You are on page 1of 1

በርግዝና ወቅት በማቅለሽለሽና ማስመለስ (morning sickness)

ይህ ችግር አብዛኛዉን ግዜ የሚከሰተው በመጀመሪያው አራት ወራት ዉስጥ ነው:: የእርግዝናው ወራት እየጨመረ
ሲመጣ ቺግሩ እየቀነሰ ይሄዳል:: ነገር ግን ችግሩ አየተባባሰ ከመጣ (ሕይፐረመሲስ ግራቪዳሩም/ hyperemesis
gravidarum) ወይም ከፍተኛ ማቅለሽለሽ ና ማስመሰል) ደረጃ ደርሶ ሊሆን ስለሚችል ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት
በተጨማሪ ሀኪም ቤት ተኚተው መታከም ይኖርቦታል ::
1. ይህ ችህግ ግዝያዊ እንደሆነ መገንዘብ አለቦት:: (Understand these symptoms are temporary)
2. የሚስማማዎትን ምግቦች በጥንቃቄ ይምረጡ:: ምልክቶችን የሚቀሰቅሱ ምግቦችን ወይም ሽታዎችን ያስወግዱ::
(Select food items carefully and avoid foods that triggers the symptoms)
3. ባዶ ሆድ መቆየትን ወይም ከመጠን በላይ ረሃብን ያስወግዱ:: ረሃብ ሳይሰማዎት ወይም ወዲያውኑ መብላት::
(Avoid an empty stomach or excessive hunger. Try eating before or as soon as you feel hungry)
4. እንደ ሽቶ፣ ኬሚካሎች፣ ቡና እና ጭስ ያሉ ሽታዎችን ያስወግዱ:: ፍሬሽ ሎሚ፣ ሜንት ወይም ብርቱካናማ ሸታዎችን ማሽተት
ይሞክሩ::
(Avoid odors like perfume, chemicals, coffee and smoke. Try smelling fresh lemon, mint, or Orange.)
5. ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን፣ ስኳር የበዛባቸው እና ከፍተኛ ቅባት ያላቸውን ምግቦች ያስወግዱ። በካርቦሃይድሬት ፣ በፕሮቲን
የበለፀጉ እና ዝቅተኛ ስብ ያላቸውን ምግቦች ሳይጠግቡ ትንሽ ፣ ትንሽ በቀን አስከ ስድስት ግዜ ይመገቡ። ጨው ያለባቸው
ምግቦችም ጠቃሚ ናቸው::
(Avoid spicy food, sugary, and high fat foods. Eat food rich with carbohydrates, protein and low fatty
foods. It’s good to add iodized salt of food.)
6. የተጨናነቁ ክፍሎች፣ ጫጫታ እና ብልጭ ድርግም የሚሉ መብራቶችን ያስወግዱ::
(Avoid stuffy rooms, noise and flickering lights)
7. ብዙ ጊዜ ደርቅ ያሉ ምግቦችን ለቁርስ እና መክሰስ መመገብ ያዘውጥሩ:: መኪና ከመንዳት, ከመጠን በላይ የአካል ብቃት
እንቅስቃሴ እና ጭንቀትን ያስወግዱ::
(Avoid driving, excessive exercise and stress)
8. ከተመገባችሁ በኋላ ወዲያውኑ ከመተኛት መቆጠብ:: ከተማገቡ በኋላ ለተዎሰነ ደቂቃ መንቀሳቀስ ጥሩ ነው:: (Avoiding lying
down immediately after eating. It’s good to ambulate for some minutes.)
9. ከተመገቡ በኋላ ጥርስዎን መቦረሽ አይርሱ:: ካስመለሶት በኋላ አፍዎን በደንብ የጉመጥመጡ:: ከሆድ ውስጥ የሚወጣው አሲድ
ጥርስዎን ሊጎዳ ይችላል:
(It is good brushing your teeth after eating. Wash your mouth after vomiting. The acid from
stomach can damage your teeth.)
10. ዝንጅብል የያዙ ምግቦችን መጠቀም (ለምሳሌ ዝንጅብል ሻይ አቀዝቅዘው : ዝንጅብል ዳቦ::
(Eat ginger containing food (e.g., ginger tea, bread))
11. አይረን ወይም ቪታሚን እየወሰዱ ስሜቱን የሚባባስ ከሆነ ሐኪሞን ያማክሩ::
(If your symptoms are getting worse while you’re taking your prenatal vitamin consult your doctor)
ዶ/ር ብሩክና ዶ/ር ሽመልስ
የመሃፀና ፅንስ እስፔሻልስት

You might also like