Professional Documents
Culture Documents
Melkam74 5
Melkam74 5
የአዘጋጇ
መልዕክት
ሰላም!
እ.ኤ.አ በ2018 ዓ.ም የተደረገ አንድ ጥናት እንዳመለከተው አንድ ኢትዮጵያዊ ሰው በዓመት 6 ገፅ ብቻ ፅሁፍ ያነባል
ሲል አስደንጋጭ የሆነ መረጃን አስፍሯል፡፡ ይህ መረጃ የአብዛኞቻችንን የንባብ ባህል ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው፡፡ አንድ
ሰው መረጃዎችን እና እውቀቶችን ሊያኝ የሚችልበት ዋነኛው መንገድ ንባብ መሆን እንዳለበት ሁላችንም የሚያስማማ
ጉዳይ ነው፡፡ ማንበብ መረጃን ከማግኘት ባለፈ አመክንዮአዊ ብቃታችንን በማዳበር ረገድ የሚኖረው ጥቅም ሳይታለም
የተፈታ ነው፡፡ ታድያ በዓመት 6 ገፅ ያነበበ ሰው እውቀትን እና አመክንዮን ከየት ያገኝ ይሆን?
ውድ አንባቢ ሆይ እርስዎም በአካባቢዎት ያሉትን ሰዎች የንባብ ባህላቸውን ያዳብሩ ዘንድ በማበረታታት የበኩሎን
አስተዋፅኦ እንዲወጡ እንማፀናለን፡፡ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ሲባል ያለምክንያት አይደለም እና በጀንበር ንባብ
ሙሉ ሰው መሆን ባይቻል እንኳን ወደ ሙሉነት የምናደርገውን ጉዞ ዛሬ ‘ሀ’ ብለን እንጀምር እላለሁ፡፡
04 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ሽክ እንዴት?
05 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ሽክ እንዴት?
06 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ሽክ እንዴት?
07 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ስለ ጤና እናውራ
የማህፀን በር ጫፍ
ካንሰር
ቤተልሄም አምባቸው
ካንሰር በሰውነት ውስጥ ያሉ ህዋሳት ከቁጥጥር ውጪ የፓፕ ፣ የኤች.ፒ.ቪ. አልያም ሁለቱንም ምርመራዎች
በሆነ ሁኔታ በፍጥነት እንዲራቡ የሚያደርግ በሽታ ነው:: ሊያደርግ ይችላል፡፡
ምንም እንኳን ካንሰር ከቆይታ ወደ የተለያዩ የሰውነት የፓፕ ምርመራ በማህፀን በር ላይ የተከሰቱ የህዋስ
ክፍሎች የመዛመድ ባህሪ ቢኖረውም ስሙን የሚያገኘው ለውጦችን ወይንም ቅድመ ካንሰር ምልክቶችን ለመለየት
ግን በሽታው ከሚጀምርበት ቦታ ነው፡፡ ካንሰር በማህፀን የሚረዳ ሲሆን በዚህም ደግሞ በሽታው ከመከሰቱ በፊት
በር ጫፍ ላይ በሚጀምርበት ግዜም የማህፀን በር ጫፍ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያግዛል፡፡ በሽታው ምናልባት
ካንሰር በመባል ይጠራል፡፡ የማህፀን በር ማለት የማህፀን ተከስቶ እንኳን ቢሆን ቀድሞ ለማወቅ የሚረዳ የምርመራ
ጠባቡ እና የታችኛው ክፍል ማለት ነው፡፡ አይነተ ነው፡፡
ይህ አይነት ካንሰር ካሉት ሌሎች የካንሰር አይነቶች ሁሉ በሌላ በኩል ደግሞ የኤች.ፒ.ቪ. ምርመራ ኤች.ፒ.ቪ.
በቀላሉ በቅድመ ምርመራ መለየት የሚቸል አይነት ቫይረስን ማለትም የማፀን በር ጫፍ ካንሰርን
ሲሆን በቅድመ ምርመራ ወቅት የሚታዩ ምልክቶችንም የሚያመጣውን ቫይረስ ለመለየት የሚረደ ምርመራ ነው፡፡
በመከተል ካንሰሩ እድገቱን ሳይጀምር በቀላሉ መቆጣጠር በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ማን ሊጠቃ ይችላል?
ይቻላል፡፡ አንዲት በዚህ ካንሰር የመጠቃት ምልክት ያሳየች
ሴትም ብትሆን በሽታው ቀድሞ ከታወቀ በህክምና ሙሉ ምንም እንኳን በአብዛኛው እድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ
ለሙሉ የመዳን እድል ይኖራታል፡፡ ባሉ ሴቶች ላይ ችግሩ ጎልቶ ቢታይም የትኛዋም ሴት ግን
በዚህ ካንሰር ልትጠቃ ትችላለች፡፡ በአሁኑ ግዜ በአለማችን
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰርን ቀድሞ በአመት ቁጥራቸው አምስት መቶ ሰባ ሺህ የሚደርስ ሴቶች
ለመለየት የሚያስችሉ ምርመራዎች በዚህ በሽታ ሲጠቁ በሀገራችን ደግሞ ቁጥራቸው በርከት
ይኖሩ ይሆን? ያሉ ሴቶች የዚህ በሽታ ሰለባ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰርን ቀድሞ ለመከላከል አልያም ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ የዚህ ካንሰር ዋነኛ መንስኤ
በሽታው ገና የመጀመርያ ደረጃው ላይ እያለ ለመለየት ነው፡፡ ይህ ቫይረስ በግብረስጋ ግንኙነት ግዜ ከአንድ ሰው
የሚረዱ ሁለት አይነት ምርመራዎች አሉ፡፡ ወደ ሌላው ይተላለፋል፡፡ ሆኖም ግን የተወሰኑ ሴቶች ብቻ
እንደ ታካሚዋ እድሜ በማየት አንድ የህክምና ባለሙያ የካንሰሩ ተጠቂ ይሆናሉ፡፡
08 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ስለ ጤና እናውራ
የአንዲትን ሴት በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር የመያዝ እድል በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን ያሉ የተለያዩ የመንግስት እና የግል
ምን ሊጨምር ይችላል? የጤና ተቋማት ይህንን የቅድመ ካንሰር ምርመራ እየሰጡ
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ኤች.ፒ.ቪ በተባለው ቫይረስ ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹም ተቋማት ምርመራውን ከክፍያ ነፃ
አይነት የሚከሰት ነው፡፡ ማንኛዋም የግብረስጋ ግንኙነት ይሰጡታል፡፡ ስለዚህ ማንኛዋም እድሜዋ ከ21 ዓመት በላይ
ማድረግ የጀመረች ሴት ይህ ቫይረስ ሰውነቷ ውስጥ ያለች ሴት ይህንን ምርመራ እንድታደርግ እና ራሷን ከዚህ
ይኖራል፡፡ ሆኖም ግን በትንሽ እድሜዋ ግንኙነት መፈፀም አይነት በሽታ እንድትከላከል ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
09 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
አይ ሄት ፖለቲካ
በአዱኛ
የወጉን ርዕስ በእንግሊዝኛ ያደረኩት ስድስት ወር ሙሉ አሜሪካ ስለነበርኩ አማርኛ ጠፍቶብኝ ሊመስላቹ
ይችላል ወይም ደግሞ አማርኛ የስራ ቋንቋ መሆን የለበትም ብዬ ለመቃወም አስቤ እንደሆነም ልታስቡ
ትችላላቹ፤ ግን አይደለም!! ዝም ብላችሁ ነገር ባትበሉና ያላሰብኩትን እያሳሰባችሁ ባትዘባርቁ የተሻለ
ይመስለኛል...
ከቅርብ አመታት በፊት የቅርብ ጓደኛዬ በከፍተኛ ወንጀል ተጠርጥሮ በመታሰር ስምንት አመት ተፈርዶበት
ነበር። ባለፈው ግን ምንም አላጠፋህም ተብሎ ካሳ ተከፍሎት ከእስር ቤት ተፈታ። የታሰረው የግራ እጅ
ክንዱ ላይ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሚል ፅሁፍ ተነቅሶ ተይዞ መሃከል ላይ ለምን ሰማያዊ ኮከብ የሚል ፅሁፍ
አልጨመርክበትም በሚል ምክንያት ነበር... ዛሬ ግን ማንም አይናገረውም ደረቱን ነፍቶ በጃፖኒ ይዞራል!!!
10 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ፀባዩ የሚቀያየር ሰው እስስት ሲባል አውቃለሁ፤ ብሄሩ የሚቀያየር ሰው ግን ምን ሊባል እንደሚችል እንጃ!!!
አንድ ክፉ የፌስቡክ ጓደኛ ነበረኝ ሰኞ ሰኞ ኦሮሞ ነው። ከጠዋት ጀምሮ ፊንፊኔ ኬኛ ምናምን የሚሉ ፅሁፎቹን
በፎስቡክ ገፁ ላይ ሲለጥፍ ይውላል፤ አመሻሽ ላይ አማራ ሁኖ እስከ ንጋት ድረስ ንቃ አማራ መደራጀት ነው
ሚሻለን እያለ ሲዘባርቅ ያነጋል፤ ማክሰኞ ጠዋት ከንቅልፌ ስነቃ ጉራጌ ሆኖ አገኘዋለሁ!! ወደ ፌስ ቡክ ገፄ
ስገባ... እቺን ሃገር እኛ ጉራጌዎች ብንመራት ኢትዮጵያ እንደቻይና በልፅጋ አለምን ባስደመመች ነበር የሚል
ልጥፉ ከፊቴ መቶ ግምጭር ይላል... ማምሻውን ወደ ትግሬነት ተለውጦ... ትግስት ፍራቻ አይደለም፤ ትግራይ
እኔን ጨምሮ መለስን፣ ይኋንስን ያፈራች የጀግና አገር ናት ምናምን የሚሉ ፅሁፎችን ይፅፍብናል...
እኔ ዘረኞችን ንቆ የማለፍ እንጂ መልስ የመስጠት ልማድ የለኝም ግን በዚህ ልጥፉ ላይ ምላሽ ፅፌለታለሁ...
አትሊስት በራስ አሉላ ተመካ የሚል... እሱ ግን ለኔ መልስ ለመመለስ ጊዜ አልነበረውም። እንዳልኳችሁ በቀን
ሁለቴ ብሄሩን እየቀያየረ በእልህና በክፋት እኛን በመናጥ ስራው ተጠምዷል!!
አንድ አሳ አስጋሪ ነበር... አሶቹን በሚገባ ይንከባከባቸዋል፣ እየመጣ ተረት ያወራላቸዋል፣ ፍርፋሪ መኖ እየቀለበ
ያንደላቅቃቸዋል... ታድያ ይሄ አሳ አስጋሪ የአሳ ሃብቱ በጣም በመጨመሩ ምክንያት እሱን የሚያግዘውና
አገልጋዩ ሆኖ የሚሰራ ገበሬ ይቀጥራል። ገበሬው ስለ አሶቹ ሁኔታ ምንም አያውቅም እሱ የነበረበት ክፍለሃገር
JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL CLICK HERE
የእርሻ መሬት እንጂ የአሳ እርባታ ያልነበረ በመሆኑ አሶቹን እንዴት መንከባከብ እንዳለበት ባለማወቁ እግሩን
በአሶቹ መዋኛ ውስጥ እየታጠበ ውሃቸውን ያደፈርስባቸው ጀመር። አሶቹ ሸሹ አንደኛ አሳ አስጋሪው በየቀኑ
አየመጣ የሚነግራቸው ተረት ናፈቃቸው ሁለተኛ እነሱን ለመንከባከብ የተቀጠረው ገበሬ የአሶቹን ህይወት
ባለማወቁ ምክንያት ውሃቸውን ስለሚያደፈርስባቸው አሶቹ አመፁ የሚጣለው መረብ ውስጥ የሚገባ
አንድም አሳ በመጥፋቱ አሳ አስጋሪው ከሰረ ተመልሶ መቶ የድሮ ተራቱን ቢተርትም አሶቹ አልሰሙም መረቡ
ውስጥ አልገባ ብለው አመፁ...
እኔ ፖለቲካ አሎድም... ግን አሳ አስጋሪው አሶቹን ወደቀድሞ ሰላማቸው መመለስ ከፈለገ አሶቹን ለመጠበቅ
የቀጠረውን ገበሬ ወደ እርሻው መልሶ የደፈረሰውን ውሃ ማፅዳት ያለበት ይመስለኛል!!!
11 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ሔዋን
ቤተልሄም አምባቸው
እጅ የሚያስቆረጥም የቃቄ ውርድወት ፣ ድገሙኝ የስራ እድል ተመቻችቶላቸዋል፡፡ ምንም እንኳን ቀዳሚ
የሚያስብል ጣይቱ ፍርፍር ፣ ባለሙያ የከሸነችው የላጤዋ እድሉ ለእንደዚህ አይነት ሴቶች ቢመቻችም የኢኮኖሚ
ሽሮ የት እንደሚያኙ ያውቃሉ? እንግዲያውስ ሳር ቤት ጥያቄ ያለባት ማንኛዋም ኢትዮጵያዊት ሴት የስራ ቦታ
ወደሚገኘው “ተምሳሌት ኪችን” ልውሰዳችሁ እና ምግብ እስካለ ድረስ በተምሳሌት ውስጥ የመስራት አጋጣሚው
ቤቱን ላስቃኛችሁ፡፡ ይኖራታል፡፡
“ተምሳሌት ኪችን” የዛሬ 4 ዓመት ገደማ ሳምራዊት በማህበረሰቡ ውስጥ ማንኛውንም የቤት ውስጥ ስራ
ጴጥሮስ ፣ ፍትህ አስራት እና ማስረሻ አየለ በተባሉ ሴቶች ማከናወን በሴት ጫንቃ ላይ የተጣለ ማብቂያ የሌለው
ላይ አተኩረው መስራትን ባለሙ ሶስት ሴት ጓደኛሞች ሀላፊነት ነው፡፡ ምንም እንኳን ይህ የቤት ውስት ስራ የገንዘብ
ሲመሰረት አያሌ አላማዎችን ሰንቆ ነበር፡፡ ሴቶች በህብተሰቡ ተመን አልያም የምስጋና ቃል ባይሰጠውም ሴቶቻችን
ውስጥ ያለባቸው የኢኮኖሚ ጥገኝነት መፈታት እንዳለበት ለዘመናት ሲከውኑት ኖረዋል፡፡ ይህንን የተረዳው ተምሳሌት
እና ራሳቸውን የማስተዳደር የገንዘብ አቅም ሊኖራቸው ኪችንም ሴቶቹ በዚህ ምግብ ቤት ውስጥ ስራ ፍለጋ
እንደሚገባ ያመኑት እነዚህ ጓደኛሞች ይህንን ምግብ ቤት ሲመጡ የቀደመው የቤት ውስጥ የስራ እንቅስቃሴያቸውን
መሰረቱ፡፡ ይህ ምግብ ቤት የተለያዩ ሴቶችን በተለይም በቂ በቂ የስራ ልምድ አድርጎ ይወስዳል፡፡ ይህንን ልምድም
የሆነ የትምህርት ዝግጅት የሌላቸውን እና የስራ ልምድ ከዘመናዊው የምግብ ቤት ስነ-ምግባር ጋር ያዋድዱትም
ያላካበቱትን ወደ ተለያየ ቦታ ስራ ፍለጋ በሚሰማሩበት ግዜ ዘንድ ስራ ከመጀመራቸው በፊት በቂ የሆነ ስልጠና
ከሚደርስባቸው እንግልት እና እንግልቱም ከሚፈጥረው እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ ስልጠናውም በምግብ ቤቱ ውስጥ
ተስፋ መቁረጥ ለመታደግ ያለመም ነው፡፡ በምግብ ቤቱ ላላቸው ቆይታ ብቻ ሳይሆን ከምግብ ቤቱ ውጪም ቢሆን
ውስጥ ልጆቻቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ እናቶች ፣ ለሚኖራቸው ቀሪ የስራ ግዜ እና ተጨማሪ የስራ እድሎች
ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ሴቶች እና ወደ አበይት ግብዓት ይሆናል፡፡ ስልጠናው በአብዛኛው በተግባር
አረብ ሀገራት ለመሄድ በመሰናዳት ላይ ያሉት ቀዳሚ ላይ ያተኮረ እንዲሆን የሚደረግ ሲሆን ይህም ደግሞ ሴቶቹ
12 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ሔዋን
ስልጠናው ባለቀበት ሰዓት ወዲያውኑ ያለምንም ተጨማሪ የተነሳ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን እስከ አሁን የገጠሙትን
ግዜ ማጥፋት ስራውን እንዲቀላቀሉ ይረዳል፡፡ የንግድ አልያም ሌሎች ፈተናዎች በራሱ ሲፈታ ቆይቷል፡፡
JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL CLICK HERE
በተምሳሌት ውስጥ ያሉ ሴቶች የሚያገኙት የስራ ስልጠና አሁንም ቢሆን ይህንን የመቀጠል አላማ አለው፡፡ ነገር ግን
ብቻም አይደለም፡፡ በሌላ ዘርፍ ያለ የትምህርት እድልም ከድርጅቱ አላማ ጋር የኛም ሀሳብ ይዋደዳል የሚል አካል
ይመቻችላቸዋል፡፡ ምግብ ቤቱ ከሰነቃቸው አላማዎች ካለ ከተምሳሌት ጋር ጥምረት የመፍጠር በር ሊከፈትለት
መካከል አንዱ ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት ነው እና እንደሚችል ለመገንዘብ ችለናል፡፡
ማንኛዋም የምግብ ቤቱ ሰራተኛ ለነገዋ የሚሆንን ተጨማሪ ተምሳሌት በዋናነት ሴቶችን በኢኮኖሚ ማበልፀግ ላይ
ችሎታ እና እውቀት ይዛ እንድትወጣ ይፈለጋል፡፡ በዚህም አተኩሮ ቢሰራም አብዛኞች በተሳሳተ መልኩ እንደሚረዱት
ፍላጎት ውስጥ ታድያ ሰራተኞች ራሳቸውን በትምህርት ግን የእርዳታ ድርጅት አይደለም፡፡ ይልቁንም ማህበረሰብ
እንዲያዳብሩ የሚችሉበት መንገድ ተመቻችቷል፡፡ ተኮረ የሆነ የንግድ ድርጅት እንጂ፡፡ ይህ ማህበረሰብ ተኮር
በተምሳሌት ውስጥ ያለች ሴት የመማር ፍላጎት ካላት የሆነ ድርጅት ለመሰል ድርጅቶች አልያም በዚህ አይነት
ምግብ ቤቱ ሙሉ የትምህርት ወጪን እስከመሸፈን የንግድ ዘርፍ ለመሰማራት ለሚያስቡ ሁሉ ከተሞክሮው
የሚደርስን ድጋፍ ሊያደርግላት ይችላል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ምክርን ሳያካፍል አላለፈም፡፡ የድርጅቱ ኦፕሬሽናል ማናጀር
ተምሳሌት በስሩ 23 የሙሉ ግዜ ሰራተኞች ሲኖሩት ከዚህ የሆነችው ትዕግስት ወርቅነህ እንዲህ ስትል ምክሯን
በተጨማሪም 6 የአስተዳደር ሰራተኞች አሉት፡፡ ከሌላው ታካፍላለች “በመጀመርያ አንድ ሰው ወይንም ድርጅት
ድርጅት ለየት ባለ ሁኔታም ሁሉም የአስተዳደር ሰራተኞች በእንደዚህ አይነት የንግድ ዘርፍ ለመሰማራት ሲያስብ
ምንም አይነት ክፍያ ከተምሳሌት ሳያገኙ በበጎ ፈቃደኝነት ይህንን አይነት ስራ መስራት መፈለጉን እርግጠኛ መሆን
የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ አለበት፡፡ ሁለተኛ ነገር ደግሞ የሚያጋጥሙትን ችግሮች
ተምሳሌት ሴቶችን በኢኮኖሚ ከማብቃት በዘለለ ሁሉ ለመጋፈጥ ሙሉ ፈቃድ ሊኖረው ይገባል፡፡ አለበለዚያ
ጠቅላላውን የማህበረሰብ ክፍል የሚነኩ ጉዳዮችም ላይ ብዙ ርቀር መጓዝ ሊከብደው ይችላል፡፡ ተምሳሌት አራት
በማተኮር ይታወቃል፡፡ በተለያዩ ርዕሶች ዙርያ በየወሩ አመት ይህንን ስራ ሳያቋርጥ መስራት የቻለው ከላይ
የሚዘጋጀው “ዘ ስታንድ” የተሰኘውን የውይይት መድረክ ያልኩሽ ቁርጠኝነት ውስጣችን ስላለ ነው፡፡ “
ለዓብነት ማንሳት ይቻላል፡፡ በዚህ ወርሀዊ መድረክ ላይ ድርጅቱ በምግብ ቤት ብቻ ሳይገደብ ለወደፊቱ የተለያዩ
ማንኛውም ሰው መሳተፍ የሚችል ሲሆን በሚነሱት ስራዎች ላይ የመሰማራት ሀሳብ ሲኖረው ከእነዚህም
ዘርፈ ብዙ ርዕሶችም ላይ ሙያዊ አስተያየቶችን ጨምሮ መካከል አንደኛው የህፃናት መዋያ በመክፈት በተለይም
የፕሮግራሙ ተሳታፊዎችም ሀሳባቸውን እንዲያጋሩ ልጆቻቸውን በሚጠብቅላቸው ሰው እጦት ምክንያት
ይደረጋል፡፡ ከወርሀዊ መድረኩ በዘለለም ለልዩ ልዩ ስራቸውን ማከናወን ያልቻሉ ሴቶችን ማገዝ እና ወደ ስራ
ከተምሳሌት አላማ ጋር ኩታ ገጠም ለሆኑ ዝግጅቶች ገበታቸው እንዲመለሱ መርዳት ነው፡፡
ሬስቶራንቱ ቦታ ያመቻቻል፡፡ ማንኛውም ውይይቶችን እና እኔም በቦታው ተገኝቴ ከታደምኩት የቤቱ እጅ
ህብረተሰብ ተኮር የሆኑ ዝግጅቶችን አልያም ትርኢቶችን እና የሚያስቆረጥም ምግብ እና መንፈስን ከሚያድሰው
የጥበብ ምሽቶችን ማዘጋጀት የሚፈልግ ግለሰብ ወይንም የምግብ ቤቱ ድንቅ ድባብ እርስዎም ይካፈሉ ስል
ድርጅት የሚዘጋጀው ዝግጅት ተምሳሌት የተነሳበትን አላማ በመልካም74 ስም ግብዣዬን አስተላልፋለሁ፡፡
የሚደግፍ ከሆነ በምግብ ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ዝግጅቱን
የማድረግ አጋጣሚው ሊፈጠርለት ይችላል፡፡ አድራሻ፡ ሳር ቤት ከአዳምስ ፓቪሊዮን አለፍ ብሎ ኮይካ
ተምሳሴት በራስ ሰርቶ ራስን ማበልፀግ የሚል ሀሳብን ይዞ ህንፃ ስር
13 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ከጀርባ ማን ነበር ?
ከእንጦጦ
ቤተ-ዕደጥበባት
ጀርባ ማን ነበር?
ከእንጦጦ ተራራ ስሙን ያገኘው እንጦጦ ቤተ-ዕደ ጥበባት ትረቱን የኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያሉ
ሴቶችን በኢኮኖሚ ራሳቸው እንዲችሉ ማድረግ ላይ አድርጎ የሚሰራ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ለእንደዚህ አይነት
ሴቶች የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ የሚሰሩትን የእጅ ስራ ውጤቶች በሙሉ ለውጪ ገበያ በማቅረብ የሀገራችን
የራስ ምታት የሆነውን የውጪ ምንዛሬ ችግር ለመቅረፍ አበክሮ ይሰራል፡፡ ከዚህ ውጤታማ ከሆነ ድርጅት ጀርባ
ካለችው እና የድርጅቱ መስራች ከሆነችው ከቤተልሄም ብርሃነ ጋር ቆይታ አድርገን ነበር፡፡ መልካም ንባብ!
ብሎም ሀገራቸውን መጥቀም እንዲችሉ ለማድረግ መልካም74፡ ወደዚህ አይነት ስራ እንዴት ልትገቢ ቻልሽ?
በማሰብ በዋነኛነት እነዚህን ሴቶች ሙያ በማስተማር ምን አይነት አጋጣሚ ነው ወደዚህ ስራ የሳበሽ?
የተለያዩ ለወጪ ንግድ የሚቀርቡ ጌጣ ጌጦችን እንዲያመርቱ
እናደርጋለን ማለት ነው፡፡ ቤተልሄም፡ እንግዲህ እኔ ከኮሌጅ ማርኬቲንግ ተምሬ
እንደወጣሁ የኢትዮጵያ ቱሪስት ትሬዲንግ ውስጥ ባለ
መልካም74፡ እንጦጦ አተኩሮ እየሰራ ያለው ኤች.አይ.ቪ አንድ ሱቅ ላይ በሴልስ ፐርሰንነት ተቀጠርኩ፡፡ ነገር ግን
ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያሉ ሴቶች ላይ ነው፡፡ እነዚህን ሴቶች እዛ ያሉትን እቃዎች ሳያቸው አያምሩም፡፡ እኛ ደግሞ
መምረጥ ያስፈለገበት ምክንያት ምንድን ነው? የምንመርጠው እቃ የሚያብረቀርቅ ወይንም የሆነ አይነት
የውጪ ስሜት ያለው ነው እንጂ የራሳችን የባህላችን
ቤተልሄም፡ እንጦጦ በዋነኛነት እንደ ድርጅት እኩል የሆነ የሆኑት እቃዎች ብዙም አይስቡንም፡፡
የሀብት ክፍፍል በህብረተሰብ ውስጥ መኖር እንዳለበት እዛ እየሰራሁ እራሴን አንድ ነገር ጠየኩት፡፡ ማነኝ ፣ምንድን
ያምናል፡፡ በዚህም የተነሳ እነዚህን ሴቶች ስናያቸው ብዙም ነኝ ፣ ወዴት ነው የምሄደው ፣ ምንድን ነው የምፈልገው፣
ትኩረት ያልተሰጣቸው እና በህብረተሰቡ የተገፉ ስለሆኑ ለምንድን ነው ወደዚህ ምድር የመጣሁት የሚለውን ጥያቄ
ስራ የማግኘት እና ራሳቸውን የመደገፍ እድላቸው በጣም ራሴን ጠየኩ፡፡ በሰዓቱ 22 ዓመቴ አካባቢ ነበር፡፡ ከዛ ደግሞ
ዝቅተኛ ነው፡፡ ለዚህም ነው እንደ ድርጅት እነዚህ ሴቶች ዲግሪ መማር ነበረብኝ፡፡ አካውንቲንግ ልማር? ቤተሰብ
ላይ አተኩረን መስራት የፈለግነው፡፡ ደግሞ መርዳት ነበረብኝ ፤ በዛ ሁሉ መሀል ራሴን ፈልጌ
አገኘሁት ማለት ነው፡፡ እኔ አካውንቲንግ መማር አልችልም፡፡
መልካም74፡ ሌላው ደግሞ ምንድን ነው እቃዎቹን ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብዬ መስራት ሳይሆን የምችለው እኔ
ለማምረት የምትጠቀሙባቸው እቃዎች ጌጣጌጦችን ለማምረት ሴልስ መሆን ነው የምችለው ብዬ ለራሴ ወሰንኩ፡፡ ከዛ
ይጠቅማሉ ተብለው የሚታሰቡ አይነት አይደሉም፡፡ ከቡና ደግሞ የራሴን ስራ ስሰራ የምወደውን ስራ መስራት አለብኝ
የተሰራ የአንገት ጌጥ አይቻለሁ:: ከጥይቅ ቀለሀ የተሰራ አለ፡ ብዬ አሰብኩኝ፡፡ የምሰራበት ቦታ ያሉትን እቃዎች ደግሞ
፡ ከወዳደቁ ብረቶች ጌጦችን ትሰራላችሁ እና እንደዚህ አይነት ሳስተውላቸው የራሳችን ወግ እና ልማድ የሚገለጥበት
እቃዎችን የመረጣችሁበት ምክንያት ምንድን ነው? የእኛው የሆነ ነገር እንደሆነ ገባኝ፡፡ ማንኛውንም ነገር
ስንጀምር ደግሞ በቅርብ ካለው መሆን አለበት እና እንደነሱ
ቤተልሄም፡ በነገራችን ላይ እነዚህ ጌጦች እኮ አዲስ አይነት እቃዎችን መሸጡ ላይ ለማተኮር ወሰንኩ፡፡ በግዜ
የፈጠርናቸው አይደሉም፡፡ ወሎ ብትሄዱ ወይንም ሂደት ደግሞ እቃዎቹን በጣም እየወደድኳቸሁ መጣሁ፡፡
ወደ ጎጃም ብትሄዱ እነዚህን ጌጦች የአካባቢው ሰዎች ለኔ በፊት የነበርኩበት የስራ ቦታዬ በጣም ብዙ ትምህርት
በስፋት ሲጠቀሙባቸው ታያላችሁ፡፡ እኛ ምንድን ነው ያገኘሁበት ነው፡፡ እዛ ለነበሩ ሰዎች ሁሉ ፣ ላገኘኃቸው ሰዎች
ያደረግነው ባህላዊ የሆኑትን ጌጦች ዘመናዊ መልክ ፣ ለመንግስት ትልቅ ምስጋና እና አክብሮት አለኝ፡፡
እንዲይዙ አደረግናቸው፡፡ እነዚህን ጌጦች እኛ አይደለንም
የፈጠርናቸው፡፡ ቡናውንም ፣ ብረቱንም ምኑንም ወደ መልካም74፡ እዚህ ቤት የሚሰሩት ስራዎች የዕደ-ጥበባት
ጌጥነት ቀይሮ በቀላሉ መስራት ይቻላል፡፡ ስራዎች ናቸው፡፡ ይህ አይነተ ስራ ደግሞ በባህሪው የሆነ አይነት
ችሎታን ወይንም ሙያን የሚጠይቅ ነው፡፡ አንቺ ከዚህ በፊት
መልካም74፡ እንጦጦ እየሰራ ያለው ነገር ፤ እየደረሰ ያለውም ለሙያው የመጋለጥ አጋጣሚ ነበረሽ ወይስ ሙያውን ተምረሽው
የሰው ቁጥር በጣም ሰፊ ነው፡፡ የዚህን ድርጅት ስራ ያየ ወይም ነው ይህንን ስራ የመረጥሽው?
የሰማ ሁሉ ደግሞ ከድርጅቱ ጀርባ ያለችው ማናት ብሎ መጠየቁ
አይቀሬ ነው፡፡ ማን ብለን እንንገራቸው? ቤተልሄም ብርሀነ ቤተልሄም፡ እኔ ቅድም እንዳልኩሽ ዲዛይነር አይደለሁም፡፡
ማናት? እዚህ ላይ እውነቱን ነው መናገር የሚያስፈልገው፡፡
ለዲዛይነሮች ትልቅ አክብሮት አለኝ ግን ዲዛይነር
ቤተልሄም፡ ቤተልሄም ብርሃነ የ40 ዓመት ሴት:: ባለትዳር እና አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የሆኑ ነገሮች የሆነ ቦታ ማድረግ
የሁለት ልጆች እናት ፤ በዛም ላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊት ናት፡፡ እችላለሁ፡፡ ለምሳሌ እኔ ዲዛይን ያደረኳቸው ቦርሳዎች
15 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ከጀርባ ማን ነበር ?
፣ ያንገት ጌጦች እዚህ ቤት ታገኛለሽ፡፡ የዚህንም ሱቅ መድሀኒት እያቀበለ ነው ማለት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ከመንግስት
ኢንቲሪየር ዲዛይን እኔ በሰፊው ተሳትፌበታለሁ፡፡ ስለዚህ የተለየ ድጋፍ እና አትኩሮት ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ፡፡ ነገር ግን
ይሄ ነገር የኔ የውስጥ ፍላጎት ወይንም ደግሞ ፓሽኔ ነው:: እውነታውን የምታውቂው አንቺ ነሽ እና ከመንግስት በኩል
አንዳንዱ ነገር ባይሸጥ እንኳን እንደዚሁ ተሰርቶ ሲቀመጥ ያለው ትኩረት በተለይም ለወጪ ንግድ እንቅስቃሴ ምን
እና ሳየው ደስ ይለኛል፡፡ አንዳንድ ነው የእውነት ዲዛይነር ይመስላል? በምን ተደግፋችኃል በምን ደግሞ ችላ ተብላችኃል?
JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL CLICK HERE
ሁሉም ማት ቢከብድም እንኳን አብዛኞቹ እንደዛ እኛ የራሳችንን ምርት ብቻ ሳይሆን ባሉን ሱቆች ሁሉ
ናቸው፡፡ ስለዚህ እኛ በፈረነጆቹ ፌብሩዋሪ ላይ እንጦጦ የሌሎች አምራቾችንም ምርቶች እንሸጣለን፡፡ አሁን
ኤል.ኤል.ሲ ሚኒአፖሊስ ላይ መሰረትን፡፡ ስለዚህ አራት ሱቆች ናቸው ያሉን 6 ኪሎ ፣ አትላስ አካባቢ
ስራዎቻችንን በራሳችን ሱቅ ለመሸጥ እንቅስቃሴ ላይ ፣ ኤርፖርት ውስጥ እና ሂልተን ሆቴል፡፡ አሁን ደግሞ
ነን፡፡ የምናደርገውም ያንን ነው፡፡ ስካይ ላይት ሆቴል ውስጥ ልንከፍት ነው፡፡
መልካም74፡ ውጪ ከሚወጡት እቃዎች በተጨማሪ ሀገር መልካም74፡ ምን ያህል ሰራተኞች አሉ በስራችሁ አሁን?
ውስጥ ካሉ የተለያዩ አምራቾች ጋርስ ያለው የገበያ ትስስር ምን ቤተልሄም፡ እንድዲህ አሁን ኮንስትራክሽን ውስጥም
የመስላል? በምን መልኩ ነው አብራችሁ እየሰራችሁ ያላችሁት? ገብተናል፡፡ ስለዚህ ወደ 250 አካባቢ ሰራኛ ይኖረናል፡፡
ያው በተለያየ ቦታ ላይ ስለሆነ ሰራተኞቻችን ያሉት
ቤተልሄም፡ የገበያ ትስስር የተፈጠረልን የተለያየ ክልል ይህን ያህል ብሎ ትክክለኛ ቁጥር መስጠቱ ይከብደኝ
ላይ ካሉ አምራቾች ነው፡፡ ለምሳሌ የተለያዩ የስፌት ይሆናል፡፡
ስራዎችን ከ ባህር ዳር እና አክሱም እናመጣለን ፣
ጌጦችን ከወሎ እና ከጎጃም እናመጣለን ፣ ደቡብ ላይ መልካም74፡ የማምረት አቅሙስ ምን ላይ ደርሷል፡፡ በጅምላ
ማር እና ቡና የሚያቀርቡልን አሉ ፣ በተለይም ደግሞ መግዛት የሚፈልጉ ሰዎች ካሉ ያንን ፍላጎት የማሟላት አቅም
ካዌ ከተባለው ድርጅት ጋር - እነ ወ/ሮ ንግስት ማለት አላችሁ?
ነው ከእነሱም ጋር እንሰራለን፡፡ ለኔ ወ/ሮ ንግስት ማለት ቤተልሄም፡ እኛ ትልቁ ችግራችን የመስሪያ ቦታ እጥረት
ከእናቴ ቀጥላ አስተማሪዬ ናት፡፡ ክብር የሚገባት ሴት ነው፡፡ ከዛ ውጪ በጅምላ አንድ እና ሁለት መቶ ሺ
ናት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት የወረደ ስራ ስትሰራ ስራዎችን በአንድ ሲዝን የሚያዝ ሰው ቢመጣ ያንን
ያየኃት እኔ እሷን ነው፡፡ እንግዲህ ይህንን ይመስላል ፍላጎት ለሁለት አመታት ማሟላት የሚችል ጥሬ እቃ
ያለን ትስስር፡፡ እጃችን ላይ አለ፡፡ ግን መስሪያ ቦታ የለንም፡፡
17 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ከጀርባ ማን ነበር ?
መልካም74፡ እስከዛሬ ድረስ ብዙ ስራዎችን ሰርተሻል እና ማህበራዊ ሀላፊነት ላይ ማተኮር በጣም የምፈልገው
በእኔ እይታ ስኬታማ ነሽ ብዬ አስባለሁ፡፡ አንቺስ ስኬታማ ነኝ እና የምታገልለለትም ጉዳይ ነው፡፡ ድርጅቶች
ብለሽ ታስቢያሽ? ስኬትስ ላንቺ ምንድን ነው? ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን በተወጡ ቁጥር የሀብት
ክፍፍሉ ፍትሀዊ እየሆነ ይመጣል፡፡ ይህ ደግሞ አሁን
ቤተልሄም፡ እኔ ስኬታማ ነኝ ማለት ይከብደኛል፡ የምናያቸውን ችግሮች ሁሉ የሚቀርፍልን ነው፡፡
፡ አይደለሁም ማለትም በጣም ይከብደኛል፡፡ የእኛን አሁን ሀገራችን ውስጥ ያሉ ችግሮችን ሁሉ የፈጠረው
ሴቶች ሳስብ እንዴት እድለኛ ነኝ እላለሁ፡፡ ትልቁ ፍትሀዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል አለመኖር ነው፡፡ እኔ
አላማዬ ኢኮኖሚውን መቆጣጠር ነው፡፡ ያልተወሰነ እየበላሁ ፣ ልጆቼን ጥሩ ትምህርት ቤት ስያስተማርኩ
የገነዘብ ሀብት ውስጥ መግባት ነው ህልሜ፡፡ ይህ ግን ሌላው ግን የሚበላው አንኳን አጥቶ እያየሁ ዝም ብዬ
JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL CLICK HERE
የቅንጦት ህይወትን ለመምራት አይደለም፡፡ አለም ላይ ማለፍ አልፈልግም፡፡ ያንን ለማድረግ የሚደፍር ሰው
ስትኖሩ ገንዘብ አቅም ነው፡፡ ተቀባይነትን የምታገኙት ራሱ ምን አይነት ህሊና እንዳለው አላውቅም፡፡ ለዚህ
በምታወጡት ገንዘብ ልክ ነው፡፡ ነው በተለይ ማበራዊ ሀላፊነትን መወጣት እና ፍትሀዊ
የሆነ የሀብት ክፍፍል ማስፈን ላይ ማተኮር የፈለኩት፡፡
መልካም74፡ እንጦጦ በዋናነት ማበረሰባዊ ሀላፊነቱን ሌሎች ድርጅቶችም ይህንን ተግባር እንዲከተሉ እና
መወጣት ላይ አተኩሮ ነው እየሰራ ያለው፡፡ ይህን ነገር ደግሞ የበኩላቸውን እንዲያደርጉ እመክራለሁ፡፡
አብዛኛው ድርጅት ሲተገብረው አላየንም፡፡ በዛም ላይ ደግሞ
ተጨማሪ ወጪዎችን ስለሚጠይቅ ድረጅቶች በአብዛኛው መልካም74፡ እኔ እግዲህ ያለኝን ጥያቄ ጨርሻለሁ፡፡
ሲሸሹት ይስተዋላል፡፡ ለመሰል ድርጅቶች ማበራዊ ሀላፊነትን ቤቲ ግዜሽን ሰጥተሸኝ ይህንን ቃለ-መጠይቅ
ከመወጣት አንፃር ምን ቢያደርጉ ብለሽ ትመክሪያለሽ? ከእንጦጦ ስለሰጠሸኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡
ምን ይማሩ? ቤተልሄም፡ እኔም እዚህ ድረስ መጥታችሁ
ስላደራችሁልኝ ቃለ መጠይቅ እጅግ በጣም
ቤተልሄም፡ ማህበራዊ ሀላፊነትን የተመለከተው አመሰግናለሁ፡፡
ጉዳይ እኔ በበኩሌ ሙሉ ቃለ መጠይቁ ቢሆን
እንኳን ደስ የሚለኝ ጉዳይ ነው፡፡ በስነ-ምግባር እና
18 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL CLICK HERE
እኩል አይበርደንም
በሰይፈ ተማም
ያልተቃኘ ድምፅ
ብርሀኑ
የአለም የጤና ድርጅተ 466 ሚሊየን ሰዎች የመስማት ፡ መርፍ ወድቃ ከምታሰማው እስከ መድፍ ተኩስ ድምፅ
ችግር እንዳለባቸው ገልጿል፡፡ እንዲሁም በአውሮፓውያኑ ድረስ የራሱ የሆነ የራሱ የሆነ ልኬት አለው፡፡ ይህም ልኬት
አቆጣጠር በ2050 የመስማት ችግር ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ዴሲብል በመባል ይታወቃል፡፡ ጆሮ የተመጠነ የድምፅ
በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል፡፡ መጠን ከ90 ዴሲብል ያነሰ እንደሆነ ይታመና፡፡ ማንኛውም
በአለማችን ብሎም በሀገራችን የመስማት ቀን ተበሎ ሰው በንግግር ወቅት ድምፁ 60 ዴሲብል የሚያክል
ይከበራ፡፡ ይሁን እንጂ የመስማት ቀንን ከማክበር በዘለለ ጥንካሬ አለው፡፡ አንዳንድ ድምፆች 120 ዴሲብል ሲደርስ
የምንሰማውን ድምፅ ለጆሯችን መጥነን ስንጠው ጆሮን ያሳምማል፡፡
አይስተዋልም፡፡ ተፈጥሮ መርቃ የሰጠችውን የመስማት በአካባቢያችን ከተለመዱ ድምፆች መካከል
ችሎን እድሜ እየገፋ ሲሄድ እየተዳከመ መሄዱ የማይቀር የተወሰኑት ልኬታቸው እንደሚከተለው ነው፡፡
ሀቅ ነው፡፡ አብዛኛውን ግዜ ሰዎች የመስማት ችሎታቸውን
የሚያጡት በእርጅና ምክንያት ብቻ ሳይሆን ጫጫታ • የባቡር እንቅስቃሴ - 100 ዴሲብል
የሚባባቸው ስራዎች ፣ ከፍተኛ ድምፅ የሚሰማባቸው • የመኪናዎች እንቅስቃሴ - 80 ዴሲብል
ስፍራዎች የሚያስከትሉት ጉዳት አንድ ላይ ሲደመር • የኤሌክትሪክ መጋዝ - 110 ዴሲብል
የመስማት ችሎታ ያዳክማል፡፡ ታድያ ዛሬ በሀገራችን ፣ • አውሮፕላን ሰያልፍ - 120 ዴሲብል
በአካባቢያችን ፣በቤታችን ያሉ ተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን • የጠመንጃ ድምፅ - 140 ዴሲብል
የሚያሰሟቸው ድምፆች ተመጥነው ይሆን?
ጎዳናዎች ከሚርመሰመሱ መኪናዎች ፣ አውቶቡሶች አዘውትረን ከማንሰማቸው ድምፆች ደግሞ
እና ከባድ የጭነት መኪናዎቸ እንዲሁም በስራ ቦታዎች • ስንተነፍስ - 10 ዴሲብል
ከሚገኙ መሳርያዎች የሚወጡ ከፍተኛ ድምፆች ጎዳናችን • ስናሾካሹክ - 20 ዴሲብል
ሲበጠበጥ ይውላል፡፡ ማኛውም ድምፅ የራሱ ልኬት አለው፡ • ንግግር - 60 ዴሲብል
20 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
አረንጓዴ
ለመሆኑ ድምፅን እንዴት እንሰማለን? ስለሚችል ሊድን የማይችል የጆሮ ጉዳተ ያደርሳል፡፡ እነዚህ
ህብረ ህዋሳት አንድ ግዙ ከተጎዱ እንደገና ሊድኑ አይችሉም፡
ጆሮ የውጨኛው ፣ የመካከለኛው እና የውስጠኛው ፡ በዚህ ምክንያት የጆሮ መጮህ ችግር ሊያጋጥም ይችላል፡፡
ተብለው የሚጠሩ ሶስት ክፍሎች አሉት፡፡ ውጫዊው የመስማት ችሎታን ማራዘም
የጆሮ ክፍል በአይን የሚታየው ሲሆን ወደ ጆሮ ታምቡር ሰዎች በፈጥሮ የሚያገኙት የመስማት ክህሎት አንድ ግዜ
የሚገባውን ድምፅ የሚመጥን በመሆኑ መጣ ገባ እና ብቻ በመሆኑ ከተጎዳ ወደ መጀመርያው መመለስ በጣም
ጠመዝማዛ ቅርፅ ይዞ ተፈጥሯል፡፡ በውጫዊ የጆሮ ክፍል አስቸጋሪ ስለሆነ በየግዜው የጆሮዎቻቸውን ጤንነት
የገባው የተመጠነው ድምፅ ደግሞ በመካከለኛው የጆሮ መከታተል ግድ ይላቸዋል፡፡ ስለዚህ የመስማት ክህሎት
ክፍል ውስጥ ይስተናገዳል፡፡ በመካከለኛው የጆሮ ክፍል እድሜ ለማራዘም የሚከተሉትን ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
ውስጥ ሶስት ጥቃቅን አጥንቶች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ አጥንቶች • የምናዳምጠው ሙዚቃ በኢርሴት ከሆነ የድምፁን
ከውጫዊ የጆሮ ክፍል የገቡ የጆሮ ድምፆች የጆሮ ታምቡር መጠን መቀነስ እ በዙያችን ያለውን ድምፅ መስማት
ንዝረት እንዲፈጥር ያደርጉታል፡ በውስጠናው የጆሮ ክፍል በሚያስችለን መልክ ዝቅ ማድረግ
የሚገኙ ጥቃቅን ፀጉሮች ከድምፅ ሞገዱ ጋር በሚፈጥሩት • ጫጫታ በበዛበት አካባቢ የድመምፅ መከላከያ
ግንኙነት መገዶቹ ወደ ፈሳሽ መልክ አስተላላፊነት ማድረግ
ይቀየራሉ፡፡ በዚህ አማካኝነት ጥቃቅን ፀጉሮች በፈሳሽ • ከፍተኛ የድምፅ ሞገዶች የሚበዙበት ስፍራን
የድምፅ ነርቮች ተሸካነት መልዕክቱን ወደ አንጎል ይልኩና አለማዘወተር
ድምፅ ሆነው ይሰማሉ፡፡ • ጆሮዎች በጆሮ ማፅጃዎች ማፅዳት
ከፍተኛ ድምፅ (በካይ ድምፅ) በውጫዊው ጆሮ • አካባቢ የሚረብሹ ነገሮችን ማወቅ
በኩል ሳይመጠኑ የገቡት ሣይመጠኑ የገቡት ድምፆች • ለማህበረሰቡ በቂ እውቀት መስጠት
በውስጠኛው የጀሮ ክፍል ላይ በሚገኙ በቀለሉ ሊጎዱ የሚሉ ከሁሉም በላይ በየመንገዳችን የመኪናዎች ድምፅ የሚበዛ
ፀጉር መሰል ህዋሳት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ያለ በዚ ምክንያት የመኪናውን
፡ በድንገት የሚባርቅ ድምፅ የውስጠኛውን ጆሮ ህብረ ጥሩንባ እንዲያሰሙ የተቻለንን ማድረግ ከጆሮዎች ዋስትና
ህዋሰትን ሊደን እና ሊድን የማይችል ጠባሳ ሊያስቀር ከፍተኛ ነው፡፡
21 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
የኛ
በ1860 ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉት አቀላጥፎ መናገሩ ነበር፡፡ በተጨማሪም አለቃ ዝርዓት እና
ጦርነት ልጃቸው ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ወደ እንግሊዝ አቶ ገብረመድህን የተባሉ ሁለት ኢትዮጵዊያን ሞዚቶች እና
ሀገር ተወስዶ ነበር፡፡ በዛሬው የኛ አምዳችንም የዚህን ልዑል አጫዋቾች¬ ተመረጡለት፡፡
ባዕድ ሀገር ኑሮ ልናስቃኛችሁ ወደድን፡፡ አለማየሁ ከጠባቂው ስፒዲ ጋር ፌሬዝ በተባለችው መርከብ
ልዑል አለማየሁ ሚያዚያ 5 ቀን 1853 ዓ.ም በደብተረ ተሳፍሮ በ1860 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ አቀና፡፡ በመርከቢቱ
ታቦር ከተማ ነበር ውልደቱ፡፡ በልዑሉ ውልደት የተደሰቱት ላይ በነበራቸውም ቆይታ ስፒዲ እና አለማሁ እጅግ የጠበቀ
አፄ ቴዎድሮስም በእለቱ መድፍ ያስተኮሱ ሲሆን 500 ወዳጅነትን መስርተው ነበር፡፡ ስፒዲ በሄደበት ቦታ ሁሉ
ያህል እስረኞችንም ፈትተዋል፡፡ ከልዑሉ ጋር ሲጫወቱ አለማየሁን ማስከተል ያዘወትር ነበር፡፡ ይህንን የሁለቱን
መዋል አፄውን እጅግ የሚያስደስት ነገር ነበር፡፡ ተናደው እና ፍቅር ያየው ጀነራል ናፒየርም ኢትዮጵያውያን ሞግዚቶቹ
ተበሳጭተው ከነበር እንኳን አለማየሁን ታቅፈው ሲስሙ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ይልቁንም የአለማየሁን
ንዴታቸው ይበርድ ነበር ይባላል፡፡ ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ካፕቴን ስፒዲ እንዲረከብ ስለወሰነ
ልዑል አለማየሁ እንግሊዞች እጅ ከገባ ቡሀላ ከእድሜው ሁለቱ ሞግዚቶች ጉዞው ተጠናቆ እንግሊዝ ሀገር ሳይደርሱ
ለጋነት የተነሳ የሚጠብቀው እና የሚንከባከበው ሰው ከስዊዝ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ፡፡ ምንም
ሊኖር ግድ ነበር፡፡ ይህንን የተረዳው ጀነራል ናፔር ካፕቴን እንኳን የእንግሊዛውያኑ የታሪክ ድርሳናት ይህንን ቢሉም
ስፒዲ የተባለን ሰው የአለማየሁ ጠባቂ እንዲሆን መደበው፡ ልዑሉ ኢትዮጵያውያን ሞግዚቶቹን በተባለው መጠን
፡ ምክንያቱ ደግሞ ካፕቴኑ የአማርኛ ቋንቋን አምርሮ ይጠላቸው እና ባያቸውም ቁጥር በብስጭት
22 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
የኛ
24
መ ል ካ ም7 4 |
ፌብሩወሪ 1,2019
እኛ አቢሲኒያዎች ነን !
የጥንት ስልጣኔ ባለቤት ፣ ሀገራችንን በፊት ወደንነበረችበት ሀያልነት ፣ አንድነት
24
፣ መ ል ካሆና
ተወዳጅነት እና ተሰሚነት ለመመለስ እንሰራለን ። ሀገራችን ከፊት
24 መ ል ካ ም7
4 | ፌብሩወሪ
ም7ሳናያት
4 | ፌብ ሩዋሪ
1,2019
1,2019
አንተኛም ። ማንኛውም ሀገሩን ለመቀየር የተነሳ ግለሰብም ሆነ ድርጅት የኛን ራእይ
መጋራት ይችላል ።
እናመሰግናለን!
ቻናሉን ለመጎብኘት እዚህ ይጫኑ
24
24 ም744| ሜ
መልልካካም7
መ | ማ
ይር 1ች, 210, 21 09 1 9
በልዑል ሀይሌ
ፓንዲ
ክፍል ፩
“ዛሬ የምንማማረው ስለ ኢትዮጵያ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ነው” ይላል አጠር ያለው መላጣ ጂኦግራፊ አስተማሪያችን
“ዛሬ የምማረው ስለ ፓንዶራ ጥልቅ ዓይኖችና የሰውነት አቀማመጥ ነው”(እኔ) አቤት ፓንድዬንኮ ስወዳት ለጉድ ነው፡፡
ይኸው ስለምወዳትምኮ ነው ሁሉም የክፍላችን ተማሪዎች(እሷን ጨምሮ) ስለ ኢትዮጵያ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ
ሲማሩ እኔ ስለ እሷ አቀማመጥ በተመስጦ የምማረው…
“ኢትዮጵያ የምትገኘው በምስራቃዊው የአፍሪካ ቀንድ ሲሆን በሰሜን ኤርትራ ፤ በምስራቅ ጅቡቲና ሶማሊያ ፤ በምዕራብ
ሱዳን፤ በደቡብ ደሞ ኬንያ ያዋስኗታል” (አጭሩ ጂኦግራፊ አስተማሪያችን) “ፓንዶራ የምትገኘው በክፍላችን ሁለተኛው
መደዳ አራተኛው ወንበር ነው፡፡ ከፊት እነ ጀሚላና ቶማስ፤ ከኋላ እነ ሳምሶንና ትዕግስት፤ በግራዋ
በኩል ከድር በቀኟ ደሞ እኔ አፍቃሪዋ እናዋስናታለን” (እኔ) የሌሎቹን ባላውቅም እኔ ግን የሷ አዋሳኝ በመሆኔ ትልቅ ኩራት
ይሰማኛል፡፡ በርግጥ አንድም ቀን እንደምወዳት ነግሬያት ወይም በሰፊው አጫውቻት ባላውቅም እንደዚሁ ሳያት መዋሉ
በራሱ በደስታ
ያንሳፍፈኛል፡፡ ከፓንዲ ጋር እንድቀመጥ የረዳኝ ይሄ ደግሞ ጂኦግራፊ አስተማሪያችን ስለሆነ ውለታውን ለመመለስ
በሚል የኔን የፍቅር ውሎ
ከሱ ትምህርት ጋር እያዛመድኩኝ ቀኑን ሙሉ አሰላስላለሁ፡፡ በዚህም ጂኦግራፊ ትምህርቴን ሁሌም እንደደፈንኩኝ ነው፡
፡ምክንያቱም ሳጠና ከፓንዲ ጋር እያዛመድኩኝ ስለሆነ መቼም አልረሳውም….እንዴት ብዬ?….ጂኦግራፊን ከፓንዲ ጋር
አዛምጄ ….ፓንዲ እንዴት ትረሳለች?..ኧረ በጭራሽ!! ፓንዲን እርሳት ከምትሉኝ ራስህን እርሳ ብትሉኝ ይቀለኛል፡፡
ለነገሩ ራሴንማ ከረሳሁት ቆየሁኝ…..ምግብ ዘግቶኝ እኛ ቤት ያለወትሮው እንጀራ መሻገት ጀምሯል፡፡ (እኔ ነበር
የማወድመው ለካ!) ልብስም ከሰፈራችን አንደኛ ለባሽ የነበርኩት ልጅ አሁን ግን ከዩኒፎርሜ ውጪ ምንም አይነት ልብስ
መልበስ አስጠልቶኛል፡፡ ምክንያቱም ፓንዲን ያገናኘኝ ይሄ ዩኒፎርም ስለሆነ አልቀይረውም፡፡ ፓንዲን
ልቀይራት?!..አይደረግም!! …..ደሞም ልብስ ሆኖ የሚያሞቀኝ ምትሃታዊ ፍቅሯ ወዴት ሄዶ?!....ደብተሮቼን እንዳለ
ብታዩዋቸው በተወጉ የልብ ቅርፆች ያሸበረቁ ናቸው፡፡ ሁሉም አስተማሪዎቻችን የየራሳቸውን ትምህርት በፅሁፍ
ሲያስገለብጡን ‘P’ የሚለውን ፊደል በተለየ ውበት ተለቅ አድርጌ
በጥንቃቄ ነው የምፅፈው….ብቻ ምን ልበላችሁ እንቅስቃሴዬ ሁሉ በፓንዶራ ዙሪያ ነው፡፡…….በዚህ ሃሳብ መሀል
እያለሁ የሆነ ነገር ሲነካኝ ተሰማኝና ብንን አልኩኝ(ጂኦግራፊ አስተማሪያችን ነበር ተጣርቶ አልሰማ ስለው በቾክ ወርውሮ
ከገባሁበት ጣፋጭ ህልም የቀሰቀሰኝ)
“በል እንጂ መልስ!!”…..በድንጋጤ የማደርገው ነገር ሲጠፋኝ የክላሳችን ተማሪዎች በሙሉ ሳቁብኝ…..ድዳቸው ለሙቅ…..
ለነገሩ እነዚህ ሙቅም ሙድም አይገባቸውም……ግልፍጥ ሁላ ጥርሱን
መክፈቻ ያድርገኝ?…. “አንተንኮ ነው!!... በዓለም በቆዳ ስፋት ትንሿ ሃገር ማናት?”
ሲለኝ ወዲያው በድንጋጤ ከአፌ የመጣልኝ የምወደው ቃል አሟለጨኝ
25 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
“ፓንዶራ!....” አልኩና የክላሱ ተማሪ ሲያፈጥብኝ “ፓንዶራ የምትባል ሃገር” ስል መምህሩ የሹፈት ሳቅ ሳቀና “ፓንዶራ
የት ነው የምትገኘው? …” ሲለኝ ካጠገቤ ልለው አሰብኩኝና መልሼ ዋጥኩት “እዚህ (በአፌ ወደ ፓንዶራ አቅጣጫ
እያመለከትኩኝ) ምዕራብ አፍሪካ” ስል መምህሩ በንዴት በሱ ክላስ እንዳልገባ አስጠንቅቆ ወደ ውጪ አስወጣኝ፡፡ ቆይቼ
ስሰማ ፓንዶራ ሳይሆን አንዶራ የምትባል ሃገር አውሮፓ ውስጥ እንደምትገኝ አወቅኩኝ፡፡እኔ ታዲያ መች አወቅኩኝ
የኔዋ ፓንዲን እንጂ ሀገሪቷን ከየት አመጣታለሁ ምን አይነት ክፉ አጋጣሚ ነው? …… ከፓንዲ ጋር ያቆራኘሁት ጂኦግራፊ
አለመማር ማለት ወፌ ላላ ተሰቅሎ 400 ጅራፍ መገረፍ ማለት ነው፡፡ ….ለነገሩ ፓንዲ እንደሆነች ሁሌም
ከጎኔ አለች ስለዚህ ከሌላ ትምህርት ጋር ለምን አላቆራኛትም አልኩና ከባይሎጂ ትምህርት ጋር ማቆራኘት ጀመርኩኝ…
ቻው ቻው ጂኦግራፊ!!....አንተ መላጣ አስተማሪ ምን ይዋጥህ?…ምንም!!..ባይሎጂ አስተማሪያችን እንደ ጂኦግራፊ
አስተማሪያችን መላጣ አይደለም፡፡ ደስ ሲል!!... ሴት ነች ፀጉሯ ወርዶ ወርዶ ሲቆጨው መሰለኝ ተመልሶ ወጥቶ ከጆሮዋ
በላይ ተሰንቅሯል፡፡
መምህርታችን ጋዋኗን አውልቃው አታውቅም …እስከዛሬ በሌላ ልብስ
አይቻት አላውቅም፡፡ ወይ ማን ያውቃል እንደኔ ጋሽ ፎንቃ ሰፍሮባት ይሆናላ!!....በኔም ስለደረሰ አልፈርድባትም ታፍቅር…..
ብቻ ግን ያንን
የፓንዲን ስም ያቀለለውን ጂኦግራፊ አስተማሪያችንን አፍቅራ እንዳይሆንና ፊልድ እንዳልቀይር!!...ለነገሩ ምኑ
ይፈቀራል!...በቴሌስኮፕ ካላየችው
ለዓይኗም አይሞላ!!....ቴሌስኮፕ ደሞ እኛ ትምህርት ቤት የለም ደስ ሲል!!...ምን ይዋጥህ ጂኦግራፊ አስተማሪያችን
….ምንም!..... “ዛሬ የምንማማረው ስለ ሴክሹዋል ሪፕሮዳክሽን” ስትል ‘ቱ! ቲቸር ምን አይነት ባለጌ ነች?’ እያሉ በሳቅ
በመጎሻሸም በእፍረት ያዩዋታል
ከፊታችን የተቀመጡት እነ ቶማስ… .ግማሹ የክላሱ ተማሪዎች ደሞ
በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ምዕራፍ በመድረሱ ዓይናቸው ተጎልጉሎ ሊወጣ ምንም አልቀረውም “ሴክሹዋል ሪፕሮዳክሽን
ማለት ዘርን ለመቀጠል ስለሚረዱ የመራቢያ አካላት የሚያጠና ነው፡፡ ለምሳሌ በሰው ልጅ ስናየው ሴቷም ወንዱም
የየራሳቸው የመራቢያ አካላት አሏቸው፡፡ እስቲ ከወንዱ የመራቢያ አካል እንጀምር!!...” ስትል ክፍላችን በተቃውሞ
ሹክሹክታ ታመሰ “ምንድነው ሚያንሾካሹካችሁ?” ….የክፍላችን ደፋር ተናጋሪ ቢኒያም ተነስቶ ፀጉሩን እየጠቀለለ “አይ
ቲቸርዬ!..ማለት ቅድሚያ ለሴቶች በሚለው ህግ መሰረት ከሴቶች ቢጀመር አሪፍ ነው!!” ሲላት ባይሎጂ አስተማሪያችን
በንዴት “ና ውጣ!!..ከዚህ በኋላ በኔ ክላስ እንዳላይህ!...” ቢኒያም ከወጣ በኋላ ቀጠል አድርጋ “የወንድ የመራቢያ ክፍል
ዘር ሲያዘጋጅ ሴቷ ደሞ እንቁላሉን ታዘጋጃለች ማለት ነው፡፡….የወንዱ የመራቢያ አካል (ባይሎጂ መፅሀፍ ገለጥ ገለጥ
አደረገችና) ከፍ
አድርጋ ወደኛ አዙራ መለመላውን ስታሳየን ሴቶች በኩራት ሲሳለቁብን እኛ ወንዶች በመሸማቀቅ አጀብናት፡፡ “ለነገሩ
ፎቶ አስነስቶ ያዋረደንኮ በየሰፈሩ ቱቦ በጠራራ ፀሐይ የሚሸናው ወንድ ነው ምናለ ምች ባጣመመለት!!...መዘዝ አድርጎ
ሲያወጣውኮ ሻሞላ የመዘዘ ጀግና የሆነ ነው ሚመስለው” ይላል የክፍላችን ሰቃይ ተማሪ ከድር ከጎኔ
ስለሆነ ሹክሹክታውም ይሰማል፡፡
በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ የክፍላችን አብዛኞቹ ሴቶች የኛን በማየታቸው
ተደስተው ይሁን ምን ይሁን ሲገለፍጡ ፓንዲ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ብላ ትከታተላለች….አይ ፓንዲ! ጨዋ!!
የጨዋ ልጅ!! የጨዋ የልጅ ልጅ ልጅ!!....ለዚህ እኮነው የምወዳት
ጨዋነቷ!...
(ይቀጥላል......)
26 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ስራ ፈጠራ
ሀሜክ ዲዛይን
ቤተልሄም አምባቸው
ወጣት ሀይማኖት ሆነልኝ በትምህርቷ የማኔጅመንት ምሩቅ ዲዛይንን መሰረተች፡፡ ሀሜክ ማለት ሀይማኖት የሚለውን
ናት፡፡ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርቷን ጨርሳ እንደወጣችም ስም በማቆላመጥ የተገኘ የቁልምጫ ጥሪ ነው፡፡
በተማረችበት የሙያ መስክ ለመስራት በማሰብ የስራውን ሀይማኖት ስራዋን ስትጀምር በጆሮ ጌጥ ምርቶች ብቻ ነበር፡
አለም ተቀላቅላ ነበር፡፡ ለሁለት ዓመታትም ያህል በተለያዩ ፡ የተለያዩ የአፍሪካ ጨርቆችን በመጠቀም በመጠናቸው
ድርጅቶች ውስጥ ሰርታለች፡፡ ነገር ግን የምትሰራው ስራ ገዘፍ ያሉ እና በቀለማቸው ደመቅ ያሉ ጆሮ ጌጦችን ትሰራ
የነፍሷ ጥሪ እንዳልነበር ለመረዳት ግዜ አልወሰደባትም፡፡ ነበር፡፡ ይህም ስራ የሀሜክ ዲዛይን መለያ ነው፡፡ በጊዜ
በድርጅቶች ውስጥ መስራትን እርግፍ አድርጋ ትታ በቤቷ ሂደትም የአንገት እና የእጅ ጌጦችን በመጨመር ስራዋን
ውስጥ በእጅ የተሰሩ የጆሮ ጌጦችን ማምረት ጀመረች፡፡ አሰፋች፡፡ በዚህ ብቻ ያልተገደበችው ወጣት ሀይማኖት
ይህንን ስራ ስትጀምር ምንም አይነት ትምህርትን ተምራ በአሁኑ ሰዓት የመብራት ጌጦችን ፣ እቃ ማስቀመጫ
ሳይሆን በግል ካላት ፍላጎት የተነሳ እና ለራሷ አየሰራች ሳጥኖችን ፣ የማስታወሻ ደብተሮችን እንዲሁም የሶፋ
ከምትጠቀምባቸው የጌጣጌጥ ስራዎች በቀሰመችው ልምድ ትራሶችን እነዚህኑ የአፍሪካ ህትመት ያለባቸውን ጨርቆች
ብቻ ነበር፡፡ የምትሰራቸውንም ስራዎች እያዩ የወደዱላት በመጠቀም ትሰራለች፡፡
ሰዎች በሚሰጧት መልካም አስተያየት የተነሳ ምርቷንም የሀሜክ ዲዛይን ምርቶች ሁሉ በእጅ የተሰሩ እና ምንም
ለመጠቀም የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥራቸው እያየለ ሲመጣ አይነት ማሽን ያልነካቸው ናቸው፡፡ በውጪው አለም
ይህንን ስራ በንግድ መልክ ለመጀመር በማሰብ ሀሜክ ለእንደዚህ አይነት ምርቶች ከፍተኛ ቦታ እና አክብሮት
27 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ስራ ፈጠራ
ሲሰጥ እናስተውላለን፡፡ በሀረጋችን ግን ያለው እውነታ የመሰማራትን ህልም ሰንቃለች፡፡ በቅርብ ግዜያት ማምረስ
ከዚህ የራቀ መሆኑ ስራውን ፈታኝ እንዳደረገባት ሀይማኖት ጀመረቻቸውን የሶፋ ትራሶች እማስ በማስፋት የቤት
ትናገራለች፡፡ በዚህም ያለመረዳት ችግር ምክንያት ውስጥ እና የቢሮ መገልገያ የእንጨት ውጤቶች ምርት
አብዛኞቹ የሀሜክ ዲዛይን ደንበኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ላይ የመሰማራት እቅድ እንዳላት ሀይማኖት ነግናለች፡
የሚኖሩ የውጪ ሀገር ዜጎች እና በውጪው አለም በነዋሪነት ፡ በተጨማሪም ሀሜክ ዲዛይን ልብሶችን በማምረት
የሰነበቱ ኢትዮጵያውያን ብቻ እንዲሆኑ አድርጎታል፡፡ ነገር ለተጠቃሚ የማድረስ ህልምም አለው፡፡ ሁሉም ምርቶች
ግን ሌላውም ኢትዮጵያዊ በእጅ ለተሰሩ ምርቶች ያለውን ታድያ የሀሜክ መለያ የሆኑትን የደመቁ የአፍሪካ ጨርቆችን
ክብር ቢጨምር በዚህ ኢንደስትሪ ላይ ያሉ ወጣቶችን የሚጠቀሙ ይሆናሉ፡፡
በማበረታታት የኢንደስትሪውን አለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ለመሰል ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ደግሞ ይህንን መልዕክት
መጨመር ይቻላል፡፡ አስለታልፋለች
ከንቃት በለለ ያለው ችግር የጥሬ እቃ አቅርቦት እንደሆነ “ማንኛውም ሰው መጀመርያ ማድግ የሚፈልገውን ነገር
ሀይማኖ አፅንኦት ሰጥታ እገልፃለች፡፡ የሀገራችን የገበያ ማወቅ አለበት፡፡ ራሱ ማድረግ የሚችለው እና የሚፈልገው
ሁኔታ ከሌላው አለም እጅግ የተገለለ ከመሆኑ እና ነው እንጂ ጓደኛ ያደረገውን አይደለም ማድረግ ያለበት፡፡
የኦንላይን ግብይትን ካለመፍቀዱ ጋር ተያይዞ ለስራዎቹ ይህንነ ካወቀ ውሳኔን ወስነ ወደ ስራ መግባት ይቻላል፡፡
ግብዓት የሚሆኑትን ምርቶች ለማግኘት እጅግ አሰልቺ በእርግጥ ቀላል አይሆንም ነገር ግን ሁሉንም ነገር በመሞክ
ረጅም ጉዞን መጓዝ ለወጣቷ የግድ ሆኖባታል፡፡ እቃዎቹ ነው እና የምናገኘው ከመሞከር ወደ ኃላ አንበል፡፡ ሌላው
ሲገኙ ደግሞ እቃዎቹን ለማኘት በሚደረገው ሂደት መሀል በስራ ፈጣሪ ወጣቶች ዙርያ ያሉ ሰዎች ያንን ሰው በደንብ
ዋጋቸው እጅግ እየናረ የተጠቃዎች ቁጥር መጨመር ላይ ሊደግፉት ይገባል፡፡ የሚሰራው ስራ ባይገባቸው እንኳን
ጋሬጣ ሆኗል፡፡ ሞራሉን ቢጠብቁ እላለሁ፡፡ መንግስትም ስራ ፈጠራ ላይ
ሆኖም ግን ዛሬም ወጣት ሀይማኖት እነዚህን የተዋቡ የራሱ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ ሁኑታዎችን ከማመቻቸት ጀምሮ
የእጅ ስራ ውጤቶች በመስራት ለፈላጊው ማቅረቡን በዚህ ዙርያ ከፍተኛ ጥኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል እላለሁ፡
ተያይዛዋለች፡፡ ወጣቷ ዛሬ ከምትሰራቸው መገልገያዎች ፡”
በዘለለ ለወደፊቱ ትልቅ እና ሰፊ በሆነው የኢንደስትሪ መስክ
28 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ዘመንኛ
ዘመንኛ
ዛሬ ዛሬ በሞባይል ስልካችን የምንፈጽማቸው ጉዳዮች ሰላምታ ከመለዋወጥ እና መልእክት ከመላላክ አልፈዋል:: ምስልና
ድምጽ ቀርጸን ከማስቀመጥ ጀምሮ የተለያዩ መተግበሪያዎችን (Mobile Applications) በመጠቀም ረቀቅ ያሉ
ተግባራትን በስልካችን ላይ መፈጸም የምችልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል::ታዲያ የእነዚህ የሞባይል መተግበሪያዎች መጎልበትና
የአይነታቸውን መብዛት ያክል ይኸው የዲጂታሉ አለም አይነተ ብዙ ተግዳሮቶችንም ፈጥሮልናል:: ከእነዚህ ተግዳሮቶች
ውስጥ ታዲያ የመረጃ ጠላፊዎች (hackers)መፈጠር አንዱና ዋነኛው ነው::የመረጃ ጠለፋ ከፍቃዳችን ውጪ በስልካችን
ወይም ኮምፒውተራችን ላይ የሚደረግ የመረጃ ስርቆት ወይም ኮምፒውተር ነክ እቃዎቻችን በመጠቀም የሚደረግ
የዲጂታሉ አለም ስውር ስለላ ነው:: ለመሆኑ የሞባይል ስልካችን ለመረጃ ጠለፋ መጋለጡን አልያም በስልካችን አማካኝነት
ስለላ እየተካሄደብን እንደሆነ በምን ልናውቅ እንችላለን?
6 የመተግበሪያዎች ድንገቴ ስራ
ማቆም
8 መተግበሪያዎችን ወይም
ኢንተርኔትን ተከትለው ብቅ
JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL CLICK HERE
31 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ዘመንኛ
32 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ከስፖርት ማህደር
የኋላው ከሌለ…
በዮናስ ድንቁ
ታሪክ በታሪከኞች ሲሰራ የጸሃፊው ድርሻ የሚሆነው ይህ ግብጽ እነ ባዳዊ አብደል ፈታህን በመሳሰሉ በዛን ጊዜ
ታሪክ ከጊዜ በላይ ሆኖ ከፍ ብሎ እንዲታይ ማድረግ የአጉሪቱ ምርጥ በሚባሉ ተጫዋቾቿ ታግዛ ሌላ የአፍሪካ
ነውና እኛም ይህን ብለን በዚህ ወር የስፖርት ማህደራችን ቡድን አንዴም እንኳን ዋንጫውን ለማንሳት ዕድሉን
በኢትዮጵያ የእግርኳስ ታሪክ ትልቅ ቦታ ስላለው አንድ ቀን ሳያገኝ ለሶስተኛ ጊዜ ሻምፒዮን ለመሆን ወደሜዳ ትገባለች።
ልናወራቹ ወደድን። መልካም ንባብም ተመኘን። ኢትዮጵያ በበኩሏ በ1949 ዓ.ምበተመሳሳይ ሁኔታ በግብጽ
ጥር 13፣1954 ዓ.ም, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ። ቀዳማዊ 4 ለ 0 ተሸንፋ ያጣችውን ዋንጫ የቫሳሎ ወንድማማቾችን
ሃይለስላሴ ስታድየም መፈናፈኛ እስኪታጣ ድረስ ከ መንግስቱ ወርቁ ጋር ባጣመረ ቡድኗ በዚህ አመት
እግርኳስን በተጠሙ ከ25,000 በላይ በሚሆኑ ደጋፊዎች ለማሳካት ቋምጣለች።
ተሞልቷል። ጨዋታው ደግሞ ኢትዮጵያን ከግብጽ የዕለቱ የመሃል ዳኛ የነበሩት ኡጋንዳዊው ኢንስትራክተር
ያፋጠጠውየ3ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ። ጆን ብሩክስ በፊሽካቸው የጨዋታውን መጀመር
ወደ ውድድሩ ግብጽ የቀድሞው የዋንጫ ባለቤት በመሆኗ አበሰሩ።ደጋፊውም ዝማሬውን በድምቀት ቀጥሎ የኳሷን
ኢትዮጵያ ደግሞ አዘጋጅ ስለነበረች ያለማጣሪያ በቀጥታ አቅጣጫ ተከትሎ ያፈጥ ገባ። ደቂቃዎች አለፉ። 35ኛው
መግባት ሲችሉ በማጣሪያ ውድድሩን የተቀላቀሉትን ደቂቃ ላይ ባዳዊ ግብጽን ቀዳሚ ያደረገችውን ጎል ከመረብ
ቱኒዚያንና ኡጋናዳን በማሸነፍም ነው ለፍጻሜው ያለፉት። አሳረፈ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ዝም አሉ፣
የጨዋታው መጀመሪያ ሰአት ተቃርቧል። በሃገሪቱ ሰንደቅ ሁሉም ተደናገጠ፣ ጨዋታውም ቀጠለ።
አላማ ቀለም ያሸበረቁ ደጋፊዎች፣ በአሸናፊነት ተስፋ አሁን ኢትዮጵያውኑ ተጭነው መጫወት ጀመሩ። የውጤት
የተሞሉ ልቦች በዝማሬ ለቦታው ልዩ ድምቀት ሰጥተውታል። ለውጥ ግን አልነበረም። የመጀመሪያው አጋማሽም በግብጽ
የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ዋንጫ ማንሳት የቻለችው መሪነት ተጠናቀቀ።ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ተሽለው
34 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
ከስፖርት ማህደር
የቀረቡት ኢትዮጵውያኑ በ74ተኛው ደቂቃ በግርማ ተክሌ 4 ለ 2 በሆነ ውጤት በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
የአቻነቷን ጎል አስቆጠሩ። ደጋፊው እንደአዲስ ተስፋው የቡድኑ አንበል የነበረው ሉቺያኖ ቫሳሎም ከቀዳማዊ
አንሰራርቶ ሳይጨርስ ግን ባዳዊ ለግብጽ 2ኛውን ጎል ሃይለስላሴ እጅ ዋንጫውን ተቀበለ።ሌሊቱን ሙሉ ደስታና
በሰከንዶች ልዩነት ውስጥ አስቆጥሮ ዋንጫው ወደግብጽ ሀሴት እጅና እግር አውጥተው በከተማው ላይ በድምቀት
ምድር መሄዱ እርግጥ መሰለ። ታዩ። ቀኑም በታሪክ መዛግብት ላይ ትልቅ አሻራውን ጽፎ
የኢትዮጵያ የእግርኳስ ታሪክ ካያቸው ድንቅ ተጫዋቾች አለፈ።
መካከል አንዱ የሆነው መንግስቱ ወርቁ በ85ኛው ደቂቃ ይህ ስብስብ ኢትዮጵያ በእግርኳስ ብሎምበስፖርት ታሪኳ
ላይ ከማዕዘን ምት የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ካየችው ስብስብ ውስጥ ምርጡ ነው ቢባል ብዙዎችን
አስቆጥሮ ውጤቱን ወደ 2 ለ 2 ቀየረው። በዚህም መሃል የሚያከራክር አይሆንም።
የግብጹ ግብ ጠባቂ ኳሷን ስቶ በስህተት የመንግስቱን ግራ አሁን ላይ ግን ሀገራችን ኢትዮጵያ ለዋንጫ ከመፎካከር
ዓይን በቡጢ መትቶታል። በኋላም መንግስቱስለዚህ ጉዳይ ይልቅ ውድድሩ ውስጥ ለመግባት የሚደረገውን ማጣሪያ
ተጠይቆ ሲመልስ በቀልድ መልክ እንዲህ ብሎ ነበር። እንኳን ማለፍ ተስኗት እናያለን።
ታዲያ ኋላችን እንዲህ እያማረ አሸብርቆ ሲታይ አሁናችን
ላይ ምን ተፈጠረ? ፊታችንስ ከኛ ምን ይጠብቃል?
አባቴ የሞተው ለኢትዮጵያ ክብር በሁሉም የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቤተሰብ ውስጥ ሊመላለሱ
ጣልያንን ሲዋጋ ነው። ስለዚህ የሚገቡ የሚመለከተው አካል ደግሞ ምላሽ ሊሰጥባቸው
ለኢትዮጵያ አንድ ቡጢ መቅመስ ለኔ የሚያስፈልጉ ጥያቄዎች ናቸው። አበቃሁ።
ያን ያህል ከባድ አልነበረም።
#ተጨማሪ
መደበኛው 90 ደቂቃ ተጠናቆ አሸናፊውን ለመለየት • በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ያሰለጥኑ
30 ተጨማሪ ደቂቃዎች ጨዋታውን መቀጠል አስፈላጊ የነበሩት ዩጎስላቪያዊ አሰልጣኝ ስላቭኮ ሚሎሴቪች
ነበር። በስታዲየሙ ውስጥም ከፍተኛ ውጥረት ነገሰ። በውድድሩ ወቅት አገሪቱ ውስጥ ስላልነበሩ እሳቸውንን
ነገር ግን በ101ኛው ደቂቃ ላይ በግብጽ ተጫዋቾች በመተካት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ቡድኑን ለዋንጫ
በተፈጠረ ስተት ኢታሎ ቫሳሎ ኢትዮጵያን መሪ ማድረግ አብቅተውታል።
ቻለ።የኢትዮጵያውያን ፊት በብርሀን ተሞላ። • በውድድሩ ታሪክ በዋንጫም ሆነ በሜዳልያ ብዛት
117ኛው ደቂቃ ላይ አፍሪካ እስካሁን ድረስ በሙሉ አፏ ግብጽን የሚስተካከላት የለም።
የምታወራለት ግብ ከመረብ ላይ አረፈ። መንግስቱ ወርቁ • የ2019 አፍሪካ ዋንጫ በቶታል ስፖንሰርነት እንደ
በአስደናቂ ብቃት 4 የግብጽ ተጫዋቾችን አታሎ በማለፍ ኢትዮጵያን አቆጣጠር ከሰኔ 14 እስከ ሀምሌ 12 2011
4ኛውን የኢትዮጵያን ጎል ከመረብ አሳረፈ። ስታድየሙ ዓ.ም ይካሄዳል።
በአንድ እግሩ ቆመ፣ አዲስ አበባ ጮቤ ረገጠች።ጨዋታው
35 መ ል ካ ም7 4 | ሜ ይ 1 , 2 0 1 9
*805*ፍቅር#
በልዑል ሀይሌ
*805*............
ጎዶሎ ጎን መሙያ
ያልተፋቀውን ካርድ ዕጣ ስትሞላበት
እሷን ነው?...’ሌላ’ን ነው?
በፍቅር ህይወቴ ስሟን ያኖርክበት
.
አላውቅም!
.
*805*...............
.
ይሄን ቁጥር ፅፌ
ሄዋን እየሞላሁ ደውዬም አውቃለሁ
ያገለገለ ካርድ እየተባለብኝ
ካርዴን የሚሞላ ኔትውርክ አጥቻለሁ
.
ይሁን!
.
*805*.................
እናም አሁንም
.
ካርዴ ውስጥ ያለሽው አንቺ ትሆኚ እንደው
ከኮከብ ቀጥለሽ ተፅፈሽ ገብተሻል
እስከመቼ አትበዪኝ
መሰላሉን ስጫን ኔትወርክ ይነግርሻል
.
*805*.................
.
ስማኝ ፈጣሪዬ...
በሙከራ ብዛት ቻርጅ ከሚያልቅብኝ
በተሞሉ ካርዶች ጊዜ ከሚያልፍብኝ
..
የፃፍካትን ስጠኝ
ከኮከብ ቀጥዬ የሷን ስም ልፃፈው
መሰላል ተጭኜ በሞላኸው ቤቴ
አንተው ጋ ደውዬ በምስጋና እንዳልፈው
*805*ፍቅር#