You are on page 1of 4

64% 6:49 AM

87.73k/s

ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀት General

knowledge ethiohakim

December 13, 2019 at 4:47 PM. Facebook for Android

የእንጉዳይ የጤና በረከቶች

እንጉዳይ በቀደምት ህዝቦች ዘንድ ለጥንቆላና ለመሳሰለው ተግባር

ያገለግላል ተብሎ ይታመን ነበር።

የግብጽ ፈርኦኖች እንጉዳይን ለራሳቸው ብቻ በመያዝ ተራው ህዝብ

እንዳይመገበው ይከለክሉ እንደነበር ይነገራል።

ሮማውያንም እንጉዳይ የአማልክት ምግብ food of the gods” "

ነው የሚል ህግ አጽድቀው ተራው ህዝብ እንዳይመገበው ሲያደርጉ

እንደኖሩም የኃላ ታሪካቸው ይመሰክራል።

ግሪካዊያን ደግሞ ለተዋጊ ጦረኞች ሀይልን ያጎናጽፋል ብለው ያምኑ

ነበር፡፡

እንጉዳይ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ 1600 ዎቹ ጀምሮ

በተለይም በፈረንሳይ ለምግብነት መዋል እንደጀመረ ይነገራል፡፡

በአለማችን 14 ሺህ አይነት እንጉዳዮች ቢኖሩም 3 ሺህ ያህሉ ብቻ

ናቸው ለምግብነት የሚውሉት።

በሀገራችንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት እየተመረተ ለሀገር ውስጥና

ለውጭ ገበያ በመቅረብ ላይ ይገኛል።

እንጉዳይ የሚያስገኛቸውን የጤና በረከቶች ደግሞ ቀጥለን

እንመልከት፡

1. ክብደት ለመቀነስ ይረዳል

እንጉዳይ ዝቅተኛ ካሎሪ በመያዙ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች

ይሰጣል፡፡
ክብደታችንን ለመቀነስ ለምንፈልግ ሰዎች ብናዘወትረው የሚመከር

የምግብ አይነት ነው። ዝቅተኛ ካርቦሃይድሬትና ስብ የያዘ መሆኑም

ተመራጭ ያደርገዋል።

2. እንጉዳይና ቫይታሚን ዲ

ለበጥና ጥመ 1 ለህ ጋጠ ና መ መበጠ..ጢ |

ተመራጭ ያደርገዋል።

2. እንጉዳይና ቫይታሚን ዲ

በሀገራችንም ሆነ በሌላው አለም የሚዘወተረው button mush

room የተሰኘ ነጭ እንጉዳይ የቫይታሚን B2 እና D3 ጥሩ መገኛ

ነው። ይህም በሽታ የመከላከል አቅማችን ያሳድጋል።

የአሜሪካ የስነ ምግብ ማህበር በነጭ እንጉዳይ ላይ ባካሄደው አንድ

ጥናት በሰውነታችን ውስጥ የአንቲቫይራል እና የፕሮቲኖችን መመረት

በማፋጠን የሰውነት ጤንነት እንደሚጠብቅ አረጋግጧል።

እንጉዳይ ከመቅኔ የሚሰሩ dendritic cells የተሰኙ በሽታዎች

ተከላካይ ህዋሳትን መመረት ያበረታታል የሚለውም በሌላ ጥናት ይፋ

ተደርጓል።

3. ኮሌስትሮል ይቀንሳል

እንጉዳይ ኮሌስትሮልና ስብ የሌለው የተጣራ ፕሮቲን ይሰጣል።

ከዚህም በተጨማሪ ኮሌስትሮልን የሚቀንሱ ኢንዛይሞችን ስራም

ያግዛል። ስታርች አልባ የሆኑትን chitin እና beta-glucan የተሰኙ

ፖሊሳካራይደስ በማቅረብ የኮሊስትሮል መጠን እንዲቀንስ ያግዛል።

4. የስኳር በሽታና እንጉዳይ

እንጉዳይ ዝቅተኛ ሃይል ሰጪ መሆኑ ለስኳር ህመምተኞች ተመራጭ

ምግብ አድርጎታል።

ከፍተኛ ፕሮቲን፣ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችና ቫይታሚኖች እንዲሁም በቂ

ውሃና የሚፈጭ አሰር መያዙም በርካታ ጥቅም እንዲኖረው


አድርጎታል።

በተጨሚሪም ሙሉ ለሙሉ ተፈጥሯዊ የሆኑ ኢንሱሊንና ኢንዛይሞችን

በመያዙ ስኳርና ስታርችነት ያለባቸውን ነገሮች ለመሰባበር ይረዳል።

የስኳር ህመምተኞች በተደጋጋሚ በኢንፌክሽን (በተለይም

በእግሮቻቸው ላይ) ይጠቃሉ፡፡ እንጉዳይ ከዚህ ችግር በሚገላግሉ

ተፈጥሯዊ አንቲባዮቲኮች የተሞላ ነው።

5. ካንሰርን ይከላከላል

እንጉዳይ በውስጡ በያዛቸው በሽታ ተከላካይ ፖሊስካራይድስ እና

antitumor agente poco+Mbabaha..

በመያዙ ስኳርና ስታርችነት ያለባቸውን ነገሮች ለመሰባበር ይረዳል።

የስኳር ህመምተኞች በተደጋጋሚ በኢንፌክሽን (በተለይም

በእግሮቻቸው ላይ) ይጠቃሉ፡ እንጉዳይ ከዚህ ችግር በሚገላግሉ

ተፈጥሯዊ አንቲባዮቲኮች የተሞላ ነው።

5. ካንሰርን ይከላከላል

እንጉዳይ በውስጡ በያዛቸው በሽታ ተከላካይ ፖሊስካራይድስ እና

anti-tumor agents የካንሰር በሽታን ለመከላከል ያግዛል።

6. የምግብ ውህደትን ያፋጥናል

እንጉዳይ በቫይታሚኖች የበለጸገ ሲሆን በተለይም በውስጥ የያዘው

ቫይታሚን ቢ ሰውነታችን ምግብን በቀጥታ ወደ ሃይል ምንጭነት

እንዲቀይር ያግዛል።

ይህ የምግብ ኡደት መፋጠንም ክብደታቸውን ለመቀነስና

ለመቆጣጠር ለሚፈልጉ ሰዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።

7. የቆዳ ጤንነትን ይጠብቃል

ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ የሚይዘው እንጉዳይ ለቆዳ ጤንነት ጠቃሚ

ነው።

ቆዳን ከማቀዝቀዙም በላይ ወዙን እንዲጠብቅም ያስችላል።


እንጉዳይ ቆዳን ማሳመር ብቻ ሳይሆን ሽፍታዎችንና በማሳከክ

የሚከሰቱ ቁስሎችን ይቀንሳል።

8. የደም ግፊትን ይቀንሳል

እንጉዳይ የደም ግፊትን በሚቀንሰውና በልብ ድካም መጠቃትን

በሚያስቀረው ፖታሲየም የበለጸገ ነው።

የፖታሲየም ይዘቱ ከሙዝና ከአንድ ብርጭቆ የብርቱካን ጭማቂ

እንደሚበልጥ ነው የሚነገረው።

መልካም ጤንነት!!

| ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

ዶክተር ቤዛ አያሌው የቴሌግራም ገፅ ፦

@yourhealthethiopia

https://t.me/yourhealthethiopia/2562

You might also like