You are on page 1of 8

ጤናማ የአልሆነ የሴት ብልት ፈሳሽ (Abnormal Vaginal discharge)

የሴት ብልት ፈሳሽ ምንድነው?

 ከሴት ብልት የሚወጣ የፈሳሽ፣ የሕዋሳት እና የንፋጭ ጥምረት ነው፡፡ የሴት ብልት አካሎችን ከበሽታ እና

ከብግነት በመከላከል የሴት ብልት አካሎች ጤናማ እንዲሆኑ ያደርጋል። 

የሴት ብልት ፈሳሽ እንዴት ይፈጠራል?

 የሴት ብልት ፈሳሽ በዋነኝነት በሴት ሆርሞን (ኢስትሮጂን) አማካኝነት በብልት እና በማሕፀን ሽፋን

ሕዋሳት ይሠራል፡፡ 

- ባላአረጡ ሴቶች የሚኖር ጤናማ የሴት ብልት ፈሳሽ ይዘት፤

 መጠን፡- በግምት በየቀኑ ከአንድ እስከ ግማሽ የሻይ ማንኪያ (ከ 2 እስከ 5 ሚ.ሊ ) 

 ቀለም፡- ውሃ የሚምስል፣ ነጭ ወይም ደፍረስ ያለ ነጭ 

 ይዘት፡- ቀጭን ወይም ወፈር ብሎ እንደ ንፍጥ ያለ ፈሳሽ ሊሆን ይችላል። 

 ሽታ፡- መጠነኛ ሽታ ወይም ሽታ አልባ ሊሆን ይችላል ፡፡

  
 
- የሴት ብልት ፈሳሽ ይዘት፣ መጠን እና ቀለም፤ በእርግዝና ወቅት፣ በወር አበባ ዑደት ደረጃ እና በሆርሞን

የወሊድ መቆጣጠሪያ መድኃኒቶች መሠረት ይለያያል፡፡ ይዘቱ ነጭ የሚያጣብቅ እስከ ንጹሕ እና ውሃማ ቀለም

ሊቀያየር ይችላል፡፡ ይህ ፈሳሽ የሽንት ቧንቧን ከኢንፌክሽን ይከላከላል፡፡ በተጨማሪም እንደ ቅባት በመሆን

የሴት ብልትን በማለስለስ ብግነትን ይቀንሳል።

- በአጠቃላይ የአረጡ ሴቶች ዝቅተኛ የኢስትሮጅን መጠን ስለሚኖራቸው አነስተኛ  የብልት ፈሳሽ ይኖራቸዋል፡፡

ጤናማ የአልሆነ የሴት ብልት ፈሳሽ

ጤናማ የአልሆነ የሴት ብልት ፈሳሽ ምልክቶች ምንድናቸው? 

 የብልት ፈሳሽ አረፋማ መሆን ወይም ቀለሙ መቀየር (መወየብ፣ አረንጓዴ፣  ነጭ ወይም እንደ አይብ

ዓይነት ይዘት ይኖረዋል)   

  ደም የቀላቀለ ፈሳሽ

 ከባድ ሽታ  

 ከዚያም በተጨማሪ የእነዚህ ምልክቶች መኖር


 የብልት ማሳከክ፣ ማቃጠል፣ መቅላት፣ እብጠት ወይም ሕመም መኖር

 ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ወይም ከሽንት በኋላ ሕመም መኖር

 የሆድ ወይም የወገብ ሕመም።

የፈንገስ ኢንፌክሽን   ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ        ትሪኮሞናሲስ           


 

ደም የቀላቀለ ፈሳሽ

ያልተለመደ የሴት ብልት ፈሳሽ መንሥኤዎቹ ምንድናቸው?

 ኢንፌክሽን 

 የፈንገስ ኢንፌክሽን፣ ባክቴሪያል ቫጂኖሲስ፣ ትሪኮሞናያሲስ ያሉ ኢንፌክሽኖች ናቸው።

 የአባላዘር በሽታዎች 

 በማሕፀን ውስጥ የተረሱ ባእድ ነገሮች (ታምፖን፣ ኮንዶም) ወይም የወንድዘር ፍሬን የሚገድሉ ቅባቶችን

መጠቀም ለኢንፌክሽን ሊዳርግ ይችላል።


 ሌሎች መንሥኤዎች

 አንዳንድ የንጽሕና አጠባበቅ ድርጊቶች፤ ለምሳሌ ሳሙና ወይም የንጽሕና መጠበቂያ በመጠቀም ማሕፀንን

ማጽዳት 

 የማሕፀን ጫፍ ካንሰር

 ከማረጥ በኋላ የሚከሠቱ የሴት ብልት ለውጦች፤ ይህም የሴት ብልት ድርቀት፤ በተለይም ከግብረ ሥጋ

ግንኙነት በኋላ የብልት ፈሳሽ መቀየር ናቸው። 

 የሴት ብልት ካንሰር፣ ፊስቱላ

 ጤናማ የአልሆነ የሴት ብልት ፈሳሽ ምርመራ

 በምርመራ ወቅት የጤና ባለሙያው ምልክቶቹን ይጠይቃል፤ የአካላዊ እና የማሕፀን ምርመራ ጨምሮ

ያደርጋል። እንዲሁም ከፈሳሹ ናሙና በመውሰድ ምርመራ ሊያደርግ ይችላል። 

 አስፈላጊ ከሆነ የአልትራሳውንድ ምስል ምርመራ ሊደረግ ይችላል።

ሕክምና

 በዋነኝነት የሕክምና እና የመከላከያው መንገድ ሕመሙን በአመጣው መንሥኤ ላይ የሚወሰን ይሆናል። 

 የሚከተሉት ሕክምናዎች አብዛኛውን ጊዜ በወጣት ሴቶች ላይ ለሚከሠት ጤናማ የአልሆነ የብልት ፈሳሽ 

የሚሰጡ ሕክምናዎች ናቸው። 

 መንሥኤው የፈንገስ ወይም የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ከሆነ አብዛኛውን ጊዜ የፀረ ፈንገስ እና አንቲባዮቲክስ

መድኃኒቶች ከምርመራ በኋላ ወዲያውኑ እንዲጀመሩ ይደረጋል። 

 መንሥኤው በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ የአባለዘር በሽታ ከሆነ  አንቲባዮቲክስ መድኃኒት ይታዘዛል፡፡

በተጨማሪም የትዳር አጋር እንዲታከም ይደረጋል።

በቤት ውስጥ የሚደረግ ሕክምና

 ረጠብ እና ቀዝቀዝ ያለ ጨርቅ ማድረግ፤ ይህም የብልት ማሳከክ፣ ማቃጠል ወይም ምቾት ማጣትን

ይቀንሳል። 

 በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ኮንዶም መጠቀም፤ ይህ ሕክምና ከተጀመረ በኋላ እስከ አንድ ሳምንት ድረስ

ቢቀጥል ይመከራል።
 ብልትን ለማጽዳት ውሃ ወይም ከሳሙና ነፃ የሆኑ ማጽጃዎችን መጠቀም፡፡ ሞቅ ያለ ውሃ ቢሆን

ይመረጣል፤ ለማጽዳት ጨርቅ ከመጠቀም ይልቅ በእጅ ቢሆን ይመረጣል።

 ከጥጥ የተሠሩ የውስጥ ሱሪዎችን መጠቀም እና

 ጥሩ መዓዛ የአላቸው የንጽሕና ምርቶችን፣ የሕፃናት መጥረጊያዎችን ጨምሮ (wipes) አለመጠቀም

ናቸው።

 በተጨማሪም ምልክቶቹ እየባሱ ከሔዱ ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል።  

You might also like