You are on page 1of 2

ለዶሮ እርባታ ስራ የተዘጋጀን ገንዘብ

ለዶሮ ግዥ ለመኖ ግዠ ለመሳሰሉት እንዴት ይደለደላል ?


ሁሉም ሰው ወደ አንድ ስራ ሲገባ ወይም ሊጀምር ሲል ስራውን ለመጀመር ለመስራት የሚያዘጋጀው መነሻ ካፒታል ይኖረዋል፡፡ ወደ
ዶሮ እርባታ ስራም ሲገባ እንደዚሁ
ይህ ጥያቄ የብዙዎች ስለሆነ የአንድ ወንድማችንን ጥያቄ መሰረት አድርገን የበጀት ድልድሉን አብረን እንሰራው እሰቲ
ያለኝ የገንዘብ መጠን መቶ ሺ ብር ነው
ቦታዉ አለኝ እና ምን ያክል የእንቁላል ዶሮዎችን
ገዝቼ እንደምጀምር ብትነግረኝና ብታብራራልኝ
ደስ ይለኛል እንደውለታም ቆጥረዋለው
1) 100 ሺ ብር አለኝ ምን ያህል የእንቁላል ዶሮ ገዝቼ ለእንቁላል ምርት ላደርሳቸው እችላለው ነው
2) የተዘጋጀ ቦታ አለኝ ብሏል
100 ሺ ብሩ ሲደለደል መጀመሪያ ለሕክምና ለመሳሰሉት ወጪዎች 10% ለተቀማጭ ይያዛል
የ 100 ሺ ብር 10% 10 ሺብር ነው
10 ሺ ብር መጠባበቂያ ሲቀመጥ 90 000 ሺ ብር ይቀራል ይህ ብር ለዶሮ ግዢ እና ለመኖ ሲደለደል
Gh yone
ምን ያህል 45 ቀን የሞላቸው የዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ገዝቶ ማርባት ይችላል ?
መልሱ የሚሆነው 150 ይሆናል እንዴት ብሎ ለሚጠይቅ ሰው 150 እንቁላል ጣይ ዶሮችን
ከ 45 ቀናቸው ጀምሮ ለእንቁላል እስኪደርሱ ድረስ በአንድ ዶሮ 13,50 ኪሎ ግራም መኖ ይፈልጋሉ ወደ ገንዘብ ሲቀየር 500 ብር ይሆናል
የ 150 ዶሮች ሲባዛ 500 ይሆናል
75000 ብር ለመኖ ወጪ ይሆናል ማለት ነው
45 ቀን የሆናቸው 150 እንቁላል ጣይ ዶሮች
ዋጋቸው አንዱ በኛ አከባቢ ዋጋ 150 ብር ሒሳብ 150 ሲባዛ በ 150 ይሆናል 22500
75000+22500 = 97 500 ይመጣል
7000 ብር ጭራሽ ከመጠባበቂያ ብር ከመጠባበቂያ ወደዚህ ሒሳብ ይሸጋሸጋል
ከ 45 ቀን ጀምሮ እንቁላል መጣል እስኪጀምሩ ድረስ
ማለትም እስከ 22 ተኛ ሳምንት በአንድ ዶሮ 13.50 ኪሎ ግራም ይፈጃል
በ 150 ዶሮ 20.25 ኩንታል ይፈጃል
ለዶሮ እርባታ የተዘጋጀ ገንዘብ 70% ለመኖ የሚቀመጥ ሲሆን ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዎች ይህንን ከግንዛቤ አያስገቡትም
ወደ አንድ አዲስ ስራ ሲገባ መጀመሪያ እነዚህን የሠሳሰሉ ስሌቶችን ማስላት ይኖርብናል
ማሳሰቢያ
የዶሮ እና የመኖ ዋጋ ከቦታ ቦታ ይለያያል እዚህ ፅሁፍ ላይ የተጠቀሱ ዋጋዎች እኔ የምኖርበት አከባቢን ብቻ ነው የሚገልፀው

ጥሩ እይታ ነው። ነገር ግን:-


1. የንግድ ፈቃድ እና ህጋዊነት መመስረቻ ወጭ... 5,000
2. የሙቀት መጠን ማስተካከያ፣ የክትባት፣ የንፅህና እና የተጨማሪ መኖ (የቀጣይ 22 ሳምንት) ወጪዎች.... 10,000 ብር
3. የትራንስፖርት ወጭ... 2,000 ብር
4. የሰው ሃይል ወጭ (ጠያቂ የራሱ ጉልበት ቢጠቀም እንኳ በዜሮ ማሰብ ባዶ ሃሳባዊነት ነው) ... 1,000 * 4 ወር = 4,000 ብር
አጠቃላይ!!
፨ ለመጠባበቂያ የተቀመጠው 10,000 + 21,000 = 31,000 ብር።
፨ ቀሪ ብር 69,000 ይሆናል። ይህ ለመኖ እና ዶሮ መግዣ ሲካፈል:-
* 70% ለመኖ = 48,300 ብር
* 30% ዶሮ መግዣ = 20,700 ብር
ይህ ማለት የ 45 ቀን ዶሮ በ 150 ብር ብታገኝ....
20,700 ÷ 150 = 138 ዶሮ ይሆናል።
ሲጠቃለል!!
ከ 138 ዶሮ በላይ መነሻው መሆን አይችልም።

መልካም ቀን

You might also like