You are on page 1of 8

ንብ ማነብ

¾U`T’ƒ ThhÁ“ ÑuÁ


eŸ?ƒ (IPMS) ýaË¡ƒ ¾c?ƒ
c”cKƒ (value-chain) TuMçÑ>Á
}V¡a­­­­­­­­­ዎ‹ Ø”p` መቅድም
በአገራችን ኢትዮጵያ ከሶስተኛዉ
መቶ ክፍለ ዘመን ከንጉሥ ኢዛና
ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የንብ ማነብ
ሥራ ይታወቅ ነበር፡፡ ከትዉልድ
ትዉልድ ለዘመናት ሲተላለፍ
የነበረዉ ባሕላዊ የማነብ ዘዴ ይህ
ነው የሚባል የዉጪ ሙያ እርዳታ
ሳይታከልበት ማር ይመረት ነበር፡፡

በ1960ዎቹ ውስጥ የኢትዮጵያ


መንግሥት በዘመናዊ ቀፎ ላይ
ትኩረት ያደረገ የንብ ማነብ ልማት
ጀመረ፡፡ እነዚህ ዘመናዊ ቀፎዎች
የማር ምርቱን ጥራት መጠበቅና
የተሻለ ብዛት ማስገኘት ብቻ ሳይሆን
የማር ምርቱ መድረስ አለመድረሱን
ማወቅ ያስችላሉ፡፡

በኢትዮጵያ በባህላዊ ቀፎዎች


የሚጠቀሙ ብዙ አናቢዎች ምርትና
ምርታማነት በጣም ዝቅተኛ ነዉ፡፡
በዓመት ከ5-6 ኪሎ የሚሆን ማር
ብቻ ይቆርጣሉ፡፡ የተሻሻሉ ወይም
ዘመናዊ ቀፎዎች ደግሞ ከ15-40
ኪሎ ማር ድረስ ሊያስገኙ ይችላሉ።
በ1993 አጋማሽ ላይ ብሔራዊ
የማር ምርት በአመት እስከ 24,600
ቶን ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል።
ግምቱ የተወሰደዉ 7.5 ሚሊዮን
የ’ሚሆኑ ባህላዊ ቀፎዎችና 20,000
ከሚሆኑ የተሻሻሉ ዘመናዊ ቀፎዎች
65 ፐርሰንት እና 75 ፐርሰንት
እንደ ቅደም ተከተላቸው የሚደርስ
ምርታማነትን መሰረት በማድረግ
ነዉ፡፡

በአገሪቱ አብዛኛዉ ክፍል፣ በጣም


ቆላማ ወይም በጣም ደጋማ ከሆኑት
አከባቢዎች በስተቀር ንብ ማነብ
እንደ ጓሮ ሥራ የሚወሰድ ተግባር
ነዉ፡፡
www.ipms-ethiopia.org

የእሴት ሰንሰለት ማበልጸጊያ ዘዴ


ምርታማነት ማሻሻያና የገበያ አድርጎ ይወስዳል፡፡ የእውቀት መጋራት
ስኬት ፕሮጀክት የአነስተኛ አርሶ እና የአቅም ግንባታ ጥረቶች ፈጠራንና
አደሮችን ምርትና ምርታማነት ምርታማነትን የሚያጎለብቱ በመሆናቸው
ለማሻሻል አሳታፊ የሆነ ገበያ የሚበረታቱ ናቸው፡፡ የፆታ እኩልነት
ተኮር የእሴት ሰንሰለት ማበልፀጊያ ተመሳሳይ እድል ማግኘትንና የአካባቢ ሀብት
ዘዴ አስተዋውቋል፡፡ ዘዴው ጥበቃ ለዘላቂ እድገት ምሰሶ በመሆናቸው
በራሱ ጥቅል ዘዴ ሲሆን በውስጡ አስፈላጊነታቸውን ያካተተ ዘዴ ነው፡፡ ሊሰራ
ግብአት አቅርቦትን፤ ምርትን፤ የታሰበውን ሥራ መርጦ ያቅዳል፣ ችግሮችን
የግብርና አገልግሎቶችን ይፈትሻል፣ የማሻሻያ ድጋፎችን ያዘጋጃል፡፡
ግብይትንና የንግድ ሥራ ድጋፍ በመጨረሻም ፕሮጀክቱ ከግልና ከመንግሥት
አሰጣጥን እንደ አስፈላጊነቱ የዘርፉ ተዋናይ ጋር በመተባበር ዘዴውን
ያካተተ ነው፡፡ የገበያ ፍላጎትን በተግባር ይተረጎማል፡፡
እና የንግድ መርሆችን (ትርፍ
እና ኪሳራ በመለየት) መሰረት
ያደረገ የአመራረት ስርአት
መከተል የሚያስችል ዘዴ ሲሆን
የግል እና የመንግስት ዘርፍን
የእሴት ሰንሰለቱ ቁልፍ ተዋናይ

የንብ ማነብ የእሴት ሰንሰለት ፍተሻ

ከምርታማነት ማሻሻያና ገበያ ስኬት ከነዚህ የማር ምርቶች ከፊሎቹ ልዩ ስም • ከዚህ በተጨማሪ ዘለቅ ተደርጎ በተሄደ
ፕሮጀክት አስሩ የሙከራ ወረዳዎች ውስጥ ይሰጣቸው ጀመረ፡፡ ለምሳሌ ‹‹የአፅቢ ነጭ ፍተሻ የግሉ ዘርፍ በግብዓት አቅርቦት
በስድስቱ ማለትም በአፅቢ፤ በፎገራ፤ ማር›› የመሳሰሉት፡፡ ወይም አገልግሎት አቅርቦት ላይ
በቡሬ፤ በአድአ፣ በጎማና በአላባ ንብ ማነብ የኢኮኖሚ አቅሙ ደካማ በመሆኑ የተነሳ
እንደ ቀዳሚ ገበያ ተኮር ምርት ተደርጎ በስድስቱ የማር አምራች ወረዳዎች መንግስት በንብ ማነብ የእሴት ሰንሰለት
ተለይቷል፡፡ በነዚህ ወረዳዎች ቀዳሚ የገበያ ውስጥ አሳታፊ የሆነ የመወያያ መድረክ ውስጥ ዋና ተዋናይ ወይም አጋር
ተኮር ምርት ተደርጎ እንዲወሰድ ካስቻሉ በመጠቀም በተጠናቀሩ አስተያየቶች በመሆን በተለይ የዘመናዊ ቀፎዎች
መሰረት የማር ምርት የዕሴት ሰንሰለት አቅርቦትና ማቀናበሪያ መገልገያዎች
እሳቤዎች መሃል፣ ነባሩ ወይም እያደገ ያለው
ውስጥ የሚከተሉት ተግዳሮቶች አቅርቦት ላይ ጉልህ ሚና እንደተጫወተ
የገበያ ፍላጎት፣ የአርሶ አደሩ የማር ምርት
ተስተውለዋል፡፡ ለማስተዋል ተችሏል፡፡
ግንዛቤና ተሳትፎ፣ እንዲሁም የስነምህዳሩ
ተስማሚነት ናቸው፡፡ • ምናልባት በቴክኖሎጂ አቅርቦት
• አምራቾችና አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ትኩረት በመሰጠቱ ይመስላል
በአገራችን የማር ፍላጎት በአብዛኛው በዘመናዊ የንብ ማነብ ልማት ላይ ኤክስቴንሺኑ የተሻሻሉ ዘመናዊ
ያላቸው ዕውቀትና ሙያ ውስን መሆን፣ ቀፎዎች ላይ ትኩረት ያደረገ በዘመቻ
መሰረት ያደረገው የአልኮል ይዘት ያለውን
የጠጅ ወይም አልኮል አልባ የሆነውን • የግብዓትና ልዩ ልዩ መገልገያዎች የሚካሄድ የአሰራር ዘዴን በመከተል
የብርዝ መጠጥ ለማዘጋጀት ነው፡፡ እነዚህ አቅርቦት እጥረት፡- ለምሳሌ የንብ ቀሰም የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል፡፡
መጠጦች አብዛኛውን ግዜ በየቤቱ ወይም ተክሎች፣ የንብ መንጋ፣ የንብ እንጀራ፣ • የተሻሻሉ የንብ ማነብ ማነቆዎች
ጠጅ ቤቶች ውስጥ ይዘጋጃሉ፡፡ ጠጅ መከላከያ ትጥቆች የንብ ማናቢያ በአጠቃላይ ሲታዩ አነስተኛ የንብ
ቁሳቁሶች (ማር መቁረጫ፣ እንጀራ ቀፎዎች ይዞታ እንዲፈጠርና ብሎም
አብዛኛውን ጊዜ በሴቶች ተመርቶ ገቢ
መጋገሪያ ፣ንግስቲቱን ማገጃ፣ወ.ዘተ) አነስተኛ መጠንና በጥራቱ ያነሰ የማር
ያስገኛል፡፡ ዘልማዳዊው የግብይት መንገድ
ጠጅ ጠማቂዎችንና ተጠቃሚዎችን • ለአዲስ የማር ምርቶች እየመጣ ስላለው ምርት እንዲመረት ምክንያት ሆኗል፡፡
ያስተሳስራል፡፡ ገበያ ያለው እውቀትና ተሳትፎ ማነስ፣
• በንብ አናቢዎችና በንብ ማነብ እሴት
ከዚህ ቀደም ብዙም ያልተጻፈለትና ሁለተኛው ሰንሰለት ተዋናዮች መሃል ያለው ትስስር
የማር ምርት ዓይነት በባሕላዊ መንገድ አናሳ መሆን ወይም የትስስሩ ጨርሶ
የሚመረት ሲሆን ማሩ ሳይጣራ ለረጅም ጊዜ አለመኖር፣
እንዲቆይ በማድረግ በተፈጥሯዊ መንገድ
ከተብላላ በኋላ የሚገኝ የማር ምርት ነው፡፡
የዚህ ዓይነቱ የማር ምርት ፍጆታው ለአገር ሰንጠረዥ 1 የማር ግብይት ይዘት
ውስጥ ብቻ ነው፡፡
ነባር ምርት አዲስ ምርት
አዲስ የማር ምርት ለገበያ ማቅረብ ነባር ገበያ ገበያ ውስጥ ዘልቆ ምርትን ማሻሻል
የተጀመረው ከተሻሻሉ የንብ ቀፎዎች መግባት
ትውውቅ ጋር ነው፡፡ ምርቱም ለአገር ውስጥ የግል ነጋዴዎችና ንፁህ ማር ከተሻሻሉ ዘመናዊ
ወይም ከአገር ውጪ ለገበያ ሊውል የሚችል ሸማቾች ጥሬ ማር ከባህላዊ ቀፎዎች
ንፁህ ማር ነው፡፡ በመጀመሪያ የዚህ አይነቱን ቀፎዎች
ማር የማቅረብ ሥራ የተጀመረው በመንደር
አዲስ ገበያ ስራውን ማስፋት
ደረጃ ነበር፡፡ ቀጥሎ ግን ትላልቅ ኩባንያዎች
በአገር ውስጥም በውጭም በከፍተኛ ደረጃ ከተሞችና የውጪ ንግድ ንፁህ ማር ከዘመናዊ ቀፎዎች
ለግብይት በሚሆን መልኩ ማሰናዳት ጀመሩ።

2
የእሴት ሰንሰለት-ንብ ማነብ

የእሴት ሰንሰለት ማበልፀግ


መመሪያዎችን አጠቃሎ ይዟል፡
፡ በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማእከልና
በወረዳ የዕውቀት ማዕከላት ለሚገኙ
የኤክስቴንሽን ሰራተኞች የስልክ
መስመር ካላቸው የኢንተርኔት ግንኙነት
እንዲያገኙ አመቻችቷል፡፡ የኢንተርኔት
ግንኙነት ለማግኘት አስቸጋሪ በሆነባቸው
ወረዳዎች የድረገፁ ግልባጭ ወይም ቅጂ
በDVD እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡
• ፕሮጀክቱ የንብ ማነብ ስራን ግንዛቤ
ለማስፋት ለአምራቾች፣ ለግብርና ልማት
ሰራተኞችና ለአከባቢ አስተዳደሮች
የተሻሻሉ የንብ ማነብ ስራዎች
በሚገኙባቸው ቦታዎችና ዘመናዊ የማር
ማቀናበሪያ ባላቸው ኩባንያዎች ውስጥ
ጥናታዊ ጉብኝት አመቻችቷል፡፡
• ፕሮጀክቱ ተመራቂ ተማሪዎችን
በመደገፍ የመመረቂያ ጽሁፋችዉን ንብ
ማነብ ላይ እንዲሰሩና የጥናት ግኝቶች
በወረዳው ለሚገኙና ለሚመለከታቸው
አካላት እንዲያቀርቡ አድርጓል፡፡
የግብርና ኤክስቴንሽን • ፕሮጀክቱ እውቀትን ለብዙሃን
አሰራር ላይ፣ በስርዓተ ፆታና በኤችአይቪ
ኤክስቴንሽንና በፈጣን የገበያ ጥናት ታዳሚዎች ለማድረስና በጽሁፍ ለመያዝ
እንዲያስችል
በተደረገው ምርምር እንደሚታወቀው ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የእነዚህን
ዘዴዎች አጠቃቀም ለማሳደግና • ‹‹ንብ ከሌለ ማር የለም›› በሚል ርዕስ
የዘመናዊ የንብ ማነብ ልማት ዋና
ለማሰራጨት እንዲቻል የፕሮጀክቱ ህብረ ንብን በከፈላ ማባዛት እንደሚቻል
እንቅፋት ሆኖ የተገኘው በወረዳ
ባልደረቦች ጽሁፎችንና መመሪያዎችን የሚያሳይ ቪድዮ አሰናድቷል፡፡
ደረጃ እውቀትና ክህሎት በበቂ
ሁኔታ አለመኖሩ ነው፡፡ ፈጠራን አዘጋጅተዋል፡፡
በሚያበረታታ መንገድ ሙያውን
መገንባትና እውቀትን መጋራት
እግረመንገዱንም ከብዙ አጋሮች ጋር
የዕውቀት አስተዳደር የእሴት ሰንሰለት ተዋናዮች
ትስስር መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡ • ፕሮጀክቱ ከግብርናና ገጠር ልማት ተሳታፊነትና ትስስር
ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ
የግብርና ፖርታል (EAP-www.eap. በወረዳው የሚገኙ የኤክስቴንሽንና
gov.et) አዘጋጅቷል፡፡ ፖርታሉ የፕሮጀክቱ ባለሙያዎች ከግብዓት
ክህሎትን ማዳበር ከሌሎች ማስተማሪያ መረጃዎች አቅራቢዎች፣ አገልግሎት ሰጪዎችና
በተጨማሪ በንብ ማነብ ላይ የተዘጋጁ ግብይት ድርጅቶች ጋር በመተባበር ቀጥሎ
በወረዳ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሃይል አናሳ ሰነዶች ማለትም አመራረትን፣ ተጠቃሎ በቀረበው የእሴት ሰንሰለት
በመሆኑ ከምርታማነት ማሻሻያና ገበያ ግብይትን፣ የንግድ አገልግሎት የማሻሻያ ድጋፎች መሰረት ትስስር
ስኬት ፕሮጀክት ውጪ ካሉ አሰልጣኞች አሰጣጥ ትምህርቶችንና የስልጠና አንዲፈጠር አድርጓል፡፡
ጋር ትስስር እንዲፈጠር ተደርጓል፡
፡ የገበያ ተሞክሮ ባላቸው መሪ አርሶ
አደሮች (በአፅቢ) ከንግድ ኩባንያ
ባልደረቦች (በአፅቢና ጎማ) ከሆለታ
የንብ ምርምር ማዕከል (አላባና ጎማ)፣
ከአንዳሳ ምርምር (ቡሬና ፎገራ)፣ የግል
አማካሪዎች ከአድአና ከምርታማነት
ማሻሻያና የገበያ ስኬት ፕሮጀክት
አባሎች ጋር ትስስር ተፈጥሯል፡፡ቀደም
ብሎ ከተደረጉት ስልጠናዎች በተቃራኒው
ይህ የቅድሚያ ስልጠና በመስክ ስልጠና
እንዲታገዝ የተደረገና ለተጨማሪ አርሶ
አደሩ እውቀቱንና ክህሎቱን ለማካፈልና
ለማስፋት የሚችልበት የመስክ ጉብኝት
ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በንብ ማነብ ዘዴዎች
ላይ የማሰልጠኛ ጽሁፎችና መመሪያዎች
ተዘጋጅተው ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ እነዚህ
የስልጠና ጽሁፎች ከግብርናና ገጠር
ልማት ሚንስቴር ምርጥ ተሞክሮዎች
ውስጥ አብዛኛውን ክፍል የያዙ ናቸው ፡፡

አሳታፊ በሆነ የእሴት ሰንሰለት ማበልፀጊያ


ዘዴ የስራ ባልደረቦቹን ዝግጁ ለማድረግ
በአሳታፊና ገበያ ተኮር የኤክስቴንሽን

3
www.ipms-ethiopia.org

ግብይትን የሚመለከቱ ድጋፎች አድርጓል፡፡ ምክንያቱም ንብ አናቢዎች


ፕሮጀክቱ የተለያዩ የግብይት መንገዶችን የደረሰውን ማር እየለዩ መቁረጥ
የማስተዋወቅ ስራ በተለይ ለአዲሱና ሲገባቸው ሁሉንም ቀፎዎች በአንድ
ለተሻሻለው የማር ምርት ሰርቷል፡፡ ጊዜ ስለሚቆርጡ በጥራቱ አነስተኛ
ደረጃ የሆነ ማር ይመረታል፡፡
• ከአዳዲስ የግብይት አጋሮች ጋር ትስስር • አነስተኛና ጥቃቅን የህብረት ሥራ
መፍጠርና የዋጋ መረጃ ማቅረብ ማህበራት በቡሬ፣ በአድአ፣ በጎማና
• የአከባቢ የግል ወይም የሕብረት ስራ በአላባ እንዲጠናከሩና ልምዳቸውን
ማህበራት የማቀነባበርና የገበያ አቅም ከአምራቾች ጋር እንዲለዋወጡ
እንዲጠናከር ማድረግ ተደርጓል፡፡ አብዛኛው የህብረት ስራ ሥዕል 1 እርስበርስ ትስስር ያላቸው አራቱ የማር
ማህበራት፣ ቡሬ ከሚገኘው ከግብርናና ማምረቻ ዘዴዎች /ክፍሎች/
• ጥራትን ማሻሻል
ገጠር ልማት ቢሮ ካገኘው ብድር
• የገበያ አቅምንና ተዋናዮችን ለማወቅ በስተቀር ማር ከአባላቱ ገዝቶ ለአዲስ የህብረ ንብ ማር ለማምረት መኖ፣ ውሃና
ፕሮጀክቱ ከግብርናና ገጠር ልማት አበባ ነጋዴዎች የሚሸጥ የለም፡፡ መጠለያ ያስፈልገዋል፡፡ እነዚህን አስፈላጊ
ቢሮዎች በተውጣጡ ሰራተኞችና ነገሮች በአግባቡ ጠብቆ የሚያገናኝና ወጪ
በተማሪዎች አማካኝነት የአካባቢ የእሴት ቆጣቢ በሆነ መንገድ ማር የሚያመርት
ሰንሰለት ጥናት አድርጓል፡፡ የተገኘውም ጥራትን ማሻሻል
ንብ አንቢ መኖር አስፈላጊ ነው፡፡
ውጤት ትስስር ለመፍጠርና የገበያ መረጃን • አብዛኛው የማር ምርት በከፊል
ለመስጠት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ የተቀነባበረም ይሁን ያልተጣራ ማር ዋናዋና የምርት ድጋፍ ዝርዝር
ከወረዳው ውጪ ሲሸጥ አነስተኛ ጥራት መግለጫዎች የነዚህ ድጋፎችና የአጠቃቀም
ባላቸው ማሸጊያዎች ታሽጎ ነው(ለምሳሌ
ከአዳዲስ የግብይት አጋሮች ጋር ዘዴዎች በስልጠና መመሪያዎች ውስጥ
የማዳበሪያ ከረጢት)፡፡ ከንግድ ተገልፀዋል፡፡
ትስስር መፍጠርና የዋጋ መረጃ ማቀናባበሪያዎች ጋር ትስስር በመፍጠር
• የገበያ ትስስር ከተፈጠረባቸው መሃል አምራቾች ምርታቸውን ከፕላስቲክ
የሚከተሉት በምሳሌነት ይጠቀሳሉ በተሰሩ መያዣዎች ወይም በማይዝጉ የተሻሻሉ ዘመናዊ ቀፎዎች
ቆርቆሮዎች እንዲሸጡ ተበረታተዋል፡፡
• የአፅቢ አምራቾች ከዲማ ማር አምራች አጠቃቀም
ድርጅትና ከመቀሌ ነጋዴዎች ጋር
በመሰረቱ ሁለት ዓይነት የተሻሻሉ
• የአድአና የቡሬ አምራቾች ከምሥራቅ ቀፎዎችን መጠቀም ይቻላል፡፡ እነሱም
ሸዋ ንብ አናቢዎች ማህበርና ከቤዛ ማር
ባለፍሬም ቀፎ ወይም ዘመናዊ ቀፎና
ማቀነባበሪያ ጋር
የርብራብ (Top bar) ወይም ሽግግር ቀፎ
• የቡሬ ህብረት ሥራ ማህበራት፣ ከአዲስ የሚባሉ ናቸው፡፡ ባለፉት ጊዜያት ዘመናዊ
አበባ ነጋዴዎችና ህብረት ሥራ ማህበራት ቀፎን መጠቀም በስፋት ተነግሮለታል።
ጋር ይህም ሆኖ የንግድ አገልግሎት ሰጪዎች
• የናዝሬቱ ቤዛ ማርና የኮምቦልቻ የዓለም በሌሉበት ቦታ ፕሮጀክቱ ከዘመናዊ
የማር ሰም ማዘጋጃ ፋብሪካ ከጎማ አምራቾች ቀፎዎች ይልቅ የሽግግር ቀፎዎችን
ጋር መጠቀምን ሲያበረታታ ቆይቷል፡፡
• የቤዛ ማር ማቀነባበሪያ ከአላባ ማር
አምራቾች ጋር የተሻሻሉ ቀፎዎችን ለማስተዋወቅ
በግብርናና ገጠር ልማት ቢሮዎች፣
የአካባቢ፣ የግል ወይም የህብረት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በምግብ
ዋስትና ፕሮግራሞች አማካኝነት የብድር
ሥራ ማህበራት ማቀናበሪያና አገልግሎቶች ተሰጥተዋል፡፡ እነዚህ
የግብይት ሥራን ማጠናከር ድርጅቶችና ፕሮግራሞች ብድሩን በቀጥታ
• ዘመናዊ ቀፎዎች የማር ማጣሪያ ወይም በአነስተኛና ጥቃቅን የብድር
ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቀደም ሲል ይህ የማር ተቋማት አማካኝነት ይሰጡ ነበር፡፡
ማጣሪያ ለሰርቶ ማሳያ ተብሎ በግብርና በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በአላባ፣ በአፅቢና
ቢሮዎች ለተመረጡ ቀበሌዎች ይታደል በጎማ እንደሚፈለገው የቀፎ ብዛትና
ነበር፡፡ ይህ አይነቱ ድጋፍ በመጀመሪያ እንደብድሩ የአመላለስ ሁኔታ እየታየ
ላይ እንደ ትክክለኛ አሰራር ተወስዷል፡፡ በማይክሮ ፋይናንስ በኩል ብድር እንዲሰጥ
ምክንያቱም በየመንደሩ አነስተኛ የንግድ አመቻችቷል፡፡
ማቀናበሪያ ለመጀመር በቂ ደረጃ ላይ
አልነበረም፡፡
• በምሳሌነት ሊቀርቡ የሚችሉ የአከባቢ ምርትን የሚመለከቱ ድጋፎች የቀፎዎች ማስቀመጫ ቦታ
የንግድ ማቀናበሪያዎች ብቅ ብቅ ማለት የማር ምርትን ለማሻሻል ፕሮጀክቱ አያያዝ
ጀምረዋል፡፡ ይሁንና በአፅቢና በአድአ የሚከተሉት አሰራሮች ላይ እገዛ • ቀደም ሲል ቀፎዎች የሚሰቀሉት ለንብ
አንዳነድ (ተንቀሳቃሽ) አገልግሎቶች አድርጓል። የሚሆን የቀስም ተከል ባለበት አካባቢ
በንግድ ተቋማት ይሰጣሉ፡፡ በተመሳሳይ
ነበር፡፡ ይህ ዘዴ ለዘመናዊ ቀፎዎችም
መልኩ በጎማ የዘመናዊ ቀፎዎች ቁጥር • የተሻሻሉ ዘመናዊ ቀፎዎች አጠቃቀም
ተሞክሮ ነበር፡፡ ይሁንና በንቦቹ ላይ
ላቅ ባለበት (ከ8000 ቀፎዎች በላይ) ብዙ • የቀፎ ማስቀመጫ አካባቢና የቀፎ በዱር እንሰሳት፣ በአእዋፋት፣ በጉንዳን፣
በመንደር ደረጃ የሚገኙ ማቀነባበሪያዎች አያያዝ በተባይና በመሳሰሉት የመጠቃት አደጋ
(ከመቶ በላይ) ከራሳቸውና ከጎረቤታቸው
• የንብ አያያዝ ከመድረሱም በላይ ለስርቆት የተጋለጡ
ቀፎዎች ማር መቁረጥ ወይም ማውጣት
• የተጣራ ማር አመራረት ነበሩ፡፡ ለምሳሌ በአፅቢ በማገገም ላይ
ጀምረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ለነዚህ አነስተኛ
በነበሩ ጫካዎች በተሰቀሉ ቀፎዎች ውስጥ
ማቀናበሪያዎች ብድር አመቻችቷል፡፡
የነበሩ ንቦች በጥቁር ወፎች ጥቃት
• በአንዳንድ ቦታዎች እንደሚታየው ደርሶባቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ ባሁኑ
የማቀነባበሪያ መሳሪያ እጦት አነስተኛ ሰዓት ቀፎዎች ከቤት ጓሮ ወይም በቤት
ጥራት ወደአለው የማር ምርት እንዲያመሩ ዙሪያ ጥላ ባለበት አካባቢ ይቀመጣሉ።

4
የእሴት ሰንሰለት-ንብ ማነብ

ንቦችና ቀፎዎችን ከጉንዳን መከላከል፣ የግብዓት አቅርቦትና የመገልገያዎችና የሰም እንጀራ


የቀፎዎች አያያዝ ዓይነተኛ ዘዴ የአገልግሎት አሰጣጥ ድጋፎች አቅርቦት
ነው። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ አካባቢያዊ
የተሻሻለ የማር ምርት የማምረት ሂደትን ከዘመናዊ ቀፎዎች ተገቢውን ጥቅም ልናገኝ
ዘዴዎችና መሳሪያዎች መጠቀም
ይቻላል፡፡ በስራ ለመተርጎም እንዲቻል ፕሮጀክቱ የምንችለው በዘመናዊ መገልገያዎች
በሚከተሉት መንገዶች እገዛ አድርጓል። መጠቀም ስንችል ነው፡፡ ዘመናዊ ቀፎዎች
የሰም እንጀራ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቀደም
የህብረ ንብ አያያዝ • የህብረ ንብ አቅርቦት ሲል የሰሙ እንጀራ በግብርናና ገጠር
ከባህላዊ ወደ ተሻሻሉ ቀፎዎች የተሸጋገሩ • ቀፎዎችንና የንብ ማናቢያ መሣሪዎችን ልማት ቢሮዎች ይቀርብ ነበር፡፡ በጎማ
ህበረ ንብ ብዙውን ጊዜ የተሸጋገሩበትን ቀፎ አቅርቦት ወረዳ ግን አንድ የንብ እርባታ መገልገያ
ለቀው ይወጣሉ፡፡ ይህን ችግር ለማቃለል • የንብ ቀሰም ተክል አያያዝ መሸጫ ሱቅ ጥያቄው ሲቀርብለት ሰሙ
እንዲቻል በህብረ ንብ ማዛወርና አየያዝ ከጥያቄ አቅራቢው አርሶ አደር እየተሰጠው
ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የህብረ ንብ ማባዛትና አቅርቦት ወይም ራሱ ሰሙን እየገዛ ሰርቶ በማቅረብ
ወደ ገበያው መግባት ቻለ፡፡ በተመሳሳይ
• በተለምዶ የንብ መንጋ ማር
መንገድ ማጠኛዎችን፣ መከላከያ
የቀለብና የውሃ አቅርቦት ከሚመርትበት አካባቢ በአርሶ አደሮች
ልብሶችንና ሌሎች መገልገያዎችን ገዝቶ
ይያዛል፡፡ በሌሎች አካባቢዎች
የህብረ ንብ በተለምዶ ከተለያዩ ዕጽዋት በማምጣት ለንብ አናቢዎች በጥሬ
ማለትም ንብ እርባታ ባልተለመደባቸው
የሚያስፈልገውን አበባ መቅሰምና ቦታዎችና የንብ እጥረት ላለባቸው ገንዘብ ወይም ማሩ ከተቆረጠ ወይም
ውሃም ከተፈጥሮ አካባቢ ማግኘት አካባቢዎች ይሸጣል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ከተመረተ በኋላ በማር ምርት የሚከፍሉት
ቢችልም በወቅቶች መለዋወጥ ምክንያት የሚሆኑት አላባ፣ እንዲሁም በጥቂቱ ታስቦ ይሸጥላቸው ጀመረ፡፡ ይህ ንግድ
የሚከሰተውን የንብ ቀሰም ተክሎች እጥረት አፅቢና ቡሬ ናቸው፡፡ እንዲያስፋፋ የመሸጫ ሱቁ ባለቤት
ለመከላከል ሲባል ተጨማሪ ቀለብ መስጠት ብድር ተመቻችቶለታል፡፡ ይህ ተምሳሌት
• ብዙ ወረዳዎች ውስጥ አዲስ የተዋወቁት
እየተለመደ መጥቷል፡፡ በሚገርም ሁኔታ የዘመናዊ ቀፎ ይዞታ በጣም ዝቅተኛ በፎገራ ተከታይ ሊያፈራ ችሎ የግል ሱቅ
ንብ አናቢዎች የራሳቸውን የአመጋገብ ሆኖ ተገኝቷል (በቡሬ 20%ብቻ)፡፡ ተከፍቷል፡፡ በአድአ ደግሞ የምሥራቅ
ስርዓት በመዘርጋት እንደ ዱቄትና ለዚህ ምክንያቱ የንብ መንጋውን ወደ ሸዋ ንብ አናቢዎች ህብረት የንብ ማነቢያ
ስኳር በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ በርበሬ ዘመናዊ ቀፎ የማስገባት እውቀትና መገልገያዎችና ግብአት የሚሸጥበት ሱቅ
የመሳሰለውን ተጨማሪ ምግብ ማቅረብ ክህሎት አነስተኛ መሆንና በተጨማሪ አቋቁመዋል፡፡
ጀምረዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ንብ አርቢዎች ደግሞ በአንዳንድ አካባቢዎች
የውሃ ማቅረቢያ ወይም ማጠጫ እቃዎች በተፈጥሮ ሃብት መመናመን ምክንያት
ንቦችን ውሃው ውስጥ እንዳይሰምጡ የንቦች አለመኖር ሊሆን ይችላል። የንብ ቀሰም ዕፅዋት አያያዝ
በሚከላከል መልኩ መስራት ችለዋል፡፡ ስለዚህ ፕሮጀክቱ የንብ መንጋን የንብ ቀሰም ዕፅዋት የሚገኘው በተፈጥሮ
እንዴት ማካፈል እንደሚቻል ስልጠና ከበቀሉ ወይም ሰው ተክሎ ካበቀላቸው
ሰጥቷል። ዕፅዋቶች ነው፡፡ የንብ ቀሰም ዕፅዋት
በሽታና ተባይን መከላከል አቅርቦት ከቦታ ቦታና ከወቅት ወቅት በእጅጉ
በንቦችና ቀፎዎች አያያዝ ውስጥ ቀፎ መሥራት የሚለያይና የተስተካከለ የአቅርቦት ስልት
ከሚጠቀሱት ዋና ዋና ተግባሮች አንዱ አብዛኛውን ጊዜ ዘመናዊ ቀፎዎች ለመንደፍ የዳሰሳ ጥናት የሚያስፈልገው
ተገቢውን የንፅህና አሰጣጥ መንገዶችን የሚመረቱት በመካከለኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ በተለያዩ አካባቢዎችና ወረዳዎች
መከተል ነው፡፡ ንፅህና ከተለያዩ ፈንገሶችና በሚገኙ ኩባንያዎች ነው፡፡ የቀፎዎቹን ለምሳሌ በአፅቢና በፎገራ በተደረጉ የግጦሽ
ከሰም በልትል ሊከላከልልን ችሏል፡፡ ጥራት የሚቆጣጠሩት የግብርናና ገጠር መሬት ማሻሻያ ድጋፎች የተነሳ የአበባ
ልማት ቢሮዎች ናቸው ፡፡ እነዚህ ምርቶችና የተፈጥሮ አበቦች የአበቃቀል
ዘመናዊ ቀፎዎች ግን ለአርሶ አደሩ ወቅታቸውን ጠብቀው የሚበቅሉት
የተጣራ ማር ማምረት እንዲስፋፉ ረድቷል፡፡ ፕሮጀክቱ በእነዚህ
ውድ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ዋጋቸው
በመጨረሻም አብዛኛው ባህላዊ ቀፎ ማር ከተጨማሪ መገልገያዎች ውጪ ብር የአበባ ክምችቶች አካባቢ የሚኖሩ አርሶ
ሲቆረጥባቸው ጉዳት በሚያስከትልና 550.00 ይደርሳል፡፡ ስለዚህ የአካባቢ አደሮችን የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ጥራት በሌለው መንገድ ስለሚቆረጥ አናፂዎችና ፈጠራን የሚያበረታቱ አርሶ አበረታቷል፡፡ ከተተከሉ ዕፅዋቶች
ማሩ ከሰፈፍና ከእጭ ጋር የተደበላለቀ አደሮች ከአካባቢው በሚገኝ ቁሳቁስ የሚገኘው የንብ ቀሰም ዕፅዋት አብዛኛውን
ነው። ዘመናዊ ቀፎ መጠቀም ከዚህ ጉዳት የርብራብ ቀፎ ወይም ቶፕ ባር ቀፎ ጊዜ ለከብት መኖ ከተተከሉ ተክሎች
የሚከላከልና በቀላሉ ማሩን በመቁረጥ የሚባለውን መስራት እንዲችሉ ስልጠና ወይም ለምግብነት ከሚውሉ ተክሎች
ንፁህ ምርት ማግኘት ያስችላል፡፡ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህም በወረዳ ደረጃ የሚገኝ ነው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው
ተጨማሪ ገቢ ሊያስገኝ የሚችል የስራ የአልፋአልፋ ተክል፣ ሴስፓንያ ሊዩካኒያ
መስክ ሊፈጠር ችሏል፡፡ የመሳሰሉት ሲሆኑ ከምግብ ተክሎች ደግሞ
የቡና ተክል፣ የቅባት እህሎችና የፍራፍሬ
ዛፎች የመሳሰሉት ናቸው፡፡

5
www.ipms-ethiopia.org

ተጨባጭ ወይም ሊለኩ የሚችሉ ግኝቶች

ምርት፣ ምርታማነትና ገቢ
በ2000 ዓ.ም ፕሮጀክቱ ዘመናዊ ቀፎ
በሚጠቀሙና በባህላዊ ቀፎ በሚጠቀሙ
ቤተሰቦች መሃል ያለውን ልዩነትና
ያሳደረውን ተፅዕኖ ለማወቅ የዳሰሳ ጥናት
አድርጎ ነበር፡፡ በተደረገው ጥናት በሁሉም
ጣቢያዎች የተሻሻሉ ዘመናዊ ቀፎዎችን
ከዘመናዊ አሰራር ጋር የሚጠቀሙ
ቤተሰቦች በአማካይ የተሻለ ቁጥር ያለው
ቀፎ አላቸው (ዘመናዊም ባህላዊም)።
የዓመት የማር ምርታችውም ከፍተኛ
ስዕል2: አማካኝ የማር ምርታማነት በቀፎ አይነት ስዕል2 አማካኝ የማር ምርታማነት በቀፎ አይነት
ነው፡፡ የተሻለ ዓመታዊ ገቢም አግኝተዋል
(ግራፍ 2 እና 3 ይመልከቱ)፡፡ በአላባ
ወረዳ እያንዳንዳቸው 5 የተሻሻሉ ቀፎዎች የአገልግሎት ዋጋ 60
ባሏቸው 17 አርሶ አደሮች ላይ የቀፎ ሳንቲም ለያንዳንዱ የሰም 30
ምርታማነት መረጃ ተወስዶ በአማካይ 13 እንጀራ ያስከፍላል፡፡ 25
ኪሎ ግራም ማር በቀፎ በመጀመሪያው
ዓመት የተገኘ ሲሆን በሁለተኛው ዓመት በአከባቢ በተሰሩ 20
38 ኪሎ ግራም ማር በቀፎ ማምረት የማር ማጣሪያ
መቻላቸውን ያረጋግጣል፡፡ የሚጠቀሙ አነስተኛ 15
የማር ማቀናበሪያዎች
በአብዛኛው ማር 10
የግብዓት አቅርቦትና ግብይት አምራቾች ለራሳቸው
ቀፎ ይጠቀሙባቸዋል። 5
የህብረ ንብ ማራባት በአፅቢ፣ በፎገራ፣ ለጎረቤት አርሶ
በቡሬና በአላባ በሚገኙ አንዳንድ ማር አደሮችም በቀን 50 0
አምራቾች ተጀምሮ ነበር፡፡ ነገር ግን ብር ወይም በቀፎ 10
እስካሁን ድረስ አብዛኛው አምራች ብር ሂሳብ የአገልግሎት ስዕል3: አማካይ የማር ምርት በቤተሰብ
ያረባውን ንብ ለገበያ አያቀርብም። በቡሬ ያስከፍላሉ፡፡
የሚገኙ አንዳንድ የሰለጠኑ አርሶ አደሮች
ከስልጠናው ያገኙትን አዲስ ትምህርት
ለጎረቤት አርሶ አደሮች ሲያካፍሉ
ስርዓተ ፆታ እጥረት ሊከሰት ይችላል፡፡ በሌላ በኩል
በባህላችን የማር ማምረት ሥራ በወንዶች ደግሞ በመሬት አያያዝ ወይም በአፈር
ተስተውለዋል፡፡ የህብረ ንብ ፍላጎት
የበላይነት የተያዘ ስራ ነው። ምክንያቱም አጠባበቅ ስራ ላይ በተደረጉ ለውጦች
እየጨመረ በመሄዱ ገበያ ላይ በአንዳንድ
ቀፎዎች የሚሰቀሉት በጫካ ውስጥና ረዘም እንዲሁም የግጦሽ መሬት እንዲያገግም
ቦታዎች ዋጋው በእጥፍ እያደገ ሄዷል።
ባለ ዛፍ ላይ ስለሆነና የማር አቆራረጡም ሲደረግ (በአፅቢና በፎገራ እንደታየው)
የአንድ ህብረ ንብ ዋጋ እስከ ብር
ብክነት የተሞላበትና ቆራጩን ለአደጋ በበጋ ወራት ብዙ አበቦች እንደበቀሉና
500.00 ድረስ ማውጣት ችሏል (ዋጋው
የሚያጋልጥ ነው፡፡ ይሁንና ጥቂት አዎንታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ተስተውሏል።
እንደገበያው ሁኔታና የህብረ ንቡ መንጋው
ሴቶች ጠጅ ጠምቀው ከመሸጥ ጥቅም የመስኖ ስራዎችም በድርቅ ወራት አበቦች
ጥራት ሊለያይ ይችላል)፡፡ ከዚህ የተነሳ
እንደሚያገኙ ታውቆአል፡፡ በብዛት እንዲበቅሉ ያደርጋሉ (ለምሳሌ
የህብረ ንብ ማርባት አትራፊ የሆነ ስራ
የሽንኩርት ዘር)፡፡
ሆኗል፡፡ በዚህም ምክንያት ፕሮጀክቱ
አሁን ግን ፆታን ከግምት ያስገባ ስልጠና
እጥረት በታየባቸው ቦታዎች የህብረ ሆኖም የተለያዩ የፀረ ተባይ መድሃኒቶችና
ስለሚሰጥና አሰራሩን ቀና የሚያደርግ
ንብ ማርባት ለሚችሉ ልዩ አርሶ አደሮች የፀረ አረም መድሃኒቶች በንብ መንጋ
የተሻሻለ ቀፎ በጓሮ በማስቀመጥ የንብ
ስልጠና እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ
ማነብ ሥራ መስራት መቻሉ ለሴቶች
የተመቻቸ ሥራ ሆኗል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
በቡሬ፣ በጎማ፣ በፎገራና በአላባ የአካባቢ
አናፂዎች ወይም አርሶ አደሮች ቀፎ በአንዳንድ ወረዳዎች ጥቂት ሴት ንብ
መስራት እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ ይህ አናቢዎች ይገኛሉ፡፡ ተዋናዮችና ተሳትፎ
ነው ሊባል የሚችል ችግር እስካሁን
የንብ ሃብት የእሴት ሰንሰለት ማሻሻያ ዘዴ
አልገጠመም፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ከመጠቀም የተነሳ ከአዳዲስ የንብ እርባታ
በጎማ የሰም እንጀራ አቅርቦት እንደቀጠለ የንብ ማነብ ስራ ከሌሎች የግብርና እሴት ተዋናዮች ጋር ትስስር መፍጠር
ነው፡፡ የሰም እንጀራ መጋገሪያ መሳሪያ ስራዎች ጋር ባለው አዎንታዊ ግንኙነት ከመቻሉም በላይ አዳዲስ ተሳትፎዎችም
ለመግዛት ከብር 5000 እስከ ብር 7000 ይታወቃል፡፡ ይኸውም ንቦች ከአበባ ወደ ብቅ እያሉ ናቸው፡፡
ያስፈልጋል፡፡ በጎማ የሚገኝ አንድ አበባ በሚያደርጉት የመቅሰም ሂደት
ባለሱቅ የሰም እንጀራን በተለያየ መጠን ሰብሉ ጥሩ ፍሬ እንዲያፈራ ስለሚያደርጉ
ያመርታል፡፡ ሙሉ መጠን የሆነው የግብርና ስራውን ይደግፋሉ፡፡
እያንዳንዱ ብር 10 ሲሸጥ አነስተኛ
መጠን ያላቸው ደግሞ ከብር 2-3 ይሁንና በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን
ያወጣሉ። የሰም መግዣ ዋጋ በኪሎ 60 በአንዳነድ ቦታዎች በንብ ማነብ
ብር ነው። 1 ኪሎ ሰም 10 ትልልቅ መጠን ሥራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲደርስ
ያለው እንጀራ ይወጣዋል፡፡ የራሳቸውን ተስተውሏል፡፡ ይኸውም የሰብል ዓይነት
ሰም ይዘው ለሚመጡ ማር አምራቾች ሲለወጥ (በፎገራ የቅባት እህል ላይ
እንደታየው አይነት ለውጥ) የንብ መኖ

6
የእሴት ሰንሰለት-ንብ ማነብ

አስተምሮቶች፣ ተግዳሮቶችና ጠቃሚ አስተያየቶች


የግብርና ኤክስቴንሽን ግብይት ምርት
የምርታማነት ማሻሻያና የገበያ ስኬት በከፍተኛ መጠን ለንግድ ከሚያቀነባብሩ ንብ ማነብ ወደ ንግድ ለመግባት ገና
ፕሮጀክት የተጠቀመው ዘዴ በንብ ማነብ ተዋናዮች ጋር የሚደረገው ግንኙነት በሆነበት ጊዜና ለግብዓት አቅርቦት፣
እሴት ሰንሰለት ውስጥ ለየወረዳው እስከ አሁን ወደ መደበኛ ኮንትራት ማቀናበርና ግብይት የሚቀርቡ ድጋፎች
ተስማሚ የሚሆነውን የግብይት፣ የግብዓት ውስጥ አልገባም፡፡ ምክንያቶቹም ውሱን በሆኑበት ጊዜ የኬንያ ቶፕ ባር
አቅርቦትና የማር ምርት ማሻሻያዎችን አንደኛ አቅርቦቱ አናሳ በመሆኑ ሁለተኛ (Kenya Top Bar) ወይም የሽግግር
ለመንደፍ አስችሏል፡፡ የፍላጎት መዋዠቅ ስለሚታይበት ሶስተኛ ቀፎዎችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
ጥራት ያለው ማር ባለመኖሩና በዋጋ ላይ
የንብ ማነብ የእውቀትና የሙያ እጥረት በአየር ንብረት መዛባት የተነሳ ምርት
ከስምምነት አለመድረስ እንዲሁም የዋጋ
በመንግስት ሰራተኞችና በንብ አንቢዎች ባልታሰበ መጠን ሊዋዥቅ ይችላል፡፡
ማበረታቻ ባለመኖሩ ናቸው፡፡
መኖሩ ስለሚታወቅ አማራጭ የእውቀት አብዛኛው አርሶ አደር በቂ ምርት ለማግኘት
አጠቃቀምና የክህሎት ማዳበር ስርዓት በንብ አናቢዎችና በንግድ ተዋናዮች ቢያንስ ሁለት ዓመት ያስፈልገዋል፡፡
በተሳካ መልኩ ስራ ላይ ውሏል፡፡ መካከል ያለውን ግጭት ለማስቀረት በአካባቢ ከሚኖረው የንብ ቀሰም ዕፅዋት
በተጨማሪም የንብ አንቢዎች ያመነጩት ወኪሎቻቸው ወይም ባሕላዊ ነጋዴዎች ክምችትና ከአርሶ አደሩ የግል ችሎታና
እውቀት ወይም ከኢንተርኔት ላይ ከአቀነባባሪ ተቋም ተዋናይ ጋር ትስስር አቅም ጋር እየታየ አንድ አርሶ አደር
የተገኘ እውቀት እንዲሁም ከንብ ማነብ መፍጠር የሚያስችል ዘዴና ብልሃት ሊኖረው የሚገባ የንብ ቀፎ ብዛት ከፍና
ኢንዱስትሪ የተገኙ አሰልጣኞች ተሳትፎ መፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡ ዝቅ ሊል ይችላል፡፡ ለንብ ማነብ ቴክኖሎጂ
እንደ አንድ የእውቀትና የክህሎት የሚሰጥ የብድር ድጋፍም ይህንን መሰረት
ማዳበሪያ ዘዴ ተወስደዋል፡፡ በተወሰነ መልከዓ ምድራዊ ክልል ውስጥ ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡
በበቂ ሁኔታ የደረጀ ማለት ከ50-60
ፕሮጀክቱ የኤክስቴንሽን ሰራተኞችንና የሚደርሱ ቀፎዎች ላይ ማምረት ከተቻለ
የአምራቾችን እውቀትና ሙያ የግል ወይም የህብረት ስራ ማህበራት የግብዓት አቅርቦት
የሚያበረታታ ዘዴ የሚጠቀም ቢሆንም በዘመናዊ ቀፎ መስራት አዋጪ ለተለያዩ ግብዓቶችና አገልግሎቶች
ለወደፊቱ በንብ ማነብ ብቃት ያላቸው ይሆንላቸዋል፡፡ የአነስተኛና ጥቃቅን አቅርቦት አማራጭ ዘዴዎች ብቅ ብቅ
ባለሙያዎችና አምራቾችን የማፍራት የብድር ተቋማትም እነዚህን አነስተኛ እያሉ ነው፡፡ አብዛኛውን አማራጭ የያዙት
ሃላፊነት የተሰጠው የትምህርት ተቋም ላይ ማምረቻዎችን በገንዘብ መደገፍ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች ናቸው፡፡ አማራጭ
ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይኖርባቸዋል፡፡ አቅርቦት፣ የህብረ ንብ ማምረትን፣ የሰም
የንብ ማነብ የእሴት ሰንሰለትን ለማበልፀግ እንጀራ መስራትን፣ መገልገያዎችን
የተጣራ ማር አቅርቦት የአካባቢ
ቁልፍ የሆኑትን የንብ አንቢዎች ማምረትና ማቅረብ እንዲሁም በባለሙያ
የገበያ ፍላጎትን እየበለጠ ከሄደ ያሉት
የእውቀትና የግብዓት አቅራቢዎች አርሶ አደሮችና አናፂዎች ቀፎ መስራትን
የግል ወይም የህብረት ስራ ማህበራት
የአገልግሎት ሰጪዎችና የግብይት ያጠቃልላል፡፡
አምራቾችን ከከተማ የግብዓት ማዕከላት
ተጠሪዎች የእርስ በርስ ትስስር መፍጠር ወይም አቀነባባሪዎች ጋር ለማገናኘት ለዘመናዊ ቀፎዎች የሚያስፈልገውን
ነው፡፡ ይጠቅማሉ፡፡ እንጀራ መስሪያ ሰም ለመስራትና
እየጨመረ የሚሄደውን የሰም ፍላጎት
ለማርካት ባህላዊና የሽግግር ቀፎዎችም ጎን
ለጎን እንዲያመርቱ መደረግ አለባቸው፡፡

7
የሕብረት ሥራ ማህበራት ተመሳሳይ
ግበዓት ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ይህን
ለማድረግ የግብርና ንግድ ሥራ
አስተሳሰብ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

በገበያ መር የንብ ማነብ ሥራ ላይ


በተሰማሩ ወረዳዎች ውስጥ የማር
ምርት ግብይትንና የግብዓት አቅርቦትን
እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥን
አጣምረው በግልም ይሁን በማህበር
የሚሰሩ ክፍሎች እንደ ንግድ ሥራ
ሞዴል ሊታዩ ይገባል፡፡ይህን ለመደገፍና
ለማበረታታት ብድርም ሊመቻችላቸው
ይገባል፡፡

የምርምር ውጤቶችና ህትመቶች

ለህትመቶችና ሌሎች ዶክመንቴሽን

ፕሮጀክት ድረ ገፅ: http//:www.ipms-ethiopia.org

የኢትዮጵያ ግብርና ፖርታል: http//:www.eap.gov.et

በኢትዮያ ፌደራል ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ


Canadian International Agence canadienne de የግብርና ሚኒስቴር
Development Agency développement international Federal Democratic Repulic of Ethiopia
Ministry of Agriculture

የህ ፅሁፍ ክርኤቲቭ ኮመንስ የሚባለውን የፈጠራ መብት የያዘ ስለሆነ ያለ ባለመብቱ ፍቃድ ከንግድ በስተቀር ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል። ታህሳስ 2005

You might also like