You are on page 1of 2

የሰውነት ቅባት መጠን ልኬት: (lipid profile)

የሰውነት ቅባት ብለን የምንጠራቸው በዋናነት ኮሌስትሮል እና ትራይግላይሰራይድ የሚባሉት


ናቸው፡፡ በባህሪያቸው በውሃ የማይሟሙ ስለሆነ ሰውነታችን በደም ውስጥ በሚዘዋወር
ሊፖፕሮቲን ከተባለ ፕሮቲን ጋር በማያያዝ እና እንዲሟሙ በማድረግ ሰውነታችን ለኃይል
ምንጭነት፣ ሰውነትን ለማደስ እና የተለያዩ እድገንጥሮችን/ ሆርሞኖችን፣ የሀሞት ፈሳሽ ወዘተ…
ለማምረት ይጠቀምባቸዋል፡፡

ስለዚህም እነኚህ የሰውነት ቅባት ዓይነቶች ለጤና የሚያስፈልጉ ሲሆኑ ሰውነታችን


ከሚፈልገው በላይ የሰውነት ቅባት ሲከማች ደግሞ ለልብ ህመም (CAD) ፣ ለጭንቅላት የደም ቱቦ
መዘጋት አደጋ (Stroke) እና ለተለያዩ የጤና እክሎች የመጋለጥ እድላችን ክፉኛ ይጨምራል፡፡

ለመሆኑ የሰውነት ቅባት ወይም ኮሌስትሮል ምንድን ነው?

ኮሌስትሮል በጉበታችን የሚመረት ንጥረ ነገር ሲሆን የተለያዩ የኮሌስትሮል ዓይነቶች


በሰውነታችን ይገኛሉ፡፡

 LDL cholesterol –መብዛቱ የማይፈለገው የኮሌስትሮል ዓይነት ነው፡፡ ሰዎች ብዙ ጊዜ


“ጎጂ” ኮሌስትሮል ብለው ይጠሩታል ምክንያቱም በሰውነታችን ከመጠን በላይ ሲገኝ ለልብ ሕመም
ለጭንቅላት የደም ቱቦ መዘጋት አደጋ እና ለተለያዩ የጤና እክሎች ሊያጋልጠን ይችላል፡፡ ነገር ግን
በትክክለኛው (እጅግ አነስተኛ በሆነ) መጠን ለሰውነታችን አስፈላጊ ነው፡፡

 HDL cholesterol – መብዛቱ የሚፈለገው የኮሌስትርል ዓይነት ነው፡፡ ሰዎች ብዙ ጊዜ


“ጠቃሚ” ኮሌስትሮልብለው ይጠሩታል ምክንያቱም የዚህ ዓይነት ኮሌስትሮል በሰውነታችን በብዛት
መገኘቱ ከላይ ከጠቀስናቸው ዓይነት በሽታዎች የመጠቃት እድላችንን አነስተኛ ያደርጋል፡፡

 Triglycerides – የሰውነት ቅባት ዓይነት ቢሆኑም ኮሌስትሮል አይደሉም፡፡ ነገር ግን


ኮሌስትሮል መጠንን በምንለካበት ጊዜ የምንለካቸው ሲሆን የትራይግላይሰራይድ በሰውነታችን
መጨመር ልክ መብዛቱ እንደማይፈለገው ዓይነት ኮሌስትሮል ለልብ ሕመም፣ ለጭንቅላት የደም ቱቦ
መዘጋት አደጋ እና ለተለያዩ የጤና እክሎች ሊያጋልጠን ይችላል፡፡

በሰውነታችን መኖር ያለበት የኮሌስትሮል መጠን እንደ ቅባት ዓይነቶቹ ይለያያል፡፡

1. ጠቅላላ የኮሌስትሮል መጠን ከ 200 mg/dL በታች

2. መብዛቱ የማይፈለገው የኮሌስትሮል ዓይነት (LDL cholesterol) መጠን ጤናማ ለሆኑ


ሰዎች አንደ አጠቃላይ ከ 130 mg/dL በታች፤
ቀድሞውኑ የልብ ሕመም ወይም የጭንቅላት የደም ቱቦ መዘጋት አደጋ
የነበረባቸው አልያም ደግሞ ለችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በህክምና አነጋገር የ 10
ዓመት የልብ ሕመም ተጋላጭነት እድላቸው ከ 20% በላይ ለሆኑ ሕሙማን ከ 130
mg/dL እጅግ ያነሰ መሆን አለበት፡፡

3. መብዛቱ የሚፈለገው የኮሌስትሮል ዓይነት (HDL cholesterol) መጠን ከ 60 mg/dL


በላይ

4. መብዛቱ ከሚፈለገው የኮሌስትሮል ዓይነት (HDL cholesterol) ውጪ ያሉ የኮሌስትሮል


ዓይነቶች በአንድነት ከ 160 mg/dL በታች፤

ለዚህም ቀድሞውኑ የልብ ሕመም ወይም የጭንቅላት የደም ቱቦ መዘጋት አደጋ


የነበረባቸው አልያም ደግሞ ለችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በህክምና አነጋገር የ 10
ዓመት የልብ ሕመም ተጋላጭነት እድላቸው ከ 20% በላይ ለሆኑ ሕሙማን ከ 130
mg/dL በታች መሆን አለበት፡፡)

5. ትራይግላይሰራይድ (Triglycerides) ከ 150 mg/dL በታች መሆን አለባቸው፡፡

የሰውነት ቅባት መብዛት በደማችን ውስጥ መብዛታቸው የማይፈለገው የኮሌስትሮል ዓይነቶች


እና የትራይግላይሰላይድ መጠን መጨመሩን የሚገልጽልን ሲሆን ይህም ለልብ የደም ስር ትቦ
መዘጋት ችግር የመጋለጥ እድላችንን በከፍተኛ መጠን ይጨምራል፡፡ ከእነኚህ ቅባቶች አብዛኞቹ
በሰውነታችን መጨመር በልብ ጡንቻዎች ውስጥ የሚገኙትን የደም አስተላላፊ ቱቦዎች
እንዲወፍሩ እና እንዲጠነክሩ በማድረግ ደም በበቂ ሁኔታ እንዳይተላለፍ ያደርጋል፡፡ በዚህም
ምክንያት የግራ ደረት ውጋት እና ድንገተኛ የልብ ሕመም ያስከትላል፡፡

You might also like