You are on page 1of 2

በሶላር ቪለጅ ኢትዮጵያ የተደረገ አጠር ያለ ስልጠና እና እይታ

ዛሬ 15/02/2015 በቤተመንግስት ያየናቸውና መሰራት ያለበት ነገሮች

1.የቨርሚ የተፈጥሮ ፈሳሽ ማዳበርያ ክትትል እና እንክብካቤ

 በየቀኑ እርጥበቱን ማየት ይኖርበታል በጣም መርጠብ የለበትም ወይም ጭቃ መሆን የለበትም.
 በየቀኑ 10 ሊት ውሃ በእያንዳንዱ አልጋላይ መጨመር።
 ምርት ከበዛ ያንኑ ማዳበርያ ደጋግሞ መርጨት ይቻላል የበለጠ ያጠነክረዋል
 በ 15 ቀን አንድ ግዜ መነካካት ይኖርበታል ወይም ጥንቃቄ አርጎ መኮትኮት
 ጥቅሙም ትሎቹ ክፍት እና አየር ያገኛሉ በዚን ግዜ ጥሩ ይሰራሉ።
 በ ከ እርሻ የሚወገዱ ተረፈ ምርቶች
 ከካፌ የሚወጡ ውጋጅ በቅድመ ማበስበሻ ቦታ ማስቀመጥ
 በቅድመ ብስበሳ ቦታ እንዲበሰብሱ ማረግ ከበሰበሰ በኋላ ወደ ኮምፖስት አልጋው በፎርካ መውሰድ
 ከዚያ በኋላ አልጋው ላይ በ 15 ቀን መጨመር
ማሳሰቢያ:-
ፈፅሞ አፈር መጨመር የለብትም
ከ አልጋው ላይ ምንም አይነት ጠጣር ኮምፖስት መነሳት የለበትም ምክኛቱም
የትሎችን እንቁል እና ትሎች አብረው ይወሰዳሉ!
የታዩ ክፍተቶች ፦-
ኮምፖስቱ እርጥበት ማነስ
አፈር መጨመር
አካባቢው ፅዳት ጉድለት
በ ፎደር ወይም የእንሰሳት አዘገጃጀት ላይ የተሰጡ ሀሳቦች
ፎደር ከገብስ፣ከስንዴ፣ከቦቆሎ ወይም በሌሎቾ ጥራጥሬ ይሰራል
ጥቅሙም በአጭር ግዜ ማለትም ከ ሳምንት እስከ 15 ቀን የሚደርስ የአሳ መኖ፣የዶሮ ፣የወተት ላም መኖ ነው
አዘገጃጀቱ ገብስ ወይም ሌላ ጥራጥሬ ለ 24 ሰአት ውሃ ውስጥ መዘፍዘፍ
ከዚያ ገንዳ ውስጥ ወይ የተዘጋጀ ቦታ ላይ መዘርጋት ወይም መረስስ
ከዚን በቀን ውስጥ እርጥበቱን እያዪ ውሃ ማርከፍከፍ ሳሳ አርጎ ማርከፍከፍ እንደ ሚስቲንግ ሳይበዛ
የምርት አሰባሰብ
ከተዘራ አንድ ሳምት ሲሞላው መጠቅለል ወይም ማጨድ ይቻላል።
እንዲጠነክር ካስፈለገ 15 ቀን አቆይቶ ለተዘገጀለት አላማ ማዋል ይቻላል ።
የታው ክፍተት
ውሃ በአግባቡ አለጨመር በዚህም የተነሳ ደርቋል ፎደሩ
ዳክዊድ እና አዞላ
ይህ ተክል ውሃ ላይ ተንሳፍፊ ነው በአጭር ግዜ የሚደርስ
በየ 2 ቀን ውስጥ እራሱን ደብል ሁለት እጥፍ ነው የሚበዛው ነው
ጥቅሙም ፕሮቲን ስላለው አኩሪ አተርን ይተካል።
አበቃቀሉ ቀላል ነው ውሃ ገንዳ ውስጥ ከ 10_20 ሴትር ጥልቀት በሞምላት 0.72 ሜትር ሊይ አንድ ሌትር
ቨርሚ ኮምፖስት
100gram በካሬ ሜትር ስኬር መዝራት ይቻላል።
ምርቱም ከ ሳምንት እስከ 15 ቀን መሰብሰብ ይቻላል።
ከተመረተ በኋላ ውሃውን ለአትክልት መጠቀም ይቻላል።
ማሳሰቢያ
የመጀመሪያ የተመረተበትን ውሃ መቀየር ደግሞ መጠቀም አይቻልም
የታየው ክፍተት
ምንም አይነት ክትትል አልተደረገም ተትቷል
ውሃ አልተቀየረም
ዳክዊድ ከናካቴው ጠፍቷል

You might also like