You are on page 1of 59

በዶሮ እርባታ ላይ ያተኮረ የስልጠና ሰነድ

ዶ/ር ዋሲሁን ቸርነት


ህዳር 2015
አድስ አበባ
12/29/2022
መግቢያ

እንስሳት እርባታ በአለም ውስጥ አንድ ሚሊዬን ለሚያህል ድሃ ህዝብ ዋና


መተዳደሪያ ነው። ከጠቅላላው የዶሮ ቁጥር ውስጥ 80%ቱ የሚገኜው
አነስተኛ ገቢ ባላቸው ምግብ አጠር አገሮች ውስጥ ነው።

በኢትዮጵያ፣ከጠቅላላ ለማዳ እንስሳት ውስጥ አብዛኛውን ቁጥር የያዘው


ሲሆን ከሞላ ጎደል ሁሉም የገጠር ቤተሰብ አለው ።

የአገራችን ጠቅላላ የዶሮ ብዛት 60 million እንደሆነ ይገመታል።


በማእከላዊ ስታስቲክስ መረጃ መሰረተ ከጠቅላላ የሀገራችን ዶሮዎች
ውስጥ 88.5% ቱ አገረሰብ፣ 6.25% ቱ ድቅል እና 5.25% ቱ የውጭ
ዝርያዎች ናቸው።
1 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022
የዶሮ ዕርባታ ማለት የተለያዩ የዶሮ እርባታ ስልቶችን በመጠቀም ዶሮዎች እና የዶሮ ዉጤቶች የምናገኝበት የስራ ዘርፍ
ነዉ፡፡

የስልጠናዉ አላማ

 ይህ ስልጠና የተዘጋጀው በዶሮ ርባታ ሥራ ለተሰማሩ ሰዎች ስራቸዉን


እንድያሻሽሉ

 አርቢወች ትክክለኛዉን የአረባብ ዘደ በመገንዘብ ዉጤታማ የሆነ እርባታ እንድያካሂዱ ለማድረግ

 ህብረተሰቡ ጥራቱን የጠበቀ እንቁላል እና ስጋ እንድያገኝ ማስቻል

 አርቢዉ ከዶሮ እርባታ ተገቢዉን ጥቅም እንድያገኝ

 አንድ ዶሮ አርቢ ስለ ዶሮ እርባታ መሰረታዊ እዉቀት እንዲያገኝ ማድረግ

3 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 በአሁኑ ሰአት የእንቁላል ምርት 141.81 ሚሊዬን እንደሆነም ይገመታል
ይሁን እንጅ የግብዓት፣ የእርባታ እና መሰረተ-ልማት እንቅፋቶች
በመኖራቸው ምክንያት የዶሮ እርባታ ለኢኮኖሚው የሚያበረክተው
አስተዋጾ ከቁጥሩ ከፍተኛነት ጋር ተመጣጣኝ አይደለም።

 በዚህ ምክንያት እርባታው ለአጠቃላይ አገር አቀፍ ኢኮኖሚና ለስርአተ


ምግብ ያለው አስተዋጾ ከሌሎች አፍሪካ አገሮች ጋር ሲነጻጸር በጣም
ዝቅተኛ ነው።

2 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


ዶሮ
ቤተሰብ ፍጆታ/5/
ስራ እድል በግለሰብ ደረጃ
ስራ እድል በማህበር
በሀገራችን ዶሮ ርባታ ስራ አለመስፋፋት የሚጠቀሱ ችግሮች

 የሀገራችን ዝርያዎች ምርታማነት አነስተኛ መሆን

 በተጠቃሚው ዘንድ ርባታው የሚካሄደው እንደ ትርፍ ሥራ እንጂ እንደ ዋነኛ ገቢ

ማስገኛ አለመታየቱ

 የዶሮ ተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር አነስተኛ መሆን

 የዶሮ ግብዓት አቅርቦት ውስንነትና ዋጋ መወደድ

6 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 የቴክኖሎጂ አቅርቦት ውስንነት

 የገበያ ትስስር አለመዘርጋት

 የግል ባለሀብቶች ተሳትፎ ውስንነትና ተገቢውን ትኩረት ዘርፉ ማግኘት አለመቻሉ

ዋንኞቹ ናቸው

 የኤክስቴንሽንና የምርምር አገልግሎቶች አለመጠናከር

7 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


በአዲስ አበባና አካባቢዋ ለዶሮ ርባታ ስራ የሚታዩ ምቹ ሁኔታዎች

 በአሁኑ ወቅት በመንግስት ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱ

 ከሌሎች አርቢዎች ልምድ ለማግኘት የተመቻቸ ሁኔታ መፍጠር ማስቻሉ

 በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የተለያዩ ድጋፎች ማግኘት መቻሉ

 የእርባታውን ስራ ከአነስተኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ለማስፋፋት


የሚያገለግሉ ቴክኖሎጂዎች ማግኘት መቻሉ

8 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 አዋጭነት ያለው ፕሮጀክት ማዘጋጀት ከተቻለ የብድር አቅርቦታ ማግኘት መቻሉ

 የግብዓት አቅርቦት በተሻለ ሁኔታ ላይ መገኘቱ

 የዶሮ ርባታ ሥራ ከፍተኛ ጉልበት የማይጠይቅ መሆኑ በቀላሉ የሥራ ባሕልን


የመፍጠር ሀይል ያለው መሆኑ

 የሙሉ ግዜን በማይፈልግ ሁኔታ ማርባት መቻሉ አስተማማኝ ተጨማሪ የቤተሰብ


ገቢ በማስገኘት ጠቀሜታ መኖሩ …….ወዘተ የዶሮ ርባታ ሥራ ለከተማ ግብርና
ተስማሚ የሥራ መስክ ነው፡፡

9 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


10 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022
ጥሩ የገቢ ምንጭ
ዶሮን የማርባት የአመጋገብ ስርዓትን ያስገኛል፤ በተለይ
ለሴቶች የገንዘብ
ጥቅሞች ማሻሻል ያስችላል እጥረት ለመቅረፍ
ያስችላል

በዶሮ እርባታ ወጭን ለሌሎች ማህበራዊ


ኩሳቸው ለአትክልትና በአጭር ጊዜ መመለስ ጉዳዮች ያገለግላል፤
ሰብል ማዳበሪያነት ይቻላል ምክንያቱም በማረድ በቤት ውስጥ
ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል በአጭር ጊዜ ለሽያጭ እንግዳ ለመቀበል፤ በዓል
ስለሚደርሱ ነው ለማክበር ይውላል Ÿ

በአነስተኛ የመነሻ
ካፒታል፤ መሬት እና
ጉልበት ማርባት
ያስችላል Ÿ

11 12/29/2022
Dr. Wasihun Whernet
የእርባታ ጠንካራ ጎኖች

በአንጻራዊነት
አነስተኛ መነሻ ዶሮዎች መኖን
ካፒታል ይፈልጋል ወደ ምግብነት
ዶሮዎችና ዶሮዎች የአየር የመቀየር ከፍተኛ
ቀጣና ሳይመርጡ ዶሮዎች ባጭር
Ÿ አነስተኛ እንቁላሎቻቸው ጊዜ ውስጥ ምርት ችሎታ አላቸው
ጉልበትና ቦታ በማንኛውም ሰው በሁሉም
ይፈልጋል በምግብነት አካባቢዎች ሊረቡ መስጠት ይችላሉ፣ (ከ 2 ኪግ መኖ 1
ተፈላጊ ናቸው ይችላሉ Ÿ Ÿ ኪግ ስጋ ወይም
(በሴቶችና እንቁላል ማግኘት
በህጻናት ሊሰራ ይቻላል
ይችላል

12 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


የሚጠቀሙት መኖ አቅርቦት

የዶሮ እርባታ ቅርብና የቀን ከቀን ክትትል መፈለጉ Ÿ

የዶሮ
እርባታ
ደካማ ጎኖች
Ÿ
በበሽታና በአዳኝ እንስሳት በቀላሉ የሚጠቁ መሆናቸው

13 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 የዶሮ እርባታ ስልቶች በሶስት ይከፈላሉ።

ይህም በዋናነት መሰረት ያደረገው በዝርያ ዓይነት፣ በግብዓት አቅርቦትና በሚሰጡት


ምርት፣ በሞት መጠን በአርቢው አይነትና በእርባታው ዓይነት፣ ዶሮዎች ጭር ብለው በሚቆዩበት
ጊዜ እና አርቢዎች በሚይዙት የዶሮ መጠን ነው።

ሦስቱ የደሮ እርባታ ስልቶች

ከፊል የቤት ውስጥ


ሙሉ በሙሉ የቤት
እርባታ (ከፊል
የጭሮሽ የዶሮ እርባታ ውስጥ እርባታ (ዘመናዊ
ዘመናዊ/የተሻሻለ የዶሮ
የዶሮ እርባታ)
እርባታ)

14 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


Ÿ
ከ95-98% የሚሆነውን ከጭሮሽ (ባህላዊ) እርባታ
የሀገራችንን የዶሮ እርባታ ስልት ትንሽ በተሻለ ሁኔታ
ለአውሬ የማያጋለጥ፣ በተሻለ ሁኔታ የመኖ፣
አይነት ይሸፍናል፣ Ÿ ዶሮዎች የመጠለያ፣ የጤና፣ የግብዓት
መኖአቸውን ከአካባቢው ግብአቶችን (መኖ፤ ክትባት፤
በጭሮሽ ያገኛሉ፣ Ÿ መጠለያ፤ ወዘተ) በተሻለ ደረጃ አገልግሎቶች የሚሰጡበት
በእርባታው አንድ ቤተሰብ የሚጠቀም ሲሆን የዶሮዎችም የእርባታ ዘርፍ ነዉ
እንቅስቃሴ በተወሰነ መልኩ
በአማካኝ 5-20 የሃገረሰብ የተገደበ ነው።
ዶሮዎችን ይይዛል

15 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


የጭሮሽ
የዶሮ
እርባታ

16 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


ከፊል
የቤት
ዉስጥ
እርባታ

17 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


ዘመናዊ
የዶሮ
እርባታ

18 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


የተለያዩ የዶሮ ዝርያዎች መለያ ባህሪያትና መገኛ ምንጮች

የአካባቢ የዶሮ ዝርያዎች Ÿ

 ከተዳቀሉ የዶሮ ዝርያዎች ይልቅ የአካባቢ የዶሮ ዝርያዎች ርካሽና አካባቢውን በቀላሉ
የመላመድና በሽታንም በቀላሉ የመቋቋም አቅም አላቸው::

 ጣእማቸው ተወዳጅ የሆነና ጠንካራ የእንቁላል ቅርፊት ያላቸው ናቸዉ::Ÿ

 የአካባቢ የዶሮ ዝርያዎች ከተዳቀሉትና ከውጭ የዶሮ ዝርያዎች በክብደትም ይሁን በእንቁላል
ምርት ዝቅተኛ ናቸው። Ÿ

 የአገረሰብ ዝርያ ምርታማነት በዋናነት የሚወሰነው በዝርያው በተፈጥሮ ባህሪው፣ በዶሮ


አያያዛችን፣ በአካባቢው ምቹነት እና በመኖ አቅርቦታችን ነው::

19 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 በሙሉ ለሙሉ የጭሮሽ አረባብ ስልት ከአንድ የሀገረሰብ ዶሮ ዝርያ በአመት ከ 46 እስከ 60
እንቁላል ድረስ እናገኛለን።

 በምቹ ሁኔታ የተዳቀሉ የዶሮ ዝርያዎች በአመት ከ180 እስከ 270 እንቁላል ይጥላሉ::

 በሌላ መልኩ የአካባቢ ዝርያዎች ከተዳቀሉ የዶሮ ዝርያዎች ይልቅ በጭሮሽ የአካባቢን
ጥራጊና የምግብ ቅሪት በተሻለ መልኩ እየተጠቀሙ እና አካባቢን በቀላሉ ተላምደው መኖር
ይችላሉ:: Ÿ

20 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


21 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022
 የዶሮ አያያዝ፣ መጠለያ፣ መኖ እና የጤና ሁኔታ ከተሻሻለ የአካባቢ የዶሮ ዝርያን የእንቁላል
ምርት ከ80 እስከ 120 ማሳደግ ይቻላል፡ Ÿ

 የአካባቢ ዶሮ የእንቁላል ክብደት ግን በአማካኝ 40 ግራም ብቻ ነው።

22 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


የተሻሻሉ ዝርያዎች (የውጭ እና ድቅል ዝርያዎች) Ÿ

 የእንቁላል ጣይ ዶሮ ዝርያዎች Ÿ የእንቁላል ጣይ የዶሮ ዝርያዎች በእንቁላል


ምርታማነታቸው የታወቁ ናቸው፣ Ÿ

 የኋይት ሌግሆርን ዝርያ ሁለቱም ጾታዎች ቀለማቸው ሙሉ በሙሉ ነጭ ነው። Ÿ


እንቁላል የመጣል ችሎታቸው ከፍተኛ ነዉ

23 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 የእንቁላል ጣይ ዶሮ ዝርያዎች እንቁላል መጣል የሚጀምሩት ከ18ኛ ወር ዕድሜያቸው
በፊት ቢሆንም ከ72 እስከ 78 ወር እድሜያቸው ድረስ እንቁላል መጣል ይቀጥላሉ::

 የእንቁላል ጣይ ዶሮ ዝርያዎች 1 ኪሎ ግራም እንቁላል ለመጣል እስከ 2.5 ኪሎ ግራም


መኖ ይመገባሉ:: Ÿ

24 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


ሁለት አይነት እንቁላል ጣይ የዶሮ ዝርያዎች አሉ

ነጭና ቡናማ እንቁላል ጣይ ዶሮዎች ናቸው Ÿ

 በቡናማ እንቁላል ጣይ የዶሮ ዝርያዎች የሚጣል የእንቁላል መጠን በጣም ትልቅ ሲሆን
የሚመገቡት መኖም ከነጭ የእንቁላል ጣይ የዶሮ ዝርያዎች ይበልጣል፣

 የተለያዩ የውጭ እንቁላል ጣይ የዶሮ ዝርያዎች ለሀገራችን አርቢ አርሶ አደሮች በጣም
አስፈላጊ ናቸው። ምክንያቱም የአካባቢ የዶሮ ዝርያዎች የሚሰጡት ምርት ዝቅተኛ
በመሆኑ ነው።

25 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


ቡናማ እንቁላል ጣይ የዶሮ
ዝርያዎች

ነጭ እንቁላል ጣይ የዶሮ
ዝርያዎች

26 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


ለዶሮ እርባታ የተመረጡ የዝርያ አይነቶች

 ብዙ የእንቁላል ጣይ ዶሮ ዝርያወች ሲኖሩ በእንቁላል ምርታቸዉ እንድሁም ከኛ አገር


የአየር ሁኔታ ጋር የሚስማማ ባህሪያት Ÿያላቸዉ የዶሮ ዝርያዎች አሉ፡፡

 ኋይት ሌግ ሆርን እና ብራውን ሌግ ሆርን ይባላሉ፣ Ÿ በአመት ከ240 እንቁላል በላይ


የሚጥሉ፣ Ÿ በክብደት ቀላል የሆኑ ናቸዉ፡፡

27 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


ብራ
ኋይ ውን
ት ሌ ሌግ
ግ ሆ ሆርን
ርን እ
ዶሮ ና

28 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


Ø\
¾
°”lLM
Êa vI`Áƒ

29 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


ዶሮች ከመኖሪያ ቦታቸዉ ከመድረሳቸው በፊት Ÿ

 ለገበያና ለፍጆታ ዶሮ እርባታ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት፣ Ÿ

 ዶሮች ከመድረሳቸው በፊት መጠለያውን ማጽዳት ማለትም የቆየውን ጉዝጓዝ


ማስወገድ

 መኖሪያ ቦታዉን ማጠብና ጸረ ጀርም ረጭቶ (Disinfect) ለአንድ ሳምንት እንዲቆይ


ማድረግ ይገባል፣ Ÿ

 ከመድረሳቸው ከ12 ሰዓት በፊት መጠለያውን በአግባቡ ማሞቅ በሚገቡበት ጊዜ ምቾት


እንዲያገኙና ወዲያውኑ መኖ እና ውሀ እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል፡፡

30 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 አዳዲስ ዶሮዎችን ወደ መጠለያ ቤት ከማስገባታችን በፊት ከዚህ በፊት የነበሩ ደሮዎችን
እና ልዩ ልዩ ጥቅም የማይሰጡ ቁሳቁሶችን ከ15 ቀናት አስቀድሞ ማግለል፣ ማስወገድ እና
ማፅዳት ያስፈልጋል። Ÿ

 የቤቱ ወለልና ግድግዳ በአግባቡ መፅዳት እና እንደ ፎርማሊን ባሉ የፀረተባይ መድሃኒት


መረጨት ይኖርበታል። Ÿ

31 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 ደሮዎቹን ወደ ተዘጋጀው ቤት ከማስገባታችን በፊት ከ5-7 ሴንቲ
ሜትር በሚደርስ ጥልቀት ወለሉን በጭድ፣ ድርቆሽ፣ ሳጋቶራ፣ ወዘተ…
ባሉ ቁሶች መጎዝጎዝ ያስፈልጋል። Ÿ

 የመመገቢያ፣ መጠጫ እና ሌሎች የደሮ ቤት መገልገያ መሳሪያዎች


በአግባቡ መቀመጥ ይኖርባቸዋል።

32 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


የዶሮ ቤትን ማፅዳትና ማዘጋጀት (ማጠብና ፀረ-ተባይ መርጨት)

 የቤቱ አቧራና ቆሻሻ በደረቅ መጥረጊያ መጀመሪያ መጠረግ አለበት


Ÿ

 የቆየው ጉዝጓዝ ከቤቱ መወገድ አለበት Ÿ

 በሽታን መከላከል እንዲያስችል የተጠረገው ጉዝጓዝ ከደሮ ቤቱ እርቆ


መወገድ አለበት Ÿ የቤቱ ጥራጊ/ኩስ ለማዳበሪያነት ወይም
ለእንስሳት መኖነት መሸጥ አለበት

33 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022



የት








የትወ








የዎ
ገሮ




























የማ



የፋ





ነው




















ነስ



6


0




-መ




ገን

7 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


34
0

የዶሮ መኖ አምስት ዋና ዋና የንጥረ ምግብ ይዘቶች ሊኖሩት የሚገባ ሲሆን
እነዚህም

የሀይል ሰጭ

የአካል ገንቢ

ቫይታሚን

ሜኔራል እና

ውሃ ናቸው

35 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


ውሃ Ÿ

 ውሃ ለዶሮዎች በህይወት ለመኖርና ተገቢውን ምርት ለመስጠት በጣም


አስፈላጊ ነው፣ Ÿ

 በዶሮዎች ደም ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለው ሲሆን ንጥረ ምግቦች


ለሰውነት እንዲደርሱና በሰውነት ውስጥ የሚፈጠሩ ቆሻሻዎች በአገባቡ
እንዲወገዱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፣

Ÿለምግብ ውህደት እና የሰውነት ሙቀትን ለማስተካከል ይጠቅማል Ÿ


የዶሮዎች የውሃ አወሳሰድ ከመኖ አወሳሰድ ጋር ከፍተኛ የሆነ ዝምድና
አለው፤ ስለሆነም የውሃ አወሳሰዳቸው ሲቀንስ የመኖ አወሳሰዳቸውም
በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀንሳል፣ Ÿ
36 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022
የዶሮዎችን የውሀ አወሳሰድ ሊወሰን የሚችለው

 በመኖ አቅርቦት እና ይዘት

 ዶሮዎች በተለያየ ምክንያት ድካም ሲኖርባቸው፣ በምንሰጣቸው የውሀ


መጠጫ ቦታ እና መጠጫው ከመሬት በላይ ባለው ከፍታ

 ዶሮዎች የሚመገቡትን መኖ መጠን ከ2-3 እጥፍ ድረስ ውሃ ያስፈልጋቸዋል፣


Ÿ ስለዚህ ሁል ጊዜ ዶሮዎች ንጽህናው የተጠበቀና ቀዝቀዝ ያለ ውሃ
ከፊታቸው ማጣት የለባቸውም።

37 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


የዶሮ ቤት
Ÿ
 የዶሮ ቤት ከተለያዩ እቃወች መስራት ይቻላል ወይንም ለዚህ ተግባር ተሰርተዉ
የሚሸጡ በመግዛት መጠቀም ይቻላል፡፡Ÿ

 ጉዝጓዝ ዶሮዎች ከወለሉ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳይኖራቸው በማድረግ ቤቱ


እንዳይቀዘቅዛቸው ለማድረግና በተጨማሪም ሙቀት ለመስጠት ይጠቅማል Ÿ

 ምንጊዜም ንጹህ፣ ደረቅና ከሻጋታ ነጻ መሆን አለበት Ÿ በዶሮ ቤት ውስጥ የተጋገረ


ወይም ደግሞ የሻገተ ጉዝጓዝ በሚያጋጥምበት ጊዜ የተጋገርውንና የሻገተውን አካባቢ
አውጥቶ በአዲስ ጉዝጓዝ መተካት አስፈለጊ ነው

 በአጠቃላይ ጉዝጓዝን በቤት ውስጥ የምንቆጣጠረው፤ Ÿ ደረቅ እንዲሆን፣ Ÿ


እንዳይጋገር፣ Ÿ መጥፎ ሽታ እንዳይኖረውና Ÿ ባጠቃላይ ዶሮዎችን የሚስብ መሆን
አለበት፡፡
38 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022
የተለያዩ የዶሮ ቤት አሰራሮች
39 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022
የተለያዩ የዶሮ ቤት አሰራሮች …

40 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 በዶሮ ቤት ውስጥ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች

ዶሮዎችን በአግባቡ ለመያዝ እና አስፈላጊውን እንክብካቤ ለመስጠት በዶሮ


ቤት ውስጥ የተለያዩ ቁሳቁሶች ያስፈልጉናል

1. መመገቢያና መጠጫ፡- Ÿመመገቢያና መጠጫዎች ሁል ጊዜ ንጹህ ሆነው


መጠበቅ አለባቸው ይህም በሽታን ለመከላከል ትልቅ ጠቀሜታ አለው

2. የዶሮ መመገቢያና መጠጫ በአካባቢ በሚገኙ ነገሮች ሊሰሩ ይችላሉ::


- ከፕላስቲክ (ከጀሪካን ወይም የፕላስቲክ ቱቦ) በመጠቀም
መስራት ይቻላል፣ Ÿ የመጠጫ እቃዎች እንደ ዶሮዎች እድሜ ከፍ እና
ዝቅ ብለው ሊዘጋጁ ይችላሉ፡፡ Ÿ

41 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 በቤት ውስጥ ከማዘጋጀት በተጨማሪ በፋብሪካ የተመረቱ መመገቢያና
መጠጫዎችንም በገበያ ላይ ማግኜት ይቻላል

 መኖ ወደ መመገቢያው በምንሞላበት ጊዜ አፍ እስከ አፍ መሙላት


ለመኖ ብክነት ስለሚዳርግ የመመገቢያውን እስከ 1/3 (ሲሶ
እሰኪቀረው) ድረስ መሞላት አለበት።

42 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 የጥሩ መጠጫ መገለጫዎች Ÿ ንጹህ ውሃ ለመስጠት የሚያስችል Ÿ
ውሃ የማያንጠባጥብ Ÿ ጠንካራና በቀላሉ የማይዋልል Ÿ በቀላሉ
ውሃ ለመሙላት የሚያስችል Ÿ ለማጽዳት ምቹ የሆነ Ÿ በዋጋ ርካሽ
የሆነ

 የጥሩ መመገቢያ መገለጫዎች Ÿ የመኖ ብክትን የሚከላከል/


የሚቀንስ (ከኩስ እና አቧራ ከመሳሰሉት) Ÿ ጠንካራና በቀላሉ
የማይዋልል Ÿ በቀላሉ መኖ ለመጨመር የሚያስችል Ÿ ለማጽዳት
ምቹ የሆነ Ÿ በዋጋ ርካሽ የሆነ

43 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


Drin
k er a
feed nd
er

44 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


ትክክለኛ መሆን
አቀማመጥ የሌለበት

45 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 ትክክለኛ የዶሮ እርባታ ለማካሄድ የሚከተሉትን መከተል
ያስፈልገል። Ÿ የዉሀና መኖ አቅርቦትን ማስተካከል፤ Ÿ የአየር
ዝዉዉርና የሙቀት ሁኔታን ማስተካከል

 ማስታወሻ፡ የ ቤቶችንና መገልገያ እቃዎችን ከማጠባችን በፊት


በላያቸዉ ላይ ያለዉን ቁሻሻ (ኦርጋኒክ የሆነ ነገር) ማስለቀቅ
ይኖርብናል

46 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


በተፈጥሮ በእናት ዶሮ ጫጩት ማስፈልፈል Ÿ

በተፈጥሮ አንድ እናት ደሮ ጫጩት ለመፈልፈል መታቀፍ የምትችለው ከ8 እስከ 10


እንቁላል ብቻ ነው፣ Ÿ

በተፈጥሮ እናት ደሮ ከታቀፈችው እንቁላል ውስጥ 70% ያህል ብቻ ማለትም ከ6 እስከ 7


ጫጩት ቢፈለፈልም የሚሞቱት ጫጩቶች ብዛት በጣም ከፍተኛ ሊሆን ይችላል፣ Ÿ

የሚፈለፈል እንቁላል ለመለየት የሚከተሉትን መስፈርቶች ተጠቀሙ


Ÿ
የተጣለው እንቁላል አውራ ዶሮ ባለበትና የለማ መሆኑን ማረጋገጥ፣

 Ÿ ለማስፈልፈል የሚውል እንቁላል ንጹህ፣ ያልተሰበረ፣ በመጠን በጣም ትንሽ ወይም


ትልቅ ያልሆነ መሆን ይኖርበታል፣ Ÿ

47 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


ከለማ እንቁላል የተሻለና ጤናማ ጫጩት ለማግኘት እንቁላሉ ከጥሩ
እንቁላል ጣይ ደሮ የተጣለ መሆን አለበት፣ Ÿ

ለማስፈልፈል አገልግሎት የሚውል እንቁላል በቀን ሶስት ጊዜ


መሰብሰብና ወዲያውኑ መቀዝቀዝ አለበት፣ Ÿ

ይህ እንቁላል ከተሰበሰበ በኃላ መቆየት ያለበት ከአንድ ሳምንት ላልበለጠ


ጊዜ ብቻ ነው

48 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


በሽታ ምንድን ነዉ?

 በሽታ ማለት የእንስሳትን የዉስጥ ወይም የዉጭ የሰዉነት አካልን


በማጥቃት የቀን ተቀን እንቅስቃሴን የሚገታ ማለት ነዉ፡፡

 የበሽታ መተላለፊያ መንገዶች፡ በሽታ ከታመሙ ዶሮዎች ከሚወጣ ኩስና


ከአፍ ከሚወጣ ፈሳሽ በተበከለ ምግብና ዉሀ ወደ ጤነኞች ይተላለፋል።

 በሽታዉን ለመከላከል የቤትን፤ የመመገቢያና መጠጫዎችን ንጽህና


መጠበቅ ያስፈልጋል። ክትባት መስጠት

 ምልክቶች፡- የመድከም፤ የመደንዘዝ፤ ጭንቅላትን የመዘቅዘቅ፤ የላባ


መንጨፋረር፤ ደም የቀላቀለ ተቅማጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ። Ÿ
49 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022
ሽ ታ
የበ
ያዩ ች
ለ ቶ
የተ ልክ

50 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


 ህክምናዉ፡ - መድሀኒቶችን ከሚጠጣ ዉሀና ከምግብ ጋር መስጠት።

 የመከላከያ መንገዱ፡- Ÿ ቁጥራቸዉ የበዛ ዶሮዎችን በአንድ ላይ


ያለማድረግ፤ Ÿ በእድሜ የተለያዩ ዶሮዎችን በአንድ ላይ
ያለማድረግ፡፡
o Ÿ መመገቢያና መጠጫዎችን ጽዳት መጠበቅ፤ Ÿ
በመኖሪያቸዉና በአካባቢዉ እርጠበት አዘል ሀኔታዎችን ማስወገድ/
ማዳረቅ፡፡

o ክትባት መስጠት እና ጤናቸዉን በየግዜዉ መከታተል

51 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


የበሽታ ክስተትን እንዴት ቀድሞ መከላከል ይቻላል Ÿ

 አዲስ ተገዝተዉ ወይም ከሌላ እርባታ ጣቢያ የሚመጡ ዶሮዎች ለሦስት


ሳምንታት በተለየ ቦታ /Quarantine/ እንዲቆዩ በማድረግና በመከታተል
አቆይቶ ከበሽታ ነጻ መሆናቸዉ ሲረጋገጥ ወደ መደበኛ የዶሮ ቤት ማስገባት
ያስፈልጋል።

 Ÿ የታመሙ ዶሮዎችን የመለያና የመከታተያ (የማግለያ) ክፍል ማዘጋጀት


የግዴታ ሲሆን በማግለያ ቤታቸዉ ዉስጥ የህክምናና የእንክብካቤ ስራ
መሰራት አለበት። Ÿ

 የበሽታ ስርጭትን ለመከላልና ለመቀነስ ዶሮዎች በእድሜ እኩያ ተደርገው


እና በጾታ ተለይተዉ መያዝ አለባቸዉ።
52 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022
የዶሮ እርባታ ለስርአተ ጾታ መሻሻል የሚኖረው ጠቀሜታ

እርባታ በሴቶች ህይዎት ላይ ጉልህ ሚና እንደሚጫዎት ግልጽ


ነው። በአብዛኛው የገጠራማ ማህበረሰቦች ውስጥ፣ ዶሮዎችን ቀን
ከቀን የሚከታተለሉ ሴቶች ናቸው

Ÿ የቤተሰብ የዶሮ እርባታ አነስተና መነሻ ካፒታል የሚጠይቅና


ፈጣንና ተከታታይ ገንዘብ የሚያስገኝ ስለሆነ፤ ይህ ደግሞ ሴቶች
የቤተሰቡን በጀት ለማስተዳድር ስለሚያመቻቸው፣

53 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


54 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022
ዶሮ እርባታ ለስርአተ ምግብ መሻሻል የሚኖረው ሚና

 ከእንስሳት የሚገኙ ምግቦች የአስፈላጊ ሰውነታችን የሚፈልጋቸው ንጥረ


ነገሮች ምንጭ ናቸው። ለምሳሌ፣ ወተትና ስጋ አንድ ሰው የሚወስዳቸውን
ካልሲየምና ፕሮቲን 60% እና 55% በቅደም ተከተል ይሰጣሉ፣ Ÿ

 ከእንስሳት የሚገኙ ምግቦች ከተክሎች ብቻ በበቂ መጠን ለማግኘት አስቸጋሪ


የሆኑትን የተለያዩ ጥቃቅን ንጥረነገሮችን ይሰጡናል፣ Ÿ አትክልት ተመጋቢ
ሰዎች ቫይታሚን ኤ፣ የቫይታሚን ቢ-12፣ የካልሲየም፣ የብረትና የዚንክ እጥረት
ስለሚገጥማቸው ለተለያዩ ችግሮች ይጋለጣሉ፡፡

 ከእንስሳት የሚገኙ ምግቦች ለሰውነታችን አስፈላጊ በሆኑት ስድስቱም


ንጥረምግቦች የበለጸጉ ስለሆኑ አትክልትን በሚጠቀሙ ሰዎች ምግቦች ላይ
በጥቂቱ ቢጨመሩ እንኳን የንጥረነገሮችን መጠን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራሉ።

55 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022


56 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022
57 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022

ሮች

አሰ
ቤት
ዶ ሮ
ዩ የ
ለያ
የተ
58 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022
አመሰግናለሁ !!

59 Dr. Wasihun Whernet 12/29/2022

You might also like