You are on page 1of 18

ታይፈስ/ Typhus

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

ታይፈስ ሪኬትስያ በሚባል የባክቴሪያ ዓይነት አማካኝነት የሚመጣ የሕመም ዓይነት ሲሆን፣ የታይፈስ
ዓይነቶች በዋነኛ ደረጃ በሁለት ይከፈላሉ፡፡ ነገር ግን ሌሎች የታይፈስ አይነቶችም ይገኛሉ፡፡

✔ Epidemic Typhus (በወረርሽኝ መልክ የሚመጣ ታይፈስ) - ይህ የታይፈስ ዓይነት በሪኬትሲያ ፕሮዋዚክ
በሚባል ባክቴሪያ ዓይነት የሚከሰት ሲሆን ባክቴሪያውን አስታላላፊዎች ደግሞ በሰውነት ላይ በሚገኙ
ቅማሎች ናቸው፡፡

✔ Murine Typhus (ሙሪን ታይፈስ) - የምንለው ሁለተኛው የታይፈስ ዓይነት ሲሆን ይህ ደግሞ ሬኬትሲያ
ታይፈስ በሚባለው ባክቴሪያ ምክንያት የሚመጣ ነው፡፡ የባክቴሪያው አስተላላፊዎች በአይጦች ላይ የሚገኝ
ቁንጫ (Fleas) ናቸው፡፡

1) በወረርሽኝ መልክ የሚመጣ የታይፈስ ሕመም (Epidemic Typhus)

ምልክቶቹ

• ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት


• የመገጣጠሚያ ሕመም
• የጀርባ ሕመም ስሜት
• የደም ግፊት መጠን መቀነስ
• የሰውነት ላይ ሽፍታ
• ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት
• ከፍተኛ የሆነ የጡንቻ ሕመም

2) ሙሪን ታይፈስ (Murine Typhus)

ምልክቶቹ

• እጅግ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት


• የሆድ ሕመም ስሜት
• የጀርባ ሕመም ስሜት
• ደረቅ ሳል
• ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት ስሜት
• የሚገጣጠሚያ ሕመም ስሜት
• የጡንቻ ሕመም
• ማስመለስ
• በሰውነት ላይ የሚወጣ ሽፍታ
• ብርድ ብርድ ማለት ናቸዉ፡፡

✔ ለታይፈስ ሕመም ተጋላጭ የሚያደርጉ ሁኔታዎች

• በተጨናናቀ እና ሰው በበዛበት አካባቢ መኖር


• ከከተማ/ከአገር የወጡ ከሆነ
• የታይፈስ ወረርሽኝ በመኖሪያ አካባቢዎ የመጣ ከሆነ
✔ የታይፈስ ሕመም ሊያስከትል ከሚችላቸዉ ሌሎች ሕመሞች

• የጉበት ሕመም (ኢንፌክሽን)


• የአንጀት ውስጥ መድማት የመሳሰሉት ናቸው፡፡

✔ የታይፈስ ሕመምን ለመከላከል መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች፣

• የግል ንጽሕናን በሚገባ መጠበቅ


• በቤትዎ ውስጥ የሚገኙ የአይጥ ዝርያዎችን ማጥፋት
• የታይፈስ ሕመም ወረርሽኝ ያላባቸው አካባቢ አለመሄድ ናቸው፡፡

የታይፈስ ሕመምን በምልክቶች ብቻ መለየት ከባድ የሚሆን ሲሆን ይህም ከሌሎች ሕመሞች ጋር ተመሳሳይ
ምልክቶች ስለሚያሳይ ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሲሰማዎ ወደ ሐኪም በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ጤና ይስጥልኝ

10 የእንቁላል የጤና ጥቅሞች


(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

እንቁላል ሁሌም በገበያ ላይ የሚገኝ እና ለብዙ ምግቦች በአዘገጃጀት ወቅት የምንጠቀምበት እና በውስጡ
ለሰውነት ጠቀሜታ ያላቸውን ንጥረ ነገሮችን የያዘ የዘምግብ አይነት ነው፡፡

1. እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ የምግብ አይነት ሲሆን 6 ግራም የሚሆን ፕሮቲኖችን ይዟል፡፡ እነዚህ
ፕሮቲኖችም ለሰውነት እድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው፡፡

2. እንቁላል ኮሊን (choline) የሚባል ለአእምሮ እና ለልብ ተስማሚ እና አስፈላጊ የሆነ ንጥረ ነገርን ይዟል፡፡

3. እንቁላል ዓይናችን በጸሃይ ጨረር እንዳይጎዳ የሚያደርግ ጠቃሚ ንጥረ ነገርም በውስጡ ይገኛል፡፡

4. ጥናቶች እንደሚያሳዩት እንቁላል የተለያዩ የካንሰር አይነቶችን የመከላከል አቅም አለው ፡፡ በተለይም የጡት
ካንሰርን ከመከላከል አንጻር አፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

5. እንቁላል የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል፡፡

6. እንቁላል ለሰውነት ጤንነት ተስማሚ እና የተመጣጠነ ክብደት እንዲኖረን የሚያደርግ የቅባት አይነት
በወስጡ ይዟል፡፡

7. እንቁላል ከፍተኛ የሃይል ምንጭ ነው

8. እንቁላል በወስጡ ተፈጥሯዊ ቫይታሚን ዲ (vaitamin D) ስላለው ጤናማ እና ጠንካራ የአጥንት ጥርስ
እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
9. በእንቁላል ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚመለክቱት እንቁላል ከድንገተኛ የልብ ህመም፣ የደም መርጋት
እና ድንተኛ ከሆነ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስን ይከላከላል ፡፡

10. እንቁላል ለጸጉር ተስማሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ስለያዘ ለጸጉር እና ለጥፍር እድገት ከፍተኛ ሚና
ይጫወታል፡፡

የትርፍ አንጀት ሕመም (APPENDICITIS)


(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

የትርፍ አንጀት ሕመም የምንለው የህመም ዓይነት የሚከሰተው ከትልቁ አንጀት ቀጣይ በሆነው እና የ 3 ½
inch ርዝመት ባለው የአንጀት ክፍል ነው፡፡

እስካሁን ድረስ የትርፍ አንጀት ጥቅም በእርግጠኝነት ያልታወቀ ሲሆን ያለ ትርፍ አንጀት ጤናማ ኑሮንም
መምራት እንደሚቻል የሚታወቅ ነው፡፡

የትርፍ አንጀት ሕመም በአፋጣኝ ሕክምና ማግኘት ያለበት ሲሆን ሕክምና ካልተደረገለት ግን በሰውነት ውስጥ
ይፈነዳና ኢንፌክሽን አምጪ ተዋስያንን በሆድ ዕቃ ውስጥ የከፋ ኢንፌክሽን እንዲፈጥሩ ያደርጋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ መግል የያዘ ኢንፌክሽን ከሌላው የሰውንት ክፍል ራሱን ለይቶ ስለሚቆይ በጣም አጣዳፊ
ባይሆንም እንኳን በእርግጠኝነት ለመለየት ግን ቀዶ ጥገና አስፈላጊ ስለሆነ ሁሉም የትርፍ አንጀት ሕመሞች
የቀዶ ጥገና ሕመምና ያስፈልጋቸዋል፡፡

✔ የትርፍ አንጀት ሕመም በምን ይከሰታል?

የትርፍ አንጀት ሕመም የሚመጣው በትርፍ አንጀትና በትልቁ አንጀት መካከል የሚገኘው አንገት ሲዘጋ ነው፡፡
ይህ በሠገራ፣በቁስ አካል ወይንም በካንሰር አልያም በኢንፌክሽን ምክንያት ሊዘጋ ይችላል፡፡

✔ የትርፍ አንጀት ሕመም ምልክቶች

• ከእምብርት አካባቢ ጀምሮ ወደ ታችኛው የቀኝ የሆድ ክፍል የሚወርድ የህመም ስሜት
• የምግብ ፍላጎት ማጣት
• ማቅለሽለሽና ማስመለስ ከሆድ ሕመሙ በመቀጠል ይከሰታል
• ትኩሳት
• አየር ለማስወጣት መቸገር
• ለመንቀሳቀስ መቸገር

ከላይ የተጠቀሱትን ዓይነት የህመም ስሜት ከተሰማዎ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ተገቢ ነው፡፡ ይህም
የሚሆነው በአፋጣኝ ሕመሙ ታውቆ ሕክምና ሊደረግ ስለሚገባው ነው፡፡
ምንም ዓይነት ምግብ ወይንም መጠጥ ወይንም ሕመም ለማስታገስ የሚወሰዱ የቤት ውስጥ መድኃኒቶች
እንዳይወሰዱ ይመከራል፡፡ ይህም ያበጠው ትርፍ አንጀት እንዳይፈነዳ ያደርጋል፡፡

✔ የትርፍ አንጀት ሕመም ምርመራዎች


በምልክቶች ብቻ የትርፍ አንጀት ሕመምን በእርግጠኝነት ለማወቅ ስለሚያስቸግር ሌሎች በመሳሪያ የታገዙ
ምርመራዎች ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
• የሆድ አልትራሰውንድ
• የደም እና የሽንት ምርመራዎች የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

✔ የትርፍ አንጀት ሕክምና ምንድን ነው?

• በቀዶ ጥገና የትርፍ አንጀቱን ቆርጦ ማውጣት ይህም በህክምናዉ (Appendectomy) የምንለዉ ዋነኛው
ሕክምና ሲሆን መግል የያዘ ትርፍ አንጅት መጀመሪያ መግሉን በማስወገድ አልያም ፀረባክቴሪያ መድኃኒቶችን
በመጠቀም የቀዶ ጥገና ጊዜው የሚራዘምበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡

✔ ቀዶ ጥገናው ከተደረገ በ 12 ሰዓት ውስጥ እቅስቃሴ መጀመር የሚቻል ሲሆን፣


• የማይቆም ማስመለስ
• ከፍተኛ የሆድ ሕመም
• ራስ ማዞር
• ደም የቀላቀለ ማስመለስና ሽንት ከጋጠምዎ
• በስፌቱ ላይ ሕመም እና መቅላት ካመጣ
• ትኩሳት እና መግል ከቁስሉ የወጣ ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ሐኪምዎ በመሄድ እንዲያማክሩ ይመከራል፡፡

የትርፍ አንጀት እንዳይመጣ ለመከላከል የማይቻል ቢሆንም፣ ጥናቶች እንደሚሳዩት ከሆነ ግን በፋይበር የበለፀጉ
ምግቦችን (ፍራፍሬዎችና አትክልት) የሚመገቡ ሰዎች ላይ የመከሰት ዕድሉ እንደሚቀንስ ነው፡፡

ጤና ይስጥልኝ

ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የስኳር ሕመም ምልክቶች


(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

የስኳር ሕመምን በተመለከተ በተለያዩ የጤና ምክር መስጫ ፕሮግራሞች ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ የማስጨበቻ
ሥራዎች እየተሰሩ ናቸው፡፡
ከዚህ በታች ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የሕመሙን ጠቋሚ ምልክቶች እንግራችኋለሁ፡፡ ስለስኳር ሕመም
በዝርዝር በቅርቡ የሚያስገባችሁ ይሆናል፡፡

1) ከተለመደው ጊዜ በተለይ ውሃ መጠማትና በተደጋጋሚ የውኃ ሽንት መምጣት፡፡


የስኳር ሕመም ለኩላሊት ችግር በማጋለጥ ቀዳሚ ደረጃን የሚይዝ ሲሁን በደምውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠን
መጨመር የኩላሊት ሥራ ያዛባል፡፡

2) የድካም ስሜት መሰማት


የስኳር ሕመም ከፍተኛ የድካም ስሜትን ያስከትላል፡፡ የሰውንት ክብደት መጨመር በራሱ ለስኳር ሕመም
ከማጋለጥ ባለፈ የድካም ስሜት እንዲበረታ ያደርጋል፡፡

3) የዓይን ችግር
ማናኛውም ዓይነት የዓይን ችግር የስኳር ሕመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ሕክምና ቦታ
በመሄድ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

የስኳር ሕመምተኞች ለግላውኮማ የመጋለጥ ዕድላቸው ስለሚጨምርና በካታራክት (በዓይን ሞራ) ሊጠቁ
ስለሚችሉ የዓይን ሕመም ከተሰማ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይመከራል፡፡

4) የእግር መደንዘዝ
የስኳር ሕመም የነርቭ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ ይህም ጉዳት በአብዛኛው የሚከሰተው በእጃችንና በእግራችን ላይ
ባሉ ነርቮች ላይ ነው፡፡ በነርቭ ወይንም በደም ሥር ላይ የሚደርስ ጉዳት የእግር መደንዘዝ ቀጥሎም የሕመም
ስሜትን ያስከትላል፡፡ ሕመሙ በጊዜ ብዛት እየባሰ የሚሄድ ሲሆን መጠጥ እና ሲጋር ማጨስ ሕመሙን
ያባብሰዋል፡፡

5) የቆዳ ላይ ኢንፌክሽንና በቶሎ የማይድን ቁስለት


የስኳር ሕመም ቆዳችንን ጨምሮ ማንኛውንም የሰውነት ክፍላችንን ሊጎዳ ይችላል እንዲያውም የስኳር
ሕመም ያለበት ሰው በቀላሉ በባክቴሪያ እና በፈንገስ የሚመጣ ለቆዳ ላይ ኢንፌክሽን ያጋልጣል እነዚህም
ኢንፌክሽኖች ቁስለትን ያስከትላሉ በቶሎ ሊድኑም አይችሉም፡፡

ጤና ይስጥልኝ

ከብጉር ነፃ የሆነ ቆዳ እንዲኖሮ መመገብ ያለቦዎት ምግቦች


(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1. በኦሜጋ ፍሬ የበለፀጉ ምግቦች


ተልባ፣ አሳ፣ ዘይት የመሳሰሉት

2. በአንቲ ኦክሲደንት የተሞሉ ምግቦች


ኢንጆሪ፣ ቦሎቄ፣ የመሳሰሉት

3. ሴሊኒየም የበለፀጉ ምግቦች


አሳ፣ ስጋ፣ ዶሮ፣ እንቁላል፣ ወይም እንጉዳይ
4. በፋይታሚን ኢ የበለፀጉ ምግቦች
አቦካዶ፣ ጎመን፣ አሳ፣ ወይራዘይት፣ ብሮክሊ

5. ብዙ የውሀ መጠን በውስጣቸው የያዙ ምግቦች


ሀብሀብ፣ ኢንጆሪ፣ አናናስ፣ ዝኩኒ፣ ቲማንቲም የመሳሰሉት

6. በፋይታሚን ኤ የበለፀጉ ምግቦች


ካሮት፣ ስኳር ዲኒች፣ አሳ፣ ማንጎ

7. ማግኒዢየም ያላቸው የምግብ አይነቶች


አሳ፣ አቦካዶ፣ ባቄላ፣ ሙዝ

ጣፋጭ የሆኑ ምግቦችን ባይመገቡ ይመከራል

ጤና ይስጥልኝ

የአይናችንን ጤና እንጠብቅ
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

* በመጀመሪያ አይኖ በምን አይነት የጤና ሁኔታ ላይ እደሚገኝ ወደ ህክምና ቦታ በመሄድ ማረጋገጥ፡፡

እንደ ስኳር ህመም ባሉና ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው በሚመጡ የጤና እክሎች በአይን ውስጥ
የሚፈጠረው ከፍተኛ ግፊት ምክንያት ለብርሃን ማጣጥ መንስኤ የሆኑትን የአይን ህመሞች ቅድሚያ ምልክት
ስለማይሰጡ በህክምና ያረጋግጡ፡፡

* አይናችንን ሁልግዜ ማለዳ በንጹህ ውሃ መታጠብ ፡፡

ይህም የግል ንጽህናን ከመጠበቅ ባለፈ እንደ ትራኮማ ካሉ በሽታች ለመከላከል ይጠቅማል፡፡

* የክብደት መጠንዎን ይቆጣጠሩ

እንደ ሰኳር ህመም ያሉ ለዓይናችን ጤና መታወክ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ በሽታዎች በክብደት መጠን
መጨመር ሊከሰቱ ይችላሉና

* ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ እንደ ተልባ ፣ አሳ ፣ ካሮት እና ጎመን የመሳሰሉ የምግብ አይነቶችን
መመገብ ለጤናችን ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

* አብዛኛዎቻችን ለብዙ ሰአታት በአንድ ቦታ ላይ በአትኩሮት በመመልከት ዓይኖቻችን ማሳረፍ እንዘነጋለን


ነገር ግን ቢያንስ በየ 20 ደቂቃ ልዩነት ውስጥ ለ 20 ሰከንዶች ያህል አይናችንን ማርገብገብና ማሳረፍ ይገባል፡፡

* ሲጋራ ማጨስን ያስወግዱ


* ዓይንዎ በጸሃይ ጨረር እንዳይጎዳ የጸሃይ መነጽር በማድረግ ይከላከሉ፡፡ (Wear UV protective sunglasses)

* የኮንታክት ሌንስ(wearing contact lenses) ተጠቃሚ ከሆኑ ከ 19 ሰዓት በላይ በ አይኖ ላይ መቆየት
የለበትም ስለዚህ በሚተኙበት ወቅት ማስወገድ የገባዎታል

ጤና ይስጥልኝ

የአስም ህመም ጉዳት ፣ ምልክቶች አና ሊወሰዱ የሚገቡ ቅድመ እና ድህረ ጥንቃቄዎች


(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

የአስም በሽታ ሳንባችንን የሚጎዳ የህመም አይነት ሲሆን በዓለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የበሽታው
ተጠቂዎች ይገኛሉ፡፡

የአስም ህመም በአብዛኛው ከልጅነት ጀምሮ በመከሰት ደረጃ በደረጃ እያደገ የሚሄድ የመተንፈሻ አካል ህመም
ቢሆንም አልፎ አልፎም ቢሆን እድሜ ከገፋ በኋላም የሚጀምር የህመም አይነት ነው፡፡

ለአስም በሽታ መከሰት ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎች በትክክል ያልተወቁ ሲሆን እስካሁንም ድረስ በሽታው
ሙሉ በሙሉ ሊፈውስ የሚችል መድሃኒት አልተገኘም፡፡

በአብዘኛው አንድ የቤተሰብ አባል የበሽታው ተጠቂ ከሆነ በዘር የመተላለፍ ባህሪም አለው፡፡

የአስም በሽታ የሚያጠቃው የሳንባችንን የአየር ቧንቧዎች ሲሆን እነዚህን ቧንቧዎች በማጥበብ እና በቂ አየር
ወደ ሳንባችን እንዳይገባና እና እንዳየወጣ በማድረግ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል፡፡

የአስም በሽታ ምልክቶች

1. ሳል ፡- በተለይም በምሽት ግዜ የሚበረታ


2. ትንፋሽ (አየር) ማጠር
3. የደረት መጨምደድ ወይም መውጋት
4. ደረት አካባቢ በምንተነፍስበት ወቅት የሚሰማ ሲር ሲርታ (Wheezing)

የአስም በሽታን ሊቀሰቅሱ ከሚችሉ ነገሮች ውስጥ አንዳንዶቹ ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል ነገር ግን ከሰው ሰው
ሊለያዩ እንደሚችሉ መገንዘብ ያስፈላጋል፡፡

1. ሲጋራ ማጤስ ፡-

ሲጋራ ማጤስ የጤና ጠንቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡በተለይም ለአስም በሽታ ተጠቂዎች ማጨስም ሆነ ሲጋራ
የሚጤስበት አካባቢ መሆን በሽታው እንዲቀሰቅስ እና እንዲያገረሽ ያደርጋል፡፡

2. የአየር ብክለት ፡-

ከተለያዩ ፋብሪካዎች እና ተሽከርካሪዎች ከሚለቀቁ በካይ ጭሶች እና የአካባቢን አየር ከሚበክሉ ሽታዎች
ካላቸው ቆሻሻዎች ተጋላጭነትን ማስወገድ አሊያም መቀነስ ያስፈልጋል፡፡
ይህ ጉዳይ በግለሰብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በከተማ እና በሃገር ደረጃ ሊሠራበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

3. በረሮዎች

ጥናቶች እንደሚመለክቱት ከሆነ በረሮዎች እና የሚያመነጩት ብናኝ ለአስም በሽታ መቀስቀስ ምክንያት
ናቸው፡፡ በረሮዎች በአብዛኛው በቤታችን የሚገኙ እና ለጤና ጠንቅ ስለሚሆኑ ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡

4. የቤት እንስሳት

የቤት እንስሳትን በመኖሪያ ከማኖር ይልቅ ከመኖሪያ ቤት ውጪ ቤት መስራት እና ንጽህናቸውን ጠብቆ ማኖር
ያስፈልጋል፡፡

እነዚህ እንስሳት ብናኝ ስለሚኖራቸው ለአስም ህመም መቀስቀስ ምክንያት ይሆናሉ፡፡

5. ከዚህ በተጨማሪ እንደ ጉንፋን ፣ የተለያዩ የሳንባ ህመሞች (ኢንፌክሽኖች) ፣ ቅዝቃዜ ፣ የአየር ለውጥ እና
የተለያዩ መኣዛ ያላቸው ሽቶዎች የአስም በሽታን ሊቀሰቅሱ እና እንዲያገረሽ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

ሁሉም የአስም በሽታ ተጠቂዎች የህክምና መድሃኒት መውሰድ አይጠበቅባቸውም፡፡ የአስም በሽታን ከላይ
የተዘረዘሩትን የበሽታው ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮችን በማስወገድ እና የአካል ብቃት እንቀቅስቃሴ በማድረግ
መቆጣጠር ይችላል፡፡

የአስም ህክምና መከታተል የጀመረና መድሃኒት የሚወስድ የበሽታው ተጠቂ ሃኪም በሚያዘው መንገድ
መድሃኒቶቹን በአግባቡ እና በትክክል መውሰድ ይኖርበታል፡፡

ወላጆች አስም በሽታ ተጠቂ ከሆኑ ልጆች በሚወልዱበት ግዜ የህክምና ምርመራ እንዲዲርጉ እና በሃኪሞች
የሚሰጡ ምክሮችን መከታተል ተገቢ ነው፡፡

ጤና ይስጥልኝ

የምግብ መመረዝ/የአንጀት ቁስለት


(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

የምግብ መመረዝ ወይንም የአንጀት ቁስለት የምንለው የሕመም ዓይነት የሚከሰተው በቫይረስ፣በባክቴሪያ፣እና
በፓራሳይት አማካኝነት የተበከለን ምግብ በምንመገብበት ወቅት ነው፡፡

እነዚህ ተህዋስያን ምግብን በምናበስልበት ወቅት ሊበከሉ ስለሚችሉ ለምንመገበው ምግብ ንፅህና ጥንቃቄ
መውሰድ ተገቢ ነው፡፡

✔ ለአንጀት ቁስለት ተጋላጭንትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች

• በእድሜ የገፉ ሰዎች ሕመም የመከላከል አቅማቸው እየተዳከመ ስለሚመጣ ተጋላጭ ይሆናሉ፣

• ነፍሰጡር ሴቶች ለአንጀት ቁስለት ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው


• ሕፃናት በሽታን የመከላከል አቅማቸው ጠንካራ ስላልሆነ በቀላሉ ለአንጀት ቁስለት ይጋለጣሉ

• ተጓዳኝ ሕመም ያለባቸው ሰዎች እንደ ስኳር ሕመም፣ጉበት ሕመም፣ በኤድስ የተጠቁ ሕሙማን
ተጋላጭነታቸው የሰፋ ነው፡፡

✔ የአንጀት ቁስለት ምልክቶች

የምግብ መመረዝ/የአንጀት ቁስለት ሕመም ምልክቶች የተበከለ ምግብን ከተመገብን ከሰዓታት በኋላ
የሚከሰቱ ሲሆን
• ምልክቶቹም፡- ማቅለሽለሽ
ማስመለስ
ተቅማጥ
የሆድ ቁርጠት እና ትኩሳት ናቸው፡፡ እነዚህ ምልክቶች ለቀናት ሊቆዮ ይችላሉ፡፡

✔ ሐኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?

• በተደጋጋሚ የሚያስመልስዎ ከሆነ

• ደም የቀላቀለ ትውከት ወይንም ተቅማጥ ከኖረ

• ከ 3 ቀናት በላይ የሚቆይ ተቅማጥ ከኖረ

• ከፍተኛ የሆነ የሆድ ቁርጠት ካለ

• ከፍተኛ ትኩሳት ካለዎት

• ከፍተኛ የውሃ ጥማት፣የአፍ መድረቅ፣የድካም ስሜት፣ማዞር እና አነስተኛ የውኃ ሽንት ካለዎት ናቸው፡፡

✔ የምግብ መመረዝን ለመከላከል ምን ማድረግ ያስፈልግናል?

• የእጅን፣ ምግብ ማብሳያን እና መመገቢያ ቁሳቁሶችን ንፅሕና መጠበቅ

• ጥሬ /ያልበሰሉ/ ምግቦችን አለመመገብ

• ምግብዎን በፅዱ ቦታ ማስቀመጥና በተስማሚ የሙቀት መጠን ማብሰል

• ምግብዎን ለማቆየት ከፈለጉ በማቀዝቀዣ ውስጥ በማስቀመጥ እንዳይበከል መከላከል

• ምግብዎ የተበከለ ከመሰለዎ በአፋጣኝ ማስወገድ ተገቢ ነው

የአንጀት ቁስለት/የምግብ መመረዝ/ ለሕፃናት፣ለነፍሰጡር ሴቶች፣በእድሜ ለገፉ እና ተጓዳኝ ሕመም ላላቸው


ሰዎች አደገኛ እና ሕይወት እስከማጥፋት የሚያደርስ ሕመም ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ጥንቃቄዎች
መተግበር ተገቢ ነው፡፡

የሕመም ምልክቶችም ከታየ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ መፍትሔ ማግኘት ይገባል፡፡


እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ!!!
ጤና ይስጥልኝ

ጡት የማጥባት ጥቅሞች
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

• የእናት ጡት ወተት ለጨቅላ ሕፃናትም ሆነ እጅግ ከፍተኛ ጠቃሚ የሆነ ለልጅዎ የምግብ ዓይነት ሲሆን
ጨቅላ ሕፃናት ከተወለዱ ከ 1 ሰዓት በኋላ ጀምረው ለተከታታይ 6 ወራት የጡት ወተት ብቻ መጥባት
ይኖርባቸዋል፡፡ ከ 6 ወር በኋላም ከተጨማሪ ምግቦች ጋር ቢያንስ እስከ አንድ ዓመት ያህል ጊዜ ማጥባት
ያስፈልጋል፡፡

ጡት የማጥባት ጥቅሞች

ለሕፃኑ
• ከተለያዩ ኢንፌክሽን አምጪ ተሕዋሲያን ይከላከላል እነዚህም፣
1) ተቅማጥ
2) ሳንባ ኢንፌክሽን
3) የጆሮ ኢንፌክሽን
4) የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን

• ለአለርጂ እና አስም ተጋላጭነት ይቀንሳል


• ለስኳር ሕመም ተጋላጭነትን ይቀንሳል
• ለአጥንት ጥንካሬ እና ዕድገት ይረዳል
• ለአእምሮ ዕድገት ጠቀሜታ አለው
• በአፍ ውስጥ ለሚገኙ ጡንቻዎች ጥንካሬ እና ለፊት ጡንቻዎች እድገት ይጠቅማል
• ጤናማ ዓይን እንዲኖራቸው ይረዳል
• የሆድ ድርቀት ይከላከላል
• በሽታን የመከላከል አቅም እንዲኖራቸዉ ያደርጋል

ለእናቲቱ
• በእናት እና ልጅ መካከል ያለውን ትስስር ይጨምራል
• ለጡት ካንሰር ሕመም ተጋላጭነት ይቀንሳል
• ለማኅፀን ካሰር ሕመም ተጋላጭነት ይቀንሳል
• የአጥንት መሳሳትን ይከላከላል
• በእርግዝና ምክንያት የመጣውን የሰውነት ክብደት ይቀንሳል

እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ!


ጤና ይስጥልኝ
የወይራ ዘይት የጤና ጥቅሞች
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

• የካንሰር ሕመምን ይከላከላል


• የልብ ሕመምን ይከላከላል
• የደም ግፊት መጠን እንዳይጨምር ያደርጋል
• ከስኳር ሕመም ይከላከላል
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዳይኖር ይረዳል
• የአጥንት መሳሳትን ይከላከላል

ጤና ይስጥልኝ

የድካም ስሜት የሚሰማዎ ለምን እንደሆነ ያውቀሉ?


(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

• አካል ብቃት እንቅስቃሴ አያደርጉም


• በቂ ውሃን አይጠጡም
• አይረን የሚባል ንጥረ ነገር ያላቸውን ምግቦች አያዘወትሩም
• ቁርስዎን አይመገቡም
• ለጤና ተስማሚ ከሆኑ ምግቦች ይልቅ ጣፋጭ እና ቅባታማ ምግቦችን ይመገባሉ
• የሥራ ቦታዎ የተዘበራረቀ እና ያልተስተካከለ ከሆነ ነው
• በሥራ ምክንያት ሰለሚያመሹ በቂ እንቅልፍ አለማግኝትዎ ነው፡፡

ጤና ይስጥልኝ

የአልኮል መጠጥን አብዝቶ በመጠጣት ምክንያት የሚጎዱ የሰውነት ክፍሎች


(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1) ልብ
ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጥ ማዘውተር የልብ ጡንቻዎችን በማዳከም የደም ፍሰት መዛባትን ያሰከትላል፡፡
በአልኮል መጠጥ ብዛት የሚከሰት የልብ ሕመም የትንፋሽ ማጠር፤ የተዛባ የልብ ምት፤ድካም፤የማያቋርጥ ሳልን
ያስከትላል በተጨማሪም ለደም ግፊት እና ለድንገተኛ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ይዳርጋል፡፡

2) አንጎል
የአልኮል መጠጥ በአንጎል ላይ መልዕክት መተላለፍን ያዘገያል፡፡አልኮል መጠጥን ማዘውተር የተለያዩ የአንጎል
ክፍሎችን ስለሚጎዳ የባሕርይ ለውጦችን እንደ መደበት፤ጭንቀት እና የመርሳት ችግር የመሳሰሉትን
ሊያስከትል ይችላል፡፡

3) ጉበት
ጉበት የምግብ መፈጨት፤ንጥረ ነገሮችን ማከማቸት፤ኢንፌክሽን የመቆጣጠር እና መርዛማ ነገሮችን ከሰውነት
የማስወገድ ተግባርን የሚያከናውን የሰውንት ክፍል ነው፡፡ ታድያ አልኮልን የምናዘወትር ከሆነ በጉበት ላይ
ከፍተኛ ጉዳትን እናደርሳለን፡፡

4) ኩላሊት
የአልኮል መጠጥ በብዛት መውሰድ በኩላሊት የሥራ ሂደት ላይ መዛባትን ስለሚፈጥር በሰውነታችን ውስጥ
የሚገኙ ንጥረ ነገሮች መመጣጠንን በመረበሽ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ይህም ለከፍተኛ የደም ግፊት መጠን
መጨመር ይዳርጋል፡፡ ኩላሊትንም ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ይዳርጋል፡፡

5) ቆሽት
ልክ እንደ አንጎል ሁሉ ከፍተኛ አልኮልን መውሰድ የቆሽትን ሥራ ያዛባል፡፡ ቆሽት የሚያመነጫቸው
ኤንዛየምዎች(Enzymes) በውስጡ እንዲጠራቀም በማድረግ ቆሽት እንዲቆጣ ያደርጋል፡፡ ይህም የሆድ
ሕመምን፤ማቅለሽለሽና ማስመለስ፤የልብምት መጨመር ተቅማጥና ትኩሳት ያስከትላል፡፡የቆሽት መቆጣት
በሚቆይ ጊዜ የቆሽትን ሥራ ስለሚያስተጓጉል ለስኳር ሕመም አልፎም ለሞት ይዳርጋል፡፡

የአልኮል መጠጥ ማዘውተር ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችም ጉዳቶችን ስለሚያስከትል ለጤንንትዎ ሲሉ


እንዲያቆሙ ይመከራል፡፡

ጤና ይስጥልኝ

ይህ ቪዲዮ ከላይ የተጠቀሱተን አልኮል የሚያስከትላቸውን ችግሮች በምስል ያሳያል ይከታተሉ።

የፕሮስቴት ዕጢ
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

የፕሮስቴት ዕጢ ከወንዶች የሥነ ተዋልዶ አካላት ውስጥ ነው፡፡ ይህ ዕጢ የሚገኘው ከሽንት ፊኛ በታች ሲሆን
የሽንት ቱቦ መሃከለኛ ክፍልን ዙሪያ ከቦ ይገኛል፡፡

ይህ የፕሮስቴት ዕጢ ለወንድ ዘር ፈሳሽ የሚሆነውን ፈሳሽ ከሚያመነጩ


የሰውነት አካል ውስጥ አንዱ ሲሆን ዕድሜ በገፋ ቁጥር መጠኑም አብሮ ይጨምራል፡፡

✔ የፕሮስቴት ዕጢ መጠን መጨመር ምክንያቶች፡-


- የካንሰር ጠባይ የሌለው የፕሮስቴት ዕጢ እድገት
- የፕሮስቴት ካንሰር

✔ የካንሰር ጠባይ የሌለው የፕሮስቴት ዕጢ ዕድገት


ከዕድሜ መጨመር ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሲሆን የፕሮስቴት ዕጢ ከሚገባው በላይ የሚያድግበት መሠረታዊ
ምክንያት ባይታወቅም የሆርሞን መለዋወጥ እንደ ምክንያት ይጠቀሳል፡፡
የፕሮስቴት ዕጢ በሽንት ቱቦ ዙሪያ ስለሚገኝ መጠኑ በጨመረ ቁጥር የሽንት የማጥበብ ሁኔታን ሊያስከትል
ይችላል፡፡

✔ የፕሮስቴት ዕጢ ዕድገት ምልክቶች


• ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣትና፣
• በአንድ አንድ ሁኔታ ሽንት ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ መፍሰስ፣
• ሸንተው ከጨረሱ በኋላ ሽንት ጨርሶ ያልወጣ መስሎ መሰማት፣
• ሽንት ሸንተው ከጨረሱ በኋላ ማንጠባጠብ፣
• በሌሊት በተደጋጋሚ ከእንቅልፍ ለሽንት መነሳት፣
• ሽንት በሚሸኑበት ወቅት የፍሰቱ መጠን መቀነስ፣መቆራረጥና እንዲሁም ለመሽናት ማስማጥ፣
• ደም የቀላቀለ ሽንት መኖር፣
• የሽንት ቱቦ ሙሉ በሙሉ ከተዘጋ በታችኛው የሆድ ክፍል ከፍተኛ የህመም ስሜት መሰማት፣

✔ የፕሮስቴት ካንሰር
የፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ የሚታይ የህመም ሁኔታ ሲሆን መንስዔው በእርግጠኝነት አይታወቅም፡፡
የፕሮስቴት ካንሰር ቀስ በቀስ የሚያድግና የሚሠራጭ ስለሆነ አስከፊ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ምንም
ዓይነት የህመም ስሜት ላያስከትል ይችላል፡፡

✔ የፕሮስቴት ካንሰር ምልክቶች


የፕሮቴስት ካንሰር ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሊኖሩት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን መሰራጨት ከጀመረ በኋላ
ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሕመም ስሜቶችን ያስከትላል ወደ ጀርባና የጎን አጥንት፣ኩላሊት አና
አንጎልም ይሰራጫል፡፡

እርስዎ ከላይ የተጠቀሱት የህመም ስሜቶች የሚኖሩት ከሆነ ወደ ሀኪም በመሄድ ምርመራ ማድረግ
ይኖርቦታል፡፡

የህክምናዉ ሁኔታም እንደ ምርመራዉ ዉጤት የሚለያይ ሲሆን የተጠቀሱ ስሜቶች የሌላ ሕመም መገለጫ
ሊሆኑ ስለሚችሉ ተገቢዉን ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡

ጤና ይስጥልኝ

እጅግ የሚያጠብቁ ጅንስ ሱሪዎችን የሚያደርጉ ሰዎች ራሳችውን ለጡንቻ እና ለነርቭ ህመም
እንደሚያጋልጡ አዲስ የወጡ ጥናቶች አስታውቀዋል።

በቅርቡ አንዲት አውስትራሊያዊት ሴት ጠባብ የሆነ ጅንስ ለብሳ እና ቁጢጥ በማለት ስራ ስታከናውን ቆይታ
ለመነሳት ከመቸገሯ ባለፈ እግርዋ በማበጡ እና በመደንዘዙ ምክንያት ወደ ህክምና ቦታ ተወስዳ ለአራት ቀናት
መቆየቷም ተገልፇል።

ድንችን የመመገብ የጤና ጥቅሞች


(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

• በሽታን የመከላከል አቅምን ያዳብራል


• የምግብ መፈጨትን ሂደትነ ያግዛል
• የልብን ጤናማነት ይጠብቃል
• ለአንጎል ጤናማነት
• ለደም ግፊት
• ለቆዳ ጤናማነት
ጤና ይስጥልኝ

አኖዝሚያ(Anosmia) - Loss of smell


(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

በህክምና ቋንቋዉ አኖዝሚያ(Anosmia) በመባል የሚጠራዉ የአፍንጫ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ


ያለማሽተት ችግር ነዉ፡፡

ይህ ችግር በአብዛኛዉ የሚከሰተዉ በቅዝቃዜ ጊዜ እና የጉንፋን ቫይረስ በሚያጠቃን ጊዜ ሲሆን ለአጭር ጊዜ


የሚቆይም ነዉ፡፡ ነገር ግን በአንዳንድ ሠዎች ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ወይንም ፈጽሞ ማሽተት ያለመቻል
ችግር ይስተዋላል፡፡

✔ ይህ ችግር ለምን ይከሰታል?

በቅዝቃዜ፣ በጉንፋን ህመም፣ በአለርጂ እና አየር ጥራት አለመኖር ምክንያት


በአፍንጫ ዉስጥ የሚገኝ እባጭ መኖር (Nasal polyp)
በአፍንጫ እና ለማሽተት በሚረዱ ነርቮች ላይ የደረሰ አደጋ
አንዳንድ መድሃኒቶች
o ጸረ ባክቴሪያዎች
o ለመደበት ህመም የሚወሰዱ መድሃኒቶች
o የልብ እና ሌሎች ናቸዉ

በእድሜ መግፋት
ሌሎች የጤና እክሎች እንደ የነርቭ ችግር እና የሆርሞኖች መዛባት
ለጭንቅላት እና ከአንገት በላይ የሚደረግ የጨረር ህክምና ናቸዉ፡፡

✔ ሀኪምዎን ማማከር የሚገባዉ መቼ ነዉ?


ከቅዝቃዜ ወይንም በታወቀ አለርጂ ምክንያት የመጣ ያልሆነ እና ከሁለት ሳምንታት በላይ ይሚቆይ ማሽተት
አለመቻል ካጋጠምዎ ወደ ሀኪም በመሄድ መንስኤዉን ማወቅ ተገቢ ነዉ፡፡
ህክምናዉን በተመለከተ ችግሩን እንዳስከተለዉ ሁኔታ ተገቢዉን ምርመራ ካደረጉ በኋላ አስፈላጊዉን
የህክምና እርዳታ ያገኛሉ፡፡

በእድሜ ምክንያት የሚመጣ ያለማሽተት ችግር ዘላቂ ስለሚሆን ራስን አሳምኖ መኖር ተመራጭ ነዉ፡፡

እባክዎን ለወዳጅዎችዎ ያካፍሉ!


ጤና ይስጥልኝ

ከልክ ያለፈ ላብ (ሃይፐርሃይድሮሲስ)


(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

ከልክ ያለፈ ላብ ከእጅ፣ከእግር፣ከብብት እና ፊት አካባቢ በመመንጨት ሙሉ ሰውነትን በላብ እንዲዘፈቅ


ያደርጋል።
በዚህ ችግር የሚጠቁ ሰዎች መጠነኛ የሚባል የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ለማድረግ እስኪቸገሩ ድረስ በከባድ
ላብ ይዘፈቃሉ። ከዚያም ባለፈ ለማህበራዊ ችግሮችና በሰው ፊት ለመሳቀቅ እና መሸማቀቅ ይዳርጋቸዋል።

✔ መፍትሄዎች
• ሰውነትዎን በየቀኑ መታጠብ
• ሰውነትዎን ከታጠቡ በኃላ በሚገባ ማድረቅ
• እግርዎ አየር እንዲያገኝ ማድረግ ፣ ጥጥነት ወይም ሱፍነት ያለዉ ካልሲ መጠቀም

✔ ሃኪምዎን ማማከር የሚገባዎት መቼ ነዉ


• የላብ መጠኑ እጅግ በዝቶ የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎ ላይ ችግር ካስከተለ
• ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ የሚያልቦት ከሆነ
• ያለምክንያት ማታ በላብ የሚዘፈቁ ከሆነ ናቸው።

ጤና ይስጥልኝ

አቮካዶን የመመገብ ጥቅሞች በጥቂቱ


(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

✔ የኮሌስትሮል መጠን ይቀንሳል


አቮካዶ በውስጡ የያዘው ንጥረ ነገር (betasisterol) በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘዉን የኮሌስትሮል መጠን
እንደሚቀንስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

✔ ለዓይናችን ጤና ጠቃሚ ነው
በውስጡ የሚገኘው ካሮቲኖይድ ሉቲየን (carotenoid lutien) ዓይናችንን ከዕድሜ ጋር በተያያዘ ምክንያት
የሚመጡ ሕመሞችን እንድንከላከል ይረዳል፡፡

✔ በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን ይቀንሳል


በአቮካዶ ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው (folate) ፎሌት በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን እንደሚቀንስ
የተደረጉ ጥናቶቸድ ያሳያሉ፡፡

✔ ከካንሰር ይከላከላል
አቮካዶ የሚመገቡ ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው እንደሚቀንስና ወንዶችን ደግሞ ከፕሮስቴት
ካንሰር የመከላከል የመከላከል አቅም እንዳለው የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

✔ መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል


አቮካዶ ተፈጥሮአዊ ከሆኑ የመጥፎ አፍ ጠረን መከላከያዎች አንዱ ነው፡፡

✔ ለቆዳችን ጥቅም
የኦቮካዶ ቅባት በብዙ የውበት መጠበቂያዎች ውስጥ የሚገባና ለቆዳ ተስማሚ እና ጤናማነት ጠቃሚነት
ያለው የፍራፍሬ ዓይነት ነው፡፡

ጤና ይስጥልኝ
ቴምርን የመመመገብ የጤና ጥቅሞች
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

✓ ለአጥንት ጤናማተትና ጥንካሬ


ቴምር በውስጡ የያዛቸው ንጥረ ነገሮች እንደ ሴሌኒየም ማንጋኒዝ፣ኮፐር እና ማግኒዚየም ለአጥንት ጤናማ
እድገት እና ጥንካሬ እጅግ ጠቃሚ እንዲሆን ይደርገዋል።

✓ ለሆድ ድርቀት
ቴምርን መመገብ የሆድ ድርቀትን ይከላከላል። የሆድ ድርቀት የሚያስቸግርዎ ከሆነ ቴምርን በውሃ ዘፍዝፈው
በማሳደር ጠዋት መመገብ እጅግ ውጤታማ የሆነ መፍትሄን ይሰጣል።

✓ ሀይልን ይሰጣል
በተፈጥሮአዊ ስኳር ፤ ጉሉኮስ፣ ፍሩክቶስ እና ሱክሮስ የበለፀጉ ስለሆነ ጥሩ ሀይል ሰጬ መክሰስ መሆን ይችላል።

✓ ለልብ ጤናማነት
ቴምር ለልብ ጤናማነት ጠቃሚ ነው። ቴምር መትፎ የሚባለውን የኮሌስቴሮል መጠን የመቀንስ እቅም
ስላለው ለድንገተኛ የልብ ህመም የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል።

ጤና ይስጥልኝ

ሊያውቋቸው የሚገቡ የማስነጠስ እውነታዎች


(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1. የምናስነጥስበት ምክንያት በአፍንጫችን ላይ የሚገኙና በዓይን የማይታዩ ቆሻሻዎችን ለማስወገድ ነው።

2. በምናስነጥስበት ጊዜ ልባችን ለሰከንዶች መምታቷን ታቆማለች እየተባለ የሚነገር ቢሆንም ይህ ከእውነት


የራቀና የተሳሳተ አባባል ነው።

3. በአብዛኛው ጊዜ ከአንድ ጊዜ በላይ እናስነጥሳለን ይህም እንደምናስወግደው ቆሻሻ መጠን ይወስናል።

4. በምናስነጥስበት ወቅት የድምፅን መጠንና የምናስወጣውን አየር መጠን የሚወስኑት የአፍንጫችን


ቀዳዳዎች ስፋት ናቸው።

5. የምናስነጥሰው አየር ፈሳሽ የቀላቀለ ሲሆን፣ የፈሳሹ አይነት ውሀ መሰል ወይንም ቀለም የሌለው መሆን
አለበት። ፋሳሹ ቢጫ ቀለም ወይንም ደም የቀላቀለ ከሆነ የህመም (ኢንፌክሽን) ምልክት ሊሆን ስለሚችል
ወደ ህክምና ቦታ በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል።

ጤና ይስጥልኝ

የጨጓራ ሕመምዎን ለማስታገስ የሚጠቅሙ የጤና ምክሮች


(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)
• ከጥጋብ በላይ አለመመገብ

• ምግብን በዝግታ መመገብ

• ቅባታማ ምግቦችን ማስወገድ

• ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች አለመመገብ

• ሲጋራ ያለማጤስ

• ቡና፤አልኮል እና የለስላሳ መጠጦችን አለማዘውተር

• የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል

• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

• አዕምሮዎን ዘና በማድረግ ጭንቀትን ማስወገድ

ጤና ይስጥልኝ

ቲማቲምን የመመገብ የጤና ጥቅሞች


(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

• ቲማቲምን መመገብ ለቆዳ ጥራት ጠቃሚ ነው፡፡ ቲማቲም በውስጡ ያዘው ንጥረ ነገር ለቆዳ ተስማሚ የሆነ
ሲሆን ቲማቲምን ልጦ የልጣጩን ውስጠኛ ክፍል በፊትዎ ላይ በመለጠፍ ለ 10 ደቂቃ በማቆየት መታጠብ
ንፁህና የሚያበራ ፊት እንዲኖርዎ ያደርጋል፡፡

• ቲማቲም ለተለያዩ የካንሰር ዓይነቶችን ይከላከላል የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቲማቲም ውስጥ
የሚገኘው ሊኮፒን የተባለ ንጥረ ነገር በፕሮስቴት ካንሰር፣የጨጓራ እና የአንጀት ካንሰርን የመከላከል አቅም
አለው፡፡

• ጠንካራ አጥንት እንዲኖረን ያደርጋል


ቲማቲም በውስጡ ካልሲየም እና ቫይታሚን ኬን ያዘ ሲሆን ሁለቱም ንጥረ ነገሮች አጥንትን ጠንካራ እንዲሆን
ያስችላሉ፡፡

• ቲማቲም ለልባችን ጠቀሜታም አለው


ቲማቲም በቫይታሚን ቢ እና በፖታሺየም የበለፀገ ሲሆን ኮሌስትሮልን እና የደም ግፊትን የመቀነስ አቅምም
አለው፡፡ ቲማቲምን በዕለት ተዕለት የምግብ ስርአትዎ ውስጥ ማስገባት ከድንገተኛ የልብ ሕመም እና
ኮሌስትሮል እራስዎን ይከላከላሉ፡፡

• ለፀጉርዎ ጠቀሜታ አለው


በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ፀጉርዎን ጠንካራና አንፀባራቂ እንዲሆን ያደርጋል
• ቲማቲም ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ ዕድልዎን ይቀንሳል

• ለዓይንዎ ጥራት
ቫይታሚን ኤን ያዘውን ቲማቲም መመገብ ለዓይንዎ ጥራት እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ጥናቶች ይገልጻሉ፡፡

ጤና ይስጥልኝ

ጤናማ የሆኑ የመክሰስ ምግቦች


(በዶር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

✓ እርጎ በእንጆሪ ፈጭቶ አንድ ብርጭቆ መጠጣት


✓ የወይን ፍሬን መመገብ
✓ ኦቾሎኒ
✓ አጃ በወተት
✓ ሙዝ
✓ ፈንዲሻ
✓ ፖም
✓ ሰላጣ
የተለያዩ ጣፋጮችን ከመመገብ ይልቅ በእነዚህን ጤናማ የሆኑ ምግቦች ቢተኳቸው ተመራጭ ነው።

You might also like