You are on page 1of 3

ሃይፐርቴንሽን

(Hypertension)
ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ወይም ሃይፐርቴንሽን ከ ልብ እና ከ ደም ስሮች ጋር በተያያዘ ከሚከሰቱ በሽታዎች በጣም
የተለመደው እና ዋናው ነው፡፡
የደም ግፊት ማለት ደም በ ሰውነታችን ውስጥ ሲንሸራሸር በ ደም ስር ግድግዳዎች ላይ የሚፈጠር ጫና ወይም ግፊት ነው፡፡
ልክ አየር የመኪና ጎማ ውስጥ እንደሚገባ ወይንም ውሃ ጎማ ውስጥ እንደሚገባው ደምም በስሮች ላይ ግፊት የሚያሳድረው
እስከተወሰነ መጠን ነው፡፡ ከመጠን በላይ የሆነ አየር የመኪና ጎማን ሊቀድ እንደሚችለው ከመጠን በላይ የሆነም የደም
ግፊት ጤናማ የሆኑ የደም ስሮችን በመጉዳት ህይወታችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ እንደ የልብ ድካም ወይንም የአንጎል ውስጥ
የደም መፍሰስ አይነት በሽታዎችን ሊያስከትል ይችላል፡፡
ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ካለብዎ በተደጋጋሚ የህክምና ክትትልዎ ጊዜ ሊደርሱበት ይችላሉ፡፡ ወይንም የራስዎን ደም ግፊት
በሚለኩበት ሰአት ሊያስተውሉት ይችላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ርግጠኛ መሆን ስላለብዎ ሃኪምዎ ጋ መሄድ ይጠበቅቦታል፡፡ ይህም
ከፍተኛ የሆነውን የደም ግፊትዎን በቁጥጥር ስር ለማዋል ምን ማደረግ እንዳለቦት ግንዛቤ ይሰጥዎታል፡፡

የደም ግፊት እንዴት ይለካል


የደም ግፊት መጠንዎ ሲለካ ውጤቱ በሁለት ቁጥሮች የሚገለፅ ነው፡፡ ይህም እንደ ክፍልፋይ አንዱ ቁጥር ከላይ ሌላኛው
ደግሞ ከታች ነው፡፡ የላይኛው ቁጥር የ “ሲስቶሊክ” “systolic” ግፊት ይባላል፡፡ ይህ ልብ ሲመታና ስሮችን በደም
ሲሞላቸው የሚፈጠር ነው፡፡ የታችኛው ቁጥር ደግሞ በልብ ምቶች መሀከል ያለውን የደም ግፊት የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ
የ “ዳያስቶሊክ ” “diastolic” ግፊት በመባል ይታወቃል፡፡
የደም ግፊት ልክ ስንወለድ ካለው ከ 90/60 ለአቅመ አዳም ወይም ሄዋን ስንደርስ ወደ 120/80 ያድጋል፡፡ የደም ግፊትዎ
ንግግር እንዳደረጉ ወይንም ሩጫ እንደሮጡ ቢለካ ያለምንም ጥርጥር ከፍ ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ ይህ ሊያሳስብዎ
አይገባም፡፡ ምክንያቱም የደም ግፊት ከ ሰውነት እንቅስቃሴ እና ከስሜታችን ጋር ከፍ ወይም ዝቅ የማለት ባህሪ ስላለው
ነው፡፡
በተጨማሪም የደም ግፊት ከሰው ሰው ይለያያል፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን ከአንዱ የሰውነት ክፍል ወደ ሌላው የሰውነት ክፍል
ብንሄድም ሊለያይ ይችላል፡፡ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ልብ ላይ ከፍተኛ የሆነ የስራ ጫና ከማሳደሩም
በላይ የደም ስሮችን ሊቀድ፣ ኩላሊትና አእምሮን ሊጎዳ ይችላል፡፡
በሁለት የልኬት ንባብ የደም ግፊታቸው ከ 140/90 በላይ የሆን ሰዎች ሃይፐርቴንሽን (Hypertension) አለባቸው ማለት
ይቻላል፡፡ የደም ግፊታቸው ከ 180/120 በላይ የሆነ ሰዎች ደግሞ አጣዳፊ የሆነ ህክምና ያስፈልጋቸዋል፡፡
የጤና ተመራማሪዎች የደም ግፊታቸው ከ 120/80 በላይ በጥቂቱ ከፍ ያለ ሰዎች በሃይፐርቴንሽን የመያዝ እድላቸው በጣም
ከፍተኛ እንደሆነ ያረጋግጣሉ፡፡ ይህ ሁኔታ ቅድመ-ሃይፐርቴንሽን በመባል ሲታወቅ በአሜሪካን ሀገር ውስጥ እስከ 50
ሚሊዮን ሰዎችን እንደሚያጠቃ ይገመታል፡፡
ሃይፐርቴንሽን (Hypertension) በልጆች ላይ
በአብዛኛው ሰው ዘንድ ያለ የተሳሳተ አመለካከት አለ፡፡ ይህም ሃይፐርቴንሽን ወይም ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት በእድሜ
የገፉ ሰዎችን የሚያጠቃ እንደሆነ ማሰብ ነው፡፡ ይህ በድሮ ጊዜ ትክክል ሊሆን ይችላል፣ በአሁኑ ጊዜ ግን ሃይፐርቴንሽን
በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን ያጠቃል፡፡
ከልጅነት እድሜ ክልል ውጪ ያሉ ሰዎችን የደም ግፊት በመለካትና በፊት ከነበሩት ንባቦች ጋር በማነፃፀር ሃይፐርቴንሽን
መኖር አለመኖሩን ማወቅ ይቻላል፡፡ በልጅነት እድሜ ክልል ውስጥ ላሉትም ልኬቱ አንድ አይነት ሲሆን የንባቡ አተረጓጎም
ግን ለየት ያለ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የልጁ ቁመት፣ ፆታ እና ልኬት ታይቶ ነው ሃይፐርቴንሽን መኖር አለመኖሩን ማወቅ
የሚቻለው፡፡
ሃይፐርቴንሽን በ ልጆች ላይ ያለው አሉታዊ ተፅእኖ
ልክ በ ትልልቅ ሰዎች ላይ እንዳለው በ ልጆች ላይም ከፍተኛ የሆነ እና ለዘለቄታው የሚቆይ የልብ ድካም፣ የኩላሊት ህመም
እና በአንጎል ውስጥ የደም መፍሰስ ጉዳት ያስከትላል፡፡
ያለቅጥ መወፈር እና ሃይፐርቴንሽን
ያለቅጥ መወፈር እና የወላጆች የጤና ታሪክ ልጆችን ለሃይፐርቴንሽን ተጋላጭ የሚያደርጉ ሁለቱ ዋና ዋና ምክንያቶች
ናቸው፡፡በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ሌላው ተጋላጭነትን የሚያሰፋ ምክንያት ነው፡፡
ያለቅጥ መወፈር እንዴት ይከሰታል
ይህ በ ሁለት ምክንያቶች ይከሰታል:
 ከመጠን ያለፈ ምግብ
ብዙ ልጆች ለ ሰውነታቸው ከሚያስፈልገው በላይ ይመገባሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሁልጊዜ ስኳር ያለበት ምግብ የሚያዘወትሩ
ከሆነ ያለቅጥ መወፈር ይከሰታል፡፡ ስለዚህ ልጅዎ የሚመገበውን ምግብ መጠንም ሆነ ጥራት መከታተል ይኖርቦታል፡፡
 ከመጠን ያነሰ የአካል እንቅስቃሴ
ብዙ ልጆች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማያደርጉ ሲሆን አብዛኛውን ሰአታቸውን ቴሌቪዥን በመመልከት እና ቪድዮ ጌም
በመጫወት ነው የሚያሳልፉት፡፡
በ ልጆች ላይ የሚከሰት ሃይፐርቴንሽን ህክምና
ለልጆች የሚሰጠው ህክምና ለትልልቆቹ ከሚሰጠው እንብዛም የተለየ አይደለም፡፡ አሁን ድረስ ይበልጥ ውጤታማ የሆነው
መንገድ የቱ እንደሆነ ለማወቅ ጥናቶች እየተደረጉ ነው፡፡ ከልጅዎ ሃኪም ጋር በመነጋገር የቱ የህክምና አይነት ይበልጥ
ለልጅዎ እንደሚስማማ መወሰን ይችላሉ፡፡ ከዚህ በታች ያሉት በሰፊው ጥቅም ላይ የዋሉ ናቸው፡፡
የ DASH አመጋገብ እቅድን መከተል
DASH (Dietary Approaches to Stop Hypertension) ፡፡ ይህ እቅድ ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች በመቀነስና
ይበልጥ አትክልትና ፍራፍሬ በመመገብ የሚተገበር ነው፡፡ ምግብ ውስጥ ያለውን የጨው መጠን በመቀነስም የልጆችን የደም
ግፊት መቀነስ ይቻላል፡፡ የ ስነ-አመጋገብ ባለሞያዎች ልጅዎ የሚወደውን ምግብ ሳያጣ ግቦቹን መምታት እንዲችል ምክር
ሊሰጥዎ ይችላሉ፡፡
 የልጅዎን ክብደት ይከታተሉ
 ሲጋራ ማጨስን ያስወግዱ
መድሃኒቶችን ይጠቀሙ

የልጅዎ የደም ግፊት በጣም ከፍተኛ ከሆነ እና ያኗኗር ዘይቤን በመቀየር ሊስተካከል ካልቻለ ሃኪምዎ መድሀኒት ሊያዝልዎ
ይችላል፡፡ የሚከተሉት መድሃኒቶች ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚሰጡ መድሃኒቶች ናቸው፡፡

· ዲዩሬቲክስ (Diuretics)

በሰውነት ውስጥ ያለውን የሶዲየም (sodium) መጠን በመቀነስ ሠውነት የማይጠቀምበትን አላስፈላጊ ውሀ ያስወግዳል::

· ኤኢሲ ከልካይ፣ ዐልፋ ገዳቢ፣ ካልሲየም ገዳቢ (AEC Preventor Alpha preventor Calcium Preventor)

እነዚህ ደግሞ የደም ስሮች ከሚገባው በላይ እንዳይወጣጠሩ ይከላከላሉ፡፡

· ቤታ ከልካይ (Beta Preventor)

ይህ ሰውነት አድሬናሊን የሚባለውን ሆርሞን እንዳያነመርት ይካላከላል፡፡ አድሬናሊን (adrenalin) የጭንቀት ሆርሞን
ሲሆን ጠልብ ምት ፍጥነትን በመጨመር የደም ስሮች የበለጠ እንዲወጣጠሩ የሚየደርግ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የደም ግፊት
ይጨምራል፡

You might also like