You are on page 1of 29

“The company advertising will have

two major parts. One is done via

television platform while the other

uses radio.”

Call Us
+251-917-071-427
+251-946-637-372
Cover photo by : Samuel Adamu
Powered By

Advertising

የአዘጋጇ
መልዕክት
ሰላም!
ባሉበት ሰላምታዬ ይድረስዎት!

ይህ ከዚህ ገፅ ቀጥሎ የሚያነቡት የመልካም 74 ዲጂታል መፅሄት የመጀመርያ ቅፅ ነው፡፡ ይህን ዲጂታል መፅሄት
ምግበ ነፍስ ይሆንዎት ዘንድ ብዙ ተጠበን እና ተጨንቀን አዘጋጅተነዋል፡፡ በይዘቱም የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስስ
አንዲሆን ጥረናል፡፡ ጤናን ፣ አካባቢን ፣ ጥበብን የሚዳስሱ አምዶችን አካተን እንደፍላጎትዎ በዘርፍ በዘርፉ ሰድረን
አቅርበንልዎታል፡፡ እንደሚማሩበት ፤ እንደሚዝናኑበትም እርግጠኞች ነን፡፡

74 ቁጥር በኒዩመሮሎጂ- ለቁጥሮች ትርጉምን በመስጠት ጥበብ ስሌት መሰረት መልካም ግንኙነትን ፣ መልካም
ጓደኝነትን ፣ መልካም ጥበብን፣ መልካም እና የተቀናጀ የቡድን ስራን እንዲሁም የተጠበቀ አስተማማኝ ደህንነትን
የሚገልፅ ቁጥር ነው፡፡ እኛም ለዚህ ነው ይህቺን ዲጂታል መፅሄታችንን “መልካም 74” ብለን የሰየምናት፡፡በዚች
ዲጂታል መፅሄታችን መልካም መልካሙን ፤ ድግ ደጉን እናስነብቦታለን፡፡ ለሀሳብ እንዲሁም ለአስተያየትዎ በራችን
ክፍት ነው፡፡

መልካም ንባብን ተመኘሁ!!

ቤተልሄም አምባቸው
ዋና አዘጋጅ
+251 911 921 477
betty.melkam74@gmail.com
Bethlehem Ambachew

የመፅሄት ዲዛይን በ ጭምዴሳ እምሩ ፎቶ በሳሙኤል አዳሙ


+251 917 071 427 +251 946 637 372
chimdesadebela@gmail.com Samueladamu1986@gmail.com
Chimdesa E Debela Shalom Sami

መልካም74 | 4 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


መልካም74 | 5 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019
መልካም74 | 6 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019
መልካም74 | 7 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019
ስለ ጤና እናውራ

ከመኪና ፍሰት

የፀዱ ቀናት
ቤተልሄም አምባቸው
- ኢትዮጵያ


መጀመርያው ከመኪና ፍሰት የፀዱ ቀናት - ኢትዮጵያ የተደረገ አንድ ጥናት አንደሚጠቁመው በሳምንት ለ75 ደቂቃ
“ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለጤናማ ሕይወት” ብቻ የእግር መንገድ ማድረግ የቻሉ ሰዎች ያንን ካላደረጉ
በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ፣ በባህር ዳር ፣ በሀዋሳ ሰዎች የተሻለ የአካል ጤንነት ላይ መገኘት ችለዋል፡፡
፣ በጅማ እንዲሁም በሌሎች የክልል ከተሞች ህዳር
30 ቀን 2011 ዓ.ም ተከብሮ ውሏል፡፡ በዚህ በሀገራችን የእግር መንገድ ማድረግ በጣም ቀላል ፣ ምንም አይነት መሳርያ
የመጀመርያ በሆነው እና በየወሩ በወሩ የመጨረሻ እሁድ የማይጠይቅ ፣ በማንኛውም ሰዓት ልናደርገው የምንችለው
እንደሚከበር በተገለፀው በዓል መክፈቻ ላይ የኢፌዴሪ ጤና ከመሆኑም ባሻገር ማንኛውም ሰው በራሱ የፍጥነት መጠን
ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን ፣ የኢፌዴሪ ሊሰራው የሚችለው የእንቅስቃሴ አይነት ነው፡፡ ሌላ አይነት
ትራንስርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት እንቅስቃሴዎችን ብንሰራ ሊደርሱብን ከሚችሉ የሰውነት
ሞገስ እና የአፍሪ ሄልዝ ቴሌቪዥን መስራች ዶ/ር ሜሮንን ጫናዎች ስጋት ሙሉ በሙሉ ነጻ ሆነን አንቅስቃሴውን
ጨምሮ ክቡራን ሚኒስትሮች ፣ አትሌቶች እንዲሁም ተፅዕኖ ማድረግ እንችላለን፡፡ በተለይም ከፍተኛ የክብደት መጠን
ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ነበር፡፡ ያላቸው ሰዎች እና አረጋውያን በቀላሉ አጭር የእግር መንገድ
በማድረግ ሰውነታቸውን ማፍታታት እና የጤንነታቸውን
ይህ በኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፣ በአፍሪ ሄልዝ ቴሌቪዥን ሁኔታ ማስተካከል ይችላሉ፡፡
እንዲሁም በአጋር ድርጅቶች የጋራ ትብብር የተዘጋጀው በዓል
ኢትዮጵያውያንን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በሚኖሩበት አካባቢ አልያም አረንጓዴ በሆነ እና ሊያዝናናዎት
እና የእግር መንገድን እንዲያዘወትሩ ለማበረታታት የተዘጋጀ በሚችል ቦታ የእግር መንገድን ማድረግ እንቅስቃሴውን
መሆኑን አስተባባሪዎቹ ይገልፃሉ፡፡ ሳይሰለችዎት እንዲያደርጉት ይረዳዎታል፡፡ በተለይም ይህንን
እንቅስቃሴ ከቤተሰብ አባልዎ ጋር ፤ ከጓደኞቾት ወይም
የእግር መንገድ ማዘውተር የሚያስገኛቸው በአካባቢዎ ካሉ ልክ እንደርስዎ እንቅስቃሴውን ማድረግ
የጤና በረከቶች ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር ቢሰሩት የበለጠ ሊዝናኑበት እንደሚችሉ
በቀን ለ30 ደቂቃ ብቻ የእግር ጉዞ ማድረግ ጠንካራ አጥንት ፣ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡
የተስተካከለ የኮሌስትሮል መጠን እንዲሁም ብርቱ ጡንቻዎች
እንዲኖሩን ያደርጋል፡፡ ለልብ ህመም ፣ ለስኳር በሽታ እንዲሁም
ለካንሰር አይነቶች የመጋለጥ እድላችንንም በከፍተኛ መጠን
ይቀንሳል፡፡ ከሌሎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነቶች በተለየ
Photo by : Samuel Adamu

የእግር ጉዞ ማድረግ ነፃ እና ምንም አይነት ወጪን የማይጠይቅ


ሲሆን የአሰልጣኝን ወይንም ደግሞየባለሙያን እገዛ ሳንፈልግ
በቀላሉ ራሳችን ልናደርገው የምንችለው የእንቅስቃሴ አይነት
ነው፡፡
የአካል እንቅስቃሴዎች ሁሉ ከባድ ፣ የመስርያ መሳርያዎችን
የሚፈልጉ እንዲሁም በአንድ ለእንቅስቃሴ በተመደበ ቦታ
ብቻ የሚሰሩ አይነት መሆን የለባቸውም፡፡ ባሳለፍነው አመት

መልካም74 | 8 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ስለ ጤና እናውራ

የእግር ጉዞ
ማድረግን ቢያዘወትሩ፡

• የልብ ጤንነትዎ የተስተካከለ ይሆናል


• ለስትሮክ የመጋለጥ እድልዎን ይቀንሳል
• የደም ግፊትን ፣ የኮሌስትሮል መጠንን ፣ የስኳር መጠንን ፣
የመገጣጠሚያ አጥንቶች ችግርን ፣ እንዲሁም ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ
በሽታዎችን ለመቆጣጠር እና ለመከላል ይረዳዎታል፡፡
• ጠንካራ አጥንቶች እንዲኖርዎት ያደርጋል
• ጠንካራ ጡንቻዎች እንዲኖርዎት ያደርጋል
• በሰውነትዎ ውስጥ ያለውን የስብ መጠን ተስተካከለ እንዲሆን
ያደርጋል፡፡
የሚከተሉትን አማራጮች በለት ተዕለት እንቅስቃሴዎት
ውስጥ ቢያካትቱ የእግር ጉዞን በቀላሉ

ሊለምዱት ይችላሉ:
• ሕንፃዎች ላይ በሚወጡበት ሰዓት አሳንስር ከሚጠቀሙ
የተወሰኑትን ፎቆች በእግርዎ ለመውጣት ይሞክሩ፡፡
• የህዝብ ትራንስፖርት ሲጠቀሙ ከመውረጃዎ አንድ ፌርማታ
ቀደም ብለው በመውረድ የቀረውን መንገድ በእግርዎ ለመሄድ
ይሞክሩ፡፡
• በቀርበት ወደሚገኙ ቦታዎች ለመጓዝ ሲያስቡ መኪና
ከመጠቀም ይልቅ የእግር መንገድን ይምረጡ፡፡
Photo by : Samuel Adamu

መልካም74 | 9 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ስለ ጤና እናውራ

ያስታውሱ!
• በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ ጤናዎን በእጅጉ
የተስተካከለ ያደርግልዎታል፡፡

• 30 ደቂቃውን ሙሉ በአንዴ መራመድ ካልቻሉ በቀን ሁለቴ ለ15


ደቂቃ ያህል በመራመድ ተመሳሳይ ውጤታ ማግኘት ይችላሉ፡፡

• ከሌሎች ሰዎች ጋር የእግር ጉዞ ማድረግ እንቅስቃሴውን የበለጠ


አዝናኝ ያደርገዋል፡፡
Photo by : Samuel Adamu

መልካም74 | 10 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ሔዋን

ቤተልሄም አምባቸው

በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የሴቶችን በማጠናከር በሴቶች መካከል እህትማማችነትን


ጥቃት ለመከላከል ብሎም ስለችግሩ ስፋት ግንዛቤ ማጎልበት ተግባሯ እንደሆነ በንቅናቄዋ የተዘጋጀችው
ለማስጨበጥ ብለው የተቋቋሙ በርካታ ድርጅቶች በራሪ ወረቀት ታስገነዝባለች::
አሉ:: ከነዚህም ድርጅቶች መካከል አንዷ የሴታዊት
እንቅስቃሴ ናት:: በአሁኑ ሰዓት ሴታዊት በስሯ በሁለት ዋና ዘርፎች
የተከፈሉ የተለያዩ መርሀ ግብሮችን ታካሂዳለች::
ሴታዊት የዛሬ 4 አመት ገደማ ነበር የተጠነሰሰቸው:: አንደኛዋ ክፍል ንቅናቄዋ ስትሆን ሁለተኛዋ ዘርፍ
ከመስራቾቹ መካከል አንዷ የሆነቸው ዶ/ር ደግሞ ንቅናቄዋን የምትደጉመው እና የንቅናቄዋም
ስህን ተፈራ እና ጓደኞቿ በመሆን በተደጋጋሚ የበላይ ጠባቂ የሆነችው የንግድ ዘርፏ ናት:: በንቅናቄ
በሚሰበሰቡበት ሰዓት ሴቶች ላይ ስለሚደርሱ ዘርፏ ስር የወንዶች እና የሴቶች ወርሃዊ የውይይት
ተደጋጋሚ ጥቃቶች ብሎም ችግሩን መቅረፍ ክበባት ፣ በየሁለት ወሩ የሚደረግ ወንዶችን እና
ስለሚቻልበት መንገድ ሀሳቦችን ይለዋወጡ ነበር:: ሴቶችን በጋራ የሚያሳትፍ የውይይት መድረክ
ታድያ የችግሩ ስፋት እረፍት የነሳችው እነዚህ ሴቶች እንዲሁም የማህበራዊ ሚድያ ግንዛቤ ማስጨበጫ
አንድ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ስራ መስራት እንቅስቃሴዎችን ስታደርግ በንግድ ዘርፏ ስር ደግሞ
እንዳለባቸው ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ:: በዚህም የስርዓተ ፆታ ምርምሮችን እና ስልጠናዎችን
ውሳኔአቸው መሰረት በየወሩ በወሩ በሁለተኛው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ፣
ማክሰኞ ላይ የሚውለውን የሴታዊት ክበብ መሰረቱ:: ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና ለግል ድርጅቶች
በዚህ ክበብም ማንኛዋም ሴት መሳተፍ የምትችል ትሰጣለች::
ስትሆን ሴቶችን አብዝተው የሚመለከቱ ጉዳዮች
እየተነሱ ውይይት ይደረግባቸው ነበር:: አሁንም ሴታዊት በስራ በቆየችባቸው ጊዜያት የፆታ እኩልነትን
ቢሆን ግን ይህ ክበብ በመስራቾቹ አይን በቂ ሆኖ በሚያስተምሩ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተጠምዳ
አልተገኘም:: በዚህም ምክንያት ሴታዊትን በንቅናቄቆይታለች:: ከነዚህም መካከል እንቅስቃሴዋ በተለያዩ
ደረጃ ለማዋቀር ሂደቶች ተጀመሩ:: ሴታዊትም ግዜያት ያደረገቻቸው ትምህርት ሰጪ አውደ ርዕዮች
የመጀመርያዋ የኢትዮጵያዊያን የፌሚኒስት ንቅናቄ ፣ የውይይት መድረኮች እና በተለያዩ ቦታዎች
ሆና ተመሰረተች:: የሰጠቻቸው ስልጠናዎች ለአብነት ይጠቀሳሉ::
በተለይም በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ
ሴታዊት በአሁንዋ ኢትዮጵያ የመጀመርያዋ የፆታ ትምህርት ቤቶች በንቅናቄዋ እየተሰጡ ያሉ
ንቅናቄ ስትሆን ስሟ እንደሚያመለክተው የንቅናቄዋ ስልጠናዎች ወጣቱ ማህበረሰብ የተስተካከለ የስርዓተ
አላማ በኢትዮጵያ የፆታ እኩልነትን ለማስከበር ፆታ አመለካከት እንዲኖረው በማድረግ ረገድ
የሚደረገውን ትግል ማጠናከር ነው:: ገንቢ የሆነ እየተጫወተ ያለው ሚና ቀላል የሚባል አይደለም::
ውይይት በማድረግ እና በህብረት የመስራት ባህልን በዚህ ስልጠና ውስጥ የሁለተኛ ደረጃ
መልካም74 | 11 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019
ሔዋን

ተማሪዎች በተለይም ሴቶች የተስተካከለ የራስ ግምት ርዕዩም አላማ የነበረው ሴቶችን ጥቃት በተለይም
እና የዳበረ በራስ መተማመን እንዲኖራቸው እያደረገ የመደፈርን ወንጀል ህብረተሰቡ ምክንያት ሳይደረድር
ይገኛል:: መቃወም እንዳለበት ለማስገንዘብ ነው:: ዝግጅቱ
ንቅናቄዋ ከምታደርጋቸው የንግድ ዘርፍ እንቅስቃሴ እጅግ ውጤታማ የነበረ ሲሆን በቦታው ተገኝተው
መካከል ደግሞ የጥናት እና ምርምር ስራዎች ለመመልከት የቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎችም ችግሩን
ይገኙበታል:: እነዚህን እንቅስቃሴዎች ከተለያዩ ለመቅረፍ የበኩላቸውን እንደሚያደርጉ ቃል ሲገቡ
ለጋሾች በምታገኘው የገንዘብ ድጋፍ የምታደርጋቸው ተስተውለዋል::
ሲሆን እስካሁንም ድረስ በተለያዩ የፌሚኒዝም በተጨማሪም ንቅናቄዋ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች
ርዕሶች ዙርያ የጥናት እና ምርምር ስራዎችን ስትሰራ በሚያጋጥሙዋት ግዜ ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ
ቆይታለች:: በቀጣይም ምርምሮቹን አጠናክሮ ሴቶች ማህበር ጋር በመሆን የህግ ድጋፍ እንዲያገኙ
ከመቀጠል በተረፈ ኢትዮጵያዊ የፌሚኒዝም እሴትን ስትሰራ ቆይታለች:: በአሁኑ ግዜም የራሷን ማዕከል
ለማስተዋወቅ ያለመ ዓለም አቀፍ የውይይት መድረክ በማቋቋም ከህግ ከለላ በተጨማሪ የስነልቦና ድጋፍ
በአዲስ አበባ ለማድረግ አስባለች:: የሚያገኙበትን ሁኔታ እያመቻቸች ትገኛለች::
ማንኛውም በንቅናቄዋ ውስጥ መሳተፍ የሚፈልግ
የፆታ እኩልነትን ለሰፊው ህብረተሰብ ለመስበክ ግለሰብ ወይንም ድርጅት በቀላሉ ይህንን ማድረግ
ንቅናቄዋ ከምትጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ ይችላል:: ንቅናቄዋ በቢሮዋ ውስጥ በቋሚነት
ዓውደ ርዕዮችን ማዘጋጀት ነው:: ለአብነትም ከሚሰሩ ባለሙያዎች በተጨማሪ የአባልነት ፣
ያህል ባሳለፍነው ዓመት ከስዊድን ኤምባሲ ጋር የበጎ ፈቃደኝነት እንዲሁም የተለማማጅ ሰራተኝነት
በመተባበር የተዘጋጀው እና ትክክለኛ የአባቶችን አማራጮችም አሏት:: እርስዎም ከዚህ በታች
ሚና ለማሳወቅ ያለመው “አሪፍ አባት” የተሰኘው በተጠቀሰው ድረ-ገፅ ላይ በመሄድ ንቅናቄዋን
የፎቶግራፍ አውደርዕይ አንዱ ነው:: በተጨማሪም በፈለጉት ዘርፍ እንዲቀላቀሉ እንጋብዛለን:: ፆታዊ
በፈረንጆቹ ከወርሀ ኖቬምበር አጋማሽ ጀምሮ ለ16 ጥቃት ሀገራዊ መልክ በያዘበት እና በተስፋፋበት
ተከታታይ ቀናት የቆየውን አለም አቀፍ የፆታዊ በዚህ ግዜ ለችግሩ እልባት እንሰጥ ዘንድ የእርሶ
ጥቃት ተቃውሞ ንቅናቄን ተንተርሶ የተዘጋጀው ተሳታፊነት አማራጭ የሌለው ነው::
“ምን ለብሳ ነበር?” የተሰኘ አውደ ርዕይ አዘጋጅታ
ነበር:: በዚህም አውደ ርዕይ የተለያዩ ሴቶች
የመደፈር ጥቃት በደረሰባቸው ወቅት ለብሰውት
የነበረውን ልብስ ለዕይታ አቅርባ የነበረ ሲሆን የአውደ

የሴታዊት አድራሻ
22 ማዞርያ ኮሜት ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ ፤ ቢሮ ቁጥር 303
Phone Number :+251118225451
Website : www.setaweet.com
Email : setaweetmovement@outlook.com
Facebook: www.facebook.com/setaweetmovement
Linkedin: Setaweet Movement
Instagram: Setaweet
Twitter: @setaweet1

መልካም74 | 12 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ከጀርባ ማን ነበር ?

ከቤቲ ጂ ወገግታ
አልበም ጀርባ ማን ነበር ?
ቤተልሄም አምባቸው መልካም 74፡የትምህርትህስ ሁኔታ እንዴት
ይመስላል?
በአፍሪካ ከሚደረጉ የሙዚቃ እና ሙዚቀኞች
ሽልማቶች መካከል አንዱ እና ትልቁ አፍሪማ ነው:: ያምሉ፡ የትምህርት ሁኔታዬ ሰነፍ ከሚባሉት
ይህ የሙዚቃ ሽልማት የምርጫው ሂደት ረጅም ፤ ውስጥ አልነበርኩም:: በርግጥ ብዙ አላጠናም::
ዳኞቹም አለም አቀፍ እና በዘርፉ አንቱታን ያተረፉ ጂንየስ ሆኜ ግን አይደለም:: ብቻ ትምህርት
ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የውድድሩን ሂደት እጅግ ፈታኝ ላይ እስከ ሶስት ዓመት የሙዚቃ ትምህርት ድረስ
ያደርገዋል:: ተምሬአለሁ:: ዩኒቨርሲቲ አልገባሁም እና ሙዚቃ
እንድጀምር የሆነበት አንዱም ምክንያት ያ ነበር::
ዘንድሮ በተካሄደው ውድድር ላይ የቤቲ ጂ “ወገግታ” በ1994 ዓ.ም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ጨረስኩ
አልበም በስድስት ዘርፎች ሲታጭ የዓመቱ ምርጥ ከዛም በቀጥታ ወደ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ነው
አልበም የሚለውን ሽልማት ጨምሮ በሶስት ዘርፎች የገባሁት:: ሶስት ዓመት የጃዝ ሙዚቃ ትምህርት
አሸናፊ መሆን ችሏል:: ታድያ እኛም ከዚህ ስኬታማ ቤት ውስጥ ቆይቻለሁ:: የት እንደተማርኩ መናገር
አልበም ጀርባ ያለውን ወጣት ሙዚቀኛ -ያምሉ ባልፈልግም ግን አስተማሪዎቼን ልንገርሽ:: ሄኖክ
ሞላን ይዘንላችሁ ቀርበናል መልካም ንባብ:: ተመስጌን አስተምሮኛል:: ፊሊፕ የሚባል የፒያኖ
አስተማሪም ነበረን:: በየመሀሉ ብቻ እንደ አጋጣሚ
መልካም 74፡ በመጀመርያ ያምሉ ማን ነው በሚመጡ በትልልቅ ሚዚቀኞች የመማር እድል
ከሚለው ልጀምር:: ያምሉ ማን ነው? የት ተወለደ? ነበረኝ:: በልዮ ሁኔታ ደግሞ ሰላም ፌስቲቫሎች
የት ተማረ? አስተዳደጉ ምን ይመስላል የሚለውን እኔን ፣ ኪሩቤል ተስፋዬን ፣ ሚካኤል ሀይሉን
ንገረኝ እስቲ:: ፣ አቤል ጳውሎስ ሆነን ለስድስት ወር ያህል ሳውንድ
ኢንጂነሪንግ እና ሚክሲንግ አስተምረውናል::
ያምሉ፡ ያምሉ ያደገው ወደ ጦር ሀይሎች አካባቢ ከትምህርት ባለፈ ግን ሙዚቃ በራስሽ የምታደርጊው
ነው:: ከድሮም ጀምሮ መልካም ነገሮችን የማስቀጠል ጥረት ነው:: በራስሽ በምትወስጂው ግዜ የበለጠ
፤ መልካም ያልሆኑትን ደግሞ የመለወጥ ህልም መማር ትችያለሽ:: አሁን በተለይ ግዜው ለዚህ
ያለው ሙዚቀኛ ነኝ:: በተለይም እኔ ያለሁት ሙዚቃ ምቹ ይመስላል::
ውስጥ ስለሆነ ማለት ነው:: ምናልባት የሚያውቁኝ
ሰዎች ያወቁኝ በዚህ ሶስት እና አራት ዓመት ውስጥ መልካም 74፡ እንዴት ነው ወደ ሙዚቃው
ሊሆን ይችላል:: እኔ ግን ወደ አስራ ስድስት ዓመት የገባኸው? ትምህርት ቤት ሙዚቃን ለመማር
ገደማ በሙዚቃ ውስጥ አሳልፌአለሁ:: ብዙው ከመሄድህ በፊት ምንድን ነበር ያየኸው? ምንድን ነው
ሙዚቀኛ ነው ያምሉ:: ይህን ይመስላል:: ወደ ሙዚቃው የሳበህ?

መልካም74 | 13 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ከጀርባ ማን ነበር ?
ያምሉ፡ በኛ ሀገር ሰው ጥበብን ምርጫ ሲያጣ እሰማ ነበር፡፡ የፖፕ ሙዚቃ በ90ዎቹ ይሰማ
የሚመርጠው ተደርጎ ይወሰዳል:: የኔ ግን እንደዛ የነበረ ሙዚቃ ነው፡፡ ግን እንዳልኩሽ የገባሁት
አይደለም:: ስምንተኛ ክፍል ላይ ሆኜ ፕሮዲውሰር ጃዝ ትምህርት ቤት ነው እና እኔ የምፈልገውን
መሆን እፈልግ ነበር:: ምን ማለት እንደሆነ ያኔ ሙዚቃ አልነበረም ያስተማረኝ፡፡ ያጠናሁት ፒያኖ
አላውቀውም ነበር:: ምንም አይነት የሙዚቃ ነው ግን የተለየ የፒያኖ ፍቅር ኖሮኝ አይደለም፡፡
መሳርያም አልጫወትም ግን እንዲሁ ምናልባትም ለኔ ሁሉም የሙዚቃ መሳርያ አንድ ነው፡፡ ጃዝንም
የነበርኩበት አካባቢ እና ጓደኞቼም ይሆናሉ ግን ብዙ አልረዳውም ነበር፡፡ ዝም ብዬ ጋሽ ሙላቱን
ፕሮዲውሰር እንደምሆን ለጓደኞቼ ሁሉ እነግራቸው አያለሁ ግን ከዛ የተለየ ነገር ብዙ አልነበረም፡፡ ከዛ
ነበር:: ውጪ እነ ዶክተር ድሬ ፣ ፌረል ዊሊያምስ ፣
በተለይም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከጀመርኩ በኃላ ቲምበርላንድ የተባሉ ሙዚቀኞች በጣም የገነኑበት
በጣም ለሙዚቃ ተጋለጥኩኝ:: የቤተሰቦቼን ካሴት ግዜ ነበር፡፡ እነዚህን ሙዚቃዎቸ ነበር በይበልጥ
ሁሉ እየደመሰስኩ ሌሎች ሙዚቃዎች እቀዳባቸው የምሰማው፡፡
ነበር:: በይበልጥ በዚህ ግዜ ነበር ሙዚቃ የምወደው
ነገር እንደሆነ የተረዳሁት:: ከዛም በቡድን ሆነን መልካም 74፡ ዩትዩብ ላይ ያንተን ስራዎች ስፈልግ
የተወሰነ ነገር መስራት ምናምን ተጀመረ:: ግን ከዚህ በፊት የሰራሀቸውን የመንፈሳዊ ራፕ ሙዚቃዎች
በጣም ዝንባሌዬ የተለየበት ግዜ ልክ ሁለተኛ ደረጃ አገኘሁ፡፡ ትሰማቸው የነበሩት ሙዚቃዎች ተፅእኖ
ትምህርቴን ጨርሼ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜዬ ሲደርስ ነው ወደዚህ አይነት ምርጫ የከተተህ ብለን ማለት
እናቴ ዝንባሌዬን አይታ ስለነበር አንተ ሙዚቃ እንችላለን?
ትምህርት ቤት ብትገባ ወጤታማ ትሆናለህ ብላ
አባቴን አሳመነችው እና እንደቀልድ በሚመስል ነገር ያምሉ፡ የሚገርምሽ በክርስቲያን ሙዚቃ ውስጥ
በደምብ ሙዚቃን እንድለየው ሆነ:: ብዙ አሳልፌአለሁ እና ግን በዛ ሰዓት እሰራ የነበረው
እኔ የምወደውን አይነት ሙዚቃ ነበር፡፡ በእርግጥ
መልካም 74፡ ምን አይነት ሙዚቃዎች ነበሩ ያንተ ይሄንን ብዬው አላውቅም ግን ራፕ ማድረግ በጣም
ምርጫ የነበሩት? እንደነገርከኝ የጃዝ ሙዚቃን ነው እወድ ነበር፡፡ ከዛም ኬሚ ከሚባል ልጅ ጋር
ያጠናኸው ነገር ግን ከዛ በፊት ምን አይነት ሙዚቃ ስተዋወቅ እኔ የምፈልገውን ነገር ሲሰራ አየሁት፡፡
ይስብህ ነበር? የነበረኝን ጥም ወይንም ደግሞ እኔ ባደርገው ብዬ
እመኝ የነበረውን ነገር ነው የተወጣሁበት፡፡ ያው
ያምሉ፡ በብዛት አር ኤን ቢ እና ሂፕ ሃፕ ሙዚቃችን ባልተለመደ የቤተክርስቲያ አካባቢ ሂፕ ሀፕ ሙዚቃን
ነበር የምንሰማው፡፡ በዛ ትውልድ ውስጥ እነ ሳም ሰርቻለው፡፡ ስለዚህ አዎ ልክ ነሽ፡፡
ቮድ ፣ ሀበሻ ፌኖሜኖን የመሳሰሉትን ሙዙቀኞች

መልካም74 | 14 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ከጀርባ ማን ነበር ?
መልካም 74፡ ተቀባይነቱ ግን እንዴት ነበር? ምክንያቱም
ከተለመደው የኢትዮጵያ የክርስቲያን ሙዚቃ ወጣ ብለህ ራፕ
ስታደርግ ትንሽ ተግዳሮት ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ::

ያምሉ፡ ምን መሰለሽ ኬሚ ከመምጣቱ አምስት እና ስድስት


ዓመት ቀደም ብዬ ይሄንን አይነት ሙዚቃ አስለምጄ ነበር::
እንግሊዘኛም ቢሆን አማርኛም ቢሆን እሰራ ነበር እና እንዴት
እንደዚህ ይደረጋል የሚለውን ትችት ለመድኩት::

መልካም 74፡ ግን ያለመቀበሉ ነገር እንዳለ ነው::

ያምሉ፡ እንደ እብድም እታይ ነበር:: ሰው ይቀበለኛል የሚለው


ግምት ለኔ ዜሮ ነው:: እኔ የማስብ የነበረው ለትውልዱ የሆነ
ነገርን መቀየር ብቻ ነበር:: የኬሚ አልበም ሲወጣ እነግረው
የነበረው ‘ይኸወልህ ኬሚ ብዙ ስድብ ፤ ብዙ ደስ የማይል
ነገር ሊኖር ይችላል:: ግን ይህንን የምንሰራው ስለምንወደው
ብቻ ነው:: ‘ ደግሞም እናስብ የነበረው ለሚወዱት ሰዎች
እንዲሆናቸው ብቻ ነበር:: ግን አልበሙ ሲወጣ ፍንዳታ ነበር
የሆነው:: እንኳን ስድብ ቀርቶ ተቀባይነቱ እራሱ እኛ በፍፁም
ከጠበቅነው በላይ ነበር የሆነው:: BandCamp የሚባል
ዌብሳይት ላይ ጭነነው በሶስት ቀናት ውስጥ ወደ አስራ አምስት
ሺ ሰው ሲሰማው ግርምት ነበር የሆነብን::

መልካም 74፡ በምን አይነት እድሜ ውስጥ ያሉ ሰዎች ነበሩ


የተቀበሉት? ወጣቱ? ጎልማሳው ወይስ በዕድሜ የገፋው?

ያምሉ፡ ወጣቱም ፣ ጎልማሳም በዕድሜ የገፋውም ተቀብሎት


ነበር:: ቤተክርስቲያናት ውስጥ ሁሉ ይከፈት ነበር:: ኬሚ ሁሉ
እየተጋበዘ ስራዎቹን ያቀርብ ነበር እና ስራው ይሄን ያህል ተፅዕኖ
ማምጣት ችሎ ነበር::

መልካም 74፡ ስለዚህ ያንን ከሰራህ በኃላ ሌሎች ሙዚቃዎችን


መስራት ጀመርክ ማለት ነው?

ያምሉ፡ ከዛ ፊትም እሰራ ነበር:: አንደውም ቸሊናን ካወቅሻት


ከእርሷ ጋር እሰራ የነበረው ከኬሚም በፊት ነው ግን ያው
በአንዳንድ ምክንያቶች ስራው ተቋረጠ:: ግን የቸሊና ሳይ ባይ
የሚለው ስራ ተለቆ ነበር::

መልካም 74፡ ከቸሊና በተጨማሪ ከነማን ጋር የመስራት አጋጣሚ


ነበረህ?

ያምሉ፡ አሁን ላይ ከዘሩባቤል ሞላ ጋር

መልካም74 | 15 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ከጀርባ ማን ነበር ?

መልካም74፡ ከወንድምህ ጋር ማለት ነው?


ያምሉ፡ አዎ ከወንድሜ ጋር እየሰራሁ ነው፡፡ በጣም ጎበዝ
ሙዚቀኛ ነው፡፡ በዛም ላይ እኔ እና እሱ ከወንድምነትም
ሰው
ባለፈ በጣም ጥሩ ጓደኛሞች ነን እና ይሄ ደግሞ ስራችንን በጣም
አቅልሎልናል፡፡ ዘሩ የትም ብትወስጂው ሀገሩን የሚያኮራ ፤
የማያስፍር አርቲስት ነው፡፡ በጣም ትልቅ እና ጥልቅ የሆነ
ይቀበለኛል
የሙያ ስነ-ምግባር አለው፡፡ ከሱ ጋር እየሰራሁ ነው፡፡ ሌላው
ከሀሴት አኩስቲክ የባንድ መሪ ከሚኪ ጋር አልበም ጨርሰናል፡፡ የሚለው
ዝናር ዜማዎች ፣ መረዋ ኳየር ሌላ… እንዳታጣይኝ (ሳቅ)፡፡
ብቻ ከአንጋፋም ከወጣቾቹም ጋር እየሰራሁ ነው፡፡ ቤቲ ጂም
አለች፡፡ የሷ ስራ ደግሞ አስደናቂ ነው የሆነው፡፡
ግምት
መልካም74፡ ወደ ወገግታ አልበም ልውሰድህ፡፡ ወገግታ ለኔ ዜሮ
እንዴት ነበር የተሰራው? ምን ያህል ግዜ ፈጀባችሁ? ባጠቃላይ
የነበረው ሂደት ምን ይመስላል?
ያምሉ፡ ከወገግታ በፊት ከቤቲ ጋር እንተዋወቅ ነበር፡፡
ነው::
ወደ ገፅ 20 ዞሯል

Click here

መልካም74 | 16 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


74 አረንጓዴ

የውሀ መያዣ ፕላስቲኮች አጠቃቀማችን

ምን ይመስላል?
ቤተልሄም አምባቸው


ነገር ግን በሌሎች ሀገሮች፤ኢትዮጵያን ጨምሮ
ክክለኛ የሆነ የፕላስቲክ ውሀ መያዣዎችን ማለት ነው ይህ ስርዓት ብዙም ያልዳበረ ብቻ
የማስወገድ ስርአት ጥያቄ አለም አቀፋዊ ሳይሆን በመንግስት እንዲሁም በሌሎች ድርጅቶችም
የሆነ ችግር ነው፡፡በየአመቱ በሚሊየን ቢሆን ትኩረት የተነፈገው ነው፡፡
የሚቆጠሩ ለአንድ ግዜ ጥቅም ብቻ የሚውሉ የውሀ
መያዣ ፕላስቲኮች በውቅያኖሶቻችን እና በየመሬቱ
ተጥለው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም የውሀ ፕላስቲኮች እያደገ የመጣው
መካከል ለድጋሚ ጥቅም የሚውሉት ወይንም የውሀ መያዣ ፕላስቲኮች ክምር
ሪሳይክል የሚደረጉት በጣም ጥቂት መጠን ያላቸው
ብቻ ናቸው፡፡ የውሀ መያዣ ፕላስቲኮች ችግር መሆን የሚጀምሩት
ውሀውን ከተጠቀምን በኃላ በአግባቡ ማስወገድ እና
ምንም እንኳን በሀገራችን ምን ያህል የውሀ ድጋሚ ጥቅም ላይ ማዋል ሲያቅተን ነው፡፡ምንም
ፕላስቲኮች በየግዜው እንደሚጣሉ የተደረገ ጥናት እንኳን በተለያዩ ሀገራት ውስጥ የፕላስቲክ ውሀ
ባይኖርም እያደገ ከመጣው የታሸጉ ውሀዎች መያዣዎችን ድጋሚ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚደረጉ
አቅራቢ ፋብሪካዎች ቁጥር አንጻር መጠኑ ጥረቶች ቢኖሩም ኮንቴይነር ሪሳይክሊንግ ኢንስቲትዩት
በየግዜው እያደገ እየመጣ እንደለ በቀላሉ መገመት የተባለው ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት ግን
ይቻላል:: ግሪንፒስ የተባለው አለም አቀፍ የአካባቢ 86 በመቶ የሚሆኑት የውሀ መያዣ ፕላስቲኮች
ጥበቃ ድርጅት ባደረገው ጥናት መሰረት በየቀኑ በአግባቡ እንደማይወገዱ ይልቁንም መጨረሻቸውን
በአሜሪካን ሀገር ብቻ 50 ሚሊየን የውሀ መያዣ በውቅያኖሶች እና ቆሻሻ መጣያ ባልሆኑ ስፍራዎች
ፕላቲኮች እንደሚጣሉ ገልፆ በእንግሊዝ ሀገር እንደሚያደርጉ ይገልጻል፡፡ ይህንንም ጥናቱ
ደግሞ እያንዳንዱ ቤት በአመት በአማካይ 480 በቁጥር ሲያስቀምጠው አለማችን አሁን በዓመት
የፕላስቲክ ውሀ መያዣዎችን ሲጠቀም 270ዎቹን 583 ቢሊየን ያህል የውሀ መያዣ ፕላስቲኮችን
ብቻ ለድጋሚ ጥቅም እንዲውሉያደርጋል ሲል ጥናቱ ስትጠቀም ከነዚህም መካከል 401 ቢሊየን ያህሉ
ያስቀምጣል:: ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ በስዊድን ወደ ከባቢያችን በመግባት ለብክለት ይዳርጉናል ሲል
ሀገር በጣም የተራቀቀ እና ውጤታማ የሆነ የውሀ ጥናቱ አፅንኦት ሰጥቶ የችግሩን ሥፋት ይጠቅሳል፡
መያዣ ፕላስቲኮችን ድጋሚ ጥቅም ላይ የማዋል ፡ ከዚህም ባሻገር ነገሩን የከፋ የሚያደርገው እነዚህ
ስርዓት ከመኖሩ የተነሳ ጥቅም ላይ ውለው የተጣሉ የውሀ መያዣ ፕላስቲኮች ለመበስበስ 700 ዓመታትን
የውሀ ፕላስቲኮችን ከሌሎች ሀገሮች እስከመግዛት መጠየቃቸው ነው፡፡
እንደደረሱ ጥናቱ እንዲሁ ያትታል፡፡

መልካም74 | 17 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


74 አረንጓዴ
በውሀ መያዣ ፕላስቲኮች ውስጥ ያሉ
የአደገኛ ኬሚካሎች ጥርቅም
የውሀ መያዣ ፕላስቲኮችን ለመስራት የምንጠቀምባቸው
ኬሚካሎች እጅግ አደገኛ እና በሰዎች እና በእንስሳት
ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳትን የሚያደርሱ ናቸው፡፡
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እነዚህን የውሀ መያዣዎች
ለማምረት በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለው ፖሊካርቦኔት
የተባለ ኬሚካል በቆይታ ቢስፌኖል - ኤ የተባለ
አደገኛ ኬሚካል እንደሚያመነጭ እና ይህም ኬሚካል
በሂደት ይዞት ወዳለው ውሀ በመስረግ ከዛም ውሀውን
ወደሚጠጣው ሰው ሰውነት ውስጥ በመግባት ከፍተኛ
ለሆነ የጤና መዛባት ይዳርጋል፡፡

እንደ healthnews.org የተባለው ድረ-ገፅ ገለፃ ይህ


ኬሚካል የሰው ልጆችን ሆርሞኖች ይዘት ከመቀየር አንስቶ
ሌሎች ከባድ የሆኑ የጤና እክሎችን ያስከትላል፡፡
የሰው ልጆችን ጤና ከመጉዳትም ባሻገር የፕላስቲክ ውሀ
መያዣዎች በአግባቡ ካልተወገዱ በአካባቢያችን ያሉ
እንስሳትን በመጉዳት እስከ መመናመን ሊያደርሳቸው
ይችላል፡፡

የውሀ መያዣ ላስቲኮችን እንዴት በድጋሚ

ጥቅም ላይ እናውል?
አንዱ የውሀ መያዣ ፕላስቲኮች በረከት እንደገና ጥቅም
ላይ የማዋል እድል መኖሩ ነው፡፡ በአለም ላይ ድጋሚ
ጥቅም ላይ ከሚውሉ ነገሮች መካከል ከወረቀተ እና
አሉሚንየም በመቀጠል የፕላስቲክ ውሀ መያዣዎች
በሶስተኛ ደረጃ ይቀመጣሉ፡፡ ድጋሚ ከተፈጩ እና
ከኬሚካል ጋር ከተዋሃዱም በኃላ ለጫማዎች ፣
ለሻንጣዎች ፣ ለልጆች መጫወቻ ፣ ለመኪና አካላት
፣ ለልብስ አካላት እንዲሁም ለሌሎች የእለት ተዕለት
መገልገያ እቃዎች ጥሬ እቃነት ይውላሉ፡፡

በሀገራችንም እነዚህን የውሀ መያዣ ፕላስቲኮች


ፈጭተው ለዳግም ጥቅም እንዲውሉ በጥሬ እቃነት
የሚያቀርቡ ድርጅቶች ቢኖሩም ካለው የላስቲኮች
ብዛት እና እያስከተለ ካለው የአካባቢ ብክለት አንፃር
ቁጥራቸው እምብዛም ነው፡፡

ባለሀብቶችም ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም


አንደኛ ቀላል በሆነ መንገድ ገንዘብ ማግኘት ሲችሉ
ሁለተኛ ደግሞ የአካባቢን ብክለት ከመቀነስ አንፃር
የሚኖራቸው አስተዋፅኦ እጅግ በጣም ትልቅ
እንደሚሆን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

መልካም74 | 18 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


74 አረንጓዴ

ለተጠቃሚዎች እና ለአምራቾች

አማራጭ ሀሳብ
• የጠርሙስ ማሸጊያዎችን እንደ አማራጭ እንጠቀም፡፡የጠርሙስ ማሸጊያዎች ለማጽዳት ቀላል
ከመሆናቸውም ባሻገር ከአንድ ግዜ እጥበት በኃላ ምንም አይነት መርዛማ ኬሚካል ሳያመነጩ ለጥቅም
መዋል ይችላሉ፡፡ በተደጋጋሚ እስከ መቶ እጥበት ድረስ ብንጠቀምባቸውም ይዘታቸውን ሳይቀይሩ
ስለሚያገለግሉን የአካባቢን ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር ለተጠቃሚውም ጤና እጅግ አስተማማኝ
አማራጮች ናቸው፡፡ ከዚህም ባለፈ በውስጣቸውየተቀመጡትን ፈሳሾች ሽታም ሆነ ጣዕም በምንም
መልኩ አይቀይሩም፡፡
• በቤትዎ ውስጥ ውሀን ሲጠቀሙ አልያም የሬስቶራንት እና ምግብ ቤት አገልግሎት ሰጪ ከሆኑ ሁልግዜ
የታሸገ ውሀን ከማቅረብ ይልቅ የቧንቧ ውሃን እንደ አማራጭ ይጠቀሙ፡፡ ወጪን መቆጠብዎ እንዳለ
ሆኖ ለአካባቢያችን ደህንነትም የራስዎን የማይናቅ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወይም በስራ ቦታዎ በሚውሉበት ግዜ ለአንድ ግዜ ጥቅም
ብቻ የሚውሉ የውሀ ፕላስቲኮችን ከሚጠቀሙ ይልቅ ለተደጋጋሚ ይቅም የሚውሉ የውሀ መያዣዎችን
በመጠቀም ውሀን ከቤትዎ ይዘው ቢሄዱ የተሻለ ጥቅም ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ከዛም ባለፈ የታሸገ
ውሀን ለመግዛት የሚወስዱትን ጊዜ እና ገንዘብ ይቆጥባሉ፡፡ደግሞም የፕላስቲክ ውሀ መያዣዎች
ውስጥ ካሉ አደገኛ ኬሚካሎች ራስዎን ያድናሉ፡፡
• የሬስቶራንት እና የምግብ ቤት ባለቤት ከሆኑ እና ድርጅትዎ የታሸጉ ውሀዎችን ማቅረቡ የግድ ከሆነ
የተስተካከለ እና እነዚህን የውሀ መያዣ ፕላስቲኮች በአግባቡ ለማስወገድ የሚረዳ የተዘጋጀ ማስወገጂያ
ቦታ ማዘጋጀትዎን በመጀመርያ እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ ከዛም በተረፈ እነዚህ ፕላስቲኮች ለድጋሚ ጥቅም
የሚያውሉ ድርጅቶች ጋር ህብረት በመፍጠር ተጨማሪ የገቢ ምንጭን መፍጠር ይችላሉ፡፡
• የታሸጉ ውሃዎችን ስንከፍት ከላይ ክዳኑ ላይ የምናገኘውን የማሸጊያ ፕላስቲክ በየመንገዱ አይጣሉ፡
፡ ይልቁንም ማሸጊያውን አጣጥፈው በውሀ መያዣው ወገብ ላይ ወዳለው የውሃውን ስም ወደያዘው
ፕላስቲክ ውስጥ ይክተቱት፡፡ በዚህ ሁኔታ ከውሀ ፕላስቲኩ ጋር ብሮ በቀላሉ ሊወገድ ይችላል፡፡
ያም ደግሞ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ይረዳናል፡፡

መልካም74 | 19 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ከጀርባ ማን ነበር ? መልካም 74፡ አብራችሁ የሰራችሁት ስራ ነበር ማለት ነው?

ያምሉ፡ ከዛ በፊት አልነበረም:: ቤቲ እረፍት የማታውቅ ሰው

ለባህላዊ ናት:: እንደ ማሽን ነው የምትሰራው እና የመጀመርያ አልበሟ


ከወጣ በኃላ ቶሎ ብላ ሁለተኛ ስራ መስራት ትፈልግ ነበር::
ስለዚህ ሚካኤል ሀይሉ ጋር ሄዳ ስላላት ሀሳብ ስታዋራው “የምር
ሙዚቃ እና ሙዚቃ መስራት ከፈለግሽ ያምሉ የሚባል ልጅ አለ እሱ ጋር ሂጂ”
ይላታል:: እሷም ታውቀኝ ስለነበር ደወለችልኝ:: ዝም ብለን ሁለት
ለባህላዊ ሶስት ዘፈን ሰራን:: ሁለቱን ወሰደችው ግን አልወጣም::

የሙዚቃ መልካም 74፡ አልበሙ ውስጥም የለም?

መሳርያዎች ያምሉ፡ አልበሙ ውስጥም የለም:: ግን አልበሙን ስንሰራ


ምን አሰብን እሷም ፣ እኔም የመጣንበት መንገድ አለ:: ቤቲ

የተለየ አዘፋፈኗን ካየሽው ጠንከር ብሎ ልክ እንደነ አሪታ ፍራንክሊን


አይነት ዘይቤ ነው ያላት:: እኔ ደግሞ ከድሮ ጀምሮ ለባህላዊ
ሙዚቃ እና ለባህላዊ የሙዚቃ መሳርያዎች የተለየ አትኩሮት ነበረኝ
አትኩሮት እና አልበሙን ስንሰራ እነዚህን ሁለቱን አንድ ላይ ለማካተት አስበን
ነበር የሰራነው:: ስራውን ስንጀምረው ግን በምንፈልገው መልኩ
ነበረኝ የባህል ሙዚቃ ተጫዋች ማግኘት ትንሽ ተቸግረን ነበር::
የሆነ ግዜ ከጓደኛዬ ጋር ሆነን ፈንድቃ ሄድን እና ሀዲንቆን ማሲንቆ
ሲጫወት አየሁት:: ስራውን በጣም ስለወደድኩት አናገርኩት::
እሱም የተለያዩ ሙዚቃዎችን መሞከር ይወዳል፤እኔም የለመድኩት
ነው ስለዚህ ማሲንቆዋን አንደ ቫዮሊን ፣ እንደ ቼሎ ፣ እንደ ጊታር
እያደረግን ሰራንባት:: ዋሽንት ደግሞ ጣሰው ነበር የተጫወተው::
ከበሮ መሳይ ተጫወተልን:: በተረፈ ወገግታ ላይ ከአንድ ዘፈን
ውጪ ግጥሙንም ፣ ዜማውንም ፣ ማቀናበሩንም እኔ ነበርኩ
የሰራሁት:: ሙዚቃዎቹን ስንቀዳ አንዳንዶቹን ሁለት እና ሶስት ግዜ
ብቻ ነበር መቅዳት ያስፈለገን:: ቤቲ በጣም ጎበዝ ዘፋኝ ናት::
በጣም ቶሎ ነገሮችን ትይዛለች ስለዚህ እሷ ምንም አላስቸገረችኝም
ነበር:: በ6 ወር ውስጥ ሁሉንም ነገር መጨረስ ችለን ነበር::

መልካም 74፡ አልበሙ በዚህ ደረጃ ስኬታማ ይሆናል የሚል


ግምት ነበረህ?

ያምሉ፡ በፍጹም አልነበረኝም:: ያው በእኛ ማህበረሰብ ለነገሮች


የሚኖርሽ አጠባበቅ የወረደ እንዲሆን ያደርግሻል:: በእርግጥ ጥሩ
አይደለም ግን የወረደ አጠባበቅ እንዲኖረኝ አድርገውኝ ነበር::
ስለዚህ ብዙ ስኬት ይኖረዋል የሚለው ነገር ውስጤ አልነበረም::
ጥልቅ ስሜት የሚለው ሙዚቃ ላይ ያለው መልዕክት እንዲያውም
ይሄ ነበር::

መልካም74 | 20 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ከጀርባ ማን ነበር ?
በዛ ላይ ሚድያው ሙዞቃውን ለማጫወት ቢይዝ ነው:: ቅስቀሳው ያስፈለገበት
ትንሽ ይዟቸው ነበር፡፡ ምን አልባት ምክንያት ደግሞ እኛ ምረጡን ብለን
ከተለመደው ወጣ ያለ ስለሆነ ሊሆን ስንቀሰቅስ አፍሪማ የሚባውን ነገር
ይችላል፡፡ ግን አልበሙ አፍሪማን እናስተዋውቅላቸዋለን:: ያ ነው እንጂ
ካሸነፈ በኃላ ሁሉም የሬድዮ ጣቢያዎች ዋናው የምርጫ ሂደት እንዳልኩሽ
ሙዚቃውን ያጫውቱት ነበር፡፡ በዳኞች ጉባኤ ነው የሚደረገው::

መልካም 74፡ አፍሪማ ላይ የነበረውስ መልካም 74፡ በሽልማቱ ላይ የነበሩት


ነገር እንዴት ነበር? በ6 ዘርፍ መታጨት ሰዎች እርግጠኛ ነኝ ሽልማቱን ካሸነፋችሁ
ትልቅ ውጤት ነው:: ማሸነፉ ደግሞ በኃላ ኢትዮጵያ የሚለውን ነገር ፤
ሌላ ስኬት ነው:: እጩ መሆናችሁን የኢትዮጵያ ሙዚቃ የሚባለውንም
ስታውቁ እናሸንፋለን ብላችሁ አስባችሁ የማወቅ አጋጣሚው ተፈጥሮላቸዋል::
ነበር? ከዛ በፊትስ ስለ ሙዚቃችን እና
ሌላው ቀርቶ ፤
ያምሉ፡ እንዳልኩሽ ነው:: ግምታችን አርቲስቶቻችን ምን አይነት አመለካከት
በጣም የወረደ ነበር:: ሀገር ውስጥ እንዳላቸው ለመገምገም ሞክረሀል?
እንኳን
የነበረው አቀባበል ተፅእኖ ስላደረገብን አርቲስቶቻችንንስ ያውቋቸዋል? ሙዚቃችንን
ውጤቱን ብዙ አልጠበቅነውም ነበር:: የነፃነት
አኔ በበኩሌ በጭራሽ አልገመትኩም ያምሉ፡ በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው:: ታሪካችንን
ነበር:: በተለይም አብረውን ታጭተው የሚገርምሽ በቆየንባቸው ቀናት በሙሉ
አያውቁትም::
የበሩትን ባለሙያዎች ትልልቅነት እና የማገኛቸውን ሰዎች ስጠይቅ ነበር እና
ያላቸውን አለምዓቀፋዊ ተቀባይነት ምንም ስለኢትዮጵያ የሚያውቁት
ሳይ በቃ ማሸነፍን አላሰብኩም ነበር:: ነገር የለም:: ምንም! ትልልቅ
የውድድሩን ትልቁ ሽልማት የሆነውን የምንላቸውን አርቲስቶቻችንን እንኳን
የዓመቱ ምርጥ አልበም የሚለውን አያውቋቸውም:: ያሰደነግጣል
ሽልማት ስናሸንፍ ህልም ውስጥ ያለሁ በጣም:: ሌላው ቀርቶ እንኳን
ነበር የመሰለኝ:: አይቀሰቅሱኝም እንዴ ሙዚቃችንን የነፃነት ታሪካችንን
ሁሉ ብዬ ነበር:: አያውቁትም:: ይሄ ደግሞ የማንም
ድክመት ሳይሆን የራሳችን ነው::
መልካም 74፡ የአሸናፊዎች ምርጫ
ግን የነበረው እንዴት ነበር? በተመልካች መልካም 74፡ ታድያ ይህንን የሰፋ
ድምጽ ነው ወይንስ ሌላ መንገድ አለው? ክፍተት ለመሙላት ምን አስበሀል?
እናንተም የምረጡን ቅስቀሳ ስታደርጉ
ነበር እና ቅስቀሳቀው ያመጣው የውጤት ያምሉ፡ ሌላው አለም ሙዚቃ ይሁን
ለውጥ አለ? እንጂ ቋንቋው ምንም ይሁን ምን
ይሰሙታል:: ስለዚህ የኢትዮጵያንም
ያምሉ፡ ምርጫው በዳኞች ጉባኤ ነው ሙዚቃ አለም ሊረዳው በሚችለው
የሚደረገው:: ዳኞቹ ደግሞ ሶኒን እና መልኩ ዘመናዊ አድርጌ ግን ደግሞ
ዩኒቨርሳል ሚዩዚክን ከመሳሰሉ ትልልቅ ኢትዮጵያዊ ቃናውን ሳይለቅ የመስራት
ካምፓኒዎች የተወጣጡ አፍሪካዊ ማንነት ሀሳብ አለኝ የሰራኃቸውም አሉ::
ያላቸው ባለሙያዎች ናቸው:: ዋናው የራሴንም ስሜት የማወጣበቅ አይነት
ያ ነው:: የህዝብ ድምፅ ምናልባት የኢትዮጵያ ሙዚቃ ያካተተ የራሴን
ከጠቅላላው ውጤት ሀያ በመቶ አልበም የመስራት ሀሳብ አለኝ::
መልካም74 | 21 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019
ከጀርባ ማን ነበር ?

መልካም 74፡ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ማለት ግን መልካም 74፡ በመጨረሻ ማመስገን የምትፈልገው
ምንድን ነው? የትኛውን ሙዚቃ ነው የኢትዮጵያ ሰው፤ ማስተላለፍ የምትፈልገው መልዕክት ካለ
ብለን የምንጠራው? ኢትዮ ጃዝን ምናልባት እድሉን ልስጥህ::
ኢትዮጵያዊ ማለት አንችል ይሆናል:: ግን ሌላውስ ያምሉ፡ መጀመርያ ሙዚቃ መስራት ስጀምር
የሙዚቃ አይነት? ምክንያቱም በየአካባቢው ብንሄድ አሴምብልድ የሆነ ኮምፒውተር የሰጠኝ ምንተስኖት
ኢትዮጵያዊ የሆኑ ሙዚቃዎች አሉ:: ይህ ሁሉ የሚባል ልጅ ነበር:: አሁን በርግጥ ብዙ አንገናኝም ግን
ህብር ባለበት የትኛውን ነው የኢትዮጵያ ሙዚቃ እሱን ማመስገን እፈልጋለሁ:: ሌላው ሙዚቃዎችን
ብለን የምንጠራው? ከኢንተርኔት እያወረደ ያመጣልኝ የነበረ እስራኤል
የሚባል ጓደኛዬ ነበር:: እሱንም እጅግ በጣም
ያምሉ፡ ምናልባት ለነጮቹ መጀመርያ የሰሙት አመሰግናለሁ:: ትንሽ ይመስላል ግን ለኔ በግዜው
የኢትዮጵያ ሙዚቃ ሊሆን ይችላል:: ለኛ ግን በጣም የማይታመን ነገር ነበር:: ሌሎችም ልጆች አሉ
እንዳልሽው በጣም ብዙ ያልነካናቸው ሙዚቃዎች እንደዚህ ይረዱኝ የነበሩ እነሱንም አመሰግናለሁ፡፡
አሉ:: በጣም ብዙ ልንሰራቸውና ልናጠናቸው ቤተሰቤን ለነበራቸው ድጋፍ በጣም አመሰግናለሁ::
የምንችላቸው ሙዚቃዎች አሉ:: ስለዚህ የነዛን ሁሉ ባለቤቴ አይዳ ለምታደርግልኝ ነገር ሁሉ በጣም
ህብር የኢትዮጵያ ብለን ልንለው እንችላለን:: እኔ አመሰግናለሁ:: ቤትሽ ሰላም ሲሆን ውጪሽ በጣም
ራሴ ብችል እና በየቦታው እየሄድኩ ሙዚቃዎችን አሪፍ ይሆናል እና በህይወቴ ትልቅ ቦታ አላት::
ብሰማ ፤ ብቀዳ በጣም ደስ ይለኝ ነበር:: ማስተላለፍ የምፈልገው ነገር ፤ የተጀመረውን
ነገር ቢቻል ማገዝ ካልሆነ ዝም በማለት የራሳችንን
መልካም 74፡ ከዚህ ቀጥሎስ ከያምሉ ምን አይነት ሀላፊነት እንወጣ ፤ ይሄ እንደ ሀገር ነው:: እንደ
ስራዎችን እንጠብቅ? አሁንስ ምን እየሰራህ ነው ሙዚቀኛ ደግሞ ቆሽሾ ያለውን የሙዚቃ ስነምግባር
ያለኸው? እባካችሁ እናፅዳው:: እጅግ ይቃማል ፤ እጅግ
ያምሉ፡ አሁን የቸሊና አልበም ወቷል:: የሚኖረውን ይጠጣል ፤ ራሳችንን ጎድተን ሌሎችን ታናናሾቻችንን
ተቀባይነት አንግዲህ አሁንም መገመት አልችልም:: ደግሞ ወደ የማይፈልግ ነገር ውስጥ አንግፋቸው::
ግን ጥሩ ስራ ሰርተናል:: አሁንም አዲስ ነገር
ለማሰማት ሞክሬአለሁ:: በሙዚቃ መሳርያ እነ መልካም 74፡ ያምሉ ያለህን ግዜ አጣበህ
ዘሩባቤል ሞላ ፣ ጆርጋ መስፍን ፣ ሄኖክ ተመስገን ጥያቄዎቼን ለመመለስ ፈቃደኛ ስለሆንክ እጅግ አድርጌ
ተሳትፈውበታል:: ሌላ ፌላ ከምትባል ልጅ ጋር አመሰግናለሁ:: መልካሙን ሁሉ እመኝልሀለው::
እየሰራን ነው:: የዘሩም አልበም አለ:: እነዚህን
የመሳሰሉ ስራዎች እየሰራሁ ነው:: ያምሉ፡ እኔም በጣም አመሰግናለሁ::
የኛ

አዲስ ዓመት
በወላይታ - ጊፋታ
ቤተልሄም አምባቸው

በሀገራችን ኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ ብሄሮች ፤ ጊፋታ ዋናው በዓል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አከባበሩም
ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መካከል አብዛኞቹ የራሳቸውቢሆን በወጪ በኩል ኪስን መፈተሹ አይቀርም::
የሆኑ የዘመን መለወጫ በዓላት አሏቸው:: ምንም ታድያ ይህንን በዓል ደማቅ እና ሙሉ ለማድረግ
እንኳን አብዛኞቹ በዓላት ብዙም የግዜ ልዩነት የዘንድሮ ጊፋታ ሲከበር ለመጪው ደግሞ ቁጠባ
ሳይኖራቸው የሚከበሩ ቢሆኑም ሁሉም ግን እንደሚጀመር ይነገራል:: አባቶች፣እናቶች እና
የየራሳቸው የሆነ የተለያየ የአከባበር ስነ-ስርዓት
ወጣቶች በተሰጣቸው የስራ ድርሻ መሰረት ስራቸውን
አላቸው:: ለዛሬም ወደ ደቡባዊቷ የሀገራችን ክፍል
የሚያከናውኑ ሲሆን ለስራቸውም የሚጠየቀውን
ተጉዘን የወላይታን የዘመን መለወጫ በዓል ጊፋታንወጪ የመቆጠብ ሀላፊነት አለባቸው :: በየፊናቸው
አናስቃኛችኃለን፡፡ ሁሉም ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ:: የጊፋታ እርድ
ተደርጎ እንዳለቀ በታረደው በሬ እርጥብ ቆዳ ላይ
የወላይታ ህዝብ የፀሀይን ዙረት ተከትሎ ቀናተን ብር በማስቀመጥ ለሚቀጥለው ጊፋታ አባቶች
እና ወራትን ቆጥሮ አመት ሲሞላው እና “የኮርማ ቁጠባቸውን ይጀምሉ::
ጪሻ”አበባ ሲያብብ ጊፋታን አክብሮ ሌላ ዙረትን
፤ ሌላ ዓመትን ይቀበላል:: የጊፋታ በዓል የእንሰት ተክል ለወላይታ ህዝብ ትልቅ ትርጉም
ከሚሸኘው አመት ሶስት ቀናትን ከመጪው ደግሞ ያለው ነው፡፡ ለእንሰት ያላቸውን ክብር በተለያየ
አራት ቀናትን በማዋሀድ በመሀል በሚገኘው እሁድ መልኩ ሲያሳዩ በተለይም “የእንሰት ዘር የሆነው ቆጮ
ይከበራል:: ጊፋታ ማለት በኩር ማለት ሲሆን ከሚበተን የከብት ዘር የሆኑት ጥጆች ቢበተኑ ይሻላል”
አዲሱ አመት ሲጀምር ያለው የመጀመርያ ወር የሚለው የወላይታ አባባል ለተክሉ ያላቸውን አቻ
በወላይታ ባህል ጊፋታ ተብሎ ይጠራል:: ሌላው የሌለው ክብር ያሳያል:: ታድያ በዚህ የበዓላት በኩር
ደግሞ በወላይታ ብሄረሰብ ከሚከበሩ የተለያዩ በሆነው በጊፋታም አብዛኛው ምግብ የሚዘጋጀው
በዓላት መካከል ዋናው እና በኩሩ ጊፋታ ስለሆነ ከዚሁ ከእንሰት ተክል ነው:: ምንም እንኳን እንሰቱን
በዓሉ በኩር በዓል ይባላል:: ወንዱ ይትከለው እንጂ ለጊፋታ የሚሆን እንሰትን
የመለየቱን ተግባር የምትከውነው ሴቷ ናት:: ጊፋታ
ሊከበር ሁለት ወር ሲቀረው እንሰቱ ተለይቶ ተቆርጦ
ይፋቃል::

መልካም74 | 23 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


የኛ
ታድያ የተፋቀው እንሰት እንዲሁ አይቀመጥም ባህል ነው::
አስፈላጊ የሆኑት ቅመማት ጋር ከተቀላቀለ በኃላበጊፋታ ሰው ብቻ ሳይሆን እንስሳውም ጠግቦ
ንፋስ እንዳይገባበት ተደርጎ በእንሰቱ ቅጠል መዋል አለበት:: ስለዚህም ከቀናት በፊት
ታስሮ እንዲበስል በጉድጓድ ውስጥ ይቀበራል:: ለእንስሳት የሚሆንን የእርጥብ ሳር መኖ አባ
በዚህ መልክ ተዘጋጅቶ የተቀመጠው ቆጮ ወራው እና ወንድ ልጆቹ አጭደው ይከምራሉ::
ጊዜው ደርሶ ከወጣ በኃላ ለጊፋታ የቁርጥ ሳሩ ራሱ ለጊፋታ የሚታጨድ ተብሎ “ቆሮ”
ማባያ ሆኖ ይቀርባል:: የሚል ስያሜ ይሰጠው እና ተጠብቆ እንዲቆይ
ይደረጋል:: የተበላሸ እና መታደስ ያለበት ቤት
ከእንሰተ ቀጥሎ ለጊፋታ በከፍተኛ ሁኔታ ካለም ጎረቤት ተሰብስቦ በደቦ ቤቱን ያድሳል::
ፍጆታ ላይ የሚውለው ቅቤ ነው:: ቅቤውን ለጊፋታ አሮጌ እና ውበት የሌለው ነገር በፍፁም
የማዘጋጀት ሀላፊነቱ በሴቷ ጨንቃ ላይ የወደቀ አይታሰብም::
ነው:: ለዚህም ደግሞጊፋታ ከመድረሱ
ሶስት እና አራት ወራት ቀደም ብሎ ሴቶች ሌላው የበዓሉ ማድመቂያ “ጎልያ” ነው::
የቅቤ እቁብ መጣል ጀምራሉ:: በእቁቡ “ጎልያ” እንደ ደመራ የተደረደረ እንጨት
የተሰበሰበውንም ቅቤ ለጊፋታ በዓል ለሚዘጋጁ ማለት ነው:: ለዚህ ዝግጅት የሚሆነውን
ምግቦች ማጣፈጫነት ብሎም እንደ ዋና እንጨት ወጣቶች ወደ ጫካ በመግባት ቆርጠው
የምግብ መስርያ ግብአትነት ይጠቀሙታል:: ያመጡና ይደምሩታል:: ከዛም ግዜው ሲደርስ
ሌላው በጊፋታ በዓል ከገበታ የማይጠፋው “ጎልያውን” በእሳት ለኩሰው በዙርያው
ዳታ ነው:: ይህ ከበሰለ የእርጥብ ሚጥሚጣ እየተሽከረከሩ ጭፈራውን ያስነኩታል::
ዛላ የሚዘጋጀው ዳታ ዝግጅቱ እንደሌላው ነገር ይህ ጨዋታ ለወንዶች ብቻ የተተወ ነው::
ሁሉ ከወር በፊት ይጀምራል:: እማ ወራዋ ሴቶቹም ደግሞ የራሳቸው ወግ አላቸው::
በየግዜው ትንሽ ትንሽ እየሰራች እስከ በዓሉ በእርድ ቀን እንሾሽላ የሚሞቁበት ስነ-ስርዓት
መዳረሻ ድረስ ታጠራቅመዋለች:: የበዓሉ ይከናወናል:: ይህንንም ስርዓት በእናት መሪነት
ቀንም ከቁርጥ ስጋ ጋር አብሮ ይቀርባል:: ነው የሚከውኑት:: የአንድ ሰፈር ሴቶች አንድ
ከበቆሎ እና ከገብስ ብቅል የሚሰራው ቦርዴ ላይ ይሰበሰቡ እና ከበሮ እየመቱ ፣ እየዘፈኑ
ደግሞ የጊፋታ በዓል ልዩ መጠጥ ነው:: እና እየተጫወቱ እንሾሽላውን ይሞቃሉ::
የእንሾሽላው በእጅ ላይ ደምቆ መያዙ ወይም
ወላይታ በጊፋታ ባዶ ማጀትን ፣ ጥልን መፍዘዙ ለወላይታ ሴት የራሱ ትርጉም
እና ኩርፊያን አይፈልግም:: ማጀቱንም አለው:: እጇ ላይ እንሾሽላ የደመቀላት ሴት
ሙሉ ለማድረግ ለበዓሉ ወር ሲቀረው ጎበዝ እና ባለሙያ ስትባል ያልደመቀላት
ሸመታው ይጦፋል፡፡”ሀሪ ያይቆ”፣ ደግሞ ሰነፍ ተደርጋ ትቆጠራለች:: የእንሾሽላ
“ቦቦዳ”፣”ቦሻጊያ”እና “ቃኤ”ገበያዎችም መሞቁ ስርዓት በጨዋታ የተሞላ ነው::
ቀናቸውን እየጠበቁ መዋላቸውን ይቀጥላሉ:: የተሰበሰቡት ሴቶች በየተራ እየተነሱ ዘፈናቸውን
ወላይታም የበዓላት በኩር የሆነውን ጊፋታ እየዘፈኑ ፤ ከበሮአቸውን እየደለቁ ሲጫወቱ
ከነዚህ ገበያዎች በገዛው አስቤዛ አድምቆት ያመሻሉ::
ያሳልፋል:: የተጣላም ሰው ካለ ለጊፋታ በጊፋታ ዘመድ ወዳጅን ብሎም ያሳደጉ
ማዕድ ከመቅረቡ በፊት ከተጣላው ሰው ጋር ወላጆችን እንኳን አደረሳችሁ ማለት በወላይታ
እርቀ ሰላም ማውረድ አለበት:: ነፍስ ያጠፋ ወግ ነው:: ማንም የወላይታ ተወላጅ የትም
እንኳን ይቅርታውን የሚያገኘው በጊፋታ ነው ቢሆን የት ቢያንስ ለጊፋታ ሀገሩ ገብቶ ፤
ይባላል:: ይህ ዘመን ተሻግሮ እዚህ የደረሰ በዓሉን አክብሮ ከዛም ምርቃትን ተቀብሎ
የወላይታ አኩሪ የሰላም ወዳድነት ማሳያ የሆነ ወደመጣበት መመለሱ ደንብ ነው::

መልካም74 | 24 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ዘመድ ለመጠየቅ ሲኬድ ታድያ በጊፋታ ብቻ የሚበቅለውን ኮርማ ጪሻ አበባ ይዞ “ሀሹ ሳሮ ጋጢስ” -
እንኳን አደረሳችሁ መባባል በወላይታ የተለመደ ነው::

ጊፋታ ከመድረሱ ቀደም ብሎ ባለው ማክሰኞ ጀምሮ ወንዶች እና ሴቶች አብረው የሚጫወቱት ጨዋታ ወይም
“ገዜ” መቆም ይጀምራል:: ይህ ለዚህ በዓል ብቻ የሚደረግ ልዮ ጨዋታ ነው:: ይህ ጨዋታ ወጣቶች
የሚተጫጩበትም መድረክ ነው:: ያላገባች ሴት ወደዚህ ጨዋታ ስትሄድ ሎሚ ይዛ ትሄዳች:: ከዛም
አይኗ ባረፈበት ፤ ልቧ በከጀለው ጉብል ፊት ለፊት ሎሚውን ትጥለዋለች:: ያ ማለት ወድጄሀለው ማለት
ነው:: ወጣቱም ጎበዚቷን ከከጀላት በወላይታ ወግ እና ልማድ መሰረት ለሰርግ መዘጋጀት ይጀምራሉ::

ጊፋታ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይከበራል:: በዚህ በዓል ወቅት ምንም አይነት ስራ አይሰራም:: ሁሉም
ስራ በዓሉ ከመድረሱ በፊት ተጠናቆ ስለሚያልቅ 15ቱን ቀን ሙሉ በገዜ ቦታዎቸ እየተዘዋወረ ወላይታ
ሲጨፍር እና ሲደሰት ፤ ለመጪውም አመት የሚሆነውን የስራ ብርታት ሲሰንቅ ጊዜውን ያሳልፋል:: በዚህ
መልኩ የጊፋታ አከባበር ከተጠናቀቀ በኃላ “ጊፋታ በሰላም ሄደሽ በሰላም ተመለሽ:: አሮጌውን አመት
ጥለን አዲስን ተቀብለናል” ብለው የተቃጠለ እንጨት ይወረውራሉ:: ይህ ማለት የዘንድሮው ጊፋታ በዓል
አከባበር አለቀ ማለት ነው::

የጊፋታ በዓል አከባበር የወላይታን ማንነት ፣ ባህሉን ፣ ወጉን ፣ አብሮ የመኖር ልምዱን፣ መቻቻሉን
፣ ጭፈራውን ፣ ምግቡን ፣ አልባሳቱን ሁሉ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ድንቅ ሁነት ነው::

Click here

መልካም74 | 25 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ስራ ፈጠራ

ቲ.ኢ.ኤ.
ኮንሰልታንሲ ኤንድ ትሬይኒንግ

ቤተልሄም አምባቸው

ነገር ግን ይላል ኤባ ትዝብቱን ሲቀጥል


ቲ.ኢ.ኤ ኮንሰልታነሲ ኤንድ ትሬይኒንግ የዛሬ
“ነገር ግን ድርጅቶች ሌሎች ጉዳዮች ላይ
ሰባት አመት ገደማ ነበር በሶስት የስራ ሸሪኮች
የሚያወጡትን ወጪ ግማሽ ያህል እንኳን
ህብረት የተቋቋመው:: ድርጅቱ ሲቋቋም ለተለያዩ
አውጥተው ሰራተኞቻቸውን ማብቃት ላይ ቢሰሩ
ድርጅቶቸ የስራ ሂደት ስልጠናዎችን እና የማማከር
ውጤቱን በአጭር ግዜ ሊያዩት ይችላሉ::”
አገልግሎት መስጠትን አላማ አድርጎ ነበር ስራ
የጀመረው:: ስራውን ስንጀምር እጅግ ብዙ ቲ.ኢ.ኤ ኮንሰልታነሲ ኤንድ ትሬይኒንግ በስራ
ከባድ ውጣ ውረዶችን ማለፍ ነበረብን የሚለው በቆየባቸው ግዜያት ከተለያዩ ድርጅች ጋር
ከመስራቾቹ አንዱ የሆነው ኤባ ተስፋዬ ስራውን የመስራት አጋጣሚዎች ነበሩት:: የስልጠና እና
ሲጀምሩት ድርጅቶችን አሳምኖ የአገልግሎቱ የማማከር አገልግሎት ከሰጣቸው ድርጅቶች
ተጠቃሚ ማድረግ ትልቅ ፈተና ሆኖባቸው መካከል ፓራዳይዝ ሎጅ ፣ ሀይሌ ሪዞርት ፣
እንደነበር ያስታውሳል:: የዚህንም መንስኤ ሲናገር ጂ.አይ.ዜድ ፣ ኮካ ኮላ እና ሌሎችም ድርጅቶች
“በኛ ሀገር ያሉ ድርጅቶች የሰራተኞች ስልጠናን ይገኙበታል:: አብዛኞቹ ድርጅቶች ከፍተኛ የሆነ
አበል እየተከፈለበት የሚደረግ የቅንጦት ጉዳይ የምርታማነት እመርታን ማስመዝገብ ሲችሉ በሀገር
አድርገው ይወስዱታል:: በዚህም ሰራተኞቻቸውን አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ የሆኑም ይገኙበታል::
በስልጠና ለማብቃት ብዙ ጥረቶችን ሲያደርጉ
አይስተዋሉም” ሲል ትዝብቱን ይገልፃል:: በዋናነት ድርጅቱ ስልጠና መስጠት ላይ ቢያተኩርም
ግን ለሁሉም ድርጅት አንድ አይነት ስልጠና
አንሰጥም ሲል ኤባ ተስፋዬ ይናገራል::

መልካም74 | 26 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019


ስራ ፈጠራ
ይልቁንም እያንዳንዱ ድርጅት ወርዱን ሁሉ ከአመክንዮአዊ ጥንካሬአቸው
እና ስፋቱን የሚመጥን የስልጠና አንፃር እናያቸዋለን:: ያኔ ውሀ ያነሳው
አይነት እና ይዘት በልኩ ተሰፍቶ ሀሳብ ድጋፍ ያገኛል:: ከዛ ውጪ
ይዘጋጅለታል:: ከ50 በላይ የሆኑ ግን ስለተማርኩኝ የኔ ሀሳብ ትክክል
ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዱ ነው ብሎ ነገር አይሰራም:: ሌላው
ስልጠናዎችን ማዘጋጀታቸውን ለአብሮ መስራታችን እና ለውጤታችን
የሚገልፁት አሰልጣኞች ድርጅቶች ግብአት የሆነው የአንዳችን ችሎታ
ያለባቸው ክፍተት እየታየ ለሌላው ስኬት ግብዓት እንደሆነ
የሚያስፈልጋቸው የድጋፍ አይነት መረዳት መቻላችን ነው:: የምንሰራቸው
እንደሚመረጥላቸው ነግውናል:: ስራዎች እና ያሉን ችሎታዎች ሁሉ


ተመጋጋቢ መሆናቸውን አመንን::
በተጨማሪም ስልጠናዎችን ከሌሎች ከዛም እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ የስራ
መሰል ድርጅቶች እና ግለሰቦች ድርሻ እንዲሰጠው እና ያንን በአግባቡ
ፈጥነህ መሄድ
ጋር በጥምረት የመስጠት ልምድ እንዲሰራ ማድረግ መቻላችን ለስራችን ከፈለክ ብቻህን
እንዳላቸውም ነግረውናል:: “በርግጥ በስኬት መዝለቅ ትልቅ አስተዋፅኦ
ውድድር ጥሩ ነገር ቢሆንም የጥምረትን አድርጎልናል::”
ተራመድ ፤ ሩቅ
ግን የሚያህል ሀይል እንደማይሰጥ ለመሄድ ካሰብክ
እናምናለን” ይላል ኤባ ተስፋዬ:: “ሌላው ነገር” ይላል ኤባ የሽርክና ስራን
“ፈጥነህ መሄድ ከፈለክ ብቻህን ስኬታማ የሚያደርጉ ነገሮች ሲዘረዝር
ግን ከሌሎች ጋር “
ተራመድ ፤ ሩቅ ለመሄድ ካሰብክ “ሌላው ነገር ሌላኛው ወገን የመጣበትን ተራመድ
ግን ከሌሎች ጋር አብረህ አብረህ ልማድ ፣ ወግ ፣ ሀይማኖት ወይንም
ተራመድ እንደሚባለው ሁሉ እኛም ደግሞ ሌሎች ግላዊ የሆኑ ጉዳዮችን
ፈጥነን ከመሄዱ ይልቅ ሩቅ መጓዙን ማወቅ እና አክብሮ መንቀሳቀስ
ስለምንፈልግ ሌሎች እኛን ከመሰሉ ነው:: ምንም እንኳን ከኛ ልምድ ጋር
አሰልጣኞች ጋር ተጣምረን ስንሰራ የማይሄዱ ጉዳዮች ከሸሪካችን በኩል
ቆይተናል::” አሁንም ቢሆን እንግሊዝ ቢያጋጥሙንም ነገሮችን አቻችሎ
ሀገር ከሚገኘው ከሼፍልድ ዩኒቨርሲቲ መሄድ ግን ለማንኛውም የሽርክና ስራ
ጋር በአብሮነት እየሰሩ እንዳሉ ነው ውጤታማት አማራጭ የሌለው ነገር
መገንዘብ የቻልነው:: ነው”ሲል አስተያየቱን ይሰጣል::

በሽርክና መስራት ያሉት ተግዳሮቶች አንድን ድርጅት ስኬታማ ከሚያደርጉት


ምን እንደሚመስሉ እና በምን መልኩ ነገሮች መካከል ድርጅቱ
ደግሞ ተግዳሮቶቹን ማለፍ እንደሚቻል የሚያስፈልገውን የስራ ዘይቤ ማወቅ
መልካም74 ላነሳችው ጥያቄ ኤባ ነው:: ለዚህም ነው ቲ.ኢ.ኤ
ተስፋዬ የሚከተለውን መልስ ሰጥቷል:: ኮንሰልታንሲ የስራ ሰዓት የሚባለውን
አረዳድ በመቀየር ሰራተኛው
“በሽርክና መስራት ብዙ ተግዳሮቶች በፈለገው ሰዓት መስራት እንዲችል
ይኖሩታል:: በተለይም ሁላችንም የስራ ነፃነትን እየሰጠ የሚገኘው::
በትምህርታችን የገፋን ከመሆኑ ጋር ድርጅቱ ለሰራተኞቹ የሚሰጠውን ስራ
ተያይዞ እኔ የበለጠ አውቃለሁ የሚል በተቀመጠው የሰዓት ገደብ ማጠናቀቅ
ነገር ትንሽ ሊያስቸግረን ይችላል:: እስከቻሉ ድረስ የትኛውም ሰራተኛ
ነገር ግን ደግሞ ያንን ሁኔታ ሀሳቦችን ቢሮ ውስጥ ተቀምጦ የመቆየት ግዴታ
ማሳመን የቻለ ሰው ውሳኔን እንዲወስን የለበትም:: ይህንንም ሲያብራሩ
ወይንም ደግሞ መወሰን ያለበት “ስራን እንጂ የስራ ሰዓትን መጠበቅ
ውሳኔ በዛ ሰው ሀሳብ ላይ የተመሰረተ ውጤታማ አያደርግም” ይላሉ::
እንዲሆን በምንፈግበት ግዜ ሀሳቦችን ስለዚህም ሌሎች ድርጅቶችን እንደዚህ
መልካም74 | 27 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019
ስራ ፈጠራ

አይነት መንገዶችን እንዲሞክሩ ያበረታታሉ:: መታየት አለበት::


ማንኛውም በቲ.ኢ.ኤ ኮንሰልታንሲ ኤንድ ትሬይኒንግ ምክንያቱም የትኛውም ደረጃ ላይ ያለ ሰራተኛ የዛ
ውስጥ መስራት የሚፈልግ ሰው መጀመርያ ድርጅቱ ድርጅት መገለጫ ነው:: በተቻለ መጠን ድርጅቶች
የሚሰጠውን ስልጠና ይወስዳል:: ሰራተኞችን ድርጅቱ ሰራተኛው ተመችቶት እንዲሰራ ማድረግ መቻል
በሚፈልገው መልኩ ማብቃት ለስራቸው ስኬት አለባቸው:: ብዙ ግዜ አለቆች የማይረዱት አንድ
ሌላው ምስጢር እንደሆነ መስራቾቹ ይናገራሉ:: ነገር አለ:: ሰራተኛ ስራ ለቆ ሲሄድ እነሱን ነው
ነገር ግን ስልጠናውን የወሰደ ሁሉ ለድርጅቱ እንጂ ትቶ የሚሄደው ስራውን አይደለም:: ሌላው
የመስራት ግዴታ የለበትም:: እስከዛሬ ከድርጀቱ ደግሞ ሰራተኞች ከቀድሞ አሰሪያችሁ ደብዳቤ
ጋር የሰሩ ከአንድ ሺ በላይ የሆኑ ግለሰቦች ሁሉ አምጡ ተብለው እንደሚጠየቁ ሁሉ አሰሪም ከቀድሞ
በድርጅቱ የማብቃት ስልጠናዎች ያለፉ ናቸው:: ሰራተኛ የምስክርነት ደብዳቤ አምጣ ተብሎ ቢጠየቅ
በአሁኑ ግዜም በድርጅቱ ውስጥ ከ500 በላይ የሙሉ ስንቱ ድርጅት ከስራ ውጪ እንደሚሆን ማሰብ
እና የትርፍ ግዜ ሰራተኞች ስራቸውን እያከናወኑ አይከብደንም:: ስለዚህ ድርጅቶች ቢሮ ማሳመር ላይ
ይገኛሉ:: የድርጅቱንም የስራ ብቃት በመመልከት የሚያወጡትን ያህል ሰራተኞቻቸውን ማብቃትም
ዳሽን ባንክ አዲሱን የአሞሌ አገልግሎቱን የሽያጭ ላይ ወጪ ለማውጣት መሰሰት የለባቸውም::”
ሂደት በዚህ ድርጅት ስር እንዲሆን አድርጓል:: ሲል ለድርጅቶች መልዕክቱን ያስተላልፈል::

በመጨረሻም ኤባ ተስፋዬ ለድርጅት ባለቤቶች


የሚከተለውን መልዕክት ያስተላልፋል “ድርጅቶች
አንድ መረዳት ያለባቸው ነገር አለ:: ምንም እንኳን
ደንበኛ ንጉስ ቢሆንም ሰራተኛም ደግሞ እንደ ልዑል

T.E.A
መልካም74 | 28 POWERED BY YOSA ጃንዋሪ 1, 2019
በየወሩ የሚወጣውን መፅሄታችንን ከቴሌግራም
ቻናላችን ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን


አድራሻዎች ይጠቀሙ

+251-917-071-427
+251-911-921-477

ወይም በቴሌግራም አድራሻችን ላይ


መልዕክት ይላኩልን
@betsyalpha
@chimdesa

You might also like