Professional Documents
Culture Documents
ደም ማነስ
ደም ማነስ
ቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ
ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣ እንዲሁም ትኩረቴ በቀላሉ ይከፋፈል ነበር።
ሐኪሜ የብረት ማዕድን አዘዘልኝ። ኪኒኖቹን መውሰድ ጀመርኩ፤ አመጋገቤንም
አስተካከልኩ። ብዙም ሳይቆይ ጤንነቴ ተሻሻለ።”
ቤት የያዛት በሽታ በጣም የተለመደ የጤና እክል ነው። የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው
ከሆነ ሁለት ቢሊዮን ሕዝብ ማለትም ከዓለም ሕዝብ 30 በመቶ የሚያህለው ደም ማነስ
አለበት። በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ ከነፍሰ ጡር ሴቶች መካከል 50 በመቶ የሚሆኑት፣
ዕድሜያቸው ለትምህርት ካልደረሰ ሕፃናት መካከል ደግሞ 40 በመቶ የሚሆኑት ደም ማነስ
አለባቸው።
ደም ማነስ ከባድ ችግር ሊያስከትል ይችላል። በሽታው ሲባባስ የልብ ሕመም አንዳንድ
ጊዜም የልብ ድካም ያስከትላል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደተናገረው በአንዳንድ አገሮች
ውስጥ “20 በመቶ የሚሆኑት እናቶች የሚሞቱት” በደም ማነስ ነው። በብረት እጥረት
ምክንያት የሚመጣ ደም ማነስ (በጣም የተለመደው የደም ማነስ ዓይነት) ያለባቸው እናቶች
የሚወልዷቸው ሕፃናት ጊዜያቸው ሳይደርስ ሊወለዱ ወይም ክብደታቸው በጣም አነስተኛ
ሊሆን ይችላል። ደም ማነስ ያለባቸው ሕፃናት እድገታቸው ዘገምተኛ ሊሆን ወይም
ለኢንፌክሽን ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ይሁንና አብዛኛውን ጊዜ፣ በብረት እጥረት ምክንያት
የሚመጣውን ደም ማነስ መከላከል ወይም ማዳን ይቻላል። a
ደም ማነስ የጤና እክል ነው። በዚህ በሽታ የሚጠቁ ሰዎች በቂ የሆኑ ጤናማ ቀይ የደም
ሴሎች የሏቸውም። ይህ የሚሆነው በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ነው። እንዲያውም
የሳይንስ ሊቃውንት ከ 400 የሚበልጡ የደም ማነስ ዓይነቶች እንዳሉ ይናገራሉ! በሽታው
የሚድን ወይም የማይድን እንዲሁም ቀላል ወይም ከባድ ሊሆን ይችላል።
ብዙ ደም በመፍሰሱ የተነሳ በሰውነታችን ውስጥ ያሉት ቀይ የደም ሴሎች
ሲመናመኑ።
በዓለም ላይ በጣም የተስፋፋው የደም ማነስ ዓይነት በብረት እጥረት ምክንያት የሚከሰተው
ደም ማነስ ነው። ቀይ የደም ሴሎች ኦክስጅን ማጓጓዝ እንዲችሉ የሚያደርገው ሂሞግሎቢን
ነው፤ ሰውነታችን በቂ የብረት ማዕድን ካላገኘ ጤናማ ሂሞግሎቢን በበቂ መጠን መሥራት
አይችልም።
በደም ማነስ የተያዘ ሰው መጀመሪያ አካባቢ በሽታው እንዳለበት እንኳ ላያስተውል ይችላል።
በብረት እጥረት ምክንያት የሚከሰተው ደም ማነስ የተለያዩ ምልክቶች ሊኖሩት ይችላሉ፤
አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
አቅም ማጣት
የቆዳ መገርጣት
ራስ ምታትና ማዞር
መከላከል ወይም ማዳን የሚቻለው ሁሉንም የደም ማነስ ዓይነቶች አይደለም። ሆኖም
በብረት ወይም በቫይታሚን እጥረት ምክንያት የሚከሰት ደም ማነስን አብዛኛውን ጊዜ
መከላከል ወይም ማዳን ይቻላል፤ ይህን ማድረግ የሚቻለው በሚከተሉት ንጥረ ነገሮች
የበለጸገ አመጋገብ በመከተል ነው፦
a በዚህ ርዕስ ውስጥ የሚገኘው ስለ አመጋገብና ተያያዥ ነገሮች የሚገልጸው መረጃ በዋነኝነት የተውጣጣው ከሜዮ ክሊኒክ እና ዘ ጌል
ኢንሳይክሎፒዲያ ኦቭ ነርሲንግ ኤንድ አላይድ ኸልዝ ነው። ደም ማነስ እንዳለብህ ከጠረጠርክ የሕክምና ባለሙያ አማክር።
b ሐኪም ሳታማክር የብረት ማዕድን የያዙ ኪኒኖችን መውሰድ ወይም ለልጆችህ መስጠት የለብህም። ከመጠን ያለፈ የብረት ማዕድን
መውሰድ ጉበትን ሊጎዳ እንዲሁም ሌሎች ጉዳቶችን ሊያስከትል ይችላል።
c አንዳንድ ጊዜ ደም ማነስ የሚታከመው ደም በመውሰድ ነው፤ የይሖዋ ምሥክሮች እንዲህ ያለውን ሕክምና አይቀበሉም።—የሐዋርያት
ሥራ 15:28, 29
ቀይ የደም ሴሎች