You are on page 1of 10

የ 2015 የአዛን አካዳሚ ሠመራ ቅርንጫፍ የ 1 ኛ ክፍል አከባቢ ሳይንስ የ 1 ኛ ሰሚስተር ሚድ ፈተና

I. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል የሆነውን "እውነት" ትክክል ያልሆነውን "ሀሰት" በማለት መልሱ።

1. የሙዚቃ መሳሪያዎች የተለያዩ ድምፆች ያወጣሉ ።

2. ጊታር ባህላዊ የሙዚቃ የመሳርያ ነው።

3. ምላስ ለመቅመስ የሚጠቅም የስሜት ህዋስ ነው።

4. ሸንኮራ አገዳ ከምጣጣ ጣዕም አለው ።

5. ሽንት ቤት መልካም የሽታ መአዛ አለው ።

II. ከተሰጡት አማራጮች ውሰጥ ትክክለኛ መልስ የያዘ ፊደል ምረጡ።

1. ከሚከተሉት ውስጥ ኮምጣጤ ጣዕም ያለው የትኛው ነው?

ሀ. ከሪሜላ ለ. ስኳር ሐ. ፓፓያ ጁስ መ. ሎሚ

2. ከሚከተሉት ውሰጥ ጥሩ መአዛ ያለው የትኛው ነው?

ሀ. የሞት እንስሳ ለ. የጫማ ሽታ ሐ. ሰንደል መ. ሽንት ቤት

3. ከሚከተሉት ውስጥ ባህላዊ የሙዚቃ መሳርያ ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ማሲንቆ ለ. ሳክስፎን ሐ. ክራር መ. ከበሮ

4. ከሚከተሉት ውስጥ ብርሃን የማይሰጠው የትኛው ነው?

ሀ. ወንበር ለ. ፀሐይ ሐ. ሻማ መ. አምፑል

5. ከምግብ በፊትና በኋላ መታጠብ ያለብን የትኛው ነው።

ሀ. ገላችን ለ. ፀጉራችን ሐ. እጃችን መ. እግራችን

6. "ሚያው" የሚለውን ድምፅ ያለው እንስሳ ማን ነው?

ሀ. ውሻ ለ. ደሮ ሐ. ድመት መ. አህያ

7. ወተት ምን አይነት ቀለም አለው?

ሀ. ቀይ ለ. አረንጓዴ ሐ. አረንጓዴ መ. ብጫ

8. ከሚከተሉት ውስጥ የዱር እንስሳት የሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ግመል ለ. በሬ ሐ. ነብር መ. ደሮ

9. የግል ንፅህና ለመጠበቅ የሚጠቅም የትኛው ነው ?


ሀ. እጅን መታጠብ ለ. ልብስን ማቆሸሽ ሐ. አቧራ ላይ መጫወት መ. ጥፍርን ማሳደግ

10. በመፋቅያ የምንቦርሸው የሰውነታችን ክፍል የትኛው ነው?

ሀ. ጥርስ ለ. አፍንጫ ሐ. አይን መ. ጆሮ

III. በምድብ "ለ" የተዘረዘሩትን ከምድብ "ሀ" የተዘረዘሩት ጋር አዛምዱ

ሀ ለ

1. አይን ሀ. ለማሽተት ይጠቅማል

2. ጀሮ ለ. ለመቅመስ ይጠቅማል

3. አፍንጫ ሐ. ለመዳሰስ ይጠቅማል

4. ምላስ መ. ለማየት ይጠቅማል

5. እጅ ሠ. ለመስማት ይጠቅማል
የ 2015 የአዛን አካዳሚ ሠመራ ቅርንጫፍ የ 2 ኛ ክፍል አከባቢ ሳይንስ የ 1 ኛ ሰሚስተር ሚድ ፈተና

I. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል የሆነውን "እውነት" ትክክል ያልሆነውን "ሀሰት" በማለት መልሱ።

1. ምግብ ለሰውነታችን ጠቃሚ ነገር ነው።

2. ወተት ከእፅዋት ይገኛል

3. ልብሰን ብርድ ይከላከላል

4. የህመም ስሜት ሲሰማን ወደ ህክምና መሄድ አለብን

5. ቤት መጠልያ ነው

II. ከተሰጡት አማራጮች ውሰጥ ትክክለኛ መልስ የያዘ ፊደል ምረጡ።

1. ከሚከተሉት ውስጥ ምግብ ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ዳቦ ለ. ወተት ሐ. እንቁላል መ. ቤት

2. በሰውነታችን የበሽታ ስሜት ሲሰማን ማድረግ ያለብን ነገር የትኛው ነው?

ሀ. ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ለ. ወደ ጨዋታ መሄድ ሐ. ወደ ህክምና መሄድ መ. ወደ እንቅልፍ መሄድ

3. ፍራፍሬ ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ዳቦ ለ. ብርቱኳን ሐ. እንጀራ መ. ጎመን

4. ባህላዊ መጓጓዣ የሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ግመል ለ. መኪና ሐ. ባቡር መ. አውሮፕላን

5. ለማገዶነት የማያገለግል የትኛው ነው?

ሀ. እንጨት ለ. ኩበት ሐ. ከሰል መ. ልብስ

6. አንድ ሰው ጥሩ ስነምግባር እንዲኖረው ምን ማድረግ አለበት ?

ሀ. መጣላት ለ. እየበሉ ማውራት ሐ ወላጅን ማክበር መ. መሳደብ

7. ከሚከተሉት ውስጥ እፅዋት ያልሆነው የትኛው ነው

ሀ. ሽንኩርት ለ. አሳ ሐ. ግራር መ. ወይራ

8. በመሬት ውሰጥ የሚገኘው የእፅዋት ክፍል የቱ ነው?

ሀ. ሥር ለ. ግንድ ሐ. ቅጠል መ. አበባ

9. ከሚከተሉት ውስጥ ቅጠሉ የሚበላ የቱ ነው?


ሀ. ጎመን ለ. ቀይስር ሐ. ድንች መ. ሽንኳር አገዳ

10. ከሚከተሉት ውስጥ ሥሩ የሚበላ የቱ ነው?

ሀ. ቃርያ ለ. ስንዴ ሐ. ብርቱኳን መ. ካሩት

III. በምድብ "ለ" የተዘረዘሩትን ከምድብ "ሀ" የተዘረዘሩት ጋር አዛምዱ

ሀ ለ

1. ሥር ሀ. ሣር

2. ግንድ ለ. ቁጥቋጦ

3. ትላልቅ ተክሎች ሐ. ዛፎች

4. መካከለኛ ተክሎች መ. ከመሬት ውስጥ የሚገኝ የተክል ክፍል

5. ትናንሽ ተክሎች ሠ. ከመሬት በላይ የሚገኝ የተክል ክፍል


የ 2015 የአዛን አካዳሚ ሠመራ ቅርንጫፍ የ 3 ኛ ክፍል አከባቢ ሳይንስ የ 1 ኛ ሰሚስተር ሚድ ፈተና

I. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል የሆነውን "እውነት" ትክክል ያልሆነውን "ሀሰት" በማለት መልሱ።

1. የአመጋገብ ስርአቶች እንደየአካባቢው ይለያያሉ ።

2. ማንኛውም ሠው ጤናማ ሆኖ ለመኖር የተመጣጠነ ምግብ ያስፈልገዋል ።

3. ምግብ በተለያዩ መንገዶች ሊበከል ይችላል ።

4. በአንድ ቀን ውስጥ 48 ሰአታት አሉ።

5. አፈር ለዕፅዋቶች እድገት በጣም አስፈላጊ የተፈጥሮ ሀብት ነው።

II. ከተሰጡት አማራጮች ውሰጥ ትክክለኛ መልስ የያዘ ፊደል ምረጡ።

1. ምግብ ከብክለት የምንከላከልበት መንገድ ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ምግብ ከድኖ ማስቀመጥ ለ. ምግብ የሚያዘጋጁ ሰዎች ንፅህናቸው መጠበቅ።

ሐ. የምግብ ማብስያ ዕቃ ንፅህናውን መጠበቅ መ. እጅን አለመታጠብ

2. ከሚከተሉት ውስጥ በቀዝቃዛ ቦታ ወይም ፍሪጅ ውስጥ ማስቀመጥ የሌለበት የቱ ነው።

ሀ. ቲማቲም ለ. ብርቱኳን ሐ. ዱቄት መ. ቃርያ

3. ከሚከተሉት ውስጥ የግልን ንፅህና ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ጥርስ መረበሽ ለ. አፈር ላይ መጫወት ሐ. ጥፍርን መቋረጥ መ. ልብስን ማጠብ

4. የታይፎይድ በሽታ ምልክት ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. መሳቅና መጫወት ለ. ከፍተኛ ትኩሳት ሐ. የጀርባ ህመም መ. ራስምታት

5. የግዜ መለክያ ያልሆነው የትኛው ነው

ሀ. ሴኮንድ ለ. ደቂቃ ሐ. ሰአት መ. ሜትር

6. በአመት ውስጥ ስንት ቀናት አሉ?

ሀ. 250 ለ. 300 ሐ. 365 መ.200

7. ለእርሻ የሚያገለግለው የአፈር አይነት የትኛው ነው?

ሀ. አሸዋማ አፈር ለ. ደቃቅ/ለም/ አፈር ሐ. ሸክለማ አፈር መ. ድንጋያማ አፈር

8. ከሚከተሉት ውስጥ የአፈር እንክብካቤ ዘዴ ያልሆነው የትኛው ነው ?

ሀ. ዛፍ መቁረጥ ለ. እርከን መስራት ሐ. ዛፎች መትከል መ. የግጦሽ ስራዎች መጠበቅ


9. ከሚከተሉት ውስጥ የውሃ መገኛ ያልሆነው የትኛው ነው ?

ሀ. ምንጭ ለ. ሐይቅ ሐ. ወንዝ መ. አስፋልት

10. የውሃ ጥቅም ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ለመጠጥ ያገለግላል ለ. ንፅህና ለመጠበቅ ያገለግላል ሐ. ምግብ ለማዘጋጀት ያገለግላል መ.ለማጎዶነት ያገለግላል ።

III. በምድብ "ለ" የተዘረዘሩትን ከምድብ "ሀ" የተዘረዘሩት ጋር አዛምዱ

ሀ ለ

1. የጥራጥሬ አይነት ሀ. አሳ

2. የወተት ውጤቶች ለ. ስላጣ

3. የስጋ ምግቦች ሐ. ፓስታ

4. አትክልት አይነት መ. አሬራ

5. የዳቦ ዝርያዎች ሠ. ሽምብራ


የ 2015 የአዛን አካዳሚ ሠመራ ቅርንጫፍ የ 4 ኛ ክፍል አከባቢ ሳይንስ የ 1 ኛ ሰሚስተር ሚድ ፈተና

I. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል የሆነውን "እውነት" ትክክል ያልሆነውን "ሀሰት" በማለት መልሱ።

1. ደም ከጠጣርና ከፈሳሽ የተሰራ አካላዊ ፈሳሽ ነው።

2. ማንኛውም ሊበላና ሊጠጣ የሚችል ነገር ሁሉ ምግብ ይባላል

3. የተመጣጠነ ምግብ ሁሉም ንጥረ ምግቦች አጣምሮ የያዘ አይደለም ።

4. ኤድስ በደም ንክኪ፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት አይተላለፍም ።

5. የወሊድ መከላከያ በአግባቡ አለመጠቀም ያልተፈለገ እርግዝና እንዲከሰት ያደርጋል ።

II. ከተሰጡት አማራጮች ውሰጥ ትክክለኛ መልስ የያዘ ፊደል ምረጡ።

1. ምግብን ከአፍ ማኘክ እስከ በአንጀት ውስጥ ማሳረግ ድረስ ያለው ሂደት ምን ይባላል ?

ሀ. ንጥረ ምግብ ለ. የደም ዝውውር ሐ. የመተንፈስ ስርአት መ.ስርዓተ ልመት

2. ከአፍ ጀምሮ እስከ ፊንጢጣ ድረስ የተዘረጋ ቱቦ ምን ይባላል ?

ሀ. የምግብ ቱቦ ለ. የደም ውሃ ሐ. የልመት ዕጢ መ. የደም ህዋስ

3. የጠጣር ቁስ አካል ባህሪ ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ይዘት አላቸው ለ. ቅርፅ የላቸውም ሐ. ክብደት አላቸው መ. ቅርፅ አላቸው

4. የቁስ አካሉ አጠቃላይ ቅርፅ፣ መጠን፣ ቀለም የሚያሳይ ባህሪ የትኛው ነው?

ሀ. የቁስ አካል ባህሪ ለ. ከሚካላዊ ባህሪ ሐ. ፊዚካላዊ ባህሪ መ. የተፈጥሮ ባህሪ

5. ከሚከተሉት ውስጥ ታዳሽ የተፈጥሮ ሀብት ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. እንስሳት ለ. እፅዋት ሐ. አፈር መ. ማዕድናት

6. በአንድ ቦታ ለረጅም ግዜ የሚታየው የአየር ሁኔታ ምን ተብሎ ይጠራል ?

ሀ. የአየር ንብረት ለ. የአየር ለውጥ ሐ. የአየር ፀባይ መ. የተፈጥሮ አየር

7. ከሚከተሉት ውስጥ የእፅዋት ጥቅም ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ለቤት መስርያ ያገለግላል ለ. ለምግብነት አያገለግልም ሐ. ለልብስ መስርያነት ያገለግላል

መ. ለመዝናኛነት ያገለግላል ።

8. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክለኛ ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ከምድር ወገብ ስንርቅ ሙቀት ይቀንሳል ለ. ከፍታ ሲጨምር የአየር ግፊት ይቀንሳል
ሐ. ከፍታ ሲጨምር ሙቀት ይጨምራል መ. ከፍታ ሲቀንስ ሙቀት ይጨምራል

9. የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ከምድር ወገብ ያለው ርቀት ለ. የባህር ሞገድ ሐ. ከባህር ወለል ያለው ከፍታ መ. የአየር ለውጥ

10. ከሚከተሉት ውስጥ ኢ-ታዳሽ የተፈጥሮ ሀብት የትኛው ነው?

ሀ. አየር ለ. አፈር ሐ. ውሃ መ. ነዳጅ ዘይት

III. በምድብ "ለ" የተዘረዘሩትን ከምድብ "ሀ" የተዘረዘሩት ጋር አዛምዱ

ሀ ለ

1. ክረምት ሀ. መስከረም፣ ጥቅምት፣ ህዳር

2. መኸር ለ. ሰኔ፣ ሐምሌ፣ ነሐሴ

3. በልግ ሐ. ታህሳስ፣ ጥር፣ የካቲት

4. በጋ መ. መጋቢት፣ ሚያዝያ፣ ግንቦት

5. የዝናብ ወቅት ሠ. ከፍተኛ ዝናብ የሚገኝበት ወቅት


የ 2015 የአዛን አካዳሚ ሠመራ ቅርንጫፍ የ 5 ኛ ክፍል አከባቢ ሳይንስ የ 1 ኛ ሰሚስተር ሚድ ፈተና

I. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል የሆነውን "እውነት" ትክክል ያልሆነውን "ሀሰት" በማለት መልሱ።

1. 78% የአየር አከባቢ በኦክስጂን የተሸፈነ ነው ።

2. አየር ቁስ አካል ነው ።

3. ሜሪኩሪ በጠጣር መልክ የሚገኝ ብረት እስተኔ ነው።

4. አየር በህይወት ለመኖር በጣም አስፈላጊ ነው ።

5. በአፋችን ውስጥ የሚገኙትን ትናንሽ ፀጉሮች አቧራና ጀርሞች ወደ ሳምባችን እንዳይገቡ ለማጣራት ይጠቅማሉ።

II. ከተሰጡት አማራጮች ውሰጥ ትክክለኛ መልስ የያዘ ፊደል ምረጡ።

1. ከሚከተሉት ውስጥ በፈሳሽ መልክ የሚገኝ ኢ-ብረት እስቴኔ የትኛው ነው?

ሀ. ኦክስጂን ለ. ናይትሮጂን ሐ. ክሎሪን መ. ብሮሚን

2. ከሚከተሉት ውስጥ የአየር ባህሪ ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ጠጣር ነው ለ. ቦታ ይይዛል ሐ. ክብደት አለው መ. ግፊት አለው

3. ከሚከተሉት ውስጥ የመተንፈሻ አካል ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ስርን ለ. ልብ ሐ. አፍ መ. ዋና የአየር ቧምቧ

4. ሲጋራና አንጋዳ በውስጣቸው የማይገኘው የቱ ነው?

ሀ. ኒኮቲን ለ. ታር /ቅርጠን/ ሐ. ኦክስጂን መ. ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ

5. የንፁህ ውሃ መለያ ባህሪ ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ቀለም አልባ ነው ለ. ሽታ አልባ ነው ሐ. ጣዕም አልባ ነው መ. ብርሃን አያስተላልፍም

6. ከመሬት የተነነ ውሃ በንፋስ አማካኝነት ቀዝቅዞ በአካባቢ አየር የሚፈጠረው የትናንሽ የውሃ ቅንጣት ክምችት ምን
ይባላል? ሀ. ደመና ለ. ዝናብ ሐ. ውቅያኖስ መ. ንፋስ

7. ሁለት እና ከሁለት በላይ ንጥረ ነገሮች በኬሚካላዊ ጥምረት ተቀናጅተው የሚፈጥሩት ልዩ ቁስ ምን ተብሎ ይጠራል ?

ሀ. ቅይጥ ለ. ውሁድ ሐ. ጥጣር መ. ፈሳሽ

8. ከሚከተሉት ውስጥ ዘረ ብዙ ቅይጥ ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. የሩዝና የበቆሎ ድብልቅ ለ. የዘይትና የውሃ ድብልቅ ሐ. የውሃና የጨው ብጥባጥ መ. የአሸዋና የአፈር ድብልቅ

9. ከሚከተሉ ውስጥ ኦክሳይድ ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ሃይድሮጅን ኦክሳይድ ለ. ካርቦን ኦክሳይድ ሐ. ብረት ኦክሳይድ መ. ሶድየም ክሎራይድ


10. ከሚከተሉት ውስጥ የብረት እስቴኔ ባህሪ ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. አብረቅራቂ ናቸው ለ. ተጣጣፊ ናቸው ሐ. ተመዛዥነት ባህሪ አላቸው መ. ሙቀትና ኮረንቲ አያስተላልፉም

III. በምድብ "ለ" የተዘረዘሩትን ከምድብ "ሀ" የተዘረዘሩት ጋር አዛምዱ

ሀ ለ

1. የጉድጓድ ውሃ ሀ. ከሚካላዊ ያልሆነ ጥምረት

2. የባህር ውሃ ለ. ከሚካላዊ ጥምረት

3. ኦክሳይድ ሐ. ከኦክስጂን ጋር የሚደረግ ውህደት

4. ውሁድ መ. በከርሰ ምድር ይገኛል

5. ቅይጥ ሠ. በምድር ላይኛው ክፍል ይገኛል

You might also like