You are on page 1of 24

ዋና ማጠቃለያ

በኢትዮጵያ ውስጥ የእህል ገበያ የዋጋ መለዋወጥ መገለጨው ሲሆን ለዚህም በዋነኝነት መንስኤዎቹ የምርት ወቅታዊ
መሆን፣ ውስን መጋዘን መኖር እና የበርካታ አርሶአደሮች ዝቅተኛ የማከማቸት ስርአት/ልምምድ በምክንያትነት
ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ንግድ በሚገኝባቸው ስፍራዎች አርሶአደሮች እህል የሚያመርቱት በዓመት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ነው፡፡
በቁጥር አብላጫዎቹ አርሶአደሮች ተገቢ የሆነ ማከማቸት የማያውቁ እና ዝቅተኛ የማከማቸት ስርአት የሚከተሉ
ናቸው፡፡ ስለሆነም ይህ የንግድ በሠብል ግብይት ውስጥ ያለውን ክፍተት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አመቱን ሙሉ
በተፎካካሪ ዋጋ የእህል አቅርቦትን ወጥ ማድረግ ላይ ያተኩራል፡፡

ይህ ንግድ ደንበኞች የሚፈልጉትን የጥራት ደረጃ በማቅረብ እና ቢያንስ በሁለት ደረጃ የበቆሎ እህል በተለያየ ኪሎግራም
መጠን ማቅረብን ያካትታል፡፡ በተጨማሪም፤ ሌሎች ሠብሎች በገበያ ካሉ ለምሳሌ ባቄላ፣ ስንዴ እና ጤፍ በተመጣታኝ ዋጋ
ያቀርባሉ፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ እንተርፕራይዝ የሚሰጠው ሌላ አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ ለበርካታ አርሶአደሮች
የመመዘን፣ የማሸግ እና በመጋዘን ማከማቸትን ያካትታል፡፡ ይህ ንግድ በተመጣጣኝ ዋጋ ያልተስተጓጎለ የሰብል አቅርቦት
ለደንበኞች በአመቺ ሁኔታ ያቀርባል፡፡

ይህ ንግድ “ናቡር አርሶአደሮች ህብረት ሥራ ማህበር” በሚል መጠርያ የተመዘገበ ሲሆን ይህም የመጀመርያ ደረጃ
ህብረት ሥራ ማህበር ሲሆን ባለቤትነቱ የህብረት ሥራ ማህበር አባላቶች ነው፡፡ የንግድ አድራሻው በመስካን ወረዳ፣
በጉራጌ ዞን፣ ደቡባዊ ክልል ውስጥ የተመዘገበ ነው፡፡

የታቀደው የንግዱ ጠቅላላ ኢንቨስተመንት ዋጋ 520,820.00 ይሆናል፡፡ መህበሩ ከጠቅላላው 520,820.00 ውስጥ 99,166.70

የመሬት፣ ሕንጻ እና ሌሎች ቅድመ-ሥራ ወጪዎች ለመሸፈን ችሏል፡፡ ለቀሪው የፕሮጀክት ዋጋ ማለትም 421,653.30 ብድር

አስፈላጊ ይሆናል፡፡ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ለ 10 አመታት በሚገመትበት ወቅት ይህ ንግድ የተጣራ የአሁኑ ዋጋ 931,281 ብር እና

42 በመቶ ዓመታዊ የዕድገት መጠን ይኖረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በዓመት ለ 5 ግለሰቦች ቋሚ እንዲሁም ለ 76 የትርፍ ሰአት የቀን

ሠራተኞች የስራ እድል ይፈጥራል፡፡


1. የሁኔታ ትንተና

1.1. የኢንዱስትሪ አጠቃላይ ምልከታ፡- ግብርና ንግድ በኢትዮጵያ ውስጥ

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ አግሪቢዝነስ/የግብርና ንግድ በለጋ ደረጃው ላይ የሚገኝ ሲሆን በበርካታ እርስ በእርስ በተያያዙ
ምክንያቶች የተገደበ ነው፡፡ እነዚህም የገበያ መረጃ አለመኖር (ምን አይነት መረጃ እንደሚያስፈልግ እና እንዴት መጠቀም
ወይም ማግኘት እንደሚቻል አለማወቅ)፣ ገንዘብ አለመኖር (ብድር ወይም ንብረት) (የመነሻ ካፒታል አለመኖር
እንዲሁም ብድር አለመኖር)፣ ዝቅተኛ መሠረተ ልማት (ዝቅተኛ ምርት ካለባቸው አካባቢዎች እና ከአለምአቀፍ አየር
መንገዶች የራቀ ትስስር)፣ ደካማ የምርምርና ስርጸት አገልግሎት (ሰፊ ፤ ምርት መሰረት ያደረገ የምርምር እጦትና የበለጸገ የስርጭት
ስልት/ዘዴ የግብርና ንግድ ዕድገት መገደብ)፣ ዝቅተኛ የንግድ እውቀት (የንግድ ድርጅት ባለቤቶች እና ሠራተኞች ተገቢ የንግድ
እውቀትና የማስተዳደር ክህሎት ክሌላቸው ንግዱን በውጤታማነት ማንቀሳቀስ አይችሉም)፡፡

እነዚህን አነስተኛ አምራቾች ከእሴት ጨማሪ ድርጅቶች ጋር እንዲመቻቹ ለማድረግ በርካታ አካላት በቅርበት
አብረዋቸው እየሰሩ የሚገኝ ሲሆን አምራች በእህል ማምረት ዘርፍ ላይ በማተኮር አስፈላጊ የሆኑ የድጋፍ አገልግሎቶችን
በማቅረብ ወደ ከፍተኛ ትርፍ ወይም ወድተሸለ ጥራት የሚመራ ይሆናል፡፡ ከእነዚህ የድጋፍ አገልግሎት አቅራቢዎች
ወይም እሴት ጨማሪ ተዋናዮች መካከል ዋነኛ የሆኑት ማህበረሰብ ተኮር የቤተሰብ ድርጅቶች ፣ የግብይት ህብረት ስራ
ማህበራት፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ድርጅቶች እና ሌሎች ጅምላ አከፋፋዮች እና ችርቻሮ ነጋዴዎች ናቸው፡፡

ከእነዚህ መካከል፤ ጥቃቅንና አነስተኛ እንተርፕራይዞችና እና የግብርና ምርቶች ግብይት ላይ የሚሰሩት የህብረት ሥራ
ማህበራት በዋነኝነት ደረጃ በመስጠት፣ ጥራትን በማሻሻል እና የገበያ ተደራሽነትን በመጨመር፣ በብዛት ና በአነስተኛ
መጠን በመሸጥ እሴት መጨመርን ያካተተ ነው፡፡

የበቆሎ መገኛ ከአሜሪካ ሞቃታማ ክፍል ሲሆን አሁን በአለም አቀፍ ደረጃ በስፋት የሚበቅል የሠብል ምርት ሆኗል፡፡
በተለይም ባላደጉ ሀገራት በጣም ጠቃሚ ሰብል ነው፡፡ በተጨማሪም በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ በስፋት እየተመረተ የሰብል
ዓይነት ነው፡፡ከ 16 ኛ እስከ 17 ኛ ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ የሚታመን ሲሆን በጣም ጠቃሚ የሰብል አይነት
በመሆን በስፋት ከባህር ወለል በላይ ከ 500 እስከ 2400 ሜትር ስነምህዳር ሊበቅል የሚችል ሰብል ነው፡፡ እንደ ማዕከላዊ
ስታትስቲክስ ባለስልጣን (2013) ሪፖርቶች መሠረት በቆሎ በሀገሪቷ የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ በመብቀል ላይ ይገኛል፡፡
በምርት ረገድ በቆሎ የኢትዮጵያ መሪ/ዋና የሰብል እህል ለመሆን ችሏል፡፡ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያዊ
አርሶአደሮች በቆሎ የሚያመርቱ ሲሆን አብዛኛዎቹም ለመተዳደርያነት ይገለገሉበታል፡፡ በ 2013/14 እንደ አውሮፓ
አቆጣጠር 8.8 ሚሊዮን የሚሆኑ አርሶአደሮች 6.5 ሚሊዮን ቶን የሚሆን በቆሎ በ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ
አምርትዋል ፡፡

1.2. ሰብሉ የሚመረትበትና የሚሸጥበት አካባቢ


መስካን ወረዳ በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን፣ ውስጥ ይገኛል፡፡ ወረዳው የበቆሎ ሰብል በማምረት ይታወቃል፡፡
በአካባቢው/ወረዳው ውስጥ የሚመረቱ ሌሎች ሰብሎች ባቄላ፣ ስንዴ፣ ጤፍ እና ማሽላን ያካትታል፡፡ በአካባቢው የሚገኙ
አብዛኛዎቹ አርሶአደሮች በዋነኝነት በቆሎ እና ባቄላ ያመርታሉ፡፡

1.3. የንግድ ዝርዝር መግለጫ

ፕሮጀክቱ የእህል ግብይት ህብረት ስራ ማህበር በተለይም በበቆሎ ሰብል ሽያጭ ዘርፍ ላይ ማቋቋምን ያካትታል፡፡ ይህ
የበቆሎ ሰብል ግብይት ህብረት ስራ ማህበር በዋናነት የበቆሎ ሰብል እሴት በመጨመር በጣም ተፎካካሪ በሆነ ዋጋ ደንበኞችን
ታሳቢ ባደረገ ዋጋ በመሸጥ (ችርቻሮ፣ ግለሰብ ደንበኞች፣ ሌላ አቀናባሪ ጥቃቅንና አነስተኛ እንተርፕራይዞች እና ህብረት
ስራ ማህበራት) ያለመ ነው፡፡ ሌሎች በአካባቢው የሚመረቱ እንደ ባቄላ፣ ስንዴ፣ ጤፍ ያሉ ሰብሎች የድርጅቱን ስጋት/አደጋን
በአነስተኛ መጠን ይሸጣሉ፡፡

በቆሎ በውስን ዋጋ ከአካባቢው አርሶአደሮች እና አባላቶች የሚገዛ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ጥራትን መሠረት በማድረግ
ተመርምሮ፣ ክብደቱ ተመዝኖ እና በተቀመጠለት ጥራት ደረጃ ተሰጥቶት በስተመጨረሻ ለሽያጭ ዝግጁ እስከሚሆን ድረስ
በመጋዘን የሚከማች ይሆናል፡፡

የህብረት ስራ ማህበሩ ለደንበኞቹ በተወዳዳሪ ዋጋ በተለያየ የኪሎግራም መጠንና እና ደረጃ በቆሎን የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

2. አካባቢያዊ ትንተና

የአጠቃላይ አካባቢዎች ትንተና በድርጂቱ የንግድ ሁኔታ ላይ የሚኖሩ ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ተጽዕኖዎች ያሏቸውን ውጫዊ
ተግዳሮቶችን እንዲሁም በሦስቱ ተዋናዮች፡- አቅራቢዎች፣ ደንበኞች እና ተወዳዳሪዎች መካከል የሚኖሩ እድሎችን እና
ስጋቶችን ለመለየት የሚያስችል ነው፡፡

2.1. ፖለቲካዊ ምክንያቶች

ለንግዱ ጠቃሚ የሆኑ ፖለቲካዊ ምክንያቶች የሚያካትቷቸው፡-

 የመንግስት ድንጋጌዎች እና እገዳዎች፡- መንግስት በአለም የንግድ ድርጅት መርሆዎች ውስጥ ያሉ ህግጋቶችን
እና ድንጋጌዎችን በሙሉ ያከብራል፡፡ በፖሊሲ አወጣጥ እና አተገባበር ውስጥ ወጥ የሆነ አሰራር ይኖራል፡፡
 በተለያዩ የመንግስት ኤጀንሲዎች መካከል የፖለቲካ ኃላፊነቶች ክፍፍል፡- በአንድ ኤጀንሲ ላይ የሚኖረውን
ከፍተኛ ስጋት የሚቀንሱ በርካታ የመንግስት ኤጀንሲዎች አሉ፡፡ ነገር ግን በተቃራኒው ይህ ስራውን የማከናወን
እና ምስክር ወረቀቶችን እንዲሁም ክሊራንሶችን የማግኘት ጊዜን እና ወጪን ይጨምራል፡፡
 የቁጥጥር ልምምዶች፡- የቁጥጥር ልምምዶች ከአለም አቅፍ መርሆዎች ጋር የተቀናጁ ሲሆን ይህም ሀገሪቷ
“ስራ የመስራት ቀላልነት” ደረጃዋን እንድታሻሽል ረድቷል፡፡
 የመንግስት ሽግግር እና የፖሊሲ ለውጥ፡- አንድ መንግስት ከሌላ መንግስት ጋር በፖሊሲ አወጣጥ ላይ ወጥነት
አለ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ መንግስታት ከሁሉም ተዋዋይ ወገኖች ጋር በቀድሞ መንግስታት በተፈጸሙ ስምምነቶች
የሚስማማ ይሆናል፡፡
 አክባቢያዊው መንግስት የሚጫወተው ሚና፡- የአከባቢ መንግስታት በፖሊሲ ማውጣት ሂደት እንዲሁም
አተገባበር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የማሳደር አቅም አላቸው፡፡ በርካታ ፖሊሲዎች እና ድንጋጌዎች የሚተገበሩት
በአከባቢ መንግስት ህግ አስፈጻሚ ተቋማት ሲሆን አብዛኛዎቹ ተጠሪነታቸው በበርካታ ህጎች መሠረት ለክልል
መንግስታት ይሆናል፡፡

2.2. ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች

ጠንካራ የምጣኔ ሃብት ስራ አፈጻጸም ከ 2000 ቹ ጀምሮ ኢትዮጵያን በአህጉሩ ውስጥ ነዳጅ ሳያመርቱ ፈጣን የኢኮኖሚ
እድገት ያላቸው ሀገራት ውስጥ አንዷ አድርጓታል፡፡ ይህም ከ 2004 እስከ 2008 መካከል ባስመዘገበችው አማካኝ
ዓመታዊ እድገት ተመን 11 በመቶ እንዲሁም ከ 2012 – 2020 በትንሹ ከ 7 – 9 በመቶ እድገት በማስመዝገቧ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በትራንስፎርሜሽን ወደ ክፍት ኢኮኖሚ እየተሸጋገረች ሲሆን የኢንዱስትሪያላይዜሽን


አስፈላጊነት አትኩሮት እየተሰጠው እና ግብርናው በንግድ ላይ በማተኮር ላይ ነው፡፡ የሚገነቡ ዋና ዋና የመሠረተ ልማት
ግንባታዎች ንግድን ለማቀላጠፍ እና አገሪቱን ወደ አዲስ የግልጽነት እና የኢንቨስትመንት ደረጃ እንደሚወስዱ
ይታመናል፡፡ የንግድ ሥራ ዕድገትን የሚያመቻቹ ሌሎች አስፈላጊ ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች፡-

የላቀ ማህበራዊ መረጋጋት

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት፣ የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኢፍን) ጨምሮ ከተለያዩ አካላት
አዲስ የፖለቲካ እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ አግኝታለች፡፡ የሀገሪቱ ትላልቅ የመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንቶች ፍሬ
ማፍራት የጀመሩ ሲሆን እንደ ትምህርት እና ጤና ያሉ የህዝብ አገልግሎቶች አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ ይህ
ንግድ እድገት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

የወጣቶች አቅም

በኢትዮጵያ ውስጥ ከ 70% በላይ ዜጎች ከ 30 እድሜ በታች ሲሆኑ ወደ 50% የሚሆኑት ደግሞ ከ 15 ዓመት በታች
ናቸው፡፡ በ 2017 የዓለም ባንክ ባጠናቀረው ሪፖርት የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ምዝገባ ከ 2005 አንስቶ በ 5 እጥፍ
አድጓል፡፡ ይህም በዚያ ጊዜ ውስጥ የህዝብ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከ 8 ወደ 36 በማደጋቸው ነው፡፡ የሰው ኃብት
በፍጥነት ኢኮኖሚን ለማሳደግ የሚያስችል ቁልፍ ሀብት እየሆነ ነው፡፡

ተስፋ ሰጭ የኢኮኖሚ ምህዳር ጅምሮች

የኢትዮጵያን የሚያክል ስፋት ላላት ሀገር በእንቅስቃሴ፣ በግብርና፣ በመሰረተ ልማት እና በጤና አጠባበቅ ዙሪያ ያሉ
ተግዳሮቶች በጅምር እንቅስቃሴው ውስጥ ተከታታይ ወደ ሆኑ እድሎች እየተለወጡ ናቸው፡፡ ጠንካራ የኢትዮጵያን
ኢኮኖሚ በዘላቂነት ለማስቀጠል የሀገር ውስጥ ጅምር የኢኮኖሚ ምህዳር ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም፤ የጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች እና የህብረት ሥራ ማህበራት ድርጅቶች በጣም ይበረታታሉ፡፡ የአከባቢው ሥራ ፈጣሪዎች ከታች
ከዝቅተኛ ደረጃ እንዲነሱ እና ደረጃቸውን ከፍ እንዲያደርጉ መንግስት እንደ ዩኒቨርስቲዎች፣ ትልልቅ ኩባንያዎች፣
አገልግሎት ሰጭዎች፣ የምርምር እና የገንዘብ አደረጃጀቶች ያሉ አካላት ተሰባስበው በሚሰሩበት አካባቢ ላይ መንግስት
ትኩረት እያደረገ ነው፡፡

2.3. ማህበራዊ ምክንያቶች

በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቃቅን እና አነስተኛ እንተርፕራይዞች እና የህብረት ስራ ማህበራት ልማት የሚያነቃቁ የተለያዩ
ማህበራዊ ምክንያቶች አሉ፡፡ (ዕድሜያቸው ከ 15 እስከ 24 ዓመት ( አማካይ 17.7 ዓመት) የሆኑ ወደ 20 ሚሊዮን
የሚሆኑ ወንዶችና ሴቶች ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሥራ ኃይል መኖር፣ ብዙ ቋንቋዎች፣ ብዙ ባህላዊ
ማህበረሰብ፣ ብዙ ጎሳ እና ብዝሃነት ያለው ማህበራዊ ቡድን ለንግድ ልማት ትልቅ ዕድል ናቸው፡፡

2.4. የቴክኖሎጂ ምክንያቶች

ኢትዮጵያ በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በመንግስት ተጠቃሎ ከተያዙ ጥቂት የአፍሪካ አገራት አንዷ ነች፡፡
ሆኖም አገሪቱ ባለፉት አምስት ዓመታት - እ.ኤ.አ. ከ 2010 እስከ 2015 ባሉት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ እድገት
አሳይታለች፡፡ በሪሰርች አፍሪካ ተቋም እንደዘገበው የኢትዮጵያ የሞባይል ቴሌኮሙኒኬሽን እ.ኤ.አ. በ 2007 ከነበረው ከ
1.2 ሚሊዮን ተመዝጋቢዎች ወደ 28 ሚሊዮን ተመዝጋቢዎች በ 2015 መጨረሻ አድጓል፡፡ ይህ የቴክኖሎጂ ዕድገት
በኢትዮጵያ የገጠር አከባቢ ለገበያ ዕድገት ምቹ ሁኔታ እንዲኖር ያደርጋል፡፡

2.5. አካባቢያዊ ምክንያቶች

ኢትዮጵያ ከደን መመንጠር ፣ ከአፈር መሸርሸር እና በገጠር አካባቢዎች በረሃማነትን ጨምሮ እስከ ከፍተኛ የአየር
ብክለት እና በመዲናዋ አዲስ አበባ ውስጥ የቤት ውስጥ እና የኢንዱስትሪ ቆሻሻዎች የተሳሳተ አወጋገድ ጉልህ ድርሻ
አላቸው፡፡ ኢትዮጵያ የአካባቢን መበላሸት ለመከላከል ጥረት እያደረገች ነው ፡፡ አገሪቱ ባዮሎጂያዊ ብዝሃነትን ፣ የአየር
ንብረት ለውጥን ፣ የበረሃማነትን እና የኦርጋኒክ/ተፈጥሮአዊ ብክለትን ጨምሮ ከአስር በላይ የዓለም አቀፍ ሁለገብ
ስምምነቶች ተፈራርማለች፡፡

በረሃማነት፣ የአፈር መሸርሸርና የተፈጥሮ ሀብት ማለቅ ተያያዥነት አላቸው፡፡ የአፈር መራቆት የግብርና ምርታማነትን
በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳ በመሆኑ የግብርና ምርቶች ንግድ ዕድገት በጉልህ ይጎዳል፡፡

2.6. የሕግ ምክንያቶች

ኢትዮጵያ የፓርላሜንታዊ የአስተዳደር ሥርዓት ያላት በፌዴራላዊ መንግሥት የሚትተዳደር ሀገር ነች፡፡ ሀገሪቱ የሲቪል
ህግ ስርዓት የሚትከተል ሲሆን የፌዴራል ህገ-መንግስት የአገሪቱ የህጎቹ ሁሉ የበላይ ህግ ነው፡፡ በፌዴራል መንግስት በርካታ
የህግ ማዉጣት ክዋኔዎች ተፈጽመዋል፡፡ ለምሳሌ ለግሉ ዘርፍ ልማት የበለጠ ተስማሚ አካባቢን ለመፍጠር እና ዓለም አቀፍ
ኢንቬስትመንትን ለመሳብ ግልፅነትን ማሳደግ ዓላማ አድርጎ የውድድር/ፉክክር ሕግ እና የከተማ መሬት የሊዝ ሕግ
የፌዴራል መንግስት አውጥቶአቸዋል፡፡
3. የጥንካሬዎች፣ ድክመቶች፣ ዕድሎችና ስጋቶችትንተና

ነቡር የአርሶአደሮች ህብረት ሥራ ማህበር የሚከተሉት ከውስጣዊ ትንተና የተገኙ ጥንካሬዎች እና ድክመቶች እንዲሁም
የበቆሎ ንግድ እድሎች እና ስጋቶች አሉት፡፡

ጥንካሬዎች

- የጉልበት የሠራተኛ የክፊያ ዋጋ ዝቅተኛ መሆን


- በድህረ፟ ምርት አያያዝ የሠለጠኑ ሠራተኞች መቦር

ድክመቶች

- ዘመናዊ ግልጋሎቶች/መሣርያዎች አለመኖር


- በቂ መጋዘን አለመኖር

እድሎች

- ምርትን መጨመር ወደ ዘላቂ በቆሎ አቅርቦት ይመራል


- ከሚጨምረው የህዝብ ቁጥር ጋር አብሮ በሚጨምረው ፍጆታ ምክንያት የምርት ፍላጎት መጨመር
- በአካባቢው የማቀነባበርያ ኢንዱስትሪዎች ብዛት መጨመር

ስጋቶች

- የሠብል በሽታዎች
- ውስን የብድር አገልግሎቶች
- ከተለያዩ ቸርቻሪዎች ግፊት መጨመር
- የማምረት ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት አርሶ አደሮች ከፍተኛ የሸያጨ ዋጋ መፈለጋቸው
4. የተወዳዳሪዎች ትንተና

በርካታ ሻጮች (ከአርሶ አደሮች አንስቶ በቀጥታ ወደ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎች፣ ደላላዎች እና ሌሎች በእህል ገበያው
ውስጥ ያሉ ተዋናዮች ጨምሮ) በምርቱ ባህሪ መለያየት ምክንያት ለምርቱን ለመለየት (እሴት የሚጨምሩ እንቅስቃሴዎች)
አነስተኛ ወሰን/ስፋት ያለውን ሰብል ለመሸጥ በብርቱ ስለሚፋለሙ የሠብል ግብይት አልፎ አልፎ ከፍተኛ ፉክክር
የሚታይበት የውጊያ ሜዳ ሊሆን ይችላል፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ጤናማ የሆነ ትርፍ ማግኘት በተለየ ሁኔታ
ደግሞ ገበያው በአንድ ስፍራ የበዛ ከሆነ እና ተወዳዳሪዎች እለታዊ አማካኝ ተመናቸውን ለማሳደግ እንደርስዎ ጠንክረው
የሚሰሩ ከሆነ እጅግ ከባድ ይሆናል፡፡

5. የግብይት እቅድ

5.1. የአገልግሎት እና መገልገያዎች መግለጫ (የህብረት ሥራ ማህበሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች)

ነቡር አርሶ አደሮች ህብረት ስራ ማህበር ለደንበኞች በሚፈልጉት የጥራት ደረጃ እንዲሁም ቢያንስ ሁለት ደረጃ የበቆሎ
ሰብል በተለያየ ኪሎግራም ማቅረብ ዓላም አድርጎ የሚሰራ የእህል ግብይት ህብረት ስራ ማህበር ነው፡፡

 ሁለት ደረጃ የበቆሎ ሰብል፡- ህብረት ስራ ማህበሩ በምርቱ ጥራት እና ተፈጥሮ/ባህሪ ላይ በመመስረት በተለያየ
ኪሎግራም መጠን ባለ ሁለት ደረጃ በቆሎ ሰብል ያቀርባል፡፡
 ሌሎች ሰብሎች በሁለተኛ ምርትነት፤ ህብረት ስራ ማህበሩ በአካባቢው የሚመረቱን እንደ ቦሎቄ፣ ስንዴ እና
ጤፍ ያሉ በርካታ ሰብሎችን ይሸጣል፡፡ ህብረት ስራ ማህበሩ እነዚህን ሰብሎች የሚወስደው ሰብሎቹ ማህበሩን
ትርፋማ የሚያደርጉት ከሆነ ወይም በአነስተኛ መጠን ሊሸጡ የሚችሉ ከሆነ ነው፡፡
 ለደንበኞች የማይቋረጥ የበቆሎ ሰብል አቅርቦት ማረጋገጥ፤ ህብረት ስራ ማህበሩ በመጋዘን አስተዳደር ድጋፍ
በወቅትም ሆነ ያለ ወቅት የበቆሎ ሰብሉን ያቀርባሉ፡፡
 በተመጣጣኝ ዋጋ ጥሩ ጥራት ያለው ምርት ማቅረብ፤ ህብረት ሥራ ማህበሩ ለደንበኞቹ ምርቱን በተመጣጣኝ
ዋጋ ያቀርባል፡፡
 የሚዛንና የማሸግ ተግባር፡- የጥራት ግምገማ ከተደረገ በኃላ ህብረት ሥራ ማህበሩ በተለያየ መጠን ሰብሉን
በመመዘን እና በማሸግ ለሽያጭ ዝግጁ ያደርገዋል፡፡
 ማከማቸት፡- የተፈተሸው/የተገመገመው ሰብል ገበያ እስከሚገኝ እና ትዕዛዝ እስከሚቀርብ ድረስ በመጋዘን ውስጥ
ይቀመጣል፡፡ የህብረት ሥራ ማህበሩ መጋዘን ምርታቸውን ማከማቸት ለሚፈልጉ አባል አርሶ አደሮች
አገልግሎት ይሰጣል፡፡
5.2. ዋና ደንበኞች

የህብረት ሥራ ማህበሩ የሚከተሉትን ደንበኞች ታሳቢ አድርጓል፡፡ እነዚህም፡-

1. ሌሎች ማቀነባበርያ ጥቃቅንና አነስተኛ እንተርፕራይዞች /ህብረት ሥራ ማህበራት፡- ህብረት ሥራ ማህበሩ


በዋነኝነት በወረዳው እና በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የማቀነባበርያ ህብረት ሥራ ማህበራትን እላማ አድርጓል፡፡ ህብረት
ሥራ ማህበሩ የተመረጡ ማቀነባበርያ ህብረት ሥራ ማህበር/ራት ለወደፊት ውል በመዋዋል፣ ናሙናዎችን እና
ቀጥታ አቅርቦትን ጨምሮ በተለያዩ በርካታ መንገዶች ይቀርባል፡፡
2. ሌላ የግብይት ህብረት ሥራ ማህበር/ጥቃቅንና አነስተኛ እንተርፕራይዞች፡- ህብረት ሥራ ማህበሩ በአቅራቢያ
ካሉ ወረዳዎች፣ ዞኖች እና አካባቢዎች የሚገኙ ተጠቃሚ ህብረት ሥራ ማህበራትን እ ሌሎች እንተርፕራይዞች
እላማ አድርጓል፡፡
3. ማንኛውንም ተጠቃሚ ግለሰቦች፡- በተጨማሪም ህብረት ሥራ ማህበሩ በተወዳዳሪ ዋጋ ሰብሉን ማግኘት
የሚፈልጉ የግለሰብ ተጠቃሚዎችን እላማ አድርጓል፡፡

5.3. የገቢ ምንጭ እና የገበያ ድርሻ

ነቡር አርሶ አደሮች ህብረት ሥራ ማህበር ክሚከተሉት ዋና ዋና የንግድ እንቅስቃሴዎቹ ገቢ ያገኛል፡፡ እነዚህም፡-

 ለተለያዩ ደንበኞች በተለያየ ኪሎግራም መጠን የበቆሎ እህል በመሸጥ

 በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች እህል በመመዘን

 በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች የመጋዘን አገልግሎት በመስጠት

የተፎካካሪዎች ቁጥር ብዙ ነገር ግን የተበጣጠሱ (አርሶ አደር፣ ቸርቻሪ፣ እና ጥቂት ጅምላ ነጋዴዎች ) ሲሆን እንዲሁም
መጠናቸው አነስተኛ እና ምርታቸው ደረጃውን የጠበቀ አይደለም፡፡ ህብረት ሥራ ማህበሩ ለደንበኞቹ በሚያቀርበው
አስተማማኝ የሰብል ጥራት አቅርቦት እና ደረጃ በገበያው ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ተገቢ በሆነ መንገድ 20
በመቶ የገበያ ዋጋ እንደሚኖረው ይገመታል፡፡

5.4. የሽያጭ ስትራቴጂ እና የግብይት በጀት

ነቡር የአርሶ አደሮች ህብረት ሥራ ማህበር በዋነኝነት ሰብሉን በመጋዘን እና በአቅራቢያ ለሚገኙ መንደሮች እንዲሁም
ከከተማው በህዝብ ማጓጓዣ የሁለት ሰአት መንገድ ለሚሆኑ ከተሞች ለማከፋፈል ያቅዳል፡፡ ይህ አካባቢ የተመረጠበት
ምክንያት፡- ሀ) በህብረት ሥራ ማህበር በቀላሉ ተደራሽ ነው፣ ለ) ለመጋዘኑ መገኛ ቅርብ ነው ሐ) በአከፋፋዮች ወይም
በሌሎች ነጋዴዎች በብዛት ችላ የተባለ በመሆኑ ነው፡፡ ስትራቴጂው ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲተገበር ህብረት ሥራ
ማህበሩ በመጀመርያው ዓመት 2000 ብር በጀት እንዲሁም በሚቀጥለው የሥራ ዓመት በጀት 10 በመቶ ይመድባል፡፡
ሽያጮች እና የግብይት ወጪ

እንደሚተነበዩ የሚጠበቁ ዝርዝሮች ዓመታዊ ዋጋ ለ 1 ኛ ዓመት


ኮሚሽን ጥቅማ ጥቅሞች 1000
የማስታወቅያ ህትመት 500
ቀጥተኛ ማስታወቅያ 500
ጠቅላላ የግብይት ወጪ 2000

5.5. የመሸጫ ዋጋ

የመሸጫ ዋጋው “ተወዳዳሪ ዘዴን” መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ሕብረት ስራ ማህበሩ ከዚህ በፊት የነበረው ዋጋ ጉልህ የገበያ
ሽያጭ ለማግኘት እና እሴት የሚጨምሩ ምርቶችን (ግምገማ፣ ደረጃ አሰጣጥ፣ ሌሎች የሚጨመሩ አገልግሎቶች) ጋር
ትርፍ የሚያስገኝ እንደሆነ ያምናል፡፡ በተጨማሪ ይህ ዋጋ በጅምር ደረጃ ተወዳዳሪ እንደሆነ ያምናል፡፡

ምርት እና የመሸጫ ዋጋ፡-

ምርቶች ደረጃ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ የሕብረት ስራ ዋጋ


1 በቆሎ ደረጃ 1 950 - 1100 1100
ደረጃ 2 900 - 1000 1000
2 ስንዴ 1500 - 1800 1800
3 ባቄላ 980 - 1400 1350 - 1400
4 ጤፍ 3300 - 3600 3600

5.6. የሽያጭ ትንበያ

በወረዳ ብቆሎ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ይመረታል፡፡ በዚህ ዓመት ዓመታዊ የምርት መጠን ትንበያ 130,500 ኩንታል ነው፡፡
የሕብረት ስራ ማህበሩ በዓመት 1000 ኩንታል እንደሚሸጥ በማሰብ እና የገበያው መጠን ድርሻ 0.76 በመቶ ይሆናል፡፡
ይሁን እንጂ በዓመት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለው የታቀደው የገበያ መጠን 95 በመቶ ብቻ ሲሆን በዚህም ለሽያጭ
ትንበያ 10,000 ኪግ X 95/100 ወይም 9500 ኩንታል ይሆናል፡፡

የሕብረት ስራ ማህበሩ በመጀመሪያ ዓመት 75 በመቶ አቅም ስራ የሚያከናውን ሲሆን በሁለተኛው ዓመት 100 በመቶ
አቅሙ ይሰራል፡፡ በእያንዳንዱ የስራ ጊዜ መጨረሻ ስራን ለማሳለጥ ሕብረት ስራ ማህበሩ 5 በመቶ ንብረት የሚይዝ
ይሆናል፡፡ በመሆኑም በመጀመሪያው ዓመት 70 በመቶ እንዲሁም በፕሮጀክቱ ሁለተኛ ዓመት 95 በመቶ ይገመታል፡፡

6. የሥራ እቅድ
6.1. የሥራ ሂደት

የነቡር አርሶ አደሮች ሕብረት ስራ ማህበር ለደንበኞቹ አገልግሎትን ለማቅረብ በርካታ ሂደቶችን ያልፋል፡፡ እነዚህ የስራ
ሂደቶች የሚያካትቱት፡-

1. በመቀበያ ማዕከል የእህል ስብስብ መቀበል

የህብረት ስራ ማህበሩ ከፍተኛ እና ዋና የስራ ተግባሩ በአካባቢው ከሚገኙ አባላቶች እና አምራች አርሶ አደሮች የበቆሎ
ሰብልን መሰብሰብ ነው፡፡ ሕብረት ስራ ማህበሩ በአቅራቢያ ከሚገኙ አካባቢዎች ካሉ አባላቶች እና አርሶ አደሮች ሰብል
ይሰበስባል፡፡ ሁሉም ሰብሎች ተገምግመው፣ ደረጃ ተሰጥቷቸው ክብደታቸው ይመዘናል፡፡

2. ግምገማ

የተሰበሰቡት ሰብሎች በመጀመሪያ ደረጃ በመብሳት የሚታዩ ይሆናል፡፡ ለግምገማ ናሙና ተወስዶ የሰብል ጥራት
ለመገምገም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

3. ደረጃ ማውጣት እና ክብደት መለካት

ግምገማው ከተከናወነ በኋላ የቀረበው ሰብል ደረጃ ተሰጥቶት፣ ተመዝኖ እና ታሽጎ በሰብል ገበያ ደረጃ መሰረት
ይዘጋጃል፡፡ የክብደት መመዘኛ ማሽን የተለያየ ኪ.ግ ያላቸውን ሰብሎች ለመመዘን ያገለግላል፡፡

4. የክምችት ቁጥጥር

የተከማቹትን ሰብሎች ከተባይ ለመከላከል በፀሀይ ማስጠት እና በባህላዊ ዘዴ በማሳ ላይበጭስ ከማጠን በሰፊው በጨረር
የማድረቅ ዘዴ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

እነዚህን ዘዴዎች በምንመርጥበት ወቅት በታሰበው ተባይ ላይ ውጤታማ መሆናቸውን፣ በአርሶ አደሮችና እና ተጠቃሚው
ላይ ችግር የማያመጡ መሆኑን እና ውጤቱ ለሕክምና የወጣውን ዋጋ የሚሸፍን መሆኑን ግምት ውስጥ ማስገባት
አስፈላጊ ነው፡፡

 ንጽህና፡- አዲስ ምርት ከቆየ ምርት ጋር አይቀላቀልም፤ የቆየ ሰብል መወገድ ወይም በሚገባ መታጠን አለበት፡፡
የማከማቻ መዋቅሮች እና ማሽኖች እንዲሁም መያዣ ከረጢቶች መጽዳት ወይም በኬሚካል መታከም
ይኖርባቸዋል፡፡ ከፍተኛ መጠን ያላቸው መዋቅሮች የኬሚካል ርጭት የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ለአነስተኛ
መጋዘኖች ጭስ መጠቀም በቂ ሊሆን ይችላል፡፡
 ተፈጥሮአዊ መከላከያ፡- የሰብል አይነቶች ለመጋዘን ተባዮች ባላቸው ተጋላጭነት የሚለያዩ ይሆናል፡፡ ነባር
የሰብል ዝሪያዎች አብዛኛውን ጊዜ ከአዳዲስ የሰብል ዝሪያዎች የማከማቻ ተባዮችን የመቋቋም ባህሪ ይታይባቸዋል፡፡
ለምሳሌ ጥሩ ሽፋን ያለው በቆሎ የማሳ ላይ የተባይ ወረራ ይቀንሳል፡፡
 ሄርሜቲክ መጋዘን፡- አየር በሚያንስባቸው ሁኔታዎች፣ የኦክስጅን መጠን ቀንሶ የካርቦንዳይኦክሳይድ መጠን
በሚጨምርባቸው አካባቢዎች የተባዮች እድገት ይቀንሳል፡፡
 የኬሚካል ቁጥጥር፡- በመጋዘን ውስጥ ሰብል የማስቀመጥ ባህላዊ ዘዴ ሰብሉን በጭስ ወይም ልዩ ልዩ ተክሎች
ለማከም የሚጠቀም ሲሆን በሌላ በኩል በተዘጉ ኮንቴነሮች ውስጥ ሲቀመጡ ሰብሉን ከአሸዋ ወይም አቧራ ጋር
በመደባለቅ ከተለያዩ አደጋዎች ሰብሉን ይጠብቃሉ፡፡ ይህ ዘዴ አነስተኛ መጠን ላላቸው ሰብሎች ለምሳሌ - ለዘር
በስፋት ጥቅም ላይ ሲውል ከፍተኛ መጠን ላላቸው ይህ ዘዴ አስቸጋሪ ነው፡፡

5. ሰብሎችን ለግብይት ማጓጓዝ

ሰብሎች ከመጋዘን ወደ ስርጭት ማዕከል/ሱቆች የሚጓጓዙት በእጅ በሚገፉ ጋሪዎች እና ሰራተኞች ነው፡፡

6.2. የታቀደ አሠራር እና የወደፊት አቅም (የመጋዘን አቅም መጠን፣ የስርጭት ማዕከል እና የአገልግሎት አቅም
ወ.ዘ.ተ…)
1. ህንጻ (መጋዘን እና መቀበያ እንዲሁም ጽ/ቤት)

ነቡር የአርሶ አደሮች ሕብረት ስራ ማህበር ሕንጻ መጋዘን (የከረጢት ማከማቻ)፣ ከመጋዘን ውጪ ያለ የተሸፈነ ስፍራ፣
አጠቃላይ የመጋዘን አቅርቦቶች እና ጽህፈት ቤትን የያዘ ነው፡፡

የሕንጻ እና ሌሎች የሲቪል ስራዎች ወጪ


ቁ. ግንባታ ብዛት ስፋት ሜ 2/ፒሲ የሲቪል ስራዎች ጠቅላላ የሲቪል
ወጪ በሜ 2 ስራዎች ወጪ

1 መጋዘን 1 200 1550 310,000.00


2 የተሸፈነ ስፍራ (ከውጭ) 1 26 800 20,800.00
3 ጽ/ቤት 1 12 1200 14,400.00
4 ጠቅላላ የአቅርቦት መጋዘን 1 12 400 4,800.00
ድምር 250 350,000.00
የነቡር ገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ከዝናብ እና ፀሀይ ብርሀን የተጠበቀ፣ የሻንጣዎች ማከማቻ እና እህል
የሚስተካከልበት የከረጢት መጋዘን እና ከመደብሩ ውጭ የተሸፈነ ቦታን ያካተተ ነው፡፡ ማከማቻ መጋዘን ያለበት ስፍራ
በዓመቱ ዉስጥ አብዛኛውን ጊዜመንገዱ ተደራሽ መሆኑ ጠቃሚ ሲሆን እንዲሁም ማከማቻው፡-

• ጣሪያው የማያፈስ
• እርጥበት መከላከያ ሽፋን ያለው እና ስንጥቅ የሌለበት ለስላሳ የኮንክሪት ወለል ያለው
• በሮች ወደ ውስጥ እና ወደ ውጭ የሚንቀሳቀሱ ጆኒያዎች/ምርት መያዣ ዕቃዎች (በተለይም የብረት ድርብ
ተንሸራታች በሮች) ለማንቀሳቀስ የሚያስችላቸው በቂ፣ አይጥ የማያስገቡ በመቆለፊያ በቀላሉ የሚከፈቱ እና
የሚዘጉ
• የአየር ማዘዋዎሪያዎች (ማስገቢያዎች) በቀላሉ የሚከፈቱና የሚዘጉ፣ ከውጭ በኩል ፀረ-ወፍ ጥብስ (2 ሴ.ሜ ያህል
ጥልፍ ሸቦ) ያለው መሆን አለበት፡፡

የታቀደ አቅም

የነቡር አርሶ አደሮች ህብረት ስራ ማህበር 1000 ኩንታል የመያዝ አቅም ያለው መጋዘን የታቀደ ነው፡፡ በጅምር ደረጃ
በሙሉ አቅም መሥራት አይታሰብም፡፡ የጅምር ወቅት ችግሮች፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት/እጥረት፣ የስርጭት ችግሮች፣ ወዘተ
መከሰታቸው አይቀርም ስለማይቀር በአንደኛው ዓመት አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ የታቀደው 50 በመቶ ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም በአንደኛው ዓመት አገልግሎት እንዲሰጥ የታቀደው 75 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ህብረት ስራ ማህበሩ
በመጀመሪያ ደረጃ በሁለተኛው ዓመት 75 በመቶ እና ከዚያ በኋላ በሙሉ አቅሙ ይሠራል፡፡

የወደፊት አቅም

ተጨማሪ አቅም፣ በተለይም ከመጋዘኑ፣ ከመሥሪያ ቤቱ እና ከአጠቃላይ አቅርቦቶች ማከማቻ ውጭ በተሸፈነው አካባቢ
የሚገኝ ሲሆን ጥቅም ላይ የሚውለው ፍላጎቱ በበቂ ሁኔታ ሲጨምር እና ከፍተኛ በሆነ በምርት ወቅት ላይ ብቻ ነው፡፡
የኅብረት ሥራ ማህበሩ ምርቶችን ለጊዜው ለማከማቸት የፕላስቲክ ሽፋን ይጠቀማል፡፡

6.3. ግብአቶች (ጸረ ተባይ ወ.ዘ.ተ…)፣ መገልገያ መሣርያዎች እና የጽ/ቤት ቁሳቁሶች


i) የተገዛ ሰብል

ነቡር አርሶ አደሮች ሕብረት ስራ ማህበር ሰብሎችን የሚገዛው መልሶ ለመሸጥ ሲሆን በዋነኝነት የሚገዛው በቆሎ ነው፡፡
የሕብረት ስራ ማህበሩ መልሶ ሊሸጣቸው የሚገዛቸው ሌሎች ሰብሎች ባቄላ፣ ስንዴ እና ጤፍን ያካትታል፡፡ የሰብሎች
ጠቅላላ ዋጋ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

የግዢ ሰብሎች በ 1 ኛ ዓመት ከ 1 ኛ ዓመት ወጪ በኩንታል የ 1 ኛ ዓመት ከ 1 ኛ ዓመት


የሚገዛ ብዛት በኋላ የሚገዛ ጠቅላላ ዋጋ በኋላ ጠቅላላ
ብዛት ዋጋ
በቆሎ ደረጃ 1 400 500 800 320000 400000
በቆሎ ደረጃ 2 200 300 750 150000 225000
ስንዴ 50 50 1700 85000 85000
ባቄላ 50 50 900 45000 45000
ጤፍ 40 40 3400 136000 136000
740 940 736000 891000
ii) ግብአቶች/ጥሬ እቃዎች (ጸረ ተባይ እና ሌሎች ማጽጃ ግብአቶች)

በሕብረት ሥራ ማኅበሩ ውስጥ ያገለገሉ ግብዓቶች/ጥሬ ዕቃዎች ለመጋዘን አስተዳደር ያገለግላሉ፡፡ በማከማቸት ወቅት
እህልን የሚያጠቁ ዋና ዋና ተባዮች፤ ነፍሳት (በአብዛኛው ጥንዚዛዎች እና ብራብሮዎች) ፣ አይጦች (በአብዛኛው አይጥ እና
አይጠሞጎጥ) እና ሻጋታዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ተባዮች ለመቆጣጠር ተለያዩ ፀረ -ተባዮች ውጭ በወር ወደ 2500 ብር
ይገመታል፡፡

በፀረ-ነፍሳት ሌሎች ነፍሳትን ለመከላከል የሚቻልበት ሌላኛው መንገድ ሄርሜቲክ መያዣ መጠቀም ነው፡፡ ሄርሜቲክ
መያዣ ሰብሉን ከአንድ ዓመት በላይ ረዘም ላለ ጊዜ ከነፍሳት ጥቃት ይጠብቀዋል፡፡ ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ እና ኪሳራቸውን
ለመቀነስ ሰብሎችን በማጠራቀሚያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ለማቆየት ይረዳል፡፡

iii) መሣርያዎች

መሣሪያዎቹ ሁለቱንም የስራ እና ሌሎች የቢሮ ዕቃዎችን ያጠቃልላሉ፡፡ የሥራው መሳሪያዎች የክብደት መለኪያ ማሽንን፣
የጥራት ቁጥጥር መሳሪያዎችን፣ የኬሚካል መርጫ፣ የማሸጊያ ቁሳቁሶችን እና ሌሎችንም ያጠቃልላሉ፡፡ የሚያስፈለጉ
የቤት ዕቃዎች ወንበሮችን፣ ጠረጴዛዎችን እና መሳቢያዎችን ያጠቃልላል፡፡

ለህብረት ሥራ ማህበሩ መጋዘን አስፈላጊ የሆኑ የመገልገያ መሣሪያዎች ማቅረብ አለበት፣ እነዚህም ቁሳቁሶች
የሚከተሉትን ያካትታሉ፡፡

 የከረጢት ማስቀመጫዎች
 የሚገባውን እና የሚወጣውን የሰብል ክብደት የሚመዝን ሚዛን
 የሰብሉን ጥራት ለመፈተሻ ናሙና መቀበያ መውጊያ
 መጋዘኑ ንፁህ ሆኖ እንዲቆይ የሚያስችል መጥሪጊያ
 ታርፓውሊን (ሽፋን) ሰብሉን ከተባይ ወረራ ለመከላከል ከረጢት መሸፈኛ
 የተቀደዱ ከረጢቶችን የሚተካ ትርፍ ከረጢት እና በወለል ላይ የፈሰሱ ሰብሎችን የማከማቻ ከረጢት
 በመጋዘኑ የሚገባ እና የሚወጣ ሰብል መመዝገቢያ ደብተር/መዝገብ

የእቃ ዝርዝር ብዛት የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ


1 ክብደት መለኪያ ሚዛኖች 2 13,000 26,000
2 ናሙና መውሰጃ መውጊያ 2 400 1200
3 ሀሄርሜቲክ ከረጢት 50 300 15000
4 መሸፈኛ ፕላስቲክ 2 (9 ሜ*9 ሜ) 2,500 5000
5 መርጫ 1 1000 1000
6 የእንጨት ማስቀመጫ 10 250 2500
ጠቅላላ የእቃ ወጪ 50,700
የቢሮ መገልገያ
1 አነስተኛ የቢሮ ጠረጴዛ 2 1200 2400
2 አነስተኛ የቢሮ ወንበር 2 600 1200
3 መሳቢያ 1 1600 1600
ጠቅላላ የቢሮ መገልገያ ወጪ 5200
ጠቅላላ የእቃ እና የቢሮ መገልገያ 55,900

iv) ቴክኖሎጂያዊ ሁኔታ

የነቡር አርሶ አደሮች ህብረት ስራ ማህበር በሀገር ውስጥ የሚገኙትን መሳሪያዎች/ቁሳቁሶችና ቴክኒኮችን ለማከማቸት ፣
ለመፈተሽ እና ለመጋዘን አስተዳደር ይጠቀማል፡፡

v) ቋሚ ካፒታል እና የዋጋ ቅነሳ

የነቡር አርሶ አደሮች ህብረት ስራ ማህበራት ቋሚ ካፒታል የሚባሉትመሬቶች፣ ሕንፃዎች እና መሳሪያዎች/ቁሳቁሶች


ናቸው፡፡ ቋሚ የንግድ ካፒታል ዝርዝር እና የኢንቬስትመንት ዋጋ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

ቋሚ ካፒታል ዝርዝር
ሕንፃዎች
- መጋዘን፣ አጠቃላይ መጋዘን፣ ጽ/ቤት 350,000.00
መገልገያ ቁሳቁሶች
- ቋሚ የስራ መሣርያዎች 50,700
- የቢሮ እቃዎች 5200.00
ጠቅላላ ድምር 405,900

የህንጻ እና ማሽኖች አገልግሎት ዘመን

ዓመታዊ የቅናሽ ዋጋ ለመድረስ፣ በሚጠበቀው ቆይታ መጨረሻ ላይ የተቆራረጠ ዋጋ መቀነስ እና በመቀጠል የንብረቱን
ዋጋ በምርታማነት ቆይታው ዓመታት ብዛት ያካፍላሉ። የተቆራረጠ እሴት ከሌለው በቀላሉ እሴቱን በዓመታት ቁጥር
ያካፍላሉ። በአገራችን የታክስ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አጠቃላይ የዋጋ ቅነሳን ያትማል፡፡ በብዙ አገሮች አጠቃላይ
አሠራሩ አንዳንድ ልዩነቶች ቢኖሩትም እንደሚከተለው ቅርቦአል፡፡

የማይንቀሳቀስ ንብረት ቆይታ ዓመታዊ ተቀናሽ ተመን


ማሽን 10 ዓመታት 10%
ህንጻ 20 ዓመታት 5%
የቢሮ እቃ 5 ዓመታት 20%

የሕንፃው ቆይታ (መጋዘን እና ቢሮዎች) 20 ዓመት ሲሆን ለመገልገያዎች እና ቢሮ ዕቃዎች ደግሞ እንደ ቅደም
ተከተላቸው 10 እና 5 ዓመታት እንደሚኖራቸው ይታሰባል፡፡ የዋጋ ቅናሽ ክፍያ እሳቤ ለህንፃ 5% እና ለቢሮ
መሣሪያዎች/ቁሳቁሶች 20% ይሆናል፡፡ ስለሆነም ትርፍ እሴት ሳይታሰብ ዓመታዊው ተቀናሽ ዋጋ የሚከተለው ይሆናል፡፡

መግለጫ ዋና እሴት (በብር) ዋና ዋጋ ዓመታዊ ተቀናሽ


መቶኛ (በብር) ዋጋ (በብር)

1 ህንጻ እና ግንባታዎች 350,000 5% 17,500


2 መገልገያዎች 50,700 10% 5,070
የቢሮ እቃዎች 5,200 20% 1,040
ጠቅላላ ተቀናሽ 405,900 23,610

7. ድርጅታዊ እቅድ

7.1. የንግድ ይዘት

ይህ ቢዝነስ “ናቡር አርሶአደሮች ህብረት ሥራ ማህበር” በሚል መጠርያ መሰረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር ተብሎ የተመዘገበ
ሲሆን ባልቤትነቱ ይህብረት ሥራ ማህበር አባላቶች ነው፡፡ የንግድ አድራሻው በመስካን ወረዳ፣ጉራጌ ዞን፣ በደቡብ ክልል
ውስጥ ይገኛል፡፡

7.2. ድርጅታዊ መዋቅር፣ ሚና እና የሠራተኞች ኃላፊነቶች

የማንኛውም ንግድ ስኬት በድርጅቱ የስራ መዋቅር ላይ እንዲሁም ያሉትን ሚናዎች በያዙ ግለሰቦች ላይ በከፍተኛ ደረጃ
ይደገፋል፡፡ ነቡር አርሶአደሮች ህብረት ስራ ማህበር በንግድ ተቋሙ መዋቅር ጋር መሰረት በመስራት የሰራተኞችን የፈጠራ
አቅማቸውን በማውጣት፣ የባለቤትነት ስሜት ብመስጠት እንዲሁም ከድርጅቱ ጋር በጋራ ለማደግ ለሠራተኞች ስፍራ
የሚሰጥ ነው፡፡

ነቡር አርሶአደሮች ህብረት ስራ ማህበር ቢሮክራሲን/የአሰራር እንቅፋቶችን የሚቀንስ እና ድርጅቱ በተገቢ ሁኔታ ምላሽ
እንዲሰጥ የሚረዳ እንደ ሁኔታ ለዋዋጭነት የሚጨምር ቀላል ድርጅታዊ መዋቅር የሚኖረው ይሆናል፡፡
ዋና ሥራ አስኪያጅ

ፋይናንስ እና ግዢ ግብይት ምርመራ፣ ጥራት መጋዘን ጠባቂ


ቁጥጥር

7.3. የሠው ኃይል /ቋሚ ሠራተኛ/

የሚፈለጉ ቋሚ የሠው ኃይል ሠራተኞች ዝርዝር እንዲሁም የሠራተኛ ዓመታዊ ክፊያ ዋጋ ከዚህ በታች በሚታየው
ሠንጠረዥ ብዝርዝር ተጠቅሷል፡፡

ተ.ቁ የሥራ መደብ ቁጥር የትምህርት ዝግጅት ወርሃዊ አማካይ ዓመታዊ


ደመዎዝ (ብር) ደመዎዝ (ብር)
1 የህብረት ስራ ማህበር ስራ 1 በማኔጅመንት ወይም ተያያዥ 2500 30,000
አስኪያጅ መስክ ዲፕሎማ ወይም ከዚያ
በላይ
2 ጥራት ገምጋሚ 1 በመጋዘን አስተዳደር 1500 18,000
ዲፕሎማ/የስልጠና ምስክር
ወረቀት ያለው
3 ፋይናንስ እና ግዢ 1 ዲፕሎማ በሂሳብ 1500 18,000
አያያዝ/አካውንትንግ
4 ማርኬቲንግ 1 በማርኬቲንግ ወይም ተያያዥ 1500 18,000
መስክ ዲፕሎማ
5 መጋዘን ጠባቂ 1 10 ኛ/12 ኛ ያጠናቀቀ 1000 12,000
4,500 96,000
ማስታወሻ፡- ደመዎዝ በየአመቱ 5 በመቶ ያድጋል፡፡

7.4. ቀጥተኛ የጉልበት ሠራተኛ መኖር እና መሥፈርት

እነዚህ ሠራተኞች በጉልበታቸው በጊዢ ወቅት እህሉን ወደ መጋዘን ተሸክመው ለማስገባትና እና በሽያጭ ወቅት ከመጋዘን
ለማውጣት ያስፈልጋሉ፡፡ የዚህ አይነት ሥራ የሚያስፈልጉ ሠራተኞች አመቱን ሙሉ የሚገኙ ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ
ሥራዎች የበፊት ክህሎቶችን የማይፈልጉ በመሆናቸው ምንም አይነት ሊተነበዩ የሚችሉ ችግሮች የሉም፡፡
ከዚህ በታች ያለው ሠንጠረዥ አማካይ ዓመታዊ የጉልበት የሠራተኛ መስፈርቶች እና ተያያዥ ዋጋ የሚያብራራ ነው፡፡

የሰብል ግልጋሎት ቀጥተኛ ሠራተኛ ድግግሞ ጠቅላላ በአመቱ ቀናት 70 ብር በዋጋ


አይነት ያስፈልጋል ሽ የሚያስፈልግ (ተጨማሪ 5 በመቶ
(በቀናት) ለወቅቱ ቀናት ዓመታዊ)
1 በቆሎ መሸከም፣ ማሸግ እና መጫን 10 4 40 2,800
መሸጥ 2 10 20 1,400
2 ሌላ ሰብል ማጓጓዝ፣ ማሸግ፣ መጫን እና 4 4 16 1,120
መሸጥ

ጠቅላላ ዓመታዊ የጉልበት የሠራተኛ ዋጋ 5,320

7.5. የቅድመ-ሥራ እንቅስቃሴዎች እና ወጪዎች (አዲስ ከሆነ)

ነቡር አርሶአደሮች ህብረት ስራ ማህበር ክንግድ ስራዎቹ በፊት የሚተገበሩትን እንቅስቃሴዎች እንደሚከተለው
ዘርዝሯል፡፡ እነዚህም፡-

 ለመሬት ማመልከቻ ማቅረብ - 3 ሣምንታት

 መሬት ማግኘት እና ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የማግኘት ሂደት - 2 ሣምንታት

 ለብድር ማመልከቻ ማቅረብ እና ገንዘብ ማግኘት - 7 ሣምንታት

 መጋዘን እና ቢሮዎች ለመገንባት - 1 ዓመት

 የመገለገያ እቃዎች አቅራቢዎችን ለማነጋገር - 1 ሣምንት

 መገልገያ መሣርያዎቹን እና አስፈላጊ እቃዎችን ለመግጠም - 2 ወራቶች

እነዚህ ቅድመ-ሥራ እንቅስቃሴዎች የተለያየ ወጪዎች አሏቸው፡፡

ዝርዝሮች ዋጋ
የሰነዶች ቅጂ/ማባዛት እና ምዝገባ ወጪ 500.00
የምስክር ወረቀት ወጪ 400.00
ለብድር ማመልከት 200.00
ስልክ 200.00
የማጓጓዣ ወጪ 300.00
የንግድ ምልክት፣ ማህተም እና ሌሎች የቢሮ ማስታወቅያዎች 400.00
ጠቅላላ ወጪ 2000.00
7.6. አጠቃላይ እና አስተዳደራዊ ወጪዎች

እነዚህ ወጪዎች ለማዘጋጃ/ማመቻቻ እና አስተዳደራዊ ወጪዎች ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡ የህብረት ሥራ


ማህበራት በይበልጥ ትርፋማ ለመሆን ዋጋቸውን ዝቅተኛ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ አስተዳደራዊ ወጪ በዓመት 5 በመቶ
እንደሚጨምር ይተነበያል፡፡ ስለሆነም የሥራ አስተዳደራዊ ወጪ የሚያካትተው፡-

ዝርዝሮች ጠቅላላ ዋጋ
የኤሌክትሪክ ፍጆታ ወጪ 1,200
የደመዎዝ ወጪ 96,000
የነዳጅ፣ ዘይት እና ቅባት ወጪ 600
የውሃ ፍጆታ ወጪ 600
የጥገና እና እድሳት ወጪ 1,000.00
የጉዞ ወጪ 2,400
የማጽዳጃ አቅርቦቶች ወጪ 960
የግብይት እና ሽያጭ ወጪ 5,500.00
የጸ ማጥፍያ ኬሚካሎች ወቺ 3,000
ልዩ ልዩ ወጪዎች 1,200
8. የፋይናንስ እቅድ

8.1. የፕሮጀክት/ኢንቨስትመንት ዋጋ

የታቀደው ንግድ ማስፋፋት ጠቅላላ ኢንቨስትመንት ዋጋ 520,820.00 ብር ይደርሳል፡፡ የፕሮጀክቱ ማጠቃለያ ከዚህ
በታች ቀርቧል፡፡

የኢንቨስትመንት ዋጋ ማጠቃለያ
ተ.ቁ መግለጫ ጠቅላላ ዋጋ

1 ህንጻ እና ግንባታ ወጪ 350,000


2 የእርሸ መገልገያዎች እና የቢሮ እቃዎች 55,900
ንዑስ ድምር 237,900
3 የቅድመ-ምርት ዋጋ 2,000
4 የሥራ ካፒታል 112,920
ንዑስ ድምር 331,283.30
ጠቅላላ ድምር 520,820.00

8.2. የፋይናንስ እቅድ እና የብድር ክፍያ

የህብረት ሥራ ማህበሩ የመሬት፣ ህንጻ እና የቅድመ-ሥራ ወጪዎችን በመሸፈን ከጠቅላላው 520,820.00 ውስጥ
99,166.70 መሸፈን ይችላል፡፡ ለቀሪው የፕሮጀክት ወጪ ለመሸፈን ማለትም 421,653.30 ብድር አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ተ.ቁ መግለጫ እዳ ሀብት-


1 ህንጻ እና ግንባታ 350,000
2 የእርሸ መገልገያዎች እና የቢሮ እቃዎች 55,900
ንዑስ ድምር 35,100.00 405,900.00
3 የቅድመ-ምርት ዋጋ 2,000
4 የሥራ ካፒታል 15,753 97,167
ንዑስ ድምር 163,400.00 15,753.30
ጠቅላላ ድምር 421,653.30 99,166.70

8.3. የብድር ዋስትና


የህብረት ሥራ ማህበሩ መገልገያዎቹን፣ መጋዘኑን እና አንዳንድ የግል ግብአቶችን ለብድር ዋስትና ያስይዛል፡፡

8.4. የትርፍ እና ኪሣራ መግለጫ

ከዚህ በታች ንግዱ የሦስት ዓመት ገቢ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ነቡር አርሶ አደሮች ህብረት ሥራ ማህበር

የሥራዎቹ የተተነበየ ውጤት መግለጫ

(የገቢ መግለጫ)

በመጠናቀቅ ላያ ላሉት ሦስት አመታት

መግለጫ የፕሮጀክት አመታት


1 2 3
የበቆሎ ደረጃ 1 ሽያጭ 440,000 550,000 550,000
የበቆሎ ደረጃ 2 ሽያጭ 210,000 315,000 315,000
የስንዴ ሽያጭ 87,500 87,500 87,500
የቦሎቄ ሽያጭ 67,500 67,500 67,500
የጤፍ ሽያጭ 144,000 144,000 144,000
ጠቅላላ ገቢ 949,000 1,164,000 1,164,000
ሌላ ገቢ (የጠቅላላ ገቢ 10 እጅ) 94,900 94,900 94,900
የተጣራ ገቢ 1,043,900 1,258,900 1,258,900
ተቀንሶ፡- የሥራ ወጪዎች 848,580 1,007,196 1,007,196
ጠቅላላ ትርፍ 195,320 251,704 251,704
ተቀንሶ፡- ዋጋ ቅናሽ 23,610 23,610 23,610
ትርፍ ከወለድ እና ከግብር በፊት 171,710 228,094 228,775
ተቀናሽ፡- ወለድ 21,785 27,407 27,785
የተጣራ ትርፍ/ኪሣራ 149,925 200,687 200,989
8.5. የጥሬ ገንዘብ ፍሠት መግለጫ

ነቡር አርሶ አደሮች ህብረት ሥራ ማህበር

የጥሬ ገንዘብ ፍሠት መግለጫ

በመጠናቀቅ ላያ ላሉት ሦስት አመታት

መግለጫ የፕሮጀክት አመታት


0 1 2 3
የጥሬ ገንዘብ ገቢዎች
የባለቤቱ/የማህበሩ ሀብት 99,167
ብድር 421,653
የተጣራ ትርፍ 149,925 200,687 200,989
ዋጋ ቅናሽ 9,575 9,575 9,575
ጠቅላላ የጥሬ ገንዘብ ገቢዎች 520,820 159,500 210,262 210,564
የጥሬ ገንዘብ ወጪዎች
ጠቅላላ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች 405,900
ቅድመ-ምርት ዋጋ 2,000
የሥራ ካፒታል 112,920
የሥራ ካፒታል መጨመር - (1,400) 420
የብድር ተመላሽ 74,409 74,409 74,409
መተካት/የተተካ - - - -
ወጪ (10 በመቶ) - 14,992 20,069 20,099
ጠቅላላ የጥሬ ገንዘብ ወጪዎች 520,820 89,402 93,078 94,928
የተጣራ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት - 70,098 117,183 115,633
የተከማቸ ጥሬ ገንዘብ ቀሪ - 70,098 187,281 302,917
የተያዘ ትርፍ - 134,932 180,618 180,890
8.6. የሂሳብ መግለጫ ትንበያ
ነቡር አርሶ አደሮች ህብረት ሥራ ማህበር
ሂሳብ መግለጫ
በመጠናቀቅ ላያ ላሉት ሦስት አመታት
መግለጫ የፕሮጀክት አመታት
0 1 2 3
ሀ) ንብረቶች
የአሁን ያሉ ንብረቶች
ጥሬ ገንዘብ 134,932 315,550 496,440
ዝርዝር ንብረት ቆጠራ (በሥራ ላይ ያለ ካፒታል) 112,920 112,920 111,520 111,940
ጠቅላላ አሁን ያሉ ንብረቶች 112,920 247,852 427,070 608,380
የማይንቀሳቀሱ/ቋሚ ንብረቶች
ህንጻ እና ግንባታ 350,000 332,500 315,000 297,500
ማሽን እና መገልገያዎች 50,700 45,630 40,560 35,490
የቢሮ እቃዎች 5,200 4,160 3,120 2,808
ጠቅላላ ቋሚ/የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች 405,900 382,290 358,680 335,070
ተጨባጭ ያልሆነ/የማይታዩ ንብረቶች
የቅድመ-ሥራ ወጭዎች 2,000 1,800 1,600 1,400
ጠቅላላ ንብረቶች 520,820 631,942 787,350 944,850
ለ) እዳዎች
የረዥም ጊዜ እዳዎች
ብድር 421,653 347,244 272,835 198,425
ጠቅላላ የአሁን/ወቅታዊ ያልሆኑ እዳዎች 421,653 347,244 272,835 198,425
ወቅታዊ እዳዎች
የአጭር ጊዜ ብድሮች እና አቅርቦቶች 50,599 99,799 150,818
ሐ) ካፒታል
የሐብት ክፍፍል 99,167 99,167 99,167 99,167
የተጣራ የተያዘ ንብረት 134,932 315,550 496,440
ጠቅላላ ካፒታል 99,167 234,099 414,717 595,607
ጠቅላላ እዳ እና ካፒታል 520,820 631,942 787,350 944,850

8.7. የፋይናንስ ትንተና


የፕሮጀክቱን አዋጭነት ለመለካት የሂሳብ ትንተና ተሰልቷል፡፡ ስለሆነም የ 10 ዓመት ግምታዊ ጥሬ ገንዘብ ፍሰት ግምት
ውስጥ ሲገባ ፕሮጀክቱ 931,281 ብር የተጣራ የአሁኑ ዋጋ እና 42 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት ይኖረዋል፡፡

ሀ) በ 10 ዓመት ጊዜ ውስጥ የዚህ ንግድ የተጣራ ወቅታዊ ዋጋ = 931,281 ብር

ለ) በ 10 ዓመት ጊዜ ውስጥ የዚህ ንግድ ውስጣዊ የትርፍ ተመን ዓመታዊ ዕድገት = 42 በመቶ

You might also like