You are on page 1of 14

ትኩሳት

ትኩሳት ጊዜያዊ የሆነ የሰዉነት ሙቀት መጨመር ችግር ሲሆን ብዙዉን ጊዜ የሚከሰተዉ በህመም ምክንያት ነዉ፡፡
የትኩሳት መከሰት/መኖር የሚያሳየዉ የሆነ ትክክል ያልሆነ ነገር በሰዉነትዎ ዉስጥ እየተካሄደ መሆኑን ማሳያ ነዉ፡፡
በአዋቂዎች ላይ የትኩሳት መከሰት ምቾት እንዳይሰማዎ ቢያደርግም የትኩሳትዎ መጠን 39.4 ዲግሪና ከዚያን በላይ
ካልሆነ በቀር ብዙም ላያሳስብዎ ይችላል፡፡ ነገር ግን በጨቅላና ታዳጊ ህፃናት ላይ የሰዉነት ሙቀት በትንሽ መጠን
መጨመር መኖር እንኳ ካለ አሳሳቢ የሆነ ኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
ባጠቃላይ ሲታይ ትኩሳት ከጥቂት ቀናት በኃላ የሚጠፋ ነዉ፡፡ የተለያዩ ያለሀኪም ትእዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ
መድሃኒቶች ቢኖሩም አንዳንድ ጊዜ መድሃኒት ሳይወስዱ መቆየት ተመራጭ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንቱም ትኩሳት
የሰዉነት የበሽታ መከላከያ ዘዴዎች የተለያዩ እንፌክሽኖችን እንዲዋጉ ስለሚረዳ ነዉ፡፡

ምልክቶች
ትኩሳት የሚከሰተዉ የሰዉነት ሙቀት ከተለመደዉ/ከኖርማል በላይ ከፍ ሲል/ሲጨምር ነዉ፡፡ ለርስዎ
የተለመደዉ/ኖርማል የሆነዉ የሰዉነት ሙቀት ከሌላ ሰዎ ጋር ሲነፃፀር ከኖርማል የሰዉነት ሙቀት (37°C) በተወሰነ
መጠን ከፍ ወይም ዝቅ ሊል ይችላል፡፡ ትኩሳቱን እንዳመጣብዎ ምክንያቶች የተለያዩ ተጨማሪ የህመም ምልክቶች
ሊታዩ የሚችሉ ሲሆን ከእነዚህም ዉስጥ፡-
• ማላብ
• የራስ ምታት
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• መደካከም
• ብርድ ብርድ ማለት
• የጡንቻ ላይ ህመምና
• የሰዉነት መጠዉለግ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
የትኩሳትዎ መጠን በጣም ከፍተኛ (ከ39.4°C እስከ 41.1°C) ከሆነ የሚከተሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡ እነርሱም
• ቅዠት
• መነጫነጭ
• የሰዉነት መጠዉለግ መባባስ
• መዘባረቅ
• እንደ የሚጥለዉ ሰዉ ማንቀጥቀጥ መከሰት ናቸዉ፡፡

የትኩሳት ምክንያቶች
ትኩሳት የሚከሰተዉ በአዕምሮችን ዉስጥ ያለና የሰዉነትን ሙቀት የሚቆጣጠረዉ አካል ወይም
ሀይፖታላመስ/ቴርሞስታት ሴንተር የሰዉነትን ሙቀት ከተለመደዉ/ከኖርማሉ በላይ ከፍ እንዲል ሲደርገዉ ሲሆን
ይህ ሲከሰት ሰዉነትዎን ብርድ ብርድ ስለሚልዎ ተጨማሪ ልብስ እንዲደርቡ አሊም ተጨማሪ ሙቀት ለማመንጨት
ሰዉነትዎ መንዘፍዘፍ/መንቀትቀጥ እንዲጀምር ያደርጋል፡፡ በዚህ ሂደት ዉስጥ የሰዉነት ሙቀትዎ ከኖርማሉ በላይ
ይጨምራል፡፡
የሰዉነትዎ ሙቀት በቀን ዉስጥ በተለያዩ ሰዓታት ሊለያይ ይችላል፡፡ ስለሆነም ጧት ጧት የሰዉነትዎ ሙቀት
የሚቀንስ ሲሆን ወደ አመሻሽና ማታ ላይ ደግሞ ከፍ ይላል፡፡ ምንም እንኳ የብዙ ሰዎች ኖርማል የሰዉነት ሙቀት
መጠን 37°C መሆኑን ቢረዱም ኖርማል የሰዉነት ሙቀት መጠን ከ36.1°C እስከ 37.2°C ሊሆን ይችላል፡፡
ትኩሳት ወይም የሰዉነት ሙቀት መጨመር በሚከተሉት ምክንያቶች ይከሰታል፡፡ እነርሱም
• የቫይረስ ኢንፌክሽን
• የባክቴሪያል እንፌክሽን
• በከፍተኛ ሙቀት፣ የፀሃይ ቃጠሎ
• የተወሰኑ የሰዉነት መቆጣት ህመሞች/ inflammatory conditions
• የተለያዩ እጢዎች
• የተወሰኑ መድሃኒቶች
• የተወሰኑ ክትባቶችና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
በትኩሳት ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶች/ Complications
• ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የሰዉነት ድርቀት/ severe dehydration
• መቃዠት/ Hallucinations
• ከትኩሳት ጋር ተያይዞ የሚመጣ እንደሚጥለዉ ሰዉ ማንቀጠቀጥ፡- ይህ በአብዛኛዉ ከ6 ወራት እስከ 5 ዓመታት
ድረስ ባሉ ህፃናት ላይ ይታያል፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
ለእርስዎም ይሁን ለልጅዎ ትኩሳት በሚኖርበት ወቅት ምቾት እነዲሰማዎ
• በቂ ፈሳሽ መዉሰድ፡- ትኩሳት የሰዉነትዎ ፈሳሽ እንዲቀንስና ለሰዉነት መጠዉለግ ስለሚያጋልጥዎ በቂ ዉሃ፣
ጅዉስ/ጭማቂ ወይም ሁለቱንም መዉሰድ ይገባል፡፡ እድሜያቸዉ ከአንድ አመት በታች ላሉ ህፃናት ኦ አር ኤስ (ORS)
መጠቀም ይችላሉ፡፡
• በቂ እረፍት ማግኘት፡- ዕረፍት ማድረግ ትኩሳት እንዲቀንስ ይረዳል
• ተትኩሳትዎ እንዲቀንስ ቀለል ያሉ አልባሳትን መልበስ፣ የክፍሉን ሙቀት እንዲቀንስና ቀዝቀዝ እንዲል ማድረግ፤
እንዲሁም በሚተኙበት ወቅት አንሶላ ብቻ ወይም ስስ ብርድልብስ መልበስ
መድሃኒቶች
የትኩሳትዎ መጠን መጠነኛ ከሆነ የትኩሳት ማስታገሻ መድሃኒቶችን መዉሰድ ብዙም አይመከርም፡፡ ምክንያቱም
ይህን ማድረግ የህመሙ ጊዜ እንዲራዘም አሊያም ህመሙን ያመጣዉ ምን እንደሆነ ለመለየት ሊያዳግት ይችላል፡፡
ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ መድሃኖቶች፡- እንደ አሴታሚኖፌን (ፓራስታሞል)፣ አስፒሪን( ለአዋቂዎች ብቻ)
መዉሰድ፡- መድሃኒቶቹን ሲወስዱ ከመጠን ማለፍ የለብዎትም፡፡ አጠቃቀሙን ከህክምና ባለሙያዎ/ ፋርማሲስት
መጠየቅ ይገባል፡፡

http://am.hesperian.org/hhg/New_Where_There_Is_No_Doctor:%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%8
8%B5_%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%8B%88%E1%88%88%E1%8B%B1_%E1%88%95%E1%8D%
83%E1%8A%93%E1%89%B5_%E1%8B%A8%E1%8C%A4%E1%8A%93_%E1%89%BD%E1%8C%8D
%E1%88%AD

አዲስ የተወለዱ ሕፃናት የጤና ችግር

ይህ ምእራፍ ውስጥ፦
 ምዕራፍ 27: አራስ፡እና፡ጡት፡ማጥባት
 ከወሊድ፡በኋላ፡መደረግ፡ያለባቸው፡እንክብካቤዎች
 ከወሊድ፡በኋላ፡ያሉት፡ሰዓታት
 የመጀመሪያው ሁለት ወር በደንብ ልጅን መከታተል ያስፈልጋል
 አዲስ የተወለዱ ሕፃናት የጤና ችግር
 ጡት ማጥባት
 መድኀኒቶች

ጤናማ ሕፃን ያለችግር መተንፈስ ይችላል። ሕፃኑ ጡት በየ2 እስከ 4 ሰዓት መጥባት አለበት እና ሲርበው
ወይንም ጨርቁን ሲያረጥብ በራሱ መነሳት መቻል አለበት። የተወለደ ሕፃን ቆዳው ንጹ ወይንም ትንሽ
ቅላት ወይንም ከትንሽ ቀን በኃላ የሚጠፋ መንደብደብ ሊኖረው ይችላል። እነዚህን ምልክቶች ካልታዩ ቶሎ
ሕፃኑ እርዳታ ያስፈልገዋል።

አዋቂን ለመግደል ቀናት የሚወስድ በሽታ ሕፃንን በትንሽ


ሰዓት ሊገል ይችላል

ኢንፌክሽን

ለተወለደ ሕፃን ኢንፌክሽን አደገኛ ስለሆነ ወድያውኑ በአንቲባዮቲክ(antibiotics) መታከም አለበት።


አካባቢያችሁ የጤና ጣቢያ ካለ እዚያ ቶሎ መሄድ። ካለዚያ የጤና ጣቢያውን ርቀት እና ያላችሁን መድኃኒት
በማመዛዘን ቶሎ ዕርዳታ ማግኘት ወይንም መድኃኒት እናንተው መስጠት ምንም እንኳን በመንገድ
እርዳታ ለማግኘት እየሄዳችሁም ቢሆን።

አደገኛ ምልክቶች

 ፈጣን አተነፋፈስ፦ ሲተኙ ወይንም ሲያርፉ በደቂቃ ከ60 በላይ ከተነፈሱ


 አየር ለማግኘት መታገል፦ ሕፃን ሲተኛ ወይንም ሲያርፍ ደረት ወደውስጥ መሳብ፣ አየር ለመሳብ
የጥረት ድምጽ ሲሰማ፣ የአየር መውሰድ ጥረት አፍንጫን ሲገፋ

ደረት ወደውስጥ መሳብ


አፍንጫ ትንፋሽ ሲገፋ
 ትኩሳት ከ37.5º ሴንቲግሬድ በላይ ወይንም በጣም ሲቀዘቅዙ ከ35.5ºሴንቲግሬድ በታች
 ሀይለኛ መንደብደብ ከብዙ ብጉር ጋር ወይንም የቆዳ መነፋፋት (ትንንሽ መንደብደብ የተለመደ
ነው)
 አለመመገብ
 አልፎ አልፎ ብቻ ከእንቅልፍ መነሳት እና ምንም መልስ ከሕፃን አለማየት ለምታረጉት ነገሮች
 መንቀጥቀጥ፦እራስ መሳት ወይንም የመፈራገጥ ንቅናቄ

ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች የኢንፌክሽን ምልክት ሊሆኑ ስለሚችል ሕፃኑ ህክምና ያስፈልገዋል።

ህክምና

ኢንፌክሽን ከጠረጠራችሁ ግን ኀይለኛ ካልሆነ ወድያውኑ አምፒሲሊን(Ampicillin) ወይንም


አሞክስሊን(Amoxicillin) ስጡ። ኢንፎክሽኑ ኀይለኛ ከሆነ ወድያውኑ አምፒሲሊን(Ampicillin) እና
ጀንታሚሲን(gentamicin) መከተብ እና የህክምና እርዳታ ባስቸክዋይ መፈለግ። ምን ያህል መሰጠት
እንዳለበት የሕጻኑ ኪሎ ይወስነዋል።

ሕጻኑ በሁለተኛው ቀን እየተሻለው መምጣት አለበት።በሁለተኛው ቀን እየተሻለው ካልመጣ ሌላ ዓይነት


አንቲባዮቲክ(antibiotics) ያስፈልጋል።

የክኒን አንቲባዬቲክ ተፈጭቶ ከእናት ወተት ጋራ ተቀላቅሎ ሊሰጥ ቢቻልም አንዳንድ አንቲባዬቲክ በመርፎ
ክትባት መሰጠት አለባቸው። በመርፌ/በክትባት የሚሰጠው አንቲባዬቲክ መድኃኒት የጎን ረጅም የታፋ
ጡንቻ ላይ ይሁን።ለተጨማሪ ማብራርያ እንዴት ክትባት በትክክል
እንደሚሰጥመድኃኒት፣ምርመራ፣እና፣ሕክምናን እዩ (በመቀናበር ላይ ነው)።

በምጥ ግዜ እናት ትኩሳት ካላት ከላይ የተጠቀሱት አደገኛ ምልክቶች ሕፃን እንዳለው ወይንም እንደሌላው
በደንብ መከታተል ያስፈልጋል።በተጨማሪ ሕፃኑ መኀጸን ውስጥ አይነ ምድር ካደረጉ አይነ ምድሩን ወደ
ውስጥ ሊተነፍሱ ይችላሉ። (አይነ ምድር መኀጸን ውስጥ አርገው ከሆነ ውሀው ቡና አይነት ነገሮች ወይንም
ቀለሙ አረንጎዴማ ይመስላል ወይንም የሕፃኑ ቆዳ ቢጫማ/ለየት ያለ ይሆናል።) ይህ የሳንባ ኢንፌክሽን
በትንሽ ቀን ውስጥ ሊያመጣ ስለሚችል የኢንፌክሽን ምልንክቱ ሲታይ ሕፃኑን ቶሎ ለማሳከም/ለማከም
ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል።

ማልቀስ

አንቺ ስታርፊ እኔ ልጃችንን ልንከባከብ

አንዳንድ ሕፃናት በኀይል ከሌሎች ሕፃናት የበለጠ ያለቅሳሉ ግን የጤና ችግር ምልክቶች እስካልታየባቸው
ድረስ ደህና ናቸው።ለማረጋገጥ በማታለቅስበት ጊዜ ሕፃንዋ ትክክል እንደምትተነፍስ አረጋግጡ።

ተከታታይ እና ረዘም ያለ ለቅሶ ምሽት ላይ የሚብስ ኮሊ ይባላል። በሶስት ወር ውስጥ እየተሻለ ይሄዳል
ተብሎ ይገመታል። ይህ ከሕጻኑ ይልቅ ለቤተሰብ ችግር ነው። ይህንን በመረዳት ለእናት ደግ ሁኑ እና በቂ
ዕረፍት እና እርዳታ እናት እንድታገኝ አርጉ።

ሕጻንዋ ቀኑን ሙሉ በአብዛኛውን ጊዜ ካለቀሰች፣አልመገብም ካለች እና ትኩሳት ወይንም የመተንፈስ ችግር


ካላት የኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል።

ማስታወክ

አንዳንዴ ወተት ከበዛ ሕፃናት ወተት በአፋቸው ወይንም በአፍንጫ ያቀረሻሉ። ሕፃን በተገቢ እስከጠባ እና
ኪሎ እስከጨመረ ማቀርሸት ምንም አደገኛ አይደለም። ልጅ ከጠባ በኋላ ወደ ላይ ከፍ አርጋችሁ ያዙ።
በቀላሉ ወተቱ ከልጅ ከፈሰሰ ማቀርሸት ሲሆን የልጅ ሰውነት ደግሞ ሀይል ሲያቀረሽ ከተጠቀመ ማስመለሰ
ነው።

አደገኛ ምልክቶች

 በተደጋጋሚ ማስመለስ ወይንም ሆድ ውስጥ ምግብ አለመቆየት


 ደም ማስመለስ
 በቂ ፈሳሽ ሰውነት ውስጥ አለመኖር (ዲሀይድሬሽን)

ሕጻኑ ከጠባ በኋላ ትከሻ ላይ ወይንም ጉልበት ላይ አርጋችሁ በቀስታ ጀርባውን መታ መታ በማድረግ
እንዲያገሳ አርጉ።

ውሀ ሰውነት ውስጥ ማነስ (ዲሀይድሬሽን)

የሕፃናት ሰውነት በቀላሉ ውሀ ስለሚያጣ የሰውነት ውሀ ማጠር ለሕፃናት አደገኛ መሆኑን ማወቅ
ያስፈልጋል

ምክንያቱ ምልክት

 ተቅማጥ  ትንሽ መሽናት፣ጠቆር ያለ ሽንት፣ ሀይለኛ


 ትውከት ሽታ ያለው
 ከሁለት እስከ አራት ሰዓት ጊዜ ውስጥ  ደረቅ አፍ እና ደረቅ ምላስ
አለማጥባት  የፈዘዘ ዓይን ወይንም ከተለመደው ውጭ
 የእናት ጡት ያልሆነ ወተት መመገብ (እንደ የሆነ አይነት ቆዳ
ፎርሙላ፣ ወተት፣ ወይንም ውሀ)
 ሙቅ የአየር ጠባይ

ሀይለኛ ውሀ ማጠር የጐደጐዱ ዓይን፣ ለስላሳ እና የጐደጐዱ ቦታዎች ጭንቅላት ላይ መታየት፣ የኪሎ
ማነስ፣ ወይንም ብዙ አለመነቃነቅ/ያለመንቃት ሊያስከትል ይችላል።
ህክምና

የሰውነት የፈሳሽ ማጠር ምልክት ሲታይ፣ ሕፃኑ ተቅማጥ ካለው ወይንም እያስታወከ ከሆነ ሕፃኑ እሺ
እስካለ ድረስ በየ ሁለት ሰዓት ቶሎ ቶሎ እየቀሰቀሳችሁ አጥቡ። በተጨማሪ የፈሳሽ ማጠርን ለማስወገድ
ውሀ ከትንሽ ጨው እና ከስኳር ጋር መስጠት ይቻላል። ይህን አይነት የፈሳሽ ማጠር ማስወገጃ ካጠባችሁ
በኋላ ስጡ። አንዳንድ ጊዜ እናት በቂ ብታጠባም ሰውነትዋ በቂ ወተት ላይሰራ ይችላል (ስለዚህ በደንብ
ለመረዳት ይህንን ተጫኑ)።

የሰውነት ፈሳሽ ያጠረው ሕፃኑ እየተሻለው ካልሄደ በትንሽ ሰዓት ውስጥ የልጁ ሰውነት ውስጥ በቂ ውሀ
እንዲኖር የሚያስፈልገውን ለማድረግ አፋጣኝ ህክምና ፈልጉ።

መንደብደብ

አዲስ የተወለዱ ሕፃናት መንደብደብ፣ እንደ ጭርት የሚመስል፣ ወይንም የሰውነት ቀለማቸው ለየት ሊል
ይችላል እንደዚህ አይነት ነገሮች በአብዛኛው ጊዜ ምንም ጉዳት የለውም እና ምንም ሳይደረግበት በራሱ
ይድናል። የልጆች መቀመጫ ላይ መንደብደብ ብዙ ጊዜ የሚከሰተው በሽንት ወይንም በአይነ ምድር
እርጥበት ነው ስለዚህ መቀመጫቸውን በየጊዜው አጽዱ። በተጨማሪም ጨርቃቸው/ ዳይፐራቸው
እንደረጠበ ወይንም እንደቆሸሸ ቶሎ ቀይሩላቸው። ተለቅ ላለ ሕፃን ወይንም በሙቅ ቀናት መንደብደቡ
እንዲሻለው መቀመጫቸውን አለመሸፈን እና ዚንክ ኦክሳይድ የሚባል ቅባት ሊረዳ ይችላል። በትንሽ ቀን
ውስጥ ካልዳነ የይስት ኢንፌክሽን ሊሆን ይችላል። ለይስት ኢንፌክሽን ናይስታቲን ክሬም ( nystatin
cream) ተጠቀሙ።

ሕፃኑ ውሀ የመቋጠር ወይንም ብዙ ቡጉር ካለው እና በተለይ ሕፃኑ የታመመ ከመሰለ ወይንም ራስ ምታት
ካለው ኢንፌክሽን ሊኖረው ይችላል። ምንም የመሻል ምልክት ካልታየ ወይንም የኢንፌክሽኑ ምልክቶች
እየባሱ ከሄዱ እዚህ የተጠቀሱትን አንቲባዮቲክ(antibiotics) ስጡ።

ቢጫ አይን
ቢጫ ዓይን ወይንም ቢጫ ቆዳ ጆንዲስ(jaundice) በሽታ ይባላል ለጠይም/ለጥቁር ሕፃኑ ዓይናቸውን
መርምሩ። የጆንዲስ(jaundice) በሽታ ሕፃኑ በተወለደ ከሁለተኛ ቀን እስከ አምስተኛ ቀን ድረስ አደገኛ
አይደለም። ለጆንዲስ(jaundice) በሽታ ጠቃሚ ህክምና ወይንም እንክብካቤ ጡት ቶሎ ቶሎ ማጥባት
ነው። ቶሎ ቶሎ ማጥባት የሕፃኑን ዓይን ቢጫ ያደረገውን ኬሜካል ከሕፃኑ ሰውነት ውስጥ እንዲወጣ
ይረዳል። ለማጥባት በየ ሁለት ሰዓት ሕፃኑን ቀስቅሱ በተጨማሪ ሕፃኑን አስራ አምስት ደቂቃ ያህል
ራቁትዋን/ራቁቱን አርጎ የተወሰነ ጊዜ በቀን ውስጥ የፀሐይ ብርሀን እንዲያገኝ ማድረግ ይረዳል።

አስጊ ምልክቶች

 ጆንዲስ(jaundice) በሽታ ወድያውኑ ይጀምራል-ሕፃኑ በተወለደች በ24 ሰዓት ውስጥ


 ጆንዲስ(jaundice) በሽታ ቆየት ብሎ ሲጀምርና አጠቃላይ ሰውነትን ሲሸፍን
 ጆንዲስ(jaundice) በሽታ የያዛት ሕፃን በሀይል እንቅልፍ እንደያዛት ስትሆን ወይንም ለመመገብ
ሕፃንዋን መቀስቀስ ከባድ ነው

ከነዚህ ምልክቶች አንዱ ከታዩ አፋጣኝ እርዳታ ፈልጉ

ዓይን

ዓይን እንባ እና ቅባት እንዲያገኝ የሚረዱት ትንንሽ የዓይን ቀዳዳዎች ሊደፈኑ እና ዓይን አር አይነት ነገር
ሊከማች ይችላል። በንጹህ ሞቅ ባለ እርጥብ ጨርቅ አጽዱት ስታጸዱ የተለያየ ንጹህ ጨርቅ ተጠቀሙ
ምክንያቱም አንዱ ዓይን ኢንፌክሽን ካለ ሌላው አይን ላይ እንዳይተላለፍ።

ብዙ ሴቶች ክለሚዲያ ወይንም ጎነሪያ ቢኖራቸዎም በሽታው እንዳላቸው አያቁም። ከወሊድ በኀላ
ወድያውኑ አንቲባዮቲክ ለአይን መሰጠት ከናት ወደ ልጅ የተላለፈው ጎነርያ የአይን ችግር እንዳያመጣ
ይረዳል።

ሕፃን ከተወለደ ከ5 ቀን በኋላ ደም ያለው ዓይን አር፣ቀይ ከሆነ እና ካበጠ የዓይን ሽፋን ጋር ከታየ
ሕፃንዋ/ሕፃኑ ክላሚድያ ወይንም ጎነሪያ(gonorrhea) የተባለው በሽታ ይዟት ይሆናል። ስለዚህ ህክምናው
ለክለሚዲያው በአፍኢራይትሮሚሲን(erythromycin) የተባለውን መድኃኒት ፈጭታችሁ ከእናት ጡት
ወተት ጋር በመደባልቃችሁ ለሕፃኑ/ንዋ በመስጠት ነው። የትኛው በሽታ ህመሙን እንዳመጣ መመርመር
ካልተቻለ ወይንም ካልታወቀ የሁለቱንም ህክምና/መድኀኒት ስጡ(26ተኛ ገጽ እዩ)። ክለሚድያ ወይንም
ጎነሪያ(gonorrhea) የተባለው በሽታ ሕፃንዋ/ሕፃኑ ካላት/ካለው የአባለዘር በሽታ ስለሆነ እናትዋ እና አባትዋ
መታከም ይኖርባቸዋል።የብልት ችግሮች እና ኢንፌክሽኖች ለመረዳት ይህንን ጎብኙ(እየተቀናጀ ነው)።
የዓይን ኢንፌክሽን በአንድ ወይንም ሁለት ቀን ውስጥ ካልዳነ ሌላ አንቲባዮቲክ(antibiotics) ሕፃንዋ/ሕፃኑ
እንዳትታወር/እንዳይታወር ያስፈልጋል ስለዚህ አፋጣኝ እርዳታ ፈልጉ።

ለስላሳው ቦታ

የሕፃኑ ጭንቅላት ላይ ያለው ለስላሳው ቦታ ጠፍጣፋ መሆን አለበት። የሕፃን ጭንቅላት ላይ የጐደጐደ
ወይንም ያበጠ ለስላሳው ቦታ የአደገኛ ነገር ምልክቶች ናቸው።

የጐደጐደ ለስላሳው ቦታ የሰውነት ፈሳሽ ያበጠ ለስላሳው ቦታ የመንጋጋ


ማነስ ምልክት ነው። በተደጋጋሚ ሕፃንን ቆልፍ(meningitis) ምልክት ነው።
አጥቡ እና የሰውነት ፈሳሽን ለመጨመር አንቲባዮቲክ(antibiotics) ስጡ
የሚረዳን ፈሳሽ ስጡ

እትብት

እትብቱ ከተቆረጠ በኋላ የቀረውን ትርፍ እትብት አትነካኩት ወይንም አትሸፍኑ። የሽንት ጨርቅ እና ዳይፐር
እንዳይነካው። ላለመንካት ሞክሩ መንካት ካለባችሁ በሳሙና እና በውሀ እጃችሁን ታጠቡ።እንብርቱ
ወይንም አካባቢው ከቆሸሸ ወይንም የደረቀ ደም ካለ በሳሙ እና በውሀ በንጹሕ ጨርቅ አጽዱ። እናት
እንብርቱን ከሸፈነች በንጹሕ ጨርቅ ይሁን፣አይጥበቅ እና በቀን ውስጥ በተጋጋሚ ጨርቁን ቀይሩ።

የሕፃንን እትብት አትነካኩ ይህንን ማረግ ኢንፌክሽን እንዳይኖር ይረዳል

ከአንድ ሳምንት በኋላ እትብቱ ደርቆ ይወድቃልእትብት አካባቢው ቀይ ከሆነ፣መጥፎ ከሸተተ፣ ወይንም
መግል ካለው ኢንፌክሽን ይዟል ማለት ነው። በደንብ አጽዱት እና ለሕፃንዋ አሞክሲሊን(amoxicillin)
ስጡ። የሕፃንዋ ፊት ከተለመደው ውጭ ቆጣ ወይንም ቀየር ካለ፣መጥባት ካልቻለች፣ወይንም
የሕፃንዋ/የሕፃኑ ሰውነት ጭንቅ ያለ ከመሰለ፣ እና በተጨማሪ ኢንፌክሽን እትብቱ አካባቢ ካለ ቲታነስ
ሕፃኑትዋ ይዟት ይሆናል (እየተቀናጀ ነው)። ይህ በጣም አስጊ እና አፋጣኝ ጉዳይ ነው። የመጀመርያ
እርዳታ

https://wol.jw.org/am/wol/d/r93/lp-am/102003890

ልጃችሁ ትኩሳት ሲይዘው

“አሞኛል!” ልጃችሁ እንዲህ ቢላችሁ በአፋጣኝ የምትወስዱት እርምጃ የሰውነቱን ሙቀት መለካት ነው።
ትኩሳት ካለው እንደምትደነግጡ የታወቀ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ባልቲሞር፣ ሜሪላንድ በሚገኘው በጆን ሆፕኪንስ የልጆች ማዕከል በተደረገው ጥናት
መሠረት 91 በመቶ የሚሆኑት ወላጆች “መጠነኛ ትኩሳትም እንኳን ራስን አስቶ ሊጥል ወይም እንደ
አእምሮ በሽታ ያለ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል” ያምናሉ። ይኸው ጥናት እንዳመለከተው “89 በመቶ
የሚሆኑት ወላጆች የልጃቸው ትኩሳት 38.9 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ከመድረሱ በፊት ትኩሳት የሚያበርድ
መድኃኒት ሰጥተዋል።”

ልጃችሁ ትኩሳት ሲይዘው መደናገጥ የማይኖርባችሁ ለምንድን ነው? ትኩሳቱን ለማብረድ ምን ማድረግ
ትችላላችሁ?

ትኩሳት ያለው ጥቅም

አንድን ሰው ትኩሳት እንዲይዘው የሚያደርገው ምንድን ነው? የአንድ የጤናማ ሰው ሙቀት (ቴርሞሜትሩ
አፍ ውስጥ ተደርጎ ሲለካ) 37 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ገደማ ቢሆንም የአንድ ሰው የሰውነት ሙቀት በቀን
ውስጥ በአንድ ወይም በሁለት ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።* የሰውነትህ ሙቀት
ጧት ላይ ዝቅ ሊል ከሰዓት በኋላ ደግሞ ከፍ ሊል ይችላል። ከአንጎል ሥር የሚገኘው ሃይፖታላመስ
የሚባለው የአንጎል ክፍል ልክ እንደ ሙቀት መቆጣጠሪያ መሣሪያ የሰውነትን ሙቀት ይቆጣጠራል።
ባክቴሪያ ወይም ቫይረስ ወደ ሰውነታችን ሲገባ የሰውነት በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት በደም ውስጥ
ፓይሮጅንስ የተባሉ ቅመሞችን ያመነጫሉ። ይህም ትኩሳት ያስከትላል። በዚህ ጊዜ ሃይፖታላመስ
የተባለው የአንጎል ክፍል የሰውነታችን ሙቀት ከፍ እንዲል ያደርጋል።

ትኩሳት ሕመም ሊያስከትልና የሰውነት ፈሳሽ እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል። ሆኖም እነዚህ ሁኔታዎች
መከሰታቸው ጉዳት አለው ማለት አይደለም። እንዲያውም የማዮ የሕክምና ትምህርትና ምርምር ተቋም
ትኩሳት ሰውነት በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ የሚከሰቱ ሕመሞችን እንዲያስወግድ በመርዳት ረገድ ቁልፍ
ሚና ሳይጫወት እንደማይቀር ገምተዋል። “ጉንፋንንና ሌሎች የመተንፈሻ አካል በሽታዎችን የሚያስከትሉ
ቫይረሶች ቀዝቃዛ የአየር ጠባይ ይወዳሉ። ሰውነትህ መጠነኛ ትኩሳት እንዲፈጠር በማድረግ ቫይረሶቹ
እንዲወገዱ ያደርጋል።” ይኸው ምንጭ አክሎ እንደገለጸው “መጀመሪያ ላይ የተፈጠረውን አነስተኛ
የትኩሳት መጠን መቀነሱ አላስፈላጊ ከመሆኑም በላይ የልጃችሁን የተፈጥሮ የፈውስ ሂደት እንዲቃወስ
ሊያደርግ ይችላል።” እንዲያውም በሜክሲኮ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል አንዳንድ በሽታዎችን የሚያክመው
የሰውነትን ሙቀት ከፍ በማድረግ ሲሆን ይህም ሃይፐርተርሚያ ተብሎ ይጠራል።
አሜሪካ የሚገኙት ዶክተር አል ሳክሼቲ እንዲህ በማለት ተናግረዋል:- “አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ትኩሳት
በራሱ ችግር አያስከትልም። ሆኖም በሰውነታችን ውስጥ በሽታ ሊኖር እንደሚችል የሚጠቁም ምልክት
ይሰጣል። ስለዚህ አንድ ሕፃን ትኩሳት ሲይዘው ትኩረት ልናደርግ የሚገባን በልጁና ባጋጠመው ሕመም ላይ
እንጂ ሙቀት መለካቱ ላይ መሆን የለበትም።” አሜሪካ የሚገኝ አንድ የልጆች አካዳሚ የሚከተለውን
አስተያየት ሰጥቷል:- “ልጃችሁ አመመኝ እያለ ካላስቸገራችሁ ወይም ከዚህ በፊት በትኩሳት የተነሳ የሰውነት
መንቀጥቀጥ አጋጥሞት ካልነበረ በስተቀር ከ38.3 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በታች ለሆነ ትኩሳት ሕክምና
አያስፈልግም። ልጃችሁ ከዚህ በፊት በትኩሳት የተነሳ የሰውነት መንቀጥቀጥ ወይም ሥር የሰደደ በሽታ
አጋጥሞት የሚያውቅ ካልሆነ በስተቀር ከ38.3 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀትም እንኳን
ቢሆን በራሱ አደገኛ ወይም አሳሳቢ አይደለም። ከዚህ ይልቅ የልጃችሁን ሁኔታ መከታተሉ ብቻ በቂ ሊሆን
ይችላል። በጥሩ ሁኔታ የሚበላና የሚተኛ እንዲሁም የሚጫወት ከሆነ ሕክምና ላያስፈልገው ይችላል።”

መጠነኛ ትኩሳትን ማከም የሚቻለው እንዴት ነው?

ይህ ማለት ግን ልጃችሁን ለመርዳት ልታደርጉ የምትችሉት ምንም ነገር የለም ማለት አይደለም። አንዳንድ
የሕክምና ባለሞያዎች መጠነኛ ትኩሳትን ለማከም የሚረዳ የሚከተለውን ምክር ይሰጣሉ:- ልጃችሁን
ቀዝቀዝ ባለ ክፍል ውስጥ አስተኙት። ቀለል ያለ ልብስ አልብሱት። (ከልክ በላይ እንዲሞቀው ማድረግ
ትኩሳቱን ሊያባብስበት ይችላል።) ትኩሳት የሰውነትን ፈሳሽ ሊያሟጥጥ ስለሚችል እንደ ውኃ፣ ውኃ
የተደባለቀበት የፍራፍሬ ጭማቂና ሾርባ የመሳሰሉ ፈሳሾችን አጠጡት።* (እንደ ለስላሳ መጠጥ ወይም ሻይ
ያሉ ካፌይን ያለባቸው መጠጦች ብዙ የማሸናት ባሕርይ ስላላቸው ከሰውነት ውስጥ ብዙ ፈሳሽ እንዲወጣ
ሊያደርጉ ይችላሉ።) ሕፃናት ከጡት እንዳይነጠሉ ማድረግ ያስፈልጋል። ትኩሳት ጨጓራ ሥራውን
በቅልጥፍና እንዳያከናውን ስለሚያደርግ ልጃችሁን በቀላሉ የማይፈጩ ምግቦችን አትመግቡት።

የልጁ ትኩሳት ከ38.9 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሲያልፍ እንደ ፓራሴታሞል ወይም አይቢዩፕሮፈን ያሉ ትኩሳት
የሚቀንሱ መድኃኒቶችን መስጠት ይቻላል። ይሁንና በመድኃኒቶቹ ላይ የሚገኘውን መመሪያ መከተል
አስፈላጊ ነው። (ከሁለት ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ሐኪም ሳያማክሩ ምንም ዓይነት መድኃኒት መስጠት
አይገባም።) ትኩሳት የሚያበርዱ መድኃኒቶች ቫይረሶችን አይገድሉም። ስለዚህ መድኃኒቶቹ ሥቃይ
ለማስታገስ ካልሆነ በስተቀር ልጁ ከያዘው ጉንፋን ወይም ጉንፋን መሰል ሕመም ቶሎ እንዲድን አይረዱም።
አስፕሪን ሬየስ ሲንድሮም የተባለ ለሕይወት አስጊ የሆነ የነርቭ በሽታ ሊያስከትል ስለሚችል ትኩሳት
ለማብረድ ብሎ ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች መስጠት ተገቢ እንዳልሆነ አንዳንድ ባለሞያዎች
ይመክራሉ።*

እስከ ቁርጭምጭሚት የሚደርስ ለብ ያለ ውኃ ሳፋ ውስጥ ጨምሮ ልጁን እዚያ ውስጥ ካስቀመጡ በኋላ
ስፖንጅ ወይም ጨርቅ በውኃ እያራሱ ሰውነቱ ላይ በማፍሰስ ትኩሳቱ እንዲቀንስ ማድረግ ይቻላል።
(መርዝነት ሊኖረው ስለሚችል ገላውን ለማሸት አልኮል አትጠቀሙ።)

ሣጥኑ አንድ ሰው ልጁን ወደ ሐኪም ቤት መቼ መውሰድ እንዳለበት አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎችን ይዟል።
እንደ ጉድፍ፣ ኢቦላ፣ ታይፎይድ ወይም ቢጫ ወባ ያሉ በቫይረስ የሚመጡ ተዛማች በሽታዎች ባሉበት
አካባቢ የሚኖር ሰው ትኩሳት ሲይዘው ቶሎ ብሎ ወደ ሐኪም ቤት መሄድ ይኖርበታል።
በአጠቃላይ ሲታይ በቅድሚያ ማድረግ ያለብህ ልጅህን ማረጋጋት ነው። በትኩሳት ምክንያት የነርቭ ችግር
ወይም ሞት ሊያጋጥም የሚችለው አልፎ አልፎ እንደሆነ መዘንጋት የለብህም። በትኩሳት ምክንያት ራስን
ስቶ መውደቅ ሊያጋጥም ቢችልም ይህ ሁኔታ ከማስደንገጡ በቀር የሚያስከትለው ዘላቂ መዘዝ አይኖርም።

እርግጥ ነው፣ ከሁሉ የተሻለው ልጃችሁ እንዳይታመም ጥንቃቄ ማድረግ ነው። እንዲህ ማድረግ
የሚቻልበት ከሁሉ የተሻለው ውጤታማ መንገድ ንጽሕናን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል ልጃችሁን
ማስተማር ነው። ልጆች በተለይ ምግብ ከመብላታቸው በፊት፣ ከተጸዳዱ በኋላ፣ ሕዝብ በበዛበት አካባቢ
ከቆዩ ወይም ለማዳ እንስሳትን ካሻሹ እጃቸውን እንዲታጠቡ አስተምሯቸው። የተቻለህን ሁሉ ጥረት
አድርገህ ልጅህ መጠነኛ ትኩሳት ቢይዘው መደናገጥ አይኖርብህም። እስካሁን እንዳየነው ልጅህ
እንዲያገግም ለመርዳት ልታደርገው የምትችለው ብዙ ነገር አለ።

[የግርጌ ማስታወሻ]

የሰውነት ሙቀት በሚለካበት ቦታና በመለኪያው መሣሪያ ዓይነት ሊለያይ ይችላል።

ተቅማጥና ማስመለስ የታከለበት ትኩሳት ሲያጋጥም የሰውነትን ፈሳሽ ለመጠበቅ የሚያገለግል መመሪያ
በሚያዝያ 8, 1995 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 11 ላይ ወጥቷል።

ሬየስ ሲንድሮም በቫይረስ የሚመጣ ሕመምን ተከትሎ የሚከሰት ከባድ የልጆች የነርቭ በሽታ ነው።

[በገጽ 27 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

ትኩሳት የያዘው ልጅ ሐኪም ቤት መወሰድ የሚኖርበት. . .

▪ ዕድሜው ገና ሦስት ወር ወይም ከዚያ በታች ከሆነና ትኩሳቱ 38 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ወይም ከዚያ በላይ
ከሆነ

▪ ዕድሜው ከሦስት እስከ ስድስት ወር ሆኖ የሰውነት ሙቀቱ 38.3 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ወይም ከዚያ በላይ
ከሆነ

▪ ዕድሜው ከስድስት ወር በላይ ሆኖ የሰውነት ሙቀቱ 40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ

▪ ፈሳሽ መውሰድ እምቢ ካለና የሰውነቱ ፈሳሽ እንደተሟጠጠ የሚያሳይ ምልክት ሲኖር

▪ ራሱን ስቶ ከወደቀ ወይም ከልክ ያለፈ መዝለፍለፍ ከታየበት

▪ ሰባ ሁለት ሰዓት ካለፈ በኋላም ትኩሳቱ ካልበረደለት

▪ ያለማቋረጥ ካለቀሰ፣ እንደ ቅዠትና የአእምሮ መታወክ ከገጠመው

▪ ገላው ላይ ሽፍታ ከወጣበትና የመተንፈስ ችግር ካጋጠመው፣ የሚያስቀምጠው ወይም በተደጋጋሚ


የሚያስመልሰው ከሆነ
▪ አንገቱን ማዞር ካቃተው ወይም ከባድ ራስ ምታት ከገጠመው

[ምንጭ]

ምንጭ:- የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ

https://www.mahderetena.com/archives/3577

ትኩሳትን የሚያመጡ በሽታዎች የትኞቹ ናቸው?

በሀገራችን ውስጥ ትኩሳትን እንደ ዋና ምልክት በማሳየት ከፍተኛውን ደረጃ የያዙት በሽታዎች ወባ፣
ታይፎይድ፣ ታይፈስ እና ግርሻ (Relapsing Fever) ናቸው። ሌሎች ትኩሳትን አምጪ በሽታዎች
የሚከሰቱት በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ ሊሆን ይችላል። ከነዚህም መካከል ቲቢ፣ የሳንባ ምች፣ የኩላሊት
ኢንፌክሽን፣ የጉበት በሽታ፣ ካንሰር፣ ማጅራት ገትር፣ የተቅማጥ በሽታዎች ይጠቀሳሉ።

የወባ በሽታ

የወባ በሽታን የምታስተላልፈው የወባ ትንኝ በሞቃትና የረጋ ውሃ ባለባቸው አካባቢዎች በብዛት ትራባለች።
በንክሻዋም ከአንድ ሰው ወደሌላ በቀላሉ ታስተላልፋልች። ጥገኛ ህዋሳቱ የደም ሴሎችን በማጥቃት
ስራቸውን እንዳያከናውኑ ያግዷቸዋል። በወባ የተጠቃ ሰው ከትኩሳቱ በተጨማሪ የራስ ምታት፣ ትውከት፣
ብርድ ብርድ ማለት፣ ድካም እንዲሁም የጡንቻ ህመም ሊያጋጥመው ይችላል።

በበሽታው የተጠቃ ሰው በአፋጣኝ ህክምና ካላገኘ፤ ወደ ጭንቅላት ሊወጣ ወይም ሌሎች በሽታዎች
ሊደረቡበት ይችላሉ። በዚህም ምክኒያት የደም ማነስ፣ የደም ስኳር መጠን ማነስ፣ የጥገኛ ሀዋሳት በደም
ውስጥ መሰራጨት፣ የሳንባ በሽታ፣ የሰውነት መድማት ባህሪ፣ የሰውነት/አይን ቢጫ መሆን ሊከሰቱ
ይችላሉ። የበሽታውን መኖር በቀላል የደም ምርመራ ማረጋገጥ ይቻላል። በሽታው እንዳለ ከተረጋገጠ
እንደበሽታው አይነት ከ3-10 ቀናት የሚፈጅ ህክምና ሊሰጥ ይችላል። የበሽታው መዘዞች ችግር ካስከተሉ፤
ለረዥም ጊዜ ሊሰጥ ይችላል።

በሽታው እንዳይከሰት ለመከላከል፤ አጎበር በአልጋ ላይ መጠቀም፣ ማታ ማታ ከቤት አለመውጣት፣ የተባይ


ማጥፊያ በቤት ውስጥ መንፋት ይቻላል።

ታይፈስ

ይህ በሽታ በባክቴሪያ የሚከሰት ሲሆን ከጽዳት ማነስ የሚመጡትን ቅማልን የመሳሰሉት ነፍሳት በሽታውን
ከሰው ወደሰው ያስተላልፋሉ። የበሽታው ምልክቶች ትኩሳት፣ ራስምታት፣ ሽፍታ (ከደረት ጀምሮ ሁሉንም
የሰውነት ክፍል የሚሸፍን)፣ የዓይን ህመም፣ የምላስ መድረቅ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

በሽታው በቶሎ ካልታከመ የቆዳ መበላሸት፣ ጋንግሪን፣ የደም መርጋት፣ የሣንባ ምች፣ እንዲሁም የኩላሊትና
የልብ በሽታዎችን ሊያመጣ ይችላል። የበሽታውን መኖር በደም ምርመራ ማረጋገጥ ይቻላል። ከዚህም
በኋላ ከ7 እስከ 15 ቀን የሚፈጅ የሚዋጥ ፀረ-ተህዋስ መድሀኒት ይሰጣል።
በሽታውን ለመከላከል እንዲያስችል የግል እና የአካባቢ ጽዳት ወሳኝነት አለው። ከዚህም በተጨማሪ፤ ቤትን
የተባይ ማጥፊያ በመንፋት አስተላለፊ የሆኑትን ነፍሳት ማስወገድ ይቻላል።

ታይፎይድ

ይህ በሽታ በባክቴሪያ የሚመጣ ሲሆን ዋና ዋና ምልክቶቹም ትኩሳትና የሆድ ህመም ናቸው። በሽታው
የሚመጣው ንጽህና የሌለው ምግብ ከመመገብ፣ ያልተጣራ ውሀ ከመጠጣትና እጅን ሳይታጠቡ ምግብ
በመመገብ ነው።

የበሽታው ምልክቶች ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የሆድ ህመም፣ ነስር፣ ግራ መጋባት፣ እና ክብደት መቀነስ
ናቸው። በሽታው ሳይታከም ከዘገየ የጉበት ኢንፌክሽን፣ ማጅራት ገትር፣ ጆሮ ደግፍ፣ የኩላሊት እና የልብ
በሽታ፣ እና የሳንባ ምች በበሽታው ላይ ሊደረቡ ይችላሉ።

የደም እና የሰገራ ምርመራ የበሽታውን መኖር የሚያሳውቁ ዋና ዋና መንገዶች ናቸው። የበሽታው መኖር
ከተረጋገጠ ከ10 እስከ 14 ቀን የሚዋጥ መድሀኒት ይታዘዛል።

የግልና የአካባቢ ጽዳት መጠበቅ እንዲሁም ምግብን ከማዘጋጀት በፊት፣ ከመፀዳጃ ቤት መልስ እንዲሁም
ከመመገብ በፊት እጅን መታጠብ፤ በሽታውን ለመካላከል የሚረዱ ወሳኝ ጥንቃቄዎች ናቸው።

ግርሻ (Relapsing Fever)

በባክቴሪያ የሚመጣ በሰውነት ቅማል የሚተላለፍ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ በብዛት
የሚገኝ በሽታ ነው።

ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ የመገጣጠሚያዎች ህመም፣ ድካም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣
ውሃ ጥማት፣ የዓይን መቅላት፣ የሆድ ህመም እና ሽፍታ የበሽታው መገለጫዎች ናቸው። በሽታው
ሳይታከም ከቆየ የዓይን ቢጫ መሆን እና ግራ መጋባትን ሊያመጣ ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ነስር፣
ደም የቀላቀለ አክታ፣ ማጅራት ገትር፣ ያሳንባ ምች፣ የልብ በሽታ እንዲሁም የጣፊያ መፍረስ? ሊያመጣ
ይችላል።

ህክምናውን ለመስጠት የደም ምርመራ እንዲሁም የጀርባ ፈሳሽ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ህክምናውም ለ7 ቀናት የሚዋጥ መድሃኒት ይሆናል። በሽታውን ለመከላከል ጽዳት እና ፀረ ተባይ
መድሀኒቶች እጅጉን ይረዳሉ።

You might also like