You are on page 1of 35

KEC 2018-11

የዶሮ እርባታ
የዶሮ እርባታ መምሪያ መፅሃፍ
2
ይዘቶች
ገፅ
መግቢያ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .. . . . . . . 2
-የዶሮ ዝርያዎች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3
የዶሮ ምርት. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 9
-የዶሮ እርባታ ዘዴ አይነቶች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . 9
-ዶሮዎችን የመምረጫ መስፈርት . . . . . . . . . . . . . . . 10

የዶሮ መኖሪያ እና እቃዎች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . 12

አያያዝ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 16
-ሙቀት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 22
- በሽታዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 24
-መኖ. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 26
-ክትባት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .28

3
1. መግቢያ

የስነ-እንስሳት ስም : Gallus gallus domesticus.

ስም: ወንድ ዶሮ፣ አውራ ዶሮ ወይም ትንሽ አውራ ዶሮ ይባላል።


ሴትዋ ደግሞ ዶሮ ትባላለች።

የዶሮ መነሻ ሃገራት: ደቡብ ምስራቅ አስያ፣ ምስራቅ አስያ፣ ደቡብ አስያ

ዶሮ የአዕዋፍ ወገን ሲሆን ንኡስ ብቸኛ ዝርያው ደግሞ ቀይ የደን አዕዋፍ ነው።
የእ.ኤ.አ 2011 ዘገባ እንደሚያመለክተው ዶሮ በቍጥር 19 ቢሊየን ሲደርስ በብዛት የ
ሚገኙ እና የተለመዱ የቤት እንስሳት ውስጥ አንዱ ነው።

ከሌሎች የወፍ ወይም የአዕዋፍ ዝርያ በላይ ዶሮዎች በብዛት በአለም ላይ ይገኛሉ።
ሰዎች ዶሮዎችን በዋነኝነት ለምግብነት (እንቁላል እና ስጋ ) እንዲያገለግሉ ያሳድጓቸዋል
ያልተለመደ ቢሆንም እንደ ለማዳ እንስሳ ያሳድጓቸዋል።

በቀደምትነት በሄለንስቲክ ዘመን (4-2ኛ ክፍለ-ዘመን)ሰዎች ዶሮዎችን ለአውራ ዶሮዎች


ድብድብ ወይም ለተለያዮ ዝግጅቶች በማሰብ እንጂ ለምግብነት ብለው አያሳድጓቸው
ም ነበር።

ዶሮዎች ሁሉን በይ ናቸው። አብዛኛውን ጊዜ ጥሬ ለማግኘት አፈር ይጭራሉ፣


ነፍሳትን፣ እንደ እንሽላሊት፣ ትንንሽ እባብ፣ ትንንሽ አይጦች ያሉ እንስሳትን ይበላሉ።

በአጠቃላይ ክብደታቸው ቀላል የሆኑ ወፎች አጭር ርቀት እንደ አጥር፣ ዛፍ ያሉ


አጭር ርቀቶችን መብረር ቢችሉም ዶሮዎች ረጅም ርቀት መብረር አይችሉም።
ዶሮዎች አልፎ አልፎ አካባቢያቸውን ለመቃኘት ለአጭር ጊዜ መብረር ይችላሉ፣
ነገር ግን በአጠቃላይ የሚበሩት የሚታወቁትን አደጋ ለመሸሽ ብቻ ነው።

. 4
የዶሮ ዝርያ
ዶሮዎች እንደሚሰጡት ጥቅም እንቁላል ጣይ ዶሮ፣ ለስጋነት የሚውል እና
ጥምር አገልግሎት የሚሰጡ ዶሮዎች ተበለው ይከፈላሉ። በዋናነት እንቁላል
ጣይ ዶሮዎች ለእንቁላል፣ ለስጋነት የሚውሉ ዶሮዎች ለስጋ፣ ጥምር አገልግሎት
የሚሰጡ ዶሮዎች ደግሞ ለእንቁላል እና ለስጋነት ያገለግላሉ። ዶሮዎችን
በምናሳድግ ጊዜ የምንፈልገውን ዝርያ አውቆ ማሳደግ አስፈላጊ ነው።

እንቁላል ጣይ ዶሮ
1) ሌግሆርን
ቀለማቸው ነጭ እና በአለም በበርካታ ሃገራት
እንደእንቁላል ጣይ ዶሮ ያገለግላሉ። ሌላ ነጭ
ዝርያ አልተለመደም።

እንቁላላቸው : 180-250 ፣ ትላልቅ፣ ነጭ

ክብደት
አውራ ዶሮ: 3.4 ኪሎ
የሴት ዶሮ: 2.5ኪሎ

5
2) አንዳሉሲያን
የአንዳሉሲያን ዶሮ ዝርያዎች የጆሮ
መዳፋቸው ለስላሳ፣ ነጭ እና የለው
ዝ ቅርጽ ያለው ነው። ጉትዬአቸው
አንድ ወጥ ሆኖ መካከለኛ መጠን ያ
ለው ሲሆን ባለ አምስት ጫፍ ቅርጽ
ያለው ነው።
እንቁላላቸው፡ በዓመት ከ160 እስከ
200 ነጭ እንቁላል ይጥላሉ።
ክብደት፡
አውራ ዶሮ፡ 3.2 – 3.6 ኪሎ ግራም
ሴት ዶሮ፡ 2.25 – 2.7 ኪሎ ግራም

3) ሚኖርካ

ጠንካራ የዶሮ ዝርያዎች ቢሆኑም በ


ብርድ ወቅት ጉትዬአቸው ሊጠቁር ይ
ችላል።
እንቋላላቸው፡ 170 ግራም እስከ 220
ግራም
ክብደት፡
አውራ ዶሮ፡ 3.2 – 3.6 ኪሎ ግራም
ሴት ዶሮ፡ 2.25 – 3.2 ኪሎ ግራም

6
የሥጋ ዶሮዎች
1) ኮቺን

የኮቺን ዶሮ ዝርያዎች ዝግ ያሉ እና የማይተ


ናኮሉ የዶሮ ዝርያዎች ሲሆኑ ለማደግ ረዘም
ያለ ጊዜ ይፈጅባቸዋል። ሰውነታቸው ትልቅ
ሲሆን ትናንሽ እንቁላሎችን በብዛት ይጥላሉ
ለሥጋ የሚሆኑ ዝርያዎች ናቸው።
ክብደት፡
አውራ ዶሮ፡ 4.5 – 5.1 ኪሎ ግራም
ሴት ዶሮ፡ 4.1 – 5 ኪሎ ግራም

2) ብራህማ

ከዶሮ ዝርያዎች ሁሉ ሰውነታቸው ትልቅ


ነው። በባህርያቸው ዝግ ያሉ ናቸው።
ክብደት፡
አውራ ዶሮ፡ 4.55 – 5.45 ኪሎ ግራም
ሴት ዶሮ፡ 3.2 – 4.10 ኪሎ ግራም

7
የእንቁላል እና የሥጋ ዶሮዎች
1) የፕሊመዝ ዓለት ቀለም ያለው ዶሮ
ለእንቋላል እና ለሥጋ እርባታ የሚሆን
የዶሮ ዝርያ ነው። እድገታቸውን በደንብ
ሲጨርሱ ሥጋቸው ተፈላጊ እና ብዛት ያለ
ው ነው ።
እንቁላላቸው፡ ከ190 እስከ 240 እንቁላል
በዓመት ይጥላሉ።
ክብደት፡
አውራ ዶሮ፡ 3.4 ኪሎ ግራም
ሴት ዶሮ፡ 2.95 ኪሎ ግራም

2) የሮድ ደሴት ቀይ ዶሮ
የሮድ ደሴት ቀይ ዶሮ ዝርያዎች ምር
ታማ የሆኑ የዶሮ ዝርያዎች ሲሆኑ ነ
ጣ ያለ ቡኒ እንቁላል ይጥላሉ።
አውራ ዶሮውች በስርያ ወቅት
ቁጡ እና ተተናኳሽ ሊሆኑ ይችላሉ።

እንቁላላቸው፡ እንክብካቤ ከተደረገላ


ቸው 250 እና ከዚያ በላይ ነጣ ያለ
እንቁላል ይጥላሉ።
ክብደት፡
አውራ ዶሮ፡ 3.85 ኪሎ ግራም
ሴት ዶሮ፡ 2.95 ኪሎ ግራም

8
2. ዶሮ እርባታ
2-1. የዶሮ እርባታ ዘዴዎች

የዶሮ እርባታ በገጠር ላለው ማህበረሰብ ባህላዊ፣ ሕብረተሰባዊ እንዲሁም


ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦው ላቅ ያለ ነው። በተለምዶው ዶሮ እርባታ በሴቶች፣
በሕጻናት፣ በአካል ጉዳተኞች እንዲሁም በአዛውንቶች የሚከናወን ሲሆን የዕለ
ት ጉርሳቸውን እንዲያሟሉ እና ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ አቅም ይሆናቸዋል
። በአሁን ወቅት ዶሮ እርባታ ለብዙዎች መደበኛ ሥራ እና የገቢ ምንጭ ሆኖ
ያገለግላል።

ምስል 2. መንደር ሀ)ያልተቀናጀ ለ)በከፊል የተቀናጀ ሐ)በሙሉ የተቀናጀ የዶሮ እርባታ

9
በኢትዮጵያ ሦስት አይነት የዶሮ እርባታ ዘዴዎች በመተግበር ላይ አሉ።
እነዚህም መንደርን መሰረት ያደረጉ እርባታዎች፣ በከፊል የተደራጁ የዶ
ሮ እርባታ ዘዴዎች ፣ እና ሙሉ በሙሉ የተደራጁ/ዘመናዊ የእርባታ አ
ሰራር/ ናቸው።

2-2 የዶሮ አመራረጥ መርሆዎች

እንቁላል የመፈልፈል ሁኔታ: የዶሮዎች እንቋላል የመፈልፈል ልምዳቸ


ው ዋና የመምረጫ መመዘኛ ተደርጎ ባይወሰድም ለሥጋ ተብለው የሚ
ረቡ ዶሮዎችን ለእንቋላል ምርት መጠቀም ከተፈለገ እንቁላል መፈልፈ
ል በደንብ አለባቸው። ይህንንም ለማወቅ የክንፋቸው ርዝመት፣ የሰውነ
ታቸው ቅርጽ እና ለረጅም ሰዓት መቀመጥ እና አለመቀመጣቸው መታ
የት አለበት።

10
2. ከፍተኛ የሆነ የእድገት ሁኔታ፡ ፈጣን የሆነ እድገት የሚያሳዩ ዶሮዎ
ች ተፈላጊ ናቸው። ለመራባት አዝጋሚ የሆነ እድገት የሚያሳዩ እንዲ
ሁም ለእርድ የደረሱ ትርፍ አውራ ዶሮውች ካሉ እነሱን ማረድ እና
ወጪ መቀነስ ያስፈልጋል።

3. ለመፈልፈል የሚሆኑ እንቁላሎችን መለየት፡ መካከለኛ የሆነ መጠን


ያላቸው፣ ቅርፊታቸው ጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ (ቅርጹ ያልተበላሸ እንዲሁ
ም ስንጥቅ የሌለው) እና ቅርጻቸው ልከኛ የሆነ (ታቹ ሰፊ የሆነ እና የ
ላይኛው ጫፍ ሾል ያለ) መሆን አለበት።

4. የተፈለፈሉ ጫጩቶች፡ ጥሩ የሆነ ሰውነት ያላቸው እንዲሁም እግ


ራቸው እና አይናቸው ላይ ምንም እክል የሌለባቸው መሆን አለበት።
በተጨማሪም መኖ አመጋገባቸው እና ውሃ አጠጣቸውን መከታተል ያ
ስፈልጋል።

5. በሽታን መቋቋም፡ በሽታን የመቋቋም አቅማቸው ጥሩ የሆነ ዶሮዎ


ችን መምረጥ ወረርሽኝ በሚከሰትበት ጊዜ ብዙ ዶሮ ሞቶ ከሚደርስ
ኪሳራ ያድናል።

11
3. መጠለያ እና ሌሎች ቁሳቁሶች

የዶሮ መጠለያ
በአንስተኛ ደረጃ የሚደረጉ የዶሮ እርባታዎች በዶሮ ብዛት፣ በአርቢ
ዎቹ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና አርቢዎቹ በሚጠቀሙባቸው የኮንስትራክ
ሽን መሳሪያዎች ይለያያሉ። የዶሮ መጠለያ መስራት ከአውሬ እና
ተላላፊ በሆኑ በሽታዎች ቶሎ እንዳይጠቁ ዶሮዎቹን ይጠብቃል።
መጠለያው ቢያንስ 2.5 ሜትር እና በር የተገጠመለት እንዲሁም አየ
ር እንዲገባ በሽቦ የታጠሩ ቀዳዳዎች/ክፍተቶች ያስፈልጋሉ። ከገበያ የ
ሚገዛ ሽቦ በአቅራቢያ ከሌለ አውሬ የማያሳልፍ እና አየር የሚያስገባ
ሽቦ መሰል ነገር መስራት/ማድረግ ይቻላል።

12
\

ቆጥ
ለእያንዳንዱ ዶሮ የሚሰራው ቆጥ ከ24 – 30 ሴ.ሜ ክፍል ለእያንዳንዱ ዶሮ
ቦታ ሊኖረው ይገባል። በተጨማሪም ከ40 እስከ 45 ሴ.ሜ የተራራቁ መሆ
ን አለባቸው። ቆጦች በተለምዶ ከ60 እስከ 90 ሚሊሜትር እፀቴ ተክል ይ
ሰራሉ። ቆጦቹ ጥግ ላይ ሊሰሩ ይችላሉ። ነገር ግን ዶሮዎቹ እንዳይጎዱ የላይ
ኛውን ጠርዝ ማለስለስ ያስፈልጋል።

13
ጫጩት ማሳደጊያ

እንቁላል ጣይ ዶሮዎች እንቁላል ለመፈልፈል የሚወስድባቸውን ጊዜ ለመ


ቀነስ እና የጫጩቶቹን ሞት ለመከላከል በአቅራቢያ ከሚገኝ መሳሪያዎች
የጫጩት መፈልፈያ/ማሳደጊያ መስራት ያስፈልጋል።

ምስል 5. ሀ) የከሰል መፈልፈያ ለ) የሳጥን መፈልፈያ ሐ)የኤሌትሪክ ማሞቂያ መፈልፈያ

14
እንቋላል መጣያ ቆጥ

እንቋላል መጣያ ቆጥ በአግባቡ የተሰራ መሆን አለበት። አቀማመጡም በቅርብ ያለ


ቦታ፣ ጨለም ያለ፣ እና ለስላሳ በሆኑ መሳሪያዎች የተሰራ መሆን አለበት።
ይህም እንቁላሎች እንዳይጎዱ ያደርጋል።

ሁለት አይነት እንቁላል መጣያ ቆጥ አሉ፡


 የጋራ እንቁላል መጣያዎች በአንድ ጊዜ እስከ 5 ዶሮዎች እንቋላል ይጥሉባቸዋል
 የግል እንቁላል መጣያዎች በአንድ ጊዜ አንድ ዶሮ ብቻ እንቋላል መጣል ያስችላል

እያንዳንዱ መጣያ 40 ሳሜ በ 35 ሳሜ በ 40 ሳሜ (ቁመት፣ ርዝመት፣ እና ስፋት)


ሆኖ የተሰራ መሆን ይኖርበታል።

የጋራ እንቋላል መጣያዎች የግል እንቋላል መጣያዎች

ምስል 6. በቀላሉ የተሰራ የእንቁላል መጣያ ቤቶች

15
ዶሮዎቹም መጠጫቸውንና እና መመገቢያቸውን ቀለል ባለ መልኩ በአቅራቢ
ያ ከሚገኙ ዕቃዎች ማዘጋጀት ማዘጋጀት ይቻላል። በየጊዜው (በቀን ከ2 እስከ
3 ጊዜ) ውሃቸውን መቀየር እንዲሁም በየቀኑ መመገቢያቸውንና መጠጫቸው
ን ማጽዳት በተበከለ ምግብ እና ውሃ አማካይነት የሚመጡ ተላላፊ በሽታዎች
ን ይከላከላል።

ምስል 7. በቀላሉ የተሰራ የእንቁላል መጣያ ቤቶች

16
4. አያያዝ እና ቁጥጥር

በሽታዎች በብዛት ዶሮዎችን በመግደል ለከፍተኛ ኪሳራ ይዳርጋሉ። ይህም ጥንቃ


ቄ በታከለበት መልኩ ጤናቸውን በመከታተል ቅድሚያ መከላከል እና ሲከሰትም
የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ ይቻላል። የዶሮ መንጋ ጤናቸውን በአግባቡ
ለመጠበቅ ዶሮዎቹ ተጋላጭ የሆኑባቸውን መንስኤዎች መለየት ያስፈልጋል።

በዋንኛነት የሚጠቀሱትም፡
• የተበከሉ መገልገያዎች
• ከመጠን በላይ የሆነ የሰው ምልልስ (ብዛት)
• ሌሎች የቤት እንስሶች
• የዱር እንስሶች እና ወፎች
• የታመሙ ወፎች
• ያልተገለሉ አዲስ የተገዙ እና የታመሙ ዶሮዎች
መነሻው ያልተለየ የዶሮ ወረርሽኝ (የትኛው ዶሮ መጀመሪያ እንደታመመ)

ስለዚህ የከፋ ወረርሽኝ በሚከሰት ጊዜ እነዚህን ማድረግ ያስፈልጋል

• አዲስ የዶሮ መንጋን ለ14 ቀን ያህል መለየት


• የበሽታ ምልክት የሚያሳዩ ዶሮዎችን መለየት ወይም መክላት
• የተከሉ ዶሮዎችን መቅበር ወይም ማቃጠል

17
• ከአውሬ መከላከያ እና ከበሽታ መጠበቂያ እንዲሆኑ አጥሮችን
ማጠናከር
• የእንስሳት ሀኪም፣ የዶሮ ባለሙያዎችን እና ሌሎች ተቋሞችን
ማማከር

ምስል 8 ሀ) በቀላሉ የተገነባ የመለያ ቤት ለ)አጥር

ለበሽታ መስፋፋት ሊዳርጉ የሚችሉ እና መቆም ያለባቸው ደካማ ተግባራት ምሳሌዎች

 በመንጋው ውስጥ የበሽታ መኖር ጥርጣሬ በሚፈጠርበት ወቅት የታመሙትን ዶሮ


ዎች ጨምሮ በአጠቃላይ ዶሮን አለመሸጥ
 በጋራ መንደር አካባቢዎች ወይም የውሃ ምንጮች ባሉበት አካባቢ የሞቱ ዶሮዎችን
አለመጣል
 የሞተ ወፍን እንደ ውሾች ወይም ድመቶች ላሉት የቤት እንስሳት አለመመገብ ፣
 የዶሮ መጠለያዎች እንዲቆሽሹ አለመፍቀድ (በየጊዜው ማፅዳት)

18
ተፈጥሮአዊ ደህንነት ሕይወት ባላቸው ዶሮዎች ገበያ

በኢትዮጵያ የሚገኙ የዶሮ ገበያዎች በአብዛኛው ክፍት ገብያዎች ናቸው።


ክፍት ገበያዎች ከሰው ወደ ዶሮዎች እንዲሁም ከዶሮ ወደ ሰዎ በሽታ እ
ንዲተለለፍ አመቺ ሁኔታ ይፈጥራሉ። ይሄ ደግሞ ብዙ ጊዜ የሚሆነው ከ
ንጽህና ጉድለት ሲሆን ለንጽህና እና ከበሽታ ለመከላከል የሚሆኑ በቂ መ
ሳሪያዎች እና ልብሶች ስለማይኖሩ ነው።

ክፍት ገበያዎች በባህሪያቸው ተፈጥሮአዊ የበሽታ መራቢያ ቦታዎች ተብ


ለው ሊመደቡ የሚችሉ ሲሆን፣ የታመሙ ዶሮዎች ገበያ ላይ ሲቀርቡ
እዚያው ለሚገኙ ዶሮዎች በሽታ ሊያስተላልፉ እንዲሁም ከእርድ በኋላ
ለሰዎች መታመም መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።

ምስል 9. የአገር ውስጥ የዶሮ እርባታ ግብይት ስርዓት

19
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የጥንቃቄ መመሪያዎች ዶሮዎች በሚሸጡባቸው
ክፍት ገበያዎች ሊተገበሩ ይገባል።

• በጽዳት እና ዲሲንፌክት በማድረግ የግል ንጽህናን መጠበቅ እንደሚቻል


ማሳወቅ እና ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል
• ዶሮዎች ከመጓጓዛቸው በፊት ጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ መሆናቸውን
ማረጋገጥ ያስፈልጋል
• የቤት ለቤት የዶሮ ሽያጭ ሊከለከል ይገባዋል
• ያልተሸጡ ዶሮዎች የሚገለሉበት አግባብ ሊዘጋጅ ያስፈልጋል

ከአውሬ መከላከል

ዶሮዎች ለግብርና ሲመረጡ አውሬ ሲመጣ በሚያሳዩት ባህርይ (ፈሪ አለ


መሆናቸውን) ብቻ ማየት የራሱ አሉታው ተጽዕኖ አለው። ምክኒያቱም
ሌሎች ከምርታማነት ጋር የተያያዙ ነገሮች ችላ ሊባሉ ይችላሉ። ስለዚህ
አውሬን ለመከላከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ዝግጅቶች ማድረ
ግ ያስፈልጋል።

14
20
• ለዶሮዎች የሚሆን መጠለያ በተለይም በጠዋት እና ከመሸ በኋላ
የሚቆዩበት ስፍራ ያስፈልጋቸዋል
• ጫጩቶችን በሰው ሰራሽ መፈልፈያ መፈልፈል እና ማሳደግ
• ጫጩቶች እስኪጎለምሱ እና ራሳቸውን መከላከል እስኪችሉ ድረስ በየጊዜው
መከታተል
• ወጥመድ ማጥመድ ወይም ተከታትሎ ማደን (ለድመት፣ ለውሾች፣ እንዲሁ
ም ለሌሎች አውሬዎች)
•ጫጩቶቹ ከቤት ርቀው ምግብ ፈለጋ እንዳይሄዱ በደንብ መቀለብ

በሀገሪቷ የዶሮ እርባታውን ዘርፍ ምርታማነት እና የምርት ጥራት ለማሳደ


ግ ጥሩ የሆነ የማስፋፊያ ስልት እና በየቦታው ላሉ ገበሬዎች እንደየሁኔታ
ቸው ስልጠና ማዘጋጀት ወሳኝ ነገሮች ናቸው። በዘርፉ ላይ እንዚህን ነገሮ
ች አድርጎ ለውጥ ለማምጣት በባለሙያ የታገዘ እና ያላሰለሰ ክትትል ያስ
ፈልገዋል። ስለዚህ ገበሬዎች የማስፋፊያ ወኪሎችን እና ባለሙያዎችን
በማግኘት ሙያዊ ድጋፍ ማግኘት ያስፈልጋቸዋል።

21
4-1. ሙቀት

ሙቀትን መቆጣጠር

ሙቀትን መቆጣጠር ምርትማ የሆነ የዶሮ እርባታ ለማካሄድ ወሳኝ ነገር ነ


ው። የሙቀት ቁጥጥር ለዶሮዎቹ እንደየዕድሜአቸው የሚደረግ ይሆናል።
በአፍላ ወቅት (ከ1 እስከ 4 ሳምንት) ላሉ ጫጩቶች ከፍ ያለ ሙቀት የሚ
ፈልግ ይሆናል። ለንግድ በተቋቋሙ የዶሮ እርባታ ተቋሞች ይህ ሙቀት ሰ
ው ሰራሽ በሆኑ መንገዶች የሚደረግ ይሆናል። ይህም በኢንፍራ ሬድ አሞ
ፖሎች፣ መከለያ መፈልፈያዎች፣ እና የማሳደጊያ ሳጥኖች ውስጥ በማኖር
የሚቻል ይሆናል። በተጨማሪም ጫጩቶቹ ከመፈልፈያዎቹ ርቀው እንዳ
ይሄዱ ጠባቂ ያስፈልጋቸዋል። ይህም ርቀው ሲሄዱ ከሚያጋጥማቸው
ይጠብቃቸዋል። መፈልፈያዎች ለእያንዳንዱ የጫጩት ጀማ የታጠቡ እና
የበሽታ ማጥፊያ የተረጨባቸው እንዲሆኑ ያስፈልጋል።

 መፈልፈያዎቹም ጠርዛቸው ስል ሳይሆን ዱልዱም እና ክብ መሆን አለ


በት። ይህም ጫጩቶቹ በሚተራመሱበት ሰዓት እንዳይጎዱ ያደረጋቸዋል።
 ለጫጩት በሚሆን አስፈላጊ መሳሪያ የተሰራ መሆን አለበት።
 የማይታጠብ ከሆነ የሚጣል መሆን አለባቸው።

22
የዶሮዎች
መከለያ

ኢንፍራ ሬድ
አምፓል

ምስል 10. 1 በአግባቡ ታቅዶ የተዘጋጀ የዶሮዎች መከለያ ያለው ማሞቂያ


Figure

በቤቱ ውስጥ ያለው ማሞቂያ ችግር ካጋጠመው ጫጩቶቹ ለየት ያለ ባህርይ


ማሳየት ይጀምራሉ። ለምሳሌ ሙቀት መጠኑ ከመደበኛ ወረድ ያለ ከሆነ
ጫጩቶቹ ማሞቂያው ዙሪያ መከማቸት ይጀምራሉ። ሙቀት መጠኑ ደግሞ
ከፍ ካለ ጫጩቶቹ ተበታትነው ብዙ ውሃ መጠጣት፣ ማለክለክ፣ ክንፋቸውን
መክፈት እና ምግብ መመገብ ይቀንሳሉ።

23
Table 2.
ሠንጠረዥ 1. ለጫጩቶች የሚሆን ተመጣጣኝ የሙቀት መጠን

የጫጩቶች እድሜ ተመጣጣኝ የሙቀት መጠን ((℃)


የመጀመሪያው ሳምንት 32-35

ሁለተኛ ሳምንት 30

ሶስተኛ ሳምንት 26

አራተኛ ሳምንት እና ከዚያ በላይ 23

4-2. በሽታ

ያልተለመዱ የዶሮ በሽታዎች

1. የማሬክ በሽታ

ማሬክ ቫይረስ “ኸረፒስ ቫይረስ” ከሚባሉ ቫይረሶች የሚመድብ ሲሆን በዚህ


ቫይረስ የተለከፉ ጫጩቶች ሊምፎሳይታቸው (በሽታ መከላከያ ህዋሳት) ከፍ
ሲል እንዲሁም ሌሎች በነርቮች እና በውስጣዊ አካል ክፍሎች ላይ እጢ የሚ
ፈጥሩ ገዳይ በሽታዎች (ለምሳሌ የአጥንት በሽታዎች) ተጋላጭ ይሆናሉ።

24
2. የኒውካስትል በሽታ
አስከፊ የሆኑ ለሞት የሚዳርጉ የአዕዋፍ (ዶሮዎች፣ ተርኪዎች፣
ዋኖሶች) በሽታዎች ወደ ሰዎች የመተላለፍ አዝማሚያ አሳይተዋል።
የእስያ ዝርያ (በጣም አደገኛ እና አጣዳፊ) የሆኑ ማለትም ከፍተኛ የሆነ
የደም መፍሰስ የሚያሳዩ፣ ተቅማጥ፣ የነርቭ ምልክቶች፣ ፊት ላይ ያለ እብ
ጠት፣ ከመተንፈሻ አካል ጋር የተያያዘ ፈሳሾች፣ እና ኮንጃንክቲቫይቲስ፣
በተለይም በጃፓን ታይተዋል።

3. የራስ ወገን በላነት

በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ አነስተኛ የወፍ እርባታ ቤቶች ውስጥ


የራስ ዘር በላነት በሽታ ይስተዋላል። ዶሮዎችን ወደራስ ዘር በላነት እንዲ
ያመሩ የሚያደርጓቸው ምክኒያቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።

• የመቆያ ቤታቸው ሙቀት እጅግ በጣም ከፍ ሲል (ተመጣጣኝ ከሆነው


የሙቀት መጠን በላይ ከፍ ሲል)
• ማጎር - ዶሮዎች በብዛት በሚታጎሩበት ወቅት ተፈጥሮአዊና ተለምዶአዊ
ባህርያቸው ውጪ እንዲሆኑ ያደረጋቸዋል
• ለረጅም ሰዓት በከፍተኛ ብርሃን ውስጥ መቆየት
• በምግባቸው ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ማዕድናት እጥረት

25
4-3 አመጋገብ
ሰንጠረዝ 2. ለንግድ ተብሎ የተዘጋጀ የመኖ ውህድ ምሳሌ

ቀለብ (በኪሎግራም) አይነት የዶሮ ዝርያ አይነት ተጨመሪ


መደብ ታዳጊ ጫጩቶች ብሮይለር ብሮይለር መደገፊያዎ
(መጀመሪያ (መጨረሻ ች
) )
ማሽላ ሀይል ሰጪ 47 55 43 47 54 65
የኑግ ኬክ ፕሮቲን 10.55 15 15.6 20 13 19.7
የስንዴ ሚድሊንግ ሀይል ሰጪ 16 13.6 14 19 17 15
የአኩሪ አተር ኬክ ሀይል/ ፕሮቲን 15 12 23 7.5 10 -
ፕሪሚክስ ቫይታሚን 0.5 0.5 0.5 0.5 0.5 -
ላይሲን አሚኖ አሲድ 0.3 0.3 0.25 0.7 0.4 -
ሚትዮኒን አሚኖ አሲድ 0.15 0.1 0.15 0.3 0.2 -
ኖራ ድንጋይ ማዕድናት 7.0 1.0 1 0.4 0.2 -
የአጥንት መኖ ማዕድናት/ፕሮቲን 3 2 2 4.3 4.3 0.3
ጨው ማዕድናት 0.5 0.5 0.5 0.3 0.4
ጠቅላላ 100 100 100 100 100 100

የመኖ ቅልቅል፡ መኖን መቀላቀል ዶሮዎች የመምገብ ዋናው አካል ነው። የተዘጋ
ጀው ቅልቅል መኖ አግባብ ያለው ካልሆነ የመኖው ጥራት የወረድ እና የዶሮዎ
ቹም ምርታማነት የቀነሰ ይሆናል። መኖ በሰው እንዲሁም ያለሰው እገዛ በማሽን
ሊዘጋጅ ይችላል። በዚህ መመሪያ ጥርዝ ከዚህ በኋላ በእጅ የሚዘጋጅ መኖ ቅደ
ም ተከተል እናያለን።

26
•በቅልቅሉ ላይ የተጠቀሱትን እያንዳንዱ ግብዓቶች መሰብሰብ እና ማዘጋ
ጀት
• ለመቀላቀል የምንጠቀምበትን ዕቃ ወይም ግድግዳ ማጽዳት
• እያንዳንዱን ግብዓት በአግባቡ መመዘን
• ለመደባለቅ የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት
• ግብዓቶቹን በቅደም ተከተል መጨመር
• በጎንዮሽ በመግፋት ማደባለቅ
• የተደባለቀውን መኖ በተዘጋጀ ከረጢት ውስጥ መጨመር

አስተውሎት፡ የተደባለቀ የዶሮ መኖ የቆይታ ዕድሜው ሁለት ወር ነው።


ነገር ግን የተዘጋጀው መኖ ርጥበት እና ከመደበኛው የተለየ ነገር ካሳየ ለዶ
ሮዎቹ መመገብ አያስፈልግም።

27
4-4 . ክትባት

ክትባት መንጋው በበሽታ እንዳይጠቃ የምንከላከልበት አንዱ መንገድ ነው።


መንጋውን በጅምላ ከሚያጠቁ እና ከፍተኛ ኪሳራ ላይ ሊዳርጉ ከሚችሉ በሽ
ታዎች (የኒውካስትል በሽታ፣ ፎውል ታይፎይድ፣ ፎውል ፖክስ) ማሳከተብ በ
ጣም አስፈላጊ ነው።

ለመንደር አግልግሎት የሚውል የኒውካስትል በሽታ ክትባት፡ ለኒውካስትል


በሽታ መከላከያ ተብሎ በመንደር ለመንደር የሚሰጥ ክትባት ከ88% እስከ
100% የሚደርስ የመከላከል ብቃት የለውም። ነገር ግን መንደር ውስጥ ለሚ
ረቡ ዶሮውች በNCD በኩል የሚሰጡ ክትባቶች ወጤታማነታቸው የተረጋገ
ጠ ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የቬተርናሪ ተቋም 50 መጠን ያለው
ቫይራል የሆነ ክትባታ አዘጋጅቶአል። ከውጤታማነቱ የተነሳ ከባድ ማቀዝቀ
ዣ ያለው ማጓጓዣ እና መሳቀመጫ ሳይስፈልገው ሊዳረስ ይችላል። ክትባቱ
በአፍ፣ በአይን ጠብታ እና በመረጨት ሊሰጥ ይችላል። ለበለጠ መረጃ በአቅ
ራቢያ ያለ የእንስሳት ሀኪም ማማከር ይቻላል።

28
ሠንጠረዥ 3. ሠንጠረዥ 9. የክትባት መርሃግብር

የክትባት አይነት መደብ ብሮ የአሰጣጥ መንገድ


የማሬክ ክትባት ቀን 1 HB1 ሰብኪዩታኒየስ
NCD HB1 ክትባት ቀን 3 የአይን ጠብታ
ጉምብሮ ክትባት ቀን 3 እና 21 ቀን 7 እና 19 የአይን ጠብታ/ በውሃ
ላሶታ NCD ክትባት ቀን 27፣ 63፣ 112 እና በ3 ወር ቀን 27 የአይን ጠብታ/ በውሃ
ፎውል ታይፎይድ ክትባት ሳምንት 6 እና 12 ሰብኪዩታኒየ
ፎውል ፖክስ ክትባት ከ70 እስክ 90 ቀን በክንፍ መረብ

ለተወሰነ ቦታ የሚሰጥ የክትባት መርሃግብር የአካባቢው ሁኔታ ባማከለ መልኩ


መዘጋጀት ይኖርበታል። ማለትም የአዕዋፍ እርባታ አይነት፣ የተለያዩ የአዕዋፍ
ዝርያ ብዛት፣ ያለው የበሽታ ሁኔታ፣ የክትባቶቹ መገኘት እና አለመገኘት፣ የሌ
ሎች በሽታዎች ሁኔታ፣ ያለው የአቅርቦት እና የበጀት መጠን ይወስኑታል። ስለ
ዚህም ለአዕዋፋቱ ክትባት ከመስጠት በፊት በአቅራቢያ ያለ የእንስሳት ሀኪም
ማማከር ያስፈልጋል።

29
ማጣቀሻ
RDA , KAFACI «chicken management manual-A manual for sma
ll and medium scale chicken producers in Ethiopia » , RDA http:/
/www.rda.go.kr, https://simple.wikipedia.org/wiki/Chicken, https:
//terms.naver.com/, https://en.wikipedia.org/wiki/Andalusian_chi
cken, https://poultrykeeper.com/chicken-breeds/minorca-chicken
s/, https://poultrykeeper.com

- ፎቶዎች -
RDA , KAFACI «chicken management manual-A manual
for small and medium scale chicken producers in
Ethiopia »
Cover Eggs - https://www.indiamart.com/proddetail/kada
knath-poultry-eggs-13971989762.html
Fried egg- https://www.foodnetwork.com/holidays-and-p
arties/articles/easter-eggs-101
Leghorn - https://dominant-cz.cz/produkt/dominant-legh
orn-d-229-2/?lang=en
Andalusian- https://www.mypetchicken.com/chicken-bre
eds/Andalusian-B15.aspx

30
- ፎቶዎች -

Minorca-https://poultrykeeper.com/chicken-breeds
/minorca-chickens/
Cochin- https://poultrykeeper.com/chicken-breeds/c
ochin-chickens/
Brahma- https://poultrykeeper.com/chicken-breeds/b
rahma-chickens/
Plymouth rock- http://m.doopedia.co.kr/mo/doopedi
a/master/master.do?_method=view2&MAS_IDX=1
01013000837333
Rhode Island Red- https://poultrykeeper.com/chick
en-breeds/rhode-island-red-chickens/

31
የዶሮ እርባታ መምሪያ መፅሃፍ

የታተመበት ቀን ታህሳስ, 2018

አሳታሚ ዳይሬክተር, ዶሃም ፔ (ዶ/ር)

ኤዲተር ተመራማሪ, ፓርክ ጆንግኦን

ትርጉም ረድኤት ሳህሉ

ተቋም ኮፒያ ኢትዮጵያ ማዕከል


የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት, ፖ.ሳ.ቁ 2003, አዲስ አበባ፣
አድራሻ
ኢትዮጵያ
ኢሜል ethiokopia@gmail.com

43

You might also like