You are on page 1of 2

Safari Academy ሳፋሪ አካዳሚ

“Your Kids Our Kids!” “ልጆችዎ ልጆቻችን ናቸው!”


+251(0)116-607203/04 +251(0)911-469878 www.safariacademy.com Addis Ababa Ethiopia

የ ፳፻፲፪ የትምህርት ዘመን የ2ኛ ክፍል የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ማስታወሻ

የአካል ብቃት (Physical Fitness)

 የአካል ብቃት ማለት ዕለታዊ ስራዎችንም ሆነ ስፖርታዊ ውድድሮችን ያለምንም ችግር


በቀላሉ የማከናወን ችሎታ ነው፡፡
 የአካል ብቃት ለሰው ልጅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ እድሜና ፆታ ሳይለይ ሁሉም
የአካል ብቃት ሊኖረው ይገባል፡፡
 የአካል ብቃት ሊዳብር የሚችለው የተለያዩ የአካል ክፍሎቻችንን ሊያጠነክሩ እና ሊያዳብሩ
በሚችሉ እንቅስቃሴዎች አማካይነት ነው፡፡

ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጠቀሜታዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል

 ጤናማ እንድንሆን

 ቀልጣፋና ፈጣን እንድንሆን

 እምሮአችን እንዲጐለምስ

 በምንሠማራበት የሥራ ዘርፍ ውጤታማ እንድንሆን

 ከድብርትና ጭንቀት እንድንላቀቅ

 ጠንካራ እና የተስተካከለ የሰውነት አቋም እንዲኖረን

 በአብዛኛው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ተመራጭ የሚሆነው ከምግብ በፊት ሲሆን
ልጆቻችን ከእንቅልፋቸው ከተነሱ በኋላ ቀጥታ ወደ ምግብ ከመሄዳቸው በፊት የአካል ብቃት
እንቅስቃሴን ቢያከናውኑ ተመራጭ ይሆናል፡፡
 ዘወትር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በዋናነት ልጆቻችን ቀኑን ሙሉ ቤት ሲውሉ የተሻለ
መነቃቃት እና ጥሩ የምግብ ፍላጐት እንዲኖራቸው እንዲሁም የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውኑ
አካላቸው እንዲነቃቃ እና ጥሩ የጥናት ጊዜ እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል፡፡
 ውድ ልጆቻችን ፡- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከማድረጋችሁ በፊት በቤት ውስጥ ባለው ክፍት
ቦታ ላይ እየተመላለሱ በመራመድ (Walk) በማድረግ ሰውነታችሁ በደንብ ከሞቀና ከተፍታታ
በኋላ የሚከተሉትን እንቅስቃሴዎች ማድረግ ይመከራል፡፡

 በመቀጠል እርምጃን ወደ ዱብዱብ መቀየር

1 “ ፈጣሪ የምንወዳቸውን ልጆቻችንን፣ ህዝባችንን እና ሃገራችንን ይጠብቅ! ”


 ዱብ ዱብን የተወሰነ ፍጥነት ወዳለው ሩጫ መቀየር
 ከሩጫው በኋላ ባሉበት ቆመው ዱብዱብ ማለት
 እግርን በየተራ እያፈራረቁ ጉልበትን እያጠÕ እየዘረጉ መንቀሳቀስ
 እጆችን ወደፊት ወደ ኋላ እያሽከረከሩ ማዞር
 እግርና እጅን እየከፈቱና እየዘጉ በዝላይ መልክ መስራት
 እግርና እጅን ወደፊትና ወደኋላ እያደረጉ በዝላይ መልክ መስራት
 ከፍ ያለ ደረጃ ላይ እግሮችን እያፈራረቁ በየተራ ማውጣትና ማውረድ
 ያልበዛ ቁጭ ብድግ እንዲሰሩ ማድረግ
እነዚህን የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎችን ካከናወናችሁ በኋላ የሞቀው ሰውነታችሁ መፈታታት ስላለበት
ተከታይ ተግባሮችን ማከናወን ተገቢ ነው፡፡
 እጆቻችሁን ወደላይና ወደታች እንዲሁም ወደጐን እግሮቻችሁን የተወሰነ በመክፈት እንዲሳሳቡ
ማድረግ፡፡
 እግሮቻችሁን በደንብ በመክፈት ወደ አንደኛው ጐን ጉልበትን በማጠፍ ሌላኛውን እግር ቀጥ አድርጐ
በመዘርጋት ማሳሳብ ከተወሰነ ኬኮንድ በኋላ በተቃራኒውም ተመሳሳዩን ማድረግ፡፡
 የሰውነታችሁን ሚዛን (balance) መጠበቅ እንድትችሉና እግራችሁ እንዲሳሳብ በአንድ እግር ቆሞ
ሌላኛውን እግር ከጉልበት በማጠፍ እጆቻችንን ወደ ደረት ስቦ በመያዝ የተወሰነ ኬኮንድ መቆየት
ሲጨርሱ እግር ቀይሮ ተመሳሳዩን ማድረግ፡፡
 አንገታችን ወደፊት እና ወደኋላ ወደቀኝ እና ወደግራ በእጆቻችን ጫን እያልን ማዘንበልና መያዝ
ወዘተ …. የመሳሰሉት እንቅስቃሴዎች የሞቀው ሰውነታችን እንዲፍታታ ይረዳል፡፡
 በአጠቃላይ ከላይ የዘረዘርናቸው እንቅስቃሴዎች በየእለቱ ቢያንስ ለ30 ደቂቃዎች ቢከናወኑ
የሚመከር ሲሆን ነገር ግን ልጆቻችን እንቅስቃሴውን ሲሰሩ እንዳይሰለቹ ወይም ጫናው በዝቶባቸው
ለጉዳት እንዳይዳረጉ የወላጆች ክትትል አስፈላጊ ነው፡፡

ማስታወሻ፡- ልጆቻችን የተስተካከለ እድገት አቋምና ጤንነትን ይዘው እንዲያድጉ የአካል እንቅስቃሴ
ከማድረግ በተጨማሪ የአመጋገብ ስርዓትም ወሳኝ በመሆኑ ምግቦቻቸው ውስጥ
አትክልት እና ፍራፍሬ እንዲያዘወትሩ እንመክራለን፡፡

- እንቅስቃሴዎችን ሲያከናውኑ ድካም ሊኖር ስለሚችል እረፍት እንዲያደርጉና ትንሽ


ውሃም እንዲጐነጩ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

2 “ ፈጣሪ የምንወዳቸውን ልጆቻችንን፣ ህዝባችንን እና ሃገራችንን ይጠብቅ! ”

You might also like