Professional Documents
Culture Documents
63735872
63735872
በተሇያዩ ዘመናት ዓሇማችንን ያስጨነቁ በርካታ ወረርሽኞች ተከስተዋሌ፡፡ በወረርሽኞቹም ሳቢያ በርካታ
ሕዝብ ሇሞት ተዲርጓሌ፡፡ በላልች የዓሇም ሀገራት መነሻቸውን አዴርገው በኢትዮጵያ የተስፋፉና በርካታ
ሕዝብ ሇሞት የዲረጉ ወረርሽኞች በርካታ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከሌ በተሇምድ የህዲር በሽታ በመባሌ
የሚታወቀው ወረርሽኝ አንደ ነው፡፡ ወረርሽኙ የህዲር በሽታ የተባሇው በኢትዮጵያ በመስከረም ወር
መታወቅ ቢጀምርም በከፍተኛ ዯረጃ የተስፋፋው በህዲር ወር ስሇሆነ ነው፡፡
‹‹
የህዲር በሽታ ስፓኒሽ ፍል›› ወይም ‹‹
ፓንዯሚክ ፍለ›› በመባሌ የሚታወቅ የኢንፊልዌንዛ ወረርሽኝ
ነው፡፡ ወረርሽኙ እ.ኤ.አ ከ1918-1920 ዴረስ በበርካታ የዓሇም ሀገራት የተዛመተ ሲሆን ከ20 እስከ 50
ሚሉዮን የሚገመት ሰው ገዴሎሌ፡፡ ይህ ወረርሽኝ በአገራችንም በ1911 ዓ.ም በህዲር ወር ተከስቶ
ከፍተኛ ቁጥር ያሇውን ሕዝብ ሇሞት ዲርጓሌ፡፡
የህዲር በሽታ በአዱስ አበባ ከተማ ምን ያህሌ ጉዲት እንዲዯረሰና የነበረውን ጭንቀት በስፍራው
‹‹
ተገኝተው የተመሇከቱትን መርስዔ ኀዘን ወሌዯ ቂርቆስ የሏያኛው ክፍሇ ዘመን መባቻ›› በሚሌ
መጽሏፋቸው እንዯሚከተሇው ይገሌጻለ፡፡
አንዲንዴ ስፍራ ቤተሰቡ በሙለ ይታመም ስሇነበር አስታማሚ በማጣት በርሃብና በውኃ
ጥም ብዙ ሰው ተጎዲ፡፡ ስሇዚህ በአዱስ አበባ ከተማ በየቀኑ ሁሇት፣ ሶስት መቶ ከዚያም
በሊይ ይሞት ጀመር፡፡ በአንዴ መቃብርም ሁሇቱን ሶስቱን ሬሳ እስከመቅበር ተዯረሰ፡፡
አንዲንድቹንም ሰዎች ሬሳ ተሸካሚ በማጣት በየግቢያቸው ውስጥ ቀበሯቸው፡፡
አፍሊው በሽታ ከህዲር 7 እስከ 20፣ ሇ14 ቀን ያህሌ ነበር፡፡ በተሇይም ህዲር 12 ቀን
የህዲር ሚካኤሌ ዕሇት ብዙ ሰው ሞተ፡፡ ….. በዚያ ሰሞን መቃብር የሚቆፍርና ሬሳ
ተሸክሞ የሚወስዴ ሰው ሇማግኘት ችግር ሆነ፡፡ በቤተሰብ ውስጥ ከበሽታው ያመሇጡ
ሲገኙ ሁሇት ሰዎች ሬሳ ተሸክመው እየወሰደ ይቀብራለ፡፡
በማሇት በወቅቱ የነበረውን አሳዛኝ ሁኔታ ይገሌጻለ፡፡ በተመሳሳይም የህዲር በሽታን አስከፊነት በሏረር
‹‹
ከተማ ያዩት ሌዐሌ ራስ እምሩ ኃይሇሥሊሴ፤ ካየሁት ከማስታውሰው›› በሚሇው መጽሏፋቸው ሊይ
እንዱህ ሲለ ገሌጸውታሌ፡፡
በሺህ ዘጠኝ መቶ አሥራ አንዴ ዓመተ ምህረት በሮፓና በእስያ አዴርጎ የመጣው የንፋስ
(የግሪፕ) በሽታ በኢትዮጵያም በመሊው አገር ገብቶ ብዙ ሰው ሞተ፡፡ ያንጊዜም ሏረር
ነበርኩ፡፡ እዚሁም ሏረርጌ ከህዲር ወር ጀምሮ እስከ ጥር መጨረሻ ሰሞን ዴረስ በጣም
ከፍቶ በከተማው ውስጥ ብቻ እንኳን ከሰማንያ እስከ መቶ ሃያ በየቀኑ ይሞት ነበር፡፡
የታመመው ሰው ሌክ አሌነበረውም፡፡
በሽታውም ትኩሳቱ በጣም እየበዛ፣ እራስ እያዞረ፣ አእምሮ እያጠፋ፣ ዯም እያስታወከ
ነው፡፡ በቶልም ካንደ ወዲንደ የሚተሊሇፍ በመሆኑ ብዙም ቤተሰብ እንዲሇ እየተኛ
አስታማሚው ብዙ ችግር ሆነ፡፡ የነበሩት ጥቂት ሏኪሞች ምንም ያህሌ ሰው ሇማዲን
አሌቻለም፤በሽታው እያጣዯፈ የሚገዴሌ ስሇሆነ፡፡
በማሇት የሕመሙን አስከፊነት ይገሌጻለ፡፡ በህዲር በሽታ ምክንያት አዱስ አበባ ከተማ የሞተው ሕዝብ
ቁጥር 9 ሺህ፤ በመሊው ኢትዮጵያ ዯግሞ እስከ 40 ሺህ ይሆናሌ ተብል እንዯሚገመት መርስዔ ኀዘን
ወሌዯ ቂርቆስ ይገሌጻለ፡፡ በዚህ በሽታ ሳቢያ ከሞቱ ታዋቂ ግሇሰቦች መካከሌ በአዱስ አበባ ከተማ ከንቲባ
ወሰኔ ዛማኔሌ፣ በዴሬዯዋ ከተማ ነጋዴራስ አፈወርቅ ገብረየሱስ ይጠቀሳለ፡፡
እነዚህን መሰሌ የዓሇማችን አስጨናቂ ወረርሽኞች በርካታ ህዝብን ጨርሰዋሌ፡፡ ከእነዚህ ወረርሽኞች
በማህበረሰቡ የራሱን ሀገር በቀሌ ዕውቀት መሰረት በማዴረግ በሽታዎችን ሲከሊከሌና ጤንነቱን ሲጠብቅ
ቆይቷሌ፡፡ አሁንም እየተከሊከሌ ይገኛሌ፡፡
ሇፎክልር ጥናት መሰረት የፎክ ዕውቀት (Folk knowledge) ነው፡፡ የፎክ ዕውቀት ማሇት በአንዴ
በተወሰነ ሕዝብ፣ ማህበረሰብ፣ ባህሌ ወይም አካባቢ ውስጥ ያሇ ሌዩ ዕውቀት ነው፡፡ ይህ ዕውቀት
የተሇያዩ ህዝባዊ ቴክኖልጂዎችን፣ ክህልቶችንና ውስብስብ ዕውቀቶችን የሚይዝ በመሆኑ ሇማህበረሰቡ
ህይወት መሰረት ነው፡፡
የፎክ ዕውቀት ማህበረሰቡ በህይወት ዘመን ተመክሮው ያጠራቀመው፣ የትውሌዴን ሌምዴ የሚወክሌ፣
የማህበረሰቡን ማንነትና የእዴገት ዯረጃ የሚያሳይ በመሆኑ ሌዩ ትኩረት ሉሰጠው የሚገባ የዘመን
ሙከራ አሻራ ነው፡፡
በፎክ ዕውቀት ዘርፍ ውስጥ ከሚካተቱ ሌዩ ሌዩ ዕውቀቶች መካከሌ ሀገር በቀሌ የህክምና ዘዳ አንደ
ነው፡፡ በተሇያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ የሚከሰቱ የተሇያዩ የጤና ችግሮች መነሻ ምክንያታቸውን ሇማወቅና
ችግሩንም ሇመፍታት ማህበረሰቡ ባሇው ባህሌ መሰረት ሇረጅም ዘመን የተጠቀመባቸውና አሁንም
እየተጠቀመባቸው ያለ የፎክልር ዕውቀቶች በሀገረሰባዊ ህክምና (Folk Medicine) ዘርፍ ውስጥ
ይመዯባለ፡፡
የዓሇም የጤና ዴርጅት (2001) ስሇሀገረሰባዊ ህክምና ብያኔ ሲሰጥ ሀገረሰባዊ ህክምና ጤና ነክ
ዴርጊቶችን፣ የአቀራረብ መንገድችን፣ ዕውቀትንና እምነቶችን፣ እፀዋትን፣ እንሰሳትን፣ ማዕዴናትን፣
መንፈሳዊ ቁሶችንና መንፈሳዊ ክዋኔዎችን መሰረት በማዴረግ ህመሞችን የማወቅ፣ የመከሊከሌና
የመፈወስ ስርዓት እንዯሆነ ይገሌጻሌ፡፡
በማህበረሰቡ በሕይወት ውስጥ ሇሚያጋጥሙ የጤና ችግሮች መፍትሄ ሇማግኘት በሚሌ የማህበረሰቡ
አባሊት የሚከውናቸው አጠቃሊይ ዴርጊቶች በሀገረሰባዊ ህክምና ውስጥ የሚጠኑ ጉዲዮች ናቸው፡፡
እነዚህ ዴርጊቶችም ማህበረሰቡ ስሇ ህመምና ጤና ያሇው እሳቤ፣ ስሇህመምተኛው ያሇው አመሇካከት፣
ስሇህክምና ባሇሙያዎቹ ያሇው አመሇካከት፣ አንዴን የህመም አይነት ሇመሇየት የሚጠቀምበት ዘዳ፣
ሇበሽታዎቹ መከሊከያ ወይም ማጥፊያ የሚሆኑ መዴኃኒቶችን ከምን ከምን እንዯሚያዘጋጅ፣ እንዳት
እንዯሚያዘጋጅ፣ መቼ እና የት እንዯያሚዘጋጅ፣ የመዴኃኒቶቹ የአወሳሰዴ ስርዓት እና ሇህክምናው
የሚያስፈሌጉ ቅዴመ ሁኔታዎች የመሳሰለትን ነጥቦች ናቸው፡፡
ሀገረሰባዊ ህክምናዎች ማህበረሰቡ በረጅም ዘመን የህይወት ተመክሮው ባካሄዯው ምርምር በአካባቢው
የሚያገኛቸውን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ግብዏቶችን በመጠቀም የራሱን ሕዝባዊ ዕውቀት መነሻ
በማዴረግ የሚያዘጋጃቸው ናቸው፡፡ ህክምናዎቹም በአካባቢው ሇሚከሰቱ የጤና ችግሮች ሁለ መፍትሄ
የሚሰጥባቸው፣ የጤና ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት የሚዯረጉ ቅዴመ ጥንቃቄዎች፣ ችግሮቹ ዲግመኛ
እንዲይከሰቱ የሚዯረጉ ዘሊቂ መፍትሄዎች ወዘተ. የሚሰጡበት ህዝባዊ ጥበቦች ናቸው፡፡
በዓሇማችን ሊይ በሚገኙ ህዝቦች ዘንዴ በርካታ የሀገረሰባዊ ህክምና አይነቶች አለ፡፡ እነዚህ የህክምና
አይነቶች እንዯማህበረሰቡ ባህሌ፣ ፍሌስፍና፣ ርዕዮተ ዓሇማዊ እይታና መሰሌ ሁነቶች የሚሇያዩ ናቸው፡፡
ሀገረሰባዊ ህክምናዎችን ማህበረሰቡ በሰው፣ በእንሰሳት እና በእፀዋት ሊይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን
ሇመከሊከሌ ይጠቀምባቸዋሌ፡፡
ድን ዮዯር (1972) የተባሇው ዕውቁ የፎክልር ባሇሙያ ሀገረሰባዊ ህክምናዎችን ተፈጥሯዊ የሀገረሰብ
ህክምና (Natural folk medicine) እና እምነታዊ-ሀይማኖታዊ የሀገረሰባዊ ህክምና (Magico- religious
folk medicine) በሚሌ በሁሇት ይመዴባቸዋሌ፡፡
በተሇያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ በሚገኙ እምነቶችና ሀይማኖቶች የአስተምህሮ ስርዓት መሰረት የተሇያዩ
መንፈሳዊ ቁሳቁሶች እንዯመስቀሌ፣ የሀይማኖት መጽሏፍ፣ ጸበሌ፣ ዘምዘም፣ ክታብ ወዘተ. በመጠቀም፣
በቅደስ ስፍራዎች እንዯቤተክርስቲያን፣ መስጊዴ፣ የጸበሌ ቦታ፣ ሀገረሰባዊ ሀይማኖቶች የሚከወኑበት
ስፍራ ወዘተ. አማካኝነት፣ በሀይማኖቱ ወይም በእምነቱ ስርዓት ውስጥ ትሌቅ ስፍራ በሚሰጣቸው
ግሇሰቦች በሚዯረጉ ጸልቶች፣ ሇፈጣሪያቸው ወይም ላሊ ህመምን ያመጣሌ ብሇው ሇሚያምኑበት አካሌ
በሚያቀርቧቸው መስዋዕቶችና መሰሌ መንፈሳዊ ዴርጊቶች አማካኝነት የተሇያዩ በሽታዎችን የመሇየት፣
የመከሊከሌና የመፈወስ ስርዓቶች ይካሄዲለ፡፡
በተሇያዩ አገራት ከተፈጥሮ በሚገኙ ግብአቶች የሚዘጋጁ መዴኃኒቶችን መጠቀም የተሇመዯ ነው፡፡
በተሇይ በማዯግ ሊይ ባለ አገራት ሰማንያ እጅ (80%) የሚሆነው ህዝብ ከእፀዋት፣ ከእንሰሳትና
ከማዕዴናት የሚገኙ የህክምና ግብአቶችን ሇመጀመሪያ ዯረጃ ህክምናዎች የሚጠቀሙ መሆናቸውን
ጥናቶች ያሳያለ፡፡
ከኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥም ሰማንያ እጅ (80%) የሚሆነው ህዝብ በአካባቢው የሚከሰቱ የጤና
ችግሮችን ሇመከሊከሌና መፍትሄ ሇማግኘት ሀገረሰባዊ ህክምናዎችን እንዯሚጠቀም የተሇያዩ ጥናቶች
ይጠቁማለ፡፡
በዘመናዊ የህክምና ሳይንስ መፍትሄ ያሌተገኘሊቸው ወይም ውስብስብ የህክምና ስራ የሚጠይቁ በርካታ
በሽታዎች በዓሇማችን ሊይ አለ፡፡ ነገር ግን የተሇያዩ የአገራችን ማህበረሰቦች ከእነዚህ በሽታዎች ሇመዲን
ተፈጥሯዊ መዴኃኒቶችን በሀገር በቀሌ ዕውቀት በመጠቀም መፍትሄ ያገኙሊቸዋሌ፡፡
በአገራችንም በሚገኙ በተሇያዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እነዚህን ተፈጥሯዊ የመዴኃኒት
አይነቶችን በመጠቀም በአካባቢያቸው ሇሚከሰቱ የተሇያዩ በሽታዎች መፍትሄ በመስጠት የራሳቸውን፣
የእንሰሳትንና የእፀዋትን ጤና ሇረጅም ዘመን ሲጠብቁ ቆይተዋሌ፡፡
የህዲር በሽታ በ1911 ዓ.ም ተከስቶ ከፍተኛ ጉዲት ባዯረሰብን በዚያ አስጨናቂ ወቅት ማህበረሰቡ ሀገር
በቀሌ መዴኀኒትን በመጠቀም ከበሽታው ተፈውሷሌ፡፡ ሌዐሌ ራስ እምሩ ኃይሇ ሥሊሴ በወቅቱ
ሇተከሰተው የህዲር በሽታ መዴኃኒት ምን እንዯሆነ እንዯሚከተሇው ገሌጸውታሌ፡፡
እሳቸው የ‹‹ካሉፕቱስ›› ቅጠሌ በሚሌ የገሇጹት የባህር ዛፍ ቅጠሌ ነው፡፡ የባህር ዛፍ ቅጠሌን በውኃ
በመቀቀሌ በመታጠን፣ ውኃውንም በመጠጣት ከወረርሽኑ ዴነዋሌ፡፡ የባህር ዛፍ ቅጠሌ፣ የሀረግሬሳ
ቅጠሌ፣ የዲማከሴ ቅጠሌ በሙቅ ውኃ ቀቅል መታጠን ከጉንፋን ጋር ቀረቤታ ያሊቸው መሰሌ
የኢንፊልዌንዛ ሕመሞች ፍቱን መዴኀኒት ነው፡፡ ማህበረሰቡ አሁንም ሇጉንፋንና መሰሌ ሕመሞች
እነዚህን እጸዋት ይጠቀማሌ፡፡
በአሁኑ ወቅትም ዓሇምን እያስጨነቀ የሚገኘው የኮሮና በሽታ (ኮቪዴ-19) ሇበርካታ ሕዝብ የሕይወት
ማሇፍ ምክንያት ሆኗሌ፡፡ በአገራችንም ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯሌ፡፡ ይህን ጽሐፍ በማዘጋጅበት ወቅት
በአገራችን 19 ሰዎች በበሽታው ተይዘዋሌ፡፡ የኢትዮጵያ ኢኖቬሽን እና ሳይንስ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ
ምሁራን በመሰራት ሊይ ያሇ ተስፋ ሰጪ ሀገር በቀሌ መዴኀኒት በሙከራ ሊይ መሆኑን ገሌጸዋሌ፡፡
ይህ ትሌቅ ተስፋ ነው፡፡ የራሳችንን ሀገር በቀሌ ዕውቀቶች ዕውቅና መስጠታችን፣ ሇእኛም ሆነ ሇዓሇም
መዴህን እንዯምንሆን አምነን ወዯ ተግባር መግባታችን እጅግ ዯስ ያሰኛሌ፡፡ ሇኢትዮጵያ ክብርም ነው፡፡
‹‹
በጋሞ ብሔረሰብ ዯርዯሬ›› እና ‹‹
አክርሳ›› የሚባለ ተክልች ስር በአንዴ ሊይ በመውቀጥ ጭማቂውን
በጉበት በሽታ ሇተጠቁ ሰዎች እንዯ እዴሜያቸው በተሇያየ መጠን ይሰጣቸዋሌ፡፡ የጉበት መዴኃኒቱንም
‹‹
ጠላ›› በሚሌ ስያሜ ይጠሩታሌ፡፡
እነዚህንና መሰሌ ሀገር በቀሌ መዴኀኒቶች በሳይንሳዊ መንገዴ ማጥናት አስፈሊጊ ነው፡፡ የኮሮና በሽታን
ሇመከሊከሌ ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብሌ፣ ፊጦ፣ ልሚ፣ ዲማከሴ፣ የባህር ዛፍ ቅጠሌ ወዘተ. ይጠቅማለ
ብል በስማበሇው በመሻማት ከመጠቀም መታቀብ ይኖርብናሌ፡፡ በተቃራኒው ዯግሞ እነ ነጭ ሽንኩርት
ምንም ጥቅም የሊቸውም ብል ዜና ሇመስራት ከመሯሯጥ መቆጠብ ይኖርብናሌ፡፡