Professional Documents
Culture Documents
Fast Foods For Short Term
Fast Foods For Short Term
እንቁላል ቁጭቁጭ
ታህሳስ 2010
መግቢያ
የቅቤንና ዘይትን መጠን በመቀነስ አስተካክሎ ጣፋጭ ምግብ የማቅረብ ንግድ ወጤት
Total
የሚፈጀዉ ጊዜ
አጠቃላይ ዓላማ
ትርጉም
ንጥሬ ምግቦች ማለት በምግብ ውስጥ የሚገኙና ለሰውነታቸን የተለያየ ጥቅሞች የሚሠጡ
የምግብ ክፍሎች ናቸው፡፡ እነሱም፡- ፕሮቲን፣ ካርቦሃይድሬት፣ ቫይታሚን፣ ማዕድንናት፣ ቅባትና
ውሃ ናቸው፡፡
1. ፕሮቲን
ፕሮቲን እጅግ ጠቃሚ የሆነ አልሚ ምግብ ነው፡፡ ለዕድገት ጡንቻዎችን ለማዳበር፣ አጥንቶችንና
ጥርሶችን ለማጠንከር ሰውነታችን በየዕለቱ ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሮቲን ያስፈልገዋል፡፡ ፕሮቲን
የሚገኝባቸው የምግብ አይነቶች ሥጋ፣ ዓሣ፣ ወተትና የወተት ውጤቶች ከቂቤ በስተቀር፣ አተር፣
ሽንብራ፣ እንቁላል፣ ባቄላና ምስር እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
2. ቅባትና ካርቦሃይድሬት
ለሰው ልጅ ሰውነት ኃይልን ይሰጣል፡፡ የሚገኘውም ከድንች፣ ከስኳር፣ ከማር፣ ከቂቤ፣ ከዘይት፣
ከጤፍ፣ ከበቆሎ፣ ከማሽላ፣ ከዳጉሳ፣ ከአጃና ከመሳሰሉት ነው፡፡
3. ማዕድናት
እንደ ብረት፣ ካልሺየም፣ እና የመሳሰሉት በምግብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ብረት ለቀይ ደም ሴሎች
የሚያገለግል ከፍተኛ ንጥሬ ምግብ ነው፡፡ ካልሺየም አጥንትንና ጥርስን ለማጠንከር የሚጠቅም
ነው፡፡ የካልሺየም ምንጭ የሆኑ የምግብ ዓይነቶች ወተትና የወተት ውጤቶች ጤፍ፣ ቦለቄ፣ ዳጉሳ፣
እንሰት፣ ሽንብራ ወዘተ ናቸው፡፡
4. ቫይታሚን
የቫይታሚን ምንጭ የሆኑ የምግብ አይነቶች ወተት፣ ቂቤ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ እንቁላል እና
የመሳሰሉትን ይይዛል፡፡
የእነዚህ ንጥሬ ምግቦች በሰውነታችን ውስጥ በበቂ ሁኔታ ተሟልቶ አለመገኘት ሰውነታችንን
ለተለያዩ በሽታዎች ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
የምግብ ደህንት አጠባበቅ ማለት ምግብ በተለያዩ መንገዶች ሳይበላሹ የማቆየት ዘዴ ነው፡፡ ምግብ
ለብዙ ጊዜ ሲቆይ ለብልሽት የሚዳረግባቸው መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ምግብ ከምርት አንስቶ ለሰው ልጅ ፍጆታ እስከሚውል ድረስ ልዩ እንክብካቤ መደረግ ይኖርበታል ፡፡
ምግብ በሚዘጋጅበት ቦታና ለማዘጋጀት የሚውሉ ዕቃዎችን ንፅህና መጠበቅ አለበት፡፡ እንደዚሁም
ከምግብ ጋራ ንክኪ ያለው ሰው የግል ንፅህናውና ጤንነቱን ጭምር በደንብ መጠበቅ ይኖርበታል ፡፡
ንጽህና የጎደለው አካባቢ የዝንብና የተላላፊ በሽታ መንስኤ ሲሆኑ የሚችሉ ጥቃቅን ሕዋሳት
መራቢያ ይሆናል፡፡ የግል ንጽህና በተለይም የእጅና የሌሎች የአካል ክፍሎች ንጽህና ጉድለት፣
በሚዘጋጀው ምግብ ዙሪያ ማስነጠስና ማሳል የመሳሰሉት፣ የምግብ ማዘጋጃ ዕቃዎች አጠቃቀምና
ንፅህና ጉድለት፣ ተገቢውን ዕቃ በተገቢው አገልግሎት ላይ አለማዋል የምግብን መበከል ያስከትላል፡፡
የምግብ መበከል ተመጋቢውን መመረዝና በሽታ ላይ መጣል ብሎም ሞትን ሊያስከትል ሲችል
በአቅርቦትም በኩል ሲታይ የጥራትን ማነስና፣ ተፈላጊነትን ማጣት እና ባጠቃላይ ኪሣራን በግልና
በሀገር ደረጃ ያስከትላል፡፡ አንድ ምግብን የሚያዘጋጅ ሰው የግል ንጽህናውን መጠበቅ አለበት፡፡
ይኸውም፡
ይዘት
ለአጫጭር ስልጠና
1. የአትክልት ሳላድ
2. ኒኮየስ ሳላድ/ቱና እንቁላልና የተለያዩ አትክልቶች ሳላድ
3. ቪነግረት ሶስ/vinegret sauce
4. ማዮኔዝ ሶስ /mayonnaise sauce
5. እንቁላል ቁጭቁጭ / Sunny Side Up /
6. /ፖችድ ኤግ/ POACHed egg/በዉሀ የበሰለ እንቁላል ቁጭቁጭ
7. የእነቁላልፍረፍር/Scrambled Eggs
8. ተመትቶ የተጋገረ እንቁላል /Omlets
9. የተቀቀለ እንቁላል /Boiled Eggs/
10. የእንቁላል ሳንደዊች
11. ሐምበርገር ሳንድዊች
12. ክለብ ሳንደዊች /Club Sandwich
13. የዶሮ ፓይ / pai/
14. እስፒሪነረገረ ሮል /spring roll/
15. የዶሮ መላለጫ ጥብስ ለአንድ ሰዉ/Stir Fried Chicken
16. ጉላሽ / gulash/
17. ፒሣ በቲማቲም ሱጎ ቺዝ /ፒዛ ማርገሪታ / Pizza Margherita /
18. የሙዝ ማፍን ኬክ / Banana Muffins
19. የካሮት ኬክ
20. የካሮት ካናፔ
21. ቀይ ስር ካናፔ
22. የቆስጣ ካናፔ
23. መት ቦል
24. ራይስ ቦል/ የሩዝ ካናፔ
25. የስጋ ስስጎ
26. የቲማቲም ስጎ
27. ሩዝ በስጋ ስጎ
28. ሩዝ በአትክልት
29. ሩዝ በቲማቲም ስጎ
30. ፓስታ በስጋ ስጎ
31. ፓስታ በአትክልት
32. ፓስታ በቲማቲም ስጎ
ለጋ የብግ ጥብስ
ደረቅ ጥብስ
የጥብስ ፍርፍር
ዱሌት
አሳምቡሳ
ቆቆር
ቦንቦሊኖ
የቡላ ግንፎ
ሙቾ ( በእንፋሎት የበሰለ ቡላ) (የቡላ ፍርፍር)
ቡሪሳሜ ከቡላና ቆጮ
ጩካሜ ከቡላና ቆጮ
የቡላና ቆጮ ቂጣ በኪትፎ /በአይብ/ጮጳሮ ማለት የጎምነ ኪትፎ/ በጎመን በሥጋ/
ከድንች ምርት የሚዘጋጁ ምግቦች
1. የድንች ችፒስ
2. የድንች ቅቅል
3. የድንች ዶራቶ
4. የድነች ፍርፍር
5. የድንች ገንፎ
6. የድንች ሾርባ
7. የድንች ቀይ ወጥ
8. የድንች ጥብስ
9. የድንች ክሮኬት
10. የድንች ኬክ
11. ከነልጣጩ የተጋገረ ድንች ጃኬት ፖታቶ ወይም ፕሬዝደንሻል
12. ተፈጭቶ በወተት የተሰራ ድንች ዱቼ ፖታቶ
13. በተንሽ ዘይት ደርቆ የተጠበሰ ድንች ፍረንች ፈራይድ ፖታቶ
14. የድንች አሮስቶ
15. የድንች አልጫ ወጥ
16. በኦቬን ቀንበር ያለ ድንች ግራትኔት ፖታቶ
17. የድንች ሰላድ
18. የድንች ድቡል
19. ተልጦና ተሰነጣጥቆ የተጋገረ ድንች ወዘተ…….
1. የአትክልት ሳላድ
ሰላድ ካሳቴ ካርሴ/Appetizer የምግብ ፍላጎት መክፈቻ ምግብነት ወይም እንደፍላጎት በዋና
ምግብነት ሊቀርብ የሚችል የምግብ ዕይነት ነዉ ፡፡
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
½ ኪሎ ሳላጣ
½ ኪሎ ቲማቲም
1 ራስ ቀይ ሽንኩረተ
2 ቃሪያ
200 ግራም ኪያር/ኩኬመበር
1 ኩባያ ቬኔግሬት ደርሰሲነግ/ቀዝቃዛ ማባያ/ስጎ
አዘገጃጀቱ
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
አዘገጃጀቱ
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
ሁለት እንቁላል
አንድ የሾርባ ማኒኪያ ዘይት ወይም ቅቤ
አዘገጃጀቱ
1. ዘይቱን ማጋል
2. አንዱን እንቁላል ሰብሮ በሳህን ማድረግ
3. በጋለዉ መጥበሻ ላይ ማፍሰስ
4. በምፈለገዉ ልክ ስበስል ማዉጣት
5. ሁ ለ ተ ኛ ዉ ን ም እ ን ቁ ላ ል በ ዚ ሁ መ ል ክ ማ ብ ሰ ል
6. በትማቲም ስጎ አስዉቦ ማቅረብ
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
ሁለት እንቁላል
ግማሽሊትር ዉሀ
ግማሽ ሻይ ማኒኪያ ጨዉ
አንድ ሻይ ማኒኪያ አቼቶ
አዘገጃጀቱ
አስፈላጊ ጥሬ እቃዎች
4 እንቁላል
50 ሚሊ ሊተር ወተት
1 የሾርባ ማኒኪያ የገበታ
ቅቤ
ጨዉና ቁንዶ ብርበሬ
ለጣዕም
አዘገጃጀቱ
1. እንቁላሉንና ወተቱን በእነቁላል መምቻ መምታት ጨዉና ቁንዶ በርበሬዉን ጨምሮ ማዋሄድ
2. ቅቤዉን በማይዝ መጥበሻ ላይ ማጋል
3. የተመታዉን እንቁላል ጨምሮ ለጥቅት ማማሰልና እነድ ስል ለአንድ ደቂቃ መተወ
4. ስበስል ማገላበበጥና ማዉጣት
5. ከዳቦ ጋር ማቅረብ
አዘገጃጀት
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
100 ሚሊ ሊትር ማዮነዝ
3 00 ግራም የተፈጨ ሥጋ
2 እንቁላል
100 ግራም የዳቦ ዱቄት
½ የሻይ ማንኪያ የደቀቀ ፐርሰሊ
100 ግራም ደቆ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
1 የሾርባ ማንኪያ የተፈቸ ነጭ ሽንኩርት
ቸዉና ቁንዶ በርበሬ ለጣዕም
1 የሾርባ ማንኪያ ፉርኖ ዱቄት
1 የሻይ ማኒኪያ የደቀቀ ሮዝመዘርኖ
1 የሻይ ማኒ ኪያ በርበሬ
2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
2 ዝንጣፊ የሰላጣ ቅጠል
3 ክብ የሐምበርገር ዳቦ
አዘገጃጀት
1. ከዘይት ከሰላጣ ከዳቦና ከቲማተም በስተቀር ሌሎቹን ጥሬ ዥቃዎች በሙሉ ቀላቅሎ በደንብ
በ.እጅ ማሸት
2. ሦስት ቦታ ከፍሎ በክብ ማድቦልቦልና መጠፍጠፍ
3. በግርል ወይም መጥበሻ ላይ በጋሌ ዘይት መጥበስ
4. ዳቦዉን ለሁለት ከፍሎ ማዮኔዙን መቀባት
5. አንዶ ቁራጭ ላይ የተጠበሰዉን ሥጋ ቀጥሎ ሰላጣ ዝንጣፊ ከዝያ አንድ ቲማቲም ካደረጉ
በኃላ ሌላ ቁራጭ ዳቦ ከላይ መደረብ
6. በዝህ መልኩ ቀሪዎቹን አዘጋጅቶ መጨረስ
7. ከድንች ጥብስና ካሮት ጋር ልቀርበ ይችላል፡፡
11. ክለብ ሳንደዊች ለ 6 ሰዉ /Club Sandwich /
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
1 ከሎ ግራም ዳቦ
150 ግራም ማዮኔዝ
200 ግራም ተቀቅሎ የተከተፈ የዶሮ ሥጋ
100 ግራም የተከተፈ ቲማቲም
100 ግራም የተከተፈ የሰላጣ ቅጠል
100 ግራም የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
3 የተከተፈ ቃሪያ
4 ተቀቅሎ የተከተፈ እነቁላል
200 ግራም ተቀቅሎ የተከተፈ የበሬ ሥጋ
200 ግራም ሶቴ ተደርጎ የተከተፈ ሞርተደላ
ጨዉና ቁንዶ በርበሬ ለጣዕም
አዘገጃጀት
1. ከዳቦ በስተቀር ጥሬ ዕቃዎቹን በሙሉ ከ ማዮኔዝ ጋር ቀላቅሎ መለወስ
2. ዳበዉን መጥበስ
3. በተጠበሰዉ ዳቦ በቂ ማዮኔዝ ማድረግ 2 ተኛዉን ዳቦ መደረብና ጫንጫን ማድረግ
4. በ2 ተኛዉ ዳቦ ላይ በቂ ማዮኔዝ ማድረግ
5. 3ተኛዉን ዳቦ መደረብ፤ ጫንጫን ማድረግና ዙሪያዉነ መስተካከል
6. በዝህ መልክ ሁሉንም ማዘገጀት
7. በ3 ማዕዘን አስተካክሎ መቁረጥና ከድንች ችፕስና ካቻፕ ጋር ማቅረብ፡፡
2 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
2 የሻይ ማንኪያ ነጭ ሽንኩርት
1 ቀይ ሽንኩረት
2 የደሮ መላላጫ
1 ካሮት
1 ደቆ የተከተፈ ቃሪያ
100 ግራም ትናንሽ ዳይሰ ካት የተደረገ ድንች
100 ሚሊ ሊትር የዶሮ መረቅ
1የ ሻይ ማንኪያ ሶያ ሶስ
1የ ሻይ ማንኪያ ስካር
ጨዉና ቁንዶ በርበረ ለጣዕም
ለልጡ
200 ግራም ዱቀት
1 የሾርባ ማንኪያ ስካር
ጨዉ ለጣዕም
2 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
1 እንቁላል
½ ኩባያ ዉሀ
1የእነቁላል አስካል ለኤግ ዋሽ
አዘገጃጀት
ማባያዉን ለማዘጋጀት
እስፒሪነረገረ ሮል
አዘገጃጀት
1. የዶሮ መላለጫዉን በቁመቱ መክተፍ
2. የዶሮ ሥጋዉን በትንሥ ዘይት መጥበስ
3. የአበባ ጎመኑን መጨመር
4. ወይኑን ጨምሮ ፍላንቤ ማድረግና በሳህን መገልበጥ
5. ኮርን እስታርቹን በዉሀዉ ማዋሄድና ሶያ ሶስ መጨመሮ የዶሮ ሥጋዉን በተጠበሰበት መጥበሻ
ማንተክተክ
6. ማባያዉ ስወፍር የዶሮ ሥጋዉን ጨምሮ ባገላበጥና ትኩሱን ማቀረብ
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
1. ቅቤዉን ማጋል
2. ሥጋዉን መጨመርና ወርቃማ እስኪመስል ማቁላላት
3. ቀይ ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ መብሰል
4. በርበሬዉን ጨምሮ ማማሰል
5. የቲማቲም ድልሁን ጨምሮ ማማሰል
6. መረቁን ከሙኑንና ቁንዶ በርበሬዉን ጨምሮ ትንሽካዋሄዱ ቦኃላ ማንተክተክ
7. ላዉሮ ቅጠሉን ጨምሮ ማብሰል
8. ተንተክትኮ መረቁ ስወፍር ማዉጣትና ከሩዝ ወይም ከድንች ቅቅል ጋር ማቅረብ፡፡
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
1ኪሎ ግራም ዱቀት
1 የሾርባ ማንኪያ እርሾ
1 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
ለብ ያለ ወሀ
1 የሾርባ ማንኪያ ስካር
3ጭልፋ የቲመቲም ስጎ
አዘገጃጀት
ዱቀቱን እርሾዉን ዘይቱንና ሱካሩን ጨምሮ ማሸትና እንዲቦካ መተዉ
ስቦካ መልሶ ማሸት
ሊጡን 10 ቦታ መከፋፈልና አድቦልቡሎ በመዳመጫ ክብ ቅርጽ
አንደወጣ አድርጎ መዳመጥ
ትንሽ ዘይት በተቀባ መጋገሪያ አድርጎ ቶማቶ ሶስ መቀባትና ቺዙን
መነስነስ
4. በ220 ድግሪ በሞቀ መጋገሪያ ለ20 ደቂቃ ማብሰልና በትኩሱ ማቀረብ፡፡
16. የሙዝ ማፍን ኬክ / Banana Muffins
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
1 ½ የመለኪያ ኩባያ ዱቀት
1 የሻይ ማኒኪያ ቤክንግ ፓዉደር
1 የሻይ ማኒኪያ ቤክንግ ሶዳ
1/2 የሻይ ማኒኪያ ጨዉ
3 ትላልቅ የተዳጠ ሙዝ
3/4 የመለኪያ ኩባያ ስካር
1 እንቁላል
1/3 የመለኪያ ኩባያ የቀለጠ ቅቤ
አዘገጃጀት
1. ኦቬኑን (175 ድጊሪ ማጋል). የማፍን መጋገሪያዉን መቀባት ወይም በየማፍን መጋገሪያዉ ቅርጽ
የተዘጋጀዉን ወረቀት ማድረግ
2. ዱቀቱን በክንግ ፓዉደሩንና በክንግ ሶዳዉን መቀላቀል
3. እንቁላልና ስኳሩን መምታት
4. ሁሉንም ጥሬ እቃዎች ማቀለቀል/መዋሄድና በማፍንመጋገሪያዉ መቅዳት
5. በሞቀዉ ኦቬን ከ 10-15 ደቂቃ መጋገር.
ድንች በሀገራችን በስፋት ከሚመረቱ ተክሎች አንዱ ከመሆኑም በላይ ዘርፌ ብዙ ጥቅሞችን የያዜ ነዉ
ይሄዉም ለምሳሌ፡-
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
. ደንች
. ጨዉ
. አቼቶ ወይም ሎሚ
. ዘይት
የአዘገጃጀት ቅድም ተከተል
ሐ. በክብ መቁረጥ
አዘገጃጀቱ
የ 3 ቱ ማዎች ትግበራ
ማስቀመጥ
ማስቀመጫ ቦታ፣ የማሻሻያ ዘዴና መመሪያ፡-
በኮሌጃችን ውሰጥ ካይዝንን በተፈለገው ደረጃ ለመተግበር እያንዳንዱን ትግበራ በትግበራ መመሪያ መፈጸም ውጤቱን የላቀ
እንደሚያደርገው በመገንዘብ አብይ የካይዝን ቡድን ይህንን የማስቀመጥ ትግበራ መመሪያ በሁሉም ከልቡዎች እንዲተገበር
አስተላልፋል
5 ክፍተቱንና ያስከተለውን ተፅዕኖ መዝኖ በማስቀመጥ መሻሻል የሚፈልገውን ደረጃ በግብ ማውጣት
6 አስፈላጊ ዕቃዎች እንደየአስፈላጊነታቸው በየቀኑ የሚፈለግ፤በሳምንት የሚፈለግ፤በወራት የሚፈለግ ተለየተው
እንዲቀመጡ
7 እንቅስቃሴን በመመጠንና ለእይታ ቁጥጥር በሚያመች መልኩ ሁሉም የከልቡ አባላት እንዲጠቀሙበት ማድረግ
8 የ 30 ሰከንድ አሠራር ውጤት ላይ ማድረስ
9 በማስቀመጥ ተግባር ተሻሽለው የተገኙ ውጤቶችን (ምርታማነት፣ ጥራት፣ ወጪን መቀነስ፣ አቅርቦትን
ማፋጠን፣ የሥራ ላይ ደህንነት፣ ከልቡዎችን ማነቃቃት፣ የሥራ አከባቢ እንዳይበከል ማድረግ፣
የሴቶች ተሳትፎ፣ የሥራ ቦታ ደረጃ) ውጤቶች ተመዝነው ለሁሉም የከልቡ አባላት ግልፅ በሆነ መልኩ
መረጃ ማድረስ
2 የማስቀመጥ እስታንዳርድ
ማጽዳት
1/ የማጽዳት ተግባር የሚከናወንበትን ቦታ፣ ቀንና ሰዓት መወሰን
4/ በወጣው የጽዳት ህግ መሰረት ሥራ ክፍፍል ተደርጎ ሁሉም ከልቡዎች በራሳቸው ተነሳሽነት መተግበር አለባቸው
8/ ሁሉም የሥራ ቦታዎችና ማሽኖች ከወዳደቁ ነገሮች፣ ከአቧራና ብናኝ የነፁ፣ ማራኪና አንፀባራቂ ማድረግ
የማጽዳት እስታንዳርድ
3/ ሰልጣኞች፤ አሰልጣኞች፤እና የተለያየ ክፍል ሰራተኞች የስራ ልብሶቻቸው በፕሮግራሙ መሰረት ማጥዳት
4/ ማሽኖች በጽዳት ጊዜ መሸፈን አለባቸው 4
የማላመድ ጥቅሞች
ብክነቶችን ማስወገድ
ጥራትን ማሻሻል
ወጪን መቀነስ
የ 5 ቱማ ፍተሻ ማድረግ
5
የካይዘን ስርዓት
የሰውና የማሽን ደህንነት አጠባበቅ መመሪያ በአንድ ድርጅት መኖር ማንኛዉም ሰዉም ሆነ ባለሙያ በመ/ቤቱ ዉስጥ
በሚነቀሳቀስበት ጊዜና በሚሰራበት ወቅት አዉቆትና አክብሮት በመተግበር ራሱንና የመ/ቤቱን ንብረት ከአደጋ
የሚከላከልበት ስልት ነዉ፡፡
ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የሚተገበር ሲሆን ቅድሚ የሚሰጠዉ በአሰልጣኙም ሆነ በሰልጣኙ ላይ ሊፈጠር የሚገባ የራስን
የደህንነት አጠባበቅ ደንቦች ላይ ነዉ፤፤ እነዚህም በመረጃ ሰሌዳ ላይ በመለጠፍና በዉይይቶች ጊዜ በአጀንዳነት በመያዝ
የራስ ሊያደርጋቸዉ ይገባል፡፡
ምስጋና
ይህ በወቅቱ ወጥ በሆነ መልኩ ስልጠና ለመስጠት ተፈልጊ የሆነዉን የዘርፉም እቅድ የነበረዉን በተገባር ላየ
በማዋል የሠልጠና መርጃ መሣሪያ ለማዘጋጀት ቅድመ ሁነታዎችን በማመቻቼት ዉጠት ተኮር ሥራ እንድሰራ
የረዳንን የደቡብ ቴ/ሙ/ት/ሥ/ብሮና አቶ ግረማ በፈቃዱና ባልደረቦቹን በሙያ አጋሮቼ ስም አመሰግናለሁ፡፡