You are on page 1of 52

ሞዱል 2᎓ ተጨማሪ ምግቦችና ማይክሮኒውትረንት

1
2
ማውጫ
ትምህርት 1᎓ ከ6 - 8 ወራት ዕድሜ ላላቸው ሕፃናት ተጨማሪ ምግብ አመጋገብ .......... 3

ትምህርት 2᎓ ከ 9 - 11 ወራት ዕድሜ ላላቸው ሕፃናት ተጨማሪ ምግብ አመጋገብ ....... 10

ትምህርት 3᎓ ከ 12 – 24 ወራት ዕድሜ ላላቸው ሕፃናት ተጨማሪ ምግብ አመጋገብ ..... 16

ትምህርት 4᎓ ንፅህናና የምግብ ዝግጅት .............................. 22

ትምህርት 5᎓ የህጻን ምግብ አዘገጃጀት .............................. 28

ትምህርት 6᎓ ወደ ጤና ተቋማት ስለ መሄድ ............................ 31

ትምህርት 7᎓ የታመመን/ችን ልጅ መመገብና መንከባከብ .................... 38

ትምህርት 8᎓ ማይክሮኒውትረንት - ቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ዲና አዮዲን ............. 46

3
ትምህርት 1᎓ ከ6 - 8 ወራት ዕድሜ ላላቸው ሕፃናት ተጨማሪ ምግብ አመጋገብ

1. እያንዳንዱን ትምህርት 2. ሁሉም መገኘታቸውን 3. የተማሩትን ተግባራዊ 4. የእያንዳንዱን ስእል ትርጉም


በጨዋታ ጀምሩ አረጋግጡ ችግር ያለበትም ካለ ስለማድረጋቸው ጠይቁ ንገሯቸው
ጠይቁ

በስድስተኛው ወር ዕድሜ ላይ የሚሰጡ የመጀመሪያ ምግቦች

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

በስድስተኛ ወር ላይ ጡት ካጠቡ በኋላ ለህጻናት ለስላሳ ምግቦችን ይስጡ


 የጡት ወተት ለህጻናት አሁንም በጣም አስፈላጊ የሆነ የምግብ ምንጭ ነው
 ምግብ ከመስጠትዎ በፊት ዘወትር ጡት ያጥቡ
 ለአካሉ/ሏ እድገት እንዲረዳው/ት ከስድስት ወር ጀምሮ ህጻኑ/ኗ ተጨማሪ ምግብ ያስፈልገዋል/ታል

ከጤፍ፣ ከቦቆሎ፣ ከስንዴ፣ ከአጃ፣ ከገብስ ዱቄት ወይም ከዱባ ገንፎ ያዘጋጁ። ካገነፉ በኋላ የምግብ ዘይት ወይም ቅቤ
ይጨምሩበት።

 እሳት ከነካው ዘይት ይልቅ እሳት ያልነካው ዘይት ለህጻናት የተሻለ ነው።
 የእህል ዘሮች ለልጆች ሃይል ይሰጧቸዋል
 ህጻናት ገንፎውን እንዲበሉ ለማበረታታት በየመሃሉ ጡት ያጥቧቸው

? ለልጅዎ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጡት/ጧት ምግብ ምን ነበር?


? ልጅዎ በተወለደ/ች በስንት ጊዜው ነው ምግብ መስጠት የጀመሩ ?

4
በስድስተኛው ወር ዕድሜ ላይ የሚሰጡ የመጀመሪያ ምግቦች

በስድስተኛ ወር
ጡት ካጠቡ በኋላ
ለስላሳ ምግቦችን
ይስጡ

ከጤፍ፣ ከቦቆሎ፣ ከስንዴ፣


ከአጃ፣ ከገብስ ዱቄት
ወይም ከዱባ ገንፎ
ያዘጋጁ። ካገነፉ በኋላ
የምግብ ዘይት ወይም ቅቤ
ይጨምሩበት።

5
ከ6 – 8 ወራት ዕድሜ የሆነው/ናት ህጻን በቀን ስንት ጊዜና ምን ያህል ይመገባል

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ለልጅዎ ለስላሳ ገንፎ በቀን ሦስት ጊዜ ይስጡ።


 ጠዋት፣ ቀትርና በምሽት ገንፎ ይስጡት/ጧት። ህጻናትን በዝግታና በትዕግስት ይመግቧቸው።
 እንዲበሉ አበረታቷቸው፣ ነገር ግን አታስገድዷቸው።

በእያንዳንዱ የምገባ ወቅት አንድ የቡና ስኒ ገንፎ ለልጁ/ቷ ይስጡ።


 በተለያየ የቡና ስኒ አድርገው ይመግቡት/ቧት።

ወፈርና ለስለስ ያለ ገንፎ ያዘጋጁ።

 ልክ እንደ ማር ወፈርና ለስለስ ያለ ገንፎ ያዘጋጁ።


 ቀጭን ገንፎ (አጥሚት) በህፃኑ/ኗ አፍ ተመልሶ ይፈስሳል።
 በጣም ወፍራም ገንፎ ደግሞ የህፃኑን/ኗን ጉሮሮ ሊያንቀው ይችላል።
 ወፈርና ለስለስ ያለ ገንፎ ግን በአፉ ውስጥ ቆይቶ ህፃኑ/ኗ ተጨማሪ ምግብ ይሆነዋል/ናታል።

6
ከ6 – 8 ወራት ዕድሜ ያላቸው ህጻናት በቀን ስንት ጊዜና ምን ያህል ይመገባሉ

ለስላሳ ገንፎ በቀን ሦስት ጊዜ ይስጡት/ጧት።

በእያንዳንዱ የምገባ ወቅት አንድ የቡና ስኒ ገንፎ ለህፃኑ/ኗ ወፈርና ለስለስ ያለ ገንፎ
ይስጡ። ያዘጋጁ።

7
ከ6 – 8 ወራት ዕድሜ ላላቸው ህጻናት የምግቡ አይነት ከፍ ይበል

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ለህጻናት በሚያዘጋጁት ገንፎ ላይ አዳዲስ የምግብ አይነቶች ይጨምሩ

 ከእህል ብቻ የሚዘጋጅ ገንፎና ዘይት ለህፃኑ/ኗ ሃይል ይሰጠዋል/ጣታል።


 ሌሎች የምግብ አይነቶችን መጨመር ህፃናት በደንብ እንዲያድጉ ይረዳቸዋል።

ለህፃናት ጤንነት በሚያዘጋጁት ምግብ ውስጥ አሳና አተር ይጨምሩበት።

 የደረቀውን አሳ አድቅቆ መውቀጥ በቀላሉ ለመዋጥ ያስችላል።


 ህጻናትን ከመመገብዎት በፊት ጠንካራ የሆኑትን መርጦ ማውጣት ያስፈልጋል።
 አሳና አረንጓዴ አተር በብረት ማዕድን የበለጸጉ ናቸው።
 የብረት ማዕድን የደም ማነስን ይከላከላል።

እንቁላል፣ ባቄላና ምስር መጨመር ለአጥንትና ለጡንቻ ጥንካሬ ይጠቅማል።

 ባቄላውንና ምስሩን ገንፎው ውስጥ ከመጨመርዎ በፊት አልመው መፍጨት ይገባዎታል።


 እነዚህን የምግብ ዓይነቶች የተመገቡ ልጆች ጠንካራና ረጅም ሆነው ያድጋሉ።

ቆስጣ፣ ካሮት፣ ዱባ፣ ሙዝና ማንጎ መጨመር በሽታን ይከላከላሉ።

 አትክልቶችና ፍራፍሬዎች በሽታ ተከላካይ ምግቦች ናቸው።


 በሽታ የሚከላከሉ ቫይታሚኖችን በውስጣቸው ይዘዋል።

? ልጅዎ እንዲያድግ ነገ በገንፎው ውስጥ ከእነዚህ ምግቦች መካከል የትኞችን መጨመር ይችላሉ?

5. ተግባራት 6. እንቅፋቶች ላይ 7. ማለማመድና ማሰልጠን 8. አስተያየቶችን ጠይቁ


ተወያዩ

8
ከ6 – 8 ወራት ላሉ ህጻናት የምግቡ አይነት ከፍ ይበል

የደም ማነስን ለመከላከል አሳና አተር


ይጨምሩበት።
ጠንካራ ጡንቻና አጥንት ለመገንባት
እንቁላል፣ ባቄላና ምስር ይጨምሩበት።

ቆስጣ፣ ካሮት፣ ዱባ፣ ሙዝና ማንጎ


መጨመር በሽታን ይከላከላሉ።

9
ትምህርት 2᎓ ከ 9 - 11 ወራት ዕድሜ ላላቸው ሕፃናት ተጨማሪ ምግብ አመጋገብ

2. ሁሉም መገኘታቸውን
1. እያንዳንዱን ትምህርት አረጋግጡ ችግር ያለበትም ካለ 3. የተማሩትን ተግባራዊ 4. የእያንዳንዱን ስእል ትርጉም
በጨዋታ ጀምሩ ጠይቁ ስለማድረጋቸው ጠይቁ ንገሯቸው

ከ 9 - 11 ወራት ዕድሜ ላላቸው ሕፃናት ተጨማሪ አመጋገብ

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ቀንም ሆነ ሌሊት ህፃኑ/ኗ የመራብ ምልክት ባሳየ/ ቁጥር ጡት ያጥቡት/ቧት።

 ለህፃኑ/ኗ በጣም አስፈላጊው ምግብ የእናት ጡት ወተት ነው።


 የእናት ጡት ወተት ከፍየል፣ ከላም ወተትም ሆነ ከውሃ የበለጠ ጠቃሚ ነው።
 ለሁለት ዓመታት ጡት ማጥባት ይቀጥሉ።
 ሁልጊዜም ምግብ ከማብላትዎ በፊት ጡት ያጥቡ።

በዘጠነኛው ወር አነስ ብሎ የተከተፈ ወይም ጠንከር ያለ ምግብ ይስጡት።

 ጠንከር ያለ ምግብ ህፃኑ/ኗ ማኘክን እንዲለማመዱ ያግዛቸዋል።


 በእጆቹ/ቿ ምግብ እንዲያነሳ/እንድታነሳ ያበረታቷቸው።
 ምግቡ እንዳያንቀው/እንዳያንቃት ሲከተፍ ደቀቅ ብሎ መሆን አለበት።

? ትናንትና ለልጅዎ ምግብ እንዴት ነበር ያዘጋጁት?


? ልጅዎ ማኘክና በገዛ እጁ/ጇ መመገብ እንዲማር/እንድትማር ነገ ምን አይነት ምግብ ማዘጋጀት ይችላሉ?

10
ከ 9 - 11 ወራት ዕድሜ ላላቸው ሕፃናት ተጨማሪ ምግብ አመጋገብ

ቀንም ሆነ ሌሊት
ህፃኑ/ኗ የመራብ
ምልክት ባሳየ/ች ቁጥር
ጡት ያጥቡ።

በዘጠነኛው ወር አነስ ብሎ የተከተፈ ወይም ጠንከር ያለ ምግብ ይስጡት።


11
ከ9 –11 ወራት ያሉ ህጻናት በቀን ስንት ጊዜና ምን ያህል ይመገባሉ

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ጡት ካጠቡ በኋላ በቀን 4 ጊዜ ምግብ ይመግቡ


 ንጋት፣ እኩለ ቀን፣ ከሰአት በኋላና ምሽት ላይ ምግብ ይስጡ።
 ወፍራም ገንፎና በደቃቁ የተከተፈ ምግብ ይስጡ።
 ምግብ ከማብላትዎ በፊት ሁልጊዜ ጡት ማጥባት አለበዎት።
 በቀን አንድ ወይም ሁለት ጊዜ መክሰስ ይስጡ።
 መክሰስ የሚባለው በቁርስና በምሳ መካከል ወይም በምሳና በእራት መካከል የሚበላ ቀለል ያለ ምግብ ነው።

በእያንዳንዱ የምገባ ወቅት አንድ የቡና ስኒ ምግብ ለህፃኑ/ኗ ይስጡ።


 በተለያየ የቡና ስኒ ይመግቡ፤ ይህን ሲያደረጉ ህፃኑ/ኗ ምን ያህል እንደተመገበ/ች ማወቅ ይችላሉ።
 ይህንንም መግበው ልጅዎ የማይጠግብ/የማትጠግብ ከሆነ ምግብ ይጨምሩላቸው።

? ልጅዎን ትናንትና ስንት ጊዜ መገቡ?

? ከምግብ ሰዓት በፊት ምን አይነት ምግብ ለመክሰስ ሰጡ?

12
ከ9 –11 ወራት ያሉ ህጻናት በቀን ስንት ጊዜና ምን ያህል ይመገባሉ

ጡት ካጠቡ በኋላ በቀን 4 ጊዜ ምግብ ይመግቡ

በእያንዳንዱ የምገባ ወቅት


አንድ የቡና ስኒ ምግብ
ለህፃኑ/ኗ ይስጡ።

13
ከ9 – 11 ወር ለሆናቸው ህጻናት ለመክሰስ የሚሰጡ የምግብ አይነቶች

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ያልተቀቀለ ቲማቲም፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ አቡካዶና ሀብሀብ የመሳሰሉትን ለመክሰስ ይስጡት።

 የተለያየ ቀለም ያላቸውን ምግቦች ይስጡ።


 የተለያየ ቀለም ያላቸው ምግቦች በውስጣቸው የተለያየ ቫይታሚኖች አሏቸው።
 ቀይ ቀለም ያላቸው ምግቦች ቢጫ ቀለም ካላቸው ምግቦች የተለየ ንጥረ ምግቦች አላቸው።
 ያልተቀቀሉ ምግቦችን ለመክሰስ ማዘጋጀት ለእናቶች ቀላል ነው። የስራ ጫና የለውም።

እንደ ስጋ፣ እንቁላል፣ ድንች ወይም ዱባ የመሳሰሉትን ቀቅለው ወይም ጠብሰው ለመክሰስ ይስጡ።

 የሚበስሉ ምግቦችን በጠዋት ያዘጋጁ።


 እነዚህን የበሰሉ ምግቦች በዕለቱ ይመግቧቸው።
 ከቤት ወጣ ካሉ መክሰስ የሚሆኑ ምግቦችን ይዘው ይሂዱ።

ለምሳሌ ብስኩት፣ የኦቾሎኒ ቅቤ ወይም እንጀራ የመሳሰሉትን የተዘጋጁ ምግቦች ለመክሰስ


ይስጡ።

? በትናንትናው ዕለት ከ9 – 11 ወራት ለሆነው/ናት ህፃን ለመክሰስ ምን ሰጡ?


? ለመክሰስ የሚሆኑ ምን አይነት ምግቦችን ማዘጋጀት ይችላሉ?

5. ተግባራት 6. እንቅፋቶች ላይ 7. ማለማመድና ማሰልጠን 8. አስተያየቶችን ጠይቁ


ተወያዩ

14
ከ9 – 11 ወር ለሆነው ህጻን ለመክሰስ የሚሰጡ የምግብ አይነቶች

ያልተቀቀለ ቲማቲም፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣


ፓፓያ፣ አቡካዶና ሀብሀብ
የመሳሰሉትን ለመክሰስ ይስጡት።

እንደ ስጋ፣ እንቁላል፣ ድንች ወይም ዱባ


የመሳሰሉትን ቀቅለው ወይም ጠብሰው 15
ለመክሰስ ይስጡ።
ትምህርት 3᎓ ከ 12 – 24 ወራት ዕድሜ ላላቸው ሕፃናት ተጨማሪ ምግብ አመጋገብ

1. እያንዳንዱን ትምህርት 2. ሁሉም መገኘታቸውን 3. የተማሩትን ተግባራዊ 4. የእያንዳንዱን ስእል ትርጉም


በጨዋታ ጀምሩ አረጋግጡ ችግር ያለበትም ካለ ስለማድረጋቸው ጠይቁ ንገሯቸው
ጠይቁ
ከ1 – 2 ዓመት ድረስ ጡት ማጥባትዎን ይቀጥሉ

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ልጁ አመት ከሞላው በመጀመሪያ ምግብ ቀጥሎ ጡት ይስጡት

 በዚህ ዕድሜ ላሉ ህፃናት ሀይል ለማግኘትና ለእድገት ምግብ ያስፈልጋቸዋል።


 ህፃኑ/ኗ በፈለገ/ች ጊዜ ሁሉ ጡት ያጥቡ
 ለሁለት ወይም ከዚያም በላይ ለሆኑ አመታት ጡት ማጥባትዎን ይቀጥሉ።

ጡት በመጥባት የቀጠሉ ልጆች ጤናማና ጠንካራ ይሆናሉ።

 የእናታቸውን ጡት የሚጠቡ ልጆች የላም ወይም የፍየል ወተት ብቻ ከሚጠጡት ልጆች የበለጠ ጤናማዎች
ናቸው።
 የእናት ጡት ወተት ልጆችን ከበሽታ ይከላከላል።

? ትልቁ/ቋን ልጅዎን ለስንት ዓመት አጠቡ?


? ለሁለት አመት ወይም ከዚያ ለበለጠ ጊዜ ስለማጥባት እናቶች ምን ይሰማቸዋል?
? እናቶች ጡታቸውን ማጥባት እንዲቀጥሉ እንዴት ልናበረታታቸው እንችላለን?

16
ከ1 – 2 ዓመት ድረስ ጡት ማጥባትዎን ይቀጥሉ

ህፃኑ/ኗ አመት
ከሞላው/ት
በመጀመሪያ ምግብ
ቀጥሎ ጡት ይስጡ

ጡት በመጥባት
የቀጠሉ ልጆች
ጤናማና ጠንካራ
ይሆናሉ።

17
1 - 2 ዓመት ያሉ ህጻናት በቀን ስንት ጊዜና ምን ያህል ይመገባሉ

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ዕድሜአቸው ከአንድ እስከ ሁለት አመት ላሉ ህጻናት በቀን አምስት ጊዜ ይመግቡአቸው።

 በቀን አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ገንፎ ይስጡ።


 በቀን ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ ያህል መደበኛ የቤተሰቡን ምግብ ያብሉ።
 በየቀኑ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ መክሰስ ይስጡ።
 አቡካዱ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ዳቦ ወይም የተቀቀለ ድንች የመሳሰሉትን ለመክሰስ ይስጡ

በእያንዳንዱ የምገባ ወቅት አንድ ተኩል የቡና ስኒ ምግብ ይስጡ።


 ህፃኑ/ኗ ካልጠገበ/ች ተጨማሪ ምግብ ይስጡ።

ለማኘክና ለመዋጥ አስቸጋሪ የሆነውን ምግብ ደቀቅ አድርጎ መክተፍ ወይም መፍጨት።

 ስጋው ደቀቅ ብሎ ይከተፍ።


 ህፃናት በቀላሉ ሊውጡት የማይችሉትን ምግብ አድቅቆ መክተፍ፣ መውቀጥ ወይም መፍጨት ይገባል።

18
1 - 2 ዓመት ያሉ ህጻናት በቀን ስንት ጊዜና ምን ያህል ይመገባሉ

ዕድሜአቸው ከአንድ እስከ ሁለት አመት ላሉ ህጻናት በቀን አምስት ጊዜ ይመግቡአቸው።

በእያንዳንዱ የምገባ ወቅት አንድ ተኩል የቡና


ስኒ ምግብ ይስጡ።

ለማኘክና ለመዋጥ አስቸጋሪ የሆነውን ምግብ ደቀቅ


አድርጎ መክተፍ ወይም መፍጨት።

19
ከ 1 – 2 ዓመት ለሆናቸው ህፃናት የሚሰጡ የምግብ አይነቶች

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

በሽታን ለመከላከል ቀይ፣ ብርቱካናማና አረንጓዴ ቀለም ያላቸውን ምግቦች ለህፃናት ይስጡ።

 ካሮት፣ ዱባ፣ ጎመን፣ ማንጎና ፓፓያ ይስጡ።


 እነዚህ ምግቦች ቫይታሚን ኤ አላቸው።
 ቫይታሚን ኤ ከበሽታ ይከላከላል።

ለአጥንት ጥንካሬና ለጤናማ ደም ስለሚያገለግሉ ጉበት፣ ቀይ ስጋ፣ እንቁላል፣ የዶሮ ስጋና አሳ


ህፃኑ/ኗ ይስጡ።

 እነዚህ ምግቦች በብረትና በፕሮቲን ማዕድን የበለጸጉ ናቸው።


 የብረት ማዕድን የደም ማነስ በሽታን ይከላከላል።
 የፕሮቲን ማዕድን ጠንካራ ጡንቻና አጥንት ለመገንባት ያግዛል።
 ለቤተሰቡ በሚዘጋጀው ምግብ ውስጥ አዮዲን ያለበት ጨው ይጨምሩበት።

? ለልጆች እድገት የሚያስፈልጉ ሌሎች ምግቦች የትኞቹ ናቸው?


 ቅቤ፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ጤፍና ሌሎች የእህል አይነቶች ሀይል ሰጪ ምግቦች ናቸው።
 ባቄላና ምስር ወዘተ
 ሀብሀብና ዘይቱና የመሳሰሉ ፍራፍሬዎች

5. ተግባራት 6. እንቅፋቶች ላይ 7. ማለማመድና ማሰልጠን 8. አስተያየቶችን ጠይቁ


ተወያዩ

20
ከ 1 – 2 ዓመት ለሆናቸው ህፃናት የሚሰጡ የምግብ አይነቶች

በሽታን ለመከላከል ቀይ፣ ብርቱካናማና አረንጓዴ ለአጥንት ጥንካሬና ለጤናማ ደም ስለሚያገለግሉ


ቀለም ያላቸውን ምግቦች ለህፃኑ/ኗ ይስጡ። ጉበት፣ ቀይ ስጋ፣ እንቁላል፣ የዶሮ ስጋና አሳ
ህፃኑ/ኗ ይስጡ።

21
ትምህርት 4᎓ ንፅህናና የምግብ ዝግጅት

1. እያንዳንዱን ትምህርት 2. ሁሉም መገኘታቸውን 3. የተማሩትን ተግባራዊ 4. የእያንዳንዱን ስእል ትርጉም


በጨዋታ ጀምሩ አረጋግጡ ችግር ያለበትም ካለ ስለማድረጋቸው ጠይቁ ንገሯቸው
ጠይቁ

ከመጸዳዳት በኋላ እጅን መታጠብ

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ከሽንት ቤት መልስ እጅን በሳሙና ወይም በአመድ ይታጠቡ።


 ሰገራ በሽታ የሚያስከትሉ ተህዋስያን በውስጡ አሉት።
 በእጅ ላይ የሚቀር ሰገራ ለራስዎም ሆነ ለልጆች በሽታ ያስከትላል።
 በእጅ ላይ የሚገኙ ተህዋስያንን ሳሙና ወይም አመድ ብቻ ነው የሚገድላቸው።

ህጻንን ካጸዳዱ በኋላ እጅዎን በሳሙና ወይም በአመድ ይታጠቡ።


 የህጻን ሰገራም ቢሆን በሽታን የሚያስከትሉ ተህዋስያንን በውስጡ ይዟል።
 በእጅዎ ላይ የሚቀር ሰገራ የሚነኩትን ማንኛውንም ነገር ይበክላል።
 ምንጊዜም ሰገራም ሆነ ሽንትን ካጸዳዱ በኋላ እጅዎን በሳሙና ወይም በአመድ ይታጠቡ።

? በዚህ ማለዳ እጅዎን ለመታጠብ ምን ተጠቀሙ?

? እናቶች ሽንት ቤት ደርሰው ሲመለሱ ወይም ልጃቸውን ካጸዳዱ በኋላ እጃቸውን መታጠብ እንዳለባቸው
እንዲያስታውሱ ምን ማድረግ አለባቸው?

22
ከመጸዳዳት በኋላ እጅን መታጠብ

23
የቤተሰብንና የህጻኑን ምግቦች ማዘጋጀት

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ለቤተሰብዎ ምግብ ከማዘጋጀትዎ በፊት እጅዎን በሳሙና ይታጠቡ።


 በእጃችን ላይ የሚገኙ ተህዋስያን የምንነካቸውን ምግቦች ሁሉ ይበክላሉ።
 በእጃችን ላይ የሚገኙ ተህዋስያን ቤተሰባችን እንዲመገብ የምናዘጋጃቸውን ምግቦች ሁሉ ይበክላሉ።
 ሳሙና ከሌለዎት ለመታጠቢያ አመድ ይጠቀሙ።

ልጆች ከመመገባቸው በፊት እጆቻቸውን በውሃና በሳሙና እንዲታጠቡ ይርዷቸው።


 በቆሸሸ እጅ መብላት በሽታን ያስከትላል።
 ሳሙና በእጃን ላይ የሚገኙ ተህዋስያንን ይገድላል።
 የቤተሰቡ አባላት በሙሉ ከመመገባቸው በፊት እጃቸውን በውሃና በሳሙና መታጠባቸውን ያረጋግጡ።

? ቤተሰቡ ሳሙና ባይኖረው አጃቸውን ለመታጠብ ምን ሊጠቀሙ ይችላሉ?


? በዚህ ማለዳ እጅዎትን የታጠቡት ምንጊዜ ነው?
? እጅዎን ለመታጠብ የተጠቀሙት ምንድን ነው?

ምግብን በንጽህና ማዘጋጀት ጠቀሜታው ምንድን ነው?

24
ለቤተሰብና ለህጻኑ ምግብ ማዘጋጀት

ለቤተሰብዎ
ምግብ
ከማዘጋጀትዎ
በፊት እጅዎን
በሳሙና
ይታጠቡ።

ልጆች
ከመመገባቸው
በፊት
እጆቻቸውን
በውሃና
በሳሙና
እንዲታጠቡ
ያድርጉ።

25
ምግብን ማሞቅ፣ ማቅረብና የምግብ ዕቃዎችን ማጽዳት

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ለቤተሰቡ የሚቀርቡ የተዘጋጁና የተረፉ ምግቦች በደንብ እስኪንተከተኩ ድረስ


ያሙቋቸው።
 ምግቦች እንደተዘጋጁ ወዲያውኑ ተመገቧቸው።
 ተዘጋጅተው የቆዩ ምግቦች ከመቅረባቸው በፊት እስኪንተከተኩ ድረስ በደንብ መሞቅ አለባቸው።
 የተረፈ ምግብ ሲቆይ ተህዋስያን ይራቡበታል።
 የተረፈ ስጋም ሆነ መረቅ በደንብ ተደርጎ እስኪንተከተክ ድረስ መሞቅ አለበት።

ከተመገባችሁ በኋላ የተበላባቸው ሳህኖች ይታጠቡ፣ በፀሀይም እንዲደርቁ ያድርጉ።


 ከፀሀይ የሚገኘው ሙቀት ሳህኖቹ በፍጥነት እንዲደርቁ ያደርጋል።
 ሙቀቱ በሳህኑ ላይ የቀሩትን ተህዋስያንን ይገድላቸዋል።
 ዝንቦች እንዳያርፉባቸው የታጠቡ ሳህኖችን ይሸፍኗቸው።

5. ተግባራት 6. እንቅፋቶች ላይ 7. ማለማመድና ማሰልጠን 8. አስተያየቶችን ጠይቁ


ተወያዩ

26
ምግብን ማሞቅ፣ ማቅረብና የምግብ ዕቃዎችን ማጽዳት

ለቤተሰቡ የሚቀርቡ
የተዘጋጁና የተረፉ
ምግቦች በደንብ
እስኪንተከተኩ ድረስ
ያሙቋቸው።

ምግብ ካዘጋጁ በኋላ


ሳህኖችንና ኩባያዎችን
በውሃና በሳሙና
ይጠቧቸው።

27
ትምህርት 5᎓ የህጻን ምግብ አዘገጃጀት

1. እያንዳንዱን ትምህርት 2. ሁሉም መገኘታቸውን 3. የተማሩትን ተግባራዊ 4. የእያንዳንዱን ስእል ትርጉም


በጨዋታ ጀምሩ አረጋግጡ ችግር ያለበትም ካለ ስለማድረጋቸው ጠይቁ ንገሯቸው
ጠይቁ

ከ6-11 ወራት እድሜ ላላቸዉ ህጻናት ተጨማሪ ምግብ አዘገጃጀት


ዕድሜአቸው ከ6 - 11 ወራት የሆናቸው ህጻናትን ከእናት ጡት በተጨማሪ በቀን ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ ድረስ ተጨማሪ ምግብ (ገንፎ)
ሊመገቡ ይችላል።

የሚከተለው ሰንጠረዥ ተጨማሪው ምግብ ከምን ዓይነት የእህል አይነቶች ማዘጋጅት እንደሚቻል ዝርዝሩን ይዟል።

የሚያስፈልጉ የእህል አይነቶች መጠን


የገብስ/የበቆሎ/ የጤፍ/ የስንዴ/ የማሽላ ዱቄት ግማሽ የቡና ስኒ
የአተር/የባቄላ/የሽንብራ ዱቄት አንድ የሻይ ማንኪያ
አነስ ያለ መጠን ያለው ካሮት አንድ
ቲማቲም አንድ
ወተት ግማሽ የቡና ስኒ
ቅቤ/ የምግብ ዘይት ሁለት የሻይ ማንኪያ ሙሉ
ውሃ ሦስት የቡና ስኒ
አዮዲን ያለበት ጨው ለጣእም
መካከለኛ መጠን ያለው ሙዝ አንድ
አዘገጃጀት
1. የገብሱን ወይም የበቆሎውን ዱቄት ከአተሩ ወይም ከባቄላው ዱቄት ጋር ማደባለቅ
2. ውሃና ወተት በመጨመር ከዱቄቱ ጋር አደባልቆ ማንተክተክ
3. ቲማቲሙን ቀቅሎ መላጥና መክተፍ
4. ካሮቱን አጥቦ መላጥ፣ አድቅቆ በመክተፍ መቀቀልና መፍጨት
5. የተፈጨውን ካሮት፣ ቲማቲምና ቅቤ/የምግብ ዘይት ገንፎው ውስጥ በመጨመር እያማሰሉ በደንብ ማብሰል
6. ለጣዕም ያህል አዮዲን ያለበት ጨው መጨመር
7. ከበሰለ በኋላ በማውጣት እንዲቀዘቅዝ ማድረግ፤ ልጁን/ልጅቱን ለመመገብ ማዘጋጀትና በትዕግስት መመገብ
ለመክሰስ የሚሆን ሙዝ ማዘጋጀት

ሙዙን ማጠብና መላጥ


ሙዙን በንጹህ ኩባያ ዉስጥ በማንኪያ መፍጨት
ማንኪያ በመጠቀም ህጻኑን መመገብ

28
ከ6 – 11 ወራት ዕድሜ ላላቸው ህጻናት ተጨማሪ ምግብ ማዘጋጀት

29
ከ12-24 ወራት እድሜ ላላቸዉ ህጻናት ተጨማሪ ምግብ አዘገጃጀት

ዕድሜአቸው ከ12 - 24 ወራት የሆናቸው ህጻናትን ከእናት ጡት በተጨማሪ በቀን እስከ አምስት ጊዜ ድረስ ተጨማሪ ምግብ (ገንፎ)
ሊመገቡ ይችላል።
 የሚከተለው ሰንጠረዥ ተጨማሪው ምግብ ከምን ዓይነት የእህል አይነቶች ማዘጋጅት እንደሚቻል ዝርዝሩን ይዟል።

የሚያስፈልጉ የእህል አይነቶች መጠን


የገብስ/የበቆሎ/ የጤፍ/ የስንዴ/ የማሽላ ዱቄት አንድ የቡና ስኒ
የአተር/የባቄላ/የሽንብራ ዱቄት አንድ የሻይ ማንኪያ
ጎመን አንድ ቅጠል
እንቁላል አንድ
አነስተኛ መጠን ያለው ቲማቲም አንድ
ወተት ግማሽ የቡና ስኒ
ቅቤ/የምግብ ዘይት ሁለት የሻይ ማንኪያ ሙሉ
ውሃ አራት የቡና ስኒ
አይኦዲን ያለበት ጨው ለጣዕም ያህል
የበሰለ ፓፓያ መካከለኛ መጠን ያለው ግማሹ

አዘገጃጀት

1) የገብሱን ወይም የበቆሎዉን ዱቄት ከዉሃና ከወተት ጋር ማዋሃድና በእሳት ላይ መጣድ


2) ጎመኑን ማጠብና መቀቀል
3) ጎመኑን ከእሳት ላይ ማዉጣትና አድቅቆ መፍጨት
4) እንቁላሉን መምታትና የተፈጨዉ ጎመን ጋር መቀላቀል
5) ጎመኑንና እንቁላሉን እንዲሁም ቅቤ ወይም ዘይት በገንፎ ላይ መጨመርና በማማሰል እንዲበስል ማድረግ
6) በአዮዲን የተቀመመዉን ጨዉ ለጣእም መጨመር
7) ገንፎዉ እንዲቀዘቅዝ ማድረግና ህፃኑ/ኗ እንዲበላ/እንድትበላ በማበረታታት በትእግስት መመገብ

ለመክሰስ የሚሆን ፓፓያ አዘገጃጀት

ፓፓያዉን ማጠብ፣መቁረጥና ፍሬዉን ማዉጣት


ፓፓያዉን በትናንሹ መቁረጥና ህጻኑ እንዲመገበዉ መስጠት
ማሳሰቢያ
የህጻናትን ምግብ ከድንች፣እንጀራ፣ ስጋ፣ዱባ እና ሌሎች በአካባቢ ከሚገኙ ምግቦች ማዘጋጀት ይቻላል፡፡
የህጻናትን ምግብ አዘገጃጀት ወደየቤታችሁ ሄዳችሁ ምን ያህል ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ?

5. ተግባራት 6. እንቅፋቶች ላይ 7. ማለማመድና ማሰልጠን 8. አስተያየቶችን ጠይቁ


ተወያዩ

30
ከ12 – 24 ወራት ዕድሜ ላላቸው ህጻናት ተጨማሪ ምግብ ማዘጋጀት

31
ትምህርት 6᎓ ወደ ጤና ተቋማት ስለ መሄድ

1. እያንዳንዱን ትምህርት 2. ሁሉም መገኘታቸውን 3. የተማሩትን ተግባራዊ 4. የእያንዳንዱን ስእል ትርጉም


በጨዋታ ጀምሩ አረጋግጡ ችግር ያለበትም ካለ ስለማድረጋቸው ጠይቁ ንገሯቸው
ጠይቁ
የህጻናት የእድገት ክትትል

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

በእድገት ክትትል ወቅት መደበኛ በሆነ መልኩ ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን ክብደትና
ቁመት በየወሩ መለካት አስፈላጊ ነዉ።

 የጤና ባለሙያዋ የህፃኑ/ኗን ቁመትና ክብደት ትለካለች።


 የጤና ባለሙያዋ ልጁ/ቷ በጥሩ ሁኔታ እያደገ/ች እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ለእናትየዋ ታስታውቃለች።
 ትክክለኛ ያልሆነ እድገት ካለ የጤና ባለሙያዋ ስለ ህፃኑ/ኗ አመጋገብ ሁኔታ ከቤተሰብ ጋር ምክክር ማድረግ
ያስፈልጋታል።
 እናቶች የልጅዎን እድገት በተመለከተ ጥያቄ ካለዎት የጤና ባለሙያዋን ጠይቁ።

? የታመመን ልጅ ለእድገት ክትትል መውሰድ ተገቢ ነው?


o አዎን። እንዲሻለው ምን ማድረግ እንደሚገባዎት የጤና ባለሙያዋን ይጠይቁ።
o የጤና ባለሙያዋ በጣም የታመሙ ልጆችን ለተሻለ ህክምና ወደ ሆስፒታል ወይም ወደ ህጻናት
ክሊኒክ ሊልኳቸው ይችላሉ።

? የ3 ዓመት ልጅ ለእድገት ክትትል በየስንት ጊዜው መወሰድ አለበት?


o ከ2-5 ዓመት የሚሆናቸውን ልጆች በየሦስት ወሩ ለእድገት ክትትል ይውሰዷቸው።

በእናንተ አካባቢ የልጆችን እድገት ክትትል ማድረግ የተለመደ ነው? ካልሆነ፣ ለምን?

32
የህጻናት የእድገት ክትትል

በእድገት ክትትል ወቅት መደበኛ በሆነ መልኩ ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን ክብደትና ቁመት በየወሩ
መለካት አስፈላጊ ነዉ።

33
የእድገት መከታተያ ሰንጠረዠን መረዳት

በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

የህፃኑ/ኗ እድገት ማሳያ መስመር የዜሮ ምልክት ካለበት ደማቅ መስመር በላይ ከሆነ፣ ህፃኑ/ኗ
በመልካም ሁኔታ እያደገ ነው ።

 ደማቁ መስመር የአንድ ጤነኛ ህፃን የክብደት ማሳያ ነው።


 የህፃኑ/ኗ የክብደት ማሳያ መስመር ወደ ደማቁ መስመር ከተጠጋ ወይም ከመስመሩ በላይ ከሆነ ህፃኑ/ኗ
በመልካም ሁኔታ እያደገ ነው።
 ህፃኑ/ኗ በሚታመምበት/በምትታመምበት ጊዜ የክብደት ማሳያው መስመር ከደማቁ መስመር በታች
ሊወርድ ይችላል።
 ከህመም በኋላ የህፃኑ/ኗ ክብደት እንዲሻሻል እናትዮዋ በፍጥነት ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ አለባት።

የህፃኑ/ኗ የእድገት መስመር የዜሮ ምልክት ከተደረገበት ደማቅ መስመር በታች ሲወርድ፣ ህፃኑ/ኗ
በቶሎ እንዲያገግም/እንድታገግም ምን መደረግ እንዳለበት ከጤና ባለሙያዋ ጋር ተነጋገሩ።

 ተቅማጥና ህመም የህፃኑ/ኗን እድገት ሊያዘገይ ወይም ሊያቆመው ይችላል።


 ለበርካታ ተከታታይ ወራት ህፃኑ/ኗ ክብደት ካልጨመረ/ች፣ አካላዊና አእምሮአዊ እድገታቸው ይቀጭጫል።
 ህፃኑ/ኗ እንዲያገግም/እንድታገግም ከጤና ባለሙያዋ ምክር ለማግኘት ተወያዩ።

? የልጅዎን እድገት ለመከታተል ወዴት ነው የሚወስዱት?


? ለመጨረሻ ጊዜ የልጅዎ ክብደት የተለካ መቼ ነው?

34
የእድገት መከታተያ ሰንጠረዥን መረዳት

የህፃኑ/ኗ እድገት ማሳያ መስመር የዜሮ ምልክት ካለበት ከደማቁ መስመር በላይ ከሆነ፣ ህፃኑ/ኗ በመልካም ሁኔታ እያደገ ነው ።

የህፃኑ/ኗ የእድገት መስመር የዜሮ ምልክት ከተደረገበት ከደማቁ መስመር በታች ሲወርድ፣ ህፃኑ/ኗ በቶሎ
እንዲያገግም/እንድታገግም ምን መደረግ እንዳለበት ከጤና ባለሙያዋ ጋር ተነጋገሩ።

35
ክትባት

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ህፃናት እንደተወለዱ፣ በስድስት ሳምንት፣ በ10 ሳምንት፣ በ14 ሳምንትና በ9 ወር ለክትባት ወደ


ጤና ተቋም ይውሰዷቸው።

 ክትባት ልጅዎን ከገዳይ በሽታዎች ይከላከላል።


 የተከተቡ ልጆች በተደጋጋሚ አይታመሙም።
 ክትባት ልጅዎን ከህመምና ከሞት ይከላከላል።

? እናቶች ልጆቻቸውን ወደ ክትባት ጣቢያ ከማይወስዱባቸው ምክንያቶች ጥቂቶቹ የትኞቹ ናቸው?


? ልጅዎ ሁሉንም ክትባቶች ወስዷል? ለምን? ካልወሰደስ ለምን?

5. ተግባራት 6. እንቅፋቶች ላይ 7. ማለማመድና ማሰልጠን 8. አስተያየቶችን ጠይቁ


ተወያዩ

36
ክትባት

ህፃናት እንደተወለዱ፣ በስድስት ሳምንት፣ በ10 ሳምንት፣ በ14 ሳምንትና በ9ኛ ወር ለክትባት ወደ ጤና ተቋም
ይውሰዷቸው።

37
ትምህርት 7᎓ የታመሙ ህፃናትን መመገብና መንከባከብ

1. እያንዳንዱን ትምህርት 2. ሁሉም መገኘታቸውን 3. የተማሩትን ተግባራዊ 4. የእያንዳንዱን ስእል ትርጉም


በጨዋታ ጀምሩ አረጋግጡ ችግር ያለበትም ካለ ስለማድረጋቸው ጠይቁ ንገሯቸው
ጠይቁ

የታመሙ ህፃናትን መመገብ

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

የራባቸው ባይመስሉም እንኳ የታመሙ ህጻናት እንዲበሉ አበረታቷቸው።


 የታመሙ ህጻናት የመራብ ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ።
 የታመሙ ህጻናትን እያጫወቱና እየዘመሩ በማባበል እንዲበሉ አበረታቷቸው።
 በማበረታት አዋሩአቸው።
 ከስድስት ወራት በታች የሆነ ህፃኑ/ኗ በታመመ/ች ጊዜ ከወትሮዉ በበለጠ ሁኔታ በተደጋጋሚ ጡት ማጥባት
ያስፈልጋል ይህም ከህጻኑ/ኗ የወጣዉን ፈሳሽ እንዲተካና ህጻኑ/ኗ በቶሎ እንዲያገግም/እንድታገግም
ይረዳዋል/ታል፡፡

የታመሙ ልጆች አጥሚት፣ ወተት፣ የፍራፍሬ ጭማቂ፣ ወፈር ያለ ሾርባና የሩዝ ውሃ የመሳሰሉትን
ፈሳሾች በተጨማሪ እንዲመገቡ አበረታቷቸው።
 የሚወሰደው ፈሳሽ በተቅማጥና በትኩሳት ከሰውነት የሚወጣውን ውሃ ይተካል።
 ሾርባና ገንፎ ልጆች በቀላሉ ሊመገቧቸው ይችላሉ።
 አጥሚትና ገንፎ ከህመም በኋላ የሚከሰተውን የክብደት መቀነስ ለማስተካከል ወፈር ብለው መዘጋጀት
አለባቸው።

? ልጅዎ የራበው ባይመስልም እንዲበላ እንዴት ነው የሚያበረታቱት?

38
የታመሙ ህፃናትን መመገብ

የራባቸው ባይመስሉም እንኳ


የታመሙ ልጆችን እንዲበሉ
አበረታቷቸው።

የታመሙ ልጆች
አጥሚት፣ ወተት፣
የፍራፍሬ ጭማቂ፣ ወፈር
ያለ ሾርባና የሩዝ ውሃ
የመሳሰሉትን ፈሳሾች
በተጨማሪ እንዲመገቡ
አበረታቷቸው።

39
ተቅማጥ የያዛቸው ልጆች

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

አንድ ከረጢት/ እሽግ ህይወት አድን (ወዝ መላሽ) ንጥረ ነገርን በአንድ ሊትር (አንድ ጆግ)
ተፈልቶ በቀዘቀዘ ወይም በተጣራ ውሀ መበጥበጥ።

 የህይወት አድን (ወዝ መላሽ) ንጥረ ነገር ዱቄቱ ከውሃው ጋር እስኪዋሃድ ድረስ መበጥበጥ።
 የህይወት አድን (ወዝ መላሽ) ንጥረ ነገር ዱቄቱ ከውሃው ጋር በደንብ መዋድ አለበት።
 የህይወት አድን (ወዝ መላሽ) ንጥረ ነገር ዱቄቱ ፈልቶ በቀዘቀዘ ወይም በተጣራ ውሃ ብቻ ይበጥብጡት።
 ያልተፈላ ወይም ያልተጣራ ውሃ ተቅማጡን ያባብሰዋል።
 አኳታብስ ወይም ውሃ አጋር በመጨመር ውሃውን ያጣሩት።

ከሰውነት የሚወጣውን ፈሳሽ ለመተካት ህፃኑ/ኗ ባስቀመጠው/ጣት ቁጥር ግማሽ ስኒ


የተበጠበጠውን የህይወት አድን (ወዝ መላሽ) ንጥረ ነገር ውሁድ ይስጡ።

 የታመመው/ችው ልጅ የሚያስመልሰው/ሳት ከሆነ በትንሽ በትንሹ ያጠጡ።


 ህፃኑ/ኗ ውሃ በጠማው/ት ቁጥር ውሁዱን በተጨማሪ ያጠጡ።

? እናቶች የህይወት አድን (ወዝ መላሽ) ንጥረ ነገር ዱቄቱ ከየት ያገኛሉ?
? ልጄን ድንገት ተቅማጥ ቢይዘው/ቢይዛት በማለት የህይወት አድን (ወዝ መላሽ) ንጥረ ነገር ዱቄት በቤትዎ
ውስጥ አስቀምጠዋል?

40
ተቅማጥ የያዛቸው ልጆች

አንድ ከረጢት/ እሽግ


ህይወት አድን (ወዝ
መላሽ) ንጥረ ነገርን
በአንድ ሊትር (አንድ
ጆግ) ተፈልቶ በቀዘቀዘ
ወይም በተጣራ ውሀ
መበጥበጥ።

ከሰውነት
የሚወጣውን ፈሳሽ
ለመተካት ህፃኑ/ኗ
ባስቀመጠው/ጣት
ቁጥር ግማሽ ስኒ
የተበጠበጠውን
የህይወት አድን
(ወዝ መላሽ)
ንጥረ ነገር ውሁድ
ይስጡ።

41
የታመመን ልጅ መመገብ

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

በህመም ጊዜ ከቀድሞው በበለጠ ልጃችሁን ደጋግማችሁ ጡት አጥቡ እንዲሁም በየቀኑ ተጨማሪ


መክሰስ ስጡት።
 ህፃኑ/ኗ በወሩ መጀመሪያ ሳምንት ታሟል/ታማለች።
 ወላጆቹ በመደጋገም ጡት በማጥባትና ከሌላው ጊዜ በበለጠ ደጋግመው ምግብ ሰጡ።
 በታመሙ ጊዜ ልጆች የሚበሉትና የሚጠጡት ከሌላው ጊዜ ያነሰ ነው።
 ደጋግሞ ጡት እንዲጠቡ ልጆችን ማበረታታት።
 የጡት ወተት ልጁ ጥንካሬው እንዲመለስ ይረዳዋል።

ህመሙ ከተሻለው ከሁለት ሳምንት በኋላ ከሌላ ጊዜ በበለጠ ደጋግሞ ጡት ማጥባትና አንድ
ተጨማሪ ጊዜ መክሰስ በየቀኑ ይስጡት።

 ህፃኑ/ኗ ከተሻለው/ላት በኋላ ያሉት ሁለት ሳምንታት በቀን መቁጠሪያው ላይ ግራጫ ናቸው።
 ወላጆቹ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ደጋግመው ጡት ማጥባታቸውንና ተጨማሪ ምግብ መስጠታቸውን ቀጥለዋል።
 ተጨማሪ ምግብና ፈሳሽ የምግብ እጥረትን ይከላከላል።
 ተጨማሪ ምግብና ፈሳሽ በህመም ጊዜ ልጁ ያጣውን ክብደት ለመመለስ ይረዳል።

? አንዲት እናት ስድስት ወርና ከዚያ በታች እድሜ ያለው ህጻን በታመመ ጊዜ እንዴት መንከባከብ አለባት?
o ህፃኑ/ኗ በታመመ/ች ጊዜና ከተሻለው/ላት በኋላ ባሉት ሁለት ሳምንታት ከሌላው ጊዜ በበለጠ
ደጋግማ ጡቷን ማጥባ አለባት።

42
ቀን መቁጠሪያ

በህመም ጊዜ ከቀድሞው በበለጠ ልጃችሁን ደጋግማችሁ ጡት አጥቡ እንዲሁም


በየቀኑ ተጨማሪ መክሰስ ስጡት።

ህመሙ ከተሻለው ከሁለት ሳምንት በኋላ ከሌላ ጊዜ በበለጠ ደጋግሞ ጡት ማጥባትና አንድ ተጨማሪ ጊዜ
መክሰስ በየቀኑ ይስጡት።

43
በልጅ ላይ የሚታዩ አደገኛ ምልክቶች

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

ከዚህ በታች ከተመለከቱት ምልክቶች አንዱን እንኳ ካዩ ህጻናትን በአስቸኳይ ወደ ጤና ተቋም


ይውሰዱ᎓

 ህፃኑናት ሲበሉ ወይም ሲጠጡ የሚየስመልሳቸው ከሆነ


 ትኩሳት ካላቸው
 የሚያንቀጠቅጣቸው ከሆነ
 ራሳቸውን የሚስቱ ከሆነ
 ለመብላት ወይም ለመጠጣት እምቢ ካሉ
 የማያቋርጥ ሳል ካላቸው
 ከመደበኛው አተነፋፈስ በተለየ ትንፋሻቸው ቁርጥ ቁርጥ የሚል ከሆነ
 እነዚህ ምልክቶች የህጻናት ህይወት አደጋ ላይ መሆኑን አመልካቾች ናቸው።
 ይሻላቸዋል ብላችሁ ዝም ብላችሁ አትጠብቁ።
 ባስቸኳይ ወደ ጤና ተቋም ህጻናቱን ውሰዷቸው።

? የህጻናት ህይወት አደጋ ላይ መሆኑን የሚያመለክቱ ሌላ ምን ምልክቶች አሉ?


? የጤና ተቋሙ ራቅ ያለ ከሆነና ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ እናትዬዋ ምን አይነት ዝግጅት ልታደርግ
ይገባታል?
o የሚጠጣ ውሃ መያዝ
o በመንገድ ላይ እያሉ ህፃኑ/ኗ ጡት ማጥባት
o የህፃኑ/ኗ እድሜ ከ6 ወራት በላይ ከሆነው ለመክሰስ የሚበላው ምግብ መያዝ
o ለህክምና የሚከፈለውን ገንዘብ መያዝ

5. ተግባራት 6. እንቅፋቶች ላይ 7. ማለማመድና ማሰልጠን 8. አስተያየቶችን ጠይቁ


ተወያዩ

44
በልጅ ላይ የሚታዩ አደገኛ ምልክቶች

 ህጻናት ሲበሉና ሲጠጡ የሚየስመልሳቸው ከሆነ፣ ትኩሳት ካላቸው፣


የሚያንቀጠጣቸው ከሆነ፣ ራሳቸውን ከሳቱ፣ ለመብላት ወይም ለመጠጣት
እምቢ ካሉ፣ የማያቋርጥ ሳል ካላቸው፣ ከመደበኛው አተነፋፈስ በተለየ
ትንፋሻቸው ቁርጥ ቁርጥ የሚል (የሚያቃስቱ) ከሆነ ባስቸኳይ ወደ ጤና
ተቋም ይውሰዷቸው።

45
ትምህርት 8᎓ ማይክሮኒውትረንት - ቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ዲና አዮዲን

1. እያንዳንዱን ትምህርት 2. ሁሉም መገኘታቸውን 3. የተማሩትን ተግባራዊ 4. የእያንዳንዱን ስእል ትርጉም


በጨዋታ ጀምሩ አረጋግጡ ችግር ያለበትም ካለ ስለማድረጋቸው ጠይቁ ንገሯቸው
ጠይቁ

ቫይታሚን ኤ

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

የልጅዎ አካል ጠንካራና ጤናማ ሆኖ እንዲያድግ ከስድስት ወር እድሜ ጀምሮ በየስድስት


ወሩ የቫይታሚን ኤ ንጥረ ነገር ይውሰዱ።
 ቫይታሚን ኤ ለህጻናት የዓይን ጤንነት እንዲሁም በሽታን መቋቋም እንዲችሉ የሚረዳ ጠቃሚ ንጥረ ነገር
ነዉ
 በጣም ትንሽ ቢሆንም እንኳ የቫይታሚን ኤ እጥረት ካለ ለአይነ-ስውርነት ይዳርጋል።
 አምስት ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ህጻናት ቫይታሚን ኤ ንጥረ ነገር እንዲወስዱ ወደ ጤና ተቋም
በየስድስት ወሩ ይውሰዷቸው።
 በጤና ተቋማትና በክትባት ዘመቻ ወቅት ቫይታሚን ኤ ይገኛል።
እንደ ካሮት፣ ጎመን፣ ጉበት፣ ዱባ፣ ፓፓያና ማንጎ የመሳሰሉ በቫይታሚን ኤ
የበለጸጉ ምግቦችን ማዘጋጀት።
 ጡት የሚያጠቡ እናቶች በሽታ ለመከላከልና ጤናማ ሆኖ ለመቆየት እንዲችሉ በቫይታሚን ኤ የበለጸጉ
ምግቦችን ይመገቡ።
 እናቶች በሽታን ለመከላከልና ጤናማ እንዲሆኑ ለልጆችዎ በቫይታሚን ኤ የበለጸጉ ምግቦችን ይስጧቸው።
 በየእለቱ ለቤተሰቡ በሚዘጋጅ ምግብ ውስጥ ቫይታሚን ኤ ያላቸውን ምግቦች ይጨምሩ።

? ትናንትና ከእነዚህ ምግቦች መካከል የትኛውን ምግብ መገቡት?


? ነገ ለልጅዎ ምግብ ሲያዘጋጁ የትኞችን ምግቦች ለመጨመር ይችላሉ?

46
ቫይታሚን ኤ

የልጅዎ አካል ጠንካራና ጤናማ ሆኖ እንዲያድግና ከስድስት ወር እድሜው ጀምሮ በየስድስት ወሩ የቫይታሚን
ኤ ንጥረ ነገር መውሰድ ይስጡ።

እንደ ካሮት፣ ጎመን፣ ጉበት፣ ዱባ፣ ፓፓያና ማንጎ የመሳሰሉ በቫይታሚን ኤ የበለጸጉ ምግቦችን ማዘጋጀት።

47
አዮዲን

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

እንቅርትንና ደካማ የልጅን እድገት ለመከላከል በየቀኑ በገንፎና ለቤተሰቡ በሚዘጋጀው


ምግብ ላይ አዮዲን ያለበት ጨው ይጨምሩ።

 በርካታ ኢትዮጵያውያን ልጆች በአዮዲን እጥረት ይሰቃያሉ።


 ትንሽም ቢሆን የአዮዲን እጥረት የአእምሮ እድገት ዝግመት ወይም ጉድለትን ያስከትላል።
 አዮዲን ልጆች በትምህርታችው ጎበዝ እንዲሆኑ ያግዛል።
 አዮዲን የሌለበት ጨው አይግዙ።
 ጨው ሲገዙ በማሸጊያው ላይ “አዮዲን” ተብሎ የተጻፈበትን ብቻ ይግዙ።

? በቤትዎ ውስጥ ያለው ጨው ምን አይነት ነው?


? አዮዲን ያለበት ጨው ከየት መግዛት ይቻላል?

? በአካባቢያችሁ አዮዲን ያለበት ጨው ከየት ታገኛላችሁ?


? ህብረተሰቡ አዮዲን ያለበት ጨው እንዲጠቀም ምን መደረግ አለበት?

48
አዮዲን

እንቅርትንና ደካማ የልጅን እድገት ለመከላከል በየቀኑ በገንፎና ለቤተሰቡ በሚዘጋጀው


ምግብ ላይ አዮዲን ያለበት ጨው ይጨምሩ።

49
ቫይታሚን ዲ

? በዚህ ስእል ላይ ምን ትመለከታላችሁ?

የህጻናት አጥንት በደንብ እንዲያድግ በየቀኑ ለ30 ደቂቃ ያህል ፀሐይ ይሙቁ።

 የህጻናት ቆዳ የፀሐይ ሙቀትን በመሳብ ለአጥንት እድገትና ለመልካም ጤንነት አስፈላጊ የሆነዉን ቫይታሚን
ዲ ሰዉነታቸው እንዲያመርት ይረዳል፡፡
 ቫይታሚን ዲ ለአጥንትና ለጥርስ ጥንካሬ ወሳኝ ነው።
 ያለ ቫይታሚን ዲ የህጻናት አጥንት ልፍስፍስና ለመራመድ የማይችል ይሆናል።

? ለመጨረሻ ጊዜ ልጅዎን ፀሐይ ያሞቁ መቼ ነው?


እናቶች ልጆቻቸውን በየእለቱ ፀሐይ እንዲያሞቁ እንዴት ማሳሰብ እንችላለን ?

5. ተግባራት 6. እንቅፋቶች ላይ 7. ማለማመድና ማሰልጠን 8. አስተያየቶችን ጠይቁ


ተወያዩ

50
ቫይታሚን ዲ

የህጻናት አጥንት በደንብ እንዲያድግ በየቀኑ ለ30 ደቂቃ ያህል ፀሐይ ያሙቁ።

51
ምስጋና

አስቀድመን የአሜሪካ መንግስት የልማት ተራድኦ ድርጅት (USAID) ይህን የማስተማሪያ


ካርድ ለማሳተም ላበረከቱት የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

እንዲሁም ለምግብ ለተራቡ አሜሪካ በተለይም በዚህ ማስተማሪያ ካርድ ውስጥ የተካተቱ
የተለይዩ ስእሎችንና ማብራሪያዎችን ለሰጡን ለሚዚ ሃኖልድ ምስጋናችን ይድረስ።

ይህን የማስተማሪያ ካርድ የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ፣ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣


የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በተለያየ ጊዜ ካሳተሟቸው የማስተማሪያ ካርዶችና መልእክቶች ውስጥ
በመምረጥና በማሰባሰብ በምግብ ለተራቡ ኢትዮጵያ ተዘጋጅቶ ታትሟል።

ለዚህ የማስተማሪያ ካርድ ዝግጅት ስዕሎቻቸውን ላበረከቱ ለሚከተሉት ሰዓሊዎች የከበረ


ምስጋናችን ይድረሳቸው᎓
 Jeff Del Nero: ገጽ 5, 7, 11, 15 እና 19.
 Ir Leonidas Nisabwe: ገጽ 9, 27, 35, 37
 IYCN, USAID, and the Ethiopian Ministry of Health Maternal
Infant and Young Child Nutrition counseling Cards : ገጽ 33 and 51.

52

You might also like