You are on page 1of 94

ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር

የስልጠና ፓኬጅ

መግቢያ

ዶሮ በኢትዮጵያ በገጠርም ሆነ በከተማ በተለያየ የእርባታ ደረጃ ይካሄዳል፡፡ ዶሮ ማርባት የተለያዩ ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ይኼውም ለገቢ ምንጭ ማስገኛነት ፣ ለምግብነት እና የስራ ዕድል መፍጠር
በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ኢትዮጵያ 41 ሚሊዮን ዶሮዎች እንዳሏት ይገመታል፡፡ አንድ የሀገር ውስጥ ዝርያ ዶሮ
በዓመት ከ 40 – 60 ዕንቁላሎችን ስትጥል የተሻሻሉ የውጪ ዝርያዎች ደግሞ በተመሳሳይ ጊዜ የሚጥሉት
ዕንቁላል 380 ይደርሳል፡፡

የዶሮ ዕርባታ በመጠነኛ ካፒታል ሊጀመርና ሊካሄድ የሚችል ቢሆንም ብዙ ሰዎች እንደሚያምኑት ያለምንም
ትኩረትና ጥንቃቄ ውጤት የሚገኝበት አይደለም፡፡ የዶሮ ዕርባታን እንደመተዳደሪያ የማድረግ ሀሳብ ያለው
ሰው ስለ ዶሮዎች ተፈጥሮና መሰረታዊ የአያያዝ ዘዴዎች ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህ መማሪያ ማንዋል
የተዘጋጀው ሰልጣኝ ተማሪዎች ከታች በቀረቡት ዋና ዋና አርዕስቶች አስፈላጊውን መረጃ እንዲያገኙና
ዕውቀትና ክህሎታቸውን ማሳደግ እንዲችሉ ነው፡፡

 የዶሮ ዕርባታ ሁኔታ


 የዶሮ ዕርባታ ከሌሎች የእንስሳት ዕርባታ ጋር ያለው ልዩነት
 የዶሮ ዕርባታ አመሰራረት
 የዶሮ ዝርያዎችና ባህሪያቸው
 የዶሮ ዝርያ አመራረጥና ምርታማ ዶሮዎችን የመለያ ዘዴዎች
 የዶሮዎች መኖና አመጋገብ
 የዶሮዎች ጤና አጠባበቅ
 የዶሮዎች አያያዝ
 የዶሮዎች መጠለያ(ቤት) እና አሰራር
 የዶሮ ዕርባታ መረጃ አያያዝ

ይህ ማንዋል በአጭር ስልጠና ፓኬጅ የተጠቀሱትን የዶሮ ዕርባታ የብቃት ዓህዶችን በብቃት ለማጠናቀቅ
የሚያግዝ ሲሆን ይህን መማሪያ ማንዋል ካጠናቀቁ በኃላ የሚከተሉትን ማወቅና በብቃት ማከናወን
ያስችሎታል ፡-

 በአገራችን የዶሮ ዕርባታ ሁኔታና የዘመናዊ ዶሮ ዕርባታ አጀማመር


 የዶሮ ዕርባታ ያለው ጥቅምና ጉዳት
 የዶሮ ዕርባታ አመሰራረት መሰረታዊ ታሳቢዎችና ሊተኮርባቸው የሚገቡ ነጥቦች
 ተስማሚ ዘመናዊ የዶሮ ዝርያዎችና ምርታማነታቸው
 ተስማሚ የዶሮ ዝርያ የመምረጫ መስፈርቶችና ምርታማ የሆኑ ዶሮዎችን የመለያ ዘዴዎች
 የዶሮ መኖ ንጥረ-ምግብ እና ጥሬ ዕቃዎች
 የዶሮ በሽታ መከላከያ መንገዶች
 የጫጩት ፣ የታዳጊ ፣ የዕንቁላል ጣይ እና የሥጋ ዶሮ አስተዳደግ
 የዶሮ ቤት አስፈላጊነትና ዓይነት
 የዶሮ ዕርባታ መረጃ አያያዝና የተለያዩ የመረጃ ቅፆች

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 1


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ይህን የመማሪያ ማንዋል እንዴት ይጠቀሙታል?

1. የመማሪያ ማንዋልን በአግባቡ አንብቦ መረዳት


2. በገለፃ-1 ፣ 2 ፣ 3 የተገለፁትን ዝርዝር መረጃዎች በአግባቡ አንብቦ መረዳት
3. በሙከራ-1 የተቀመጡትን የገለፃ-1 ፣ 2 ፣ 3 ጥያቄዎች በመስራት ራስን መመዘን
4. በሙከራ-1 የተቀመጡትን ጥያቄዎች በመስራት አጥጋቢ ውጤት ካመጡ ወደ ገለፃ-4 ፣ 5 መሸጋገር
ነገር ግን አጥጋቢ ውጤት ካላመጡ አሰልጣኝ መምህሮን ለተጨማሪ እገዛ ያማክሩ ወይም ወደ ገለፃ-1
፣ 2 ፣ 3 በመመለስ በድጋሚ በጥንቃቄ አንብበው ይረዱ
5. የሙከራ-1 መልስ ለአሰልጣኝ መምህሮ ይላኩ፡፡ የሰልጣኝ ተማሪዎች ውጤት በፋይል ይቀመጣል፡፡
6. በገለፃ-4 ፣ 5 የተገለፁትን ዝርዝር መረጃዎች በአግባቡ አንብቦ መረዳት
7. በሙከራ-2 የተቀመጡትን የገለፃ-4 ፣ 5 ጥያቄዎች በመስራት ራስን መመዘን
8. በሙከራ-2 የተቀመጡትን ጥያቄዎች በመስራት አጥጋቢ ውጤት ካመጡ ወደ ገለፃ-6 መሸጋገር ነገር
ግን አጥጋቢ ውጤት ካላመጡ አሰልጣኝ መምህሮን ለተጨማሪ እገዛ ያማክሩ ወይም ወደ ገለፃ-4 ፣ 5
በመመለስ በድጋሚ በጥንቃቄ አንብበው ይረዱ
9. የሙከራ-2 መልስ ለአሰልጣኝ መምህሮ ይላኩ፡፡ የሰልጣኝ ተማሪዎች ውጤት በፋይል ይቀመጣል፡፡
10. በገለፃ-6 የተገለፁትን ዝርዝር መረጃዎች በአግባቡ አንብቦ መረዳት
11. በሙከራ-3 የተቀመጡትን ጥያቄዎች በመስራት ራስን መመዘን
12. በሙከራ-3 የተቀመጡትን ጥያቄዎች በመስራት አጥጋቢ ውጤት ካመጡ ወደ ገለፃ-7 መሸጋገር ነገር
ግን አጥጋቢ ውጤት ካላመጡ አሰልጣኝ መምህሮን ለተጨማሪ እገዛ ያማክሩ ወይም ወደ ገለፃ-6
በመመለስ በድጋሚ በጥንቃቄ አንብበው ይረዱ
13. የሙከራ-3 መልስ ለአሰልጣኝ መምህሮ ይላኩ፡፡ የሰልጣኝ ተማሪዎች ውጤት በፋይል ይቀመጣል፡፡
14. በገለፃ-7 የተገለፁትን ዝርዝር መረጃዎች በአግባቡ አንብቦ መረዳት
15. በሙከራ-4 የተቀመጡትን ጥያቄዎች በመስራት ራስን መመዘን
16. በሙከራ-4 የተቀመጡትን ጥያቄዎች በመስራት አጥጋቢ ውጤት ካመጡ ወደ ገለፃ-8 ፣ 9 ፣ 10
መሸጋገር ነገር ግን አጥጋቢ ውጤት ካላመጡ አሰልጣኝ መምህሮን ለተጨማሪ እገዛ ያማክሩ ወይም
ወደ ገለፃ-7 በመመለስ በድጋሚ በጥንቃቄ አንብበው ይረዱ
17. የመልመጃ-3 መልስ ለአሰልጣኝ መምህሮ ይላኩ፡፡ የሰልጣኝ ተማሪዎች ውጤት በፋይል ይቀመጣል፡፡
18. በገለፃ-8 ፣ 9 ፣ 10 የተገለፁትን ዝርዝር መረጃዎች በአግባቡ አንብቦ መረዳት
19. በሙከራ - 5 የተቀመጡትን ጥያቄዎች በመስራት ራስን መመዘን
20. በሙከራ - 5 የተቀመጡትን ጥያቄዎች በመስራት አጥጋቢ ውጤት ካመጡ ወደ ተግባር መማሪያ
መሸጋገር ነገር ግን አጥጋቢ ውጤት ካላመጡ አሰልጣኝ መምህሮን ለተጨማሪ እገዛ ያማክሩ ወይም
ወደ ገለፃ-8 ፣ 9 ፣ 10 በመመለስ በድጋሚ በጥንቃቄ አንብበው ይረዱ
21. የሙከራ-5 መልስ ለአሰልጣኝ መምህሮ ይላኩ፡፡ የሰልጣኝ ተማሪዎች ውጤት በፋይል ይቀመጣል፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 2


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

22. የተግባር መማሪያውን በአግባቡ ማንበብ፣በስሩ የተጠቀሱትን ዝርዝር የክንውን ደረጃዎች በጥንቃቄ
አንብቦ መረዳትና መተግበር፡፡ ማንኛውም ግልጽ እንዲሆንሎት የሚፈልጉት ጥያቄ ካልዎት አሰልጣኝ
መምህሩን ይጠይቁ፡
23. የሰሩትን ተግባር ለአሰልጣኝ መምህሮ በማሳየት ግብረ-መልስ ይቀበሉ
24. የተግባር ሙከራዎችን ይስሩ፣ ለአሰልጣኝ መምህሮ ያሳዩ፣ አሰልጣኝ መምህሩ የሰሩትን ተግባር
በመገምገም አጥጋቢ ወይም ደካማ በሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡ ደካማ ውጤት ከሆነ ለተጨማሪ የሙከራ
ፈተና መዘጋጀት፣ አጥጋቢ ውጤት ከሆነ ለሚቀጥለው የመማሪያ ማንዋል መዘጋጀት

1. የዶሮ ዕርባታ ሁኔታና የዘመናዊ ዶሮ ዕርባታ አጀማመር በኢትዮጵያ


1.1. የዶሮ ዕርባታ ሁኔታ
1.1.1. የተለምዶ ዕርባታ
በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሚከናወኑት የዶሮ ዕርባታዎች በስፋት የሚታየው የተለምዶ ወይም ባህላዊ
ዕርባታ ነው፡፡ ይህ በአብዛኛው የገጠር አካባቢዎች በተለምዶ ለቤተሰብ ፍጆታና ጥቂት ገቢ ለማግኘት ሲባል ፣
በጥቂት የአገር ዝርያ ዶሮዎች የሚካሄድ ነው፡፡ በመሆኑም በአነስተኛ ደረጃ የሚመደብ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ የዶሮ
ዕርባታ አትራፊና የኑሮ መሰረት ሊሆን የሚችል የስራ መስክ ሳይሆን እንደ ተጨማሪ ስራ የሚቆጠር በመሆኑ
ተገቢ ትኩረት አይሰጠውም፡፡ ዶሮዎቹ ያለምንም ግብዓት ጭረው እንዲኖሩና ምርት እንዲሰጡ የሚጠበቅ
ቢሆንም ያለግብዓት ውጤት ማግኘት ግን አስቸጋሪ ነው፡፡ ዶሮዎች ለማደግና ምርት ለመስጠት
እንደማንኛውም እንሰሳ ቢያንስ በቂ ምግብና ውሃ ማግኘት አለባቸው፡፡ በአጠቃላይ ያለምንም ቁጥጥር
የሚንቀሳቀሱ ፣ መኖሪያ ቤት የሌላቸው ፣ ተከታታይ የጤና ክትትል የማደረግላቸው ፣ አስፈላጊ የዶሮ ቤት
ቁሳቁስ ያልተሟላበት ፣ ንጽህና የማይጠበቅበት ፣ የተመጣጠነ መኖ በአግባቡ ለዶሮዎች የማቀርብበት በህላዊ
የአረባብ ሁኔታ ነው፡፡ ተከታታነት ያለው የጤና ቁጥጥር የማይደረግላቸው ፣ ከተለያዩ ዶሮዎች ጋር የሚገናኙና
የተመጣጠጠነ መኖ የማይቀርብላቸው ዶሮዎች በቀላሉ ለበሽታ ይጋለጣሉ፡፡ በተለምዶ ዕርባታ የሚገኘው
የዕንቁላል ወይም ስጋ ምርት እጅግ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ከቤተሰብ ፍጆታ አልፎ ለገበያ የሚቀርብ ምርት
አይኖረውም ወይም ዝቅተኛ ነው፡፡ ከላይ በተገለጸው መሰረት ከተለምዶ የአረባብ ሁኔታ መገለጫዎች መካከል
ልናጤናቸውና ልናተኮርባቸው እንዲሁም ልናሻሽላቸው የሚገቡ ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው ፡-

 ዓላማው የቤተሰብ የምግብ ፍጆታን መሸፈን መሆኑ (ትርፍን መሰረት ያላደረገ ዕርባታ መሆኑ)
 ጥቂት የሀገር ውስጥ ዶሮዎችን መጠቀሙ
 የዶሮ መጠለያ አለመጠቀሙ
 ለዶሮ ዕርባታ አስፈላጊ ግብዓቶችን አለመጠቀሙ
አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 3
ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 የተመጣጠነ መኖና ንጹ ውሃ አቅርቦት አለመኖሩ


 የጤና ክትትል አለመኖሩ

1.1.2 አነስተኛ ዘመናዊ እርባታዎች


እነዚህ ዘመናዊ ሊባል የሚችል የተሻለ የዶሮዎችን አያያዝን የሚከተሉ እርባታዎች ሲሆኑ ፣ ዓላማቸውም
ትርፍ ነው፡፡ እርባታዎቹ በአብዛኛው ከ 50 – 500 ዘመናዊ የዶሮ ዝርያዎችን ይጠቀማሉ፡፡ እንዲህ አይነት
እርባታዎች በተለይ እንደ አዳማ ፣ ደብረዘይት ፣ ሰበታ ባሉ ከተሞችና አካባቢያቸው በመስፋፋት ላይ የሚገኙ
ናቸው፡፡ በአነስተኛ ዘመናዊ እርባታዎች ከተለምዶ እርባታ በተለየ ለዶሮዎቹ የተመጣጠነ መኖና ንጹ ውሃ
የቀርብላቸዋል፡፡ ዘመናዊ ሊባል የሚችል የዶሮ መጠለያ ሲኖራቸው መካከለኛ የሆነ የጤና ክትትል
ይደረግላቸዋል፡፡ በተለያዩ ከተሞችና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ ስራ አጥ ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም
በጡረታ ከስራ የተፈናቀሉ አዋቂዎች በጥ/አ/ኢ/ዞች በመደራጀትና በከተማ ግብርና የስራ ዘርፎች
በመሰማራታቸው በአሁን ወቅት አነስተኛ ዘመናዊነ የዶሮ እርባታ እየተስፋፋ ያለ ዋንኛ የስራ መስክ እየሆነ
መቷል፡፡

በአጠቃላይ አነስተኛ ዘመናዊ እርባታዎች የሚከተሉት ዋና ዋና መገለጫዎች አሉት ፡-

 ትርፍን መሰረት ያደረገ መሆኑ


 ዘመናዊ የዶሮ ዝርያዎች መጠቀሙ
 የተመጣጠነ መኖና ንጹ ውሃ አቅርቦት መኖሩ
 መካከለኛ የቁሳቁስ አቅርቦት መኖሩ
 የዶሮ መጠለያ መኖሩ
 መካከለኛ የጤና ክትትል መኖሩ

1.1.3 ትላልቅ ዘመናዊ እርባታዎች


በአገራችን የተለያዩ ዘመናዊ የዶ ዝርያዎችን (የስጋና የዕንቁላል) የሚጠቀሙና ለንግድ ዓላማ የተቋቋሙ ጥቂት
የዶሮ እርባታዎች ይገኛሉ፡፡ ትላልቅ ዘመናዊ እርባታዎች ሙሉ ለሙሉ በቤት ውስጥ የማርባትና ዘመናዊ
የሆነ የዶሮ አያያዝ ዘዴዎችን በመከተል ይንቀሳቀሳል፡፡ በትላልቅ ዘመናዊ እርባታዎች ከ 10 ሺ በላይ
ዘመናዊ ዶሮዎች የማርባት አቅም ሲኖረው የተሸሻሉ የዶሮ ዝርያዎችን ለጥ/አ/ኢ/ዞች ያከፋፍላል፡፡
እጅግ በጣም ዘመናዊ የዶሮ መጠለያ ፣ ቁሳቁስ ፣ የተመጣጠነ መኖና ንጹ ውሃ ፣ ከፍተኛ የቴና

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 4


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ክትትልና ቁጥጥር የሚከተሉ ዕርባታዎች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ከትላልቅ ዘመናዊ እርባታዎች ዋና ዋና


መገለጫዎች የሚከተሉት ናቸው ፡-

 ዓላማቸው ንግድ መሆኑ


 ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዘመናዊ የዶሮ ዝርያዎችን መጠቀሙ
 ዘመናዊ የዶሮ አያያዝ መጠቀሙ
 ከፍተኛ የጠየና ቁጥጥርና ክትትል መከተሉ

1.2 የዘመናዊ እርባታ አጀማመር


የውጪ ዶሮዎች ዝርያዎችና የተሸለ የዶሮዎች አያያዝ ዘዴ ወዳገራችን የገባው ቀደም ሲል
በሚስዮናውያን አማካይነት ቢሆንም በተጨባጭ ዘመናዊ የዕርባታ ዘዴንና ዝርያዎችን ማስተዋወቅ
የተጀመረው እ.አ.አ ከ 1953 (1946 በኢትዮጵያ አቆጣጠር) ጀምሮ ነው፡፡ ይህ ከጅማ ት/ቤት ፣ አዓለማያ
እርሻ ኮሌጅ እንዲሁም ከግብርና ምርምር ጣቢያዎች (ጂማ ፣ ዓላማያ ፣ ደብረ ዘይት) መቋቋም ጋር
የተያያዘ ነበር፡፡በዚህ ወቅት አራት የውጪ የዶሮ ዝርያዎች ማለትም ፡-

 ሮድ አይላንድ ሬድ
 አውስትራሎፕ
 ኒውሃምሻየር
 ኃይት ሌግ ሆርን

የተባሉ ከኬኒያ ፣ ከዴንማርክና ከአሜሪካ ወደ ጅማና ዓላማያ ለሙከራ እንዲገቡ ተደረጉ፡፡የተለያዩ


ሙከራዎች ከተካሄዱ በኃላ ከሁለቱ ጣቢያዎች ፣ እንዲሁም ከ 1950 በኢትዮጵያ አቆጣጠር በኃላ
ከደብረ ዘይት ምርምር ጣቢያ ፣ ዝርያዎቹ በብዛት እየተራቡ መሰራጨት ጀመሩ፡፡ እነዚህ ተቋማት
ዝርያን ማሰራጨት ሳይሆን ስለተሸሻለ አመጋገብ ፣ አያያዝ ፣ ቤት አሰራር ወዘተ አስተምረዋል ፣
የኤክስቴንሽን ስራም አካሂደዋል፡፡ ብዙ ወጣት አርቢዎች ማህበራትንም አቋቁመዋል፡፡ በዚህ ዓይነት
የተቀናጀና ሰፊ እንቅስቃሴ ተጀምሮ ዘመናዊ የዶሮ ዕርባታን ለማስፋፋት የተደረገው ጥረት በሀገራችን
ዘመናዊ እርባታዎች እንዲጀምሩ መሰረት ጥሏል፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 5


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ
- ሮድ አይላንድ ሬድ - ኒውሃምፕ ሻየር

- ኃይት ሌግ ሆርን - አውስትራሎፕስ - ሴት ዶሮ

ምስል 1 ፡- ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሀገራችን ለሙከራ የገቡ


የተሸሻሉ ዘመናዊ የዶሮ ዝርያዎች

አውስትራሎፕስ - ወንድ ዶሮ

2. የዶሮ ዕርባታ ከሌሎች የእንስሳት ዕርባታ ጋር ያለው ልዩነት

በአሁኑ ወቅት በተለይ በከተማ አካባቢ እየተስፋፋ ያለ የስራ መስክ ቢኖር የዶሮ ዕርባታ ነው፡፡ ከላይ
በክፍል አንድ እንደተገለጸው በሀገራችን ገጠሮች የሚገኙ ገበሬዎች ዶሮዎችን በተለምዶ ያረባሉ፡፡ በዚህ ደረጃ
የሚካሄድ እርባታ ምንም ዓይነት ግብዓት ሳይኖረው ዶሮዎቹ በራሳቸው የሚያስፈልጋቸውን ምግብና ውሃ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 6


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ፈልገው ራሳቸውን የሚንከባከቡበት ነው፡፡ ከዚህ ዓነቱ እርባታ ከራስ ፍጆታ አልፎ ለገበያ የሚቀርብ ምርት
በጣም ትቂት ነው፡፡ በተለምዶ ዶሮ ማርባት ሁኔታ ከሌሎች የእንስሳት እርባታ ጋር ያለውን ልዩነት መረዳት
አይቻልም፡፡ የዶሮ ዕርባታ ከሌሎች እንሰሳት ዕርባታ ጋር ያለውን ልዩነት ለመረዳት ስለ ዘመናዊ የዶሮ ዕርባታ
ማሰብ ይኖርብናል፡፡ ዘመናዊ የዶሮ ዕርባታ ሊባል የሚችለው ለገቢ ምንጭነት እንዲውል ታስቦ እንደአንድ
አትራፊ የስራ መስክ ሲወሰድ ነው፡፡ በብዙ አገሮች ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በአገራችን ፣ በዘመናዊ የገበያ
ስርዓትና መርሆዎች ላይ የተመሰረቱ እርባታዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ረገድ ዘመናዊ የዶሮ እርባታ
ከሌሎች የእንስሳት እርባታ ጋር ያለውን ልዩነት በቀላሉ ለመረዳት ያስችላል፡፡ ለዚህም ትልቁ ማሳያ የሚሆነው
በአሁኑ ወቅት በተለይ በከተማው የሚገኘው ማህበረሰብ ስለ ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ያለው ግንዛቤ እየጨመረ
በመምጣቱ የዶሮ ዕርባታ ከሌሎች እንስሳት ዕርባታዎች በተለየ በመስፋፋት ላይ የሚገኝ የስራ መስክ መሆኑን
ማሳየት ይቻላል፡፡ ዘመናዊና ለትርፍ የሚካሄድ የዶሮ እርባታ ከሌሎች እንሰሳት ዕርባታ ጋር ያለውን ልዩነት
በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡

 የሚያበረታቱ ልዩነቶች
 የማያበረታቱ ልዩነቶች
2.1. የሚያበረታቱ ልዩነቶች
የሚያበረታቱ ልዩነቶች ስንል ሰዎች በዶሮ ዕርባታ እንዲሰማሩ የሚገፋፋቸውን ሁኔታዎች የሚመለከት
ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው በአሁኑ ወቅት በተለይ በከተማ አካባቢ እየተስፋፋ ያለ የስራ መስክ ዶሮ ዕርባታ
ነው፡፡ በዶሮ ዕርባታ መሰማራት ከሌሎች እንስሳት ዕርባታ ጋር ስናወዳድረው የተለየ የሚሰጠው ጥቅም
ይኖረዋል፡፡ የሚከተሉት ሁኔታዎች ዘመናዊና ለትርፍ የሚካሄድ የዶሮ ዕርባታን ለማቋቋም የሚያበረታቱ
ምክንያቶች ናቸው፡፡

 የዶሮ ዕርባታ በማንኛውም መጠን ማቋቋም ይቻላል፡፡ እርባታውን ለማከናወን የግድ ሰፊ መሬት
ስለማይጠይቅ ባለችን ውስን መሬት ላይ በአነስተኛ መጠን ወይም በከፍተኛ መጠን ዕርባታውን
ማቋቋም ያስችላል፡፡ 4 ሜትር በ 4 ሜትር በሆነ ስፍራ በመሬት ላይ የማርባት ዘዴ ከተጠቀምን እስከ
50 ዶሮዎችን ማርባት እንችላለን ፣ በቆጥ ላይ የማርባት ዘዴ ከተጠቀምን (36 Layer in one mesh-
wire Cage with 4 floor(120L x 70W x 200H cm) ከ 400 በላይ ቁጥር ያላቸውን ዶሮዎች ማርባት
ያስችለናል፡፡ ነገር ግን በሌሎች እንስሳት እርባታዎች(ለምሳሌ፡- ወተት ዕርባታ) ለማቋቋም ሰፊ
መሬትን ይጠይቃል፡፡
 የዶሮ ዕርባታን ከተለያዩ የዓየርና ሌሎች የአካባቢ ሁኔታዎች ጋር አጣጥሞ ማካሄድ ይቻላል፡፡ የዶሮ
ዕርባታ ከሌሎች እንስሳት እርባታ በተለየ በሞቃታማም(ቆላ) ሆነ በቀዝቃዛማ(በደጋማ) አካባቢዎች
ማቋቋም ይቻላል፡፡ ለምሳሌ፡- የፍየል ዕርባታ በአብዛኛው የሚከናወነው በሞቃታማ ፣ የበግ ዕርባታ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 7


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

በቀዝቃዛማ አካባቢ ነው፡፡ በአገራችን ከፍተኛ የፍየል ቁጥር ያለው በቆላ አካባቢ መሆኑና ከፍተኛ የበግ
ቁጥር የሚገኘው በደጋማ አካባቢ መሆኑ ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡
 የዶሮ ዕርባታ በማንኛውም ወቅት ሊካሄድ የሚችል ስራ ስለሆነ ዓመቱን ሙሉ ምርትና ገቢን
ሊያስገኝ ይችላል፡፡ አንዲት ዕንቁላል ጣይ ሴት ዶሮ ምርት ለመስጠጥ ከአውራ ዶሮ ጋር መገናኘት
አያስፈልጋትም ፣ ለመገናኘትም የምታሳየው ፍላጎት ከወቅቶች ተጽኖ ነፃ በመሆኑ ዓመቱን ሙሉ
ምርት መስጠት ትችላለች፡፡ ከፍየልና በግ ዕርባታ አንድ ግልገል ለማግኘት ሴቷ ፍየል ወይም በግ
ከወንዱ ፍየል ወይም በግ ጋር ለመገናኘት የምታሳየው ፍላጎት በወቅቶች ተጽእኖ ስር የወደቀ ነው፡፡
ስለሆነም ዕርባታውን ለማቋቋም ለሴቷ ፍየል ወይም በግ ተስማሚ የሆነውን ወቅት ለይተን ማወቅ
ይኖርብናል፡፡
 የዶሮ ዕርባታ ከሌሎች የርባታ ስራዎች ጋር ሲወዳደር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለገበያ የሚቀርብ ምርትን
ያስገኛል፡፡ ለምሳሌ፡- ዘመናዊ የስጋ ዶሮዎችን ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለገበያ ማቅረብ የሚቻል
ሲሆን፣ ዘመናዊ የዕንቁላል ዶሮዎችም ከአምስት ወር ተኩል ጀምረው በተከታታይ ዕንቁላል ይጥላሉ፡፡
ነገር ግን በሌሎች እሰሳት እርባታ ለምሳሌ ወተት ዕርባታ ፣ ከአንዲት ላም የወተት ምርት ለማግኘት
ጥጃ መስጠት አለባት ፣ ስለሆነም አንዲት ላም ከተወለደች በኃላ በአማካኝ አንድ ዓመት ከአምስት
ወር ዕድሜ ሲሞላት ለአቅመ-መጠቃት ትደርሳለች ፣ የመጀመሪያ ልጇን ፀንሳ ለመውለድ ዘጠኝ ወር
ይፈጅባታል፡፡ የመጀመሪያ ልጇን ከወለደች በኃላ የወተት ምርት መስጠት ትጀምራለች፡፡ በጠቅላላው
አንዲት ላም ከተወለደችበት ቀን ጀምሮ የወተት ምርት እስከምትሰጥ ድረስ ከ 2 – 2.5 ዓመት
መጠበቅ ይኖርብናል፡፡
 የዶሮ ዕርባታ ከሌሎች የእንሰሳት እርባታ ስራዎች ጋር ሲወዳደር አነስተኛ የኢንቨስትመንት መነሻ-
ካፒታል የሚጠይቅ ሲሆን ፣ በአጭር ጊዜም ወጪን ሊመልስ የሚችል የስራ መስክ ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
በቀላሉ የወተት ዕርባታን ብንመለከት የአንዲት ላም ዋጋ ከ 15,000 ሺ እስከ 20,000 ሺ ብር ነው ፣ ይህ
የሚያሳየው ከፍተኛ የሆነ መነሻ-ካፒታል እንደሚጠይቅ ነው፡፡
 አስፈላጊው ዝግጅት ከተሟላ የዶሮ ዕርባታ የሚጠይቀው የሰው ኃይል(ጉልበት) በጣም አነስተኛ ነው፡፡
 ዶሮዎች በአብዛኛው በቀጥታ ለሰው ምግብነት የማይውሉ ጥሬ-ዕቃዎችን ከብዙዎች የርባታ እንስሳት
በተሸለ ብቃት ከፍተኛ ዋጋ ወዳለውና ለሰው ምግብነት እጅግ ጠቃሚ ወደሆነ ምርት የመቀየር ችሎታ
አላቸው፡፡ ለምሳሌ፡- የኑግ ፋጉሎ - ፕሮቲን
 የሚገኘው ኩስ ለማዳበሪያነት ከሌሎች እንስሳት የበለጠ ጠቄሜታ አለው፡፡ የዶሮ ኩስ ለከብቶች ፣
ለበጎችና በኩሬ ውስጥ ለሚረቡ አሳዎች መኖነት ከፍተኛ ጥቅም ስላለው ለከብቶችና ለበጎች
ማደለቢያነት ከፍተኛ ጥቅም በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 8


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 በቀላሉ ቁጥራቸውን መጨመር ይቻላል፡፡ አንዲት ሴት ዶሮ ከ 5 ወር ተኩል ዕድሜዋ በኃላ ዕንቁላል


መጣል ትጀምራለች፡፡ በተፈጥሮ የማስፈልፈል ዘዴ አንዲት ዕንቁላል ጣይ ሴት ዶሮ ከ 8-12
ዕንቁላሎችን መታቀፍ ትችላለች በሌላ በኩል በሰው ሰራሽ ማስፈልፈያ ዘዴ(Egg Incubator) እስከ
20,000 ዕንቁላሎችን ማስፈልፈል ይቻላል፡፡ በሁለቱም የማስፈልፈያ ዘዴዎች ዕንቁላሉ ለመፈልፈል
21 ቀን በአማካኝ ይፈጅበታል፡፡ ስለዚህ በዚች አጭር ጊዜ ውስጥ ምን ያክል የዶሮ ቁጥር ሊኖረን
እንደሚችል አስተውላችዋል?? በሌሎች እንስሳት ለምሳሌ አንዲት ጊደር በ 1.5 ዕድሜዋ ትጠቃለች ፣
ከ 9 ወር በኃላ አንድ(መንታ) ጥጃ ትሰጣለች፡፡ በጠቅላላው ከ 2 ዓመት ከ 2 ወር በኃላ ቁጥራቸው 3 ሆኑ
ማለት ነው፡፡
 በቀላሉ ሊሸጡ ይችላሉ፡፡ የዶሮዎቹ የዕንቁላል ምርት ዘመን እየቀነሰ በሚመጣበት ወቅት ወይም
እርባታው አልተስማማኝም የስራ ለውጥ ማድረግ ይኖርብኛል በምትሉበት ወቅት ዶሮዎቹን በቀላሉ
መሸጥ ይቻላል፡፡
 ዘመናዊ የዶሮ ዕርባታ የአየር ንብረት ለውጥ በማስከተል ረገድ ዜሮ ሚና ነው ያለው፡፡ በአፍሪካ አህጉር
የሚገኙ አገራት ዌም በማደግ ላይ ያሉ አገራቶች ለአየር ንብረት ለውጥ ትልቁን ሚና የሚጫወቱት
ከኢንዱስትሪ በሚለቀቅ ጭስ(ካርበን ልቀት) ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ በሚታየው የህዝብ ቁትር ዕድገት
አማካኝነት በሚከሰተው የደን መጨፍጨፍ እና ባህላዊ ወይም በተለምዶ የግብርና ዘዴ በሚፈጠረው
የበረሃ መስፋፋት ነው፡፡ የዶሮ እርባታ በአነስተኛ መሬት ላይ በተፈለገው መጠን ማቋቋም በመቻሉና
የግጦሽ መሬት የሚፈልግ ባለመሆኑ የአየር ንብረት ለውጥ በማስከተል ረገድ ዜሮ ሚና ነው ያለው፡፡
2.2 የማያበረታቱ ምክንያቶች
ይሁንና እንደሌሎች የስራ ዘርፎች ሁሉ የዶሮ እርባታም ከስራው ጋር የተያያዙ ችግሮች አሉበት፡፡ ይህ ማለት
ሰዎች ወደ ዶሮ ዕርባታ እንዳይሰማሩ የማያበረታቱ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ ከዶሮዎችና
ከምርታቸው ተፈጥሮና ባህርይ ከሚመነጩ ችግሮች መካከል የሚከተሉት ዋናዎቹ ናቸው፡፡

 ዶሮዎች በተፈጥሯቸው በተለያዩ በሽታዎች በቀላሉ የሚጠቁ በመሆናቸው ለመከላከል ከፍተኛ


ትንቃቄ ይሻሉ፡፡ በሽታ ከተከሰተም ለመቆጣጠር ወጪንና ክትትልን ይጠይቃሉ፡፡
 ከዶሮ የሚገኙ ውጤቶች ፣ ማለትም ዕንቁላልና በተለይ ሥጋ በቀላሉና በአጭር ጊዜ የሚበላሹ ስለሆኑ
በወቅቱ ገበያ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለረጅም ጊዜ ሳይበላሹ ለማቆየት ከተፈለገም ከፍተኛ ወጪን
ይጠይቃሉ፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 9


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

3. የዶሮ ዕርባታ አመሠራረት


ብዙ ሰዎች የዶሮ ዕርባታን ከማንኛውም ስራ የቀለለ አድርገው ይገምታሉ፡፡
ይህ አስተሳሰብ የሚመነጨው በአገራችን በተለምዶ ዶሮዎችን ምንም አይነት
እንክብካቤና አያያዝ ሳይደረግላቸው ራሳቸውን መግበው ፣ በሽታ ሲመጣ የሞቱት
ሞተው የቀሩት ለቤተሰብ ገቢና ምግብ ሲያበረክቱ በመታየታቸው ነው፡፡ ከዚህ
ሁኔታ በመነሳት ብዙ ሰዎች ዶሮዎችን ማንም ሰው ማርባት እንደሚችልና
ከዶሮዎች ጥቅም ለማግኘት ምንም ዓይነት ግብዓት አያስፈልግም የሚል ግንዛቤ
አላቸው፡፡ ይህ አስተሳሰብ እጅግ በጣም የተሳሳተ ነው፡፡ ዓላማው ከዕርባታው
ትርፍን ለማግኘትና ለመጠቀም ከሆነ ዘመናዊ የዶሮ አያያዝ መከተል መቻል
አለበት፡፡ ተገቢውን አያያዝ ለዶሮዎች ለመስጠትና የሚፈለገውን ውጤት
ለማግኘት፡-

 የዶሮዎችን ስነ-ፍጥረት ባገናዘበ መልክ የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት


ያስፈልጋል
አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 10
ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ይህ ደግሞ የሚሆነው
 ስለ ዶሮዎች ስነ-ፍጥረት
 መሟላት ስለሚገባቸው ሁኔታዎች
 ስለ ገበያ ሁኔታ
 ስለ ምርት አያያዝ ወዘተ ግንዛቤ ማዳበርን ይጠይቃል

በመሆኑም የዶሮ ዕርባታ ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉትን መሠረታዊ ነገሮች


ማወቅና ማጥናት ተገቢ ነው፡፡

3.1. መሠረታዊ ታሳቢዎች


3.1.1. ገበያ
 በውጪም ሆነ በአገር ውስጥ ምርቱን ለመሸጥ የሚያስችል ገበያ መኖሩን ጠንቅቆ
ማወቅ
 ሸማቹ የሚፈልገውን የምርት ዓይነት ፣ የሚፈልግበትን ወቅትና እንደ ዕንቁላል አስኳል
ቀለም ያሉትን የተጠቃሚ ፍላጎቶች ማወቅ ጠቃሚ ነው
3.1.2 ስለ አካባቢው ማወቅ
 የዶሮ አርቢ ብዛት
 የምርት ዓይነት
 የምርት መጠን
ይህን ማወቃችን የሚቋቋመውን የእርባታ ዓይነትና መጠን ለመወሰን አንድ መሰረታዊ መረጃ
ይሆናል፡፡
3.1.3 የግብዓት አቅርቦት
 የመኖ ዓይነቶችና የመዳኃኒት አቅርቦት መጠን እና ዋጋ
 ሌሎች ለእርባታው የሚያስፈልጉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ከየትና እንዴት ማግኘት
እንደሚቻል ማወቅ
3.1.4 ልምድ መቅሰም
 ሌሎች በስራው የተሰማሩ አርቢዎችን ልምድ በተቻለ መጠን መቅሰም ከነሱ ችግሮች
በመማር የተሸለና ውጤታማ ስራ መስራት ያስችላል
 በተጨማሪ አግባብ ያላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶችን
ልምድና ምክር ለማግኘት መሞከር ጠቃሚ ነው፡፡
አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 11
ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ከላይ የተዘረዘሩትን ዋና ዋና መሰረታዊ ታሳቢዎች ባለመንገዘብ ወይም ባለማጤን ያለጥናት ዶሮ ላርባ ብሎ


መነሳት ትርፉ ኪሳራና ብስጭት እንዲሁም ሌሎች ወደስራው ሊገቡ የሚፈልጉ ሰዎች ስራውን እንዳይጀምሩ
ተስፋ ማስቆረጥና ማከላከል ይሆናል፡፡
3.2 እርባታው ከምን እንደሚጀምር መወሰን
ዶሮዎች ማርባት በሚፈለግበት ጊዜ ከላ እንደተገለጸው በአካባቢው የሚፈለገውን ምርት ምን እንደሆነ
አስቀድሞ መታወቅ አለበት፡፡ ኣላማው ዕንቁላል ፣ ሥጋ ወይም ሁለቱንም ለማምረት መሆኑን በቅድሚያ
መወሰን ያስፈልጋል፡፡ የዶሮ ዕርባታ ከዕንቁላል ፣ ከጫጩት ወይም ካደጉ ዶሮዎች ሊጀመር ይችላል፡፡
እያንዳንዱ አማራጭ እንደ ዕርባታው አጀማመርና ተጨባጭ ሁኔታ የራሱ የሆነ ጥቅምና ጉዳት ሊኖረው
ይችላል፡፡

3.2.1 ከዕንቁላል መጀመር


 እርባታው የራሱ የሆነ ማስፈልፈያ ሊኖረው ይገባል
 ከሚፈለገው ዝርያ እናቲቶችን ማግኘት
 በአገራችን እናቲት ዶሮዎችን የሚያቀርቡ ኩባንያዎች ባለመኖራቸው ዌም ስላልተስፋፉ
የለማ ዕንቁላል ማቅረብ ስራቸው ከሆኑ የውጪ አገር ኩባንያዎች ማስመጣት ያስፈልጋል
3.2.2 ከጫጩት መጀመር
 ሰዎች በብዛት የሚጠቀሙበት የርባታ መጀመሪያ ዘዴ ነው
 ጫጩቶችን ወዲያው እንደተፈለፈሉ ፣ ማለትም ከ 24 እስከ 48 ሰዓታት ድረስ ባለው ጊዜ
ያለምንም ምግብና ውሃ በአመቺ የማጓጓዣ ዘዴ ወደ ተፈለጉበት ቦታ ማጓጓዝ ይቻላል
 ዕንቁላል በማስፈልፈል ጫጩቶችን ለተለያዩ ፈላጊዎች የማከፋፈል ሥራ እንደ ዋና ተግባር
አድርገው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በአገራችንም በደብረ ዘይት አካባቢ በማቆጥቆጥ ላይ
ናቸው
 አብዛኛዎቹ ዘመናዊ የዶሮ እርባታዎች ግን በአሁኑ ጊዜ ጫጩቶችን የሚያገኙት ከሆላንድ
፣ ከጀርመንና ከኬንያ በአውሮፕላን በማስመጣት ነው፡፡
 ጫጩቶች እንደተፈለፈሉ በፆታ ሳይለዩ ወይም ወንድና ሴቱ ተለይቶ ሊገዙ ይችላሉ
3.2.3 ከቄብ(ታዳጊ) ዶሮዎች መጀመር
 የዕንቁላል ዶሮዎች እርባታን ጫጩቶችን አሳድገው ከሶስት ወር እድሜ ጀምሮ ያሉ ቄቦችን
ከሚሸጡ አርቢዎች ገዝቶ መጀመር ይቻላል፡፡
 ቄቦቹን ለማሳደግ የወጣው ወጪና የሚጠበቀው ትርፍም ተጨምሮባቸው ስለሚሸጡ
ዋጋቸው እንደ ዕድሜያቸው እየጨመረ የሚሄድ ነው፡፡
 በአገራችን ቄቦችን አሳድገው የሚሸጡ ኩባንያዎች ዕያቆጠቆጡ ይገኛሉ፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 12


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ይህ አይነቱ አማራጭ ጠቃሚነቱ የዕንቁላል ዶሮዎች እርባታን ለመጀመር ለሚፈልጉ ብቻ


ነው፡፡
 የሥጋ ዶሮዎች እርባታን ለመጀመር ግን ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉት የመጀመሪያዎቹ
ሁለቱ አማራጮች ብቻ ናቸው፡፡

3.3 የሚቋቋመው ዕርባታ መጠን ለመወሰን


3.3.1 የካፒታል መጠን
 ለስራ ሊመደብ የሚችለው መዋዕለ-ንዋይ አንድ እርባታ በምን ያህል መጠን እንደሚጀመር
ይወስናል፡፡ በቂ መዋዕለ-ንዋይ ካለ የርባታውን መጠን ከፍ አድርጎ መጀመር ይቻላል፡፡
3.3.2 ገበያ
 ከርባታው ለሚመረተው ምርት ያለው ገበያ የሚቋቋመውን እርባታ ዓይነት ፣ መጠንና
ደረጃ ይወስናል፡፡ ከፍተኛ ገበያ ካለ ብዙ ምርት ማቅረብ የሚያስችል አመቺ ሁኔታ
ስለሚኖር የርባታውን መጠን ሰፋ አድርጎ መጀመር ያዋጣል፡፡
3.3.3 ልምድ
 የዶሮ ዕርባታ ልምድን የሚጠይቅ ስራ በመሆኑ ልምድ ያለው ሰው ቀጥሮ ማሰራት
የማይቻል ከሆነ የርባታውን ስራ በትንሹ ጀምሮ ቀስ በቀስ ልምድ እየተገኘ ሲሄድ
ማስፋፋት ጥሩ አካሄድ ነው፡፡ ልምድ ሳይኖር በሰፊው መጀመር ያልታሰበ ችግር ሊያስከስት
ይችላል፡፡
3.3.4 የመሬት ስፋት
 ለዕርባታው ስራ የሚውለው የመሬት ስፋተም የሚቋቋመውን የርባታ መጠን ሊወስን
ይችላል፡፡ ነገር ግን ፣ የመሬቱ መጠን አነስተኛ ቢሆንም በቂ ካፒታል ካለ በአነስተኛ መሬት
ላይ የተሸለ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ዘመናዊ ተደራራቢ ቆጥ ባለው ቤት ውስጥ የማርባት ዘዴ
ብዙ ዶሮዎችን ያሉት ጣቢያ ማቋቋምና ማካሄድ ይቻላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ባደጉ አገሮች
በአንድ ቤት ውስጥ እስከ 150,000 ዕንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በትንሽ መሬት ላይ በተሰራ
ዘመናዊ ቤት ውስጥ ማርባት የተለመደ ነው፡፡
3.4 ለዶሮ ዕርባታ የሚሆን ቦታ አመራረጥ
3.4.1 የአካባቢ መረጣ
እንደማንኛውም ስራ የዶሮ እርባታ እንቅስቃሴ ከመጀመሩ በፊት እርባታው የሚቋቋምበትን አካባቢ
በመምረጥ በኩል ከፍ ያለ ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ምንም እንኳን አስፈላጊውን ወጪዎች ብናወጣም
ለዶሮዎች ተስማሚ ያልሆነ አካባቢን በመምረጣችን ብቻ ለኪሳራ ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ ይህ እንዳይሆን የዶሮ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 13


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ዕርባታ ከመጀመሩ በፊት ተስማሚ አካባቢን ለመምረጥ የሚከተሉትን ተፈላጊ ነገሮች በቅድሚያ ማጤን
ተገቢ ነው፡፡

 የትራንስፖርት አገልግሎት ያለበት አካባቢ


 የውሃና የኤሌክትሪክ አቅርቦት ያለበት
 ገበያ የሚገኝበት አካባቢ
 የሰራተኛ (የሰው ኃይል) አቅርቦት(ለከፍተኛ ዘመናዊ ዶሮ ዕርባታ)
 ሌሎች አርቢዎች በአካባቢው የሌሉበት ቢሆን ይመረጣል
3.4.2 የርባታ ቦታ መረጣ
ከላይ በተዘረዘረው ሁኔታ የዶሮ ዕርባታው የሚቋቋምበት አካባቢ ከተወሰነ በኃላ እርባታው የሚሰራበትን
ትክክለኛ ቦታ ለመምረጥ ደግሞ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ማጤን ያስፈልጋል፡፡

 የአፈር ዓይነት ፡- የዶሮ ዕርባታው ሊቋቋም የታሰበበት ቦታ የአፈር ዓይነት አሸዋማ


ቢሆን ማንኛውንም ዓይነት ፈሳሽ ከመቋጠር ወይም አካባቢውን ጭቃማ ከመሆን
ያድነዋል፡፡ መረሬ የሆነ አፈር ውሃ ስለሚቋጥርና ለዶሮዎች ጤንነት ጠንቅሊሆኑ
የሚችሉ ህዋሳት እንዲራቡ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር ለዶሮ ዕርባታ ስራ
አይመረጥም፡፡
 የቦታው አቀማመጥ ፡- ለዶሮ ዕርባታ ስራ ዘቅዛቃ ወይም ተዳፋትነት ያለው ቦታ
ቢመረጥ በዝናብ ጊዜ ውሃ የመከማቸት ዕድል አይኖረውም፡፡ በተጨማሪም እንዲህ
ያለው ቦታ ለአየር እንቅስቃሴ ስለሚያመች ተመራጭነት አለው፡፡
 ለርባታው ሥራ የሚመረጠው የቦታ ስፋት
 በጠቅላላው ለሚሰሩት ቤቶች በቂ ከሆነ ፣
 ለሰራተኞች የስራ ቅልጥፍና የሚያመች መሆኑ ከታመነበት ፣
 ለወደፊት የርባታ ስራውን እንዳስፈላጊነቱ ለማስፋፋት ቢፈለግ አመቺ
መሆኑ ፣
 የተመረጠው አካባቢ በምን ዓይነት ስራ ላይ እንደዋለና ወደፊትም ምን
ጥቅም ላይ ለማዋል እንደታሰበ ማወቅም ያስፈልጋል
 የአካባቢውን የዓየር ጠባይ መገንዘብ ለዶሮዎች ቤት በሚሰራበት ጊዜ የዓየር
ጠባዩን ለመቆጣጠር የሚረዱ ነገሮችን ለማካተት ይጠቅመናል

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 14


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

4. የዶሮ ዝርያዎችና ባህሪያቸው

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ዶሮዎች በሰውነት መጠን ፣ በቀለም ፣ በምርታማነትና በሌሎች ባህሪያት
የተለያዩ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ በአገራችን የሚገኙ ዶሮዎችን በሁለት በመክፈል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

4.1. የሀበሻ ዶሮ ዝርያና ምርታማነታቸው

በጥናት ደረጃ ስለ አገራችን የዶሮ ዝርያዎች ያለው መረጃ ውስን ስለሆነ እስካሁን ካለው መረጃ አኳያ የአገር
ዶሮዎች ዝርያ የተለያዩ መስፈርቶችን መሠረት በማድረግ እንደሚከተለው በተለያየ ክፍል እንመድባቸዋለን፡፡

 በላባቸው ቀለም መሠረት በማድረግ


 ጥቁር ዶሮ
 ነጭ ዶሮ
 ቀይ ዶሮ
 ገብስማ ዶሮ
 አንገተ መላጣ
 ከተገኙበት ወይም ከሚኖሩበት አካባቢ መሰረት በማድረግ
 ሆሮ
 ጨፌ
 ቲሊሊ
 ኩክኒን መሰረት በማድረግ
 ነጠላ ኩክኒ ያላቸው
 ሮዝ ኩክኒ ያላቸው

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 15


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

የአገር ዶሮዎች ዝርያ ምርታማነታቸውን ስንመለከት በገጠር ገበሬ አያያዝ በአማካይ ከ 30 – 60


ዕንቁላሎችን በዓመት ይጥላሉ፡፡ የአያያዝ ፣ አመጋገብና የጤና አጠባበቅ በተሸሻለበት ሁኔታ ምርታቸው
በዓመት ከ 80 – 120 ዕንቁላል ከፍ ይላል፡፡ የሚጥሉት ዕንቁላል ክብደትም ዝቅተኛ ነው፡፡ የአንድ ዕንቁላል
ክብደት በአማካይ 40 ግራም ያህል ብቻ ነው፡፡ በአንዳንድ ተቋማት(ዓለማያ ፣ ወላይታ ፣ አርሲ) በተደረጉት
ሙከራዎች በሙሉ የአገር ቤት ዶሮዎች በቤት ውስጥ በዘመናዊ አያያዝ በሚያዙበት ጊዜ ከተሻሻሉት የውጪ
ዶሮዎች ጋር ሲወዳደሩ በብዙ እጥፍ የበለጠ የሞት አደጋ ታይቶባቸዋል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ተቋማት
የተደረገው ጥናት የሀገር ዶሮዎች ዝርያ የሥጋ ምርት ችሎታ በተመለከተ የተገኘው መረጃ
እንደሚያመለክተው አውራዎች በአማካይ በ 6 ወር ዕድሜ 1.5 ኪግ ክብደት ሲደርሱ ፣ ሴቶቹ 1 ኪግ አካባቢ
ይደርሳሉ፡፡ በዚህ ዕድሜ ከታረዱ በኃላ ሊበላ የሚችለው በድን(Carcass) ክብደት 560 ግራም ያህል ብቻ ነው፡፡
ቀሪው 940 ግራም ከአውራው እና 440 ግራም ከሴቷ ዶሮ የሚጣል ይሆናል፡፡ ይህም የሀበሻ ዶሮዎች ለዘመናዊ
አያያዝ አመቺ አለመሆናቸውን ይጠቁማል፡፡

4.2. ዘመናዊ የዶሮ ዝርያዎችና ምርታማነታቸው

የአሜሪካ የዶሮ ማህበር ባጠናው ጥናት መሰረት ዘመናዊ የዶሮ ዝርያዎችን በሚገኙበት አካባቢና
ባላቸው ለመሳሳይ በስድስት (6) ክፍል መድቧቸዋል፡፡ በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ በርካታ የዶሮ ዝርያዎች ሲኖሩ
በዚህ ክፍል ግን ትኩረት ሰተን የምንመለከተው ከ 1946 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ የገቡና እስካሁንም ድረስ
ጥቅም ላይ በመዋል በሰፊው ተሰራጭተው የሚገኙትን የተሸሻሉ ዘመናዊ የዶሮ ዝርያዎችን ነው፡፡

4.2.1 የአሜሪካ የዶሮ ዝርያ ክፍል


 አጠቃላይ መገለጫ ባህሪያቸው
 በአነስተኛ መኖ ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ናቸው
 አብዛኛዎቹ ቡናማ ዕንቁላል ጣይ ናቸው
 ለዕንቁላልና ለሥጋ ምርት ያገለግላሉ(ለሁለቱም ምረት ይሆናሉ)

በዚህ ክፍል ውስጥ ከሚገኙ ዝርያዎች በአገራችን በሰፊው ተሰራጭተው ጥቅም እየሰጡ ያሉት ዋና ዋና
ዝርያዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

i. ሮድ አይላንድ ሬድ(Rhode Island Red)


 በአገራችን በተለይ ለገበሬዎች በሰፊው እየተሰራጨ ያለ ዝርያ ነው፡፡ ለዚህም ትልቁ ምክንያት
 ለዕንቁላል እና ለሥጋ ምርት ስለሚሆኑ
 ጭረው መብላት ስለሚችሉ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 16


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 የሰውነታቸው ቀለም ለበራሪ ጠላት ወይም አዳኝ ስለማያጋልጣቸው(ለምሳሌ፡-


ጭልፊት)
 የሁለቱም ፆታ መልካቸው ጥቁር ቡናማ ወይም ቀይ ቡናማ ነው
 የሰውነት ክብደታቸው፡- አውራ፡- 3.9 ኪግ ፣ ሴት፡- 3 ኪግ
 የዕንቁላል ምርት፡- 5-7 ዕንቁላል በሳምንት ፣ በአማካይ 312 ዕንቁላል በዓመት ይጥላሉ
 የሚጥሉት ዕንቁላል ቡናማ ቅርፊት ያለው ነው
 ሮድ አይላንድ ሬድ ከሌሎች ዝርያዎች ሲነጻጸር ጭር የማለት ባህሪ ይታይባቸዋል

ምስል-2 የሮድ አይላንድ ሬድ ቡናማ ዕንቁላል እና ጫጩት

ምስል-3 ትላልቅ ሴት እና ወንድ ሮድ አይላንድ ሬድ ዶሮ


ii. ኒው ሃምሻየር (New Hempshire)
አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 17
ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ሮድ አይላንድ ሬድ ዝርያ ጋር ተመሳሳይነት አለው


 ቶሎ የማደግ ችሎታ አለው
 ፈዛዛ ቀይ የሰውነት ቀለም አላቸው
 የሰውነት ክብደታቸው፡- አውራ፡- 3.9 ኪግ ፣ ሴት፡- 2.9 ኪግ
 ለሁለቱም ምርት ያገለግላሉ በተለይ ለሥጋ ምርት ተመራጭ ነው
 የሚጥሉት ዕንቁላል ቡናማ ቅርፊት ያለው ነው
 ቁጡና ቅብጥብጥ ናቸው

ምስል-4 ሴትና ወንድ ኒው ሃምሻየር

 ሌሎች የአሜሪካ የዶሮ ዝርያዎች

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 18


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል-5 ሴትና ወንድ ጥቁር ጄርሲ ጌንትስ (Black Jersy giants)

ምስል-6 ሴትና ወንድ ፕላይማውዝ ሮክ (Plymouth Rock)

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 19


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

4.2.2 የሜዴትራኒያን የዶሮ ዝርያ ክፍል


 አጠቃላይ መገለጫ ባህሪያቸው
 በተለያየ የአየር ንብረት ተስማሚ ናቸው
 አብዛኛዎቹ ነጭ ቅርፊት ያለው ዕንቁላል ጣይ ናቸው
 በአብዛኛው ለዕንቁላል ምርት ተመራጭ ናቸው
a. ኃይት ሌግ ሆርን
 በአገራችን በስፋት ተሰራጭተው ይገኛሉ
 ሙቀትን ስለሚቋቋሙ
 ነጭ ቅርፊት ያለው ዕንቁላል ስለሚጥሉ(በማህበረሰቡ ተቀባይነት አለው)
 ዕንቁላል አምራች ዶሮዎች ናቸው፡- በዓመት 300 – 320 ዕንቁላል
 ቀለማቸው ነጭ ነው
 አነስ ያለ ሰውነት አላቸው፡- ወንድ ዶሮ፡- 2.4 ኪግ ፣ ሴት ዶሮ ፡- 1.8 ኪግ
 ጭር የማለት ባህሪ የለባቸውም

ምስል-7 ኃይት ሌግ ሆርን ጫጩትና ነጭ ቅርፊት ያለው ዕንቁላል

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 20


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል-8 ወንድና ሴት ኃይት ሌግ ሆርን

 ሌሎች የሜዴትራኒያ የዶሮ ዝርያዎች

ምስል-9 አንኮና እና ሚኖክራ የዶሮ ዝርያ(Ancona and Minorca)

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 21


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል-9.1 ቡናማ እና ነጭ ቅርፊት ያላቸው ዕንቁላሎች

4.2.3 የእንግሊዝ የዶሮ ዝርያ ክፍል


 አጠቃላይ መገለጫ ባህሪያቸው
 ላባቸው የተጠጋጋና የተደራጀ ሰውነት አላቸው
 የሥጋ ዶሮዎች ናቸው
a) አውስትራሎርፕ (Australorp)
 የሰውነታቸው ቀለም ጥቁር አው
 በሥጋ ምርታቸው የተሸሉ ናቸው አውራ፡- 3.8 ኪግ ፣ ሴት፡- 2.7 ኪግ
 በዓመት አስከ 250 ዕንቁላሎችን ይጥላሉ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 22


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል-10 ሴት እና ወንድ አውስትራሎፕስ

b) ሳሴክስ (Sussex)
 ነጭ የሰውነት ቀለም ሲኖራቸው አንገታቸው አካባቢ ጥቁር የላባ ቀለም አላቸው
 ለስላሳ እና ሶፍት ጸጉር አላቸው
 በሥጋ ምርታቸው የተሸሉ ናቸው
 አውራ፡- 4 ኪግ ፣ ሴት፡- 3.1 ኪግ
 ቡናማ ቅርፊት ዕንቁላል ይጥላሉ
 በዓመት ከ 240 – 260 ዕንቁላል ይጥላሉ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 23


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል-11 ሴት እና ወንድ ሳሴክስ

 ሌሎች የእንግሊዝ ዶሮ ዝርያዎች

ምስል-12 ዶርኪንግ እና ኮርኒሽ (Dorking and Cornish)

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 24


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

4.2.4 የእስያ የዶሮ ዝርያ ክፍል


 አጠቃላይ መገለጫ ባህሪያቸው
 ምንጫቸው ከቻይና ነው
 ጸጉራም እግር አላቸው
 ቢጫ ቆዳና ቀበድ ያለ ሰውነት አላቸው
 የሥጋ ዶሮዎች ናቸው ወንድ ዶሮ፡- 5.5 ኪግ ፣ ሴት ዶሮ፡- 4.5 ኪግ
 የሚጥሉት ዕንቁላል ቡናማ ነው
 በዓመት 55-60 ዕንቁላል ይጥላሉ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 25


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ዝግ ያሉና የማይንቀዠቀዡ ናቸው

ምስል-13 ኮቺንስ (Cochins)

ምስል-14 ብራህማ (Brahama)

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 26


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል፡- 15 ለንግሽን (Lengshan)

ሌሎች የዶሮ ዝርያዎች፡-

 የግብፅ ፋዩሚ (Egyptian Fayoumi)


 መሰረታቸው ግብፅ ነው
 ገብስማ ቀለም አላቸው
 ዕንቁላል ጣይ ናቸው
 መጣም ንቁ ናቸው
 ለስጋ ምርት አያገለግሉም
 በአነስተኛ የመኖ አቅርቦት ጥሩ ምርት ይሰጣሉ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 27


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል፡-16 ወንድ እና ሴት የግብጽ ፋዩሚ

5. የዶሮ ዝርያ አመራረጥና ምርታማ ዶሮዎችን የመለያ ዘዴዎች


5.1. የዝርያ አመራረጥ
ውጤታማ የዶሮ ዕርባታን ለማካሄድ ተስማሚ ዝርያን መምረጥ ዋንኛ ጉዳይ ነው፡፡ ተስማሚ ያልሆነ
ዝርያ ተይዞ ምንም ዓይነት አመጋገብ ፣ አያያዝና ጤና አጠባበቅ ቢኖር የተፈለገውን ውጠየት ማግኘት
አይቻልም፡፡ ላሰብነው የዶሮ ዕርባታ የተሻሉ የዶሮ ዝርያዎችን ለመምረጥ የሚከተሉትን ነጥቦች በጥንቃቄ
ማጤን ይጠቅማል፡፡
 ዓላማ
ተስማሚ ዝርያን ለመምረጥ በመጀመሪያ ደረጃ የሚቋቋመው ዕርባታ ዓላማውን ማወቅ ይኖርብናል፡፡
የገበያ ጥናት በማድረግ የማህበረሰቡ ወይም የሸማቹን የምርት ፍላጎት አስቀድመን ከለየን በኃላ የዕርባታውን
ዓላማ በቀላሉ መወሰን እንችላለን፡፡ የዶሮ ዕርባታ ሲቋቋም የሚከተሉትን ዓላማዎች መሰረት በማድረግ ነው፡፡
 ዕንቁላል ማምረት
 ሥጋ ማምረት
 ሁለቱንም ዓይነት ምርት ማምረት(ሥጋ እና ዕንቁላል)

የዕርባታው ዓላማ ከታወቀ ለዕርባታው ተስማሚ ዝርያዎችን በቀላሉ መምረጥ ያስችለናል፡፡ ለምሳሌ፡-
የሚቋቋመው ዕርባታ ዓላማው ለገበያ ዕንቁላል ለማቅረብ ወይም ዕንቁላል ማምረት ቢሆን ለዕርባታው
ተስማሚ ዝርያን ከላይ በክፍል 4 ላይ እንደተገለጸው ለዕንቁላል ምርት ብቻ የሚያገለግሉትን የዶሮ ዝርያዎች
በቀላሉ በመምረጥ ዕርባታውን ማከናወን ያስችላል፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 28


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ልምድ
ከላይ ባስቀመጥነው ምሳሌ መሰረት ለዕንቁላል ምርት ተስማሚ ከሚባሉት የዶሮ ዝርያዎች
ለምሳሌ፡- ኃይት ሌግ ሆርን ምርጫችን ብናደርግ ወዲያው ወደ ግዢ መግባት የለብንም፡፡ ግዢ ከመፈጸማችን
አስቀድመን ሌሎች አርቢዎች ኃይት ሌግ ሆርን ዝርያን ተጠቅመው ምን አይነት ውጤት እንዳገኙ ከእነሱ
ልምድ መውሰድ አለብን፡፡
 የዝርያው መገኘት
በአገራችን ዝርያዎችን በዕንቁላል ፣ በጫጩት እና በቄብ ደረጃ የሚያቀርቡ አንዳንድ ኩባንያዎች
ይገኛሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ዝርያዎች ግን የግድ ከውጪ አገር በራስ ወጪ ማስገባትን ይጠይቃሉ፡፡ ስለዚህ
የምንፈልገው ዝርያ በአገር ውስጥ እንደልብ መገኘቱንና አለመገኘቱን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ በአገር ውስጥ
የማይገኝ ከሆነ ከውጭ ለማስመጣጥ የሚያስፈልገውን የሚከተሉትን ማጤን ያስፈልጋል፡-
 ወጪ
 ጊዜ
 የዕርባታ ቦታ
 የጤና አጠባበቅ

5.2 ምርታማ ዶሮዎችን የመለያ ዘዴዎች


አንድ ዓይነት ዝርያ ያላቸው ዶሮዎች ተቀራራቢ የሆነ ምርታማነት ቢኖራቸውም ሁሉም እኩል
ብቃት ስለሌላቸው የምርታማነት መገምገሚያ መመሪያን በመከተል ዶሮዎችን መምረጥ ያስፈልጋል፡፡
ጥቅሙ፡-
 ሊወገዱ የሚገባቸውን ደካማ ዶሮዎችን በጊዜ መለየት ያስችላል
 የመኖ ወጪን መቀነስ ያስችላል
 ምርታማነትን ይጨምራል
 ትርፍን ያሻሽላል
 የተሸለ ትውልድን መፍጠር ያስችላል

ለተለያዩ የምርት ዓላማዎች ፣ ማለትም ለዕንቁላልና ለሥጋ ጥሩ ምርት የሚሰጡ ዶሮዎችን ለመለየት
የተለያዩ አጠቃላይ ስምምነት የተደረሰባቸው መመዛኛዎች አሉ፡፡ ዕንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ለመምረጥ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 29


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

የሚውሉ መመዘኛዎች ለሥጋ ዶሮ መመዘኛ አይሆኑም፡፡ እነዚህንም የምርጫ መመዘኛ ለማወቅ የዶሮ
አካላትን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

ምስል 17፡- የዶሮ አካላት ክፍሎች

5.2.1 የምርታማ ዕንቁላል ጣይ ዶሮ አመራረጥ መመዘኛዎች


ዕንቁላል በብዛት የሚጥሉ ዶሮዎች በብዛት ከማይጥሉት የሚለዩባቸው ምልክቶች አሉ፡፡ እነዚህ
ምልክቶች የሚታዩት በአንዳንድ አካል ክፍሎች ላይ ነው፡፡ በነዚህ አካላት ላይ የሚታዩ ዋና ዋና ምልክቶችና
ሌሎች መመዘኛዎች ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

 ንቃት፡- ጤናማነትና ንቃት በተለይ ተፈላጊ የሆኑ መመዘኛዎች ናቸው፡፡ ይህን ሁኔታ የሚያሟሉ
ዶሮዎች በአካባቢያቸውየሚካሄደውን ማናቸውንም ነገር ይከታተላሉ፡፡ ከቦታ ቦታ በበቂ ሁኔታ
ይንቀሳቀሳሉ ፣ ይበራሉ ፣ ይጮሃሉ ፣ ለተቃራኒ ፆታ ፍላጎት ያሳያሉ ወዘተ፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 30


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 የተለያዩ የአካል ክፍሎች ሁኔታ


 ጭንቅላት፡- የጭንቅላት ቅርጽና ሁኔታ እንደዝርያው ሊለያያ ቢችልም ባጠቃላይ ትላልቅና
የወንዴነት ሁኔታ የሚንፀባረቅበት ጭንቅላት ያላቸው ዶሮዎች ጥሩ የዕንቁላል ምርት
የሚሰጡ አይደሉም፡፡
 ዓይን፡- አንፀባራቂና ጎላ ጎላ ያሉ ዓይኖች የጥሩ ምርታማነት ምልክት ናቸው፡፡ የሚሸሹና
ወደውስጥ የገቡ ዓይኖች የደካማ ምርታማነትና የበሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
 መንቆር፡- አጠር ያለ ፣ ጠንካራና ከዶሮዋ ጭንቅላት ጋር የሚመጣጠን መሆን አለበት፡፡ የላይና
የታች የመንቁር ክፍሎች በትክክል የሚገናኙ መሆን አለበት፡፡ ቅርጹ የተበላሸና በትክክል
የማይገጥም መንቁር ያላቸው ዶሮዎች በአግባቡ መመገብ ስለማይችሉ በቂ መኖ መውሰድ
አይችሉም፡፡ህ ደግሞ በዶሮዎቹ ምርታማነት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡
 ቆዳ፡- ጥሩ ዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ከቆዳቸው ስር ብዙ ስብ ስለማያከማቹ ቆዳቸው ሳሳ ያለ
ነው፡፡ ጥሩ ዕንቁላል ጣይ ያልሆኑ ግን ከሚመገቡት ምግብ የተወሰነውን ወደስብ ቀይረው
በቆዳቸው ስር ስለሚያከማቹ ቆዳቸው ወፈር የማለት ባህሪ አለው፡፡
 ኩክኒ፡- ይህ የአካል ክፍል በዕንቁላል ጣይ ዶሮ ውስጥ ፣ የዘር ማኩረቻ አካል(Ovary)
የሚካሄደውን የሥነ-ተዋልዶ ሂደት የሚያመለክት ዋንኛ ጠቋሚ የአካል ክፍል ነው፡፡ የዕንቁላል
ጣይ ዶሮ ኩክኒ ደረቅ ፣ ጠንካራና በቅርፊት የተሸፈነ ከሆነ ዶሮዋ ዕንቁላል እየጣለች
ብትሆንም በቅርብ ጊዜ እንደምታቆም ይጠቁማል፡፡ የዶሮዋ ኩክኒ ሰፊ ፣ ለስላሳ ፣ በጣም
ቀይና በእጅ ሲነካም ሞካት ከሆነ የዘር ማኩረቻ አካል በከፍተኛ ደረጃ ተግባሩን እየተወጣ
መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይህም ዶሮዋ ጥሩ ዕንቁላል ጣይ መሆኗን ያመለክታል፡፡ የኩክኒ መልክ ፣
ቅላትና ሙቀት ከማንኛውም ጊዜ ይልቅ ዶሮዋ ዕንቁላል መጣል ልትጀምር ስትል ከፍተኛ
ሲሆን ፣ ዶሮዋ ዕንቁላል እየጣለች ስትሄድ ቀስ በቀስ እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ ይህ ሁኔታ
የሚፈጠረው በምርታማ ዶሮዎች ወደ ኩክኒ የሚሄደው የደም መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው፡፡
 ፊንጢጣ፡- ይህ አካል ዕንቁላል ከዶሮዋ ሰውነት የሚወጣበት ሲሆን ፣ የወላድ ዶሮ ፊንጢጣም
በቀላሉ የሚለጠጥ ፣ እርጥብና የጎን ስፋት ያለው ነው፡፡ የማትጥል ዶሮ ፊንጢጣ ግን
የተሸበሸበ ፣ ደረቅና ክብ ነው፡፡
 የፊንጢጣ አካባቢ አጥንቶች፡- እነዚህ አጥንቶች ከፊንጢጣ ግራና ቀኝ ሁለት ጉጥ መሳይ
አትንቶች ሲሆኑ ፣ ስለ ዶሮዋ የዕንቁላል አጣጣል ጥሩ መረጃን ይሰጣሉ፡፡ በወላድ ዶሮ በነዚህ
ሁለት አጥንቶች መካከል ያለው ርቀት ሰፊ ሲሆን ፣ ርቀቱ ከሁለት ጣት ስፋት አያንስም፡፡
ወላድ ባልሆነች ዶሮ ግን ይህ ርቀት ጠባብ በመሆኑ ከአንድ የጣት ስፋት አይበልጥም፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 31


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ሆድ ዕቃ፡- ሆድ ዕቃ የሚባለው የተለያዩ የሰውነት አካላትን ሸፍኖና አቅፎ የሚይዝ ሲሆን ፣


ዕንቁላል ማጠራቀሚያም ነው፡፡ ጥሩ ዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ሰፊ ሆድቃ አላቸው፡፡ ይህም
የሚሆንበት ምክንያት የዶሮዋ አንጀት በርከት ያለ መኖ ስለሚወስድ መስፋትና መወጠር
በመከተሉ እንዲሁም በየጊዜው በሚፈጠረው ዕንቁላል የዶሮዋ የማህጸን ቱቦ ሰፋ ያለ ቦታ
በመፈለጉ ነው፡፡ በተጨማሪም የጥሩ ዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ልብ ፣ መቋደሻና ሌሎች የመኖ
መፍጫ አካላትም ጥሩ ዕንቁላል ጣይ ካልሆኑት የሚበልጡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የሆድ ዕቃ
ስፋት የሚለካው በፊንጢጣ አካባቢ አጥንቶችና በፈረሰኛ አጥንት ጫፍ መካከል ባለው ርቀት
ነው፡፡ ይህ ርቀት ጥሩ ዕንቁላል ጣይ ባልሆኑ ዶሮዎችና በቄቦች ከሁለት የጣት ስፋት
የማይበልጥ ሲሆን ፣ ብዙ ዕንቁላል በሚጥሉ ዶሮዎች ግን ርቀት እስከ አራት ጣት ስፋት
ይደርሳል፡፡

a.የምትጥል ዶሮ b. የማትጥል ዶሮ

ምስል 18 በፊንጢጣ አካባቢ ባሉ አጥንቶች መካከል ባለው ርቀት ምርታማ የሆኑና ያልሆኑ ዶሮዎችን የመለያ ዘዴ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 32


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

6. የዶሮ መኖና አመጋገብ


ዶሮዎችን በዘመናዊ መንገድ በማርባት ጥሩ ውጤት ለማግኘት በመጠንና
በዓነት ተገቢውን መኖ ማቅረብና የአመጋገብ ሥርዓት መከተል ዋንኛ ተግባር ነው፡፡
የሥጋም ሆኑ የዕንቁላል ዶሮዎችን ዝርያ በዘመናዊ መልክ ለማርባት
ከሚያስፈልገው ወጪ ውስጥ ከ 50 እስከ 70% የሚውለው ከመኖ ጋር ለተያያዙ
ወጪዎች ነው፡፡ የዶሮዎችን ስነ ፍጥረት ያገናዘበና ሳይንሳዊ መርሆዎችን የተከተለ
አመጋገብ የምርት ወጪን በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ጥሩ ውጤት ያስገኛል፡፡

ጥሩ የመኖ አቅርቦትና አመጋገብ ከደሮዎቹ በምንፈልገው የምርት አይነትና


መጠን ተመጥኖና ተሰልቶ ከተዘጋጀ የመኖ ፍጆታን ይቀንሳል፡፡ ትሩ አመጋገብ
የዶሮዎችን በሽታ የመቋቋም አቅም ለማሻሻል ስለሚያስችል በበሽታ ሊደርስ
የሚችል ጉዳትን ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ ምርት ለመስጠት እንዲችሉ
የተሸሻሉ ዘመናዊ ዶሮዎችን በመጠቀም ለዶሮዎቹ አስፈላጊውን መኖ በተገቢው
መንገድ ካቀረብን በሙሉ የማምረተረ አቅማቸው እንዲያመርቱ ዕድል
እንሰጣቸዋለን፡፡

6.1 የንጥረ ምግብ ዓይነቶችና ተግባራቸው

ንጥረ ምግብ የሚባለው በመኖ ውስጥ የሚገኝና በእንሰሳት ህይወት ፣ ጥበቃና ፣


ምርት ተግባር ውስጥ ሚና ያለው ማንኛውም ነገር ነው፡፡ በዶሮዎች መኖ ውስጥ
የሚገኙ አስፈላጊ ንጥረ ምግቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ውሃ
ውሃ ከማንኛውም ንጥረ ምግብ ይበልጥ ለህይወት አስፈላጊ ነው፡፡ እንሰሳት
ከመኖ እጦት ይልቅ በውሃ እጦት የተነሳ በቀላሉ ይሞታሉ፡፡ ከእንሰሳት አካልም
አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 33
ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ውስጥ አብዛኛው ውሃ ነው፡፡ አንድ ጫጩት እንደተፈለፈለች ከሰውነት ክብደቷ


85% የሚሆነው ውሃ ነው፡፡ ይህ መጠን ጫጩቷ እያደገች ስትሄድ እየቀነሰ በመሄድ
የ 42 ሳምንት ዕድሜዋ ወደ 55% ዝቅ ይላል፡፡
 የውሃ ተግባራት
 ንጥረ-ነገሮችን ለማጓጓዝ እና ተረፈ-ምርቶችን ለማሶገድ
 ኬሚካላዊ ሂደቶችን ለማከናወን
o Fat – Fatty acid
o CHO - Glucose
 የሰውነት ሙቀትን ይቆጣጠራል
 የውሃ ምንጮች
 ከሚጠጡት ውሃ ………… 87%
 ከሚመገቡት ምግብ …….. 10%
 በሰውነታቸው በሚከናወን ሂደት …… 3%
 የዶሮዎች የውሃ ፍላጎት የሚለዋወጥበት ሁኔታዎች
 የመኖ ፍጆታ
o የመኖ ፍጆታ ሲጨምር - የውሃ ፍጆታ ይጨምራል
 የአካባቢ ሙቀት
o ሙቀት ሲጨምር - የውሃ ፍጆታ ይጨምራል
 የውሃው ሙቀት
o በጣም ቀዝቃዛ (˂5°c) – የውሃ ፍጆታ ይቀንሳል
o በጣም ሞቃት (˃35°c) -- የውሃ ፍጆታ ይቀንሳል
o መካከለኛ (18°c - 20°c) -- የውሃ ፍጆታ ይጨምራል
 የምርት መጠን
o ከፍተኛ ምርት - የውሃ ፍጆታ ይጨምራል
 የዶሮ አያያዝ
o በመሬት ማርባት ዘዴ - የውሃ ፍጆታ ይጨምራል
o በቆጥ ማርባት ዘዴ - የውሃ ፍጆታ ይቀንሳል
 የመኖ ይዘት
o ጨው የበዛበት መኖ - የውሃ ፍጆታ ይጨምራል
o ፕሮቲን የበዛበት መኖ - የውሃ ፍጆታ ይጨምራል
 የውሃ እትረት በዶሮዎች ላይ የሚያስከትለው ችግር
 የመኖ መፈጨትና መዋሃድ ችግር
 የዕንቁላል ምርት መቆም

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 34


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

o ለ 1 ቀን ያለ ውሃ ------------ የዕንቁላል ምርት ይቀንሳል


o ለ 2 ቀን ያለ ውሃ ------------ ላባ መርገፍ ፣ ዕንቁላል ምርት
መቆም
o ለ 3 ቀን ያለ ውሃ ------------ ሙሉ ለሙሉ ላባ መርገፍ ፣ በከፍተኛ
ደረጃ ዕንቁላል ምርት ይቀንሳል
 የደም የውሃ ይዘት መቀነስ
 የሰውነት ሙቀት መጨመር
 ሞት
ኃይል ሰጪ ንጥረ ምግብ(ካርቦሃይድሬትና ስብ)

ኃይል ለእንስሳት ምርታማነትና እድገት አስፈላጊ ከሆኑት ንጥረ ምግቦች አንዱ ነው፡፡ ኃይል ሰጪ
ንጥረ ምግብ ካርቦሃይድሬትንና ስብን ያጠቃልላል፡፡

 ካርቦሃይድሬት
ዝርዝር መግለጫ
 ኃይል ሰጪ ንጥ-ረምግብ ነው
 በእንስሳት ሰውነት ውስጥ በአነስተኛ መጠን ይገኛል(˂1%)
 በእጽዋቶች በከፍተኛ መጠን ይገኛል
o በጥራጥሬ- ˃85%
o በቅጠላቅጠል - ˃70%
ተግባራት
 ኃይል ያቀርባል
 የተለያዩ ስስ አካላትን ይሰራል
 ከፕሮቲን ጋር ይጣመራል
 የኒውክሊክ አይነቶችን በመስራት ይሳተፋል
የካርቦሃይድሬት ክፍሎች ከዶሮዎች አመጋገብ አንፃር
 ሊጠቀሙት የማይችሉት ክፍል(ቃጫ)
 ሊጠቀሙት የሚችሉት ክፍል
 ስብ
ዝርዝር መግለጫ
 ከእንስሳት ተዋፅዖ ከሚገኝ የመኖ ጥሬ ዕቃዎች የሚገኝ
 በእጽዋት የስብ መጠን አነስተና ነው
 ከፍተኛ ኃይል ያቀርባል
 በመኖ ውስጥ በአነስተኛ መጠን ይደባለቃል እስከ 5%
 በሥጋ ዶሮዎች መኖ ግን ትንሽ መጠኑ ከፍ ሊል ይችላል
 ስብ የተደባለቀበት መኖ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊበላሽ ይችላል
አካል ገንቢ ንጥረ ምግብ(ፕሮቲን)
ፕሮቲን የተሰራው አሚኖ አሲድ ከሚባሉ ውህዶች ነው፡፡ እነዚህ ውህዶች በተለያየ ቅንብር የተለያዩ
ፕሮቲኖችን ይገነባሉ፡፡ ዶሮዎች ፕሮቲንን የሚጠቀሙበት በአሚኖ አሲድ ምንጭነት ነው፡፡ ይህ በዶሮዎች

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 35


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

አመጋገብ መሰረታዊ ነው፡፡ ሌሎች እንደ ከብቶችና በጎች ያሉ የሚያመነዥጉ የርቢ እንስሳት በሆድ ዕቃቸው
ውስጥ ባሉ ትቃቅን ተዋሲያን እርዳት የሚያስፈልጓቸውን አሚኖ አሲዶች በሙላ ከማንኛውም የናይትሮጅን
ምንጭ መስራትና መጠቀም ይችላሉ፡፡ ዶሮዎች ግን ይህ ስለሌላቸው የሚያስፈልጋቸውን የአሚኖ አሲድ
መጠንና ቅንብር በአብዛኛው ከሚመገቡት መኖ ማግኘት አለባቸው፡፡

ተግባራት
 ለአካል ግንባታና እድገት
o ለጡንቻ ፣ ለቆዳ ፣ ለላባ ፣ ለጸጉር ፣ ለአጥንት ፣ ለጥፍር ፣ ለደም
 ያረጁ ሴሎችን ለመተካት፡- RBC
 ምርት ለመስጠት
 ለኃይል ምንጭነት
 እንደ ኢንዛይም ያገለግላል
o ምግብ ለመፈጨት ፣ ለማጓጓዝ ፣ ለማዋሃድ
o ፕሮቲን - ፕሮቴዝ ፣ ግሉኮስ - ኢንሱሊን
አሚኖ አሲድ
 ፕሮቲን የተሰራው አሚኖ አሲድ ከሚባሉ ውህዶች ነው
 እነዚህ ውህዶች በተለያየ ቅንብር የተለያዩ ፕሮቲኖችን ይሰራሉ
o ኮላጅን
o ኢላስቲን
o ኬራቲን
o አልቡሚን
 በአጠቃላይ የሚያስፈልጋቸው የተለያየ የፕሮቲን ዓይነት ለመስራት 21 አሚኖ
አሲድ ያስፈልጋቸዋል
 በሆድቃቸው 10 አሚኖ አሲድ ማዘጋጀት ሲችሉ 11 አሚኖ አሲድ ግን
ከሚመገቡት መኖ ያገኛሉ
 ይህን መሰረት በማድረግ 21 አሚኖ አሲዶችን ለ 2 እከፍለዋለን
o ግድ አስፈላጊ(Essencial amino acid) - (11 አአ)
o ግድ የማያስፈልግ (Non essential amino acid) - (10 አአ)
 ከ 11 ዱ አሚኖ አሲድ 5 ቱ ወሳኝና ግድ አስፈላጊ ናቸው(Critical)

ተ/
ግድ አስፈላጊ አሚኖ አሲድ(Essencial amino acid) ወሳኝ ግድ አስፈላጊ አሚኖ አሲድ(Critical)

1 ፌኒልአላኒን ላይሲን
2 ሂስቲዲን ሜትዬኒን
3 አይሶሉሲን ትሪፕቶፋን
4 ሉሲን አርጀኒን
5 ላይሲን ግላይሲን
6 ቫሊን

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 36


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

7 ትሪፕቶፋን
8 አርጀኒን
9 ሜትዬኒን
10 ትሪዬኒን
11 ግላይሲን
ሰንጠረዥ-1 ወሳኝና ግድ አስፈላጊ አሚኖ አሲዶች

ማዕድናት
 ዝርዝር መግለጫ
 ውሃን ሳይጨምር ከእንስሳት ሰውነት 30% የማዕድናት ይዘት ነው
 እንደ አጥንት ያለው የአካል ክፍል ለምሳሌ፡-
o ካልስየም ------ 36%
o ፎስፎረስ ------ 17%
o ማግኒዚየም ---- 0.8%
 የዕንቁላል ፣ በተለይ ቅርፊቱ በአብዛኛው ከካልስየም የተሰራ ነው
 ፖታሲየምና ሶድየም የሚባሉ ማዕድናቶች በጡንቻዎችና በደም ውስጥ በከፍተኛ
መጠን ይገኛሉ
 በአጠቃላይ እስካሁን 21 የተለያዩ ማዕድናት ለእንስሳት አካል አስፈላጊ መሆናቸው
ተረጋግጣል
 እነዚህ ማዕድናት ለአካል በሚፈለጉበት መጠን በሚከተሉት ሁለት ክፍሎች
ይመደባሉ
o ዓበይት ማዕድናት(Major Minerals)
o ንዑስ ማዕድናት(Minor Minerals)

ዓበይት ማዕድናት(Major Minerals) ንዑስ ማዕድናት(Minor Minerals)

ካልሲየም ብረት

ፎስፎረስ ኮባልት

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 37


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ሶዲየም መዳብ

ፖታሲየም ዚንክ

ክሎሪን አዮዲን

ማግንዚየም ሞልብደነም

ሰልፈር ሰለንየም

ፍሎሪን

ቫናድየም

ማንጋዚን

ስትሮኒየም

ኒኬል

ሲልኮን

ሰንጠረዥ-2 ለእንስሳት አካል አስፈላጊ የሆኑ ዓበይትና ንዑስ ማዕድናት

 የማዕድናት ተግባር
 ለአካል ግንባታ፡- አጥንት ፣ ጥርስ
 የሰውነት የፈሳሽ መጠን ይቆጣጠራሉ፡- ሶዲየም
 ከአምሮ የሚላኩ መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ
 ደምን ለመተካል ይሳተፋሉ፡- ሄሞግሎቢን(ብረት)
 የዶሮዎችን የማዕድናት ፍላጎት ለማርካት በመደበኛ የመኖ ቅንብር ውስጥ የሚካተቱ ወይም
በተጨማረነት የሚሰጡ የማዕድናት ምንጮች ያስፈልጋሉ
 ይህ በተለይ የካልስየምና የፎስፎረስ ምንጮችን እንዲሁም ሶዲየምና ክሎሪንን ይመለከታል
 የካልስየምና የፎስፎረስ እዲሁም እነዚህን ማዕድናት ለመጠቀም አስፈላጊ የሆነው ቪታሚን “ዲ”
የሚባለው ንጥረ ምግብ እጥረት ሲኖር ፣ በተለይ የጫጩቶችና የታዳጊዎች የአጥንት እድገት ይጓደልና
መጣመምና መሰበር ያስከትላል
 በዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች መኖ ውስጥ እትረት ካለ የዕንቁላል ምርት ይቀንሳል ፣ የዕንቁላል ቅርፊት
ይሳሳል

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 38


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 የአንድ ማዕድን መብዛት በራሱ ከሚያስከትለው ችግር በተጨማሪ የሌሎች ማዕድናትን አጠቃቀም
ሊያዛባ ይችላል
ለምሳሌ፡- ከሚፈለገው በላይ የየማግኒዚየም በዶሮዎች መኖ ውስጥ መኖርም የካልሲየም በአጥንት

ውስጥ መዋሃድን ስለሚያዛባ የዶሮዎቹ አጥንት ጥንካሬ ይቀንሳል

ቫይታሚን
 ዝርዝር መግለጫ
 ተመሳሳይ ባህርይ ፣ ነገር ግን የተለያየ ተግባር ያላቸው ብዙ ንጥረ ነገሮች ማለት ነው
 የቪታሚን ተግባር
 ለአጥንት ግንባታ(ቫ-ዲ)
 ለምርት (ቫ-ኤ)
 በሽታን ለመከላከል(ቫ-ሲ)
 የቪታሚን ዓይነት
 በስብ ውስጥ የሚከማቹ
o ቪይታሚን “ኤ”
o ቪታሚን “ዲ”
o ቪታሚን “ኢ”
o ቪይታሚን “ኬ”
 በውሃ ውስጥ የሚከማቹ
o ቪይታሚን “ሲ”
o ቪይታሚን “ቢ” ኮምፕሌክስ
 የዶሮዎችን የቪታሚን ፍላጎት ለማርካት በዶሮዎች መኖ ውስጥ ሰው ሰራሽ ቪታሚኖችን
መጨመር የግድ ነው
 መደበኞቹ የመኖ ጥሬ ዕቃዎች በቂ የቪታሚን ይዘት የላቸውም
 ብዙዎቹ ቪታሚኖች በብርሃን ፣ በሙቀት ወይም ከሌሎች የመኖ አይነቶች ጋር ተደባልቀው
ከቆዩ በቀላሉ ሚበላሹ ናቸው
 ዶሮዎች ከወቅቱ ፍላጎታቸው በላይ የሆኑ ቪታሚኖችን እንደ ጉበት ባሉት የአካላቸው
ክፍሎች የማጠራቀም ችሎታ አላቸው፡፡ ይህ ግን ለረጅም ጊዜ ሊያገለግል የሚችል ክምችት
አይደለም፡፡
6.2 የመኖ ጥሬ ዕቃዎችና ባህሪያቸው
የኃይል ምንጭ ጥሬ ዕቃዎች
በዶሮ መኖ ቅንብር ውስጥ ለኃይል ሰጪነት የሚጠቅሙ ጥሬ ዕቃዎች በአብዛኛው የእህል ዓይነቶች
ናቸው፡፡ እንደ ዶሮዎቹ የምርት ደረጃና ዓይነት እንዲሁም እንደ ዕድሜያቸው መጠን ከ 50 እስከ 75%

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 39


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

የሚሆነው የመኖ ቅንብር በእህል ዓይነቶች ይሸፈናል፡፡ በዚህም መነሻ የእህል ዘሮች ዋንኛ የኃይል ምንጭ
ናቸው፡፡ የእህል ዓይነቶች የሚከተሉት አጠቃላይ ባህሪ አሏቸው፡፡

 በቀላሉ በመፈጨት ወደ አካል ውስጥ መስረግ የሚችል ከፍተኛ የካርቦሃይድሬት


ክምችት
 ከፍተኛ የኃይል ሰጪ ንጥረ ምግብ ክምችት አላቸው
 የፕሮቲን ይዘታቸው ዝቅተኛ ነው
 የማዕድን ይዘታቸው ዝቅተኛ ነው
 የቪታሚን ይዘታቸው ዝቅተኛ ነው

በአገራችን ከሚገኙ የእህል ዘሮች ለዶሮዎች ለኃይል ምንጭ ጥሬ ዕቃ የምንጠቀማቸው የሚከተሉት ናቸው፡፡

 ገብስ
 በቆሎ
 ማሽላ
 ስንዴ

ምስል-19 የእህል ዘሮች

ከላይ የተዘረዘሩት የእህል ዓይነቶች በተለይ በእኛ አገር ለሰው ልጅ ባላቸው ቀጥተኛ ተፈላጊነት የተነሳ
በሚደባለቀው መኖ ውስጥ መጨመር ያለባቸው በዝቅተኛ መጠን ብቻ ነው፡፡ ቀሪው በቀጥታ ለሰው ምግብነት
በማይውሉ ጥሬ ዕቃዎች መሟላት ይኖርበታል፡፡ እነዚህም ተረፈ-ምርቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 40


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ብጣሪ
 የስንዴ ፍሩሽኬሎ
 ሌሎች የዱቄት ፋብሪካ ተረፈ ምርቶች
 የደረቀ የቢራ ገብስ ጭማቂ
 ሞራ
የአካል ገንቢ (ፕሮቲን) ምንጮች
በዶሮዎች መኖ ውስጥ የሚያስፈልገውን የአካል ገንቢ(ፕሮቲን) ፍላጎት ለማሟላት በድብልቅ ውስጥ
የሚካተቱ የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎች አሉ፡፡ እነዚህ ጥሬ ዕቃዎች በምንጫቸው መሰረት እንደሚከተሉት
ይመደባሉ፡፡


የእንስሳት እርድ ተረፈ-ምርት
 ደርቆ የተፈጨ ደም
 ደርቆ የተፈጨ ሥጋ
 ደርቆ የተፈጨ ሥጋና አጥንት
 ደርቆ የተፈጨ አሳ
 የፋጉሎ አይነቶች
 የጥጥ ፍሬ ፋጉሎ
 የኑግ ፍሬ ፋጉሎ
 የሎውዝ ፋጉሎ
 የተልባ ፋጉሎ
 አኩሪ አተር
 ሌሎች
o የደረቀ የቢራ እርሾ
የቪታሚን ምንጭ ጥሬ ዕቃዎች
 አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች፡- አልፋ አልፋ
 በፋብሪካ የሚመረቱ ቪይታሚኖች
የማዕድናት ምንጮች
 የተፈጨ አጥንት
 ደርቆ የተፈጨ ሥጋና አጥንት
 በሃ ድንጋይ
 ጨው
6.3 የመኖ ጥሬ ዕቃ ክምችት
የመኖ ጥሬ ዕቃና የተደባለቀ መኖ ከተገዛ በኃላ የሚከማችበት መንገድ ከፍተኛ የትራት መቀነስ
ሊያስከትል ይችላል፡፡ ትክክለኛ ያልሆነ አቀማመጥ ክምችቱ በተውሳክ ፣ በሻጋታ ፣ በአይጥና በሌሎችም
እንዲጠቃ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም በእርጥበት መነሻነት በክምችቱ ውስጥ በሚካሄዱ ኬሚካላዊ ለውጦች
ከፍተኛ ሙቀት ስለሚፈጠር የንጥረ ምግብ ይዘት መቀነስ ፣ የሽታ እንዲሁም የጣዕም መበላሸት ያስከትላል፡፡
ስለዚህ የመኖ ጥሬ ዕቃዎች ያላቸው የዕርጥበት መጠን ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይ
ጥራጥሬዎች የሚመረቱት እርጥበት ባለበት ወቅት ከሆነ የእርጥበት ይዘታቸው ከመደበኛው (8% – 12%)
አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 41
ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

በጣም ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል፡፡ የእርጥበት መጠኑ ከ 15% በላይ የሆነ እህል በማከማቻ ከገባ በአጭር ጊዜ ውስጥ
ይሻግታል፡፡ ስለዚህ ከክምችት በፊት የርጥበት በጠኑ እዲቀንስ ማድረግ ግድ ያስፈልጋል፡፡ በተሌ ለቪታሚን
ተጨማሪ የጥሬ ዕቃዎች ክምችት ልዩ ትኩረት ሊደረግ ይገባል፡፡ የሙቀት መጠኑ ከፍተኛ በሆነበት ወቅትና
በብርሃንም ጭምር በቀላሉ የንትረ ምግብነት ዋጋቸውን ያጣሉ፡፡ ስለዚህ ከፋብሪካ የሚመጣውን የክምችት
መመሪያ መከተልና ድብልቅ መኖን ማቀላቀል የሚገባው ባጭር ጊዜ ጥቅም ላይ የሚለውን ብቻ ነው፡፡ የመኖ
ጥሬ ዕቃዎች በተለይ የቪታሚን ምንጮች ከሌላ ጥሬ ዕቃ ጋር ተቀላቅለው ከሚከማቹ ለየብቻቸው ቢከማቹ
የብልሽት ደረጃው ይቀንሳል፡፡
6.4 ተግባራዊ የመኖ አመጋገብ
የዶሮዎችን ፍላጎት ባገናዘበ መልክ የመኖ ቀመር ተዘጋጅቶ ከተቀላቀለ በኃላ በተለያየ ቅርጽ ለዶሮዎቹ
ሊቀርብ ይችላል፡፡ ከተለያዩ ቅርፆች መካከልም አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
 የመኖ ቅርፅ
 ደረቅ ድቁስ፡- በጣም ሳይደቅ ተፈጭቶ የሚሰጥ የመኖ አይነት ነው፡፡ በጣም ከደቀቀ መኖ በመንቁራቸው
ውስጥ እየተለጠፈ ስለሚያቸግር ዶሮዎች በተገቢው መጠን መመገብ አይችሉም፡፡
 ትናንሽ ደረቅ ክብ ቁርጥራጮች /Pellets/፡- የዳቦ ቆሉ ዓይነት ቅርጽ ያለው የመኖ አይነት ሲሆን
አበዛኛውን ጊዜ ለሥጋ ዶሮዎች የሚዘጋጅ የመኖ አቀራርብ ነው፡፡ የሥጋ ዶሮዎች መኖ ሳይመርጡ
እነዲበሉና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለገበያ እንዲደረሱ በሚፈለግበት ጊዜ የሚዘጋጅ ነው፡፡
6.5 የዶሮዎች የአመጋገብ ስልት
 ነፃ አቅርቦት /Free choice feeding/፡- ዶሮዎች የፈለጉትን ያህል መኖ ያለ ምንም ገደብ እንዲበሉ
የሚፈቅድ የአመጋገብ ስልት ሲሆን ብዙ ጊዜ ተግባራዊ የሚሆነው ለዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ነው፡፡
 የተገደበ አቀርብት /Restricted feeding/፡- ከላይ ከተጠቀሰው የአመጋገብ ስልት የሚለይና እንደ
አስፈላጊነቱ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም የመኖ አቅርቦት የሚገደብበት የአመጋገብ ስልት ነው፡፡ ቁጥጥር
የሚደረግበት አመጋገብ ተግባር ላይ የሚውለው ፈጣን ዕድገት ያላቸውን የሥጋ ዶሮዎች ብዙ በመመገብ
የሚከሰተውን ድንገተኛ ሞት ለመቀነስ ተብሎ ነው፡፡
6.6 የአመጋገብ ዘዴዎች
 የስጋ ዶሮዎች መኖና አመጋገብ፡- የሥጋ ዶሮዎች በተቻለ ፍጥነት አድገው ለገበያ መቅረብ ስለላባቸው ጥራት ያለው
የተመጣጠነ መኖ በማንኛውም ወቅት የፈለጉትን ያህል በሁለት ደረጃ ማግኝት አለባቸው፡፡
 የጀማሪዎች መኖ (starters ration) ፡- ከተፈለፈሉ ጊዜ ጀምሮ እስከ 4 ሳምንታት ዕድሜ የሚቀርብ
ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘትና /22%/ በተነፃፃሪ አነስ ያለ የኃይል ሰጩ ንጥረ መኖ /2800-2900/ ያለው፣
 የማወፈሪያ መኖ (finisher ration) ፡- ከ 4 ሳምንታት ዕድሜ እስከ ሽያጭ ጊዜ የሚሰጥ ከፍተኛ
የሀይል ሰጪ ንጥረ ምግብ /2900/ ይዘትና በተነፃፃሪ አነስ ያለ የፕሮቲን ይዘ /20%/ ያለውን መኖ
ይመገባሉ፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 42


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

በዚህ ደረጃ የተመጣጠነውን መኖ ከሌሎች መኖ አምራቾች ወይም ጥሬ ዕቃው ገዝቶ መኖ መደባለቅ ይቻላል፡፡ በአንድ
ዙር ብዛት ያላቸው ዶሮዎችን የሚያመርት /5000/ የዶሮ እርባት ድርጅት የራሱን መኖ ቢያዘጋጅ ትርፋማ
ስለሚያደርገው በእጅጉ ተመራጭነት አለው፡፡

 የመብል እንቁላል ጣይ ዶሮዎች መኖና አመጋገብ


 የጫጩት ዶሮዎች አመጋገብ፡- ጫጩቶች በመጀመሪያቹ 8 ሣምንትት ጊዜ ውስጥ በሚገባ የተመጣጠነ
የንጥረ ምግብ ይዘት ያለው መኖ አቅርቦት ያስፈልጋቸዋል፡፡ በዚህ ደረጃ የሚሰጥ መኖ ቢያነስ ከ 18-
20% ፕሮቲን እንዲሁም 2900 ኪሎ ካሎሪ በኪሎ ግራም ሀይል ሰጪ መኖ ሊኖረው ይገባል፡፡
 የታዳጊ /ቄብ/ ዶሮዎች አመጋገብ፡- ከ 8-20 ሣምንታት ባለው ዕድሜ የቄብ ዶሮዎች አመጋገብ ለቀጣዩ
የእንቁላል ምርት ውጤታማነት ወሳኝ ነው፡፡ ቄቦች ለዝርያቸው የሚመጥን ዕድገት ኖሯቸው በተገቢው
ወቅት የእንቁላል የመጣል ተግባራቸውን መጀመር አለባቸው፡፡ በዚህ ዕድሜ ከጫጩትነት ጊዜ
የፕሮቲን ፍላጐት ይቀንሳል፡፡ በዚህ ወቅት የፕሮቲን ፍላጐት ከ 15-16% ይሆናል፡፡ ከዚህ የበለጠ
የፕሮቲን አቅርቦት የመኖ ወጪን ከመጨመሩ በላይ ቄቦች ከሚፈለገው የእድገት መጠን በላይ በማደግ
በቂ አካላዊ ዝግጅት ሳይኖራቸው እንቁላል መጣል እንዲጀምሩ ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ ቶሎ እንቁላል
መጣል እንዲያቆሙ በማድረግ የዶሮዎቹን የምርት ዘመን ውጤታማነት ይቀንሰዋል፡፡ ኃይል ሰጪ ንጥረ
ምግብን በተመለተ ከ 8-14 ሣምንታት ዕድሜ 2900 ኪሎ ካሎሪ በኪሎ የሀይል ሰጪ መኖ ሲያስፈልግ፣
ከ 14-20 ሣምንታት ባለው እድሜ ግን የስብ ክምችትን ለመከላከል ወደ 2700 ኪሎ ካሎሪ በኪሎ
ግራም መቀነስ ይኖርበታል፡፡
 የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች አመጋገብ፡- ቄብ ዶሮዎች እንቁላል መጣል ከሚጀምሩበት ጥቂት ቀደም በሎ
/አንድ ሳምንት ያህል/ የመኖ ለውጥ ሂደት መጀመር አለበት፡፡ በዚህ ወቅት ከታዳጊዎች መኖ ወደ
እንቁላል ጣይ መኖ ለውጥ ይደረጋል፡፡ በዚህ ወቅት የእንቁላል ምርት ፍላጐትን ለማርኮት የካልሲዬም
እቅርቦት መጨመር አለበት፡፡ ይህም በመኖ ውስጥ ከሚገባው 3.5% በተጨማሪ በተለየ መመገቢያ ላይ
በማድረግ ከፍተኛ የካልሴዬም ይዘት ያለው ያልደቀቀ በሃ ድንጋይ ለእንቁላል ጣይ ዶሮዎች ቀርቦላቸው
ሲፈልጉት እንዲወሰዱት ማድረግ ይገባል፡፡ የዕንቁላል ጣይ ዶሮ መኖ 2850 ኪሎ ካሎሪ በኪ.ግ መኖ
የኃይል ምንጭ ሊኖረው ይገባል፡፡ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች የፕሮቲን ፍላጐት ከእንቁላል ምርት ጋር
የተያያዘ ነው፡፡ በእንቁላል መጣያ ወቅት ያለውን አማካይ ፍለጐት ለማርካት የእንቁላል ጣይ መኖ
ቢያነስ 16.5 % ፕሮቲን ሊኖርው ይገባል፡፡
 የርቢ እናት ዶሮቻች አመጋገብ
 የእንቁላል ዝርያ እናት ዶሮዎች አመጋገብ፡- የእንቁላል ዝርያ ዶሮዎች ቀደም ሲል ለመብል እንቁላል ምርት
ተግባር የሚረቡ ዶሮዎችን አመጋገብ ስልት የተከተለ ይሆናል፡፡ ለዲቃላዎች ምርት የለማ /fertile/
እንቁላል ማምረትን ስለሚጠይቅ አውራ ዶሮዎችንም ለማደቀል ተግባር መኖር አለባቸው፡፡ አውራ
ዶሮዎች ውጤታማ የማዳቀል ተግብር ማከናወን እንዲችሉ በፕሮቲንና ቫይታሚን የዳበረ መኖ ሊመገቡ
ይገባል፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 43


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 የሥጋ ዝርያ እናት ዶሮዎች አመጋገብ፡- እነዚህ ዶሮዎች የሚረቡት ጥሩ የሥጋ ዶሮ ጫጩቶችን የሚያስገኙ
የለሙ እንቁላሎችን እንዲያመርቱ ነው፡፡ በመሆኑም ከዚህ ዝርያ ተፈጥሮ በመነሳት ከአመጋገብ መዛባት
በጣም ወፍረው የእንቁላል ምርታቸው ሊቀንስ እንዲሁም ከሚገባው በላይ ቀድመው እንቁላል መጣል
እንዳይጀምሩ ከፍተኛ ጥንቅቄ ሊደረግ ይገባል፡፡ ቀድመው እንቁላል መጣል ከጀመሩ የሚጥሏቸው
እንቁላሎች ትናንሽ ስለሚሆኑ ከዚህ የሚፈለፈሉት ጫጩቶችም ትናንሽና እድገታቸው የቀጨጨ
ይሆናል፡፡ በመሆኑም ለዚህ ዓላማ የሚረቡ ዶሮዎች እንቁላል መጣል እስከሚጀምሩበት /22 ሳምንታት/
ዕድሜ በሁለት ደረጃ የተከፈለ አመጋገብ ያስፈልጋቸዋል፡፡
የጀማሪዎች መኖ፡- እስከ 8 ሣምንታት ዕድሜ የሚሰጥ 20% ፕሮቲንና 2800 ኪሎ
ካሎሪ በኪሎ ግራም መኖ የኃይል ሰጪ ንጥረ ምግብ ያለውን የመኖ ዓይነት ይመገባሉ፡፡
የታዳጊዎች መኖ፡- ከ 9-22 ሳምንታት የሚሰጥ 16% ፕሮቲንና 2800 ኪሎ ካሎሪ
በኪሎ ግራም መኖ ሊመገቡ ይገባል፡፡

ዶሮዎች እንቁላላ መጣል ከሚጀምሩበት የ 22 ሳምንታት ዕድማ ጀሮ ቀስ በቀስ የዶሮዎቹ መኖ ወደ እንቁላል ጣዮች መኖ
ይቀየራል፡፡ የሥጋ ዝርያ እናት ዶሮዎች የተቀነሰውን የንጥረ መኖ ይዘት ለማካካስ ፍጆታቸውን እንዳይጨምሩና ያለአግባባ
ወፍረው የምርት መቀነስ እንዳይኖር የሚከተለውን አጠቃቀም የአመጋገብ መቆጣጠሪያ መርሆችን መከተል ያስፈልጋል፡፡

o የዶሮዎቹ አማካይ ፍጆታ በቀን በዶሮ 120 ግራም ከደረሰበት ጊዜ አንሰቶ ለ 10 ተከታታይ ቀናት ፍጆታቸው 150
ግራም እስከሚደርስ በየቀኑ በዶሮ 3 ግራም ሂሳብ መጨመር፣
o በዚህ ደረጃ የዶሮዎቹ ምርታማነት 60% /ከ 100 ዶሮዎች 60 እንቁላል በቀን/ የሚመረትበት ደረጃ እስኪደርስ
ማቆየትና ከዚህበኋላ የመኖውን መጠን ለእያንዳንዲ የ 2% የምርታማነት ጭማሪ በቀን 1 ግራም በዶሮ ሂሳብ ከፍ
ማድረግ፡፡
o ከዚህ በፊት ለ 5 ቀናት ያህል ምንም የምርት ዕድገት ወይም ቅነሳ ካልታየ 4 ግራም በዶሮ ሂሳብ ጭማሪ ማድረግና
እንደገና ለሚቀጥሉት 5 ቀናት የምርት ዕድገት መምጣት አለመምጣቱን ማየት፣
o የምርት ጭማሪ ከሌለ ወደ ውፍረት እንዳይሄዱ 4 ቱን ግራም መቀነስ፣
o ዶሮዎቹ 38 ሣምንታት ዕድሜ ሲሆናቸው ምርታማነታቸው ይቀንሳል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ለእያንዳንዱ 2%
የምርታማነት መቀነስ በቀን 1 ግራም በዶሮ ሂሳብ የመኖውን አቅርቦት አየቀነሱ መሄድ ያስፈልጋል፡፡ ይህም ቅነሳ
በሳምንት ሁለት ጊዜ ብቻ ይደረጋል፡፡
6.7 የመኖ ብክነትን የመከላከል ስልቶች
በማንኛውም ዓይነት የደሮ እርባታ ውስጥ እስከ 75% ድረስ የሚደርሰውን ከፍተኛ ወጪ የሚይዘው የመኖ ወጩ
ነው፡፡ በመሆኑም መኖን ከብክነት በመከላከል በአግባቡ መጠቀምና ለዶሮዎች እንዲውል ማድረግ እርባታውን ትርፋማ
ከሚያደርጉት ስልቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ የመኖ ብክነት በተለያዩ መንገዶች በተለይም በሚዘጋጅበት፣
በሚጓጓዝበት፣ በሚከማችበት፣ ለዶሮችም በሚሰጥበት ወቅትና ዶሮዎችም ሲመገቡ ሊከሰት የሚችል የዶሮዎት መመገቢያ
በዓይነትም ሆነ በጥራት በስፋት ይልያያሉ፡፡ ይሁን እንጂ ከላይ የተጠቀሱትን የብክነት መንስኤዎችን ማስወገድ አስፈላጊ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 44


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

በመሆኑ መመገብያ አለባቸው፡፡ አንድ የዶሮ መመገቢያ ዕቃ ማሟላት ያለበት ባህርይ በአጠቃይ ሚከተሉትን ያጠቃልላል፡፡
እነሱም፡-

 መመገቢያው መኖ የማያፈስ መሆን አለበት፣


 መመገቢያው በውጭ ባዕድ አካል ሊከሰት ሚችለውን የመኖ ብክለት መከላከል አለበት /ለምሳሌ ጉዝጓዝ/፣
 መመገቢያው በቀላሉ የሚጸዳ መሆን አለበት፣
 መመገቢያው ጠንካራና ለረጅም ጊዜ ማገልገል መቻል አለበት፣
 መመገቢያው በቀላሉ መኖውን መጨመር የሚያስችል መሆን አለበት፣
 መመገቢያው የማይነቃነቅ/የማይወዛወዝ/ መሆን አለበት፣
 በተመጣጣኝ ዋና መግዛት የሚቻል መሆን አለበት፣
 በገበያ ላያ በቀላሉ መገነት የሚችል መሆን አለባቸው፡፡

እነዚህን ባህርያት የሚያሟሉ መመገቢያዎች ከተገኙ /ከተገዙ በኋላ በአጠቃቀም ላይ የሚከተሉትን መኖ ሊያባክኑ የሚችሉ
ነገሮችን ማስወገድ፡-

 መመገቢያው ከንፈር /Lip/፣ ግሪል ወይም የሚሽከረከር ዘንግ በላዩ ላይ እንዲኖር በማድረግ ዶሮዎቹ መኖውን
እንዳይጭሩት በላዩ ላይ እንዳይወጡ መከላከል ይቻላል፣
 መመገቢያው በወለል ለይ ከሆነ መኖው ከጉዝጓዝ ጋር ስለሚደባለቅ ከፍ አድርጎ ማንጠልጠል ይጠቅማል፡፡ ሆኖም
ከፍታው በዶሮዎቹ ጀርበ ልክ መሆኑን መከታተል፣
 በመመገቢያው ውስጥ የሚጨመረው መኖ በጣም መሞላት የለበትም፡፡ የመመገቢያውን ጥልቀት 1/3 ኛ ብቻ
መሙላት በቂ ነው፡፡
 በአንድ ጊዜ መመገቢያውን እስከ አፉ ድረስ መሙላት ወደ 30%የሚሆን የመኖ ብክነትን የሚያስከትል በመሆኑ
መመገቢያዎችን በየጊዜው ደጋግሞ በ 1/3 ኛ መጠን መሙላት ይመረጣል፣
 የመመገቢያ ጥልቀት ከ 10 ሳ.ሜ ካነሰ የመኖ ብክነት ይጨምራል፣
 ሠራተኛው መኖውን በመመገቢያው በሚጨምርበት ጊዜ ጥንቃቄ የተሞላበትና ተገቢውን የመያዣና የመጨመሪያ
ዕቃ መያዝ አለበት /የመኖ ጭልፋና ባልዲ/፣
 በመመገቢያው ውስጥ መኖ በፍጥነት /ቢቻል በርከት ያለ ሰው ተመድቦ/ ቶሎ ቶሎ ካልተጨመረ በስተቀር በተወሰነ
ዕቃ ላይ በዝግታ የሚሞላ ከሆነ ዶሮች በሙሉ በተሞላው መመገቢያ ላይ ስለሚረባረቡ የመኖ ብክነት ከመኖሩም
በላይ ዶሮዎቹ ሊጎዱ ይችላሉ፡፡
 ዶሮዎችን ቀዝቀዝ ባለ ወቅት መመገብ መኖው በመመገቢያ ውስጥ ቆይቶ እንዳይበላሽና እንዳይባክን ይከላከላል፡፡
በመሆኑም ጧትና ከ 9፡00 ሰዓት በኋላ መመገብ ይምረጣል፡፡
 ንጹህ፣ቀዝቃዛና ተቀድቶ ያልቆየ ውሃ ምንጊዜም በመጠጫቸው ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፣

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 45


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 በመመገቢያ ውስጥ የቆየ መኖ ጥሩ ስለማይሆን በየጊዜው መመገቢያውን በማጽዳት መኖውን በመቀየር የመኖ
ብክነትን መከላከል ይቻላል፡፡

7. የዶሮ ጤና አጠባበቅ

7.1. አጠቃላይ የዶሮ በሽታ

በሽታ፡- ማንኛውም የጤና እክል በሽታ ተብሎ ይጠራል፡፡ የሰውነት ስርዓተ-ክፍል አካላት እንከን
ሲያጋጥማቸው ተግባራቸው በአግባቡ መወጣት አይችሉም፡፡ ይህም የጤና መታወክን ያስከትላል፡፡ ይህ የጤና
መታወክ ወይም በሽታ በሁለት (2) ዋና ዋና ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡
 ህይወት ባላቸው ህዋሳት
 ባክቴሪያ
 ቫይረስ
 ጥገኛ ህዋስ
የውጪ ጥገኛ ህዋስ
የውስጥ ጥገኛ ህዋስ
አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 46
ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ፈንገስ
 ፕሮቶዞዋ
 ህይወት በሌላቸው ነገሮች፡- የንጥረ-ምግብ እጥረት፣ ኬሚካልስ
በሽታ በዕርባታ ውስጥ እንዴት ሊከሰት ይችላል?

የእንስሳት ጤንነት ሊጠበቅ ወይም ለአደጋ ሊጋለጥ የሚችለው ሶስት ነገሮች በሚፈጥሩት ግንኙነት ነው
 ህይወት ያላቸው ህዋሳት፡- ባክቴርያ፣ ቫይረስ ወዘተ
 እንሰሳት፡- ዶሮ
ዶሮ
 የአካባቢ ሁኔታ፡- የምግብ አቅርቦት፣ የውሃ አቅርቦት፣ የጤና ክትትል፣ የንጽህና አጠባበቅ
በሽታ በሽታ
አምጪ አምጪ
ህዋስ ህዋስ
ዶሮ

ጥሩ
ሀ ያልሆነ
አካባቢ ጥሩ
ለ የሆነ
አካባቢ

ምስል20. ሀ) በሽታ መከሰቱን ያሳያል ለ) ከበሽታ ነፃ መሆኑን ያሳያል

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 47


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

በሽታ ለመከሰት ምቹ ሁኔታዎች


 በሽታ አምጪ ህዋስ በሽታ ለማስከተል መዋለድ ወይም መራባት ይኖርበታል
 መራባቱን እና እድገቱን ለማከናወን በዕርባታው ምቹ ሁኔታዎችን ይፈልጋል
 እነዚህ ምቹ ሁኔታዎች በአጠቃላይ ለሁለት ይከፈላሉ
ውስጣዊ ምቹ ሁኔታዎች
 ዘር
 እድሜ
 ፆታ
 በሽታ ተከላካይ ህዋስ
ውጫዊ ምቹ ሁኔታዎች
 የዶሮ ቁጥር
 የምግብ አቅርቦት
 የውሃ አቅርቦት
 ሙቀትና እርጥበት
 ንጽህና

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 48


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

የበሽታ መተላለፊያ መንገዶች

 በሽታ በተለያየ መንገድ ሊተላለፍ ይችላል


 የመተላለፊያ መንገዶች በዋናነት ለሁለት ይመደባል
የጎንዮሽ (ሆሪዞንታል መተላለፊያ መንገድ)
 ቀትተኛ ንኪኪ መተላለፊያ መንገድ፡- ጤነኛ ዶሮ በቀትታ ከበሽተኛው ዶሮ ጋር
በሚያደርገው ንኪኪ ለምሳሌ፡- ዶሮዎች ሲነካከሱ
 ኢ-ቀትተኛ ንኪኪ መተላለፊያ መንገድ፡- በሽተኛው በአካባቢው የሚገኙትን
ነገሮች በመበከል ወደ ጤነኛው ያስተላልፋል ለምሳሌ፡-
 በተበከለ ምግብና ውሃ
 በተበከለ መመገቢያና መጠጫ እቃዎች
 በአየር
 በአፈር
 በሰው
 በተባዮችና በራሪ ነፍሳት
 በዱር በአዋፋትና በሌሎች እንስሳት
ቨርቲካል መተላለፊያ መንገድ
 ከእናቲት ዶሮ ወደ ጫጩት በዕንቁላል በኩል
 በዕንቁላል ሽፋን
 ዕንቁላል በፊንጢጣ ሲያልፍ ከኩስ ጋር ሲነካካ
 ዕንቁላል ከጉዝጓዝ ጋር ሲነካካ

አጠቃላይ የዶሮ በሽታ ምልክቶች

 የዶሮ በሽታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የበሽታ ምልክቶች ሊስከትል ይችላል


 ጠቅላላ ምልክት(general signs)
መፍዘዝ
የተዘበራረቀ ላባ
በአንድ ቦታ መሰባሰብ
የምግብ ፍላጎት መቀነስ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 49


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

የክብደት መቀነስ
የዕንቁላል ምርት መቀነስ
የኩክኒ መጠን መቀነስ እና መገርጣት
 የመተንፈሻ አካል ምልክት(respiratory signs)
ከአፍንጫ ፈሳሽ
ማስነጠስ
ማሳል
ማቃሰት
ማንኮራፋት
የጭንቅላት እብጠት
የአይን መቆጣት
 የምግብ መፍጫ አካላት ምልክት(digestive signs)
የኩስ ይዘት መለወጥ(ሙኮይድ ፣ ውሃ መሰል)
የኩስ ከለር መለወጥ(ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ነጭ)
ደም የቀላቀለ ኩስ
ውጫዊ ፊንጢጣ በኩስ መጨማለቅ
 የነርቭ ስርዓት ምልክት(nervous signs)
ማነከስ
ያልተገባ እንቅስቃሴ
የባህሪ ለውጥ
የአንገት መቆልመም
ሽባነት
 ሞት(death)

የዶሮ በሽታ የሚያስከፍለን ዋጋ፡-


 የዶሮዎች መሞት
 የምርት መጠን መቀነስ
 የዕንቁላል እና ስጋ ምርት መቀነስ
 የዕንቁላል የመፈልፈል አቅም መቀነስ
 የዕድገት መጓተት እና የምርት ጥራት መቀነስ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 50


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 የገቢ መቀነስ እና የወጪ መጨመር ምክንያቱም


 በዶሮዎች መሞት፣ ለህክምና ወጪ፣ ዝቅተኛ የምርት አቅም፣ ለጽዳት
 በሽታው ወደ ሰው መተላለፍና ሞትን ማስከተል

7.2 ዋና ዋና የዶሮ በሽታ መከላከያ ዘዴዎች


 የዶሮ በሽታ መከላከያ ዘዴዎች የተለያዩ ቢሆኑም በሽታን ከመከላከል አንጻር ትኩረት ማድረግ ያለብን
በሽታ ከመከሰቱ በፊት ሊደረጉ በሚገቡ መከላከያ ዘደዎች ላይ ነው
 የዶሮ በሽታን ለመከላከል ዘመናዊ የዶሮ ቤት ከመጠቀም እና የዕርባታው ባለቤትና ሰራተኞች ስለ
መሰረታዊ የዶሮ ጤና አጠባበቅ በቂ ስልጠናን ከመውሰድ ይጀምራል
 በምርት ሂደት ውስጥ በሽታ እንዳይከሰት ለመከላከል
 የንጽህና አጠባበቅና ቁጥጥር ማድረግ፡- ይህ ተግባር እጅግ በጣም አዋጭና ከሁሉም ቅድሚያ
የሚሰጠው ተግባር ነው
 ክትባት፡- ይህ ተግባር ከንጽህና አጠባበቅና ቁጥጥር በመቀጠል የሚተገበር ሲሆን ለዕርባታ
የምንጠቀማቸው ዶሮዎች አስፈላጊውን ክትባት በወቅቱ መውሰድ አለባቸው
 ህክምና፡- በሽታ ከመከሰቱ በፊት የምንጠቀማቸው የቅድመ-መከላከያ ዘዴዎች ሲሆኑ
ከክትባት ቀጥሎ ሚናው የጎላ ነው

የንጽህና አጠባበቅና ቁጥጥር አተገባበር

 በሽታ አምጪ ህዋሳት ወደ ዕርባታ እዳይገባ አስቀድሞ መከላከል


 የታመሙ እንሰሳትንም ሆነ የተበከሉ ዕቃዎችን ከዕርባታው ማራቅ
 ዋና ዋና የንጽህና አጠባበቅና ቁጥጥር ተግባራቶች የሚከተሉት ናቸው
 ዶሮዎችን ለይቶ ማርባት እና እንቅስቃሴን መቆጣጠር/መቀነስ፡- በሽታን የሚከላከል
 የጽዳት ተግባራትን ማከናወን፡- የበሽታ ምንጮችን 80 በመቶ የሚቀንስ
 ፀረ-ህዋስን መጠቀም፡- ቀሪ የበሽታ ምጨችን 20 በመቶ የሚቀንስ

1. ዶሮዎችን ለይቶ ማርባት እና እንቅስቃሴን መቆጣጠር/መቀነስ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 51


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ጤነኛ ዶሮዎችን ለበሽታ ከሚያጋልጡ ማናቸውም በሽታ አስተላላፊ የሆኑ እንስሳት ወይም ቁሶች
ወደ እርባታው እዳይገቡ በማድረግ ወይም በመቀነስ የዶሮዎቹን ጤንነት የምንጠብቅበት ዘዴ ነው
 ይህ ዘዴ የተከለከሉና የሚያስጠነቅቁ ምልክቶችንና ከጤነኞቹ ዶሮዎች ጋር ንክኪ እንዳይፈጠር የተለየ
ወይም የተከለከለ ቦታን መጠቀም ያስፈልገናል
 እጅግ በጣም አስፈላጊና አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ማንም ምንም ነገር ለዶሮዎች የተለየውን ቦታ
ማቋረጥ አይችልም

1.1 ቁልፍና ሰንሰለት መጠቀም


 በሽታን ለማስተላለፍ የሚያሰጉ ወይም ያልተፈቀደላቸው ሰዎች ዕርባታውን አቋርጠው
እንዳይገቡ ይጠቅማል

ምስል22. በሰንሰለትና በቁልፍ የተዘጋ የዶሮ ቤት

1.2 በሽቦ መከለል


 በሽታን ሊያስተላልፉ የሚችሉ የዱር እንስሳትን እና አዋፋትን ለመከላከል ያስችላል

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 52


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል23. በሽቦ የተከለለ የዶሮ ቤት

1.3 የተለያየ ደረጃ ያላቸው የቁጥጥር ስርዓት መጠቀም


 ማንኛውም ሰራተኛ ወይም ጎብኚ ወደ ዶሮ ቤት ከመግባቱ በፊት እጁንና ጫማውን በሳሙና
መታጠብ አለበት
 ማንኛውም ሰራተኛ ወይም ጎብኚ ወደ ዶሮ ቤት ከመግባቱ በፊት የለበሰውን ልብስና ጫማ
በማውለቅ በዕርባታው የተዘጋጀውን የስራ ልብስና ጫማ መልበስ አለበት
 ማንኛውም ሰራተኛ ወይም ጎብኚ ወደ ዶሮ ቤት ከመግባቱ በፊት የቀየረውን ጫማ በፀረ-
ተባይ መንከር አለበት
 እጅግ በጣም አስፈላጊ ሰዎች ብቻ ናቸው ወደ ዕርባታ የሚገቡት ለምሳሌ የዕርባታ ሰራተኛ
እና ሀኪም
 ጎብኚዎች ወደ ዕርባታው እንዲገቡ አይፈቀድም ነገርግን አስገዳጅ ከሆነ ከፍተኛ ቁጥጥር
ተደርጎባቸው ይገባሉ
 ተሸከርካሪዎች ከዕርባታው በ 30 ሜትር ርቀው በቆም አለባቸው
 የሚገቡ የተሽከርካሪ አካላት አስፈላጊውን ቁጥትር ተደርጎባቸው መግባት አለባቸው
 እነዚህ ጥንቃቄዎች ከውጪ በሰዎች እጅ፣ ጫማ፣ ልብስ አማካኝነት ወደ ዕርባታ
ውስጥ በሚገባ በሽታ አምጪ ህዋስ ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ለመከላከል
ይጠቅማል

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 53


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል24. የቁጥጥር ስርዓት

1.4 ዶሮዎችን ከሌላ ዝርያ መለየት


 በአንድ እርባታ ውስጥ የተለያየ ዝርያ ያላቸውን አዋፋት ከዶሮዎች ጋር ማርባት አይቻልም

ዶሮ ዶሮ

ዳንክዬ ዶሮ

ምስል25. የዶሮ ዝርያና የዳንክዬ ዝርያ

1.5 ሁሉን አንድ ጊዜ ማስገባት ሁሉን አንድ ጊዜ ማስወጣት = ተመሳሳይ ዕድሜ ያላቸውን ማርባት

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 54


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 አዳዲስ ዶሮዎችን በየጊዜው ከነባሮቹ ጋር መቀላቀል ለበሽታ ያጋልጣል


 በአንድ ዕርባታ ውስጥ የተለያየ ዕድሜ ያላቸውን ዶሮዎችን ማርባት ለበሽታ ያጋልጣል
 ዶሮዎች ከ 7 ቀን በላይ የዕድሜ ልዩነት ሊኖራቸው አይገባም
1.6 አጥር + በር + ማስጠንቀቂያ ምልክት
 በዕርባታው ዙሪያ አጥር + በር + ማስጠንቀቂያ ምልክት መጠቀም የሰዎችን፣
የተሸከርካሪዎችን፣ የቁሳቁሶችን እንዲሁም የእንስሳቶችን ወደ ዕርባታው የሚያደርጉትን
እንቅስቃሴ ለመግታት ይረዳል
 ይህ ተግባር ከውጪ ሊገቡ የሚችሉትን አደጋዎች ይቀንሳል ወይም ይከላከላል



በዚህ አካባቢ ማለፍም ሆነ
መቆም አይፈቀድም!!!

ምስል26. አጥር + በር + ማስጠንቀቂያ ምልክት

2. የጽዳት ተግባራትን ማከናወን


 የዶሮ ቤት፣ ተሽከርካሪን እንዲሁም ቁሳቁሶችን ማጽዳት 80 በመቶ በሽታ አምጪ የሆኑ
ነገሮችን ያሶግዳል
 ጽዳት ማለት ማናቸውም ቁሻሻ ነገሮች ማሶገድ ሲሆን መለኪያውም በአይናችን የጸዳ፣ ውብ
እና አንጸባራቂ የሆነ ዕርባታን መመልከት ነው
 የማጽዳት ተግባር ጥረቶችን ይጠይቃል፡-
 መፈቅፈቅ
 መቦረሽ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 55


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 በኬሚካል(ዲተርጀንት)፣ በውሃ እና በሳሙና ማጠብ

ምስል27. የጽዳት ተግባራት

ምን እና መቼ መጸዳት አለበት?

 ወደ ዕርባታ ከመግባታችን በፊት መደበኛ የጽዳት ፕሮግራም መኖሩን ማረጋገጥ እና መተግበር


ተሸከርካሪዎች እና ቁሳቁሶች(የህክምና መርፌዎች፣ መንቁር መቁረጫ ማሽን፣ የዕንቁላል
ትሪዎች)
የስራ ልብስና ጫማዎች
የሰራተኞችና የጎብኚዎች እጅና ፊት

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 56


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 በዕርባታ ውስጥ መደበኛ የጽዳት ፕሮግራም መኖሩን ማረጋገጥ እና መተግበር


የምንጠቀምበት የዶሮ ቤት ቁሳቁሶች(የመጠጫ፣ የመመገቢያ እና የዕንቁላል ትሪዎች)
የስራ ልብስና ጫማዎች
የሰራተኞች እጅ በስራ መሃል
 በዕርባታ በካከል መደበኛ የጽዳት ፕሮግራም መኖሩን ማረጋገጥ እና መተግበር
የውስጥና የውጪ የዕርባታ ክፍል እና ዕቃዎች

3. በኬሚካል መንከር ወይም መርጨት


 ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራቶች ከተገበርን በኃላ የቀሩ ቁሻሻዎችን የምናሶግድበትና
የምናጸዳበት ዘዴ ነው
 የተለያዩ ፀረ-ህዋሳት በድኃኒቶችን እንጠቀማለን
 ፀረ-ህዋሳት በድኃኒቶችን ስንጠቀም ውጤታማ ለመሆን የሚከተሉትን በትክክል መተግበር
አለብን
በማጽዳት ሂደት ውስጥ ሁሉንም ቁሻሻዎች ማሶገድ
ትክክለኛና የተፈቀደ ፀረ-ህዋሳት በድኃኒቶችን መጠቀም
ፀረ-ህዋሳት በድኃኒቶችን በትክክለኛው መጠን ማዘጋጀት፣ መመሪያውን መከተል
ሁሉንም ቦታ ለማዳረስ በበቂ መጠን ፀረ-ህዋሳት በድኃኒቶችን ማዘጋጀት
ፀረ-ህዋሳት በድኃኒቶችን ስናዘጋጅም ሆነ ስንረጭ በጥንቃቄ መሆን አለበት

ምን እና መቼ መንከር/መረጨት አለበት?

 ወደ ዕርባታው ከመግባታችን በፊት መንከር ወይም መርጨት


ተሸከርካሪዎች እና ቁሳቁሶች(የህክምና መርፌዎች፣ መንቁር መቁረጫ ማሽን፣ የዕንቁላል
ትሪዎች)
 በዕርባታ በካከል መደበኛ የርጭት/መንከር ፕሮግራም መኖሩን ማረጋገጥ እና መተግበር
የውስጥና የውጪ የዕርባታ ክፍል እና ዕቃዎች

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 57


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

7.3 አጠቃላይ የንጽህና አጠባበቅና ቁጥጥር ስጋቶች


A. አዳዲስ ዶሮዎችን ማስገባት
 በነባር ዶሮዎች አዳዲስ ዶሮዎችን ማስገባት የለብንም ምክንያቱም
o በበሽታ የተጠቁ ዶሮዎች ይኖራሉ
o ከበሽታ ያገገሙ ነገርግን አስተላላፊ የሆኑ

ማስጠንቀቂያ

 አዲስ የሚመጡ ዶሮዎችን ቢያንስ ለ 2 ሳምንት ከነባር ዶሮዎች ጋር ሳይቀላቀሉ


በተዘጋጀላቸው መኖሪያ ተለይተው መቆየት አለባቸው
 የተለዩ ዶሮዎችን ማከታተልና ያልተለመደ ለውጥ ካለ ማሶገድ

ምስል28. የአዳዲስ ዶሮዎች መቆያ መኖሪያ

B. ሰዎች
 የሰዎች እንቅስቃሴ በበዛበት ዕርባታ በሽታ የመከሰት እድሉ የሰፋ ነው
 በሽታ አምጪ ህዋሳት በላባ፣ በኩስ እንዲሁም ከሰውነታቸው በሚወጡ ፈሳሾች ውስጥ
ሊገኙ ይችላሉ
 እነዚህ ነገሮች ደግሞ ሰዎች ከዶሮዎች ጋር በሚፈጥሩት ንክኪ በልብሳቸውና በጫማው ላይ
ሊቀሩ ይችላሉ

ማስጠንቀቂያ

 የሌሎች ዕርባታዎች መጎብኘት መቀነስ በተለይ በሽታ በተነሳበት ጊዜ


 ሌሎች ጎብኚዎች ወደ ዕርባታ እንዳይገቡ መከልከል አስፈላጊ ከሚባሉት ውጪ
 ለሰራተኞችም ሆነ አስፈላጊ ለሆኑ ሰዎች ልብስና ጫማ ማዘጋጀት(እንስሳት ሐኪም፣ የዕርባታ
ሰራተኛ፣ ኤሌክትሪሺአን)

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 58


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል29. ቱታና ቦት ጫማ

 ቦት ጫማን በፀረ-ተባይ በሞላበት ፉትባዝ መንከር


ፀረ-ተባዩን በየጊዜው መቀየር
ከቦት ጫማ ላይ ቁሻሻን ለማሶገድ ብሩሽ መጠቀም
ለያንዳንዱ የዶሮ ቤት የምንጠቀመው ቦተ ጫማ የቀለም ልዩነት ምልክት ያለው መጠቀም
የተሸለ ነው

ሀ ለ

ምስል30. ሀ- ቁሻሻን ለማሶገድ ብሩሽ መጠቀም ለ- የተለያየ ቀለማት ያላቸው ጫማዎች

C. የተለያዩ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች


 ተንቀሳቃሽ በመሆናቸው በሽታ አምጪ ህዋሳትን ሊይዙ ይችላሉ

ማስጠንቀቂያ

 የተለያዩ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ከመጠቀማችንና ከተጠቀምን በኃላ በፀረ-ህዋስ መነከር አለባቸው


 ጎድጎድ ያሉና ተመዛዥ እቃዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ለምሳሌ፡- የክትባት ስሪንጅ፣ መንቁር መቁረጫ
መሳሪያ፣ ከገበያ የተመለሱ የዕንቁላል ትሪዎች

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 59


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ሀ ለ

ምስል31. ሀ- ተመዛዥ የክትባት ስሪነጅ ለ- ከገበያ የተመለሰ የዕንቁላል ትሪዎች

D. ተሸከርካሪዎች
 የጫጩት ማመላለሻ፣ የመኖ መጫኛ፣ የዕንቁላል መጫኛ፣ የጎብኚዎች መኪና ወዘተ
 ተንቀሳቃሽ በመሆናቸው በሽታ አምጪ ህዋሳትን ሊይዙ ይችላሉ
በጎማቸው
በታችኛው የተሸከርካሪ ክፍል

ምስል32. የተለያዩ ተሽከርካሪዎች

ማስጠንቀቂያ
 ከዕርባታው 30 ሜትር ርቆ መቆም አለበት
 የሚቆምበትን ቦታ መወሰን
 የተሸከርካሪውን ጎማና የስረኛውን ክፍል ግፊት ባለው ውሃ ማጠብና እና ፀረ-ህዋሳት መድኃኒት
መርጨት

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 60


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል33. የተሸከርካሪ እጥበትና ማቆሚያ ቦታ

E. የዱር አዋፋት
 የተለያዩ በሽታዎችን ሊያስተላልፉ ይችላሉ
ለምሳሌ፡- በቫይረስ የሚመጣ - ፈንግል፣ የዶሮ ኢንፍሎይዛ
በባክቴሪያ የሚመጣ - ሳልሞኔላ፣ ማይኮፕላዝማ
 የዱር አዋፋት በሚከተሉት መንገድ በሽታን ሊያስተላልፉ ይችላሉ
በቀትታ ንኪኪ
ኢ-ቀትታ ንኪኪ፡- ምግብን ወይም ውሃን በኩሳቸው እና ከሰውነታቸው በሚወጣ
ፈሳሽ በመበከል

ምስል34. የዱር አዋፍ

ማስጠንቀቂያ
 አዋፋትን የማያስገባ ቤት መስራት
 የተራረፉ ምግቦችን ከመጋዘን እና ከዶሮ ቤት በፍጥነት ተከታትሎ ማንሳት/ማጽዳት
 የመኖ መጋዘን ሁል ጊዜ ማጽዳት እና ዝግ ማድረግ

F. አይጠ-መጎጥ
 በሽታ አምጪ ህዋሳትን ተሸካሚ ናቸው
 ምግብና ጉዝጓዝን በመበከል በሽታን ያስተላልፋሉ ለምሳሌ፡- የዶሮ ኮሌራ፣ ሳልሞኔላ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 61


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ዕቃዎችን ያወድማሉ፡- የኤሌትሪክ መስመሮችን፣ ፕላስቲክ ውሃ መጠጫዎችን ወዘተ

ምስል35. አይጠ-መጎጥ

ማስጠንቀቂያ
 ቁርጥራጭ ነገሮችን ማሶገድ መራቢያ ስለሚሆን
 ጢሻዎችን ማጥፋት
 የተራረፉ ምግቦችን ማሶገድና ማጽዳት
 በየጊዜው የአይጥ ወጥመድ ከምግብ ጋር ማስቀመጥ

ሀ ለ

ምስል36. ሀ. በዕርባታ ዙሪያ ጢሻ ለ. በዕርባታ ዙሪያ ቁርጥራጭ ሐ. የአይጥ ወጥመድ

G. የቤት እና ሌሎች እንስሳት


 ውሻ፣ ድመት እንዲሁም የቤት አዋፋት በሽታ አስተላላፊ ናቸው
ሳልሞኔላ በሰገራቸው

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 62


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

የዶሮ ኮሌራ በምራቅ


ሲታኮሲስ(Psittacosis) ከፓሮት የሚተላለፍ የመተንፈሻ አካል የሚያጠቃ ነው
ፈንግል

ማስጠንቀቂያ

 የቤት እንስሳት የማይገባበት የዶሮ ቤት መስራት

ምስል36. የቤት እንስሳት

ሌሎች የቤት እንስሳት


 ከብት፣ ፍየል፣ በግ ወዘተ በዶሮ ዕርባታ ዙሪያ የሚረቡ
 በራሪ ነፍሳት፣ አይጥ መራቢያ ይሆናል
 በሽታ የመከሰት እድሉ ይሰፋል

ማስጠንቀቂያ

 የዶሮ ቤት እንስሳት የማይገባበት መሆን አለበት


 በዶሮ ቤት ዙሪያ ማጠር

H. በራሪ ነፍሳት
 በሽታ አምጪ ህዋሳትን ተሸካሚ ናቸው
ትንኝ፡- የዶሮ ፈንጣጣ
ጢንዚዛ፡- ፈንግል፣ በርሳል በሽታ፣ ማሬክስ በሽታ፣ ሳልሞኔላ
ዝንብ፡- ሳልሞኔላ

ምስል37. ጢንዚዛ ዝንብ ትንኝ

ማስጠንቀቂያ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 63


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 አረሞችንና ሳሮችን በየጊዜው ማሶገድ


 ውሃ የሚያቁሩ ቦታዎችን ማስተካከል
 ለበራሪ ነፍሳት እጭ ምግብነት የሚጠቅሙ የዶሮ ኩስ፣ ብስባሽ ቅጠሎች፣ የዶሮ በድን
ማሶገድ
 በግሩፕ በመከፋፈል ፀረ-ነፍሳት መድኃኒቶችን መርጨት

I. የዶሮ ውሃ
 በሽታ አምጪ ህዋሳት ለመራባት ውሃ እጅግ በጣም ይመቻቸዋል
 የአዋፍ ኢንፍሎይዛ፣ ፈንግል፣ ኮሊፎርም፣ ሳልሞኔላ
 የውሃ መፍሰስ የጉዝጓዝ መርጠብን ያስከትላል
ኮሲዲዎሲስ በሽታ ይነሳል
የጉዝጓዝ እርጥበት የእግር ቆዳ እነዲጎዳ ያደርጋል ይህ ደግሞ ባክቴሪያዎች በቀላሉ
ቆዳን ሰርስረው እዲገቡ ይረዳቸዋል፡- የእግር እና የመገጣጠሚያ መቆጣት/መቁሰል
ያስከትላል

ማስጠንቀቂያ

 ጥራት ያለው ውሃ መጠቀም


 ከወንዝ፣ ከኩሬ እንዲሁም ከመስኖ ውሃን የምንጠቀም ከሆነ መጣራት አለበት
 በውሃ ማጠራቀሚያና መስመሮች ውስጥ አልጌና ሌሎች በአድ ነገሮችን እንዳይፈጠሩ ለመከላከል
በየሳምንቱ አዮዲን መጨመር
 ውሃ እንዳይፈስ መከታተል የሚያፈስ ቦታ ካለ መጠገን

J. የዶሮ መኖ/ምግብ
 የመኖ ጥሬ ዕቃዎች ለባክቴሪያ መራቢያነት አመቺ ናቸው ለምሳሌ፡- ሳልሞኔላ
 እርጥበት ያላቸው የመኖ ጥሬ ዕቃዎች ለፈንገስና ለሻጋታ መራቢያነት አመቺ ናቸው
አስፐርጂለስ፡- ሳንባ በሽታ ያስከትላል
ማይኮቶክሲን(አልፋቶክሲኮሲስ)፡-
 በአካል ውስጥ ደም መፍሰስ
 የእድገት መጓተት
 የበሽታ ተከላካይ ህዋስ መዳከም

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 64


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል38. የሻገቱ የመኖ ጥሬ እቃዎች

ማስጠንቀቂያ
 ጥራቱን የጠበቀ መኖ በግዛት
 የመኖ ማከማቻ ሁልጊዜ ዝግ መሆን አለበት
 የመኖ ማከማቻ ጣሪያ የማያፈስ መሆን አለበት
 መመገቢያ ዕቃዎች የጸዱ መሆን አለባቸው
 የመጠጫ ዕቃዎች ወደ መመገቢያ ዕቃዎች የሚያፈሱ መሆን የለባቸውም

K. የታመሙና የሞቱ ዶሮዎችን ማሶገድ


 የሞቱ ዶሮወች ጤነኛ ለሆኑ ዶሮዎች አደጋ ስለሆኑ በአግባቡ ማሶገድ አለብን

ምስል39. የሞቱ ዶሮዎች

ማስጠንቀቂያ
 የሞቱ ዶሮዎችን ወዲያው ማሶገድ
 የሞቱ ዶሮዎችን የምናሶግድበት መንገድ፡-
ማበስበስ(ኮምፖስቲነገ)
ማቃጠል
መቅበር

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 65


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል40. ሀ. ማቃጠል ለ. ኮምፖስቲንግ

በፍጹም የማይደረጉ ድርጊቶች !!!!!!!!


 የሞቱ ዶሮዎችን መብላት ወይም መሸጥ
 የሞቱ ዶሮዎችን በወንዝ፣ በመስኖ እና በሀይቅ መጣል
 የሞቱ ዶሮዎችን ለውሻ መመገብ

7.4 ዋና ዋና የዶሮ በሽታዎች(Poultry Diseases)


 በቫይረስ የሚመጣ(Viral Disease)
o ኒውካስትል በሽታ(Newcastle Disease)
o ማሬክስ በሽታ(Mareks Disease)
o ጉምቦሮ በሽታ(የዶሮ ኤድስ(Gumboro Disease)

o የዶሮ ፈንጣጣ(Fowl Pox)


o ተላላፊ የጉሮሮ መቆጣት(Infectious Bronchitis)
o ሊምፎይድ ሊውኮሲስ(Lymphoid Leukosis)
 ባክቴሪያል በሽታዎች(Bacterial Diseases)
o ኮሊባሲሎሲስ( Colibacillosis)
o ተላላፊ ኮራይዛ(Infectious Coryza)

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 66


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

o የዶሮ ኮሌራ(Fowl Cholera ፣ avianpasteurellosis)


o ፖሉረም በሽታ (PULLORUM DISEASE)
o ማይኮፕላዝሞሲስ (MYCOPLASMOSIS)
 ፕሮቶዞአል በሽታ(Protozoal Disease)
o ኮሲዲኦሲስ(COCCIDIOSIS)

 ፈንጋል በሽታ
o አስፐርጂሎሲስ(ASPERGILLOSIS)
o አፍላቶክሲኮሲስ (AFLATOXICOSIS)
 የጥገኛ-ህዋስ በሽታ(Parasitic Diseases)
o የውስጥ-ጥገኛ ህዋስ በሽታ(Internal(Endoparasitic Diseases)
የሳንባ ጥገኛ-ትል (Lung Worm)
የአንጀት ትል(Intestinal parasites)
o የውጪ ጥገኛ-ህዋስ(Ectoparasites(External Parasites)
የዶሮ መዥገር(Fowl Tick)
የዶሮ ቅንቅን(Fowl Mites)
ትንኝ፣ ጢንዚዛ እና በራሪ ነፍሳት

8. የዶሮዎች አያያዝ

8.1. የጫጩቶች አስተዳደግና አያያዝ


አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 67
ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ
ሁለት የጫጩት ማሳደጊያ ዘዴዎች አሉ፡፡ እነዚህም ተፈጥሯዊና ሰውሠራሽ ዘዴዎች ናቸው፡፡ ጫጩቶቹ በዶሮዎች
የተፈለፈሉ ከሆነ ቁጥራቸው አነስተኛ ነው ስለሚሆን በተፈጥሮ መንገድ ዶሮዋ ራሷ እንድታሳድጋቸው ማድረግ ይመረጣል፡፡
በሰውሠራሽ ዘዴ ዕንቁላል በሚፈለፈልበት ጊዜ በአብዛኛው በአንድ ጊዜ ብዙ ጫጩቶች ስለሚኖሩ ተመጣጣኝ ሰውሠራሽ የጫጩት
ማሳደጊያ አስፈላጊ ነው፡፡
a. ተፈጥሯዊ የጫጩቶች አስተዳደግ ዘዴ
ይህ ዘዴ በገጠሩ የአገራችን ክፍል እንደሚደረገው አነስተኛ የዶሮዎች ቁጥር ያላቸው አርቢዎች የሚጠቀሙት ዘዴ ነው፡፡
ለዚህ ተግባር ጭር የማለት ጠንካራ ባህርይ ያላቸው የአገር ዝርያ ዶሮዎችን በመጠም ዕንቁላሎቹ ከተፈለፈሉ በኃላ
ጫጩቶቻቸው የሚፈልጉትን ሙቀትና ሌላ እንክብካቤ ራሳቸው በመስጠት ያሳድጋሉ፡፡ በዶሮዋ ትልቅነት የሚወሰን
ቢሆንም አንዲት ዶሮ ከ 15 – 20 ጫጩቶችን ተንከባክባ ማሳደግ ትችላለች፡፡
b. ሰውሠራሽ የጫጩቶች አስተዳደግ ዘዴ
በዚህ ዘዴ ጫጩቶችን ማሳደግ የሚከተሉት ጠቀሜታዎች አሉት፡፡
 ጫጩቶችን በማንኛውም ወቅት ማሳደግ ያስችላል
 በአንድ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ጫጩቶችን ማሳደግ ያስችላል
 ጫጩቶች ላይ የሚደርሰው የሞት አደጋ በእጅጉ ይቀንሳል
ቅድመ ዝግጅት

 ቤት ውስጥ የተደረገውን ጉዝጓዝ ሙሉ በሙሉ በማውጣት ከአካባቢው ማራቅ፡፡

 በቤቱ ውስጥ ቀደም ሲል በግድግዳ ፣ በወለልና በጣሪያ ላይ ያለውን ማንኛውንም ደረቅ ቆሻሻ ጠርጎ በማውጣት ኃይል
ባለው ውሃ ማጠብ፡፡ የማይል አካባቢ በሚገባ በመፈግፈግ ቆሻሻው መልቀቁን ማረጋገጥ፡፡

 በፀረ-ተዋስያን (ዲስኢንፌክታንት) ቤቱን በሙሉ በሚገባ መርጨት

 በማሳደጊያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ዕዎችን በሙሉ በሚገባ ማፅዳትና ዲስኢንፌክታንት መርጨት ወይም መንከር

 የቤቱ ማፅዳቱ ሥራ ከተጠናቀቀ በኃላ በቤቱ ዙሪያ ያለውን አካባቢ በሙሉ ማፅዳት ያስፈልጋል፡፡

 አዳዲሶቹ ጫጩቶች ከመግባታቸው በፊት ቤቶቹ ለአንድና ለሁለት ሳምንታት ያህል ባዶ ሆነው እዲቆዩ ማድረግ

 ጫጩቶቹ ይደርሳሉ ተብለው ከሚጠበቁበት ጥቂት ቀናት በፊትም ቤቱ ውስጥ የሚያስፈልገው የመጨረሻ ዝግጅት
መደረግ አለበት
o ከ 7 – 10 ሳንቲ ሜትር ውፍረት ያለው አመቺ ጉዝጓዝ ማድረግ
o ዕቃዎች ተገቢ ቦታቸውን መያዛቸውንና መብራቶች ፣ ማሞቂያዎች ወዘተ በትክክል መስራታቸውን ማረጋገጥ

የጫጩቶች የወለል ስፋት ፍላጎት

 ለመጀመሪያዎቹ 5 እና 6 ሳምንታት ዕድሜ የተለያዩ የጫጩት ዓይነቶች የሚያስፈልጋቸው የወለል(ቦታ) ፍላጎት


በዶሮዎቹ ዝርያ ፣ ፆታና የዕርባታ ዓላማ ይለያያል፡፡

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 68


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

የጫጩት ዓይነት የጫጩት ብዛት በካሬ ሜትር


ሌግ ሆርን ሴት ጫጩቶች 14
ሌግ ሆርን ለማዳቀል የሚውሉ ሴት ጫጩቶች 13
ሌግ ሆርን ለማዳቀል የሚውሉ ወንድ ጫጩቶች 11
መካከለኛ ክብደት ያላቸው የዕንቁላል ዝርያ ሴት ጫጩት 13
የስጋ ዝርያ ሴት ጫጩት 11
የስጋ ዝርያ ሴት ጫጩት 9

ሰንጠረዥ-3 የጫጩት የወለል (ቦታ) ፍላጎት


የብርሃን ሁኔታ

 ጫጩቶች በተለይ ለመጀመሪያዎቹ 48 ሰዓታት ያለማቋረጥ በቂ ብርሃን ማግኘት አለባቸው

o መጠጣትና መብላል እንዲጀምሩ


o በሚጠጡት ውሃ ላይ የሚያፀባርቀው ብርሃን ጫጩቶችን እንዲጠጡ ይጋብዛቸዋል
 ጫጩቶች ከ 48 ሰዓት በኃላ መብላትና መጠጣት ስለሚጀምሩ የብርሃን መጠን ሊቀንስ ይችላል

 በዚህ ወቅት 23 ሰዓት ብርሃን ማግኘት አለባቸው፡፡ ለአንድ ሰዓት መብራት እንዲጠፋ የሚደረገው ጭለማን
እንዲለማመዱ ነው፡፡

 የብርሃኑ ጊዜ በየሳምንቱ በእኩል መጠን እየተቀነሰ 20 ሳምንት (5 ወር) በሚሆናቸው ጊዜ ከተፈጥሮ የቀን ብርሃን
ርዝመት (በኛ ሁኔታ 12 ሰዓት) ጋር እንዲስተካከል መደረግ አለበት፡፡

የሙቀት ሁኔታ

 ለስጋ ጫጩት፡- 32 OC
 ለዕንቁላል ጫጩት፡- 30 OC
 ጫጩቶች እያደጉ ሲሄዱ ፣ የሙቀቱ መጠን ከአካባቢው ሙቀት ጋር እስኪስተካከል ድረስ በየሳምንቱ ከ 3 እስከ 4 ዲግሪ
ሴንቲ ግሬድ መቀነስ ያስፈልጋል()

 ይህን ለማድረግ ተንጠልጣይ ማሞቂያዎች ከፍ ሊሉ ይገባል(ምስል)

 ሙቀቱ ለጫጩቶቹ ተስማሚ መሆኑን ለመረዳት የጫጩቶቹን ሁኔታ በቅርበት መከታተል ያስፈልጋል

 ጫጩቶች በሚገቡበት ጊዜም ቤቱ ሞቅ ብሎ እንዲጠብቃቸው ማሞቂያውን ከአንድ ቀን በፊት ስራ ማስጀመር


ይጠቅማል

 ተፈላጊውን ሙቀት ጫጩቶቹ እንዲያገኙ የተለያዩ ማሞቂያዎችን ልንጠቀም እንችላለን

 በማሞቂያው ዙሪያ የሚደረግ ጫጩቶች ከማሞቂያው እንዳይርቁ ለማድረግ የሚጠቅም ግርዶሽ እንጠቀማለን

የጫጩት ዕድሜ በሳምንት የማሞቂያው ከፍታ በሴሜ የሙቀት መጠን OC


0-1 10 32 - 30

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 69


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

1–2 15 30 - 28
2–3 20 28 - 25
3–4 25 25 - 22
4-5 30 22 - 20
5-6 35 20 - 18
ሰንጠረዥ 4 የጫጩት የሙቀት ፍላጎት

በኤሌክትሪክ የሚሰራ በጋዝ የሚሰራ

በፓራፊን የሚሰራ ማሞቂያ(ማሾ) በከሰል ፣ በእንጨት ወይም በዘይት የሚሰራ

ምስል 41 የተለያዩ የጫጩት ማሞቂያዎች

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 70


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል 42 ከእንጨትና ከሳር የተሰራ የጫጩት ማሞቂያና ማሳደጊያ(የኃይል አቅርቦት በሌለበት)

ምስል 43 ግርዶሽ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 71


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ማሞቂያ

በጣም ዝቅተኛ ሙቀት ሀይለኛ ንፋስ ሲኖር በጣም ከፍተኛ ሙቀት አመቺ ሙቀት
ሲኖር ሲኖር ሲኖር

ምስል 44 ለተለያየ የሙቀት ሁኔታ ጫጩቶች የሚያሳዩት ስርጭት

የውሃ አቅርቦት

 ጫጩቶች ምግብ ከመብላታቸው በፊት ውሃ መጠጣት ይጀምራሉ

 ምክንያቱም ጫጩቶች ከማስፈልፈያ ከወጡ በኃላ ከሰውነታቸው በሚወገደው ውሃ በአማካኝ አንድ ግራም በሰዓት
ክብደት ይቀንሳሉ

 ጫጩቶች ከመፈልፈላቸው ከ 4 ሰዓታት በፊት የጫጩት ውሃ መጠጫዎች መሞላል አለባቸው

 ይህ የውሃው ሙቀት ትንሽ ከፍ እንዲል ስለሚያደርግ ጫጩቶቹ በቀላሉ መጠጣትን ይላመዳሉ

 የውሃው ሙቀት ለብ ያለ ወይም መካከለኛ ቢሆን የውሃ ፍጆታቸው ከፍ ያደርገዋል(18 – 20 OC)


 የውሃ መጠጫዎችን በየቀኑ ማጽዳት ያስፈልጋል

 በመጀመሪያው ቀን በሚሰጣቸው ውሃ ውስጥ 8% ያህል ስኳር ማሟሟት ጫጩቶቹ በቂ ኃይል ሰጪ ምግብ እንዲያገኙ
ያግዛል

 ከላይ የተጠቀሰውን 8% ስኳር ውህድ ለማዘጋጀት በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ 80 ግራም ስኳር ማሟሟት ወይም በ 12.5
ሊትር ውሃ ውስጥ 1 ኪሎ ስኳር ማሟሟት

 በተጨማሪም የቪታሚንና የማዕድናት ድብልቅ በውሃ አሟሙቶ ከ 3 – 4 ቀን መስጠት ጫጩቶቹ በሽታን መቋቋም
እንዲችሉ ያደርጋል

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 72


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

የጫጩት ዓይነት የመጠጫ ፍላጎት (ሳንቲ ሜትር በጫጩት)


የዕንቁላል ዝርያ 1.5
የሥጋ ዝርያ ሴት 1.8
የሥጋ ዝርያ ወንድ 2.5
ሰንጠረዥ 5 የጫጩቶች የመጠጫ ፍላጎት

ዕድሜ(በቀን) ፍጆታ(ሊትር) ዕድሜ(በቀን) ፍጆታ(ሊትር)


1 8.3 8 19.6
2 9.5 9 22.3
3 10.5 10 25.4
4 12.9 11 28.8
5 13.6 12 32.9
6 15.5 13 37.9
7 17.4 14 43.5
ሰንጠረዥ 6 በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት የእንቁላል ዝርያ ጫጩቶች አማካይ የየቀኑ የውሃ ፍጆታ (ለ 1000 ጫጩቶች)

ምስል 45 የተለያዩ ዘመናዊ የጫጩት መጠጫዎች

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 73


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

የመኖ አቅርቦት

 የተደባለቀ መኖ ከአንድ ሳምንት ፍጆታ በላይ ገዝቶ ማከማቸት ጥሩ አይደለም

 ጫጩቶች መኖ በቀላሉ እንዲያገኙ በመጀመሪያዎቹ ቀናት በአጭር ጠፍጣፋ መኖ ማቅረቢያዎች መመገብ አለባቸው

 ለያንዳንዱ 100 ጫጩቶች አንድ የዚህ ዓይነት መመገቢያ ያስፈልጋል

 ጫጩቶቹ በሙሉ እየበሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል

 የሚባክን መኖ መኖሩን በየጊዜው መከታተል ይገባል

 ርዝመት ያለው መመገቢያ ከሆነ ለአንድ ጫጩት 5 ሳንቲ ሜትር ሊያዝ ይገባል ፣ ክብ መመገቢያ ከሆነ ለአንድ ጫጩት 4
ሳንቲ ሜትር

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 74


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ
ምስል 46 የተለያዩ መመገቢያዎችና መጠጫዎች

ሌሎች ተግባራት

 መንቁር ቆረጣ

o ጫጩቶች አብዛኛውን ጊዜ ከ 5 – 10 ቀን ዕድሜ ሲሆናቸው መንቁራቸውን ይቆረጣሉ


o እርስ በእርስ የመበላላትና የመነካከስ ባህሪያቸውን ለመቀነስ
o ጫጩቶች መንቁራቸውን ከተቆረጡ መነካከሳቸውና መበላላታቸው ስለሚቀንስ የዶሮዎቹ እድገትና
ምርታማነት ይሻሻላል

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 75


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ
ምስል 47 የመንቆር መቁረጫና የአቆራረጥ ዘዴ

ክትባት

 ዶሮዎች ተፈጥሮዓዊ ባህሪያቸውን ስንመለከት በቀላሉ በበሽታ ይጠቃሉ በቀላሉ ይሞታሉ

 በዕርባታ ውስጥ በሽታ ከተከሰተ አብዛኛዎቹ የሞት እድላቸው የሰፋ በመሆኑ ትልቅ ኪሳራ አለው

 አስቀድሞ በመከላከል ላይ የተመሰረተ ዕርባታ ከሆነ የዶሮ በሽታን መቀነስ ይቻላል

 ዋንኛውና እጅግ በጣም ሊተኮርበት የሚገባው የዶሮ በሽታ መከላከያ ዘዴ ክትባት ነው

 በአካባቢው እንደሚከሰቱት የበሽታ ዓይነቶችና እንደሚረቡት የዶሮዎች ዓይነትም የሚያስፈልገው የክትባት ዓይነትና
ፕሮግራም ሊለያይ ይችላል

 ደብረ ዘይት የሚገኝው ብሄራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ለፈንግል(Newcastle Disease) እና ለዶሮ
ፈንጣጣ(Fowl Pox) የሚሆኑ ክትባቶችን ያመርታል

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 76


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል 48 የፈንግል ፣ የማሬክስና የዶሮ ፈንጣጣ በሽታ ክትባቶች

8.2 የታዳጊ ዶሮዎች አያያዝ

 ጫጩቶች ከ 6 እስከ 8 ሳምንታት ዕድሜ ባለው ውስጥ ወደ ዕንቁላል ጣይ ቤት በ 20 ሳምንት ዕድሜያቸው አካባቢ
እኪገቡ ድረስ ወደሚቆዩበት የታዳጊ ቤት ይዛወራሉ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 77


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ታዳጊ ዶሮዎችን ከጫጩት ቤት ማዛወር የግድ አስፈላጊ የሚሆነው የጫጩት ቤቱ ለሌሎች ጫጩቶች ማሳደጊያ
ወዲያው አስፈላጊ ሲሆን ነው፡፡ አለበለዚያ አንዳንድ ለውጦች በቤቱ ውስጥ አድርጎ እዚያው ቤቱ ውስጥ መኖር ሊቀጥሉ
ይችላሉ
የወለል ስፋት (ቦታ) ፍላጎት

 በዚህ ዕድሜ ያሉ ዶሮዎች ከፍ ያሉ ስለሆኑ ሰፋ ያለ ቦታ ይፈልጋሉ

 ይህ ፍላጎታቸው ግነ እንደ ዶሮዎቹ ዝርያና የአካባቢው አየር ሁኔታ ይለያያል

ዝርያና ፆታ የዶሮዎች ብዛት በካሬ ሜትር


ሌግ ሆርን የእንቁላል ዝርያ ቄቦች
 እስከ 18 ሳምንት 12
 እስከ 22 ሳምንት 7
መካከለኛ ክብደት ያላቸው የዕንቁላል ዝርያ ቄቦች
 እስከ 18 ሳምንት 9
 እስከ 22 ሳምንት 6
ሌግ ሆርን ለማዳቀል የሚውሉ ቄቦች 6
ሌግ ሆርን ለማዳቀል የሚውሉ አውራዎች 6
መካከለኛ ክብደት ያላቸው ለማዳቀል የሚውሉ ቄቦች 6
መካከለኛ ክብደት ያላቸው ለማዳቀል የሚውሉ አውራዎች 5
የሥጋ ዝርያ ለማዳቀል የሚውሉ ቄቦች 4
የሥጋ ዝርያ ለማዳቀል የሚውሉ አውራዎች 3
ሰንጠረዥ 7 አማካይ የታዳጊ ዶሮዎች የወለል ስፋት ፍላጎት

የታዳጊ ዶሮዎች መመገቢያና መጠጫ

የመጠጫ ፍላጎት ሴንቲ ሜትር ለአንድ


የታዳጊ ዓይነት የመመገቢያ ፍላጎት ሴንቲ ሜትር ለአንድ ዶሮ
ዶሮ

ሌግ ሆርን የዕንቁላል ዝርያ ቄቦች 1.9 6.4


መካከለኛ ክብደት ያላቸው ቄቦች 2.2 7.6
የሥጋ ዝርያ ቄቦች 2.5 10
ሰንጠረዥ 8 የታዳጊ ዶሮዎች የመመገቢያና መጠጫ ፍላጎት

የአየር እንቅስቃሴ

 ታዳጊ ዶሮዎች በእድሜና በሰውነት መጠን ከጫጩቶች ከፍ ያሉ ናቸው

 ስለዚህ የሚፈልጉት የኦክስጅን መጠንና የሚያስወጡት የካርቦንዳይ ኦክሳይድ መጠን ከፍተኛ ነው

 ብዙ ምግብ በመመገብ በዛ ያለ ኩስ ስለሚጥሉም ፣ አሞኒያ የተባለው ጋዝ በፍጥነት ሊጨምርና ቤቱ ውስጥ በቀላሉ


መጥፎ ሽታ ሊፈጠር ይችላል

 የዚህ ሁሉ ድምር ውጠየት በቤቱ ውስጥ በቂ ያየር እንቅስቃሴ ከሌለ በታፈን ብቻ ሳይሆን ዶሮዎቹን በቀላሉ ለተለያየ
በሽታ የሚያጋልጥ ይሆናል

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 78


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 ከላይ የተጠቀሰው ሁኔታ ከፍተኛ ሙቀት ከተጨመረበት ደግሞ ችግሩ እጥፍ ነው

 ስለዚህ በታዳጊ ዶሮዎች ቤት ውስጥ ከጫጩቶች በተለየ ሁኔታ በቂ የአየር እንቅስቃሴ እንዲኖረው ማድረግ የግድ ነው

የጉዝጓዝ ሁኔታ መቆጣጠር

 በታዳጊ ቤት ውስጥ የጉዝጓዝ ሁኔታ መከታተል ያስፈልጋል

 በታዳጊ ቤት ውስጥ ያለ ጉዝጓዝ ከ 20 – 30% ሊኖረው ይገባል


 በጣም ከደረቀ የመተንፈሻ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል

 በጣምም ርጥብ ከሆነ ለበሽታ አምጪ ተዋሲያን በተለይ ኮክሲድዮሲስ ለተባለ በሽታ መስፋፋት በጣም አመቺ ይሆናል

 የጉዝጓዝ እርጥበት መጠን እዲጨምር የሚያደርጉ ዋንኛ ምክንያቶች

o የሚፋሰስ ውሃ
o በዶሮ ቤት ውስጥና ውጪ ያለው የአየር እርጥበት መጠን
o በቤት ውስጥ ያሉ ዶሮዎች ዕድሜ ፣ ቁጥርና ክብደት
o በቤት ውስጥ ያለው የአየር እንቅስቃሴ በቂ አለመሆን
o የመኖ ይዘት በተለይ የጨው መጠን
o የዶሮዎቹ የውሃ ፍጆታ

ችግር ያለባቸውን ዶሮዎች ማሶገድ

 ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ የዶሮዎቹን ሁኔታ በመቃኘት በሽተኛ የሚመስሉ ፣ ሽባ የሆኑ ፣ የቆሰሉ ፣ ቅርፃቸው በተለያየ
ምክንያት የተበላሸ ወዘተ ዶሮዎችን ማሶገድ ያስፈልጋል

በዶሮዎች ቤት ውስጥ ስለሚደረጉ ለውጦች

 ዶሮዎች በተፈጥሮዋቸው በቤታቸው ውስጥ የሚደረግ ማንኛውም ለውጥ ለመቀበል ይቸገራሉ፡፡ ስለዚህ እንደ መመገቢያ
፣ መጠጫ ወዘተ ላይ ለውጦች ሲደረጉ ቀስ በቀስ መሆን አለበት፡፡

የብርሃን ሁኔታ

 የተፈጥሮ ወይም ሰውሠራሽ ብርሃን ዶሮዎች መብላት መጠጣት ወዘተ እንዲችሉ ያስችላል

 በታዳጊ ዶሮዎች ላይ ፒቱታሪ የተባለውን ዕጢ በማነቃቃት ዕንቁላል እዲጥሉ ያስችላል

 ቄቦች ዕንቁላል መጣል የሚጀምሩበት ዕድሜ በቀጥታ ከብርሃን ጋር የተያያዘ ነው

 ለጫጩት የነበረው የብርሃን ሁኔታ ለታዳጊ ዶሮዎችም ከቀጠለ ዶሮዎቹ እንቅስቃሴ ያበዛሉ ፣ እርስ በእርስ የመበላላት
እንዲሁም የመጣላት ሁኔታ ያሳያሉ

 ስለዚህ በቀን በ 23 ሰዓት ብርሃን የተጀመረው የጫጩቶች አስተዳደግ በየሳምንቱ ይቀነሳል

8.3 የዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች አያያዝ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 79


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

የማሳደጊያና የዕንቁላል መጣያ ቤቶች የተለያዩ ከሆኑ ቄቦች ከ 16 እስከ 21 ሳምንት ዕድሜ በሚሆናቸው ጊዜ ወደ
እንቁላል መጣያ ቤት ሊዘዋወሩ ይችላሉ፡፡ ከ 22 እስከ 24 ሳመንት ዕድሜ ባለው ጊዜ ውስጥ ቄቦች ዕንቁላል መጣል ይጀምራሉ፡፡

ቅድመ ዝግጅት

 ቀደም ሲል ለጫጩቶችና ለታዳጊዎች በዝርዝር በቀረበው መልክ ቤቱ በሚገባ ፀድቶ መድሃኒት መረጨት አለበት ፣ ቤቱን
ለተወሰነ ጊዜ ባዶውን ማቆየት ፣ ጥቅም ላይ የሚውሉ ዕቃዎች በሚገባ መፀዳት አለባቸው

 ከ 5 እስከ 8 ሳንቲ ሜትር ከወለሉ በላይ ውፍረት ያለው አዲስና አመቺ ጉዝጓዝ ማንጠፍ

 ዶሮዎቹ በቀላላሉ እዲለማመዱት እንቁላል መጣል ይጀምራሉ ተብሎ ከታሰበበት አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ጉዝጓዙ
መዘጋጀት አለበት

 ቤቱ ውስጥ ለግልጋሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሙሉ በትክክል መስራታቸውን ማረጋገጥና ጥገና የሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች
እንዲሁም ቤቱም ጭምር በዚህ ወቅት አስፈላጊውን ጥገና ሊደረግላቸው ይገባል
የዶሮዎች መረጣ

 ምርታማ የማይሆኑ ዶሮዎችን ቀደም ብሎ በመለየት ወይም በማስወገድ ትርፋማነትን ማሻሻል ያስችላል

የወለል ስፋት (ቦታ) ፍላጎት

 የቦታ ስፋት ፍላጎት እንደ ዝርያው ዓይነት የሚለያይ ቢሆንም በአማካይ ለስድስት ዶሮዎች አንድ ካሬ ሜትር ቦታ በቂ ነው
መመገቢያና መጠጫ

 በረዥም መመገቢያዎች በአማካይ 10 ሳንቲ ሜትር ለአንድ ዶሮ ያስፈልጋል ፣ ለመጠጫ ደግሞ 2.5 ሳንቲ ሜትር ለአንድ
ዶሮ ሲያስፈልግ በክብ መመገቢያና መጠጫ ላይ 20% ተጨማሪ ዶሮዎችን ማስተናገድ ይቻላል፡፡

 አዲሱን ሁኔታ እስኪለማመዱት ድረስ ከሚፈለገው ቁጥር በላይ መመገቢያና መጠጫ ተሰራጭቶ መገኘት አለበት

 በቀላሉ እዲላመዱ መመገቢያዎችና መጠጫዎች በማደጊያ ቤት የነበሩበት ዓይነቶች ቢሆኑ ይመረጣል


ከፍተኛ ሙቀት በዕንቁላል ምርት ላይ ያለው ተፅዕኖ

 የዕንቁላል ምርት በአብዛኛው የቤቱ ሙቀት መጠን 27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እስከሚደርስ ድረስ አይቀንስም

 የዕንቁላል ክብደት መጠን ግን ሙቀቱ ከ 24 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ሲሆን መቀነስ ይጀምራል

 የሙቀቱ መጠን ከ 16 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ እየጨመረ ሲሄድ ፣ የምግብ አጠቃቀም መቀነስ ይታያል

 ከፍተኛ ሙቀት በዕንቁላል ምርትና መጠን ብቻ ሳይሆን በቅርፊቱ ውፍረትና በዕንቁላሉ ውስጣዊ ይዘት ላይም ተፅዕኖ
ያሳድራል
የብርሃን ሁኔታ

 ዶሮዎቹ በየቀኑ ከ 16 እስከ 18 ሰዓታት ብርሃን ማግኘት አለባቸው

 የብርሃን ሁኔታን በተመለከተ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ማጤን ተገቢ ነው

o በዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ቤት ውስጥ በሚዘረጉ አምፑሎች መካከል ያለው ርቀት ከመሬት እስከ አምፑል ያለውን
ርቀት 1 ½ ጊዜ መሆን አለበት

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 80


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

o የአምፖሎቹ ከፍታ ስራን በማያውክ መልክ ለዶሮዎቹ ቀረቤታ ቢኖረው ይመረጣል፡፡ ሁለቱን ለማጣጣም ከ 2.1
እስከ 2.4 ሜትር ከፍታ እንደ መደበኛ መውሰድ ይቻላል
o አንድ ዋት የአንፑል ኃይል ለ 0.37 ካሬ ሜትር የመሬት ስፋት የሚፈልገውን የብርሃን መጠን ይሰጣል
o በዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ቤት ውስጥ የሚገኙ አምፑሎች በአቧራ ሊሸፈኑ ስለሚችሉ ቢያንስ በ 2 ሳምንት
አንዴ ወይም ከዚህ ባጠረ ጊዜ ማፅዳት ያስፈልጋል
o ፍሎረሰንት መብራት ከሌላው ተራ አምፑል ከሶስት እስከ አራት እጥፍ ብርሃን መስጠት ይችላል
የዕንቁላል መጣያ

 በዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ቤት ውስጥ ከሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች አንድኛው ዕንቁላል መጣያ ወይም መውለጃ ነው

 መውለጃቸውን በጠዋት መክፈት ያስፈልጋል

 ቀዝቀዝ ያለ ወቅት ከሆነ ከመውለጃዎች ውስጥ ዕንቁላሎችን በቀን ሶስት ጊዜ ፣ ሞቃት ከሆነ ደግሞ በቀን አራት ጊዜ
ማንሳት ያስፈልጋል

 በመውለጃ ውስጥ የሚደረገው ጉዝጓዝ በየጊዜው እንዳስፈላጊነቱ መጨመር ወይም እንዳለ መቀየርም የሚሰበሩና
የሚቆሽሹ እንቁላሎችን ቁጥር ይቀንሳል

 መውለጃዎችን ጨለም ያለ ቦታ ማስቀመጥ

 ቄቦች እንቁላል መጣል ከመጀመራቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ መውለጃዎችን ማስቀመጥ

 ላሉት ዶሮዎች በቂ መውለጃ ማዘጋጀት ፣ አንድ ዕንቁላል መውለጃ ወይም መጣያ ለአምስት ዶሮዎች በቂ ነው

 የአንዱ ዕንቁላል መውለጃ ስፋት(መጠን) 30 x 30 x 30 ሴንቲ ሜትር ነው


 የዕንቁላል መውለጃ ከተለያዩ ማቴሪያሎች ሊሰሩ ይችላሉ

ምስል 49 የተለምዶ ዕንቁላል መውለጃ

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 81


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል 50 የዕንቁላል መውለጃ ወይም መጣያ

8.4 የስጋ ዶሮዎች አያያዝ

 መሰረታዊ አያያዘቸው ከእንቁላል ጣይ ዶሮዎች ጋር ተ መሳሳይ ቢሆንም ከተፈለፈሉ በሁለት


ወርና ከዚያ ባነሰ ጊዜ ለገበያ መቅረብ የሚችሉና ፈጣን ዕድገትና እንክብካቤ የሚሹ ናቸው
 የስጋ ዶሮ አያያዝ ከእንቁላል ዶሮ አያያዝ የተለየ ጥንቃቄና የቅርብ ክትትል የሚያሻ ነው
 የመኖና የውሃ ፍጆታቸው ከፍተኛ ነው
 ቶሎ የማደግና የመወፈር ባህሪ አላቸው
 የብርሀን ሁኔታ:

o ለጀማሪዎቹ 48 ሰዓት በቂ መብራት ማግኘት አለባቸው

o መብላትና መጠጣት እንዲጀምሩ

o በአጭር ጊዜ ለገበያ መድረስ ስላለባቸው

አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገፅ - 82


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

9. የዶሮዎች መጠለያ (ቤት)


9.1. መሠረታዊ ሁኔታዎች
የዶሮዎች ቤት እንደሁኔታው በተለያየ ደረጃና ዓይነት ሊሰራ ቢችልም የሚከተሉትን መሰረታዊ
ሁኔታዎች ማሟላት ይገባዋል፡፡

 ምቾት፡- ምቹ የዶሮ ቤት ያልተጨናነቀ ፣ በሙቀት ወቅት ውስጡ ቀዝቀዝ ያለ ፣ ንፁ አየር


የሚንቀሳቀስበት ፣ በቂ ብርሃን ያለውና መሬቱ ርጥበት የሌለው ነው

 አመቺነት፡- ቤቱ በአመቺ ቦታ ተሰርቶ በቤቱ ውስጥ ያሉት የተለያዩ መገልገያዎች ለስራ


በሚያመች ሁኔታ መቀመጥ አለባቸው ፣ ሰራተኞች ስራቸውን በተቀላጠፈ መልኩ
እንዲያከናውኑ የሚያመች መሆን አለበት

 ዶሮዎችን ከጥቃት የሚከላከል፡- ዶሮዎችን ከሚያጠቁ አውሬዎች ፣ ለውጭ ጥገኛ


ተዋሲያን መራባት የማያመች ፣ ዕንቁላል ለሚሰርቁና ጫጩቶችን ለሚያጠቁ እንደ አይጥ
ላሉ አውሬዎች መራባት የማያመች መሆን አለበት
9.2 የዶሮዎች ቤት አቀማመጥ
 ለመኖሪያ ቤት ቅርበት እንዲኖረው ሆኖ መሰራት የለበትም
 በቂ የፀሐይ ብርሃን በሚያገኝበት አቅጣጫ መሰራት አለበት
 በተዳፋት መሬት ላይ ቢሰራ ይመረጣል
 ኃይለኛ ንፋስ በሚነፍስበት አቅጣጫ መሰራት የለበትም
 አየር በበቂ ሁኔታ ሊዘዋወርበት የሚችል መሆን አለበት
 መካከለኛ የሙቀት መጠን የሚጠብቅ ቤት መሆን አለበት
 የዶሮ ቤት እርጥበት መጠን በጣም ዝቅተኛ መሆን አለበት
9.3 የዶሮዎች ቤት አሠራር ዘዴ
 የወለል አሠራር
o የዶሮ ቤት ወለል የተደለደለ አፈር ፣ ሽቦ ወይም እንደ እርባታው መጠንና
የመዋዕለ ንዋይ ደረጃ በኮንክሪት (ሲሚንቶ) ለሰራ ይችላል
o ወለሉ የተስተካከለ ፣ የውጪ ጥገኞች መራቢያ ሊሆን የሚችል ስንጥቅ የሌለው ፣
ለማፅዳት የሚመች ፣ ለአይጦች መራባት የማይመችና ረዘም ላለ ጊዜ ሊያገለግል
የሚችል ቢሆን ይመረጣል

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 83


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

o ወለሉ 0.25 ሜትር ያህል ከመሬት ከፍታ ቢኖረው ይመረጣል


 የግድግዳ አሠራር
o በእኛ አገር የአየር ንብረት ሁኔታ የቤቱ ረዥም ወገን ግራና ቀኝ የሚገኝ ሁለት
ግድግዳዎች ከግማሽ በላይ ክፍት ቢሆኑ ይመረጣል
o ክፍት የሆነው እንደ መረብ በተሰራ ሽቦ መሸፈን አለበት
o በአንዳንድ ወቅቶች ማለትም በዝናብ ወይም በቅዝቃዜ ወቅት እንደ ሽፋል
የሚያገለግል ፕላስቲክ ወይም ተመሳሳይ መሸፈኛ ሊጠቀለል በሚችል መልኩ
ቢሰራ ጥሩ ነው
 የጣሪያ አሰራር
o የዶሮ ቤት ጣሪያ ከቆርቆሮና ሳር እንዲሁም ከሌሎች ሊሰራ ይችላል
9.4 የዶሮዎች የመጠለያ ዓይነቶች
የዶሮ መጠለያ ዓይነቶች በአጠቃላይ በአራት ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡ ያሉትም አማራጮች የሚከተሉት
ናቸው፡፡
I. የጭሮሽ ዕርባታ
 በገጠሩ የአገራችን ክፍል የሚዘወተር
 ምንም ያህል እንክብካቤ ሳይደረግላቸው ምግባቸውን በመፈለግ የሚረቡበት ነው
 ዶሮዎች ማታ ተንጠልጥለው የሚያድሩበት ትንሽ ቆጥ እንደሁኔታው በቤት ውስጥ
ወይም ውጪ ይዘጋጃል
II. በከፊል የቤት ውስጥ ዕርባታ
 ከላይ ከተጠቀሰው የሚለየው የዶሮዎቹ እንቅስቃሴ በአነስተኛ ቦታ የተወሰነ መሆኑ ነው
 ለዶሮዎቹ ዕንቁላል መውለጃና ማደሪያ የሚሆን ቤት አለው
 በአንድ ወይም በሁለት በኩል ተከፍቶ ዶሮዎች ቀን ቀን ከቤቱ ወጥተው በታጠረው ቦታ
መንቀሳቀስ የሚችሉበትን ሁሜታ ያመቻቸ ነው

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 84


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል 51 በከፊል የቤት ውስጥ ዕርባታ ቤት

III. ተንቀሳቃሽ ቤቶች


 ዶሮዎችን ዙሪያውን ከላይ ጭምር በወንፊት ሽቦ በተዘጋ ከለላ ውስጥ ይቆያሉ
 ዶሮዎቹ አዲስ ጭረው የሚመገቡት ነገር እንዲያገኙ በየቀኑ ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳል
 አነስተኛ የዶሮዎች ቁጥር ለማርባት ለሚፈልጉ አርቢዎች አመጪ ነው

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 85


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

ምስል 52 ተንቀሳቃሽ የዶሮ ቤት

IV. ሙሉ በሙሉ በቤት ውስጥ የሚረቡ ደሮዎች

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 86


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 እነዚህ ዶሮዎች በዚህ ዓይነት የቤት ዓይነቶች ውስጥ መላውን የምርት ሕይወታቸውን
ያሳልፋሉ ፣ በዚህ አጠቃላይ አሰራር ስር የተለያዩ የቴክኖሎጂ ደረጃ ሶስት ዓይነት ቤቶች
ሊታሰቡ ይችላሉ፡፡
1. የመሬት ላይ ዕርባታ
 በዚህ ዓይነት ዘዴ ዶሮዎች ሠፋፊ ጉዝጓዝ በተነጠፈበት ቤት ውስጥ መሬት ላይ
ዕንዲረቡ ይደረጋል

ምስል 53 የመሬት ላይ ዕርባታ ቤት

2. ተደራራቢ (Cage) ጎጆዎች


 ይህ ዓይነት የዶሮ መጠለያ ቀደም ሲል ከተጠቀሱት ዓይነቶች ዘመናዊ ነው
 ዶሮዎቹ ተደራራቢ በሆኑና እርስ በርሳቸው በተያያዙ ትንንሽ ጎጆዎች ይረባሉ
 ከነዚህ ጎጆዎች ጋር የተያያዘ የውሃና የመኖ ማቅረቢያ እንዲሁም ዶሮዎቹ እዚያው
ጎጆው ውስጥ ዕንቁላል ከጣሉ በኃላ ዕንቁላል ከጣሉ በኃላ ዕንቁላሉ ከጎጆው ተንሸራቶ
በመውጣት ዶሮዎቹ በማይደርሱበት መልክ የሚከማችበት ስፍራ አለ

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 87


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

 የዶሮዎቹ ኩስ መቀበያም ከያንዳንዱ ደረጃ ስር ይኖረዋል

ምስል 54 የተለያዩ የዶሮዎች ተደራራቢ ጎጆዎች (Cage)

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 88


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

10. የመረጃ አያያዝ


10.1. የመረጃ አያያዝ አስፈላጊነት

 የዶሮዎችን ምርታማነት ለመከታተል


 የዶሮዎችን ጤንነትና ሁኔታ ለመከታተል
 ለዕርባታው የሚደረጉ ወጪዎችንና ገቢዎችን ለመከታተል
 እርባታውን ለማሳደግ አስፈላጊውን መረጃ በቀላሉ ያስገኛል
10.2 የመረጃዎች አይነትና ይዘት
 መያዝ የለባቸዉ የመረጃ አይነቶች

o የምርት (የዕድገት) መጠን

o የመኖ መጠን

o የጤና (የክትባት)

o የወጪና ገቢ የመሳሰሉትን ይይዛል

 መረጃዎች መቼ ይሰበሰባሉ

o በየቀኑ መመዝገብ

o በየሳምንቱ ማጠቃለል

o በየወሩ ማደራጀትና

o በየአመቱ ተጠቃለዉ መቀመጥ አለባቸዉ

10.3 የመረጃ መያዣ ናሙናዎች


 የህክምና መረጃ መያዣ
 የሥጋ ዶሮዎች ዕለታዊ መረጃ መያዣ
 የዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች እለታዊ መረጃ መያዣ
 የመኖ ፍጆታ መረጃ መያዣ

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 89


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር
የስልጠና ፓኬጅ

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 90


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር የስልጠና ፓኬጅ

10.4 የመረጃ መያዣ ቅፆች


 የህክምና መረጃ መያዣ ቅፅ
የቤት ቁጥር _______________________ ዝርያ ________________________________ የተፈለፈሉበት ቀን ________________________ የእርባታው ስም
____________________________

ሕክምና የዶሮዎች የመድሃኒት የመድሃኒት የመድሃኒቱ የመድሃኒቱ የበሽታው የህክምናው


አስተያየት
ከ እስከ ዕድሜ ዓይነት መጠን አምራች አሰጣጥ ዘዴ ስም ውጤት

 የሥጋ ዶሮዎች ዕለታዊ መረጃ መያዣ ቅፅ

የቤት ቁጥር ____________ ዝርያ ____________ የተፈለፈሉበት ቀን _____________ የእርባታው ስም ______________________________

የዶሮዎች የሞቱ(በቁጥር አማካይ የመኖ


ቀን ዕድሜ(በቀን) ክብደት
የተሸጠ የታረደ(በቁጥር) አስተያየት
ቁጥር ) ፍጆታ(በኪግ)

 የዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች እለታዊ መረጃ መያዣ ቅፅ

የቤት ቁጥር ____________ ዝርያ ____________ የተፈለፈሉበት ቀን _____________ የእርባታው ስም ______________________________

ወር ______________ መጣል የጀመሩበት ቀን ________________________

ቀን የተሰበሩ
የዕንቁላል
የዕንቁላል ለቀማ ቁጥር የቀኑ ድምር ዕንቁላሎች አማካይ ክብደት
የዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ቁጥር አስተያየት
ቁጥር
1 2 3 4

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 91


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር የስልጠና ፓኬጅ

ወደ ሌላ
የሞቱ የተዘዋወ ያሉ

 የመኖ ፍጆታ መረጃ መያዣ ቅፅ

የቤት ቁጥር ____________ ዝርያ ____________ የተፈለፈሉበት ቀን _____________ የእርባታው ስም ______________________________

ቀን የዶሮዎች ብዛት የተሰጠ መኖ(በኪግ) የተረፈ መኖ(በኪግ) የመኖ ፍጆታ(በኪግ) አስተያየት

 የክትባት መረጃ መያዣ ቅፅ

የቤት ቁጥር ____________ ዝርያ ____________ የተፈለፈሉበት ቀን _____________ የእርባታው ስም ______________________________

የክትባት የክትባት የበሽታው የክትባቱ የክትባቱ ቁጥር


የክትባት ቀን የከታቢ ስም ስም
የክትባት ዘዴ
አምራች
አስተያየት
ዕድሜ ዓይነት (Serial №)

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 92


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር የስልጠና ፓኬጅ

11. አኔክስ
11.1. ጠቃሚ መረጃዎች
 የተመጣጠነ የዶሮ መኖ ዝግጅት
ለጫጩት ለታዳጊ(ቄብ ዶሮ) ለዕንቁላል ጣይ ዶሮ
የጥሬ ዕይነት ዓይነት መጠን የጥሬ ዕይነት ዓይነት መጠን የጥሬ ዕይነት ዓይነት መጠን
ገብስ 15 ኪግ ገብስ 35 ኪግ ገብስ 16 ኪግ
በቆሎ 40 ኪግ በቆሎ 25 ኪግ በቆሎ 45 ኪግ
ፉርሽኬሎ 15 ኪግ ፉርሽኬሎ 10 ኪግ ፉርሽኬሎ 10 ኪግ
የሎውዝ ፋጉሎ 10 ኪግ የሎውዝ ፋጉሎ 10 ኪግ የሎውዝ ፋጉሎ 10 ኪግ
ስጋና አጥንት 10 ኪግ ስጋና አጥንት 10 ኪግ ስጋና አጥንት 4 ኪግ
ከአሳ አካል የተቀመመ 3 ኪግ ከአሳ አካል የተቀመመ 3 ኪግ ከአሳ አካል የተቀመመ 3 ኪግ
አልፋአልፋ 5 ኪግ አልፋአልፋ 5 ኪግ አልፋአልፋ 4 ኪግ
ኖራ 1 ኪግ ኖራ 1 ኪግ ኖራ 3.5 ኪግ
ጨው 0.5 ኪግ ጨው 0.5 ኪግ ጨው 0.5 ኪግ
ቫይታሚን 0.5 ኪግ ቫይታሚን 0.5 ኪግ ቫይታሚን 4 ኪግ
100  100 100

 የዶሮ ልብ ምት
ምት/በደቂቃ
ዶሮ
350–470

 የዶሮ አተነፋፈስ
ዶሮ ፆታ
ወንድ (መተንፈስ/በደቂቃ) ሴት (መተንፈስ/በደቂቃ)

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 93


ኢትዮ - ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር የስልጠና ፓኬጅ

12–21 20–37

አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ እንሰሳት ሐኪም (ቢቪኤስሲ) ገጽ - 94

You might also like