Professional Documents
Culture Documents
Thyphoid Fever
Thyphoid Fever
የታይፎይድ በሽታ በሳልሞኔላ (SALMONELLA THYPHI) ታይፊ በሚባል በሽታ አምጪ ባክቴሪያ የሚመጣ በሽታ
ነው፡፡ በተጨማሪም ሳልሞኔላ ፓራታይፊ(SALMONELLA PARA THYPHI) በሚባል ባክቴሪያ ሊከሰት ይችላል ፡፡
በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች በብዛት የሚያሳዩት ምልክት ትኩሳት ሲሆን ፤ በተጨማሪም የዚህ በሽታ መገለጫ ብርድ
ብርድ ማለትና የሆድ ህመም ናቸው ፡፡
- በዋነኝነት ይህ በሽታ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በንፅህና ጉደለት ነው ፡፡ በዚህ ምክንያት ሰዎች የተበከሉ
ምግብ እና መጠጥ በመመገብ በበሽታው ይያዛሉ ፡፡ የታይፎይድ በሽታ ያለበት ሰው በሽንትቤት ዉስጥ እና ከሽንትቤት
ዉጪ ከተፀዳዳ በኃላ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከሚበላ ምግብ እና ከሚጠጣ ዉሃ ጋር እጁን ሳይታጠብ በቀጥታ
ንክኪ ካለው እና ይሄን ምግብ እና መጠጥ አንድ ሰው ቢጠቀመዉ በቀላሉ በበሽታው ሊጠቃ ይችላል ነው::
1. በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ምግቡን ከመንካታቸው ወይም ከማዘጋጀታቸው በፊት በውኃና በሳሙና እጃቸውን
ካልታጠቡ፤
2. የምንጠቀመው ውሃ ሳይታከም ወይም ሳይጣራ ምግብ ለማብሰል ወይም እቃ ለማጠብ የምንጠቀምበት ከሆነ
ተሕዋስያኑ በቀላሉ ሊሰራጭ ይቻላል ፡፡
ምልክቶቹስ ምንድናቸው?
ተዋሕስያኑ ወደ ሰውነታችን በገባ ከ 5 እስከ 21 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ምልክቶችን ማየት እንጀምራለን ፡፡
ምንም አይነት ሕክምና ካላገኘን በ 3 ክፍሎች የሚመደብ ምልክቶች ይኖሩናል ፡፡
1. በመጀመሪያ ሳምንት እየጨመረ የሚሄድ ትኩሳት ይኖረናል ፡፡ በተጨማሪም ብርድ ብርድ ማለትና የልብ ምት
መቀነስ ሊታይ ይችላል ፡፡ በዚህ ጊዜ ተሕዋስያኑ በደም ውስጥ ይገኛል ፡፡
2. በሁለተኛው ሳምንት ላይ የሆድ ቁርጠት ፣ ድርቀት (አንድ አንድ ሰው ላይ ደግሞ ተቅማጥ) ይኖራል ፡፡ከዚህ
በተጨማሪም ደረት እና ሆድ ቆዳ ላይ ሮዝ ሰፖት (Rose spot) የሚባል ቀይ ሽፍታ ሊታይ ይችላል ፡፡
ከዚህ አልፎ በሽታው እየተባባሰ ሲሄድ ወደ ደም መመረዝ (sepsis) ፣ራስን መሳት እና ሞት ሊያስከትል ይቻላል ፡፡
በተጨማሪም
ላብ
መገጣጠሚያ ላይ ቁርጥማት
ሳል
ህክምናው
ታይፎይድ ተገቢውን ህክምና ካገኘ በቀላሉ የሚድን በሽታ ነው ፡፡ በዋናነት ግን ንፅህናን መጠበቅ ነው ሲሆን በበሽታው
ከተያዝን ደግሞ አቅራቢያችን ወደ ሚገኝ ጤና ተቁም በመሄድ ተገቢውን ምርመራ አድርገን ፀረ ባክቴሪያ በመውሰድ
ተገቢውን ህክምና ማግኘት አለብን ፡፡ አለበለዚያ በሽታው ተመልሶ ሊመጣ ይችላል ፡፡
2. የታይፈስ በሽታ
ታይፈስ ማለት ባጭሩ በቁንጫ እና በቅማል ተሸካሚነት የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡
በቁንጫ የሚመጣ ታይፈስ { endemic murine/ flea bourn } ድመትና ዉሻ እንዲሁም አይጥ ባለበት ቦታ
በሸረሪት የሚመጣ ታይፈስ{ scrub typhi } በብዛትበእስያ ባሉ ሃገራት ይታያል ይህም ሸረሪት በብዛት
የሚገኝበት ቦታ እና የሚያረቡ ሰዎች ይጋለጣሉ፡
ራሥ ምታት
ቁርጥማት
ሳል
ማቅለሽለሽና ማስመለስ
የሆድ ህመም
ትኩሳት