You are on page 1of 20

ራሳችንን ከኮሮናቫይረስ በሽታ እንከላከል

MINISTRY OF HEALTH, ETHIOPIA


የአወያዮች መመሪያ

ይህ መርጃ አላማው ሰዎች ስለ ኮቪድ-19 ያላቸው ግንዛቤ ከፍ እንዲል እና ራሳቸውን ከኮሮና


ቫይረስ በሽታ ለመከላከል እንዲችሉ የታሰበ ውይይትን ማገዝ ነው። ውይይቱ ፍላጎታቸውን እና
ተሞክሯቸውን ቃኝተው ለባህርይ ለውጥ እንዲነሳሱ ያግዛቸዋል። ከተወያዮች የሚነሱ ጥያቄዎችን
በአግባቡ ለመመለስ እና በአጠቃላይ ውይይቱን በተሳካ ሁኔታ ለመምራት ውይይቱን ከመጀመር
አስቀድሞ አወያዮች በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል።

በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ያሉትን ምስሎች ለተወያዮች በማሳየት እና በስተጀርባ ባለው ፅሑፍ በመመራት


ውይይት ማድረግ ይቻላል። በስተጀርባ ባለው ፅሑፍ ውስጥ ውይይቱን ለማገዝ የመወያያ ጥያቄዎች
ተዘጋጅተዋል፡፡ ጥያቄዎቹም ተወያዮቹ የራሳቸውን ተሞክሮ እና አመለካከት እንዲገልፁ እና ለባሕርይ
ለውጥ የሚያነሳሷቸውን ውይይቶች እንዲያደርጉ የሚያግዙ ናቸው። አወያዮቹ ጥያቄዎቹን አንድ
በአንድ እየጠየቁ ሲያወያዩ ዋና ዋና መልዕክቶቹን እንዳይረሱ የማስታወሻ ነጥቦቹን መመልከት
ይችላሉ፡፡
ራሳችንን ከኮሮናቫይረስ በሽታ እንከላከል

JOHNS HOPKINS
MINISTRY OF HEALTH, ETHIOPIA Center for Communication
Programs
የመወያያ ጥያቄዎች
ስለ ኮሮናቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ምን ያውቃሉ?
በሽታው በምን የሚተላለፍ ይመስልዎታል?

ማስታወሻ ነጥቦች
ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ በጣም እየተስፋፋ ያለ በዋናነት የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ በሽታ ነው።
ከምልክቶቹ ዋነኞቹ ትኩሳት፣ ደረቅ ሳል፣ ድካም፣ የማሽተት እና መቅመስ ችሎታ ማጣት
ናቸው። ከከፋ ደግሞ ለመተንፈስ መቸገር ሊያጋጥም ይችላል።
የኮሮናቫይረስ በሽታ ስናስል ወይም ስናስነጥስ ከአፍ እና ከአፍንጫ በሚወጡ እና በአይን
የማይታዩ እርጥበት ያላቸው ብናኞች ፤ ፈሳሾች አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል።
እነዚህ ፈሳሾች ወይም እርጥበት ያላቸው ብናኞች ከአየር ላይ ወደ አፍ እና አፍንጫችን ከገቡ፣
በበሽታው ልንያዝ እንችላለን።

MINISTRY OF HEALTH, ETHIOPIA


የመወያያ ጥያቄዎች
በሚኖሩበት አካባቢ በሽታው ማህበረሰቡ ላይ ምን
ተፅዕኖ አሳድሯል?
በሽታው እርስዎን ወይም የቤተሰብዎን አባል ቢይዝ ምን
ዓይነት ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ብለው ያስባሉ?

ማስታወሻ ነጥቦች
የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) በኢትዮጵያ ብዙ ሺህ ሰዎችን ገድሏል፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ
ደግሞ አሳምሟል።
በሽታው አንዳንድ ሰዎችን ብዙም ላያሳምም ይችላል። ሆኖም በበሽታው የተያዘ ማንኛውም ሰው
በሽታውን ስለሚያስተላልፍ ሌሎች በበሽታው ምክንያት በፅኑ ሊታመሙ ወይም ሊሞቱ ይችላሉ።
በበሽታው የተያዙ ሰዎች በሽታው ከሚያስከትልባቸው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ራሳቸውም ሆኑ
ቤተሰቦቻቸው ለከባድ ጭንቀት ይጋለጣሉ፤ በተመሳሳይም ለኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች
ይጋለጣሉ። MINISTRY OF HEALTH, ETHIOPIA
የመወያያ ጥያቄዎች
የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ /ማስክ/ ማድረግ ያለብዎ መቼ
ይመስልዎታል?
ማስክ ባይኖርዎ ምን ያደርጋሉ?
ራስዎን ከበሽታው ለመጠበቅ ማስክ ከማድረግ በተጨማሪ
ምን ማድረግ ይችላሉ?

ማስታወሻ ነጥቦች
ከመኖሪያ ሥፍራዎ በወጡበት ጉዜ ሁሉ የፊት ማስክ ማድረግ እንዳለብዎ አይዘንጉ።
ማስክ ሲያደርጉ አፍዎን እና አፍንጫዎን እንዲሸፍን ያድርጉ።
ማስክ ማግኘት ካልቻሉ አፍዎን እና አፍንጫዎን በነጠላ፣ በስካርፍ ወይም በሌላ ጨርቅ
መሸፈን ይችላሉ።
ማስክ ማድረግ ራስንም ሆነ ሌሎችን ከኮሮናቫይረስ በሽታ ለመከላከል ያስችላል።
ማስክ ማድረግ በሽታውን ለመከላከል አንዱ መንገድ ቢሆንም ርቀትን አለመጠበቅ ለበሽታው
ያጋልጣል።

MINISTRY OF HEALTH, ETHIOPIA


የመወያያ ጥያቄዎች
የኮሮናቫይረስ በሽታን ለመከላከል እጆቻችንን መታጠብ
ያለብን መቼ መቼ ነው?
የእጅ ንፅህናን ለመጠበቅ ሌላ ምን አማራጭ አለ?

ማስታወሻ ነጥቦች
የምንነካውን ነገር ሁሉ መቆጣጠር አስቸጋሪ ስለሚሆን እጆቻችንን በሳሙና እና በውሃ
በተደጋጋሚ መታጠብ አለብን።
በተለይ አፋችንን ፣ አፍንጫችንን እና አይኖቻችንን ከመንካታችን በፊት እጆቻችንን በሳሙና እና
በውሃ መታጠብ ።
ሳሙና እና ውሃ በማናገኝበት ሁኔታ አልኮል ባለው የጀርም ማፅጃ ተጠቅመን እጆቻችንን
ማፅዳት እንችላለን።

MINISTRY OF HEALTH, ETHIOPIA


የመወያያ ጥያቄዎች
አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ለምን ይጠቅማል?
አካላዊ ርቀታችንን መጠበቅ ያለብን መቼ መቼ ነው?

ማስታወሻ ነጥቦች
አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ቫይረሱን የያዙ ብናኞች አጠገባችን ካለ ሰው ወደ መተንፈሻ አካላችን
እንዳይገቡ እና በሽታው እንዳይዘን ይረዳል።
የኮሮና ቫይረስ በሽታ ያለበትን ሰው ማወቅ ስለማንችል ከማንኛዉም ሰው ቢያንስ ሁለት
የአዋቂ እርምጃ ልንርቅ ይገባል።
ማስክ ብናደርግም አካላዊ ርቀትን መጠበቅ አስፈላጊ ነው።

MINISTRY OF HEALTH, ETHIOPIA


የመወያያ ጥያቄዎች
እርስዎ ወይም የቤተሰብዎ አባል የኮሮናቫይረስ በሽታ
ምልክቶችን ካሳዩ ምን ያደርጋሉ?
ይህን የሚያደርጉት ለምንድን ነው?

ማስታወሻ ነጥቦች
ማንኛውንም የኮሮናቫይረስ በሽታ ምልክቶች በራስዎም ሆነ በቤተሰብዎ አባል ካስተዋሉ ፤
ራስዎን ወይም የቤተሰብዎን አባል በአቅራቢያዎ የሚገኝ የህክምና ባለሞያ ምክርና እርዳታ
እንዲያገኙ ያድርጉ፤ በተቻለ መጠን የሕክምና ዕርዳታ እስኪያገኙ ድረስ ራስዎን ወይም
የቤተሰብዎን አባል ከሌሎች የቤተሰቡ አባላት በመለየት ይቆዩ፤ ይህን ማድረግዎ በሽታው ወደ
ሌሎች እንዳይተላለፍ ያደርጋል።
የበሽታው ምልክቶች የማይታይባቸው እና እንደ ደም ግፊት ፣ የስኳር ህመም የመሳሰሉ የጤና
እክሎች የሌለባቸዉ ሰዎች በቤታቸው ራሳቸውን ለይተው እንክብካቤ እና ክትትል ማግኘት
ይችላሉ።

MINISTRY OF HEALTH, ETHIOPIA


የመወያያ ጥያቄዎች
የኮሮና ቫይረስ በሽታ ከአእምሮ ጤና/ ስነ ልቦና ጋር
እንዴት ይገናኛል?
የአእምሮ/የስነ ልቦና ችግሮችን ለመከላከል ምን
ማድረግ ይቻላል?

ማስታወሻ ነጥቦች
የኮሮናቫይረስ በሽታ ማንኛውንም ሰው (ጾታ ፣ እድሜ ፣ ወዘተ) ሳይለይ በቫይረሱ ሊያዝ
ይችላል፤ ስለሆነም አስፈላጊዉን ጥንቃቄ በተረጋጋ ሁኔታ መተግበር ያስፈልጋል፤
የኮሮናቫይረስ በሽታ ታማሚዎች የስሜት መቀያየር እና አለመረጋጋትን እዲሁም ጭንቅትን እና
እንቅልፍ ማጣት ሊያስተዉሉ ይችላሉ፤
የኮሮናቫይረስ በሽታ ታማሚ እራስን ለይቶ መቆየቱ እና በበሽታ መያዙ በራሱ ለድብርት እና
ለጭንቅት ሊያጋልጥ ይችላል።
በታመሙበት ወቅት የመረበሽ ወይም የመጨነቅ ስሜት ካስተዋሉ ክትትል የሚያደርግልዎትን
ባለሞያ ማማከር እና እራስዎን ማረጋጋት አስፈላጊ ነው።

MINISTRY OF HEALTH, ETHIOPIA


የመወያያ ጥያቄዎች
ስለ ኮሮናቫይረስ በሽታ ክትባት ምን ሰምተዋል?
ለመከተብ ምን ማድረግ አለብዎ?

ማስታወሻ ነጥቦች
የኮሮናቫይረስ በሽታ ክትባት ሲከተቡ አንዳንድ የጎንዮሽ ምልክቶች
ሊሰሙዎት ይችላል። ሆኖም እነዚህ የጎንዮሽ ምልክቶች ቀላል እና በራሳቸው የሚሻሉ ናቸው።
አንዳንድ ጊዜ ስለክትባቶች ሃሰተኛ መረጃዎች ሊወጡ ስለሚችሉ በእነዚህ ወሬዎች መዘናጋት አደገኛ
ነው። ምንም ዓይነት ጥርጣሬ ካላችሁ ወደ ጤና ጣቢያ ሄዳችሁ ትክክለኛ መረጃ ልታገኙ ትችላላችሁ።
የጤና ሚኒስቴር ክትባቱ ለሁሉም እንዲዳረስ ቅደም ተከተል አውጥቶ ሰዎች ክትባቱን እየተከተቡ
ይገኛሉ። የጤና ሚኒስቴርን መመሪያ ተከትለው ክትባቱን በማንኛውም ጤና ጣቢያ ሊያገኙ ይችላሉ።
ክትባቱ በሽታውን የመከላከል አቅማችንን ይገነባል። ሆኖም ሙሉ በሙሉ ይከላከላል ማለት
አይደለም። ስለዚህ ማስክ ማድረግ፣ ርቀትን መጠበቅ እና እጅን በየጊዜው መታጠብ መቀጠል
ያስፈልጋል።
ማሳሰቢያ - ውይይቱን ከማጠቃለልዎ በፊት ከመጀመሪያ ጀምሮ ውይይት በተደረገባቸው ጉዳዮች ወይም
በአጠቃላይ ስለበሽታው ተጨማሪ ጥያቄ ካለ ማብራሪያ ይስጡ። MINISTRY OF HEALTH, ETHIOPIA
MINISTRY OF HEALTH, ETHIOPIA

You might also like