜጎች በሀገሩ ሕጎች ተገዢ ለመሆን ዝግጁ መሆን አለባቸው
 ለሕግ ተገዢ የሆኑ ዜጎች የሀገሪቱን ሕጎች ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 ለሕግ ተገዥ የሆኑ ዜጎች ችግሮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ይጠበቅባቸዋል፡፡

3. የሕግ ተገዢነትን ለመተግበር ተማሪዎች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ድርጊቶች ውስጥ የተወሰኑ ምሳሌዎችን
ስጡ

እነዚህ ተማሪዎች የሕግ ተገዢነትን ለመተግበር ሊያደርጓቸው ከሚገቡ ድርጊቶች ውስጥ ጥቂቶች
ናቸው፡፡
 ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን ሕጎችና ደምቦች ማወቅ አለባቸው

 ተማሪዎች በመምህራኖቻቸው የተሰጧቸውን ተግባራት ማጠናቀቅ አለባቸው

 ተማሪዎች ከአቻወቻቸው ጋር የሚያደርጉት መስተጋብር በመከባበር ላይ የተመሰረት መሆን


አለበት፡፡

2.2 ክፍለ ትምህርት 2፡ ለሕግ ተገዥ የመሆን አስፈላጊነት

2.2.1 የመማር ብቃት ፡ ተማሪዎች ይህን ክፍለ ጊዜ ከተማሩ በኋላ፡-


 ለሕግ ተገዥ የመሆን አስፈላጊነትን ያብራራሉ

2.2.2 ይዘት

ለሕግ ተገዢ የመሆን አስፈላጊነት ፡- የተመደበ ሰዓት ፡ 5 ክፍለ ጊዜ

2.2.3 አጭር ገለፃ


ለምንድነው ለሕግ መገዛት አስፈላጊ የሆነው? ስለ ሕግ ተገዢነት ትርጉም ውይይት ከተደረገ በኋላ
ትኩረቱ ወደ ሕግ አስፈላጊነት ያመራል፡፡ የሕግ ተገዢነት ጥቅም ከግለሰብ እንድሁም ከማህበረሰብ
አንጻር ውይይት ይደረግበታል፡፡ ስለ እነዚህ ጠቀሜታዎች ለተማሪዎች ምሳሌዎችን በመስጠት ውይይት
ያድርጉ፡፡

2.2.4 የመማር ማስተማር ሂደቶች


ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች
- ምስሎች - ፎቶዎች

18 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ተመራጭ የማስተማሪያ ዜዴዎች

እነዚህ አማራጭ የማስተማሪያ ዜዴዎች ናቸው


•ሀሳብ ማፍለቅ
•የትምህርቱን ርዕስ ማስተዋወቅ
•ገለፃ
•መጠየቅ
•የቡድን ውይይት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


• የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ያዘጋጁ
• ተማሪዎች ከትምህርቱ በፊት በያንዳንዱ ጽንስ ሀሳብ የራሳቸውን አረዳድ እንዲያንፀባርቁ
ጊዜ ይሰጧቸው

የትምህርቱ አቀራረብ
1. የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ

መምህሩ ለሕግ ተገዢ የመሆን አስፈላጊነትን በመግለጽ ትምህርቱን መጀመር ይችላል


• የዕለቱን የትምህርት ዓላማ ለተማሪዎች ያሳውቋቸው
• ተማሪዎች ስለ ሕግ ተገዢነት እንዲያነቡና ሀሳባቸውን እንዲያንፀባርቁ በቂ ጊዜ ይሰጧቸው
• ሀሳባቸውን ሊያነሳሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን ያንሱ፡፡
ጥያቄዎቹም በሚከተለው መልኩ ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡

‹‹ለሕግ ተገዢ የመሆን አስፈላጊነት ምን ይመስላችኋል?››

2. የትምህርቱ አካል
 መምህሩ ለሕግ ተገዢ የመሆንን ዋና ዓላማ በመግለጽ ትምህርቱን መጀመር ይችላል፡፡
 ተማሪዎች በጉዳዩ ያላቸውን አረዳድ ከአቻወቻቸው ጋር ሆነው እንዲወያዩ ይፍቀዱላቸው

3. ማጠቃለያ
 የትምህርቱን ዋና ዋና ጽንስ ሀሳብ ያጠቃሉ
- የህግ ተገዢነት አስፈላጊነት

4. ግምገማና ክትትል
ሀ. ግምገማ
 ተማሪዎች ትምህርቱን መገንዘባቸውን ያረጋግጡ፡፡ ይህም ለተማሪዎች ቀለል ያለ ፈተና
ወይንም የክፍል ሥራ በመስጠት ሊከወን ይችላል፡፡
 መምህሩ ተማሪዎችን በቡድን በማደራጀት ከአቻዎቻቸው ጋር ስለ ሕግ ተገዥ የመሆን
አስፈላጊነት ውይይት እንዲያደርጉ ያግዟቸዋል፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 19


ለ. ክትትል
ስለ ህግ ተገዢነት ጥቅም አጠር ያለ ውይይት በማድረግ ተማሪዎች በመካከላቸው የሁለትዮሽ
ውይይት እንዲያደርጉ ማድረግ ይችላሉ፡፡
• ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት የበለጠ እንድረዱት የተለያዩ ተግባራት ሊሰጧቸውና
እያንዳንዱ ተማሪ በውይይቱ መሳተፉን ያረጋግጡ፡፡

• ተማሪዎች የሕግ ተገዢነትን አስመልክቶ ያንፀባረቋቸውን ሀሳቦች ይገምግሟቸው፡፡

የቡድን ስራ

መምህሩ እንደሁኔታው ተማሪዎችን 3 ወይንም 4 ቡድን እንዲመሰርቱ ሊያዟቸው ይችላሉ፡፡


• ተማሪዎቹ ትዕዛዙን መረዳታቸውን ያረጋግጡ

• እያንዳንዱ ተማሪ የታሪኩ ነጥብ እንደገባው ይመልከቱ

• እያንዳንዱ ተማሪ በውይይቱ መሳተፉን ያረጋግጡ

2.2.5 ለተግባራቱ የተሰጡ መልሶች

ተግባር 2.2. ትዕዛዝ፡- በሚከተሉት ጥያቄዎች መልሶች ዙሪያ ከአቻዎቻችሁ ጋር ተወያዩበት፡፡


1. ለሕግ የመገዛት ዓላማዎች ምንድን ናቸው?
ለሕግ ተገዢነት ብዙ አላማዎች አሉት ከነዚህም መካከል፡-
 ነፃነትን በምሉዕነቱ ማጣጣም
 ሰላምን መጠበቅ
 ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል
 ሉዕላዊነትን ማረጋገጥ
 የዜጎች የግል ፍላጎት መጠበቅ

2. የሕግ ተገዢነትን ለማስጠበቅ ዜጎች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ድርጊቶች ላይ ተወያዩ፡፡

የሚከተሉት ዜጎች ሀላፊነታቸውን እንድወጡ ሊያደርጓቸው የሚችሉ የተወሰኑ ምሳሌዎች


ናቸው፡-
• ነፃነታቸው ገደብ እንዳለው መገንዘብ፡፡ ለምሳሌ ድርጊታቸው የሌሎች መብት ላይ
በአሉታዊ መልኩ ተጽእኖ እንደማይፈጥር መገንዘብ
• የሀገራቸውን ሕጎች ማወቅና ለሕጎች መገዛት፡፡
• ሰላም መጠበቁን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መተባበር፡፡ ጥርጣሬ
ውስጥ የሚከት እንቅስቃሴ ሲያዩ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ማሳወቅን
ሊያካትት ይችላል፡፡

20 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


3. በትምህርት ቤታችሁ ውስጥ ለህግ ተገዢነት ምሳሌ የሚሆኑ ድርጊቶች ውስጥ የተወሰኑትን ጥቀሱ፡፡
የሚከተሉት ተማሪዎች በትምህርት ቤት ውስጥ ለሕግ ተገዥ የመሆናቸው ማሳያ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
 የትምህርት ቤታቸውን ሕግና ደንብ ማወቅ
 ከአቻዎቻቸው ጋር አወንታዊ መስተጋብር ማድረግ
 እያንዳንዱ ተማሪ ለትምህርት ቤቱ ደንብ መገዛት

2.3 ክፍለ ትምህርት 3 ለሕግ ተገዢ የሆነ ሰው ባህሪያት


2.3.1 የመማር ብቃት ፡ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
 ለሕግ ተገዢ የሆነ ሰው ባህሪያትን ይገነዘባሉ
 ለሕግ ተገዢ የሆነ ሰው ባህሪያት የተወሰኑ ምሳሌዎች ይጠቅሳሉ

2.3.2 ይዘት

1.ለሕግ ተገዢ የሆነ ሰው ባህሪያት ፡- የተመደበ ሰዓት፡- 5 ክፍለ ጊዜ

2.3.3 አጭር ገለፃ


አሁን ተማሪዎች ለሕግ ተገዢ መሆን ያለውን ፋይዳ አስመልክቶ የተወሰነ ሀሳብ ስለያዙ ውይይቱ ለሕግ
ተገዢ የሆነ ሰው የሚያሳያቸው ባህሪያትን ወደ መግለጽ ያመራል፡፡ በዚህ ክፍል ተማሪዎች እውነተኛ የሕግ
ተገዢ ዜጋ ለመሆን ምን እንደሚያስፈልጋቸው ይማራሉ፡፡ ለሕግ ተገዢ የሆነ ዜጋ ምን ማወቅ አለበት
እንዴትስ በህብረተሰቡ ውስጥ ጉዳዩን ያከናውናል፡፡

2.3.4 የመማር ማስተማር ሂደት


ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች
 ምስሎች - ፎቶዎች

ተመራጭ የማስተማሪያ ዜዴዎች


•ማነቃቂያ
•ትምህርቱን ማስተዋወቅ
•ገለፃ
•ጥያቄና መልስ
•የቡድን ውይይት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


•አስፈላጊ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎችን ያዘጋጁ
•ትምህርቱ ከመጀመሩ በፊት ተማሪዎች በያንዳንዱ ጽንስ ሀሳብ የራሳቸውን አረዳድ እንዲያንጸባርቁ
ጊዜ ስጧቸው፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 21


የትምህርቱ አቀራረብ
1. የትምህርቱን የትምህርት ርዕስ ማስተዋወቅ

መምህሩ ተማሪዎች ለሕግ ተገዥ የሆነ ሰው ባህሪያቶችን እንዲገልጹ በማድረግ ትምህርቱን ሊጀምሩ
ይችላሉ
• የትምህርቱን ዓላማ ለተማሪዎች ያሳውቋቸው
• ተማሪዎች ለሕግ ተገዢ የሆነ ሰው ባህሪያቶች ላይ የራሳቸውን ሀሳብ እንዲያንፀባርቁ በቂ
ጊዜ ይስጧቸው
• ሀሳባቸው ሊያነሳሱ የሚችሉ ጥያቄዎች ይጠይቋቸው
2. የትምህርቱ አካል
 መምህሩ ተማሪዎች ለሕግ ተገዢ የሆነ ሰው ባህሪያትን አስመልክቶ ያላቸውን አረዳድ
በመገመት ትምህርቱን ቢጀምሩ የተሻለ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ መምህሩ የተባሉትን ባህሪያት
በዝርዝር ወደ መግለጽ ሊያመራ ይችላል፡፡

3. ማጠቃለያ
የትምህርቱን ዋና ዋና ጽንስ ሀሳብ በማንሳት ያጠቃልሉ
 ለሕግ ተገዢ የሆነ ሰው ባህርያት

4. ግምገማና ክትትል
ሀ/ ግምገማ
 ተማሪዎች ትምህርቱን መረዳታቸውን ያረጋግጡ፡፡ ይህ አጭር ፈተና ወይንም
የክፍል ሥራ በመስጠት ሊከወን ይችላል፡፡ መምህሩም ተማሪዎችን በቡድን
አቧድኖ ከአቻዎቻቸው ጋር ሆነው ስለ ሕግ ተገዢ የሆነ ሰው ባህሪያት እንዲወያዩ
በማበረታታት ይችላል፡፡

ለ/ ክትትል
ትምህርቱን ስለ ሕግ ተገዥ የሆነ ሰው ባህርያቶች አጠር አድርጐ በመወያየትና በተማሪዎች
መካከል ቃለ ምልልስ እንዲያደርጉ በማበረታት ሊያጠቃልል ይችላል፡፡
• ተማሪዎች ትምህርቱን በተሻለ እንዲረዱት ለማረጋገጥ የቡድን ስራ ወይንም ሌላ
ተግባራት መስጠት ይቻላል፡፡

• ተማሪዎች ለሕግ ተገዢ የሆነ ሰው ባህሪያቶች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ መገምገም

2.3.5 ለተግባራት የተሰጡ መልሶች

ተግባር 2.3. ትዕዛዝ፡- የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ አሰላስሉ፡፡ በመልሶቻችሁም


ከአቻዎቻችሁ ጋር ተወያዩበት
1) ለሕግ ተገዢ የሆነ ሰው ግዴታዎቹን ለመወጣት ማድረግ ያለበት ድርጊት ላይ ተወያዩ፡፡
 ሕጎች በሰዎች ፍቃድ የተመሰረቱ እንደሆኑ መገንዘብና ለህጎቹም ተገዥ መሆን፡፡
 ለሕግ ተገዢ የሆነ ዜጋ ሕጎች ማህበራዊ ለውጥ ማምጫ መተግበሪያ መሳሪያ
መሆናቸውን ይገነዘባል

22 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


2. ለሕግ ተገዢ የሆኑ ተማሪዎች ያላቸውን ማህበረሰባዊ ሀላፊነት ዘርዝሩ፡፡
እነዚህ መልስ ሊሆኑ ይችላሉ፡-
 በማንኛውም ጊዜ የሀገርን ሕግና ስርዓት የማክበር አስፈላጊነትን መገንዘብ፡፡
 ሕግና ስርዓት በህብረተሰቡ አሸናፊ እንዳይሆን ፀር የሚሆኑ ተግባራት ሲመለከቱ ለሚመለከተው
አካል ማሳወቅ
 ለሕግ ተገዢ የሆኑ ዜጎች ሕጎች ማህበራዊ ለውጥ ማምጫ መተግበሪያ መሳሪያ መሆናቸውን
መገንዘብ
3. ለሕግ ተገዢ የሆነ ዜጋ ሊያስወግዳቸው ከሚገቡ ድርጊቶች ውስጥ የተወሰኑትን ጥቀሱ

ለሕግ ተገዢ የሆነ ሰው፡-

 የወገኑን መብት ከመጣስ መራቅ አለበት

 የህብረተሰቡን ሰላማዊ አብሮ መኖር ከሚያውኩ ድርጊቶች እንደ ስርቆትና ውሸት የመሳሰሉት
መቆጠብ አለበት

2.4 ክፍለ ትምህርት 4፡ ለሕግ ተገዢ አለመሆን የሚያስከትላቸው ችግሮች


2.4.1 የመማር ብቃት ፡ ከዚህ ትምህርት በኋላ ተማሪዎች፡
• ለሕግ ተገዢ አለመሆን የሚያስከትላቸው ችግሮችን ይገነዘባሉ
• ለሕግ ተገዢ አለመሆን የሚያስከትለውን ችግር ከአባባቢያቸው አንፃር ምሳሌ ይሰጣሉ

2.4.2 ይዘቶች

1. ለሕግ ተገዢ አለመሆን የሚያስከትላቸው ችግሮች፡- የተመደበ ሰዓት 6 ክፍለ ጊዜ

2.4.3 አጭር ገለፃ

በህብረተሰብ ውስጥ ለሕግ ተገዢ አለመሆን ብዙ አሉታዊ የሆኑ ችግሮችን ያስከትላል፡፡


እነዚህ ችግሮች የአንድ ዜጋ እንዲሁም የህብረተቡ ህይወት ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራሉ፡፡ እነዚህ
ችግሮችና ተዛማጅ ምሳሌዎቻቸው የተማሪዎቹን ግንዛቤ የበለጠ ስለሚያጎለብት አፅንኦት
ስጧቸው፡፡

2.4.4 የመማር ማስተማር ሂደት

ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪዎች

- ምስሎች - ፎቶዎች

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 23


ተመራጭ የማስተማሪያ ዜዴዎች
•ማነቃቂያ

 ትምህርቱን ማስተዋወቅ

 ገለፃ

 ጥያቄና መልስ

 የቡድን ውይይት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


 ተገቢ የሆኑ የማስተማሪያ መሳሪያዎች ማዘጋጀት

 ተማሪዎች በያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አረዳድ እንዲያንፀባርቁ በቂ ጊዜ መስጠት

የትምህርቱ አቀራረብ

1. የዕለቱን የትምህርት ርዕስ ማስተዋወቅ

መምህሩ ተማሪዎችን ለሕግ ተገዢ አለመሆን የሚያስከትላቸውን ችግሮች እንዲጠቅሱ በማደፋፈር ትምህርቱን
መጀመር ይችላል ፡፡

 የትምህርቱን ዓላማ ለተማሪዎች ማሳወቅ

 ተማሪዎች ለሕግ ተገዢ አለመሆን የሚያስከትለውን ችግር አስመልክቶ እንዲያነቡና ሀሳባቸውን


እንዲያንፀባርቁ በቂ ጊዜ መስጠት፡፡

 የተማሪዎችን ሀሳብ ሊያነሳሳ የሚችል ጥያቄ ያንሱ

2. የትምህርቱ አካል

 ይህ ክፍል ለሕግ ተገዢ አለመሆን የሚያስከትላቸው ችግሮች ላይ አጭር ገለፃ በማድረግ


ሊጀመር ይችላል፡፡ መምህሩ በክፍል ውስጥ የሚከወኑ አጭር የመወያያ ርዕስ ሊሰጧቸው
ይችላሉ፡፡

3. ማጠቃለያ፡- የትምህርቱን ዋና ዋና ነጥብ በማንሳት ያጠቃልሉ

 ለሕግ ተገዥ አለመሆን የሚያስከትለው ችግር

24 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ግምገማና ክትትል

ሀ/ ግምገማ

•ተማሪዎች ትምህርቱን መረዳታቸውን ያረጋግጡ፡፡ ይህም የክፍል ስራ ወይም አጭር ፈተና በመስጠት
ሊከወን ይችላል፡፡ መምህሩም ተማሪዎችን በቡድን በማደራጀት ከአቻዎቻቸው ጋር በመሆን የሕግ
ተገዢ አለመሆን የሚያስከትላቸውን ችግሮች እንድገልፁ ሊያደርግ ይችላሉ፡፡

ለ/ ክትትል
ለህግ ተገዢ አለመሆን የሚያስከትለውን ችግር አጠር ባለ ውይይት እንድያዩ በማበረታታት ከአቻዎቻቸው
ጋር ሀሳብ እንድለዋወጡ በማድረግ ትምህርቱን ያጠቃሉ

•መምህሩ ተማሪዎች ትምህርቱን በተሻለ መንገድ እንደተረዱት ለማረጋገጥ የቡድን ሥራ ወይም


የተለያዩ ተግባራትን በመስጠት እያዳንዱ ተማሪ በውይይት መሳተፉን ማረጋገጥ ይችላሉ

•ተማሪዎች ለሕግ ተገዢ ስላለመሆን ችግር ያላቸውን አረዳድ ይገምግሙ

የመልመጃ 2.1 መልሶች

ትዕዛዝ አንድ እውነት/ሀሰት

1. እውነት

2. ሀሰት

3. እውነት

4. ሀሰት

5. እውነት

ትዕዛዝ ሁለት ምርጫ

1. ለ

2. ሐ

3. ሐ

4. ሀ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 25


ትዕዛዝ ሦስት. የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ በመልሶቹም ዙሪያ ከአቻዎቻችሁ ጋር ተነጋገሩ፡፡
1. ለሕግ ተገዢነት ማለት ምን ማለት ነው?

 ለሕግ ተገዢነት ማለት የአንድ ሰው ለሀገሩን ሕጐች ለመታዘዝ ያለው ዝግጁነትና ቁርጠኝነት
ማለት ነው፡፡

 ለሕግ ተገዢነት የሰዎች ፍላጎትን ማክበር ነው

 ማንኛውም ድርጊት የሀገሩን ሕግ የማይጥስ መሆኑን መቆጣጠር ነው፡፡

2. ለሕግ የሚታዘዙ ዜጎች ባህሪያት ውስጥ የተወሰኑትን ጥቀሱ

 ሕጎች የሚቀመጡት የዜጎች የግል መብት ለማረጋገጥ መሆኑን የተገነዘቡ ናቸው፡፡

 ሕግ አክባሪ ዜጎች የህብረተሰቡ ሰላም የሚፃረሩ ድርጊቶችን ሲያዩ ለሚመለከተው አካል


የሚያሳውቁ ናቸው፡፡

3. በማህበረሰቡ ዉስጥ ለህግ ተገዥነት ስላለዉ አስፈላጊነት ተወያዩ፡፡

እነዚህ ሕግ ማክበር ለህብረተሰቡ ከሚሰጠው ጠቀሜታዎች ውስጥ የተወሰኑት ናቸው፡፡

 ነፃነትን እስከ ተገቢነቱ ድረስ ማጣጣም

 ሰላምን ማስጠበቅ

 ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል

 የዜጐች የግል ፍላጐት መጠበቅ

4. ለሕግ ተገዢ አለመሆን ስለሚያስከትላቸው ችግሮች ከጓደኞቻች ጋር ተወያዩ፡፡

 የሰላም አለመኖር

 የሰብዓዊ መብቶች መጣስ

 ሙስና

 የሱስ ተገዥነት

 የሕፃናት ህግወጥ ዝውውር

 ግብር ማሸሽ

 ነፃነት ማጣት

26 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ምዕራፍ ሶስት
መልካም ባህሪ
መግቢያ
በዚህ ምዕራፍ ተማሪዎች የመልካም ባህርይ ትርጉምን ይማራሉ:: መልካም ባህርያቶችንም ይዘርዝራሉ፡፡
ተማሪዎች መልካምና መጥፎ ባህሪያት ያላቸውን ልዩነት ይለያሉ፡፡ ምዕራፉ የመልካም ሰው ጥሩ ባህርያቶችና
በህይወታቸው ያላቸውን አስፈላጊነት ያጠቃለለ ነው፡፡

በተጨማሪም እንዴት መልካም ባህሪያቶችን ማጎልበት እንደሚቻል ይገልፃል፡፡ በዚህ ክፍለ ትምህርት
ተማሪዎች የመልካም ባህሪይ አለመኖር በቤተሰብ፣ በትምህርት ቤትና በማህበረሰብ ወዘተ የሚያስከትላቸውን
ችግሮች ይማራሉ ፡፡
የምዕራፉ የመማር ውጤቶች

ተማሪዎች ይህን ክፍለ ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-

•የመልካም ባህርይ ትርጉምን ያብራራሉ

•መልካም ባሕርይ ያለው ሰው መገለጫዎችን ያብራራሉ

•የመልካም ባህርይ መላበስን አስፈላጊነት ዋጋ ይሰጣሉ

•መልካም ባህርይ ማጠናከሪያ መንገዶችን ያጠናክራሉ

•የመልካም ባሕርይ አለመኖር የሚያስከትላቸውን ችግሮች ይገልጻሉ

የተመደበው ሰዓት፡ 20 ክፍለ ጊዜ

ትምህርቶች
•ክፍለ ትምህርት 1 የመልካም ባህርይ ትርጉም

•ክፍለ ትምህርት 2 መልካም ባሕርይ ያለው ሰው መገለጫዎች

•ክፍለ ትምህርት 3 የመልካም ባሕርይ የመላበስ አስፈላጊነት

•ክፍለ ትምህርት 4 የመልካም ባሕርያት ማጠናከሪያ መንገዶች

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 27


3.1 ክፍለ ትምህርት 1 የመልካም ባህርይ ትርጉም

3.1.1 የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህን ክፍለ ጊዜ ከተማሩ በኋላ፡-


• የመልካም ባህርያት ምንነትን ይረዳሉ

• የተማሪዎች የመልካም ባህርያት ምሳሌዎችን ይዘረዝራሉ

• በዕለት ተዕለት ህይወታቸው መልካም ባህርያትን ይለማመዳሉ

3.1.2 ይዘት

የተመደበ ሰዓት፡ 2 ክፍለ ግዜ

1. የመልካም ባህርያት ትርጉም

3.1.3 አጭር ገለፃ


የመልካም ባህሪን ትርጉም መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ መልካም ባህርይ መላበስ ጥሩውን
ከመጥፎው ለመለየት በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ የሆኑ ነው፡፡ ‹ባሕርይ› የሚለው ቃል እንዴት ድርጊት
እንደምንፈፅም፣ቤተሰቦቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ መምህራኖቻችንና የአካባቢያችን ማህበረሰብ እንዴት
እንደምናስተናግድ አመላካች ነው፡፡ መልካም ባሕርይ መልካም ሰሜት መኖርና እንደራስ ለሌሎችም
መልካም ነገር መስራት ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡ መልካም ባህርይ የሰብአዊነት ፣ የለጋሽነት፣ የአዛኝነት፣
የሌላ ሰው ሰሜት መካፈል፣ የአሳቢነት፣ የወዳጅነት፣ የትህትናና ወዘተ ሰሜት ማሳያ ነው፡፡ መልካም
ባህርይ ያለው ሰው ለራሱ/ሷ የሚሻውን/ የምትሻውን መልካም ነገር ለሌሎችም ያደርጋል፡፡ ከዚህ ጋር
ተያይዞ የተማሪዎች ወይንም የልጆች ባህርይ ከቤተሰቦቻቸው ከጓደኞቻቸውና ከአካባቢያቸው በሚያገኙት
ልምድ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሕፃን ልጆች አጠገባቸው ያሉት ሰዎች ሲያጭበረብሩ ካዩ አእምሮዋቸው
የማጭበርበር ድርጊት ማሰብ አቅም አለው፡፡ ባህርያት የምርጫ ውጤቶች ናቸው፡፡ ማንኛውም ሰው
መልካም ተግባር የመስራት ምርጫ አለው፡፡ ለምሳሌ አንድ ተማሪ ከጓደኞቹ መልካም ወይንም መጥፎ ነገር
የመውረስ ምርጫ አለው፡፡

3.1.4 የመማር ማስተማር ሂደት

ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች


-ምስሎች - ፎቶዎች

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች

28 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


መምህሩ የሚከተሉትን ዘዴዎች በመጠቀም ትምህርቱን መግለፅ ይጠበቅባቸዋል

• የማነቃቂያ ጥያቄዎችን መጠየቅ

• የዕለቱ ትምህርት ማስተዋወቅ

• ገለፃ ማድረግ

• የመፅሐፉን ተግባራት እንዲተገብሩ ማድረግ

• ተማሪዎች በቡድን ሆነው እንዲወያዩ አቅጣጫ መስጠትና ውይይቱን ማመቻቸት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


•መምህሩ/ሯ ተገቢ የሆነ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት አለበት

•መምህሩ/ሯ በዚህ ትምህርት ክፍል የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮችን ማስተዋወቅና ተማሪዎች በጉዳዩ


ላይ የራሳቸውን ሀሳብ እንዲያቀርቡ ማደፋፈር አለበት/ አለባት፡፡

1. የትምህርቱ አቀራረብ

መምህሩ የመልካም ባህርይ ትርጉም ላይ አፅንኦት ሰጥቶ ማስተዋወቅ አለበት፡፡

 መምህሩ/ሯ በዚህ ክፍለ ትምህርት የሚጠበቅ የመማር ብቃትን ለተማሪዎች ያስተዋውቃሉ

 ተማሪዎች ለሀሳብ ማፍለቂያ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ ያደፋፍራሉ፡፡

2. የትምህርቱ አካል

መምህሩ/ሯ የመልካም ባህርያት ትርጉምን ይገልፃል፡፡ በመቀጠልም የተማሪዎች መልካም ባህርያት


ምሳሌዎችን ያብራራሉ፡፡ በዚህም መምህሩ/ሯ መልካም ባህርያት በተማሪዎቸ የሚገለጹባቸውን
መንገድ ይገልፃል፡፡

 የባህርይን ቃል ትርጉም

 የመልካም ባሕርይ ትርጉም

 የተማሪዎች መልካም ባህሪ መገለጫዎች

 የተማሪዎች ወይንም የልጆች ለመልካም ወይንም ለመጥፎ ባህርያት የሚገፋፉ መሰረታዊ


ነገሮች
3. ማጠቃለያ፡- የዚህን ትምህርት ዋና ዋና ጽንስ ሀሳብ በማንሳት ያጠቃላሉ

 የመልካም ባህርይ ትርጉም

 የተማሪዎች መልካም ባህርያት ዝርዝሮች

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 29


4. ግምገማና ክትትል

ሀ. ግምገማ

• ተማሪዎች ትምህርቱን መረዳታቸውን ያረጋግጡ፡፡ ይህም ለተማሪዎች ቀላል ፈተና ወይንም


የክፍል ሥራ በመስጠት ሊከወን ይችላል፡፡ ምናልባትም መምህሩ ተማሪዎችን በቡድን በማቧደን
ከአቻዎቻቸው ጋር በመሆን በመልካም ባህርያት ትርጉም ዙሪያ እንዲወያዩ ማበረታታት ይችላሉ፡
፡ መምህሩ ተማሪዎች መልካም ባህሪያትን አስመልክቶ የራሳቸውን ምሳሌዎች እንዲዘረዝሩ
ሊያበረታቷቸው ይገባል፡፡

ለ. ክትትል
• የመልካ ባህርይን ትርጉም ያጠቃሉ፡፡ ተማሪዎቹም እርስ በርሳቸው እንዲወያዩ ያበረታቷቸው፡፡
መምህሩ ለተማሪዎች የተወሰኑ ስራዎችን በግልም ይሁን በቡድን እንዲሰጧቸው ይጠበቃል፡
፡ መምህር የተማሪዎችን መልካም ባህርይ አስመልክቶ የራሳቸውን ምሳሌ እንዲዘረዝሩና
እንዲጠቅሱ ያደርጉ፡፡

• እባክዎትን መምህር ተማሪዎች በውይይቱ ተሳታፊ እንዲሆኑና የተማሪዎች መልካም ባህርይ


ምሳሌዎችን እንዲሰጡ ያድርጉ፡፡

3.1.5 የተግባራት መልሶች

ተግባር 3.1. ትዕዛዝ፡- የማነቃቂያ ጥያቄዎች

1. መልካም ባህርይ ማለት ምን ማለት ነው?

መልካም ባህርይ ማለት በዕለት ተዕለት ህይወታችን ለራሳችንና ለሌሎችም የማይጎረብጥ/ የሚመች
ማንኛውም ባህርይ ማለት ነው፡፡ መልካም ባህርይ የግለሰቡ እምነትና አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡ ግለሰቡ
ከሚናገርበት፣ ድርጊት ከሚፈጽምበትና ከሌሎች ጋር መስተጋብር ከሚያደርግበት መንገድ ጋር ቀጥተኛ
ግንኙነት አለው፡፡
2. መልካም ባህርያት ተብለው ከሚገመቱ ባህርያት የተወሰኑትን ጥቀሱ

መልካም ባህርያት በቁጥራቸው ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ለጋሽነት፣ አዛኝነት፣ ትሁትነት፣ ታማኝነት፣


ቅንነት፣ በራስ መተማመን፣ ሚስጢር ጠባቂነት ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም መምህሩ ተማሪዎች
ከአካባቢያቸው ወይንም ከማህበረሰብ አርአያዎቻቸው መልካም ባህርያት መካከል እንዲጠቅሱ ይጠይቋቸው፡

3.2 ክፍለ ትምህርት 2፡- የአንድ ግለሰብ መልካም ባህርያት መገለጫዎች
3.2.1 የመማር ብቃት ፡ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማራችሁ በኋላ፡-

 መልካም ባህርይ ያለው ግለሰብ መገለጫዎችን ያብራራሉ

3.2.2 ይዘቶች

የተመደበ ሰዓት፡- 6 ክፍለ ግዜ

30 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


1) የመልካም ባህርይ አስፈላጊነት
3.2.3 አጭር ገለፃ

በዚህ ትምህርት ተማሪዎች የመልካም ሰው ባህርያትን ይማራሉ፡፡ መልካም ሰው የመልካም ሰው


መለያዎች የሚያሳይ ነው፡፡ በትምህርት ወቅት መምህሩ/ሯ የመልካም ሰው ባህርያትን ለተማሪዎች
ማስተዋወቅ አለበት/ባት ለምሳሌ የሚከተሉት የተወሰኑ የመልካም ሰው መገለጫ ባህሪያት ናቸው፡-

• ምሉዕነት

• ተዓማኒነት

• ተጠያቂነት

• ለሌሎች ዋጋ ፣ ክብርና አድናቆት መስጠት

• ራስን መግዛት

• እምነት እሚጣልበት

• ሚስጥር ጠባቂነት ወዘተ

3.2.4 የመማር ማስተማር ሂደቶች

ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች


- ምስሎች - ፎቶዎች - ተግባራት

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች

መምህሩ የሚከተሉትን ዘዴዎች በመጠቀም ለተማሪዎች ግልጽ ማብራሪያ ያደርጋል፡-

» መምህር ተማሪዎች እንዲቆሙ በማድረግ በአራት ቡድን ያቧድኗቸው፣ ከዚያ ከሌላ ቡድን ጋር
ይቀላቅሏቸው እና ስምንት ቡድን ያድርጓቸው፣ በመቀጠልም በአስራ ስድስት ቡድን ለክፍሉ በሙሉ
ያቅርቡ (ይህ ተማሪ አሳታፊ ‹‹ፒራሚዲንግ) የሚባል የማስተማር ዘዴ ነው፡፡

» የእለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ

» ገለፃ

» መምህሩ/ሯ ተማሪዎችን በአምስት ቡድን አቧድኖ ከመጽሐፍ ውስጥ ያሉ ተግባራትን በመስጠት


እንዲወያዩ ያድርጓቸው፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 31


ቅድመ- ትምህርት ዝግጅት
• መምህሩ/ሯ ተገቢ የማስተማሪያ አጋዥ መሳሪያዎች ያዘጋጁ

• በዚህ የትምህርት ክፍል የቀረቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን ያስተዋውቁ፡፡ ተማሪዎች በጉዳዮቹ ላይ የራሳቸው


አረዳድ እንዲያንፀባርቁ ያድርጉ

የትምህርቱ አቀራረብ
1. የዕለቱን የትምህርት ርዕስ ማስተዋወቅ
መምህሩ አጠር አድርጎ ትምህርቱን ያስተዋውቃል፡፡ ማስተዋወቁ መሰረታዊ የሚባሉ የመልካም ሰው
መለያዎች ማካተት አለበት፡፡

• መምህሩ/ሯ ከትምህርቱ የሚፈለጉ የመማር ብቃቶች ለተማሪዎች ማስተዋወቅ ይጠበቅበታል፡፡

• መምህሩ ተማሪዎቹ ለማነቃቂያ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ ማበረታታት አለበት፡፡

1. የትምህርቱ አካል

መምህሩ የመልካም ሰው መሰረታዊ መገለጫዎችን ይገልፃሉ፡፡ መምህሩ የመልካም ሰው አይነተኛ


መገለጫዎችን ለማቅረብ ይሞክራሉ፡፡

መምህሩ እነዚህን ያስተዋውቃሉ፡-

» የመልካም ሰው/ተማሪ ጥሩ መለያዎች

• ሐቀኝነት

• ምሉዕነት

• ክብር መስጠት

• ተጠያቂነት

• ታማኝነት

2. ማጠቃለያ

የትምህርቱን ዋና ጽንስ ሀሳብ ያጠቃሉ

 የመልካም ሰው/ተማሪ መሰረታዊ መገለጫዎች

 የመልካም ባህርያ ያለው ሰው አይነተኛ ምሳሌዎች

3. ግምገማና ክትትል

32 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ሀ .ግምገማ
• መምህሩ ተማሪዎች ትምህርቱን ምን ያህል እንደተረዱት ያረጋግጡ፡፡

ይህ ተግባር ተማሪዎች በቡድን እንዲወያዩ ወይንም በተማሪ ፊት እንዲያቀርቡ በማድረግ ሊከወን


ይችላል፡፡

ለ. ክትትል

• መምህሩ ትምህርቱን ቢያጠቃልሉ ጥሩ ነው፡፡ መምህሩ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ


የሚያደርጉትን ድርጊቶች ክትትል እንዲያደርጉ ይጠበቃል ወይንም ከትምህርቱ ጋር
ተያያዥነት ያለው ተማሪ ተኮር ተግባር መምረጥ ይችላል፡፡

3.2.5 ለተግባራቱ የተሰጡ መልሶች

ተግባር 3.2 ትዕዛዝ፡ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ስጡ፡፡ ከአቻዎቻችሁ


ጋር በመሆን በመልሶቹ ዙሪያ ተወያዩ፡፡

1. መልካም ሰው ማን ነው?

 የተከበሩ መምህር እባክዎትን ተማሪዎች በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲጠይቁና በክፍሉ


ውስጥ እንዲወያዩበት አድርጓቸው፡፡

ፍንጭ - መልካም ሰው ማለት የዕለት ተዕለት ህይወቱን ከመልካም ሰው መለያ


ባህርያት ጋር ያስተሳሰረ ማለት ነው፡፡

2. የመልካም ሰው መለያዎች ምንድን ናቸው?


አያሌ የመልካም ሰው
 ባህሪያቶች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ ለራሳችንና ለሌሎች
ክብር መስጠት፣ ምሉዕነት፣ ተጠያቂነት፣ እምነት የሚጣልበት፣ ታማኝነትና ወዘተ
ይጠቀሳሉ፡፡
እባኮትን መምህር ተማሪዎች በመልካም ሰው ባህርያት ተጨማሪ ውይይት እንዲያደርጉ
አበረታቷቸው፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 33


ተግባር 3.3 ትዕዛዝ፡ የማነቃቂያ ጥያቄዎች

1. ማክበር ማለት ምን ማለት ነው?

 ክብር መስጠት በብዙ መንገዶች ሊተረጎም ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ለውይይታችን ሲባል
ሰዎችን በስብዕናቸው፣ በችሎታቸው በጥሩ መገለጫ ባህሪያቸው ወይንም በሚያከናውኑት
ተግባር መሰረት ክብር መስጠትን ያመለክታል፡፡

2. የሌሎችን ንብረት ማክበር ማለት ምን ማለት ነው?


የሌሎችን ንብረት ማክበር የእኛ ላልሆነው ማንኛውም ንብረት ዋጋና ክብር መስጠትን ያሳያል፡፡

ተግባር 3.4. ትዕዛዝ ፡ ከክፍል ጓደኞቻችሁ ጋር በመሆን ቡድን መስርታችሁ በእነዚህ ጥያቄዎች ተወያዩ፡

1. ሀቀኛ ሰው ማን ነው? እባኮትን መምህር በመጽሐፍ በተገለጸው በያንዳንዱ ጉዳይ ተማሪዎች


ወላጆቻቸውን እንዲጠይቁና ክፍል ውስጥ እንዲያቀርቡ እርዱዋቸው፡፡

ፍንጭ፡-

 ሀቀኛ ሰው ማለት ሁል ግዜ እውነትን የሚናገር በውሸት የማይሳተፍ ንብረቶችን የማይሰርቅ


ወዘተ ማለት ነው፡፡

 ተማሪው የማጭበርበር ሀሳብን እምቢ ማለት አለበት፡፡

እባክዎትን መምህር ተማሪዎች በጉዳዩ ላይ እንዲወያዩ ይፍቀዱላቸውና በመጽሐፉ ውስጥ ላሉት ጥያቄ 1.2
እና 1.3 ትክክለኛ መልስ ይስጧቸው፡፡

ተግባር 3.5 ትዕዛዝ፡ ተማሪዎች ቤተሰቦቻችሁን በመጠየቅ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ሰጡ፡፡
1. መከባበር ለምን አስፈለገ?

 መከባበር በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ መኖር ያለበት አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ለሌሎች ክብር እንድንሰጥ
የሚገፋፋን/ የሚያነሳሱን የተለያዩ ምክንያቶች አሉ፡፡

ከነዚህ የሚያነሳሱን ምክንያቶች መካከል እነዚህ የሚከተሉት ናቸው፡-

* የሕሊና እርካታን ለማግኘት

* ችግሮችን ለመፍታት ፡፡

* ሀቀኝነትን ለማሳየት

* የተሻለ ግንኙነትን ለመመስረት

34 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


• መከባበር በሥራና በስራ መስክ አስፈላጊ ነው

• መከባበር የአእምሮ ሰላም እንድናጣጥም ይረዳናል

• መከባበር በህይወት ላይ አወንታዊ እይታን ያጠናክራል

• በሥራ መስክ መረጣ ወቅት መከባበር አስፈላጊ ነው

• መከባበር ሰዎች በህይወታቸው ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ይረዳል

• መከባበር በጣም ጥቂት ተቃርኖዎችን ይይዛል

• መከባበር መልካም ጓደኛና ቤተሰብ ይፈጥራል

• መከባበር በህይወት ውስጥ በጣም ትልቅ ሚና አለው

• መከባበር በአንድ ግለሰብ ውስጥ በራስ መተማመን ለመገንባት ይረዳል

• መከባበር አንድን ሰው ነገሮችን ከሰሜት ነፃ ሆኖ እንዲያይና አእምሮው ክፍት


እንዲሆን ያደርጋል

2. ለምን አናከብርም?

የተከበሩ መምህር ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎች በጉዳዩ ላይ እንዲወያዩ አግዙዋቸው የግል ልምድዎን
ካነበቡት መጽሀፍ ወዘተ ተመርኩዘው መልሰዎን ይስጡ፡፡

3. መከባበር ከየት መጀመር አለበት?

መከባበር ራስን ከማክበር ይጀምራል፡፡ ቀጥሎ አካባቢዎ ላሉት ሰዎች ወደ ማክበር ይሄዳል፡፡ይህ
ሀሳብ ሰውና ሰውም ላልሆነም ያገለግላል፡፡ በ

3.3 ትምህርት 3፡ መልካም ባሕርይ መላበስ ያለው ጠቀሜታ

3.3.1 የመማር ብቃቶች ፡ በትምህርቱ መጨረሻ ተማሪዎች፡-

 መልካም ባሕርይ መላበስ ጥቅሙ ያውቃሉ

 የመልካም ባህርይ መላበስ ጥቅሞች ይዘረዝራሉ

 ለመልካም ባህርይ መላበስ የሚሰጠው ዋጋ ትኩረት ይሰጣሉ

3.3.2 ይዘት

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 35


የተመደበ ሰዓት: 3 ክፍለ ጊዜ

1.የመልካም ባህርይ ገጽታዎች

3.3.3 አጭር ገለፃ የመምህሩ መምርያ


ይህ ክፍለ ትምህርት ለተማሪዎች በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ይህን ትምህርት በመማር ተማሪዎች
መልካም ባህሪን ያጎለብታሉ፡፡ ተማሪዎች መልካም ባህሪን የሚያጎለብቱበትን መንገድ እንዲያውቁ
ያግዛቸዋል፡፡ መልካም ባህሪይ የሚጎለብቱበትን ስልትም ያመላክታቸዋል፡፡ ለምሳሌ ራስን የመግዛት
ክህሎትን ማጎልበት፣ የግብረ ገብ ዕሴቶችንና መርሆችን መቀበልና ማጎልበት ለህግ ታማኝ
መሆን የመሳሰሉት መልካም ባህሪን ለማጎልበት የሚረዱ ናቸው፡፡

3.4.4 የመማር ማስተማር ሂደት

ተመራጭ የማሰተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች

Ô ስዕሎች
Ô ፎቶዎች
Ô ውስን ጥናት

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች


መምህሩ የሚከተሉትን ዘዴዎች በመጠቀም ትምህርቱን መግለፅ ይችላሉ፡
ተግባራት
ውስን ጥናት
የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ
ማብራሪያ
ለተማሪዎች ትዕዛዝ መስጠት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


• መምህሩ ለትምህርቱ ዝግጁ መሆን አለበት

• መምህሩ የመማሪያና የመምሪያ መፃሃፍትን በማንበብ መዘጋጀት አለበት

የትምህርቱ አቀራረብ
1. የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ
መምህሩ የመልካም ባህሪ ማጎልበቻ መንገዶችን አጠር አርጎ ማስተዋወቅ ይጠበቅበታል፡፡
 መምህሩ በዚህ ክፍለ ትምህርት የሚጠበቁ የመማር ብቃቶችን ማሳወቅ አለባቸው፡፡

 መምህሩ የተማሪዎቹ መፅሀፍ ላይ የተጠቀሱ ተግባራት ላይ የራሳቸውን ሀሳብ እንዲሰጡ


ይጠይቋቸዋል

36 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


2. የትምህርቱ አካል

 መምህሩ የመልካም ባህሪይ ማበልፀጊያ መንገዶች በሰፊው ያብራራሉ፡፡ በመቀጠል በያንዳነዱ ፅንሰ ሀሳብ
ላይ ይወያያሉ፡፡ መምህሩ ተግባራትና ምሳሌዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

የሚከተሉት ነጥቦች የውይይቱ መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች ይሆናሉ፡-


– የመልካም ባህሪይ ማጎልበቻ መንገዶች
– ራስን መግዛት
--ለህግ መገዛት
--የማህበረሰቡ የግብረ ገብ ዕሴቶችና መርሆች
---የትምህርት ቤት ህግና ደንቦች
3. ማጠቃለያ

የዕለቱን ትምህርት ዋና ዋና ነጥቦችን ማንሳትና ማጠቃለል መልካም ባህሪይን የመላበስ


ጥቅምን አይነተኛ ምሳሌዎች ያስታውሷቸው፡፡

4. ግምገማና ክትትል

ሀ .ግምገማ
• መምህሩ የክፍል ተግባር በመስጠት፣ስለ መልካም ባህሪ ውጤት እንዲወያዩ
በማድረግና እነዲያቀርቡ በመጋበዝ ተማሪዎች ትምህርቱን መረዳታቸውን
ያረጋግጣሉ፡፡
ለ. ክትትል
3.3.5. ለተግባራቱ የተሰጡ መልሶች
ተግባር 3.6 ትዕዛዝ 6: በቡድን በመሆ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ተወያዩባቸው፡፡

1) መልካም ባህሪ ለምን ይጠቅማል?


• ውድ መምህር የመልካም ባህሪን የመላበስ ጥቅምን በተመለከተ ለተማሪዎችዎ ወላጆቻቸውን
እንዲጠይቁ የቤትስራ ስጧቸውና ክፍል ውስጥ እንዲያቀርቡ በማድረግ ለጉዳዩ አፃንአት
ይስጡት፡፡
2) መኖርና ሌሎች እንዲኖሩ መፍቀድ ማለት ምን ማለት ነው?
• አንድ ሰው ራሱ መኖር እንደሚፈልገው ሁሉ ሌሎችም እንድኖሩ መፈለግ ማለት ነው፡
፡ ለሌሎች መኖር ማለት ሌሎችን ማስደሰትና ሀሳባቸውን ማስጠበቅ ማለት ነው፡፡ በተለያ
ምክንያት ለሌሎች እንኖራለን
• ከነዚህም ምክንያቶች ውስጥ፡-
– የሚወዱንና የምንወዳቸው ሰዎች ስላሉ
– ሰዎች ከእኛ የሚፈልጉት እንዲሁም እናም ከነሱ
የምንፈልገው ሌሎች ለመኖር እኛን ስለሚፈልጉ
እኛም ለመኖር እነሱን ስለምንፈልግ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 37


3.4 ክፍለ ትምህርት 4: መልካም ባህሪን ለመገንባት የሚጠቅሙን መንገዶች

3.4.1 የመማር ብቃት ፡ ተማሪዎች ይህን ክፍለ ጊዜ ከተማሩ በኋላ፡-


• መልካም ባህርይ የሚገነባባቸውን መንገዶች ያሳያሉ

• መልካም ባህሪይ የሚገነባባቸውን መንገዶች ይለያሉ

• መልካም ባህሪይ የሚገነባባቸውን መንገዶች ይለማመዳሉ

3.4.2 ይዘት

የተመደበ ሰዓት : 7 ክፍለ ጊዜ

1) የመልካም ባህሪይ አለመኖር የሚያስከትላቸው ችግሮች

3.4.3 አጭር ገለፃ

ይህ ክፍለ ትምህርት ለተማሪዎች በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ይህን ትምህርት በመማር ተማሪዎች
መልካም ባህሪን ያጎለብታሉ፡፡ ተማሪዎች መልካም ባህሪን የሚያጎለብቱበትን መንገድ እንዲያውቁ
ያግዛቸዋል፡፡ መልካም ባህሪይ የሚጎለብቱበትን ስልትም ያመላክታቸዋል፡፡ ለምሳሌ ራስን
የመግዛት ክህሎትን ማጎልበት፣ የግብረ ገብ ዕሴቶችንና መርሆችን መቀበልና ማጎልበት ለህግ
ታማኝ መሆን የመሳሰሉት መልካም ባህሪን ለማጎልበት የሚረዱ ናቸው፡፡
3.4.4. የመማር ማስተማር ሂደት
ተመራጭ የማሰተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች

Ô ስዕሎች
Ô ፎቶዎች
Ô ውስን ጥናት

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች


መምህሩ የሚከተሉትን ዘዴዎች በመጠቀም ትምህርቱን መግለፅ ይችላሉ፡
ተግባራት
ውስን ጥናት
የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ
ማብራሪያ
ለተማሪዎች ትዕዛዝ መስጠት

38 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ቅድመ ትምህርት ዝግጅት
• መምህሩ ለትምህርቱ ዝግጁ መሆን አለበት

• መምህሩ የመማሪያና የመምሪያ መፃሃፍትን በማንበብ መዘጋጀት አለበት

የትምህርቱ አቀራረብ

1. የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ

መምህሩ የመልካም ባህሪ ማጎልበቻ መንገዶችን አጠር አድርጎ ማስተዋወቅ ይጠበቅበታል፡፡


• መምህሩ በዚህ ክፍለ ትምህርት የሚጠበቁ የመማር ብቃቶችን ማሳወቅ አለባቸው፡፡

• መምህሩ የተማሪዎቹ መፅሀፍ ላይ የተጠቀሱ ተግባራት ላይ የራሳቸውን ሀሳብ እንዲሰጡ


ይጠይቋቸዋል

2. የትምህርቱ አካል

 መምህሩ የመልካም ባህሪይ ማበልፀጊያ መንገዶች በሰፊው ያብራራሉ፡፡ በመቀጠል በያንዳነዱ ፅንሰ
ሀሳብ ላይ ይወያያሉ፡፡ መምህሩ ተግባራትና ምሳሌዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

የሚከተሉት ነጥቦች የውይይቱ መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች ይሆናሉ፡-


– የመልካም ባህሪይ ማጎልበቻ መንገዶች
– ራስን መግዛት
--ለህግ መገዛት
--የማህበረሰቡ የግብረ ገብ ዕሴቶችና መርሆች
---የትምህርት ቤት ህግና ደንቦች
3 ማጠቃለያ
የዕለቱን ትምህርት ዋና ዋና ነጥቦችን ማንሳትና ማጠቃለል መልካም ባህሪይን የመላበስ
ጥቅምን አይነተኛ ምሳሌዎች ያስታውሷቸው፡፡
4 ግምገማና ክትትል

ሀ. ግምገማ
• መምህሩ የክፍል ተግባር በመስጠት፣ስለ መልካም ባህሪ ውጤት እንዲወያዩ በማድረግና እነዲያቀርቡ
በመጋበዝ ተማሪዎች ትምህርቱን መረዳታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 39


ለ. ክትትል

ተግባር 3.7 ትዕዛዝ ፡ ከቀደመው ተሞክሯችሁ በመነሳት የሚከተሉትን ጥያቄዎች


መለሱ፡፡

1) መልካም ባህሪን ማጎልበት ይቻላል ብላችሁ ታስባላችሁ;

 ውድ መምህር ተማሪዎቹን ለውይይቱ ያዘጋጇቸው

2) ከመልካም ባህሪይ ማሳደጊያ መንገዶች ውስጥ ቢያንስ አምስቱን ግለፁ፡፡

 ራስን መግዛት
 ህግን ማክበር
 የማህበረሰብ ዕሴቶችንና መርሆችን መቀበልና መከተል
 የትምህርት ቤቱን መተዳደሪ ደንቦች ማክበር.
• የማህበረሰቡን መርሆች ማክበር

40 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ተግባር 3.8 ትዕዛዝ: የማነቃቂያ ጥያቄዎች

1) ራስን መግዛት ማለት ምን ማለት ነው?


 ራስን መግዛት ማለት አስፈላጊ ካልሆኑ ዕሳቤዎችና ድርጊቶች ራስን የመገደብ ችሎታ ነው፡
፡ ድርጊትንናስሜትን አስፈላጊ ካልሆኑ ነገሮች መቆጠብ ማለት ነው፡፡
2) እንዴት ነው አነድ ሰው መልካም ባህሪን ማጎለብት የሚችለው?
 ውድ መምህር እባክዎን ከማህበረሰቡ አነፃር የራስወን የተወሰኑ ምሳሌ ይሠጧቸው፡፡
.ማጎልበት እነድሁም መጥፎ ባህርይን ማስወገድ የሚችሉባቸውን መንገዶች በግልፅ
ይንገሯቸው.
3) ራስን መግዛት ለምን ይጠቅማል?
 ራስን ከጥፋት ለመታድግ፣ ካላሰፈላጊ አሉታዊ ዲረጊቶች ለመራቅ እንድሁምአስፈላጊና
የተመጣጠነ ህይወት ለመኖር

ተግባር 3.9 ትዕዛዝ ከላይ የቀረበውን ምንባብ መሰረተ በማድረግ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ
ስጡ፡፡

1) ተማሪው ከችግሩ ለመውጣት እና የራሱን ውሳኔ ለመወሰን ምን ያስፈልገዋል፡፡


 ተማሪው ስህተት ከሆነ ተግባሩ ለመውጣት ጥሩ ያለሆነ ባህሪይ ከሚያስከትላቸው
ችግሮች ወስጥ የተወሰኑትን ማለትም ለምሳሌ ቢዋሽ ወይም ቢሰርቅ ማህበረሱ
ጋር ምን ሊያስከትል እነደሚችል መማርና ራሱን ካለበት መጥፎ ባህሪይ መውጣት
ይችላል፡፡
2) ለቶማስ ክፍል ውስጥ ከሚፈጥረው ብጥብጥና በአጠቃላይ ካለበት መጥፎ ባህሪይ እነዲወጣ
ምን ትመክሩታላችሁ?
 ክፍል ውስጥ የሚያደርገውን መጥፎ ተግባር ማስወገድ አለበት ፡፡
 ተግባራቶቹ በራሱም ሆነ በሌሎች ላይ የሚፈጥሩትን አሉታዊ ተፅዕኖ ግምት ውስጥ
ማስገባት አለበት፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 41


ተግባር 3.10 ትዕዛዝ በቡድን ተወያዩና የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡

1) የህግን ምንነት መግለፅ ትችላላችሁን?


ውድ መምህር, ተማሪዎች የጥሩ ባህሪን ምንነት እንዲረዱ በተግባር ይርዷቸው፡፡
2) ጥሩ ባህሪይ በምን ይገለፃል?
እባክዎ መምህር መፅሀፋቸው ላይ ያሉትን የመልካም ባህሪይ ማሳያዎች
እንዲያብራሩ ያድርጓቸው፡፡
3) በትምህርት ቤት እንዲሁም በማህበረሰብ ደረጃ ህግን የመቀበል የመተግበር
ሀላፊነት ያለበት ማን ነው
• ሁሉም ሰው ህግን የመቀበልና የመተግበር ሃላፊነት አለበትl. ለምሳሌ
እያንዳነዱ ተማሪ፣መምህራን ርዕሰ መምህራን ሁሉም የትምህርት ቤት
ማህበረሰብ፡፡

ተግባር 3.11 ትዕዛዝ፡- ወላጆቻችሁን በመጠየቅ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡


መልሶቻችሁንም ለመምህራችሁ አስረዱ፡፡

) ግብረ ገባዊ ዕሴት ማለት ምን ማለት ነው?


• ግብረገባዊ ዕሴቶች በቃል የተቀበልናቸውን ወጎች፣እምነትና ባህልን
ሊያጠቃልሉ ይችላሉ፡፡ ከማህበረሰቡ ባህልና እምነት የተቀረፁ ብዙ ዓይነት
የግብረ ገብ ህጎችም አሉ፡፡
2) በማህበረሰባችሁ የተለመደ ግብረገባዊ ዕሴት መጥቀስ ትችላላችሁን?
 ውድ መምህር ተማሪዎች በጋራ ፅንሰ ሀሳቦች ለምሳሌ ታላላቆችን
ማክበር፣ አለመዋሸት፣ መታመንና ትሁት መሆን የመሳሰሉት ጉዳዮች
ላይ እንድወያዩ ያበረታቷቸው፡፡

3) እንዴት ነው ድርጊታችሁን በማህበረሰቡ ዘንድ ትክክል ወይም ስህተት መሆኑን


የምታረጋግጡት?
 ውድ መምህር እባክዎን ተማሪዎች ድርጊታቸውን ልክ ነው ወይም
ስህተት ነው ለማለት የሚያስችላቸውን መመዘኛ ያሳውቋቸው፡፡

42 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ተግባር 3.12 ትዕዛዝ: የሚከተሉትን ጥቄዎች ከላይ በተቀመጠው ምስል
መሰረት መልሱ፡፡

1) ከላይ ከተቀመጠው ምስል ምን ተረዳችሁ ?

 ውድ መምህር, እባክዎን ምን እንደተረዱ ጠይቋቸውና ስለ ምስሉ


ምንነት መልሱን ንገሯቸው፡፡

ተግባር 3.13 ትዕዛዝ ሶስት ተማሪዎችን የያዘ ቡድን ያዋቅሩና ከሌላ ቡድን ጋር
ስለ መልሱ እንዲወያዩ አድርጉ፡፡

1) ስለ ትምህርት ቤቱ ህግና ደንብ ተረዳችሁን?

 ውድ መምህር ተማሪዎቹ የሚሰጡት መልስ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

2) የተማሪዎቹ መልስ አዎንታዊ ከሆነ ቢያንስ አምስት የትምህርት ቤቱ

ህግና ደንብ ይዘርዝሩ፡፡

 መምህሩ ተማሪዎች እንዲወያዩ ማበረታታት ይጠበቅባቸዋል፡

፡ በመቀጠልም ቀደም ብለው በመፅሀፉ የተጠቀሱትን የትምህርት

ቤቱን ህግና ደምብ ይጥቀሱ፡፡

ተግባር 3.14 ተዕዛዝ: አምስት አምስት በመሆን ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸውን ስለ


መጥፎ ባህሪ ቃለ መጠይቅ እንዲያረጉና መልሶቻቸውን ክፍል ውስጥ እንዲያቀረቡ
ያድርጓቸውና በመልሶቻቸው ዙሪያ አስተያየት ይስጡባቸው፡፡

1) ከመልካም ባህሪ አለመኖር የሚመነጩ የመጥፎ ባህሪያት ምሳሌዎችን እንዲጠቅሱ


ያርጓቸው፡፡እባክዎትን መምህር ከመጥፎ ባህሪያት ውስጥ የተወሰኑትን እንዲጠቅሱ
ያርጓቸውና ከውይይቱ በኋላ የራስዎን አይነተኛ ምሳሌዎች ይጥቀሱላቸው፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 43


3.5 የምዕራፉ ጥያቄ መልሶች

መልመጃ 3.1 ትዕዛዝ አንድ: “እውነት”/ “ሀሰት”.

1) ሀሰት
2) እውነት
3) ሀሰት
4) እውነት
5) እዉነት
ትዕዛዝ ሁለት : ምርጫ
1) ሐ
2) መ
3) ሐ
4) መ
5) መ

ትዕዛዝ ሦስት: ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡.

1) ከተማሪዎች የሚጠበቁ ቢያንስ አራት የግብረ ገብ ዕሴቶችን ዘርዝሩ፡፡


 ውድ መምህር ተማሪዎችን መፅሀፋቸውን አንብበውና ወላጆቻቸውን
ጠይቀው ተግባራትን እነዲሰሩ ያግዟቸው፡፡
2) መጥፎና ግልፍተኛ ባህሪን ማሳየት የለሌብን ለምንድን ነውʔ
 ማህበረሰቡ ጋር ያለው አዎንታዊ ዝምድና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ
ይፈጥራል፡፡
 የማህበረሰቡን ንብረትና ሃብት ያወድማል

እባክዎትን መምህር ስለ መልካም ባህሪይ አስፈላጊነት ይጥቀሱላቸው፡፡

3) መልካም ባህሪይ ያለው ሰው ለሰውና ሰውኛ ላልሆኑ ነገሮች ሁሉ ክብር


መስጠት ይጠበቅበታል፡፡

44 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ትዕዛዝ 4. እባክዎትን መምህር ቡድን መስርቱና ከታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሱትን
መረጃዎች መሰረት በማድረግ መልስ እንዲሰጡ አርጓቸው፡፡

ተ.ቁ መቼት ለራስ ክብር መስጠት ሌሎችን ማክበር ከባቢን ማክበር


1 መማሪያ ክፍል
2 ቤተ መፅሐፍት
3 የትምህርት ቤት ግቢ
4 ቤተሰብ
5 ጎረቤት
6 ማህበረሰብ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 45


ምዕራፍ አራት
በማህበራዊ- ኢኮኖሚያዊ ተግባራት መሳተፍ
መግቢያ
በዚህ ምዕራፍ ተማሪዎች ስለ ማህበራዊ ምጣኔ ምንነት ያውቃሉ፡፡ ተማሪዎች ስለማህበረሰብ ተሳትፎና
ስለ ጋራ ጥቅም ይማራሉ፡፡ይህም ስለ በጎ ፈቃድ ፅንሰ ሀሳብ ወይም ስለ ማበራዊ አገልግሎት ለተማሪዎች
ማሳወቅን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ እንዲሁም ተማሪዎች ትርፍ ጊዚያቸውን በማህበረሰብ ደረጃ እንዴት
ለጋራ ጥቅም እንደሚያውሉ ያነሳሳቸዋል፡፡ በተጨማሪም ይህ ምዕራፍ ስለ ታማኝ ግብር ከፋዮችና
ቁጠባ ምንነት እንዲሁም ለማበራዊ ምጣኔ ተግባራት ስለ ሚኖራቸው ሚና ትኩረት ይሰጣል፡፡

የምዕራፉ የመማር ውጤቶች: ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-


• ስለ ማህበራዊ- ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ምንነት ይገልፃሉ፡፡
• በበጎ ፈቃድ ተግባር ላይ መሳተፍ ላለው ጥቅም ዋጋ ይሰጣሉ፡፡
• ትርፍ ጊዜን ለጋራ ጥቅም የሚያውሉባቸውን መንገዶች ያሳያሉ፡፡
• ታማኝ የግብር ከፋዮችና የቁጠባ ባህል ለማህበራዊ ምጣኔ ተግባራት
ስለሚኖረው ሚና ይገልፃሉ፡፡

የተመደበ ሰዓት: 20 ክፍለ ጊዜ

ትምህርቶች:
• ክፍለ ትምህርት 1: የማህበራዊ ምጣኔ ተግባራት ዕሳቤ
• ክፍለ ትምህርት 2: በበጎ ፈቃድ ተግባራት መሳተፍ
• ክፍለ ትምህርት 3: ትርፍ ጊዜን ለጋራ ጥቅም ማዋል
• ክፍለ ትምህርት 4: ታማኝ ግብር ከፋዮችና ቁጠባ ለማህበራዊ
ምጣኔ የሚኖራቸው ሚና

4.1 ክፍለ ትምህርት 1: የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ዕሳቤ

4.1.1 የመማር ብቃት ፡ ተማሪዎች ይህን ክፍለ ጊዜ ከተማሩ በኋላ፡-


• የማህበራዊ ተግባራት ምንነትን ይረዳሉ፡፡
• የኢኮኖሚያዊ ተግባራት ምንነትን ይረዳሉ፡፡
• ማህበራዊ ኢኮኖሚ በግለሰብና በማህበረሰብ ዕድገት ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ይረዳሉ፡፡

4.1.2 ይዘቶች
የተመደበ ሰዓት: 5 ክፍለ ጊዜ

1) የማህበራዊ -ኢኮኖሚ ተግባራት ዕሳቤ

46 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


4.1.3 አጭር ገለፃ
ይህ ክፍለ ጊዜ በተማሪዎች ማህበራዊና ኢኮሚያዊ ህይወታቸው ላይ የራሱ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
የግለሰቦች ተሳትፎ ማህበራዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ ሊሆን ይችላል፡፡
ማህበራዊ ተሳትፎ ማለት የማህበረሰቡ አባላት በጋራ የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት የሚያደርጉት
ተግባር ነው፡
የማህበረሰቡን ችግር የመፍታቱ ተግባር እንደ ቡድን ወይም ማህበረሰብ በጋራ ሊከወን ይችላል፡፡
ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ገቢ፣ገንዘብ፣ሃብት ለማግኘት ወይም ሌላ የኢኮኖሚ ዓላማን ለማሳካት የሚከወን
ተግባር ነው፡፡
ገንዘብ ለማግኘት፣ለፍጆታ፣ ለቁጠባ፣ ለመዋዕለ ንዋይ ተግባር የሚከወን ማንኛውም ድርጊት ኢኮኖሚያዊ
ተሳትፎ ይባላል፡፡ የማህበራዊ ምጣኔ ተግባር በግለሰባዊ ህይወትና የወደፊት ዕድገት ላይ የማይናቅ ተፅዕኖ
አለው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ መምህሩ ስለ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ምንነት እንዲሁም ምሳሌወች በጥንቃቄና
በጥልቀት ማስተማር አለባቸው፡፡
4.1.4 የመማር ማስተማር ሂደት
ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች
· ምስሎች
· ፎቶዎች

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች


መምህሩ የሚከተሉትን ዘዴዎች በመጠቀም የዕለቱን ትምህርት ያብራራሉ፡፡
* የማነቃቂያ ጥያቄዎችን በመጠየቅ

* የዕለቱን ክፍለ ጊዜ ርዕስ በማስተዋወቅ

* ገለፃ በማድረግ
* የመማሪያ መፅሀፋቸው ላይ ያለ ተግባር በመስጠት
* መመሪያ በመስጠትና በቡድን እንዲወያዩ በማድረግ

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


መምህሩ የዕለቱን ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ከሚያሰተምሩት ትምህረት ጋር
ተያያዥነት ያላቸውን አጋዥ መፅሀፍት በማንበብ መዘጋጀት አለባቸው፡፡

የትምህርቱ አቀራረብ
1. የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ

መምህሩ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ምንነትና በግለሰቦች ህይወት ላይ ስለሚኖረው


ተፅዕኖ ሰፋ ባለ መንገድ ያስተዋውቃሉ፡፡ ትውውቁ የሚከተሉትን ነጥቦች ያካትታል፣
· በዚህ ክፍለ ጊዜ የሚጠበቀው አነስተኛ የማሰተማር ብቃት

· የክፍሉን ተማሪዎች ቁጥር መሰረት ያደረገ አምስት ወይም ስድስት የተማሪወች


ቡድን ያዋቅሩና የቡድኑ ሰብሳቢ የተማሪወችን የመጨረሻ ውጤት እንዲያቀርብ
ያድርጉ፡፡
የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 47
2. የትምህርቱ አካል: መምህሩ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ምንነትን ይገልፃሉ፡

የሚከተሉትን ፅንሰ ሀሳቦችም ያስተዋውቃሉ፡-
 የማህበራዊ ተግባር ምንነት
 የኢኮኖሚያዊ ተግባር ምንነት
3. ማጠቃለያ:

መምህሩ የዕለቱን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ዋና ዋና ነጥቦች በማንሳት ያጠቃልሉ


 የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ምንነት

 የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ውጤት

4.ግምገማና ክትትል
ሀ. ግምገማ
መምህሩ ተማሪወቹ የዕለቱን ትምህርት መረዳታቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ይህም የክፍል ውስጥ
ተግባር በመስጠት ሊከናወን ይችላል፡፡ መምህሩም ተማሪዎችን በቡድን በማዋቀር ስለ ማህበራዊ ምጣኔ
ተግባር ከአቻወቻቸው ጋር እንድወያዩ በማድርግ ያበረታታሉ፡፡ተማሪዎቹም የራሳቸውን ምሳሌ ያቀርባሉ፡፡
ለ. ክትትል
መምህሩ ስለ ዕለቱ ትምህርት ማጠቃለያ ቢሰጡ ጥሩ ነው፡፡ መምህሩ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ወይም
ቤታቸው ያከናወኗቸውን ተግባራት እንዲከታተሉ ይጠበቃል፡፡

5 ለተግባራቱ የተሰጡ መልሶች

ተግባር 4.1 ትዕዛዝ: ቤተሰቦቻችሁን ጠይቁና መልሶቻችሁን ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ ፡፡

ውድ መምህር, የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለተማሪዎቹ የቤት ስራ ይስጧቸው፡፡


1. ማህበራዊ ተግባር ምንድን ነው?
 በማህበረሰቡ አባላት የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት የሚከናወን
ማንኛውም ተግባር ነው፡፡ የተለያዩ የማህበራዊ ተግባራት አሉ፤
እባክዎ መምህር መፅሐፋቸው ላይ ከተቀመጡት መልሶች በተጨማሪ
የራስዎን ምሳሌዎች ይጥቀሱላቸው፡፡
2. ኢኮኖሚያዊ ተግባር ምንድን ነው?
ገቢ፣ ገንዘብ፣እንዲሁም ሀብት የምናገኝበት የተግባር አይነት ነው፡፡
3. የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ውጤት ምንድን ነው?
ውድ መምህር፡ ተማሪወቹ የተወሰኑትን የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ውጤቶች ከመፅሐፋቸው
እንዲጠቅሱ ያርጓቸው፡፡

48 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ተግባር 4.1 ትዕዛዝ: ቤተሰቦቻችሁን ጠይቁና መልሶቻችሁን ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ ፡፡

ውድ መምህር, የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለተማሪዎቹ የቤት ስራ ይስጧቸው፡፡


1. ማህበራዊ ተግባር ምንድን ነው?
 በማህበረሰቡ አባላት የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት የሚከናወን
ማንኛውም ተግባር ነው፡፡ የተለያዩ የማህበራዊ ተግባራት አሉ፤
እባክዎ መምህር መፅሐፋቸው ላይ ከተቀመጡት መልሶች በተጨማሪ
የራስዎን ምሳሌዎች ይጥቀሱላቸው፡፡
2. ኢኮኖሚያዊ ተግባር ምንድን ነው?
ገቢ፣ ገንዘብ፣እንዲሁም ሀብት የምናገኝበት የተግባር አይነት ነው፡፡
3. የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ውጤት ምንድን ነው?
ውድ መምህር፡ ተማሪወቹ የተወሰኑትን የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ውጤቶች
ከመፅሐፋቸው እንዲጠቅሱ ያርጓቸው፡፡

ተግባር 4.2 ትዕዛዝ: የሚከተሉትን ጥያቄዎች ወላጆቻችሁን ጠይቁና በመልሶቻችሁ ዙሪያ


ከጓደኞቻችሁ ጋር ተወያዩ፡፡

1)ቢያንስ አምስት የኢኮኖሚያዊ ተግባር ምሳሌዎችን ዘርዝሩ፡፡

ውድ መምህር, ተማሪወቹ የመማሪያ መፅሀፋቸው ላይ የተገለፁ የኢኮኖሚያዊ ተግባር ምሳሌወችን


እንዲያነቡ ያበረታቷቸው፡፡

2) ቢያንስ ስድስት የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ምሳሌዎችን ግለፁ፡፡

ዉድ መምህር፣ ተማሪዎችዎን የማህበራዊና የኢኮኖሚዊ ተግባራትን እንዲያስታረቁ


ያበረታቷቸውና ከማህበረሰባቸው አንፃር ይርዷቸው፡፡

ክፍለ ትምህርት 2: በበጎ ፈቃድ ተግባራት መሳተፍ


4. 2 ክፍለ ትምህርት 2: በበጎ ፈቃድ ተግባራት መሳተፍ
4.2.1 የመማር ብቃት ፡ተማሪዎች ይህን ክፍለ ጊዜ ከተማሩ በኋላ:-
• የማህበረሰብ ምንነትን ያውቃሉ
• የበጎ ፈቃድ ምንነትን ያውቃሉ
• በበጎፈቃድ ተግባር የመሳተፍ ጥቅምን ያውቃሉ
4.2.2 ይዘት
የተመደበ ሰዓት ፡ 4 ክፍለ ጊዜ

1) በበጎፈቃድ ተግባራት መሳተፍ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 49


4.2.3 አጭር ገለፃ
ይሄ ክፍለ ጊዜ ተማሪወች ሶስት ነገሮችን እንዲያቁ ያነሳሳቸዋል፡፡
1) የማህበረሰብ ምንነት
2) የማህበረሰብ ተግባር ምንነት
3) የበጎ ፈቃድ ማበራዊ ተሳትፎ ጥቅም
ማህበረሰብ ማለት የጋራ ማንነት ያላቸው የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ሰዎች በማህበረሰብ ውስጥ
የሚጋሯቸው የጋራ የሆነ ባህል ሃይማኖት ግዛት ቋንቋ እና ተመሳሳይ የሕይወት አመለካከት
አላቸው፡፡
በጎ ፈቃደኝነት ጊዜን ጉልበትን እውቀትን በፈቃደኝነት ለማህበረብ ጥቅም የማዋል ተግባር ነው፡፡ በተጨማሪም
ማህበረሰብ አገልግሎት ለማህበረሰቡ የጋራ ጥቅም በመስጠት የራሱ የሆነ አወንታዊ ጥቅም

አለው፡፡ መምህሩ፡ የማህበረሰብ ምንነት፣ የማህበረሰብ አገልግሎት እና የማህበረሰብ አገልግሎት


የሚኖረውን ጥቅም ያስተዋውቃሉ፡፡
4.2.4 የመማር ማስተማር ሂደት
ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዋች
· ምስሎች
· ፎቶዋች
ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዋች
መምህሩ፡ የሚከተሉትን መንገዶች በመጠቀም የዕለቱን ትምህርት ይገልፃሉ፡፡
• የማነቃቂያ ጥያቄዎችን መጠየቅ
• መግቢያ
• ገለፃ
• ውይይት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


¢ መምህሩ ክፍል ከመግባቱ በፊት አስፈላጊ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት
አለበት፡፡
¢ መምህሩ ክፍል ከመግባቱ በፊት መዘጋጀት አለበት፡፡ የመማሪያና ማስተማሪያ መፅሐፎችን
ማንበብ ግዴታ ነው፡፡

የትምህርቱ አቀራረብ
1. የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ:
መምህሩ ስለ ማህበረሰብ አገልግሎት እና የበጎ ፈቃድ ተግባር ጥቅም ግልፅ ሆነ መግቢያ
ያደርጋሉ፡፡

50 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


2. የትምህርቱ አካል
መምህሩ ስለ ማህበረሰብና የማህበረሰብ አገግሎት ምንነት ይገልፃሉ፡፡ ቀጥሎ መምህሩ /ሯ
የተማሪዎች የበጎ ፈቃድ ተግባር ለማህበረሰቡ የሚኖረውን ጥቅም ይገልፃሉ፡፡ ስለዚህ
መምህሩ ከተማሪዎቹ መማሪያ መፅሐፍ ላይ የተቀመጡትን የበጎ ፈቃድ ተግባራት
ምሳሌዎች በማብራራት በጥልቀት ያስተምራሉ፡፡

 የማህበረሰብ ምንነት

 የማህበረሰብ አገልግሎት ምንነት

 የማህበራዊ አገልገሎት ለማህበረሰብ የጋራ ጥቅም የሚኖረው ፋይዳ

 የማህበረሰብ አገልሎት ምሳሌዎች

3. ማጠቃለያ
መምህሩ የዕለቱን ትምህርት ዋና ዋና ነጥቦች በማንሳት ያጠቃሉ፡፡
 ማህበረሰብ
 ማህበራዊ አገልግሎት

 የማህበረሰብ አገልግሎት ጥቅም


 የማበራዊ አገልግሎት ምሳሌዎች

4. ግምገማና ክትትል

ሀ. ግምገማ
መምህሩ ተማሪዎቹ የዕለቱን ትምህርት መረዳታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡. ይህም የክፍል ስራ ወይም ፈተና
በመስጠት ሊከወን ይችላል፡፡ መምህሩ ተማሪዎችን በቡድን በማዋቀር ቀደም ብለው በተማሩት ጉዳዮች
ዙሪያ እንዲወያዩ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

ለ. ክትትል
· መምህሩ የዕለቱን ትምህርት ያጠቃልላሉ፡፡
· መምህሩ/ሯ ተማሪወች ክፍል ውስጥ ወይም ቤታቸው የሰሯቸውን ተግባራት መከታተል ይኖርባቸዋል፡፡

4.2.5 የተግባራት መልሶች

ተግባር 4.3 ትዕዛዝ : የሚከተሉትን ጥያቄዎች በቡድን ተወያዩ፡፡

1) ማህበራዊ ተሳትፎ ማለት ምን ማለት ነው?


 ማህበራዊ ተሳትፎ ማለት ማህበረሰቡን መሰረት ያደረገ በነፃ
ፈቃድና ምርጫ ማህበረሰብን ለመጥቀምና የጋራ ጥቅምን
ለማሳደግ ከትርፍና የግል ጥቅምን ከመፈለግ ነፃ በሆነ መንገድ
የሚከወን ተግባር ነው፡፡
2) ማህበራዊ አገልግሎት ማለት ምን ማለት ነው?
 ማህበራዊ አገልግሎት ማለት ያለ ምንም ግላዊ ጥቅም በህብረትም
ሆነ በግል ለሚኖሩበት አካባቢ ነፃ አገልግሎት መስጠት ነው፡፡
3) የበጎ ፈቃድ ተግባር ማለት ምን ማለት ነው?
 ውድ መምህር, በአካባቢያቸው የበጎ ፈቃድ ተግባር ምሳሌ የሚሆኑ
ነገሮችን በማንሳትና ከፅንሰ ሀሳቡ ጋር በማያዝ ያግዟቸው፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 51


ተግባር 4.4 ትዕዛዝ: የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከላይ የተቀመጠውን ምስል መሰረት በማድረግ መልሱ፡፡

ምስሉ 4.1 ላይ ተቀምጧል


1) ከላይ ከተቀመጠው ምስል ምን ተረዳችሁ?
 ከግራ ወደ ቀኝ የግለሰቦችን የተለመደ ማህበራዊ ተሳትፎ ያሣያል፡፡
2) ቢያንስ አራት የማህበራዊ አገልግሎቶችን ዘርዝሩ፡፡
 እገዛ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች መርዳት፡፡
 ችግኝ መትከል
 አካባቢን ንፁህ ማድረግ.
 እርሻ ስራ መስራት
ውድ መምህር እባክዎን ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎት ምሳሌዎችን
በራስዎ ወይም መፅሐፋቸው ላይ ከተቀመጡት ውስጥ ያብራሩላቸው፡፡

4.3 ክፍለ ትምህርት 3: ትርፍ ጊዜን ለጋራ ጥቅም ማዋል


4.3.1 የመማር ብቃት
• የትርፍ ጊዜ ምንነትን ይረዳሉ፡፡
• ትርፍ ጊዜን ለጋራ ጥቅም የማዋያ መንገዶችን ያሳያሉ፡፡
• የጋራ ጥቅምንና ትርፍ ጊዜን ያጣጥማሉ፡፡

4.3.2 ይዘት

የተመደበ ሰዓት ፡ 4 ክፍለ ጊዜ

1) ትርፍ ጊዜን ለጋራ ጥቅም መጠቀም

4.3.3 አጭር ገለፃ


ይህ ክፍለ ጊዜ የትርፍ ጊዜና የጋራ ጥቅም ፅንሰ ሀሳብን ይይዛል፡፡ በተጨማሪም ተማሪወች ትርፍ ጊዜን
ለጋራ ጥቅም እንዲያውሉ ግንዛቤ ይፈጥርላቸዋል፡፡ ትርፍ ጊዜ ከመደበኛው ስራ፣ ሀላፊነት፣ ሙያና ጉዳይ
ነፃ የሆነ ነው፡፡ መምህሩ የትርፍ ጊዜን ፅንሰ ሀሳብና እሳቤ እንዲሁም ተማሪዎች ትርፍ ጊዚያቸውን ለጋራ
ጥቅም የሚያውሉባቸውን መንገዶች እንዲለዩ የማድረግና የማስተዋወቅ ስራ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4.3.4 የመማር ማስተማር ሂደት

ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ


· ምስሎች
· ፎቶዎች
52 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል
ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች
መምህሩ የሚከተሉትን የማስተማሪያ ዘዴዎች መጠቀም ይችላሉ፡፡
· የማነቃቂያ ጥያቄዎች መጠየቅ

· የዕለቱን የትምህርት ርዕስ ማስተዋወቅ

· ገለፃ ማድረግ

· ተማሪዎችን በቡድን እንዲወያዩ በማመቻቸት


ከመፅሀፋቸው የውይይት ተግባር መስጠት፡፡

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


• መምህሩ ተገቢ የሆኑ የማስተማሪያ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት አለባቸው፡፡
• መምህሩ ክፍል ከመግባታቸው በፊት የመምህሩንና የተማሪውን መፅሀፍ በማንበብ በደንብ
መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡

የትምህርቱ አቀራረብ
1. የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ:
መምህሩ ስለ ትርፍ ጊዜ ምንነትና ለጋራ ጥቅም ያለውን ፋይዳ በሰፊው ያስተዋውቃሉ፡፡
መምህሩ/ሯ ትርፍ ጊዜን ለመዝናናት ብቻ ሳይሆን ለጋራ ጥቅም እንዴት እንደሚያውሉ
ያሳውቋቸዋል፡፡ መምህሩ የሚከተሉትን ነጥቦች ማስተዋወቅ ይኖርበታል፡-
 የዕለቱን ትምህርት የመማር ብቃት
 ከተማሪዋቹ የመማሪያ መፅሀፍ የማነቃቂያ ጥያቄዎችን መስጠት
 የዕለቱን ትምህርት በዋና ርዕስና በንዑስ ርዕስ መልክ ማሰተዋወቅ

2. የትምህርቱ አካል
 መምህሩ የትርፍ ጊዜን ምንነት ይገልፃሉ፡፡ከዛ ለማህበረሰቡ የጋራ ጥቅም ያለውን
ፋይዳ ያብራራሉ፡፡ መምህሩ ተማሪዎች በትርፍ ጊዚያቸው ሊያከናውኗቸው
የሚችሉ የማህበረሰብ የጋራ ጥቅሞችን እንዲያብራሩ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በመቀጠልም ስለ ትርፍ ጊዜ አጠቃላይ ጥቅም እንዲገልፁ ያበረታቷቸዋል፡፡

መምህሩ የሚከተሉትን ነጥቦች ማስተማር ይኖርባቸዋል፡-


– የትርፍ ጊዜ ምንነት
– ትረፍ ጊዜ ለጋራ ጥቅም
– አይነተኛ የጋራ ጥቅም ምሳሌዎች
– ትርፍ ጊዜ ለተማሪዎች ያለው ጥቅም

3. ማጠቃለያ

መምህሩ የዕለቱን ትምህር ዋና ዋና ፅንሰ ሀሳቦች በማንሳት ያጠቃልሉ፡፡


 ትርፍ ጊዜ.
 የትርፍ ጊዜና የጋራ ጥቅም ዝምድና

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 53


4. ግምገማና ክትትል:
ሀ. ግምገማ
መምህሩ ለተማሪዎች የክፍል ተግባር በመስጠት ትምህርቱን መረዳታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ እንዲሁም
ተማሪዎችን በቡድን በማዋቀር ከጓደኞቻቸው ጋር ስለ ትርፍ ጊዜና ስለሚያስገኛቸው ውጤቶች በምሳሌ
እንዲወያዩ ማበረታታት ይኖርባቸዋል፡፡
ለ. ክትትል
መምህሩ የዕለቱን ትምህርት እንዲያጠቃልሉና ተማሪዎች ክፍል ውስጥ እንድሁም ቤታቸው ያከናወኗቸውን
ተግባራት እንዲከታተሉ ይጠበቃል፡፡

4.3.5 የተግባራት መልሶች

ተግባር 4.5 ትዕዛዝ: የሚከተሉትን ጥያቄዎች በጥንድና በቡድን ተወያዩ፡፡

1) ትርፍ ጊዜ ማለት ምን ማለት ነው?

 ትርፍ ጊዜ ማለት ከመደበኛው ሙያ ስራና ሌሎች ግዴታዎችን


ከምናከናውንበት ሰዓት ውጭ ያለ ጊዜ ነው፡፡

2) የጋራ ጥቅም ምንድን ነው?

 የጋራ ጥቅም ማለት ለሁሉም የማህበረሰቡ አባላት የጋራ የሆነ


ፍላጎት ወይም መገልገያ መሳሪያ ነው፡፡.

3) ትርፍ ጊዜን እንዴት ነው ለጋራ ጥቅም የምታውሉት?

ውድ መምህር, እባክዎን ተማሪዎችዎን ትርፍ ጊዚያቸውን ለመዝናናትና


ለጋራ ጥቅም እንዲያውሉት ምክር በመስጠት ያበረታቷቸው፡፡

ተግባር 4.6 ትዕዛዝ: ከላይ በተሰጠው ምሳሌ መሰረት የሚከተሉትን ጥያቄዎች


መልሱ፡፡

1) የባለፈው ረፍታችሁን ወይም ክረምት የት አሳለፋችሁ?

ውድ መምህር ተማሪዎችዎን የባለፈው ረፍታቸውን ወይም


ክረምት የት እንዲያሳለፉ ይጠይቋቸው እንድሁም ክፍል ውስጥ
እንዲወያዩበት ያነሳሷቸው፡፡
2) የትርፍ ጊዜ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?

ውድ መምህር ተማሪዎች ስለ ትርፍ ጊዜ ምንነት እንዲገነዘቡና


በጉዳዩም ዙሪያ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያበረታቷቸው፡፡

54 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


4.4 ክፍለ ትምህርት 4: የታማኝ ግብር ከፋዮችና ቁጠባ ለማህበራዊ-ኢኮኖሚ ያለው ሚና

4.4.1 የመማር ብቃት፡ ከዚህ የክፍለ ጊዜ ትምህርት በኋላ, ተማሪወች፡-
• የንግድና የገበያ ምንነትን ይረዳሉ፡፡.

• ግብር መክፈልና ቁጠባ ምን እንደሆኑ ያውቃሉ፡፡.

• ግብር መክፈልና የቁጠባ ባህል ለማህበራዊ ምጣኔ ያላቸውን ሚና በራሳቸው ይለማመዳሉ፡፡

4.4.2 ይዘት

የታማኝ ግብር ከፋዮችና ቁጠባ ለማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ያላቸው ሚና፡፡

4.4.3 አጭር ገለፃ


ይህ ርዕስ የሚያጠነጥነው የንግድ፣የገበያ፣የግብር መክፈልና የቁጠባ ፅንሰ ሀሳብ ምንነትን በማስተዋወቅ
ይሆናል፡፡ ግብር መክፈልና ቁጠባ ለማህበራዊ ምጣኔ ተግባር ያላቸው ሚና ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡
በመጨረሻም ግብር መክፈልና ቁጠባ ለማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ለሚሰጠው ጥቅም ላይ ትኩረት
ይሰጣል፡፡ታማኝ ግብር ከፋዮችና የህዝቦች የቁጠባ ባህል ለሃገሪቱ ማህበራዊ ምጣኔ ተግባር ከፍተኛ አሰተዋፆ
አላቸው፡፡ ግብር በወቅቱ ካልተከፈለ ለሃገር እድገት መሰናክል ይሆናል፡፡ ቁጠባ ሰዎች በህይወታቸው በጣም
አስፈላጊ ዓላማዎቻቸውን ለማሳካት ይጠቅማቸዋል፡፡ ስለዚህ መምህሩ በዚህ የክፍለ ጊዜ ትምህርት የተማሪው
መፅሐፍ ላይ ለተቀመጡት ለእያንዳንዳቸው ፅንሰ ሀሳቦች ጥልቅ የሆነ ትኩረት መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.4.4 የመማር ማስተማር ሂደት


ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ

Ô ምስሎች Ôፎቶዎች

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 55


ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች
መምህሩ የሚከተሉትን ዘዴዎች በመጠቀም የዕለቱን የትምህርት ክፍለ ጊዜ መግለፅ ይችላሉ፡፡
· የማነቃቂያ ጥቄዎች በመጠየቅ
· የዕለቱን ትምህርት በማሰተዋወቅ
· ገለፃ በማድረግ
· ተማሪዎቹን መፅሀፋቸው ላይ ያለ ተግባር እንዲሰሩ በማድረግና
በቡድን እንዲዎያዩ በማመቻቸት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


• መምህሩ ተገቢ የሆኑ የማስተማሪያ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት አለበት፡፡
• መምህሩ ክፍል ከመግባቱ በፊት የተማሪዎችን እንዲሁም የመምህሩን መምሪያ የማንበብ ግዴታ
አለበት፡፡

የትምህርቱ አቀራረብ
1.ትምህርቱን ማስተዋወቅ

መምህሩ የንግድና የገበያን ምንነት አጠር አርጎ ያስተዋውቃሉ፡፡መምህሩ ግብር መክፈልና ቁጠባ
በማህበረሰቡ የኢኮኖሚያዊ ህይወት ላይ ባለው ሚና ትኩረት ማድረግ አለበት፡፡ ከዚህ ይዘት በኋላ መምህሩ
ለመንግስት ግብር መክፈል ያለው ጥቅምና ቁጠባ በማህበረሰቡ ማህበራዊ ምጣኔ ተግባር ላይ በሚኖረው
ጥቅም አጠር ያለ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
2. የትምህርቱ አካል
መምህሩ የንግድና የገበያ ምንነትን ይገልፃሉ፡፡ ከዛ ቀጥለው የግብር መክፈልና የቁጠባ ምንነትን ያብራራሉ፡
፡.ለመንግስት ግብር መክፈል ያለው ጥቅምና ቁጠባ በማህበረሰቡ ማህበራዊ ምጣኔ ተግባር ላይ በሚኖረ ው
ጥቅም ገለፃ ያደርጋሉ፡፡
 ከዚህ ትምህርት መጨረሻ መምህሩ ስለ ግብር መክፈልና ቁጠባ ለማህበረሰቡ ስላለው ፋይዳ
ከተማሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡

መምህሩ የሚከተሉትን ነጥቦች ያስተምራሉ


– የንግድ ምንነት
– የገበያ ምንነት
– ግብር መክፈል ለሀገር እድገት ያለው ሚና

– ቁጠባ ለማህበራዊ ምጣኔ ተግባር ያለው ሚና

3. ማጠቃለያ
በሚከተሉት የትምህርቱ መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች መሰረት ያጠቃሉ፡-

 ገበያ
 ግብር
 ቁጠባ
 ንግድ

56 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


4. ግምገማና ክትትል
ሀ. ግምገማ
 መምህሩ ለተማሪዎች የክፍል ስራ በመስጠት የዕለቱን ትምህርት መረዳታቸውን
ያረጋግጣሉ፡፡ መምህሩ ተማሪዎቹን በቡድን በማዋቀር ስለ ግብርና ቁጠባ ጥቅም
ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያበረታታሉ፡፡

ለ. ክትትል
• መምህሩ የዕለቱን ትምህርት ቢያጠቃሉ መልካም ነው፡፡ መምህሩ ተማሪዎች
ቤታቸውም ሆነ ክፍል ውስጥ ያከናወኗቸውን ተግባራት ይከታተሉ፡፡

ተግባር 4.7 ትዕዛዝ: ተማሪዎችን በቡድን በማድረግ የሚከትሉትን ጥያቄዎች ያወያዩ፡፡


ካስቀመጡት የትምህርቱ ዓላማና ከዕለቱ ትምህርት ተግባር አንፃር ሊሄድ የሚችል ተማሪ ተኮር
የማስተማር ዘዴ ይጠቀሙ

1) ንግድ ማለት ምን ማለት ነው?


 ንግድ ማለት በህዝቦችና በሀገራት መካከል ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን የመሸጥ፣ የመግዛትና
የመለወጥ ተግባር ነው፡፡
2) ገበያ ማለት ምን ማለት ነው?
 ገበያ ማለት ዕቃዎች የሚገዙበትና የሚሸጡበት ቦታ ማለት ነው፡፡

ተግባር4.8 ትዕዛዝ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ወላጆቻችሁን ጠይቁና ከጓደኞቻችሁ ጋር ተወያዩ፡-

1) ግብር ማለት ምን ማለት ነው?


 ግብር ማለት ግለሰቦችና ድርጅቶች ከሚያገኙት ገቢ ላይ ለመንግስት ሚከፍሉት ክፍያ
ነው፡፡ማንኛውም ሰው ከሚያገኘው ገቢ ላይ ግብር የመክፈል ህጋዊ ግዴታ አለበት፡፡
2) ሰዎች ለምን ግብር ይከፍላሉ?
 ግብር የመክፈል ዓላማ የመንግስትን ገቢ ለማሳደግ ነው፡፡ ያለ ግብር ክፍያ የጋራ ጥቅምን
ማለትም የትምህርት ፣የጤና ፣ የመከላከያ አገልግሎትን ማግኘት አይቻልም፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 57


ተግባር 4.9 ትዕዛዝ: ከትምህርቱ አላማና ከዕለቱ ትምህርት ተግባር ጋር
ሊሄድ የሚችል አሳታፊ የማስተማር ዘዴ ይጠቀሙ፡፡

1) ቁጠባ ማለት ምን ማለት ነው?


 ቁጠባ ማለት ያለንን ነገር ለፍጆታ ከመጠቀም ይልቅ ለወደፊት ማስቀመጥ
ነው፡፡ይህ ማለት በህይወታችሁ የምታገኙትን ገንዘብም ሆነ ጊዜ ሙሉ
በሙሉ ለፍጆታ ወጭ ከማድረግ ይልቅ ለወደፊት ማስቀመጥ ነው፡

2) በአካባቢያችሁ ማህበረሰብ የሚገኙ የቁጠባ ተቋማትን መዘርዘር ትችላላችሁን
ውድ መምህር እባክዎን ተማሪዎችን በቡድን ያዋቅሯቸውና ስለ ቁጠባ ተቋማት
እንዲወያዩ ያበረታቷቸው፡፡
3) በህይወታችሁ ከቁጠባ የምጠብቁት ውጤት ምንድን ነው?
ውድ መምህር ተማሪዎች የቁጠባን ጥቅም እንድረዱ መወያየት አስፈላጊ
እንደሆነ ይታመናል ስለዚህ እባክዎን ተማሪዎቹን ያግዟቸው፡፡

4.5 የምዕራፉ ጥያቄ መልሶች

ትዕዛዝ አንድ: አረፍተ ነገሩ ትክክል ከሆነ “እውነት” ትክክል ካልሆነ “ሀሰት” ብላችሁ መልሱ፡

1) ማህበራዊ ተግባራት በኢኮኖሚያዊ ህ ይወታችን ላይ ምንም ዓይነት ሚና የላቸውም፡፡
ሀሰት
2) ባንኮችና መድህን ድርጅቶች ዘመናዊ የቁጠባ ተቋማት ናቸው፡፡እውነት
3) ግብር መክፈል በሃገር እድገት ላይ ምንም ዓይነት አስተዋፆ የለውም፡፡ሀሰት
4) የትርፍ ጊዜ ሰዓት አንድ ሰው ከመደበኛ ስራው ውጭ ያለውን ትርፍ ጊዜ ያመላክታል፡
፡እውነት

5) ቁጠባ ማንም ሰው በህይወቱ ተግባራዊ ሊያደርገው የሚገባ ጠቃሚ ነገር ነው ፡፡እውነት


፡እውነት
ትዕዛዝ ሁለት: ምርጫ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ምረጡ፡፡
1) መ
2) መ
3) ሀ
4) መ

58 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ትዕዛዝ ሶስት: አጭር መልስ ስጥ: ውድ መምህር የሚከተሉት ካጠቃላይ
ምዕራፉ የወጡ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

1) ቢያንስ አስር የማህበራዊ ተግባራትን ዘርዝሩ፡፡


2) ቢያንስ አስር የኢኮኖሚያዊ ተግባራትን ጥቀሱ፡፡
3) በቡድን በመሆን ቁጠባ ለማህበራዊ- ኢኮኖሚያዊ ያለውን ጥቅም ተወያዩ፡፡
4) ትርፍ ጊዜ ለናንተና ለማህበረሰቡ ከሚሰጠው ጥቅም ውስጥ ቢያንስ
አምስቱን ጥቀሱ፡፡
5) በኢትዮጵያ ከሚገኙ ባንኮች ውስጥ ቢያንስ አምስቱን ጥቀሱ፡፡
6) በኢትዮጵያ ከሚገኙ መድህን ድርጅቶች ውስጥ የተወሰኑትን ልትጠቅሱ
ትችላላችሁን? ውድ መምህር በትምህርት ቤቱ አጠገብ የሚገኙ የባንክ ወይም ያገር
ውስጥ ገቢዎች ባለሙያ ጋብዘው ለተማሪዎች ሙያዊ ንግግር እንዲያረጉ ጋብዙላቸው፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 59


ምዕራፍ አምስት
የሀገር ፍቅር
መግቢያ
የሀገር ፍቅር ማለት አንድ ሰው ለሀገሩ ያለው ጥልቅ የሆነ ፍቅርና ስሜት ነው፡፡ የሀገር ፍቅር
ለማንኛውም የሀገር ደህንነትና ግንባታ መሰረታዊ ነገር ነው፡፡. ይህ ምዕራፍ ስለ ትምህርቱ በሰፊው
ያብራራል፡፡ ምዕራፉ ስለ ሀገር ፍቅር ምንነት በመግለፅ ይጀምራል፡፡ በመቀጠል ቀጣይ ሁለቱ ርዕሶች
ስለ ሀገር ፍቅር መገለጫዎችና ስለ ሀገር ፍቅር ጥቅም በቅደም ተከተል ያብራራሉ፡፡ ይህ ውይይት
ተገቢነት ባላቸው ምስሎችና ትረካዎች ይደገፋል፡፡ በመጨረሻም ሀገርን መውደድ ምን ማለት ነው
የሚል ውይይት ይኖራል፡፡

የምዕራፉ የመማር ውጤቶች: ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ከተማሩ በኃላ:-


• የሀገር ፍቅርን ይላበሳሉ
• የሀገር ፍቅር መገለጫወችንና ጥቅሞቹን ይገነዘባሉ
• በሀገራቸው የመኩራት ጥቅምን ይረዳሉ
• የሀገር ፍቅር መገለጫ መንገዶችን ያሳያሉ

የተመደበ ሰዓት : 19 ክፍለ ጊዜ

ትምህርቶች
• ክፍለ ትምህርት 1: የሀገር ፍቅር ምንነት
• ክፍለ ትምህርት 2: የሀገር ፍቅር መገለጫዎች
• ክፍለ ትምህርት 3: ሀገርን የመውደድ ጥቅም
• ክፍለ ትምህርት 4: የሀገር ወዳድ ግለሰብ መለያ
• ክፍለ ትምህርት5: ሀገርን መውደድ

5.1 ክፍለ ትምህርት 1: የሀገር ፍቅር ምንነት


5.1.1 የመማር ብቃት ፡ተማሪዎች ይህን ክፍለ ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
የሀገር ፍቅርን ትርጉም ይገልፃሉ

5.1.2 ይዘት

የተመደበ ክፍለ ጊዜ: 3 ክፍለ ጊዜ

1) የሀገር ፍቅር ምንነት

60 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


5.1.3 አጭር ገለፃ
ሀገር ወዳድ መሆን ምን ማለት ነው? መገለጫዎቹ ምንድን ናቸው? ይህ ክፍለ ትምህርት የሀገር ፍቅር
ምንነትን በመግለፅ ይጀምርና የሀገር ፍቅር ማሳያ መንገዶችን በሀገር ወዳድ ዜጎች ትረካዎች ጋር ተያይዞ
ይቀርባል፡፡
5.1.4 የመማር ማስተማር ሂደት
ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች
¢ ምስሎች
¢ የድምፅና
¢ የምስል መሳሪያዎች

ተመራጭ የማስተማሪያ መሳሪያዎች


• ማነቃቂያ
• ትምህርቱን
• ማስተዋወቅ
• ገለፃ
• ጥያቄ መጠየቅ
• የቡድን ውይይት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


¢ ተገቢ የሆነ መርጃ መሳሪያ ማዘጋጀት
¢ የዕለቱን የትምህርት ዋና ዋና ጉዳዮችን ማስተዋወቅና ተማሪዎች በጉዳዩ ላይ የራሳቸውን
ሃሳብ እንዲሰጡ ማበረታታት

የትምህርቱ አቀራረብ
1. ትምህርቱን ማስተዋወቅ
የሀገር ፍቅር ምንነት ላይ ትኩረት በማድረግ አጠር ያለ መግቢያ ለተማሪዎች ማቅረብ

 የዕለቱን የጥምህርት ዓላማ ለተማሪዎች ያሳውቁ

 ተማሪዎቹ ስለ ትምህርቱ ያላቸውን አረዳድ ለመገመት ሀሳባቸውን እንዲገልፁ


ያበረታቷቸው፡፡ ሀሳባቸውን ሊያነሳሳ የሚችል ጥያቄ ይጠይቋቸው ጥያቄው በዚህ
መልኩ ሊቀርብ ይችላል፡-( ኢትዮጵያዊ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ግለፁ)

2. የትምህርቱ አካል
 የሀገር ፍቅር ምንነትና ተግባራዊ የማድረጊያ መንገዶችን ምሳሌ በማቅረብ
ውይይቱን ይጀምሩ፡፡
 የሀገር ፍቅርን ለመረዳትና ለመለማመድ አስፈላጊ ነጥቦችን ግለፁ፡፡

3. ማጠቃለያ: የትምህርቱን ዋና ዋና ፅንሰ ሀሳቦች በማንሳት ያጠቃሉ፡፡


የሀገር ፍቅር ትርጉም

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 61


1. ግምገማና ክትትል
ሀ) ግምገማ
 የክፍል ስራ፣ አጭር ፈተና በመስጠት ወይም ስለ ሀገር ፍቅር
ምንነትና የመለማመመጃ መንገዶች ዙሪያ በቡድን እንዲወያዩና
የራሳቸውን አይነተኛ ምሳሌ እንዲሰጡ በማድረግ ተማሪዎች ትምህርቱን
መረዳታቸውን ያረጋግጡ፡፡

ለ) ክትትል
• የሀገርፍቅር ምንነት ፅንሰ ሀሳብ በማጠቃለልና ተማሪዎች እርስ በርስ እንዲወያዩ
በማድረግ ትምህርቱን ማጠቃለል ይችላል፡፡

--ተማሪዎቹ ትምህርቱን የበለጠ እንዲረዱት ለማገዝ የሚሰሩት የተወሰነ ተግባር ይስጧቸውና እያንዳንዱ
ቡድን በሀገር ፍቅር ምንነት ውይይት ላይ መሳተፋቸውን ያረጋግጡ፡፡
–ተማሪዎች ስለ ሀገር ፍቅር ያላቸውን አመለካከት ይገምግሙ፡፡

5.1.5 የተግባራት መልስ

ተግባር 5.1 ትዕዛዝ: ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ሊሆን የሚችል ነገር


አሰላስሉና ከጓደኞቻችሁ ጋር ተወያዩ፡፡

1) የሀገር ፍቅር ምንነትን ለጓደኛችሁ ግለፁ፡፡


የሚከተሉት ለሀገር ፍቅር የተሰጡ ትርጉሞች ናቸው፡-
 የሀገር ፍቅር ማለት አንድ ሰው ለሀገሩ ያለው ጥልቅ ፍቅር ማለት ነው፡፡
 የሀገር ፍቅር አንድ ሰው ለሀገሩ ዜጋ ያለው ፍቅር ማለት ነው፡፡
2)የሀገር ፍቅር መገለጫዎች ውስጥ የተወሰነ ምሳሌ መስጠት ትችላላችሁን?
• የሀገር ሰንደቅ ዓላማን ማክበር
• የሀገር ሉዓላዊነት ማስጠበቅ
• የሀገር ጀግኖችን ማክበር

5.2 ክፍለ ትምህርት 2: የሀገር ፍቅር መገለጫዎች


5.2.1 የመማር ብቃት ፡ ተማሪዎች ይህን ክፍለ ጊዜ ከተማሩ በኋላ፡-
• የሀገር ፍቅር መገለጫዎችን ይዘረዝራሉ፡፡
• በአካባቢያቸው የሀገር ፍቅር ምሳሌዎችን ያቀርባሉ፡፡

5.2.2 ይዘት

የተመደበ ሰዓት:5 ክፍለ

1) የሀገር ፍቅር መገለጫ

62 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


5.2.3 አጭር ገለፃ
ይህ ክፍለ ጊዜ ትኩረት የሚያደርገው የሀገር ፍቅር ምንነትን በመወያየት በሀገር ፍቅር ስሜት
መገለጫዎችና የሀገር ወዳድ ዜጋ በሚያሳያቸው ባህሪያት ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡
5.2.4 የመማር ማስተማር ሂደት
ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪዎች
Ô ምስሎች
Ô ፎቶዎች

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች


• ማነቃቂያ
• ትምህርቱን
• ማስተዋወቅ
• ጥያቄና መልስ
• የቡድን ውይይት

ቅድመ የክፍለ ጊዜ ዝግጅት


¢ አስፈላጊ የሆኑ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት
¢ ተማሪዎች ስለሚማሩት ፅንሰ ሀሳብ ያላቸውን ቅድመ ግንዛቤ እንዲገልፁ ጊዜ መስጠት

የትምህርቱ አቀራረብ
1. የዕለቱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ መግቢያ
መምህሩ የሀገር ፍቅር መገለጫዎችን በማብራራት ትምህርቱን መጀመር ይችላሉ፡፡
• የዕለቱን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ዓላማ ለተማሪዎች ማሳወቅ

• የሀገር ፍቅር መገለጫዎችን እንዲያነቡና ሀሳባቸውን እንዲገልፁ ለተማሪዎች በቂ ጊዜ


መስጠት

• የተማሪዎችን ሀሳብ ሊያነሳሳ የሚችል ጥያቄ መጠየቅ

ጥያቄዎቹም በሚከተለው መልኩ ሊሆን ይችላሉ


– ኢትዮጵያዊነት እንዴት ይገለጻል?

2.የትምህርቱ አካል

• መምህሩ የሀገር ወዳድ ዜጋ መገለጫዎችን በማብራራት ትምህርቱን መጀመር ይችላል፡፡.ተማሪዎች


በቀላል መንገድ ትምህርቱን ይረዱት ዘንድ እያንዳንዱን የሀገር ወዳድ መገለጫ ባህሪ በምሳሌ
ያስደግፉላቸው፡፡
• ስለ ተረዱት ነገር ከጓደኞቻቸው ጋር እንድወያዩ ይፍቀዱላቸው፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 63


2. ማጠቃለያ: የዕለቱን ትምህርት ዋና ዋና ነጥቦች በማንሳት ያጠቃሉ፡፡
የሀገር ፍቅር መገለጫዎች
3. ግምገማና ክትትል:
ሀ. ግምገማ
 ተማሪዎች የክፍል ስራ፣ አጭር ፈተና በመስጠት ወይም ስለ ሀገር
ፍቅር መገለጫ በቡድን እንዲወያዩ በማድረግ የዕለቱን ትምህርት
መረዳታቸውን ያረጋግጡ፡፡

ለ. ክትትል

• ስለ ሀገር ፍቅር መገለጫዎች አጠር ያለ ውይይት በማድረግ የዕለቱን ትምህርት ያጠቃሉ፡፡


ተማሪዎቹም በራሳቸው መንገድ እንዲወያዩብት ያድርጓቸው፡፡

–ተማሪዎቹ የተማሩትን ትምህርት የተሻለ እንዲረዱት የቡድን ስራ መስጠትና ሁሉም የቡድኑ


አባላት እንዲሳተፉ ያድርጉ፡፡
–ተማሪዎች ስለ ሀገር ፍቅር መገለጫዎች ያላቸውን አረዳድ ይገምግሙ፡፡

5.2.5 የተግባራት መልሶች

1) የተወሰኑትን የሀገር ወዳድ ዜጋ መገለጫዎች ግለፁ፡፡ ለምሳሌ፡-


 በሀገር መኩራት
 የሀገር የኔነት ስሜት መሰማት
 ራስን ለሀገር መስዋዕት ለማድረግ ዝግጁ መሆን
 ሙስናን መዋጋት
 የሀገር ጀግኖችን ማክበር
2) በዜጎች የሚከወኑ የሀገር ፍቅር ማሳያ ምሳሌዎችን ተጠቀሙ፡፡
ለምሳሌ፡-
 የሀገርን ጥቅም ከግል ጥቅም ማስቀደም
 ለህበረተሰብ እድገት እንቅፋት የሆነውን ሙስናን ለመዋጋት ዝግጁ
መሆን፤
 በማንኛውም የሀገሪቱ ውጤት መኩራት፤

5.3 ክፍለ ትምህርት 3: ሀገር ወዳድ የመሆን ጥቅም


5.3.1 የመማር ብቃት ፡ ተማሪዎች ይህን ክፍለ ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡
• ሀገር ወዳድ የመሆን ጥቅምን ይገነዘባሉ.
• ሀገርን የመውደድ ጥቅሞች ውስጥ የተወሰኑ ምሳሌዎችን ይጠቅሳሉ

64 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


5.3.2 ይዘት

የተመደበ ሰዓት: 5 ክፍለ ጊዜ

1) የሀገር ወዳድነት ጥቅም

5.3.3 አጭር ገለፃ


በዚህ ክፍል ትኩረቱ የሀገር ወዳድነት ጥቅሞች ላይ ይሆናል፡፡ ይህ ጥቅም ከሀገርና ከዜጋ አንፃር ይታያል፡፡
በተጨማሪም የሀገር ፍቅር በስልጣን እርከን ላይ ላሉት ሰዎች ለሚኖረው ጥቅም ውይይት ይደረጋል፡፡

5.3.4 የመማር ማስተማር ሂደት


ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ

Ô ምስሎች
Ô ፎቶዎች

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች


• ማነቃቂያ
• ትምህርቱን ማስተዋወቅ
• ጥያቄና መልስ
• የቡድን ውይይት

ማብራሪያ

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


¢ አስፈላጊ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት
¢ ተማሪዎች ስለ ፅንሰ ሃሳቡ ያላቸውን ቅድመ ግንዛቤ እንዲገልፁ ጊዜ መስጠት

የትምህርቱ አቀራረብ
1. ትምህርቱን ማስተዋወቅ
መምህሩ ተማሪዎቹ የሀገር ወዳድነትን ጥቅሞች አጉልተው እንዲገልፁ በማበረታታት
ትምህርቱን መጀመር ይችላሉ፡፡.
 ለተማሪዎች የዕለቱን የትምህርት ዓላማ ያሳውቋቸው፡፡

 ተማሪዎች ስለ ሀገር ፍቅር ጥቅም እንዲያነቡና እንዲገልፁ ይፍቀዱላቸው፡፡

 የተማሪዎችን ሀሳብ ሊያነሳሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን ያንሱላቸው፡፡ጥያቄው


በሚከተለው መልኩ ሊሆን ይችላል

– የሀገር ፍቅር ለግለሰቦች የሚኖሩት ጠቀሜታዎች ምንድን ናቸው?

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 65


2. የትምህርቱ አካል

 ለዚህ ትምህርት የተማሪዎችን ስለ ሀገር ፍቅር ጠቀሜታ ያላቸውን ግንዛቤ


ግምት ውስጥ በማስገባት ቢጀምሩ የተሻለ ነው፡፡በመቀጠል መምህሩ ሀገርን
መውደድ ለግለሰብና ለማህበረሰብ ያለውን ፋይዳ ወደ መወያት ያመራሉ፡፡

3. ማጠቃለያ: የትምህርቱን ዋና ዋና ፅንሰ ሀሳብ በማንሳት ያጠቃሉ፡፡


 ሀገርን የመውደድ ጥቅም

4. ግምገማና ክትትል
ሀ. ግምገማ
መምህሩ ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርት እንደተረዱት ለማወቅ አጭር ፈተና፣ የክፍል ስራ ወይም በሀገር
ፍቅር ጥቅም ላይ በቡድን ሆነው እንዲወያዩ በማድረግ ማጠቃለል ይችላሉ፡፡

ለ. ክትትል
• የሀገር ወዳድነትን ጥቅም አጠር አድርገው በማወያትና ተማሪወች እርስ በርሳቸው ሀሳብ
እንዲለዋወጡ በማድረግ ያጠቃሉ

–ተማሪዎች ትምህርቱን እንደተረዱት እርግጠኛ ለመሆን መምህሩ የቡድን


ስራ በመስጠት እያንዳንዱ ተማሪ በውይይቱ መሳተፉን ያረጋግጡ፡፡
–ተማሪዎች የሀገር ፍቅር ጥቅም ላይ ያላቸውን አመለካከት ይገምግሙ

5.3.5 የተግባራት መልሶች


ተግባር 5.3 ትዕዛዝ: የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሶቻችሁን አሰላስሉና
ከጓደኞቻችሁ ጋር ተወያዩባቸው፡፡

1) ሀገር ወዳድ መሆን ለአንድ ዜጋ ያለውን ጥቅም ግለፁ፡፡


ለምሳሌ፡-
 ዜጎች አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ያስችላቸዋል፡፡
 ቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ሀገር እንዲረከብ ያደርጋል፡፡
 የዜጎች ሀገርን መውደድ ለሀገር በሚሰጠው ጥቅም ዙሪያ ተወያዩ፡፡
• ሀገርን ከውጭ ወረራ ማስጠበቅ ሀገሪቱ ከዜጎቿ ማግኘት ያለባትን ጥቅም ታገኛለች፡፡

ክፍለ ትምህርት 4: የሀገር ወዳድ ዜጋ ባህሪያት


5.4 ክፍለ ትምህርት 4: የሀገር ወዳድ ዜጋ ባህሪያት
5.4.1 የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች የዚህን የክፍለ ጊዜ ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡ -
• የሀገር ወዳድ ዜጋ ባህሪያትን ይገነዘባሉ፡፡
5.4.2 ይዘት
የተመደበ ሰዓት: 4 ክፍለ ጊዜ

1) የሀገር ወዳድ ዜጋ ባህሪያት

66 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


5.4.3 አጭር ገለፃ
የሀገር ወዳድ ግለሰብ ምን ዓይነት ባህሪያት ያሳያል? ቀደም ብለን እንደተወያየነው የሀገር
ወዳድነት ከፅንሰ ሃሳብ በዘለለ ተግባር ይፈልጋል፡፡ ይህ ክፍለ ጊዜ በሀገር ወዳድ ዜጋ ባህሪያት
ላይ ያተኩራል፡፡ እንዲሁም ሀገርን በመውደድና መንግስትን በመውደድ መካከል ውይይት
ይደረጋል

5.4.4 የመማር ማስተማር ሂደት


ተመራጭ ማስተማሪያ መረጃ መሳሪያዎች
Ô ምስሎች
Ô ፎቶዎች.
ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች
 ማነቃቂያ

 ትምህርቱን ማስተዋወቅ

 ገለፃ

 ጥያቄና መልስ

 የቡድን ውይይት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


¢ አስፈላጊ የሆኑ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ ያዘጋጁ
¢ ተማሪዎች በትምህርቱ ዙሪያ ያላቸውን ቅድመ ግንዛቤ እንዲገልፁ ጊዜ ይስጧቸው፡፡

የትምህርቱ አቀራረብ
1. የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ
መምህሩ ተማሪዎቹን በራሳቸው ግንዛቤ ስለ ሀገር ወዳድ ባህሪያት እንዲገልፁ በማድረግ ትምህርቱን
መጀመር ይችላሉ፡፡.
 የዕለቱን የትምህርት ዓላማ ለተማሪዎች ያሳውቋቸው፡፡

 ተማሪዎች ስለ ሀገር ወዳድ ባህሪያት እንዲገልፁ በቂ ጊዜ ይስጧቸው፡፡

 የተማሪዎችን ሀሳብ ሊያነሳሳ የሚችል ጥያቄ ያንሱ፡፡

2. የትምህርቱ አካል

ይህ ትምህርት ስለ ሀገር ወዳድ ዜጋ ባህሪያት አጠር አድረጎ በመግለፅ ሊጀምር ይችላል፡፡መምህሩ ለተማሪዎች
ውይይት የሚሆን ርዕስ ሊሰጧቸው ይችላሉ፡፡

1. ማጠቃለያ: የዕለቱን ትምህርት ዋና ዋና ፅንሰ ሀሳቦች ያንሱና ያጠቃሉ፡፡


የሀገር ወዳድ ሰው ባህሪያት.

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 67


2. ግምገማና ክትትል
ሀ. ግምገማ
 መምህሩ ለተማሪዎች የክፍል ስራ፣ አጭር ፈትና ወይም ስለ ሀገር ወዳድ ግለብ
ባህሪያት በቡድን እንዲወያዩ በማድረግ የዕለቱን ትምህርት መረዳታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

ለ. ክትትል
• ስለ ሀገር ወዳድ ሰው ባህሪያት አጠር ያለ ውይይት በማድረግና ተማሪዎች ዕርስ በርሳቸው ሀሳብ
እንዲለዋወጡ በማበረታታት ያጠቃሉ፡፡

– ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርት የተሻለ እንደተረዱት እርግጠኛ ለመሆን


የቡድን ስራ ይስጡና ሁሉም አባላት በውይይቱ መሳተፋቸውን ያረጋግጡ፡፡
–ተማሪዎች በሀገር ወዳድ ግለሰብ ባህሪያት ላይ ያላቸውን አረዳድ ይገምግሙ፡፡

5.4.5 የተግባራት መልሶች

ተግባር 5.4 ትዕዛዝ ፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሶች አስቡና መልሶቻችሁን


በቡድን ተወያዩባቸው፡፡:

1) ሀገር ወዳድ ዜጎች በማህበረሰቡ ዘንድ ተግባራዊ የሚያደርጓቸው ድርጊቶች


ላይ ተወያዩ፡፡ ለምሳሌ፡
-
 ሀገር ወዳድ ዜጎች ሀገራቸውን ይወዳሉ እንዲሁም በሀገራቸው ባህልና ታሪክ
ይኮራሉ
 ሀገር ወዳድ ዜጎች ልጆቻቸው ሀገራቸውን እንዲያውቁና እንዲወዱ አድረገው
ያሳድጋሉ፡፡
 ሀገር ወዳድ ዜጎች ልጆቻቸውን ይንከባከባሉ፡፡
2) ሀገር ወዳድ ዜጋ ለማህበረሰቡ ከሚያሳያቸው ባህሪያቶች ውስጥ የተወሰኑ
ምሰሌዎች ጥቀሱ፡፡
ሀገር ወዳድ ዜጋ የሚከተሉትን ግደታዎች በማህበረሰቡ ውስጥ እንዲፈፅም
ይጠበቅበታል፡-
• የጎረቤቶቻቸውን ልጆች በፍቅር ይይዛሉ፡፡

• አትክልቶችን መትከልና ውሀ ማጠጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

• የሌሎችን እምነትና ባህል ያከብራሉ፡፡

5.5 ክፍለ ትምህርት 5: የሀገር ፍቅር


5.5.1 የመማር ብቃቶች ፡ ተማሪዎች ይህን ክፍለ ጊዜ ከተማሩ በኋላ፡-
 የሀገር ፍቅርን ትርጉም ይረዳሉ፡፡

68 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


5.5.2 ይዘት

አጠቃላይ የተመደ ሰዓት 2

1) የሀገር ፍቅር

5.5.3 አጭር ገለፃ


ሀገርን መውደድ ማለት ምን ማለት ነው? እስካሁን ድረስ ተማሪዎች የሀገርን መውደድ ምንነት፣ ባህሪያት
ስለተወያዩ በዚሀ ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ሀገርን በትክክል ስለመውደድ ይወያያሉ፡፡ሀገርን የመውደድ
ጥቅምና ሀገራቸውን የሚወዱ ሰዎች ባህሪያትን አስመልክቶ ውይይት ይኖራል፡፡

5.5.4 የመማር ማስተማር ሂደት


ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች
Ô ምስሎች
Ô ፎቶዎች

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች


• ማነቃቂያ
• ትምህርቱ ማስተዋወቅ
• ገለፃ
• የቡድን ውይይት
• ጥያቄና መልስ

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


¢ አሰፈላጊ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ ማዘጋጅት
¢ ተማሪዎች ስለ ፅንሰ ሀሳቡ ያላቸውን ቅድመ ግንዛቤ እንዲገልፁ ጊዜ መስጠት

ትምህርቱን ማቅረብ
1. የዕለቱን የትምህርት ርዕስ ማስተዋወቅ:
ትምህርቱ የተማሪዎችን ስለ ሀገር መውደድ ፅንሰ ሀሳብ ያላቸውን ግንዛቤ በመዳሰስ
ይጀምራል፡፡
 ለተማሪዎች የዕለቱን የትምህርት አላማ ያሳውቁ፡፡

 ተማሪዎች ሀገርን ስለመውደድ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲገልፁ በቂ ጊዜ ይስጧቸው፡፡


 ተማሪዎች ሀሳብ እንዲያፈልቁ የሚያስችል ጥያቄ ያንሱ፡፡

2. የትምህርቱ አካል

ይህ ትምህርት ሀገርን ስለ መውደድ አጭር ትውውቅ በማድረግ ይጀምራል መምህሩ


ተማሪዎች ክፍል ውስጥ የሚወያዩበት ርዕስ መስጠት ይችላሉ፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 69


3. ማጠቃለያ
የዕለቱን ትምህርት ዋና ዋና ፅንሰ ሀሳብ ማንሳትና ማጠቃለል፡፡
4. ግምገማና ክትትል
ሀ. ግምገማ
መምህሩ ለተማሪወች አጭር ፈተና ወይ ምስለ ሀገር መውደድ የቡድን ውይይት በመስጠት ዕለቱን
ትምህርት መረዳታቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ፡

ለ. ክትትል
ትምህርቱን ስለ ሀገር ፍቅር ምንነት አጭር ውይይት እንዲያደርጉና እርስ በርሳቸው ውይይት
እንዲያደርጉ በማድረግ ያጠቃሉ፡፡
– ተማሪዎች እንደገባቸው ለማረጋገጥ የቡድን ወይም የተግባር ስራ
ይስጧቸውና ሁሉም ተማሪወች መሳተፋቸውን ያረጋግጡ፡፡
– ተማሪዎች ለሀገር ፍቅር ያላቸውን አረዳድ ይገምግሙ፡፡

5.5.5 የተግባራት መልሶች

ተግባር 5.5 ትዕዛዝ በሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ዙሪያ በጋራ ሆናችሁ


ተወያዩበት፡፡

1) ሀገርን መውደድ ማለት ምን ማለት ነው?


ሀገርን መውደድ፡-
 በሀገር ታሪክና ባህል መኩራት ማለት ነው
2) ለሀገር ሰላምና እድገትን መፈለግ ማለት ነው
 ሀገርን መውደድ ለምን ይጠቅማል ?
 ሰዎችን ያስተሳስራል
 ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ይጠቅማል

5.6 የምዕራፉ ማጠቃለያ መልሶች

ትዕዛዝ አንድ ፡እውነት / ሀሰት


1) ሀሰት
2) እውነት
3) እውነት
4) ሀሰት
5) እውነት
ትዕዛዝ ሁለት: ምርጫ
1) ሐ
2) ሐ
3) ለ
4) ሐ

70 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


ትዕዛዝ ሦስት: አጭር መልስ ስጥ
1)የሀገር መዉደድን ምንነት ማብራራት ትችላላችሁን?
• የሀገር ፍቅር ማለት ሀገርን ከልብ መውደድ ነው፡፡
• ሀገር በምታሳየው ማንኛውም እድገት መኩራት ነው፡፡
• የሀገሪቷን ዜጎች መውደድም ጭምር ነው፡፡
2) የሀገር ወዳድ ዜጋ በሚወጣቸዉ ሃላፊነቶች ዙሪያ ተወያዩ፡፡
• የሀገርን ሰንደቅ ዓላማ ማክበር
• የሀገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ
• የሀገርን ጀግኖች ማክበር
3) የሀገር ወዳድነት በሃላፊት ላይ ላሉ ግለሰቦች የሚሰጠዉን ጥቅም አብራሩ
• ስልጣናቸውን ተጠቅመው የተሻለች ሀገር ለመገንባት ያስችላቸዋል
• ሙስና ላይ እንዳይሰማሩ ያስችላቸዋል
4) የሀገር ወዳድ ዜጎች ባህሪያትን ዘርዝሩ፡፡
· በሀገራቸው ይኮራሉ

· የሀገር የኔ ባይነት ስሜት ይሰማቸዋል

· ራሳቸውን ለሀገር መስዋዕት ያደርጋሉ

· ሙስናን ይዋጋሉ

· የሀገር ጀግኖችን ያከብራሉ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 71


ምዕራፍ ስድስት
ሰላምና መተባበር

መግቢያ
ይህ ምዕራፍ ተማሪዎች የሠላምን አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ ያስችላቸዋል፡፡ ሰላም በአንድ አካባቢ የጦርነትና
ግጭት ያለመኖር ሁኔታ በሚል ሊገለፅ ይችላል፡፡ ተማሪዎች ሀይልን ከመጠቀም ይልቅ ግጭቶችን
በምክንያትና በውይይት እንዲፈቱ ይረዳቸዋል፡፡ ትምህርቱ ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲገልጹና እርስ
በርሳቸው እንዲተባበሩ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡ በተማሪዎች መካከል የመረዳዳትና የመከባበር ዕሴት ዋጋ
የሚኖረው ከራሳቸው ውጭ ያሉ የተለያዩ ባህሎችን በማስተዋወቅ ነው፡፡

የምዕራፉ የመማር ብቃቶች፡ ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-

• የሰላምን ትርጉም ይገልጻሉ


• የሰላምን ጥቅም ይገነዘባሉ
• ሰላማዊ ባህሪን ያደንቃሉ
• ግጭት አልባ ባህሪን ያሳያሉ
• የመተባበር ፅንሰ ሀሳብ ላይ ይወያያሉ
• ለመተባበር ጥቅም ዋጋ ይሰጣሉ
• የመተባበር ዕሴቶችን ይለማመዳሉ
• የሰላምና የመተባበር ዝምድናን ያደንቃሉ

ምዕራፍ 6 ሰላምና መተባበር

አጠቃላይ የተመደበ ሰዓት፡- 19 ክፍለ ጊዜ

ትምህርቶች
• ክፍለ ትምህርት 1: የሰላም ትርጉም

• ክፍለ ትምህርት 2: መተባበር

• ክፍለ ትምህርት 3: የሰላምና የመተባበር ዝምድና

6.1 ክፍለ ትምህርት 1: የሰላም ትርጉም


6.1.1 የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
• የሰላምን ፅንሰ ሀሳብ ይገልፃሉ
6.1.2 ይዘት

72 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


የተመደበ ሰዓት: 7 ክፍለ ጊዜ

1) የሰላም ትርጉም

6.1.3 አጭር ገለፃ


ሰላማዊ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ የዜጎች ሚና ምንድን ነው ?
በሰላምና በትብብር መካከል ዝምድና አለን? በዚህ ክፍለ ትምህርት ተማሪዎች የሠላምና የመተባበር
ትርጉም እና ዓላማ እንዲሁም በሁለቱ መካከል ዝምድና ያብራራሉ፡፡

6.1.4 የመማር ማስተማር ሂደት


ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ
Ô የድምፅና ምስልመሳሪያዎች
Ô ምስሎች
ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች
 ማነቃቂያ
 ትምህርቱን ማስተዋወቅ
 ገለፃ
 ጥያቄና መልስ
 የቡድን ውይይት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


¢ አስፈላጊ የሆኑ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ ማዘጋጀት
¢ በዕለቱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የተነሱትን ዋና ሀሳቦች ማስተዋወቅና ተማሪዎች በጉዳዩ
ላይ ቅድመ ግንዛቤያቸውን እንዲገልፁ ማበረታታት

የትምህርቱ አቀራረብ
1. ትምህርቱን ማስተዋወቅ
የሰላም አስፈላጊነት ላይ ትኩረት በማድረግ አጭር ትውውቅ ያድርጉ
 የዕለቱን የክፍለ ጊዜ ትምህርት ዓላማ ለተማሪዎች ማሳወቅ

 ተማሪዎች በርዕሱ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማወቅ የማነቃቂያ ጥያቄ ይስጧቸው

 የተማሪዎችን ሀሳብ ሊያነሳሳ የሚችል ጥያቄ ያንሱ

ጥያቄው በሚከተለው መልኩ ሊቀርብ ይችላል ‘ሰላም ለኢትዮጵያ ያለው ጥቅም ምን ይመስላችኋል?’

2. የትምህርቱ አካል
የሰላምን ትርጉም እና ምንነት መግለፅና ሰላምን የመለማመጃ መንገዶች ምሳሌ በመጥቀስ ውይይቱን ማስኬድ
ይቻላል፡፡
ሰላምን ለመረዳትና ለመለማመድ የሚያስችሉ አስፈላጊ ፅንሰ ሀሳቦችን መግለፅ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 73


3.ማጠቃለያ
የትምህርቱን ዋና ፅንሰ ሀሳብ ያጠቃሉ
የሰላም ትርጉም
4. ግምገማና ክትትል:

ሀ. ግምገማ
ለተማሪዎቹ የክፍል ስራ፣ አጭር ፈተና በመስጠት ወይም በቡድን እንዲወያዩ በማድረግ በውይይቱም ወቅት
የራሳቸውን ምሳሌዎች እንዲጠቀሙ በማድርግ የዕለቱን ትምህርት መረዳታቸውን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
ለ. ክትትል
ስለ ሰላም ትርጉም ማጠቃለያ በመስጠት በጥቅሙ ዙሪያ ተማሪዎች እርስ በእርስ ሀሳብ
እንዲለዋወጡ በማድረግ ያጠቃሉ ፡፡
• ተማሪዎች ያስተማሯቸውን ትምህርት የበለጠ እንዲረዱልዎ ስለ ሰላም ምንነት
እንዲወያዩ የቡድን ስራ ይስጧቸውና ሁሉም የቡድኑ አባላት መሳተፋቸውን ያርጋግጡ፡፡

• ተማሪዎች ስለ ሰላም ምንነት ያላቸውን ግንዛቤ ይገምግሙ

6.1.5 ለተግባራት የተሰጡ መልሶች

ተግባር 6.1 ትዕዛዝ: የሚከተሉትን ጥያቄዎች በቡድን ተወያዩባቸው፡፡

1) ሰላም የሚለው ቃል በራሱ ምንድን ነው

 ፀጥ ያለና የተረጋጋ ሁኔታ ማለት ነው

 በማህበረሰብ ውስጥ የደህንነትና የስርዓት መኖር ማለት ነው

 የጦርነት ወይም የግጭት አለመኖር

2) ተማሪዎች በማህበረሰቡ ዘንድ ሰላም እንዲጠበቅ ሚና አላቸውን? መልሳችሁ አዎ ከሆነ


የተወሰኑትን ጥቀሱ፡፡

• አዎ! ተማሪዎቹ የማህበረሰቡ አካል እንደመሆናቸው መጠን በሰላም ማስጠበቁ ላይም


መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል

• ተማሪዎች የህብረተሰቡን ችግር በመፍታት ረገድ ለየት ያለ አመለካከት ሊኖራቸው ይችላል፡፡


ከነዚህ መካከል፡ -ያለ ዕድሜ ጋብቻን፣ሁከትን መቀነስ ወዘተ

3) የሰላም አለመኖር በህብረተሰቡ ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ መገመት ትችላላችሁን?

• ግጭትና ጦርነት

• የነፃነት አለመኖር

74 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


6.2 ክፍለ ትምህርት 2: መተባበር
6.2.1 የመማር ብቃት ፡ ተማሪዎች ይህን የክፍለ ጊዜ ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡
• የመተባበር ፅንሰ ሀሳብን ይወያያሉ
6.2.2 ይዘት

የተመደበ ሰዓት : 7 ክፍለ ጊዜ

1) የመተባበር ፅንሰ ሀሳብ

6.2.3 አጭር ገለፃ


ተማሪዎች የሰላምን ትርጉም ከተወያዩ በኋላ የመተባበር ትርጉምና ዓላማውን ይወያያሉ፡፡
ይህ መሆኑ በሰላምና በመተበበር ያለውን ዝምድና እነዲያሰላስሉና ለቀጣዩ ርዕስ የዳበረ
ውይይት እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል፡፡

6.2.4 የመማር ማስተማር ሂደት


ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ
Ô የድምፅና የዕይታ መሳሪያ
Ô ፎቶዎች

ተመራጭ የማስተማሪያ መሳሪያዎች


• ማነቃቂያ
• ትምህርቱን ማስተዋወቅ.
• ገለፃ
• ጥያቄና መልስ
• የቡድን ውይይት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


¢ አስፈላጊ የሆኑ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ያዘጋጁ
¢ ተማሪዎቹ በፅንሰ ሀሳቡ ላይ ያላቸውን ቅድመ ግንዛቤ እንዲገልፁ ጊዜ ይስጧቸው

1. ትምህርቱን ማቅረብ

የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ


መምህሩ የመተባበርን ትርጉም በመግለፅ ትምህርቱን ሊጀምር ይችላል፡፡
 የዕለቱን ትምህርት ዓላማ ለተማሪዎች ያሣውቁ

 ተማሪዎች በመተባበር ዓላማ ዙሪያ መፅሐፍትን እንዲያነቡና ሀሳባቸውን እንዲገልፁ በቂ ጊዜ


ይስጧቸው፡፡

 ሀሳባቸውን ሊያነሳሳ የሚችል ጥያቄ ይጠይቋቸው

ጥያቄዎቹም በዚህ መልኩ ሊሆኑ ይችላሉ ‘መተባበር የተማሪዎችን የክፍል ውስጥ ልምድ እንዴት
ሊያጎለብትላቸው ይችላል?’

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 75


2. የትምህርቱ አካል

መምህር ስለ መተባበር ትርጉምና ዓላማ በመግለፅ ትምህርቱን ሊጀምር ይችላል፡፡


ተማሪዎቹ ፅንሰ ሀሳቡን በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችላቸው የመተባበር ባህሪያቶች
ተዘርዝረዋል፡፡
ተማሪዎች ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጓቸው
3. ማጠቃለያ
የትምህርቱን ዋና ፅንሰ ሀሳብ ያንሱና ያጠቃሉ፡፡
የመተባበር ፅንሰ ሀሳብ

4. ግምገማና ክትትል

ሀ) ግምገማ
• ተማሪዎቹ የተማሩትን ትምህርት እንደተረዱ ለማረጋገጥ የክፍል ስራ፣ አጭር ፈተና ወይም
በመተባበር ፅንሰ ሀሳብ ዙሪያ በቡድን እንዲወያዩና ሀሳባቸውን እንዲገልፁ ማድረግ ይችላሉ፡፡

ለ) ክትትል
• በመተባበር ፅንሰ ሀሳብ ዙሪያ ተማሪዎች እርስ በርሳቸው ሃሳብ እንዲለዋወጡ በማድረግ አጭር ገለፃ
አድርጎ ትምህርቱን ማጠቃለል፡፡

–ተማሪዎች የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተግባራትን ሊሰጧቸው ይችላሉ፡፡


–ተማሪዎች በመተባበር ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ይገምግሙ፡፡

6.2.5 ለተግባራቱ የተሰጡ መልሶች

ተግባር 6.2 ትዕዛዝ: የሚከተሉትን የጥያቄ መልሶች አስቡና በመልሶቻችሁ


ዙሪያ ከጓደኞቻችሁ ጋር ተወያዩ፡፡

1) ከሌሎች ጋር መተባበር ጥቅሙ ምንድን ነው?


 መተባበር ተግባራትን ቀላልና አዝናኝ በሆነ መንገድ ለማከናወን ይረዳል፡፡
 የሰዎችን መስተጋብር ወይም ትስስር ያጠናክራል፡፡
2) በክፍል ውስጥ የመተባበር ምሳሌን ማሳየት ትችላላችሁን?
 አብሮ ማጥናት
 ችግርን በጋራ መፍታት
 ሀሳብ መጋራት
3) ተማሪዎች እነሱ ላይ ተፅዕኖ የሚያመጣ ውሳኔ ላይ ለምን ይሳተፋሉ?
 የተወሰነው ውሣኔ ተፅኖ ሰለሚያሳድርባቸው መሳተፋቸው
ለእነሱ ጠቃሚ ነው፡፡
 ተሳትፎው የመግባባትና ችግር የመፍታት ክህሎትን ያሳድግላቸዋል፡፡
 ተሳትፎው ከቤተሰቦቻቸውና ከመምህራኖቻቸው ጋር ያለውን ግንኙነት
ያሳድግላቸዋል፡

76 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


6.3 ክፍለ ትምህርት 3: የሰላምና የመተባበር ዝምድና

6.3.1 የመማር ብቃት ፡ ተማሪዎች ይህን ክፍለ ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-


• የሰላምና የመተባበር ዝምድና
6.3.2 ይዘት
የተመደበ ሰዓት: 5 ክፍለ

1) የሰላምና የመተባበር ዝምድና

6.3.3 አጭር ገለፃ


ይህ ክፍል ሰላምና መተበባበር ያላቸው ዝምድና ላይ ያጠነጥናል፡፡ የሁለቱ ዝምድና ከግለሰብና ከማህበረሰብ
አንፃር ያየዋል፡፡

6.3.4 የመማር ማስተማር ሂዴት


ተመራጭ የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች
Ô ምስሎች

ተመራጭ የማስተማሪያ ዘዴዎች


• ማነቃቂያ
• ትምህርቱን ማስተዋወቅ
• ገለፃ
• ጥያቄና መልስ
• የቡድን ውይይት

ቅድመ ትምህርት ዝግጅት


¢ አስፈላጊ የሆኑ የማስተማሪያ መሳሪዎችን ማዘጋጀት
¢ ተማሪዎች ስለ ክፍለ ጊዜው ትምህርት ያላቸውን ቅድመ ግንዛቤ እንዲገልፁ ጊዜ
ይስጧቸው፡፡

1. ትምህርቱን ማቅረብ
የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅ
መምህሩ ተማሪዎች በሰላምና በመተባበር ዝምድና ዙሪያ ያላቸውን ሀሳብ እንዲገልፁ
በማድረግ ይጀምራሉ
• የዕለቱን የትምህርት ዓላማ ለተማሪዎች ያሣውቋቸው

• ተማሪዎችን ስለ ሰላምና መተባበር ዝምድና እንዲያነቡና ሀሳባቸውን እንዲገልፁ በቂ ጊዜ ይስጧቸው፡፡

• የተማሪዎችን ሀሳብ ሊያነሳሳ የሚችል ጥያቄ ያንሱ፡፡


2.የትምህርቱ አካል

ይህ ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ስለ ሰላምና መተባበር ግንኙነት በገባቸው ልክ እንዲገልፁ በማድርግ


ቢጀምር የተሻለ ነው፡፡ በመቀጠል መምህሩ የሰላምና የመተባበር ዝምድና በማህበረሰብ ወደ
ሚለው ውይይት ይሸጋገራሉ፡፡

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 77


3.ማጠቃለያ:
የዕለቱን ትምህርት ዋና ፅንሰ ሀሳብ ያጠቃሉ፡፡
የሰላምና የመተባበር ዝምድና
4. ግምገማና ክትትል

ሀ. ግምገማ
• ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት መረዳታቸውን ለማረጋገጥ መምህሩ
የክፍል ስራ፣ አጭር ፈተና ወይም የቡድን ስራ መስጠትና ሁሉም
የቡድን ተማሪዎች መሳተፋቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

ለ. ክትትል
• በፅንሰ ሀሳቡ ላይ አጭር ውይይት ማድረግና ማጠቃለል፡፡

–ተማሪዎች የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የቡድን ስራ ይስጧቸውና ሁሉም የ ቡድኑ አባላት በውይይቱ
መሳተፋቸውን ያረጋግጡ፡፡
–ተማሪዎች በሰላምና መተባበር ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ይገምግሙ፡፡
6.3.5 ለተግባራቱ የተሰጡ መልሶች

ተግባር 6.3 ትዕዛዝ: የሚከተሉትን የጥያቄ መልሶች አስቡና በመልሶቻችሁ


ዙሪያ ከጓደኞቻችሁ ጋር ተወያዩ፡፡

1) በሰላምና መተባበር መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?


 እያንዳንዱ የማሕበረሰቡ አባል ሰላምን ለማስጠበቅ አብሮ መስራት ይጠበቅበታል
 ጦርነትና ግጭት ሠላምን ለማስጠበቅ በጋራ ካለመስራት የመጣ ውጤት ነው፡፡
2) የተማሪዎችን መተባበር የሚጠይቅ ተግባር ምሳሌ መስጠት ትችላላችሁን?
ሀ. የቡድን ስራ
ለ. አትክልቶችን መትከል.
ሐ. በዕረፍት ጊዜ መጫወት
3) ሰላም ለሀገራችሁ ከሚሰጠው ጥቅም ውስጥ የተወሰኑትን ጥቀሱ
ሀ. ልማትና እድገት
ለ. መልካም ጉርብትና

78 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


6.4 ለምዕራፉ ጥያቄ የተሰጡ መልሶች

ትዕዛዝ አንድ: እውነት / ሀሰት


1) ሀሰት
2) እውነት
3) ሀሰት
4) ሀሰት
5) ሀሰት
ትዕዛዝ ሁለት : ምርጫ
1) ለ
2) ሀ
3) መ
4) መ

ትዕዛዝ ሦስት፡ አጭር መልስ ስጡ


1) • መተማመን አብሮ ለመስራት ያስችላል፡፡
 መተማመን ግንኙነትን ያጠናክራል፡፡
 አስቸጋሪ ግዜን በጋራ ለማለፍ ይጠቅማል
2) • እርስ በርስ ለመረዳዳት
 ስራን በጋራ ለመስራት
 እፅዋቶችን መትከልና መንከባከብ
3) • አብሮነት
 ግልፀኝነት
 ሌሎችን መንከባከ

79 የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል


የግብረ ገብ ትምህርት መርሃ ትምህርት
ምዕራፍ አንድ፡ የግብረ ገብ ምሉዕነት (የተመደበለት 19 ክፍለ ጊዜ)
የመማር ውጤቶች፡-
ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ ፡-
• የግብረ ገብ ምሉዕነትን ይረዳሉ
• የባህሪይ ምሉዕነትን ይገልፃሉ
• ለግብረ ገብ ምሉዕነትና አስፈላጊነት ዋጋ ይሰጣሉ
• የግለሰብን እውነተኛ የግብረ ገብ ምሉዕነት መገለጫ ያብራራሉ፡፡
• የተሟላ ግብረ ገብ አለመኖር ውጤትን ይለያሉ

የመማር ብቃት ይዘት የመማር ስልቶች ምዘና


- የግብረ ገብ ምለዕነት 1.1. የግብረ ገብ - የግብረ ገብ ምንነትን - ስሇ ግብረ ገብ ምለዕነት
ጽንስ ሀሳብን ይገልጻለ ምለዕነት መጠየቅ ተማሪዎችን መጠየቅ
- የምለዕነት መገሇጫዎችን ትርጉም - የግብረ ገብ መገሇጫዎችን - በምዕራፍ ከተሰጣቸው ትምህርት
ይጠቅሳለ 1.2. የግብረ ገብ እንዲዘረዝሩ ማድረግ አንፃር የተማሪዎችን ውጤትና
- ሇግብረ ገብ ምለዕነት ምለዕነት - ተማሪዎች የግብረ ገብ ብቃት ተገቢነት መመልከት
ጥቅም ዋጋ መስጠት ባህሪያት አስፈላጊነትን በጋራ (መገምገም)
- የግሇሰብ እውነተኛ 1.3. የግብረ ገብነት እንዲወያዩ ማድረግ - እያንዳንዱ ተማሪ እንዴት ጥያቄ
ምለዕነት መግሇጫዎች ጥቅም - የእውነተኛ የግብረ ገብ እንደሚመልሱ መመመልከትና
ያሳያለ 1.4. የግብረ ገብነት መገሇጫዎችን በተማሪዎች ግብረመልስ በመስጠት መመዘን
- የተሟላ ግብረ ገብ ማበልፀጊያ ፊት እንዲያሳዩ መርዳት
አሇመኖር መንገዶች - የግብረ ገብነት አሇመኖር
የሚያስከትሇውን ውጤት 1.5. የግብረ ገብነት ምንነትን በጥንድ ሆነው
ይሇያለ አሇመኖር እንዲወያዩ ማድረግ
የሚያስከትሇው - ከግብረ ገብ ምለዕነት ጋር
ችግር የተያያዙ ትረካዎችን
ሇተማሪዎች መተረክ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 77


ምዕራፍ ሁለት ፡- ለህግ ተገዢነት ( የተመደበለት 20 ክፍለ ጊዜ)
የመማር ውጤቶች- ከዚህ ምዕራፍ በኋላ ተማሪዎች፡
• የህግ ተገዢነት ጽንስ ሀሳብን ይረዳሉ
• ለህግ ተገዢነት አስፈላጊነት ዋጋ ይሰጣሉ
• ለህግ ተገዢ የሆነ ግለሰብ ባህሪያትን ያሳያሉ
• ለህግ የመገዛት ባህሪያትን ይለያሉ

- ሇህግ ተገዢ የመሆን 2.1. ሇህግ ተገዢ የመሆን - ተማሪዎች በህግ አክባሪነት ጽንስ - ሇህግ ተገዢ መሆን ምን
ፅንስ ሀሳብን ማስረዳት ትርጉም ሀሳብ ዙሪያ በቡድን እንዲወያዩ ማሇት እንደሆነ ተማሪዎች
- ሇህግ ተገዢ የሆነ ሰው 2.2. ሇህግ ተገዢ የመሆን ማመቻቸት መጠየቅ
የሚያንጸባርቃቸው አስፈላጊነት - ሇህግ ተገዢ የመሆን - በምዕራፍ ከተሰጣቸው
ባህሪያት ማሳየት 2.3. ሇህግ ተገዢ የሆነ አስፈላጊነትን ተማሪዎች በተሇያየ ትምህርት አንፃር
- ሇህግ ተገዢ አሇመሆን ሰው ባህሪያት ዘዴ እንዲወያዩበት ማድረግ የተማሪዎችን ውጤትና
የሚያስከትሇውን ችግር 2.4. ሇህግ ተገዢ - ሇህግ ተገዢ የሆነ ግሇሰብ ብቃት ተገቢነት መገምገም
መግሇጽ አሇመሆን ባህሪያትን ተማሪዎች በውስን - ጥያቄና መልስ
የሚያስከትሇው ጥናታዊ ጽሁፍ ወይም የመድረክ - እያንዳንዱ ተማሪ እንዴት
ችግር ትዕይንት ተጠቅመው እንዲገልጹ ጥያቄ እንደሚመልስ
2.4.1. የሰብአዊ መብት ማድረግ መመመልከትና ግብረመልስ
ጥሰት - ሇህግ ተገዢ አሇመሆን በመስጠት መመዘን
2.4.2. ሙስና የሚያስከትሇውን ችግር በቡድን
2.4.3. ሇሱስ ተገዢነት እንዲወያዩ ማድረግ
2.4.4. ህገ ወጥ የልጆች
ስርቆትና ዝውውር
2.4.5. ግብር መሰወር

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 78


ምዕራፍ ሶስት፡- ጥሩ ሥነ ምግባር (የተመደበለት 20 ክፍለ ጊዜ)
የመማር ውጤቶች፡- ከዚህ ምዕራፍ በኋላ ተማሪዎች፡
• የመልካም ሥነ ምግባር ምንነትን ይገነዘባሉ
• ለመልካም ሥነ ምግባር ዋጋ ይሰጣሉ
• የመልካም ሥነ ምግባር መገለጫዎችን ያሳያሉ

ብቃት ይዘት የመማር ስልቶች ምዘና


- የመልካም ስነ ምግባር 3.1. የመልካም ሥነ - የመልካም ስነ ምግባር ምንነትን - በመልካም ስነምግባር እሳቤ
ምንነትን መግሇጽ ምግባር ምንነት ጥንድ ሆነው እንዲወያዩ ማድረግ ጥያቄና መልስ
- መልካም ሥነ ምግባር 3.2. መልካም ሥነ ምግባር - መልካም ስነ ምግባር የተላበሰ - የተማሪዎችን ከተማሩት
የተላበሱ ሰዎችን ( የተላበሰ ሰው ባህሪያት ሰው ባህሪን በቡድን እንዲወያዩ ትምህርት አንፃር
ባህርያት) መገሇጫዎች መገሇጫ ማድረግ የተማሪዎችን ውጤትና
መግሇጽ 3.3. የመልካም ሥነ - የመልካም ስነ ምግባር እጦት ብቃት ተገቢነት መመልከት
- የመልካም ሥነ ምግባር የመላበስ የሚያስከትሇውን ችግር - በተማሩት ዙሪያ ጥያቄና
ምግባር መላበሰ አስፈላጊነት ተማሪዎች እንዲገልጹ ማድረግ መልስ ማድረግ
ጥቅምን ማጉላት 3.4. የመልካም ሥነ - የመልካም ስነ ምግባር መኖር - እያንዳንዱ ተማሪ እንዴት
- የመልካም ሥነ ምግባር ማጠናከሪያ ጥቅምን በቡድን እንዲወያዩ ጥያቄ እንደሚመልስ
ምግባር ማጠናከናያ መንገዶች ማድረግ መመመልከትና ግብረመልስ
መንገዶችን ማሳየት 3.5. የመልካም ሥነ - ተማሪዎች አራት አራት ሆነው በመስጠት መመዘን
መግባር አሇመኖር በመልካም ስነ ምግባር ማጐልበቻ - የተማሪዎች የምዘና ፈተና
ችግሮች / ማሳደጊያ/ መንገዶች ላይ መስጠት
በተሇያየ የቡድን አቦዳደን ዘዴ
እንዲወያዩ ማድረግ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 79


ምዕራፍ አራት፡- ማህበራዊ ምጣኔ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ የተመደበለት 19 ክፍለ ጊዜ
የመማር ውጤቶች፡- ከዚህ ምዕራፍ በኋላ ተማሪዎች፡
- የማህበራዊ ምጣኔ ድርጊት ምንነትን ይገልፃሉ
- የማህበራዊ ተሳትፎ (የበጎ ፍቃድ) ተሳትፎ አስፈላጊነትን ያጐላሉ
- ትርፍ ጊዜን ለጋራ ጥቅም የማዋያ መንገዶችን ያሳያሉ
- የታማኝ ግብር ከፋይና የቁጠባ ባህል ለማህበራዊ ምጣኔ ያላቸውን ሚና ይገልፃሉ፡፡

ብቃት ይዘት የመማር ስልቶች ምዘና


- የማህበራዊ ምጣኔ 4.1. የማህበራዊ ምጣኔ - ተማሪዎች ጥንዴ ሆነው - በማህበራዊ ምጣኔ ዴርጊት
ዴርጊት ምንነት ላይ ዴርጊት ምንነት በማህበራዊ ምጣኔ ዴርጊት ጽንስ ዕሳቤ ጥያቄና መልስ
መወያየት 4.2. በበጎ ፈቃዴ ሀሳብ ላይ እንዱወያዩ ማዴረግ ማካሄዴ
- የበጎ ፍቃዴ/ማህበራዊ (በማህበራዊ - ተማሪዎች በበጎ - ከተማሩት ትምህርት አንፃር
ተሳትፎ አስፈላጊነትን አገልግሎት) መሳተፍ ፈቃዴ(በማህበራዊ አገልግሎት) የተማሪዎችን ውጤትና
ማጉላት 4.3. ትርፍ ጊዜን ሇጋራ የመሳተፍ ጥቅምን በመዴረክ ብቃት ተገቢነት መመዘን
- ትርፍ ጊዜን ሇጋራ ጥቅም ጥቅም ማዋል ትዕይንት እንዱያሳይ ማዴረግ - በተማሩት ዙሪያ ጥያቄና
የማዋያ መንገድችን 4.4. ታማኝ ግብር ከፋዮችና - ተማሪዎች በቡዴን ሆነው መልስ
መግሇጽ የቁጠባ ባህል የታማኝ ግብር ከፋዮችና የቁጠባ - እያንዲንደ ተማሪ እንዳት
- የታማኝ ግብር ከፋዮች ሇማህበራዊ ምጣኔ ባህል ሇማህበራዊ ምጣኔ ጥያቄ እንዯሚመልስ
እና የቁጠባ ባህል ያላቸው ሚና ያላቸውን ሚና እንዱወያዩ መቆጣጠርና ተገቢውን
ሇማህበራዊ ምጣኔ ማዴረግ ግብረ መልስ መስጠት
ያላቸውን ሚና ማጉላት - የቡዴን ስራ መስጠት

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 80


ምዕራፍ አምስት፡-የሀገር ፍቅርን መሻት (የተመደበበለት 19 ክፍለ ጊዜ)
የመማር ውጤቶች፡- ከዚህ ምዕራፍ በኋላ ተማሪዎች፡
• የሀገር ፍቅር ጽንስ ሀሳብን ይረዳሉ
• የሀገር ፍቅር አስፈላጊነትን ይገልፃሉ
• በሀገር የመኩራት ጥቅምን ያጐላሉ
• አወንታዊ የሀገር ፍቅር ማሳያ መንገዶችን ያሳያሉ፡፡

ብቃት ይዘት የመማር ስልቶች ምዘና


- የሀገር ፍቅር ምንነትን 5.1. የሀገር ፍቅር - ተማሪዎች በጥንድ ሆነው የሀገር - ተማሪዎች ስሇ ሀገር ፍቅር
መግሇጽ ምንነት ፍቅር ምንነትን አስመልክቶ ሇምን እንደሚማሩ መጠየቅ
- የሀገር ፍቅር 5.2. የሀገር ፍቅር እንዲወያዩ ማድረግ - ተማሪዎች ጥያቄዎችን
መገሇጫዎችን መሇየት መገሇጫዎች - ተማሪዎች በጋራ ሆነው በሀገር ሇመመሇስ ያላቸውን
- ሀገር ወዳድ መሆን 5.3. ሀገር ወዳድ ፍቅር መገሇጫዎች ዙሪያ ተሳትፎ መመልከት
ሇአንዱ ህብረተሰብና የመሆን እንዲወያዩ ማድረግ - ተማሪዎች ክፍል ውስጥ
ሀገር የሚኖረውን አስፈላጊነት - ተማሪዎች አራት አራት ሆነው ያላቸውን ተግባራት
ጠቀሜታ ማጉላት 5.4. ሀገርን መውደድ ሀገር ወዳድ የመሆን ጥቅም ላይ መመዝገብና ገንቢ ግብረ
- የሀገር ወዳድ ግሇሰብ የተሇያየ የቡድን አቦዳደን ዘዴን መልስ መስጠት
ሇህብረተሰቡና ሇሀገሩ ተጠቅመው ማወያየት፡፡ - የተማሪዎች የክፍል ውስጥ
ያሇውን ሚና ማሳየት - የሀገር ወዳድ ግሇሰብ ትረካዎች ተግባራትን መስጠት
- ሀገርን የመውደድ ሇተማሪዎች መተረክ
ምንነትን መግሇጽ - ተማሪዎች በቡድን ሆነው
ተውኔት እንደሚወዱ (ምስል)
ተጠቅመው ፈጥረው ማሳየት
- ተማሪዎች በቡድን ሆነው
ሀገራቸውን ሇምን እንደሚወዱ
ተውኔት/ምስል እንዲፈጥሩ
ማድረግ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 81


ምዕራፍ ስድስት ፡ ሰላምና ትብብር (የተመደበለት 19 ክፍለ ጊዜ)
የመማር ውጤቶች፡-ከዚህ ምዕራፍ በኋላ ተማሪዎች፡
• የሰላም ጽንስ ሀሳብን ይገነዘባሉ
• የሰላምን አስፈላጊነት ይገልፃሉ
• ሰላማዊ ባህሪን ያደንቃሉ
• ሀይልን ያለመጠቀም ባህሪያትን ያሳያሉ
• በትብብር ጽንስ ሀሳብ ዙሪያ ይወያያሉ
• የትብብር ጥቅምን ከፍ ያደርጋሉ
• የትብብር እሴትን ይለማመዳሉ
• ሰላምና ትብብር ያላቸውን ዝምድና ማድነቅ

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 82


ብቃት ይዘት የመማር ስልቶች ምዘና
- የሰላምና የትብብር 6.1. ሰላም - ተማሪዎች በጥንድ ሆነው በሰላም ምንነት ዙሪያ - ተማሪዎችን የቃል ጥያቄ መጠየቅ
ጽንስ ሀሳብን ፍቺ 6.1.1. የሰላም ጽንስ ሀሳብ ውይይት እንዲያደርጉ ማድረግ
- ተማሪዎች በውይይት ወቅትያላቸው
መስጠት 6.1.2. የሰላም አስፈላጊነት - ተማሪዎች ተሳትፎ መከታተልና ለጥያቄዎቻቸው
- ሇሰላም እሴቶች ዋጋ 6.1.3. ሰላማዊ ባህሪን ፒራሚዲያዊ
” “ ምላሽ መስጠት
መስጠት ማሳየት የውይይት ቅርጽ - የተማሪዎች የክፍል ውስጥ ተግባራትን
- የትብብር እሴቶችን  መከባበር አቀማመጥ ተጠቅመው መመዝገብና ገንቢ ግብረ መልስ መስጠት
ስሇትብብር እሴቶች - ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በተማሪዎች
መሇማመድ  መግባባት
- በእሇታዊ ህይወታቸው  ትግስት ውይይቀት ፊት ንግግር እንዲያደርጉ አለበለዚያም
የትብብር እሴቶችን  መጋራት እንዲያደርጉ ማድረግ አጭር ምዘና መስጠት
ማሳየት  መነጋገር - ተማሪዎች ስሇ ሰላም አስፈላጊነትውይይት
- የሰላምና የትብብር  በሰላማዊ መንገድ ግጭትን እንዲያደርጉ ማድረግ
ዝምድናን ማነፃፀር መፍታት - ተማረዎቸ በቡድን በመሆን በሰላምና በትብብር
6.2. መተባበር ዙሪያ እንዲወያዩ ማድረግ
6.2.1 የመተባበር ጽንስ ሀሳብ
6.2.2. የመተባበር ጥቅም
6.2.3. የመተባበር እሴቶች
 ወንድማማችነት
 ቅንነት
 ግልጽነት
 ሇሌሎች ማሰብ
6.3. የሰላምና የትብብር
ዝምድና

የግብረ ገብ ትምህርት 6ኛ ክፍል 83

You might also like