You are on page 1of 76

ማውጫ

1. መግቢያ
2. የወተት ከብቶች አመራረጥ
3. የጥጃ አያያዝ
4. የጊደር አያያዝ
5. የማዳቀል አገልግሎት
6. የወተት ላሞች አያያዝ
7. የንፁህ ወተት አመራረት
8. የወተት ከብቶች መጠለያ ዝግጅት
9. የወተት ከብት ርባታ መዝገብ /ሪከርድ/ አያያዝ
1. መግቢያ

ሀ. የአዲስ አበባ ከተማ መሠረታዊ መረጃ


የአዲስ አባበ ከተማ ስፋት ---- 54,000 ሄክታር
ከባህር ወለል በላይ ከፍታ --- 2300-3000 ሜትር
ዓመታዊ የዝናብ መጠን ----164.6 ሚ.ሊትር
የሙቀት መጠን፡-
ከፍተኛ ----25.5oc
ዝቅተኛ ---- 9.7oc
ለ. የአዲስ አበባ የእንስሳት ሀብት ብዛት
የዳልጋ ከብት ------- 97,215
በግ ------------------- 29,682
ፍየል ----------------- 18,861
ፈረስ ------------------ 2,135
አህያ ------------------- 19,623
በቅሎ ------------------ 809
ዶሮ --------------------- 100,163
የንብ መንጋ ------------ 4,231

ምንጭ፡- ማዕከላዊ ስታስቲክስ ባለስልጣን /2002 እ. ኤ. አ/


ሐ. የወተት ምርት
 በዓመት 47,000 ቶን ፈሳሽ የወተት ምርት ለፍጆታ ይውላል ተብሎ ይገመታል፣
 ከአዲስ አበባ ውጭ ተመርቶ ወደ ከተማዋ የሚገባ ፈሳሽ የወተት ምርት 20,000 -
25,000 ቶን ሲሆን፣ ጠቅላላ ለከተማዋ ለፍጆታ የሚቀርብ የፈሳሽ ወተት መጠን
ከ67,000-72,000 ቶን እንደሚገመት ነው
 ከዚህ መረጃ አሁንም በከተማው ውስጥ ያሉ ርባታዎች ለወተት ምርት አቅርቦት
ከፍተኛ ቦታ እንዳላቸው እናያለን፣
 ይሁን እንጂ በከተማው ያሉት አብዛኛዎቹ ከፍተኛ የውጭ ደም መጠን ያላቸው
ከብቶች ቢሆኑም ያለው አያያዝ፣ አመጋገብና ጤና አጠባበቅ ዘመናዊ ነው የምንለው
አይደለም፣
 የአንዲት ላም ምርት የመስጠት ባህርይ የሚወሰነው በሁለት ነገር ነው፡-
o በዘር ……35%
o በአያያዝ…..65%
• ስለዚህ በከተማችን የወተት ከብት ርባታ ላይ ያለው ትልቁ ችግር
የአያያዝ ድክመት ነው፣
• የሚታየውን የአያያዝ ችግር በምንሰጠው የኤክስቴንሽን አገልግሎት
እንዲሻሻል የማድረግ ኃላፊነት አለብን፣
• በመሆኑም ወደ ሥራው የገቡትንና ለመግባት የሚፈልጉትን
ተጠቃሚዎች ውጤታማ ለማድረግ የምክር አገልግሎትና የቴክኒክ
ድጋፍ የመስጠት የሙያ ግዴታ አለብን፣
• ብዙዎቹ ተጠቃሚዎች ሥራውን ከመጀመራቸው በፊት ለምክር
አገልግሎት ወደ ባለሙያ የመምጣት ባህል ገና የዳበረ ባለመሆኑ
አፈጻጸም ላይ ችግር እንዳለ እንረዳለን፣
• ሆኖም ከሪፖርትና ወደ ማዕከል ከሚመጡ አንዳንድ ተጠቃሚዎች
አንጻር የምክር አገልግሎት የመፈለግ ጅምር ፍላጎቶች አሉ፣
መ. በቢሮ ደረጃ የሚሰጡ የምክር አገልግሎቶች
ይዘት
አዲስ ወደ ሥራው ለሚገቡ፣
• የወተት ከብት ርባታ ሥራ ጥረት፣ ጥንካሬ፣ ቁርጠኝነት፣ የቅርብ ክትትል
እና የእንስሳት ፍቅርን የሚጠይቅ መሆኑን በቅድሚያ መገንዘብ
እንደሚያስፈልግ ሊረዱት ይገባል፣
• ልማቱ ገበያ ተኮር መሆን አለበት፣
• አዋጭነቱን ማየት ያስፈልጋል፣
• ለርባታ የሚሆኑ የወተት ላሞች/ጊደሮች ስለመገኘታቸው እርግጠኛ
መሆን ያስፈልጋል፣
• የወተት ከብት ርባታ ከሌሎች ርባታዎች የበለጠ ኃብት የሚጠይቅ
ከመሆኑም በላይ ምርት ለማግኘት የሚወስደው ጊዜ ረዥም መሆኑን
ሊያውቁት ይገባል፣
• የወተት ከብት ርባታ እውቀት ያስፈልጋል፣
o ከመጽሐፍት፣
o ከመረጃ መረብ፣
o የስልጠና ማንዎሎችን በሶፍት ኮፒ ከከተማ ግብርና ቢሮዎች ማግኘት እንደሚቻል፣
o ባለሙያን በመጠየቅና በማማከር፣
o ተሞክሮዎችን ወደ ተግባር ከገቡ ሰዎች ጠይቆ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን መግለጽ ያስፈልጋል፣
• ርባታውን ካረገዙ ጊደሮች ወይንም አንድ ጥጃ ከወለዱ እርጉዝ ላሞች መጀመር
ይመከራል፣
• ከዚህ ውጭ ተጠቃሚዎች በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ቴክኒካል ሃሳቦችን
መለዋወጥ የሚቻል ሲሆን፣ ወደ ሥራው ለመግባት ስለሚያስፈልጉት ቅድመ-
ዝግጅቶች የባለሙያ ተሳትፎ ወሳኝነት እንዳለው ሊያውቁት እንደሚገባ ማሳወቅ
ያስፈልጋል፣
• በመስክ ደረጃ ከምናየው፣ ጠይቀን ከምናገኘው መረጃና ተጠቃሚዎች ከሚያነሱት
ችግሮች ተነስተን የምክር አገልግሎትና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት ይቻላል፡፡
2. የወተት ከብቶች አመራረጥ
የአመራረጥ ዘዴዎች

ሀ. የከብትን የውጭ አቋም ተመልክቶ መምረጥ


ለ. የከብትን የሕይወት ታሪክ በማጥናት መምረጥ
ሐ. ከብቶችን በሚሰጡት ውጤት መምረጥ
መ. በጠባያቸው መምረጥ
ሠ. ጤናማ ከብቶችን መምረጥ
ረ. አቅምን ያገናዘበ የውጭ ደም መጠን አይቶ መምረጥ
ሀ. በውጭ አkም ተመልክቶ መምረጥ
 በዚህ ዓይነት ምርጫ ቀለም፣ ሻኛ፣ ቀንድ መኖርና አለመኖር፣የትከሻ
ስፋት፣ ቁመት የመሳሰሉት የአካል ክፍሎች ትኩረት ይሰጣቸዋል፣
 የወተት ላሞች ቅርጽ ጎንና ሆዳቸው ሰፋ ያለና ቅልጥማቸው ረዘም ያለ
ነው፣
 ግትና ጡታቸው የተስተካካለ ነው፣
 በአንፃሩም የሥጋ ከብቶች ድልብና አጫጭር እግሮች አላቸው፣
 የከብትን የውጭ አkም ተመልክቶ መምረጥ በአጠቃላይ የሚመረጠውን
ከብት ከፊትም ከኃላም ከጎንም አተኩሮ በመመልከትና በመጥናት ላይ
ያተኮረ ነው፣
 ይሁንና የዚህ ዓይነት አመራረጥ ከግለሰብ ግለሰብ ስለሚለያይ ብዙ
አስተማማኝ ሊሆን አይችልም፡፡
DAIRY FORM - DF

1-5 pts 25 pts 45-50 pts


Extremely tight Intermediate Extremely open
ለ. የከብትን የሕይወት ታሪክ በማጥናት መምረጥ
 የዚህ ዓይነት አሰራር የሚያተኩረው የሚመረጠው ከብት ከቅድመ
አያቶቹ ወይም ከወላጆቹ የወረሰውን ጠባይ ችሎታ አጥብቆ
በመከታተልና በማጥናት ላይ ነው፣
 የሚወረሱት ጠባዮች ሊለኩና በግልጽ ሊታወቁ የሚችሉ ስለሆነ በዚህ
መንገድ የመከናወነው መረጣ አስተማማኝና የተረጋገጠ ነው፣
 የወተት ከብቶችን ታሪክ በማጥናት ሊወሰዱ የሚችሉ መመዘኛ
ጠባዮች፡-
o የወተት ምርት መጠን፣
o የወተት ቅባት መጠን፣
o በወቅቱ ጥጃዎችን ማስገኘት፣
o በሽታን የመከላከል ኃይል፣
o የአካባቢን ጠባይ በመቀበል ለመኖር መቻል የመሳሰሉት ናቸው፡፡
 ይህ ዘዴ ከመንግስት ተkማት ካልሆነ ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ
አብዛኛዎቹ ግለ-ሰብ አርቢዎች መረጃ /ሪከርድ/ ስለማይዙ ሊጠቅመን
አይችልም፡፡
ሐ. ከብቶችን በሚሰጡት ውጤት መምረጥ
 ከብቶችን በሚሰጡት ውጤት መምረጥ መዛግብትን በመመርመር
የሚከናወን የአመራረጥ ዘዴ ነው፣
 ከብቶች በሚሰጡት ውጤት ሲመረጡ ብዙ ሊትር የመስጠት ችሎታ፣
በየቀኑ የሚሰጡት ወተት ብዙና እየጨመረ የሚሄድ ጠባይ መታየት
ይኖርበታል፣
 ይህም በተራ ቁጥር ለ እንደተገለፀው ከግለሰብ እርባታዎች ከሆነ
ከርባታዎቹ አስፈላጊውን መረጃ ካልተገኘ ብዙም የሚያስኬድ
አይደለም፡፡
መ. በጠባያቸው መምረጥ
 የመራገጥና የመዋጋት ጠባይ ያላቸው ከብቶች በተለይ በአለባ ጊዜ ስለሚያስቸግሩ
እንደነዚህ ዓይነት የማይፈለጉ ጠባዮች ያላቸውን ከብቶች መምረጥ የለብንም፡፡
ሠ. ጤናማ ከብቶችን መምረጥ
 የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአዲስ አበባና በዙሪያው ያሉ ነባር የወተት
ከብት ርባታዎች የጡት፣ የማህፀንና የሳንባ ነቀርሳ በሽታዎች ተስፋፍተውባቸው
ይገኛሉ፤
 በቅርቡ ላንድ ኦ ሌክስ ባደረገው ጥናት መሠረት በአዲስ አበባና በአካባቢው የጡት
በሽታ 94% ደርሷል፣
 በመሆኑም ተጠቃሚዎች የወተት ከብቶችን ከመግዛታቸው በፊት የእንስሳት ሐኪም
ማማከርና ከብቶቹ ከተጠቀሱት በሽታዎች ነጻ ስለመሆናቸው በእንስሳት ጤና
ላብራቶሪ መረጋገጥ አለበት፡፡
 ከብቶቹን ለመግዛት በሌሎች ምርጫዎች ስምምነት ከተደረሰ በኋላ እንኳን
በላብራቶሪ ለማስመርመር ናሙና ከከብቶቻቸው ለመስጠት ሻጮች ፈቃደኛ ካልሆኑ
ውሉ መሰረዝ አለበት፣
ረ. አቅምን ያገናዘበ የውጭ ደም መጠን አይቶ መምረጥ
 ከብቶቹ ሊኖራቸው የሚገባ የውጭ ደም መጠን
ተጠቃሚዎች ካላቸው የአያያዝ፣ የአመጋገብና የጤና
አጠባበቅ አቅም ጋር መሄድ አለበት፣

 የውጭ ደም መጠናቸው በጨመረ ቁጥር የሚፈለገውን


ምርት ለማግኘት በዚያው መጠን የአያያዝ ደረጃቸው
እንደሚጨምር ታውቆ አቅምን ያገናዘበ ግዥ መፈፀም
ያስፈልጋል፣
 በአጠቃላይ ከብቶችን ለመግዛት ስንመርጥ ትክክለኛ የወተት
ላም አቅዋም ያላቸው፣ ከተቻለ እርጉዝ ጊደሮች ወይንም
የመጀመሪያ ጥጃ የወለዱ ጤናማ እርጉዝ ላሞች ከሆነ
በአጭር ጊዜ ገቢ ማግኘት ይቻላል፡፡
3. የጥጃ አያያዝ

 ጥጆች እንደተወለዱ በሰውነታቸው ላይ ያለው


እርጥበት እንዲወገድ ላሞች እንዲልሷቸው ማድረግ
አስፈላጊ ነው፣
 የዛሬ ጥጃ የነገ ላም ስለሆነች ከእርግዝና ወቅት
ጀምሮ፣ በወሊድ ጊዜ፣ ከወሊድ በኃላና ጡት ከጣሉም
በኃላ አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግና እንደ
እድገት ደረጃቸው መመገብ ያስፈልጋል፣
 ጥጃዋ ከተወለደችበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አራት ቀን
በተከታታይ እንገር /የመጀመሪያ ወተት/ ማግኘት
አለባት፣
 እንገር በውስጡ በሽታን ሊከላከሉ የሚችሉ ሕዋሳት
ከመኖራቸውም በላይ ለጥጆች አስፈላጊ የሆኑ የምግብ
ዓይነቶች ማለትም እንደ ፕሮቲን፣ ቫይታሚንና ማዕድናት
በብዛት ይገኙበታል፣
 ጥጃዋ እንገር ወተት መመገብ እንድትችል ከተወለደችበት
እስከ አራት ቀን ድረስ ከላ ጋር እንድትቆይ ማድረግ
የሚፈለገውን ያህል እንድትጠባ ያደርጋል፣
 ጥጃዋ ልክ እንደተወለደች የምንለያት ከሆነ ግን ንፁህና
የተጎዘጎዘ ቦታ በማስቀመጥ እንገር ወተት አልበን መመገብ
መቻል አለብን፣
 ለዚህም ጥጃዋ ከባልዲ ወተት እንድትጠጣ ማለማመድ ያስፈልጋል፣
 ይኸውም ከብት ጠባቂው እንገር ወተት ከያዘው ባልዲ በስተጀርባ
ጥጃዋን በጉልበቱ መሃል ይዟት በመቆም ፊት ለፊት በባልዲ
ወደሚገኘው ወተት እርሷን በማጎንበስ አስቀድሞ በወተቱ ውስጥ
የነበሩትን ሁለት ጣቶቹን እንድትጠባ ያደርጋል፣
 በዚህ ዓይነት ለጥቂት ቀናት ካለማመዱ በኃላ በራሷ ኃይል ከባልዲው
መጠጣት ትጀምራለች ማለት ነው፣
 ለጥጆች በቀን ከ2-3 ጊዜ ወተት መስጠት ጠቃሚ ነው፣
አሰጣጡም፡-
o ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ---- በቀን 3 ሊትር
o ከሦስት እስከ ስምንት ሳምንት -- በቀን 4 ሊትር
o ከዘጠኝ እስከ አስር ሳምንት -- በቀን 3 ሊትር
o ከአስራ አንድ እስከ አስራ ሁለት ሳምንት- በቀን 2 ሊትር
o ከአስራ ሦስት እስከ አስራ ስድስት ሳምንት -- በቀን 1 ሊትር
 የጥጆችን የወተት ፍጆታ ለመቀነስ የሚያስችለው
አንዱ መንገድ ከፊሉን ወተት በመቀነስ በአሬራ
በመተካት ነው፣
 ጥጃን ከ 21 ኛው ቀን ዕድሜ ጀምሮ አንድ እጅ
ወተት አንድ እጅ አሬራ መመገብ ለጥጃ ማሳደጊያ
ሊውል የነበረውን ወተት በመቀነስ ለሌላ ጥቅም
ማዋል ይቻላል፣
 በዚህም የጥጆቹ ዕድገት ሙሉ በሙሉ በወተት ብቻ
ካደጉት ያልተናነሰ መሆኑ በምርምር ተረጋግጧል፡፡
የጥጆች ወተት አመጋገብ ---- ከአሬራ ጋረ

የጥጃ እድሜ በየቀኑ የሚሰጠው መጠን


(በቀን)
እንገር ወተት አሬራ
ከ 1-4 3.0 - -
ከ 5-15 - 3.0 -
ከ 16-20 - 4.0 -
ከ 21-42 - 2.0 2.0
ከ 43-63 - 1.5 1.5
ከ 64-70 - 1.0 1.0
 ከአንድ ሳምንት በኃላ ጥጆች ከሚሰጣቸው ወተት
በተጨማሪ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ድርቆሽ፣ እርጥብ
ሣርና እፍኝ ሙሉ ድብልቅ መኖ መስጠት ለተሻለ
ጤንነት፣ ለፈጣን ዕድገትና ለጨጒራ መዳበር ይረዳል፣
 ከአንድ ሳምንት በ|ላ ንፁህ ውሃ በንፁህ ዕቃ
እንዲጠጡ መስጠት አለብን፣
 ጥጆች ወተት መጠጣት የሚያkርጡት በአራት ወር
ዕድሜአቸው ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ክብደታቸው ቢያንስ
80 ኪሎ ግራም መሆን ይኖርበታል፣
4. የጊደር አያያዝ
 በአግባቡ ተይዛ የምታድግ ጊድር ለጥቂ እስከምትደርስ ድረስ
ከ0.5 - 1.5 ኪ ግ የተመጣጠነ መኖና ጥራቱን የጠበቀ የሣር
ድርቆሽ መመገብ ያስፈልጋል፣
 በጥሩ ሁኔታ የተያዘች ጊደር በአንድ ዓመት ተኩል ጥሩ
እድገትና ክብደት ስለሚኖራት በወቅቱ ማስጠቃት ይቻላል፣
 ዋናው ነገር ከብቶችን ለማስጠቃት የሰውነት ክብደት
ወሳኝነት እንዳለው ሊዘነጋ አይገባም፣
 እንስሳት ለጥቂ የሚደርሱበት የጉርምስና ወቅት ድርስ - ጥቂ
ይባላል፤ በዚህ ጊዜ እንስት እንስሳት የመራቢያ አካሎቻቸው
መጠናቸው ይጨምራል፣ ይደራሉ፣
 ለጥቂ መድረስ እንደ ዝርያው ይለያያል፣
 የውጭ ዝርያ ከብቶች ለጥቂ የሚደርሱበት
ጊዜያቸው እንደ ሀገር ውስጥ ዝርያ ባለመርዘሙ
ቀድመው ለምርት ይደርሳሉ፣
 የሀገር ዝርያ ከ32-38 ወር ለርቢ ሲደርሱ የውጪ
ዝርያ ከ18-24 ወር ይደርሳሉ፣
 በምርት አሰጣጥ በኩልም አንድ የሀገር ዝርያ በአንድ
የአለባ ወቅት 300 ሊትር ሲደርስ፣ የውጪዎቹ
በአማካይ 2500-3000 ሊትር እና ከዚያም በላይ
ይሰጣሉ፡፡
5. የማዳቀል አገልግሎት
 በሰው ሠራሽ ዘዴ ከብቶችን ማዳቀል ማለት ሰው ሠራሽ
በሆነ የሴቴ ብልት መሰል መሳሪያ ከኮርማው ላይ አባለ ዘርን
ሰብስቦ የተሰበሰበውን አባለዘር ሕያው እንዲሆነ በጊደር/በላም
የመራቢያ ብልት ውስጥ በዚሁ ሙያ በሠለጠኑ ቴክኒሽያኖች
መጨመርና ፅንስ እንዲፈጠር ማድረግ ነው፣
 በወተት ከብት ርባታ የተሰማሩ ከብት አርቢዎች በኮርማ
ማዳቀል ከሚያስከትሉት የተለያዩ ችግሮች በመነሳት
መጠቀም እንደሌለባቸውና ነገር ግና በድራት ላይ ያለችውን
ጊደር/ላም በሰው ሰራሽ ዘዴ መጠቀም እንደሚኖርባቸው
ነው፣
የሰው ሠራሽ ዘዴ እንስሳትን ማዳቀል ዋና ዋና ጠቀሜታዎች
 በተፈጥሮ ግንኙነት አንድ ኮርማ ሊያጠቃ ከሚችለው መቶዎች ከብቶች በብዙ ሺ የሚቆጠሩ እንስሳትን ለማስጠቃት ያስችላል፣
 በኮርማ ሲጠቁ ሊደርስባቸው ከሚችል የአካል ጉዳት ይጠበቃሉ፣
 በኮርማ ሲጠቁ ሊተላለፉ ከሚችሉ የአባለዘር በሽታዎች ይጠበቃሉ፣
 ኮርማን በመያዝ ከሚከተለው የቦታ ችግር እንዲሁም ከሚከሰቱ ተጨማሪ ወጪዎች የመኖ፣ የመድሃኒት እና ሌሎች የአያያዝ ችግሮች
ያድናል፣
 ምርጥ ሆነውን ዘር በቀላሉ በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ማሰራጨት ያስችላል፣
 አርቢዎች ኮርማ በመያዝ ከሚደርስባቸው ጉዳት ይጠበቃሉ፣

 ለኮርማ የሚውለውን ማንኛውንም የመኖም ሆነ የመድሃኒት ወጪ ምርታማ ለሆኑ ላሞቻቸውና ለሌሎች እንስሳት ያውሉታል፡፡
 በሰው ሰራሽ የከብቶች ማዳቀል ዘዴ የሀገር ዝርያ ከብቶችን ከውጭ ደም ካላቸው ከብቶች ጋር በማዳቀል የተሻለ ዘር ማግኘት ይቻላል፡፡
የደራች ላም/ጊደር የምታሳያቸው ምልክቶች፡-
 ድራት ማለት እንስት እንስሳ የኮርማ ፍላጎት እንዳላት ምልክት
የምታሳይበት ጊዜ ነው፡፡ እነዚህም ምልክቶች፡-
o ሌሎች ላሞችን ማሽተት፣
o ሌሎች ላሞች ላይ ለመውጣት መሞከርና መጮህ፣
o እረፍት ማጣት፣ የብልት መቅላት፣ ማበጥና እርጥበት ምልክት ማሳየት፤ ይህ
ምልክት ከ6-8 ሰዓት ሊቆይ ይችላል፡፡ ሰዓቱ በጨመረ ቁጥር ምልክቶቹ
ይቀያየራሉ፣
o ላ በመቆም ሌሎች ላሞች ወይም ኮርማ እንዲወጡባት ትፈልጋለች፣
o ውሃ የመሰለ ዝልግልግ ፈሳሽ ከብልቷ ይፈሳል፣ ትቅበጠበጣለች፣ ትጮሃለች፣
o የብልት ከንፈ[ ያብጣል፣ይቀላል፣
o ወገቧ በሚያዝበት ጊዜ ወገቧን የመለመጥ ባሕርይ ይታይባታል፣
o የመኖ ፍላጎቷ ይቀንሳል፣
o ወተት በመስጠት ላይ ካለች ወተቷ ይቀንሳል፡፡
 የኮርማ ፍላጎት ምልክቶችን በአግባቡ አለመከታተል ለከብቶቹ በቶሎ
አለማርገዝ ዋነኛ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ
ነው፡፡
 ለድራት የአመጋገብ ማነስና መብዛት ተፅዕኖ ያሳድራል፣
 ቀደም ሲል እንደተገለፀው ከብቶችን ለማስጠቃት የሰውነት ክብደት
ወሳኝነት አለው፡፡ ይኸውም የአንድ ሙሉ ላም 2/3 ክብደት በአማካይ
230-270 ኪሎ ግራም መድረስ ይኖርበታል፣
 የወተት ከብቶች በድራት የሚቆዩበት ጊዜ ከ18-19 ሰዓታት ይሆናል፣
 ለማስጠቃት የሚመረጠው ሰዓት ትክክለኛ የኮርማ ፍላጎት ካሳየችበት
በአማካኝ ከ6 እስከ 18 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በአጠቃላይ
ጠዋት ምልክት ካሳየች ከሰዓት በኃላ፤ ማታ ካሳየች ደግሞ በማግስቱ
ጠዋት ማዳቀል አስፈላጊ ነው፣
 አንድ ጊዜ ደርተው የሚቀጥለውን የድራት ምልክት ወይም ሁለተኛ ጊዜ
የሚደሩት በአማካይ በ21 ቀን ነው፡፡
 መረጃዎች እንደሚያስረዱት በርካታ የወተት ከብቶች ከቀን ይልቅ በማታ የድራት
ምልክት እንደሚያሳዩ ይጠቁማሉ፡፡ ስለዚህ በከብቶቹ አካባቢ የቅርብ ተከታታይ ሰው
ማድረግ በወቅቱ እንዲጠቁ ለማድረግ ያስችላል፣
 የድራት ጊዜያቸውን ካሳለፉ በ|ላ ማስጠቃት ወይም ማሳለፍ ለተጨማሪ የ21 ቀን
ወጪ ይዳርጋል፣
 ይህንን ሁኔታ ለማስተካከልና ለክትትል እንዲያመች የድሪያና ወሊድ መከታተያ
ሰንጠረዥ /ካላንደር/ መጠቀም ያስፈልጋል፣
 ለአንድ የወተት ከብት ርባታ ወቅቱን የጠበቀና አስተማማኝ የመዋለድ ሂደት መካሄድ
ለርባታው መስፋፋትና ለምርት ዕድገት መሠረት መጣያ ነው፡፡
 የድራት ምልክቶችን ጠንቅቆ ማወቅና በወቅቱ ማስጠቃት እስከ ቀጣይ የድራት ጊዜ
የሚወጣውን የመኖና ሌሎች ወጪዎችን መቀነስ ብቻ ሳይሆን በትክክለኛው የወሊድ
ርቀት የጥጃና የወተት ምርት ማግኘት ያስችላል፣
 ላ/ጊደ[ ከተጠቃች በ|ላ እርጉዝ መሆኗንና አለመሆኗን በሁለተኛዋ ወር ማረጋገጥ
በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ሆኖም ግን 8 ሳምንት ያልሞላውን ፅንስ ምርመራ ማድረግ
አደጋ ስላለው አይሞከርም፣
ላሞች የኮርማ ፍላጎት የሚያሳዩበት ጊዜ ስርጭት

ምልክት ሊያሣዩ የሚችሉበት ጊዜ ካሉት ላሞች የሚያሳዩ


በ%
ከጥዋት 12 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት 22%

ከቀኑ 6 ሰዓት እስከ ማታ 12 ሰዓት 10%

ከማታ 12 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት 25%

ከሌሊቱ 6 ሰዓት እስከ ጥዋቱ 12 ሰዓት 43%


6. የወተት ላሞች አያያዝ
ሀ. ለመውለድ ለደረሱ ላሞች የሚደረግ እንክብካቤ፣
 ክበድ ወይም ያረገዙ ላሞች ከፍተኛ እንክብካቤ ይፈልጋሉ፡፡
የመጀመሪያውና የመጨረሻው 1/3 የእርግዝና ወቅት ለሕይወታቸው
ወሳኝ ጊዜያቶች ናቸው፡፡
 በመጀመሪያው የእርግዝና ጊዜ በመረበሽ ምክንያት የመጨንገፍ፤
በመጨረሻ የእርግዝና ወቅት ደግሞ የጽንሱ የዕድገት ደረጃ በመፋጠኑና
የወተት ምርት ለመስጠት በመቃረባቸው ለዚህ ሥራ መሟላት
የሚያስፈልጉ እንክብካቤዎች ካልተደረጉ ጽንሱ የሞት አደጋ
ሊያጋጥመው ይችላል
 ከስምንተኛዋ የእርግዝና ወራት አንስቶ እስከምትወልድ ድረስ ከሚሰጣት
መኖ በተጨማሪ 2 ኪ.ግ የተመጣጠነ መኖ መስጠት የሚወለደውን ጥጃ
ጠንካራ ከማድረጉም በላይ ላሚቷን ወተታማ ያደርጋታል፣
 ላረገዙ ላሞች በተለይም በመጨረሻ የእርግዝና ጊዜያቸው ምቾት
ለመስጠት የሚከተሉት ጥንቃቄዎችና እንክብካቤዎች ሊደረጉላቸው
ይገባል፡-
o ድካም እንዳይሰማቸው ረዥም ወይም ባልተስተካከለ መንገድ እንዳይጓዙ
ማድረግ፣
o ሊጥላቸው ከሚችል የከብቶች በረት /ቤት/ ወለል መጠንቀቅ ያሻል፡፡ የወለሉ
ዓይነት የሚያዳልጥ ከሆነ ከመውድቅ የአጥንት መሰንጠቅ፣ የመውለቅና
የመሰባበር አደጋ ሊያጋጥማቸው ይችላል፣
o ልጆች ወይም ውሾች እንዳያሯሩጧቸው ማድረግ፣
o ከሌሎች እንስሳት ጋር እንዳይወጋጉ መከላከል፣
o ከሌሎች የመጨንገፍ ችግር ካጋጠማቸው ወይም እንደብሩሶሎሲስ የመሰለ የአባለ
ዘር ከሽታ ተሸካሚዎች ከሆኑ እንስሳትጋር ያለማደባለቅ፡፡
ለ. በወሊድ ጊዜ የሚደረግ እንክብከቤ
o አንዲት ላም የመውለጃ ጊዜዋ ሲቃረብ ግቷ እየሞላና እያደገ ይመጣል፡፡ ብልቷ
ያብጣል፡፡ ወፍራም ዕዥ የመሰለ ፈሳሽ መውጣት ይጀምራል፡፡ በብልቷ አናት
ግራና ቀኝ ያሉት ሁለት አጥንቶችም ሰፋ ማለት ይጀምራሉ፣
o በዚህን ጊዜ ላ/ጊደ[ በመውለጃ ቦታዋ ላይ ድርቆሽ ወይም ገለባ
መጎዝጎዝና የ|ለኛውን የሰውነት ክፍሏን እና አካባቢውን በፀረ-
ተህዋስያን ማጠብ ያስፈልጋል፣
o መውለድ የተፈጥሮ ሂደት በመሆኑ ላሚቷ በራሷ ኃይል
እንድትወልድ መተው አለብን፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የእንስሳት
ሐኪም እርዳታ ሊያስፈልግ ይችላል፣
o በትክክለኛው የአወላለድ ሂደት የመጀመሪያው ምልክት ከታየ
ከሦስት ሰዓት በ|ላ በመጀመሪያ የጥጃው የፊት እግር፣ ቀጥሎም
ጭንቅላቱና ሰውነቱ ይወጣል፤ የጥጃው አመጣጥ ትክክለኛ መስሎ
ካልታየን በአስቸኳይ የእንስሳት ሐኪምን እርዳታ መጠየቅ አለብን፡፡
ሐ. የእንግዴ ልጅ መዘግየት
 ጥጃው ከተወለደ በኃላ የእንግዴ ልጅ በተወሰነው ጊዜ
ላይወርድ ስለሚችል ላሚቷ የተለየ እንክብካቤ
ያስፈልጋታል፣
 በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለች ላም ጥጃው ከተወለደ ከጥቂት
ሰዓት በኃላ የእንግዴ ልጅ በአግባቡ ሊወርድ
እንደሚችል ይጠበቃል
 የእንግዴ ልጅ መዘግየት ካጋጠመ ምክንያቱ በተላላፊ
በሽታዎች ሊሆን ስለሚችል ላሚቷን ከሌሎች
ከብቶች በመለየት ንጽህናው በተጠበቀ፣ ሙቀት
ባለውና ምቹ በሆነ ቤት በማቆየት ክትትል ሊደረግላት
ይገባል፡፡
 በተለያዩ ምክንያቶች የእንግዴ ልጅ ከ /1/ አንድ ቀን
በኃላ ካልወረደ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ሐኪም
በመጥራት ዕርዳታ እንድታገኝ ማድረግ ያስፈልጋል፣
 ከወለደችና የእንግዴ ልጅ ከወረደ በኃላ ላሟን ማጠብ
አስፈላጊ ነው፣
 ከዚሁም ጋር ላሚቷን በአመጋገብ መንከባከብ ያስፈልጋል፣
 አመጋገብን በተመለከተ እንደ አጠቃላይ ሕግ አንድ የወተት ላም
ለእያንዳንዱ 100 ኪሎ ግራም የሰውነት ክብደት 3 ኪሎ ግራም ደረቅ
መኖ መብላት እንደምትችል ማስቀመጥ ይቻላል፣
 ጥሩ ወተት የምትሰጥ ላም አካሏ ከተጎዳና መጠባበቂያ የሆነው የመኖ
መጠን ከተነካ ወተቷም እየቀነሰ ይሄዳል፣ የኮርማ ፍላጎትም ላታሳይ
ትችላለች፣
 ስለዚህ ቀድሞ የምትሰጠውን ወተት ለመስጠት ቢያንስ ሁለት ወር
ደህና አድርጋ መመገብ ስለሚያስፈልጋትና ተጨማሪ ወጪ
ስለሚያስከትል ከመጀመሪያውኑ ጥራት ያለውን መኖ በአግባቡ
መመገብ ያስፈልጋል፣
 በተጨማሪ ላሚቷ ለምትሰጠው አንድ ሊትር ወተት ግማሽ ኪ.ግ
የተመጣጠነ መኖ ሂሳብ አስልቶ መመገብ ያስፈልጋል፣
 ውሃ ለላሞች በሰውነታቸው ውስጥ የሚካሄደውን ሂደት በአግባቡ
እንዲያከናውኑ የሚያስችል በመሆኑ የምትታለብ ላም በቀን ከ50-60
ሊትር ውሃ መውስድ ትችላለች፡፡
 ከወሊድ በ|ላ አንዲት ላም የዕረፍትና የማገገሚያ ጊዜዋ
ሁለት ወር ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የላ ማህፀን ወደ ቦታው
ይመለሳል፡፡ ከወለደች ከ2 ወር በ|ላ ስትደራ ማስጠቃት
ለመጪው ዓመት ሌላ ጥጃ ለማግኘት ያስችላል፣
 አንድ ጥጃ ተወልዶ ሌላ ጥጃ እስኪወለድ ድረስ ያለው ጊዜ
ከጥጃ - ጥጃ ያለ ጊዜ ወይም Calving Interval በመባል
ይታወቃል፡፡
 በአንድ የርባታ ጣቢያ የሚታይ ከጥጃ - ጥጃ ያለ ጊዜ መርዘም
በጣቢያው ላይ ኪሣራን ያስከትላል፡፡
 ስለዚህ በጥሩ የአያያዝ ደረጃ /Management/፣ አመጋገብና
ጤና አጠባበቅ ያለው የጊዜ ርዝመት አንድ ዓመት መሆን
አለበት፡፡
መ. ለክበድ የሚታለቡ ላሞች ዕረፍት መስጠት
 ክበድ የሚታለቡ ላሞችን በተከታታይ ለረዥም ጊዜ ከማለብ ለመውለድ ስድስት
ሳምንታት ወይም ሁለት ወራት ሲቀራቸው እረፍት እንዲያገኙ ቢደረግ የበለጠ
የወተት ምርት እንደሚሰጡ የጥናት ሙከራዎች ያረጋግጣሉ፣
 ዕረፍት የመስጠት ዋናው ጠቀሜታ ላሞች በወተት ምርት የመስጠት
ሂደት ላይ እንዳሉ ከሰውነታቸው የተጠቀሙት ማዕድናት በተለይም
ካልሲየምና ፎስፈረስ በመመለስ እንዲያገግሙ ለማድረግ ነው፣
 ላሞች ከወሊድ በፊት ዕረፍት ሳይሰጣቸው መታለብ ከጀመሩ
ምርታቸው ከመቀነሱም በላይ የወተቱ የምግብ ንጥረ-ነገር ካገገሙት
ይልቅ በጣም ዝቅተኛ ነው፣
ሠ. ላሞችን ከአለባ ማቆም
 ላሞችን ከአለባ ለማቆም ዋነኛው ዘዴ አንድ ቀን በመዝለል እንዲታለቡ
በማድረግ ነው፡፡
 ወተት እስኪቆም ድረስ በሁለት ቀን አንድ ቀን እንዲታለቡ ይደረጋል፤
በዚህም ዘዴ ሁለት ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ ይወስዳል፡፡
 ላሚቷ ከፍተኛ የወተት ምርት የምትሰጥ ከሆነ የምትመገበውን መኖ
መቀነሱ ይመረጣል፡፡ ይሰጣት የነበረውን የተመጣጠነ መኖ በመከልከል
በፕሮቲን ይዘቱ አነስተኛ የሆነ ራፌጅ /የቃጫ ይዘታቸው ከፍተኛ የሆነ
እንደ ድርቆሽ የመሳሰሉት/ ለጥቂት ቀናት ከተሰጣት የወተት ምርት ቀስ
በቀስ እየቀነሰ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ አለባው እንዲkረጥ
ማድረግ ነው፡፡
ረ. የወተት ላም አስተላለብ
 የወተት ላሞችን ትክክለኛ የአስተላለብ ዘዴ በመከተል ማለብና በአለባ
ወቅት ከፍተኛ እንክብካቤ ማድረግ ያስፈልጋል፣
ትክክለኛ ያስተላለብ ዘዴ
o ጡትን በሙሉ እጅ በመያዝ ነው፣
o ከዚያም ከላይኛው ግት ጀምሮ ወደ ታች እየጨመቁ በመውረድ ማለብ፣
o በመደጋገም በሙሉ እጅ እየያዙ ማለብ፣
o በአለባ ወቅት እጅን አለማርጠብ፤ እጅን እያረጠቡ ማለብ ጡቱን ለበሽታ
ማጋለጥ ይሆናል፣
o በሁለት ጣት በመሳብ ወይም በመዠርገግ የሚደረግ አለባ የጡቶቿን
ጫፍ ሊያቆስል ከመቻሉም በላይ በሚሰማት ስቃይ ወተቷን
ልትሰቅል ትችላለች፡፡
ሰ. በአለባ ጊዜ የሚደረግ እንክብካቤ
o ማለቢያ ቦታና ወቅት መለዋወጥ በምርት ውጤት ላይ ተጽዕኖ ስለሚኖረው
ዘወትር የሚታለቡበትን ስፍራና ወቅት መወሰን፣
o በአለባ ጊዜ አለመንጫጫት፣ በተቻለ መጠን አለመምታት፣ አለማዋከብ፣
o ላሞች ወተታቸውን እንዲለቁ የማለቢያ ስፍራ እንደደረሱ ወይንም ባሉበት
ቦታም ቢሆን መኖ መስጠትና ጡታቸውን ለብ ባለውሃና በንጹህ ጨርቅ አጥቦ
ግታቸውን ማሻሸት፡፡ ግትን ማሻሸት ላሟ ወተቷን እንድትለቅ ይረዳል፣
o በቀን 2 /ሁለት/ጊዜ ማለብ፣
o የማለቡ ተግባር ወተቱ እስኪያልቅ መሆን አለበት፡፡
7. የንፁህ ወተት አመራረት
• ወተት ከጡት አጥቢ እንስሳት የሚገኝ ምግብ ነው፣
• ወተት በምግባዊ ይዘቱ፤ ለአካል ግንባታና ለጥንካሬ የሚያስፈልጉ ንጥረ
ምግቦችን አሟልቶ የያዘ ነው፣
• በመሆኑም በዓለም ውስጥ ተፈጥሮ ሰራሽ ከሆኑ ምግቦች የላቀ
ፍጹማዊና የተመጣጠነ ምግብ ተብሎ ይጠራል፣
• በዚህም ለታዳጊ ሕፃናት፣ ለአዋቂና ለበሽተኛ ለእድገት፣ ለአእምሮ
ግንባታና ለጤና እንክብካቤ ከፍተኛ አስታዋጽኦ አለው፣
• ሕፃናትና ጥጆች ለተወሰነ ጊዜ ንፁህ ወተትን በመመገብ ወይንም
በመጠጣት መኖርና ማደግ ይችላሉ፣
• የላም ወተት 87% ውሃና 13% የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል፡፡
በወተት ውስጥ የሚገኙ ንጥረ-ነገሮች፡-

ቅባት --------------------------- 4%
ስኳር -------------------------- 5%
ፕሮቲን ------------------------ 3.3%
ማዕድንና ቫይታሚኖች ----- 0.7%
 የእነዚህ ንጥረ-ምግቦች መጠን እንደ ከብቶቹ ዝርያ፣
እንደሚመገቡት የመኖ ዓይነት፣ የወተት ምርት መጠን፣
የጤንነት ሁኔታ … ወዘተ የሚለያይ ነው፡፡
o ለምሳሌ የሀገራችን ከብቶች ወተት የቅባት /የስብ /መጠን ከውጭ
ሀገር ከብቶች ይበልጣል፡፡
የተለያዩ አጥቢ እንስሳት ወተት ምግባዊ ይዘት

የእንስሳው የፕሮቲን የላክቶስ የቅባት የማዕድን የደረቅ


ዓይነት መጠን % መጠን % መጠን % መጠን % ምግቦች
መጠን
ላም 3.3 5.0 4.0 0.7 13.0

ፍየል 3.7 4.2 4.1 0.8 12.8

በግ 5.5 4.8 7.4 1.0 19.3

ግመል 3.7 4.1 4.2 0.9 12.9


 ወተት እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም በቀላሉ የሚበላሽ
የምግብ ዓይነት ነው፡፡ የወተት አብዛኛው ክፍል ውሃ
በመሆኑ ይህ የእርጥበት መጠን ለጥቃቅን ሕዋሳት
መራባት በተጨማሪነት አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
 ጤናማና ጥራቱ አስተማማኝ የሆነ የጥሬ ወተት
ምርት ለማግኘት የሚከተሉትን መሠረታዊ ሃሳቦች
ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡-
ሀ. እርባታውን ጤናማ በሆኑ የወተት ከብቶች መጀመር አለበት፣
 ከጡት፣ ከውርጃና ከተላላፊ በሸታዎች ነፃ የሆኑ የወተት ከብቶች
በመምረጥ ርባታውን መጀመር፡፡
ለ. የወተት ላሞች ንፅህና መጠበቅ አለበት፣
 አጠቃላይ ላሚቷን በሳምንት ሁለት ጊዜ ማጠብ ያስፈልጋል፣
 ላሞች ከመታለባቸው በፊት በጉያቸውና በጡቶቻቸው ዙሪያ የሚገኙ
ረዣዥም ፀጉሮች በየጊዜው እየታዩ መቆረጥ አለባቸው፣
 የወተት ምርት የሚመረትበት የላሚቷ ግት ከአለባ በፊትና በኃላ በደንብ
ከታጠበ በኃላ በንጹህ ጨርቅ ማድረቅ፣
 የጡት በሽታ ያለመኖሩን አራቱን ጡት በትንሹ በማለብ ማረጋገጥ፣
የጡት በሽታ ያላቸው ላሞች ካሉ ለብቻቸው መጨረሻ ላይ ማለብ፣
 በጡት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጡትን በመጎተት አለባ አለመካሄዱን
ማረጋገጥ፡፡
ሐ. ንፁህ በረትና የማለቢያ ስፍራ መኖር አለበት፣
 በቂ ብርሃን የሚያስገባ፣ አየር የሚዘዋወርበትና ንፅህናው የተጠበቀ ምቹ
የከብቶች መጠለያ እንዲኖር ማድረግ፣
 የወተት ከብቶችን መጠለያና የማለቢያ ቤቶች ከአቧራ፣ ከተለያዩ
ነፋሳትና ከመጥፎ ሽታዎች ማፅዳት፣
 የወተት ከብቶች በጨቀዩ ቦታዎችና ንፅህናቸው ባልተጠበቀ የግጦሽ
ስፍራዎችና የመንገድ ዳርቻዎች እንዳይውሉ ማድረግ፣
መ. የወተት አላቢው ንፅህናውን መጠበቅ አለበት፣
 በወተት አለባ ሥራ የተሰማራ ግለሰብ የግል ንፅህናው በደንብ የተጠበቀና
በአለባ ጊዜ የሚለብሰው ልብስ ንፁህ መሆን አለበት፣
 የወተት ማለብ ሥራ ከመጀመሩ በፊት እጆቹን ሽታ በሌለው ሳሙና
በደንብ መታጠብና ማድረቅ ይኖርበታል፣
 የእጆቹ ጥፍሮች በደንብ የተቆረጡና ንጹህ መሆን አለባቸው፣
 ከተላላፊ በሽታ፣ ከጉንፋንና ከሳል የነፃ ጤነኛ አላቢ መሆን
ሲኖርበት፣ በየዓመቱ በተላላፊ በሽታዎች ያልተያዘ ስለመሆኑ
የጤና ምርመራ ማድረግ አለበት፡፡
ሠ. የወተት ዕቃዎች ንፅህና መጠበቅ አለበት፣
 የወተት ዕቃዎች ከዝገት የፀዱና ጥቅም ላይ ከመዋላቸው
በፊትና በኃላ በደንብ ታጥበው መድረቅ አለባቸው፣
 ወተት ከታለበ በኃላ በባዕድ ነገሮችና በጎጂ ነፍሳት
እንዳይበከልና ከመጥፎ ጠረን ለመከለላከል ወዲያውኑ ንፁህ
በሆነ እቃና የራሱ ክዳን ባለው መከደን ይኖርበታል፣
ማጠቃለያ

 ንፁህ ላም + ንፁህ አላቢ + ንፁህ የወተት ዕቃ +


ንፁህ በረትና የማለቢያ ስፍራ = በከፍተኛ ደረጃ ንፁህ
የሆነ ወተት እንዲመረት ያደርጋል፡፡
ወተት ከታለበ በኋላ
 ወተት ከታለበ በኃላም ንፅህናው መጠበቅ አለበት ፣ ማለትም
አነስተኛ የባክቴሪያ ቁጥር እንዲኖረው ያስፈልጋል፣
 ወተት እንደታለበ የወተቱ ሙቀት ከፍተኛ ስለሆነ ለባክቴሪያ
መበራከት ወሳኝ ጊዜ በመሆኑ ከታለበ በኃላ በቀዝቀዘ ቦታ
መቀመጥ አለበት፣
 በሙቀት ጊዜ ባክቴሪያዎች ቶሎ ይራባሉ፣
 ወተትን ከ15oc በታች ማቀዝቀዝ የባክቴሪያ እድገት
ይቀንሳል፤ የወተት የመጠቀሚያ ዕድሜ ያራዝማል፣
ወተት ከ12 ሰዓት በኋላ

ሙቀት oc የባክቴሪያ ቁጥር/ሚ.ሊ


0 2,400
4 2,500
5 2,600
6 3,100
10 11,100
13 18,000
16 180,000
20 450,000
30 2,400,000
35 25,000,000
ወተትን ለማቀዝቀዝ የሚረዱ ዘዴዎች
 በወተት ቤት ውስጥ ጥልቀቱ የወተት መያዣውን ቢዶን 3/4ኛ ያህል
የሚይዝ የማቀዝቀዣ ገንዳ ተሰርቶ ውሃ በመሙላት በውስጡ ወተት
ያዘውን ቢዶን በማድረግ፣
 ቢዶኑን እስከ ጆሮው ድረስ በጆንያ በመጠቅለል በተወሰነ የሰዓት ልዩነት
በጆንያው ላይ ውሃ በማፍሰስና ጥላ ቦታ በማስቀመጥ እንዲሁም ሌሎች
ዘዴዎችን መጠቀም ይቻላል፣
 የማታ ወተት ረዘም ያለ ጊዜ ስለሚቆይ ከፍተኛ የባክቴሪያ ቁጥር
ስለሚኖረውና የጠዋቱን ወተት ጥራት ስለሚያሳንሰው የጠዋትና የማታ
ወተት በተለያዩ ዕቃዎች መቀመጥ ይኖርባቸዋል፣
 በዚህም ንጽህናው የተጠበቀና ለጤና ተስማሚ የሆነ ወተት ወደ ተሻለ
ገበያ ለማቅረብ ከማስቻሉም በላይ ከንፁህ ወተት የተገኘ ቅቤ፣ አይብና
ሌሎች ምርቶች በንፅህናቸው የተጠበቁና ጥሩ ጣዕም ያላቸው በመሆኑ
ከፍተኛ ገቢ ያስገኛሉ፤ ለጤንነትም ተስማሚ ናቸው፡፡
 በንፅህና የተመረተን ወተት በቀጥታ ለማቀነበባሪዎች ወይንም ለወተት
አሰባሳቢዎች ማቅረብ ይቻላል፣

 ሆኖም አስተማማኝ ገበያ በማይኖርበትና በጾም ወቅት የተለያዩ


አነስተኛ ማቀነባበሪያዎችን በመጠቀም ወተትን ጥራታቸውን የጠበቁ
ወደ ተለያዩ የወተት ምርቶች ቅቤ፣ አይብ፣ ፎርማጆ፣ አይስክሬም…
ወዘተ በመለወጥ የመጠቀሚያ ጊዜውን በማራዘም ጥራቱንም
በመጠበቅ የተሻለ ዋጋ ማግኘት ይቻላል፡፡
 እዚህ ላይ አሁን የመጣውን የቅቤ መናጫ ቴክኖሎጂ ማሰብ ይቻላል፡፡
8. የወተት ከብቶች መጠለያ ዝግጅት

 የወተት ከብት ርባታ ከመጀመሩ በፊት የከብት መጠለያ ማዘጋጀት ቅድሚያ ትኩረት
የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡
የእንስሳት መጠለያ አስፈላጊነት፣
o ከዝናብና ከኃይለኛ ንፋስ ለመከላከል፣
o ከከፍተኛ ሙቀትና ብርድ ለመከላከል፣
o የመኖ ብክነትን ለማስወገድ፣
o አስሮ የመመገብ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ፣
o አዛባን ለማሰባሰብና ጥቅም ላይ ለማዋል፣
o ለዕለት እንቅስቃሴዎች አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር፣
o የእንስሳቱን ምቾት ለመጠበቅ፣
o እንስሳቱን ከጠላት ለመጠበቅ፡፡

 እዚህ ላይ ማጤን ያለብን የወተት ከብቶች ቤት/በረት ለመስራት የሚወጣውን ወጪ


በተቻለ መጠን ለመቀነስ ለመስሪያ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች አነስተኛ ዋጋ ያላቸውና
በቀላሉ በአካባቢው ሊገኙ በሚችሉ በቆርቆሮና በጭቃ ቢሰራ እንዲሁም ቀላል ወጪ
የሚጠይቅ የበረት ዲዛይን መምረጥ የተሻለ ወጪን ይቀንሳል፤ ትርፋማም ያደርጋል፡፡
የከብት መጠለያን ለመስራት በምናቅድበት ጊዜ በአጠቃላይ
ልንከተላቸው የሚገባን መመሪያዎች ፡-
o የአካባቢውን የንፋስ አቅጣጫ ለይቶ በማወቅ በተቻለ መጠን
መጠለያው ንፋስ ከሚነፍስበት አቅጣጫ በግድግዳ መከለል
ይገባዋል፣
o በተቻለ መጠን መጠለያው ከሰሜን ወደ ደቡብ ቢሰራ የማታ
ወይም የጠዋት ፀሐይን ሊያገኝ ይችላል፣
o የከብቶች መጠለያ የሚሰራበት ቦታ ደረቅና ውሃ የማይቋር
/የማይkጥር/ መሆን አለበት፤ እንደአካባቢው ሁኔታ ትንሽ
ተዳፋትነት እንዲኖረው ያስፈልጋል፣
o የተሠራው መጠለያ አየር መዘዋወር የሚችልበት ክፍተት ያለውና
የፀሐይ ብርሃን በመጠኑ እንዲያገኝ የሚያስችል ሆኖ መሠራት
አለበት ፡፡
 በወተት ከብት ርባታ የተለያዩ ቤቶች አስፈላጊ ቢሆኑም
አቅም በፈቀደ መጠን የላሞች ቤት፣ የጥጆች ቤት፣ የመዝናኛ
ቦታ፣ የድርቆሽ መጠለያ እና የመኖ መጋዘን አስፈላጊ ናቸው፣
 በከብቶች መጠለያ ውስጥ የድርቆሽ መመገቢያና
የተመጣጠነ መኖ መመገቢያ ገንዳ አስፈላጊና መሠረታዊ
ናቸው፣
 የድርቆሽና የተመጣጠነ መኖ መመገቢያዎች አስፈላጊነት
የከብቶች መኖ በየመልኩ እንዲቀርብ የሚያስችሉ
በመሆናቸው፣ የከብቶቹ መኖ ከቆሻሻ ጋር እንዳይደባለቅና
መኖ እንዳይባክን ስለሚረዳ ነው፣
 የውሃ መጠጫ ገንዳ ከቤቱ ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡
የከብት መጠለያ ዓይነቶች
የከብት መጠለያ ዓይነቶች ሁለት ናቸው፡፡
o ባለሦስት ግድግዳ
o ባለአራት ግድግዳ የከብት በረት ተብለው ይታወቃሉ፡፡
ሀ. ባለሦስት ግድግዳ የከብት በረት
 ባለሦስት ግድግዳ የከብት በረት ንፋስ፣ ዝናብና ወጨፎ በማይመጣበት
አቅጣጫ ያለው ግድግዳ ክፍት ሲሆን ሌሎቹ ሦስት ግድግዳዎች ድፍን
ናቸው፣
 ጣሪያው በቆርቆሮ ወይም በሣር ይሸፈናል፣
 በውስጡ የድርቆሽና የተመጣጠነ መኖ መመገቢያ አለው፣
 የበረቱ ወለሉ የድንጋይ ንጣፍ ሳይሆን ሊሾ መሆን አለበት፡፡
 በዚህ የበረት አሰራር ክፍት በሆነው የበረት ሥፍራ በኩል የቤቱን
ወለል እጥፍ ስፋት ያለው አጥር ይኖረዋል፣
 ይህ አጥር እንደመጠለያው ወለል በሲሚንቶ ቢሰራ ለንጽህናና
የከብቱን ጤና ለመጠበቅ ያስችላል፣
 የውሃ መጠጫ በአጥር ግቢ ውስጥ እንደአመቺነቱ ይዘጋጃል፡፡
 ባለሦስት ግድግዳ መጠለያ ከባለ አራት ግድግዳ መጠለያ ያነሰ ወጪ
በመጠየቁ፣ በቀላሉ ሊስፋፋ ስለሚችልና የእንስሳት ቁጥርን በቀላሉ
መጨመር በማስቻሉ የተሻለ ነው፣
 በዚህ መጠለያ ውጥ እንስሳት በተፈለገ ጊዜ በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ
ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ላሞችን ነፃ መለቀቅ ጉዳቱ
ስለሚያመዝን ባለሦስት ግድግዳ መጠለያ ሠርቶ ማሠሩ አስፈላጊ
ነው፡፡
በቀላሉ ሊሰራ የሚችል ባለ 3 ግድግዳ መጠለያ
ሀ. ባለ አራት ግድግዳ የከብት በረት

 ዙሪያውን ግድግዳ ያለው መጠለያ ሲሆን፣ ለብርሃንና


ለንፋስ መግቢያ ባለወንፊት መስኮት ያለው ነው፣
 ጣሪያው የቆርቆሮ መይም የሣር ክዳን ያለው ነው፣
 ከብቶቹ በአንድ ጣሪያ ስር ቢኖሩም በዕድሜ ተለይተው
የላም፣ የጊደር፣ የጥጃ ማደርያ ተብለው የሚከፋፈሉ
ናቸው፡
የአየር ማስገቢያ በጣሪያ ላይ
የአየር ማስገቢያ በግድግዳ ላይ
የከብቶች መቆሚያና መመገቢያ ገንዳ
ለወተት ከብቶች የሚያስፈልግ የመጠለያ ስፋት መጠን
o ለላሞች ወይም ጊደሮች የሚሰራ መጠለያ ቁመቱ 1.75 ሜትር ጎኑ 1.10
ሜትር ስፋት ለእያንዳንዱ ከብት በማሰብ ሊሠራ ይችላል፣
o የመመገቢያ ገንዳ ከወለል ከፍታ 50 ሳ. ሜ ጎን 60 ሳ.ሜ እና ጥልቀቱ 40 ሴ.ሜ፣
o የሽንት መውረጃ ቦይ 30 ሳ.ሜ፣
o በሁለት መመገቢያዎች መካከል ያለው መተላለፊያ አንድ ሜትር ቢሆን
ይመረጣል፣
o የከብቶች መግቢያና መውጫ በር ሰፋ ብሎ መሠራት ይኖርበታል፣
o የጥጆች መጠለያ ከመሬት ከፍ ብሎ 1 ሜትር x 1.10 x 1 ሜትር ሳጥን መሰል
እንዲሰራላቸው ያስፈለጋል፡፡ ጥጆች ታዳጊ እንደመሆናቸው መጠን ቅዝቃዜ
እንዳይሰማቸው ወለሉ መጎዝገዝ ያስፈልጋል፣
o ከብቶቹ በጤንነት እንዲኖሩ መጠለያቸው በየቀኑ መጠረግ አለበት፡፡ ጠዋት
ከብቶቹ ከበረት እንደወጡ አዛባውን ወደ ውጭ ማውጣትና ለጉዝጓዝ
የተጠቀሙበትን ሣር ሰብስቦ በማውጣት በአዲስ መተካት ያስፈልጋል፡፡
የጥጆች ሣጥን
9. የወተት ከብት ርባታ መዝገብ /ሪከርድ/አያያዝ
 ሪከርድ ማለት ርባታውን አስመልክቶ የሚፈለጉትን መረጃዎች በዓይነት
በዓይነቱ የሚሰፍርበት መዝገብ ወይም የመረጃዎች ማህደር ማለት
ነው፣
 በስኬታማ የወተት ከብቶች ርባታ ሪከርድ ወሳኝነት አለው፣ የርባታው
ጠንካራና ደካማ ጎን የሚገመገመው፣ እንዲሻሻል ወይም ባለበት
እንዲቆይ ውሳኔ የሚሰጠው በሪከርድ በሚገኙ መረጃዎች መሠረት
ነው፣
o ለምሳሌ የትኞቹ ከብቶች ከበረት መወገድ እንዳለባቸው፣ ስንቶቹ መቼ መጠቃት
እንዳለባቸው፣ ምን ዓይነት በሽታ ወይንም ሕመም በከብቶች ላይ እንደሚታይና
ምን ዓይነት ሕክምና መቼ መሰጠት እንዳለበት፣ ስንት ጥጆች እንዳሉ፣ የትኞቹ
መሸጥ አለመሸጥ እንደሚገባቸው፣ ክትባት መቼ መሰጠት እንዳለበት … ወዘተ
ለመወሰን መነሻው ሪኮርድ ነው፡፡
o ከዚህ አልፎ ርባታው አክሳሪ ነው ወይንስ አትራፊ የሚለው ጥያቄ
የሚገመገመው፣ ወጪና ገቢው የሚተነተነው፣ ምን ያህል ምርት እንደተመረተ
የሚሰላው ከዚሁ መዝገብ /ሪከርድ/ ነው፡፡
የመዝገብ መያዝ /ሪከርድ/ አስፈላጊነት
o በርባታው ውስጥ ያሉትን ችግሮች ለማወቅ፣
o የድቀላ ፕሮግራም ለማቀድ፣
o የበሽታ ሁኔታን ለመከታተል፣
o በርባታው ውስጥ ያሉ ከብቶችን ዝርያ፣ የወተት ምርት አቅም … ወዘተ
ለማወቅ፣
o በየደረጃው ለውሳኔ የሚረዳ መረጃ ለመሰብሰብ፡፡
አንድ ርባታ ሪከርድ ለመያዝ የሚከተሉትን አበይት ነጥቦች በቅድሚያ
ማሟላት ይገባዋል፡-
o ጥሩ የተጠረዘ የባሕር መዝገብ እና የተለያዩ የሪከርድ ቅጾች፣
o መጻፍና ማንበብ የሚችል ወንድ/ሴት በተለይ የርባታውን የዕለት ተዕለት
እንቅስቃሴ የሚከታተል የቤተሰብ አባል፣
o ለከብቶቹ ስያሜ ወይም መለያ መስጠት፡፡
ለከብቶች ስያሜ ወይም መለያ ወይም መታወቂያ የመስጠት ጠቀሜታ፡-
o አንድን ከብት ከመንጋ መሀል በቀላሉ ለይቶ ለማውጣት፣
o ስለእያንዳንዱ ከብት ማንኛውንም መረጃ ማለትም መቼ እና ምን ዓይነት
ሕመም እንደታመመች፣ የሰጠችውን የወተት ምርት መጠን፣ የወሊድ ሁኔታ፣
የኮርማ ፍላጎት ወዘተ በማያዳግም እና ትክክለኛ በሆነ መልክ ለመያዝ ይረዳናል፡፡

የከብቶች መለያ ወይም መታወቂያ ዓይነቶች፡-


o የጆሮ ሎቲ /ጉትቻ/፣
o የአንገት ሰንሰለት፣
o የአንገት ቀበቶ … ወዘተ
በአንድ ርባታ ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው ዋና ዋና የሪከርድ ዓይነቶች፡-
o የመኖ ሪከርድ
o የጤንነት ሪከርድ
o የወሊድ ሪከርድ
o የምርት ሪከርድ
o የወጪና የገቢ ሪከርድ
o አጠቃላይ ሪከርድ
ቅጽ 1 -- የወተት ምርት /በሊትር/ መዝገብ አያያዝ

ቀን ጠዋት ማታ ድምር

ድምር

የተመዘገቡ ቀኖች
ቅጽ 2 --- የወተት ምርት አጠቃቀም መዝገብ

ቀን አጠቃላይ ለጥጃ ለቤት የተበላሸ የተሸጠ የአንድ ጠቅላላ


ምርት የተሰጠ ውስጥ (የባከነ) ሊትር ዋጋ የሽያጭ
ፍጆታ ዋጋ
የዋለ

ቀን
የተመዘገቡ ቀኖች
ቅጽ 3 -- የፋይናንስ እንቅስቃሴ መዝገብ

ቀን ዝርዝር መግለጫ ቁጥር የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ

ድምር
ቅጽ 4 -- የትርፍና ኪሳራ መግለጫ

ሀ. አጠቃላይ ገቢ መጠን (ብር) ለ. ወጪ መጠን(ብር)

ድምር (ገቢ) ድምር(ወጪ)


የተጣራ ትርፍ

You might also like