You are on page 1of 2

ILRI

International Livestock Research Institute Better lives through livestock


www.ilri.org

የአልፋልፋ (Alfalfa) ተክልን ለከብት መኖነት


በአነስተኛ እርሻ ላይ ማልማት
ዓላማ
በሞቃታማ ከፍተኛና መለስተኛ ቦታዎች ገበሬዎች
ለሚያቀርቧቸው ከብቶች ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው
መኖ ለማቅረብ ነው፡፡
የተክሉ ሁኔታ መግለጫ
• ወደ መሬት የጠለቁ ስሮች ያሉት ከአንድ
አመት በላይ የሚቆይ ቋሚ ተክል ነው፣
• በተለያዩ የአየር ሁኔታዎች ውስጥ ይበቅላል፣
• ከብቶች በደንብ የሚበሉትና ከፍተኛ የፕሮቲን
ይዘት ያለው ነው፣
• እርጥቡን ቆርጦ ለማብላት የሚመች ነው፣
• ተክሉ በከፍተኛ ሁኔታ ለድርቆሽ እንዲሁም
ለግጦሽ ያገለግላል።
ዘር አዘራር
ደካማ ጎኖች
• መስኖ ባለበት ቦታ ዘር በመበተን ወይም
• በጣም በከብቶች መጋጥን አይቋቋምም፣ በጉድጓድ በመስመር በሄክታር ከ12—20 ኪ.ግ.
• ደረቅ የሆነ አካባቢ አይስማማውም ስለሆነም መዝራት በዝናብ ከሆነ ደግሞ ከ10—12
አመቱን ሙሉ ለማምረት ውሃ ወይም መስኖ ኪ.ግ. ዘር በመስመር ከ55—72 ሳ.ሜ. አራርቆ
ያስፈልጋል፣ መዝራት።
• አሲድነት ያለውና ውሃ የሚያቁር አፈር የማዳበሪያ አጠቃቀም
አይስማማውም፣
• በሄክታር 100 ኪ.ግ. ዳፕ ወይም ከ10—15
• በብዙ ተባዮችና በሽታዎች በቀላሉ ይጠቃል፣
ቶን ፍግ በሄክታር መጠቀም ይቻላል።
• ከብቶች ብቻውን ሲግጡት በሰውነታቸው ላይ
አረም ማረም
የሆድ መንፋትን ያስከትላል።
• በመጀመሪያዎቹ የዕድገት ጊዜያት ማረም
አሰራር ያስፈልጋል፡፡ ከዚያም ተክሉ ካደገ በኋላ
የማሳ ዝግጅት በተከታታይ መኮትኮት።
አጨዳ
• በደንብ የተዘጋጀና የታረሰ ማሣ ያስፈልጋል።
• ተክሉ በሚያብበት ጊዜ 5 ሳ.ሜ. ከፍታ ላይ
በመቁረጥ መከመር።

headquarters principal site Asia office


PO Box 30709, Nairobi 00100, Kenya PO Box: 5689, Addis Ababa, Ethiopia New Delhi 110 012, India
Phone: 254 20 422 3000 Phone: +251 11 617 2000 P +91-11 2560 9800
Fax: +254 20 422 3001 Fax: +251 11 617 2001 P +91-11 2560 9815 (direct)
e-mail: ilri-kenya@cgiar.org e-mail: ilri-ethiopia@cgiar.org F +91-11 2584 7884
ውጤት አጠቃቀም
• በደንብ ከተያዘ ማሣ ከ6—8 ጊዜ በማጨድ
በሄክታር እስከ 20 ቶን ደረቅ መኖ ሊገኝ • ተክሉ እያደገ ሲሄድ የአልሚ ምግብ ይዘቱ
ይችላል። ከዚህ ተክል የሚገኘው መኖ እያሽቆለቆለ ስለሚሄድ በመኖነት የሚሰጠው
የፕሮቲን ይዘት ከ20—25% ይደርሳል። ጥቅም የሚወሰነው እንደ ተክሉ የእድገት
መኖው እስከ 70% ሊልም ይችላል። ደረጃ ነው። አልፋልፋን አጭዶ ወስዶ
ዘር ማባዛት ማብላት የተለመደ ዘዴ ነው። ጥሩ ድርቆሽም
ይወጣዋል። አልፋልፋን ርጥቡንና ብቻውን
• ትክክለኛው የዘር መሰብሰቢያ ወቅት መጠበቅ ከመመገብ መቆጠብ ያስፈልጋል። ምክንያቱም
ይኖርበታል። ይህም ሶስት አራተኛው የዘር የሆድ መንፋት ያስከትላል። ስለዚህ ከሌሎች
ማቀፊያ ጥቁር ቡናማ መልክ ሲያመጣ መኖዎች ጋር መቀላቀል ወይም ጠውለግ
መሰብሰብ ጥሩ ነው። በመስኖ ከለማ በሄክታር እስከሚል ማቆየት ይገባል።
ከ100 እስከ 300 ኪ.ግ. ዘር ማግኘት
ይቻላል።

Information leaflet on livestock feeds and feeding For further information, contact:
technologies for small-scale farmers developed through Fodder Adoption Project
collaboration between ILRI and its partners fodderadoption.wordpress.com
Forage Diversity Project
June 2010 International Livestock Research Institute,
PO Box 5689, Addis Ababa, Ethiopia
Email: a.duncan@cgiar.org or j.hanson@cgiar.org

You might also like