You are on page 1of 36

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር

የከተሞች የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ

በከተማ ግብርና
የሥጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ

ግንቦት 2009 ዓ.ም

አዲስ አበባ

i
ማውጫ

1. መግቢያ..............................................................................................................................................- 1 -

2. የፓኬጁ ዓላማ......................................................................................................................................- 2 -

3. የፓኬጅ ይዘት/ዓይነቶች...........................................................................................................................- 2 -

ክፍል አንድ..................................................................................................................................................- 3 -

1. ከእርሻና እርባታ አገልግሎት የተወገዱ እንስሳትን የማድለብ ፓኬጅ...........................................................................- 3 -

1.1 የፓኬጅ ጥንቅርና የአሰራር ስልቶች............................................................................................................- 3 -

1.1.1 የሚደልቡ ከብቶችን መምረጥ...........................................................................................................- 3 -

1.1.2 መጠለያ......................................................................................................................................- 4 -

1.1.3 የመኖ ዝግጅትና አመጋገብ................................................................................................................- 5 -

1.1.4 የሚደልቡ ብዛትና የማድለያ ወቅት..............................................................................................- 8 -

1.1.4 ፓኬጁ ተግባራዊ የሚሆንባቸው አካባቢዎች መለየት................................................................................- 8 -

1.1.5 የተሳታፊ መምርጫ መስፈርቶች.........................................................................................................- 9 -

1.1.6 የግብዓት አቅርቦት፣ ሥርጭትና የግብይት ሁኔታ.....................................................................................- 9 -

ክፍል ሁለት...............................................................................................................................................- 13 -

1. ከወተት ከብት እርባታ ጣቢያዎች የሚገኙ ክልስ ወንድ ጥጆችን (Dairy Beef) የማሳደግ ፓኬጅ.............................- 13 -

1.1 የፓኬጅ ጥንቅርና የአሰራር ስልቶች..........................................................................................................- 13 -

1.1.1 የሚያድጉ ጥጆች አመራረጥ............................................................................................................- 13 -

1.2. የመኖ ዝግጅትና የአመጋጋብ ስልት.....................................................................................................- 14 -

1.3 የመጠለያ አሰራና መሟላት ያለባቸው ቁሳቁሶች...........................................................................................- 16 -

1.4 ለስጋ የሚያስፈልጉ ጥጆችና የማሳደጊያ ወቅት.............................................................................................- 18 -

1.5 ፓኬጁ ተግባራዊ የሚሆንባቸው አካባቢዎች...............................................................................................- 19 -

1.6 የፓኬጅ ተሳታፊ መምረጫ መስፍርቶች....................................................................................................- 20 -

1.7 የግብዓት አቅርቦትና ሥርጭትና የግብይት ሁኔታ.........................................................................................- 20 -

ክፍል ሶስት................................................................................................................................................- 23 -

i
1. የበግ/ፍየል ሥጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ.......................................................................................................- 23 -

1.1 የፓኬጅ ጥንቅርና የአሰራር ስልቶች..........................................................................................................- 23 -

1.1.1 የሚደልቡ በጎች/ፍየሎች አመራረጥ...................................................................................................- 23 -

1.1.2 የእንስሳት መኖ ምንጮች፣ዝግጅትና አመጋገብ፣....................................................................................- 26 -

1.1.3. የሚደለቡ በጎች/ፍየሎች ብዛትና የማድለቢያ ወቅት..............................................................................- 29 -

1.1.5 የፓኬጅ ተሳታፊ መምረጫ መስፍርቶች......................................................................................- 30 -

1.1.5 የግብዓት አቅርቦትና ሥርጭትና የግብይት ሁኔታ..................................................................................- 30 -

ክፍል አራት................................................................................................................................................- 31 -

1. የግብዓት አቅርቦትና ሥርጭትና የግብይት ሁኔታ...........................................................................................- 31 -

2. የፓኬጁ አተገባበር አቅጣጫ....................................................................................................................- 32 -

3. ስልጠና.........................................................................................................................................- 32 -

4. መረጃ አያያዝ...................................................................................................................................- 32 -

5. ክትትልና ድጋፍ.................................................................................................................................- 33 -

ii
1. መግቢያ
አገራችን ሰፊ የእንስሳት ሀብት ያላት ሲሆን የኢትዮጵያ ማእከላዊ የእስታሰቲክስ ኤጀንሲ (CSA,2008) ያወጣዉ መረጃ
እንደሚያመለክተዉ 57 ሚሊየን የዳልጋ ከብት፤ 28 ሚሊየን ፍየል፤29.8 ሚሊየን በግ እና 21.9 ሚሊየን ግመል የሚገመት
ቢሆንም የነፍስ ወከፍ ምርታቸው ግን በጣም ዝቅተኛ ሆኖ ይታያል፡፡ በዚህም ምክንያት የሀገር ውስጥ የሥጋ ፍጆታን
ማሟላት ካለመቻሉም በላይ የሚመረተው ስጋ ጥራቱን የጠበቀ ባለመሆኑ ከሀብቱ ሊገኝ የሚችለው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም
እየተገኘ አይደለም፡፡ ለዕርድ የሚቀርብ የሀገራችን የዳልጋ ከብት አማካይ የሥጋ ምርት 107 ኪ.ግ፣ በግ 13 ኪ.ግ እና ፍየሎች
11 ኪ.ግ ብቻ ሲሆን ከሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች ጋር እንኳ ሲወዳደር ዝቅተኛ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ለዚህም መንስዔ ከሆኑት የቴክኒክ ችግሮች መካከል በማድለብ ስራ የሚሳተፉ ፓኬጁን በተሟላ መንገድ ተግባራዊ
አለመተግበር፣ የሚደልቡ እንስሳት ወደ ማድለብ ከማስገባቱ በፊት በቂ ቅድመ ዝግጅት አለማድረግ፣ በቂ መኖ
አለማቅረብና የተሻሻለ አመጋገብ ሥርዓት አለመከተል፣ በቂ እንስሳት ጤና አገልግሎት አለመስጠት፣ የሚደልቡ እንስሳትን
በአግባቡ አለመምረጥ፣ ወዘተ… የሚጠቀሱ ሲሆን ተቋማዊ ከሆኑት ደግሞ ለፓኬጅ ተሳታፊዎችና በስጋ ምርት ላይ
ለሚሰማሩ ድጋፍ አለማድረግ፣ በፓኬጅ ተሳታፊዎችን እንደ ፍላጎታቸውና አቅማቸው መደገፍ አለመቻል፣ የተሻሻሉ
ቴክኖሎጂዎች በመንግስትም ሆነ በግል ባለሃብቶች ከውጭ በማስገባት ማሰራጨት አለመቻል፣ የስጋ ምርት ጥራት
አለመኖር፣ በቂ የብድር አቅርቦትና ሥርጭት አለመኖር ወዘተ… ዋና ዋናዎቹ ናቸው:: በመሆኑም ይህን ሁኔታ በማሻሻል
ተጠቃሚው ህብረተሰብም ሆነ ሀገሪቱ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ እንደ አካባቢው ሁኔታ፣ በዘርፉ በሚሳተፉ ግለሰቦች አቅምና
የመፈፀም ብቃት ላይ በመመስረት የተሻለ አያያዝና የአመጋገብ ዘዴን መቀየስ ተገቢ የሆናል፡፡

ስለሆነም የከተሞችን መስፋፈትና የነዋሪውን የእለት ፍላጎት እድገት ከግምት በማሰገባት የስጋ ምርት አቅርቦት በብዛትና
በጥራት እንዲሻሻል በስፋት መሰራት ይገባዋል፡፡ በተለይም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና በዘርፉ የስራ እድል ፈጠራን
ለማጠናከር የተሸሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀምና ምርታማ የአመራረት ስርአትን በመከተል በመስኩ መሰማራት
ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች የሚረዳ አማራጭ አነስተኛና ከፍተኛ የዳልጋ ከብትና በግ/ፍየል ስጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ
ተዘጋጅቷል፡፡

1. የፓኬጁ ዓላማ

የዳልጋ ከብትና በግ/ፍየል ሥጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፤


 የተሸሻለ የአመራረት ዘዴን በመጠቀም የስጋ ምርትን መጠንና ጥራን በመጨመር ለከተማ ነዋሪው ማቅረብ፤
 የተሳታፊውን የገቢ ምንጭ በማዳበር ኑሮው እንዲሻሻል ማድረግ፤
 በዘርፉ ስራ እድል እንዲጠናከር ለማድረግ፤
1
2. የፓኬጅ ይዘት/ዓይነቶች

የዳልጋ ከብት፣ በግና ፍየል ስጋ ምርት ቀደም ሲል በከተሞች በአነስተኛ ቴክኖሎጂና በዝቅተኛ ድጋፍ ብዙም ትኩረት
ሳይሰጠው ሲካሄድ መቆየቱ ያታወቃል፡፡ ሆኖም በሀገራችን እየተመዘገበ ባለው እድገት ምክንያት በከተሞች ያለው የስጋ
ፍላጎት በብዛትም ይሁን በጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ በመሆኑ የስጋ ምርት ለማሻሻል የሚያስችሉ የከተማ
ግብርና ልማት ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል አስፈላጊ ነው፡፡

በከተሞች የሚገኙ አድላቢዎች የተሸሻሉ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችና በመጠቀም የስጋ ምርትን በብዛትና በጥራት
በማሳደግ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የሚመጣውን የነዋሪዎች ፍላጎት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ለማርካት እንዲችሉ
አማራጭ ፓኬጆች ማዘጋጀት ያስፈልግል፡፡ ይህ የስጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ ተግባራዊ የሚደረገው የተለያዩ የከተማ
አካባቢዎችን የአመራረት ስልቶችን መሰረት በማደረግ ይሆናል፤ በዚህ ፓኬጀ ደልበው የሚወጡ እንስሳት በአብዛኛው
ጥራትንና የከተሞችን የገበያ ፍላጎት መሰረት በማድረግ የሚከናወን ይሆናል፡፡

በዚህ ፓኬጅ ተሳታፊ የሚሆኑት የግል አድላቢዎች፣ የተደራጁ ቡድኖች፣ ማሀበራትና ኢንተፕራይዞች ምርቶቻቸውን
ከሚረከቡ አካላት ጋር በሚገቡት የውል ሥምምነት ወይም በቀጥታ ለተጠቃሚው ለማቅረብ በሚያሰችል መንገድ
የዳልጋ ከብትና በግ/ፍየል ላይ በማተኮር በአብዛኛው ከ 90-120 የማድለቢያ ቀናት የሚካሄድ ይሆናል:: የሚደልቡ
እንስሳት ቁጥር አድላቢው እንደሚኖረው የገንዘብ አቅም የመኖ አቅርቦትና የገበያ ምቹነት መሰረት በማድረግ በዓመት
ከ 3-4 ዙሮች ሊከናወን ይችላል፡፡ በአንድ ዙር ለአነስተኛ አድላቢዎች ቢያንስ 3 የዳልጋ ከብቶችንና 6 በጎች/ፍየሎች፣
ለመካከለኛ ደረጃ አድላቢዎች ደግሞ ቢያንስ 15 የዳልጋ ከብቶችንና 30 በጎች/ፍየሎችና ከፍተኛ አድላቢዎች ደግሞ
ቢያንስ 50 የዳልጋ ከብቶችና 100 በጎች/ፍየሎችን ሊያደልቡ ይችላሉ፡፡ በፓኬጁ የታቀፉ ተሳታፊዎች የማድለቢያው
ወቅት በሃገራችን የሚታወቁ የተለያዩ በዓላትንና ሌሎች የገበያ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ እንስሳት ለገበያ
የሚያቀርቡበትን ስልት መንደፍ ያስፈልጋል፡፡

ስለሆነም ፓኬጁ አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ሊያሳትፍ የሚችል የተለያዩ ቴከኖሎጂዎች ተጠቅመው ሥጋን
በማምረት የከተማ ነዋሪውን የስጋ ፍላጎት በተወሰነ መልኩ ለመደገፍ ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ከዘርፉ የሚገኘውን
ጠቀሜታ ማጎልበት ያስፈልጋል:: በመሆኑም የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የዳልጋ ከብት የማድለብ ስራ
ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ሶስት አማራጭ ፓኬጆች ተዘጋጅተው ቀርበዋል::

ክፍል አንድ

1. ከእርሻና እርባታ አገልግሎት የተወገዱ እንስሳትን የማድለብ ፓኬጅ


ይህ አማራጭ ፓኬጅ ትኩረት የሀገር ውስጥ የገበያ ፍላጎት ስብ የበዛበት ስጋ በመሆኑ ሲያርሱ የቆዩ ወንድ ከብቶችን
በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ሃይል ሰጪ መኖዎችን በመመገብ ለማድለብ የሚያስችል ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ፓኬጅ
በእርሻ ስራ አገልግሎት የሰጡ በሬዎችን በአንድ በተወሰነ ቦታ አሰባስቦ የተሸለ አያያዝና አመጋገብ በመጠቀም በአጭር
ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የስጋ ምርት እንዲሰጡ ለማድረግ የተዘጋጀ ፓኬጅ ነው::

2
1.1 የፓኬጅ ጥንቅርና የአሰራር ስልቶች

1.1.1 የሚደልቡ ከብቶችን መምረጥ

ሀ. ዝርያ

ለዚህ ፓኬጅ በአካባቢው የሚመረጡ የሀገር ዝርያ በሬ( እርሻ ያላረሱም ሊሆኑ ይችላሉ) መጠቀም የሚቻል ቢሆንም
ከጥናቶች ለመረዳት እንደተቻለው የሆሮ፣ የቦረና፣ የደንከልና የፎገራ ዝርያዎችን መጠቀም የተሸለ ውጤት ሊያስገኝ
ይችላል፡፡ ከላይ በዝርዝር የቀረቡትን ዝርያዎች በሚገኙበት አካባቢ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቢሆንም በሌሎች አካባቢዎች
በገበያ የሚገኙትን በመረጣ መጠቀም ይቻላል፡፡

ለ. ዕድሜ

ለማድለብ ስራ የሚመረጡ የዳልጋ ከብቶች እድሜ እድገታቸውን የጨረሱ ሆነው በጣም ያላረጁ መሆን የገባቸዋል፡፡
ስለዚህ ለዚህ ፓኬጅ እድሜ ከ 4-8 ዓመት ተስማሚ ይሆናል፡፡ የዳልጋ ከብቶች እድሜ ጥርሳቸውን በመመልከት መገመት
ይቻላል፡፡

የፊት ጥርስ ብዛት እድሜ


2 ከ 1.5 – 1.75 ዓመት
4 ከ 2.0 – 2.5 ዓመት
6 ከ 3.0 – 3.5 ዓመት
8 ከ 3.5 – 4.00 ዓመት
ሐ. የሰውነት አቋምና ክብደት

የሚደልቡ ከብቶች የስጋ ምረት መያዝ ችሎታቸው በሰውነታቸው አቋም (frame) ስለሚወሰን የሚመረጡ ከብቶች
ቁመትና ርዝመታቸው በአይን ግምት ሲታዩ ከሌሎች የላቀ ቁመትና ርዝመት ኖሮዋቸው አጥንተ ሰፋፊ መሆን
አለባቸው፡፡ ለማድለብ የሚገዙ ከብቶች ክብደታቸው ከ 250 ኪ.ግ ያላነሱ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ደልበው ሊወጡ
ስለሚችሉ የማድለቡን ሥራ ፈጣንና ትርፋማ ያደርገዋል፡፡

መ. ጤና

የእንስሳቱን ንቃትና እንቅስቃሴ በመየት በአይን የሚታይ የጤና ችግር የሌለበት መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡
ግዢው በእንስሳት ጤና ባለሙያ ቢታገዝ የተሸለ ይሆናል፡፡ከብቶቹም ከተገዙ በኋላ በጤና ባለሙያዎች መሰጠት ያለበት
ድጋፍ፡-

 በአካባቢው በተደጋገሚ ለሚከሰቱ በሽታዎች ክትባት መስጠት፤


 ለውስጥና የውጭ ጥገኛ መድሃኒት መስጠት
 ከብቶች ደልበው እስከሚወጡ ድረስ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮች ህክምና እንደአስፈላጊነቱ መስጠት ያስፈልጋል::

3
1.1.2 መጠለያ
ለሚደልቡ ከብቶች የሚሰራ መጠለያ እንደ አየር ንብርቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ የማድለቡ ሰራ በሚካሄድበት አካባቢ በሚገኝ
የአካባቢ ቁሳቁስ የተሰራ መጠለያ በማዘጋጀት የሚደልቡ ከብቶችን ከፀሀይና ከብርድ እንዲከለሉ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
ስለሆነም ለሞቃታማና ቀዝቃዛማ አካባቢዎች የሚሰራው በረት የውጭ አጥር ዙሪያው ቢቻል በቆርቆሮ ወይም
በእንጨት ቢሰራ ጥሩ ነው፡፡ እንደ ከብቱ ዝርያና የአየር ሁኔታ የሚለያ ሆኖ ለአንድ የአገረሰብ ዝርያዎች ከ 1.75 -
2.25 ካ.ሜ የሚያስፈልግ ሲሆን ለውጭ ዝርያዎች ወይም ዲቃላዎች ከ 2.5-3.5 ካሜ ቦታ ያስፈልጋል፤ በውስጡም
የመመገቢያና ውሃ መጠጫ ሊኖሩት ይገባል፡፡ በረት በሚሰራበት ጊዜ ፍሳሹ በቀላሉ ሊወገድ እንዲችል 2-5% ተዳፋነት
ሊኖረው የገባል፡፡ የበረቱ ወለል በተለይ በመመገቢያው አካባቢ እንዳይጨቀይ 2 ሜትር ርዝመት ያለው የድንጋይ ወይም
የኮንክሪት ወለል መሰራት አለበት፡፡

የማድለብ ሥራ የሚካሄድበት አካባቢ ሽታን እንዳያስከትል ሰው ከሚኖርባቸው አካባቢዎች ራቅ ብለው ሊሰሩ ይገባል፡፡
በበረት ውስጥ ለሚደልቡ ከብቶች የፍሳሽ መውረጃ ማዘጋጀት ይገባል፡፡ የፍሳሽ ማጠራቀሚያና የእበት ማስወገጃ
ለብቻው ተቆፍሮ እነዲዘጋጅ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ማንኛውም ፍሳሽ 40 ሴ.ሜትር ቦይ ተሰርቶለት ወደ ተቆፈረው
ጉድጓድ እንዲሄድ መደረግ ይኖርበታል፡፡

በተጨማሪም ቢሮ፣ የሞላሰስ ማስቀመጫ ገንዳ ፣የህክምና መስጫ ማጎሪያ (crush)፣ የተመጣጠነ መኖ ማስመጫ
መጋዘን ያስፈልጋል፡፡

ለ 50 ከብቶች የመጠለያ አሰራር (ለምሳሌነት የቀረበ)

የግንባታው ዓይነት ለሞቃት አካባቢ ለቀዝቃዛ አካባቢ


በረት ለ 50 ከብቶች /50x 7 / = 350 ካሬ.ሜትር ለ 50 ከብቶች (50x4m2)=
ክፍት በረት ሆኖ ከዚህ ውስጥ 11x7= 77 ካሬ (200 m2) 3 ሜትር ቁመት
ሜትር/ ጥላ ያለው ያለው 3 ጎን ግድግዳና ጣርያ
ያለው
የመመገቢያ ገንዳ 25 x 0.04 x0.4 m ትር ኩብ ሁለት ገንዳዎች 25 x0.4 x0.ሜትር ኩብ ሁለት
ገንዳዎች
የውሃ መጠጫ ገንዳ 4x0.5 x0.4 m ትር ኩብ ሁለት ገንዳዎች 10 x0.4 x0.4 ሜትር ኩብ
አንድ ወጥ ገንዳ
የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ 5x 0.5 x0.4 ሜትር ስፋትና ጥልቀት ያለው 0.5 x0.5 ሜትር ስፋትና
ጥልቀት
የመኖ መጋዘን/ 6 x 6 ካሬ ሜትር 6 x 6 ካሬ ሜትር
የተመጣጠኘ/
የሞላሰስ ማጠራቀሚያ 2000 ሊትር ሞላሰስ የሚየዝ ´ 2000 ሊትር የሚየዝ
ገንዳ
ቢሮ 4 x4 ካሬ ሜትር 16 ካሬ ሜትር
የህክምና መስጫ 7 x0.4 x 0.05 ሜትር ኩብ 7 x 0.4 ካሬ ሜትር`
ማጎሪያ

4
አጥር የውጭ 140 ሜትር 140 ሜትር
ውስጥ ለውስጥ መንገድ 4 ሜትር ስፋት 4 ሜትር ስፋት

1.1.3 የመኖ ዝግጅትና አመጋገብ

1.1.3.1 የመኖ ዓይነቶችና አዘገጃጀት

መኖ ለማድለብ ስራው ከሚያስፈልገው ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ በመሆኑ የማድለብ ስራን ውጤታማ ለማድረግ
የሚዘጋጀው መኖ ስራው በሚካሄድበት አካባቢ በስፋት የሚገኝና ርካሽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም በዚህ ስራ ላይ
የሚሰማሩ ግለሰቦች ካካባቢያቸው የሚገኘውን መኖ ሊጠቀሙበት የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይኖርባቸዋል፡፡

በበዘመናዊ መንገድ የዳልጋ ከብት ማድለብ ስራ የመኖ ምንጭ በእህል፣ በተረፈ ሰብል፣ በሳርና በኢንዱስትሪ ውጤቶች
ላይ መሰረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡ በዘመናዊ መልኩ የዳልጋ ከብቶችን ለማድለብ ጥቅም ላይ የሚውሉ የመኖ
ዓይነቶች concentrates እና Roughages በመባል በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ሊመደቡ ይችላሉ፡፡

ሀ. የተመጣጠነ መኖ (concentrate)

የተመጣጠነ መኖ በሀይል ሰጪና በገንቢ ንጥረ ነገር መኖዎች የዳበሩና የአሰሩ (Fiber) መጠናቸው አናሳ የሆኑ ናቸው፡፡
በመሆኑም የተመጣጠነ መኖ እንደየሁኔታው ከአጠቃላይ ፍጆታው ከ 60-90% ሊካተት ይችላል፡፡ የመኖ አቅርቦቱም
ለዚሁ ስራ ተቀነባብሮ በሽያጭ ገበያላይ ከሚቀርብ ወይም በሚሰጣቸው ስልጠና መሰረት በተመጣጣኝ ዋጋ ሊዘጋጅ
ይችላል፡፡ ለዚህም ከበቆሎ፣ ከፉርሽካ፣ ብሪወርስ ግሬይን፣ ፋጉሎ፣ ሞላሰስ …..ወዘተ በጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፡፡

ለ. ደረቅ መኖ (Roughages)

እነዚህ የመኖ ዓይነቶች ከፍተኛ የአሰር (fiber) መጠን ያላቸውና በአብዛኛው የሳር ድርቆሽና የሰብል ተረፈ ምርቶች
ሲሆኑ እነዚህ መኖዎች በሚደልቡ የከብቶች መኖ ውሰጥ የሚገቡት የመኖ ብዛትን ለመጨመር፣ ለትክክለኛ የመኖ
መብላላት እንዲረዱና መጠነኛ የሆነ የገንቢና የሃይል ሰጪ ንጥረ መኖ ጠቀሜታ ይሰጣል፡፡

ውሃ - ለሚደልቡ ከብቶች በጣም አስፈላጊ ስለሆነ በየቀኑ ንጹህ ውሃ ከመጠጫ ገንዳቸው መለየት የለበትም፡፡

1.1.3.2 የመኖ አዘገጃጀት አማራጮች

በዚህ ፓኬጅ ለሚደልቡ የዳልጋ ከብቶች አድላቢዎች የተለያዩ የመኖ ዓይነቶቸን በመጠቀም የተመጣጠን መኖ አዘገጃጀት
አማራጮች ከአካባቢው በሚገኙ የመኖ ምንጮች ሊዘጋጁ የሚችሉትን መርጠው መጠቀም ይችላሉ፡፡ በሚቀጥለው
ሰንጠረዥ አማካይ ክብደታቸው 300 ኪግ የሆኑና በቀን 750 ግራም የክብደት ጭማሪ ሊያስገኙ የሚችሉ የተለያዩ
አማራጮች ተዘርዝረዋል፡፡ስለሆነም የቀረቡትን የመኖ ቅንብር አማራጮችን በማየት አድላቢው የሚያዋጣውን
ሊጠቀም ይችላል፡፡

5
ለመነሻነት ለሚደልቡ ከብቶች የተዘጋጀ የመኖ አማራጭ/መነሻ ክብደት 300 ኪግ. የቀን ጭማሪ 750 ግራም)

መኖ 1 መኖ 2 መኖ 3 መኖ 4

የመኖ ዓይነት የመኖ የመኖ የመኖ የመኖ የመኖ የመኖ የመኖ የመኖ ዓይነት
ዓይነት በ ዓይነት ዓይነት በ ዓይነት ዓይነት በ ዓይነት ዓይነት በ በኪ.ግ.
% በኪ.ግ. % በኪ.ግ. % በኪ.ግ. %

ድርቆሸ 30 2.4 20 1.6 25 2.0 -- --

የበቆሎ እህል 20 1.7 -- -- 25 2.1 20 1.6

ጭድ -- -- 30 2.6 -- -- 20 1.7

የገብስ ገለባ -- -- -- -- -- -- -- --

ፉርሽካ 2 0.5 15 1.3 20 1.7 20 1.7

ፉርሽኬሎ 18 1.5 10 0.8 -- -- 15 1.3

የደረቀ የቢራ አተላ -- -- 10 0.8 -- -- -- --

የዘይት ጭማቂ/ ፋጉሎ 30 2.4 -- -- 10 0.8 5 0.4

ሞላሰስ -- -- 15 1.5 -- -- 20 2.4

የስናር በእህል መልክ -- -- -- -- 10 0.8 -- --

ጓያ በእህል መልክ -- -- -- -- 10 0.8 -- --

ድምር 100 8.7 100 8.6 100 8.2 100 8.7

1.1.3.3 የመኖ አመጋገብ ስልት

አድላቢው የተፈለገውን ውጤት እንዲያገኝ አዋጭ የሆኑ የአመጋገብ ስልቶችን በመጠቀም ከብቶቹ ደልበው
ሚወጡበትን ጊዜ መወሰን ይቻላል፡፡ ይህም በመኖው ዓይነት፣ መጠንና ጥራት ይወስናል፡፡

የሚደልቡ የዳልጋ ከብቶች ከገበያ ተገዝተው ወደ ድለባው በሚገቡበት ወቅት አብዛኛውን ጊዜ ለተመጣጠነ መኖ አዲስ
ስለሚሆኑ ቀጥሎ በተመለከተው ዘዴ መሰረት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የድለባ ወቅት ቀስ በቀስ እየጨመረ እንዲሄድ
በማድረግ አዲስ ለማድለብ የሚገቡት ከብቶች የማድለቢያ መኖውን እንዲለምዱት ማድረግ ይገባል፡፡

6
 በመጀመሪያ ቀን ድርቆሽ ብቻ መመገብ፤
 ከ 2 – 4 ኛው ቀን የሳር ድርቆሽና 10 - 30% የተመጣጠነ መኖ መመገብ፤
 ከ 5 – 14 ኛው ቀን 70% ማንኛውንም ሳር ወይም ተረፈ ምርትና 30% የተመጣጠነ መኖ
መመገብ፤
 ከ 15 – 21 ኛው ቀን 30% ሳር ወይም ተረፈ ምርትና 70% የተመጠጠነ መኖ መመገብ፤
 ከ 22 ኛው ቀን እስከሚሸጡ ድረስ 10% ሳር ወይም ተረፈ ምርትና 90% የተመጣጠነ መኖ
መመገብ፤

1.1.4 የሚደልቡ ብዛትና የማድለያ ወቅት

የገበያ ሁኔታና የመኖ አቅርቦት አስተማማኝ በማድረግ አንድ የዚህ ፓኬጅ ተጠቃሚ መአመት ሶስት ዙርና በአንድ ዙር
ለአነስተኛ አድላቢዎች ቢያንስ 3-6፣ ለመካከለኛ ደረጃ አድላቢዎች ደግሞ ቢያንስ 15-20፣ ከፍተኛ አድላቢዎች ደግሞ
ቢያንስ 50-100 በሬዎችን ከአካባቢው በማሰባሰብ ሊያደልብ ይችላል፡፡ በአንድ የድለባ ጊዜ ከ 90120 ቀናት ባለው ጊዜ
አድልቦ ለገበያ የሚያቀርብበትን ስልት መንደፍ ይኖርበታል፡፡ አድላቢው የማድለብ መርሃ ግብሩን ከህዝብ በዓላት ጋር
በማያያዝ ቢሰራ የተሸለ ገበያ ሊያገኝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የዘመን መለወጫ፣ ገና፣ ፋሲካ፣ አረፋና የመውሊድ በዓላትን
መሰረት በማድረግ ቢከናወን አመርቂ ውጤት ሊያገኝ ይችላል፡፡

አድላቢው ለማድለብ በሚወስንበት ጊዜ በየትኛው በዓል ከብቶቹን እንደሚሸጥ በቅድሚያ ለማወቅ እነዲያስችለው
በየአካባቢው ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል የጊዜ ሰሌዳ በማዘጋጀት በአንድ ወቅት ከአንድ በላይ በዓላት ሊኖሩ ስለሚችል
አድላቢው ይህን በመገንዘብ ከተሰጡት የማድለቢያ ወቅት አማራጮች የተስማማውን በመምረጥ ሊያደልብ ይችላል፡፡

1.1.4 ፓኬጁ ተግባራዊ የሚሆንባቸው አካባቢዎች መለየት

ይህ ፓኬጅ ተግባራዊ የሚደረግባቸው አካባቢዎች በቅድሚያ የሚከተሉትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ መምረጥ
ያስፈልጋል፡፡

ሀ. የአየር ንብረት

የማድለብ ስራ ውጤታማ ይሆን ዘንድ ተስማሚ የሆነ የአየር ንብረት መምረጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ በጣም ቀዝቃዛ
ወይም በጣም ሙቀት የሌለው አካባቢ ቢሆን ይመረጣል፡፡ የአየር ንብረቱ በጣም ቀዝቃዛ ከሆነ እነስሳቱ የሚመገቡትን
ምግብ ለብርድ መከላከያ ስለሚያውሉት የሚፈለገውን የክብደትና የስብ መጠን ሊያከማቹ አይችሉም፡፡ በአንጻሩም
አካባቢው ሞቃት ከሆነ እንስሳቱ በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን ሙቀት ከውጭ ካለው ሙቀት መጠን ለማመጣጠን
ስለሚገደዱ የምግብ ፍላጎታቸው ይቀንሳል፤ በዚህም ምክንያት የሚፈለገውን የክብደት ጭማሪ ሊኖራቸው አይችልም፡፡
ስለዚህ የማድለቢያው አካባቢ በቀዝቃዛ ቦታዎች ከሆነ ብርድን ሊከላከል በሚያስችል ቦታ እንዲሆንና ሞቃት በሆነ
አካባቢ ደግሞ እንስሳት የፀሃይ ሙቀትን ለመከላከል ከአካባቢው ከሚገኝ ቁሳቁስ ጥላ ሊሰራላቸው ይገባል፡፡ በአጠቃይ ግን
የማድለብ ፓኬጅ ውጤታማ ለማድረግ መካከለኛና ትንሽ ሞቅ ያለ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎችን መርጦ ማካሄድ
ይመረጣል፡፡

ለ. የመሬት አቀማመጥ
7
ማድለቢያው የሚቋቋምበት ቦታ የመሬት አቀማመጥ ፍሳሽን ለማስወገድ በቂ ተዳፋትነት ያለውና በከባድ ንፋስ
የማይጠቃ መሆን አለበት፡፡

ሐ. በቀላሉ ሊስፋፋ የሚችል መሆኑ

በዚህ ፓኬጅ የሚሳተፉ አድላቢዎች የማድለቡ ሥራ ባላቸው አቅም ሥራውን በአነስተኛ ቦታ ጀምረው አስፈላጊ ሆኖ
ሲገኝ በቀላሉ ሊስፋፋ እንዲችል ሆኖ ቢሰራ ተመራጭነት ይኖረዋል::

መ. አስፈላጊ አገልግሎቶች በቅርብ የሚገኙበት

እንስሳት ጤና አገልግሎት፣ የውሃ፣ ገበያ፣ ትራንስፖርት፣ መብራ፣..ወዘተ በቅርበት ሊገኝ የሚችልበት አካባቢ ቢሆን
ይመረጣል፡፡ የመኖ አቅርቦት በዋጋ፣ በመጠንና በጥራት በአስተማማኝ ሁኔታ ሊገኙ የሚችሉበትና በቂ የአግሮ
ኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶችና የመኖ ማደራጃዎች የሚገኙበትአካባቢ መሆን ይኖርበታል፡፡

1.1.5 የተሳታፊ መምርጫ መስፈርቶች

የዚህ ፓኬጅ ተሳታፊዎች በሚከተሉት መስፈርቶች መሠረት መመረጥ ይኖርባቸዋል፡፡

 ለማድለብ ስራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው፤


 ቢቻል ቀደም ሲል በማድለብም ሆነ በእንስሳት እርባታ ልምድ ያለው፤
 የሚሰጠውን ምክርና የስራ ዘዴ ተቀብሎ ለመተግበር ፈቃደኛ የሆነ፤
 ለማድለብ ስራው በቂ ቦታ ያለው፤

1.1.6 የግብዓት አቅርቦት፣ ሥርጭትና የግብይት ሁኔታ

ፓኬጁን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች /እንስሳት፣ መኖ፣ ክትባትና መድሃኒት/ በመሰረታዊነት በአድላቢው
አካባቢ ከሚገኙ ጥሬ ዕቃዎች በአነስተኛ ወጪ የሚገኝበትን ሁኔታ ማመቻቸተ ያስፈልጋል፡፡ ድርቆሽና የሰብል ተረፈ
ምርቶችን በማሰባሰብ ለአድላቢዎች በመሸጥ ገቢ ማግኘት የሚቻል በመሆኑ በዚህ በኩል በከተሞች ዙሪያ የሚገኙ አርሶ
አደሮች ተሳታፊ በመድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል፡፡ በቂ የእንስሳት ጤና አገልግሎት ለመስጠት በየደረጃው
የሚገኙ ክሊኒኮችን በባለሙያ፣ በውስጥ ቁሳቁስ፣ በመድሃኒትና በክትባት አቅርቦት ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን
የግል ጤና ተቋማትን አቅም በማጎልበት አገልግሎቱን ማሻሻል ይገባል፡፡

ይህ ፓኬጅ የሃገር ውስጥ ገበያን ትኩረት ያደርግ ስለሆነ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ገበያው የሚፈልገውን
ለማምረት ስጋ በብዛትን በጥራት የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪም በእርሻ ስራ የቆዩ ያገለገሉ ከብቶችን ለተወሰነ ጊዜ
ከፍተኛ ኃይል ሰጨ መኖ በመመገብ የሚገኘውን ስብ የበዛበት ሥጋ በሚኖረው ፍላጎት መሰረት የማድለብ ስራው
እነዲከናወን ማድረግ ይቻላል፡፡

ሊገኝ የሚችል ምርት

8
 በዚህ ፓኬጅ አሰራር ክብደቱ 300 ኪግ የሚመዝን በሬ በ 90 ቀን ውስጥ 68 ኪግ በመጨመር ወደ 368 ኪግ ከፍ
ይላል፤
 በዚህ አሰራር በ 90 ቀን ክብደት ጭማሪ ባሻገር ጤንነቱ የተሟላና የስጋ ጥራቱም የገበያውን ፍላጎት የሚያሟላ
ከብት ይገኛል፤
 በአመት እስከ 60 ኩል ወይም በቀን 4 ጥፍጥፍ ኩበት የሚደርስ ደረቅ ለማዳበሪያ ወይም ለማገዶ የሚሆን ፍግ
ይገኛል፤
የአዋጭነት ስሌት

 በዚህ ፓኬጅ አዋጭነት ስሌት የተሰራው 50 ከብቶችን በአንድ ጊዜ በ 90 ቀናት ማድለብ የሚችል አድላቢ እንደ
ምሳሌ በመውሰድ ስለሆነ ይህንን ምሳሌ በመውሰድ በተለያየ አቅም የሚስማማ የአዋጪነት ስሌት መስራት
ይቻላል፡፡

 ለማድለብ የሚገዙት ከብቶች ክብደት 300 ኪግ እንደሚሆን ዋጋቸውም 6500 ብር በከብት እንደሚሆንና
በድለባ ወቅት እያንዳንዱ ከብት 700 ግራም ጭማሪ እንደሚያሰዩ ተገምቷል፡፡

 አድላቢው በአመት 3 ጊዜ የማድለብ ስራውን እንደሚያከናውንና በአጠቃላይ 150 ከብቶችን በዓመት


እንደሚያደልብ ታሳቢ ተወስዷል፡፡

የአዋጭነት ስሌቱም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የአዋጭነት ትንተና

ሀ. የወጪ ታሳቢዎች

1. የከብት ግዢ

- አማካኝ የመነሻ ክብደት 300 ኪግ

- የአንድ በሬ ዋጋ 6500 ብር

- በአመት ውስጥ ጠቅላላ የከብት ዋጋ 6500*5*3

- ጠቅላላ ወጪ - 97500

2. የመኖ ወጪ

የመኖ ዓይነት % የቀን ፍጆታ በኪግ የመኖ ዋጋ በኪግ ለ 50 ከብቶች ለ የአመት የመኖ
በብር 90 ቀን የሚበቃ ወጪ በብር
በከል

ድርቆሽ/ገለባ 40 3.3 0.60 14.85 2673

ፉርሽካ 20 1.7 3 7.65 1327

ፉርሽኬሎ 15 1.3 2.5 5.85 5265

9
ፋጉሎ 5 0.4 5. 1.8 2700

ሞላሰስ 20 2.4 0.85 10.8 2754

ድምር 100 40.95 14719

3. የጤና አገልግሎት ወጪ 50 ብር በከብት ለ 90 ቀናት

 ጠቅላላ ወጪ = 50*5*3 = 750 ብር

4. ዲፕሪሲየሽን /የእልቀት/ ታሳቢዎች

ዓመታዊ የእልቀት መጠን


ዓይነት ዋጋ በብር የእልቀት መጠን በ
በብር

በረትንና የተለያዩ 21040 5 1052


ህንጻዎች

የስራ መሳሪያዎች 1200 10 120

ድምር 22240 1172

የሰራተኛ ደሞዝ

 ሁለት የቀን ሰራተኛ 50 ብር * 90 ቀን * 1 = 13500


 የስራ ልብስ ለአንድ ሰው 100 ብር * 3 = 300
 ሌሎች ወጪዎች በአመት = 700
o ድምር 14500
 ጠቅላላ ወጪ (1+2+3+4+5) = 128631

ለ. የገቢ ታሳቢዎች

1. አንድ ዙር ማድለብ ጊዜ የሚፈጀው 90 ቀን


2. በቀን ከአንድ ከብት ሊገኝ የሚችል የክብደት ጭማሪ 750 ግራም
3. በዓመት ሊኖር የሚችል የድለባ ዙር 3
4. በአንድ ዙር የሚኖሩ ከብቶች ብዛት 5
5. በአመት የሚደልብ መጠን 15
6. በአመት ሊከሰት የሚችል የሞት መጠን 2 በመቶ
7. በዓመት ለገበያ ሊቀርብ የሚችል መጠን 15
8. የእያንዳንዱ ከብት የመሸጫ ክብደት 368 ኪግ
9. በአመት የሚገን ጠቅላላ ክብደት 5520 ኪግ

10
10. የእያንዳንዱ ኪግ የመሸጫ ዋጋ 35 ብር
11. ከማድለብ የተገኘ ሽያጭ በብር 165600 ብር
12. ከኩበት/ፍግ የተገኘ ሽያጭ 13500
13. ጠቅላላ ገቢ 179100
ሐ. ማጠቃለያ
(ጠቅላላ ገቢ - ጠቅላላ ወጪ) 179100 – 128631 = 50469
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በላይ የቀረበው የአዋጭነት ስሌት ሁሉንም አካባቢዎች የማይወክልና የወቅታዊ የገበያ ጥናት
መረጃን መሰረት ያላደረገ እና አሰራሩን ለማመላከት የቀረበ እንደሆነ በመረዳት በየአካባቢው ወቅታዊ የገበያ
መረጃን መሰረት በማድረግ እና በአካባቢው የሚገኝ ሃብትን መሰረት በማድረግ መሰራት ይኖርበታል፡፡

ክፍል ሁለት

1. ከወተት ከብት እርባታ ጣቢያዎች የሚገኙ ክልስ ወንድ ጥጆችን (Dairy Beef) የማሳደግ
ፓኬጅ
ይህ ፓኬጅ ከተለያዩ የወተት ከብት እርባታ ጣቢያዎች የሚገኙትን ጡት የጣሉ ክልስ ወንዶች ጥጆችን በማሰባሰብ
የሚከናወን የማድለብ ስራ ነው፡፡ በርካታ አርቢዎች ክልስ ወንድ ጥጆችን በተገቢው መንገድ ባለመያዛቸው ተጠቃሚ
ሲሆኑ አይታይም፤ በመሆኑም በጥሩ አመጋጋብና አያያዝ በአጭር ጊዜ አሳድጎ ለእርድ እንዲደርሱና በትልልቅ ከተሞች
ለሚገኙ ሆቴሎች፣ ሱፐርማርኬቶችና ተጠቃሚዎች የቀይና ለስላሳ ስጋ (Lean and Tender meat) በማምረት በቀጥታ
ለስጋ በመሸጥ ወይም ለወይፈን አድላቢዎች ማቅረብ የሚያስችል ፓኬጅ በማዘጋጀት ዘርፉን የበለጠ ተቃሚ እንዲሆን
ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

1.1 የፓኬጅ ጥንቅርና የአሰራር ስልቶች

1.1.1 የሚያድጉ ጥጆች አመራረጥ

ሀ. ዝርያ

ለዚህ የማሳደግ (Stocker feeder) ፓኬጅ የሚፈለጉት ጥጆች ፈጣን እድገት ያላቸው በሀገራችን የወተት ከብት እርባታ
ጣቢያዎች የሚገኙት ፍሪዥያን ክልስ ወንድ ጥጆች ናቸው፡፡

11
ለ. ዕድሜ

በዚህ ፓኬጅ ጡት የጣሉ ጥጆችን የማሳደግ (Stocker Feeder) ፓኬጅ እንደመሆኑ መጠን ለዚህ ፓኬጅ የሚያስፈልጉ
ከብቶች ከ 6 ወር እድሜ በላይ ያላቸው ክልስ ወንድ ጥጆች ናቸው፡፡

ሐ. ክብደት

ለዚህ ፓኬጅ የሚያስፈልጉ ጥጆች የመነሻ ክብደታቸው በተቻለ መጠን ከፍተኛ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ምንም እንኳን
የሀገራችን ጥጆች የ 6 ወር ክብደታቸው ከ 80 ኪግ.የማያልፍ ቢሆንም ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በሀገራችን
ከሚገኙት የወተት ከብት እርባታ ጣቢያዎች የሚወጡ ክልስ ጥጆች የ 6 ወር አማካኝ ክብደታቸው ከ 125 -
130 ኪግ.ነው፡፡ በመሆኑም ለዚህ ፓኬጅ የሚመረጡ ጥጆች የመነሻ ክብደት ከ 125 ኪግ.በላይ ሆነው የተሻሻለ አያያዝና
አመጋገብ ተጠቅሞ በአጭር ጊዜ በማሳደግ በ 18 ወር እድሜአቸው እስከ 323 ኪግ.በማድረስ በቀጥታ ለገበያ አቅርቦ
መሸጥ ወይም ለወይፈን አድላቢዎች ለመጨረሻ የእድገት ደረጃ የሚረዳ መኖ /Finishing Ration/ደረጃ የሚረዳ መኖ
በመመገብ የሚፈለገውን 400 ኪ.ግ ወይም ከዚያ በላይየሆነ ክብደት እስኪሞላው ለሚያደልቡ አድላቢዎች እንዲያቀርቡ
ይመከራል::

መ. ጤና

በዚህ ፓኬጅ የሚካተቱት ከብቶች ታዳጊና ክልስ ጥጆች በመሆናቸው ተከታታይና ጥብቅ የጤና ክተትል ማግኘት
ይኖርባቸዋል፡፡ ጥጆቹ ከርባታ ጣቢያው ተገዝተው እንደወጡ ፡-

 በደህና ሁኔታ ፀድተው በተዘጋጁ የመመገቢያና መጠጫ ገንዳዎች መጠቀምና ዕቃዎችን በማጠብ
አድረቆ ለሚቀጥለው አገልግሎት ማዘጋጀት ያስፈልጋል፤
 ለበሽታ አስተላላፊ ህዋሳት ተጋላጭነትን መቀነስ፤
 በበሽታ የመቋቋም አቅምን የሚያዳክሙ ሁኔታዎችን ማስወገድ/መቀነስ፤
 የታመሙ ጥጆች ካሉ ተለይተው አስፈላጊው ህክም እንዲሰጠቸው ያስፈልጋል፤
 በጤና ባለሙያ አማካኝነት በአካባቢው ለሚከሰቱ የጥጃ በሽታ ክትባት መሰጠት ይኖርበታል፤
 ለውስጥና ለውጭ ጥገኛ ምርምራ ከተደረገላቸው በኋላ አስፈላጊውን መድሃኒት ማግኘት
ይኖርባቸዋል፤
ከእርባታው ጣቢያዎች አዲስ ተገዝተው ለሚመጡ ጥጆች አንድ ወር እስኪሞላቸው ድረስ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ
አንዲደረግላቸው ያስፈልጋል፡፡ ምቹ ንጹህና ደረቅ በረት፣ በቂ የመኖና የውሃ አቅርበት እንዲመቻች ማድረግ ያፈልጋል፡፡

1.2. የመኖ ዝግጅትና የአመጋጋብ ስልት


የክልስ ጥጆች የመኖ ጥንቅር ከ 20-25% ድርቆሽና ከ 75 - 80% የተመጣተነ መኖ ቢሆን አመርቂ ውጤት እንደሚያስገኝ
ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ታዳጊ ጥጆች ለተዘጋጀላቸው መኖ (Ration) አዲስ ስለሚሆኑ መኖውን ቀስ በቀስ ደረጃ በደረጃ
በመስጠት መላመድ ያስፈልጋል፡፡ ይህንለማድረግ ቀጥሎ የተጠቀሰውን የአመጋገብ ዘዴ መጠቀም ያሻል፡፡

 በመጀመሪያው ቀን ለስላሳ ድርቆሽ መመገብ፤


 ከ 2 – 4 ኛወ ቀን የሳር ድርቆሽና ከ 10 - 30% Concentrate መመገብ
 ከ 5 – 21 ኛው ቀን የመነሻ መኖ( starter Ration)ማለትም 28% የሳር ድርቆሽና 72% concentrate
መመገብ
 ከ 22 ኛው ቀን እስከሚሸጡ ድረስ 10% ድርቆሽና 90% ምጥን መኖ መመገብ፤
12
በፓኬጁ ውስጥ የተካተቱት ታዳጊዎች (Stockers) የእድገት ፍጥነት እንደ እድሜአቸው ሊለያዩ ስለሚችሉ የተለያዩየ
መኖ አማራጮች ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡

በዚህ መሰረት እድሜአቸው ከ 6 ወር እስከ 12 ወር የሆኑ ታዳጊ ጥጆች (Stocker calves) በፍጥነት ስለሚያድጉና
በአንጻሩ ከ 12 – 18 ወር እድሜ ያላችው yearling stocker’s አነስ ባለ ፍጥነት የሚያድጉ ስለሆነ ለነዚህ ሁለት የዕድሜ
ክልል ተስማሚ የሆኑ ሁለት አማራቾች ተዘጋጅተዋል፡፡ በዚህም መሰረት አድላቢ በአካባቢው በተሸለ ዋጋ
ሊጠቀምባቸው የሚችሉትን ጥንቅሮች ሊመርጥ ይችላል፡፡

ከ 6-12 ወር ዕድሜ ላላቸው ክልስ ጥጆች የተዘጋጁ የመኖ አማራጭ/መነሻ ክብደት 125 ኪ.ግ የቀን ጭማሪ 700 ግራም/

መኖ 1 መኖ 2 መኖ 3

የመኖ ዓይነት መኖ መኖ መኖ መኖ
መኖ በ% መኖ በ%
በኪግ በ% በኪግ በኪግ

ድርቆሽ 22 0.9 22 0.9 22 0.9

የበቆሎ እህል 20 0.9 30 1.4 15 0.7

ባቄላ 1 0.04 1.3 0.06 3 0.1

ፉርሽካ 10 0.5 5 0.2 10 0.5

ፉርሽኬሎ 38 1.7 28 1.3 33 1.5

የኑግ ፋጉሎ 7 0.3 8 0.4 4 0.2

የቦሎቄ እህል -- 5 0.2 10 0.5

የጓያ እህል 1.8 0.1 0.5 0.02 2 0.09

የተፈጨ አጥንት 0.5 0.02 0.5 0.02 0.5 0.02

ጨው 0.5 0.02 0.5 0.02 0.5 0.02

ድምር 100 4.52 100 4.52 100 4.52

ከ 12-18 ወር እድሜ ላላቸው ክልስ ጥጆች የተዘጋጀ የመኖ አማራጭ/ የቀን ጭማሪ 400 ግራም/

መኖ 1 መኖ 2 መኖ 3
የመኖ ዓይነት
መኖ በ% መኖ በኪግ መኖ በ% መኖ በኪግ መኖ በ% መኖ በኪግ
ድርቆሽ 19 0.95 19 0.95 19 0.95
ፉርሽኬሎ 30 1.5 10 0.5 30 1.5
ፋጉሎ የተልባ 14 0.7 15 0.75 20 1.0
13
የበቆሎ እህል 8 0.4 23 1.2 10 0.5
ባቄላ 1 0.05 2 0.1 1 0.05
ፉርሽካ 20 1.0 20 1.0 10 0.5
የኑግ ፋጉሎ 6 0.3 3 0.2 5 0.3
የባቄላእህል 1 0.05 5 0.3 3 0.2
የጓያ እህል 2 0.1 1 0.05
የተፈጨ አጥንት 0.5 0.03 0.5 0.03 0.5 0.03
ድምር 0.5 0.03 0.5 0.03 0.5 0.03
ድምር 100 5 100 5 100 5

1.3 የመጠለያ አሰራርና መሟላት ያለባቸው ቁሳቁሶች

የክልስ ጥጆች ማሳደጊያ መጠለያ/በረት እንደ ዕድሜያቸውና ክብደታቸው ተለያይቶ ሊሰራ ይችላል፡፡ በተፈጥሮ ጥጆች
ንጹህ የሆነ፣ብርሃን ያለውና ተገቢ የአየር ዝውውር ያለው ሥፍራ ይፈልጋሉ፡፡ በተለይ እርጥብ በረት፣ የሚጋጭ ነፋስና
የረጠበ ጉዝጓዝ የጥጃውን በሽታን የመቋቋም አቅም ሊያሳንሰው ይችላል፡፡ስለዚህ የሚሰሩት በረቶች/ጉረኖ ጥሩ የአየር
ዝውውር ያላቸውና ለማጽዳት ቀላል መሆን አለባቸው፡፡ የጥጆች ማሳደጊያ በሁለት ዓይነት መልኩ መስራት ይቻላል፡፡
የመጀመሪያው በመጠለያው ውስጥ የተናጠል የጥጃ ክፍል ወይም ጉረኖ ሲሆን ሌላው ደግሞ ከመጠለያ ውጭ የተናጠል
የጥጃ ክፍል ወይም ጉረኖ መስራት ይቻላል፡፡

ሀ. መጠለያ/በረት/ጉረኖ

ለዚህ ፓኬጅ የሚዘጋጀው በረት ባለ 3 ጎን ግድግዳ ሆኖ ጥላያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡ ግድግዳዎቹ ከቆርቆሮ ወይም
ከጭቃ ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ ግድግዳ ያልተሰራበት አንደኛው ጎን ከከባድ ነፋሰ አቅጣጫ በተቃራኒ ሆኖ ቢቻል በስተምስራቅ
ወይም ደቡብ ምስራቅ ወይም ደቡብ አቅጣጫ ቢሆን መረጣል፡፡ የጣራው ክዳን የመመገቢያና መኝታ ቦታን እንዲሸፍን 4
ሜትር ስፋት እንዲኖረው ያሰፈልጋል፡፡ የጣራ ከፍታው 3 ሜ ሆኖ ከቆርቆሮ ወይም ከሳር ሊሰራ ይችላል፡፡ የጥላው
ረዝመት እንደ ከብቶቹ ብዛት የሚወሰን ነው፡፡ ከጥላ በተጨማሪ ፀሃይ የሚሞቁበትና መንቀሳቀሻ እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡
በረቱም የታጠረ መሆን ይኖርበታል፡፡

ለ. ወለል

የበረቱ ወለል ፍሳሽ ለማስወግድ እንዲያመች 2 - 5% ተዳፋትነት ያለው ሆኖ ግማሹ ማለትም የመመገቢያውና
የመኝታው ቦታ በኮንክሪት ወይም በድንጋይ ንጣፍ ቢሰራ ይመረጣል፡፡ ቀሪው ወለል እንዳይጨቀይ ቀይ አሸዋ ቢፈስበት
ተገቢ ይሆናል፡፡ በወለሉ ጠርዝ ተዳፋትነቱን የጠበቀ በቂ የፈሳሥ መውረጃ ቦይ መኖር አለበት፡፡

ሐ. የመመገቢያ ገንዳ
14
የመመገቢያው ገንዳ የጥላ ግድግዳውን አቀማመጥ ይዞ በርዝመት በኮንክሪት የተሰራና 0.4 ሜ ስፋትና 0.4 ሜ ጥልቀት
ያለው መሆን አለበት፡፡ በዚህ ፓኬጅ አሰራር መሰረት ጥጆችን በቡድን ለያይቶ ለመመገብ ያመች ዘንድ በረቱንኩል ቦታ
በእንጨት መክፈልና ለእያንዳንዱ ክፍል የተመደቡትን ጥጆች ያለምንም ችግር አንድ ጊዜ መመገብ የሚያስችል
የመመገቢያ ገንዳ መሰራት ይኖርበታል፡፡

መ. የውሃ መጠጫ ገንዳ

የወሃ መጠጫ ገንዳ በያንዳንዱ የበረት ክፍል ውስጥ ለመዝናኛነትና ለፀሀይ መሞቂያ በተዘጋጀው ስፍራ አማካኝ ቦታ ላይ
ጥጆች በሁለት ጎን መጠጣት እንዲያስችላቸው ተደርጎ መሰራት ይኖርበታል፡፡ ገንዳው በኮንክሪት የሚሰራ ሆኖ በበረቱ
ለሚኖሩት እንስሳት ማስተናገድ የሚችል ስፋትና ርዝመት ያለው መሆን አለበት፡፡

ሠ. የህክምና መስጫ በረት (crush)

የታመሙ ከብቶችን ለማከም፣ ክትባት ለመስጠትና የውጭ ትገኛ መከላከያ መድሃኒት ለመርጨት የሚስችል ከዋናው
በረት ተነጥሎ በእንጨት የተሰራ ማጎሪያ (crush) ያስፈልጋል፡፡ አሰራሩም መግቢያው አካባቢ ለከብቶች መሰብሰቢያ
የሚሆን ሰፋ ያለ (4*5 ሜትር) ቦታ ሲኖረው መውጫው አካባቢ ረዘም ያለና በአንድ ጊዜ አንድ ከብት ብቻ ለማሳለፍ
የሚችል (7*0.4*0.8) የሆነ የህክምና መስጫ ቦታ ኖረዋል፡፡

ረ. ሌሎች ግንባታዎች

ከበረት በተጨማሪ የተመጣጠነ መኖ ማከማቻ መጋዘን፣ ቢሮ፣ ውጭ አጥር ወዘተ መሰራት ይኖርበታል፡፡

ለሚደልቡ 150 ክልስ ጥጆች የሚያስፈልግ የመጠለያና የስራ መገልገያ መሳሪያዎች ግምት

የግንባታ ዓይነት ብዛት ዓይነት


በረት 1 480 m2
የመመገቢያ ገንዳ 3 3.2 m3
የውሃ መጠጫ ገንዳ 3 0.32 m3
የህክምና መስጫ በረት 1 2.8 m2
የመኖ መጋዘን 1 36 m2

15
ቢሮ 1 16 m2
አጥር የውጭ 1 140 m
የሚያስፈልጉ የመገልገያ መሳሪያዎች ዓነትና ግምት
የመርጫ መሳሪያ 2 15 ሊትር
የእጅ ጋሪ 4
አካፋ 4
ውሃ ጎማ 1/2 200 ሜትር
ፕላስቲክ ባልዲ 6
ጠረጴዛ 1
ወንበር 3

1.4 ለስጋ የሚያስፈልጉ ጥጆችና የማሳደጊያ ወቅት

በዚህ ፓኬጅ አሰራር መሰረት የ 6 ወር ክልስ ጥጆች በፍጥነት አሳድጎ በ 18 ወራቸው 323 ኪግ ደርሰው ለእርድ ወይም
ለቀጣይ የማድለብ ስራ (Finishing) ለማቅረብ 360 ቀናት ይፈጃል፡፡ ይህ አሰራር ቅልጥፍና እንዲኖረው አሳዳጊው
በአራት ወር ልዩነት በአመት 3 የጥጆች ቡድን Batch) በማስገባት በቀጣዩ አመት ሶስቱንም የጥጃ ቡድኖች እንደ
አገባባቸው ቅደም ተከተል በየ 4 ወሩ ማውጠት ወይም መሸጥ ይችላል፡፡ በዚህ አሰራር አንድ ቡድን እንደ አቅማቸው
ለአነስተኛ ቢያንስ 60፣ ለመካከለኛ ደረጃ ቢያንስ 90፣ ከፍተኛ ደረጃ አሳዳጊዎች ቢያንስ 150 ጥጆችን ቢይዙ
አሳዳጊዎች በ 4 ወር ልዩነት 3 ቡድኖች ለቅለባ ቢያስገቡ በመጀመሪያ ዓመት በጠቅላላ በአነስተኛ ደረጃ የሚመደቡ
አሳዳጊዎች 60፣ በመካከለኛ ደረጃ የሚመደቡ አሳዳጊዎች 90፣ በከፍተኛ ደረጃ ደግሞ 150 ጥጆችን ሲቀልብ በሁለተኛው
አመት በየ 4 ወሩ አነስተኛ አሳዳጊዎች 20፣ መካከለኛ አሳዳጊዎች 30፣ ከፍተኛ አሳዳጊዎች ደግሞ 50 ጥጆችን መሸጥ
ይችላሉ፡፡

የታዳጊ ጥጆች (Stockers) የቅላባና የሽያጭ ጊዜ ሰሌዳ / ለምሳሌነት ቀረበ/

ወራት
ሚያ
መጋ
መስ

ታህ

ጥር

ነሐ
ግን

16
የመጀመሪያ 2ኛ 3ኛ የመጀመሪያዎ
የጥጆች ቡድን የጥጃ የጥጃ ቹ ለሽያጭ
ለቅለባ ቡድን ቡድን የሚወጡበት
የሚገባበት ለቅለባ ለቅለባ
የሚገባበ የሚገባበ
ት ት

በሁለተኛ ዓመት የአንደኛዓ የሁለተኘ አንደኛ የ2ኛ የ 2 ኛ ዓመት


የመጀመሪያው መት 2 ኛ ዓመት አመት 3 ኛ ዓመት የመጀመሪያ
ቡድን ለቅለባ ቡድን 2ኛ ቡድን 3ኛ ቡድን
የሚገባበት የሚሸጥበ ቡድን የሚሸጡበ ቡድንለቅ የሚሸጥበት
ት የሚሸጥበ ት ለባ
ት የሚገባበ

ከላይ የተጠቀሰው የቅለባና የመሸጫ የጊዜ ሰሌዳ በምሳሌነት የቀረበ ስለሆነ አሳዳጊው ጥጃ የሚያስገባበትና የሚሸትበት
ወር ከገበያው ሁኔታና ከመኖ አቅርቦቱ አንፃር ራሱን የጊዜ ሰሌዳ ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡

1.5 ፓኬጁ ተግባራዊ የሚሆንባቸው አካባቢዎች

 የሚፈለጉትን ክለስ ጥጆች ለማግኘት ይረዳ ዘንድ የስራጭት አካባቢው ወተት ክብት እርባታ ጣቢያዎች
/የግል ወይም የመንግስት/ የሚገኙበት አካባቢ ቢሆን ይመረጣል፡፡
 ለመኖ ማደራጃ ፋብሪካዎች ወይም አግሮ ኢንዱስትሪዎች የቀረበ ቢሆን ይመረጣል፡፡
 ፓኬጁን በተናጠል ከመተግበር በተደራጀ መልኩ መፈፀም ውጤታማነቱን ሊያጎለብተው ስለሚችል
የተደራጁ ስራ ፈላጊዎች ነዋሪዎች ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም የወተት ማህበራትና ዩኒየኖች
የሚገኙበት አካባቢ መምረጥ ያስፈልጋል፡፡

1.6 የፓኬጅ ተሳታፊ መምረጫ መስፍርቶች

በተዘጋጀው ፓኬጅ ተሳታፊ የሚሆኑ ስራው ከፍተኛ ክትትል ወጪንም የሚጠይቅ በመሆኑ በስራው ለመሳተፍ ፍላጎትና
የመስራት አቅም ያላቸው በማህበር ተደራጅተው እንዲሰሩ ማድረግ ይቻላል፡፡ በግለሰብ ደረጃ በዚህ ፓኬጅ ለመሰማራት
የሚቻል ሲሆን ውጤታማ ለመሆን ሙሉ ፍላጎት፣ የገንዘብ አቅም ወይም ቀጥሮ ማሰራት የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡

1.7 የግብዓት አቅርቦትና ሥርጭትና የግብይት ሁኔታ

ለዚህ ፓኬጅ ክልስ ወንድ ጥጆች ምንጭ የግል ወይም የመንግስት የተሸሻሉ የወተት ከብት እርባታዎች ይሆናሉ:: የክልስ
ጥጆቹን አሰባሰብ የተሳለጠና ትስስሩ ቀጣይነት እንዲኖረው የእርባታ ጣቢያዎቹና አድላቢዎቹ በሚገቡት የውል

17
ስምምነት ጥጆችን በወቅቱ ያቀርባሉ፡፡ የክልስ ጥጆች አሳዳጊዎች የሚያገኙዋቸውን ክልስ ጥጆች በመረከብ
በተቀመጠው የማሳደጊያ ወቅት አሳድገው ለገበያ ያቀርባሉ ወይም ወይፈኖችን ለሚያደልቡ አድላቢዎች ያቀርባሉ፡፡
ይህን ፓኬጅ ውጤታማ ለማድረግ በተደራጀ መልክ መስራትና የአቅርቦትና የሽያጭ ትስስሩ ቀጣይነት እንዲኖረው
ወጥነትና ባለው መንገድ መስራትን ይጠይቃል፡፡ ስራው በግልም ሆነ በጋራ ሊሰራ የሚችል ቢሆንም በማህበር
ተደራጀተው በመስራት የግብአት ችግርን፣ የብድር አቅርቦትንና ሌሎች ችግሮችን በጋራ በመፍታት የበለጠ ውጤታማ
መሆን ይቻላል፡፡

ሊገኝ የሚችል ምርት

- አንድ 125 ኪግ የሚመዝን ጥጃ በአመት ውስጥ 198 ኪግ በመጨመር ክብደቱ ወደ 323 ኪግ ከፍ


ይላል፤
- እስከ 1000 ኪግ የሚደርስ ለማዳበሪያ የሚሆን ፍግ በአመት ይገኛል፤
የአዋጭነት ስሌት

የዚህ ፓኬጅ አዋጭነት ስሌት የተሰራው 150 ክልስ ጥጆችን በአመት አሳድጎ ለገበያ ለማቅረብ ምሳሌ በመውሰድ ነው፤

ለዚህ ስራ ሚገዙ ጥጆች አማካኝ ክብደት 125 ኪግ እንደሚሆንና እንደሚሆን ተገምቷል፡፡ በተጨማሪም ከብቶቹ በቅለባ
ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ እያንዳቸው 550 ግራን የክብደት ጭማሪ እንደሚያሳዩ ተገምቷል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ነትቦች
መነሻ በማድረግ የአዋጭነት ስሌቱ እንደሚከተለው ቀርባል፡፡

ሀ. ወጪዎች

1/የከብት ግዢ

በአመት የሚገዙ ጠቅላላ ጥጆች ዋጋ 800*150=120000 ብር

2/የመኖ ወጪ

የመኖ ዓይነት የአንድ ጥጃ የአንድ ኪግ የመኖ ለ 150 ጥጆች የዓመት ጠቅላላ


የቀን ፍጆታ ዋጋ በብር በዓመት የሚበቃ ወጪ በብር
በኪግ መኖ በኩል
ድርቆሽ 0.9 0.60 486.00 29160
የበቆሎ እህል 0.9 5.0 486.00 243000
ፉርሽካ 0.5 4.5 270.00 121500
ፉርሽኬሎ 1.7 3.0 918.00 275400
የኑግ ፋጉሎ 0.3 5.0 162.00 81000
የጓያ እህል 0.1 2.0 54.00 10800
የተፈጨ አጥንት 0.02 2.00 10.80 2160
ጨው 0.02 2.00 10.80 2160
ድምር 4.48 -- 2419.2 765180
18
3/ የጤና አገልግሎት ወጪ 30 ብር በጥጃ በአመት ጠቅላላ ወጪ

150*50=7500

4/ የሰራተኛ ደሞዝ

 3 የቀን ሰራተኞች በቀን 35 ብር *360 *3 = 6480 ብር


 አንድ ዘበኛ በቀን 20 ብር *360**1 = 7200 ብር
 የስራ ልብስ ለአንድ ሰው 100 ብር *4 = 400 ብር
 ሌሎች ወጪዎች በዓመት 700 ብር
ድምር 14780 ብር

5/ ዲፕሪሲየሽን /እልቀት/ ታሳቢ ወጪዎች

የእልቀት መጠን
የነዋይ ዓይነት የመጀመሪያ ዋጋ በብር ዓመታዊ የእልቀት መጠን
በብር

በረትና የተለያዩ 50000 5 5000


መጠለያ

የስራ መሳሪያዎች 1888 10 189

ድምር 22372 5189

ጠቅላላ ወጪ (1+2+3+4+5) = 912649 ብር

ለ. ገቢዎች

1. አማካይ የመነሻ ክብደት 125 ኪግ


2. ጠቅላላ ቅለባ ጊዜ 360 ቀናት
3. በቀን ከአንድ ከብት ሊገኝ የሚችል ጭማሪ 550 ግራም
4. በዓመት አድገው ሊወጡ የሚገባቸው ጥጆች 150
5. የሞት መጠን 2
6. በጠቅላላው ለገበያ የሚቀርቡ ጥጆች 148
7. የእያንዳንዱ ጥጆች የመሸጫ ክብደት 323 ኪግ
19
8. በአመት ሊገኝ የሚችል ጠቅላላ ክብደት (148*323) = 47804 ኪግ
9. የአንድ ኪግ የሽያጭ ክብደት ዋጋ = 24.76 ብር

10. ከሚደልቡ ሽያጭ 1183627.04


11. ከፍግ/ኩበትሽያጭ 216000
12. ጠቅላላገቢ 1399627

ማጠቃላያ፤- አመታዊ የገቢና ወጪ ማጠቃለያ


ጠቅላላ ገቢ - ጠቅላላ ወጪ (1399627 – 912649)= 486978 ብር
ማሳሰቢያ፡- የአዋጭነት ትንተናው ለመነሻነት የተዘጋጀ ስለሆነ ስራው ተግባራዊ በሚሆንበት አካባቢ ባለው
ወቅታዊ ዋጋና ተጨባጭ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡

ክፍል ሶስት

1. የበግ/ፍየል ሥጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ

በአብዛኛው የሀገር ውስጥና ዲቃላ በጎችንና ፍየሎች ለእርባታ አገልግሎት የሰጡ ተባዕት በጎችን/ፍየሎችን እና
ዕድገታቸውን ያልጨረሱና ለእርባታ የማይፈለጉ በጎችን/ፍየሎችን በመምረጥ ከ 3-4 ወራት አወፍሮ ለገበያ የማቅረቡ
ሥራ አየተካሄደ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን የተሻለ ዝርያዎችንና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተሻለ ውጤት በሚያስመዘግብ
መልኩ እየተካሄደ አለመሆኑ የተደረጉ የመስክ ዳሰሳ ውጤቶች ያመላክታሉ:: ስለሆነም በጎችን/ፍየሎችን በማድለብ
ለከተሞች ገበያ ለማቅረብ የሚያስችሉ ፓኬጅ ቀርበዋል::

1.1 የፓኬጅ ጥንቅርና የአሰራር ስልቶች

1.1.1 የሚደልቡ በጎች/ፍየሎች አመራረጥ

ሀ. ዝርያ፣

20
ለበግና ፍየል ሥጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ አገልግሎት የሚውሉ በግ/ፍየሎች አድላቢው ለእርባታ አገልግሎት
ሲጠቀምባቸው የነበሩ የሀገር በቀል ወይም ዲቃላ በጎች/ፍየሎችን ከአካባቢው ገበያ ገዝቶ ሊጠቀም ይችላል፡፡

ለ. ዕድሜ፣

ለዚህ ስራ የሚመረጡ በግ/ፍየል የተሰጣቸውን መኖ በአግባቡ በመመገብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈለገውን ውጤት
ሊያስገኙ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ስለዚህ ለስጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ አገልግሎት የሚውሉ በግ/ፍየል ቢያንስ 50%
ዕድገታቸውን የጨረሱ (mature body weight) ማለትም ለጥቂያ የደረሱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህ የሚሞከቱ
በጎች/ፍየሎች ከ 2 አመት ያላነሰና ከ 4 ዓመት ያልበለጠ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ ለመሆናቸው
በተወሰነ ደረጃ በጥርሳቸው መለየት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ለስጋ ምርት ማሻሻል ፓኬጅ አገልግሎት የሚውሉ በግ/ፍየሎች
ሲመረጡ እድሜአቸው ከ 2-4 ዓመት ማለት 3 ኛው ጥንድ ቋሚ የፊት ጥርስ ሲበቅል ጀምሮ መጨረሻዎቹ ቋሚ ጥርሶች
ሲበቅሉ ይሆናል ማለት ነው፡፡

21
ሐ. የሰውነት አቋምና ክብደት፣

22
ከፍተኛ ስጋ ምርት ሊሰጥ የሚችሉ አቋሙ ትልቅ የሆነ በግ/ፍየል በጥንቃቄ መመረጥ አለበት:: ለሙክት የሚመረጥ
በግ/ፍየል ከእድሜው አንጻር ሲታይ የእግሮቹ አጥንቱና የሽንጡ ስፋትና ርዝመት ትልቅ ከሆነ በዚያው መጠን ስጋ
የመያዝ ችሎታው ከፍተኛ ስለሚሆን እነደዚህ ዓይነቱን በጥንቃቄ መምረጥ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም የሰውነት
ሁኔታ(Body condition) በጣም ያልከሳ ወይም በጣም ያልወፈረ መሆን አለበት:: ይህንን ለማወቅ የበጉን/ፍየሉን
ሽንጡን በእጅ ሲዳሰስ በመጠኑ በሥጋ የተሸፈነ ሆኖ በመጠኑ አጥንት መኖሩ የማይታወቅ መሆን አለበት፡፡

የሚደልበው በግ/ፍየል የመነሻ ክብደቱ መጨረሻ ይገኛል ተብሎ ለሚታሰበው የክብደት መጠን ወሳኝነት አለው፡፡ ስለዚህ
በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አንድ የሚደልብ በግ/ፍየል ክብደቱ ከ 20 ኪ.ግ ያላነሰ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም
ከተጠቀሰው ኪ.ግ በታች ከሆነ የበጉን/ፍየሉን አቋም ለማሻሻል ወይንም ለማሞከት ረዘም ላለ ጊዜና ከፍተኛ ወጪን
ይወስዳል፡፡

መ. ጤና

በጎችና/ፍየሎች ለስጋ ምርት ማሻሻያ ሥራ ሲመረጡ ጤንነታቸው የተሟላ መሆኑ መረጋገጥ አለበት፡፡ አንድ አሞካች
የማሞከት ስራውን ከመጀመሩ በፊት የውስጥ ጥገኛ ህዋሳት ማስወገጃ መድሃኒት መስጠትና እንደ አሰፈላጊነቱ ለውጭ
ጥገኛ ርጭት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡ በማናቸውም ጊዜ የህመም ምልክት ሲታይ በቅርብ የሚገኘውን የእንስሳት ህከምና
ባለሙያ እርዳታ መጠየቅ አስፈላጊ ነው፡፡

ሠ. አያያዝ

አንድ የሚደልብ በግ/ፍየል የሚመገበው መኖ ወደ ተፈለገው የስጋ መጠን እንዲለወጥ ለማስቻል በአንድ ቦታ አስሮ
መመገብ አለበት፡፡ ሆኖም ለተወሰነ ሰዓት ጧትና ማታ ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲዝናኑ ማድረግ ተገቢ ይሆናል፡፡ ያልተኮላሹ
ከሆኑም ሊያጠቃ ስለሚችል እንዳያጠቃ መጠበቅ ይኖርብናል፡፡

የተኮላሹ በግ/ፍየሎች ካልተኮላሹት በክብደታቸው መጠን መኖ እንደሚያስፈልጋቸው ከመረጃዎች መገንዘብ የሚቻል


ሲሆን ያልተኮላሹ ከተኮላሹት የበለጠ የቀይ ስጋ መጠን ሲኖራቸው የተኮላሹ ደግሞ የበለጠ የስብ መጠን ይኖራቸዋል፡፡
ስለዚህ ሙከታው ለስብ ወይም ለቀይ ስጋ መሆኑን ለይቶ በማወቅ የምርቱን ዓይነት ኢላማ ያደረገ ቢሆን ውጤቱ
የተሸለ ይሆናል፡፡

1.1.2 የእንስሳት መኖ ምንጮች፣ዝግጅትና አመጋገብ፣

ሀ. የመኖ ዝግጅት

አድላቢው ለሥጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ያለውን መኖ በአግባቡ መግቦ ለውጤታማነት
ለማብቃት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለበት፡፡ ከፍተኛ የሃይል ሰጪ ንጥረ መኖ ይዘት ያላቸው የመኖ ምንጮች ወሳኝነት
ስላላቸው የመኖ ጥንቅሩ በአብዛኛው በጥራጥሬ የመኖ ምንጮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ እንደ ምሳሌ ያገለግል ዘንድ 20 እና
30 ኪግ ክብደት ላላቸውና በየእለቱ የ 150 እና 200 ግራም ክብደት ለሚጨምሩ በጎች የተዘጋጀ የመኖ አማራጭ መሰረት

23
በማድረግ አድላቢው በአካባቢው የሚገኘውን የመኖ ዓይነት ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደ አስፈላጊነቱ ማዘጋጀት
ይቻላል፡፡

ሠንጠረዥ - በግ ለማሞከት የተዘጋጀ የመኖ አማራጭ

የመኖ የሚሞከት በግ በ 20 ኪግ ክብደት የቀን ጭማሪ የሚሞከት በግ በ 30 ኪግ ክብደት የቀን ጭማሪ 200
ዓይነት 150 ግራም ግራም
መኖ 1 መኖ 2 መኖ 1 መኖ 2
የሚሰጠ የሚሰጠ የሚሰጠው የሚሰጠ የሚሰጠው የሚሰጠው የሚሰጠው የሚሰጠ
ው መኖ ው መኖ መኖ ው መኖ መኖ በድርቆሽ መኖ በኪግ መኖ ው መኖ
በድርቆሽ በኪግ በድርቆሽ በኪግ መኖ በ% በድርቆሽ በኪግ
መኖ በ% መኖ በ% (DM)% መኖ በ%
(DM)% (DM)% (DM)%
ድርቆሽ -- መብላት መብላት መብላት መብላት
እስከቻለ እስከቻለ እስከቻለ* እስከቻለ
* *
በቆሎ እህል 70 0.5 30 0.4
የተከካ ሲናር 85 0.6 40 0.6
የዘይት 10 0.07 25 0.4
ጭማቂ
አደንጓሬ 10 0.07
እህል
ባቄላ እህል 15 0.11 10 0.15
ጓያ እህል -- -- 50 0.8
ፉርሽካ 10 0.07 25 054
ሞላሰስ 20 053
ድምር 100 0.71 100 0.71 100 1.6 100 1.5
የድርቆሽ 2.3 0.46 2.3 0.46 1.29 1.29
መኖ ፍጎት
በኪግ
የሃይል ሰጪ
መኖ MJ/kg 6.7 6.7 10.5 10.5

ገንቢ ንጥረ 13.5 13.5 16 16


መኖ በ%
የክብደት
ጭማሪ በቀን 150 150 200 200
መግራም
* በሰንጠረዡ ውስጥ እያንዳንዱ የመኖ ጥንቅር የሚያስፈልገውን የሃይል ሰጪና የገንቢ ንጥረ መኖ ባያሟላም
ቀሪውን ከሚሰጠው ድርቆሽ እንደሚያሟላ ይጠበቃል ::

ለ. አመጋገብ

24
በጎች/ፍየሎች የተማጣጠና መኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመገቡ ከሆነ የተመጣጣነ መኖውን ቀስ በቀስ
ማለማመድ ያስፈልጋል፡፡ የተመጣጣነ መኖውን እንዲለማመዱ መጀመሪያ ከዚህ ቀደም ከሚመገቡት መኖ ጋር
በመስጠት ቀስ በቀስ የሚመገቡትን መኖ በመቀነስ የተመጣጠነውን መኖ መተን በመጨመር ማለማመድ
ያስፈልጋል፡፡ ሞላሰስ የሚመገቡ ከሆነ ከሚሰጠው ጠቅላላ መኖ 10% መብለጥ የለበትም፡፡ ምክንያቱም
ሞላሰስ ከዚህ በላይ ከተሰጠ ጉዳት ስለሚያስከትል ነው፡፡

ለሚደልቡ በጎች የንጥረ ምግብ ፍላጎት

ክብደት (በኪግ) የቀን ክብደት የቀን ድርቆሽ መኖ ኃይል ሰጪ ገንቢ %


ጭማሪ ፍጆታ የክብደቱን በ% MJ/kg (Protein)
20 100 2.0 5.9 11.9
150 2.3 6.7 13.5
200 2.6 7.5 15.0

25 100 1.9 7.1 12.2


150 2.2 7.1 14.1
200 2.5 8.0 16.0
30 100 2.1 8.0 16.1
150 2.4 9.1 18.2
200 2.7 10.2 20.4

ሐ. የመጠለያ አሰራር

የሚሞክት በግ/ፍየል ታስሮና ተጠልሎ የሚደልብ እነደመሆኑ መጠን ከብርድ፣ ከፀሀይና ከነፋስ የሚከለልበት መጠለያ
ያስፈልገዋል፡፡ የሚሰራውም መጠለያ ከአካባቢው ከሚገኝ ቁሳቁስ ሆኖ ወለሉ ለመተኛ፣ ለመቆሚያ፣ ለመመገቢያ
የተመጨ መሆን ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የውሃ መጠጫ ገንዳ ሊኖረው ይገባል፡፡

የሚሰራው መጠለያ በሞቃት አካባቢ ከሆነ ጣራው ከፍ ያለና ገረድግዳው እንደልብ ነፋስ ማስገባት እንዲችል ሆኖ
መሰራት አለበት፡፡ ሆኖም የሚሰራው በቀዝቃዛ አካባቢ ከሆነ ግድግዳው ብርድ የማያሰገባ /ቢቻል የተመረገ/ ሆኖ ጣያው
ዝቅ ያለ መሆን ይናርበታል፡፡

ለአንድ በግ/
በግ/ፍየል የሚያስፈልግ የመጠለያ መጠን

ለመቆምያ 1ሜ*0.55=0.66ሜካ
*0.55=0.66ሜካ
ለመመገቢያ ገንዳ 00.5ሜ
00.5ሜ*0.55ሜ
*0.55ሜ=0.28ሜካ
=0.28ሜካ
ለበጠጥና ሽንት መውረጃ 0.3ሜ
0.3ሜ*0.39ሜካ
*0.39ሜካ=0.17
=0.17ሜካ
ሜካ
25
ለመዝናኛና ውሃ መጠጫ 1.0ሜ
1.0ሜ*0.39ሜ
*0.39ሜ=0.39ሜካ
=0.39ሜካ
ለአንድ በግ/
በግ/ፍየል የሚያስፈልግ ቦታ ስፋት 1.5ሜካ
1.5ሜካ

1.1.3. የሚደለቡ በጎች/ፍየሎች ብዛትና የማድለቢያ ወቅት

የመኖ አቅርቦትነና የአካባቢው ገበያ አሰተማማኝ ከሆነ የማድለቡ ስራ በአመት ውስጥ እስከ 3 ዙሮች ሊከናወን ይችላል::
በአንድ ዙር በአነስተኛ ደረጃ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች ቢያንስ 7 በጎችን/ፍየሎችን፣ በመካከለኛ ደረጃ ለሚገኙ አድላቢዎች
ቢያንስ 15 በጎችን/ፍየሎችንና በከፍተኛ ደረጃ የሚያደልቡ ደግሞ ቢያንስ 50 በጎችን/ፍየሎችን በማድለብ ለገበያ
እንዲያቀርቡ ይመከራል፡፡

አድላቢው ማድለብ እንደሚችለው ማድለቢያው ጊዜ ከ 90-120 ቀናት ድረስ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በላይ ተጨማሪ
ጊዜን ማራዘሙ ተጨማሪ መኖና ወጭን ስለሚያስከትል በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ አድልቦ ለገበያ ማቅረብ ተገቢ ነው፡፡

አድላቢዎች የማድለብ ስራ ለመስራት በሚወስንበት ጊዜ ለሀገር ውስጥ ገበያ የህዝብ በዓላትን ሁኔታ መረጃ በመንተራስ
ለመሸጥ በሚያመች መልኩ መሆን ይኖርበታል:: ስለሆነም በተለይ የሀገር ውስጥ ገበያዎችን ለመጠቀም አድላቢው
በየትኛው በዓል መሸጥ እንደሚኖርበት ለመወሰን እንዲችል በአካባቢው የሚታወቁ በዓላት መሰረት በማድረግ የጊዜ
ሰሌዳ ሊያዘጋጅላቸውና በስልጠና አቅማቸው ሊጎለብት ይገባል፡፡ ይህ ደግሞ አድላቢዎች ከቀረቡለት የማድለቢያ ወቅት
አማራጮች የተስማማውን ለመምረጥና በአንድ ወቅት ሊኖር የሚችለውን ከአንድ በላይ በዓላት መጠቀም ያስችላል፡፡

ሠንጠረዥ - የህዝብ በአላትን መሰረት ያደረገ የጊዜ ሰሌዳ

የስራው ዓይነት የክንውን ወቅት

መ ጥ ሕ ታ ጥ የካ መጋ ሚ ግ ሰ ሀ ነ
   
ለድለባ ማስገባት
  
የውጭ ጥገኛ ህክምና
  
ውስጥ ጥገኛ ህክምና
መስጠት
  
ክትባት መስጠት

የመሸጫ ጊዜ

ዘመን መለወጫ

ገናና ጥምቀት

ፋሲካ

ኢድ

26

መውሊድ

አረፋ

1.1.5 የፓኬጅ ተሳታፊ መምረጫ መስፍርቶች

በበግና ፍየል ስጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ ተሳታፊዎችን በርካታ የህብረተስብ ክፍሎችን በቀላሉ ሊያሳትፍ የሚችል መስክ
ነው፡፡ አድላቢው ሙሉ በሙሉ ለፓኬጁ የሚያስፈልገውን ግብአቶች በራሱ አሟልቶ የቴክኒክ ድጋፍ ብቻ ተሰጥቶት
መስራት የሚቸል ሲሆን በከፍተተኛ ደረጃ የሚሰሩ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ግብአቶችን በብድር በመውሰድ ፓኬጁን
ተግባራዊ ሊያደርጉ ይችላል፡፡

ፓኬጁ የታለመለትን ግብ እንዲመታና ያለውን ውስን የሰው ኃይልና ግብአት በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል በበግና ፍየል
ስጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ በተለይ በሁለተኛው አማራጭ የሚሳተፉ አሞካቾችን በጥንቃቄ ለመመረጥ እንዲቻል ከዚህ
በታች የተሰጠውን የመመዘኛ ነጥብ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡

 በጓሮ በቂ የተሸሻለ መኖ ለማልማት ወይም በቂ መኖ ለማቅረብ ሙሉ ፈቃደኛ የሆነ፡


 ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር በስራ ላይ የሚያውል፤
 ፓኬጁ ውጤታማ ይሆን ዘንድ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን መያዝ የሚችል፤

1.1.5 የግብዓት አቅርቦትና ሥርጭትና የግብይት ሁኔታ

ይህን ፓኬጅ ለማካሄድ የሚያስፈለጉ በጎች/ፍየሎች አካባቢዎች ከሚገኙ እንስሳት ገበያዎች በማሰባሰብ ማድለብ
ይቻላል። በተለይም ለመካከለኛና ከፍተኛ አቅም ላላቸው የሚደልቡ እንስሳትን ከአካባቢው ማግኘት የማይችሉ
አድላቢዎች ግብዓቱን ከተደራጁ ወጣቶችና ማህበራት እንዲሁም ከቁም እንስሳት ነጋዴዎች በመረከብ ማድለብ
ይችላሉ፡፡ የደለቡ እንስሳት በቀጥታ ለአካባቢው ገበያ እንዲቀርቡ ይደረጋል::

የበግና ፍየል ማሞከት የአዋጭነት ስሌት

ሀ. የወጪ ታሳቢዎች /በብር/

 የ 5 በግ መግዣ ያንዱ ዋጋ (5x600)= 3000 ብር

በቀን 150 ግራም ክብደት ለሚጨምር በግ መኖ በቀን 800 ግራም

ለ90 ቀን 5x800x90=360

በኪግ 3.00 ሂሳብ

 የመኖ ወጪ 3 x 360=1080

27
 የመድሀኒት ወጪ 9.0015=135

ጠቅላላ ወጪ = 4215

ለ. የገቢ ታሳቢዎች

በቀን በበግ 150 ግራም ክብደት እንደሚገኝ በመገመት በ90 ቀን ውስጥ ከ3ቱ በጎች 67.5 ኪግ ተጨማሪ ክብደት ይገኛል፡፡
የመግዣ ዋጋም ይሁን የመሸጫ ዋጋ በአይን ግምት ሚካሄድ በመሆኑ የሽያጭ ዋጋው በተመሳሳይ በግምት ስሌት
ተወስዷል፡፡ በዚህ መሰረት

ጠቅላለ ሽያጩ 5 x 1200 = 6000 ብር

ጠቅላላ ወጪ - ጠቅላላ ገቢ (6000-4215) = 1785 ብር

ሰራተኛ ወጪ በቤተሰቡ አባላት ሊሸፈን እንደሚችል ስለሚገመት የወጪ ስሌት አልተሰራም፡፡

ክፍል አራት

1. የግብዓት አቅርቦትና ሥርጭትና የግብይት ሁኔታ

በዚህ የስጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆነ አድላቢ ሙሉ በሙሉ ለፓኬጁ የሚያስፈልገውን ግብአት
በራሱ አሟልቶ የቴክኒክ ድጋፍ በመጠየቅ ወይም በከፊል የገብአት ብድር በመመሪያው መሰረት ተበድሮ ሊሰራ ይችላል::
የሚደልቡ እንስሳትን የበግ/ፍየል ዝርያዎችን ሃብቱ በብዛት ከሚገኝበት አካባቢዎች ከሚገኙ ትላልቅና ትናንሽ ገበያዎች
በማሰባሰብ ማድለብ ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ለእርባታና ለሥጋ አገልገሎት ተብለው የሚሰራጩ የአዋሲና የዶርፐር
በጎችን/የቦር ፍየሎችን ዲቃላ ዝርያዎችን ከመንግስት የብዜት ማዕከላት፣ ከግለሰብ አርቢዎች፣ ከኒኩለስ ጣቢያዎች፣
ከምርምር ማዕከላትና ዩኒቨርስቲዎች በመግዛት የማድለብ ሥራው መካሄድ ይኖርበታል፡፡

በሁለቱም አማራጮች የሚደልቡ የሀገር በቀልና ዲቃላ በጎች/ፍየሎች በአካባቢው በሚገኙ ገበያዎች ገበያው
የሚፈልገውን የምርት ዓይነት ማቅረብና መሸጥ ይቻላል፡፡ እነዚህን ሁኔታዎች ለማሟላት አድላቢው ሥራውን
ከመጀመሩ በፊት የገበያው ሁኔታ መዳሰስና የተጠቃሚና አቅራቢዎችን ፍላጎት ሊያረካ የሚችል የኮንትራት ውል
ስምምነት በጋራ በማዘጋጀት በተደራጀ አግባብ ቢሰራ በግብይት ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታትና
ተጠቃሚነቱን ሊያጎለብት ያስችለዋል፡፡

2. የፓኬጁ አተገባበር አቅጣጫ


የቀረቡ አማራጭ ፓኬጆችን ውጤታማእንዲሆኑ የሚከተሉት የአተገባበር አቅጣጫዎች መከተል ይገባል::

 በቀረቡ አማራጭ ፓኬጆችን ላይ ፍላጎት ለመፍጠርና ተግባራዊ ለማድረግ ተከታታይነት ያለው ስልጠና ይሰጣል።

 ለፓኬጅ ማስፈጸሚያ የሚያስፈልጉ የግብዓትና ብድር አቅርቦት በመጠን፣በጊዜና በጥራት እንዲቀርብ ይመቻቻል።

28
 በሳይንሳዊ መንገድም ሆነ በባህላዊ መንግድ የተሻለ ውጤት ያስገኙ የስራ ተሞክሮዎችን በየአግሮ ኢኮሎጂው በመለየት
በስፋት በሁሉም አርሶ አደሮች የሚተገበሩበት ስልት ይቀይሳል፤

 የሚዘጋጁ ፓኬጆችና በየፓኬጁ የሚሰጡ ስልጠናዎች የተጠቃሚዎችን ችግርና ፍላጎት መሰረት ያደረገና ችግር ፈቺ
ሊሆን እንደሚገባ በእምነት ተይዞ ይሰራል፤

 እንደ አካባቢው ሁኔታ ታሳቢዎችን በመውሰድ የፓኬጆችን አዋጭነት ስሌት ይሰራል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ፓኬጁ
በሚተገበርበት አዋጭነቱን በመገንዘብ ወደ ሥራው እንዲገባ የፓኬጆች ቢዝነስ ፕላን ለተሳታፊዎች ይሰራሉ፡፡

3. ስልጠና
የተዘጋጁ የፓኬጅ አማራጮች ከመሰራጨቱ በፊት በየደረጃ ለሚገኙ ባለሙያዎች የማስተዋወቂያና ተግባር ተኮር
የአሰልጣኞች ስልጠና በተከታታይነት ይሰጣል። በተመሳሳይ መንገድ በየደራጃው ወደ ስራ ለመግባት የተለዩ አድላቢዎች
በፓኬጁ አተገባበር ስልጠና ይሰጣል፡፡ የስልጠናውም ይዘት እንደተሳታፊዎቹ የእውቀት ደረጃና ፍላጎት ሊለያይ ይችላል::
በተለይ ለአነስተኛ አድላቢዎች በቀበሌ ደረጃ የሚሰጡ አጠቃላይ ስልጠናዎች በመጠቀም የንድፈ ሃሳብና የተግባር
ስልጠናዎችን አቀናጅቶ በመስጠት በስልጠናው ያገኙትን ክህሎት በራሳቸው መንደር/ጣቢያ ተግባራዊ ያደርጋሉ።
በየደራጀው ያሉ የግብርና ባለሙያዎች በተሰጠው ስልጠና መሰረት እንዲተገበር ይደግፋሉ፣ መተግበሩንም ይከታተላሉ።

4. መረጃ አያያዝ
መረጃ ፓኬጁን በማቀድ፣ በትግበራ፣ በክትትልና ግምግማ የሚታዩ ጥንካሬዎችና ድክመቶችን የሚያመልት ስለሆነ
ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም የስጋ ምርት ማሻሻያ ፓኬጅን በሚፈጸምበት ወቅተት የእንስሳው የመነሻ
ክብደት፣ ከድለባ ሲወጣ ሊኖረው የሚችለው ክብደት፣ የመግዣና መሸጫ ዋጋ ፣ የመኖ ፍጆታ መመዝገቢያ፣ የወጪና ገቢ
መመዝገቢያ፣ የተሰጡ የህክምና አገልግሎቶች ሌሎች መሰረታዊ መረጃዎች ለማጠናከር የሚያስችል ማሰባሰቢያ ቅጽ
በማዘጋጀት ለአድላቢዎች ስለጠቀሜታው አሰባሰቡና አተናተኑ በቂ ስልጠና መስጠት ይገባል፡፡ በመጨረሻም በየአካባቢው
የተሰበሰቡ መረጃዎች በአግባቡ በመተንተን በተሳታፊዎች ዘንድ ፓኬጁ ያመጣውን ኢኮኖሞያዊ ጠቀሜታ ለማወቅ
ችግሮችም ካጋጠሙ መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ጠቃሚ ሃሳቦችን መጠቆም ማስቻል ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ
አስፈላጊነታቸው የታመነባቸው መረጃዎች በጥንቀቄ ማሰባሰብና በተገቢው መልክ ለመጠቀም ጥረት ሊደረግ ይገባል፡፡

5. ክትትልና ድጋፍ

ፓኬጁ የሚያስገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማወቅ፣ አፈጻጸም ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አስፈላጊውን መፍትሄ
ለመስጠትና የተሸለ ውጤት ለማስገኘት እንዲችል በየደረጃው ተከታታይነት ያለው ክትትልና ግምገማ ማድረግ
ወሳኝነት ይኖረዋል፡፡ ፓኬጁን የማሰራጨት የማስፈጸምና የክትትልና ግምገማ ስራ በየደረጃው ባሉ የከተማ ግብርና
ባለሙያዎች ይፈጸማል:: ከፌደራል ጀምሮ ባሉ ከተሞች ፓኬጁን በማስፈጸም፣ ግብዓቶችን በማሰራጨት፣ በፓኬጁ
ውስጥ የተካተቱት ጥንቅሮች በተገቢው መንገድ መተግበራቸውን በመከታታል በየደረጃው ባሉ ባለሙያዎች በየጊዜው
ግምገማ ይደረጋል::

29
 የመረጃ አሰባሰብ፣ አያያዝና ልውውጥ ሥርዓት መንደፍና መከታተል
 ቼክሊስት በማዘጋጀት ወቅታዊ ስራዎችን መደገፍና መከታተል
 መጠይቅ በማዘጋጀት ልዩነቶችን ወይም ለውጦችን መገምገም
 በመስክ በመገኘት የታቀዱት ስራዎች በአግባቡ መከናወናቸውን መከታተል
 በአካባቢው በሚገኙ የመገናኛ ዘዴዎች ተጠቅሞ ማነቃቃት
 በየደረጃው ለሚቀርቡ ችግሮች/ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት
 የስራዎችን ዘላቂነት ወይም ቀጣይነት መገምገምና መለካት
 የሚከናወኑ ተግባራትን ግብረ መልስ(Feed back) መስጠት
 አሰራርን ለማሻሻል የለውጥ መገምገሚያ(Impact Assessment) ጥናት ማካሄድ ወዘተ በተጨማሪም
በሥራ ላይ ለሚከሰቱ ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ በመስጠት ፓኬጁ ውጤታማ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በመጨረሻም የተገኙ ተሞክሮዎችን በመቀመር ለሚመለከተው አካላት በማስተላለፍ ልምድ
እንዲቀሰምባቸውይደረጋል፡፡

30
°´M

¨`H© ¾S• õЁ S[Í Tcvcu=Á pî

¨`G© õЁ (Ÿ=.Ó) ¾›”É Ÿ=.Ó ªÒ ÖpLL ªÒ U`S^

¾S• ¯Ã’ƒ (w`)

ÉU`

¾T>V¡~ uÔ‹“ õ¾KA‹ w³ƒ '

KTV¡ƒ ¾Ñu<uƒ k” 'KTVŸƒ c=Ñu< ÁK¬

›T"à ¡wŃ

ŸS<Ÿታ ¾¨Ö<uƒ k” 'ŸTVŸ‰ c=¨Ö< ÁK¬

›T"à ¡wŃ

›T"à ¾¡wŃ ßT]

vKu?~ eU

¡MM

1
µ”

¨[Ç

 ¾Ñu=“ ¨Ü SS´Ñu=Á pî

¾¨Ü SÖ” (w`) ¾Ñu= SÖ” (w`) U`S^

¾Ñu=/¨Ü ¯Ã’ƒ (´`´`)

ÉU`

¾T>V¡~ uÔ‹/õ¾KA‹

KTVŸƒ ¾Ñu<uƒ k” '

ŸTVŸƒ ¾¨Ö<uƒ k” '

¾TVŸ‰ ÖpLL ¨Ü ' ÖpLL Ñu=

¾}×^ ƒ`õ

2
vKu?~ eU

¡MM

µ”

¨[Ç

You might also like